binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

በአዳም ምክኒያት ወደ ህይወታችን የገባው #ኃጢአት በህይወታችን ላይ ዲያቢሎስ ባለ ሙሉ መብትና ገዢነት እንዲኖረው ለዲያቢሎስ Access እንደሰጠው ሁሉ በክርስቶ ኢየሱስ ምክኒያት ወደ ህይወታችን የገባው የእግዚአብሔር #ፅድቅ ለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለእግዚአብሔር ህልውና፥ ለእግዚአብሔር ህይወት Access ሰጥቶታል።

ኃጢአት በኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ላይ ተወግዶ የእግዚአብሔር ፅድቅ በእኛ ላይ ነግሷል🔥❤️


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመለኮት መኖሪያ መቅደሶች ነን።

መለኮት ሰማይ ባለው ክብሩ በሙላት በምድር ለመገለጥ መቅደስ ይፈልጋል🔥🔥🔥

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
— 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥16

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

🚨 #አለም_ላይ ለ2000 አመታት ገደማ #ጣዕማቸው ያልጠፋ እና #ሃይላቸው ያለተለያቸው 10 ስሞች አሉ:: 🚨

1.
#ኢየሱስ 🔥
2.
#ኢየሱስ 🔥
3.
#ኢየሱስ 🔥
4.
#ኢየሱስ 🔥
5.
#ኢየሱስ 🔥
6.
#ኢየሱስ 🔥
7.
#ኢየሱስ 🔥
8.
#ኢየሱስ 🔥
9.
#ኢየሱስ 🔥
10.
#ኢየሱስ🔥

🚨 ስንቶቻችሁ ናችሁ ይህ ስም
#የሚጣፍጣቹ?
🚨 ስንቶቻችሁ ናችሁ ይህን ስም
#የምታፈቅሩት?

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢሳይያስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ።

⁶ ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ።

⁷ አፌንም ዳሰሰበትና፦ እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ አለኝ።

⁸ የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በኢየሱስ ስም ህይወታችሁ እንደመስታወት በኃይልና በጥራት ኢየሱስን በትውልድ ሁሉ ፊት አድምቆና አጥርቶ እንዲያሳይ ፀለይኩላችሁ🔥

ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል።
— ገላትያ 4፥19

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ደግማችሁ ደጋግሞችሁ ይሄን
መዝሙር ስሙት 😭😭
ትርጉም ያለው ሕይወት ለመኖር
7:46 MIN🕟 952 KB💾
━ ━ ━ ━ ━ ━⊱✿⊰━ ━ ━ ━ ━ ━

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ🔥❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የፍጥረት ናፍቅት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ነው።

ለምንድነው ፍጥረት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት የሚጠብቀው?

የእግዚአብሔር ልጆች ሲገለጡ ምን ይፈጠራል?

የእግዚአብሔር ልጅ ነህ/ሽ?
ከእግዚአብሔር በመወለድ የእግዚአብሔርን ዘር ተካፍለሃል/ሻል?
ፍጥረት በናፍቆት እየጠበቃችሁ ነው🔥🔥🔥🔥🔥

መስማት ያለባችሁ ትምህርት እና ፀሎት ነው እየሰማችሁ አብራችሁኝ ተቀጣጠሉ🔥🔥🔥🔥🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
— ሮሜ 8፥19

በዚህ መጨረሻ ዘመን የእግዚአብሔር ልጆች ይገለጣሉ ምክኒያቱም የእግዚአብሔር ክብርና መልክ በሙላት ያለው በእግዚአብሔር ልጆች ውስጥ ስለሆነ 🔥🔥🔥

የዲያቢሎስን መልክ የሚያጠፉ
የኃጢአትን መልክ የሚናጠፉ
የጨለማን መልክ የሚያጠፉ
የእግዚአብሔርን መልክና ክብር በሙላት በምድሪቱ ላይ የሚገልጡ የእግዚአብሔር ልጆች ይገለጣሉ🔥

የእግዚአብሔር ልጆች በእግዚአብሔር መልክና ክብር ሙላት ልክ በብርሃን ሲገለጡ የፍጥረት ነፃነት ይሆናል።

ፍጥረት ከተያዘበት ባርነት ነፃ የሚወጣውና እግዚአብሔርን የሚያመሰግነው የእግዚአብሔር ልጆች በእግዚአብሔር ብርሃን ሲገለጡ ነው።

ማቴዎስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።

¹⁵ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

¹⁶ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።

ጨለማ የሚገፈፈው የእግዚአብሔር ልጆች በብርሃን ሲገለጡ ነው።

የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
— ሮሜ 8፥19


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ስሜቴን ሳይሆን እምነቴን አውጃለሁ🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አሮጌው አዳም በመስቀል ላይ ተሰቅሏል።
አሮጌው አዳም ሞቷል።
አሮጌው አዳም ተቀብሯል።
አሮጌው አዳም ተገድሎ ተወግዷል።

የክርስቶስን ህያውነት መሸከም የሚችለው አዲስ ፍጥረት የሆነው ዳግም ከመንፈስ የተወለደው አዲሱ አዳም ሰማያዊው ሰው በዚህ ስጋ ህያው ሆኖ ይኖራል።

አሁን በዚህ ስጋ ህያው ሆኖ የሚኖረው የመለኮት መቅደስ የሆነው የመለኮትን ዘር የተካፈለው አዲሱ ፍጥረት ነው።

ከክርስቶስ ጋር
#ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ #አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም #በሥጋ #የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር #ልጅ ላይ ባለ #እምነት_የምኖረው ነው።
— ገላትያ 2፥20

ወይስ
#ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? #በዋጋ_ተገዝታችኋልና #ለራሳችሁ_አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20

ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው
#አሁን ደግሞ #በስጋዬ_ይከብራል
  — ፊልጵስዩስ 1፥20


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በልቦና አይኖቻችን እንዴት በመንፈሳዊው ዓለም አጥርተን ማየት እንችላለን??

የልቦና አይኖቻችን ሲበሩ በህይወታችን የሚሆኑ ጠቃሚ ነገሮች...

መስማት ያለባችሁ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ነው አሁን አውርዳችሁ አስሙት🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

“አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።”
— መዝሙር 27፥8

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢሳይያስ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።

⁴ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መዝሙር 40
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።

² ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።


እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
— መዝሙር 105፥4

አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።
— መዝሙር 27፥8

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ብርሃናችሁ የምድሪቱን ጨለማ ሲገፍና ዓለምን ሲሸፍን አያለሁ🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አንተ በፍፁም የስህተት ውጤት አይደለህም።
ምክኒያቱም አምላክህ እግዚአብሔር በፍፁም አይሳሳትም።

#አገልጋይ_ቢና❤

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እመኑኝ እግዚአብሔርን የተራቡ እና እግዚአብሔርን የሚፈልጉ እንደእግዚአብሔር ልጅ የሚገለጡበት ጊዜ እጅግ በጣም ቅርብ ነው🔥🔥🔥

ብቻ ዘይታችሁን ሙሉ
ብርሃናችሁ በኃይል ይብራ እግዚአብሔር በኃይል ሲጠቀምባችሁ አያለሁ🔥🔥🔥

እግዚአብሔር ሚሊዮኖችን በእናንተ ነፃ ሲያወጣ አያለሁ🔥🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የምንጠብቀው ጌታችን ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል😍

ወገባችሁ የታጠቀ 🔥
ዘይታችሁ የሞላ🔥
ብርሃናችሁ የበራ ይሁን🔥

ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
— ሉቃስ 12፥35

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወንጌልን አብረን እንስራ❤️🙏

እባካችሁ ይህንን መልእክት ቢያንስ ለ 10 ሰው ላኩላቸው በጌታ😭😭🙏🙏

የነብሳት መዳን ግድ የሚላችሁ ከሆነ ኢየሱስን የምትወዱ ከሆነ ይህንን መልእክት ለብዙ ሰውች እንድትልኩላቸው በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ😭😭🙏🙏❤️❤️

በአንዲት ነፍስ መዳን በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል እናንተም የዚህ ደስታ ተካፋይ እንድትሆኑ በጌታ በኢየሱስ ለማያምኑ ወገኖቼ አሁን ላኩላቸው❤️


inbox👇👇
@Binajesus

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እንዳትጠራጠሩ...👇👇👇

እግዚአብሔር አብ ልጁን ኢየሱስን በወደደበት
#ልክ ይወደናል🥺😭❤️

አብ አንድያ ልጁን እስከመስጠት ወዶናል❤️😭
ኢየሱሰ ደሞ ነፍሱን እስከመስጠት ወዶናል
😭❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኃጢአት Nature እንደሆነ ሁሉ ጽድቅም Nature ነው።

ኃጢአትን የሆነ ጌዜ አይደለም መስራት የጀመርነው ስንወለድም ኃጢአተኛ ማንነት ይዘን ነው የተወለድነው።

በስጋ ስንወለድ ኃጢአተኛ ማንነትን ይዘን እንደተወለድን ሁሉ በክርስቶስ የማዳን ስራ አምነን ዳግም ስንወለድ የእግዚአብሔር ጽድቅ ማንነታችን ይሆናል።

ኃጢአትን ሰርተን ኃጢአተኛ እንዳልሆንን ሁሉ ጽድቅን ሰርተን ጻድቅ አንባልም።

ኃጢአትም ጽድቅም Nature ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰራልንን ስራ በማመን ዳግም ከመንፈስና ከውሃ ስንወለድ ኃጢአት የማያውቀውና ማንነቱ የእግዚአብሔር ጽድቅ የሆነ አዲስ ፍጥረት ነው የሆነው።

2ኛ ቆሮ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።

… 
²¹ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በኢየሱስ ስም ባረኳችሁ ህይወታችሁ በፀሎት የተሞላ ይሁን🔥🔥🔥

ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥
— ማቴዎስ 21፥13
🔥🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እናንተ...🔥🔥

እናንተ የዓለም
#ብርሃን ናችሁ
እናንተ የምድር
#ጨው ናችሁ
እናን ልትሰወር የማትችል
#በተራራ ላይ ያለች #ከተማ ናችሁ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር መልካም #ብቻ ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

“ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ #እግዚአብሔርን_የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም።”
  — መዝሙር 34፥10

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር በሚያያችሁ እይታ እራሳችሁን ማየት ጀምሩ...

አሁን እግዚአብሔር እናንተን የሚያየው በክርስቶስ እጅግ በጣም የተወደዳችሁና ወጋ የተከፈለላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆናችሁ ነው።

አብ አትረፍርፎ ፍቅሩን ያፈሰሰልን የእርሱ ልጆች እንድንሆን ነው። ስለዚህ አብ ለእኛ ያለው እይታ ልጆቹ ሊያደርገን አትረፍርፎ ባፈሰሰልን ፍቅር ነው። ስለዚህ አብ እኛን በክርስቶስ እንደሚያየን ሁሉ እኛም አብን በክርስቶስ ልጆቹ ሊያደርገን ባፈሰሰልን ፍቅር በክርስቶስ በኩል ልናየው ይገባል።

አብ የእኛ ድካም ወይም ከሳሹ ዲያቢሎስ እንደሚነግረን ሳይሆን በክርስቶስ በኩል እንደተገለጠልን ዘላለማዊ አባትና ፍቅር ብቻ ነው።

1ኛ ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።

² ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።

³ በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ነፍሳችሁ እግዚአብሔርን የምትጠማና የምትራብ ከሆነ መንፈሳዊ ጤንነት ላይ ናችሁ ማለት ነው።

እግዚአብሔር ከእናንተ ጉዳይ እንዳለው አንዱ ምልክት በውስጣችሁ እግዚአብሔርን መራባችሁ እና እግዚአብሔርን መፈለጋችሁ ነው።

ረሃባችሁ በመንፈሳዊ ዓለም ላይ ትልቁ ሀብታችሁ ነው።

የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ እግዚአብሔርን መራብና መጠማት የህይወታችሁ ዋና ነገር ሊሆን ይገባል።

ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር የሚመዘነው ለእግዚአብሔር ባላችሁ መሻትና ረሃብ ነው።

መዝሙር 42
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።
² ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?

መዝሙር 63
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
² ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።

መዝሙር 143
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ ተመለከትሁ።
⁶ እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።

በኢየሱስ ስም እግዚአብሔርን መራባችሁና ፊቱን መፈለጋችሁ በኃይል ይጨምር🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለሆነ በጠላቶቻችሁ አጅ አትወድቁም።

“ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።”
— መዝሙር 129፥2

“ከአንተ ጋር ይዋጋሉ፥ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሡህም፥ ይላል እግዚአብሔር፦”
— ኤርምያስ 1፥19

“ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም።”
— ኤርምያስ 15፥20

“እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ።”
— ኤርምያስ 20፥11

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ለ21 ቀን የሚቆይ የፆምና የፀሎት ጊዜ
ኢየሱስን መገናኘት🔥🔥
Encounter with Jesus🔥🔥

በጌታ የምወዳችሁና የማከብራችሁ ወዳጆቼ ከ21 ቀን በኋላ በክብር እንገናኛለን መልካም ቆይታ ይሁንላችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ ❤️❤️❤️

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
  — 2ኛ ቆሮ 13፥14

Читать полностью…
Subscribe to a channel