ኢየሱስ መስቀሉን ሲያይ ውርደት ሳይሆን ክብር ነበር የሚታየው።
ኢየሱስ ጫፍ ጫፉ ላይ አጥንት በታሰረበት ዘግናኝ ጅራፍ ሊገርፉት ሲያይ ጀርባው መገሽለጡን፣ ስቃዩንና መከራውን ሳይሆን የሰው ልጆችን ከእግዚአብሔር የለየውን ኃጢአት ሊቀጣና ሊገረፍ፣ ሊወገድ መሆኑን ነው የሚያየው።
ኢየሱስ መስቀሉን ሲያይ መከራና ስቃዩን ሳይሆን የሚያየው በመስቀሉ ላይ ምጥ የሚወለዱትን የእግዚአብሔርን ልጆች ነው የሚያየው።
ኢየሱስ መቃብሩን ሲያይ መበስበሱን ሳይሆን በትንሳኤ መንፈስ እልፍ የሆኑ የትንሳኤ ልጆችን ነው የሚያየው።
ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
— ኢሳይያስ 53፥11
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
📖We proclaim God's knowledge with the idea of WHO WAS BORN and WHY WAS HE BORN!✝️
The challenges has three hash tags, lists;
#10_Days_Challenge
#THE_GOD_OF_HEAVEN_ON_EARTH
#Title_Of_The_Day
You Are Invited To Join The Challenge👍
Hosted BY:- Addis Ababa University Christian Fellowships (EiABC, 6Kilo, 5Kilo, 4 Kilo, Sefere Selam and Tikur Anbesa campuses)!!
መዝሙር 89
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፥ ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት።
²¹ እጄም ትረዳዋለች፥ ክንዴም ታጸናዋለች።
²² ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም፥ የዓመፃ ልጅም መከራ አይጨምርበትም።
²³ ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ፥ የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ።
²⁴ እውነቴና ምሕረቴም ከእርሱ ጋር ነው፥ በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ኃጢአት ነፍስን የሚገድል መርዝ (Poison) ነው መድኃኒቱ ደግሞ የኢየሱስ ደም ብቻ ነው።
በኃጢአት የተመረዘች ነፍስ በአፋጣኝ መድኃኒቱን ካልወሰደች ክፉኛ ሞትን ትሞታለች ያውም የዘለአለምን ሞት።
በኃጢአት በሽታ የምትሰቃዩ በአፋጣኝ ይህንን መድሃኒት የኢየሱስን ደም በመውሰድ ፈውሳችሁን ተቀበሉ።
ይህ መድሃኒት በገንዘብ አይገዛም አይሸጥምም በእምነት ብቻ የምትቀበሉት ነፃ ስጦታ ነው።
“...የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።”
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥7
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
እግዚአብሔር በሕይወታችን ይበልጥ እንዲገባና እንዲቆጣጠረን Access የሚሰጠው አምልኮ ወይም Worship ይባላል ለዛም ነው አብዝተን እንድናመልከው የሚፈልገው።
ከእግዚአብሔር ጋር አንድ መንፈስ የምንሆነው በአምልኮ ነፍሳችንን በፊቱ ስናፈስ ነው።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
#ኢየሱስ ሲወራ አልቅስ አልቅስ ሳቅ ሳቅ ዝለል ዝለል የማይልህና ውስጥህ ላይ ምንም ስሜት እየልተሰማህ ካልሆነ አጥብቀህ ፀልይ የሆነ መጋረጃ አይኖችህን ጋርዶታል።
ኢየሱስ🔥❤️
ምሳሌ 3 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ጥበብን የሚያገኛት፣ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው ቡሩክ ነው፤
¹⁴ እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና።
¹⁵ ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤ አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።
¹⁶ በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።
¹⁷ መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
¹⁸ ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤ የሚይዟትም ይባረካሉ።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ኢየሱስን የገፋና የናቀ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።
ኢየሱስን በሕይወታችሁ ላይ እንደ ጌታ እና እንደ አዳኝ አድርጋችሁ ያልተቀበላችሁ ዛሬ ነገ ሳትሉ ቶሉ ወደ ሕይወታችሁ አስገቡት ከኢየሱስ ውጪ ሌላ ተስፋ የላችሁም ኢየሱስ ይወዳችኋል።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
1ኛ ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።
² ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ካህኔ ሊቀ ካህኔ ኢየሱስ ሊቀ ካህኔ
በእኔና አብ መሃል ያለኸው ወገኔ(×2)
እንደ አሮን ልጆች ሞት አይገድብህም
እንደ ሌዋውያን ነውር የለብህም
የማይለዘጥ ነው ፍፁም ክህነትህ
በመሃላ የፀና ነውና ሹመትህ❤️❤️
ቤዛዬ ቤዛዬ ኢየሱስ ቤዛዬ
ለነፍሴ የወጣ የጽድቅ ፀሃዬ(×2)
ልሙትልህ ብሎ ማን ለኔ ቀደመ
ከኢየሱስ በቀር ማን ለኔ ታመመ
አላውቅም አይኖርም የለም ሌላ ቤዛ
ጠላቱን በዋጋ ደም ከፍሎ የገዛ ❤️❤️
አዳኜ አዳኜ ኢየሱስ አዳኜ
የሞት መድሃኒቴ የሕይወት እልፍኜ(2×)
የዚያ ክፉ እባብ የመርዙ ማርከሻ
የጠጣሁት መጠጥ ፍቱን መፈወሻ
በመገረፍ ቁስል በጀርባ ላይ ሰንበር
አንዴ ተሰበረ የኃጢአቴ ቀንበር ❤❤
አለቴ አለቴ ኢየሱስ አለቴ
የተተከልኩብህ ጽኑ መሰረቴ (2×)
የሕያው አምላክ ልጅ ማለት አይደክመኝም
ይህንን ስጋና ደም አልገለጠልኝም
በዚህ አለትነት ተመስርቻለሁ
የማዕዘኑ ራስ አግኝቼሃለሁ ❤❤
መልህቄ መልህቄ ኢየሱስ መልህቄ
ላትለቀኝ የያስከኝ የእግዚአብሔር ልጅ ጽድቄ(×2)❤️❤️
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
መርህን መከተል....
✍️ ሕይወት በመርህ የተመራ ከሆነ ስኬታማ ነው፤ መርህን የማናከብር ከሆነ ግን ውድቀት ውስጥ መግባታችን የማይቀር ነው። በሚዘራበት ወቅት መተኛት በሚታጨድበት ወቅት መለመን መርህን ያለመከተል ውጤት ነው።
ያልበለፀጉ ሀገራት ያልበለፀጉት የአየር ሁኔታቸው የሚመችና የማያስቸግር ስለሆነ ነው፤ የበለፀጉ ሀገሮች ደግሞ ያልተመቻቸ የአየር ሁኔታ ስላላቸው እርሱን ለማሸነፍ ተግተው ሰርተው በልፅገዋል።
#የምንተጋበትን_ሰዓት_አንተኛ_በምንተኛበት_ሰዓት_አንትጋ!
የዘር ጊዜያአችን እና ወቅታችንን ማወቅ እና መትጋት ነገ ላይ ከጨዋታ ውጪ እንዳንሆን ያደርጋል።
ስለዚህ ሁልጊዜ የምናደርገውን ስናደርግ ነገሩ በሚሰራበት መርህ እና ጊዜ ልናደርገው ይገባል። እንዲሁም መርህን በመከተል ልንነቃ ይገባል።
ዘፍጥረት 8:22 NASV
[22] “ምድር እስካለች ድረስ፣ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት፣ አይቋረጡም።”
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ሶፊያ ሽባባው
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ነፍስን የሚያሰጠው😭😭😭😭😭
ይህንን ድንቅ መዝሙር ተባረኩበት❤️❤️
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
በእኛ ስራ ሳይሆን በእርሱ ስራ ወደ ሕይወት ገብተናል።
በእርሱ (በክርስቶስ ኢየሱስ) #ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።
— ኤፌሶን 2፥18
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
የማያረጅና ዘመን የማያልፍበት ዜና🔥❤
እግዚአብሔር የመጨረሻ ኃይሉን የገለጠው #በወንጌል ሲሆን ወንጌል ደሞ ስልጁ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሆነ ለሰዎች ሁሉ የተበሰረ የእግዚአብሔር ማዳን የተገለጠበት የምስራች ነው።❤🔥
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥18
ኢየሱስ ከዘለአለም ሞት ያድናል🔥❤️
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist