binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

. ምንም ብሆን
ሶፊያ ሽባባው -ቁ-2[1999]
እጅግ በጣም ድንቅ መዝሙር ነው ተጋበዙልኝ😍❤️


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዘማሪ እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ
ዝም ብዬ ወደፊት🔥
ከፍፍ በሉበት ድንቅ መዝሙር ነው🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መዝሙር 105
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
⁴ እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

Part 1
🚨በአምሮ መንፈስ መታደስ💡🔥

እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ ትምህርት ነው ስሙትና ተቀጣጠሉበት🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሞትን ጥቅሙ ያደረገ ብቸኛው ፍጥረት ኢየሱስን ሕይወቱ ያደረገ አዲሱ ፍጥረት ነው😂😂❤️❤️🙏🙏

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።
  — ፊልጵስዩስ 1፥21


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የዲያቢሎስን ሽንገላ እና ውሸት ከሕይወታችሁ በቀላሉ ማሸነፍ ከፈለጋችሁ ይሕንን አድርጉ👇👇

ኤፌሶን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።

¹¹ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።

¹² መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።

¹³ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።

¹⁴-¹⁵ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤

¹⁶ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤

¹⁷ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

¹⁸ በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤


ዲያቢሎስን ለማሸነፍ እውነት በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሳትናወጡ ቁሙ።

የዲያቢሎስን ሽንገላ እና ውሸት ማሸነፍ የምትችሉት እውነት በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስትቆሙ ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ ላልበራላቸው አይሁዳውያንና ፈሪሳውያን ግሪካውያን ሰዎች አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ ሲሆን እግዚአብሔር ላበራላቸው ሰዎች ግን የማዕዘን ራስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

በጥበበኞችና በአዋቂዎች አይን ኢየሱስ አናጢዎች እንደማይጠቅም ድንጋይ የጣሉት ድንጋይ ሲሆን በእግዚአብሔር እይታና እግዚአብሔር ላበራላቸው ሰዎች ግን እርሱ የእግዚአብሔር ጥበብና የማዕዘን ራስ ነው።

ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤
— መዝሙር 118፥22

እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው።
— ሐዋርያት 4፥11

ለዛም ነው ኢየሱስ የአዋቂዎችና የጥበበኞች ነን ባዮች የምርምር ውጤት ሳይሆን የመለኮት መገለጥ ውጤት የሆነው።

ኢየሱስን መረዳት የምትችለው በሰበሰብከው መረጃዎች ሳይሆን መለኮት ሲያበራልህ ብቻ ነው።


እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን፤...
— መዝሙር 118፥27

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
— ማቴዎስ 16፥17


በምድር ላይ እንደእናንተ እድለኛ አለ ብዬ አላምንም ምክኒያቱም ከጥበብ ሁሉ የሚበልጥ እራሱ ጥበብ የሆነው ከመገለጥ ሁሉ የሚበልጥ እራሱ መገለጥ የሆነው ኢየሱስን የሚያክል የእግዚአብሔር ጥበብና መገለጥ ነው የበራላችሁ።

በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
— ሉቃስ 10፥21


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።
— ኤፌሶን 6፥24 (አዲሱ መ.ት)

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እኛ የቆፈርነው የውኃ ጉድጓድ የነፍሳችንን ጥም ሊቆርጥና ሊያረካ አይችልም።

የነፍሳችንን ጥም ሊቆርጥና ሊያረካ የሚችለው ብቸኛው የሕይወት ውኃ ምንጭ ጉድጓድ ኢየሱስ ነው።

ኢየሱስ ከሚባለው ጉድጓድ ውስጥ ጥምን ፈፅሞ የሚያረካና የሚቆርጥ የሕይወት ውኃ ምንጭ ይፈልቃል።

ኢየሱስን ያገኘች ነፍስ ጥማትና ምድረበዳነት ፈፅሞ አይሆንባትም ዘላለሟ የእርካታና የልምላሜ ነው ምክኒያቱም ኢየሱስ የማይነጥፍ የሕይወት ውሃ ምንጭ ጉድጓድ ነው። 


ዮሐንስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤

¹⁴ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን አለና፤ #ከአምላካችንስ በቀር #ዐለት ማን ነው?
— 2ኛ ሳሙኤል 22፥32 (አዲሱ መ.ት)


ዘጸአት 33
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥
#በዓለቱም ላይ ትቆማለህ፤

²² ክብሬም ባለፈ ጊዜ
#በሰንጣቃው_ዓለት አኖርሃለሁ፥ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ፤

እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ
#በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።
— ዘጸአት 17፥6

ሁሉም ከአንድ መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤
#ይከተላቸው ከነበረው #መንፈሳዊ_ዐለት ጠጥተዋልና፤ ያ #ዐለት #ክርስቶስ ነበረ።
— 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥4 (አዲሱ መ.ት)


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መዝሙር 91
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
² እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።
³ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።
⁴ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
⁵ ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥
⁶ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።
⁷ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
⁸ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።
⁹ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
¹⁰ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
¹¹ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
¹² እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
¹³ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወዳጄ በእግዚአብሔር ፊት ለመፅደቅ ካንተ የሆነ ምንም አይነት የሕግ ስራ ለመስራት ስትጥር መፅሐፍ ከእርግማን በታች እንደሆንክ ይነግርሃል።

ገላትያ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና።

¹¹ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።

ፅድቅ አንተ ለፍትህ ዋጋ ከፍለህ ተራራ ወጥተ ሸለቆ ወርደህ ፆመህ ፀልየህ ሰግደህ ባዶ እግርህን ሄደህ የምታመጣው ሳይሆን የእግዚአብሔር ፅድቅ የተገለጠበትን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን እንዲሁ በፀጋ የምትቀበለው ነፃ ስጦታ ነው።

ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።
  — ሮሜ 4፥5

ሮሜ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።

²¹ አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥

²² እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤

²³ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤

²⁴ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።

በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና
#የጽድቅን_ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ።
  — ሮሜ 5፥17

ፅድቅ የእግዚአብሔር ነፃ ስጦታ እንጂ የእኛ የስግደታችን፣ የፆማችን፣ የምፅዋታችን፣ ውጤት አይደለም።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወንጌል ማለት አይምሮ ለመቀበል የሚያስቸግረው የምስራች ማለት ነው ።

ሎተሪ ሳይቆርጥ አንደኛው ዕጣ ያንተ ነው ሲባል 🤔‼

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በእየሱስ አዳኝነት ተምነለህ በ አማላጅነቱስ????????

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በእየሱስ አዳኝነት ተምነለህ በ አማላጅነቱስ????????

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ይህንን ቃል እያሰባችሁት ዋሉ😭👇

#በሆድ_ሳልሠራህ #አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።
— ኤርምያስ 1፥5

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
— ራእይ 12፥10


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

Part 2
🚨በአምሮ መንፈስ መታደስ🔥💡

ሁሉም ሰው መስማት ያለበት እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ አይን የሚከፍት ትምህርት ነው ሁላችሁም አሁን ስሙት🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።
— 1ኛ ዮሐንስ 5፥4


በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
— ሮሜ 8፥37

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በልጁ የሚያምን #የዘላለም_ሕይወት #አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ #ሕይወትን_አያይም
— ዮሐንስ 3፥36

የዘለአለም ሕይት የማግኘትም ከዘለአለም ሕይወት የመጉደልም ዋነኛ ምክኒያቱ
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው።

የዘለአለም ሕይወት የሚገኝበት ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ሲሆን ከዘለአለም ሕይወት መጉደልም ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ አለማመን ነው።

በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያለው ሕይወት የእግዚአብሔር አይነት ሕይወት ነው። ሰው በኢየሱስ ሲያምን የሕይወቱ ስርአት የእግዚአብሔር አይነት ሕይወት ነው።

መፅሐፍ ሕይወት ብሎ ሲናገር መብላት መጠጣትና የተለያዩ የምድር ላይ የመኖርን የሕይወት ስርአት እየተናገረ ሳይሆን የእግዚአብሔር አይነት ስለሆነው የሕይወት ስርአት እየተናገረ ነው።

የእግዚአብሔር የሕይወት ስእአት ምንድነው ብለን ስንጠይቅ ዞዌ ሕይወት ማለት ነው።

ዞዌ ሕይወት በፅድቅ በቀሰድስና በፍቅር በደስታ በቸርነት በርህራሄ በክብር የተሞላ ሕይወት ነው። በእግዚአብሔር ሕይወት ውስጥ ከእነዚህ ሰማያዊ ሕይወት በስተቀር ክፉ የሆኑ የሕይወት ስርአት ፈፅሞ የሉም።

ሰው በኢየሱስ ሲያምን የሚኖረው የሕይወት ስርአት ይህ የእግዚአብሔር አይነት የሕይወት ስርት ነው።

ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ካላመነ የሚኖረው የእግዚአብሔርን የሕይወት Standard ሳይሆን የወደቀውን ዓለም የሕይወት ስርአት ነው የሚኖረው።

ስለዚህ መፅሐፍ ሕይወት ብሎ ሲናገር ከመብላት ከመጠጣት የተለያዩ luxury ሕይወት ከመኖር ያለፈ የእግዚአብሔርን ዓይነት ሕይወት መኖርን ነው የሚናገረው።

ኢየሱስ እኔ ትንሳኤና ሕይወት ነኝ ሲል ሰው በአዳም ምክኒያት ለእግዚአብሔር የሕይወት ስርዓት የሞተ ነበር ስለዚህ ኢየሱስ የሞተውን ሰው በትንሳኤ መንፈስ ለእግዚአብሔር ዓለም የሕይወት ስርአት ሕያው በማድረግ የሚኖረውንም ሕይወት ወይም የሕይወት ስርአት እራሱ ኢየሱስ ይሆናል ማለት ነው።

ኢየሱስ አንደኛ ለእግዚአብሔር ዓለም የሕይወት ስርአት ሙታን ለሆኑት ትንሳኤ ሲሆን።

ሁለተኛ ደግሞ ሰው በኢየሱስ አምኖ ለእግዚአብሔር ዓለም የሕይወት ስርአት ሕያው ከሆነ በኃላ ወይም ለእግዚአብሔር ዓለም ከነቃ በኃላ የሚኖረው ሕይወት የራሱን ሕይወት ሳይሆን ክርስቶስ ኢየሱስን ነው።

ዳግም የተወለደ አዲስ ፍጥረት የሆነ ሰው የሚኖረው የሕይወት ስርአት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
  — ገላትያ 2፥20

2ኛ ቆሮ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤

¹⁵ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።
  — ፊልጵስዩስ 1፥21


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በኢየሱስ ደም ከነገድ ከዘር ከቋንቋ ከወገን የተዋጁ የእግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን በአምላካቸውና በአባታቸው ፊት በአንድነት በእግዚአብሔር ፊት ሆነው እግዚአብሔርን በአንድ ልብ ሲያከብሩት እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም😍😍😍😍

ይህንን የሰማይ ከዋክብት የምድር ጨው የዓለም ብርሃን በአንድነት ተሰብስቦ አምላኩን እግዚአብሔርን ሲያመልክ አየሰቶ የሚበሳጭ የጨለማው አለቃ አጋንንት ብቻ ነው።

እግዚአብሔር አምላካችን በላይ በአርያም በምድራችን በኢትዮጵያ ከፍ ብሎ ይታይ ኢየሱስ ብቻውን በምድራችን ላይ ጌታ አዳኝ እና ንጉስ ነው😍😍❤️❤️


አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ፥ ምስጋናህ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና።
  — መዝሙር 8፥1


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የሕይወቴ ጉዳይ ኢየሱስ
ልቤ ሚርድልህ ኢየሱስ😭😍❤

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

.              ነው ከላይ  
      ጥበቡ ወርቅዬ - Live
በዚህ አምልኮ በመንፈስ አለመረስረስ አይቻልም🔥🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

🛑📵 ሰበር ዜና በ አጭር ግዜ ተወዳጅነትን የገኙ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዝኛ የሚለቀቁ አስተማሪ ና አዝናኝ ቻነሎችን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇
Free promotion የሚትፈልጉ
Channel ያላችሁ በ @seer_lewi አነግሩኝ 👇👇👇

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።
— ዘዳግም 32፥10


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#ፀጋ ለእኛ ለተቀባዮቹ በነፃ የተቀበልነው ነፃ ስጦታ ቢሆንም ለሰጪው ግን ልጁንና ሕይወትን ያስከፈለ ትልቅ ዋጋ ነው።

ለዛ ነው ፀጋ ሊቀልብን የማይገባው። 

የእግዚአብሔርን
#ጸጋ_አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።
  — ገላትያ 2፥21


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

🛑📵 ሰበር ዜና በ አጭር ግዜ ተወዳጅነትን የገኙ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዝኛ የሚለቀቁ አስተማሪ ና አዝናኝ ቻነሎችን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇
Free promotion የሚትፈልጉ
Channel ያላችሁ በ @seer_lewi አነግሩኝ 👇👇👇

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

There is Power in The Name of Jesus🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

16 ሰዎች ጌታን የተቀበሉበት ድንቅ ቀን ❗️
@ᴡᴇʟɪsᴏ ᴄɪᴛʏ ( በወሊሶ ከተማ ) 🔥🔥

👉 “ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤”
— 2ኛ ቆሮ 2፥14

👉 በወሊሶ ከተማ አስደናቂ የጀማ እና አንድ ለአንድ አገልግሎት ነበረን ክብር ሁሉ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን 😍🙏

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#ታላቅ_የወንጌል_ስርጭት_በወሊሶ_ከተማና_አካባቢዋ
ከ sᴘɪʀɪᴛ ʟɪғᴇ ᴄʜᴜʀᴄʜ ጋር በመተባበር
👉የካቲት 30 - መጋቢት 1 ( ቅዳሜና እሁድ )
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
— ማቴዎስ 28፥19-20

Читать полностью…
Subscribe to a channel