binyamzechristos | Unsorted

Telegram-канал binyamzechristos - Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

2518

ከእውነት ማዕድ ተቆርሰው፣ ከጥሩ ምንጭ ተቀድተው፣ ለሕይወተ ሥጋ ወ ነፍስ የሚሆኑ፣ ወደ ክርስቶስ የሚጠቀልሉ ኦርቶዶክሳዊ ትሩፋቶችና፣ በኦርቶዶክሳዊ መነጽርነት የሚታዩ የተለያዩ እይታዎች ይቀርቡበታል።‼️ ኣስተያየት ለመስጠት => @ZeChristosComments_Bot

Subscribe to a channel

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

📌ቅዱስ ሚካኤል ኣብ ኩሉ ቦታ ይርከብ ዶ⁉️
ናይ ቅዱስ ሚካኤል በዓል ኣብ ሙሉእ ዓለም ዘለው ኦርቶዶክሳውያን የኽብሩዎ ኣለው። እሞ ደኣ ቅዱስ ሚካኤል ከመይ ገይሩ ምስ ኹልና ይውዕል? ከመይ ገይሩ ናይ ኹልና ፍቕርን ልመናን ክርኢ ኾነ ክሰምዕ ይኽእል? እንተይልና መልሱ:- ቅዱስ ሚካኤል ኣብ ሙሉእ ዓለም ምስ ዘለና ሰባት #ክርከብን #ከድሕነናን ዝኽእል ዓብዪ መልኣኽ ምዃኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዝናገር እዩ። ኸመይ? ብኣመክንዮ (Deductive Argument) ነቐምጣ!

#Premise 1:- «መልኣኽ እግዚኣብሄር ኣብ ዙርያ እቶም ዝፈርሕዎ ይሰፍር
የድሕኖም ከኣ እዩ» (መዝ 34:7)
#Premise 2:- ንእግዚአብሔር ዝፈርሑን ካብ ብዙሕ ነገር ክድሕኑ ዝድለዩን ሰባት ኣብ ሙሉእ ዓለም ኣለው!
#Conclusion:- ቅዱስ ሚካኤል ኣብ ሙሉእ ዓለም ኾይንና ንጎይታ ንእንፈርሕን ንቅዱስ ሚካኤል ንእንፈቱን ኦርቶዶክሳውያን ኣብ ዙርያና ይሰፍር፣ የድሕነና ድማ እዩ።
#ሕዳር_ሚካኤል
©Binyam ZeChristos ሕዳር 11 - 2016

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

መ/ር ግርማ ትናንት በደሴ ለነበሩት ስደተኞች ከ2 ሚልዮን በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጋቸው እንደ ሰው፣ እንደ ኢትዮጵያውያንም ሆነ እንደ ክርስቲያን ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። በደሴ ከተማ ያሉት ምንዱባን እንደኛው የሚራቡ ሰዎች፣ ያውም የሀገራችን ንጹሐን ዜጎች ናቸውና ፣ ማንም "እሰይ፣ እስኪ የቀመስናትን ይቅመስዋት" ሊላቸው የማይገቡ ናቸው። አውቃለሁ ትግራይ ላይ ከዚህ ጋር የማይነፃፀር እጅግ ክባድ ረሃብና ስቃይ ኣለ፣ ግን ደግሞ "በኔ የደረሰ በእናንተ አይድረስ" ይባላል እንጂ "ሌላውም እንደኛ በጨለማ ተዘግቶ በረሃብ ይለቅ" አይባልም። ይልቁንም የተቻለንን ሁሉ እንርዳ፣ ለታራቡ ለተጠሙ የሚደርሱ እጆች ብጹዓን ናቸውና!

ይህ እንዳለ ሆነ፣ ላለፉት 10 ወራት ካለ መብራትና ካለ ውሃ ለተዘጋው፣ ካለ ስልክና ኢንተርኔት ለተሸበበው፣ ከላይና ከታች በእሣት ለተጠበሰው ትግራዋይ ወገናቸው ምነው ትንሽ እንኳን አልደገፉም? "የጁንታ ተባባሪ" እንዳይባሉ ይሆን? ከ2 ሚልዮን በላይ ተጋሩ ወደ ሱዳን ሲሰደዱ፣ ከ4 ሚልዮን በላይ ከድህነት ወለል በታች ሆኖ ዓለም ሲደንቀው ምነው ድምፃቸውን አጣነው? ብቻ ክፋ ዘመን ያስተዛዝባል!
#ወሎን_እንድረስለት
#ትግራይ_ትስዕር

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

https://youtu.be/JdLZYegcRLw

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#በእንደነሱ
❓ጥያዌ:- የትግራይ ሠራዊት ለምንድነው ወደ አማራ ክልል ይገባው?
❇️መልስ:- ስለ 2 ምክንያት ነው የገባው። 1ኛው ልክ ብልጽግና ሕግ ለማስከበር ትግራይ እንደሀባው ዓይነት፣ TDF ሕግ ለማስከበር ነው ወደ አማራ የገባው። ፋሽስታዊውን የዓብዪን መንግስት ለሕግ ለማቅረብ ካልሆነም ለማጥፋት! 2ኛው ደግሞ ሻዕብያ ራሱን ለመከላከል ወደ ትግራይ እንደገባ፣ TDF'ም ራሱን ለመከላከል ነው የአማራ ድንበር ውስጥ የገባው።

❓ጥያቄ:- ወደ አማራ ክልል ስትገቡ የአማራ ኃይሎች እየመከቱ እንደሆነ ይነገራል። እውነት ነው?
❇️መልስ:- የጠላት ወሬ ነው። የአማራ ኃይል፣ ብልጽግናም ሆነ ምልሻ የሚባል አንድ ብርጌድ የሚያህል እንኳን የለውም፣ ተመቷል! ከአሁን በኋላ የብልጽግና ሠራዊትም ሆነ የአማራን ልዩ ኃይል ዱቄት አድርገን በትነነዋል። እንግዲህ የተበተነን ዱቄት ሰብስበን አንድ ልናደርገው አንችልም።

❓ጥያቄ:- በአማራ ክልል በአንዳንድ ቦታዎች ንጹሐን ዜጎች እየተገደሉ ነው ይባላል፣ ይሄስ?
❇️መልስ:- ይህ ፈፅሞ ሐሰት ነው። የአማራ ተስፋፊ ኃይል ራሱን ለመደበቅና ሕዝባዊ ለማድረግ የሚያራግበው ሴራ ነው። ብልጽግና መቐለ እስኪገባ አንድም ሰው እንዳልሞተ፣ እኛም ወልድያንና ደብረታቦርን እስክናካልል ድረስ አንድም ሰው አልሞተም።

❓ጥያቄ:- ወሎና አንዳንድ ቦታዎች ላይ ረሃብ አለ የሚባለውስ ነገር?
❇️መልስ:- There is No Hunger in Amhara, there is only a problem in Amhara. (አማራ ላይ ችግር እንጂ ረሃብ የለም) አታሟርቱ!

❓ጥያቄ:- ግንኮ ብዙ ሰዎች ቡትቶ ለብሰው፣ ሰውነታቸው ተጎሳቁሎ፣ መንገዱን ሞልተውት በረሃብ ምክንያት ሲሰደዱ እያየን ነው።
❇️መልስ:- እሱ ምን መሰለህ፣ የኃይሌ ገ/ሥላሴን ታላቁን ሩጫ ከአንድ ሀገር ወሰዱና፣ እሱን በፎቶ ሾፕ ቡቱቶ ልብስ አለበሱና፣ ፊታቸውን አገርጥተው፣ ስደተኞች አስመስለው ኢዲት አደረጉት። በዚህ ነው ሕዝቡን የሚያታልሉት።

❓ጥያቄ:- TDF ከአንዳንድ የአማራ ከተሞች እየወጣ ያለው በኃይል እየተመታ ስለሆነ ይሆን?
❇️መልስ:- (ረጅም ሳቅ) ኣይደለም! እኛ ከአንዳንድ ከተሞች የወጣነው ወቅቱ የክረምት እንደመሆኑ መጠን የአማራ ገበሬ ሕዝባችን ነውና መሬቱን እንዲያርስ ነው። ከአንዳንድ ቦታዎች እንደምንሰማው ደግሞ ከብልጽግና ነፃ ሊያደርጋቸው የገባውን የTDFን ሠራዊት በደቦ በገጀራ ይጨፈጭፉታል። ኣንዳንድ የTDF ኣመራሮችም ኣማራው ሕዝብ ላይ ኣንተኩስም ብለው የራሳቸውን ጥይት ጠጥተዋል። ስለዚህም ለሕዝቡ ጥቂት የፅሞና ጊዜ ለመስጠት ነው ያፈገፈግነው። ሌላው ምክንያት ደግሞ ዓላማችን ከተሞችን መያዝ ሳይሆን የጠላትን አከርካሪ መስመር ነው በምንፈልገው ቦታ እየጠበቅን እንደመስሰዋለን፣ እየደመሰስነውም እንገኛለን።

❓ጥያቄ:- ፋሽስታዊውን የብልፅግናን ፓርቲ ለማስወገድ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?
❇️መልስ:- ብውስጥም በውጭም ነው ስራው! በትግራይ ክልል ውስጥ ከሆነ ብዙ የአማራ ብሔር ተወላጆች ሲኖሩ የጠላት ሰላዮችም አሉ። ስለዚህም ይህንን ፋሽስት ለማጥፋት እነዚህን ጠላትን የሚደግፉ የብሔሩ ተወላጆች ወንጀል ቢገኝባቸውም ባይገኝባቸውም የሆነ ማጎርያ ካምፕ ውስጥ መግባት አለባቸው።

❓ጥያቄ:- በስተመጨረሻ:- ይህንን የጠላት ቡድን በምን ይጉልፁታል።
❇️መልስ:- የአማራ ኃይልና ብልጽግና የሁላችን ጠላት ነው። ይህ ሕዝብ የትግራዋይ ጠላት ነው፣ ይህ ሕዝብ የኦሮሞው ጠላት ነው፣ ይህ ሕዝብ የአፋሩ የሶማሌው ጠላት ነው፣ ይህ ሕዝብ የኢትዮጵያ ጠላት ነው፣ ስለዚህ ሁላችን ከምድረ ገጽ ልናጠፋው፣ ለልጆቻችንም እንደ ተረትና ማስፈራርያ ብቻ ልንጠቀመብት ይገባል።

©Binyam ZeChristos መስከረም 9 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

ሓደ መሳርሕተይስ Screen Shot ክቕበል ላብ ሮማናት ኸይዱ። ዕዳጋ ብዕራይ እምበይ ዕዳጋ ስክሪን ሻት ኣይመስልይ። ላብ ማእኸል ሕውስ ኢሉስ "ናይዙ ሰለስተ መዓልቲ እዙይ ይህልወካ ዶ?" በሎ ልቱ ልሸጥ። ኣብ ጎኑ ልነበራ ሓንቲ ዓባይ ሰበይቲ መናዕ ኢለን ብገፀን ፅይፍ ፣ ብዓይነን ሓፍ በጠቕ ብለበልኦ "ኣታ ኣጥዒሙልኻ ድዩ ስክሪን ሻት ደሊኻ መፂኻ? ሃም ኣዕርኽትኻ Gun Shot'ኻ ለይትእልሽ" ኢለን ኣሕፈርኦ፣ ብኽልተ አፃብዕተን ናይ ምትኳስ ምልክት እላርአያ።

እሞሲ ልዚኣተን ብሓምሳ ልገዝአኒ ዶ እኒሆ?

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

⁉️«ወያነ» ወይስ «ህወሓት»⁉️
ደብተራ የሚለው ቃል ትርጉሙ "የታቦቱና የጽላቱ መኖርያ፣ የንዋያተ ቅድሳቱ መገኛ ተንቀሳቃሽ መቅደስ" ማለት ነበር። ቅድስናን በልባቸው፣ ቅዱስ ቃሉን በአፋቸው ለሚገኝላቸው የቤ/ክ ሊቃውንትም "ደብተራ እከሌ" እያልን እንደ መጠርያ እንጠቀምበታለን። ድብትርናቸውን ትተው ከሰይጣን ጋር የሚሰሩ ምስኪኖች ሲበዙ ግን ቃሉን መፍራትና መፀየፍ ጀመርን። ግን ልክ አልነበርንም፣ ቃሉ የክብር ቃል ነውና የሰዎቹን ግብር እንጂ ቃሉን መጸየፍ ሞኝነት ነው። በዚህ ዘመንም በእውቀትም ይሁን ካለ እውቀት የጥላቻ መግለጫ፣ የስድብ መተከያ ሁኖ እያገለገለ ያለ ቃል ቢኖር "ወያነ" የሚለው ነው።

‹ወያነ› የሚለው የትግርኛ ቃል «ወይኑ» ከሚል ግስ የወጣ ሁኖ «ምውያን፣ ወያናይ» እያለ የሚረባ ሆኖ ‹ምውያን› ማለት «አልገዛም ባይነት፣ እምቢተኝነት፣ አልምበረከክም ማለት፣ ኣምባገነኖችን አለመታገስ፣ ባርነትን ላለመቀበል የሚሸፍት፣ ለፋሽስት እጅ የማይሰጥ» ማለት ነው። ቃሉ የመልካምነት፣ የአርበኝነትና የጀግንነት ምልክት ነው! ትግራይ ላይ አንድ ወጣት "አያቴ ወያነ ነበር" ካለህ "አርበኛ ነበር" እያለህ ነው። በታሪክ ደረጃ ስናጠናው ደግሞ ተጋሩ ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ ለመብታቸው 9 ዓበይት ወያነዎችን (ትግሎችን) ያሳለፉ ሲሆን፣ በዘመናዊው የትግራይ ታሪክ ውስጥ ደግሞ (ከ20ኛው ክ/ዘ ወዲህ) 3 ወያነዎች ተደርጓል ተብሎ ይታመናል።

የመጀመርያው በብላታ ኃይለማርያም እየተመራ የትግራይ ገበሬዎች በአጼ ኃይለ ሥላሴ ላይ ያነሱት፣ የተጋሩን መጨፍጨፍና ጭቆና፣ እንዲሁም "ትግሬ ክዶኛል" የሚል ብሔርን መሠረት ያደረገውን ጥቃት ለመቃወም የተደረገ እምቢተኝነት ነው። ይህ «ቀዳማይ (1ይ) ወያነ» ይባላል። 2ኛውና «ኻልኣይ ወያነ» እየተባለ የሚጠራው ደግሞ በደርግ ላይ የተነሳው በትግራዋይነትና በትግርኛ ቋንቋ ላይ ይደረግ በነበረው ዘግናኝ ጭቆናና ፋሽስታዊነት ላይ የተደረገ፣ በኋላም ራሱን "ህወሓት" ብሎ የጠራው ኃይል ነው። 3ኛው ወያነ ደግሞ የአሁኑ ከብልጽግና ጋር የሚደረገው የተጋሩ ትግል መሆኑ ብዙዎች ይጠቅሳሉ። ያም ሆን ይህ፣ እኛ ተጋሩ "ወያነ" የሚለው ቃል የራሳችን መጠርያ፣ የአባቶቻችን የክብር ስም አድርገን ምንቀበለው ነው።

ተጋሩ ብቻ ግን ኣይደሉም ‹ወያነ›ነት የነበራቸው። ኦሮሞው፣ አማራው፣ ሐረሩ፣ ጉሙዙ በተለያዩ ዘመናት ለፋሽስቶች እጅ አንሰጥም፣ ለፈርዖናውያን አንምበረከክም ያሉባቸው ብዙ ትግሎች ፈፅመዋል! እነዚህ ትግሎች የዚያ ሕዝብ ‹ወያነ›ነትን ማሳያ ናቸው! እንደ ኢትዮጵያውያንም ዮዲት ጉዲት ላይ፣ ግራኝ ኣሕመድ ላይ፣ ጣልያን ላይ፣ እንግሊዞችና ማህዲስቶች ላይ ያደረግነው የነጻነትና የአልገዛም ባይነት ትግል ሁሉ የኢትዮጵያ ‹ወያነ›ነት የሚያረጋግጡ ናቸው። ምናልባት ግብ ይህ ሁሉ ሲሆን አንተ የምታውቀው ‹ወያነ›ነት 2ኛው የትግራይ ወያነና በኃላ ራሱን ህወሐት ብሎ የጠራውን ቡድን ብቻ ሊሆን ይችላል። ለዚያም ነው ህወሓትን ስትቃወም "ወያነ ይጥፋ፣ ወያነ ይውደም" የምትለው። ህወሐትን መቃወምም ሆነ መጥላት ሕገ መንግስታዊ መብትህ ነው፣ ክፋት የለውም! አንድን ፓርቲ ከአንድ ሕዝብ ጋር ጨፍልቀህ "ወያነን እጠላለሁ" ስትል ግን፣ አገኘሁ ተሻገር የትግራይን ሕዝብ «ይህ ሕዝብ የአማራ ጠላት ነው፣ የኦሮሞ ጠላት ነው» ብሎ እንዳለው አንተም "ተጋሩን እጠላለሁ" እያልክ መሆንህን አስብ።

ስለዚህ እንዲጠፋ ምትፈልገው ‹ወያነ›ን ነው ወይስ ‹ህወሐት›ን? ሁሉም ትግራዋይና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወያነ ነው፣ ሁሉ ትግራይ ግን ህወሓት አይደለም። ህወሓት ፓርቲ ነውና ህወሓትን መጥላት መብት ሲሆን፣ ወያነ ግን ትግራዋይነት ነውና ወያነን መጥላት ዘረኝነት ነው። ህወሓት እንዲጠፋ መለመን - ሰውነት ፣ ወያነ እንዲጠፋ መጸለይ ግን ሰይጣናዊነት ነው። ታድያ ጉዳይህ ከህወሓት ጋር ወይስ ከወያነ ጋር? እኔ "ህወሓት ነኝ" አልልም፣ አይደለሁምና። መሆንም አልፈልግምና! በኩራት ሁኜ ግን ይህንን እነግርሃለሁ።

#ኣነ_ወያነ_እየ ~ #እኔ_ወያነ_ነኝ

©Binyam ZeChristos መስከረም 6 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #አቋሜን_ለማጥራት_ያህል‼️
ያለፉት 8 ወራት በፋሽስቱ የዓብዪ ጦርና በአረመኔው የሻዕብያ ሠራዊት የግፍ ግፍ ተፈፅሞብናል። በሕክምና ሥራዬም ከመላው ትግራይ የመጡትን ደም የሚያስለቅሱ ታሪኮች ጠግቤአለሁ። ከዚህ ሁሉ ሰቆቃና መከራ በኋላ ወደ ሚድያ ስመለስ በመንፈሳዊ ከፍታ ላይ የተውኳቸው ሰዎች አቋም ቀይረው አገኘሁ (የተቀየርከው አንተ ነህ የሚሉም አሉ) ሰው ዛፍ ኣይደለምና የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረጉ ባሕርያዊ ነው! የኔ ስህተት 8 ወር ሙሉ የዓብዪ ዲስኩር ሲጠጣ ከኖረ ሰው ጋር ለመግባባት ቀላል አድርጌ መገመቴ ነው። ያም ሆኖ ግን ከዚህ በኋላ የምጽፋቸው ጽሑፎች፣ በስህተት መንገድ ወስደው ድኩም ወንድሜን እንዳያሰናክሉት አስቀድሜ እነዚህን ጽኑ አቋሞቼን እንዲታወቁልኝ እፅፍ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

1) የትግራይን ሕዝብ እንደ ሕዝብ እንዲጠፋ በላይ በአየር የደበደበ፣ በምድር በታንክና በከባድ መሣርያ ያጋየ፣ በመከላከያ ወታደሮች እህቶቼና እናቶቼን የደፈረ፣ ገዳማቶችን ያስበረበረ፣ የቀሩትንም በፎስፈረስ ኣሲድ ያለበለበ፣ አረመኔውን የኤርትራን ሠራዊት ጠርቶ የራሱን ሕዝብ ያስጨፈጨፈ ይህ የዓብይ መንግስት የእኔ መንግስት እንዳልሆነና እንደማልቀበለው፣ ኢትዮጵያ ሰላም የምትሆነውም በዋናነት ብልጽግና ሲጠፋ ነው ብዬ አምናለሁ! እንዲጠፋም እተጋለሁ!

2) የትግራይ ሠራዊት (TDF) ጀግና ኢትዮጵያዊ ነውና እንደ አባቶቹ "አልገዛም፣ አልምበረከክም" ብሎ የእናቱን ደፋሪ፣ የእህቱን አራጅ፣ የገዳሙን ኣፍራሽ ያጠፋ ዘንድ ተነስቷል። በጌታ ኃይል በራሱም ቆራጥነት ሻዕብያንና ብልጽግናን ጠራርጎ በማስወጣት ትግራይን ከሞላ ጎደል ከወራሪ ነጻ አድርጎታል። እነዚህም ለሕዝብ ብለው የሚሞቱ የዘመኔ ጀግኖች ናቸውና የዓድዋውን ታሪክ ከሚደግሙ ከትግራይ ሠራዊት (TDF) ጎን ጋር እቆማለሁ!

3) ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ትግራዋይም ነኝ። ትግራዋይነቴ ከኢትዮጵያዊነቴ ነጥዬ ኣላየውም። እንደ ነፍስና ሥጋ ተዋሕደውና ተጠባብቀው ይኖሩብኛል። ስለ ኢትዮጵያ ሳስብ ስለ ትግራይ ቸል በማለት አይደለም። ስለ ትግራይ ስናገር ኢትዮጵያዊነቴን በመዘንጋት ኣይደለም። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ለመሆን ትግራዋይነቴን እንድጥል የሚነግረኝ ካለ የትግራይ ጠላትና ፍፁም ዘረኛ ነውና ከእርሱ ጋር ሕብረት የለኝም ኣይኖረኝምም።

4) ከአማራ ሕዝብም ይሁን ከኤርትራ ሕዝብ ጋር የሚወራረድ ሒሳብ አለ ብዬ አላምንም፣ ሊኖርም ኣይችልም። እንዲህ ብሎ የሚናገር ቂል ማንም ሊቀበለው አይገባም። የሚወራረድ ሒሳብ ቢኖር ኖሮ ትግራይ ውስጥ ባሉ አማራና ኤርትራውያን ላይ ይወራረድ ነበር። ይህ ግን ተጋሩን አይመጥነንምና፣ የምናወራርደው ሒሳብ ግን ከዚያ ፋሽስታዊ ብልፅግናና አረመኔያዊ ሻዕብያ ጋር ነው፣ መሆንም አለበት። የአማራ ሕዝብ ጠላቴ አልነበረም፣ ሊሆንም አይችልም፣ የትግራይ ሕዝብም የአማራ ጠላት አልነበረም አይደለምም ብዬ በጽኑ ኣምናለሁ!

5) ትግራይ የኢትዮጵያ ዋና አካል ነች! ስለዚህም መገንጠል የሚለውን በግሌ አልስማማበትም። ግን ደግሞ ትግራዋይም ይሁን ዓፋሩ "ለብቻዬ ልሁን" የማለት ሙሉ መብት እንዳለው አውቄለሁ፣ ስለዚህም ሐሳቡን አከብራለሁ። ትግራይ ሀገር መሆን ይሻለኛል ካለ ይህ መብቱ ነው። ይህ ኢትዮጵያን ማፈራረስ የሚመስለው ካለ የፈረሰ ሐሳብ እንዳለው ይወቅ። እንዲያ ቢሆን ኢትዮጵያ ሺህ ጊዜ ፈርሳለች ያስብል ነበር። የቅርቡን የኤርትራን መውጣት እንኳን ብናይ ኢትዮጵያን አፈራርሷታልን? ስለዚህን ትግራይ "ለብቻዬ ልሁን" ካለ:- "አብረን ሆነን ደም ከመቃባትና የማይበርድ የእርስ በርስ ጦርነት ከመግጠም፣ ጥሩ ጌረቤታሞች ሆነን ተከባብረን መሆን ይሻላል" ማለቱ ነውና ባልስማማበትም ሐሳቡን ግን አከብርለታለሁ።

6)ተጋሩ ጠላታችንን፣ የሚደመሰሰው ተደምስሶ የሚማረከው ተማርኮ ከምድራችን ካስወጣነው በኃላ አንድ ጥያቄ ጠየቅን! "ጠላታችን እስካልጠፋ ድረስ መልሶ ሊጨፈጭፈንና ሊያጠፋን ይሞክራልና ምን እናድርግ?" ለዚህም መልሱ ኣምባገነኑን ብልፅግናንን አረመኔውን ሻዕብያን የገባበት ገብቶ ማጥፋት ይገባል። ዛሬ በትግራይ ላይ የተረጨው አሲድ ነገ ኦሮሞውና ጋምቤላው ላይ ይረጭ ዘንድ ወደ ኋላ የማይል ነው መደምሰስ ነበረበት። ይህም ፅኑ አቋሜ ነው። ምዕራብ ትግራይን "የኔ ነው" እያለ ወሮት ያለውን የአማራ ልዩ ኃይልም መውጣት አለበት። በዚህም እስማማለሁ። እነዚህ 2ቱ እንዲሳኩ ግን TDF ከትግራይ ውጭ ጠላትን ለመቅበር መዝመቱን እደግፋለሁ። የምደግፈው ህወሓትን አይደለም፣ እንደማልደግፈው የታወቀ ነውና፣ ይልቁንስ ድጋፌ ለሕዝባዊውው ሠራዊት ነው!

7) ነገር ግን TDF በአማራም ሆነ በኦሮሞ መሬት ውስጥ ገብቶ "መሬቱ የኔ ነው" ብሎ የሚወር ከሆነ አልደግፈውም። ንጹሐን ዜጎችን የሚገድልና የሚያሰቃይ ከሆነ እቃወመዋለሁ። ለ8 ወራት ያየሁትን ስቃይ አማራው ላይ እንዲፈፀም አልፈቅም! "እሰይ፣ እስኪ እነሱም በተራቸው ይቅመሷት" የሚል የዘቀጠ ሓሳብ የለኝም። በኔ ላይ የተፈፀመው በማንም ላይ እንዲፈፀም አልሻምና።

በነዚህ አቋሞቼ ፀንቼ እቀጥላለሁ፣ የማይስማማ ካለ የተሳሰትኩትን በማረም፣ በሓሳብም በመከራከር ይቀጥል። ለዚህ አቅም የሌለውም በጊዜ ከቤቴ ይሰናበት። ቀጠልኩ

#ትግራይ_ትስዕር

©Binyam ZeChristos መስከረም 5 - 2014 ዓ/ም

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#በእንተ_ኣሙ
ዘማሪ አማኑኤል ይባላል፣ የምወደውና የማከብረው በመቐለ ቅ/ቂርቆስ ቤ/ክ ያደገ መንፈሳዊ ጓደኛዬም ወንድሜም ሲሆን የምንቀርበው ሁሉ በፍቅር ቃል "ኣሙ" እንለዋለን። ከዓመታት በፊት ስለ ቀጥተኛዋ እምነት (ኦርቶዶክስ) አንድ ግሩም የመዝሙር ካሴት ያበረከተልን፣ በዝማሬና በስብከት በመድረክ የሚያገለግል ወንድም ነው! አሁን ደግሞ ስለ ቀጥተኛዋ እውነት ሲል ድምፁን ሳይሆን ደረቱን ሊሰጥ፣ መድረክ ላይ ሳይሆን ግንባር ላይ ሊያገለግል ወጥቷል። ኣሙ ከመድረክ ወደ ግንባር ለምን ሄደ? ብዬ ጠይቄው አላውቅም! ልጠይቀውም አልችልም! ዘመዶቹ በጥይት ሲረግፉ፣ እህቶቹ የማንም እንስሳ ይሁን ሰው ያልለየለት ውርጋጥ የወሲብ ማብረጃ ሲሆኑ፣ የተሳለማቸው ገዳማትና አድባራት ሲፈርሱና ሲመዘብሩ፣ በረከትዎ ይድረስ ብሎ የጠየቃቸው መነኮሳት ግንባራቸው በጥይት ሲፈርስ ፣ የትግራይ ከተሞች መንገድ ላይ አቁሞ የመኪናህን ቁልፍ ተቀብሎ መኪናህን በሚነጥቅ ዱርዬ ወታደር ሲከበቡ፣ የታወጀው ጦርነት ከአንድ ፓርቲ ጋር ሳይሆን ከትግራዋይ ማንነት ጋር መሆኑን በዓይኑ ኣይቶ በጆሮው ሰምቶ ሲረዳ፣ ለይትኛው ኑሮ ለየትኛውስ ሕይወት እንደሚቀመጥ ራሱን ጠየቀ?

ኣሙ መንፈሳዊና ዘማሪ ሆኖ ሳለ፣ ስለተገፋውና ስለተጮጨቆነው ሕዝብ ይሞት ዘንድ መምረጡ፣ ከጌታው ዘንድ ያስመሰግነው እንደሆነ እንጂ እንደማያስነቅፈው ገብቶታል። ኣባቶቹ በዓድዋ ድል ጊዜ አረመኔውን ወራሪ ከባንዳዎቹ ጋር ለመመከት ራሳቸውንና ታቦተ ጊዮርጊስን ይዘው እንደዘመቱ ሁሉ፣ እሱም ትግራይን ከአረመኔውን ወራሪ ሻዕብያንና ከባንዳውን ብልጽግና ይመክት ዘንድ ሥዕለ ቅዱስ ቂርቆስን ይዞ ወጥቷል። ኃጢኣት ማለት በግፍ የአንድን ንጹሕ ወንድም ደም ማፍሰስ እንጂ ራስንና ሕዝብን መከላከል እንዳልሆነ ቀድሞ ተምሮታል። እንዲያውም ለሕዝብ ብለህ በረሃብና በብርድ መጠበሱ፣ እህቶቹን ለማትረፍ ብሎ ደረቱን ለብረት ግንባሩን ለጥይት መስጠቱ የ"ፍቅረ ቢጽ" አንድምታው መሆኑ አንብቦታል።

ወዳጃ፣ ተጋዳላይ ዘማሪ ኣሙ የህወሓት አባል ወይም ቅጥረኛ ከመሰለህ የቂልነትህን ጥልቀት ወደር አይኖረውም። ደሙን ለማፈሰስና ህይወቱን ለመስጠት የወጣው የሕዝብ ፍቅር እንጂ የፓርቲ ፍቅር ቀስቅሶት ከመሰለህ የጅልነትህን ባሕር አድማስ ኣይኖረውም!/ሕዝብን ከሚጨፈጭፍ ሠራዊት ጎን ጋር "ከአንተ ጋር እቆማለሁ" እያሉ መሰለፍ ልክ ከሆነ፣ ለምትደፈረው እህቱ ለምትታረደው እናቱ ሲል "እሞትላታለሁ" ማለቱ የቅድስናና የፍጽምና ክብር ይይዛል። ንጉሥ ካሌብ የክርስቲያን ጠላቶችን ከየመን ያስወጣ ዘንድ በአባ ጰንጠሌዎን ተባርኮ እንደሄደው፣ የትግራይ ኦርቶዶክሳውያንም ከንስሐ አባታቸው ጋር ተነጋግረው፣ ንስሐቸውና ቁርባኑን ተቀብለው እየወጡ ነው። በእውነት ክብር በሰው ብዛት ሳይሆን በጌታ ጉልበት ለሚያምኑት ይሁን። ኣቤቱ እንጨብጣቸዋለን ያሉት ሲጨበጡ ኣይተናልና፣ ክንድህ ኃይል ስምህም ጉልበት ይሁነን! ወንድሜን ኣሙን ፍጹም መጠበቅን ጠብቅልኝ! በቂርቆስ ሕፃንህ፣ በድንግል እናትህ ብሥጋና በደምህ ለዘላለሙ አሜን!

@Binyam ZeChristos መስከረም 3 - 2014 ዓ/ም

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#የእኔና_የአንተ_ልዩነት
√ያኔ ሲጀመር፣ "ሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጠረ የተባለው ነገር ተጣርቶ ወንጀለኛው ይጠየቅ" ብዬ ስልህ፣ አንተ ግን "ትግራይ መመታት አለበት" ብለህ ለጦር እጅህን ያነሳህ የጦር ሰው ነህ።

√ "ሕዝብና ፓርቲ ይለያያል" ብሎ የመጣው የብልጽግና ሠራዊት እግሩ እንደገባ ፓርቲን ትቶ ሕዝቡን እየገደለና እያረደ መሆኑን በመረጃም በማስረጃም ነገርኩህ። አንተ ግን "ከመከላከያ ጎን ጋር እቆማለሁ" ብለህ በመጮህ ከደም አፍሳሾች ጋር መቆምህን ነገርከኝ።

√ "የአማራ ልዩ ሐይል ከትግራይ መውጣት እንዳለበት፣ የመሬት ጥያቄ ካለበትም በጠረቤዛ ዙርያ ያድርገው እንጂ እንደ አረመኔ ተጋሩን ገድሎና ጨፍጭፎ የሚወስደው ቦታ የለም" ብዬ ስልህ፣ መሬታችን ስለሆነ እንወስደዋለን ብለህ የደነፋክ፣ ግን ደግሞ ሱዳን የአማራን መሬት "መሬቴ ነው" ብላ ስትወር "እንዴት በሃይል መሬት ይወረራል?"' ብለህ የምታለቅስ ማበድህን ያላወቅህ ሰው ነህ።

√ ሕዳር 19 ቀን ብልጽግና መቐለ ሲገባ፣ ከተማውን እንዴት ባለ ከባድ መሣርያ ሲደበድባት እንደዋለና ብዙ ንጹሓን ዜጎች ደማቸው ፈሶ ሰውነታቸው ተቆራርጦ እንደሞተ የዓይን ምስክር ሆኜ ነገርኩህ። አንተ ግን ከዚያ ይልቅ "በገብርኤል በዕለተ ቀኑ መቐለ ተያዘች" ብለህ የፈሪሳዊነትህን ጥግ የመሰከርክ፣ "አንድ ሰው ሳይሞት ነው መቐለ የገባነው" ለሚለው ዜና ያጨበጨብክ ምስኪን ሰው ነህ።

√ የእህቶቼን በአሲድ መቃጠል በሺድዮ ሳሳይህ፣ የእናቶቼን መደፈር በፎቶ ሳስረዳህ፣ የህፃናቶች ሰውነት መቆራረጥ ከራሳቸው ከገዳዮቹ ወታደሮች አንደበት እንካን እያሰማሁህ፣ በኢትዮጵያዊነት ወግ "ያሳዝናል፣ እውነት ከሆነ ይህንን አወግዛለሁ" የምትልበትን አቅም አጥተህ "ውሸት ነው! የህወሐት ፕሮፓጋንዳ ነው" ብለሀኝ ያረፍከውና ሰውነትህን እንድጠረጥረው ያደረከኝ ሰው ነህ።

√ የሻዕብያ ወታደሮች ጨዋ እህቶቼን ለ10 ሲደፍሯቸው፣ ብልታቸው ውስጥ ሚስማርና ድንጋይ ሲከቱበት፣ ቤት እያቃጠሉ ማንካና ሹካ ሲሰርቁ ለምን ዝም እንዳልክ ስጠይቅህ፣ የዓለም ሚድያዎች እንኳን የተቀበሉትን እውነት "የኤርትራ ወታደሮች አልገቡም" ብለህ የሸመጠጥከኝ፣ መንግስት ራሱ ሻዕብያዎች መግባታቸው ሲያምን ደግሞ "ራሳቸውን ለመከላከል ነው የገቡት" ብለህ በእህቶቼ ላይ ያፌዝክ፣ ካንተ ጋር እኩል ኢትዮጵያዊ ተብዬ በመጠራቴ እንዳፍር ያደረከኝ ማፈርያ ሰው ነህ።

√ የብልጽግና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ መከላከያ ሠራዊት (TDF) ተቀጥቅጦ ነው ከትግራይ የወጣው ብዬ የተማረኩትን የሠራዊቱ የበላይ አመራሮችን ምስክር አድርጌ ነገርኩህ፣ አንተ ግን አሁንም "የትግራይ ገበሬ እንዲያርስ" ፣ አልያም "የፅሞና ጊዜ ለመስጠት ነው" ብለህ የምታስብ ድኩም፣ ሠርዊቱ እንኳን እንዲያ ብሎ ቢወጣ በዓብዪ የተሾሙት ጊዜያዊ ኣመራሮች ለምን እንደፈረጠጡ እንኳን መጠየቅ ያቃተህ ምስኪን!

√ አንተኮ በትግራይ የተማረኩትን ከ50,000 በላይ ወታደሮች መንገድ ላይ እንደ በግ ሲግተለተሉ ኣይተህ "የታላቁ ሩጫ ከሆነ ሀገር ኣምጥታችሁ ሬንጀር ልብሳቸውን ደግሞ ኢዲት አድርጋችሁ ነው እንጂ የተማረከ የለም" ብለህ በራስህ ላይ ይምታሾፍ ሰው እኮ ነው! ይህንን ጭንቅላት የተሸከመውን የአንገትህን የትዕግስቱን ፅናት አደንቃለሁ!

√ ባንተ ጭብጨባና ድጋፍ ተጋሩን ለመጨፍጨፍ የመጡ ሺዎች የሚቆጠሩ፣ ግን ደግሞ የተማረኩ ወታደሮችን በረሃብ ከደረቀው ጉሮሮኣችን እያበላንና እያጠጣን እንደሆነ ነገርኩህ። አንተ ግን አሁንም ያለንን አብስለን እንኳን እንዳንበላ "ለትግራይ መብራትና ስልክ እንዳይለቀቅላት" ከሚሉት ዘንድ ተሰልፈሃል።

√ እኔ በምግብ እጦት ምክንያት ስንት ሰው እየረገፈ እንደሆነን እርዳታዎች እንዲገቡ የቻልከውን እንድታደርግ ነገርኩህ። አንተ ግን አሁንም "እርዳታውን ህወሐት ልትወስዱው ትችላለችና ምንም ዓይነት የምግብ እርዳታ መቅረብ የለበትም" ብለህ፣ አሁንም በተጋሩ ሞት ልትረማመድ መሻትህን ገለፅክ።

√ አንተ ህወሓት እንዲጠፋ ትጸልያለህ፣ እኔም ብልፅግና እንዲደመሰስ እሻለሁ። ምኞታችን ባልከፋ፣ አንተ ግን ህወሐትን ለማጥፋት አስፉላጊ እርምጃ መወሰድ አለበት ብለህ የተጋሩን መጨፍጨፍ Justifiy ለማድረግ ትደክማለህ፣ እኔ ግን ብልጽግናን ለማጥፋት የአንድም አማራም ሆነ ኦሮሞ ወንድሜ ደም እንዲፈስ አልፈቅድም!

©Binyam ZeChristos. ነሐሰ 30 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

🔥... በዓለ_ጰራቅሊጦስ ~ #ጾመ_ሐዋርያት ...🔥
✝ሎሚ ሰንበት ካብቶም 9 ዓበይቲ ናይ ጎይታ በዓላት (ጽንሰት፣ ልደት፣ ጥምቀት፣ ደብረታቦር፣ ሆሳዕና፣ ስቕለት፣ ትንሳኤ፣ ዕርገት፣ ጰራቅሊጦስ) ሓደ ዝኾነ በዓለ ጰራቅሊጦስ እንትኸውን እዚ ድማ መንፈስ ቅዱስ ኣብ ልዕሊ ሓዋርያት ዝወረደሉን፣ ብመንፈስ ተጠሚቖም ጸግኡ ዝተቐበሉሉን መዓልቲ እዩ። ጰራቅሊጦስ (Parakletos) ዝብል ቃል ግሪክኛ እንትኸውን "መጽናንዒ" ማለት ኮይኑ ንእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዝቕጸል ስያመ እዩ። ጎይታ እውን ንሓዋርያቱ መጽናንዒ መንፈስ ከምዝልእኸሎም ነጊርዎም ነይሩ። "እቲ ኣቦይ ብስመይ ዝሰዶ #መጸናንዒ #መንፈስ ቅዱስ፡ ንሱ ዅሉ ክምህረኩም፡ ዝነገርኩኹም ዘበለውን ከዘክረኩም እዩ>(ዮሐ14:16/26) ፣ <እቲ ኣነ ኻብ ኣቦ ዝሰደልኩም #መጸናንዒ፡ ካብ ኣቦ ዝወጽእ መንፈስ ሓቂ ምስ መጸ ግና፡ ንሱ ኺምስክረለይ እዩ>(ዮሐ15:26) ፣ <ኣነ እንተ ዘይከድኩስ፡ እቲ #መጸናንዒ ናባኻትኩም ኣይመጽእን እዩ እሞ፡ እንተ ኸድኩ ግና ንእኡ ኽሰደልኩም እየ>(ዮሐ16:7)

✅ ጎይታ ካብ ሙታን ተሲኡ ኣብ 40 መዓልቱ ናብ ሰማይ እንትዓርግ እውን <ንስኻትኩም ግና ካብ ላዕሊ #ሓይሊ ኽሳዕ እትለብሱ ኣብ ከተማ የሩሳሌም ጽንሑ> (ሉቃስ 24:49) ከምዝበሎም፣ <#መንፈስ ቅዱስ ናባኻትኩም ምስወረደ ግና #ሓይሊ ኽትቅበሉ፣ ኣብ የሩሳሌምን ኣብ ኲላ ይሁዳን ኣብ ሰማርያን ክሳዕ ወሰን ምድሪ ምስክር ክትኰኑኒ ኢኹም> (ግብሪ 1:8) ኢሉ እውን ተስፋ ከምዝሃቦም ነንብብ።

❤️ክርስቶስ ምስ ዓረገ ሐዋርያት ኣብ የሩሳሌም ተኣኪቦም እናሃለዉ "በዓለ ሓምሳ" ዝበሃል ናይ አይሁድ በዓል በጽሐ (ብግሪክ ጴንጠቆስጤ Pentekoste ይበሃል። ትርጉሙ ሓምሳ ማለት እዩ። ሓደ ሓደ መናፍቃን ግና ትርጉሙ ካብዘይምፍላጥ መጸውዒ ስሞም ይገብርዎ። ጴንጤ/ጴንጤቆስጤ ማለት ግና 50 ማለት እዩ) "በዓለ ሓምሳ" ዝተብሃለሉ ምኽንያት ድማ፣ አይሁድ ድሕሪ ፋሲካኦም ን7 ሰሙናት (49 መዓልቲ) በዓል ገይሮም ኣብ መወዳእታ መበል 50 መዓልቲ ብድሙቕ መልክዑ ስለዝኽበር እዩ። (ዘጸ34:22፣ ዘሌዋ 23:15-22) ነዚ በዓል ንምኽባር ድማ ኣብ ዝተፈላለዩ ከባቢታት ዝነብሩ አይሁድ ናብ ኢየሩሳሌም ተኣከቡ። በዚ ጊዜ እቲ ጎይታ ዝነገሮም ሓያል መጽናንዒ መንፈስ ዝወረደሎም። <ብድንገት ከዓ ከም ብርቱዕ ህቦብላ ንፋስ ካብ ሰማይ ደሃይ መጸ። ነታ ኣብኣ ተቐሚጦም ዘለውዋ ቤትውን ንብዘላ መልኣ። እተመቓቐለ ልሳን ሓዊ ዝመስል ድማ ተራእዮም። ኣብ ልዕሊ ነነፍሲ ወከፎም ከኣ ተቐመጠ። ኲሎም ድማ መንፈስ ቅዱስ መልኦም፤ መንፈስ ቅዱስ ኪዛረቡ ኸም ዝሀቦም'ውን ብኻልእ ቋንቋታት ክዛረቡ ጀመሩ> (ግብሪ 2:2-4) ልሳን ወይድማ ቋንቋታት ዝተቀበሉሉ ምኽንያት ድማ ናብ ዝተፈላለዩ ከባቢታት ዓለም ብምኻድ ንከስተምህሩ እዩ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነዚ በዓል "ናይ ቤተክርስቲያን ልደት" ብምባል ይጽውዖ! ኣብ ልዕሊ ሐዋርያት ወሪዱ ሓይሊ ዝሃበ መንፈስ ቅዱስ ንዓና እውን ሓይልን ጥብአትን ይሃበና።

✝በዓለ ጰራቅሊጦስ ምስኣኽበርና ድማ ሰኑይ እቲ ብሃንቀውታ እንጽበዮ ጾመ ሐዋርያት ይኣቱ። (ጾመ ሰነ ዝብል ናይ ዘይተምሃረ ጨዋ ዘረባ እዩ) ልክዕ ምስቲ ጾም ድማ "ጾመ ድኅነት" ይጅምር። እዚ ድማ ናይ ረቡዕን ዓርብን ጾም እዩ። ጾመ ሐዋርያት እንጾመሉ ምኽንያት ድማ፣ ጎይታ ንባዕሉ "መርዓዊ" ንሐዋርያት ድማ "ኣዕሩኽ መርዓዊ" ኢሉ ብምምሳል መዓዝ ክጾሙ ከምዘለዎም እንትምህረና <ኢየሱስ ከኣ በሎም፦ ኣዕሩኽ መርዓዊኸ፡ መርዓዊ ምሳኣቶም ኽሳዕ ዘሎ፡ ከመይ ኢሎም #ክጾሙ ይዀነሎም? መርዓዊ ኻብኣታቶም #ዝውሰደላ መዓልቲ ግና ክትመጽእ እያ፡ ሽዑ ኸኣ #ይጾሙ> ይብል! (ማቴ9:15፣ ማር2:19፣ ሉቃ5:34) መርዓዊ ዝተብሃለ ጎይታ ካብኣቶም ዓሪጉ እንፍለ ከምዝጾሙ ንምግላፅ እዩ። ሐዋርያት ድማ ድሕሪ ዕርገት ጎይታናን መንፈስ ቅዱስ ድሕሪ ምቕባሎምን <ንእግዚኣብሄር ከገልግሉን ክጾሙን ከለዉ ኸኣ መንፈስ ቅዱስ "በርናባስን ሳውልን ነቲ ዝጸዋዕክዎም ዕዮ ፍለዩለይ" በሎም።ሽዑ #ጾሙን ጸለዩን ኣእዳዎም ከኣ ኣንበሩሎም እሞ ሰደድዎም> (ግብሪ 13:2-3) በዚ ምኽንያት በረኸትን ኣማላድነት ሐዋርያት ንምቕባል ጾመ ሐዋርያት ንጾም። ቡሩኽ በዓልን፣ ቅዱስ ጊዜ ጾምን ይኹነልና ትብለኩም ኦርቶዶክሳዊት ቤ.ክ!

👇ንኻልኦት መንፈሳዊ ጽሑፋት👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc2WXYXfdEtME6smg
©Binyam ZeChristos ሰነ 12 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

ኣብ ጊዜያዊ ኹነታት ትግራይ መሰረት ገይሩ፣ ኣታዊኡ ንተጋሩ ተፈናቐልቲ ንክኾን ዝተዳለወ "ንብዓት ራሔል" ዝብል ናይ ዲ/ን ክብሮም ናይ ትግርኛ መዝሙር፣ ፅባሕ ሰንበት ሰዓት 8:00 ኣብ ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ኣዳራሽ ስለዝምረቕ ናይ ድጋፍ ትኬት ብምግዛእ ንክትርከቡ ብትሕትና ንዕድም።

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #ካልሳይ_ምዕራፍ_ህፁጽ_ሓገዝ ‼️
ግፍዒ ሕዝቢ ትግራይ ሐዚ እውን እናቐጸለ ዘሎን ክሳብ ኮነ ሓገዝናን ድጋፍናን ቐጻልነት ክህልዎ ይግባእ:: ናይ ትግራይ ፕሮፋይል ምግባር ጥራሕ ነቲ ኣብ በረኻ ወዲቑ ብጥምየት ዝፈሓስ ብጻምእ ዝመውት ዘሎ የዋህ ትግራዋይ ድራር ኣይኾነይ:: መጽሓፍ "እንጀራኻ ኣብ ቕድሚ ማይ ደርብዮ! ድሕሪ ዝተወሰነ ጊዜ ክትረኽቦ ኢኻ" ከምዝበሎ (መክ 11:1)እንጀራና ብማይ ብዝተመሰለ ከርሰ ርኁባንን ጉርዔ ጽሙኣንን ንክድርብዮ ይግባእ:: ደሓር ድማ ብምድሪ ኽኦነ ብሰማይ ካብ ኣምላኽ ክንቕበሎ ኢና! ንሓን እውን ኣብ 1ይ ዙር ኣብ መቐለ ንዝነብሩ ተመዛበልቲ ናይ ፍርናሽ፣ ሳሙና ሞዴስን ድጋፍ ዝተገበረ እንኸውን እዚ 2ይ ዙር ድማ ኣብ መቐለን ከበቢኣን ከምኡ ኣብ መላእ ትግራይ ንዝረኸብናዮም ኣብ ገዛ ተዓፅዮም መዓልቲ ሞቶም ንዝፅበዩ ዝተገበረ ሓገዝ እዩ:: ናይ ጥረ ገንዘብ ሓገዝ ብምቕዳም እንሆ ሓገዝ 3ይ ዙር!

1⃣ #ኣብ_መቐለ:- ዳ ገብርኤል ሰፈር ን15 ዝተጸገሙ ወገናት ከኪ 2000 ቅርሺ፣ ኣብ ዳ ገብርኤል 17 ቀበሌ እውን ን15 ጽጉማት ከኪ 2000 ቅርሺ፣ ከባቢ ኩሓ ን10 ጽጉማት ከኪ 2000 ቅርሺ፣ ከባቢ ዓዲሓ ን10 ጽጉማት ከኪ 2000 ቅርሺ ብምሕጋዝ ብጠቕላላ ካብቲ ዝለኣኽኩምዎ 100,000 በጺሑ ኣሎ::

2⃣ #ዕዳጋ_ሓሙስ:- ኣብ ከባቢ ዕዳጋ ሓሙስ ድማ ን20 ጽጉማት ከኪ 2000 ብምሃብ 40,000 ኣብ ሓገዝ ውዒሉ::
3⃣ #ሰሜን_ምብራቕ_ትግራይ:- ከባቢ ዛላምበሳ፣ ፋፂ፣ ጉዕተሎ፣ ፍረዳሹምን ደንገላት ማርያም ንዝረኸብናዮም 22 ጽጉማት ተጋሩ ድማ ከኪ 2000 ቅርሺ ብምሃብ 44,000 ሓገዝ ተገይሩ አሎ::
4⃣ #ወጀራት:- ኣብ ከባቢ ወጀራት ድማ ንዝረኸብናዮም 10 ጽጉማት ከኪ 2000 ቅርሺ ብምሃብ 20,000 ሓገዝ ተገይሩ እዩ::
5⃣ #ዓዲሽሁ_ቦራ:- ኣብዚ ከባቢ ድማ ንዝረኸብናዮም 5 ጽጉማት ምዕመናን ከኪ 2000 ቅርሺ ብምሃብ 10,000 ሓገዝ ተገይሩ እዩ::
6⃣ #ወረዳ_ዳ_መኾኒ:- ከባቢ ሽምጣ ገለውሳ ድማ ብሰንኪ ስደትን ምዕፃው መንገድን 1 ወላዲ ዝተረኸቡ ኾይኖም 2000 ቅርሺ ተሓጊዞም እዮም::
7⃣ #ገዳም_ዋልዳብ:- ካብ ዋልድባ ገዳም ተሰዲዶም ንዝመፁ ኣቦታት ድማ 50,000 ቕርሺ ሓገዝ ተገይሩ እዩ:: እዚ ብጠቕላላ ካብ ዝለኣኽኩምዎ 266,000 ቕርሺ ኣ ሓገዝ ውዒሉ ኣሎ:: ብተወሳኺ ድማ ኣብ መቐለ ፍሬምናጦስ መሐብሐቢ አረጋውያንን ሕጻናትን ንዝነበሩ ኣረጋውያን 450 ዓበይቲ ዳይፐራት ብምግዛእ (1 ዳይፐር - 17 ቅርሺ) 7650 ቅርሺ ሓገዝ ዝኾነ እንትኸውን፣ ምስቲ ናይ ቕርሺ ሓገዝ ድማ 273,650 ቕርሺ ናብ ትግራይ ምዕመናን በጺሑ ኣሎ::

‼️ካብ ምቑዛም ሓሊፍና ለውጢ ብዘምፅእ ሓገዝ ንትግራይና ንብፀሐላ።‼️

ባንክ ንግዲ ኢ/ያ (CBE)
1000 372639044
Hayelom G/medhin
Mahder G/eyesus

©Binyam ZeChristos ግንቦት 12 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌ #መሕጠዪ_ጾም ❌
እቲ "ጾመ ትግራይ" እናተብሃለ ዝውጋዕ ዘሎ ብዓይኒ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከመይ ይረአ? ዝብል ናይ ብዙሓት ሕቶ ስለዝቐረበ እምበር ብዛዕባ እዚ ንኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን መልሲ ምሃብ ምሕፈሪ እዩ። ክንደይ ዓመት ዝተምሃርናዮ፣ ኩሉ ሻብ ኣብ ማሕበራዊ ሚድያ እንጽሕፎን ብቐሊሉ ናብ ንስሐ ኣቦና ደዊልንን እንርድኦ ጉዳይ ስለዝኾነ! እዚ ካብ ግንቦት 17 - 21 ጾመ ትግራይ ተባሂሉ ዝውረ ዘሎ ነገር ብዓይኒ ቤ/ክ ብብዙሕ መንገዲ ዝተጋገየን ዝተወገዘን ስራሕ እዩ። እተን ፪ መሰረታዊ ጌጋታት ከብራህርህ።

1⃣ #ጾም_ኣብ_ዘመነ_ፋሲካ:- ካብ ዕለተ ትንሳኤ - ጰራቅሊጦስ ዘለዋ 50 መዓልትታት "ሰሙነ ፋሲካ" ፣ "ዘመነ ፋሲካ" ፣ "በዓለ ሓምሳ" እናተብሃላ ይጽውዓ። 50 መዓልቲ ከም ሓንቲ መዓልቲ ከም ትንሳኤ እየን ዝኽበራ። ስለዚ ብዘይካ ቀዳም ሥዑር ድማ፣ ቀዳም ኾነ ሰንበት (እሑድ) ኣይጽወምን፣ ውጉዝ እዩ። ነዚ ድማ ናይ ቤ/ክ ናይ ሥርዓት መጽሓፍ ዝኾነ ፍትሐ ነገስት (ፍትሐ መንፈሳዊ) መረዳእታ ንፀውዕ።
📌ፍት.መን.ዓንቀጽ 723:- "ኢይጹሙ በዕለተ እሑድ ወሰንበት ዘእንበለ ሰንበት ዘኮነ ባቲ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅቡረ ውስተ መቃብር - ብዘይካ ጎይታና ኢየሱስ ክርስቶስ ዝተቐበረላ ቀዳም መዓልቲ (ቀዳም ሥዑር)፣ ብቀዳምን ብእሑድን #ኣይጹም»

ትንሳኤ ጎይትነት ክርስቶስ ዝተገለፀሉ፣ ሞይትና ከምዘይንተርፍ ዘረጋገፅናሉ ናይ ሓጎስን ደስታን ዕለትን ዘመንን እዩ። ጾም ድማ ናይ ብሓዘንን ብተዋርዶን ናብ ኣምላኽ እንጠርዐሉ ጊዜ እዩ። ኣብ መርዓ ኣይተእውን፣ ኣብ ቐብሪ ኣይትዕልልን! ስለዚ ድማ ብግልፂ ቋንቋ ኣብ በዓለ ሓምሳ ጾም ኾነ ዋላ ሓዘን ዝተወገዘ እዩ፣ ዝጾመ ሰብ እውን ከም ሓጡኣተኛ ዘቑፅሮን ቅፅዓት (ቀኖና) እውን ዘውህቦ እዩ። ሰማይን ምድርን ዝሕጎስሉ ዘመነ ፋሲካ ንዒቑ ብጾም ስለዘሕለፈ!
📌ፍት.መን.ዓንቀጽ 739:- «ወዘሰ ይጸውም በዕለተ እሑድ፣ ዘውእቱ ዕለተ ትንሣኤ #ኃጥእ ውእቱ። ወይደልዎ #ኲነኔ። ወከማሁ ይገብር በበዓለ ሓምሳ አው ዘየሓዝን በዕለተ በዓላት ዘእግዚእነ ዘይደሉ ለነ ፍሥሐ መንፈሳዊ ቦሙ ወአኮ ሐዘን --- ናይ ትንሳኤ ዕለት ዝኾነ ብሰንበት ዝጾም ሰብ #ሓጢኣተኛ እዩ፣ #ቅፅዓት እውን ይግቦኦ። ኣብ በዓለ ሓምሳ እውን ከምኡ ዝጸውም፣ ሐዘን እንተይኮነስ መንፈሳዊ ታሕጓስ ክንገብረለን ዝግባኣ ናይ ጎይታ በዓላት እውን ሐዘን ዝገብር ከምኡ #ቅፅዓት ይግቦኦ»

ካበይ ዝመፀ እዩ ደኣ ኣብ ዘመነ ፋሱካ "ጾመ ትግራይ" እናበልካ ሰብ ምድንጋር? ኣሽምባይዶ ባዕልና እንእውጆ ጾም እሞ ይትረፍ፣ ዓበይቲ ዝኾኑን ጾመ ድህነት ዝበሃሉን ዓርብን ረቡዕን እኳ ኣብ በዓለ ሐምሳ ኣይንጾምን። ረቡዕን ዓርብን ዘይንጾም ዘለና ነቲ ዝጾምናዮ 40 ጾም ንምክሕሓስ እንተይኮነስ፣ ናይ በዓለ ሓምሳ ልዕሊ ኹሉ ኽቡር ስለዝኾነ እዩ።
📌ፍት.መን.ዓንቀጽ 603:- «ወጾመ ረቡዕሰ ወዓርብ ይጹሙ ወትረ #ዘእንበለ_በዓላት #ወበዓለ_ሐምሳ --- ናይ ረቡዕን ዓርብን አጽዋማትን እውን ብዘይካ በዓላትን #ብዘይካ_በዓለ_ሓምሳን ይጹሙ»

ኣሽምባይዶ ባዕልና ንእውጆ ጾም እሞ ይትረፍ፣ ሓደ ሰብ እንተይተፈለጦ ጾመ አርበዓን ሕማማትን እንተሓሊፈዎ፣ ድሕሪ በዓለ ሓምሳ እምበር ኣብ ውሽጢ በዓለ ሓምሳ ኣይፍቀድን።
📌ፍት.መን.ዓንቀጽ 588:- "ወለእመ ኮነ አሐዱ ውስተ ቀላይ ወኢያእመረ ዕለተ ሕማማት፣ ይጹም #እምድኅረ_በዓለ_ሓምሳ - ሓደ ሰብ ብባሕሪ እናኸደ ሕማማት መዓዝ ምዃኑ ተዘይፈሊጡ (እንተሓሊፉዎ) #ድሕሪ_በዓለ_ሓምሳ ይጹሞ»

ስለዚ ንትንሳኤኡ ዝደፍእን ዝንዕቕን ኣብ ቅድሚ ኣምላኽ ዝተንዓቐን ጾም እናምፃእኹም ንባዕልኹምን ንየዋሃትን ኣይተሕጥዩ!

2⃣ እቲ ኻልኣይ መሰረታዊ ጥፍኣት ድማ፣ ብሱሩ ዘለናዮ ጊዜ ዘመነ ፋሲካ ተዘይኸውን ኸ፣ ባዕልና ዲና ጾም ክንእውጅ ደሊና ነይርና? ናይ ፖለቲካ ጽሑፋትና ሰባት ላይክን ሼርን ገይሮሞ ማለት ኣብ ሃይማኖት እውን ከምኡ ማለት ኣይኮነን። ንክንፈልጦ ግን፣ ጾም ክእውጅ ዝኽእል ሊቀጳጳስ ወይድማ ቅ/ሲኖዶስ እዩ! ካልኦትና ግን እምነትና ንፈልጥ! ብኸምዚ ዓይነት ተራ ወግዕታት ተዘይንደናገፅ። እምነትና ኣብ መጽሓፍ እምበር ኣብ ፌስቡክ ኣይንግበሮ። ናይ ጽባሕ ትግራይ ቤ/ክ እውን ከየጋጥማ ዘስግአኑ እዚ እዩ፣ መፃወቲ መናፍቃን ከይንኸውን።
©Binyam ZeChristos ግንቦት 11 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

✝ ‼️ #የቅዱስ_ያሬድ_ወንጌል!‼️ ✝

✅ ቅዱስ ያሬድ ከመላክእት ዜማ ተምሮ መጥቶ ያተማራቸው ትህርቶችና ዜማዎች በ3 የዜማ ዓይነቶችና በ10 የዜማ ምልክቶች የተቀነባበሩ ሲሆኑ እያንዳንዱም ከወንጌል ጋር እንዲገናኙ በማድረግና በውስጣቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ያዘሉ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል:: እነዚህም ምልክቶች ድፋት፣ ሂደት፣ ቅናት፣ ይዘት፣ ቁርጥ፣ ጭረት፣ ርክርክና ደረት ፤የሊቃውንቱ ደግሞ "ድርስ"ና "አንብር" ሲሆኑ የየራሳቸው ምሳሌና ትርጉም አላቸው::

1⃣ #ድፋት:-ዜማውን ወደታች ረገጥ አድርጎ የሚባል ሲሆን ይህም ወልድ ከሰማያት መውረዱን፣ በማሕጸነ ድንግል ማደሩንና ሰው መሆኑን ያሳያል::
2⃣ #ሂደት:-ሳታቆም አዚም ለማለት ሲሆን የጌታ 3 ዓመት ከ3ወር በስጋ መመላለሱን ደግሞ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ የነበረው እንግልትን ያስታውሰናል::
3⃣ #ቅናት:-የቃልን የመጨረሻ ፊደል ይዞ ቆረጥ በማድረግ ዜማውን አንቅ ማድረግ ሲሆን ጠማማ ቅርጽ አለው::ይህም የአይሁድ ምሳሌ ሁኖ የልባቸውን ክፋት የሐሳባቸውም ጠማማነትን ይናገራል
4⃣ #ይዘት:-በፍጥነት ከሚዜመው ቃል የመጨረሻውን ቃል ያዝ ማድረግን ሲያሳይ ምልክቱም አንድ ነጥብ ናት:: ጌታም ጭማሪ የሌለው ንፁሐ ባሕርይ ቢሆንም በክፉዎች እጅ መያዙን ይመሰክራል
5⃣ #ቁርጥ:-ድምጽን ቀንሶና አምቆ በመያዝ እንደገና ገፋ አድርጎ መጮህን ሲያሳይ ይህም የዮሐንስ ስብከት "ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ይቆረጣል"የሚለውንና የጌታ "ይሰቀል" ውሳኔን ለማሳሰብ ነው::
6⃣ #ጭረት:-አንድ ፊደል ጫር አድርጎ የሚዜም ሲሆን ጠመም ያለ ጎባጣ ምልክት አለው::ይህም ጌታ ራሱን የመቱበት በትረ ሕለትን ለማዘከር ነው::

7⃣ #ርክርክ:-አጭሩን ዜማ ለማርዘም የሚጠቅም ሲሆን ምልክቱም የ2 ነጥብ(:) ነው:: ይህም የጌታ ለሰው ፍቅር ብሎ ያፈሰሰው የደም ነጠብጣብ ያስታውሰናል::
8⃣ #ደረት:-ቃሉን ከፍ በማድረግ አንዷን ፊደል ቆንጠጥ አድርጎ በማንሳት የሚዜም ሲሆን ይሄም የክርስትናችም ኩራት የሆነውን የጌታ ትንሳኤን ብስራት ለመግለፅ ነው::
9⃣ #ድርስ:-የቃልን የመጨረሻ ሆሄ ወደ ኋላ በመሳብ የሚዜም ሁኖ ምልክቱ "ስ" ነው::ይሄም "ስ"ፊደል ቀና ያለ ነውና አዳምና ልጆቹ በኢየሱስ ደም ከባርነት መውጣታቸውን ይናገራል
1⃣0⃣ #አንብር:-አንድን ፊደል ያለ ርክርክና ያለ ተጨማሪ ዜማ ማቆም ማለት ሁኖ ምልክቱ "ር" ነው:: ይህም ር ወደ ቀኝ የተከፈተች መሆን ኢየሱስ በአብ ቀኝ መቀመጡንና አንድም ጻድቃን አግዚአብሔር ቀኝ እንዲቆሙ ለማጠየቅ ነው:: ምልክቶቹ 10 መሆናቸው የ10ቱ ሕዋሳት(5 ሕዋሳተ ሥጋና 5 ሕዋሳተ ልቦና) ምሳሌ ሲሆኑ ሕዋሳቱን የጠበቀ ጌታን እንዲያስደስት በ10ቱ ምልክቶችም መዘመር ጌታን እንዲያስደስት፣ ልቦናን ወደ ጌታ እንደሚያንበረክክ ለማስረዳት ነው:: በዚህም ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ በትምህርትዋ፣ በዝማሬዋና በምልክቶችዋም ሳይቀር ጌታን ትሰብካለች::

💚 #ግዕዝ:- ይህ ዜማ ጠንከር ያለ ሲሆን የአብ ምሳሌ ነው:: ይህም የአብ ቃል ኪዳን መፈጸሙና መጠበቁ ያሳያል::በጾመ እግዚእ(ሁዳዴ) በ5ቱ የመጀመርያ ሳምንታት መዜሙ ደግሞ 5500 ዘመናትን ለማስታወስ ሲሆን ከ2ቱ ዜማዎች ቀድሞ መዜሙ ደግሞ ስመ ሥላሴን ስንጠራ አስቀድመን ስመ አብን ለመጥራታችን ለማሳየት ነው(የስም ቅደም ተከተል ግን ስልጣንን አያሳይም)

💛 #ዕዝል:- ትርጉሙ ታዛይ ተደራቢ ማለት ሲሆን የወልድ ምሳሌ ነው ይህም በድንግል ማሕጸን በማርያምም ጀርባ ታዝሏልና ነው:: በነብያትና በሰሎሞንም ሲዜም 5ቱ መስመሮች በግዕዝ 2ቱ መስመሮች ግን በዕዝል ስለሚዜም ተደራቢ ተብሏል:: በሁሉም የጌታ በዓላትም ዕዝል ቅዳሴ መቀደሱ የወልድ ምሳሌ መሆኑ ነው ይላሉ ሊቃውንቱ::አንድም ዕዝል ዜማ የሚያሳዝን ሲሆን ይህም የጌታ መከራና የቀራንዮ ውሎ የሚያሳዝን መሆኑን ለመግለጽ ነው:: ይሄ ዜማ በ6ኛው ሳምንት(ገብርኄር) መዜሙ ወልደ አብ በ6ኛው ሺ ወልደ ማርያም እንደሆነ ለማጠየቅ ነው::

❤️ #ዓራራይ:-የሚያራራ ማለት ሲሆን ምሳሌነቱም ለሚራራውና ለሚያራራው ለሚያጽናናውም ለመንፈስ ቅዱስ ነው::ይሄ ዜማ ከዕዝል ቀጥሎ በኒቆዲሞስ መዜሙ ጌታ የስጋ ስራውን ፈፅሞ ካረገ ብኋላ ለሐዋርያት መውረዱ ለማሳየት ነው:: የግዕዝ ዜማ ከ2ቱ ጋር አብሮ መዜሙ አብ የወልድ ወላዲ የመነፈስ ቅዱስም አስራጺ መሆኑን ለማጠየቅ ሲሆን ሶስቱም አብረው መገኘታቸው የአንድነታቸው ምሳሌ ነው:: ዕዝልና ዓራራይ ግን አንድ ላይ አለመጣመራቸው ወልድና መንፈስ ቅዱስ በግብር አለመገናኘታቸው ለማመስጠር ነው:: በዚህ መልኩ ቅድስት ቤ/ክ ጌታን በሙላት ታመልከዋለች:: በመጻሕፍቷ ብቻ ሳይሆን በዜማዋና በምልክቶችዋም ሳይቀር ክብርና ጌጥ የሆነላትን ኢየሱስን ትገልጠዋለች ትሰብከዋለች:: ታድያ አሁን ማነው ጌታን አታውቅም የሚላት?ማን ነው ከ 1-30 ቀናት ጌታን አትሰብክም የሚላት? ራሳችሁን ፈትሹ! እኛ ግን ንጉሳችንን ሾመናል!!...ቅዱስ ያሬድ ብዙ ደቀ መዛሙርት አፍርቶ ፣ በተለያዩ ቦታዎች አስተምሮ መጽሕፍትንም ጽፎ ተከዜን በመሻገር "ደብረ ሐዊ" ገዳም በምናኔ እየኖረ በ75 ዓመቱ የዛሬ 1433 ዓመታት ግንቦት 11 ቀን በዳግም ምጸአት ይመለስ ዘንድ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተነጠቀ:: በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን!
❌ #Reposted - ከ6 ዓመት በፊት የተለጠፈ
👇 በቴሌግራም ቻናላ እንገናኝ 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc2WXYXfdEtME6smg

©Binyam ZeChristos ~ ግንቦት 11 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

የትግራይን ሰቆቃ ለመቃወም ትግራይ ውስጥ መኖር የለብህም። ለነገሩ ብትኖርም አፈሙዝ ተደቅኖብህ ዝም ብሎ ማልቀስ እንጂ መቃወም ከየት ይመጣል! የትግራይን ችግር ለማስቆም ትግራዋይ መሆን አይጠበቅብህም። ኢትዮጵያዊ አንዱ ለአንዱ ክብር ነውና! ይህ ሁሉ ግን ስለ ትግራይ ዘግናኝ ግፍ ለመናገር ኢትዮጵያዊም መሆን እንደማይጠበቅብህ በለንደን የግብጹ ጳጳስ አቡነ አንጌሎስ አረጋግጠውልናል። «I pray that this is all fake news, but every report indicates it is not" የሚለው ቃላቸው እንዴት አንጀት እንደሚበላ! የያዙት መስቀል ከተበደሉት ጎን እንዲቆሙ፣ የተሸከሙት ቆብ ለሚገደሉት ምዕመናን ድምፅ እንዲሆንላቸው አውቀዋልና! ሕሊናን የሚያቆስል ግፍ ለመቃወም ከአንገትህ ላይ ሕሊናን መያዝ ብቻ በቂው ነውና!
#StopTigrayGenocide
#I_SrandWithAbuneMatyas

©Binyam ZeChristos ግንቦት 10 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

📌 ንቅዱስ ሚካኤል ምልማን ጌጋ ድዩ⁉️
ቅዱሳን መላእኽቲ ንዓና ድሕነት ንክንወርስ ዘገልግሉ ቅዱሳን ንፁሃን ዓበይቲ ኣሕዋትና እዮም። ስለዚ ድማ ድሕነትና ንክንፍፅምን ናብ ክርስቶስ ንክንበፅሕን ምስኣቶም ንዘራረብ፣ ንዓኣቶም ንሓትት ንልምን። ንምንታይ? ብኣመክንዮ (Deductive Argument) ነቕምጣ!

#premise 1:- ያዕቆብ ምስቲ መልኣኽ ምስተቓለሰ፣ ነቲ መልኣኽ #በኽዩ_ለመኖ። (ሆሴዕ 12:4)
#Premise 2:- ንቀዳሞን ኣቦታትና ብእምነት ንክንመስሎም ቅዱስ ጳውሎስ ይእዝዝ  (ዕብ 13:7)
#Conclusion:- ስለዚ ንሕና እውን ከም ኣቦና ያዕቆብ ንቅዱስ ሚካኤል በኺና ንልምኖ፣ ሓግዘና ኣማልደና ንብሎ‼️
#ሕዳር_ሚካኤል
©Binyam ZeChristos ሕዳር 11 - 2016

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌« ... #የሱዳንና_የአማራ_ኃይሎች ...» ❌
ሱዳንና ኢትዮጵያ ተዋደውና ተከባብረው የሚኖሩ ወዳጅ አገሮች ናቸው:: አማራን ትግራይም ተዋደውና ተከባብረው የሚኖሩ ወዳጅ ክልሎች ናቸው:: የሱዳን ኃይል የሱዳንን ሕዝብ እወክላለሁ ብሎ ሲቆም የአማራ ልዩ ኃይልም የአማራን ሕዝብ እወክላለሁ ብሎ እንደቆመ ነው:: የሱዳን ኃይል "የሱዳን መሬት በኢትዮጵያ መንግስት ተወሮ ተወስዶብኛል" ብሎ ያምናል:: የአማራ ልዩ ኃይልም "የአማራ መሬት በኢትዮጵያ መንግስት (ህወሓት) ተወሮ ተወስዶብኛል" ብሎ ያምናል:: የሱዳን ኃይል ይህን ያህል ጊዜ ጠብቆ አሁን ኢትዮጵያ ተዳክማለች ብሎ ሲያስብ የ«መሬት ይገባኛል» ጥያቄ ይዞ ተነሳ:: የአማራ ልዩ ኃይልም ይህን ያህል ጊዜ ጥበቆ አሁን ትግራይ ሰው የላትም ብሎ ሲያስብ የ«መሬት ይገባኛል» ጥያቄን ይዞ ዘመተ።

የሱዳን ኃይል የፈለገውን የመሬት ጉዳይ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መከራከርንና በሕጋዊ መንገድ ተነጋግሮ ማሸነፍን ችላ ብሎ የተወሰነውን የኢትዮጵያ ክፍል በኃይል መውሰድን ሻተ:: የአማራ ልዩ ኃይልም የፈለገውን የመሬት ጉዳይ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መነጋገርን፣ በጠረቤዛ ዙርያ መወያየትንና በሕጋዊ መንገድ ተነጋግሮ ማሸነፍን ችላ ብሎ የትግራይ የሆነውን ወልቃይት፣ራያንና ሑመራን በኃይል መውሰድን ሻተ::

የሱዳን ኃይል "የኔ ይዞታ ነው" ብሎ ያመነበትን የአማራን ክልል ቦታ በጦር ኃይል ወሮ፣ የተከበረውን የአማራን ገበሬ እያፈናቀለና እየገደለ በማስወጣት ተቆጣጠረ:: የአማራ ልዩ ኃያልም "የኔ መሬት ነበር" ብሎ ያመነበትን የትግራይ ክልል መሬት በጦር ኃይል ወሮ፣ የተከበረውን የትግራይን ሕዝብ እየጨፈጨፈ፣ ገበሬዎችን እየገደለ፣ ሴቶችን እየደፈረና እያፈናቀለ አስወጥቶ ያዘ:: የሱዳን ኃይል ለምን እንዲህ እንዳደረገ ሲጠየቅ "በኃይል የተወሰደብኝን መሬት በኃይል ወሰድኩ" ብሎ ሲል፣ የአማራ ኃይልም ለምን ትግራይን እንደወረረ ሲጠየቅ፣ "ህወሓት በኃይል የወሰደብኝን መሬት በኃይል ወሰድኩ" ብሎ አለ::

ከዚህ ተነስተን የሱዳን ኃይል ወራሪና ጨፍጫፊ ነው ካልን የአማራ ልዩ ኃይልም አስበልጦ ጨፍጫፊና ወራሪ መሆኑን መተማመን ይኖርብናል:: የአማራ ልዩ ኃይል መሬቴ ነው ብሎ ያሰበውን ለመንጠቅ ያደረገውን ወረራ "ልክ ነው! ደግ አደረገ" የምንል ከሆነም፣ የሱዳን ኃይልም መሬቴ የሚለውን ክፍል ለመንጠቅ አማራውን ማፈናቀሉንና መግደሉን "ልክ ነው" እንል ዘንድ ግድ ይላል:: የሱዳን ኃይል ከኢትዮጵያ ይውጣ ብለህ ለመናገር ከደፈርክ፣ የአማራ ኃይልም ከትግራይ እንዲወጣ ትናገር ዘንድ ግድ ይላል::

ሱዳንስ እኛን ስለማትመስል ወረረችን፣ የአማራ ልዩ ኃይል ግን የሚመስለውን የሚቀርበውን የትግራይን ሕዝብ ወሮ ጨፈጨፈ። ከሱዳን ይልቅ አረመኔነቱን አረጋገጠ። እኛ ግን የሱዳንና የአማራ ኃይሎች ወራሪዎች ናቸውና ከወረሩት ምድር ይወጡ ዘንድ እንጮሃለን! ካልሆነም ሱዳንን ከኢትዮጵያ፣ የአማራን ኃይልን ከትግራይ በኃይል እናስወጣቸው ዘንድ እንነሳለን! ተነስተናልም!!
(ከወራት በፊት በብልጽግና አገዛዝ ውስጥ የተጻፈ)

©Binyam ZeChristos መስከረም 10 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❤️ #ጠላትህ_ቢራብ_ኣብላው» [ሮሜ 12:20] ❤️
እህቶችህን የደፈረልህን፣ እናትህን ያረዳትህን፣ ወንድሜችህን ጋዝ አርከፍክፎ ያቃጠለብህን፣ ንብረትን የዘረፈብህን፣ በአየር ደብድቦ፣ በከባድ መሣርያ ቀጥቅጦ ሊያጠፋህ የሞከረውን፣ ፎስፎረስ ጋዝ ረጭቶ ቆዳህን ገሽልጦ ሥጋህን የጠበስህን፣ ልጆችህ ማህፀን ላይ ሚስማርና ድንጋይ የጨመረውን .... አቅፎ ደግፎ ማብላትና ማጠጣት፣ አልብሶ አጉርሶ ማኖር እንዴት ዓይነት የላቀ የሞራል ልዕልና፣ እንዴት ዓይነት የመጠቀ ቅን ልቦና ቢኖረው ነው?! ፍቅር ያሸንፋል!
‼️ #ትግራይ_ታሸንፋለች ‼️

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

😭 #እንዳይደገም_እንዳይረሳ 😭
ይህ የተጋሩ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ታሪክ በሩዋንዳ የሃቱና ቱትሲ የጎሳ መገዳደል ላይ አልተሰማም። ተጋሩን ገድለህ በእሣት የማቃጠል አውሬነት በሂትለር የናዚ ጭፍጨፋ ላይ አልታየም። ይህ ታሪክ የተፈፀመው በትግራይ ክልል ብቻ ነው! ይህ ታሪክ የተፈፀመው በኢትዮጵያውያን ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ነው። ይህ የተደረገው "ሕግ እናስከብራለን" ተብሎ ነው። የገደሉትን ሰው በእስር ማቃጠል በዘመነ ብሉይ እንጂ በሐዲስ እንኳንስ ሲደረግ ሲተረትም አልሰማሁም።

አንድ ነገር አስተዋልኩ:- ትግራይ ላይ ከ50,000 ሺህ በላይ ምርኮኞች አሉ። እነዚህ ተጋሩን በእስር ያቃጠሉ አረመኔዎች የሚበሉትና የሚጠጡት በየሰዓቱ፣ የሚለብሱትና የሚጫሙት በየዕለቱ እየተሰጣቸው እየኖሩ ነው። ከነዚህ አውሬዎች የተወሰኑትም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በእሣት ያቃጠልህን ቀዝቃዛ ውሃ መስጠት፣ ቤንዚን ያርከፈከፈብህን ምግብ ማብላት እንዴት ዓይነት የሞራል ምጥቀት ነው? ይህን ቪድዮ ካየሁ በኋላ እነዚህን ስሜቶች ተሰሙኝ።

⁉️አራጆቻችንን ለምን እንቀልባለን? እኛም እዚህ ያሉትን ለምን በእሣት አናቃጥላቸውም? - ልቦናዬ ግን "የአውሬዎቹ ሥራ በመድገም ከአውሬ መብለጥ አይቻልም" አለኝ።

⁉️በእሣት ማቃጠሉ ቢቀር፣ ስለደፉሯቸው እህቶቻችን፣ የጋለ ብረት ማሕፀናቸው ውስጥ ስለከተቱባቸው እናቶቻችን ስንል ግንባራቸው በጥይት ብለን አናሰናብታቸውም? - መንፈሴ አልተስማማም "ወንድምህን በማዳን እንጂ በመግደል ዕረፍት ኣይገኝም" አለኝ።

⁉️ይህንን እያዩኮ ታድያ "ጁንታ ስለሆኑ ነው፣ ሲጀመር ሰሜን ዕዝን ለምን ነኩ፣ ትግሬ መጥፋት አለበት" እያሉ Justify ለማድረግ የሚደክሙ አጋንንት አሉ። ሕሊናዬ እሺ ኣላለም "ያንተ መልካምነት በሌሎች ጭራቅነት አትመዝነው፣ ዝም ብለህ ስራህን ስራ" አለኝ።

❇️ታድያ ምን እናድርግ? - ሁለት ነገር!
#1ኛው:- ይህ ቪድያ #እንዳይረሳ፣ በሁሉም ማሕበራዊ ሚድያዎች ይበተን፣ ስለዚህ ቪድዮ እንፃፍ፣ እንወያይ፣ እናውግዝ። በተለይ ብትዊተር እንቀባበለው፣ ተናግሮ የማያልቀውን የትግራይን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ዓለም ይወቀው። ያላየ ይየው፣ በሁሉን የዜና ማሰራጫ ይመልከተው። እኛም ገና ለልጅ ልጆቻችን እያሳየንና እየነገርን እናስበዋለን። ለበቀል ሳይሆን ለታሪክ መቼም አንረሳውም!

#2ኛው:- ይህ ቪድያ #እንዳይደገም ደግሞ፣ ይህን ሥራ የሰራውን አረመኔውና ፌሽስቱ የኢትዮጵያ መንግስት ዳግም በኢትዮጵያ ታሪክ ላይመለስ መገርሰስ አለበት። ከትግራይ ተጠራርጎ ስለወጣ አይመለስም ማለት አይደለምና የሄደበት ድረስ ሄደን ማጥፋት ይገባል።

©Binyam ZeChristos መስከረም 8 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❤️ #ወፈነዎሙ_ዕራቆሙ_ለብዑላን ❤️
የዛሬ የቅድስት ሥላሴ በዓል ከዚህ ቪድዮ ጋር ሲመሳሰልብኝ ዋለ። ታላቁ አምላካችን እጅግ ትልቅና የማይደፈረውን የሰናዖርን ግምብ ለማፍረስ፣ መሬት ማንቀጥቀጥ ወይም በኃይለኛ ነፋስ በመግፋት አልያም ደግሞ በደማሚት በመምታት አላፈረሰውም። ማድረግ ቢችልም ግን ለተአምራቱ ሌላ ቀላል መንገድን ፈጠረ። ቋንቋቸው በመደባለቅ ብቻ የማይፈርሰው አፈረሰ። ያንን በጥበቡ የተመካውን ትዕቢተኛውን ሕዝብ ባዶ እጁን አስቀረው። (ዘፍ 11:1-7) ቅድስት ሥላሴ ይህንን ታሪክ ከ4000 ዘመናት በኋላም በኢያሪኮ ከተማ ላይ ደግሞታል። ለዘመናት የማይነካውንና በብዙ መንግሥታት የተፈራውን የኢያሪኮን ግምብ በሠረገላ ብዛት አልያም በሰው ብዛት ሳይሆን በሰው ጩሀት ብቻ አፈር አደረገው። ትምክሕተኛውን የኢያሪኮን መንግስት ተዋርዶ ለእስራኤል እጅ ሰጠ። (ኢያሱ 6:1-20) አምላካችን ገናናነቱን በተናቁ ነገሮች ላይ እያደረገ የተናቁትን ሲያከብር፣ የተዋረዱትን ከፍ ከፍ ሲያደርግ በመጽሐፍም በታሪክም አይተናል። ይህ ቪድዮ ይህንን ታሪክ ያስታውሳል።

በአየር በግፍ ሲደበደብ የነበረ ሰው፣ በመድፍ ሲረሸን የቆየን ክልል፣ በፎስፈረስ አሲድ ሲቃጠልና ሥጋው ይበጣጠስ የቆየን ሕዝብ፣ የአክሱም ጽዮን በዓል ሲጸልይ የታረደው አማኝ፣ ደንገላት ማርያም ለንግስ ሂዶ ታፍሶ የተረሸነው ክርስቲያን፣ እንደ በሻሻ አደረገነው ተብሎ ተንቆና ተጥሎ ይኖር ዘንድ የተገረደበትን ከተማ፣ ሊሰበሰብ የማይችል የተበተነ ዱቄት ነው የተባለለት ሠራዊት፣ 99% ከውጭ መሳርያ ማስገባት አይችልም የተባለለት ኃይል.... ዕውር አሞራን የማይረሳው ጌታ "ስንቁን ከሕዝቡ፣ ትጥቁን ከጠላቱ" አድርጎለት፣ በጠላቶቹ ጫንቃ ላይ ወጥቶ ስታይ "አቤት የሥላሴ ስራ!" ብለህ ከማድነቅ ውጭ ሌላ ምን ትላለህ?

ተአምርና መንክር የሚባለው ደካማ ኃይለኛውን ሲረታ እንጂ ኃይለኛው ደካማውን ሲያሸንፍ አይደለም። እስከ አፍንጫው የታጠቀውን፣ በአየር ኃይል የተደገፈውን፣ ከዓረቦች ድሮን የተሰጠውን፣ ነሙሉ የኤርትራ ሀገር ሠራዊት የታገዘውን፣ በመቶ ሺህ ወታደሮች ያለውን፣ ከባድ መሣርያዎች በየዓይነታቸው ያነገበውን ወራሪውንና ጨፍጫፊውን ኃይል፣ ይህ ምስኪን የገበሬ ልጅ በባዶ ሆዱና በባዶ እጁ ሲደመስሰው ከማየት በላይ ምን "መንክር" ፣ ምንስ ተአምር የሚባል ይኖራል?/ክላሽ ይዞ አየር የሚጥል፣ ጥይት ይዞ ሮኬት የሚማርክ፣ በእግሩ እየሮጠ ታንክ የሚያባርር፣ ከዚህ በላይ ተአምር አለ እንዴ? ይህ በተአምረ ማርያም ቢፃፍ፣ በድርሳነ ሚካኤል ቢሰነድ፣ በዜና ሥላሴ ቢከተብ በዕልልታና በስግደት እንቀበለው ነበር። የእመቤታችንን ግሩም ጸሎት ይህንን ይጠቀልለዋል። "ትዕቢተኞችን አዋረዳቸው፣ ባለጸጎችን ባዶ እጃቸው ሰደዳቸው"

‼️ #ትግራይ_ትስዕር ‼️

©Binyam ZeChristos መስከረም 7 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌ #በእኔ_የደረሰ_በወሎዎቹ ❌
ሁሌም ቢሆን የጦርነት ዋናው ሰለባ ሕዝቡ ነው! ለፍቶ አዳሪው ሕዝብ! አሁን ደግሞ የትግራይ ረሃብና ሰቆቃ ሳይበቃን ወሎ ላይም ረሃብና ስደት እንዳለ እየተነገረ ነው። ሌሎችም "የውጭ ሀገራት ዓይን ለመሳብ እንጂ ረሃብ የለም" እያሉ ነው። ምንም ይሁን ምንም ግን በሕዝብ ጒሮሮ ላይ ቆመህ ድርድር ኣያምርምና ሁላችን እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን ልንረዳቸው ይገባል። የወሎን ሕዝብ ረሃብ የሚያመኝ "ሁሉም ሰው እኩል ነው" የምል ክርስትያን ስለሆንኩ ብቻ ኣይደለም። ነገር ግን በ21ኛው ክ/ዘ ሰው ሰራሽ ረሃብን ላለፉት 11 ወራት ስለማውቀው፣ ወላጆቻቸው የታረዱባቸው ሕፃናት ከወራት በኋላ በረሃብ ሲታመሙ ሲሞቱ ኣይቻለሁና ነው። "ሐዘነ ዘፈተነ የአምር ሐዘነ" እንዲል ረሃብን የሚያውቅ በረሃብ አይቀልድም!

ስለዚህም ገራገሩ የሰሜን ወሎ ወገኔ ክፉኛ የረሀብ አደጋ ተጋርጦበታልና በምንችለው ሁሉ እንድረስለት:: በሁሉም አካባቢዎች በረሀብ ለሚሰቃዩ ወገኖች እንረባረብ:: ረሀብ ጊዜ አይሰጥም። ለወሎ ሕዝብ እርዳታ የምጠይቀው ግን የትግራይ ሕዝብ በሞት እያለቀ ባለበት ሰዓት መሆኑን አውቃለሁ። ማንም የገዛ ቤተሰቡን እንኳን እንዳያግዝ በባንክ ቤቶች ብር እንዳይኖር፣ መብራት እንዳይታይ፣ ስልክ እንዳይሰማ በማድረግ ትግራይን በሞትና በጨለማ ውስጥ ትቷታል። በትግራይ የደረሰውና እየደረሰ ያለው ሰቆቃ ግን በወሎ እንዲደርስ አልፈቅድም! በእኔ የደረሰ ብወሎ ኣይድረስ!

እውነትነታቸው እያረጋገጣችሁ በነዚህ ኣካውንቶች ኣግዙ!
📌ንግድ ባንክ፦ 1000 022 084 473
📌ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ፦ 1600 1400 46 995
📌ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፦ 7000 002 289 429

©Binyam ZeChristos መስከረም 06 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#ሓሽሻም_ሠራዊት - TDF
ሓሽሽ የሚጠቀም ሰው አስቀድሞ ሓሽሹን ለመውሰድም ሆነ ለመተው ነጻ ፈቃድ አለው። ሓሽሹን ከወሰደ በኋላ ደግሞ ያ ሰው ቀድሞ ያልነበረውና ኖሮት የማያውቀውን ኃይል ብርታትና አብርሆት ይሰጠዋል። ሓሽሹን ሲያቆም ደግሞ የነበረው ኃይል መልሶ ይጠፋል፣ ከእርሱም ይርቃል! ስለዚህም ሐሽሹን በእጁ፣ በኪሱ፣ በቤቱ ይይዘዋል! ይህ ዓይነቱን ሐሽሽ ነው እንግዲህ የትግራይ መከላከያ ሠራዊት አንገቱ ላይ ካለው መስቀል ዝቅ ብሎ ተንጠልጥሎ ተገኘ የተባለው። እውነትም ተገኝቷል!

ሕጻን እያለን ስንታመም እናቶቻችን የሚያደርጉት አንድ ነገር ነበር፣ ከቤት ካስቀመጡት ጸበል ወይም ጠበል ያቀምሱናል። ሲጮህ የነበረው ይረጋል፣ ሲቃጠል የነበረው ይበርዳል፣ የወደቀው ኃይል ነስቶ ያንሰራራል! ለሌላ ግዜ ጤናና ደኅነትም ሲባል ጸበሉን በአንገታችን ከመስቀላችን ጋር ይታሰራል። አሁን አሁን በከተማ እየተረሳ ያለ ነገር ቢሆንም በገጠር የትግራይ ቦታዎች ግን ከልጅነት እስከ እውቀት የሚያስሩት፣ ዕቃቤ ርእስ መድኃኒታቸው፣ ኃይል ሰጪ ሐሽሻቸው ሆኖ ይኖራል፣ የቅዱሳኑ ጸበል!

አትሌት መሠረት ደፋር በአንድ ወቅት ሩጫዋን በአሸናፊት ካጠናቀቀች በኋላ ይህንን ልዩ ኃይልና ብርታት የሰጠቻት ስውር ሐሽሽና አበርታች መድኃኒት ማን መሆንዋን ከደርቷ ላይ አውጥታ አሳይታናለች። የእመ አምላክ ሥዕል!! በእውነት ፈጣንዋ ደመና እያለች ማን ሌላ ማፍጠኛ ሐሽሽ ይፈልጋል? ጸሐየ ጸድቅ ክርስቶስ እያለለት ማን ኣደንዛዥ ዕፅ ይጠቀማል? የሸንኮራ ዮሐንስ ጸበልን ይዞ፣ የሽንቁሩ ሚካኤል እምነቱን ቀምሶ፣ የጻድቃኔ ማርያም አፈርዋን ልሶ፣ የደብረሊባኖስ ዳቤ ቀምሶ፣ የሀብተ ማርያም ሎሚ ዳሶ፣ የአክሱም ጽዮን በረከት ተቀብሎ የተነሳን ሰው ማን ያቆመዋል? ኃይሉና ጉልበቱ ከሰማይ እንጂ ከምድር ኣይደለምና ሌላ ሐሽሽ ኣይሻም! ደግሞስ ዓይኑ እያየ እናቱ የታረደችበትን፣ እህቱ በደቦ የተደፈረችበትን፣ የቀደሰበት ቤ/ክኑ ያፈረሱበትን አካላት ለማጥፋት ሌላ ሓሽሽ ያስፈልገዋል ብላችሁ ነው? ሲፈስ ያየው ደም፣ ሲታረድ የሰማውን የጉሮሮ ሲቃ መች ይረሳውና ነው ሌላ ዕጽ ሌላ ሐሽሽ የሚጠቀመው?

እቺን አምበሲትን ተመልከት፣ እህቶችዋ ሲደፈሩ አባትዋ ሲታረድ አይታ የወጣች እህት ናት! ሓሽሽዋ አንገትዋ ላይ ያለው ፀበል ነው! የTDF አባላት በአንገታቸው የታሰረው የጊዮርጊስ ጸበል፣ የአቡነ አረጋዊ እምነት፣ የሚካኤል ድርሳን ሓሽሽ ነው መባሉ ግን እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው?! እንኳንም በሌላ ሐሽሽ አልተጠረጠሩ፣ እንኳንም ከቅዱሳኑ ውጭ ሌላ መድኃኒት አልኖራቸው። እግዚአብሔርን ይዞ የተነሳውን፣ ድንግል ማርያምን ጠርቶ የገሰገሰውን፣ ጊዮርጊስን ይዞ የዘመተውን ግን ልታቆመው አትችልም! እግዚአብሔር ተዋጊ ነውና ስሙም እግዚአብሔር ነውና!

እመቤቴ እመብርሃን ሆይ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለትግራዋይ!

©Binyam ZeChristos መስከረም 04 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

#ኢትዮጵያ - #ተዋሕዶ_በተዐቅቦ
ያለፈው ዓመት ስለ ትግራዋይነትህ መናገር፣ ስለ ኦሮሞነትህ መፃፍ፣ ስለ ሲዳማነትህ መመስከር እንደ ጸረ-ኢትዮጵያ የሚያስቆጥርበት የነ "እንደኔ ካላሰብክ" ዘመን ሆኖ አልፏል። በተለይ ‹የሀገር ፍቅር ያቃጠላቸው› እንዲባሉ፣ ‹የላቁ ኢትዮጵያውያን› እንዲሰኙ "እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ ብሔር የለኝም፣ ብሔራችን ትተን እንደ ኢትዮጵያውያን እናስብ" ሲሉ መስማት ሰልችቶን ነበር። ሀገር እያፈረሱ መሆኑን አለማወቃቸውና አለማፈራቸው እያሳፈረኝ የብሂሉ ስህተት በ፪ ሕጹጻን ምሳሌዎች ስረዳ!

በኦርቶዶክሳውያን የነገረ ሰብእ ሐተታችን፣ ሰው ሥጋና ነፍስ የሚባሉ የየራሳቸው አካልና ባሕርይ ያላቸው ነገሮች ተዋሕደው የሚሰጡት ነገር ነው። ተዋሐዱ ስንል ግን ሥጋ ሥጋነቱን ሳይተው፣ ነፍስም ነፍስነቷን እንደያዘች በመጠባበቅ (በተዐቅቦ) ነው የተዋሐዱት። አንዱ ካለ ሌላው ሰውነትን ኣይሰጥምና ሰውነት የሚፀናው በተዋሕዶና በተዐቅቦ ነው! ሌላ ምሳሌ:- በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርታችንም ክርስቶስን የምንገልፅበት ጽኑ የእምነት መሠረት አለን። እሱም:- ቃል ሥጋ ሲሆን የኣምላክነቱ ባሕርይ ሰውነቱን ሳያቃጥለውና ሳይለውጠው፣ የሰውነት ባሕርዩም ኣምላክነቱን ሳያጠፋውና ሳይለውጠው፣ ሁለቱም በተዐቅቦ (በመጠባበቅ) ፀንተው ግን ደግሞ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ፍጹም ኣምላክ ሆኖ ክርስቶስ ተባለ። ስለዚህም ኢየሱስ በተዋሕዶና በተዐቅቦ ከ2 ባሕርይ 1 ባሕርይ፣ ከ2 አካላትም 1 አካል የሆነ ሥግው ቃል እንለዋለን። "ተዋሕዶ ብቻ" አንልም የመለኮትና የሥጋ መጠፋፋትን (ውላጤን) ያመጣልና። "ተዐቅቦ ብቻ"ም አንልም 2 ባሕርይ 2 አካል (ትድምርትን፣ ቱሳሔን፣ ኅድረትን) ይሰብካልና። ነገር ግን እምነታችን ‹ተዋሕዶ በተዐቅቦ› ነው! ወዳጄ ኢትዮጵያም እንዲያ ነች!

ኢትዮጵያ:- ከብዙ ብሔሮችና ክልሎች ተደምረንና ተዋሕደን የምንፈጥራት የጋራ ማንነታችን ናት! ትግራዋዩ የሌለባት፣ አፋሩ የማይኖርባት፣ ቤንሻንጉሉ የማይከብርባት ኢትዮጵያ የለችም። ኢትዮጵያ ማለት ሁሉም ብሔሮች እኩል የሚታዩባት፣ አንዱ ብሔር ጨቋኝ ሌላው ተጨቋጭ የማይሆንባት፣ የአንዱ ቋንቋ የበላይ የሌላው የበታች የማይባልባት ነች! ስለዚህ እኔ ትግራዋይ የሆንኩ ኢ/ያዊ፣ እሱ ኦሮሞ ኢ/ዊ፣ እሷ አማራ ኢ/ዊት፣ ያኛው ሶማሌ ኢ/ዊ ነው። ብሔሮች ተዋሕደው ኢትዮጵያን ይፈጥራሉ! ሲዋሐዱ ግን በተዐቅቦ ነው! ኣማራው ወደ ኦሮሞ ሳይለወጥ፣ ትግራዋዩ ወደ ኣማራነት ሳይቀየር፣ ቤንሻንጉል በአማራ ሳይጨፈለቅ፣ ሁሉም ባለበት ፀንቶ የሚኖርባት ግን ደግሞ በተዋሕዶ አንድ የሚሆንባት! ኢትዮጵያን ትተን ብሔራችንን ብቻ ጠብቀን (በተዐቅቦ) ከያዝን፣ ተዋሕዶን ትተናልና ኢትዮጵያን እናጠፋታለን። ብሔርን ትተው ኢትዮጵያን ብቻ በአንድነት (በተዋሕዶ) የሚያምኑት ደግሞ፣ መጠባበቅን (ተዐቅቦን) ገፍተዋልና ብሔሮችን የሚደፈጥጡ፣ የቋንቋና የብሔር እኩልነትን የማይቀበሉ ፋስሽትነትን የሚሰብኩ ይሆናሉ። ስለዚህ ትግራዋይነትን የሚያጠፋ ኢ/ያዊነት፣ ኦሮሞነትን የሚፀየፍ ኢ/ያዊነት ኣይኖርም! ካለም መፍረስ ያለበት "ኢትዮጵያዊነት" ነው!

"ብሔር የመጣው በኃጢአት ምክንያት ነው" የሚል የዋህ ደግሞ አለ፣ ኢትዮጵያዊነትና ቻይናዊነት በጽድቅ ምክንያት የመጡ ይመስል! "አዳም ሲፈጠር ብሔር አልነበረውም" የሚለውንማ ተወው! አዳም ብሔር አልነበረውምና ብሔር አያስፈልግም እንዳለ፣ አዳም ሀገር አልነበረውምና ኢ/ያ አታስፈልግም ማለቱ እንደሆነ ገና አልገባውም! ወዳጄ ‹ኢ/ያ እንጂ ብሔር ኣያስፈልግም› የሚል ቢኖር:- ሰውነትን እንጂ ሥጋና ነፍስን አልቀበልም የሚል ሰነፍ፣ ስለ ኢየሱስ እንጂ ስለ ትሥብእትና መለኮት አያገባኝም የሚል መናፍቅ ይመስላል። ዋናው ጉዳይ "ብሔርህን ለምን ተጠቀምክበት?" የሚለው ነው። ተጨማሪ ቋንቋ ለማወቅ፣ ሌላ ባህልን ገንዘብ ለማድረግና የልዩነትን ውበትነት ትረዳበት ዘንድ ከሆነ ብሔር ቅዱስ ነው። ለዘረኝነት ከሆነ ግን ሰይጣናዊነት ነው። ሀገርም እንደዛው ነው እንደ አጠቃቀምህ! ኢትዮጵያዊነትህ ‹የተለየሁ ሕዝብ ነኝ› ለማለት፣ ‹አዳምኮ ኢ/ያዊ ነበር› ብሎ ለመፎከር፣ ‹ከኬንያዊው እበልጣለሁ ከኡጋንዳዊው እልቃለሁ› ለማለት ከሆነ ግን ኢትዮጵያዊነትህ መርገም ይሆናል!

ስለዚህ ብሔራችን ከሀገራችን፣ ሀገራችንም ከብሔራችን አስተባብረን በተዋሕዶና በተዐቅቦ እንኖራለን! ኢትዮጵያ በሁላችንና የሁላችን ናት! ሥጋን አልያም ነፍስን የሚጥል ሁሉ "ሬሳ"ን እንጂ ሰውን እንዳማያገኝ ሁሉ፣ ትሥብእትን ወይም መለኮትን የሚጨፈልቅ ክርስቶስም ሐሰተኛ ክርስቶስ እንደሆነው ሁሉ፣ እንዲሁ ለትግራዋይ የማትሆን፣ ኦሮሞነት የማትቀበል፣ አማራውን የምትገፋ፣ ለብሔር ብሔረሰቦች ህልውና የማትቆም ኢትዮጵያ ልትኖር አትችልም! ብትኖርም እንድትቀጥል አንፈቅድላትም
©Binyam ZeChristos መስከረም 2 - 2014

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #ሰማዕታተ_ትግራይ ‼️
ተጋሩን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የሚደረው ስራ ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው። እንሆ "ከጎኑ ጋር ነኝ" ያልከው የዓብዪ መከላከያ ኃይል፣ ከትናንት በስትያ ነበር ከመቐለ ቅርብ በምትገኘው #ቶጎጋ በንትባል አንዲት የገጠር ከተማ ላይ በሞትና በሕይወት መሃል ያለችውን ሕይወታቸውን ለማስቀጠል "የየማክሰኞ ገበያ" ላይ ሊገበያዩ የወጡትን ንጹሓን ዜጎች ላይ 2 ጊዜ የአየር የቦምብ ውርወራ በማድረግ ብዙ ተጋሩ ደማቸው ፈሶ፣ ስጋቸው ተቆራርሶ፣ አጥንታቸው ተበታትኖ ደመ ከልብ ይሆኑ ዘንድ ተወስኖባቸዋል። ሕጻናትና ሽማግሌዎች አብረው የተቀበሩበት አሳዛኝ ክስተት! ወጣቶችና ደናግል ደማቸው የተደባለቀበት የደም ቀን!

የዓብዪ መከላከያ ወታደሮች ግፋቸው በዚህ ብቻ ኣላበቃም። ከገበያው መሃል የልብ ምታቸው ያልቆመውን፣ እስትንፋሳቸው ያተቋረጠችውን ለማፋን አምቡላንሶች ወደ ቤታው ጎረፉ። አምስት ኣምቡላንሶች ትናንት ወዲያውኑ ወደ መቐለ ዓይደር ሆስፒታል ይዘው ሲመጡ፣ የተቀሩትን ግን እንዳይመጡ አምቡሌንሶቹን አግደው አሳደሯቸው። የመንግስታችን ግፍ ይጋለጣል ብለው በመፍራት። በዚሁ ምክንታይ ሕክምና እንዳያገኙ ታግደው፣ እኛም የቻልነውን እንዳናግዛቸው ተከልክለን፣ አምቡላንስ ውስጥ ነፍሳቸው የወጣች ብዙዎች ናቸው! ደማቸው ፈሶ ካለቀ በኋላ ዛሬ እንዲያልፉ ተፈቅዶላቸው 11 ኣምቡላንሶች መጥተዋል። ኣዝላው የወጣችው እናቱ መንገድ ላይ ቀርታ፣ እግሮቹ ተቆርጠው፣ በጎረቤት ሰው ታዝሎ የሚመጣው ሕጻን አንጀት ይበላል። ከፍንዳታው የተነሳ ቤቱ ፈርሶ፣ ወንድሞቹ እዛው ተቀብረው ሲቀሩ፣ እሱ ግን ሁለት እግሮቹ ተሰብረው እንደ ሬሳ ከድንጋይ ክምር ተጎትቶ የወጣው ልጅ ደም ያስለቅሳል!

ከሰውነት ተራ የወጣው፣ ሕሊናውም የሸጠው ሰው "ጁንታ ስለሆኑ ነው" የማለት አረመኔያዊ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ፣ እኛ ግን እናሸንፋለን! ትግራይ ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የቀራት!

❌ #ትግራይ_ትስዕር ❌
©Binyam ZeChristos ሰኔ 17 - 2013 ዓ/ም

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ #ትግራይ_ነዋ ፩ ‼️
📌እቺ እንቡጥ ኣበባ፣ እቺ የነገ የሀገሪቱ ተስፋ፣ እቺ ንጹሕ ሕጻን ቤቲ ትባላለች። የ6 ዓመት ልጅ ሕፃን! በአዲስ አበባ፣ በባሕርዳር፣ በአዳማ፣ በሐሳና በሌሎችም እንዳሉ እኩያዎችዋ መጫወትና መሳቅ፣ ማደግና መመርን ምትፈልግ ምስኪን የአክሱም (ማህበር ዴጎ ገዳም አካባቢ) ልጅ ነበረች። ታሕሳስ 1 ቀን ግን ሰማይና ምድሩን በሚያናጋው የከባድ ብረት ውርጅብኝ፣ የምትኖርበት ቀዬ አመድ አደረገው። በዚያች የጨለማ ቀን፣ በዚያች የተረገመች ቀን፣ እህ ብላ አምጣ የወለደቻት የእናቷ አንገት ተቆርጦ፣ አቅፈውና አዝለው እያባበሉ ያሳደጓት የአያቷ ጭንቅላት ፈርሶ፣ በስስት ዓይን ስታየው የኖረችውን የታናሽ ወንድሟ ሰውነት ተቦጫጭቆ ከዓይኗም ከሕይወቷም ለዘላለም የወጡበት ቀን ነበር። እሷም ቢሆን ዳግም እንደ ልጅ እንዳትቦርቅ፣ በእግሯ እንድትራመድ ሁለት እግሮችዋ ተቆርጠው በደም ተለውሳለች። አባትዋና ሌሎች ሰዎች የተረፈ አካልዋን አፍሰው፣ የሞቱትን ቀብረው ይዘዋት ወደ መቐለ መጡ።

📌በመቐለ ከሞት ተርፋ፣ በስንት መከራ ድና፣ አሁን በፊዝዮተራፒ ማዕከል ትገኛለች። ፈገግታዋ ላይ የታማቀ የሐዘን እሣት፣ ሳቋ ላይ የሚንተከተክ ለቅሶ ይታያል። ብመራራ ሐዘን ውስጥ ሆኖ፣ ዓይን ዓይኗን እያየ የሚያጫውታት ምስኪን ኣባትዋ ብቻ ነው! ይህ ሁሉ ሲሆን ኣቤት የምትለው አካል፣ የምትከሰው ወንጀለኛ፣ የምትጮህለት መንግስት የለም። ለምን? ምክንያቱም ይህ #ትግራይ_ነዋ!

❇️[እንሆ ዛሬ ትግራይ ላይ ጦር የተመዘዘበት፣ እሳት የተለኮሰበት፣ የሕፃናት ለጋ ሰውነት መቆራተጥ፣ የእህቶች መደፈር፣ የእናቶች መታረድ፣ የገዳማት መዘረፍ፣ የአድባራት መፍረስ የተጀመረበት #ሁለት_መቶኛው ቀን። 200 ያላቆሙ የሰቆቃና የመከራ ቀናት!]❇️

©Binyam ZeChristos ግንቦት 14 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌ #ማየ_ሰሊሆም_ዕውር ❌
ልዕሊ ኽሳድና ለሎ ርዕሲ "ዙ ጾም መንዩ ኣዊጁዎ?" ኢሉ እንተሓቲቱ ይሱርሕ ኣሎ ማለት እዩ። ዝተውሃበና መልሲ ድማ «መናንያን አበው፣ ካህናትን መናእሰይን» ጥራይ ትብል። እስኪ ዋላ ላጾምናማ ነዚኣተን ንጠይቕ!
1) #ንምንታይ_መንነቶም_ዘይተገለፀ:- ክሳብ ሐዚ ደጋጊምና "መን ኣቦ ኣዊጁ?" ኢልና ዋላ ተጠየቕና ዝናገር ሰብ ግን ኣይተረኽበን። ቶም ኣቦታት ደኣ እንመን? ኣበይ ዘለዉኸ እዮም? እቶም ካህናት ኸ?ቶም መናእሰይ ኸ? ኣድራሻ ዘይብሉ መንእሰይ፣ ካህንን ኣቦን ኣሎ ድዩ? ናብቲ ዓብዪ ቅዱስ ገዳምና ደብረ ዳሞ ዘለዉ ኣቦታት ሓቲትና "ኣብ በዓለ ሓምሳ ዝጽወም ጾም የለን፣ ኣይኣወጅናን" ኢሎም። እምበይትና ማርያም ብእግራ ዝረገፀቶ ናይ ዋልድባ ገዳም ዓበይቲ መነኮሳት እውን "ብሱሩ ከምዚ ዝበሃል ጾም ኣይንፈልጦን" ካብ በሉ፣ ካብዞም ቅዱሳን ኣቦታትና ዝበልፅ መናኒ ካበይ እዩ መፂኡ ጾም ዝእውጅ? ብሱሩኸ እቶም ኣዊጆም ዝተብሃሉ መናንያን መንነቶም ዘይተነገረ፣ ናይ ፈጠራን ሕሾትን ኣዋጅ ስለዘኾነ ዶ ኣይኮነን?

2)#መናእሰይ_ጾም_ይእውጁ?:- ብሱሩ ናይ መናንያን ኣበው ጾም እንድሕር ዝእወጅ ኾይኑ ምስ መናእሰይ ድዮም ዝማኸሩ ኾይኖም? እቶም መናእሰይኸ መን እዩ ኣዋጂ ጾም ገይሩዎም? ኣክስዮን ማሕበር ምዃኑ ድዩ ቅዱሳን ኣቦታት ምስ ንከተማ ወፂኦም ምስ መናእሰይ መኺሮም ዝውስኑ? ምስ መናንያን መኺሩ ኣብ ልዕሊ መላእ ተጋሩ ምርመናን መነኮሳትን ጳጳሳትን ጾም ዝእውጅ መንእሰይ ከመይ ዝበለ መንእሰይ እዩ ደቀይ? ኤህ!

3)#ንኣቦታት_ኣይትፃረፉ:- እቶም መን ምዃኖም ዘይተፈለጡ መናንያን እንድሕር ጾም ዝእውጁ ኾይኖም፣ ጾም ክእውጅ ዝኽእል ናይ ክህነት ስልጣን ዘለዎ ሊቀጳጳስ ጥራይ ምዃኑ ስለዝፈልጡ፣ ናብቶም ሉቃነ ጳጳሳት መልእኽቲ ብምልኣኽ "ኣምላኽ ነጊሩና እዩሞ ጾም ኣውጁ" ምበሉ። ነገር ግን ካብ ናብ ሉቃነጳጳሳትስ ናብቶም ናይ ፌስቡክ ጸሓፍቲ ድዮም ደዊሎም? እዚኣስ ነቶም መናንያን "ሥርዓት ዘይገልጡ፣ ንጳጳስ ዝንዕቑ" ኢልካ ምፅሬፍ ዶ ኣይትኸውንን? ብሱረ ኣብ ፌስቡክ ንመጀመርያ ጊዜ ዝለጠፋ ሰብ ትፈልጡዎዶ? እስኪ ዋሌ ብውሽጢ "ካብቶም ሊቀጳጳስ ንላዕሊ ዲኼ ንስኻ ቐሪብካዮም ንዓኻ ነጊሮሙኻ? ኢልኹምማ ጠይቕዎ።

4) #ብዘይ_ሥርዓት_ንጹም?:- ሓደ ሓደ የዋሃት ድማ ኣብ በዓለ ሓምሳ ኣይፅወምን እንተበልና " ንክፀውም ዶ ሥርዓት የድልየኒ እዩ?" ይብሉና። እስኪ ንጠይቆም:- እቲ ጾም ልምንታይ ካብ ግንቦት 17 ይጅመር? ምእንታይ ጎይታ ክቕበለናስ ካብ ቀዳምን ሰንበት ጀሚርና ጾምና ዘይንውዕል? ከምዚ ኢሎም ይምልሱ "ቀዳምን ሰንበትማ ብሥርዓት ኣይፅወማን"። ወዮ ሕጊ ኣፍሪሶም እናፆሙስ፣ ብሕጊ ክጾሙዎ ይደልዩ?! ኻሊእ ድማ ንሕተቶም! «በሊዕና ዲና ከም መናፍቃን ንጾሞ፣ ወይስ ጥራሕ ኸብድና? ምሸትኸ ዘይንበልዖም ምግብታት ኣለዉዶ?» መሊሶም ባዕሎም " ብሥርዓት ባ/ክ በሊዕኻ ጾም የለይ፣ ናይ ሥዕረት እውን ኣይብላዕይ» ብምባል ባዕሎም ዝነዓቕዎ ሥርዓት ቤ/ክ ዳግም ክኽተልዎ ይደልዩ! ሕንግርጢጥ እዩ ነገሩ!

5)#እዚ_ድዩ_መጨረሻና:- ብሱሩ ግን ኣብ ፌስቡክ ልፀሓፈ ኹሉ ድዩ ክገንሐና? "ኣቦታት ተናጊሮም፣ መናንያን ኣዊጆም፣ ፈለስቲ ኣዚዞም" ኢሉ ዝተናገረ ሰብ ኹሉ ድዩ ክገንሐና? ፅባሕ ኸ "ኣቦታት ኣዚዞም እዮምሞ በዓል ከይተኽብሩ፣ ቁርባን ከይትቕበሉ፣ መቅደስ ምስ ጫማ እተዉ ..." ዝብሉ ከምዘይመፁን ንሕና እውን ክርስቶስ ብደሙ ዘጥረያ ቤ/ክ ገዲፍና ምስኦም ከምዘይንውሕን ታይ መረጋገፂ ኣለና። ኣቦታት ከምዚ ይብሉ «ማየ ሰሊሆም ዕውር፣ ሃበ ወሰድዎ ይሐውር - ሰሊሆም ኣብ ትበሃል ቦታ ዘሎ ዕውር ማይ፣ ናብ ዝወሰድዎ ይኸድ"። ዝመፀ ሰብ ናብ ቃሕትኡ ዝወስዶ ሰብ ድማ "ማየ ሰሊሆም" ይብሉዎ። ንትግራይ ኣብ ጾመ ነቡያትን፣ ጾመ 40 እናጾምና ነይርና፣ ሐዚ እውብሖን ድሕሪ በዓለ ሓምሳ ክንጾም ኢና!

©Binyam ZeChristos ግንቦት 14 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️ 💚 #አስደናቂው_እውነተኛ_ታሪክ💚 ‼️
(የግንቦት 12 ~ ገድለ ተክለ ሃይማኖት)
✝ስጋቸው ከነፍሳቸው ከተለየ ከ57 ዓመታት በኋላ የካቲት 19 በጸሎት ላይ ለነበሩት ለአቡነ ሕዝቅያስ ነበር የተገለጡት:: አቡነ ተ/ሃይማኖት! እንዲህም አልዋቸው:-«ጌታ የገባልኝን ቃል ይፈፀም ዘንድ ስጋዬ የሚፈልስበት ደረሰ ቀኒቱንም በምስጋናና በጸሎት መንፈሳዊ በዓል አድርጉ (በመብል በመጠጥና በዘፈን እንዳይል ልብ ይሏል) እኔ ኃጥኡ ብሞትኩበት ቀን እንደነበረው ምስጋና አቅርቡ! (ትሑቱ አባታችን ገነትም ሁነው ራሳቸውን ኃጥእ ሲሉ እኛ ግን...ማን አስተዋለ ከትውልዱ?) ስለዚህም ሂደህ ለ12 መምህራንና (ኢ/ያን የጌታ ለማድረግ የተካፈሏት የተክልዬ ደቀ መዛሙርት) ለልጆቼ ግንቦት 12 እንዲያከብሩ ንገራቸው::በፍልሰቴ ቀን አባቴ አባቴ የሚለኝ ሁሉ ይምጣ፤ ያኔ እኔ ወዳጄ ቅ.ሚካኤልና ልጄ ፊልጶስ (የተክልዬ ደቀ መዝሙርና የደብረ ሊባኖስ 3ኛው እጨጌ) አብረን መጥተን እንባርካለን:: ምልክት ይሆንህም ዘንድ በምመጣበት ጊዜ የጠፋው የመቅረዙ ይብራት ይበራል» አለው! (በእውነት ቅዱሳን ሲጠሩ ጨለማው ልባችን ይበራል የደረቀው ማንነታችን ይለመልማል:: ተ/ሃይማኖት ፀሐይ ነፍሴን አደራ በሰማይ... ሲሉ እናቶቻችን ለካ አንትሙሰ ብርሃኑ ለዓለም ያለውን ቢያነቡ ነው (ማቴ5-5፥14)

✝ከዚህም በኋላ አቡነ ሕዝቅያስ ከተክልዬ ዘንድ ተባርኮ ሄደ:: በአራቱም አቅጣጫ ላሉት 12 መምህራንና ለክርስትያኖች ሁሉ፣ አባታችን የነገሩትን የፍልሰታቸው በዓል ስለማድረግ ወደ ፍልሰቱ በዓል ያልመጣም በዚያች ቀን (በሰማይ ለማማለድ) አባቴ እንዳይለው፣ እርሱም ልጄ እንዳይለው ጨምሮ መልእክቱን ላከላቸው! (ችግር ካላጋጠመው በስተቀር በሰርጋችን ያልተገኘውን በሐዘናችንም ያልደረሰውን ሰው መች ዘመድ እንለዋለን? ይህም መምጣት እየቻለ በንቀት ወይም በክህደት ላልመጣ ልጄ እንደማይለው ለማስረዳት ነው)

✝የአባታችን የፍልሰት በዓልና የሚካኤል በዓልም እንድ ሆነ:: ይህም የቅርብ ወዳጃቸው ስለነበረና አስተምረው ሲያቆርቡም 'ተንሥኡ' ሲልላቸው 'ሰላም' እያሉ፥ ሰማያዊ ሕብስት ከሰማይ እያወረደላቸው (በሲና በረሃ ያደረገውን መድገሙ እንደሆነ ልብ ይሉዋል)፣ እርሳቸው እየፈተቱ አብረው ይሰሩ ስለነበረ ነው::በረከታቸው ይድረሰን! እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም ከ4ቱ ማዕዘን የተክልዬ ወዳጅ የተባለ ሁሉ መጣ:: 12ቱ መምህራንም ያባታችንንን ስጋ ከዋሻው ለማውጣት ሲገቡ በሁለት ጎን መስቀል ተተክሎ፥ አስከሬኑ በዕለቱ እንደተገነዘ ትኩስ ሬሳ ይመስል ነበር። ደስ የሚል ሽታም ነበረው! (የቅዱሳንን አንዲት አጥንት የማይረሳ ጌታ በኤልሳዕም አስከሬን ሙት ያስነሳ አምላክ በእውነት ይህን አደረገ)

✝ከ12ቱ ደቀመዛመርት አንዱ የሆኑት አቡነ አኖሬዎስም መስቀሎቹን ለአቡነ ሕዝቅያስ በመስጠት በመንፈሳዊ ቅናት ተሽቃዳድሞ ያባታችንን ስጋ በእጃቸው ሲያነሳው የተክልዬ አጥንታቸው ረገፈ! ይህም ዘመናቸው ሁሉ በጾም ስላሳለፉ ነበር:: በዚህም ጊዜ ሁሉም ደነገጡ ፈሩም:: የተክልዬን አጥንት ለማንሳት ሁሉም እየተጋፉ በጭንቅ ተሽቀዳድመው መጡ:: ያኔ ነበር በመካከል የነበረው አንድ ወንድም ከሰው ብዛት የተነሳ ጉልበቱን ረግጠዉት ቢሰበርም ወዲያውኑ ‹የጻድቅ ሰው ጸሎት› ብለው በእምነት የተክልዬን የመግነዙን ጨርቅ ቢያስነኩት ወድያውኑ አጥንቱ ፀናለት! በዚህም ተ/ሃይማኖትን አከብሩ ይህንንም ክብር ላደላቸው ለክርስቶስ ኢየሱስ ምስጋናን አቀረቡ:: የጻድቁን ስጋ ካወጡት በኋላ ወደ ቤ/ክ አምጥተው (አፍልሰው) 3 ጊዜ መቅደሱን አዙረው በዓሉንም አባታችን እንዳሉት በዝማሬና በምስጋና አክብረው ወደ ውስጥ አስገቡት:: በዚህም ጊዜ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ተ/ሃይማኖት አስቀድመው እንዳሉት ጠፍቶ የነበረው መብራት ቦግ ብሎ በራ:: ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጃቸው ከአቡነ ፊልጶስ ጋር በመሆንም በዓሉን ያከብር ለነበረው የተክልዬ የፀጋ ልጅ ሁሉ ተገልጠው ይባርኩ ነበር::

✝በገድሉ ደም የዋጀንን፥ ይቅር የሚያሰኘንን፣ ኃጢአታችንንም የሚያቃልልልንን ይህንን አባታችንን ለሰጠን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና እናቅርብ! ('በገድሉ ደም' ሲል ደም ከሰውነት እንዲወጣ ከገድሉ የሚወጣዉን ቃል ያመለክታል! አንድም 'ደም' ያለው ጌታን ለማንሳት ነው::ጌታ በደሙ እንደገዛን የርሱም እንዳደረገን ለማጠየቅ/1ኛ ቆሮ 6፥19/ አባታችን ተ/ሃይማኖትም በዜና ገድላቸው በብዙ ፍቅርና ትሕትናቸው የርሳቸው ስላደረጉን ስለማረኩንና እንሆ ዛሬ በግንቦት 12 በዓለ ፍልሰታቸውን እንድናከብር ስለሰባሰቡን ለማሳየት ነው)...የተክለ ሃይማኖት ልጅ መሆን በእውነት መታደል ነው!! (በዚህች ዕለትም የታላቁ ሊቅና ቅዱስ አፈወርቅ ዮሐንስ በዓል ነው)
❤️...... #ይፍቱኝ_ተክልዬ !! ......❤️

👇መንፈሳዊ ጽሑፎችን በዚህ ቻናል ያግኙ👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc2WXYXfdEtME6smg

©Binyam ZeChristos ግንቦት 12 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

❌#ንብዓት_ራሔል_መዝሙር_ምረቓ❌
ሰንበት ዋላሓደ ሰብ ኣይተርፍን! ኣብ መቐለ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ አዳራሽ ናይ ዲ/ን ዘማሪ ክብሮም መሓሪ ቁ 2 መዝሙር ሲዲ ክንምርቕ ኢና። ንብዓት ትግራይ ብንብዓት ራሔል ተጠቕሊሉ ቐሪቡልና ኣሎ።
መዓዘ⁉️:- ግንቦት 15 ሰንበት 8:00 ሰዓት።

በረኸቱ⁉️:- ሙሉእ ኣታዊኡ ንዝተሰደዱ ተጋሩ ኣሕዋትና።

መእተዊ⁉️ ናይ 150፣ 200 300 ቅርሺ ይኬት ተዳልዩ ኣሎ። ብዝኸኣልናዮ መጠን ትኬት ብምግዛእ፣ ናይ መዝሙር ካሴት ብምዕዳግ፣ ንዲ/ን ክብሮም እውን ብምብርትታዕ፣ ከምኡ ድማ ንዝተሰደዱ ወገናትና ንደግፍ።
✝ ንብዓት ራሔል ✝

❗️ኤርሚያስ ትናገር ናይ ራማ
ራሔል ብብኽያት ደኺማ
ዋይዋይታ ኾይኑ ሰቖቓ
ምድባስ ኣብያ ስለ ደቃ❗️

ራሔል ንብዓታ በፂሑ ኣብ ሰማያት
ራሔል ሓዘና በፂሑ ኣብ ጸባኦት
ይፅውዕ ይፅውዕ ለእግዚአብሔር

ኣብ ማእከል ጎደና ውላዳ እንትመውት
ብግፍዒ እንትትግሰስ ጓላ እናበኸይ
ሽማግለታታ ክንዲ ዝጥወሩ
ሕፃናት ኣቢዶም ንብዓት ተደረሩ
ዝኾነና ረአ ሕሰብ ዝበጽሐና
ኦ እግዚአብሔር ፍረድ ገጽኻ መልሰልና

መቅደሳ ገዳማ ብኣዋጅ ፈሪሱ
ናይ ካህናታ ደም ፈሲሱ
እንታይ ተሪፉዋ ከመይ እፎይ ትበል
ብሓዘን ተሃስያ ወላድ መኻን ራሔል
ዝኾነና ረአ ሕሰብ ዝበጽሐና
ኦ እግዚአብሔር ፍረድ ገጽኻ መልሰልና

ደቃ ተሰዲዶም ፎቖዶ በረኻ
ደም ጨቅያ መሬት ራሔል ተሃዊኻ
ፈተውታ የለውን ኣብ ጊዜ ስቓያ
ሓደ ጥራሕ እዩ ካብ ሰማይ ዝረአያ
ጎይታ ጥራሕ እዩ ካብ ታማ ዝረአያ
[ ትግራይ ኣብዛ መዝሙር ተፈቲላ ኣላ ]

©Binyam ZeChristos ግንቦት 11 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

‼️... #ፃውዒት_ዘተ_ንተጋሩ_ኦርቶዶክሳውያን... ‼️
(ኣብ ጉዳይ አሰያይማ መንበር)
ኣብ ቐረባ ጊዜ ነገራት ክጠናቐቑ፣ ትግራይ እውን ሃገር ናብ ምዃን ገፃ እያ! ሃገር እንተኾይና ድማ ግድን ናይ ባዕላ ቤተ ክህነት፣ ቅዱስ ሲኖዶስን ፓትርያርክን ከድልያ እዩሞ ክተዋቕር እያ። እቲ ኹነታት ምስተፈጥረ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ቅንዕ ኢላ ምዕመናና ንከይትጓሲ፣ ነስንሳትና እናተኸራኸርና ንጸላእቲ ቦታ ንዘይምሃብ፣ ሎሚ ኣቐዲምና ተዛቲናን ፍታሕ ሓሲብናሉን ንክንሓድር፣ እቲ ነገር ምስተፈጥረ ድማ ዝድንግፅ ምዕመን ንከይህሉ ኢና ሐዚ ንምዝታይ ነቕርቦ ዘለና። ናይ ትግራይ ቤ/ክ መንበራ ብመን ስም ይፀዋዕ? ቅድሚ ናብቶም ካልኦት ዓበይቲ ዛዕባታት ምኻድና በዚ ቐሊል ዛዕባ ንጀምር።

ኣብ ሓንቲ ሃገር ዘላ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ መበቆል ክህነታ (መንበራ) ብዝደለየቶ ጻድቕ ክትፅውዕ ትኽእል እያ። እተን ክልተ ረቋሒታት ድማ
1)ጀማሪ ክርስትና:- ኣብታ ሃገር ንመጀመርያ ጊዜ ክርስትና ዝሰበኹ ቅዱሳን፣ ኽብሪ ንምሃብን ንምዝካርን ብምባል በቲ ጻድቅ ይስየማ። ንኣብነት:- ግብፂ ቤ/ክ - ናይ ሐዋርያ ማርቆስ መንበር፣ ህንዲ ቤ/ክ - ናይ ሐዋርያ ቶማስ መንበር ወዘተ።

2) እቲ ኻልኣይ ድማ ኣብታ ሀገር ዓብዪ ስራሕ ብምስራሕ ውዕለታ ዝወዓለ ጻድቕ (ብፍላይ ድማ ክብር ሃገር ዝቦቐለ) ስሙ መጸውዒ መንበራ ትገብሮ። ንኣብነት:- ሶርያ - ዋላኳ ክርስትና ዝሰበኸላ ቅ/ጴጥሮስ እንተኾነ መንበራ ግን በቲ ዓቢዪ ጻድቅ ብቅዱስ ያዕቆብ ሶርያዊ (St Jacob ትፅዋዕ። አርመንያ ቤ/ክ ድማ ዋላኳ ክርስትና ብሐዋርያ በርተለሜዎስን ታዴዎስን እንተተሰበኸላ፣ መንበራ ግን ብቅዱስ ጎርጎርዬስ (st Gregory the Illuminator) ትፅዋዕ። ናይ ኢ/ያ ቤ/ክ እውን ዋላኳ ክርስትና ብሐዋርያ ማቴዎስን ብሕፅው (ባኮስ) ደሓር ድማ ብአባ ሰለማ እንተተሰበኸ፣ መንበራ ብቅዱስ ማርቆስ ትሰሚ ዝነበረት እንትኸውን፣ ደሓር ግና ብ1950ታት ናይ ባዕላ መንበር እንትምስርት፣ በቶም ንሀገርናን ንቤ/ክን ካብ ጥፍኣት ዘድሐንዋን ኢ/ያ ጻድቕ አቡነ ተክለሃይማኖት ተሰምየት።

ስለዚ ንትግራይ በየናይ ረቋሒ ተጠቒምና፣ በየናይ ጻድቕ ስም ንስመዮ? ንምይይጥ ክጠቕመና መልዐሊ ነጥብታት ከቐምጥ።
1) ናብ ትግራይ አቐዲሙ ወንጌል ብዘምሀረ ኣቦ እንተይልና:- ሐዋርያ ማቴዎስን ባኮስን እዮም ዝኾኑ። ስለዚ ዘመንበረ ማቴዎስ፣ ዘመንበረ ሕጽው (ባኮስ) እዩ። ተደሊና እውን ንአቡነ ሰላማ ንምዝካር እንተደሊና ዘመንበረ ሰላማ ንብሎ።

2) ኣብ ትግራይ ዓብዪ ስራሕ ብዝሰርሑ ጻድቕ ስም ንምስያም ተተደልዩ ድማ፣ ከምኒ አቡነ አረጋዊ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አቡነ ተክለሃይማኔት፣ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ወዘተ ምጥቃስ ይከኣል።
❌ እዚ ኹሉ ዝኸውን ግን ትግራይ ሀገር ምስኮነት እዩ፣ ተዘይኮይኑ ግን ፓትርያርክና አቡነ ማትያስ፣ ሲኖዶስና ቅዱስ ሲኖዶስ፣ መንበረና መንበረ ተክለሃይማኖት ብዝብል ይፀንዕ!❌

ስለዚ በየናይ ምክንያት ተጠቒምና፣ መንበርና እንታይ ክስመ ኣለዎ ንብል?

[ኣብዚ ዘተ ዝሳተፉ ኣቐዲሞም ኦርቶዶክሳውያን ዝኾኑ፣ ኣብ ገዳይ ቤ/ክ ኣፍልጦ ዘለዎም መንፈሳውያን፣ ብፍልጠትን ብመንፈስን ክዛተዩ ዝኽእሉን ጥራይ እዩ። ክሳተፉ ዝኽእሉ መምህራን እውን ምፅዋዕ ይበረትታዕ! ካብ ርእሲ ወፃኢ ክርክርን ፀርፍን፣ ወይድማ ፀቢብ ብሔርተኝነትን ዘርኣውነት ተቐባልነት ስለዘይህልዎ ፅሑፉ Delete ይኸውን]
©Binyam ZeChristos ግንቦት 10 - 2013

Читать полностью…

Binyam ZeChristos (ቢንያም ዘክርስቶስ)

ከቅዱስ አባትችን ጋራ እንዘምር

" እግዚአብሔር ብርሃኔ መድኃኒቴ ነው
የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው
ኣምላኬ መመክያዬ ነው "

Читать полностью…
Subscribe to a channel