በልቦና አይኖቻችን እንዴት በመንፈሳዊው ዓለም አጥርተን ማየት እንችላለን??
የልቦና አይኖቻችን ሲበሩ በህይወታችን የሚሆኑ ጠቃሚ ነገሮች...
መስማት ያለባችሁ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ነው አሁን አውርዳችሁ አስሙት🔥🔥🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ኢሳይያስ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
⁴ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።
መዝሙር 40
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።
² ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።
እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
— መዝሙር 105፥4
አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።
— መዝሙር 27፥8
እርሱ በሰማይ #ስለእኔ አለ
እኔ በምድር ስለ #እርሱ አለው።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ኤፌሶን 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።
¹⁸ መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤
¹⁹ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤
²⁰ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።
በኢየሱስ ክርስቶስ🔥
👇👇👇👇👇
❌ኃጢአት ተሸንፏል።
❌ሲኦል ተሸንፏል።
❌ሞት ተሸንፏል።
❌ዲያቢሎስ ተሸንፏል።
“ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።”
— 1ኛ ዮሐንስ 3፥9
እግዚአብሔር ያዳነን የባህሪውን ግዴታ ሊወጣ ፈልጎ ሳይሆን #ወዶን ነው።
እግዚአብሔር እኛን ያዳነበት ምክኒያቱ #ወዶን ነው።
ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ #ወድዶኛልና አዳነኝ።
— 2ኛ ሳሙኤል 22፥20
ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ #ወድዶኛልና አዳነኝ።
— መዝሙር 18፥19
አለማትም በፈጠረ በእግዚአብሔር ተወዳችኋል።❤️
እግዚአብሔርን አንድ ነገር ለመንኩት እርሱም በፍቅሩ ልቤ እንዲነደፍ😍😍❤️❤️
በእግዚአብሔር ፍቅር ልባችሁ ይነደፍ❤️
አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።
— መዝሙር 18፥1
እኔም ሜፌቦስቴ ነኝ.....
በህይወቴ መራመድ የማልችልና ሽባ የነበርኩኝ ሎዶባር በሚባል በኃጢአትና በቆሻሻ ህይወት ውስጥ የነበርኩኝ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ሆኜ ሞቴን ስጠባበቅ የህይወቴ አዳኝ ኢየሱስ ካለሁበት ቦታ መጥቶ ከሎዶባር ከቆሻሻ ህይወት በደሙ አጥቦ በንጉስ ገበታ በአብ ቀኝ ያስቀመጠኝ እኔም ሜፌቦስቴ ነኝ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የእግዚአብሔርን ፅድቅ የሚስተካከል የተቀበልንበት የመለኮት ቀመር ነው።
እግዚአብሔር ከሲኦል ያዳነን በተአምራት ሳይሆን በመስዋእት ነው።
እግዚአብሔር አንተን/አንቺን ከዘለአለም ሞት ለማዳን አንድያ ልጁን ሰውቶታል።
አብ ለዘላለም ህይወት ጥሪ አቅርቦላችሁ ለዚህ ጥሪ ምላሽ የሰጣችሁና የዚህ የዘለአለም ህይወት ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ሁሉ ጠሪአችሁ የእምነታችን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ብቻ እንመልከት።
አብ ከኢየሱስ ውጪ እንድንመለከትለት አይፈልግም።
ኢየሱስን ብቻ ከተመለከታችሁ ማንም አያስቆማችሁም።
ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤
— ዕብራውያን 3፥1
መሰዊያችሁ እጅግ በጣም ውድ ነው🔥🔥😭😭
መሰዊያችሁ እንደ መቅደላዊት ማርያም እንባችሁ እግሩን የሚያጥብበት ፀጉራችሁ(ክብራችሁ) እግሩን የሚጠርግበትና ውድ የሆነ ሽቱአችሁ (ነገራችሁ) በፊቱ ተሰብሮ የሚሰዋበት እጅግ በጣም ውድ የሆነ ስፍራ ነው🔥🔥😭😭
እግዚአብሔር በሚያያችሁ እይታ እራሳችሁን ማየት ጀምሩ...
አሁን እግዚአብሔር እናንተን የሚያየው በክርስቶስ እጅግ በጣም የተወደዳችሁና ወጋ የተከፈለላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆናችሁ ነው።
አብ አትረፍርፎ ፍቅሩን ያፈሰሰልን የእርሱ ልጆች እንድንሆን ነው። ስለዚህ አብ ለእኛ ያለው እይታ ልጆቹ ሊያደርገን አትረፍርፎ ባፈሰሰልን ፍቅር ነው። ስለዚህ አብ እኛን በክርስቶስ እንደሚያየን ሁሉ እኛም አብን በክርስቶስ ልጆቹ ሊያደርገን ባፈሰሰልን ፍቅር በክርስቶስ በኩል ልናየው ይገባል።
አብ የእኛ ድካም ወይም ከሳሹ ዲያቢሎስ እንደሚነግረን ሳይሆን በክርስቶስ በኩል እንደተገለጠልን ዘላለማዊ አባትና ፍቅር ብቻ ነው።
1ኛ ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።
² ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።
³ በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ነፍሳችሁ እግዚአብሔርን የምትጠማና የምትራብ ከሆነ መንፈሳዊ ጤንነት ላይ ናችሁ ማለት ነው።
እግዚአብሔር ከእናንተ ጉዳይ እንዳለው አንዱ ምልክት በውስጣችሁ እግዚአብሔርን መራባችሁ እና እግዚአብሔርን መፈለጋችሁ ነው።
ረሃባችሁ በመንፈሳዊ ዓለም ላይ ትልቁ ሀብታችሁ ነው።
የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ እግዚአብሔርን መራብና መጠማት የህይወታችሁ ዋና ነገር ሊሆን ይገባል።
ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር የሚመዘነው ለእግዚአብሔር ባላችሁ መሻትና ረሃብ ነው።
መዝሙር 42
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።
² ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
መዝሙር 63
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
² ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።
መዝሙር 143
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ ተመለከትሁ።
⁶ እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
በኢየሱስ ስም እግዚአብሔርን መራባችሁና ፊቱን መፈለጋችሁ በኃይል ይጨምር🔥🔥🔥
እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለሆነ በጠላቶቻችሁ አጅ አትወድቁም።
“ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።”
— መዝሙር 129፥2
“ከአንተ ጋር ይዋጋሉ፥ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሡህም፥ ይላል እግዚአብሔር፦”
— ኤርምያስ 1፥19
“ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም።”
— ኤርምያስ 15፥20
“እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ።”
— ኤርምያስ 20፥11
ለ21 ቀን የሚቆይ የፆምና የፀሎት ጊዜ
ኢየሱስን መገናኘት🔥🔥
Encounter with Jesus🔥🔥
በጌታ የምወዳችሁና የማከብራችሁ ወዳጆቼ ከ21 ቀን በኋላ በክብር እንገናኛለን መልካም ቆይታ ይሁንላችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ ❤️❤️❤️
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
— 2ኛ ቆሮ 13፥14
እግዚአብሔር መንፈሱን በውስጣችን ለዘላለም እንዲኖር ያፈሰሰው በፆም ፀሎታችን ሳይሆን በልጅነታችን ነው።
ገላትያ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ #ልጆችም #ስለ_ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።
⁷ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
እንደርሳለን ሳይሆን #ደርሰናል
እስራኤላውያን ወደ ሲና ተራራ መውጣትና እግዚአብሔርን መቅረብ ፈሩ እጅግም ደነገጡ ሙሴንም አንተው እራስህ እግዚአብሔር አናግረውና የተናገረህን ትነግረናለህ እኛ ካየነው እንሞታለን አሉት እሱ ብቻ አይደለም ሙሴ ራሱ ተንቀጠቀጠ እጅጉን ፈራ ምክኒያቱም የእግዚአብሔር በሲና ተራራ መገለጥ ተራራውን አቀለጠው ተራራውን አጋየው ተራራው ከእግዚአብሔር ክብር የተነሳ ጨሰ ከብቶች እንኳን ወደዛ ተራራ ለመውጣት ቢሞክሩ ይሞቱ ነበር ስለዚህ ሙሴ እግዚአብሔርን ለመገናኘት እጅግ ፈራ...
አሁን ግን እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ
👉ወደ ጽዮን ተራራ
👉እግዚአብሔር እራሱ ወደሚኖርበት ወደ እግዚአብሔር ከተማ
👉ወደ ሰማያዊቱ እየሩሳሌም
👉በደስታ ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት
👉ስማቸው በሰማይ ዘደ ተጻፈውወደ በኩራት ማህበር
👉የሁሉ ዳኛ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር
👉ፍጹምነትን ወዳገኙ ወደ ጻድቃን መንፈሶች
👉የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ
👉ከአቤል ደም ይልቅ የተሻለውን ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም #ደርሰናል።
ዕብራውያን 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤
¹⁹ ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ፤
²⁰ እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትእዛዝ ሊታገሡ አልቻሉምና፤
²¹ ሙሴም፦ እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤
²² ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ #ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥
²³ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥
²⁴ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም #ደርሳችኋል።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
ወንጌል ከሆሳና 54 ከ.ሜ ርቃ በምትገኘው በቦኖሻ ገበያዎች ላይ በኃይልና በስልጣን ለብዙ ሺ ሰዎች ተሰበከ ብዙዎችም ይህንን የመዳን ወንጌል ሰሙ እጅግ ብዙዎችም ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው ተቀበሉ ክብር ሁሉ ለጌታ ይሁን🔥🔥🔥🔥
ፊልጶስም ወደ አንዲት የሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው።🔥🔥
— ሐዋርያት 8፥5 (አዲሱ መ.ት)
በ Seasonህ ከፍ ማለት ከፈለክ አሁን ራስህን በኃያሉ እግዚአብሔር ፊት ራስህን አዋርድ።
እግዚአብሔር ላንተ ባዘጋጀልህ Season ከፍ ማለት ትፈልጋለህ? ብርሃንህ ተፅእኖ እንዲፈጥር ትፈልጋለህ? የእግዚአብሔር ክብር በሙላት ተገልጦብህ ለብዙዎች የመፍትሄ ሰው መሆን ትፈልጋለህ?
ጊዜው አሁን ነው የምኑ ካልከኝ በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ባዶ የምታደርግበትና የምታዋርድበት።
አሁን በእግዚአብሔር (ህልውና) ፊት ራስህን ባዶ ካደረክ እመነኝ ጌታ ከፊትህ ባዘጋጀልህ Season በሕዝብ ፊት በእግዚአብሔር ክብር በሙላት ትገለጣለህ።
አሁን አምላክህ ፊት ባዶ ሁነህ ራስህን አዋርድ ነገ በ ጌዜህ ሙሉ ሆነህ ለትውልድ በረከት ትሆናለህ።
ያዕቆብ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።
…
¹⁰ በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።
እንግዲህ #በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥6
እግዚአብሔር #የተገባው ነገር ሰይጣን ደግሞ በጣም #የሚፈልገው ነገር ቢኖር #አምልኮ ነው።
እግዚአብሔር አምልኮ #የሚገባው ሲሆን ሰይጣን ደግሞ አምልኮ #ፈላጊ ነው።
የመንፈሳዊ ህይወትህ እድገት የሚመዘነው የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነውን ኢየሱስን በተረዳኸው ልክ ነው።
ሰው የእግዚአብሔርን ጥበብ ኢየሱስን መረዳት የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ መገለት #ብቻ ነው።
ኢየሱስ ተቀድቶ የማያልቅ የመንፈስ ቅዱስ የጥበብ ውቂያኖስ ነው።
ከአብ ዘንድ እንዲህ ያለ ታላቅ ሊቀ ካህናት አለን
1 ከኃጢአት በስተቀር በነገር ሁሉ የተፈተነ..የቸፈተነ ብቻ ሳይሆን ተፈትኖ ወርቅ ሆኖ የተገኘ ታላቁ ሊቀ ካህናት አለን።
2 የሚራራ ሊቀ ካህናት: እሱ ከኃጢአት በስተቀር በነገር ሁሉ ተፈትኖ እንከን የሌለበት የሌለበት የእግዚአብሔር በግ ሆኖ የተገኘ ስለሆነ ለሚፈተኑትና ለሚደክሙት የሚራራ ሊቀ ካህናት ነው። ምክኒያቱም የድካምን ጥግ የጭንቀትን ጥግ የረሃብን ጥግ የመጠላትን ጥግ የመረሳትን ጥግ የመከዳትን ጥግ ስለቀመሰ በነገር ሁሉ የሚፈተኑትን የሚፈርድባቸው ሊቀ ካህናት ሳይሆን የሚራራላቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ታላቁ ሊቀ ካህናት ነው።
3 ሰማያትን በትንሳኤ ኃይል ያለፈ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ በኃይል የተገለጠ ታላቁ ሊቀ ካህናት አለን።
👉ከአብ ጋር ቤተሰባዊና ዘላለማዊ ህብረት እንዲኖረን ሰማያትን ቀዶ ያለፈ የመላእክትን ዓለም የከፈተ መላእክት ወደ ሰው ዓለም እንዲወርዱና እንዲወጡ ከሰማይ ወደ ምድር የተዘረጋ #መሰላል ታላቁ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ከአብ ዘንድ አለን።
ዕብራውያን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።
¹⁵ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።
አንተን ወክሎ በአብ ፊት የቆመ ታላቁ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ አለህ። ስለዚህ አንተ አሁን በአብ ፊት ብቁ ነህ።
አንቺን ወክሎ በአብ ፊት የቆመ ታላቁ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ አለሽ ስለዚህ አንቺ አሁን በአብ ፊት ብቁ ነሽ።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ይሄ መዝሙ የሆነ እግዚአብሔርን የመፈለግ ረሃብ እየጨመረብኝ ነው😭😭😭
ተባረኩበት እናንተም🔥🔥❤️❤️
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
መሰዊያችሁ እናንተና እግዚአብሔር #ብቻ የምታሳልፉበት የእናንተና የመንፈስ ቅዱስ #የሚስጥር ስፍራችሁ ነው።
ከመሰዊያችሁ የሚበልጥ ሌላ ውድ ነገር ስለሌለ ለመሰዊያችሁ ስፍራ የከበረውን ዋጋ ስጡ።
መሰዊያችሁ የእናንተ መሻት ተሰውቶ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን አሳብና መሻት አካል የምታለብሱበት ቦታ ነው።
መሰዊያችሁ ከአባታችሁ ከእግዚአብሔር ጋር የፍቅር ጊዜ የምታሳልፉበት እጅግ የተወደደና የሚናፈቅ ቦታችሁ ነው።
ዕብራውያን 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በተለያየ ጊዜና በልዩ ልዩ መንገድ በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ፣
² በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን።
#1.እግዚአብሔር በየዘመናት ዝም የሚል ሳይሆን የሚናገር አምላክ ነው።
#2 እግዚአብሔር በየዘመናት ሲናገር የተጠቀመባቸው ብዙ አገልጋዮች ነበሩ።
#3 በዚህ መጨረሻ ዘመን እግዚአብሔር የመጨረሻ ንግግሩንና መልእክቱን በልጁ በኩል ተናገረን
#4 ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የመጨረሻ መልእክቱና መልእክተኛው ነው።
#5 ለዘመን መጨረሻ የሚሆን የእግዚአብሔር የመጨረሻው ንግግርና መልእት እንዲሁም መልእክተኛ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ሌሎቹ ሁሉ መልእክተኞች መልእክት የሆነውን ኢየሱስን የሚናገሩ ናቸው።
#6 እግዚአብሔር አስቀድሞ በተለያዩ አገልጋዮች በልዩ ልዩ ጎዳናውች ላይ ሲናገር የነበረው ስለ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር።
#7 ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የመጨረሻ መልእክትም መልእክተኛም ነው።
ማቴዎስ 17 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እርሱ እየተናገረ ሳለ፣ ብሩህ ደመና ሸፈናቸው፤ ከደመናውም ውስጥ፣ “#በእርሱ #ደስ #የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ #እርሱን #ስሙት” የሚል #ድምፅ #ተሰማ።
…
⁸ ቀና ብለው ሲመለከቱም #ከኢየሱስ #በስተቀር ሌላ #ማንንም #አላዩም።
በዚህ መጨረሻ ዘመን መነገርም መሰማትም ያለበት የመጨረሻው የእግዚአብሔር መልእክትና መልእክተኛ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።❤🙏🙏