መዝሙር 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቃና፥
³³ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።
ልዩ የሆነ እና ከመለኮት ጋር የሚያጣብቅ ፍቅር እንደገና ልባችሁን አሳባችሁንና ነፍሳችሁን በኢየሱስ ስም ይቆጣጠር🔥🔥
...እጅግ #ወዳለችና ብዙው ኀጢአቷ ተሰርዮላታል፤ በትንሹ የተሰረየለት ግን የሚወደው በትንሹ ነው።
— ሉቃስ 7፥47 (አዲሱ መ.ት)
አንተም ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህና በፍጹም ኀይልህ #ውደድ።’
— ማርቆስ 12፥30 (አዲሱ መ.ት)
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
በዙሪያቹ ካለው ጨለማ ይልቅ በውስጣችሁ ያለው ብርሃን ብርቱ ነው።
ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
— ዮሐንስ 1፥5
እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
— ይሁዳ 1፥20
But ye, beloved, building up yourselves on your most holy faith, praying in the Holy Ghost,
— Jude 1:20 (KJV)
በኢየሱስ ስም እባርካችኋለሁ🔥
ለመንፈስ ቅዱስ የተንበረከከ፣ ለመንፈስ ቅዱስ የተማረከ፣ ለመንፈስ ቅዱስ የተሸነፈ፣ ለመንፈስ ቅዱስ የተሰዋ፣ ለመንፈስ ቅዱስ የቀለጠ ልብ ይብዛላችሁ🔥🔥🔥
እንደማርያም ይህንን መዝሙር ስትዘምሩ አያለሁ🔥🔥🔥
ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁶ ማርያምም እንዲህ አለች፦
⁴⁷ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
⁴⁸ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
⁴⁹ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
ይሄ ሬማ የሆነው የመለኮት ቃል በህይወታችሁ ተፈፀመ🔥🔥🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
Part 1
🚨በአምሮ መንፈስ መታደስ💡🔥
እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ ትምህርት ነው ስሙትና ተቀጣጠሉበት🔥🔥🔥
ቀጣዩን ክፍል በቅርቡ እለቃለሁ
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
አይደለም አሁን በተሻለው ኪዳን በአሮጊው ኪዳን ራሱ እግዚአብሔር ልቡ በጣምም ፍቅር ነው።
ወዳጆቼ አባት ለልጁ ልቡ እንደሚናወጥና እንደሚንሰፈሰፍ እግዚአብሔርም ጥልቅ በሆነ በፍቅር ልቡ ይወዳችኋል በክፉ ሊቆጣችሁና ሊቀጣችሁ የሚችልበት ልብ የለውም።
ቢቆጣችሁ እንኳን ቁጣ ውስጥ የማይደበቅ ፍቅሩን ታያላችሁ ወዳጆቼ እግዚአብሔር ለእናንተ ፍቅር እና መልካም አባታችሁ ነው።
ኤፍሬም ሆይ፥ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፥ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አዳማ እጥልሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? #ልቤ_በውስጤ #ተናውጣለች፥ #ምሕረቴም_ተነሣሥታለች።
— ሆሴዕ 11፥8
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ሆሴዕ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ “ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤ #በፍቅር_ቃል_አነጋግራታለሁ።
¹⁵ በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤ የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ። በዚያም ከግብፅ እንደ ወጣችበት ቀን፣ እንደ #ልጅነቷም ጊዜ #ትዘምራለች።
¹⁶ “በዚያ ቀን፣ ‘ባሌ’ ብለሽ፣ ትጠሪኛለሽ” ይላል እግዚአብሔር። “ከእንግዲህም፣ ‘ጌታዬ’ ብለሽ አትጠሪኝም።
ሆሴዕ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ #ለእኔ_እንድትሆኚ #ለዘላለም_አጭሻለሁ፤ #በጽድቅና በፍትሕ፣ #በፍቅርና_በርኅራኄም #አጭሻለሁ።
²⁰ በታማኝነት #አጭሻለሁ፤ አንቺም #እግዚአብሔርን_ታውቂያለሽ።
በእግዚአብሔር ቅናት እቀናላችኋለሁ፤ እናንተን እንደ ንጽሕት ድንግል #ለክርስቶስ ለማቅረብ ለአንድ ባል #አጭቻችኋለሁና።
— 2ኛ ቆሮንቶስ 11፥2 (አዲሱ መ.ት)
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
እኛ በህይወታችን የመንፈስ ቅዱስን መገኘት ከምንፈልገው በላይ መንፈስ ቅዱስ የእኛን መገኘት እጅግ በጣም ይፈልጋል😍😍😍
እሱ እንደ አባት እንደ ጓደኛ እንደ ቅርብ ወዳጅ እንደ ወንድም እንደ ሚስጥረኛ ሊቀርበን ይፈልጋል😍😍
መንፈስ ቅዱስ ይበልጥ ከቀረብነው ሊቀርበን ይፈልጋል ውስጣችን ሆኖ ችላ ካልነው ዝም ካልነው ያዝናል😭😭😭
መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ ነው ድምፃችሁ ናፍቆታል እባካችሁ አታግልሉት ህይወታችሁን ስጡት አታሳዝኑት😭😭😭😭
ውዴ መንፈስ ቅዱስ ሆይ እጅግ በጣም እወድሃለሁ ካንተ ጋር ህብረት ማድረግ ፈልጋለሁ ሁለንተናዬን ሰጥቼሃለሁ በሉት😭😭😭😭
መንፈስ ቅዱስ ልክ አጠገባችሁ እንዳለ ሰው ስብእና ያለው የሚያዝን የሚደሰት የሚረዳ ሁሉን የሚያውቅ እጅግ በጣምም የሚወደድ የሚፈቀር አባትና አምላክ ነው😍😍😍
ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን #ቅዱሱን የእግዚአብሔርን #መንፈስ_አታሳዝኑ።
— ኤፌሶን 4፥30
መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ የሚፈልገው ነገር ቢኖር እናንተንና ከእናንተ ጋር የሚያሳልፈውን የህብረት ጊዜ ብቻ ነው😭😭😭
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
መጥምቁ ዮሐንስ ያጠመቀውና ያስተዋወቀው መጥምቁ ኢየሱስን ነው😍😍🔥🔥
መጥምቁ ዮሐንስ በውሃ ሲያጠምቅ መጥምቁ ኢየሱስ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃል🔥🔥🔥
ኢየሱስ አሁንም በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃል🔥🔥🔥
ተመሳሳይ ከሆነ life system የሚያወጣ ዱናሚስ የሆነው የአምላኬ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያግኛችሁ🔥🔥🔥🔥
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ #ኃይልን_ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
— ሐዋርያት 1፥8
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
የነገሮች ሁሉ ምንጭ መንፈሳዊው ዓለም ነው።
የሚታየው ዓለም ከማይታየው ዓለም ነው የመጣው።
እግዚአብሔር በነገር ሁሉ እንድንባረክ መንፈሳዊ አለማችንን ባርኮታል።
ወዳጄ በመንፈሳዊው ዓለም በሰማያዊው ስፍራ ሁሉ ከተባረክ በፍጥረታዊው ዓለም አለመባረክ አትችልም ምክኒያቱም የፍጥረታዊው ዓለም ምንጭ መንፈሳዊው ዓለም ነው።
እግዚአብሔር በመንፈሳዊው ዓለም እና በሰማያዊው ስፍራ #ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ባርኮሃል።
በመንፈሳዊው ዓለም በሰማያዊው ስፍራ ያልተባረክበት በረከት የለም።
በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
— ኤፌሶን 1፥3
በእምነት #ተባርኬያለው ብለህ በራስህ ላይ አውጅ 🔥🔥🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ጽድቅ/Righteousness
ጽድቅ ማለት የመልካም ስራ ውጤት ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ወክሎ እኛን የእግዚአብሔር ጽድቅ ለማድረግ ሙሉ በሙሉ ሰርቶልን የፈፀመውን ስራ በማመንና በመቀበል በእግዚአብሔር ፊት የመቆም መብትና ብቃት ማግአት ማሐት ነው።
ጽድቅ ማለት በእግዚአብሔር ፊት የመቆም መብትና ብቃት ማግኘት ማለት ነው።
በእግዚአብሔር ፊት በድፍረት የመቆም መብትና ብቃት ያገኘነው በእኛ መልካም ስራ ሳይሆን ኢየሱስ እኛን ወክሎ በሰራው ስራ አምነን ነው። ኢየሱስ የሰራውን የድህነት ስራ አምነን ስንቀበል ኢየሱስ የሰራ ስራ እኛ እንደሰራነው ተደርጎ በእግዚአብሔር አቆጣጠር ይቆጠርልናል።
ጽድቃችን ከእግዚአብሔር አብ የሆነው እግዚአብሔር ወልድ ነው።
በአብ ፊት የመቆም መብትና ህብረት የማድረግ ብቃት ያገኘንበት ጽድቃችን እግዚአብሔር ወልድ ነው።
ጽድቃችንን ያተመው/ያረጋገጠው ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው።
ጽድቃችን ከእግዚአብሔር አብ የሆነው እግዚአብሔር ወልድ ነው።
በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም፦ #እግዚአብሔር_ጽድቃችን ተብሎ ነው።
— ኤርምያስ 33፥16
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
እግዚአብሔር እንድታመሰግኑት ሲፈልግ ምስጋና ርቦት ሳይሆን ህይወታችሁን የድል የከፍታ የተአምራት ሊያደርገው ስለፈለገ ነው።
እግዚአብሔር ምስጋና እየበላ በምስጋና የሚኖር አምላክ አይደለም።
የእግዚአብሔር ስም ያህዌ ያለና የሚኖር ሲሆን የስሙም ትርጉም ያለማንም ረዳት ያለማንም አጋዥ መኖር የሚችል ማለት ነው።
ሰው ለመኖር survive ለማድረግ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ያስፈልጉታል እግዚአብሔር ግን ለመኖር ምንም የማያስፈልገው አምላክ ነውና የእኛ ምስጋና አያኖረውም።
እግዚአብሔር እንድናመሰግነው የሚፈልገው ክብሩን ማዳኑን ኃይሉን እና ስራውን በህይወታችን ሊገልጥ ስለሚፈልግ ነው።
#ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን #ማዳን ለእርሱ #የማሳይበት_መንገድ #ከዚያ አለ።
— መዝሙር 50፥23
የእግዚአብሔር የማዳን ስራ የእግዚአብሔር ክብር በህይወታችሁ የበዛ እንዳሆን ከፈለጋችሁ ህይወታችሁ በምስጋና ይሞላ።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
የዲያቢሎስ ጠላት መሆን የሚቻለው የእግዚአብሔር ወዳጅ/ወገን በመሆን ነው።
ዲያቢሎስን መግዛት/ማሸነፍ የሚቻለው ለእግዚአብሔር በመገዛት/በመሸነፍ ነው።
ዲያቢሎስ ከህይወታችን የሚርቀው እኛ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ ብቻ ነው።
ዲያቢሎስ ከእኛ ሩቅ የሚሆነው እኛ ለእግዚአብሔር ቅርብ ስንሆን ነው።
ያዕቆብ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል።
⁸ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ምወድህ ምክኒያት ኖሮኝ ነው ኢየሱስ😍😍😍
በቃ በነዚህ አራት ቀናት ውስጥ ብሰማው ብሰማው አልጠግብ ያልኩት እጅግ በጣም የባረከኝ መዝሙር ነው ተባረኩበት😭😭❤️❤️❤️
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ያለ መንፈስ ቅዱስ መኖር ትችላላችሁ😳😳
አንተ ደፋር እንዴት በድፍረት ያለ መንፈስ ቅዱስ መኖር ይቻላል ብላችሁ ልትቆጡ ትችላላችሁ ግን መንፈስ ቅዱስ እራሱ እንዲህ ብሎ አስተማረኝ👇👇👇👇
በኃጢአት የተጨማለቀ ህይወት
በተስፋ መቁረጥ የተሞላ ህይወት
ከኢየሱስ ክርስቶስ የራቀ ህይወት
በእግዚአብሔር ቁጣ ስር የሆነ ህይወት
ከሰላም፣ ከደስታ፣ ከሃሴት የራቀ ህይወት
እግዚአብሔርን ከመምሰል የራቀ ህይወት
ከምድር ጋር የተሰፋ ህይወት
ከዲያቢሎስ ጋር ወዳጅ የሆነ ህይወት
በኃይማኖት አጥር ውስጥ ያለ ህይወት
ከፀጋው የራቀ ህይወት
ተራና የተዋረደ ህይወት መኖር ትችላላችሁ ብቻ ሳይሆን መኖር ግዴታችሁ ነው።
ህይወታችሁ የመንፈስ ቅዱስ ብቻ ሲሆን በህይወታችሁ የኢየሱስ ሕይወት ሊገለጥ ግድ እንደ ሆነ ሁሉ ህይወታችሁ ያለ መንፈስ ቅዱስ ከሆነ ከእግዚአብሔር የራቀ እና ለዲያብሎስ ወዳጅ የሆነ ሕይወት ልትኖሩ ግድ ነው።
መንፈስ ቅዱስ እጅግ በጣም እወድሃለሁ ህይወቴ፣ ዘመኔ፣ ፈቃዴ፣ ሁለንተናዬ ያንተ ብቻ ነው ካንተ ጋር ሕብረት ማድረግ እጅግ በጣም እፈልጋለሁ😍😭😍😭😍
“መንፈስን አታጥፉ፤”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥19
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
የኢየሱስ መንፈስ የትንቢት መንፈስ ነው🔥🔥
በህይወታችሁ ላይ ትንቢትን ተናገሩ🔥🔥
ፍጥረት ሁሉ የሚያየው የእግዚአብሔር ክብር በኃይልና በሙላት በህይወቴ ሲገለጥ አያለሁ🔥🔥🔥
ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ከመፅሐፍ ቅዱስ ሁለት ሴቶችን አሳየኝ እና አንድ ነገር አስተማረኝ
የመጀመሪያዋ ሴት በመኃልየ መፅሐፍ ላይ የምናገኛት ሴት ስትሆን ሁለተኛዋ ደግሞ በአዲስ ኪዳን ላይ የምናገኛት መቅደላዊት ማርያም ነች።
መኃልየ. 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፤ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።
³ ቀሚሴን አወለቅሁ፤ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፤ እንዴት አሳድፈዋለሁ?
⁴ ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ።
⁵ ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፤ እጆቼ በደጅ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ።
⁶ ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፤ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም።
ይህቺ ሴት ውዷ በናፍቆት ሊያገኛት በምትኖርበት ቤቷ ድረስ መጥቶ ከፈቺልኝ ብሎ በሯን ሲያንኳኳ እሷ ግን ቀሚሴን አውልቄአለሁ እግሬንም ታጥቤአለሁ የሚል የስንፍና ቃል ታሰማለች የውዷ ድምፅ በተደጋጋሚ ክፈቺልኝ ካንቺ ጋር ላሳልፍ ናፍቀሺኛል አብሬሽ የፍቅርን ጊዜ ማሳለፍ እፈልጋለሁ እያለ በደጇ ይሰማታል እጁንም በበሩ ቀዳዳ ከፍቶ ያሳያታል እርሷም ልቧ ታውኮ ልትከፍትለት ተነሳች ውዷ በጣም ተማፀናት አቆየችው ደጇንም አስጠናችው ተነስታ ውዷን ለማስገባት በሯን ስትከፍት ውዷ ከሰፈር ርቆ ይሄዳል እርሷም ውዷን ለማግኘት እጅግ ብዙ ዋጋ እንደከፈለችና እንደተጎዳች መፅሐፍ ይናገራል።
ሁለተኛዋ ሴት ደግሞ በኢየሱስ ፍቅር የተነደፈችው መቅደላዊት ማርያም ነች።
ሉቃስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ ከፈሪሳውያንም አንድ ከእርሱ ጋር ይበላ ዘንድ ለመነው፤ በፈሪሳዊው ቤትም ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ።
³⁷ እነሆም በዚያች ከተማ ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፤ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደ ተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ አመጣች።
³⁸ በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።
አስተውሉ ይህቺ ሴት እንደ ቀደመቺው ሴት ውዷ ቤቷ መጥቶ ሳይሆን ሰው ቤት ሄዳ ነው ሽቶዉን በእግሩ ላይ ያፈሰሰችው አቧራ ያቆሸሸውን እግሩን በእንባዋ አጥባ ክብሯ በሆነው በፀጉሯ እግሩን ያበሰችው።
የመጀመሪያዋ ሴት ክፈቺልኝ ሲላት እግሬን ስለታጠብኩኝ ከተነሳው እግሬ ይቆሽሻል ስትል መቅደላዊት ማርያም ግን የውዷን እግር በእንባዋ አጥባ በፀጉሯ ጠርጋ አድርቃ ዘይትን ትቀባዋለች።
የመጀመሪያዋ ሴት ውዷ እቤቷ ድረስ ናፍቋት መጥቶ ሊያገኛትና ከእርሷ ጋር ሊያሳልፍ በሯን ከፈቺልኝ ሲላት እርሷ ግን ቀሚሴን አውልቄአለው ስትል መቅደላዊት ማርያም ግን እሷ ቤት መጥቶ ሳይሆን ባልተፈቀደላት በሰው ቤትና በሰው ፕሮግራም ላይ ገብታ የውዷን እግር ትስማለች😭😭😭😭
ወዳጆች ሆይ ኢየሱስን ከወደዳችሁ አይቀር እንደመጀመሪያ መክኒያትን የሚደረድር ፍቅር ሳይሆን እንደ መቅደላዊት ማርያም ሁሉን ነገር የሚያስጥል ክብርን እና ህይወትን የሚያሰዋ ያፍቅር ያግኛችሁ🔥🔥😭😭
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
🚨መንፈሳዊ እድገት🌴🌿
🚨Spiritual Growth🌴🌿
እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
— ዮሐንስ 15፥5
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
የመንፈስ ቅዱስ የቅርብ ወዳጅ ናችሁ ማለት👇👇👇👇👇👇👇👇
እውነተኛ አባት አላችሁ
እውነተኛ እናት አላችሁ
እውነተኛ ወንድም አላችሁ
እውነተኛ እህት አላችሁ
እውነተኛ ጓደኛ አላችሁ
እውነተኛ ወዳጅ አላችሁ
እውነተኛ ሚስጥረኛ አላችሁ
እውነተኛ ረዳት አላችሁ
እውነተኛ አፍቃሪ አላችሁ
እውነተኛ ደጋፊ አላችሁ
እውነተኛ አምላክ አላችሁ
በዛላይ ደሞ ኢየሱስ ለእናንተ የመፅሐፍት ታሪክ ሳይሆን ኢየሱስ አሁን የምትተነፍሱት አይራችሁ ይሆንላችኋል😍😍😍😍
የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅ ስትሆኑ የኢየሱስ አፍቃሪዎች ትሆናላችሁ😭😭😭
የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅ የእግዚአብሔር ዓለም የእናንተ ዓለም ይሆንላችኋል😍😍😍
ኦኦኦ መንፈስ ቅዱስ እጅግ በጣም እወድሃለሁ ካንተም ጋር የማሳልፈውን ጊዜ ሁልጊዜ ናፍቀዋለሁ😭😭😭😭
ዮሐንስ 14 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
¹⁶ እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
¹⁷ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን፣ አብሮአችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
መንፈስ ቅዱስ🔥🔥
ኢየሱስን ይበልጥ ለማወቅ፤ ለመውደድ ብቸኛውና ትልቁ መንገድ መንፈስ ቅዱስን ይበልጥ ወዳጅ ማድረግ ነው🔥
ድንቅ ትምህርት ነው ሰምታችሁ ተቀጣጠሉበት🔥🔥🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨቱን ያቀጣጥለዋል 🔥🔥
እሳቱም ዘወትር_ይነዳል እሳቱም አይጠፋም🔥🔥🔥🔥🔥
ዘሌዋውያን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፥ አይጠፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥልበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ በዚያም የደኅንነትን መሥዋዕት ስብ ያቃጥላል።
¹³ ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም።🔥🔥🔥
ኢየሱስ የሚለውን ስም በመረዳትና በእምነት ስትጠሩት የሆኘ ነገር ይፈጠራል🔥🔥🔥
There is power in the name of Jesus🔥🔥🔥
ከባህር ይዘልቃል ኧኸኸኸ
የፍቅርህ ጥልቀቱ ኦኾኾኾ
በኢየሱስ በኩል ሆነህ
ተገኘህ በየቤቱ😍😭😍😭
አቤት ፍቅርህ (×4)❤️❤️❤️
አቤት ትግስትህ (×4)❤️❤️❤️
#ኢየሱስ❤
እርሱ አዳኛችኝ ነው።
እርሱ ቤዛችን ነው።
እርሱ የኃጢአትን ስርየት ያገኘንበት የእግዚአብሔር በጋችን ነው።
እርሱ ትንሳኤአችን ነው።
እርሱ በኩር ወንድማችን ነው።
እርሱ ሕይወታችን ነው።
እርሱ የህይወት እንጀራችን ነው።
እርሱ የህይወት ውሃችን ነው።
እርሱ እረኛችን ነው።
እርሱ ንጉሳችን ነው።
እርሱ ጌታችን ነው።
እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ጽድቃችን ነው።
እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ሊቀ ካህናችን ነው።
እርሱ አምላካችን ነው።
የምትኖሩት ለሞተላችሁ ነው🔥❤️
በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።
— 2ኛ ቆሮ 5፥15
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
— ገላትያ 2፥20