binte_hikeaeman | Unsorted

Telegram-канал binte_hikeaeman - Allah is one

152

"ከወዳጆቻችን መራቅ ልብን የሚያሳምም ከሆነ #ከAllah መራቅ ልቦናን ከነጭራሹ ይገድለዋል"

Subscribe to a channel

Allah is one

ሚስትህን በፍቅር ማየት
ስታወራት በፍቅር
ስትስማት በስስት
ስታቅፋት በናፍቆት
...
ሁሌም አሞካሻት!....

Читать полностью…

Allah is one

Jumaa mebruk 💓💓💙💙💗💗💙💙💚💚❤❤💖💖💕💕💞💞💝💝💜💜💛💛

Читать полностью…

Allah is one

ጁሙአ መብሩክ ❤❤💜💜💝💝💛💛💚💚💙💙💚💚

Читать полностью…

Allah is one

ዘንጊዎች በዘነጉ፣አሰታዋሾች ባሰታወሱ ቁጥር፣ በረገፈው ቅጠል፣ በፈሰሰው አሸዋ፣ ሰማይን ባደመቁት ክዋክብት፣ ውቂያኖስ በያዘው ጠብታ መጠን የአላህ ሰላትና ሰላም በውዱ ነቢያችን ሙሐመድ(ﷺ)ላይ ይሁን!💚

Jumaa Mubarek! 🕋

@muslims_couple || ፍቅር ሰባኪ TemUd

Читать полностью…

Allah is one

😊ድምፁ😊

ጢር ጢር እያለ ይጠራና ስልኩ

ይወጣል በቅፅበት አንድ ድምፅ ከውስጡ
ጆሮም ተቀብሎ ለልቤ ቢያደርሰው

ሌቤ ተደናግጦ አፌን ቆላለፈው

ለመናገር ቢጥር ቃላት ለማውጣት

ልሳኔ ተዘጋ ድምፁን በመስማት

አቤት ግርማ ሞገስ የድምፅ አወፋፈር
ዝንብሎ ቢሰማ ሱስ የሚያሲዝ አይነት
ሆነና ገጠመኝ የዚህ ስልክ ባለቤት

ሲናገር ሳደምጠው ሲያወራ ሳወራው

ሲያስቀኝ ሳስቀው ሲያናደኝ ሳናደው

በቃ ሁልጊዜ እንዲነው ምንሆነው

አጋጣሚ ሆኖ ድምፁ ሲቋረጥ

በጣም ያናደኛል የቴሌ ክፋት

ምናለ ቢፈቅዱ እንድሰማ ድምፁን

ሳዳምጠው ብውል በየለትተለቱ

እኔን ካልደከመኝ ምንሆኑ እነሱ?🙄
ፈጣሪ ሲፈጥር ሙሉ አይሰጥም አሉ
ፈጣሪ ሲፈጥር አንድ ያጎላል አሉ

ምኑ ጎሎት ይሆን? ድምፁን ተቀብሎ
ስንቱን አማለለ ይህን ድምፅ ተችሮ😊

Читать полностью…

Allah is one

.╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
....... የማይሽር ሽህረት....
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝


ክፍል...........4

በቃ አሁን አገባው። የሱ ሆንኩ። ለወራት ብቻ የማውቀው ግን ያፈቀርኩት ሰው ሚስት ሆንኩ። ካሁን በኋላ ቢያንስ የሆዴን የማዋየው ሠው አለ። አሁን ይበልጥ ጠንካራ ነኝ ብዬ አሰብኩ። ሰርጋችንን ስንመረቅ ልናደርገው አሰብን። ኢትዮጲያ አብረን መተን ኒካህ ካሰርን በኋላ ትንሽ ቆይተን ተመለስን። በቃ አሁን የ emrë ሁኛለው። ቱርካዊ ባልሆንም እንደ ባህላቸው በሱ ስም መጠራት ጀመርኩ ።
Emrëን ከልቤ አምነዋለው:: አብረን ነው የምንኖረው። ከ2 አመት በፊት fashion Design ስለተማርኩ በቅርቡ ስራ እጀምራለው። እስከዚያ ግን በሱ ወጪ ህይወታችን ይቀጥላል።


* * *

አንድ ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ ዘወትር ካጠገቤ የሚገኘው ባለቤቴ የለም። ሰዓቴን አየሁት 6:09 ይላል። emrë አርፍዶ ነበር የሚነሳው። ግንዛሬ ያለወትሮው በጊዜ ተነስቷል። ከአልጋዬ ተነስቼ ግቢውን፣ ቤቱንንና ሰፈሩን እየዞርኩ ፈለኩት። የለም። የት ሁኖ ይሆን?


(ቤቴን ለመሙላት ብዬ ትምህርቴን ካቋረጥኩ 3ወር አለፈኝ። በርግጥ ዋናው ምክንያቴ emre ትምህርቱን ትቶ ለኔ ሲሯሯጥ እኔ ግን ምንም አለማገዜ፣ ዲዛይነርነቱም ኪሣራ ብቻ መሆኑ እኔና emrë የሚያጨቃጭቅ የዘወትር ርዕስ ስለሆነ ጉዳዩን ለ OZgë አማከርኳት።እሷም ትምህርቱን ትቼ ቤቴ ብሆን እንደሚሻል ነገረችኝ። በሷ ምክር መሠረት ቤቴ አሁን ሠላም ነው።)

Читать полностью…

Allah is one

.╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
....... የማይሽር ሽህረት....
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

ክፍል........3

Imam hatip secondary School, turk, 6: 57 ሰዓቱ ሄዷል።

ትምህርት ተጀምሮ እየተማርኵ ነው። በሂጃቤ ይደርስብኛል ብዬ የምፈራው ጣጣ የለም። ምክንያቱም ይሄ ኢስላማዊ ት/ቤት ነው። አልሀምዱሊላህ አሁን 12ኛ ክፍል ነኝ። አልፎ አልፎ ሀናን (እህቴ) ትመጣለች፣ እኔም መብቱ ስላለኝ በየአመቱ እሄዳለው።

እነዚ ሁለት አመታት በጣም ደስ ይላሉ። ትንሽ ቋንቋ ቢቸግረኝም የ high school ት/ቴን ጨርሻለው ።ፈተናም ቢሆን ምርጥ ውጤት ነው ያመጣሁት። አሁን እረፍት ስለሆነ ወደ ሀገሬ መመለስ እችላለሁ።


ህይወቴ በጣም በተሳካ መንገድ አየሄደ ነው። አላህ ስኬትን እየሰጠኝ ነው። በዲኔም በትምህርቴም ጠንክሬ እየኖርኩ አልጋ በ አልጋ የሆነ ህይወት ነበር። ግን ምን ያረጋል ነበር ሆነ።
ቱርክ ባለ ዩኒቨርስቲ የ Astronomy ተማሪ ሳለሁ የ2ኛ አመት ትlቴን እየተከታተልኩ በነበረበት ወቅት ነው ëmre ከተባለ ቱርካዊ ጋር በፍቅር የወደኩት። ëmre የሚኖረው ብቻውን ነው ። እናት ና አባቱ ብዙም ትኩረት ስለማይሰጡት አስተናጋጅነት እየሰራ ራሱን ያስተዳድራል። ከሰዎች ጋር አይግባባም። በግቢው ውስጥ በየሄድኩበት አገኘዋለሁ። ያም ሆነ ይህ ግን ëmre ራሱ የፍቅር ጥያቄ አቀረበልኝ። ብወደውም እንኳ ጥያቄውን መቀበል ስላልፈለግሁ እንደ ቀልድ "ሀላልህ አድርገኝ"ብዬው ሄድኩ። ëmre ግን አመረረ። በቀጣዩ ቀን በምሳ ሰዓት ላይ ተንበርክኮ ትንሽዬ የቀለበት ሳጥን ከፈተልኝ። እንዳገባው ጠየቀኝ። ብዙ ነገር ስለሱ ማወቅ እፈልጋለው ። ምንም ያህል Ëmreን ባፈቅረውም ልቤ ግን እንቢ እንድለው ወተወተኝ። ላለመቀበል አሰብኩ። ነገር ግን በዛ ሁሉ ተማሪ ፊት መሆኔ፣ የ Ëmre የ ተቅለሰለሰ ፊት፣ በዛላይ ከፎቅ ቆማ የምትመለከተኝ የ high school ጓደኛዬ OZgë የድጋፍ አስተያየት ሀሳቤን አስለወጠኝ።በድንገት የቀኝ እጄን ጣቶች ዘረጋግጄ ሰጠውት ። ህንፃው በጩኸት ተናወጠ።



#ይቀጥራል........4 ╚═════ೋೋ═════╝

Читать полностью…

Allah is one

ነገ ትምህርትይጀመራል ። እስካሁን ምንም ምላሽ የለም።በቃ የአላህ ትዕዛዝ ነውና ዘንድሮም እዚው እማራለው። ዛሬ ባይሆን ነገ ይሆናል።
አይነጋ የለ ነጋ። የ 10 ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሰኞ፡ በጣም ደባሪ ቀን።
ብቻዬን አዲስ ክፍል ተመድቤያለው፡ ፡ የማቃቸው የድሮ ተማሪዎች ቢኖሩም መልሼ ልግባባቸው ግን አልቻልኩም። በድብርት ወንበሬ ላይ ተቀምጬ ሳለ ድንገት አንድ ልጅ ወደኔ አቅጣጫ ሲመጣ ተመለከትኩት። በጣም ደነገጥኩ። አላቅም ግን... ወዲያው አዕምሮዬ አንድ ነገር ሹክ አለኝ፣ "ያባትሽ ተስፋ ፣ ሀላልሽን ብቻ " ኡፍ! እኔጋ አደለም። ከፊት ለፊቴ ያለው ወንበር ጋር ነው ጉዳዩ።
ትምርቴን በጥሩ ሁናቴ እየተከታተልኵ ነ ው፡፡
አንድ ቀን ከአጎቴ ጋር በጣም ተጣላን። ከዚያን እለት ጀምሮ ለሳምንታት ከአዕምሮዬ ጋር ስሟገት ከቆየው በኋላ ነገሩን ለጓደኛዬ አማካርኳት። ቤቱን ጥዬ የራሴን ህይወት ለመጀመር እንዳሳብኩ ነገርኳት። እሷም h Biology አስተማሪያችን ነገረችው። በጣም አዘነብኝ። እንደዚ በማሰቤ፣ ተቆጥቶ መክሮ አሳመነኝ:: አላህ ይስጠውና።


ከፊት ለፊታችን ያለው ክፍል የነሳሂብ ነው። የምቀመጥበት ቦታ ደግሞ ከበር ሲገባ ሲወጣ እንዳየው አመቺ ነው። ለምን እንደሆነ ባላቅም ሁሌ አይኔ እዚያ ክፍል ይንከራተታል። እሱም ቢሆን በሰበብ አስባቡ እኛ ክፍል ይመጣል።

እንዲህ ከራሴ ጋር እየታገልኩ ወራት ተቆጠሩ። የካቲት 2 ላይ አንድ መልዕክት በ Email ተላከልኝ። በነገራችን ላይ ባለፈለታ ለ scholarship Interview ሄጄ ነበር። በጣም ባይሆንም ጥሩ ነበር።
መልዕክቱ ደስ ይል ነበር። ለስኮላር ሺፕ ከተመረጡት 500 ተማሪዎች መሀከል አንዷ ሆንኩ። አልሀምዱሊላህ!!! በደስታ ሰላቱ ሹክር ሰገድኩ።
.... ግን.... ካሁን በኋላ ሳሂብን ዳግም አላየውም። አሁን ነበር በራሴ ያዘንኩት:: እንደዛ ስሸልል እንዳልነበር አሁን ግን ፍቅር ዳግም ይዞኝ አረፍኩት። አይ ፍቅር? በህይወት ዉስጥ ቅመም መስለህ ትገባና ሲያልሙት የኖሩትን ህልም ሁላ ጉም ታደርገው የለ?
ሆነም ቀረም ልሄድ ነው። ካልያዝኩት ፍቅር ይልቅ የያዝኩት የአባቴ ደስታ ይሻለኛል። ቤተሰቦቼ ሁሉም ደስ ብሏቸዋል። አባዬም መቶ የሸኚ ስርዓት ተደግሷል።
ድጋሚ .. ድጋሚ አዲስ ህይወት ልጀምር። ዳግም ሌላ ዕድል። ማንም ጓደኛ፣ ማንም ዘመድ በሌለበት ሀገር ሌላ የህይወት ዕጣዬን ላፅፍ።
መጋቢት 2 በረራ ይኖረኛል። ዛሬ ደግሞ ቀን 27 ነው። ልቤ ቱርክ የተባለች ሀገርን ለማየት በጣም ጓጉቷል። ልክ ያኔ አ.አን ለማየት እንደጓጓሁት። ግን ደግሞ እዚህ የምተወው ነገር ባይኖር ደስ ባለኝ ነበር። በህይወት ውስጥ ሁለት ምርጫ የለም። አላህ ላገራለት ሲቀር። አዕምሮህ ያመነበትን ነገር ምረጥ። በዛ ውስጥ አላህ መልካም ነገርን ያደርግልሀል። እኔም አዕምሮዬ ያመነበትን መርጫለው።
ከመሄዴ በፊት አንድ ነገር ለማድረግ ፈልጌያለው፡ በቀን 30 ማለትም ዕሁድ ሳሂብን ለማናገር። በርግጥ አንድም ቀን አውርቼው አላቅም። ግን ቢያንስ ልምክር። ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ስለ ፍቅሬ ልነግረው አልኩ። ቤቱን ስለማላውቀው ያለኝ አማራጭ በጓደኛው ያብስራ ማስጠራት ነበር። ሊጠራልኝ ሄደ።
መጣ. ወጣ.. በህይወቴ ልቤ እንደዚህ ሲመታ ትዝ አይለኝም። በጣም ፈራው። ከፊት ለፊቴ ቆመ:: በትኩረት እያየኝ "ምነው? "አለ በጎረነነ ድምጹ። "እ..... ያብስራ ምንም ነገር አልነገረህም? "
ከዚያ አንገቱን ደፋ አደረገና "ኧረ እኔ አለኝ (ጓደኛ )"ይህን እንዳለ እየሮጠ ሄደ። በቃ አለቀ። ሳሂብን ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናበትኩት። ሳላገኘው አጣውት።

ዛሬ መሄዴ ነው። ሁሉም እየሸኘኝ ነው። በዚህ ሰዓት አንድ ሰዉ ባይቀር ደሰ ባለኝ ነበር። ግን በቃ... ህይወት በፈለግናት ሳይሆን አላህ በፈለጋት መንገድ ትሄዳለች። ሰዓቱ እየደረሰ ስለ ነበር ከቤተሰቦቼ ተለይቼ ሻንጣዮን እየጎተትኩ ወደ አዲሱ ህይወቴ አመራሁ።


#ይቀጥራል.........3 ╚═════ೋೋ═════╝

Читать полностью…

Allah is one

ልቤ ክው ድንግጥ አለ 😭 አብዱ ከሪማን ይወደታል የራሱ መድረሳ ልጅ ።

የመድረሳው ሃላፊ አብዱን ምን ያህል እንደሚወደው ሳስብ ደሞ ተሰማኝ

.. ምንም ሳልናገር አንዴ መጣሁ ብየ ወደመታጠቢያ ቤት አመራሁ .

--------
ትረዳው ይሆናል ፣ የፍቅርን ትኩሳት
ግሎ እንደሚያቃጥል፣ ልብ ላይ እንደሳት

ጊዜው ሲፈራረቅ ሲነጋ ሲመሽ
የጨለማ ጨረቃ የቀን ፀሀይ ነሽ

የበሰለ ልጅ  መቼም ደጅ አያመሽም
ጥለሽኝ ይሆናል  አንቺ ግድ የለሽም
መድሃኒት አልከጀልኩ ለምኔ ለምኔ
የአንቺ አይን እኮ ማረፊያ ነው ለኔ
ጨዋታውም ሀላሉም ሁሉም ደግ ነበር
ወንድም መቀስ ሁኖ መለያየት ባልነበር

╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
....... አልፋና እና ከሪማ....
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
ምዕራፍ አንድ ተፈፀመ

Читать полностью…

Allah is one

" ማስጠንቀቂያ ለባልየው..."
[ ✍ ሶፊያ አህመድ ]

ውዱ ባለቤቴ እንደምን አለህ? አለሁ እኔም ደህና ነኝ። ይኸው ገና ሳንጋባ ስላንተ በማሰብ ተወጥሬያለሁ!

ምን ባክህ ላጤነት ይሰለቻል! ይኸው አንተ የምትመጣበትን መንገድ እየገመትኩ፤ በዙረት ሀገሩን እያሰስኩ እግሬ ቀጥኗል። ስትመጣ ብዙ የምትጠግነው ነገር ይኖራል።

ወደ ማስጠንቀቂያዬ ከመግባቴ በፊት ግን አንድ ልጠይቅህ የምፈልገው ጥያቄ አለ...ቆይ ግን የት ሆነህ ነው? ኧረ ቶሎ ና ወይ ደሞ ያለህበትን ንገረኝና እኔ ልምጣ...በናፍቆትህ አረርኩ እኮ!

ለማንኛውም ትንሽ የምልህ ነገር አለኝ።አንዴ ቀልብህን ሰብሰብ አድርገህ ስማኝ...
ይኸውልህ ስንጋባ ቤት አምሽቶ መግባት ምናምን እንዳታስበው! አንተን ቶሎ ለማግኘት ብዬ መሰለኝ እኔ በጊዜ ገብቼ እራቱን አዘጋጅቼ፣ ቡናውን ፏ አርጌ አቀራርቤ እኔም ፏ ብዬ የምጠብቅህ። እና አንተ ማን ስለሆንክ ነው አምሽተህ የምትመጣው? ማን ፈቅዶልህ? ከአሁኑ አስብበት.. ካመሸህ እዛው ያመሸህበት እደር እንኳን አልልህም...ሆ ደሞ በራሴ እጅ እራሴ ላይ እሳት ልለኩስ እንዴ? ባይሆን አንተን በመጠበቅ ስለሚደክመኝ ቡናውን ታፈላለህ...እስከ ቶና ድረስ...እግሬንም ታጥበኛለህ...ወደ መኝታም የምትወስደኝ አቅፈኸኝ ነው።

ደሞ ደሞ በእያንዳንዷ ደቂቃ ስላንተ ማወቅ እፈልጋለሁ..." ምግብ በላህ ፣ ጠጣህ፣ ስራ ገባህ፣ ከማን ጋር ነህ? ፣ ስንት ሰአት ነው የምትመጣው? ፣ የት ሆነህ ነው?፣ ...ምናምን ልልህ እችላለሁ...እንደጨቅጫቃ ሚስት ደሞ እንዳትቆጥረኝ። እንዳልኩህ በየጊዜው ስላንተ ማወቅ ስለምፈልግ ብቻ ነው! እንደውም ከቻልክ ቀድመህ እራስህ ደውለህ ብትነግረኝ ደስ ይለኛል።

ኧረ ዋናውን ነገር እረስቼው...ከሌላ ሴት ጋር ፈገግ እያልክ... ኧረ የምን ፈገግ ቀና ብለህ እያየሀት እንድታወራ አልፈልግም! ስለምቀና ደሞ አይደለም! " እና ለምን? " በቃ አልፈልግማ! አልፈልግም ካልኩ አልፈልግም ነው!

ደሞ አንዳንዴም ተቆጣኝ...ልክ እንደታላቅ ወንድም ቁጭ አርገህ በደንብ ተቆጣኝ! ሳጠፋ... ( ተቆጣኝ ነው ደሞ ያልኩት ስለምት ጭራሽ እንዳታስብ! ) እንደጓደኛም አማክረኝ! ካንተ ውጪ ሌላ የልብ ጓደኛ እንዲኖረኝ ስለማልፈልግ!

ሌላው በናትህ ቤቱን አታዝረክርክ! ካልሲህን እያወጣህ በየቦታው አትጣል! የበላህበትን እቃ ሳታነሳ እንዳትነሳ! ስራ መስራት አልወድም ምናምን እያልክ እንዳትቀብጥብኝ...ለነገሩ እተማመንብሀለው እንደዚ እንኳን አታደርግም!

አታድርግ ያልኩህን ነገር ደሞ እያደረክ እንዳታናድደኝ! ስናደድ በጣም ነው የማስፈራው! እስከ 3 ደቂቃ ሙሉ ጨክኜ ዝም ልልህ እችላለሁ። ስርዓት አድርግ ከተናደድኩ ዝም ብዬ ነው የማቅፍህ! የዛኔ ታድያ ምንም እንዳታዋራኝ! እቅፍፍ ብቻ...

እንግዲህ ባልየው አስበህ ግባበት። ሳቅህ ጥንካሬዬ ነውና ሁሌም ፈገግ ማለት እንዳትረሳ! ስንገናኝ እጅህን ከእጄ እንዳትለየው፤ ከእቅፍህ እንዳታወጣኝ!

የወደፊት ባሎቻችሁን ለማስጠንቀቅ ይሄንን ያጋሩ። ማን ያውቃል ይጠነቀቅበት ይሆናል። ☺️😉

Читать полностью…

Allah is one

😊አልፋና ከሪማ ❤️

ክፍል ስድስት 6⃣
(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ)

ሂወት ላይ ስኬታማ ሰወች እርሃብተኞች ናቸው ። ህልማቸው ከሌላው በተለየ መልኩ ሚርባቸው !!!


.. ይህ የእቃች የ አቅርቦት ሂደት ነው ።

እና ይህ ከሆነ የአልፋ ልጆች እና አልፋ ምን ያህል ሚና ይጫወታሉ ምንስ ግንኙነት አላቸው ስንል ደሞ ..

አሁን ይሄን በስልክ መሰልነው ከስልክ ውጭ ያሉ እቃወችም አሉ እና አልፋ እቃወች ላይ በቀጥታ አምራች እና ገዢ ሚገናኝበት ሲስተም ዘርግቷል ለዛውም በተለየ መልኩ ብዙ አቅርቦቶች በቅርብ ጊዜ ይጀምራል ።

ለጊዜው ግን ስልጠናውን በራሱ እንደ አንድ ሽያጭ አርጎታል ማለት ትምርቱ ራሱ ሽያጭ ነው ።
ምክኒያቱም ይህ ስልጠና ከአስፈላጊም በላይ ነው ለምሳሌ የጓደኞችህን ስም ንገረኝ አለኝ .
እኔም ማሜ ማሂር አብዱ አልኩት
ይህን ስልጠና ለማሜ ነገርከው አእምሮው እንዲታነፅ ስለቢዝነስ አጠቃላይ ነገር እንዲያውቅ ብለህ አልፋን አስገነዘብከው ራሱን ለመገንባት አልፋን ለተቀላቀለው አላማውን እና ግቡን እንዲቀርፅ ላደረከው አንተ በጣም ብዙ ብር ታገኛለህ ( ምክኒያቱም ወጣቱን ስለ ስራ ማስገንዘብ ስለሆነ አላማችን)
ከዛ ደሞ ማሜ ሂዶ ጓደኞቹን ዘመዶችን ወደ አልፋ ሲጠራ አንተም ታሳቢ ይሆንልሃል ከማሜ አንዱ ጓደኛ ሰውን ከጠራ ደሞ አንተም ማሜም ተጠቃሚ ትሆናለህ ። አሁንም ወደታች በወረደ ቁጥር ከላይ ያለሀው አንተ ተጠቃሚ ትሆናለህ በማሜ በኩል የጀመርከው ዝርጋታ ማሜንም አንተምም ውጤታማ ያረጋል ይህ በማሜ ብቻ ነው የዘረጋሀው ።
በአንድ በ5 ሰው ሰው ብቻ ከዘረጋሀው ስኬታማ ያረግሃል እነሱ በጠሩ ቁጥር ላይኞቹ እየተጠቀሙ ነው ሳታስበው የአልፋ አካውንትህ ላይ ብዙ ቆጥሮ ታገኘዋለህ። ስኬት ላይ የወጡ ሰወች አብዛኞቹ ይህን የአልፋ አንዱ ሲስተም ተጠቅመው ነው ለዚ የደረሱት ።
ከዚ በላይ ውጤታማ እና ሁሉም ሚሰራው ደሞ ..

አልፋ ውስጥ ያለውን ስልጠና በበቂ ሁኔታ ተምረህ እዛው የተወሰነ ለስራ ሚሆን በጀት ሰብስበህ ከዛ በተማርከው ትምርት እና ባወቅከው እውቀት የያዝከውን ብር ወደ ስራ ክህሎትህን ወዳፍላጎትህ አጠቃቀሙን አውቀህ ትጠቀመዋለህ ። ከዛ በተረፈ የራስህን grop ምስረታ የገለፃ ቢዝነሶች አሉ እነዛ ሁሉ ስትገባ ነው ምታውቃቸው በውጭ ሳትገባ ልነግርህ ምፈልገው ይሄን ብቻ ነው ።

ሰአቱ መሸ ቤት እንዳይጨነቁ ሰጋሁ ብዙ ስላወራን ተሰነባብተን ተለያየን..

እኔም በማታ ወደሰፈሬ ተጓዝኩ በምንገዴ ላይም የሆነ ነገር አሰብኩ ..

እኔ እቃ የማስመጣት እና እዚው የማስረከብ ፍላጎት አለኝ ይህን ህልሜን ከኔ በመቀጠል ትልቅ ሚና ሊጫወትልኝ ሚችለው አልፋ ነው ።ስልጠናውን በደንብ ወስጄ ከማን ጋ እና በምን መልኩ ነው ምሰራው ? እሱን ማወቅ አለብኝ ለበጀት ሚይዘውን ብር እንዴት ወደስኬት እቀይረዋለሁ ? ብየ አሰብኩ ከዛ ውጭ በራስመተማመኔ እንዲመጣ እና የነበረኝን ማንነት መተው እፈልጋለሁ ።

ለመግባት ወሰንኩ ግን እንዴት ይህን የመጀመሪያ ፓኬጅ ክፍያ ላግኝ? ከጥቅሞቹ አንፃር ትንሽ ነው ። ግን ያም ገንዘብ ለኔ ከባድ ነው! የመጀመሪያውን ፓኬጅ 5000 ምናምን ብር ከየት ላምጣው? ከአብዱ ልበደር አሰብኩ ወይስ በዚ ጭንቀት ሰአት ኡሚን ልጠይቃት ወይስ የሆነ አሪፍ ነገሬን ልሽጥ አላውቅም ብቻ ግራ ተጋባሁ ቤት እንደገባሁ ሻወሬን ወሰድኩ ልብስ ቀያይሬ የት እንደነበርኩ ተጠየቅኩ መናገር አልፈለኩም? እነሱን ሳያቸው ግን እነሱን ተለውጦ የመለወጥ ጉጉቴ ጨመረ ካለንበት ችግር እና ከሂወቴ ውጣውረድ በቃኝ ማለት እንዳለብኝ ተረዳሁ ።
ጭንቀት በቃኝ !! ማጣት በቃኝ !! ሀዘን በቃኝ። በባህሪ መተቸት በቃኝ ። ትልቁን ሰሚር ተመኘሁት። በህልሙ ሚኖረውን ሰሚር ።
Risk ወስጄ አልፋን መሞከር አለብኝ ለህልሜ ስል ብጎዳ ራሱ መቆፈር እና መዳፈር መወሰን መምረጥ !!
ስኬት ላይ እንደሚያወጣ አወቅኩ ። አልፋ አብዛኛውን ሰአት እንቅልፍ ነስቶኝ ለሊቱ አለፈ ህልማችንን በምናባችን መኖር እንዴት ነው ሚያስደስተው ።

በነገው ቀን ስለአልፋ ለአብዱ ሳልነገርው ብር እንዲያበድረኝ ጠየቅኩት ለምን ብሎ አልጠየቀኝም ያለኝን እንካ ብሎ 3000 በር ሰጠኝ
ከማሜ 1000 ብር አገኘሁ የቀረው 1700 ብር በራሴ እና ከኡሚ የተወሰነ እንደምንም ብየ ተቀበልኳት ብሩ ሀሙስ ቀን እንደሞላ ስልጠናውን በ Online እና በአካል ጀመርኩት የአላማህን እና የእቅድህን ፎርም ያስሞሉሃል ራስህን እንድትገነባ መንገድ ይጀምሩልሃል ።

በመጀመሪያው ስልጠና ስለሂወታችን ግብ ስለምንኖርለት አላማ ስለተፈጠርንበት ስለህልማችን ነገረን አረ ብዙ ብዙ ነገር .. በከሰአቱ መድረሳ ሂጄ አብዱ ሚለውን ሰማሁት .. የመጀመሪያው ስልጠና ብቻ ሂወቴ ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል ምን ላይ ነኝ? ምን እየሰራሁ ነው? ለምን አልሰግድም? ለምን ዲናዊ ሂወቴን አልኖረውም ነገ እኮ ሁሉንም ትቼ እሄዳለው !!

ስልጠናውን እየተገበርኩ ስለስራም እያወቅኩ ሳምንታት አለፉ ። መሀል ላይ ግን ሰውን ለመጥራት አሰብኩ ማሜ ሱቅ አለው ሱቁን በምን መልኩ መጠቀም እምደሚችል ከአልፋ ትምርት መውሰድ እንዳለበት ተረዳሁ ። ማሂር ቁምነገረኛ ሰው እንዲሆን ቀልዱን በመጠኑ እንዲያረገው እና ህልሙን መቅረፅ እንዳለበት ተረዳሁ ። አብዱም ከዱንያው ሂወት የራቀ እንደመሆኑ ውጩን አለም እንዲያየው ፈለኩ በዛውም በነሱ ማገኘው ጥቅም ስላለ ያን ጥቅም ለቀጣዮቹ ስልጠናወች እና ብድሬን ለመክፈል ይረዳኛል .. ሁሉንም የአልፋ ፕሮግራም ጋበዝኳቸው ማሜ ግን አልተመቸውም ነበር ለመምጣት። እነ አብዱ በጣም ወደዱት ከዛም አብዱ የአልፋን ስልጠና ምሰለጥነው ያንተን መለወጥ አይቼ ነው ። ሂወትህ ላይ ትልቅ ነገር ፈጥሯል ማሻአላህ አሁን መሆን ያለብህን ሁነሃል አለኝ ማሂርም አሽቃሸጠለት ትንሽ ..
ይህን ስሰማ በጣም ደስ አለኝ አብዱ የኔ ሁብ ስወደው እኮ የራሴ ምትለው ምርጥ ወዳጅ ሲኖርህ ወንድማማችነትህ ሲጠነክር ዱንያ ላይ ትልቁ ሀብት ወንድምነት ነው ትላለህ እኔም ወደስልጠናየ ከከሪማ ጋር እየተመላለስኩ መውሰዴን ቀጠልኩ ..

ውይ ሳልነግራቹ ከከሪማ ጋር ነው ስልጣውን ምወስደው በሷም ነው የገባሁት በጣም ጎበዝ ናት ለማንም ፊት አትሰጥም ከኔጋም እንመላለሳለን እንጂ ስንመጣም ስንሄድም ኤርፎኗን ሰክታ ትመሰጣለች ሁሌ ብቻየን ነው ምቀረው ምን አይነት ግፍ ነው በረቢ ። ግን አይኗን ብቻ ማየቴ በቂ ነው አንዳንዴ ላለመክፈል ነው ኤርፎን ምትሰካው እል ነበር ። መጎዳቴ ሲበዛባተ ነው መሰል ስትገባ ታክስ ውስ ስንገባ መክፈክ ጀምራለች ። በስኬት ጉዞ ብዙ ነገር ያጋጥመናል ።

ከአንድ ሳምንት በኋላ እነማሂር ተቀላቀሉ

ከደርሱ ከትምርቶቹ በስተጀርባ ከሪማ እኔ ላይ ኩራት ማሳየቷ እና ልዩ ስብእናዋ በጣም እንድወዳት አርጎኛል ። የአልፋ ስልጠና ሂወቴን ሰጦኛል ሙሉ ለሙሉ ሀሳቤን ለሱ ነው ማድረግ ምፈልገው ።

እና እንምወዳት መንገር አለብኝ ።
ባለኝ ሁኔታ የወጣትነትን ሂወትን ባላይም ኒካህ ብቻ ባስራለት እድሜዋ ደርሷል ታገባለች ብየ ከምፈራው ትልቅ ጭንቀት እድናለሁ። ግን እፈራለሁ ከሪማ ሂወቴ ላይ ብትገባ ምን ያህል ሂወቴ እንደሚስተካከል አሰብኩ ።

Читать полностью…

Allah is one

😊አልፋና ከሪማ ❤️
ክፍል አምስት 5⃣

(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ)

የአልፋ ስልጠና ብትፈልግም ይለውጥሃል ባትፈልግም ይለውጥሃል !!!!


ከዛ መድረክ መሪው ቆይታ እንዴት ነበር ብሎ ወደቀጣይ ፕሮግራም እንሄዳለን በማለት የሆነች ሴት ለንግግር ጋበዘ..

ይገርማል የጋበዛት ሴት ፊቷን የተሸፈነች ገና የ20ወቹ መጀመሪያ ኒቃብ የለበሰች ሙስሊም ሴት ናት ። ኮንፊደንሷ ደስ ይላል
በኩራት ነው ወጥታ መናገር የጀመረችው ..
ስሜ አሊያ ይባላል የአልፋ 3ኛ ፓኬጅ ሰልጣኝ ነኝ ። ብዙወቻችን የሆነ ነገር አልተረዳንም እና አመለካከታችንን መቀየር አለብን መጀመሪያ አእምሯችን ሲሰፋ እና ሲገነባ እና አላማችንን ስናውቅ ነው ወደራሳችን ቢዝነስ ምንገባው የራሳችንን ስራ ፈጥረንም ይሁን በተፈጠሩ ስራወች ስኬታማ ልንሆን ምንችለው። እኛ ጭንቅላታችን ለስራ ምን ያህል ክፍት ሁኗል ምን ያህልስ ለስራ ግንዛቤ አለን? ? የአልፋ ስልጠና ከምታስቡት በላይ ነው አንድ ቀን ወስዳችሁት ራሱ ሂወታችሁ ላይ ልዩ ተፅእኖ ይፈጥራል ። ስነልቦናችሁን ያሰፋል የገንዘብ አያያዝ እና የሰአት አጠቃቀም ያስተምራል ሳናስበው የሆነ ሰአት ትምርቱ ራሳችን ላይ ሰርቶ እናገኘዋለን ። ለራሳችን ያለን ግምት ይጨምራል በሂወታችን ያለንን ግብ ያሳውቃል ሂወታችን ለማስመር የአልፋ ስልጠና መውሰድ ግዴታ ነው !!!

የሰው ልጅ ሲፈልግ ተአምረኛ ሲፈልግ ሰበበኛ ነው ። ተአምረኛ መሆን የፈለገ ሚከፈለውን መስዋትነት ከፍሎ አእምሮውን ያንፃል ሰበበኛ የሆነ ደሞ በተለያዩ ሰበቦች ራሱን ከትልቅ ድግስ ያስቀራል። ነገሩን ሳያየው ሳያጣራ ውስጡ በፈጠርው ጥርጣሬ ከስኬት ይዘገያል ። በጣም እድለቢስ ሰው ማለት ለኔ እሱ ነው ።
እኛ ሀበሾች አዲስ ነገር አንወድም አዲስ ነገር ስናረግ ምንጠፋ ነው ሚመስለን አልፋን ለመቀላቀል ስለአልፋ ግንዛቤ የሌለው ሰው እንጠይቃለን ነገር ግን አላወቅንም እሱ .. የህልማችን ሰራቂ ነው የኛን ስኬት ይመኛል ነገር ግን በሱ አስተያየት እንድንመራ ይፈልጋል !!

አንተ በውስጥህ ምታልመውን ማንም አያልምም ! አላማህን እቅድህን ማንም ሊኖረው አይችልም ካንተ በላይ ማንም አያውቀውም !!
ለምን ሌሎችን በሂወትህ ወሳኝ ታረጋለህ ? ለምሳሌ እኔ አልፋን ስቀላቀል ቤተሰብ ከልክሎኝ ነበር የመጀመሪያውን ምዝገባ ለመቀላቀል ከብዙ ጓደኞቼ ተበድሬ ነበር የገባሁት ቤት በጣም እወቀስ ነበር ።

ነገር ግን እኔ ቤተሰቦቼን በጣም ስለምወድ ሂወታቸውንም መቀየር ስለምፈልግ በራሴ የሂወት ምርጫ ላይ እንዲገቡ አልፈቀድኩም ። አሁን ሂወቴ ላይ ለውጥ ሳመጣ የቤተሰቦቼን ሂወት ስቀይር በልጆቻቸው ምንገድ መግባት እንደሌለባቸው ተረዱ ዛሬ ላይ ፊት ለፊቴ ጋብዣቸዋለሁ !!

( ሁሉም አጨበጨበ) ቀጠለች ..

በርግጥ ወላጆቻችን ከኛ የበለጠ የመኖር ልምድ አላቸው እናማክራቸዋለን ። ነገር ግን ስለተጨባጩ ስላለንበት ዘመን እንደኛ ግንዛቤ የላቸውም እነሱ ሚመለከቱት ባሰቡት የአእምሮ ልክ ነው እኛን ለማሳደግ ብዙ ነገር አይተዋል በቃቹህ አሁን የኛ ተራ ነው ማለት አለብን

እኛ እነሱን ከፍ ለማድረግ ብለን ራሳችንን እንሁን !! ከቻልን እንጋብዛቸው ከኣልጣኞቹ ጋር እንዲያወሩ አርጓቸው ካልተረዱ ግን የራሳችሁን ሂወት ራሳችሁ ምሩ !! አሁን ላይ በ5 አካውንት መስመሬን ዘርግቼ ምርጥ ተከፋይ ነኝ በስልጠናው ተምሬ በተገነዘብኩት ልዩ የስራ ግንዛቤ ወደምመኘው አከፋፋይ ተቀይሬያለሁ አልሃምዱሊላህ አልፋ ለካ ሂወት ነው አሁን ደሞ ሰፈሬ ላይ የኢስላሚክ ትምርት ሚሰጥበት ልዩ ቦታ ልንገነባ ነው ።

" ብላ ንግግሯን ቋጨች ከሷ በኋላ አሰልጣኞቹ አወሩ ብዙ ብዙ ነገር አካፈሉን ።

ያኔ አልፋ እንደምገባ ውስጥ ሁኜ ወሰንኩ። ፕሮግራሙ ተጠናቀቀ


ከከሪማ ጋር ወጣን ብዙ ጥያቄ ውስጤ ላይ አለ እዛው ቦሌ የሆነ ካፌ ገብተን እንድናወራ ጠየቅኳት እሽ አለች..

ቢዝነሶቹ ምን አይነት ቢዝነስ ናቸው? እና ደሞ ስልጠናው እንዴት ነው ሂወት ሚቀይረው አንቺ ገብተሻል ወይ? ምን አይነት ነገር ፈጠረብሽ? የኔ ጥያቄወች ነበሩ ።
ካፌ ላይ ቁጭ ብላ ያ ሚያምረው አይኗን ያለእፍረት እመለከታለሁ እሷ ግን ሀያእ ( ይሉንታ) የሚያጠቃት ልጅ ስለሆነች በሙሉ አይኗ እንኳ አላየቺኝም ምናልባት በቴሌግራም ስላወራን እንጂ አንድ ላይ ካፌ ለመቀመጥ እሽ ምትለኝ አይመስለኝም።

በለዘበ አንደበት ሰሚር ስልጠናውን የወሰደ አይተሃል ።
እኔ ገና የመጀመሪያ ፓኬጅ ስልጠና ላይ ነኝ ይህ በራሱ ግን ዲኔ ላይ እና ከሰወች ጋር ያለኝን ግንኙነት አሳምሮታል በትንሽ ምክኒያት ተስፋ ቆራጭ እና ተበሳጭ ነበረኩ ።
ነገር ግን በማሳየው ፈገግታ እና ልዩ የአቀባበል ገፅታ ጓደኞቼ ቤተሰቦቼ ጋር ልዩ ትኩረት ስቤያለሁ ። ይበልጥ ለአላማየ እንድኖር እና እቅድ እንድነድፍ አርጎኛል ከዛ በተረፈ ስለቢዝነስ ለጠየቅከኝ ከኔ በላይ ነገ 22 መገናኛ የኛ Team መሪ ሂደህ አግኘው ማታ ስልኩን በቴሌግራም እልክልሃለው እሱ በደንብ ይነግርሃል " ብላኝ ሀሳቡን ዘጋችው ከዛ እንዲ አለችኝ
አልፋ ማለት .. ሰውን አመለካከቱን በማሳደግ እና በራስመተማመኑን በመጨመር ሀገራችንን እያሳደገ ያለ ካምፓኒ ነው ከተከፈተ 2 አመቱ ሲሆን ውስጥ የገባ እና አእምሮውን የተጠቀመ ስኬታማ ይሆኑበታል በደንብ ያላወቀው አላወቀውም ነው ። ነገር ግን ትምርቱ በተግባር ሚተገበርም ነው የራሱ Workout አለው አለች " እና ሰሚሬ መሽቷል እንሂድ የቦሌን ምርጥ ጎዳና ስታይ እዚው ማደር አማረሃ ብላ ሙድ ያዘችብኝ ?

እኔም አረ ቤተል ይግደለኝ ብያት ስለሸገር ሰፈሮች እያወራን ታክስ ገባን ስለቤተሰብ ስለ መድረሳቸው ብዙ ብዙ ነገር አወራን ከጀሞ 3 ትንሽ ወደላይ ከፍ ብሎ ያለው ሰፈር ፉሪ እንደምትኖር ነገረቺኝ ። ሜክሲኮ ላይ ተሰነባብተን ተለያየን እኔም ስለራበኝ ሜክሲኮ እርጥብ ብለው ሚሸጡትን እየበላሁ ወደ ሰፈሬ አቀናሁ

ቤት እንደገባሁ ኡሚን ስሚያት ተጣጥቤ ቱታ ቀይሬ ከፋዘር ጋር ቤት ቡና መጠጣት ጀመርን። ዛሬ አባየ ለምን እንደወጣሁም አልጠየቀኝም ማታውኑ ተጫወትን አባየም ትንሽ የአጎቴን ነገር እየረሳው ይመስላል ። ለነገሩ የቤታችን ኢኮኖሚ ሲያንስ ሳይወድ በግዱ ያስታውሰዋል። እዛው ቤት ኢሻ ሰግደን ወደክፍሌ ስገባ አብዱ 7 ጊዜ ደውሏል ማሂር 3 ጊዜ። ዛሬ ደሞ አዲስ ሰው ደውሏል ፉአድ ምርጡ እና የዋሁ ወዳጃችን ( አሁን ድሬድዋ ግቢ የሄደው) ነገ ስለምንገናኝ ከማሂር ጋር አንድ ላይ እንደውላለን ብየ ተውኩት ለአብዱም አልደወልኩም ።ወደቴሌግራም ስገባ የአሰልጣኙን ስልክ ከሪማ ልካዋለች ቢመሽም ወዲያውኑ ደወልኩለት እና ነገ ከሰአት ከሱ ጋር መገናኘት እንደምፍለግ ገለፅኩለት እሱም ፍቃደኝነቱን ገለፀልኝ ። እኔም ወደእንቅልፌ አቀናሁ ።

በነገዋ ሰኞ ማሂርን Class አገኘሁት ስለ ትናንት ውሎየ እና የት እንደነበርኩ ጠየቀኝ እኔም ከሞላ ጎደል የትናንቱን ተአምራዊ ቀን ነገርኩት እሱም በመገረም ታዲያ አመንካቸው አለኝ? ? እኔም አንተ ቀልድ ነዋ የያዝከው ወላሂ ቼኩን ሲሸለሙ ነው አይቼ የመጣሁት ። በዛ ላይ ስለስልጥናው ይህ ባዶ ጭንቅላትህን አሳውቀው አልኩት እሱም ቆይ ይህ አሰራር የት ነው የተጀመረው አለኝ ?
እኔም የተጀመረው ውጭ ሀገር ነው አሰራሩ ከ20 አመት በላይ አስቆጥሯል እኛ ሀገር 1 አመት ከ ምናምን ነው አሁን ላይ ። እሱም እየሳቀ ቆይ ማነው የወሰደህ አለኝ? ስለከሪማ ለማውራት ደበረኝ እና ፌስቡክ ላይ ነው ያገኘሁት አልኩት ።

Читать полностью…

Allah is one

😊አልፋና ከሪማ ❤️
ክፍል አራት 4⃣

(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ )

ህልም ማለት ስትተኛ ምታየው ሳይሆን ..እንዳተኛ እንቅልፍ ሚነሳህ ነው !!!


ያኔ ሂወቴ እንደአዲስ ተጀመረ .. የሂወቴ መስመር ከዛች ቅፅበት በኋላ ነበር ነፍስ የዘራው ሰሚር ራሱን ያወቀው ለህልሙ መኖር የጀመረው ከዛች ጊዜ በኋላ ነው ለካ ሰሚር ሂወትን አያውቃትም አይ ያ ልዩ እለት.

ፕሮግራሙ ላይ አንድ ገፅታው ሚያምር ሱፍ የለበሰ ሰው ማውራት ጀመረ ለንግግሩ ትኩረት እንድታረግ የሱ አለባበስ እና በራስ መተማመን ይጋብዝሃል በሚያምር ፈገግታ እና ሰላምታ ረዢም ንግግሩን ቀጠለ ....

" ሂወት ውሳኔ ናት ሂወት ምርጫም ናት የሰው ልጅ በፈለገው የሂወት መስመር እና መርህ መጓዝ ይችላል የጉዞውን መንገድ የአላማውን ህልም መኖር ከጀመረ የጊዜ ትርጉም ገብቶት ሚንቀሳቀሰውን እንቅስቃሴ እንዳለ ወደ እቅዶቹ መቀየር ይችላል ።
ብዙወቻችን ህልም አለን ። ህልም ስላለን ነው እዚ የመጣነው ወደፊት መኖር ምንፈልገው ሂወት አለ በወጣትነት ማሳካት ምንፈልጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ

የኔን ህልም ብትጠይቁኝ መኪና ቤት እና እናቴን እየሩሳሌም መውሰድ ነው ።
መኪናውን በፕሮግራሜ በመጓዝ አሳክቼዋለሁ ቤትም መግዛት ባለብኝ ጊዜ በርግጠኝነት እገዛለሁ ምክኒያቱም የሂወቴን መስመር እና ለኔ ሚሆነውን ትክክለኛ መንገድ አልፋ አሳውቆኛል ።

የሰው ልጅ የገንዘብ ሀብት ይፈልጋል ነገር ግን የገንዘብ ሀብት እንዳለ ሁሉ የአእምሮ ሀብትም አለ የአእምሮ ሀብታም ከሆንን የገንዘቡ በጣም ቀላል ነው ። እኛ ሰወች ፈጣሪ ልኩን ያላወቅነውን ትልቅ ጭንቅላት ሰጦናል አብዛኞቻችን አንረዳውም መጠቀም ባለብን መንገድ አልተጠቀምነውም ሰፋ ያለ አመለካከት ሊኖረን ሲገባ ሁሌ በአንድ መስመር ስራ እንፈልጋለን ውጤታማ ለመሆን ረዢም ጊዜ ያዳግተናል ።
የአብዛኞቻችን የሀገራችን ወጣቶች ሚኖሩት ኑሮ _ "ትምርታቸውን ይማራሉ አንድ የሞያ አይነት Doctor Engineer‌‌ ...... የማርኬትም የአካውንትም የተለያዩ ነገሮች ሞያ ተምረን በተማርንበት ብቻ ስራ እንፈልጋለን አእሞሯችንን በተማርንበት የመስራት አቅም ብቻ እንዳለን እንረዳለን።
ነገር ግን ብዙ የ Business‌‌ ሀሳቦች ብዙ መፍጠር ያለብን ስራወች አሉ ።
ህልም ያለው ይቆፍራል ህልም ያለው ይጥራል በአጭር ጊዜ ምን እንደሚያሳድገው ለማወቅ ከፍተኛ ጥረት ያረጋል ።

ስራ እና ሂወትን መለወጥ ሚለው ሀሳብ አእምሯችን ላይ ሲመጣ.. ብዙ በጀት ብዙ የገንዘብ Capital እናስባለን ነገር ግን የሰው ልጅ መንገዱን ካወቀ በጣም በአጭር ጊዜ መለወጥ ይችላል !!

ስለዚ ለተወሰነ ጊዜ ስለስራ .. ስላለንበት ተጨባጭ ስለ ተጠቃሚ ስለ ገዢ ስለአከፋፋይ ማወቅ አለብን !! እስቲ በሌላ ነገር በወሬ በሙዚቃ የተሞላውን አእምሮ ስለ Business‌‌ እንዲያውቅ እናርግ ሁላችንም ለስራ ያለን እይታ ከስራ ትርጉም ፍፁም የተለያየ ነው ።

በአእምሯችን ላይ ብዙ የስራ አመለካከቶች አሉ ነገር ግን አቅማችንን አናወጣውም ለማውጣት የገንዘብ የሰው በጀት ያለ ይመስለናል ከእንቁ የስራ ሀሳባችን ጋር ወጣትነት ያልፈናል

የብዙወቻችን ሂወት ይህ ነው ።
ነገር ግን ያልተረዳነው ነገር ወጣትነት ልዩ ሃይል እና ሁሉም ነገር ሚያምረው በወጣትነት ነው ።
እኔ አልፋን ኩባንያ ስቀላቀል 29 አመቴ ነበር ነገር ግን አሁን በ 31 አመቴ ተለውጬ ስኬት ላይ ወጥጬ በወር እስከ 70‘000 80‘000 በአልፋ ተከፋይ ነኝ እሱም ቋሚ ላርገው እንጂ እጅግ በርካታ ገንዘብ በአካውንቴ ሚገቡ ብዙ ጊዜወች ናቸው ።

መጀመሪያ የአልፋን ኩባንያ መቀላቀል አልፈለኩም ነበር ነገር ግን ጓደኛየ ጋብዞኝ እንደምንም ተሳተፍኩ እና ስለአልፋ የBusiness‌‌ ስልጠና መውሰድ እንዳለብኝ ተረዳሁ ምክኒያቱም አልፋ ውስጥ ሁለት ትላልቅ ነገሮችን መጠቀም ስላለብኝ

አንደኛው አልፋ ለቢዝነስ ያመጣልኝን ልዩ ሀሳብ ።
ሁለተኛው የአልፋን ቢዝነስ በምን መልኩ መስራት እንዳለብኝ እና የራሴን እምቅ ሀሳቦች እንዴት ማውጣት እንደምችል ከምን አይነት ሰው ጋር መገናኘት እንዳለብኝ እና የራሴን ክህሎት እንዳወጣ በአጭር መልኩ አረገዋለሁ ያልከውን ማድረግ እንዳለብህ ማመን የአእምሮ ሀብታም የተስፋ የህልምህን ስፋት የተመለከተ ከሰወች ጋር ያለንን ቀረቤታ ሀይማኖት ላይ ያለንን አመለካከት ለአላማችን መኖር ሚባለውን ነገር ሰፋ አድርጎ ሚሰጥ ልዩ ስልጠና ነው ።
እነዚ ሁለት ነገሮች ( Business‌‌ እና ስልጠና) ለሂወቴ ትልቅ መስመር ናቸው ብየ ከወሰንኩ በኋላ የአልፋን ሰፊ ስልጠና ለመውሰድ የመጀመሪያውን ፓኬጅ ለመግዛት አሰብኩ።
አልፋ አራት አይነት ስልጠና አለው ትንሽ ረዘም ያለ ጊዜ ሲኖራቸው ..

የመጀመሪያው የገፅታ ገንቢ yellow ሲሆን አቅማችንን እንድናውቅ ህልማችንን እንድንቀርፅ ማንነታችንን እና መጓዝ ያለብንን መንገድ ለኔ ሚሆነውን የሂወት መስመር ይቀርፀዋል ።

ሁለተኛ ሶስተኛ እያሉ ይቀጥላሉ ሙሉ ስልጠናውን ከወሰድክ ስለ ማህበረሰቡ ስለ ሀይማኖትህ ስለ አካሄድህ ስለ አጠቃላይ Business‌‌ ሙሉ ግንዛቤ ይኖርሃል በአላማህ ተጉዘህ ከ6 ወር እስከ 1 አመት ባለው ጊዜ የስኬት ማማ ላይ ያወጣሃል ።
እና እኔ ይህን ስልጠና ለመውሰድ እና የአልፋ የBusiness‌‌ ሴንተር ውስጥ ለመግባት መመዝገቢያውን መጠየቅ እና ቤተሰብ ማማከር እንዳለብኝ ተረዳሁ።

የ Business‌‌ አቅርቦቱ ልዩ ስለሆነ መግቢያ ገንዘቡ አሁን ላለሁበት ሁኔታ ቢበዛ እንኳ ከየትም አመጣዋለሁ ብየ አሰብኩ ..

(ሰውየው ሲያወራ እየጮሀ ስለነበር በዛ ጊዜ ማንም ራሱን አያውቅም እኔም ብሆን የስኬት ጫፍ ላይ እንደምደርስ በምናቤ አሳክቼዋለሁ) .. መድረክ ላይ የወጣው ሰውየ ታሪኩን ቀጠለ ..

ምክኒያቱም አንዴ ሲስተም ውስጥ ከገባሁ ሚገኘው ገንዘብ እና ስለልቦናዊ የተሟላ ስልጠና ሂወትህን ይቀይራል ሰው ስለ ዘራችን ስለ ኳስ ስለ ታዋቂ ሰወች በደንብ ያውቃል ስለ
Business‌‌ ያለን እውቀት ግን ውስን ነች ይህ ነገር ግዴታ በሂወቴ አስፈላጊ ነው ።

ቤተሰብ ሂጄ አማከርኩ በሞራል ነገርኳቸው ነገር ግን እነሱ ይህን ነገር ውድቅ አረጉብኝ አልደገፉትም ይልቁንስ የተለያየ ነገር አርገው አጣጣሉብኝ ጓደኛ ዘመድ እንዳለ .. ነገር ግን እኔ ያየሁትን የስኬትን በር ስለማያውቁ አጥበውም ነገሩን ስለሚመለከቱ አልፋንም ስላልተረዱ ሞራል ሚያከስም አስተያየቶችን ላለመቀበል ወሰንኩ ።

በዙሪያየ ያሉ ሰወች ሚያነሱት ጥያቄ ..
ለምን ይህ ሁሉ ወጣት አልፋ አልገባም?
ለምን በየሚዲያው አልተዋወቀም?

ነገር ግን የአልፋ ኩባንያ ከሚታሰበው በላይ የገንዘብ በጀት ያለው እቅዱ ትልቅ የሆነ በውጭ ሀገር የተመሰረተ እና አፍሪካ ላይ ይህ ኩባንያ ለብዙ ወጣቶች የስኬት ምንጭ የሆነ ነው ። አስተምሮ አሰርቶ ወጣቶችን ለማነፅ ሚሰራ ነው የአልፋ ስልጠና በውጮቹ ለብዙወቹ የሂወት መስመር እንዳሰመረላቸው እና በኛ ሀገር ልዩ ባለሀብት ባለሞያወች ሚሰለጥኑበት እቅድ ያላቸው ሚያሳኩበት እቅድ የሌላቸው እቅዳቸውን ራዕያቸውን ሚቀርፁበት ሁኗል ። በተሟላ የቁጥር ሀይል እና በየ ሚዲያው ሼር ማይደረገው የራሱ የሆነ ልዩ የስራ ምክኒያት እና አላማ ስላለው ነው የ።

ቤተሰቦች ዘመዶች በፍፁም ሊደግፉኝ አልቻሉም ነገር ግን አልደነቀኝም የሀበሻ ልዩ ባህሪያቶች አሉን ..

ባላየነው ባልሰማነው ባላወቅነው መፍረድ !!
ከጥሩ ጎኑ ይልቅ መጥፎ ጎኑን መፈላፈል .

Читать полностью…

Allah is one

😊አልፋና ከሪማ ❤️
ክፍል ሶስት 3⃣

(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ)

ንጋቱም የራቀ ፣ ያልወጣልን ጀንበር
ለሊቱም ጨለማ ፣ ቀኑም ሌት ነበር

አባየን በጣም በመደናገጥ ምን ተፈጠረ ? የምን ወንድም ብየ ለማረጋጋት እየሞከርኩ ስልኩን ተቀበልኩት "አጎቴ ነበር። ሄሎ...ሄሎ አህመድ እያለ ነበር ። እኔም ሰሚር ነኝ ምነው ? ምንድነው የተፈጠረው?! አልኩት እሱም " ሰሚሬ አሁን ያለኝ ትንሽ ደቂቃ ነው ፖሊሶች እስር ቤት እየወሰዱኝ ነው አለኝ " ለምን ለምን ? ስለው ስልኩ ተዘጋ ደግሜ ደወልኩ ነገር ግን የውጭ ስልክ ነበር አልሰራ አለኝ ። አባየ ደንዝዟል ኡሚ ልታረጋጋው ትሞክራለች እኔ ደሞ የቤቱን ሁኔታ እያየሁ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለሁ እንኳ ማወቅ አልቻልኩም ለሊቱ እንዲሁ ስንሆን ሊነጋ ምንም አልቀረውም። አባየን ነገ ምን እንደምናረግ እናወራለን ብየ እንደምንም አረጋጋውት
ኡሚም ይዛው መኝታቤት ወሰደችው ። የሳሎን መብራት አጥፍቼ ወዲያውኑ ክፍሌ ሄድኩ ዛሬ ማታ የተፈጠረውን ነገር ጭንቀታሙ ጭንቅላቴ ሊፈታው አልቻለም አጎቴ ለምን ታሰረ? ለምንስ ደወለ? ጊዜያዊ እስራትስ ቢሆን እኛን ለምን ይነግረናል? ምን አይነት ወንጀል ላይ ተሳትፎ አርጎ ነው? ውስጤ ተረበሸ ስልኬን ሳበራው ሰአቱ 9:17 ይላል የነገ ውሎየ እንዳይበላሽ መተኛት እንዳለብኝ ተረዳሁ ወዲያውኑ እንቅልፍ ወሰደኝ

ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ሰአቱ በጣም ሂዷል ፈጅር ለምን ኡሚ አልቀሰቀሰችኝም ለመነሳት ሁሌ ባሰቃያትም እንደሌላው ጊዜ መምጣት ነበረባት ብየ ሳጣራ እነሱ ራሱ ዛሬ ነግቶባቸዋል። የዛሬውን ቀን ከአባየ ጋር መዋል እንደፈለኩ ብጠይቀውም እሱ ግን ፍቃደኛ አይደለም። ወደትምርትህ ሂድ አለኝ ጭቅጭቅ ሳላበዛ ወደ ክላስ አመራሁ የዛሬ የትምርት ውሎ ጭንቀት ብቻ በሉት ምንም ነገር ልማር አልቻልኩም ቀኑን ሙሉ ፈዝዤ ዋልኩ ከክላስ እንደወጣን ማሜ እየሮጠ ሰላም ብሎኝ ዛሬ ምን ሁነው ነው ሰሚሬ? አለኝ " አረ ምንም አልኩት
እሱም ዋናው ሰላም መሆንህ ነው ብሎኝ ሄደ ።

ማሂርንም ዛሬ አብረን ሰፈር ለመመለስ ብጠብቀውም ቆየብኝ ዝምብየ ለብቻየ ተመለስኩ በምንገዴ ማሜን ቅድም ለምን ምንም እንዳልሆንኩ ዋሸሁት ? ብነግረውስ ምን እሆናለው አልኩ። መልሼ ግን የምነግርበት ጊዜውም አልነበረም ብየ ተውኩት ።

ሰፈር ስደርስ ከመቼው እንደቀደመኝ ማሂርን ከሴት ጓደኞቹ ጋር ሲሳሳቅ አየሁት ልክ እንዳየኝ እየሮጠ መጥቶ ዛሬ ቤተል እንሂድ ኳስ በዛውም እንይ አለኝ እኔም እደውልላሀለው ብየ ቤት ገባሁ ቤት አባየም ኡሚም አሉ ዘይሪያቸው ስለአጎቴ ዛሬ ምንም አዲስ ነገር የለም? አልኳቸው እነሱም እንደኔ ግራ ገብቷቸዋል ምንም ስልክም አልተደወለም አልሰራምም ።
ለምን እንደታሰረ ለምን እንደደወለ ? ምን አይነት ወንጀል ውስጥ እንደገባ ለማወቅ ምንም አይነት መፍትሄ የለም አላህ ነገሩን ያግራው ማለት እና ሚሆነውን ማየት ነው...

አጎቴ ችግር ላይ መሆኑ
በኢኮኖሚ በኩል እኛ ላይ ሚፈጥረው ተፅእኖ እንዳለ ግልፅ ነው !. ቀን ሙሉ ስጨነቅ ውየ አሁንም ስለሱ ማሰብ አልፈለኩም። ፈታ ለማለት እና ጭንቀቴን ለመርሳት መግሪብ ከአባየ ጋር ሰግጄ ወደ ቤተል ምሽቱን ለማሳለፍ አቀናሁ ማሂር ጋር እዛው ሰፈር ተገናኝተን አንድ ላይ ወክ ማረግ ጀመርን የማሂ ቤት እኛጋ ቅርብ ነው የማሜ ደሞ ትንሽ ራቅ ይላል የኛ አንፎ ነው የማሜ አለም ባንክ ዝቅ ብሎ ትሮፒካል በመባል ሚታወቀው ሰፈር ነው ። የአብዱ ግን በደንብ ይርቃል ማሜ ትንሽ ራሱን ስላመመው አብሮን እንደማይመጣ ለማሂ ነገሮታል። ከማሂር ጋር ምሽቱን ኳስ እያየን በዛውም ነገ ሚጀምረውን የነ አብዱ መድረሳ የተርቢያ ኮርሱን እሱም እንደሚጀምረው ነገረኝ ።
አብረን አምሽተን ወደቤታችን ገባን


በነገው እለት ከክላስ መልስ ቤት ሳልገባ መድረሳ ሄድኩ ። ገና ሳልገባ የ ማሂሬ ጩሀት ከሩቅ ይሰማል ።
እንደገባሁ ማሜ እያፈጠነ መጦ እ .ምን ልትሆን ነው ቆይ? ልትማር በቁምነገር ምናምን ብሎ ከሰላምታ በፊት ሙድ ያዘብኝ .
ፈገግ ብየ በውስጤ ይህ ደነዝ የትምርት ሰው አልሆንም ማለት ነው ምንድነው ሚለው አልኩ !!

ወደ ተርቢያ መስጫው ስንገባ ሰፋ ያለ ክፍል ነው መሀል ላይ የሆነ ግርዶ ነገር አለ የሴቶች እና የወንዶች መግቢያ መግቢያ በሩ ግን አንድ ነው ።
ትንሽ ቆይተን አስተማሪያችን አብዱ ገባ የተማሪወችን እንዳለ ስም ጠየቀ ትውውቅ ካረግን በኋላ ወደኮርሱ ተሸጋገርን ስለ ወጣትነት ማውራት ጀመረ በወጣትነት ዙሪያ ያልዳሰሰው እርእስ የለም የሆነ ትልቅ ተስፋ ውስጤ ላይ እየጫረ ይመስላል በዛ ላይ ሲናገር ይመስጣል በደንብ ሚናገረውን ስከታተል ነበር። መሀል ላይ ግን በሩ ተንኳኳ ሁለት ሴቶች አሰላሙአለይኩም ብለው ገቡ .. አንዷ ከሪማ ናት ። ድንግጥ አልኩ በእውነቱ ገርሞኛል እንዴት እንደሆነ ሳላውቅ እኛ ጀምአ ውስጥ ናት። ደስ አለኝ እሷ ከመጣች በኋላ አብዱ ትኩረቱን ወደሴቶች አብዝቶ አደረገ በዚህም ከሪማ ጎበዝ ተማሪ መሆኗን እና ልዩ ትኩረት እንደምስብ ተረዳሁ ለነገሩ የመድረሳው ሃላፊ ልጅ ናት ብዙም ሚገርም ነገር አይደለም ትምርታችንን እየተማርን እያለ የሆነ ሰው ክላስ ውስጥ ገብቶ ትልቅ መዝገብ ነገር አምጥቶ በየተራ ስማችንን ከስልክ ቁጥራችን አስመዘገበን እና ክላስ ማንመጣበት ቀናቶች ላይ ቴሌግራም እንደምንማማር Add ለማድረግ እንደሆነ አብዱ ማስተማሩን አቁሞ ነገረን የዛሬውን ተርቢያ በዚ መልኩ ጨረስን ዛሬ ፈታ እያልን ከመድረሳ ልጆች ጋር እናሳልፍ ብለን ምሳ ምርጥ ቤት በልተን እዛው ቁጭ ብለን ስንጫወት ዋልን ልጆቹ ደስ ሚል ባህሪ አላቸው ሰአቱ ወደከሰአት ሲል ወክ እያረግን ስንዛዛግ አመሸን ደስ ብሎኝ ቤት ገባሁ ቴሌግራም ላይ ስገባ የጀምአችንን ግሩፕ አየሁት ወደግሩፑ አባሎች እየሄድኩ ከሪማ ሚል አካውንት ፈለኩ .. ብዙም አልደከምኩም አገኘኋት እሷ መሆኗን በስሟ ሳረጋግጥ ወደፕሮፋይሏ በፍጥነት ሄድኩ ። ማይስቡ ፕሮፋይሎች ናቸው ዱአወች አረብኛ ጥቅሶች ምናምን ነገር ናቸው አንድ ብቻ የአባቷን ፎቶ አየሁ እና የሆነ የእርዳታ ድርጅት 10 ቀን ቀረው 5 ቀን ቀረው ይላል ።

Inbox ወሬ ለመጀመር ከበደኝ ሴት ልጅ በቴሌግራም ቀድሜ አውርቼ አላውቅም ምናልባት ካወሩኝ በመከራ ከመለስኩ ነው ። ከሴቶች ጋር ብዙም የማውራት ፍላጎቱም ልምዱም የለኝም ግን ግሩፕ ላይ ማውራት ከጀመረች ባወራችው እርእስ በመጠየቅ አስቀይሼ Chat መጀመር እንደምችል ተረዳሁ

ግን ግሩፕ ላይም ልታወራ አልቻለችም ።

ሰሞኑን ቤት ያለው ሁኔታ ደስ አይልም አጎቴ እንደታሰረ ከሰማን ወዲ የቤታችን ለዛ ጠፍቷል እኛ ቤት ላይ ከኢኮኖሚ አንፃር የፈጠረው ተፅእኖ መኖሩ እንዳያስጨንቀኝ ብሞክርም አልቻልኩም

የመጀመሪያም ብቸኛም ልጅ ነኝ የቤተሰቤን ሂወት መቀየር አለብኝ አባቴ እንደቀድሞው መስራት አይችልም ። የራሴ ሂወት አለኝ ‼ ገንዘብ ግዴታ ሁኖ ታየኝ ከበረንዳችን ወጥቼ ከኡሚ ጋር ስለሰሞኑ ሁኔታ አወራን እና መስራት እንዳለብኝ ራሷ ወሬ ጀመረች ደስ አለኝ ። በምን መልኩ መስራት እችላለሁ ብየ ጠየቅኳት እሷም ትምርትህን ተማር በተማርከው አሪፍ ስራ ታገኛለህ አለችኝ እንደመሳቅ ሁኜ በአካውንቲንግ ነው አሪፍ ስራ ማገኘው አልኳት ብዙም አልተረዳችኝም ዝምብላኝ ሄደች ተናደድኩ ..!!!!

Читать полностью…

Allah is one

❤️ አልፋና ከሪማ 😊
ክፍል ሁለት 2⃣

( ፀሃፊ ጃቢር ሙስጠፋ)

የከሪማ ገፅታ ልቤን ቢማርክ
አላማየ ሌላ ነው ታሪኬን ልተርክ

በሀሳብ ፀጥ እንዳልኩ ድንገት የቤቱ ባለቤት ከሪማ ሲል ሰማሁት
ከዛ ድጋሚ መጣችና ስለ ቡና እጣን ምናምን አወሩ ከሪማ ላትመጣ በድጋሚ ወጣች
ትመለሳለች ብየ ብጠብቅም በፍፁም ልትመለስ አልቻለችም የግብዣ ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኋላ አክብሮ የጠራንን የመድረሳውን ሃላፊ ተሰናብተን ከቤቱ እኔና ማሂር ወጣን ሀሳቤ ግን እሷ ጋር ነበር የማላውቀው ስሜት ውስጤን ወረረው ሰሚር ሰሚር ምን እያሰብክ ነው ? ለራሴ ጠየቅኩት ለሴት ልጅ ምን አይነት ስሜት ተፈጠረብህ ? አንተ እኮ ሌላ ትልቅ አላማ ያለህ ልጅ ነህ እንደኮሌጅ ልጆች መሆን ያምረሃል እንዴ? አልኩት ማሜ እና አብዱ እዛው ቤት ቀሩ እኔና ማሂ ወደሰፈር ሄድን በምንገድ ላይ ግን አእምሮየ ከከሪማ ሀሳብ ወጦ ዘውትር ወደሚጨነቀው ጉዳይ ባላወቅኩት ምንገድ ተመለሰ ወደሚረብሸው እና ሁሌ ጭንቀት ወደሆነበት ነገር

እንዴት ነው ለፈለኩትን ነገር ገንዘብ ማግኘት ምችለው ? ሰሞኑን ያለሁበትን ጭንቀት አላውቀውም ብቻ ነገሮች የሆኑ ከብደውብኛል ወጣትነቴ ሚባክን መስሎ ታየኝ ለፍላጎቶቼ አጥር የሆነው ብር ብቻ ሁነው ታዩኝ በዛ ላይ የወላጆች እኔን አለመደገፍ ሀይለኛ ራስ ምታት ሁኖኛል የምማረው ትምርት ወደፊት ይጥቀመኝም አይጥቀመኝም ትምርቱ የትልቅ ስኬት በር አርገው አስበውታል ግን ስለምማረው ትምርት እንኳ ግንዛቤ የላቸውም የአካውንቲንግ ትምርት ምን ያህል ለህልምህ መንገድ ይሆናል? ?አሁን Denmark ሁኖ በሚረዳን አጎቴ ምክኒያት ወደ አካውንቲንግ ገባሁ እንጂ ፈፅሞ ፍላጎትም የለኝም ነበር እሱ አሁን በየወሩ ለአባየ ብር ይልካል ለኔም የተወሰነ ነገር ይልካል ፋዘር እንደድሮው ስለማይሰራ ብዙ ወጪያችንን አጎቴ በሚልከው ገንዘብ ነው ምንሸፍነው ይህም ከቀንከቀን እያሳቀቀኝ መጥቷል ምንም ያህል አጎቴ ሚወደን ቤተሰብ ቢሆንም ቶሎ በግሌ መንቀሳቀስ እንዳለብኝ እንዴት እነአባየ መረዳት ይከብዳቸዋል? ?

ትምርቱ ላይ ያለኝ የወረደ እምነት እንዳለምጥበት አድርጎኛል ያ ደሞ አባየ ከኔ ሚፈልገውን ውጤት ሊያገኝ ማይችልበት ትልቅ ምክኒያት ነው
ነገሮች የተወሳሰቡ እና መፍትሄ ቢስ ሁነው ታዩኝ እንደትልቅ በዚ እድሜየ የራሴን የሂወት መስመር ካላሰመርኩ ወላጅ ጋር እስከመቼ ሚለው ሃሳብ የቤት ስራ ሆነብኝ በዚ ጭንቀቴ ሚረዳኝ ያጣሁ ብቸኛ መሆኔ ተሰማኝ ሰአታት ቀናት ውስጤን ያሳስቡት ጀምረዋል ሳቅ ሚባል ፊቴ ላይ አልተስተዋለም ቤት ገብቼ ብቻየን ማሳልፋቸው ረዢም ጊዜወች ለኡሚ ብቻ ሳይሆን ለራሴም ጨንቀውኛል ቢጨንቀኝ ትንሽ ከሀሳብ ለማገገም አብዱ ጋር ደውየ ዛሬ ማታ ለምን አንገናኝም አልኩት እሱም እሽ ሀቢቢ ብሎኝ ስልኩን ዘጋሁት ሹራብ በጃኬቴን ደርቤ በወክ እየተሟዘዝኩ ወደቀጠረኝ ካፌ መሄድ ጀመርኩ በምንገድ ላይ መግሪብ አዛን አለ አዛን እያለ ባለመስገዴ ትንሽ ጭንቅ አለኝ አዛኑ እና ሰላቱ ምንገድ ላይ እያለሁ አለቀ የጨነቀኝ ስሜት እፎይታ አገኘ ከዛሬ ነገ ሰላት ቀጥ ብየ እጀምራለሁ እያልኩ ዘመናት ነጉደዋል እኔን የተጠናወተኝማ ዋናው ሰይጣን ሳይሆን አይቀርም
ካፌው ውስጥ እንደገባሁ 3ቱም ቀድመውኛል እዛው ሰግደው ነው መሰለኝ

እነማሜ ዲናቸው ላይ ያላቸው ብዙም ስር ያልሰደደ ጥንካሬ በመጠኑ ለቅናት ይጋብዛል በተለይ አብዱ አስተዳደጉ እና መድረሳ መማሩ ለዲኑ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አርጎታል በዛ ላይ ፊቱ ላይ ደስ ሚል ነገር ይነበባል እንደ አራሚ ታላቅ ወንድም ነው እሱ አብዱ ከቤተሰቡ እና ከወዳጆቹ ጋር ያለው ቀረቤታ እጅግ ይማርካል

ወዲያውኑ ስገባ በሞቀ ሰላምታቸው አጀቡኝ ማሂ እና ማሜ በምን እንደሆነ ባላውቅም አብዱ ላይ ሙድ እየያዙ ይመስላል ምን እንደሚያስቃቸው አላውቅም ብቻ ይስቃሉ ሚሽኮረመም የዋህ አግኝተው ሁሌ ይጫወቱበታል አይ አብዱ
ስለሁኔታቸው ልጠይቃቸው አልኩና ምን እንደያዘኝ አላውቅም ድጋሚ ተውኩት ወሬ ለማስቀየስ ዘልየ ማሂርን በኳስ ማብሸቅ ጀመርኩ ማሂሬ የአርሰናል ደጋፊ ነው እሱን ለማናደድ እንጂ ኳስ ብዙም አይደለሁም አብዱና ማሜ ከኳስ ምናምን ነፃ ናቸው ማሜ ትንሽ የሊቨርፑል ጨዋታ ደስ ይለኛል ይላል ከኳሱ ባሻገር ስለክላስ ስለሰው ትንሽ እየቦጨቅን ሰአቱ ሄደ ማሜ ስለተደወለለት ወዲያኑ ተሰናብቶን ወጣ ማሂርም መታጠቢያ ቤት በሄደበት ፌስቡክ ላይ ከሚያውቀው ሰው ጋር ተገናኝቶ እሱጋር ተቀመጠ እኔና ቁምነገረኛው አብዱ ብቻ ቀረን ሰሞኑን ስለጨነቅኝ ነገር ባወጣው ከጠቀመኝ ብየ ማውራት ጀመርኩ
አብዱ አንተ አሁን የፋይናንስ እጥረት አያስጨንቅህም አልኩት? አብዱም እድሜ ለአክስቴ እና ያው መድረሳው ላይ በማስተምራቸው ልጆች ማገኘው ብር አለቺኝ በዛች መብቃቃት ነው አለኝ
እኔም ህልም እና እቅድ የለህም ? በተወሰነች ገንዘብ ፍላጎትህን ማርካት የተሻለን ነገር ማግኘት ትችላለህን አልኩት እሱም በርግጥ አልችልም ግን ያው እጥራለሁ ባለኝ ደስተኛ ነኝ አለኝ 🤷‍♂

እኔም ሰሞኑን ቤት ለስራ የጀመርኩትን አካውንቲንግ ትምርት መጨረስ እንዳለብኝ እና የገንዘብ እጥረት ችግር ከቤተሰብም መጠየቅ እንደሸከከኝ ማማከር ቢጤ አወራሁት እሱም ለምን አልነገርከኝም አለኝ እኔም ያው ምን ይሰራል ብየ ነዋ አልኩት አብዱ ፈገግ ብሎ ሰሚሬ ሁሌ ላንተ መንገር ምፈልገው ነገር አለ ምናልባት ሊያናድድህም ላያናድህም ይችላል
ሂወትህ ላይ መለወጥ ያልቻልከው ትልቅ ነገሮች አሉ ነገር ግን ለትልልቅ ነገር ቦታ አትሰጥም ለሰው ልጅ ትልቁ ወሳኝ ነገሩ ፍቅር ነው ከሰው ጋር ሚያቀራርበው መግባባት ነው ይህን ባህሪ ውስጣችን ካልተላበሰው በፍፁም ወደፊት አንጓዝም ሚያስፈልገን ሰው ነውና ፣
መሳቅ እየቻልክ ብዙም አትስቅም ፊትህን መፍታት እየቻልክ አትፈታውም ለምን ሰሚሬ ? ውስጥህ ለምን ደረቀ የኛ ግንኙነት እኮ ለሂወታችን ዘላቂ የሆነ ወንድማማችነትን መገንባት እንጂ አብሮ ለመጫወት ለመዝናናት ብቻ አይደለም ለምንድነው አፍቃሪም ሆነ ወዳጅ ልቦና ማይኖርህ ርህራሄ ውስጥህ ላይ ለምን አልተፈጠረም ኩራትህስ ገኖ ለምን ወደውጭ ይወጣል ?
በመተናነስ ከፍታን ታገኛለህ በመናገር በመሳቅ መፍትሄን ተወዳጅነትን ታተርፋለህ እኮ ሀቢቢ !! ስለጥቅሞችህ ሳይሆን ስለሌሎች ጥቅሞች ካሰብክ ሰወችም ስላንተ ያስባሉ ልብህን አርመው አለኝ ከገንዘብ ስራ በፊት ራስህ ላይ ስራ አለኝ !!
ወዲያውኑ ሰላም እደር ብሎኝ ማሂርን እንውጣ አለው ቁጭ ባልኩበት ሳይሰናበተኝ ወጣ ሲመስለኝ በጥሞና ያለኝን እንዳስተውል ነው ጥሎኝ የተነሳው ለራሴ ከሰውጋር ማያቀራርበኝን ትልቁ ችግር የተገለጠልኝ መሰለኝ ነገር ግን ላስተካክለው ምችል ሁኖ አልታይህ አለኝ የተፈጥሮ ባህሪ ነውና ቤት እንደገባሁ የአብዱን ንግግር ቀጥታ ከኡሚ ጋር አገናኘሁት ስራ ለመስራት ከሰው ጋር መግባባት አለብህ ነበር ያለቺኝ
ማሜ ደሞ ከራሴ ጋር እራሱ መግባባት እንዳለብኝ ነበር የነገረኝ
ቴሌግራም እንደገባሁ ከአብዱ ቴክስት አገኘሁ As wr wb ሀቢቢ ነገ መድረሳ መምጣት አለብህ ትልቅ ፕሮግራም አለ እንድትሳተፍ እና በጣም ይጠቅምሀል አለኝ
አይቼው ምንም ሳልል update አረጎ ብቻ ካርድ አለቀው ነገ ምን ፕሮግራም አለኝ ? ምንም የለም ብየ ማሂ ቅድም የላከልኝን ፊልም ማየት ጀመርኩ ብዙም ሳልቆይ እዛው እንቅልፍ ወሰደኝ

Читать полностью…

Allah is one

እንዴት : ያለሽ : ጥበበኛ : ነሽ ፥                
            ልቤ : ላይ : የሰራሽዉን : ጥልፍ : ባዬሽዉ ።
©️ቴዎድሮስ

Читать полностью…

Allah is one

ጅሙአ መብሩክ 💛💛💜💜💝💝💟💟💙💙💚💚❤❤💗💗

Читать полностью…

Allah is one

ውበቷ ሲደበዝዝ አያረጅም።
ጤንነቱን ሲያጣ ታሞ አልተወውም። ❤️

በአባቶቻችን ዘመን ፍቅር እንዲህ ነበር።
ፍቅር እንደዚህ የፍቅር ሰባኪ ነበር።

Читать полностью…

Allah is one

የሳምንቱ ኢድ = ጁምዐ ጁምዐ ጀሚል!😍 #ሼር❤️

For more vids JOIN @MuslimCoupleVids

Читать полностью…

Allah is one

እስከ ረፋድ አራት ሰዓት ድረስ ጠበኩት። አልመጣም። መፍራት ጀመርኩ። በጉዲፈቻ የምናሳድጋት ልጃችን ኑራን ት/ት ቤት በባዶ ሆዷ ሄዳለች።ቤቱ ዉስጥ የሚላስ የሚቀመስ ነገር የለም። ምንም ብር የለኝም። ተበድሬ እንኳ ልግዛ ብል የማቀው ሠው የለም። ያለኝ ብቸኛ አማራጭ እሱን መጠበቅ ሆነ።
ፀሐይ እየጠለቀች ነ ው።የአሱር ሰላት ሰግጄ ከኑራን ጋር ቁርዓን ቀርተን አላህን አጥብቄ ጠየኩት ባሌን በሠላም እንዲያመጣልኝ። አሁንም አልመጣም::

ይባስ ብሎ መሸ። የግድግዳውን ሰዓት ተመለከትኩ። 10:45 ይላል። ኑራን ስለራባት መተኛት አልቻለችም።አዕምሮዬ ውስጥ ብዙ ሀሳቦች ይመላለሳሉ:: በሩ በድንገት በሀይል ተንኳኳ። በጣም ደነገጥኩ። አይኔ እንባ እስኪያቀር ድረስ ተንቀጠቀጥኩ። እንደምንም ብዬ በሩን ከፈትኩት.....
ኡፍ emrë ነበር። ገና ልናገር ከአፌ ቃላት ሳወጣ ተንገዳግዶ ላዬ ላይ ወደቀ። ወዲያው ደም መትፋት ጀመረ። ኑራንን እየጮህኩ ጠራኋትና ደግፈን ሳሎን ሶፋ ላይ አስተኛነው። አልሀምዱሊላህ ፊቱን አጣጥበነው ወደራሱ ተመለሰ።ኑራንን አስተኟኋትና መነጋገር ጀመርን። ምንም አላለኝም። አይኖቼን ብቻ በስስት እያየ ራሴን ና ኑራንን እንድጠብቅ ነገረች። ቀጥሎም ምንም ቢፈጠር ሁሌ የምነግረው ቦታ ላይ ከመድረስ እንደማልቆጠብ ቃል ግቢልኝ አለ። ምነው ብዬ ጠየኩት። ቃልብቻ ግቢልኝ አለ። እሺብዬ ቃል ገባሁለት። ሊነግረኝ ያልፈለገው ነገር እንዳለ ገብቶኛል። ቢሆንም ስለመሸ ነገ አናግረዋለው ብዬ ተኛን። ጠዋት ከጎኔ እንዳላጣው እየፈራው ...
አይነጋ የለነጋ። እፎይ ዛሬማ ካጠገቤ ነው። ዛሬ አልተወኝም።
ትላንት በለበሰው ጃኬት ብር ስላገኘው አንዳንድ ነገር ለመግዛት ወጣው። መግዛት ያለብኝን ነገር ገዛዝቼ እየተመለስኩ ነበር። የቤቴ በር ተከፍቶ አየውት።በሩጫ ወደ ውስጥ ገባው። መኝታ ክፍሌ ውስጥ የጤና ሰራተኞች ነጭ ከፈን አልብሰው ሰዉ ሲያወጡ አየው። በፍርሃት ፊቱን ለመግለጥ ጠየኳቸው። ፈቀዱ። እንደምንም እጄን እየተቆጣጠርኩ ገለጥኩት።



#ይቀጥራል........5 ╚═════ೋೋ═════╝

Читать полностью…

Allah is one

. ከጎንህ ያለችው ሚስትህ•••• የላጤዎች ሁሉ ምኞት ናት
ትንሿ ቤትህ•••• ቤት የሌላቸው መንገድ ላይ የሚተኙት ሁሉ ምኞት ነው
አድካሚ ስራህ•••• ስራ የሌላቸው ሁሉ ምኞት ነው
ትንሿ ገንዘብህ•••• ምንም የሌላቸው ሁሉ ምኞት ነው
ውድ የሆነው ጤናህ••••ጤናቸውን ያጡት ሁሉ ምኞት ነው
በደስታ የተሞላ ፈገግታህ•••የተጨነቀ ያዘነው ሁሉ ምኞት ነው
አላህ የደበቀልህ ነገር••• የተዋረዱትና የተጋለጡት ሁሉ ምኞት ናት
በነፃነት ወደፈለከው የምትሄድው••• በእስር የሚሰቃይ መንቀሳቀስ የማይችለው ሁሉ ምኞት ነው

እና ጌታህን አታመሰግንም?? [ °አልሃምዱሊላህ•••••••]
.
.
@binte_hikeaeman

Читать полностью…

Allah is one

happy jumaa💜❤💙💙💚💚

Читать полностью…

Allah is one

═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
....... የማይሽር ሽህረት....
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝



በክፍሉ ውስጥ የህፃን ለቅሶ ይሰማል። የሆነ ሰዉ እቅፍ ውስጥ ነኝ። "እንኳን ደስ ባረሽም"፣ "ትትሽር ኸማ "፣ "ገገሽታውሽ ትመስር":: የሚሉ ድምፆች ይስማሉ። በቃ ተወለድኩ ማለት ነው። መጣው ወደዚች አስቀያሚ ምድር ! እስቲ እንግዲህ ልኑራት።

ስተኛ፣ ስነቃ፣ ሰበላ፣ ስጠጣ፣ ስጫወት፣ ስደሰት .. በቃ ጊዜው ዝምብሎ ይሄዳል!! አለም ጣፋጭ ሆና, ካለ ችግር, ከነ ማንነቴ እየኖርኩ ነበር። እስከ አንድ ጊዜ ድረስ። አንዴ: እናቴ ብስራት ታሰማለች። በጣም ህፃን ነበርኩ። ቢበዛ3 ወይም 4 አመቴ ላይ መንታ እህትና ወንድም ተወለደልኝ። ልክ እንደ እኔ ሌላ ሁለት ልጆች ወደዚህች አለም ተቀላቀሉ.. .
ሁሉም ሠው መቷል። አያቴ፣ አጎቶቼ፣ አክስቶቼ ብቻ ብዙ ሰው። እናቴ የአራስነት ጊዜዋ እያበቃ ነው። አያቴ ወደ ቤቷ ለመመለስ ተነሳች። እናቴ ግን አይሆንም ቢያንስ ዛሬን እደሪ ትላታለች። አያቴ ግን ለመመለስ በጣም ፈልጋለች። ከብዙ ንትርክ በኋላ አንድቀን ለማደር ተስማማች። እስከ ምሽት ድረስ ነገሮች ሰላም ነበሩ። ምሽት ላይ እናቴ ማስመለስ ያዘች። ከጥግ እኔ ተቀምጬ ሁሉንም ሰዉ አያለሁ። 3ወይም4 ሰዎች ወዲያና ወዲህ ይሯሯጣሉ-





ጠዋትላይ እንደወትሮዬ ከእንቅልፌ ስነሳ የተለየ ነገር ቤታችን ላይ ተመለከትኩ። ቤቱ ሰው ሞልቶታል።ግቢያችንን መቃኘት ጀመርኩ። አንዳንድ ሴቶች ድንጋያማው የቤታችን መግቢያ ላይ እራሳቸውን እያነሱ ይፈጠፍጣሉ። ምን እየተፈጠረ እንደሆነ አልገባኝም። መልሶ ቤታችን በሰዎች ተሞላ።
ከ2 አመት በፊት ከአጎቴ ጋር መኖር የጀመረችው እህቴም መጣች። የሆነ ሰዓት ላይ እኔና እህቴ ተጠርተን ወደ ጎረቤታችን ጋር ሄድን። ወደ አንድ ክፍልም ገባን። አንድ ፍራሽ ላይ የተኛ ሰው አለ። ፊቱን የሸፈነውን ጨርቅ ገለጡልን። ሴትናት። ፀጉሯ የተንጨባረረ ላይዋ ላይ ከተጣለው ነጭ ቀላል ጨርቅ በቀር ምንም ያለበሰች ሴት ተኝታለች። ቀና ብዬ እህቴን ተመለከትኳት። የማይቆም የእንባ ጎርፍ ከጉንጮቿ ክብልል እያሉ ይወርዳሉ:: ምክንያቱም እዛጋ የተኛቸው ሴት ዳግም ላትመለስ ያሸለበቸው የእሷና የእኔ እናት ነበረች።


. . . የለቅሶው ስርዓት አልቋል። እህቴ ከአጎቴ ጋር ልትመለስ ነው። እኔ ግን በጣም አስቸገርኩ-አብሬያት ካልሄድኩ ብዬ። ከሷ ጋር መሄድን ብቻ ሳይሆን ኣ.አ የተባለች ከተማ ማየትን ጓጓሁ። አባቴ የኔን እጅ ይዞ ከአጎቴ ጋር ያወራል። አጎቴም እህቴን ይዟታል።ከብዙ ለቅሶዬ በኋላ ወደ አ.አ እንድመጣ ተስማሙ ። ከዚያ እንደ አይን ብሌኑ ይሳሳልኝ የነበረውን አባቴን ጥዬ ለልጅነት ፍንደቃ ጉዞዬን ወደ ኣ.አ አደረግኩ። ከተማ ወደ 11 ሰዓት አካባቢ ደረስን።አክስቴ (የአጎቴ ሚስት)እጄን ይዛኝ እየተጓዝን ነበር። በድንገት አይኔ አንድ ብርቱካናማ ጫማ ላይ አረፈ። በጣም ያምር ነበር። አክስቴም ተመልክታው ስለ ነበር ያንን ጫማ ገዛችልኝ። የመጀመሪያው የአ.አ ንብረቴ ሆኖም በአዕምሮዬ ተመዘገበ። በዚህ መልኩ የከተማ ኑሮን ተቀላቀልኩ። አዲስ ህይወት.......

#ክፍል_2_ይቀጥላል.......

╚═════ೋೋ═════╝

@binte_hikeaeman

Читать полностью…

Allah is one

❤️አልፋና ከሪማ 😭

ክፍል ሰባት 7⃣
(የምዕራፍ 1 የመጨረሻ ክፍል)
(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ )



አልፋም ቤቴ ሆነ ፣ ከሪማም ባለዳ
ነፍሴም ተሸነፈች፣ በእንስቷ ጓዳ


የእሁዱ ቀን ደረሰ በሚያምር አለባበስ ፊትለፊት በኩራት ተቀምጫለሁ ። ፕሮግራሙ ጀመረ ብዙ ሰወች መናገር ጀምሩ .. አልፋ ላይ በገንዘብ እና በአስተሳሰብ ምትለወጠው ስልጠናውን ወደሂወትህ አምጥተህ ስተገብር ነው አእምሮህ ሲከፈት ብዙ ማይጠቅሙ ሃሳቦችን ውስጥህ ላይ ስታስወግድ የቀድሞ ልምድህን እርግፍ አርገህ ስትተው ከፈጣሪህም ከሰወችም ቅርብ ትሆናለህ ዛሬ ላይ በዚ 21 ቀን ውስጥ በደንብ የመጀመሪያውን ፓኬጅ ሰልጥነው የተመረቁ ልጆች እንመርቃለን አለ ሌሎችም ብዙ ሰወችም ንግግር አደረጉ ከዛም ወደመድረኩ ሁላችንንም ጠራን ..

የዛሬዋ ቀን ትለያለች 12 አመት ምናምን ተምረን ምንመረቀው ምርቃት እኮ ሂወቴን ቀጣይ ምን ላርገው የሚል ጭንቀት ነው ምናተርፈው ። በሂወትህ በለውጥህ ስትመረቅ ደስ አይልም ?

በዛ ላይ የሰራነው ዶላር ተነገረ በዚ ወር የበለጡኝ አሉ ግን እኔ ዶላሩ ብዙም አያሳስበኝም ። ወደቀጣዩ ፓኬጅ ስዘዋወር ነው ንግግር ማረገው ብየ እዛው ቦታየ ተመለስኩ ። ዛሬ ፉአድም ከድሬ መጥቷል በጣም ደስተኛ ነበርን በዚሁ የደስታ ሞራሌ ከሪማን እንደምወዳት ብነግራት ደስ ባለኝ ..

ግን ፈራሁ ። ከፕሮግራሙ መጠናቀቅ በኋላ ምሽቱን ስንጫወት እንደሙሽራ ሲያረጉኝ አመሸን በጣም ደስ አለኝ ሂወቴ በአንድ ወር መቀየሩ ሀሴት ውስጥ ከተተኝ።
በርግጥ እንዲቀየር የአብዱ ስልጠናም ጠቅሞኛል እንጂ ከመጀመሪያው ፓኬጅ ይልቅ 2 ሶስተኛው ትልቅ ተፅዕኖ አለው ሁለተኛው ሶስተኛው ከከዛሀው መጀመሪያ ከምታገኘው በላይ በዛ ያለ ተቆራጫም አለው ።

ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ነገር አብዱም ከሪማም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ። ማሂር እና አብዱ ለምን ስለተለያየ የዲን አመለካከት ይጣላሉ ?? ለምን ሀሳባቸውን አይከባበሩም ። ለምን ማሜ ዛሬ ድረስ እዛች ሱቅ ይፈጋል ? ፉአድንስ 1 አመት ግቢ ከተማረ ይበቃዋል ሂወቱን እዚ ለምን አይቀጥልም?

ብዙ ብዙ ውስጤ የነበሩ ሀሳቦችን በግልፅ አወራንባቸው ። ያለንን የባህሪ ክፍተት ደፍነን ወደፊት እንደትልቅ Grop ብዙ ነገር ከአልፋም ጋር ተያይዞ ከዛ ውጭ መስራት እንደምንችል ተማመንን።

ለአላማችን መኖር እንዳለብን እና ከዚ በኋላ የደስታ ሂወት ለመኖር አሰብን ዛሬ ከመሸ እኔና ማሂር አብዱ ቤት ልንሄድ ፈልገናል እሱ ግን መሽቷል ምን ትሰራላቹ ብሎ ላለመውሰድ ሞከረ ። እኛ ግን አንሰማም አልነው እሱም ዛሬ ቤት አላድርም ማዘርን ደውየላታለሁ አምሽተን ስገባ ደስ አይልም ዛሬ አንሄድም ሲለን አርፈን ተቀመጥን ማታውን ስናብድ አሳለፍነው ድንገት ከመሃላችን ማሜ አንድ ቤት ተከራይተን መኖር እንዳለብን ሀሳብ አመጣ በጣም ገራሚ ሀሳብ ነው ። አብዱ ደስተኛ አለመሆኑን ስናይ ተውነው ።

አብዱና ማሜ ወደነማሂር ቤት ሊያድሩ ሄዱ ። እኔ ወደቤት ተቀነጠስኩ ።

ቤት በጣም መሽቶ ነበር ስገባ አባየን ዘየርኩት ሊቆጣ ሲል. ዛሬ የጀመርኩትን የስኬት ጅማሮ በፎቶ አሳየሁት በቀጣዩ ስመረቅ እጋብዛቹሃለው አልኩት ። ሁሉም ተደሰቱ የነሱን ደስታ ሳይ ከልቤ ተደሰትኩ አሁን በአጎቴ ምክኒያት ከተፈጠረው ችግር አንፃር የአሁኑ የነሱ ደስታ ትልቅ ቦታ አለው ለኔ።

ሰአቱ በጣም ሄደ 6:35 ይላል እነኡሚን አስተኛኋቸው እና ዛሬ ይህን ትልቅ ውለታ ለዋለልኝ ጌታ ለይል ሰግጄ አመስግኜ መተኛት እንዳለብኝ ተረዳሁ ለይል ሰግጄ ውብ እጆቼን ወደሰማይ ዘረጋሁ ።

ከልቤ አመሰገንኩት የእናቴን ደስታ አሳየኝ ብየ እየተንሰቀሰቅኩ ለመንኩት የሂወቴን መጨረሻ አሳምረው የአብዱንም የማሂርንም የሌሎችን ሂወት አሳምረው በወንድማማቾች መሀል ማንም እንዲገባ አትፍቀድ ። ከነሱ ውጭ ማንም የለኝም

ጀሊሉ በጨለማ ውስጥ ብርሃንን ታሳያለህ በሞተ ልቦና ነፍስ ትዘራለህ የታል ሚለምነኝ ምሰማው ባልከው የከበሩ ቃላት ይዤሃለው የከሪማን ነገር አደራ ብየ አነባሁ 😭

በወንጀል የቆሸሸ ባሪያህ ከፊትህ ተደፍቶ ያነባል .. ያልተፈቀዱለትን ልቅ ነገሮችን ያየበትን አይን አብስለት በዘረጋው እጁ አንተን ያመፀበት እጁቹን ማሀርታ ለግሳቸው ።
ያልሰገዳቸው ሰላቶች ትእዛዝህን የደፈሩ ውሳኔወች.. ነገ የፍርዱ ቀን አንገት ያስደፋዋልና ዛሬ ማንም ሳያውቅ ከመዝገቦቹ ሰርዘው ። ወንጀሉን ምረህ ፍላጎቱን አሳካለት በልኩ የተሰፋችውን ሀዋ ለግሰው ከከሪማ ጋር በዱንያ የጀነትን ሂወት አሳየው ።
ያረሂም እዘንልኝ ያ ከሪም አክብረኝ ያ ወዱድ ውደደኝ ሰወች ዘንድም አስወድደኝ ያገፋር ወንጀሌ በኔና ባንተ መካከል ይቅር ። የቀድሞየን ሂወት ለመተው አንተው እርዳኝ ቃልህን እንድሸመድድ እገዘኝ በስንዝር ስቀርብህ በክንድ ተጠጋኝ የደካሞች ደካማ ነኝ እና አንተው አበርታኝ ። ብየ ዱአየን ጨረስኩ

አገጬ ላይ ከተርገፈገፈው እንባ ባሻገር ሀሴት ተሰምቶኝ የመኝታ ዚክር ብየ ተኛሁ ።
በነገው ቀን ሲረፋፍድ ከማሂር ጋር እነ አብዱ ቤት ሄድን የአብዱን እናት ዘየርናት እና ያሰብነውን ዋና ነገር ባማረ መልኩ አደረግነው ..
የአብዱን ትንሽ እህት ኢልሃንን ብዙ ልብሶች ገዝተን ሰርፕራይዝ አደረግናት በጣም ተደሰተች እየሮጠች ስትጠመጠምብኝ እንባ ነበር የቀረኝ በጣም ተደሰትኩ የህፃንን ደስታ ማየት እንዴት ያስደስታል ።

የአብዱ እናት እያለቀሰች አቀፈቺን ዱአም አደረገቺልን ።

እነማሜ እና ፉአድ ሲመጡ ዛሬ ኢልሃንን ቦሌ ስናዝናናት እንዋል ተባብለን ወደቦሌ አመራን ልክ እንደገባን የፈለገችውን የጨዋታ አይነት እንድትጫወት ቆርጠንላት ጩሀት እና ጫጫታ ውስጥ ገባን ። እኔና ፉአድ የሆነ ቦታ በተከፈተው ዘፈን መጨፈር ጀምረናል በሉት.
ልጆች ተሰብስበው ትንሽ ካዩን በኋላ አብረን እየዘለልን መቀወጥ ጀመርን የሆነ Parry አደረግነው ወደልጅነት ተመለስን በሉት ።
ማሂርም ከኢልሃን ጋር መኪና ውድድሩን ተያይዘውታል አብዱና ማሜ የእጅ ኳስ እየተጫወቱ ነው ማሂር ወደኛ መጣና እየጮሀ ማታ ትልቅ ሚነገርህ ነገር አለ ደስ ሚል ምናወራበት ልዩ ጉዳይ አለኝ እኔም ደስ አለኝ ።
በዛውም የከሪማን ጉዳይ ዛሬ ማታ ልነግራቸው ስለሆነ ማለት ነው
ቀን ሙሉ ስንዝናና ውለን ማታውን እነአብዱ ቤት ኢልሃን ስለተኛች አብዱ ተሸክሞ አስገባት ።
እዛው እነአብዱ ሰፈር ወዳለካፌ እንደምናመሽ ተነጋገርን ወጣን የዛሬው ቀንማ ሰኞ አይመስልም መግሪብ ሰግደን እራት እየበላን እዛው ሆንን።

ማሂር እየፈጠነ ዛሬ ሚነገር ትልቅ ነገር አለ አለን (እኔም በውስጤ የሰራውን ዶላር ሰርፕራይዝ ሊያረገን ነው ብየ አሰብኩ)
ግን ወዲያውን ከተፍ ብየ እኔም ምነግራቹህ ነገር አለ አልኩ ፉአድ ከማሂር እንጀምር ከሰሚር ሲል ጠየቀ?

ማሜ ከማሂር ይጀመር የሰሚር ትልቅ ነገር ይመስላል መጨረሻ ላይ ብንሰማው ይሻላል አለ አብዱ ቁጭ ብሎ ለብቻው እየተሽኮረመመ ይስቃል .. ማሂርም በቃ ላውራ ብሎ ጀመረ ..
የሆነ ሰው እያለ ወደአብዱ እየሳቀ እያመለካተ (እኛም አብዱ ምን ? ? ብለን ሰፍ አልን ) ማሂርም አብዱሻ ኡስታዛችን ፎንቃ ገብቶለታል ፍቅር ነገር እያጫወተው ነው አለ ማሜ ተመስጦ ምን? ማንን ማንን? አለ እኔም ማንን ነው ስል ?

ማሂር ያቺ ቆንጆዋ የመድረሳቸው ሀላፊ ልጅ አደበኛዋ ሁሌ ጥቁር ሂጃብ ምትለብሰው ልጅ እንዳለ .. ማሜ ከሪማን ? አለ .. ...

Читать полностью…

Allah is one

ከዚ ቀደም የነበረውን ማንነቴን አሳታወስኩ 😭 ሰላት አልሰግም ነበር ለማየውም ለምሰማውም ነገር አልጨነቀም አላማየ ገንዘብ እንጂ ሌላ አልነበረም ጀናባ ሁኜ እንኳን ከአባየ ጋር መስጊድ እሄድ እና ከሰወች ጋር ተቀላቅየ እሰግድ ነበር !! ሰው ለመናቅ ለከት አልነበረብኝም ምኞቴ ውስጥ መጥፎ ነገር እንጂ ሌላ አልነበረም የጀሊልን ወሰን ሳምፅ ያሳለፍኩት ጊዜ አሳመመኝ
-----------
ታሪክ ነበረኝ ፣ ውስጡ የገነነ
ባሪያውን ያጠፋ ፣ ስሜትን ያመነ
እጁ ተጨማልቆ ድጋሚ ላይፀዳ
ታሪክ ነበረኝ ፣ እኔስ  ተስፋን ሚከዳ
ማንነትን ያልተረዳ ፣ግዝፈትን ያቀለለ
ጊዜያዊን ደስታ ሰጥቶ ፣ስብእናን ያጎደለ
ምንገዱ ሲከፈት ብሩህ የመሰለኝ
ዘልአለም መዋዠቅ ልቤ ያታለለኝ
ምነው ጊዜው ከረፈደ አሁን  ታወቀኝ

መመለሻ የሌለው መንገደኛ የዋለለ
መድረሻውን ሳያውቅ ከልካዩ የሌለ
ለጥፋት መሪ እንጂ ከጥፋቱ ዝቅታ
አስተካካይ የለው ከዝቅጠቱ ኮረብታ
ወንጀል ነው ፣ተቃራኒው ፅንፍ  ያልተሰማ
ውርደት ነው፣አልታየም የልእልናው ሸማ
--------

ከሪማ ምን ያህል ሂወቴን ትቀይረዋለች?
ብጠይቃት እሽ እባላለሁ ወይስ?
አሁን ላይ ለምን ለሷ ተገቢ አልሆንም?

"ቁርአን ሂፍዝ ጀምሬያለሁ የሰላት ጊዜየን መስጊድ ነው ማሳልፈው (በርግጥ እሷ በእውቀት ትበልጠኛለች።)
ከገፅታም ሚያምር መልክ እና ቁመና ተሰጥቶኛል .የፈለገ ሂወቴ ቢበላሽ ከሌላ ሴት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ።

አላማየን አውቂያለሁ በምን ምክኒያት ላትቀበለኝ ትችላለች? አላውቅም ብቻ ያቺ ጥቁር ሂጃብ ምትለብሰዋ ቀዯ ባለ ሃያእ እንስት ሌላ ነገር ለማሰብ ጊዜም አልሰጠቺኝም።

-----------
እውቀት ለመቅሰም ድርሴን ብወድም
ልሰማ ማልጄ  መድረሳ ብሄድም፣
ጌታየን ላወድስ እልፍ ብፈልግም፣

፡እኔ ግን አልችልም

ካንቺ ሌላ እንዳስብ ሺ ምክንያት ባገኝም፣
አንቺን አለማሰብ ሀሳብ አይመስለኝም፣

አይ እኔ ምስኪኑ፣
ካንቺ ጋር ሆነና ልቤ ቃልኪዳኑ፣
በስምሽ ተሳስሮ ድምፄ እና ልሳኑ፣
ከሀለቃው ቁጭ ብሏል ስጋዬ በድኑ፣

አስተማሪው እየለፈለፈ ባየውም፣
አይኔን ለአፍታ እንኳ ዳሩ ባልከድነውም፣
እውነት አልሻለሁ ምንም አላየሁም፣
--------

..ያንንም ይሄንንም እያልኩ ሂወቴ ቀጥሏል.. ማሂር ከስልጠናው ይልቅ የአልፋን ኩባንያ ለሰወች ሼር ማድረግ ተያይዞታል ማሜን ወደአልፋ አስገባው ። የክላስ ልጆቹን በሙሉ አስገባቸው በዛ ሁሉ ሰው ምን ያህል ዶላር እየቆጠረለት እንደሆነ አሰብኩት ። እነሱ ያስገቡትም ሰው ጥቅሙ ወደላይ ይወጣል ደሞ ታሳቢ ሚደረገው ገነንዘብ ብዙ ነው በ6 ሰው ብቻ ሀብታም ይሆኑ የለ ?

እሱማ የወሩ ከግሩፓችን ሳይሆን ከሙሉ አልፋ ልዩ ተሸላሚ እንደሚሆን እጠብቃለሁ ። ዛሬ እኛ ቤት መጦ የአልፋን ስልጠና በ online ፉአድን አስገብቶት የድሬ ልጆች እየገቡ እንደገቡ ነገረኝ እና ፉአድም ማሂርም ምን ያህል እንደሚሰሩ አሰብኩት በአንዱ የአልፋ ሲስተም ብቻ ።
የእሁዱ የአልፋ ቀን አጓጉቶኛል ምመረቅበት ቀን ነው በ21 ቀን ስልጠና በ online መሰልጠን ስላቆምኩ የአልፋ አካውንቴ የቆጠረውን ብር አላየሁትም ማየት እፈልጋለሁ ግን አሁድ ላውቀው ብፈልግም አላስቻለኝም አየሁት ..
887 ዶላር ሰርቷል !!! በሀገራችን እስከ 40 ሺ ምናምን ማለት ነው
በማሂር በኩል የዘረጋሁት መስመር ምን ያህል እንደጠቀመኝ አወቅኩት ። ግን ማሂር ስንት ሰርቶ ይሁን ? የሱን ብር እሁድ እነግርሃለው ብሎኛል ጓጓሁ እስኪመረቅስ ስንት ይሰራ ይሁን? ?

አላውቅም እኔኮ ማሂርን ስልጠናው ላይ አተኩር ስልጠናው ሂወትህን ሲቀይረው አእምሮህን መጠቀም ትጀምራለህ ። ቢዝነሱ ይደርሳል ምናምን ስለው አይሰማኝም ነበር። አይ ማሂ ታዋቂነቱን እና ምላሱን ተጠቅሞ ሸቅሎታል ።

እሁድ ቀን ሱፍ ለብሰን እንድንመጣ ታዘናል የዛሬ ወር እዚ ቦታ ላይ ስኬታማ ሰወችን አይቼ መች ነው እንደነሱ ምሆነው ብየ ነበር ። እሁድ ደሞ እኔ ወጥቼ ለናገር ነው ..

የእሁዱ ቀን ደረሰ ....

ይቀጥላል ...........

Читать полностью…

Allah is one

አንተ ሚስኪን ዝምብለህ Facebook ላይ አገኘሁ ብለህ ማንንም ሳታማክር ትሄዳለሃ ጊዜህን አትፍጅ ሊበሉህ ነው አለኝ !!
አስደነገጠኝ ከንግግሩ በኋላ ግራ አጋባኝ ግን የጠራችኝ ከሪማ ናት እሷ ደሞ ልዩ ታማኝ ናት ብየ የማሂርን ንግግር ከአእምሮየ አስወጣሁት ።
ሂወት ውሳኔ ናት !! ማንም ሰው ስኬት ላይ ሲወጣ ከጎን ሚያደናቅፉት ብዙ ነገሮች አሉ የተባለውን አስታወስኩ ከclass ስንወጣ አብዱ ጋር ደወልኩ

ሰላንታ ሳይሰጥ ትናንት የት ነበርክ ? እሽ ዛሬ ማታ እንገናኝ ብሎኝ ስልኩን ቶሎ ዘጋው ።
እኔ ወደ መገናኛ ሄድኩ የtaxi ምንገድ ያሰለቻል በመጠኑ ግን ማይደረስ የለም ደረስኩ ሰአቱ ግን ሂዷል ። ኡሚ ከ class ሳልመለስ እንዳደነግጥ ደወልኩላት።

እነማሂር ቤት ነን እመጣለሁ አምሽቼ አልኳት 22 ቢሯቸው ውስጥ ገባሁ።

አዋራሁት ደስ ሚል አቀባበል እና ስብእና ተላብሷል ከዛ ስለ ስራው ዘልየ ጠየቅኩት
እሱም እንዲህ አለኝ ..

አንተ ስለ ስራው አታስብ ስራው ቀስብሎ ይመጣል ዋናው ስልጠናው ነው ስልጠናው ስትወስድ ስለ ስራም ስለሂወትም ትሰለጥናለህ ..

እኔም በቅርብ ጊዜ እንደምቀላቀል ገለፅኩለት እና እንዲህ አለኝ ..

" አልፋ ላይ ብዙ የስራ ሀሳቦች ሲኖሩ አብዛኛውን ምትሰራው ስልጠናውን በደንብ ስትወስደው ነው ምክኒያቱም ስልጠናው ስለ ቢዝነስ ስለሆነ አእምሮህ ወደሞላሀው ፎርም እና አላማ ታዞረዋለህ ።
እና በደንብ ብቁ ስትሆን ነው ያኔ በአመለካከት በራዕይ ስትጎለብት ወደራሳህ ስራ እና የሂወት ምንገፍ ትሄዳለህ ወይስ ከኛ ጋር በደንብ ሰርተህ የራስህን Team ትገነባለህ?

ያኔ ሚፈጠሩብህ ነገሮች ናቸው

በተረፈ እነሱ ረዘም ያሉ የስራ እቅዶች ሲሆኑ ብዙወቹን ስኬታማ ያረገውን እና ዋነኛውን አንድ ሃሳብ ሰፋ አርጌ ላካፍልህ በቀላሉ ብዙ ዶላር እና ገንዘብ ሚሰራበትን ማለት ነው ።

ለምሳሌ 1 እቃ አለ ብሎ ከኪሱ ያለውን Smart phone ስልኩን አወጣው ይህ ስልክ ከአምራቹ ስንት ይሸጣል ብንል እስከ 2500 ያወጣል ከአምራቹ ተቀብለው ወደ ሚመረትበት ሀገር ለስራ እየመጡ ሚሸጡ አካላቶች ደሞ በተወሰነ መልኩ አትርፈው በ4000 ብር ይሸጡታል ምክኒያቱም ግብር አለባቸው ።

ውጭ ሀገር እየተመላለሱ ሚሰሩ አካላቶች ደሞ ወደሀገር ውስጥ አከፋፋይ ሲሸጡ ደሞ በ7000 ብር ይሸጡላቸዋል ለምን ገንዘቡን አስወደዱት ስንል?
የፕሌን የቀረፅ የግብር ... አለባቸው

አከፋፋዮቹ ደሞ ለሱቅ መደብሮች በብዛት ሲያከፋፍሉ እስከ 8500 ብር ይሸጡት እና 1500 ብር ያተርፉበታል የሱቅ መደብሮች ደሞ ዋና ነገር አለባቸው የኪራይ እና የግብር ። ስለዚህ እነሱ በ10’000 ብር ለተጠቃሚ ይሸጡታል ከዛም በላይ ሊሆን ይችላል

ይሄኔ የ2500 ብር እቃ 10’000 ሚገዛው ተጠቃሚ ይጎዳል ማለት ነው ። እና አምራቹም በመጠኑ ይጎዳል መሀል ላይ ሳያመርቱ ከሚያገኙት ትርፍ አንፃር

ይህ የእቃዋች የ አቅርቦት ሂደት ነው ።

እና ይህ ከሆነ የአልፋ ልጆች እና አልፋ ምን ያህል ሚና ይጫወታሉ ምንስ ግንኙነት አላቸው ስንል ደሞ ..


ይቀጥላል .....

Читать полностью…

Allah is one

አእምሯችንን በአንድ ነገር ማጥበብ
ራሳችንን ብቁ አይደለንም ብለን ማሳመን

ብዙ የወረስናቸው መጥፎ ጥርጣሬ ሃሳቦች ወደኋላ አያስቀሩኝም ብየ ለመመዝገብ ያለኝ አማራጭ ቤት ያለውን PC መሸጥ ነበር ከመበደር ይልቅ ።

ምክኒያቱን ብሩን አልፋ ጋር በምሰራው ገንዘብ እመልሰዋለሁ የመጀመሪያ ፓኬጅ ለመግዛት ሚያስፈልገኝን 5776 የኢትዮጲያ ብር ከፈልኩ።

ወዲያወኑ ስልጠና ጀመርኩ ቢዝነሱንም ጀመርኩት ለቤተሰብ አትለወጥም ላለኝ በሙሉ ለማሳየት በቢዝነሱ ለፋሁ ስልጠናውንም እየወሰድኩ 21 ቀናት አስቆጠርኩ በአልፋ ገቢ የተደረገልኝን አካውንት ሳየው ማየት ከበደኝ 237 ዶላር ሰራሁ ይህም በኛ ሀገር እስከ 11‘000 የኢትዮ ብር ይደርሳል የ21 ቀን ስልጠናው ልዩ ምሩቅ ነበርኩ ከኔ በላይ workout ተምረው የሰሩ እና ቢዝነሱንም በደንብ ያደጉበት ስለነበሩ ከ21 ቀን በኋላ ዛሬ ላይ ቁሜ በምናገረው መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመረቅኩ አለ ።
ያኔ ነው ቤተሰብ እና ጓደኞችን የጠራሁት ያኔ እስቲ መጀመሪያ ተለወጥ እስቲ አትባክን አትለፍልፍ ያሉኝን ቤተሰቦቼ በአንድ በወር ብቻ ምሩቅ መሆኔን ለማሳየት ጠራኋቸው ።

እኛ እኮ ስንት አመት ተምረን ስራ ለማናገኝበት ትምርት ስንመረቅ ራሱ እንደዚ አንደሰትም ነገር ግን እኔ ቆረጥኩ ውስጤን ብቻ ሰማሁ ከጎኔ ሚያሳንፉኝን አትበላ ያሉኝን ሰወች አልሰማሁም !!

(ሲል ሰው እንዳለ አዳራሹ ላይ ያለው ሰው እየጮሀ አጨበጨበ እኔ ምን አይነት አለም ውስጥ ነው የገባሁት ወይስ ህልም ነው ? ጥያቄ ላይ ነበርኩ )

ሰውየው ንግግሩን ቀጠለ ..

በእለቱ የአልፋ ልዩ ስልጠና ግሩፓችንም አሸነፈ ያን እለት በ21 ቀን እስከ 600 700 ዶላር ( 35 000) በስራት የበለጡኝ ጓደኞቼ እነሱን ሳይ በመናደድ ከዚ በላይ መስራት እንዳለብኝ እና አሁን ያገኘሁትን ብር ሁለተኛ ፓኬጅ ራሴን ስለሚገነባ እና የራሴን ስራ መፍጠር ስላለብኝ ልውሰድ በዛ ላይ ፖኬጄ ከፍ ሲል ገቢየም ከፍ እያለ ነው ብየ ወደሁለተኛው ተሸጋገርኩ ቀስ በቀስ በአመቱ ልዩ ተከፋይ ሁኜ አረፍኩት ።

ፊትለፊት ምትታዩኝ ወጣቶች .. እኔ ከአዳማ እየተመላለስኩ ስኬታማ ሆንኩ እድሜየ ቢሄድም ተጠቀምኩት እናንተ 20ወቹ ያላችሁ ሰወች ምን አይነት የሂወት ደረጃ እና የከፍታ ማማ እንደምትወጡ ሳስብ ምናለ አልፋ ኢትዮጲያ በኔ እድሜ በገባ ብየ አሰብኩ

ሂወት ለወሳኞች ናት ሂወት ምንድናት?
ምርጫ ናት ብሎ አንተ ግን ከኔ ትለያለህ አንበሳ ነህ ከኔ በላይ መስራት ትችላለህ ሂወትህን ቀይር ተናግረህ ሳይሆን አሳይተህ ጋብዘህ አሳምን ብሎ ከመድረኩ ወረደ !!!

ወዲያውኑ ህዘቡ በጩሀት አዳራሹን ቀወጠው ።
ከዛ መድረክ መሪው ቆይታ እንዴት ነበር ብሎ ወደቀጣይ ፕሮግራም እንሄዳለን በማለት የሆነች ሴት ለንግግር ጋበዘ..

ይገርማል የጋበዛት ሴት ፊቷን የተሸፈነች ገና የ20ወቹ መጀመሪያ ኒቃብ የለበሰች ሙስሊም ሴት ናት ።

ንግግሯን ቀጠለች ..


ይቀጥላል ..............

Читать полностью…

Allah is one

ይህ ነው የነሱ እቅድ ከ3000 እስከ 5000 በ አንድ ወር እየተከፈለኝ መኖር

ይህ ነው የአላማየ የስኬቴ ጫፍ በቃ ‼ ?

ከዚ ጊዜ በኋላ አረጋገጥኩ ቤተሰብ ሚያይበት ምንገድ ለኔ እንደማይሆን የነሱ ውስን አላማ ከኔ ልዩ የሂወት ፍላጎት ጋር ሊገጥም አይችልም !!
ክላሶችን መግባት ከምላችሁ በላይ አስጠላኝ ደባሪ ሳምንት እያሳለፍኩ ነው እንዳሰብኩት ግሩፕ ላይ አላወራችም ግን አንድ ሀሳብ መጣልኝ የሆነ ኢስላሚክ ፅሁፍ ሼር አርጌላት መልካም ጁምአ ይሁንላቹህ ብየ ፅፌ ለሁሉም እንደ መልካም አስታዋሽ Inbox መላክ

ለሷ እንደሌሎች ላኩላት አጠር ያለች ምክር ናት ከሆነ ቻናል ያገኘኋት
ጀዛከላህ ሚል መለሰች ነበር የተርቢያ ልጅ መሆኗን ጠየቅኳት አወ ካለቺኝ በኋላ ወደሰላምታ በመግባት ለመግባባት ሞከርኩ በዚ ሳምንት ከችግሮች ባሻገር በየቀኑ ከከሪማ ጋር ውሎ እንዴት ነው ምሽቱስ የሚሉ የቴሌግራም ወሬወች ደስታ ይሰጡኛል ።
ይህን ሳምንት ቤት ስላስጠላኝ ብዙውን ጊዜ እነማሂር ቤት ያሳለፍኩት ።
የቅዳሜዋ የተርቢያ ትምርት እስክትመጣ ቸኮልኩ ከሪማንም ለማየት የአብዱም ትምርት በመጠኑ አጓጉቶኛል .

የማይደርስ የለም እና በቅዳሜ ጠዋት ከነማሜ ጋር መድረሳ ተገናኘን ሁሉንም ሰላም አልኳቸው ጁምአ ከማሜ እና አብዱ ጋር አልተገናኘንም ነበር ክላስ ገባን ትምርቱም ቀጠለ ከሪማ መምጣቷን አለመምጣቷን ለማረጋገጥ ልጠይቃት ትምርቱም መጀመሩን ለመንገር ቴሌግራም ገባሁ ተጀምሯል መጠሻል ወይስ? ብየ እንደአሰባሳቢ ኮሚቴ text ፃፍኩላት አፍወን ሰሚር ዛሬ ትልቅ ፕሮግራም አለኝ ለአብዱ ነግሬዋለሁ ብላ ወዲያውኑ መለሰች።

ዛሬ ከሪማን ባለማየቴ እየተናደድኩ አርፌ ወደ ትምርቴን ቀጠልኩ የዛሬው ክላስ ይለያል በርግጥ ምን አይነት ሃጃ ግጥሟት ነው ብየ አስባለሁ ባለፈውስ ለምንድነው ያረፈደቺው ሌላ ተርቢያ አላት ወይስ ስራ ቤት ጫና ይፈጥሩባታል ?.. ብየ አሰብኩ ተርቢያው አልቆ ወጣን ዛሬ ቤት ያለው መደብዘዝ እንዲጠፋ ብየ እነማሜ እኛ ቤት እንዲመጡ ጠራኋቸው። ስለአጎቴ ምንም አያውቁም ቤት መጠን ከዛች ጠባብ ክፍሌ ቤቱን አጨልመን ሻይ እያፈላን ፊልም አየን ስንጨርስ ወደሳሎን ኡሚ ጋር እንድንጫወት ሄድን
ስናውከው ዋልን ቤቱን ማሂር ሳቅ በሳቅ አረገን ።እናቴ በጣም ነው ምትወደው አይ ማሂር ወረኛ የሆነ ልጅ ምንም ጭንቀት ያለበት አይመስልም እኮ ። ከሱጋ ስውል እኔንም ጭንቀቴን እረሳለሁ ማለት ይቻላል ።
ቤት አምሽተን ማታ ሸኝቻቸው ተመለስኩ ወዲያውኑ ቴሌግራም ገብቼ ከሪማን ለምን እንዳልመጣች ጠየቅኳት ።

እሷ ወዲያውኑ መለሰች " የአልፋ ልዩ ገፅታ ገንቢ ላይ ነበርኩ አለችኝ"

ግራ ገባኝ ።
" የምን አልፋ ? የምን ገንቢ ? አልፋ ምንድነው ? አልኳት

እሷም ሰሚር.. ሂወት ላይ ትልቅ አላማ እና ህልም አለህ አለቺኝ?

እኔም ግራ በመጋባት በጣም ትልቅ አላማ ነው እንጂ ያለኝ ሂወት በምፈልጋት ምንገድ አልሄድም አለች እንጂ ግን ለምን ጠየቅሽኝ አልኳት ?

እሷም ጥያቄ አታብዛ ነገ እሁድ 5 ሰአት ታላቅ ፕሮግራም አለ ለጥያቄወችህ እንዳለ መልስ ታገኛለህ ያልጠበቅከውንም ልዩ ነገር ታገኛለህ ና አለቺኝ

ምንድነው ምትለው ይቺ ልጅ ??
ፕሮግራም ና !
የምን ፕሮግራም? ? ጥያቄ አታብዛ ስላለቺኝ እንደምመጣ እና የት እንደሆነ በደንብ አድራሻውን ነገሪኝ አልኳት ።

እሷም ቦሌ የሆነ ሆቴል እንደሆነ ነገረቺኝ ነገ ማርፈድ እንደሌለብኝ እና ፕሮግራሙን ለመግባት ለሆቴሉ 150 ብር ክፍያ አለው እኔ እጋብዝሃለው አታስብ ግን እንተ በፍፁም እንዳታረፍድ ብላኝ ከ Online ወጣች

ፕሮግራም ወከባ ሰው የበዛበት ቦታ ምናምን ብዙም አይመቸኝም ። ከሪማን ለማየት ብቻ ነው ምሄደው ለሊቱ አልነጋልህ አለኝ ምን አይነት ፕሮግራም ነው የጠራችኝ ለምንስ ጠየቀቺኝ? በዛ ላይ ነገ ከሪማን ላያት ነው ።

ማይነጋ ለሊት ማይጠልቅ ጀንበር የለም ለሊቱ ነጋ ቁርስ በላልቼ ምርጥ ምለውን አለባበስ ለብሼ በጠዋቱ ተነሳሁ ።
5 ሰአት አካባቢ ቦሌ ደረስኩ እሷ ግን ትንሽ አረፈደች በርግጥ የጠራቺኝን የሆቴል አዳራሽ ለማግኘት መከራየን በልቻለሁ ቢሆንም ራሴን ላለማሰደብ ቀድሜ ተገኝቻለሁ
ሆቴሉ በር ላይ ትንሽ ጥብቂያት መጣች አየኋት
ደስ አለኝ በጣም ። እሷም ጎበዝ ቀጠሮ አክባሪ ነህ ብላ ትኬት ሰጠቺኝ ወደሆቴሉ ገባን የሆቴሉ ውበት ደስ ይላል 7ኛ ፎቅ ላይ ወጣን እንደገባን የሰጠቺኝን ትኬት ሰጠኋቸው ። ፕሮግራሙን ለመግባት ስሜ ወረቀት ላይ ተፅፏል ምንድነው ኮተት ሚፈጥሩት ብየ ገባን እሷ ብዙ ሰው ታውቃለች ሰላም ትላለች እኔ በገባንበት ቀለል ያለ የሆቴል አዳራሽ ውስጥ ተመስጫለሁ ሰወች ብዙ ናቸው ፕሮግራው ተጀምሯል ቀጥታ ፊትለፊት ወሰደቺኝ ፕሮግራሙ ምንድነው? ከራሴ ጋር ለመግባባት ጦርነት ገባሁ ።

እሷ በል ሰሚሬ ተከታተል እንቆያለን እዚ ብላኝ ራቅ ብላ ከጓደኞቿ ጋር ቁጭ አለች እኔም ጉዴን ለማየት ቁጭ ብየ ተመስጬ ትኩረቴን ወደፕሮግራሙ አረኩ
------------
ያኔ ሂወቴ እንደአዲስ ተጀመረ .. የሂወቴ መስመር ከዛች ቅፅበት በኋላ ነበር ነፍስ የዘራው ሰሚር ራሱን ያወቀው ለህልሙ መኖር የጀመረው ከዛች ጊዜ በኋላ ነው ለካ ሰሚር ሂወትን አያውቃትም አይ ያ ልዩ እለት..

ፕሮግራሙ ላይ አንድ ገፅታው ሚያምር ሱፍ የለበሰ ሰው ማውራት ጀመረ ..

ይቀጥላል ................

Читать полностью…

Allah is one

በነገው የእረፍት ቀን ማለዳን ለማየት ከታደሉት ነበርኩና የመጀመሪያ ፕሮግራሜ መድረሳ መሄድ ነበር ለባብሼ ሄድኩ ከፕሮግራሙ ጋር እኩል ደረስኩ ፕሮግራሙ ሲጀመር እኔም ገባሁ ግርማሞገስ ያላቸው ኡስታዝ ወጡና ስለወንድማመችነት በመጨረሻው አለም ስላሉት ልዩ ፀጋ ይናገራል በውስጡ ስላሉ ሀሴትን ሚያመነጭ ነገርም ይሰብካል
እሱ ስለወንድማመችነት ሲያወራ ቀጥታ በውሰጤ ማስበው ከማሂር ጋር ከአብዱ ማሜ ፉዲ ጋር ያለኝን ግንኙነት ነበር ይህን እንዳስብ ይሁን አብዱ የጋበዘኝ?

ዳእዋው ለጊዜው ራሴ ላይ ትልቅ ነገር የፈጠረ ይመስላል የጓደኝነትን ቦታ ወደወንድም እየቀየርኩት እንደሆነ ይታወቀኛል በዚ ጉዳይ ጥያቄ እና አስተያየት ከወንዶችም ከሴቶችም በኩል እንዲሰነዘር ተጠየቀ ከወንዶች ብዙ ብዙ ተነሱ ከሴቶች መጀመሪያ የሆነች ሴት መናገር ስጀምር ልቤ ደነገጠ የከሪማ ድምፅ ነው ባለፈው የሰማሁት የሷ ድምፅ የራሴ ሁኔታ ግራ ገባኝ በድምፇ እንዴት እንደዚ ልሆን ቻልኩ

ኡስታዙ ለዚ የክረምት ወር ሚሰጥ ኮርስ እንዳለ እና የኛው ማሜም ከአስተማሪወች አንዱ እንደሆነ ተናገረ እኔም ደስ አለኝ
አብዱን የተርቢያ ኮርሱን ከሱ መድረሳ በራሱ አብዱ መውሰድ እንደፈለኩ እና የዛሬው ዳእዋ ውስጤን እንደሳበው ነገርኩት እሱም ሰሚሬ ይህ ላንተ ስለሚጠቅም በደንብ ትኩረት አርግበት አለኝ ለዲን የምሰጠው ቦታ መውረዱ እሱን ያስጨነቀው ነገር ይመስላል አብዱ ለካ ከማስበው በላይ ትልቅ ነው ስንሰዳደብ እየዋልን የሱን ቦታ በደንብ አላወቅነውም ከመድረሳው ስንወጣ የቀድሞ ጓደኛ ሂወታችንን ቀጠልን ስለመድረሳው መዋቀር እና ውስጡ ላይ ስለሰጡት ቦታ እያወራን ምሳ በልተን አብረን ትንሽ ውለን አሪፍ ሀሳቦችን ስንቀባበል ሰአቱ ረፈደ እሱ ሚሄድበት ጉዳይ ስላለው ሳንቆይ ተለያየን የቀረውን ቀን ሙሉ ቤት ወዲዚ ወደዚያ እያልኩ በወከባ ዋልኩ
ይህን ሁለት ቀን ሳሎን ራት ስላልበላሁ ዛሬ ሂጄ ከአባየ ጋር መብላት እንዳለብኝ ተረዳሁ አባየ እንደመጣ ፈገግታ በተሞላ ፊት ሰላም አልኩት ሰሞኑን ፈጅር ሳይቀሰቅሰኝ ጥሎኝ ሲሄድ የተቆጣ መስሎኝ ነበር ነገር ግን ምንም ነገር አልሆነም በጣም ደስ ብሎኝ እዛው ዜና ምናምን እያየን እየተጫወትን አመሸን ቤት እንደምሳሳቀው የውጭ ሰው ትንሽ እንኳ ባምን አሪፍ ነበር ግን በተፈጥሮየ ከምቀርበው ሰው ውጪ ማላውቀው ሰው ጋር ሆም ብሎ መግባባት ትርጉሙ አይታየኝም
ሰአቱ ሂዷል ወደመኝታ ክፍል ለመሄድ የተወሰኑ ደቂቃወች ነው የቀሩን አባየ እንደሆነ እዛው እንቅልፍ መጣኝ ባይልም አይኑ ቀልቷል ምሽቱን እያዛግን በቲቪ ወደለሊቱ ተጠጋን ነገር ግን ድንገት

የአባየ ስልክ ጮሀ ሰአቱ 5:37 ይላል በዚ ሰአት ማን ሊደውል ይችላል ? የአባየ ስልክ በቀንም ሲደወል ብዙም አልተለመደም እንኳን በዚ ለሊት !
መደወሉ የሁላችንንም ትኩረት ሳበው እኔ ግን የተሳሳተ ስልክ ነው ሊሆን ሚችለው ወይ ቀለል ያለ አስፈላጊ የጓደኞቹ ጉዳይ ነው ከሆነም ስላልኩ ብዙም አልደነገጥኩም አባየ ሂድ አምጣው ሲለኝ ሮጥ ብየ ስልኩን አመጣሁለት ሲያየው የውጭ ስልክ ነው አነሳው እና በተደናገጠ መልኩ ሰላምታ መለሰ ሚያዋሩቱን እየሰማ ትንሽ ቆይቶ ወይኔ ወንድኔ ለምን እንዴት? አለ አባየን በጣም በመደናገጥ ምን ተፈጠረ የምን ወንድም ብየ ለማረጋጋት እየሞከርኩ ስልኩን ተቀበልኩት አጎቴ ነበር ...

ክፍል 3 ይቀጥላል............

Читать полностью…

Allah is one

እንዳያስከፍሉኝ ሰጋሁ ይህን የኮሌጅ ክላስ ጨርሼ ወደ ትምርት አለም መመለስ አልፈልግም በአጎቴ ግዳጅ እና ክፍያም ነው ምማረው ሲጀመረም ሂወቴን በተማርኩበት ለማስመር አላደረኩትም ይህንም ያውቃሉ ለትምርት ትኩረት ካልሰጡ ልስራ ብል ምን ይላሉ ብየ ነበር ጥያቄውን ያነሳሁት ??

የቀጣዩን ቀናቶች ክላስ አልገባሁም ማሜ ስራ ቦታ ሂጄ ነበር ማሜ አሪፍ ይሰራል ግን ብር አያገኝም 😂 እዚ ግባ ማትባል ጉራንጉር የፕላስቲክ መሸጫ ሱቅ አለችው ኪሳራዋ ይበዛል 🤷‍♂

አብዱም እዛው ሱቅ ነበረ ለካ ከዛ ወዲያውኑ ሰሚሬ መጣህ እንዴ ብሎ ሰላም ካለኝ በኋላ ሰምተሃላ እኛጋ የመድረሳች ሃላፊ ቤቱ ጠርቶኛል ከናንተ ጋር ነው ምንሄደው አለኝ እኔም ደሞ ለምግብ እሽ አልኩት
በነገው እለት ከማሂ ጋር ነበር
መድረሳቸውን የገባሁት ልክ እንደገባሁ ያማረ መስተንግዶ ጠበቀን አብዱ እንደቤቱ ሽር ጉድ ይላል ምግብ በላን ገራሚ የምግብ ፕሮግራም ነበር ☺️

እንደጨረስን እጃችንን ታጥበን ቁጭ እንዳልን ድንገት የተዘጋው ሳሎን ክፍት አለ 😳
ያማረ አቋም ከውብ መልክ አይናፋር ልጅ እቃ ይዛ መጣች መልኳ ቀልቶ አይኗ ከልቡ ያምራል ጥቁር ሂጃብ ጠምጥማ ገፅታዋ ለእይታ ይማርካል ያአላህ ምን አይነት ውበት ነው እዛው አይኔን ሳልነቅል ፍራፍሬውን ቁጭ አርጋው ተመልሳ ወጣች በሀሳብ ፀጥ እንዳልኩ ድንገት የቤቱ ባለቤት ከሪማ ሲል ሰማሁት 😟
ከዛ ድጋሚ መጣችና ስለ ቡና እጣን ምናምን አወሩ ከሪማ ላትመጣ በድጋሚ ወጣች ....

ይቀጥላል ........😊

@binte_hikeaeman

Читать полностью…
Subscribe to a channel