binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

ስለምታስበው ነገር #አስብ

ወዳጄ አንተ ማለት
#አሳብህ ነህ።

አንተ እንደምታስበው እንደዚያው ነህ።

ትልቅነትን እያሰብክ ነው?? ትልቅነት ህይወትህ ይሆናል።

ትንሽነትን እያሰብክ ነው?? ትንሽነት ህይወትህ ይሆናል።

ማሸነፍን እያሰብክ ነው?? ማሸነፍ የሁልጊዜህ የህይወትህ ስርአት ይሆናል።

መሸነፍን እያሰብክ ነው?? መሸነፍ የሁለሰጊዜ የህይወት ስርአትህ ይሆናል።

ጥላቻን ክፋትን ተንኮልን እያሰብክ ነው?? ጥላቻ፣ ክፋት፣ ተንኮል ህይወትህ ይሆናል።

ፍቅርን አስብ ፍቅር የህይወትህ ስርአት ይሆናል።


ይቅርታን አስብ ይቅርታ የህይወትህ ስርአት ይሆናል።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አገለግልሃለሁ😭😭😭

እንደ ኃይሉ ሥራ እንደ ተሰጠኝም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ስጦታ መጠን የወንጌል አገልጋይ ሆንሁለት።
— ኤፌሶን 3፥7

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በ 2016 በህይወታችሁ እንዲህ ይሆናል🔥🔥💪💪

ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
— ፊልጵስዩስ 4፥13

እናንተ ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ከሚኖረው ከኢየሱስ የተነሳ የማትችሉት አንዲት ነገር የለም።

በክርስቶስ ሁሉን ትችላላችሁ በእምነት አሜንን ስትሉ ሁሉን የሚያስችል የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያግኛችሁ🔥🔥🔥🔥💪💪

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

🌼🌼🌼 2016🌼🌼🌼

1.እግዚአብሔርን የመውደድ አመታችን ነው🔥🔥🔥🔥🔥🔥

እርሱም መልሶ፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥
— ሉቃስ 10፥27

2.ብዙ ሺ ነፍሳትን ለእግዚአብሔር መንግስት የምንማርክበት አመታችን ነው🔥🔥🔥


ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፥ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ።
— ሐዋርያት 4፥4


መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ🌼🌼🌼

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መዝሙር 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቃና፥

³³ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ልዩ የሆነ እና ከመለኮት ጋር የሚያጣብቅ ፍቅር እንደገና ልባችሁን አሳባችሁንና ነፍሳችሁን በኢየሱስ ስም ይቆጣጠር🔥🔥

...እጅግ #ወዳለችና ብዙው ኀጢአቷ ተሰርዮላታል፤ በትንሹ የተሰረየለት ግን የሚወደው በትንሹ ነው።
— ሉቃስ 7፥47 (አዲሱ መ.ት)


አንተም ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህና በፍጹም ኀይልህ #ውደድ።’
— ማርቆስ 12፥30 (አዲሱ መ.ት)


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በዙሪያቹ ካለው ጨለማ ይልቅ በውስጣችሁ ያለው ብርሃን ብርቱ ነው።

ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
— ዮሐንስ 1፥5

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
— ይሁዳ 1፥20

But ye, beloved, building up yourselves on your most holy faith, praying in the Holy Ghost,
— Jude 1:20 (KJV)

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በኢየሱስ ስም እባርካችኋለሁ🔥

ለመንፈስ ቅዱስ የተንበረከከ፣ ለመንፈስ ቅዱስ የተማረከ፣ ለመንፈስ ቅዱስ የተሸነፈ፣ ለመንፈስ ቅዱስ የተሰዋ፣ ለመንፈስ ቅዱስ የቀለጠ ልብ ይብዛላችሁ🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እንደማርያም ይህንን መዝሙር ስትዘምሩ አያለሁ🔥🔥🔥

ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁶ ማርያምም እንዲህ አለች፦

⁴⁷ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤

⁴⁸ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤

⁴⁹ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።


ይሄ ሬማ የሆነው የመለኮት ቃል በህይወታችሁ ተፈፀመ🔥🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

Part 1
🚨በአምሮ መንፈስ መታደስ💡🔥

እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ ትምህርት ነው ስሙትና ተቀጣጠሉበት🔥🔥🔥
ቀጣዩን ክፍል በቅርቡ እለቃለሁ


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አይደለም አሁን በተሻለው ኪዳን በአሮጊው ኪዳን ራሱ እግዚአብሔር ልቡ በጣምም ፍቅር ነው።

ወዳጆቼ አባት ለልጁ ልቡ እንደሚናወጥና እንደሚንሰፈሰፍ እግዚአብሔርም ጥልቅ በሆነ በፍቅር ልቡ ይወዳችኋል በክፉ ሊቆጣችሁና ሊቀጣችሁ የሚችልበት ልብ የለውም።

ቢቆጣችሁ እንኳን ቁጣ ውስጥ የማይደበቅ ፍቅሩን ታያላችሁ ወዳጆቼ እግዚአብሔር ለእናንተ ፍቅር እና መልካም አባታችሁ ነው።

ኤፍሬም ሆይ፥ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፥ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አዳማ እጥልሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ?
#ልቤ_በውስጤ #ተናውጣለች#ምሕረቴም_ተነሣሥታለች
— ሆሴዕ 11፥8


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሆሴዕ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ “ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤
#በፍቅር_ቃል_አነጋግራታለሁ

¹⁵ በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤ የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ። በዚያም ከግብፅ እንደ ወጣችበት ቀን፣ እንደ
#ልጅነቷም ጊዜ #ትዘምራለች

¹⁶ “በዚያ ቀን፣ ‘ባሌ’ ብለሽ፣ ትጠሪኛለሽ” ይላል እግዚአብሔር። “ከእንግዲህም፣ ‘ጌታዬ’ ብለሽ አትጠሪኝም።


ሆሴዕ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹
#ለእኔ_እንድትሆኚ #ለዘላለም_አጭሻለሁ#በጽድቅና በፍትሕ፣ #በፍቅርና_በርኅራኄም #አጭሻለሁ

²⁰ በታማኝነት
#አጭሻለሁ፤ አንቺም #እግዚአብሔርን_ታውቂያለሽ

በእግዚአብሔር ቅናት እቀናላችኋለሁ፤ እናንተን እንደ ንጽሕት ድንግል #ለክርስቶስ ለማቅረብ ለአንድ ባል #አጭቻችኋለሁና
— 2ኛ ቆሮንቶስ 11፥2 (አዲሱ መ.ት)


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እኛ በህይወታችን የመንፈስ ቅዱስን መገኘት ከምንፈልገው በላይ መንፈስ ቅዱስ የእኛን መገኘት እጅግ በጣም ይፈልጋል😍😍😍

እሱ እንደ አባት እንደ ጓደኛ እንደ ቅርብ ወዳጅ እንደ ወንድም እንደ ሚስጥረኛ ሊቀርበን ይፈልጋል😍😍

መንፈስ ቅዱስ ይበልጥ ከቀረብነው ሊቀርበን ይፈልጋል ውስጣችን ሆኖ ችላ ካልነው ዝም ካልነው ያዝናል😭😭😭

መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ ነው ድምፃችሁ ናፍቆታል እባካችሁ አታግልሉት ህይወታችሁን ስጡት አታሳዝኑት😭😭😭😭

ውዴ መንፈስ ቅዱስ ሆይ እጅግ በጣም እወድሃለሁ ካንተ ጋር ህብረት ማድረግ ፈልጋለሁ ሁለንተናዬን ሰጥቼሃለሁ በሉት😭😭😭😭

መንፈስ ቅዱስ ልክ አጠገባችሁ እንዳለ ሰው ስብእና ያለው የሚያዝን የሚደሰት የሚረዳ ሁሉን የሚያውቅ እጅግ በጣምም የሚወደድ የሚፈቀር አባትና አምላክ ነው😍😍😍

ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን
#ቅዱሱን የእግዚአብሔርን #መንፈስ_አታሳዝኑ
— ኤፌሶን 4፥30

መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ የሚፈልገው ነገር ቢኖር እናንተንና ከእናንተ ጋር የሚያሳልፈውን የህብረት ጊዜ ብቻ ነው😭😭😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንፈስ ቅዱስ እጅግ በጣም እወድሃለሁ🔥❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ይህቺ እስትንፋስ በዚህ ስጋ ውስጥ እስካለች ድረስ😭😭😭😭

በማግኘትም በማጣትም
በደስታም በሃዘንም
በመውጣትም በመውረድም
በብርታትም በድካምም
በከተማም በገጠርም
በተራራም በሸለቆም

አገለግልሃለሁ ወደምትልከኝ ቦታ ሁሉ ሄድልሃለሁ አንተን ማገልገል ለኔ ከክብርም የሚበልጥ ክብር ነው😭😭😭😭😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ብዙ ወጣቶች ወንጌልን ከእግዚአብሔር ኃይል ጋር ይዘው በየከተማው ሲገቡ እና ብዙዎችን ነፃ ሲያወጡ ብዙዎችን ሲፈውሱ ብዙዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሲማርኩ እግዚአብሔር በህልሜ አሳይቶኛል ተዘጋጁ🔥🔥🔥

የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ።
— ኢሳይያስ 6፥8

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

2016 የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅ ሆናችሁ የእናንተ መልክ ተደብቆ የኢየሱስ መልክ በእናንተ ላይ ደምቆ በሰዎች ሁሉ ፊት ብርሃናችሁ እየበራ በሰማይ ያለውን አባታችሁን የምታስጠሩበት ድንቅ የክብርና የድል የመከናወንና የፍሬአማ አመታችሁ ነው🔥🔥🔥🔥🔥

በኢየሱስ ስም ይሄ በህይወታችሁ ሆነ🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ለጌታ ያላችሁ ረሃብ እጅግ ትልቁ ሃብታቹ ነው።
መንፈሳዊ ረሃብ አላችሁ ማለት በጌታ ፍቅር ወድቃችኃል ማለት ነው።

ለጌታ ያላችሁን ረሃባ ከሚቀንሱ ነገሮችና ሰዎች ራቁ
ረሃባችሁን ጨምሩ ትልቁ ሃብታችሁ ረሃባችሁ ነውና🔥🔥🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር እንድታመሰግኑት ሲፈልግ ምስጋና ርቦት ሳይሆን ህይወታችሁን የድል የከፍታ የተአምራት ሊያደርገው ስለፈለገ ነው።

እግዚአብሔር ምስጋና እየበላ በምስጋና የሚኖር አምላክ አይደለም።

የእግዚአብሔር ስም ያህዌ ያለና የሚኖር ሲሆን የስሙም ትርጉም ያለማንም ረዳት ያለማንም አጋዥ መኖር የሚችል ማለት ነው።

ሰው ለመኖር survive ለማድረግ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ያስፈልጉታል እግዚአብሔር ግን ለመኖር ምንም የማያስፈልገው አምላክ ነውና የእኛ ምስጋና አያኖረውም።

እግዚአብሔር እንድናመሰግነው የሚፈልገው ክብሩን ማዳኑን ኃይሉን እና ስራውን በህይወታችን ሊገልጥ ስለሚፈልግ ነው።

#ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን #ማዳን ለእርሱ #የማሳይበት_መንገድ #ከዚያ አለ።
— መዝሙር 50፥23

የእግዚአብሔር የማዳን ስራ የእግዚአብሔር ክብር በህይወታችሁ የበዛ እንዳሆን ከፈለጋችሁ ህይወታችሁ በምስጋና ይሞላ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የዲያቢሎስ ጠላት መሆን የሚቻለው የእግዚአብሔር ወዳጅ/ወገን በመሆን ነው።

ዲያቢሎስን መግዛት/ማሸነፍ የሚቻለው ለእግዚአብሔር በመገዛት/በመሸነፍ ነው።

ዲያቢሎስ ከህይወታችን የሚርቀው እኛ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ ብቻ ነው።

ዲያቢሎስ ከእኛ ሩቅ የሚሆነው እኛ ለእግዚአብሔር ቅርብ ስንሆን ነው።

ያዕቆብ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል።

⁸ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ምወድህ ምክኒያት ኖሮኝ ነው ኢየሱስ😍😍😍

በቃ በነዚህ አራት ቀናት ውስጥ ብሰማው ብሰማው አልጠግብ ያልኩት እጅግ በጣም የባረከኝ መዝሙር ነው ተባረኩበት
😭😭❤️❤️❤️

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ያለ መንፈስ ቅዱስ መኖር ትችላላችሁ😳😳

አንተ ደፋር እንዴት በድፍረት ያለ መንፈስ ቅዱስ መኖር ይቻላል ብላችሁ ልትቆጡ ትችላላችሁ ግን መንፈስ ቅዱስ እራሱ እንዲህ ብሎ አስተማረኝ👇👇👇👇

በኃጢአት የተጨማለቀ ህይወት
በተስፋ መቁረጥ የተሞላ ህይወት
ከኢየሱስ ክርስቶስ የራቀ ህይወት
በእግዚአብሔር ቁጣ ስር የሆነ ህይወት
ከሰላም፣ ከደስታ፣ ከሃሴት የራቀ ህይወት
እግዚአብሔርን ከመምሰል የራቀ ህይወት
ከምድር ጋር የተሰፋ ህይወት
ከዲያቢሎስ ጋር ወዳጅ የሆነ ህይወት
በኃይማኖት አጥር ውስጥ ያለ ህይወት
ከፀጋው የራቀ ህይወት
ተራና የተዋረደ ህይወት መኖር ትችላላችሁ ብቻ ሳይሆን መኖር ግዴታችሁ ነው።

ህይወታችሁ የመንፈስ ቅዱስ ብቻ ሲሆን በህይወታችሁ የኢየሱስ ሕይወት ሊገለጥ ግድ እንደ ሆነ ሁሉ ህይወታችሁ ያለ መንፈስ ቅዱስ ከሆነ ከእግዚአብሔር የራቀ እና ለዲያብሎስ ወዳጅ የሆነ ሕይወት ልትኖሩ ግድ ነው።

መንፈስ ቅዱስ እጅግ በጣም እወድሃለሁ ህይወቴ፣ ዘመኔ፣ ፈቃዴ፣ ሁለንተናዬ ያንተ ብቻ ነው ካንተ ጋር ሕብረት ማድረግ እጅግ በጣም እፈልጋለሁ😍😭😍😭😍


“መንፈስን አታጥፉ፤”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥19


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የኢየሱስ መንፈስ የትንቢት መንፈስ ነው🔥🔥

በህይወታችሁ ላይ ትንቢትን ተናገሩ🔥🔥

ፍጥረት ሁሉ የሚያየው የእግዚአብሔር ክብር በኃይልና በሙላት በህይወቴ ሲገለጥ አያለሁ🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር ለብዙዎች ብርሃን ሲያደርጋችሁ አያለሁ🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ከመፅሐፍ ቅዱስ ሁለት ሴቶችን አሳየኝ እና አንድ ነገር አስተማረኝ

የመጀመሪያዋ ሴት በመኃልየ መፅሐፍ ላይ የምናገኛት ሴት ስትሆን ሁለተኛዋ ደግሞ በአዲስ ኪዳን ላይ የምናገኛት መቅደላዊት ማርያም ነች።

መኃልየ. 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፤ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።

³ ቀሚሴን አወለቅሁ፤ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፤ እንዴት አሳድፈዋለሁ?

⁴ ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ።

⁵ ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፤ እጆቼ በደጅ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ።

⁶ ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፤ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም።

ይህቺ ሴት ውዷ በናፍቆት ሊያገኛት በምትኖርበት ቤቷ ድረስ መጥቶ ከፈቺልኝ ብሎ በሯን ሲያንኳኳ እሷ ግን ቀሚሴን አውልቄአለሁ እግሬንም ታጥቤአለሁ የሚል የስንፍና ቃል ታሰማለች የውዷ ድምፅ በተደጋጋሚ ክፈቺልኝ ካንቺ ጋር ላሳልፍ ናፍቀሺኛል አብሬሽ የፍቅርን ጊዜ ማሳለፍ እፈልጋለሁ እያለ በደጇ ይሰማታል እጁንም በበሩ ቀዳዳ ከፍቶ ያሳያታል እርሷም ልቧ ታውኮ ልትከፍትለት ተነሳች ውዷ በጣም ተማፀናት አቆየችው ደጇንም አስጠናችው ተነስታ ውዷን ለማስገባት በሯን ስትከፍት ውዷ ከሰፈር ርቆ ይሄዳል እርሷም ውዷን ለማግኘት እጅግ ብዙ ዋጋ እንደከፈለችና እንደተጎዳች መፅሐፍ ይናገራል።

ሁለተኛዋ ሴት ደግሞ በኢየሱስ ፍቅር የተነደፈችው መቅደላዊት ማርያም ነች።

ሉቃስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ ከፈሪሳውያንም አንድ ከእርሱ ጋር ይበላ ዘንድ ለመነው፤ በፈሪሳዊው ቤትም ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ።

³⁷ እነሆም በዚያች ከተማ ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፤ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደ ተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ አመጣች።

³⁸ በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።

አስተውሉ ይህቺ ሴት እንደ ቀደመቺው ሴት ውዷ ቤቷ መጥቶ ሳይሆን ሰው ቤት ሄዳ ነው ሽቶዉን በእግሩ ላይ ያፈሰሰችው አቧራ ያቆሸሸውን እግሩን በእንባዋ አጥባ ክብሯ በሆነው በፀጉሯ እግሩን ያበሰችው።

የመጀመሪያዋ ሴት ክፈቺልኝ ሲላት እግሬን ስለታጠብኩኝ ከተነሳው እግሬ ይቆሽሻል ስትል መቅደላዊት ማርያም ግን የውዷን እግር በእንባዋ አጥባ በፀጉሯ ጠርጋ አድርቃ ዘይትን ትቀባዋለች።

የመጀመሪያዋ ሴት ውዷ እቤቷ ድረስ ናፍቋት መጥቶ ሊያገኛትና ከእርሷ ጋር ሊያሳልፍ በሯን ከፈቺልኝ ሲላት እርሷ ግን ቀሚሴን አውልቄአለው ስትል መቅደላዊት ማርያም ግን እሷ ቤት መጥቶ ሳይሆን ባልተፈቀደላት በሰው ቤትና በሰው ፕሮግራም ላይ ገብታ የውዷን እግር ትስማለች😭😭😭😭

ወዳጆች ሆይ ኢየሱስን ከወደዳችሁ አይቀር እንደመጀመሪያ መክኒያትን የሚደረድር ፍቅር ሳይሆን እንደ መቅደላዊት ማርያም ሁሉን ነገር የሚያስጥል ክብርን እና ህይወትን የሚያሰዋ ያፍቅር ያግኛችሁ🔥🔥😭😭


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

🚨መንፈሳዊ እድገት🌴🌿
🚨Spiritual Growth🌴🌿

እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
— ዮሐንስ 15፥5


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመንፈስ ቅዱስ የቅርብ ወዳጅ ናችሁ ማለት👇👇👇👇👇👇👇👇

እውነተኛ አባት አላችሁ
እውነተኛ እናት አላችሁ
እውነተኛ ወንድም አላችሁ
እውነተኛ እህት አላችሁ
እውነተኛ ጓደኛ አላችሁ
እውነተኛ ወዳጅ አላችሁ
እውነተኛ ሚስጥረኛ አላችሁ
እውነተኛ ረዳት አላችሁ
እውነተኛ አፍቃሪ አላችሁ
እውነተኛ ደጋፊ አላችሁ
እውነተኛ አምላክ አላችሁ
በዛላይ ደሞ ኢየሱስ ለእናንተ የመፅሐፍት ታሪክ ሳይሆን ኢየሱስ አሁን የምትተነፍሱት አይራችሁ ይሆንላችኋል😍😍😍😍
የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅ ስትሆኑ የኢየሱስ አፍቃሪዎች ትሆናላችሁ😭😭😭
የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅ የእግዚአብሔር ዓለም የእናንተ ዓለም ይሆንላችኋል😍😍😍


ኦኦኦ መንፈስ ቅዱስ እጅግ በጣም እወድሃለሁ ካንተም ጋር የማሳልፈውን ጊዜ ሁልጊዜ ናፍቀዋለሁ😭😭😭😭

ዮሐንስ 14 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
¹⁶ እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤

¹⁷ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን፣ አብሮአችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንፈስ ቅዱስ🔥🔥

ኢየሱስን ይበልጥ ለማወቅ፤ ለመውደድ ብቸኛውና ትልቁ መንገድ መንፈስ ቅዱስን ይበልጥ ወዳጅ ማድረግ ነው🔥

ድንቅ ትምህርት ነው ሰምታችሁ ተቀጣጠሉበት🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨቱን ያቀጣጥለዋል 🔥🔥
እሳቱም ዘወትር_ይነዳል እሳቱም አይጠፋም🔥🔥🔥🔥🔥

ዘሌዋውያን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፥ አይጠፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥልበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ በዚያም የደኅንነትን መሥዋዕት ስብ ያቃጥላል።

¹³ ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም።
🔥🔥🔥

Читать полностью…
Subscribe to a channel