ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሳትሆን የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ እናት ነች።
እንዴ እና የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም እንዴ? የሚለውን ጥያቄ እንደፈጠረባችሁ እርግጠኛ ነኝ.
ነገር ግን ቅድስት ድንግል ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ኢየሱስ ነው።
ቅድስት ድንግል ማርያም የወለደችው አምላክን ሳይሆን #ሰው የሆነውን ኢየሱስን ነው።
ከሰው መለኮት አይወለድም ከሰው የሚወለደው ሰው ብቻ ነው።
ቅድስት ድንግል ማርያም የኢየሱስን ሰውነት እንጂ መለኮትነቱን አልወለደችም።
አስተውል መለኮት ወይም አምላክ ተወለደ ካልክ አምላክ ተገኘ፣ ተፈጠረ፣ ሕያው ሆኖ Exist ማድረግ ጀመረ እያልክ ነው።
እኛ የምናመልከው አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የተገኘ ወይም የተፈጠረ ሕያውነትን ወይም መኖርን ከድንግል ማርያም በመወለደ የጀመረ እና ከሰው የተገኘ ሳይሆን ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለማቱን ሁሉ ያስገኘ መጀመሪያ እና መጨረሻ የሌለው አልፋ እና ኦሜጋ እኔ ነኝ ያለ መለኮት ነው።
ስለዚህ ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን የወለደች ወይም አምላክን ያስገኘች ሳትሆን የኢየሱስን ሰውነት የወለደች ሰው የሆነውን ኢየሱስን የወለደች የአምላክ እናት ሳትሆን የኢየሱስ እናት ነች።
እያልኩኝ ያለሁትና በደንብ እንድታስተውሉልኝ የምፈልገው ነገር ኢየሱስ ሰው ብቻ ሳይሆን ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነው ከድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ ሰው ብቻ ነው እያልኩኝ እንዳልሆነ እንድትረዱኝ እፈልጋለሁ ነገር ግን ኢየሱስ ከድንግል ሲወለድ ሰውነቱ ነው እንጂ አምላክነቱ አልተወለደም እያልኩኝ ነው በዚህም ምክኒያት ማርያም የኢየሱስ እናት እንጂ የአምላክ እናት አይደለችም።
አምላክ እናት የለውም አምላክ ፈጣሪ እንጂ ተፈጣሪ አይደለም አምላክ አስገኚ እንጂ የተገኘ አይደለም።
ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን ነው የወለደችው የሚለው ስሁት ትምህርት የኢየሱስን ፍፁም ሰውነትና ፍፁም አምላክነት የካደ እንዲሁም እግዚአብሔር ለመረጣት ለቅድስት ድንግል ማርያም የማይሆን መልክ የሚሰጥ የአሮጊቶች ተረት የሆነ ትምህርት ነው።
እንደ እነዚህ ያሉትን ከመፅሐፍ ቅዱስ የራቁ ስሁት ትምህርቶችን በእግዚአብሔር ቃል እናፈርሳለን። እውነተኛ የሆነውንና ድነት የሚገኝበትን የክርስቶስን ወንጌል የሚጋርዱ የአሮጊቶችን ተረትንና የአጋንንትን ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን እናጋልጣለን እናፈርሳለን።
ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
³¹ እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
³² እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤
የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ #የተገለጠ_ሰው ነበረ፤
— ሐዋርያት 2፥22
ይህ ማርያም ጠል ትምህርት ሳይሆን የመፅሐፍ ቅዱስ እውነት ነው።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
የአሮጊቶች ተረት ክፋቱ ሕይወት የሚገኝበትን የክርስቶስን ትምህርትና መስቀል ላይ የተፈፀመውን የደህንነት ትምህርት መጋረዱና ከሰዎች ልብ ላይ ማጥፋቱ ነው።
ሰዎች ለአሮጊቶች ተረት ጆሮአቸውን ሲከፍቱ ሕይወት የሚገኝበት የክርስቶስ ወንጌል ይቀልባቸዋል።
የክርስቶስን ወንጌል ከሰዎች ልብ ላይ በማደብዘዝ በሰው አእምሮ ላይ መጋረጃ ሆኖ የተጋረደውን የአሮጊቶችን ተረት የኃይማኖትን ግንብ በእግዚአብሔር ቃል እውነት እናፈርሳለን።
እግዚአብሔርን ከማያከብር ርባናቢስ አፈ ታሪክና ከአሮጊቶች ተረታ ተረት ራቅ፤ ይልቁንም ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስህን አሠልጥን።
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7 (አዲሱ መ.ት)
በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።
— 2ኛ ቆሮንቶስ 10፥5 (አዲሱ መ.ት)
ወንጌል አይሸፈንም።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ሮሜ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።
⁷ ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።
⁸ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።
⁹ ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።
¹⁰ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤
¹¹ ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።
ክርስትና ሐዋርያ ወይ ደግሞ ነብይ ለመሆን የሚደረግ ጉዞ ሳይሆን በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ ኢየሱስ እውቀት የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን የመምሰል የሕይወት ጉዞ ነው።
ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
— ሮሜ 8፥29
Note ሐዋርያነትና ነብይነት የምንሆነው ሳይሆን የምንደረገው ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሐዋርያ ወይ ደግሞ ነብይ ወይ ደግሞ ወንጌላዊ ሌሎቹንም ያደርግሃል እንጂ አንተ በራስህ አትሆነውም።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥
— ገላትያ 1፥15-16
ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፥ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ፤
— ኤፌሶን 3፥8-9
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
2ኛ ቆሮ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ #በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን።
⁵ ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤
⁶ እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
⁷ ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥
⁸ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም?
⁹ የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና።
¹⁰ ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና።
¹¹ ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና።
¹² እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን እጅግ ገልጠን እንናገራለን፥
¹³ የዚያንም ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።
¹⁴ ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና።
¹⁵ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤
¹⁶ ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል።
¹⁷ ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።
¹⁸ እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
በመሰረቱ (በክርስቶስ) ላይ ስራችሁ እስካልሰደደ ድረስ በመሳዊ ሕይወታችሁ ማደግ መለምለም ማበብና ማፍራት መጠንከር መንዠርገግ ለሌሉች ጥላ መሆን አትችሉም።
በክርስቶስ ላይ ስር መስደድ ማለት ክርስቶስን በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ በቃሉ መረዳትና ማወቅ ማለት ነው።
በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ በክርስቶስ ስር
ስር ስትሰድዱ የውስጠኛው ማንነታችሁ ጠንካራ ይሆናል የገሃነም ደጆችም አይቋቋሟችሁም🔥
በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።
— ኢሳይያስ 27፥6
ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፥ ወደ ላይም ያፈራል።
— ኢሳይያስ 37፥31
ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፥ ወደ ላይም ያፈራል።
— 2ኛ ነገሥት 19፥30
በክርስቶስ እውቀት ስር ስንሰድድ በፍሬ በሰዎች ሁሉ ፊት እንገለጣለን🔥🔥🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
🚨ሰላም ወዳጆቼ አንደ የሚጠቅማችሁን መንፈሳዊ ነገር በግልጥ የሚያስተላልፉ ቻናሎች ልጋብዛችሁ ተጋበዙልኝ!!! Channel ያላችሁ አናግሩኝ @srofgod
Читать полностью…🪽ለክርስቲያኖች ና ለ አገልጋዮች እንዱሁም ለ መንፈስ ቅዱስ ረሃበተኞች ብቻ የተከፈተ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው ቻናሎች እንሆ ከታች ያለውን በመንካት ተባረኩበት ።
🧊🧊🧊🧊🧊🧊🧊
1ኛ ዮሐንስ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በእርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ።
¹⁰ ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው።
#የክርስቶስ_አገልጋይ_ቢና❤️🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
📌ክርስቲያን ሆናችሁ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ውስጥ ከሌላችሁ እውነት ነው የምላችሁ እጅግ በጣም እየባከነችሁ ነው አይዞአችሁ አሁንም አልረፈደም ከዚህ በታች የለውን በመምረጥ አንዱን ይጫኑ ይቀላቀላሉ መንፈሳዊ ህይወታቸውን ይለውጡ !!!!!
Читать полностью…❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ መንፈሳዊ ህይወቶንም ይቀይሩ
መልካም ዕድል!!!
የዛሬው የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በመካከላችን የገለጠበት እጅግ በጣም ከፍ ያልንበት ድንቅ ምሽት ነበረ😍😍😍🔥🔥🔥
ክብር ሁሉ ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን ሃሌሉያ🔥🔥🔥
ዛሬ የነበራችሁ ወዳጆቼ ብሩካን ናችሁ ፀጋሀ ይብዛላችሁ❤️🔥
ሰው እግዚአብሔርንም እራሱን (ሰውን) የሚያውቀው በክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
ምክንያቱም ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ስለሆነ ነው።
የእግዚአብሔርን ስም ማንነት ክብር ባህርይ መልክ በሙላት በምድር ላይ የገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ምክኒያቱ እግዚአብሔርን ያየው ከእግዚአብሔር የሆነው ኢየሱስ ብቻ ነው።
መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው #አንድ ስንኳ #የለም፤ #በአባቱ እቅፍ ያለ #አንድ #ልጁ እርሱ #ተረከው።
— ዮሐንስ 1፥18
ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች #ስምህን_ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ ቃልህንም ጠብቀዋል።
— ዮሐንስ 17፥6
እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ #ስምህን #አስታወቅኋቸው_አስታውቃቸውማለሁ።
— ዮሐንስ 17፥26
አብን ያየ ማንም የለም፤ #ከእግዚአብሔር #ከሆነ_በቀር፥ #እርሱ_አብን_አይቶአል።
— ዮሐንስ 6፥46
ከእግዚአብሔር የሆነው አብን አይቶታል ከእግዚአብሔር የሆነው ደግሞ ልጁ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
እኔ ግን #ከእርሱ_ዘንድ_ነኝ እርሱም ልኮኛልና #አውቀዋለሁ ብሎ ጮኸ።
— ዮሐንስ 7፥29
“ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? #እኔን_ያየ #አብን #አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ?”
— ዮሐንስ 14፥9
#እኔንስ_ብታውቁኝ #አባቴን ደግሞ #ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው።”
— ዮሐንስ 14፥7
እርሱም #የክብሩ_መንጸባረቅና #የባሕርዩ #ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤
— ዕብራውያን 1፥3
#በእርሱ (ክርስቶስ) የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤”
— ቆላስይስ 2፥9
ሰው እግዚአብሔርን በሙላት የሚያውቀው በክርስቶስ እንደሆነ ሁሉ ሰው እራሱን ወይም ሰውን የሚያውቀው በክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ምክኒያቱም ኢየሱስ የመለኮትን ሙላት የገለጠ ብቻ ሳይሆን የሰውነትንም ሙላት የገለጠ person ነው።
ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ያለውን ከፍታ ፍቅር ክብር ማንነት position ልጅነት በሙላት በሰውነቱ የገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
የሰውነትን ተክክለኛ ማንነት ማለትም ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ታስቦ የተፈጠረበትንና የተሰራበትን ትክክለኛ ዓላማ በምድር ላይ በሰውነት ተገልጦ በሙላት ሰውነትን የኖረው ኢየሱስ ነው።
የእግዚአብሔር ልጅነትን ጠርዙንና ጥጉን የገለጠው ኢየሱስ ነው።
ስለዚህ የሰውን ክብር የሰውን ማንነት የሰውን ስብዕና የሰውን ዋጋ የሰውን ሁሉ ነገር ለመረዳት ኢየሱስን ማወቅ ግድ ይለናል።
ሰው ኢየሱስን ሲያይና ሲያውቅ ለእግዚአብሔር ያለው ቦታ እንደሚቀየር ሁሉ ለሰውም ያለው አመለካከት ለሰው ያለው ክብር ለሰው ያለው ፍቅር ለሰው ያለው ቦታ ይቀየራል።
ዕብራውያን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።
¹⁵ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ + የለንም።
ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፥ ከደመናውም፦ #የምወደው_ልጄ ይህ ነው፥ #እርሱን_ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
— ማርቆስ 9፥7
#Christ_Centered🔥
#Servant_Bina🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
1ኛ ዮሐንስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ከእግዚአብሔር የተወለደ #ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ #ዓለምንም #የሚያሸንፈው #እምነታችን ነው።
⁵ ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ #ከሚያምን_በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?
ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ማለትም ዓለምን የሚያሸንፍበት አቅም በውስጡ አለ።
ዓለምን የሚያሸንፈው ግን እንዴት ነው? ወይም ዓለምን የሚያሸንፍበትን አቅም ግን እንዴት ነው የሚገልጠው? ወይም እንዴት ነው የሚጠቀመው? ብለን ስንጠይቅ መልሱንም ውስጡ ባለው እምነት ልክ ነው ይሆናል።
አማኝ ዓለምን የሚያሸንፍበትን ማንነትና አቅም የሚገልጠውና የሚጠቀመው ውስጡ ያለውን #እምነት ሲገልጥ ነው።
ዳግም የተወለደ አማኝ ሁሉ ውስጥ እምነት ቢኖርም የእያንዳንዱ አማኝ የእምነት መጠን ግን እኩል አይደለም። እያወራሁኝ ያለሁት በኢየሱስ አምነን ስለዳንበት እምነት ሳይሆን ዳግም በተወለደው ማንነታችን ላይ የተካፈልነውን መለኮታዊ ሕይወት በምድር ላይ የምንገልጥበትን እምነት ነው ያወራሁት።
አየህ መፅሐፍ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን የሚያሸንፍበት አቅምና ማንነት እንዳለው ይነግርህና ዓለምን የሚያሸንፍበት አቅሙንና ማንነቱን የሚገልጠው ደግሞ በእምነቱ እንደሆነ ይነግርሃል።
ስለዚህ ዓለምን ለማሸነፍ የመጀመሪያው ከእግዚአብሔር መወለድህ መሰረታዊ ጉዳይ ቢሆንም ይህንን የማሸነፍ ማንነትህን የሚገልጠው ደግሞ በውስጠኛው ማንነትህ መጠንከርና የእምነት ጉልበትህን መጨመር ደግሞ እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው።
ክርስትና መወለድ ብቻ ሳይሆን በተወለደው ማንነትህ ማደግና መጠንከር ነው የውስጠኛው ማንነትህ ሲጠነክር ደግሞ የእምነት አቅምህ ከፍተኛ ይሆናል የእምነት አቅምህ ከፍተኛ ሲሆን ደግሞ ዓለምንና በዓለም ያለውን ክፋትና ዲያቢሎስንና የዲያቢሎስን ሽንገላ ሁሉ ማሸነፍ ትችላለህ።
እምነት ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል የሚጠነክርና የሚያድግየሚገለጥ መለኮታዊ ዘር ነው።
የቃሉን መገለጥና የቃሉን ብርሃን በተሞላን ልክ ውስጣችን ያለው እምነት እያገደ እየጨመረ መለኮታዊ አቅም በሕይወታችን እየተገለጠ ይመጣል።
ያለ እግዚአብሔር ቃል እምነት ሊጨምርና ሊያድግ አይችልም።
እንግዲያስ #እምነት_ከመስማት ነው መስማትም #በእግዚአብሔር_ቃል ነው።
— ሮሜ 10፥17
ስለዚህ ዓለምንና በዓለም ያለውን ክፋት ለማሸነፍ እምነታችን ማደግና መጠንከር ይኖርበታል እምነታችን እንዲጠነክርና እንዲያድግ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል መሞላት አለብን።
አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ #የእግዚአብሔርም_ቃል #በእናንተ_ስለሚኖር #ክፉውንም ስለ #አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።
— 1ኛ ዮሐንስ 2፥14
ኤፌሶን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን #የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ #ልታጠፉ #የምትችሉበትን #የእምነትን_ጋሻ አንሡ፤
¹⁷ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም #የእግዚአብሔር_ቃል ነው።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ነገ እሁድ ማታ 3:30 የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን እንቀጥላለን🔥😍
መፅሐፍት ሁሉ ስለ ኢየሱስ ይናገራሉ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ኢየሱስን የሚገልጥ መንፈስ ነው እንደተለመደው መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በቃሉ ብርሃን ይገልጥልናል በቃሉ ብርሃን እንጥለቀለቃለን🔥🔥🔥🔥❤️❤️
አገልጋይ ቢና❤️🔥
❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ መንፈሳዊ ህይወቶንም ይቀይሩ
መልካም ዕድል!!!
#የኢየሱስ_ስም🔥
ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው #ከአለቅነትና_ከሥልጣንም #ከኃይልም #ከጌትነትም #ሁሉ #በላይና #በዚህ_ዓለም ብቻ #ሳይሆን ነገር ግን #ሊመጣ ባለው #ዓለም ደግሞ #ከሚጠራው_ስም #ሁሉ_በላይ በሰማያዊ ስፍራ #በቀኙ #ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ #የብርታቱ #ጉልበት ይታያል፤
— ኤፌሶን 1፥20-21