binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

በሐዋርያት ዘመን የተገለጠው ክብር ሲገለጥ ሰዎች ክብር #የተገለጠበትን (person) ማየት ትተው #የተገለጠውን ክብር ( #ኢየሱስን) ማየት ይጀምራሉ።

ይሄ ደግሞ በቅርቡ የእግዚአብሔርን ክብር በተራብነውና በተጠማነው በእኛ ላይ ይሆናል እግዚአብሔርም
#ያደርገዋል🔥🔥🔥

አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።
  — ሐዋርያት 4፥29-30


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ አይኔ በርቶ አንዴ ልይህ😭😭😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር በሽታን የሚሰጥ አምላክ ሳይሆን ከበሽታ የሚፈውስ አምላክ ነው።

አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ።
  — ዘጸአት 23፥25

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር በሚመጡ ዘመናቶች በኃይልና በሙላት እንዲጠቀምባችሁ ትፈልጋላችሁ???

እግዚአብሔር ብዙ የትንቢትን ቃል ነግሯችኃል???

እንግዲያውስ አንድ ነገር ልበላችሁ በእግዚአብሔር ቃልና በፀሎት እራሳችሁን
#አዘጋጁ

እመኑኝ እግዚአብሔር
#ባልተዘጋጀ ማንነት ክብሩን በሙላት አይገልጥም።

ቃሉን በጥልቀትና በቀጣይነት በማጥናት
#ተዘጋጁ

ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ረዘም ላለ ሰአት በፆምና በፀሎት
#ተዘጋጁ

የተለያዩ የእግዚአብሔር ሰዎች የፃፉትን መንፈሳዊ ረሃብን የሚጨምሩ መፅሐፍትን በማንበብ
#ተዘጋጁ

አስተውሉ ኢየሱስ 3 አመት ተኩል ዘመናት የሚተርኩትንና የእግዚአብሔርን አጀንዳ በምድር ለመግለጥ ሰላሳ አመት ሙሉ ተዘጋጅቷል።

ኃዋርያትም የኢየሱስን አገልግሎት በምድር በሙላት ለማስቀጠል 3 ተኩል አመት በኢየሱስ እግር ስር ቁጭ ብለው በመማር ተዘጋጅተዋል።

በታሪክም ሆነ አሁን ላይ ያሉ ጀነራሎች የእግዚአብሔርን ኃይል በምድር ላይ በሙላት የገለጡበት ትልቁ ምስጢር የሆነ ጊዜ የዝግጅት ጊዜ ነበራቸው።

ዝግጅት ደግሞ የአንድ ቀን ወይ የአንድ ወር ወይ የአንድ አመት ጉዳይ ሳይሆን እግዚአብሔር እናንተን በምድሪቱ ላይ ሊገልጥበት እስከወሰነላችሁ ጊዜ የየእለት ተግባራችሁ ነው።

የዝግጅት ሕይወት ይኑራችሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የእግዚአብሔርን ቃል እንደ አባባል ከቆጠርከው በአባባልነቱ ብቻ ታውቀዋለህ እንደ መለኮታዊ ቃል ደግሞ ከቆጠርከው የምትፈልገውን ትቀበላለህ።

#መንፈስ_ሕይወትን ይሰጣል፤ ሥጋ ግን ምንም አይጠቅምም። #እኔ የነገርኋችሁ #ቃል #መንፈስም #ሕይወትም ነው፤
— ዮሐንስ 6፥63 (አዲሱ መ.ት)

የእግዚአብሔር
#ቃል #ሕያውና #የሚሠራ_ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል።
— ዕብራውያን 4፥12 (አዲሱ መ.ት)

የእግዚአብሔር ቃል አንደኛ ወረቀት ላይ የምናነበው ፊደል ብቻ ሳይሆን ሕያው ነው ይህ ማለት ሕይወት ያለው የሚንቀሳቀስ Person ነው እርሱም ኢየሱስ ነው።

ሁለተኛ የእግዚአብሔር ቃል
#የሚሰራ ነው። ስለዚህ ቃሉን በእምነት ከራሳችን ጋር ስናዋህድ ቃሉ ውስጥ ያለው ሕይወትና መንፈስ በሕይወታችን ላይ ተፅእና እያረገ የቃሉ አይነት ሕይወት በሕይወታችን ይገለጣል።

ቃሉ ከእኛ ጋር ሊዋኻድ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ የቃሉን ሬማ በእምነት በመቀበል ብቻ ነው።

የእግዚአብሔር ቃል መንፈስና ሕይወት ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሰራ ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ማርቆስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ እውነት እላችኋለሁ፥
#ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት #ቢያምን በልቡ #ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል #ይሆንለታል

²⁴ ስለዚህ እላችኋለሁ፥
#የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም #ሁሉ #እንዳገኛችሁት #እመኑ#ይሆንላችሁማል

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ራእይ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴-⁵...ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥

⁶ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።


ኢየሱስ😭😭😭🙏🙏🙏

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የኔ ጌታ ኢየሱስ ከሞት ብቻ ሳይሆን ከመኖርም ነው ያዳነኝ።

ከራሴ በራሴ ለራሴ የምኖረው ሕይወት የለኝም አሁን በስጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት የምኖረው ኑሮ ነው ኢየሱስ ብቻ በእኔ ይኖራል።

2ኛ ቆሮ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤

¹⁵ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አምልኮ ከእግዚአብሔር ጋር ማሳለፍ እግዚአብሔርን በጥልቅ ፍቅር መውደድ በእግዚአብሔር መደሰት ማለት ነው።

እውነተኛ አምልኮ ማለት ከእውነተኛ አፍቃሪ ልብ የሚፈልቅ በአንደበት የሚፈስ ወይም በሕይወት ላይ የሚታይ የፍቅር ቋንቋ ነው።

ሬማ እና ሎጎስ ከሚለው ከሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ መፅሐፍ የተወሰደ

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ ላልበራላቸው አይሁዳውያንና ፈሪሳውያን ግሪካውያን ሰዎች አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ ሲሆን እግዚአብሔር ላበራላቸው ሰዎች ግን የማዕዘን ራስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

በጥበበኞችና በአዋቂዎች አይን ኢየሱስ አናጢዎች እንደማይጠቅም ድንጋይ የጣሉት ድንጋይ ሲሆን በእግዚአብሔር እይታና እግዚአብሔር ላበራላቸው ሰዎች ግን እርሱ የእግዚአብሔር ጥበብና የማዕዘን ራስ ነው።

እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው።
— ሐዋርያት 4፥11

ለዛም ነው ኢየሱስ የአዋቂዎችና የጥበበኞች ነን ባዮች የምርምር ውጤት ሳይሆን የመለኮት መገለጥ ውጤት የሆነው።

ኢየሱስን መረዳት የምትችለው በሰበሰብከው መረጃዎች ሳይሆን መለኮት ሲያበራልህ ብቻ ነው።


እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን፤...
— መዝሙር 118፥27

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
— ማቴዎስ 16፥17


በምድር ላይ እንደእናንተ እድለኛ አለ ብዬ አላምንም ምክኒያቱም ከጥበብ ሁሉ የሚበልጥ እራሱ ጥበብ የሆነው ከመገለጥ ሁሉ የሚበልጥ እራሱ መገለጥ የሆነው ኢየሱስን የሚያክል የእግዚአብሔር ጥበብና መገለጥ ነው የበራላችሁ።

በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
— ሉቃስ 10፥21


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የዘላለም ፈጣሪ
ሀና ተክሌ
ከቁ~2 አልበም | 2005 ዓ.ም
ይህንን መዝሙር ጋበዝኳችሁ😭😭😭


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገባህ ሲበራልህ ብቻ ነው።

በክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ይሰጠን ዘንድ፣ “በጨለማ ብርሃን ይብራ” ያለው እግዚአብሔር ብርሃኑን በልባችን አብርቶአልና።
  — 2ኛ ቆሮንቶስ 4፥6 (አዲሱ መ.ት)


በዚህ ምድር ላይ ካወካቸው እውቀቶች ሁሉ የሚበልጥ እውቀት ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ያወከው እውቀት ነው ይሕ እውቀት የታላላቅ አዋቂዎች ነን ባዮች ምርምር ውጤት ሳይሆን የመለኮት መገለጥ ውጤት ነው።

ይሔው እውቀት ነው ዘላለማዊ ድነትን ያስገኘው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በእየሱስ አዳኝነት ተምነለህ በ አማላጅነቱስ????????

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በእየሱስ አዳኝነት ተምነለህ በ አማላጅነቱስ????????

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።...
— 1ኛ ዮሐንስ 3፥9

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር ሊሰራባችሁ ሲፈልግ የሚሰጣችሁ መድረክ ሳይሆን ረሃብ ነው።

መዝሙር 42
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።

² ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?

እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
— መዝሙር 143፥6

መዝሙር 63
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።

² ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

Holy spirit 😍😍😭😭🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የምታየውና የምትሰማው ነገር ከተቀየረ በእርግጥ የምትናገረው ይቀየራል፤ የምትናገረው ከተቀየረ በእርግጥ ልማድህ ይቀየራል፤ ልማድህ ከተቀየረ፤ አጠቃላይ ድርጊትህ ይቀየራል፤ ድርጊትህ ከተቀየረ ደግሞ ሕይወትህ ለዘላለም ይቀየራል።

ኃይልህ ትኩረት ያደረክበት ነገር ላይ ነው ያለው ትኩረትህ ደግሞ በምታየውና በምትሰማው ነገር ላይ ነው።

ስለዚህ ሕይወትህን ለመቀየር እይታህንና የምትሰማውን ነገር ቀይር።

ማቴዎስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²²
#የሰውነት #መብራት #ዓይን ናት። #ዓይንህ እንግዲህ #ጤናማ ብትሆን፥ #ሰውነትህ #ሁሉ_ብሩህ ይሆናል፤

²³
#ዓይንህ ግን #ታማሚ ብትሆን፥ #ሰውነትህ_ሁሉ #የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ #በአንተ ያለው #ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ #ጨለማውስ እንዴት #ይበረታ!

ማርቆስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።

²⁴ አላቸውም፦ ምን
#እንድትሰሙ #ተጠበቁ።...

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ከእግዚአብሔር ቃልና ከመንፈስ ቅዱስ ውጪ ምንም አይነት መንፈሳዊ እድገት የለም።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የእግዚአብሔርን #ልጆነት ፆመህ ፀልየህ፣ ተራራ ወጥተህ ሸለቆ ወርደህ፣ ባዶ እግርህን ሄደህ፣ ድንጋይ ተሸክመህ፣ ጥረህና ግረህ፣ ተጎሳቁለህ የምትሆነውና የምታመጣው ነገር ሳይሆን #በመወለድ #ብቻ የምትካፈለው #ዘር ነው።

የእግዚአብሔር
#ልጅ የምትሆነው ጥሩ  ኃይማኖተኛ ስትሆን ሳይሆን ከእርሱ ስትወለድና #ዘሩን ስትካፈል ብቻ ነው።

የእግዚአብሔር ልጅ
#ጨዋው አዳም ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ ዳግም #የተወለደውና አዲስ ፍጥረት የሆነው ነው።

ልጅነት ያለው
#በመወለድ ብቻ ነው።

#እነርሱም #ከእግዚአብሔር #ማዳንህ ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ #አልተወለዱም
  — ዮሐንስ 1፥13


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኢየሱስ😭😭😭😭😭😭🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዘዳግም 33
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።

²⁷ መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።

²⁸ እስራኤልም ተማምኖ፥ የያዕቆብም ምንጭ ብቻውን፥ እህልና የወይን ጠጅ ባለባት ምድር ይኖራል፤ ሰማያቱም ጠልን ያንጠባጥባሉ።

²⁹ እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወንጌል ሕይወቴ ነው።
ወንጌል ራዕዬ ነው።
ወንጌል ስራዬ ነው።
ወንጌል ሕልሜ ነው።

የምኖረለትና የምሞትለት የሕይወቴ ዓላማ ወንጌል ነው ቢናን ከወንጌል ውጪ ለይታችሁ ካያችሁት በሎዶባር የተጣለ ተራ ሰው ነው።

1ኛ ጢሞቴዎስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤

¹³ አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥

… 
¹⁵ ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤

¹⁶ ስለዚህ ግን፥ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ....
ኢየሱስ አዳኝ እንደሆነ....
ኢየሱስ ሕይወት እንደሆነ....
እየሱስ እውነት እንደሆነ.....
ኢየሱስ መንገድ እንደሆነ....
ኢየሱስ ፍቅር እንደሆነ....
ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ....
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ....

ተብራርቶልኝ ሳይሆን በርቶልኝ ነው የገባኝ🔥❤️

እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን፤...
— መዝሙር 118፥27

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
— ማቴዎስ 16፥17

በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
— ሉቃስ 10፥21


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው፦ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ #የአብርሃም_አምላክ #የይስሐቅም_አምላክ #የያዕቆብም_አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ #ለዘላለሙ_ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።
— ዘጸአት 3፥15

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ እንደዚህ አለ👇👇

በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።
  — ዮሐንስ 12፥46

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በእየሱስ አዳኝነት ተምነለህ በ አማላጅነቱስ????????

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መዝሙር 119:123 NASV
123 ዐይኖቼ [[ማዳንህን]]፣ የጽድቅ ቃልህን በመጠባበቅ ደከሙ።

ከላይ
#ማዳንህ የሚለው ቃል የተጻፈበት የዕብራይስጥ ቃል {יְשׁוּעָה} [yᵉshûwʻâh] ነው የሚለው Yeshuwan በመጠበቅ አይኖቼ ደከሙ ማለትም ኢየሱስ(ማለት አዳኝ ማለት አይደል?) ኢየሱስን በመጠበቅ አይኖቼ ደከሙ ይላል።

ዳዊት ማዳንህን ሲል ምናልባት person ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰበ ላይሆን የሰችላል ግን በእግዚአብሔር ዓለም ማዳኑ person የሆነው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ by default ንጉሥ ዳዊት ቢያውቅም ባያውቅም YESHUA እያለ የመሲሑን የኢየሱስን ስም እየጠራ ነው።

አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ ሕግህም ተድላዬ ነው።” መዝ 119፥174

እዚህም ጋር YESHUAን (ኢየሱስን) ናፈቅሁ እያለ ነው ቢያውቅም ባያውቅም እግዚአብሔር ሆይ ኢየሱስህ ናፍቆኛል እያለ ነው፤ የብሉይ ኪዳኑ ዳዊት።

የዳዊትን መዝሙር ሲያነብብ የኖረው ሽማግሌው ስምኦን ማዳንህን አሳየኝ ብሎ ያን ሁሉ አመት ጠብቆ አሁን የእግዚአብሔር ማዳን (Yeshua) Person እንደሆነ ሲገባው ህፃኑን ኢየሱስን ስያይ እንዲህ አለ👇

“ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን [ማዳንህን] አይተዋልና፤”
  — ሉቃስ 2፥30-31
'This is Salivation ይሄ ነው እውነተኛው ማዳን እውነተኛው Yeshua ይሔ ነውና ከዚህ የተሻለ ማዳን ስለማላይ ባርያህን አሰናብተኝ' አለ። ምክኒያቱም በብሉይ ኪዳን የተስፋ ቃል ብቻ የነበረው የእግዚአብሔር ማዳን Personified ሆኖ እጁ ውስጥ ስለገባ አካል ስለያዘ ሌላ የሚጠብቀው የማዳን(Yeshua) hope አጣ። ዳዊት በተስፋ የናፈቀውን የእግዚአብሔር ማዳን(Yeshuaን) ስምዖን ግን በክንዶቹ አቀፈው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሕይወት person ከሆነ ሞትም person ነው።

እውነት person ከሆነ ውሸትም person ነው።

ኢየሱስ እኔ ሕይወት ነኝ ካለ ሰይጣን ደግሞ እኔ ሞት ነኝ ነው የሚለው።

ጌታ ኢየሱስ እኔ እውነት ነኝ ካለ ሰይጣን ደግሞ እኔ ውሸት ነኝ ነው የሚለው


በመስቀል ላይ ሞት በሕይወት ተሰንፏል።

በመስቀል ላይ ውሸት በእውነት ተሸንፏል


ቆላስይስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤

¹⁵ አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ የሚለው ስም ለአስቄዋ ልጆች ባለ አራት ፊደል ሆሄ ነው።

ለጳውሎስና ለእኔ ግን በሽታን፣ ጨለማን፣ አጋንንትን፣ ሞትን፣ እርግማንን፣ መናፍስቶችን ያሸነፍንበትና ያባረርንበት ኃይላት፣ ስልጣናትና፣ ጉልበቶች ሁሉ የሚገዙበትና የሚንበረከኩበት
#ስልጣን ነው።

ፊልጵስዩስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤

¹⁰ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥

¹¹ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…
Subscribe to a channel