binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

በኢየሱስ ስም ባረኳችሁ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት በውስጣችሁ በዙሪያችሁ በኃይል ይለቀቅላችሁ🔥🔥🔥

መንፈስም በፊቴ አለፈ የሥጋዬ ጠጕር ቆመ።
— ኢዮብ 4፥15

መንፈስ ሽው ብሎ በፊቴ አለፈ፤ የገላዬም ጠጒር ቆመ።
— ኢዮብ 4፥15 (አዲሱ መ.ት)


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንፈስ ቅዱስ እሳት አይደለም ግን ያቀጣጥላል🔥🔥🔥🔥

መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ መቀጣጠል ሲጀምር ሁለት ነገር በህይወታችሁ እየሆኑ ነው🔥🔥🔥

አንደኛው ከእናንተ ላይ ያልተገባውን የሕይወት ስርአት ያቀቃጥለዋል ያስወግደዋል🔥🔥🔥🔥

ሁለተኛው ደግሞ እናንተን  ያጠራችኋል ያበስላችኋል🔥🔥🔥🔥

ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤
#በመንፈስ #የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤🔥🔥🔥
  — ሮሜ 12፥11

እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበረ፥ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ
#በመንፈስ_ሲቃጠል ስለ #ኢየሱስ ይናገርና #በትክክል #ያስተምር ነበር።🔥🔥🔥🔥
  — ሐዋርያት 18፥25


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

😭😭😭😭😭😭😭👇👇👇👇

ዮሐንስ 19
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
²⁸ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፦
#ተጠማሁ አለ።

²⁹ በዚያም
#ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም #ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ #አቀረቡለት።

³⁰ ኢየሱስም
#ሆምጣጤውን_ከተቀበለ በኋላ፦ #ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።

ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና የሕይወትን ውሃ ይጠጣ ያለው የሕይወት ውሃ የሆነው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ተጠማሁኝ አለ።😭😭😭

ተጠማሁኝ ያለው እራሱ የሕይወት ውሃ የሆነው ኢየሱስ ነው😭😭😭

የሰውነቱን ቆዳና ስጋ ቦጭቆ በሚነሳው ጫፍ ጫፉ ላይ ረጃጅም የሆኑ አጥንቶ ያሉበት ጅራፍ በከባድ ጭካኔ የኔ ውድ ኢየሱስ ስለተገረፈ ውስጡ ምንም ደም አልቀረም ነበር ከዛ የተነሳ የሕይወት ውሃ የሆነው ኢየሱስ ተጠማሁኝ አለ😭😭😭😭😭😭

እኔን ለማርካት እሱ ተጠማ😭😭😭

ታዲያ ኢየሱስ በዚህ በከባድ ጥም ውስጥ ሆኖ ተጠማሁኝ ሲል ያቀረቡለት ቀዝቃዛ ውሃ ሳይሆን መራራ ሆምጣጤን ነው😭😭😭😭

እኔን ከመንፈስ ቅዱስ የሕይወትን ውሃ ጠጥቼ እንድረካ እና እንድለመልም እሱ ተጠማሁኝ ሲል መራራ ሆምጣጤን ጠጣ😭😭😭😭


ምወድህ ምክኒያት ኖሮኝ ነው ኢየሱሴ😍😭❤️

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በለገጣፎ ከተማ በአንድ ለአንድ እና በ ጀማ ወንጌል ስርጭት ስለ ኃጢአተኞች በመስቀል ላይ የተሰቀለውን በመንፈስ ቅዱስ እእዳታ ሰብከነዋል ብዙዎችም ወንጌልን ሰምተዋል ነፍሳትም ወደእግዚአብሔር መንግስት ተጨምረዋል ክብር ሁሉ በኢየሱስ ለአብ ይሁን🔥🔥🔥🔥

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥23


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በዚህ ቻናል እየተባረካችሁና እየተቀጣጠላችሁ ያላችሁ ወዳጆቼ ዛሬ ወደ እናንተ አንድ የምስራች ይዤላችሁ መጥቻለሁ😍🔥

እሱም በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ምሽት ከ 4 ሰአት ጀምሮ አብረን የእግዚአብሔርን ቃል የምንካፈልበት አብረን ጌታን የምናመልክበትና አብረን በመንፈስ ቅዱስ የምንቀጣጠልበትን ፕሮግራም እንዳደርግ ጌታ ተናግሮኛል
ስለዚህ ዘውትር እሁድ ምሽት ከ 4 ሰአት ጀምሮ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ድንቅ ምሽት ስለሚኖረን ሁላችሁም ከእኛ ጋር አብራችሁ እንድትፀልዩ እና ለወዳጆቻችሁ ይህንን ማስታወቃያ እንድትልኩላቸውና ልጆችን እንድትጋብዙ በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለሁ❤️❤️🔥

እንዳትጠራጠሩ በሚቀጥሉት ዘመናት የሚገለጠው የእግዚአብሔር ክብር በእናንተ ነው።

የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
— ሮሜ 8፥19


ፕሮግራሙን የምንጀምረው እሁድ ጥቅምት 11 ነው አብረን የክብር ምሽት እናሳልፋለን🔥❤️

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሞያተኛ እረኛ ሳይሆን ነፍሱን አስይዞ ነፍሳችሁን የሚጠብቅ እረኛ ኢየሱስ አላችሁ❤️

መዝሙር 23
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
² በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
³ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
⁴ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
⁵ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
⁶ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።


ዮሐንስ 10
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹¹ መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።

…
¹⁴-¹⁵ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እቅፍ ድግፍ እቅፍ በቃሉ ድግፍ😭😭
ዘማሪት አዜብ ኃይሉ
በጣም ያበረታኝ ዝማሬ ነው ተባረኩበት❤️


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ መስቀሉን ሲያይ ውርደት ሳይሆን ክብር ነበር የሚታየው።

ኢየሱስ ጫፍ ጫፉ ላይ አጥንት በታሰረበትን ዘግናኝ ጅራፍ ሊገርፉት ሲያይ ጀርባው መገሽለጡን፣ ስቃዩንና መከራውን ሳይሆን የሰው ልጆችን ከእግዚአብሔር የለየውን ኃጢአት ሊቀጣና ሊገረፍ፣ ሊወገድ መሆኑን ነው የሚያየው።

ኢየሱስ መስቀሉን ሲያይ መከራና ስቃዩን ሳይሆን የሚያየው በመስቀሉ ላይ ምጥ የሚወለዱትን የእግዚአብሔርን ልጆች ነው የሚያየው።

ኢየሱስ መቃብሩን ሲያይ መበስበሱን ሳይሆን በትንሳኤ መንፈስ እልፍ የሆኑ የትንሳኤ ልጆችን ነው የሚያየው።


ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
— ኢሳይያስ 53፥11


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ #የጮኸበትን ጉዳይ ዝም አልልም እኔም አፌን ከፍቼ #እጮሃለሁ🗣🗣🗣

ዮሐንስ 12
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁴⁴
#ኢየሱስም_ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤

⁴⁵ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።

⁴⁶ በእኔ
#የሚያምን ሁሉ #በጨለማ_እንዳይኖር #እኔ_ብርሃን #ሆኜ ወደ #ዓለም_መጥቻለሁ።

⁴⁷ ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና
...

ኢየሱስ ጨለማውን የምታሸንፉበት የሐይወታችሁ ብርሃን ነው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እንደ ድመት ሆነህ ገብተህ እንደ አንበሳ ሆነህ የምትወጣበት ብቸኛው ስፍራ የፀጋው ዙፋን ነው።
 
ቢደክምህም ወደ ፀጋው ዙፋን በእምነት ግባ  ስትወጣ ከነ ድካምህ አትወጣም እንደ ሌላ ሰው፣ ብርቱ ሰው፣ ሃያል ሰው፣ ሆነህ ትወጣለህ ምክኒያቱም የገባኸው ሚያስፈልግህን አቅምና ጉልበት ልትቀበል ወደምትችለው ፀጋ ዙፋን ፊት ነው የገባኸው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔርን በፍፁም ልባችሁ እመኑት ተደገፉትም የእናንተ እያንዳንዱ ነገር በእጁ ላይ ነው።

“እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፥ እግርህም እንዳይጠመድ ይጠብቅሃልና።”
— ምሳሌ 3፥26

ኤርምያስ 17
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁷ በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።

⁸ በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አብን አባ ያልኩት ስሙ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን በቀራንዮ መስቀል ላይ በከባድ ምጥ አምጦ ወልዶኝ ልጁ ሆኜ ነው።

አብን አባ ያልኩት ስሙ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ዳግም ወልዶኝ የልጅነትን መንፈስ በውስጤ አፍስሶልኝ ነው።


አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ...
— ሮሜ 8፥15


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ የሚጠባበቁትን እንደ ዶሮ ሳይሆን እንደ ንስር ነው የሚያያቸው።

ንስር መንገዱ ሰማይ መኖሪያውም በተራራ ላይ ነው።

“የንስር መንገድ በሰማይ፣...”
— ምሳሌ 30፥19 (አዲሱ መ.ት)

ንስር ከሌሎች አእዋፍ ለየት የሚያደርገው ከብዙ ሺ ርቀት አጥርቶ ማየት የሚችል ድንቅ ፍጥረት ነው።

ንስር የሞተና የሸተተ ምግብ አይመገብም የንስር ምግብ ትኩስ (fresh) ነው።

ንስር 40 አመት ከሞላው በኋላ ሰውነቱን በማደስ ለሁለተኛ ጊዜ መኖር የሚችል ድንቅ አእዋፍ ነው።

ንስር 40 አመት ከኖረ በኋላ ያረጃል መንቁሩ አድጎ ስለሚጣመም ምግብ መመገብ አይችልም የእግሮቹ ጥፍሮች መጣመም ስለሚጀምሩ የሚፈልገውን ነገር ማንሳት አይችልም የሚበርባቸው ላባዎቹም ስለሚያረጁ መብረር ይከብደዋል ስለዚህ ንስር ሁለት ምርጫ አለው ወይ መሞት ወይ ደግሞ ራሱን በማደስ ቀጣዩን ሰለሳ አመት መኖር።

ንስር ራሱን ለማደስ የሚያደርገው ነገር ወደተራራ በመወጣት ከአለት ጋር በመጋጨት መንቁሩን ጥፍሩንና ላባዎቹን መነቃቀል ይጀምራል።

ንስር አይኖቹ የበለጠ አጥርተው እንዲያዩ ፀሃይዋን ለረጅም ሰአት ይመለከታል።

ንስር እራሱን ለማደስ 150 ቀናት ይወስድበታል።

ከ150 ቀናት በኃላ ንስር በአዲስ ኃይል እና በአዲስ ማንነት ድጋሚ ለ30 ዓመት መኖር ይችላል።

እግዚአብሔር ለዚህ ነው እግዚአብሔርን በተስፋ የሚጠባበቁትን እንደ ንስር የሚመስላቸው።


“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
— ኢሳይያስ 40፥31


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር እንዲህ አለ ደካማው ብርቱ ነኝ ይበል አለ🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አብና ወልድ የተሳሰሩበት እና አንድ የሆኑበት ገመድ #ፍቅር ይባላል።

“አብ ወልድን ይወዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል።”
— ዮሐንስ 3፥35 (አዲሱ መ.ት)


አብ እኛን ለማዳን የተጠቀመውና ያስከፈለው የፍቅር መጠን ከልጁ ጋር ከተሳሰረበት ፍቅር ፈፅሞ አያንስም።

እግዚአብሔር እኛን የወደደበት የፍቅረ መጠን ልጁን ኢየሱስን በወደደበት መጠን ነው የወደደን እንዴት ካላችሁኝ አብ ሰዎችን የወደደበት ፍቅር ኢየሱስን ያክላል። አብ ከኢየሱስ አስበልጦ የሚወደው ነገር የለውም።

አብ የሰው ልጆችን ከኃጢአት ለማዳን ያስከፈለው ዋጋ ፍቅር ነው ያ ዋጋ ኢየሱስ ይባላል።

ለዚህ ነው አብ ኢየሱስን በወደደበት ልክ ይወደኛል የምለው።


“ይህም እኔ በእነርሱ፣ አንተም በእኔ መሆንህ ነው። አንተ እንደ ላክኸኝና እኔን በወደድኸኝ መጠን እነርሱንም እንደ ወደድሃቸው ዓለም ያውቅ ዘንድ፣ አንድነታቸው ፍጹም ይሁን።”
— ዮሐንስ 17፥23 (አዲሱ መ.ት
)

እግዚአብሔር አባቴ ሊቀንስ በማይችል ፍቅር ወዶኛል እንደዚህ የወደደኝ ከእኔ ሁኔታ ተነስቶ ሳይሆን እሱ ማንነቱ ፍቅር ስለሆነ ነው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመንፈስ ቅዱስ እሳት ሕይወታችሁን በኃይል ሞላው🔥🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር ፈልጉኝ ሲል ድብብቆሽ እንጫወት እያለ ሳይሆን እሱን በመፈለገግ ውስጥ የእርሱን ሕይወት ስለምንካፈል ነው።

እግዚአብሔርም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤
— አሞጽ 5፥4

ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም።
— መዝሙር 34፥10


ልባችሁና አሳባችሁ እግዚአብሔርን በመፈለግና በመራብ በኢየሱስ ስም ይሞላ🔥🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ውሸት 1000 ዓመት ቢቆይም ውሸት ነው።

ውሸት ብዙ እድሜ ስላስቆጠረ እውነት አይሆንም።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እረኛዬ ነህ
ግርማ በለጠ
ሰሞኑን በጣም የባረከኝ መዝሙር😍😍

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ነፍሴ ከእረኛዬ ጋር ጥልቅ ፍቅር ይዟታል😭😭😭

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።”
— ዮሐንስ 10፥14-15


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዲያቢሎስ ወደ አሳባችሁ ከሚወረውረው የውሸት እውቀት እራሳችሁን ልትከላከሉበት የምትችሉት የእውነት እውቀት በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ጋሻ ነው።

የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ #የእግዚአብሔር_ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ (በቃሉ) #ለሚታመኑት ሁሉ #ጋሻ ነው።
— መዝሙር 18፥30

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
— 2ኛ ቆሮ 5፥17

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ክርስትና ያለ Encountere በጣም አሰልቺ ነው።

የመፅሐፍ ቅዱሱ ያሕዌ የሚዳሰስ የሚጨበት የሚገለጥ የሚታወቅ አምላክ ነው።

በሕይወቱ እንደቀድሞ ህይወቱ ሊኖር የማይችል ብቸኛ ሰው ከመለኮት ጋር Encountere ያለው ሰው ነው።

በሕይወቱ ተመሳሳይ የሆነ ሕይወት ሊኖር የማይችል ሰው ከመለኮት ጋር Encountere ያለው ሰው ነው።

ጳውሎስ ሳኦል ሆኖ መቀጠል ያቃተው ከመለኮት ጋር Encountere አግኝቶት ነው።

ከመለኮት ጋር ያላችሁ አንድ Encountere ሕይወታችሁን Forever ይቀይረዋል🔥🔥🔥

መለኮትን እስክትነኩት፣ እስክትዳስሱት፣ እስክትጨብጡትና እስክታዩት ድረስ ፀልዩ🔥🔥🔥


ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥1


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መልህቄ😍😭😍😭

ኸረ ይሄ መዝሙር ግን ኡኡ😍😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ።
  — ኢሳይያስ 2፥5

የእግዚአብሔር ብርሃን የእግዚአብሔር እውቀት ነው።


ከፊታችሁ ያለውን መንገድ በእግዚአብሔር እውቀት ከሄዳችሁት እያንዳንዱን ፌርማታ እንዴት ማለፍ እንዳለባችሁ መለኮታዊ እውቀት ይኖራቹሃል።

ሁላችንም በእግብሔር የተሰመረልን የህይወት መንገድ አለን ከፊታችን ያለውን የህይወታችንን መንገድ በእግዚአብሔር እውቀት ከሄድነው ሌሎች የዛሉበትና የደከሙበት ያው መንገድ እኛን አያደክመንም አያዝለንም።

ከፊታችን ያለው የህይወት መንገድ በእግዚአብሔር እውቀት ከሄድነው ሌሎችን በእንቅፋት እየመታና እያቆሰለ ተስፋ ያስቆረጠ፤ ከመንገድ ውጪ ያደረገ እኛን ግን አይጎዳንም እንዴት መራመድ እንዳለብን በየትኛው ቀያስ ላይ መታጠፍ እንዳለብን የትኛው ፌርማታ ላይ ማረፍ እንዳለብን እናውቃለን ምክኒያቱም እየሄድን ያለነው በራሳችን ብርሃን (እውቀት) ሳይሆን በመለኮት ብርሃን ወይም እውቀት ስለሆነ ነው።

ከፊታችን ያለውን የህይወታችንን መንገደና ጉዞ የስኬታማ፣ የድል፣ የበረከት፣ ያመከናወን፣ የፍሬአማነትና፣ እግዚአብሔር የሚከብርበት፣ የህይወት ጉዞ እንዲሆንልን በራሳችን ብርሃን ወይም እውቀት ሳይሆን በእግዚአብሔር እውቀትና፣ ብርሃን መሄድ ይኖርብናል።


በእግዚአብሔር እውቀት ወይም ብርሃን መሄድ ማለት መንገዱን እግዚአብሔር በሚያውቀው እውቀት መራመድ ማለት ነው እያንዳንዱን እርምጃችንን በእግዚአብሔር እውቀት ከተራመድን እያንዳንዱ እርምጃችን ከክብር ወደ ክብር ከኃይል ወደ ኃይል ከእምነት ወደ እምነት እየሆነ የተፅእኖ ፈጣሪ መንገድና የፍሬአማ መንገድ ይሆንልናል።

መንገዳችንን በእግዚአብሔር እውቀት እንጓዘው🔥

“እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ።”
  — ኢሳይያስ 2፥5


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

.|| - ሰላም ደስታ
ደሙ😭😭❤️❤️
ይሄ መዝሙር ጌታን ነው የምላችሁ ከባድ ሃይል አለበት😭😭😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ቆላስይስ 2
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁴ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤

¹⁵ አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እነሱ አምላክ እንደሆነ በመረጃ ያውቁታል እኔ ደሞ አምላክ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን አባቴ እንደሆነ በመገለጥ አውቄዋለሁ።

“...የሚያከብረኝ #እናንተ_አምላካችን የምትሉት #አባቴ ነው፤”
— ዮሐንስ 8፥54

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የተካፈልነው የመለኮት ሕይወት እኛን ለውጦን እኛው ጋር የሚቆም ሕይወት ሳይሆን ከእኛ አልፎ ወደ ሌሎች የሚፈስ እና የሚትረፈረፍ ሕይወት ነው🔥🔥🔥🔥

“...እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።”
— ዮሐንስ 10፥10 (አዲሱ መ.ት)


ይሕንን ፀሎት በእምነት ይፀልዩ🔥👇

እኔ የእግዚአብሔር ሕይወት አለኝ፤ የእግዚአብሔር የሕይወት ስርአት በእኔ ይገለጣል፤ የተካፈልኩት ሕይወት ጽድቅ፣ ቅድስና፣ ደስታ፣ ሰላም፣ በረከት፣ ሞገስ፣ ድል፣ አሸናፊነት ነው ይህ ሕይወት በእኔ በሙላት ይገለጣል በኢየሱስ ስም አሜንን🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ያሕዌ: ለመኖር ምንም የማያስፈልገው😭😭😭😭😭

በጣምምም የተነካሁበት ቃል ነው አሁን ስሙት በጌታ😭😭😭😭


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…
Subscribe to a channel