binyamzechristos | Unsorted

Telegram-канал binyamzechristos - Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

2518

ከእውነት ማዕድ ተቆርሰው፣ ከጥሩ ምንጭ ተቀድተው፣ ለሕይወተ ሥጋ ወ ነፍስ የሚሆኑ፣ ወደ ክርስቶስ የሚጠቀልሉ ኦርቶዶክሳዊ ትሩፋቶችና፣ በኦርቶዶክሳዊ መነጽርነት የሚታዩ የተለያዩ እይታዎች ይቀርቡበታል።‼️ ኣስተያየት ለመስጠት => @ZeChristosComments_Bot

Subscribe to a channel

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #አቋሜን_ለማጥራት_ያህል‼️
ያለፉት 8 ወራት በፋሽስቱ የዓብዪ ጦርና በአረመኔው የሻዕብያ ሠራዊት የግፍ ግፍ ተፈፅሞብናል። በሕክምና ሥራዬም ከመላው ትግራይ የመጡትን ደም የሚያስለቅሱ ታሪኮች ጠግቤአለሁ። ከዚህ ሁሉ ሰቆቃና መከራ በኋላ ወደ ሚድያ ስመለስ በመንፈሳዊ ከፍታ ላይ የተውኳቸው ሰዎች አቋም ቀይረው አገኘሁ (የተቀየርከው አንተ ነህ የሚሉም አሉ) ሰው ዛፍ ኣይደለምና የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረጉ ባሕርያዊ ነው! የኔ ስህተት 8 ወር ሙሉ የዓብዪ ዲስኩር ሲጠጣ ከኖረ ሰው ጋር ለመግባባት ቀላል አድርጌ መገመቴ ነው። ያም ሆኖ ግን ከዚህ በኋላ የምጽፋቸው ጽሑፎች፣ በስህተት መንገድ ወስደው ድኩም ወንድሜን እንዳያሰናክሉት አስቀድሜ እነዚህን ጽኑ አቋሞቼን እንዲታወቁልኝ እፅፍ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

1) የትግራይን ሕዝብ እንደ ሕዝብ እንዲጠፋ በላይ በአየር የደበደበ፣ በምድር በታንክና በከባድ መሣርያ ያጋየ፣ በመከላከያ ወታደሮች እህቶቼና እናቶቼን የደፈረ፣ ገዳማቶችን ያስበረበረ፣ የቀሩትንም በፎስፈረስ ኣሲድ ያለበለበ፣ አረመኔውን የኤርትራን ሠራዊት ጠርቶ የራሱን ሕዝብ ያስጨፈጨፈ ይህ የዓብይ መንግስት የእኔ መንግስት እንዳልሆነና እንደማልቀበለው፣ ኢትዮጵያ ሰላም የምትሆነውም በዋናነት ብልጽግና ሲጠፋ ነው ብዬ አምናለሁ! እንዲጠፋም እተጋለሁ!

2) የትግራይ ሠራዊት (TDF) ጀግና ኢትዮጵያዊ ነውና እንደ አባቶቹ "አልገዛም፣ አልምበረከክም" ብሎ የእናቱን ደፋሪ፣ የእህቱን አራጅ፣ የገዳሙን ኣፍራሽ ያጠፋ ዘንድ ተነስቷል። በጌታ ኃይል በራሱም ቆራጥነት ሻዕብያንና ብልጽግናን ጠራርጎ በማስወጣት ትግራይን ከሞላ ጎደል ከወራሪ ነጻ አድርጎታል። እነዚህም ለሕዝብ ብለው የሚሞቱ የዘመኔ ጀግኖች ናቸውና የዓድዋውን ታሪክ ከሚደግሙ ከትግራይ ሠራዊት (TDF) ጎን ጋር እቆማለሁ!

3) ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ትግራዋይም ነኝ። ትግራዋይነቴ ከኢትዮጵያዊነቴ ነጥዬ ኣላየውም። እንደ ነፍስና ሥጋ ተዋሕደውና ተጠባብቀው ይኖሩብኛል። ስለ ኢትዮጵያ ሳስብ ስለ ትግራይ ቸል በማለት አይደለም። ስለ ትግራይ ስናገር ኢትዮጵያዊነቴን በመዘንጋት ኣይደለም። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ለመሆን ትግራዋይነቴን እንድጥል የሚነግረኝ ካለ የትግራይ ጠላትና ፍፁም ዘረኛ ነውና ከእርሱ ጋር ሕብረት የለኝም ኣይኖረኝምም።

4) ከአማራ ሕዝብም ይሁን ከኤርትራ ሕዝብ ጋር የሚወራረድ ሒሳብ አለ ብዬ አላምንም፣ ሊኖርም ኣይችልም። እንዲህ ብሎ የሚናገር ቂል ማንም ሊቀበለው አይገባም። የሚወራረድ ሒሳብ ቢኖር ኖሮ ትግራይ ውስጥ ባሉ አማራና ኤርትራውያን ላይ ይወራረድ ነበር። ይህ ግን ተጋሩን አይመጥነንምና፣ የምናወራርደው ሒሳብ ግን ከዚያ ፋሽስታዊ ብልፅግናና አረመኔያዊ ሻዕብያ ጋር ነው፣ መሆንም አለበት። የአማራ ሕዝብ ጠላቴ አልነበረም፣ ሊሆንም አይችልም፣ የትግራይ ሕዝብም የአማራ ጠላት አልነበረም አይደለምም ብዬ በጽኑ ኣምናለሁ!

5) ትግራይ የኢትዮጵያ ዋና አካል ነች! ስለዚህም መገንጠል የሚለውን በግሌ አልስማማበትም። ግን ደግሞ ትግራዋይም ይሁን ዓፋሩ "ለብቻዬ ልሁን" የማለት ሙሉ መብት እንዳለው አውቄለሁ፣ ስለዚህም ሐሳቡን አከብራለሁ። ትግራይ ሀገር መሆን ይሻለኛል ካለ ይህ መብቱ ነው። ይህ ኢትዮጵያን ማፈራረስ የሚመስለው ካለ የፈረሰ ሐሳብ እንዳለው ይወቅ። እንዲያ ቢሆን ኢትዮጵያ ሺህ ጊዜ ፈርሳለች ያስብል ነበር። የቅርቡን የኤርትራን መውጣት እንኳን ብናይ ኢትዮጵያን አፈራርሷታልን? ስለዚህን ትግራይ "ለብቻዬ ልሁን" ካለ:- "አብረን ሆነን ደም ከመቃባትና የማይበርድ የእርስ በርስ ጦርነት ከመግጠም፣ ጥሩ ጌረቤታሞች ሆነን ተከባብረን መሆን ይሻላል" ማለቱ ነውና ባልስማማበትም ሐሳቡን ግን አከብርለታለሁ።

6)ተጋሩ ጠላታችንን፣ የሚደመሰሰው ተደምስሶ የሚማረከው ተማርኮ ከምድራችን ካስወጣነው በኃላ አንድ ጥያቄ ጠየቅን! "ጠላታችን እስካልጠፋ ድረስ መልሶ ሊጨፈጭፈንና ሊያጠፋን ይሞክራልና ምን እናድርግ?" ለዚህም መልሱ ኣምባገነኑን ብልፅግናንን አረመኔውን ሻዕብያን የገባበት ገብቶ ማጥፋት ይገባል። ዛሬ በትግራይ ላይ የተረጨው አሲድ ነገ ኦሮሞውና ጋምቤላው ላይ ይረጭ ዘንድ ወደ ኋላ የማይል ነው መደምሰስ ነበረበት። ይህም ፅኑ አቋሜ ነው። ምዕራብ ትግራይን "የኔ ነው" እያለ ወሮት ያለውን የአማራ ልዩ ኃይልም መውጣት አለበት። በዚህም እስማማለሁ። እነዚህ 2ቱ እንዲሳኩ ግን TDF ከትግራይ ውጭ ጠላትን ለመቅበር መዝመቱን እደግፋለሁ። የምደግፈው ህወሓትን አይደለም፣ እንደማልደግፈው የታወቀ ነውና፣ ይልቁንስ ድጋፌ ለሕዝባዊውው ሠራዊት ነው!

7) ነገር ግን TDF በአማራም ሆነ በኦሮሞ መሬት ውስጥ ገብቶ "መሬቱ የኔ ነው" ብሎ የሚወር ከሆነ አልደግፈውም። ንጹሐን ዜጎችን የሚገድልና የሚያሰቃይ ከሆነ እቃወመዋለሁ። ለ8 ወራት ያየሁትን ስቃይ አማራው ላይ እንዲፈፀም አልፈቅም! "እሰይ፣ እስኪ እነሱም በተራቸው ይቅመሷት" የሚል የዘቀጠ ሓሳብ የለኝም። በኔ ላይ የተፈፀመው በማንም ላይ እንዲፈፀም አልሻምና።

በነዚህ አቋሞቼ ፀንቼ እቀጥላለሁ፣ የማይስማማ ካለ የተሳሰትኩትን በማረም፣ በሓሳብም በመከራከር ይቀጥል። ለዚህ አቅም የሌለውም በጊዜ ከቤቴ ይሰናበት። ቀጠልኩ

#ትግራይ_ትስዕር

©Binyam ZeChristos መስከረም 5 - 2014 ዓ/ም

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#በእንተ_ኣሙ
ዘማሪ አማኑኤል ይባላል፣ የምወደውና የማከብረው በመቐለ ቅ/ቂርቆስ ቤ/ክ ያደገ መንፈሳዊ ጓደኛዬም ወንድሜም ሲሆን የምንቀርበው ሁሉ በፍቅር ቃል "ኣሙ" እንለዋለን። ከዓመታት በፊት ስለ ቀጥተኛዋ እምነት (ኦርቶዶክስ) አንድ ግሩም የመዝሙር ካሴት ያበረከተልን፣ በዝማሬና በስብከት በመድረክ የሚያገለግል ወንድም ነው! አሁን ደግሞ ስለ ቀጥተኛዋ እውነት ሲል ድምፁን ሳይሆን ደረቱን ሊሰጥ፣ መድረክ ላይ ሳይሆን ግንባር ላይ ሊያገለግል ወጥቷል። ኣሙ ከመድረክ ወደ ግንባር ለምን ሄደ? ብዬ ጠይቄው አላውቅም! ልጠይቀውም አልችልም! ዘመዶቹ በጥይት ሲረግፉ፣ እህቶቹ የማንም እንስሳ ይሁን ሰው ያልለየለት ውርጋጥ የወሲብ ማብረጃ ሲሆኑ፣ የተሳለማቸው ገዳማትና አድባራት ሲፈርሱና ሲመዘብሩ፣ በረከትዎ ይድረስ ብሎ የጠየቃቸው መነኮሳት ግንባራቸው በጥይት ሲፈርስ ፣ የትግራይ ከተሞች መንገድ ላይ አቁሞ የመኪናህን ቁልፍ ተቀብሎ መኪናህን በሚነጥቅ ዱርዬ ወታደር ሲከበቡ፣ የታወጀው ጦርነት ከአንድ ፓርቲ ጋር ሳይሆን ከትግራዋይ ማንነት ጋር መሆኑን በዓይኑ ኣይቶ በጆሮው ሰምቶ ሲረዳ፣ ለይትኛው ኑሮ ለየትኛውስ ሕይወት እንደሚቀመጥ ራሱን ጠየቀ?

ኣሙ መንፈሳዊና ዘማሪ ሆኖ ሳለ፣ ስለተገፋውና ስለተጮጨቆነው ሕዝብ ይሞት ዘንድ መምረጡ፣ ከጌታው ዘንድ ያስመሰግነው እንደሆነ እንጂ እንደማያስነቅፈው ገብቶታል። ኣባቶቹ በዓድዋ ድል ጊዜ አረመኔውን ወራሪ ከባንዳዎቹ ጋር ለመመከት ራሳቸውንና ታቦተ ጊዮርጊስን ይዘው እንደዘመቱ ሁሉ፣ እሱም ትግራይን ከአረመኔውን ወራሪ ሻዕብያንና ከባንዳውን ብልጽግና ይመክት ዘንድ ሥዕለ ቅዱስ ቂርቆስን ይዞ ወጥቷል። ኃጢኣት ማለት በግፍ የአንድን ንጹሕ ወንድም ደም ማፍሰስ እንጂ ራስንና ሕዝብን መከላከል እንዳልሆነ ቀድሞ ተምሮታል። እንዲያውም ለሕዝብ ብለህ በረሃብና በብርድ መጠበሱ፣ እህቶቹን ለማትረፍ ብሎ ደረቱን ለብረት ግንባሩን ለጥይት መስጠቱ የ"ፍቅረ ቢጽ" አንድምታው መሆኑ አንብቦታል።

ወዳጃ፣ ተጋዳላይ ዘማሪ ኣሙ የህወሓት አባል ወይም ቅጥረኛ ከመሰለህ የቂልነትህን ጥልቀት ወደር አይኖረውም። ደሙን ለማፈሰስና ህይወቱን ለመስጠት የወጣው የሕዝብ ፍቅር እንጂ የፓርቲ ፍቅር ቀስቅሶት ከመሰለህ የጅልነትህን ባሕር አድማስ ኣይኖረውም!/ሕዝብን ከሚጨፈጭፍ ሠራዊት ጎን ጋር "ከአንተ ጋር እቆማለሁ" እያሉ መሰለፍ ልክ ከሆነ፣ ለምትደፈረው እህቱ ለምትታረደው እናቱ ሲል "እሞትላታለሁ" ማለቱ የቅድስናና የፍጽምና ክብር ይይዛል። ንጉሥ ካሌብ የክርስቲያን ጠላቶችን ከየመን ያስወጣ ዘንድ በአባ ጰንጠሌዎን ተባርኮ እንደሄደው፣ የትግራይ ኦርቶዶክሳውያንም ከንስሐ አባታቸው ጋር ተነጋግረው፣ ንስሐቸውና ቁርባኑን ተቀብለው እየወጡ ነው። በእውነት ክብር በሰው ብዛት ሳይሆን በጌታ ጉልበት ለሚያምኑት ይሁን። ኣቤቱ እንጨብጣቸዋለን ያሉት ሲጨበጡ ኣይተናልና፣ ክንድህ ኃይል ስምህም ጉልበት ይሁነን! ወንድሜን ኣሙን ፍጹም መጠበቅን ጠብቅልኝ! በቂርቆስ ሕፃንህ፣ በድንግል እናትህ ብሥጋና በደምህ ለዘላለሙ አሜን!

@Binyam ZeChristos መስከረም 3 - 2014 ዓ/ም

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#የእኔና_የአንተ_ልዩነት
√ያኔ ሲጀመር፣ "ሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጠረ የተባለው ነገር ተጣርቶ ወንጀለኛው ይጠየቅ" ብዬ ስልህ፣ አንተ ግን "ትግራይ መመታት አለበት" ብለህ ለጦር እጅህን ያነሳህ የጦር ሰው ነህ።

√ "ሕዝብና ፓርቲ ይለያያል" ብሎ የመጣው የብልጽግና ሠራዊት እግሩ እንደገባ ፓርቲን ትቶ ሕዝቡን እየገደለና እያረደ መሆኑን በመረጃም በማስረጃም ነገርኩህ። አንተ ግን "ከመከላከያ ጎን ጋር እቆማለሁ" ብለህ በመጮህ ከደም አፍሳሾች ጋር መቆምህን ነገርከኝ።

√ "የአማራ ልዩ ሐይል ከትግራይ መውጣት እንዳለበት፣ የመሬት ጥያቄ ካለበትም በጠረቤዛ ዙርያ ያድርገው እንጂ እንደ አረመኔ ተጋሩን ገድሎና ጨፍጭፎ የሚወስደው ቦታ የለም" ብዬ ስልህ፣ መሬታችን ስለሆነ እንወስደዋለን ብለህ የደነፋክ፣ ግን ደግሞ ሱዳን የአማራን መሬት "መሬቴ ነው" ብላ ስትወር "እንዴት በሃይል መሬት ይወረራል?"' ብለህ የምታለቅስ ማበድህን ያላወቅህ ሰው ነህ።

√ ሕዳር 19 ቀን ብልጽግና መቐለ ሲገባ፣ ከተማውን እንዴት ባለ ከባድ መሣርያ ሲደበድባት እንደዋለና ብዙ ንጹሓን ዜጎች ደማቸው ፈሶ ሰውነታቸው ተቆራርጦ እንደሞተ የዓይን ምስክር ሆኜ ነገርኩህ። አንተ ግን ከዚያ ይልቅ "በገብርኤል በዕለተ ቀኑ መቐለ ተያዘች" ብለህ የፈሪሳዊነትህን ጥግ የመሰከርክ፣ "አንድ ሰው ሳይሞት ነው መቐለ የገባነው" ለሚለው ዜና ያጨበጨብክ ምስኪን ሰው ነህ።

√ የእህቶቼን በአሲድ መቃጠል በሺድዮ ሳሳይህ፣ የእናቶቼን መደፈር በፎቶ ሳስረዳህ፣ የህፃናቶች ሰውነት መቆራረጥ ከራሳቸው ከገዳዮቹ ወታደሮች አንደበት እንካን እያሰማሁህ፣ በኢትዮጵያዊነት ወግ "ያሳዝናል፣ እውነት ከሆነ ይህንን አወግዛለሁ" የምትልበትን አቅም አጥተህ "ውሸት ነው! የህወሐት ፕሮፓጋንዳ ነው" ብለሀኝ ያረፍከውና ሰውነትህን እንድጠረጥረው ያደረከኝ ሰው ነህ።

√ የሻዕብያ ወታደሮች ጨዋ እህቶቼን ለ10 ሲደፍሯቸው፣ ብልታቸው ውስጥ ሚስማርና ድንጋይ ሲከቱበት፣ ቤት እያቃጠሉ ማንካና ሹካ ሲሰርቁ ለምን ዝም እንዳልክ ስጠይቅህ፣ የዓለም ሚድያዎች እንኳን የተቀበሉትን እውነት "የኤርትራ ወታደሮች አልገቡም" ብለህ የሸመጠጥከኝ፣ መንግስት ራሱ ሻዕብያዎች መግባታቸው ሲያምን ደግሞ "ራሳቸውን ለመከላከል ነው የገቡት" ብለህ በእህቶቼ ላይ ያፌዝክ፣ ካንተ ጋር እኩል ኢትዮጵያዊ ተብዬ በመጠራቴ እንዳፍር ያደረከኝ ማፈርያ ሰው ነህ።

√ የብልጽግና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ መከላከያ ሠራዊት (TDF) ተቀጥቅጦ ነው ከትግራይ የወጣው ብዬ የተማረኩትን የሠራዊቱ የበላይ አመራሮችን ምስክር አድርጌ ነገርኩህ፣ አንተ ግን አሁንም "የትግራይ ገበሬ እንዲያርስ" ፣ አልያም "የፅሞና ጊዜ ለመስጠት ነው" ብለህ የምታስብ ድኩም፣ ሠርዊቱ እንኳን እንዲያ ብሎ ቢወጣ በዓብዪ የተሾሙት ጊዜያዊ ኣመራሮች ለምን እንደፈረጠጡ እንኳን መጠየቅ ያቃተህ ምስኪን!

√ አንተኮ በትግራይ የተማረኩትን ከ50,000 በላይ ወታደሮች መንገድ ላይ እንደ በግ ሲግተለተሉ ኣይተህ "የታላቁ ሩጫ ከሆነ ሀገር ኣምጥታችሁ ሬንጀር ልብሳቸውን ደግሞ ኢዲት አድርጋችሁ ነው እንጂ የተማረከ የለም" ብለህ በራስህ ላይ ይምታሾፍ ሰው እኮ ነው! ይህንን ጭንቅላት የተሸከመውን የአንገትህን የትዕግስቱን ፅናት አደንቃለሁ!

√ ባንተ ጭብጨባና ድጋፍ ተጋሩን ለመጨፍጨፍ የመጡ ሺዎች የሚቆጠሩ፣ ግን ደግሞ የተማረኩ ወታደሮችን በረሃብ ከደረቀው ጉሮሮኣችን እያበላንና እያጠጣን እንደሆነ ነገርኩህ። አንተ ግን አሁንም ያለንን አብስለን እንኳን እንዳንበላ "ለትግራይ መብራትና ስልክ እንዳይለቀቅላት" ከሚሉት ዘንድ ተሰልፈሃል።

√ እኔ በምግብ እጦት ምክንያት ስንት ሰው እየረገፈ እንደሆነን እርዳታዎች እንዲገቡ የቻልከውን እንድታደርግ ነገርኩህ። አንተ ግን አሁንም "እርዳታውን ህወሐት ልትወስዱው ትችላለችና ምንም ዓይነት የምግብ እርዳታ መቅረብ የለበትም" ብለህ፣ አሁንም በተጋሩ ሞት ልትረማመድ መሻትህን ገለፅክ።

√ አንተ ህወሓት እንዲጠፋ ትጸልያለህ፣ እኔም ብልፅግና እንዲደመሰስ እሻለሁ። ምኞታችን ባልከፋ፣ አንተ ግን ህወሐትን ለማጥፋት አስፉላጊ እርምጃ መወሰድ አለበት ብለህ የተጋሩን መጨፍጨፍ Justifiy ለማድረግ ትደክማለህ፣ እኔ ግን ብልጽግናን ለማጥፋት የአንድም አማራም ሆነ ኦሮሞ ወንድሜ ደም እንዲፈስ አልፈቅድም!

©Binyam ZeChristos. ነሐሰ 30 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

🔥... በዓለ_ጰራቅሊጦስ ~ #ጾመ_ሐዋርያት ...🔥
✝ሎሚ ሰንበት ካብቶም 9 ዓበይቲ ናይ ጎይታ በዓላት (ጽንሰት፣ ልደት፣ ጥምቀት፣ ደብረታቦር፣ ሆሳዕና፣ ስቕለት፣ ትንሳኤ፣ ዕርገት፣ ጰራቅሊጦስ) ሓደ ዝኾነ በዓለ ጰራቅሊጦስ እንትኸውን እዚ ድማ መንፈስ ቅዱስ ኣብ ልዕሊ ሓዋርያት ዝወረደሉን፣ ብመንፈስ ተጠሚቖም ጸግኡ ዝተቐበሉሉን መዓልቲ እዩ። ጰራቅሊጦስ (Parakletos) ዝብል ቃል ግሪክኛ እንትኸውን "መጽናንዒ" ማለት ኮይኑ ንእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዝቕጸል ስያመ እዩ። ጎይታ እውን ንሓዋርያቱ መጽናንዒ መንፈስ ከምዝልእኸሎም ነጊርዎም ነይሩ። "እቲ ኣቦይ ብስመይ ዝሰዶ #መጸናንዒ #መንፈስ ቅዱስ፡ ንሱ ዅሉ ክምህረኩም፡ ዝነገርኩኹም ዘበለውን ከዘክረኩም እዩ>(ዮሐ14:16/26) ፣ <እቲ ኣነ ኻብ ኣቦ ዝሰደልኩም #መጸናንዒ፡ ካብ ኣቦ ዝወጽእ መንፈስ ሓቂ ምስ መጸ ግና፡ ንሱ ኺምስክረለይ እዩ>(ዮሐ15:26) ፣ <ኣነ እንተ ዘይከድኩስ፡ እቲ #መጸናንዒ ናባኻትኩም ኣይመጽእን እዩ እሞ፡ እንተ ኸድኩ ግና ንእኡ ኽሰደልኩም እየ>(ዮሐ16:7)

✅ ጎይታ ካብ ሙታን ተሲኡ ኣብ 40 መዓልቱ ናብ ሰማይ እንትዓርግ እውን <ንስኻትኩም ግና ካብ ላዕሊ #ሓይሊ ኽሳዕ እትለብሱ ኣብ ከተማ የሩሳሌም ጽንሑ> (ሉቃስ 24:49) ከምዝበሎም፣ <#መንፈስ ቅዱስ ናባኻትኩም ምስወረደ ግና #ሓይሊ ኽትቅበሉ፣ ኣብ የሩሳሌምን ኣብ ኲላ ይሁዳን ኣብ ሰማርያን ክሳዕ ወሰን ምድሪ ምስክር ክትኰኑኒ ኢኹም> (ግብሪ 1:8) ኢሉ እውን ተስፋ ከምዝሃቦም ነንብብ።

❤️ክርስቶስ ምስ ዓረገ ሐዋርያት ኣብ የሩሳሌም ተኣኪቦም እናሃለዉ "በዓለ ሓምሳ" ዝበሃል ናይ አይሁድ በዓል በጽሐ (ብግሪክ ጴንጠቆስጤ Pentekoste ይበሃል። ትርጉሙ ሓምሳ ማለት እዩ። ሓደ ሓደ መናፍቃን ግና ትርጉሙ ካብዘይምፍላጥ መጸውዒ ስሞም ይገብርዎ። ጴንጤ/ጴንጤቆስጤ ማለት ግና 50 ማለት እዩ) "በዓለ ሓምሳ" ዝተብሃለሉ ምኽንያት ድማ፣ አይሁድ ድሕሪ ፋሲካኦም ን7 ሰሙናት (49 መዓልቲ) በዓል ገይሮም ኣብ መወዳእታ መበል 50 መዓልቲ ብድሙቕ መልክዑ ስለዝኽበር እዩ። (ዘጸ34:22፣ ዘሌዋ 23:15-22) ነዚ በዓል ንምኽባር ድማ ኣብ ዝተፈላለዩ ከባቢታት ዝነብሩ አይሁድ ናብ ኢየሩሳሌም ተኣከቡ። በዚ ጊዜ እቲ ጎይታ ዝነገሮም ሓያል መጽናንዒ መንፈስ ዝወረደሎም። <ብድንገት ከዓ ከም ብርቱዕ ህቦብላ ንፋስ ካብ ሰማይ ደሃይ መጸ። ነታ ኣብኣ ተቐሚጦም ዘለውዋ ቤትውን ንብዘላ መልኣ። እተመቓቐለ ልሳን ሓዊ ዝመስል ድማ ተራእዮም። ኣብ ልዕሊ ነነፍሲ ወከፎም ከኣ ተቐመጠ። ኲሎም ድማ መንፈስ ቅዱስ መልኦም፤ መንፈስ ቅዱስ ኪዛረቡ ኸም ዝሀቦም'ውን ብኻልእ ቋንቋታት ክዛረቡ ጀመሩ> (ግብሪ 2:2-4) ልሳን ወይድማ ቋንቋታት ዝተቀበሉሉ ምኽንያት ድማ ናብ ዝተፈላለዩ ከባቢታት ዓለም ብምኻድ ንከስተምህሩ እዩ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነዚ በዓል "ናይ ቤተክርስቲያን ልደት" ብምባል ይጽውዖ! ኣብ ልዕሊ ሐዋርያት ወሪዱ ሓይሊ ዝሃበ መንፈስ ቅዱስ ንዓና እውን ሓይልን ጥብአትን ይሃበና።

✝በዓለ ጰራቅሊጦስ ምስኣኽበርና ድማ ሰኑይ እቲ ብሃንቀውታ እንጽበዮ ጾመ ሐዋርያት ይኣቱ። (ጾመ ሰነ ዝብል ናይ ዘይተምሃረ ጨዋ ዘረባ እዩ) ልክዕ ምስቲ ጾም ድማ "ጾመ ድኅነት" ይጅምር። እዚ ድማ ናይ ረቡዕን ዓርብን ጾም እዩ። ጾመ ሐዋርያት እንጾመሉ ምኽንያት ድማ፣ ጎይታ ንባዕሉ "መርዓዊ" ንሐዋርያት ድማ "ኣዕሩኽ መርዓዊ" ኢሉ ብምምሳል መዓዝ ክጾሙ ከምዘለዎም እንትምህረና <ኢየሱስ ከኣ በሎም፦ ኣዕሩኽ መርዓዊኸ፡ መርዓዊ ምሳኣቶም ኽሳዕ ዘሎ፡ ከመይ ኢሎም #ክጾሙ ይዀነሎም? መርዓዊ ኻብኣታቶም #ዝውሰደላ መዓልቲ ግና ክትመጽእ እያ፡ ሽዑ ኸኣ #ይጾሙ> ይብል! (ማቴ9:15፣ ማር2:19፣ ሉቃ5:34) መርዓዊ ዝተብሃለ ጎይታ ካብኣቶም ዓሪጉ እንፍለ ከምዝጾሙ ንምግላፅ እዩ። ሐዋርያት ድማ ድሕሪ ዕርገት ጎይታናን መንፈስ ቅዱስ ድሕሪ ምቕባሎምን <ንእግዚኣብሄር ከገልግሉን ክጾሙን ከለዉ ኸኣ መንፈስ ቅዱስ "በርናባስን ሳውልን ነቲ ዝጸዋዕክዎም ዕዮ ፍለዩለይ" በሎም።ሽዑ #ጾሙን ጸለዩን ኣእዳዎም ከኣ ኣንበሩሎም እሞ ሰደድዎም> (ግብሪ 13:2-3) በዚ ምኽንያት በረኸትን ኣማላድነት ሐዋርያት ንምቕባል ጾመ ሐዋርያት ንጾም። ቡሩኽ በዓልን፣ ቅዱስ ጊዜ ጾምን ይኹነልና ትብለኩም ኦርቶዶክሳዊት ቤ.ክ!

👇ንኻልኦት መንፈሳዊ ጽሑፋት👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc2WXYXfdEtME6smg
©Binyam ZeChristos ሰነ 12 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

ኣብ ጊዜያዊ ኹነታት ትግራይ መሰረት ገይሩ፣ ኣታዊኡ ንተጋሩ ተፈናቐልቲ ንክኾን ዝተዳለወ "ንብዓት ራሔል" ዝብል ናይ ዲ/ን ክብሮም ናይ ትግርኛ መዝሙር፣ ፅባሕ ሰንበት ሰዓት 8:00 ኣብ ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ኣዳራሽ ስለዝምረቕ ናይ ድጋፍ ትኬት ብምግዛእ ንክትርከቡ ብትሕትና ንዕድም።

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #ካልሳይ_ምዕራፍ_ህፁጽ_ሓገዝ ‼️
ግፍዒ ሕዝቢ ትግራይ ሐዚ እውን እናቐጸለ ዘሎን ክሳብ ኮነ ሓገዝናን ድጋፍናን ቐጻልነት ክህልዎ ይግባእ:: ናይ ትግራይ ፕሮፋይል ምግባር ጥራሕ ነቲ ኣብ በረኻ ወዲቑ ብጥምየት ዝፈሓስ ብጻምእ ዝመውት ዘሎ የዋህ ትግራዋይ ድራር ኣይኾነይ:: መጽሓፍ "እንጀራኻ ኣብ ቕድሚ ማይ ደርብዮ! ድሕሪ ዝተወሰነ ጊዜ ክትረኽቦ ኢኻ" ከምዝበሎ (መክ 11:1)እንጀራና ብማይ ብዝተመሰለ ከርሰ ርኁባንን ጉርዔ ጽሙኣንን ንክድርብዮ ይግባእ:: ደሓር ድማ ብምድሪ ኽኦነ ብሰማይ ካብ ኣምላኽ ክንቕበሎ ኢና! ንሓን እውን ኣብ 1ይ ዙር ኣብ መቐለ ንዝነብሩ ተመዛበልቲ ናይ ፍርናሽ፣ ሳሙና ሞዴስን ድጋፍ ዝተገበረ እንኸውን እዚ 2ይ ዙር ድማ ኣብ መቐለን ከበቢኣን ከምኡ ኣብ መላእ ትግራይ ንዝረኸብናዮም ኣብ ገዛ ተዓፅዮም መዓልቲ ሞቶም ንዝፅበዩ ዝተገበረ ሓገዝ እዩ:: ናይ ጥረ ገንዘብ ሓገዝ ብምቕዳም እንሆ ሓገዝ 3ይ ዙር!

1⃣ #ኣብ_መቐለ:- ዳ ገብርኤል ሰፈር ን15 ዝተጸገሙ ወገናት ከኪ 2000 ቅርሺ፣ ኣብ ዳ ገብርኤል 17 ቀበሌ እውን ን15 ጽጉማት ከኪ 2000 ቅርሺ፣ ከባቢ ኩሓ ን10 ጽጉማት ከኪ 2000 ቅርሺ፣ ከባቢ ዓዲሓ ን10 ጽጉማት ከኪ 2000 ቅርሺ ብምሕጋዝ ብጠቕላላ ካብቲ ዝለኣኽኩምዎ 100,000 በጺሑ ኣሎ::

2⃣ #ዕዳጋ_ሓሙስ:- ኣብ ከባቢ ዕዳጋ ሓሙስ ድማ ን20 ጽጉማት ከኪ 2000 ብምሃብ 40,000 ኣብ ሓገዝ ውዒሉ::
3⃣ #ሰሜን_ምብራቕ_ትግራይ:- ከባቢ ዛላምበሳ፣ ፋፂ፣ ጉዕተሎ፣ ፍረዳሹምን ደንገላት ማርያም ንዝረኸብናዮም 22 ጽጉማት ተጋሩ ድማ ከኪ 2000 ቅርሺ ብምሃብ 44,000 ሓገዝ ተገይሩ አሎ::
4⃣ #ወጀራት:- ኣብ ከባቢ ወጀራት ድማ ንዝረኸብናዮም 10 ጽጉማት ከኪ 2000 ቅርሺ ብምሃብ 20,000 ሓገዝ ተገይሩ እዩ::
5⃣ #ዓዲሽሁ_ቦራ:- ኣብዚ ከባቢ ድማ ንዝረኸብናዮም 5 ጽጉማት ምዕመናን ከኪ 2000 ቅርሺ ብምሃብ 10,000 ሓገዝ ተገይሩ እዩ::
6⃣ #ወረዳ_ዳ_መኾኒ:- ከባቢ ሽምጣ ገለውሳ ድማ ብሰንኪ ስደትን ምዕፃው መንገድን 1 ወላዲ ዝተረኸቡ ኾይኖም 2000 ቅርሺ ተሓጊዞም እዮም::
7⃣ #ገዳም_ዋልዳብ:- ካብ ዋልድባ ገዳም ተሰዲዶም ንዝመፁ ኣቦታት ድማ 50,000 ቕርሺ ሓገዝ ተገይሩ እዩ:: እዚ ብጠቕላላ ካብ ዝለኣኽኩምዎ 266,000 ቕርሺ ኣ ሓገዝ ውዒሉ ኣሎ:: ብተወሳኺ ድማ ኣብ መቐለ ፍሬምናጦስ መሐብሐቢ አረጋውያንን ሕጻናትን ንዝነበሩ ኣረጋውያን 450 ዓበይቲ ዳይፐራት ብምግዛእ (1 ዳይፐር - 17 ቅርሺ) 7650 ቅርሺ ሓገዝ ዝኾነ እንትኸውን፣ ምስቲ ናይ ቕርሺ ሓገዝ ድማ 273,650 ቕርሺ ናብ ትግራይ ምዕመናን በጺሑ ኣሎ::

‼️ካብ ምቑዛም ሓሊፍና ለውጢ ብዘምፅእ ሓገዝ ንትግራይና ንብፀሐላ።‼️

ባንክ ንግዲ ኢ/ያ (CBE)
1000 372639044
Hayelom G/medhin
Mahder G/eyesus

©Binyam ZeChristos ግንቦት 12 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌ #መሕጠዪ_ጾም ❌
እቲ "ጾመ ትግራይ" እናተብሃለ ዝውጋዕ ዘሎ ብዓይኒ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከመይ ይረአ? ዝብል ናይ ብዙሓት ሕቶ ስለዝቐረበ እምበር ብዛዕባ እዚ ንኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን መልሲ ምሃብ ምሕፈሪ እዩ። ክንደይ ዓመት ዝተምሃርናዮ፣ ኩሉ ሻብ ኣብ ማሕበራዊ ሚድያ እንጽሕፎን ብቐሊሉ ናብ ንስሐ ኣቦና ደዊልንን እንርድኦ ጉዳይ ስለዝኾነ! እዚ ካብ ግንቦት 17 - 21 ጾመ ትግራይ ተባሂሉ ዝውረ ዘሎ ነገር ብዓይኒ ቤ/ክ ብብዙሕ መንገዲ ዝተጋገየን ዝተወገዘን ስራሕ እዩ። እተን ፪ መሰረታዊ ጌጋታት ከብራህርህ።

1⃣ #ጾም_ኣብ_ዘመነ_ፋሲካ:- ካብ ዕለተ ትንሳኤ - ጰራቅሊጦስ ዘለዋ 50 መዓልትታት "ሰሙነ ፋሲካ" ፣ "ዘመነ ፋሲካ" ፣ "በዓለ ሓምሳ" እናተብሃላ ይጽውዓ። 50 መዓልቲ ከም ሓንቲ መዓልቲ ከም ትንሳኤ እየን ዝኽበራ። ስለዚ ብዘይካ ቀዳም ሥዑር ድማ፣ ቀዳም ኾነ ሰንበት (እሑድ) ኣይጽወምን፣ ውጉዝ እዩ። ነዚ ድማ ናይ ቤ/ክ ናይ ሥርዓት መጽሓፍ ዝኾነ ፍትሐ ነገስት (ፍትሐ መንፈሳዊ) መረዳእታ ንፀውዕ።
📌ፍት.መን.ዓንቀጽ 723:- "ኢይጹሙ በዕለተ እሑድ ወሰንበት ዘእንበለ ሰንበት ዘኮነ ባቲ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅቡረ ውስተ መቃብር - ብዘይካ ጎይታና ኢየሱስ ክርስቶስ ዝተቐበረላ ቀዳም መዓልቲ (ቀዳም ሥዑር)፣ ብቀዳምን ብእሑድን #ኣይጹም»

ትንሳኤ ጎይትነት ክርስቶስ ዝተገለፀሉ፣ ሞይትና ከምዘይንተርፍ ዘረጋገፅናሉ ናይ ሓጎስን ደስታን ዕለትን ዘመንን እዩ። ጾም ድማ ናይ ብሓዘንን ብተዋርዶን ናብ ኣምላኽ እንጠርዐሉ ጊዜ እዩ። ኣብ መርዓ ኣይተእውን፣ ኣብ ቐብሪ ኣይትዕልልን! ስለዚ ድማ ብግልፂ ቋንቋ ኣብ በዓለ ሓምሳ ጾም ኾነ ዋላ ሓዘን ዝተወገዘ እዩ፣ ዝጾመ ሰብ እውን ከም ሓጡኣተኛ ዘቑፅሮን ቅፅዓት (ቀኖና) እውን ዘውህቦ እዩ። ሰማይን ምድርን ዝሕጎስሉ ዘመነ ፋሲካ ንዒቑ ብጾም ስለዘሕለፈ!
📌ፍት.መን.ዓንቀጽ 739:- «ወዘሰ ይጸውም በዕለተ እሑድ፣ ዘውእቱ ዕለተ ትንሣኤ #ኃጥእ ውእቱ። ወይደልዎ #ኲነኔ። ወከማሁ ይገብር በበዓለ ሓምሳ አው ዘየሓዝን በዕለተ በዓላት ዘእግዚእነ ዘይደሉ ለነ ፍሥሐ መንፈሳዊ ቦሙ ወአኮ ሐዘን --- ናይ ትንሳኤ ዕለት ዝኾነ ብሰንበት ዝጾም ሰብ #ሓጢኣተኛ እዩ፣ #ቅፅዓት እውን ይግቦኦ። ኣብ በዓለ ሓምሳ እውን ከምኡ ዝጸውም፣ ሐዘን እንተይኮነስ መንፈሳዊ ታሕጓስ ክንገብረለን ዝግባኣ ናይ ጎይታ በዓላት እውን ሐዘን ዝገብር ከምኡ #ቅፅዓት ይግቦኦ»

ካበይ ዝመፀ እዩ ደኣ ኣብ ዘመነ ፋሱካ "ጾመ ትግራይ" እናበልካ ሰብ ምድንጋር? ኣሽምባይዶ ባዕልና እንእውጆ ጾም እሞ ይትረፍ፣ ዓበይቲ ዝኾኑን ጾመ ድህነት ዝበሃሉን ዓርብን ረቡዕን እኳ ኣብ በዓለ ሐምሳ ኣይንጾምን። ረቡዕን ዓርብን ዘይንጾም ዘለና ነቲ ዝጾምናዮ 40 ጾም ንምክሕሓስ እንተይኮነስ፣ ናይ በዓለ ሓምሳ ልዕሊ ኹሉ ኽቡር ስለዝኾነ እዩ።
📌ፍት.መን.ዓንቀጽ 603:- «ወጾመ ረቡዕሰ ወዓርብ ይጹሙ ወትረ #ዘእንበለ_በዓላት #ወበዓለ_ሐምሳ --- ናይ ረቡዕን ዓርብን አጽዋማትን እውን ብዘይካ በዓላትን #ብዘይካ_በዓለ_ሓምሳን ይጹሙ»

ኣሽምባይዶ ባዕልና ንእውጆ ጾም እሞ ይትረፍ፣ ሓደ ሰብ እንተይተፈለጦ ጾመ አርበዓን ሕማማትን እንተሓሊፈዎ፣ ድሕሪ በዓለ ሓምሳ እምበር ኣብ ውሽጢ በዓለ ሓምሳ ኣይፍቀድን።
📌ፍት.መን.ዓንቀጽ 588:- "ወለእመ ኮነ አሐዱ ውስተ ቀላይ ወኢያእመረ ዕለተ ሕማማት፣ ይጹም #እምድኅረ_በዓለ_ሓምሳ - ሓደ ሰብ ብባሕሪ እናኸደ ሕማማት መዓዝ ምዃኑ ተዘይፈሊጡ (እንተሓሊፉዎ) #ድሕሪ_በዓለ_ሓምሳ ይጹሞ»

ስለዚ ንትንሳኤኡ ዝደፍእን ዝንዕቕን ኣብ ቅድሚ ኣምላኽ ዝተንዓቐን ጾም እናምፃእኹም ንባዕልኹምን ንየዋሃትን ኣይተሕጥዩ!

2⃣ እቲ ኻልኣይ መሰረታዊ ጥፍኣት ድማ፣ ብሱሩ ዘለናዮ ጊዜ ዘመነ ፋሲካ ተዘይኸውን ኸ፣ ባዕልና ዲና ጾም ክንእውጅ ደሊና ነይርና? ናይ ፖለቲካ ጽሑፋትና ሰባት ላይክን ሼርን ገይሮሞ ማለት ኣብ ሃይማኖት እውን ከምኡ ማለት ኣይኮነን። ንክንፈልጦ ግን፣ ጾም ክእውጅ ዝኽእል ሊቀጳጳስ ወይድማ ቅ/ሲኖዶስ እዩ! ካልኦትና ግን እምነትና ንፈልጥ! ብኸምዚ ዓይነት ተራ ወግዕታት ተዘይንደናገፅ። እምነትና ኣብ መጽሓፍ እምበር ኣብ ፌስቡክ ኣይንግበሮ። ናይ ጽባሕ ትግራይ ቤ/ክ እውን ከየጋጥማ ዘስግአኑ እዚ እዩ፣ መፃወቲ መናፍቃን ከይንኸውን።
©Binyam ZeChristos ግንቦት 11 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

✝ ‼️ #የቅዱስ_ያሬድ_ወንጌል!‼️ ✝

✅ ቅዱስ ያሬድ ከመላክእት ዜማ ተምሮ መጥቶ ያተማራቸው ትህርቶችና ዜማዎች በ3 የዜማ ዓይነቶችና በ10 የዜማ ምልክቶች የተቀነባበሩ ሲሆኑ እያንዳንዱም ከወንጌል ጋር እንዲገናኙ በማድረግና በውስጣቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ያዘሉ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል:: እነዚህም ምልክቶች ድፋት፣ ሂደት፣ ቅናት፣ ይዘት፣ ቁርጥ፣ ጭረት፣ ርክርክና ደረት ፤የሊቃውንቱ ደግሞ "ድርስ"ና "አንብር" ሲሆኑ የየራሳቸው ምሳሌና ትርጉም አላቸው::

1⃣ #ድፋት:-ዜማውን ወደታች ረገጥ አድርጎ የሚባል ሲሆን ይህም ወልድ ከሰማያት መውረዱን፣ በማሕጸነ ድንግል ማደሩንና ሰው መሆኑን ያሳያል::
2⃣ #ሂደት:-ሳታቆም አዚም ለማለት ሲሆን የጌታ 3 ዓመት ከ3ወር በስጋ መመላለሱን ደግሞ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ የነበረው እንግልትን ያስታውሰናል::
3⃣ #ቅናት:-የቃልን የመጨረሻ ፊደል ይዞ ቆረጥ በማድረግ ዜማውን አንቅ ማድረግ ሲሆን ጠማማ ቅርጽ አለው::ይህም የአይሁድ ምሳሌ ሁኖ የልባቸውን ክፋት የሐሳባቸውም ጠማማነትን ይናገራል
4⃣ #ይዘት:-በፍጥነት ከሚዜመው ቃል የመጨረሻውን ቃል ያዝ ማድረግን ሲያሳይ ምልክቱም አንድ ነጥብ ናት:: ጌታም ጭማሪ የሌለው ንፁሐ ባሕርይ ቢሆንም በክፉዎች እጅ መያዙን ይመሰክራል
5⃣ #ቁርጥ:-ድምጽን ቀንሶና አምቆ በመያዝ እንደገና ገፋ አድርጎ መጮህን ሲያሳይ ይህም የዮሐንስ ስብከት "ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ይቆረጣል"የሚለውንና የጌታ "ይሰቀል" ውሳኔን ለማሳሰብ ነው::
6⃣ #ጭረት:-አንድ ፊደል ጫር አድርጎ የሚዜም ሲሆን ጠመም ያለ ጎባጣ ምልክት አለው::ይህም ጌታ ራሱን የመቱበት በትረ ሕለትን ለማዘከር ነው::

7⃣ #ርክርክ:-አጭሩን ዜማ ለማርዘም የሚጠቅም ሲሆን ምልክቱም የ2 ነጥብ(:) ነው:: ይህም የጌታ ለሰው ፍቅር ብሎ ያፈሰሰው የደም ነጠብጣብ ያስታውሰናል::
8⃣ #ደረት:-ቃሉን ከፍ በማድረግ አንዷን ፊደል ቆንጠጥ አድርጎ በማንሳት የሚዜም ሲሆን ይሄም የክርስትናችም ኩራት የሆነውን የጌታ ትንሳኤን ብስራት ለመግለፅ ነው::
9⃣ #ድርስ:-የቃልን የመጨረሻ ሆሄ ወደ ኋላ በመሳብ የሚዜም ሁኖ ምልክቱ "ስ" ነው::ይሄም "ስ"ፊደል ቀና ያለ ነውና አዳምና ልጆቹ በኢየሱስ ደም ከባርነት መውጣታቸውን ይናገራል
1⃣0⃣ #አንብር:-አንድን ፊደል ያለ ርክርክና ያለ ተጨማሪ ዜማ ማቆም ማለት ሁኖ ምልክቱ "ር" ነው:: ይህም ር ወደ ቀኝ የተከፈተች መሆን ኢየሱስ በአብ ቀኝ መቀመጡንና አንድም ጻድቃን አግዚአብሔር ቀኝ እንዲቆሙ ለማጠየቅ ነው:: ምልክቶቹ 10 መሆናቸው የ10ቱ ሕዋሳት(5 ሕዋሳተ ሥጋና 5 ሕዋሳተ ልቦና) ምሳሌ ሲሆኑ ሕዋሳቱን የጠበቀ ጌታን እንዲያስደስት በ10ቱ ምልክቶችም መዘመር ጌታን እንዲያስደስት፣ ልቦናን ወደ ጌታ እንደሚያንበረክክ ለማስረዳት ነው:: በዚህም ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ በትምህርትዋ፣ በዝማሬዋና በምልክቶችዋም ሳይቀር ጌታን ትሰብካለች::

💚 #ግዕዝ:- ይህ ዜማ ጠንከር ያለ ሲሆን የአብ ምሳሌ ነው:: ይህም የአብ ቃል ኪዳን መፈጸሙና መጠበቁ ያሳያል::በጾመ እግዚእ(ሁዳዴ) በ5ቱ የመጀመርያ ሳምንታት መዜሙ ደግሞ 5500 ዘመናትን ለማስታወስ ሲሆን ከ2ቱ ዜማዎች ቀድሞ መዜሙ ደግሞ ስመ ሥላሴን ስንጠራ አስቀድመን ስመ አብን ለመጥራታችን ለማሳየት ነው(የስም ቅደም ተከተል ግን ስልጣንን አያሳይም)

💛 #ዕዝል:- ትርጉሙ ታዛይ ተደራቢ ማለት ሲሆን የወልድ ምሳሌ ነው ይህም በድንግል ማሕጸን በማርያምም ጀርባ ታዝሏልና ነው:: በነብያትና በሰሎሞንም ሲዜም 5ቱ መስመሮች በግዕዝ 2ቱ መስመሮች ግን በዕዝል ስለሚዜም ተደራቢ ተብሏል:: በሁሉም የጌታ በዓላትም ዕዝል ቅዳሴ መቀደሱ የወልድ ምሳሌ መሆኑ ነው ይላሉ ሊቃውንቱ::አንድም ዕዝል ዜማ የሚያሳዝን ሲሆን ይህም የጌታ መከራና የቀራንዮ ውሎ የሚያሳዝን መሆኑን ለመግለጽ ነው:: ይሄ ዜማ በ6ኛው ሳምንት(ገብርኄር) መዜሙ ወልደ አብ በ6ኛው ሺ ወልደ ማርያም እንደሆነ ለማጠየቅ ነው::

❤️ #ዓራራይ:-የሚያራራ ማለት ሲሆን ምሳሌነቱም ለሚራራውና ለሚያራራው ለሚያጽናናውም ለመንፈስ ቅዱስ ነው::ይሄ ዜማ ከዕዝል ቀጥሎ በኒቆዲሞስ መዜሙ ጌታ የስጋ ስራውን ፈፅሞ ካረገ ብኋላ ለሐዋርያት መውረዱ ለማሳየት ነው:: የግዕዝ ዜማ ከ2ቱ ጋር አብሮ መዜሙ አብ የወልድ ወላዲ የመነፈስ ቅዱስም አስራጺ መሆኑን ለማጠየቅ ሲሆን ሶስቱም አብረው መገኘታቸው የአንድነታቸው ምሳሌ ነው:: ዕዝልና ዓራራይ ግን አንድ ላይ አለመጣመራቸው ወልድና መንፈስ ቅዱስ በግብር አለመገናኘታቸው ለማመስጠር ነው:: በዚህ መልኩ ቅድስት ቤ/ክ ጌታን በሙላት ታመልከዋለች:: በመጻሕፍቷ ብቻ ሳይሆን በዜማዋና በምልክቶችዋም ሳይቀር ክብርና ጌጥ የሆነላትን ኢየሱስን ትገልጠዋለች ትሰብከዋለች:: ታድያ አሁን ማነው ጌታን አታውቅም የሚላት?ማን ነው ከ 1-30 ቀናት ጌታን አትሰብክም የሚላት? ራሳችሁን ፈትሹ! እኛ ግን ንጉሳችንን ሾመናል!!...ቅዱስ ያሬድ ብዙ ደቀ መዛሙርት አፍርቶ ፣ በተለያዩ ቦታዎች አስተምሮ መጽሕፍትንም ጽፎ ተከዜን በመሻገር "ደብረ ሐዊ" ገዳም በምናኔ እየኖረ በ75 ዓመቱ የዛሬ 1433 ዓመታት ግንቦት 11 ቀን በዳግም ምጸአት ይመለስ ዘንድ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተነጠቀ:: በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን!
❌ #Reposted - ከ6 ዓመት በፊት የተለጠፈ
👇 በቴሌግራም ቻናላ እንገናኝ 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc2WXYXfdEtME6smg

©Binyam ZeChristos ~ ግንቦት 11 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

የትግራይን ሰቆቃ ለመቃወም ትግራይ ውስጥ መኖር የለብህም። ለነገሩ ብትኖርም አፈሙዝ ተደቅኖብህ ዝም ብሎ ማልቀስ እንጂ መቃወም ከየት ይመጣል! የትግራይን ችግር ለማስቆም ትግራዋይ መሆን አይጠበቅብህም። ኢትዮጵያዊ አንዱ ለአንዱ ክብር ነውና! ይህ ሁሉ ግን ስለ ትግራይ ዘግናኝ ግፍ ለመናገር ኢትዮጵያዊም መሆን እንደማይጠበቅብህ በለንደን የግብጹ ጳጳስ አቡነ አንጌሎስ አረጋግጠውልናል። «I pray that this is all fake news, but every report indicates it is not" የሚለው ቃላቸው እንዴት አንጀት እንደሚበላ! የያዙት መስቀል ከተበደሉት ጎን እንዲቆሙ፣ የተሸከሙት ቆብ ለሚገደሉት ምዕመናን ድምፅ እንዲሆንላቸው አውቀዋልና! ሕሊናን የሚያቆስል ግፍ ለመቃወም ከአንገትህ ላይ ሕሊናን መያዝ ብቻ በቂው ነውና!
#StopTigrayGenocide
#I_SrandWithAbuneMatyas

©Binyam ZeChristos ግንቦት 10 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

https://www.facebook.com/100011217017922/posts/1372932286423992/

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#መቐለዎች_ከቅዱስነታቸው_ጋር_ቆመናል_እናንተስ?
የወንድማችን የአማኑኤል አረመኔያዊ ግድያ እያወገዝን፣ እኛ በመቐለ የምንገኘው 1) የመቐለ ሀገረ ስብከት 2) የመቐለ ሰንበት ት/ቤቶች ሕብረት 3) የመቐለ ቲኦሌጂ ምሩቃን ማሕበር በሕብረት ሆነን ከቅዱስነታቸው ጋር መቆማችንን አውጀናል! ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በየክልሉና በየወረዳው ያላችሁ አህጉረ ስብከቶች፣ ሰንበት ት/ቤት ህብረት፣ ጴጥሮሳውያን ሁላችሁም ከአባትችን ጋር ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን አቅርበናል። እንሆ የመግለጫችን የአማርኛ ትርጉም!!

#የመቐለ_ሃገረ_ስብከት_የድጋፍ_መግለጫ!
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

♦ #የብፁእ ወቅዱስ ኣቡነ ማትያስ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መግለጫን እንደግፋለን!

♦ #እኛ የትግራይ ርእሰ ከተማ መቐለ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኣቡነ ኢሳይያስ በሚመሩት ጉባኤ የተገኘን የክፍል ኃላፊዎች፣የወረዳ ቤተክህነት ሰራተኞች፣ኣብነት መምህራን፣ማህበረ ካህናት፣ማህበረ ምእመናን፣የሰንበት ት/ቤቶች ህብረት እና የነገረ መለኮት ምሩቃን ህብረት በኣንድነት በመሆን የትግራይ ህዝብ ዘር ለማጥፋት የኢትዮጵያ መንግስት፣ኣማራ፣ኤርትራ፣ሶማሌና የተባበሩት ዓረብ ኢምሬት ያካሄዱት ወረራ ያስከተለውን ጥፋት ኣስመልክተው ብፁእ ወቅዱስ ፓትሪያሪክ ኣቡነ ማትያስ ከብዙ አፈናና ክልከላ በኋላ የሰጡትን ሃቀኛና ሚዛናዊ ማብራርያ ከኣንድ መንፈሳዊ ኣባት የሚጠበቅ መግለጫ በመሆኑ በታላቅ ኣክብሮት እንቀበለዋለን።

♦ #እድሜና ፆታ ሳይለይ ተጋሩ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እየተካሄደ ያለው የግፍ ጭፍጨፋ ኣንዳችም ምክንያት የሌለው ከመሆኑም በተጨማሪ በሴቶቻችን ላይ የደረሰውና እየደረሰ ኣረመኔያዊ ግፍ ትውልድ የማይረሳው ክፉ የታሪክ ጠባሳ እንደሆነ ቅዱስነታቸው በከባድ ሃዘን ሆነው መግለፃቸውና ወረራው የትግራይ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ማጥፋትን ዓላማ ያለው ነው በማለት ሃቁን በሚገባ ይፋ ኣድርገዉታል።

♦ #ቅዱስነታቸው በሃገሪቱ በተለይ ደሞ በትግራይ እየተካሄደ ያለው ወቅታዊ ኩነቶችን ኣስመልክተው የሰጡት ተደጋጋሚ መግለጫ በመንግስትና በቤተክህነቱ እየታፈነ እንዳይናገሩና ቃላቸው እንዳይሰማ እንደተደረገ የገለፁ ሲሆን ይሄ ትክክለኛውን የኣፈና መልክ ያለው የኣሁኑ የኢትዮጵያን ኣገዛዝ ቁልጭ ኣድርጎ የሚያሳይ ነው።

♦ #ምንም እንኳን የሃገር ኣንድነትንና የቤተክርስቲያን ኣንድነትን ለመበታተን የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን፤ሆን ተብሎ የተጋሩ ዘር ለማጥፋት የተካሄደውንና እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በፋይናንስ በሓሳብ የደገፉን ያሰማሩ ቢሆንም እንደታሰበው ለቤተክርስቲያኒቱና ለሃገሪቱ ግን ነጻነትና ሰላም ሊያስገኙ ኣለመቻላቸው ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው።

♦ #ቅዱስነታቸው የሰጡት መግለጫ ትግራይ ላይ ከሆነው እና ከተፈጸመው ጭፍጨፋና ግፍ ኣንፃር ጥቂቱን እንጂ የበዛውንና ሙሉ ነገሩን እንዳልሆነ ግልፅ ነው። ሆኖም ግን የቅዱስነታቸውን መግለጫ ተከትሎ ትግራይ ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ግፍ ዓለም እንዳያውቀው እንዲታፈን በከፍተኛ ጥረት ላይ የሚገኙ ኣካላትን በጽኑ እንቃወማለን። ከቅዱስነታቸው ጎን እንደምንቆም ደሞ እናረጋግጣለን። ቅዱስነታቸው እውነት ነፃ እስክታወጣቸው ድረስም ለእውነት በመቆማቸው ያለንን ኣድናቆት እየገለፅን ኣሁንም መሬት ላይ ያለውን ሃቅ በመግለፅ እንዲቀጥሉበት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

♦ #ቅዱስነታቸው እንዳሉት የትግራይ ህዝብ በደል መንስኤውና ኣላማው ግልፅ ባይሆንም በዓለም ታይቶ የማይታወቅ ሁሉ ዓይነት ግፍና ማዋረዶች ኣሉ። ኣሁንም ለቤተክርስቲያንና ለሃገር ፈተና ለሆኑ ኣካላት መንቀፍና ማውገዝ ያልቻሉ ኣካላት በቅዱስነታቸው ላይ የጀመሩት ሃቅ ኣትናገሩ የሚል የማብጠልጠል ዘመቻ የጀመሩ ክፉ መንፈስ የተጠናወታቸው ሰዎችን ኣጥብቀን እናወግዛለን።

♦ #የኢትዮጵያ መንግስት፣ኣማራ፣ኤርትራ፣ሶማሌና የተባበሩት ዓረብ ኢምሬት በትብብር በትግራይ ህዝብ ላይ ያካሄዱት ወረራና ጭፍጨፋ በዚህ ክፉ ዘመን ኣብዛኛው ኢትዮጵያዊ የገዛ ወገኑ የትግራይን ህዝብና የትግራይን ኣብያተክርስቲያኖችን ኣናውቃችሁም ብለው ክደውታል።ኣሁን ያለንበት ወቅት ዘመነ ትንሳኤ የደስታ ሰሞን ቢሆንም ለኛ ለትግራይ ቤተክርስቲያንና ለትግራይ ህዝብ ግን የመሪር ሃዘን ወቅት ነው። የፆምና የፀሎት ግዜ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወዳጆቻችንና ደጋፊዎቻችን መስለው በችግራችን ላይ ችግር ለመጨመር የሚቀላውጡ ኣካላትን በሃገር ውስጥም በውጭም የምትገኙ ተጋሩዎች ቆቅ ሆነን እንድንከታተላቸው እያሳሰብን የኣባታችን የብፁእ ወቅዱስ ኣቡነ ማትያስን መግለጫ ሙሉ ለሙሉ የምንደግፈው መሆኑን በዚህ ደብዳቤ እንገልፃለን።

እግዚአብሔር ኣምላካች የትግራይን ግፍና መከራ ያርቀው!! ኣሜን!!

ግንቦት 2013ዓ/ም(ትርጉም ከ እ.ማ.እ))

©Binyam ZeChristos ግንቦት 6 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #ቋሚ_ሲኖዶሳችን_ቋሚ_በደል_እንዳይበድል‼️
የፈራነው አልቀረም! የሰጋነው እውን ሆኗል! ቋሚ ሲኖዶስ በመንግሥት የውስጥ ትእዛዝ ቅዱስ ፓትርያርኩን ተቃወመ ተባለ። አቡነ ዮሴፍ የግላቸውን ሐሳብ ነው በቋሚ ሲኖዶስ ስም መግለጫ የሰጡት! የግላቸው አቋም ከሆነ የአቡነ ዮሴፍ በትግራይ ላይ ያለውን እይታ የሚያሳብቅ ነው። እውን ቋሚ ሲኖዶስ ተቃውሞ ከሆነ ግን አልያም ደግሞ የሚቃወም ከሆነ፣ የቅዱስነታቸው ምስክርነት "ሕገወጥ፣ የግላቸው እንጂ የቋሚ ሲኖዶስ ሐሳብ ያልሆነ" በማለት ከተቃወመ የበደል በደል ይሆናል።- «የቅዱስ አባታችን ሐሳብ ምን የሚል ነበር?» ብዬ ጠይቄ ለራሴ መልሻ መለስኩ። "የትግራይ ሕዝብ ዘር ማጥፋት እየተደረገበት ነው፣ የትግራይ ቤ/ክ እየተበደለች ነው አሉ" አልኩኝ። ታድያ አቡነ ዮሴፍ "ይህ መልዕክት የቋሚ ሲኖዶስ ኣይደለም" ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? ቋሚ ሲኖዶስስ ይህን እያለ ከሆነ (ወይም ወደፊት የሚል ከሆነ ምን ማለቱ ይሆን?
√ የትግራይ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት አልታወጀበትም
√ የትግራይ ቤ/ክ ላይ ግፍና በደል አልተፈፀመም

ኦርቶዶክሳዊ ነኝ! ተቃውሞዬን በኦርቶዶክሳዊ መንገድ እንጂ በወረደ ቃላት "ዳውን ዳውን ቋሚ ሲኖዶስ" እያልኩ፣ ብጹዓን አባቶችን አላዋርድም! አባቶቼ ከተሳሳቱት በላይ ስሕተቴ እንዳይበዛ አልሳደብም! ብጹዓን አባቶቼን በማይመጥናቸው ለዛ መግለፅ በእኔ ዘንድ የተጣለም የተጠላም ነው። ግን ደግሞ የምፀየፈውን ዘረኝነት ስለሰበኩ፣ 95% ኦርቶዶክሳዊ ያለበትን ክልል ይመለሳል ለማለት በሚያስቸግር መልኩ ስለቆረጡ የምነቅፍባቸው ነገር አለኝ። ድጋፍና ተቃውሞ በቤተ/ክ ውስጥ ያለና የሚኖር ቢሆንም ቋሚ ሲኖዶሱ የተቃወሙት ነገርና የተቃወሙበት መንገድ ግን ትልቅ በደል ሆኖ በታሪክ ሲወሳ ይኖራል። ይህም:-

"ከመከላከያ ጎን ጋር ነኝ" ብለው መርቀው ከላኩት በኋላ የትግራይን ሕዝብና ቤ/ክ ሲያጠፋ መልሰው ይቅርታ አለመጠየቃቸውም ሆነ የሐዘን መግለጫ አለመስጠታቸው የትግራይ ኦርቶዶክሳዊውን ክፉኛ ኣሳዝኖታል! በኦርቶዶክሳዊነቱ ኣፍሮ፣ በቤ/ክ ላይ የማይፋቅ ቅሬታ አሳድሮበታል። ብዙ ምስኪን ምዕመናንም ከእምነት ወጥተው ክደዋል! ይህ ሳይበቃ አሁን ደግሞ "ትግራይ እየጠፋች ነው" ሲባል "የእኛ አቋም አይደለም" ብለው አቡነ ዮሴፍ እንደ ቋሚ ሲኖዶስ ቃል አስመስለው ካሉ፣ ለትግራይ ሰቆቃ ዋና ተጠያቂው ቢያንስ አቡነ ዮሴፍ ምናልባትም ቋሚ ሲኖዶሱ (ካለ ወይም የሚል ከሆነ) ለመሆኑ ሌላ ማረጋገጫ አንሻም!

በከባድ መሳርያ የታረሰው የደበረዳሞ ገዳም ዋይታ፣ የደንገላት ማርያም መነኮሳት ደም፣ ከዋልድባ የተሰደዱት የባሕታውያኑ ዕንባ፣ በአክሱም ጽዮን የተደፋው የካህናቱ ክቡር አካል፣ በየገዳማቱ የተደፈሩት የመነኮሳይያት ሰቆቃ፣ በየገጠሩ አንገቱ የታረደው ኦርቶዶክሳዊ ገዓር በብጹዓን አባቶች ዘንድ ይፈርዳል! ይህ ደግሞ ለዘመናት የማይረሳ የቋሚ ሲኖዶሱ ቋሚ በደል ሆኖ ይኖራል! ጌታ ሆይ አባቶቼን ይቅር በላቸው!!
(የአቡነ ዮሴፍ መግለጫ የግላቸው ከሆነ እሰየው፣ ሰከን ብለው ብጹዓን አባቶች ይምከሩበት። ነገር ግን መግለጫው የቃሚ ሲኖድስ ከሆነ፣ አልያም ቋሚ ሲኖዶሱ ይህን ቃል ከደገመ: ብዙ አስደንጋጭ ነገሮች ይዞ ይመጣል! እመለስበታለሁ)
©Binyam ZeChristos ግንቦት 02 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

🚫 #ንኩለኹም_መናእሰይ_ትግራይ 🚫
ብዙሓት ኣሕዋተይ ካብ ዝተፈላለዩ ከባቢታት ትግራይ «ስለ ትግራይ ኢልና ናብ በረኻ ወፂና እንተተዋጊእና ሓጢኣት ዶ ይኸውን?» እናበሉ ይሓቱኒ ኣለው። ብፍላይ ድማ ኣብ ትግራይ ዘለው ኦርቶዶክሳውያን አባላት ቤት ት/ቲ ሰንበት! መልሰይ:-

1⃣ ጦርነት ሓጢኣት ወይድማ ጽድቂ ዝገብሮ ጦርነቱ እንተይኮነስ ምኽንያትን ዕላማን እቲ ጦርነት እዩ። ሃይማኖትኻ ንምስፋሕ፣ መሬት ንምውራር፣ ግፍዒ ንምፍፃም እተልዕሎ ሰይፊ እዩ እቲ ሓጢኣት! ጎይታ ድማ «ሰይፊ ዘልዕሉ ብሰይፊ ይሞቱ» ይብል! (ማቴ 26:52) ነገር ግን ከምዚ ሀገርኻ ንከጥፍእ፣ እነኻ ንክሓርድ፣ ሓፍትኻ ንክደፍር፣ አብያተ ክርስቲያናትን ገዳማትን ክዘርፍን ከፍርስን ንዝመፅእ ባዕዳዊ ፀላኢ ንምምካት ዝግበር ዓርስኻ ናይ ምካኻል ውግእ ግን ሓጢኣት ኣይኮነን! ክኸውን እውን ኣይክእልን! ዋላኳ ጽድቂ ኣይኹን፣ ንሓውኻን ሓፍትኻን ኢልኻ ንስኻ ንበረኻ ምውፃእ፣ ብጥምየትን ፅምእን ምስቓይ፣ ካልኦት ንከይሞቱ ኣብ ቕድሚ ሓዊ ምስሞት ምፍጣጥ ዓቢዪ ዓብዪ ፍቕሪ ሰብ እዩሞ፣ ካብ ኣምላኽ በረኸት ከምዝህልዎ ይኣምን።

2⃣ ስለዚ ኣብ መላእ ትግራይ ትርከቡ ኦርቶዶክሳውያን አሕዋተይን አሓተይን፣ መእንተ ፍትሕን ሰላምን ኢልኩን ናብ በረኻ እንተወፂኹም፣ ቅድሚ ምውፃእኹም 3 ነገራት ንክትገብሩ ይሕብር።
✏️1)ንስሐ:- ሓጢኣት ዘይብሉ ሰብ የለንሞ፣ ዋጋ ሓጢኣት ድማ ሞት እዩሞ፣ ብሓጢኣትና ንኸይንመውት ንስሐ ኣቲና ነፍስና ኣብ ቕድሚ ጎይታ ነቐምጥ። ንስሓ እተዉ! «ንስሃ ተዘይኣቲኹም ኩልኹም ክትጠፍኡ ኢኹም» (ሉቃ 13:13)

✏️2)ቁርባን:- ድሕሪ ንስሃ ድማ ሓጢኣትና ዘፅሪ፣ በደልና እውን ዝድምስስ እቲ ምእንታና ኣብ ቀራንዮ ጎቦ ዝፈሰሰ ደም እዩሞ፣ ናይ ጎይታ ስጋን ደምን ተቐበሉ። «ደም ኢየሱስ ክርስቶስ ካብ ኩሉ ሓጢአት የንጽሀና» (1ዮሐ 1:7) ቁርባኑ ተቐቢልና ናይ ሰማይ ህይወትና ውሕስ ገይርና ንበረኻ ንውፃእ። «ስጋይ ዝበልዕ ደመይ እውን ዝሰቲ ናይ ዘለዓለም ሕይወት አላቶ» (ዮሐ 6:54)

✏️3)ጸሎት:- ቕድሚ ንበረኻ ምውፃእኹም ንንስሐ አቦኹምን ንዓበይቲ ገዳማውያ ኣቦታት እውን ብጸሎቶም ንክሕልዉና ተማሕጺና ይኹን! ምግዳል ናትና፣ ምሕላው ግን ናይ ጎይታ እዩሞ። ንሕና አንጻር ባዕዳውያን ንቃለድ፣ ዓወት ግን ካብ ጎይታ እዩ! «እግዚአብሔር ንከተማ እንተዘይሓለዋ፣ ሓላዊ ብከንቱ ይነቅሕ» (መዝ 117:1)

📌እግዚአብሔር ትግራይና ይሓሉ📌

©Binyam ZeChristos ሚያዝያ 27 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

⁉️ #ሕቶታትን_መልስታትን_ብዛዕባ_ትንሳኤ ⁉️
1⃣ ድሕሪ ትንሳኤ ንምንታይ ረቡን ዓርብን ዘይፅወም? :- ካብ ትንሳኤ ጀሚርና ክሳብ በዓለ ጰራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ ንሐዋርያት ዝወረደሉ ዕለት) ዘለዋ 50 መዓልትታት "#በዓለ_ኀምሳ" ወይድማ "ዘመነ ፋሲካ" እናተብሃላ ዝፅውዓ እንትኾና ጾም ዝበሃል ኣይብለንን:: እዚ ድማ ነቲ ዝጾምናዮ ጾም ንምክሕሓስ እንተይኮነስ እዚ ዘመን ልክዕ ከም ሓደ መዓልቲ ከም ሰንበት ትንሳኤ ዝሕሰበሉ ስለዝኾነን፣ ናይ መንግስተ ሰማያት ህይወትና እውን ምሳሌ ስለዝኾነ ረቡዕን ዓርብን ይኹን ኻሊእ ጾም የለን!
2⃣ ኣብ በዓለ ኀምሳ ንስሐ ይፍቀድ ዶ?:- ንስሐ ማለት ካብ ሓጢአትካ ተፀፂትካ፣ ይቕሬታ ሓቲትካን ተናዚዝካን ምምላስ ማለት ስለዝኾነ ንስሓ ዘይእተወሉ ጊዜ የለን::(ኣብ ሕማማት እውን ንካህን ምንዛዝ እምበር እናሰገድና ንንሳህ ኢና) እኳደኣስ ትንሳኤ ማለት ካብ ሓጢኣት ወፂና ናብ ጽድቂ እንትስአሉ በዓል ስለዝኾነ ኣብ በዓለ ሓምሳ ዝበለፀ ንስሐ ክንኣቱ ይግባእ:: ንስሃ ኣቦና ግና ቀኖና ስግደት ኣይህቡናን።

3⃣ ድሕሪ ትንሳኤ ይስገድ ዶ?:- ስግደት 3 ዓይነት እንትኸውን ናይ ኣምልኮ፣ ናይ ጸጋ/ኽብርን፣ ናይ ንስሃን/ግሊ ይበሃሉ:: ናይ ኣምልኮት ስግደት ዝበሃል ቤ/ክ እንትንኣቱን ብፍላይ ድማ ኣብ ጸሎተ ቅዳሴ እንሰግዶም ስግደታትን እንትኾኑ፣ ናይ ጸጋ ድማ ኣብ ቅድሚ ቅዱሳት ሥዕሊ ወይ ታቦት እንሰግዶ እዩ:: እዘን ስግደታት ኩሉሻብ ዘይተርፋን ዘይኽልከላን እንትኾና፣ እቲ ዘይፍቀድ ግና እቲ 3ይ ናይ ንስሃ ወይ ናይ ግሊ ስግደት እዩ:: እዚ ድማ ስጋና ንምግዛእ፣ ካብ ዝሙት ንምርሓቕ ወይ ብንስሃ ኣቦና ተኣዚዝና እንሰግዶ እዩ:: እዚ ስግደት እዚ ኣብ በዓለ ሓምሳን ኣብ ዝተወሰኑ በዓላትን (ቀዳም፣ ሰንበት፣ 12 ሚካኤል፣ 21 ማርያም፣ 29 በዓለ ወልድ) ምስጋድ ኣይፍቀድን::
4⃣ ቅድሚ ክርስቶስ ሞይቶም ዝተልዓሉ ኣለዉዶ?:- እወ ኣለዉ! ንኣብነት ኣብ ብሉይ ኪዳን ብኤልያስ ጸሎት ዝተሰአ ህፃን (2ነገ 4:34)፣ ዓጽሚ ኤልሳዕ ተንኪፉ ዝተሰአ ሰብ (2ነገ 13:21) ኣብ ሐዱሽ ኪዳን እውን ጎይታ ባዕሉ ኾነ ሃዋርያት ዘልዐሉዎም ብዙሓት ኣለው:: ናይ ክርስቶስ ትንሳኤ ግን ካብዚኦም ብ3 መሰረታዊ ነጥብታት ይፍለ:: 1ይ) ኩሎም ብናይ ጎይታ ሓይሊ ዝተስኡ እንትኾኑ ጎይታ ግን ብናይ ባዕሉ ሓይሊ ዝተሰአ ምዃኑ! 2ይ) ኩሎም ምስተልዓሉ ደጊሞም ዝሞቱን ኣብ ጊዜ ምጽአት ድማ ትንሳኤ ዝፅበዩን እዮም:: ክርስቶስ ግን ሓደ ሻብ ምስተሰአ ዳግም ሞት ዘይለኽፎ እዩ:: 3) ካልኦቶም ካብ ሞት ምልዓሎም ንባዕሎም እምበር ንኻሊእ ሰብ ረብሓ የብሉን:: ጎይታ ግን ትንሳኤኡ ንሞትን ንሙስና መቓብርን ኣጥፊኡ ትንሳኤና ዝኣወጀልና እዩ::

5⃣ ኣብ ትንሳኤ ክንደይ ሰዓት ኢና ክንበልዕ ዝግባእ?:- ብጾም ጸኒሕና ናይ ክርስቶስ ናይ ትንሳኤኡ ኣዋጅ ምስተኣወጀን ቅዳሴ ምስተቀደሰን ክንበልዕ ይግባእ:: ከቀድስ ዘይኽእል እንተኾይኑ ግና ተገደደ "ክርስቶስ ተንስኣ እሙታን" ክሳብ ዝበሃል ክጸንሕ ይግባእ::
6⃣ ጎይታ ምስተሰአ ክሳብ ዝዓርግ ኣበይ ነይሩ?:- ጎይታ ምስተሰአ ን40 መዓልቲ ንሓዋርያት እቲ "ጸሎተ ኪዳን" እንብሎ መጽሐፈ ኪዳን እናመሃሮምን ብዝተፈላልየ ጊዜ እውን እናተገለፀ የጸናንዖምን ነይሩ::
7⃣ ቅድሚ ትንሳኤ፣ ስጋ ምሕራድ ይፍቀድ ዶ?:- ብዙሕ ጊዜ ስጋ ቅድሚ ትንሳኤ ከምዘይሕረድ ወይድማ ረቡዕን ዓርብን ዝተሓረደ ከምዘይብላዕ ንፈልጥ ኢና:: ነገር ግን ዓበይቲ ናይ መጽሓፍ ሊቃውንቲ ሓቲተ ከምዝረኸብኩዎ እዚ ነገር ንጾም ቦታ ንምሃብ ዝመጸ ልማድ እምበር መጽሓፋዊ ከምዘይኮነ እዩ:: ስጋ እንተተሓሪዱ ንምብላዕ እውን ቀረባ ስለዝኸውን ብምባልን "ኣርሒቖም ንምሕፃር"ን ዝመፀ ልማድ እዩ:: ቅድሚ በዓል ይኹን ኣብ ረቡዕን ዓርብን ዝሓረደ ሰብ ግን ከም ሓጢአት ክቑፀር የብሉን:: እቲ ዝተሓረደ እውን ትንሳኤ ምስኮነ ብጸሎት ተባሪኹ ክብላዕ ከምዝኽእል ካብ ሊቃውንቲ ረኺበ ኣለኹ:: ካልኦት ሕቶታት እንተሃልኩም ብኮመንት ክንመሃሃር ንኽእል::
✝ #ከምቲ_ዝተናገሮ_ተሲኡ (ማቴ 28:6) ✝

©Binyam ZeChristos ሚያዝያ 24 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#በዓድዋ_ቀን_የእኅቶች_ሰቀቀን ✅
📌በዓድዋ የድል ቀን ይሄንን ነገር ባልነግራችሁ ምንኛ ደስ ባለኝ:: ነገር ግን ይህንን ሳልናገር መውጣት ኣላስችል ስላለኝ ነው:: መቐለ ውስጥ በሁለቱም (በዓይደር ሪፈራል እና በመቐለ አጠቃላይ) ሆስፒታሎች ያገኘኋቸው የተደፈሩት እኅቶች ከ50 በላይ ናቸው:: ብዓይደር ብቻ 45 የሚያህሉ ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው (ቁጥሩ በየቀኑ እየጨመረ ያለ ቢሆንም) እህቶች ሲኖሩ 24 የሚሆኑት ደግሞ ከ18 ዓመት በታች ናቸው:: ከነዚህ ውስጥ ትንሹ ዕድሜ የ8 ዓመት ሕጻን ትልቁ ደግሞ የ60 ዓመት አዛውንት አሉበት:: ከነዚህ ውስጥ 2 ከዓይደር ሆስፒታል 1 ደግሞ ከመቐለ ሆስፒታል ታሪካቸውን የነገሩኝን ላካፍላችሁ::

1⃣ ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍ ያደረገቺኝ እሷ ናት! የ18 ዓመቷ ሞናሊዛ ኣብርሃ! በመቐለ ሆስፒታል አግኝቺያት ታሪኳን ከነገረችኝ በኋላ ማንነቷን ሳልናገር ታሪኳን እንድገልጥ ነግራኝ ነበር:: ኣሁን ግን አልጀዚራ መቐለ ሆስፒታል ድረስ ሂዶ ታሪኳን ስላወጣው እኔም በግልጽ ለመጻፍ ደፈርኩ:: ሞናሊዛ በዓብዪ ዓዲ ሰ/ት/ቤት ኣገልጋይ የነበረች መንፈሳዊ እኅቴ ናት:: በዚህ ጦርነት ውስጥ ግን አረመኔዎቹ የኤርትራ ወታደሮች ገብተው አንገትዋን ኣንቀው ሊደፍሯት ሱሪያቸውን እያወለቁ ሳለ እሷም ስትጮህና ስትንፈራገጥ ነበር:: ጩሀትዋ ሰውን እንደሚጠራ የተረዱት ወታደሮቹ ኣፏ ስር ሆነው በጠበንጃ ተኩሰው ቀኝ ክንዷ ሁለቴ መቷት:: ክንዷ ከትክሻዋ ትበጥሶ ከመሬት ወደቀ:: ደሟ እንደ ቧንቧ ይፈሳል:: ኣሁንም ግን ጉሮሮዋ እስኪሰነጠቅ ጉልበትዋም እስኪዝል ድረስ መጮህዋን ቀጠለች:: ሌላኛው ወታደር ኣናትዋ ላይ ቆሞ ቀኝ ታፋዋ ላይ ሲተኩስ እግሯ ተሰብሮ በደም ታጠበ:: ያኔ ነበር ሊሎች ሰዎች መጥተው የወታደሮቹን ትኩረት ወደነዚያ ሰዎች የሆነው:: የሚያውቋት ወጣቶች አፍሰው ወደ ሆስፒታል መጣች:: ስትስቅ በጣም ታምራለች! የሚጠይቃት ሰው ሳይኖር ሲቀር መዝገበ ጸሎትዋን ከፍታ ከጌታዋ ጋር ታወራለች:: ታሪኳን ለመናገር ስትጀምር ግን ከንፈሯ ይንቀጠቀጣል ፊቷ ብዕንባ ይታጠባል:: ኣሁን የቀኝ እጇን ብታጣም የእግሯ ስብራት ግን እየታከመች ትገኛለች:: እኅታችንን በጸሎትና በቻላችሁት መንገድ እንርዳት!

2⃣.ብዓይደር ሆስፒታል ካገኘኋቸው እህቶች አንዷ በሲቃ ውስጥ ሆና እንዲህ ታሪኳን አካፈለችኝ:: ዕዳጋ ሓሙስ የሚባል አካባቢ ላይ 3 የመከላከያ ወታደሮች ጭንቅላትዋን እየደበደቡ ደረሱባት:: በደም ተጨማልቃ ስታቃስት እንኳን አልራሩላትም:: መሬት ላይ ለጅብ ጥለዋት ሄዱ:: በዚያ የሚያልፉ ወገኖች ኣይተው እንደ ሳምራዊው ኣዘኑላት:: ተሸክመው ወስደውም ከጤና ጣብያ ኣደረሷት:: ለተወሰኑ ቀናት ብትቆይም ጤና ጣብያው የተሟላ መሳሪያዎች ስለሌሉት ወደ መቐለ ሪፈር ተላከች:: የዛለው ጉልበትዋ የተረፈችው እስትንፋስዋን ይዛ ወደ መቐለ በመኪና ትገሰግሳለች:: ነገር ግን ድንገት መንገድ ላይ የኤርትራ ወታደሮች አገኟቸው:: ሴቶቹን ለብቻ ኣስወርደው ሌሎቹን እንዲያልፍ በማድረግ ሁሉንም ሴቶች በኣሰቃቂ ሁኔታ ተገናኟቸው:: ያቺ እኅት ነፍሷ ልትወጣ ሆነ:: የተወለደችበትን ቀን እየረገመች፣ "ኢሃሎኑ በሰማይ - ኣብ ሰማይ የለኻይ ዲኻ" እያለች፣ በቁጥር ከ5 በላይ የሚሆኑ ወታደሮች እየተፈራረቁ ደረሱባት:: ሌሎቹ እህቶች አፍሰው ዓይደር ሆስፒታል ኣስገቧት:: አሁን ከሳምንታት በኋላ እንኳን ስለተፈፀመባት ነገር እንዲሁ ስታነሳላት አዕምሮዋ ይለዋወጣል:: እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዲምራል እንማልዳለን::

3⃣.እቺንም እኅት ያገኝኋት በዓይደር ሆስፒታል ነው:: የ2 ልጆች እናት ናት:: የኤርትራ ወታደሮች ከኣካባቢዋ ኣፍነው ወደ ካምፓቸው በመውሰድ ለ2 ሳምንት ተራ በተራ እየገረፉና እያሰቃዩ የደፈሯትና የወሲብ ባርያ ኣድርገው ያስቀመጧት ነበረች:: ከ2 ሳምንት በኋላ ወደ ቤትዋ የመለስዋት ሲሆን ሁሌም ማታማታ ሰዓት እላፊ ሆኖ ሰው ሁሉ ሲገባ በማታ እየመጡ ወደ ካምፓቸው በመውሰድ በየተራ ይደፍሯታል:: ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ልጆችዋን ወደ ገጠር ልካ እሷ ወደ መቐለ ለመታእም መጣች::

❌የዚህ ጽሑፍ ዓላማ❌:- ይህን ነገር ያካፈልኳችሁ አዕምሯችሁ እንዲጨነቅ፣ ልባችሁ እንዲታወክ፣ አልያም በቁጭት ለበቀብል ለማነሳሳት ኣይደለም:: ነገር ግን ትግራይ ላይ የተደረገው ጦርነት አንድን ፓርቲ ለመያዝ ሳይሆን ተጋሩን የማጥፋት ሴራም የታከለበት እንደነበረ እንዲታወቅ ነው:: እና አሁን ምን ይደረግ? 1)የነዚህ ምስኪን እኅቶች ጩሀታቸውን እንጩህላቸው፣ ዕንባቸውን ባንጠርግም እንባ ኣፍሳሹን እናውግዘው! በየሚድያው ከንጹሐን ተጋሩ ጎን መሰለፋችን እናውጅ! ኣይዟችሁ ከጎናችሁ ጋር ነን እንበል:: 2)ይህንን የሚያደርጉትን የኤርትራን ሰራዊት ከሀገራችን እንዲወጣና መንግስት ይህንን ግፍና መከራ እንዲይቆም ግፊት እናድርግ! 3)በተቻለን መጠን የገንዘብ፣ የምግብ፣ የሕክምና መሳሪያዎችና መድኃኒቶች በመላክ የተቻለንን እንርዳቸው:: (የዓድዋ በዓል ድባባችሁ ስለረበሽኩት ይቅርታ)
©Binyam ZeChristos የካቲት 23 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#ሓሽሻም_ሠራዊት - TDF
ሓሽሽ የሚጠቀም ሰው አስቀድሞ ሓሽሹን ለመውሰድም ሆነ ለመተው ነጻ ፈቃድ አለው። ሓሽሹን ከወሰደ በኋላ ደግሞ ያ ሰው ቀድሞ ያልነበረውና ኖሮት የማያውቀውን ኃይል ብርታትና አብርሆት ይሰጠዋል። ሓሽሹን ሲያቆም ደግሞ የነበረው ኃይል መልሶ ይጠፋል፣ ከእርሱም ይርቃል! ስለዚህም ሐሽሹን በእጁ፣ በኪሱ፣ በቤቱ ይይዘዋል! ይህ ዓይነቱን ሐሽሽ ነው እንግዲህ የትግራይ መከላከያ ሠራዊት አንገቱ ላይ ካለው መስቀል ዝቅ ብሎ ተንጠልጥሎ ተገኘ የተባለው። እውነትም ተገኝቷል!

ሕጻን እያለን ስንታመም እናቶቻችን የሚያደርጉት አንድ ነገር ነበር፣ ከቤት ካስቀመጡት ጸበል ወይም ጠበል ያቀምሱናል። ሲጮህ የነበረው ይረጋል፣ ሲቃጠል የነበረው ይበርዳል፣ የወደቀው ኃይል ነስቶ ያንሰራራል! ለሌላ ግዜ ጤናና ደኅነትም ሲባል ጸበሉን በአንገታችን ከመስቀላችን ጋር ይታሰራል። አሁን አሁን በከተማ እየተረሳ ያለ ነገር ቢሆንም በገጠር የትግራይ ቦታዎች ግን ከልጅነት እስከ እውቀት የሚያስሩት፣ ዕቃቤ ርእስ መድኃኒታቸው፣ ኃይል ሰጪ ሐሽሻቸው ሆኖ ይኖራል፣ የቅዱሳኑ ጸበል!

አትሌት መሠረት ደፋር በአንድ ወቅት ሩጫዋን በአሸናፊት ካጠናቀቀች በኋላ ይህንን ልዩ ኃይልና ብርታት የሰጠቻት ስውር ሐሽሽና አበርታች መድኃኒት ማን መሆንዋን ከደርቷ ላይ አውጥታ አሳይታናለች። የእመ አምላክ ሥዕል!! በእውነት ፈጣንዋ ደመና እያለች ማን ሌላ ማፍጠኛ ሐሽሽ ይፈልጋል? ጸሐየ ጸድቅ ክርስቶስ እያለለት ማን ኣደንዛዥ ዕፅ ይጠቀማል? የሸንኮራ ዮሐንስ ጸበልን ይዞ፣ የሽንቁሩ ሚካኤል እምነቱን ቀምሶ፣ የጻድቃኔ ማርያም አፈርዋን ልሶ፣ የደብረሊባኖስ ዳቤ ቀምሶ፣ የሀብተ ማርያም ሎሚ ዳሶ፣ የአክሱም ጽዮን በረከት ተቀብሎ የተነሳን ሰው ማን ያቆመዋል? ኃይሉና ጉልበቱ ከሰማይ እንጂ ከምድር ኣይደለምና ሌላ ሐሽሽ ኣይሻም! ደግሞስ ዓይኑ እያየ እናቱ የታረደችበትን፣ እህቱ በደቦ የተደፈረችበትን፣ የቀደሰበት ቤ/ክኑ ያፈረሱበትን አካላት ለማጥፋት ሌላ ሓሽሽ ያስፈልገዋል ብላችሁ ነው? ሲፈስ ያየው ደም፣ ሲታረድ የሰማውን የጉሮሮ ሲቃ መች ይረሳውና ነው ሌላ ዕጽ ሌላ ሐሽሽ የሚጠቀመው?

እቺን አምበሲትን ተመልከት፣ እህቶችዋ ሲደፈሩ አባትዋ ሲታረድ አይታ የወጣች እህት ናት! ሓሽሽዋ አንገትዋ ላይ ያለው ፀበል ነው! የTDF አባላት በአንገታቸው የታሰረው የጊዮርጊስ ጸበል፣ የአቡነ አረጋዊ እምነት፣ የሚካኤል ድርሳን ሓሽሽ ነው መባሉ ግን እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው?! እንኳንም በሌላ ሐሽሽ አልተጠረጠሩ፣ እንኳንም ከቅዱሳኑ ውጭ ሌላ መድኃኒት አልኖራቸው። እግዚአብሔርን ይዞ የተነሳውን፣ ድንግል ማርያምን ጠርቶ የገሰገሰውን፣ ጊዮርጊስን ይዞ የዘመተውን ግን ልታቆመው አትችልም! እግዚአብሔር ተዋጊ ነውና ስሙም እግዚአብሔር ነውና!

እመቤቴ እመብርሃን ሆይ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለትግራዋይ!

©Binyam ZeChristos መስከረም 04 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#ኢትዮጵያ - #ተዋሕዶ_በተዐቅቦ
ያለፈው ዓመት ስለ ትግራዋይነትህ መናገር፣ ስለ ኦሮሞነትህ መፃፍ፣ ስለ ሲዳማነትህ መመስከር እንደ ጸረ-ኢትዮጵያ የሚያስቆጥርበት የነ "እንደኔ ካላሰብክ" ዘመን ሆኖ አልፏል። በተለይ ‹የሀገር ፍቅር ያቃጠላቸው› እንዲባሉ፣ ‹የላቁ ኢትዮጵያውያን› እንዲሰኙ "እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ ብሔር የለኝም፣ ብሔራችን ትተን እንደ ኢትዮጵያውያን እናስብ" ሲሉ መስማት ሰልችቶን ነበር። ሀገር እያፈረሱ መሆኑን አለማወቃቸውና አለማፈራቸው እያሳፈረኝ የብሂሉ ስህተት በ፪ ሕጹጻን ምሳሌዎች ስረዳ!

በኦርቶዶክሳውያን የነገረ ሰብእ ሐተታችን፣ ሰው ሥጋና ነፍስ የሚባሉ የየራሳቸው አካልና ባሕርይ ያላቸው ነገሮች ተዋሕደው የሚሰጡት ነገር ነው። ተዋሐዱ ስንል ግን ሥጋ ሥጋነቱን ሳይተው፣ ነፍስም ነፍስነቷን እንደያዘች በመጠባበቅ (በተዐቅቦ) ነው የተዋሐዱት። አንዱ ካለ ሌላው ሰውነትን ኣይሰጥምና ሰውነት የሚፀናው በተዋሕዶና በተዐቅቦ ነው! ሌላ ምሳሌ:- በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርታችንም ክርስቶስን የምንገልፅበት ጽኑ የእምነት መሠረት አለን። እሱም:- ቃል ሥጋ ሲሆን የኣምላክነቱ ባሕርይ ሰውነቱን ሳያቃጥለውና ሳይለውጠው፣ የሰውነት ባሕርዩም ኣምላክነቱን ሳያጠፋውና ሳይለውጠው፣ ሁለቱም በተዐቅቦ (በመጠባበቅ) ፀንተው ግን ደግሞ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ፍጹም ኣምላክ ሆኖ ክርስቶስ ተባለ። ስለዚህም ኢየሱስ በተዋሕዶና በተዐቅቦ ከ2 ባሕርይ 1 ባሕርይ፣ ከ2 አካላትም 1 አካል የሆነ ሥግው ቃል እንለዋለን። "ተዋሕዶ ብቻ" አንልም የመለኮትና የሥጋ መጠፋፋትን (ውላጤን) ያመጣልና። "ተዐቅቦ ብቻ"ም አንልም 2 ባሕርይ 2 አካል (ትድምርትን፣ ቱሳሔን፣ ኅድረትን) ይሰብካልና። ነገር ግን እምነታችን ‹ተዋሕዶ በተዐቅቦ› ነው! ወዳጄ ኢትዮጵያም እንዲያ ነች!

ኢትዮጵያ:- ከብዙ ብሔሮችና ክልሎች ተደምረንና ተዋሕደን የምንፈጥራት የጋራ ማንነታችን ናት! ትግራዋዩ የሌለባት፣ አፋሩ የማይኖርባት፣ ቤንሻንጉሉ የማይከብርባት ኢትዮጵያ የለችም። ኢትዮጵያ ማለት ሁሉም ብሔሮች እኩል የሚታዩባት፣ አንዱ ብሔር ጨቋኝ ሌላው ተጨቋጭ የማይሆንባት፣ የአንዱ ቋንቋ የበላይ የሌላው የበታች የማይባልባት ነች! ስለዚህ እኔ ትግራዋይ የሆንኩ ኢ/ያዊ፣ እሱ ኦሮሞ ኢ/ዊ፣ እሷ አማራ ኢ/ዊት፣ ያኛው ሶማሌ ኢ/ዊ ነው። ብሔሮች ተዋሕደው ኢትዮጵያን ይፈጥራሉ! ሲዋሐዱ ግን በተዐቅቦ ነው! ኣማራው ወደ ኦሮሞ ሳይለወጥ፣ ትግራዋዩ ወደ ኣማራነት ሳይቀየር፣ ቤንሻንጉል በአማራ ሳይጨፈለቅ፣ ሁሉም ባለበት ፀንቶ የሚኖርባት ግን ደግሞ በተዋሕዶ አንድ የሚሆንባት! ኢትዮጵያን ትተን ብሔራችንን ብቻ ጠብቀን (በተዐቅቦ) ከያዝን፣ ተዋሕዶን ትተናልና ኢትዮጵያን እናጠፋታለን። ብሔርን ትተው ኢትዮጵያን ብቻ በአንድነት (በተዋሕዶ) የሚያምኑት ደግሞ፣ መጠባበቅን (ተዐቅቦን) ገፍተዋልና ብሔሮችን የሚደፈጥጡ፣ የቋንቋና የብሔር እኩልነትን የማይቀበሉ ፋስሽትነትን የሚሰብኩ ይሆናሉ። ስለዚህ ትግራዋይነትን የሚያጠፋ ኢ/ያዊነት፣ ኦሮሞነትን የሚፀየፍ ኢ/ያዊነት ኣይኖርም! ካለም መፍረስ ያለበት "ኢትዮጵያዊነት" ነው!

"ብሔር የመጣው በኃጢአት ምክንያት ነው" የሚል የዋህ ደግሞ አለ፣ ኢትዮጵያዊነትና ቻይናዊነት በጽድቅ ምክንያት የመጡ ይመስል! "አዳም ሲፈጠር ብሔር አልነበረውም" የሚለውንማ ተወው! አዳም ብሔር አልነበረውምና ብሔር አያስፈልግም እንዳለ፣ አዳም ሀገር አልነበረውምና ኢ/ያ አታስፈልግም ማለቱ እንደሆነ ገና አልገባውም! ወዳጄ ‹ኢ/ያ እንጂ ብሔር ኣያስፈልግም› የሚል ቢኖር:- ሰውነትን እንጂ ሥጋና ነፍስን አልቀበልም የሚል ሰነፍ፣ ስለ ኢየሱስ እንጂ ስለ ትሥብእትና መለኮት አያገባኝም የሚል መናፍቅ ይመስላል። ዋናው ጉዳይ "ብሔርህን ለምን ተጠቀምክበት?" የሚለው ነው። ተጨማሪ ቋንቋ ለማወቅ፣ ሌላ ባህልን ገንዘብ ለማድረግና የልዩነትን ውበትነት ትረዳበት ዘንድ ከሆነ ብሔር ቅዱስ ነው። ለዘረኝነት ከሆነ ግን ሰይጣናዊነት ነው። ሀገርም እንደዛው ነው እንደ አጠቃቀምህ! ኢትዮጵያዊነትህ ‹የተለየሁ ሕዝብ ነኝ› ለማለት፣ ‹አዳምኮ ኢ/ያዊ ነበር› ብሎ ለመፎከር፣ ‹ከኬንያዊው እበልጣለሁ ከኡጋንዳዊው እልቃለሁ› ለማለት ከሆነ ግን ኢትዮጵያዊነትህ መርገም ይሆናል!

ስለዚህ ብሔራችን ከሀገራችን፣ ሀገራችንም ከብሔራችን አስተባብረን በተዋሕዶና በተዐቅቦ እንኖራለን! ኢትዮጵያ በሁላችንና የሁላችን ናት! ሥጋን አልያም ነፍስን የሚጥል ሁሉ "ሬሳ"ን እንጂ ሰውን እንዳማያገኝ ሁሉ፣ ትሥብእትን ወይም መለኮትን የሚጨፈልቅ ክርስቶስም ሐሰተኛ ክርስቶስ እንደሆነው ሁሉ፣ እንዲሁ ለትግራዋይ የማትሆን፣ ኦሮሞነት የማትቀበል፣ አማራውን የምትገፋ፣ ለብሔር ብሔረሰቦች ህልውና የማትቆም ኢትዮጵያ ልትኖር አትችልም! ብትኖርም እንድትቀጥል አንፈቅድላትም
©Binyam ZeChristos መስከረም 2 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #ሰማዕታተ_ትግራይ ‼️
ተጋሩን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የሚደረው ስራ ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው። እንሆ "ከጎኑ ጋር ነኝ" ያልከው የዓብዪ መከላከያ ኃይል፣ ከትናንት በስትያ ነበር ከመቐለ ቅርብ በምትገኘው #ቶጎጋ በንትባል አንዲት የገጠር ከተማ ላይ በሞትና በሕይወት መሃል ያለችውን ሕይወታቸውን ለማስቀጠል "የየማክሰኞ ገበያ" ላይ ሊገበያዩ የወጡትን ንጹሓን ዜጎች ላይ 2 ጊዜ የአየር የቦምብ ውርወራ በማድረግ ብዙ ተጋሩ ደማቸው ፈሶ፣ ስጋቸው ተቆራርሶ፣ አጥንታቸው ተበታትኖ ደመ ከልብ ይሆኑ ዘንድ ተወስኖባቸዋል። ሕጻናትና ሽማግሌዎች አብረው የተቀበሩበት አሳዛኝ ክስተት! ወጣቶችና ደናግል ደማቸው የተደባለቀበት የደም ቀን!

የዓብዪ መከላከያ ወታደሮች ግፋቸው በዚህ ብቻ ኣላበቃም። ከገበያው መሃል የልብ ምታቸው ያልቆመውን፣ እስትንፋሳቸው ያተቋረጠችውን ለማፋን አምቡላንሶች ወደ ቤታው ጎረፉ። አምስት ኣምቡላንሶች ትናንት ወዲያውኑ ወደ መቐለ ዓይደር ሆስፒታል ይዘው ሲመጡ፣ የተቀሩትን ግን እንዳይመጡ አምቡሌንሶቹን አግደው አሳደሯቸው። የመንግስታችን ግፍ ይጋለጣል ብለው በመፍራት። በዚሁ ምክንታይ ሕክምና እንዳያገኙ ታግደው፣ እኛም የቻልነውን እንዳናግዛቸው ተከልክለን፣ አምቡላንስ ውስጥ ነፍሳቸው የወጣች ብዙዎች ናቸው! ደማቸው ፈሶ ካለቀ በኋላ ዛሬ እንዲያልፉ ተፈቅዶላቸው 11 ኣምቡላንሶች መጥተዋል። ኣዝላው የወጣችው እናቱ መንገድ ላይ ቀርታ፣ እግሮቹ ተቆርጠው፣ በጎረቤት ሰው ታዝሎ የሚመጣው ሕጻን አንጀት ይበላል። ከፍንዳታው የተነሳ ቤቱ ፈርሶ፣ ወንድሞቹ እዛው ተቀብረው ሲቀሩ፣ እሱ ግን ሁለት እግሮቹ ተሰብረው እንደ ሬሳ ከድንጋይ ክምር ተጎትቶ የወጣው ልጅ ደም ያስለቅሳል!

ከሰውነት ተራ የወጣው፣ ሕሊናውም የሸጠው ሰው "ጁንታ ስለሆኑ ነው" የማለት አረመኔያዊ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ፣ እኛ ግን እናሸንፋለን! ትግራይ ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የቀራት!

❌ #ትግራይ_ትስዕር ❌
©Binyam ZeChristos ሰኔ 17 - 2013 ዓ/ም

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #ትግራይ_ነዋ ፩ ‼️
📌እቺ እንቡጥ ኣበባ፣ እቺ የነገ የሀገሪቱ ተስፋ፣ እቺ ንጹሕ ሕጻን ቤቲ ትባላለች። የ6 ዓመት ልጅ ሕፃን! በአዲስ አበባ፣ በባሕርዳር፣ በአዳማ፣ በሐሳና በሌሎችም እንዳሉ እኩያዎችዋ መጫወትና መሳቅ፣ ማደግና መመርን ምትፈልግ ምስኪን የአክሱም (ማህበር ዴጎ ገዳም አካባቢ) ልጅ ነበረች። ታሕሳስ 1 ቀን ግን ሰማይና ምድሩን በሚያናጋው የከባድ ብረት ውርጅብኝ፣ የምትኖርበት ቀዬ አመድ አደረገው። በዚያች የጨለማ ቀን፣ በዚያች የተረገመች ቀን፣ እህ ብላ አምጣ የወለደቻት የእናቷ አንገት ተቆርጦ፣ አቅፈውና አዝለው እያባበሉ ያሳደጓት የአያቷ ጭንቅላት ፈርሶ፣ በስስት ዓይን ስታየው የኖረችውን የታናሽ ወንድሟ ሰውነት ተቦጫጭቆ ከዓይኗም ከሕይወቷም ለዘላለም የወጡበት ቀን ነበር። እሷም ቢሆን ዳግም እንደ ልጅ እንዳትቦርቅ፣ በእግሯ እንድትራመድ ሁለት እግሮችዋ ተቆርጠው በደም ተለውሳለች። አባትዋና ሌሎች ሰዎች የተረፈ አካልዋን አፍሰው፣ የሞቱትን ቀብረው ይዘዋት ወደ መቐለ መጡ።

📌በመቐለ ከሞት ተርፋ፣ በስንት መከራ ድና፣ አሁን በፊዝዮተራፒ ማዕከል ትገኛለች። ፈገግታዋ ላይ የታማቀ የሐዘን እሣት፣ ሳቋ ላይ የሚንተከተክ ለቅሶ ይታያል። ብመራራ ሐዘን ውስጥ ሆኖ፣ ዓይን ዓይኗን እያየ የሚያጫውታት ምስኪን ኣባትዋ ብቻ ነው! ይህ ሁሉ ሲሆን ኣቤት የምትለው አካል፣ የምትከሰው ወንጀለኛ፣ የምትጮህለት መንግስት የለም። ለምን? ምክንያቱም ይህ #ትግራይ_ነዋ!

❇️[እንሆ ዛሬ ትግራይ ላይ ጦር የተመዘዘበት፣ እሳት የተለኮሰበት፣ የሕፃናት ለጋ ሰውነት መቆራተጥ፣ የእህቶች መደፈር፣ የእናቶች መታረድ፣ የገዳማት መዘረፍ፣ የአድባራት መፍረስ የተጀመረበት #ሁለት_መቶኛው ቀን። 200 ያላቆሙ የሰቆቃና የመከራ ቀናት!]❇️

©Binyam ZeChristos ግንቦት 14 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌ #ማየ_ሰሊሆም_ዕውር ❌
ልዕሊ ኽሳድና ለሎ ርዕሲ "ዙ ጾም መንዩ ኣዊጁዎ?" ኢሉ እንተሓቲቱ ይሱርሕ ኣሎ ማለት እዩ። ዝተውሃበና መልሲ ድማ «መናንያን አበው፣ ካህናትን መናእሰይን» ጥራይ ትብል። እስኪ ዋላ ላጾምናማ ነዚኣተን ንጠይቕ!
1) #ንምንታይ_መንነቶም_ዘይተገለፀ:- ክሳብ ሐዚ ደጋጊምና "መን ኣቦ ኣዊጁ?" ኢልና ዋላ ተጠየቕና ዝናገር ሰብ ግን ኣይተረኽበን። ቶም ኣቦታት ደኣ እንመን? ኣበይ ዘለዉኸ እዮም? እቶም ካህናት ኸ?ቶም መናእሰይ ኸ? ኣድራሻ ዘይብሉ መንእሰይ፣ ካህንን ኣቦን ኣሎ ድዩ? ናብቲ ዓብዪ ቅዱስ ገዳምና ደብረ ዳሞ ዘለዉ ኣቦታት ሓቲትና "ኣብ በዓለ ሓምሳ ዝጽወም ጾም የለን፣ ኣይኣወጅናን" ኢሎም። እምበይትና ማርያም ብእግራ ዝረገፀቶ ናይ ዋልድባ ገዳም ዓበይቲ መነኮሳት እውን "ብሱሩ ከምዚ ዝበሃል ጾም ኣይንፈልጦን" ካብ በሉ፣ ካብዞም ቅዱሳን ኣቦታትና ዝበልፅ መናኒ ካበይ እዩ መፂኡ ጾም ዝእውጅ? ብሱሩኸ እቶም ኣዊጆም ዝተብሃሉ መናንያን መንነቶም ዘይተነገረ፣ ናይ ፈጠራን ሕሾትን ኣዋጅ ስለዘኾነ ዶ ኣይኮነን?

2)#መናእሰይ_ጾም_ይእውጁ?:- ብሱሩ ናይ መናንያን ኣበው ጾም እንድሕር ዝእወጅ ኾይኑ ምስ መናእሰይ ድዮም ዝማኸሩ ኾይኖም? እቶም መናእሰይኸ መን እዩ ኣዋጂ ጾም ገይሩዎም? ኣክስዮን ማሕበር ምዃኑ ድዩ ቅዱሳን ኣቦታት ምስ ንከተማ ወፂኦም ምስ መናእሰይ መኺሮም ዝውስኑ? ምስ መናንያን መኺሩ ኣብ ልዕሊ መላእ ተጋሩ ምርመናን መነኮሳትን ጳጳሳትን ጾም ዝእውጅ መንእሰይ ከመይ ዝበለ መንእሰይ እዩ ደቀይ? ኤህ!

3)#ንኣቦታት_ኣይትፃረፉ:- እቶም መን ምዃኖም ዘይተፈለጡ መናንያን እንድሕር ጾም ዝእውጁ ኾይኖም፣ ጾም ክእውጅ ዝኽእል ናይ ክህነት ስልጣን ዘለዎ ሊቀጳጳስ ጥራይ ምዃኑ ስለዝፈልጡ፣ ናብቶም ሉቃነ ጳጳሳት መልእኽቲ ብምልኣኽ "ኣምላኽ ነጊሩና እዩሞ ጾም ኣውጁ" ምበሉ። ነገር ግን ካብ ናብ ሉቃነጳጳሳትስ ናብቶም ናይ ፌስቡክ ጸሓፍቲ ድዮም ደዊሎም? እዚኣስ ነቶም መናንያን "ሥርዓት ዘይገልጡ፣ ንጳጳስ ዝንዕቑ" ኢልካ ምፅሬፍ ዶ ኣይትኸውንን? ብሱረ ኣብ ፌስቡክ ንመጀመርያ ጊዜ ዝለጠፋ ሰብ ትፈልጡዎዶ? እስኪ ዋሌ ብውሽጢ "ካብቶም ሊቀጳጳስ ንላዕሊ ዲኼ ንስኻ ቐሪብካዮም ንዓኻ ነጊሮሙኻ? ኢልኹምማ ጠይቕዎ።

4) #ብዘይ_ሥርዓት_ንጹም?:- ሓደ ሓደ የዋሃት ድማ ኣብ በዓለ ሓምሳ ኣይፅወምን እንተበልና " ንክፀውም ዶ ሥርዓት የድልየኒ እዩ?" ይብሉና። እስኪ ንጠይቆም:- እቲ ጾም ልምንታይ ካብ ግንቦት 17 ይጅመር? ምእንታይ ጎይታ ክቕበለናስ ካብ ቀዳምን ሰንበት ጀሚርና ጾምና ዘይንውዕል? ከምዚ ኢሎም ይምልሱ "ቀዳምን ሰንበትማ ብሥርዓት ኣይፅወማን"። ወዮ ሕጊ ኣፍሪሶም እናፆሙስ፣ ብሕጊ ክጾሙዎ ይደልዩ?! ኻሊእ ድማ ንሕተቶም! «በሊዕና ዲና ከም መናፍቃን ንጾሞ፣ ወይስ ጥራሕ ኸብድና? ምሸትኸ ዘይንበልዖም ምግብታት ኣለዉዶ?» መሊሶም ባዕሎም " ብሥርዓት ባ/ክ በሊዕኻ ጾም የለይ፣ ናይ ሥዕረት እውን ኣይብላዕይ» ብምባል ባዕሎም ዝነዓቕዎ ሥርዓት ቤ/ክ ዳግም ክኽተልዎ ይደልዩ! ሕንግርጢጥ እዩ ነገሩ!

5)#እዚ_ድዩ_መጨረሻና:- ብሱሩ ግን ኣብ ፌስቡክ ልፀሓፈ ኹሉ ድዩ ክገንሐና? "ኣቦታት ተናጊሮም፣ መናንያን ኣዊጆም፣ ፈለስቲ ኣዚዞም" ኢሉ ዝተናገረ ሰብ ኹሉ ድዩ ክገንሐና? ፅባሕ ኸ "ኣቦታት ኣዚዞም እዮምሞ በዓል ከይተኽብሩ፣ ቁርባን ከይትቕበሉ፣ መቅደስ ምስ ጫማ እተዉ ..." ዝብሉ ከምዘይመፁን ንሕና እውን ክርስቶስ ብደሙ ዘጥረያ ቤ/ክ ገዲፍና ምስኦም ከምዘይንውሕን ታይ መረጋገፂ ኣለና። ኣቦታት ከምዚ ይብሉ «ማየ ሰሊሆም ዕውር፣ ሃበ ወሰድዎ ይሐውር - ሰሊሆም ኣብ ትበሃል ቦታ ዘሎ ዕውር ማይ፣ ናብ ዝወሰድዎ ይኸድ"። ዝመፀ ሰብ ናብ ቃሕትኡ ዝወስዶ ሰብ ድማ "ማየ ሰሊሆም" ይብሉዎ። ንትግራይ ኣብ ጾመ ነቡያትን፣ ጾመ 40 እናጾምና ነይርና፣ ሐዚ እውብሖን ድሕሪ በዓለ ሓምሳ ክንጾም ኢና!

©Binyam ZeChristos ግንቦት 14 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ 💚 #አስደናቂው_እውነተኛ_ታሪክ💚 ‼️
(የግንቦት 12 ~ ገድለ ተክለ ሃይማኖት)
✝ስጋቸው ከነፍሳቸው ከተለየ ከ57 ዓመታት በኋላ የካቲት 19 በጸሎት ላይ ለነበሩት ለአቡነ ሕዝቅያስ ነበር የተገለጡት:: አቡነ ተ/ሃይማኖት! እንዲህም አልዋቸው:-«ጌታ የገባልኝን ቃል ይፈፀም ዘንድ ስጋዬ የሚፈልስበት ደረሰ ቀኒቱንም በምስጋናና በጸሎት መንፈሳዊ በዓል አድርጉ (በመብል በመጠጥና በዘፈን እንዳይል ልብ ይሏል) እኔ ኃጥኡ ብሞትኩበት ቀን እንደነበረው ምስጋና አቅርቡ! (ትሑቱ አባታችን ገነትም ሁነው ራሳቸውን ኃጥእ ሲሉ እኛ ግን...ማን አስተዋለ ከትውልዱ?) ስለዚህም ሂደህ ለ12 መምህራንና (ኢ/ያን የጌታ ለማድረግ የተካፈሏት የተክልዬ ደቀ መዛሙርት) ለልጆቼ ግንቦት 12 እንዲያከብሩ ንገራቸው::በፍልሰቴ ቀን አባቴ አባቴ የሚለኝ ሁሉ ይምጣ፤ ያኔ እኔ ወዳጄ ቅ.ሚካኤልና ልጄ ፊልጶስ (የተክልዬ ደቀ መዝሙርና የደብረ ሊባኖስ 3ኛው እጨጌ) አብረን መጥተን እንባርካለን:: ምልክት ይሆንህም ዘንድ በምመጣበት ጊዜ የጠፋው የመቅረዙ ይብራት ይበራል» አለው! (በእውነት ቅዱሳን ሲጠሩ ጨለማው ልባችን ይበራል የደረቀው ማንነታችን ይለመልማል:: ተ/ሃይማኖት ፀሐይ ነፍሴን አደራ በሰማይ... ሲሉ እናቶቻችን ለካ አንትሙሰ ብርሃኑ ለዓለም ያለውን ቢያነቡ ነው (ማቴ5-5፥14)

✝ከዚህም በኋላ አቡነ ሕዝቅያስ ከተክልዬ ዘንድ ተባርኮ ሄደ:: በአራቱም አቅጣጫ ላሉት 12 መምህራንና ለክርስትያኖች ሁሉ፣ አባታችን የነገሩትን የፍልሰታቸው በዓል ስለማድረግ ወደ ፍልሰቱ በዓል ያልመጣም በዚያች ቀን (በሰማይ ለማማለድ) አባቴ እንዳይለው፣ እርሱም ልጄ እንዳይለው ጨምሮ መልእክቱን ላከላቸው! (ችግር ካላጋጠመው በስተቀር በሰርጋችን ያልተገኘውን በሐዘናችንም ያልደረሰውን ሰው መች ዘመድ እንለዋለን? ይህም መምጣት እየቻለ በንቀት ወይም በክህደት ላልመጣ ልጄ እንደማይለው ለማስረዳት ነው)

✝የአባታችን የፍልሰት በዓልና የሚካኤል በዓልም እንድ ሆነ:: ይህም የቅርብ ወዳጃቸው ስለነበረና አስተምረው ሲያቆርቡም 'ተንሥኡ' ሲልላቸው 'ሰላም' እያሉ፥ ሰማያዊ ሕብስት ከሰማይ እያወረደላቸው (በሲና በረሃ ያደረገውን መድገሙ እንደሆነ ልብ ይሉዋል)፣ እርሳቸው እየፈተቱ አብረው ይሰሩ ስለነበረ ነው::በረከታቸው ይድረሰን! እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም ከ4ቱ ማዕዘን የተክልዬ ወዳጅ የተባለ ሁሉ መጣ:: 12ቱ መምህራንም ያባታችንንን ስጋ ከዋሻው ለማውጣት ሲገቡ በሁለት ጎን መስቀል ተተክሎ፥ አስከሬኑ በዕለቱ እንደተገነዘ ትኩስ ሬሳ ይመስል ነበር። ደስ የሚል ሽታም ነበረው! (የቅዱሳንን አንዲት አጥንት የማይረሳ ጌታ በኤልሳዕም አስከሬን ሙት ያስነሳ አምላክ በእውነት ይህን አደረገ)

✝ከ12ቱ ደቀመዛመርት አንዱ የሆኑት አቡነ አኖሬዎስም መስቀሎቹን ለአቡነ ሕዝቅያስ በመስጠት በመንፈሳዊ ቅናት ተሽቃዳድሞ ያባታችንን ስጋ በእጃቸው ሲያነሳው የተክልዬ አጥንታቸው ረገፈ! ይህም ዘመናቸው ሁሉ በጾም ስላሳለፉ ነበር:: በዚህም ጊዜ ሁሉም ደነገጡ ፈሩም:: የተክልዬን አጥንት ለማንሳት ሁሉም እየተጋፉ በጭንቅ ተሽቀዳድመው መጡ:: ያኔ ነበር በመካከል የነበረው አንድ ወንድም ከሰው ብዛት የተነሳ ጉልበቱን ረግጠዉት ቢሰበርም ወዲያውኑ ‹የጻድቅ ሰው ጸሎት› ብለው በእምነት የተክልዬን የመግነዙን ጨርቅ ቢያስነኩት ወድያውኑ አጥንቱ ፀናለት! በዚህም ተ/ሃይማኖትን አከብሩ ይህንንም ክብር ላደላቸው ለክርስቶስ ኢየሱስ ምስጋናን አቀረቡ:: የጻድቁን ስጋ ካወጡት በኋላ ወደ ቤ/ክ አምጥተው (አፍልሰው) 3 ጊዜ መቅደሱን አዙረው በዓሉንም አባታችን እንዳሉት በዝማሬና በምስጋና አክብረው ወደ ውስጥ አስገቡት:: በዚህም ጊዜ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ተ/ሃይማኖት አስቀድመው እንዳሉት ጠፍቶ የነበረው መብራት ቦግ ብሎ በራ:: ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጃቸው ከአቡነ ፊልጶስ ጋር በመሆንም በዓሉን ያከብር ለነበረው የተክልዬ የፀጋ ልጅ ሁሉ ተገልጠው ይባርኩ ነበር::

✝በገድሉ ደም የዋጀንን፥ ይቅር የሚያሰኘንን፣ ኃጢአታችንንም የሚያቃልልልንን ይህንን አባታችንን ለሰጠን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና እናቅርብ! ('በገድሉ ደም' ሲል ደም ከሰውነት እንዲወጣ ከገድሉ የሚወጣዉን ቃል ያመለክታል! አንድም 'ደም' ያለው ጌታን ለማንሳት ነው::ጌታ በደሙ እንደገዛን የርሱም እንዳደረገን ለማጠየቅ/1ኛ ቆሮ 6፥19/ አባታችን ተ/ሃይማኖትም በዜና ገድላቸው በብዙ ፍቅርና ትሕትናቸው የርሳቸው ስላደረጉን ስለማረኩንና እንሆ ዛሬ በግንቦት 12 በዓለ ፍልሰታቸውን እንድናከብር ስለሰባሰቡን ለማሳየት ነው)...የተክለ ሃይማኖት ልጅ መሆን በእውነት መታደል ነው!! (በዚህች ዕለትም የታላቁ ሊቅና ቅዱስ አፈወርቅ ዮሐንስ በዓል ነው)
❤️...... #ይፍቱኝ_ተክልዬ !! ......❤️

👇መንፈሳዊ ጽሑፎችን በዚህ ቻናል ያግኙ👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc2WXYXfdEtME6smg

©Binyam ZeChristos ግንቦት 12 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌#ንብዓት_ራሔል_መዝሙር_ምረቓ❌
ሰንበት ዋላሓደ ሰብ ኣይተርፍን! ኣብ መቐለ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ አዳራሽ ናይ ዲ/ን ዘማሪ ክብሮም መሓሪ ቁ 2 መዝሙር ሲዲ ክንምርቕ ኢና። ንብዓት ትግራይ ብንብዓት ራሔል ተጠቕሊሉ ቐሪቡልና ኣሎ።
መዓዘ⁉️:- ግንቦት 15 ሰንበት 8:00 ሰዓት።

በረኸቱ⁉️:- ሙሉእ ኣታዊኡ ንዝተሰደዱ ተጋሩ ኣሕዋትና።

መእተዊ⁉️ ናይ 150፣ 200 300 ቅርሺ ይኬት ተዳልዩ ኣሎ። ብዝኸኣልናዮ መጠን ትኬት ብምግዛእ፣ ናይ መዝሙር ካሴት ብምዕዳግ፣ ንዲ/ን ክብሮም እውን ብምብርትታዕ፣ ከምኡ ድማ ንዝተሰደዱ ወገናትና ንደግፍ።
✝ ንብዓት ራሔል ✝

❗️ኤርሚያስ ትናገር ናይ ራማ
ራሔል ብብኽያት ደኺማ
ዋይዋይታ ኾይኑ ሰቖቓ
ምድባስ ኣብያ ስለ ደቃ❗️

ራሔል ንብዓታ በፂሑ ኣብ ሰማያት
ራሔል ሓዘና በፂሑ ኣብ ጸባኦት
ይፅውዕ ይፅውዕ ለእግዚአብሔር

ኣብ ማእከል ጎደና ውላዳ እንትመውት
ብግፍዒ እንትትግሰስ ጓላ እናበኸይ
ሽማግለታታ ክንዲ ዝጥወሩ
ሕፃናት ኣቢዶም ንብዓት ተደረሩ
ዝኾነና ረአ ሕሰብ ዝበጽሐና
ኦ እግዚአብሔር ፍረድ ገጽኻ መልሰልና

መቅደሳ ገዳማ ብኣዋጅ ፈሪሱ
ናይ ካህናታ ደም ፈሲሱ
እንታይ ተሪፉዋ ከመይ እፎይ ትበል
ብሓዘን ተሃስያ ወላድ መኻን ራሔል
ዝኾነና ረአ ሕሰብ ዝበጽሐና
ኦ እግዚአብሔር ፍረድ ገጽኻ መልሰልና

ደቃ ተሰዲዶም ፎቖዶ በረኻ
ደም ጨቅያ መሬት ራሔል ተሃዊኻ
ፈተውታ የለውን ኣብ ጊዜ ስቓያ
ሓደ ጥራሕ እዩ ካብ ሰማይ ዝረአያ
ጎይታ ጥራሕ እዩ ካብ ታማ ዝረአያ
[ ትግራይ ኣብዛ መዝሙር ተፈቲላ ኣላ ]

©Binyam ZeChristos ግንቦት 11 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️... #ፃውዒት_ዘተ_ንተጋሩ_ኦርቶዶክሳውያን... ‼️
(ኣብ ጉዳይ አሰያይማ መንበር)
ኣብ ቐረባ ጊዜ ነገራት ክጠናቐቑ፣ ትግራይ እውን ሃገር ናብ ምዃን ገፃ እያ! ሃገር እንተኾይና ድማ ግድን ናይ ባዕላ ቤተ ክህነት፣ ቅዱስ ሲኖዶስን ፓትርያርክን ከድልያ እዩሞ ክተዋቕር እያ። እቲ ኹነታት ምስተፈጥረ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ቅንዕ ኢላ ምዕመናና ንከይትጓሲ፣ ነስንሳትና እናተኸራኸርና ንጸላእቲ ቦታ ንዘይምሃብ፣ ሎሚ ኣቐዲምና ተዛቲናን ፍታሕ ሓሲብናሉን ንክንሓድር፣ እቲ ነገር ምስተፈጥረ ድማ ዝድንግፅ ምዕመን ንከይህሉ ኢና ሐዚ ንምዝታይ ነቕርቦ ዘለና። ናይ ትግራይ ቤ/ክ መንበራ ብመን ስም ይፀዋዕ? ቅድሚ ናብቶም ካልኦት ዓበይቲ ዛዕባታት ምኻድና በዚ ቐሊል ዛዕባ ንጀምር።

ኣብ ሓንቲ ሃገር ዘላ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ መበቆል ክህነታ (መንበራ) ብዝደለየቶ ጻድቕ ክትፅውዕ ትኽእል እያ። እተን ክልተ ረቋሒታት ድማ
1)ጀማሪ ክርስትና:- ኣብታ ሃገር ንመጀመርያ ጊዜ ክርስትና ዝሰበኹ ቅዱሳን፣ ኽብሪ ንምሃብን ንምዝካርን ብምባል በቲ ጻድቅ ይስየማ። ንኣብነት:- ግብፂ ቤ/ክ - ናይ ሐዋርያ ማርቆስ መንበር፣ ህንዲ ቤ/ክ - ናይ ሐዋርያ ቶማስ መንበር ወዘተ።

2) እቲ ኻልኣይ ድማ ኣብታ ሀገር ዓብዪ ስራሕ ብምስራሕ ውዕለታ ዝወዓለ ጻድቕ (ብፍላይ ድማ ክብር ሃገር ዝቦቐለ) ስሙ መጸውዒ መንበራ ትገብሮ። ንኣብነት:- ሶርያ - ዋላኳ ክርስትና ዝሰበኸላ ቅ/ጴጥሮስ እንተኾነ መንበራ ግን በቲ ዓቢዪ ጻድቅ ብቅዱስ ያዕቆብ ሶርያዊ (St Jacob ትፅዋዕ። አርመንያ ቤ/ክ ድማ ዋላኳ ክርስትና ብሐዋርያ በርተለሜዎስን ታዴዎስን እንተተሰበኸላ፣ መንበራ ግን ብቅዱስ ጎርጎርዬስ (st Gregory the Illuminator) ትፅዋዕ። ናይ ኢ/ያ ቤ/ክ እውን ዋላኳ ክርስትና ብሐዋርያ ማቴዎስን ብሕፅው (ባኮስ) ደሓር ድማ ብአባ ሰለማ እንተተሰበኸ፣ መንበራ ብቅዱስ ማርቆስ ትሰሚ ዝነበረት እንትኸውን፣ ደሓር ግና ብ1950ታት ናይ ባዕላ መንበር እንትምስርት፣ በቶም ንሀገርናን ንቤ/ክን ካብ ጥፍኣት ዘድሐንዋን ኢ/ያ ጻድቕ አቡነ ተክለሃይማኖት ተሰምየት።

ስለዚ ንትግራይ በየናይ ረቋሒ ተጠቒምና፣ በየናይ ጻድቕ ስም ንስመዮ? ንምይይጥ ክጠቕመና መልዐሊ ነጥብታት ከቐምጥ።
1) ናብ ትግራይ አቐዲሙ ወንጌል ብዘምሀረ ኣቦ እንተይልና:- ሐዋርያ ማቴዎስን ባኮስን እዮም ዝኾኑ። ስለዚ ዘመንበረ ማቴዎስ፣ ዘመንበረ ሕጽው (ባኮስ) እዩ። ተደሊና እውን ንአቡነ ሰላማ ንምዝካር እንተደሊና ዘመንበረ ሰላማ ንብሎ።

2) ኣብ ትግራይ ዓብዪ ስራሕ ብዝሰርሑ ጻድቕ ስም ንምስያም ተተደልዩ ድማ፣ ከምኒ አቡነ አረጋዊ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አቡነ ተክለሃይማኔት፣ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ወዘተ ምጥቃስ ይከኣል።
❌ እዚ ኹሉ ዝኸውን ግን ትግራይ ሀገር ምስኮነት እዩ፣ ተዘይኮይኑ ግን ፓትርያርክና አቡነ ማትያስ፣ ሲኖዶስና ቅዱስ ሲኖዶስ፣ መንበረና መንበረ ተክለሃይማኖት ብዝብል ይፀንዕ!❌

ስለዚ በየናይ ምክንያት ተጠቒምና፣ መንበርና እንታይ ክስመ ኣለዎ ንብል?

[ኣብዚ ዘተ ዝሳተፉ ኣቐዲሞም ኦርቶዶክሳውያን ዝኾኑ፣ ኣብ ገዳይ ቤ/ክ ኣፍልጦ ዘለዎም መንፈሳውያን፣ ብፍልጠትን ብመንፈስን ክዛተዩ ዝኽእሉን ጥራይ እዩ። ክሳተፉ ዝኽእሉ መምህራን እውን ምፅዋዕ ይበረትታዕ! ካብ ርእሲ ወፃኢ ክርክርን ፀርፍን፣ ወይድማ ፀቢብ ብሔርተኝነትን ዘርኣውነት ተቐባልነት ስለዘይህልዎ ፅሑፉ Delete ይኸውን]
©Binyam ZeChristos ግንቦት 10 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

ከቅዱስ አባትችን ጋራ እንዘምር

" እግዚአብሔር ብርሃኔ መድኃኒቴ ነው
የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው
ኣምላኬ መመክያዬ ነው "

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️« ... #በተለይም_የትግራይ_ሕዝብ ... »‼️
❇️ዱርዬነቱን ያልጨረሰው ዶ/ር ዘሪሁንም ሆነ አስቀድመው ቅዱስ ፓትርያትኩን ሲዘልፉ የነበሩ አካላት መነሻቸው "በተለይ የትግራይ ሕዝብ ላይ የተደረገው የለያል" የሚለው የቅዱስነታቸው ቃል መሆኑን እንገነዘባለን። ዘሪሁንማ "የትግራይ ሕዝብን ካላጠፋሁ ኣላርፍም የሚል አካል እንዳለ አድርገው ማወጅ ከአንድ ሽማግሌ ይጠበቃል?" ብሎ መንግስትን ወክሎ ነው ፖትርያርኩን የሚወቅስ! ሲጀምር:- የትግራይ ይለያል ማለት "ሌላው ሰላም ነው፣ ሌላው አልተጎዳም" ማለት ነውን? አይደለም። ምሳሌ:- በ1977 ዓ/ም ሁሉም የኢትዮጵያዊ አካባቢዎች በድርቅ ተመትቶ ነበር። ስለዚህ ሁሉም ትኩረትና ድጋፍ ይሻ ነበር። #በተለይም የወሎና የትግራይ ድርቅ ግን ይለይ ነበር። ስለዚህ ተጨማሪ እርዳታ ፈልጎ ነበር። ሌላ ምሳሌ:- ሁሉም ኢትዮጵያዊ ገዳይ ለሆነው ኮሮና ተጋላጭ ነው። ስለዚህም ሁሉም ክታባቱን ቢወስድ የተሻለ ነው። #በተለይም ተጓዳኝ ነባር በሽታዎች (Chronic Illness) ያላቸው ወገኖች ይበልጥ ትኩረትን ይሻሉ። የትግራይ ያለያል ሲባልም እንዲሁ ተረዳው! ግን የትግራይ በምን ይለያል የሚለውን 5 መሠረታዊ ነገር ልንገርህ።

1⃣ #መንግስታዊነቱ:- ሻሸመኔና ጅግጅጋ፣ አጣዬና ሸዋሮቢት ላይ የተደረጉት ግፎች ራሳቸውን የተለየ ዓላማ ያላቸው ኃይሎች አድርገው ባቆሙ፣ የትኛውንም ሕዝብ ባማይወክሉ፣ ተደብቀውና ጊዜ ጠብቀው በተነሱ፣ ከገደሉም በኋላ ከቦታው በሚሰወሩ፣ ደም በጠማቸው አሸባሪዎች የተፈፀመ ነበር። ትግራይ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመውና እየተፈፀመ ያለው ግን በሽፍቶች ወይም በአሸባሪዎች ሳይሆን ራሱን የኢትዮጵያውያን ሕዝብ ወኪል ነኝ በሚለው፣ ሃይ ባይ በሌለው፣ በጠራራ ጸሓይ በሚገድለው፣ ከገደለም በኋላ ዜና ሰርቶ በሚያሰራጨው "የራሳችን መንግስት" መሆኑ ነው ዘግናኝ ያደረገው! ሌላ አካል ቢገድልህ ለመንግስት አቤት ትላለህ፣ መንግሥት ቢገድልህ ግን ለማን ትጮሃለህ?

2⃣ #ሕዝብን_ያታለለም_ሕዝባዊም_መሆኑ:- በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈፀሙት ግፎች ስንመለከት፣ ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ሌሎች ሕዝቦች (ክልሎች) ድርጊቱን አምርረው በመቃወም፣ ፈፃሚውን አካል ደግሞ በማውገዝና ፍትሓዊ ፍርድን እንዲቀበል በምሬት በመግለፅ፣ ለተበደለው አካባቢ ደግሞ የገንዘብ፣ ቁሳቁስና የሞራል ድጋፉን በመላክ ድጋፉን ይገልፃል። ትግራይ ግን ለዚህ አልታደለችም! ሲጀምር መንግስት "አሸባሪውንና ህወሓትን ላጠፋ ነው" ብሎ እንጂ "የትግራይ ሴቶችን ደፍሬ፣ ማሕፀናቸው ላይ የጋለ ብረትና ሚስማር ከትቼ፣ ንብረታቸውንና ቤታቸውን አቃጥዬ፣ ካህናቶችዋን ኣርጄ አጠፋታለሁ" ብሎ አልተነሳምና፣ ከጫፍ እስከ ጫፍ "ከመከላከያ ጎን ጋር ነኝ" ብሎ፣ ገንዘቡን ከልጆቹ ኣፍ እየነጠቀ ለመከላከያ ሲያወጣ ነበር። የኢ/ያ ሕዝብ እንዲህ ማድረጉ ኣይደለም ችግሩ! ችግሩስ፣ ለሀገር ጥበቃ ብሎ ያዋጣው ብር፣ ገዳማት ማፍረሻ መትረይስ፣ ሕጻናት መፍጃ ፈንጅ፣ ካህናት ማረጃ ካራ እንደተገዛበት ኣለማወቁና፣ ያወቀ ጊዜም ድጋፉን አለመቃወሙና ድርጊቱን ኣለማውገዙ ናቸው። ታድያ የትግራይ ሰቆቃ ኣይለይምን?

3⃣ #ባዕድ_ወራሪ_መምጣቱ:- በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሀገራችንን ያጠፋ ዘንድ ከውጭ ወራሪ (እንደ ድርቡሽ፣ ጣልያን፣ እንግሊዝ ያለ) ሲመጣ፣ ቀፎው እንደተነካ ንብ በሕብረት መዝመቱ የነበረ ነው። ግራኝ አሕመድ ብዙ ጥፋት ያጠፋው የቱርኮች ድጋፍም ስለታከለበት ነው። በሌሎች የሀገራችን ቦታዎች የተደረጉት ዘግናኝ ግፎች አጡገባችን ባሉ በራሳችን ሰዎች የተፈፀመ ሲሆን፣ ትግራይ ላይ በኢቶጵያም ሆነ በዓለም ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፣ "መንግስታችን" ያልነው የራሳችን መንግስት ባዕድ የሆነውን አረመኔውን የኤርትራን ሠራዊት ጠርቶ ዘግናኝ ግፍ ፈፀመብን። መስቀል የያዙ ካህናት እጃቸው እየተቆረጠ፣ የትግራይ ማህጸን ቢወልድም ወያነን ነው እያሉ መነኮሳይያት ሳይቀር ሲደፈሩ፣ ትግራይ ከፈጣሪዋ ውጭ ማንም ሊረዳትም ሊረ'ዳትም የፈለገ እንደሌለ አወቀች። ታድያ የትግራይ አይለይምን?

4⃣ #አንድ_ሙሉ_ክልል_መሆኑ:- አንድ ሰውም ሆነ 10 ሰው ቢሞት በሰብኣዊነታችን ለሁሉም እናለቅሳለን! ድርጊቱን እናወግዛለን። ነገር ግን አንድን ሰው የገደለና 10 ሰው የገደለ ቅጣቱ፣ አንዲት ሴትን ያረደና እርጉዝ ሴትን ያረደ ፍርዱ ይለያያል! የአንድን በደል አስከፊነትን ከምንለካበት መለኪያ አንዱ ብዛት ነው። ስንት ሰዎች ሞቱ? ስንቶች ተሰደዱ? ስንቶች ተደፈሩ? የሚለው የግፉን ጽዋ መሙላት ያሳያሉ። በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎችና ከተሞች ብዙ ሰዎች በብዙ ስቃይና መከራ አልፈዋል። ትግራይ ላይ ግን አንድን አካባቢ ወይም ከተማ ሳይሆን ሙሉ ክልሉን፣ በ4ቱም አቅጣጫ ነው የታረደው። ወዳጄ የተሰደደው ብቻ 4 ሚልዮን ኣላለፈም ወይ? በረሃም የሞቱት 1 ሚልዮን አልሆነውም ወይ? የተደፈሩት በመቶ ሺ እንደተቆጠሩ ታውቆ የለ ወይ? የትግራይ ሰቆቃ "የባሰ አስከፊ ነው" ለማለት ስንቶች መታረድ፣ ስንቶችስ ወደ ገደል መወርወር ነበረባቸው? ስለዚ ከብዛትም ከስፋትም አንጻር የትግራይ ይለያልም ይብሳልም ቢባል ስሕተት ነውን?

5⃣ #የአፅናኞች_ዝምታ:- በዚህ ሁሉ ቁስል ላይ ጨው የጨመሩብን ደግሞ የሃይማኖት ኣባቶች ናቸው። ሌሎች ቦታዎች ላይ ግፍ ሲፈፀሙ የሃይማኖት አባቶች ጸሎትና ማፅናኛ ቃል ይሰጣሉ። ትግራይ ከ95℅ በላይ ኦርቶዶክሳዊት እንደመሆንዋ መጠን፣ ኦርቶዶክሳውያን ኣባቶች ከጎንዋ ይቆሙ ዘንድ ይገባ ነበር። ጭራሽ "ባርከው" ላኩልን። እሱም ባልከፋ። የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ መሆኑንም ሰምተው፣ ለመዘግየታቸው ይቅርታን፣ ለድርጊቱም ውግዘትን ቢሰጡም መልካም በሆነ። ጭራሽ ፓትርያርኩ ቢቱነፍሱት፣ በነጋታው የተቃውሞ መግለጫ ተሰጠን። ታድየ የትግራይ አይለይም እያልክ ትቀልድብናለህን?

©Binyam ZeChristos ግንቦት 9 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

✝ #የማህበሩ_ጭላንጭል_ብርሃን✝
ማህበር ቅዱሳን ትግራይ ላይ ሌላ ገጽታ ነው ያለው። በተለይም ደግሞ ባለፉት 6 ወራት ትግራይ ላይ ያሳየው 'ባልሰማና ባላየ' የማለፍ ክፍተት ዋጋ አስከፍሎታል። በጣም ብዙ ዋጋ! ታላላቅ አድባራትና ገዳማት በቦምብ ሲታረሱ፣ ካህናትና መነኮሳት ሲታረዱ፣ መነኮሳይያትና የሰ/ት/ቤት እህቶች ሲደፈሩ፣ በተደፈሩበት ማህጸን ብረትና ሚስማር ሲጨመርበት ማሕበሩ የት ነበር? ያ በሻሸመኔ፣ በኦሮሚያ፣ በጅግጅጋና በአጣዬ ለተሰደዱት ክርስቲያኖች፣ ዜና ሲሰራላቸውና ጩሀታቸውን ሲጬህላቸው "ይበል" ብለን የመረቅነው ማሕበር፣ ትግራይ ላይ ሲሆን ግን እንደ ባሕታዊ ፎቁ ውስጥ ተውሽቆ የቆየው ለምንድነው? የራሱ የማህበሩ አባላት በሽሬና በአክሱም፣ በሑመራና በማይጨው ወደ በረሃ ሲሰደዱ፣ ንብረታቸው ሲቃጠልባቸው፣ ቤታቸው ሲፈርስባቸው፣ በጥይት ግንባታቸው ተመተው የሞቱት ኣባላቶቹ እንኳን የሐዘን መግለጫ አልሰጠም። ለራሱ አባላት እንኳን የማይገደው ማህበር አልነበረምን? ለዚህም ብዙ ወቀሳ የተገባው ሆነ!

ግን ደግሞ እርግጥ ነው፣ እንኳን ማሕበሩ ታላቁ ቅዱስ ሲኖዶስም ምንም አላለም! ጠቅላይ ቤተ ክህነትም አልተነፈሰም! ጴጥሮሳውያንም ሆኑ የሰ/ት/ቤቶች ሕብረት ቃል አላወጡም። ቢሆንም ከማሕበሩ ብዙ እንጠብቅ ነበርና ብዙዎቻችን የማህበሩ ዝምታ በእጅጉ ቅር ብሎናል። ግን ደግሞ በ11ኛው ሰዓት ቢሆንም እንኳን ከየትኛውም ሀገራዊም ሆነ መንፈሳዊ ሚድያ በፊት ስለ ትግራይ ሰቆቃ በአማርኛና በትግርኛ የተናገረና ያጋለጠ ማሕበር መሆኑን አንዘነጋም!! ያኔ EOTC TV የቅዱስ ፓትርያርኩን ድምፅ በሚያፍንበር ወቅር፣ ያኔ የተናገሩትን ቆርጦ በሚያስቀርበት ዘመን፣ ማሕበሩ በድፍረት ስለ ትግራይ ሰቆቃ ተንፍሷል! ይህንን አንረሳውም! ስለዚህም መጽሓፍ «በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል» እንዳለ [ሮሜ 2:10]፣ ከነ ብዙ ቅሬታችን ስላደረገው ነገር እናመሰግነዋለን።

ቅዱስ ፓርትርያርኩን ደግፎ፣ የመንግስትን ድርጊት አውግዞና የቤ/ክንን ስደት አውጆ ያወጣውን የትናንቱ መግለጫ ግን ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከተቀመጡበት ተነስቶ የሚያስጨበጭብ፣ ራስን በአድናቆት ላይ ታች የሚያስነቀንቅና የሚያስመሰህን ስራ ነው። ለምን?
📌1⃣ ስለ ትግራይ ሰቆቃ መናገር ጁንታ ተ ለህ በምትታሰርበትና በምትወገድበት ጊዜ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሐሳብ ደግፎ፣ በሌላ ኣነጋገር በትግራይ ላይ የደረሰው አሰቃቂውን ሰቆቃ አምኖ ተቃውሞያልና ስለ ድፍረቱ አድናቆትን፣ ስለ መግለጫው ምስጋናና እንቸረዋለን። ይህንን እንዲያደርግ እንጂ ሌላ ምንም ፈለግን?!

📌2⃣ በትግራይ ያለችው ቤ/ክ ሰቆቃ እጅግ ዩከፋ ቢሆንም፣ በመላው ኢትዮጵያ ያለችው ቤ/ክ እየተሰደደች እንዳለች መመስከራቸውም ደግሞ ዓስበ ሰማዕታትን ይስጥልን ያሰኛል። ክርስቲያናችን ከመግደል፣ መነኮሳይያትን ከመድፈር፣ ካህናትን ከማረድ፣ ገዳማትና አድባራትን ከመዝረፍ፣ ምዕመናንን ከማሳደድ በላይ ቤተክርስቲያን እንዴት ልትሰደድ ትችላለች? ከዛሬ ጀምሮ የቤ/ክ ታሪክ ስናነሳ ከነ ኔሮን፣ ትራጃን እና ዲዮቅልጢያኖስ ቀጥሎ ዐብዪ አሕመድ በጸረ-ኦርቶዶክሳዊ እርምጃዎቹ እንደሚጠቀስ ግድ ሆኗልና።

ስለዚህ ማህበር ቅዱሳን ከተሳሳታቹውና ከበደላቸው ብዙ በደሎች ውስጥ እንደ ንጋት የአጥቢያ ኮከብ የሚያበራ፣ በጨለማው ዘመን ውስጥ እንደ ጭላንጭል የሚያንፀባርቅ ግብር ነውና ማሕበሩን በዚሁ ያፅናህ እንበለው!

‼️#ከቅዱስነታቸው_ጎን_እንቆማለን ‼️

©Binyam ZeChristos ግንቦት 04 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌ ፓትርያርኩ ተሳስተዋል ❌
ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አባ ማትያስ የላኩልን ንግግር ብዙዎች ሲቃወሙት አየሁ። ንግግራቸእ ብዙ ስሕተቶች ያለው ነበረና ተቃውሞው ልክ ነበር እላለሁ። እኔም ተቃውሞዬን ላሰማ!

1) የመጀመርያው የአባታችን ስሕተት ከትግራይ ምድር የወጡ አባት መሆናቸው ነው። ለምን ትግራዋይ ሆኑ? ከትግራይ ባይወለዱ መች እንዲህ ይባሉ ነበር? በቅርቡ ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ በጥብዓት መንግሥትን ሲቃወሙ፣ አቡነ ፋኑኤል የሕዝብን ሰቆቃ ሲናገሩ ማን ተናገራቸው? ትልቁ ስሕተታቸው ከትግራይ ምድር መገኘታቸው ነው!

2) ቅዱስ አባታችን አምናና ካቻምና በኦሮሚያ ስለተገደሉት ክርስቲያኖች ሲያለቅሱ አልተቃወምናቸውም፣ በሻሸመኔ በግፍ ስለታረዱት ኦርቶዶክሳውያን ሲያነቡ ሁላችን "አቡነ አቡነ" አልናቸው። ቢጨንቃቸው "ኦርቶዶክሳውያን ሆይ ታጠቁና ራሳችሁን ጠብቁ" አሉ፣ እኛም አጨበጨብንላቸው! አሁን ግን ስለ ትግራይ ሰቆቃ ሲናገሩ ሰምተን የዘንዶውን ኣፍ ከፈትንባቸው! ለምን? ስለ ትግራይ ሰቆቃ መነገር የለበትማ! ትግራይን የምንፈልጋት ልጆቻችን "የኢትዮጵያ የታሪክ መሰረት ከየት ነው?" ብለው ሲጠይቁን መልስ እንዳናጣ ብቻ ነው። ታድያ የቅዱስነታቸው ስሕተት ስለ ትግራይ ስቃይ መናገራቸው አይደል?

3) አባታችን የተሳሳቱት ሌላው ጉዳይ በግልፅ መናገራቸው ነው። እስካሁን ድረስ ሙኃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በጤናው ያለ የሚመስላቸው፣ ዐብይ አሕመድ ሕሊናውን እንደሳተ ያልተረዱ ሰዎች ይሄንን የቅዱስነታቸው ቃል እንደ ሬት ይመራቸዋል። ለምን? "መንግስት እንዳይናገሩት አፈናቸው" መባሉ "እንደ ዘንድሮ የሐሳብ ነጻነት አልተገኘም" ከሚለው ቅዠታቸው ጋር ስለሚጋጭባቸው! ስለዚህ አባታችን መታፈናቸውን፣ የሚራዷቸው አገልጎዮች መታሰራቸውንና መግለጫቸውም መሰረዙን በግልፅ መናገራቸው ነው ስሕተታቸው!

4) በሕይወታችው ተወራርደው፣ ከውስጥም ከውጭም ሊመጣባቸው የሚችለውን ኣደጋ እያወቁ በጥብዓት መናገራቸውስ ቢሆን ስሕተት ኣይደለምን? ከዚህ በኋላ ዳንኤልና ዐብይ አንዳንድ የፓትርያርኩን የቅርብ ሰዎች ሊያስሩና ሊገድሉ እንደሚችሉ፣ ቅጥረኞችም ቋሚ ሲኖዶስን ተጭነው በቅዱስነታቸው ላይ የተቃውሞና የዛቻ መልዕክት ሊያወጡ እንደሚችሉ ያውቃሉ። ነገር ግን ጊዜው ለ3 ቀናት መቃብር ውስጥ የቆየውን ሥጋ የተነሳበት ነውና፣ ለ6 ወራት ተቀብሮ የነበረውን እውነት መግለጣቸው ነው ስሕተታቸው!

©Binyam ZeChristos ግንቦት 1 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #ሰኑይ ~ ~ ~ #ማዕዶት ‼️
(ካብ ትንሳኤ ክሳብ ዳግማይ ትንሳኤ)

✝ካብ ትንሳኤ ክሳብ ዳግማይ ትንሳኤ ዘለዋ መዓልትታት ነናይ ባዕለን ስያመን ትርጉምን ዘለወን እየን። በዚ መሰረት ፅባሕ ሰኑይ ማዕዶት ተባሂላ ትጽዋዕ። #ማዕዶት_ማለት_ምስግጋር ማለት ኾይኑ፣ ጎይታ ብዕለተ ዓርቢ ብኣካለ ነፍስ ናብ ሲኦል ወሪዱ ንኹሎም ነፍሳት «ሰላም ንዓኻቱም ይኹን» ብምባል ካብ ሲኦል ናብ ገነት፣ ካብ ጸልማት ናብ ብርሃን፣ ካብ እስራት ናብ ሓርነት ከምዘሰጋገሮም እንዝክረሉን እንዝምረሉን መዓልቲ ስለዝኾነ እዩ። (ዮሓ19፡18፣ ሮሜ5፥10-17) ንሕና ካበይ ናበይ ተሻጊርና ንኸውን? ቅድሚ ትንሳኤ ዝነበረና ዘርኣውነት ብሰብኣውነት ተሻጊርናዮ ዶ? ማዕፆ ዘይብሉ ኣፍና ሓላዊ ዘይብሉ ኣንደበትና ተሻጊሩዶ ይኸውን? ኦ ጎይታ ብፍቕርኻ ኣሻግረና!

✝ ጎይታናን መድሓኒናን ኢየሱስ ክርስቶስ ካብ ዝተንስኣላ ሰንበት ክሳብ በዓለ ጰራቅሊጦስ (50 መዓልቲ) ዘሎ ግዜያት ትንሳኤኡ እናዘከርና እንሕጎሰሉ ጊዜ እንትኸውን «በዓለ ሓምሳ» እናተብሃለ ድማ ይፍለጥ። እዚ ቅንያት እዚ ሓጎስና ብብልዕን መስተን እንገልጸሉ #እንተይኮነስ፤ ዝተቐይምናዮም ይቕረ እናተባሃሃልና ብዝቐደመ ሓጢኣትና ተጣዒስና፣ ብንስሓ ተሓጺብና፣ ካብ ዝወደቕናሉ ብሓድሽ ህይወት ምስ ክርስቶስ እንትስኣሉ ግዜ እዩ። ብፍላይ ድማ ካብ ሰንበት ትንሳኤ ኣትሒዙ ክሳብ በዓለ ሓምሳ (ጰራቅሊጦስ) ኣብ ዘሎ ጊዜ ነገረ ትንሳኤኡ ብሰፊሑ ዝንገረሉን ዝስብኸሉን ጊዜ እዩ።

✝ እዚ ጊዜ እዚ ድማ ብክርስቶስ ትንሳኤ ዝረኸብናዮ ጸጋን በረኸትን ንዝክረሉ ስለ ዝኾነ ናይ ሓጐስን ፍስሓን ጊዜ እዩ። ኣብዚ ጊዜ ረቡዕን ዓርብን ዘይንጾመሉ ምክንያት እውን፣ 50 መዓልትታት በዓለ ሓምሳ ልክዕ ከም ሓንቲ ናይ ትንሳኤ መዓልቲ ስለዝቑፀራን፣ ናይ መንግስተ ሰማያት ምሳሌ እውን ስለዝኾናን እዩ እምበር፣ ናይ ዝጾምናዮ መዓልቲ ንምክሕሓስ ኣይኮነን።

#ሠሉስ ~ #ቶማስ ~ ክቕፅል'ዩ

©Binyam ZeChristos ሚያዝያ 14 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

✝ #ብትንሳኤኡ_ብርሃን_ሂቡና ✝
📌ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~ በዓብይ ኃይል ወሥልጣን
📌አሰሮ ለሰይጣን ~ አግዓዞ ለአዳም
📌ሰላም ~ እምይእዜሰ
📌ኮነ ~ ፍስሐ ወሰላም
✅ዋይ ዛ መዓልቲ ከመይ ደስ ትብል! ሓቂ ልዕሊ መቓብር ዝወጸትሉ፣ ኹርዓት እምነትና ዝኾነ ትንሳኤኡ ዝተግሃደሉ ዕለት! ክርስቶስ ጎይታ እዩሞ ካብ ማእኸል ሙታን ኣይርከብን! መሐመድ ሞይቱ እዩ! ቡድሃ እውን ብሕይወት ኣይነበርን! ማርቲን ሉተር እውን እንተኾነ ወይከ የለን! ኦሾ እውን ዓጽሙ ኣብ መቓብር አሎ:: ናትና ጎይታ ግን ዘለዓለም ሕያዋይ! ተሲኡ ካብ ሙታን ዓሪጉ ናብ ሰማይ! ክርስቶስ ካብ እምበይተና ማርያም ድንግልናኣ ከይኸፈተ ከምዝወፀ ኹሉ፤ ኸዚ እውን ነቲ መዕፀዊ መቓብር ዝኾነ ዓብዪ ደንጎላ እንተይኸፈተ ወጸ:: መላእኽቲ ቕድሚ ኹሉ ዝረኣይዎ ዜና ብስራት፣ ኣንስቲ ቕድሚ ኹሉ ዝሰመዐኦ ወረ ሰላም፤ እነሆ ሎመዓንቲ ሰንበት ጋህዲ ኾነ! ትንሳኤ!!

✅ድሕሪ ደጊም ንክርስቶስ ብመለኮቱ እምበር ብስጋ አይንፈልጦን! ድሕሪ ሐዚ ንዝጠመዩ ይምግብ እምበር ኣብ ሰማይ ኮይኑ ኣይጠምን! ንዝደኸሙ የበርትዕ እምበር ንሱ ኣይደክምን! ንዝልምኑን ንዘማልዱን ልመነኦምን መልሲ ይህብ እምበር ንሱ ኣይፅልይን #ኣይየማልድን! ምስ ቅዱስ ኣቡኡ ምስ ኣብ፣ ምስ ቅዱስ መንፈሱ ምስ መንፈስ ቅዱስ ማዕረን ትኽክልን ኾይኑ ኣብ ሰማየ ሰማያት በቅዱሳንን በመላእኽትን ተኸቢቡ ነጊሱ ኣሎ! ብዙሓት ጓሶት ኣለዉ! ኹሎም ጓሶት ግና ዝሓለዉዎን ዘህጠርዎን በጊዕ ዕዳጋ ወሲዶም ንበላዒ ሰብ ይሸጥዎ! ጎይታና ግን ናይ ኻሊእ ንከይንኸውን ብደሙ ገዚኡ፣ ንዘለዓለም ናቱ ዝገበረና ሓቀኛ ጓሳ አባጊዕ እዩ! (ዮሐ 10:1) ኻልኦት ጓሶት ድማ ካብ ኣፍ ተኹላን ዝብእን ዝሓለውወን ኣባጊዕ መሊሶም ባዕሎም ይበልዕወን። እንተዘይበልዑ እውን ኣብ ዕዳጋ ንበላዒ ብምሻጥ ኣሕሊፉም ይህቡ። እቲ ፍቕሪ ዝኾነ ክርስቶስ ግና ኣሽምባይዶ ክበልዐናስ "ስጋይ ብልዑ ደመይ እውን ስተዩ" ኢሉ ኣንገደና! ከምዚ ዝበለ ፍቕርስ ንመንከ ይህልዎ?

❤️ዓለም ኹሉ ይስመዐለይ! ንሱ እዩ ንጉሰይ! ህዝቢ ኹሉ ይርአየለይ ንሱ እዩ መድሕን ህይወተይ! ዘይንሱ እዩ ካብ ኣስናን ኣጋንንቲ፣ ካብ ኹርምቲ ሰይጣውንቲ ሓራ ዘውፀአኒ! ዘይንሱ እዩ ካብ ማሰርቲ ሓጢኣት፣ ካብ አርዑት መርገም ዘናገፈኒ!! ዘይንሱ እዩ ስግኡ ቖሪሱ ደሙዉን ኣፍሲሱ ዝሃበኒ!! ሞይተ ከምዘይተርፍ፣ ኣብ ውሽጢ ሓመድ ከምዘይቐርን ብመንፈሳዊ ሓይሊ ካብመቓብር ከምዝትስእን ብትንሳኤኡ ኣረጋጊፁለይ! እስቲ ኸማየ እትፈትዉዎ፣ ኸማየ ብፍቕሩ ሓጢኣትኹም ልሓደገልኹም እንተሃለኹም ምሳይ ብሓደ ኣመስግንዎ!❤️
✝ #ትንሳኤከ_ለእለ_አመነ ✝
✝ #ብርሃነከ_ፈኑ_ዲቤነ ✝

#ሕቶታት_ብዛዕባ_ትንሣኤን_መልሶምን ~ ክቕፅል'ዩ
👇መንፈሳውያት ጽሑፋት ብቴሌግራም የንብቡ👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc2WXYXfdEtME6smg

©Binyam ZeChristos ሚያዝያ 10 - 2012

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️... #ለትግራይ_የላካችሁት_ብርስ? ... ‼️
አንድ ፓርቲ ላይ ታውጆ ነገር ግን በንጹሑ የትግራይ ሕዝብ ላይ የተደረገው ጦርነት እንሆ 4 ወር ሊሞላው ቀናቶች ብቻ ቀርተዉታል:: በዚህም ምክንያት ለረሃብ፣ ለርዛት፣ ለሕመም፣ ለመሰደድ፣ ለመቁሰል፣ ለመደፈርና ለሞት የተጋለጠው ሕዝብ ስፍር ቁጥር የለውም:: በዚም ምክንያት ደግሞ እኛን የምታውቁን ወገኖቻችን "እንጀራችሁን በውሃ ላይ ለመጣል" መርዳት እንደምትፈልጉና መቐለ በሚኖሩ 3 ሰዎች በተሰራው አካውንት ድጋፋችሁን እንደላካችሁ ይታወቃል:: ድጋፉ 3 ደረጃዎችን የያዘ ነው::

1⃣ኛ ደረጃ:- ከመላው ትግራይ ወደ መቐለ የተሰደዱትን የማገዝ ስራ ሲሆን ባሉት 8 ካምፖች ተዘዋውረን ችግራቸውን ለማጥናት ስንሞክር ደግሞ የምግባን የመጠጥ ችግር እምብዛም እንደሆነና ይህም በመቐለ ሕዝብ እየተሸፈነ እንደሆነ ከምስጋና ጋራ ይገልፃሉ:: የቀራቸው የንጽሕና መጠበቂያ እንደ ሳሙና፣ ለእህቶች ሞዴስ፣ ፍራሽና ብርድ ልብስ ችገር አለ::
2⃣ኛ ደረጃ:- ቀጣይ ስራ ደግሞ በመቐለና አካባቢዋ ባሉት ቦታዎች ኗሪዎች ሆነው፣ የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው፣ ለምነው፣ በቆሎ ጠብሰው፣ ሎተሪ ኣዙረው ይኖሩ የነበሩት አሁን ግን ባዶ ቤት ላይ ተጥለው፣ በየ 3 ቀኑ ደረቅ እንጀራ በውሃ የሚበሉ ብዙዎች ናቸው:: በተለይ አንዱ ያጋጠመኝ:- የ15 ዓመት ልጅ ለሳምንት ምግብ በኣፉ ሳያልፍ ቆይቶ መጨረሻ ላይ መርዝ ጠጥቶ ሕይወቱን ኣሳልፏል:: ይህ ያማል! ቢያንስ አንድ እንጀራ መስጠትን ከማዘግየት የተነሳ የሚሞት ወንድም/እኅት እንዳይኖር በማለት ነው::
3⃣ኛ ደረጃ:- ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ እግዚአብሔር ቢረዳንና መንገዶች ከተከፈቱ በመላው ትግራይ ያሉትን የተቸገሩ ሕዝቦች ለመርዳት ጌታን ተስፋ ኣድርገን ተነስተናል:: በዚህ ሁኔታ የመጀመርያውን ደረጃ ላይ በመቐለ ካሉት 8 የስደተኞች ካምፖች በማጥናት ችግሩ የበዛባቸው 2 መጠለያዎች ላይ በላካችሁት ድጋፍ እንዲህ ተደረገ::

✅1.የኢትዮ ቻይና ት/ቤት መጠለያ:-
📌1350 ሳሙና= ለ1 ሳሙና 7.6$ = 11,500 ብር
📌500 ሞዴስ= ለ1 ሞዴስ 20.9 $ = 10,460 ብር
💠በአጠቃላይ 21,960 ብር ለዚህ የስደተኞች መጠለያ ድጋፍ የዋለ ሲሆን ደረሰኞቹ በፎቶ ኣቅርበናል::

✅2.የንግስተ ሳባ ት/ቤት መጠለያ:-
📌25 ፍራሽ= ለ1 ፍራሽ 950$ = 23,750 ብር
📌200 ብርድ ልብስ= ለ1 ብ.ል 250$ = 48,000 ብር
💠በአጠቃላይ 71,750 ብር ለዚህ የስደተኞች መጠለያ ድጋፍ የዋለ ሲሆን ደረሰኞቹ በፎቶ ኣቅርበናል::

‼️በጠቅላላ ከላካችሁት ድጋፍ 93,710 ብር በድጋፍ መልክ ተሰጥቷል:: ከዚህ በማስቀጠል በ2ኛ የተደረገውን ድጋፍ እናቀርባለን:: በዚሁ ደግሞ ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውሮፓና ዓረብ ሀገራት የረዳችሁ ወገኖች ሁላችሁም በተቸገረው የትግራይ ሕዝብ ስም እያመሰገንኩ፣ ለመርዳት የምትፈልጉ ወገኖቻችን ደግሞ ይህን አካውንት መጠቀም እንደምትችሉ በማሳሰብ ነው::‼️
የኢ/ያ ንግድ ባንክ (CBE)
1000 372639044
Hayelom G/medhin
Mahder G/eyesus

©Binyam ZeChristos የካቲት 22 - 2013

Читать полностью…
Subscribe to a channel