bookfor | Unsorted

Telegram-канал bookfor - @Book for all

-

ማንበብ ማንበብ ማንበብ ‹‹ሰፊ ይለበሳል ጠባብ ይቀደዳል›› @መባ ለማንኛውም አስተያየት @Dasolo

Subscribe to a channel

@Book for all

በዜማ ማንሰፍሰፍ፤ አበበ ብርሃኔ
(ዮናስ ታምሩ ገብሬ)
‹‹ሰደድ ነው አንገቷ፤
እንደ ዥንጉርጉሩ፣ እንደ መቀነቷ፤ [አበበ ብርሃኔ]

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወንዴው ባሕርይ የተጫነው እንዲሆን ዕሙን ነው፤ በሀገራችን የተቀነቀኑ የበርካታ ዘፈኖች ግጥም እና ዜማቸው ወንዳዊ ጠባይ በጉልህ የሚንጸባረቅባቸው ናቸው። ለአብነት እንኳን ከተባእት ጾታ ድግምግሞሻዊ መገለጫዎች መካከል፡- መደለቅ፣ መርገጥ፣ መጋለብ፣ ማካለብ እና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው፤ የተጠቀሱ ባሕርያት በሙዚቃችን ገላ ውስጥ ጥላ ጥለው ከርመዋል። አሁን፣ አሁን በመጠኑም ቢሆን ሙዚቃችን ሴቴአዊነትን እየተላበሰ መጥቷል - ከ1980-81 ዓ.ም. ወዲህ፤ ከመደለቅ፣ ከመርገጥ እና ከመጋለብ አልፎ ወደ ሴቴአዊ መንሰፍሰፍ እያደላ መጣ ሙዚቃችን - በአበበ መለሠ። ስፓኛዊው ሰዓሊ ፐብሎ ፒካሶ ጥበብ ከውስጥ ስትመነጭ ጣዕመኛ ነች የሚላት ይትባሃል አለቺው፤ አቤም እንዲያ ነው - በሥራዎቹ የውስጣችንን ድብቅ ሚስጥር ጫር አድርጎ ያልፋል፤ በእንስፍስፍ ስልት የተብሰለሰለ ውስጣችንን ጎብኝቶ ለሌላ ተመስጦ አምነሽንሾን ሸርተት ይላል፤ ማሳተፍ ጠባዩ ሆነ ማለት ነው።

የሴት ሥነ-ልቡና የዘለቀው ሙዚቀኛ ነው አቤ፤ ወንድ ሆኖ ሳለ በሴት ይትባሃል የማንሰፍሰፍ ክኅሎት ያደለው ደራሲ። የሚደርሳቸው የዘፈን ዜማዎች ብርክ የማድረግና የማራድ ጉልበት አላቸው። ኩልል ያለ የቆለኛ ድምጽ ዓይነት ዜማዎች እና ስርቅርቅ ስልቶች በድርሰቶቹ ገላ ውስጥ ይስተዋላሉ። ከስምንት መቶ (800) በላይ የዜማ ድርሰቶችን ጀባ ብሏል። አመለ ሸጋ እና ተጫዋች ነው፤ ከዘፈን ዜማ አልፎ ክራር እና ኪቦርድ በወጉ ይጫወታል። 1978 ዓ.ም. መገባደጃ አካባቢ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ተከተተ - ከፋሲለደስ የኪነት ቡድን ጋር ለወጣቶች ፌስቲቫል ወደ ኮሪያ ሊዘምት። አልሆነም ነበር ታዲያ፤ በአዲስ አበባ ቲያትር ቤቶች ሲያንዣብብ እያዩ ማንያዘዋል (የ‹‹ዕድሌ ጠማማ›› ዘፈን አቀንቃኝ) ጋር ይገናኛሉ። የ‹‹ልቤ ገራገሩ››ን ዘፈን ግጥም በአንድ ምሽት ደርሶ ጀባ ካለው በኋላ ወደ ጎንደር ይተማል - ብዙም ሳይቆይ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ…

…ከግጥም እና ዜማ ደራሲው ከጸጋዬ ደቦጭ ጋር ለጸጋዬ እሸት፣ ለኬኔዲ መንገሻ እና ለአሠፉ ደባልቄ በሠራቸው ሥራዎች ተወዳጅነትን አተረፈ። አቤ በግጥምና ዜማ ድርሰቶቹ ማንሰፍሰፍ ያውቅበታል፤ ወንድ ደራሲ የሴት ዓይነት ማራድን በሙዚቃ ሥራዎቹ…

…የእናት ዓይነት የአንጀት መንሰፍሰፍ እና ተብሰልስሎት በዋናነት በዜማ ድርሰቶቹ ውስጥ ይንጸባረቃሉ፤ አዚሞ ማንሰፍሰፍን ተክኖበታል። እውስጥ የሚቀሩ ዜማዎችን ለበርካታ ድምጻዊያን አበርክቷል፤ ለማሳያ ያህል፡-

1. ለጌታቸው ካሳ፡- ‹‹ቀና ብዬ ሳየው›› (ዜማ) (ግጥም ጸጋዬ ደቦጭ)
2. ለኤፍሬም ታምሩ፡- ‹‹ቢልልኝ›› (ዜማ)
3. ለሂሩት በቀለ፡- ‹‹የእኔ ዓለም››፣ ‹‹ጠላኝ እንዳልለው›› (ዜማ)
4. ለባለቤቱ/ፍቅርአዲስ፡- ‹‹እርሳኝ›› (ዜማ)፣ ‹‹አልገባኝም›› (ግጥምና ዜማ)፣ ‹‹ዝም እላለሁ›› (ዜማ) - ካሴት 1984 ዓ.ም.፣ ‹‹ላባብለው›› 1989፣ ‹‹ሳብ በለው›› 1993 ካሴቶች
5. ለአሠፉ ደባልቄ፡- ‹‹የሆዴን›› (ግጥምና ዜማ)
6. ለሰርጉዓለም ተገኝ፡- ‹‹ሳላያት አመሸሁ›› (ዜማ)
7. ለየሺእመቤት ዱባለ፡- ‹‹ለዚህ በቃሁ››፣ ‹‹ትዝ አለኝ›› (ዜማ)
8. ለጸጋዬ እሸቱ፡- ‹‹ሆዴ ክፉ ዕዳዬ›› (ዜማ)፣ ‹‹መሸ›› (ግጥምና ዜማ)፣ ‹‹ያየ አለ›› (ዜማ)፣ ‹‹ተከለከለ አሉ›› (ዜማ)
9. ለማሐሙድ አሕመድ፡- ‹‹ስንቱን አሳለፍኩት›› (ዜማ)
10. ለኬኔዲ መንጋሻ፡- ‹‹ፋንታዬ›› ካሴት - ‹‹ፋንታዬ›› ‹‹አንቺ ዓለም›› ‹‹እንግባ ሀገራችን/ከየሺእመቤት ጋር›› (ግጥምና ዜማ)
11. ለቴዎድሮስ ታደሠ እና አሠፉ ደባልቄ፡- ‹‹ላጉርስሽ›› (ዜማ)
12. ለአበበ ተካ፡- ‹‹ወፍዬ››፣ ‹‹ሰው ጥሩ/ማን አላት ሰው ሐገር›› - ካሴት ሙሉውን ዜማ (ግጥሙ የአያ ሙሌ - ሙሉጌታ ተስፋዬ ነው)
13. ለሐመልማል አባተ፡- ‹‹ይዳኘኝ ያየ›› (ዜማ)
14. ለጎሳዬ ተስፋዬ፡- ‹‹የሐመሯ›› (ዜማ)
15. ለሞኒካ ሲሳይ፡- ‹‹ቀኑ አጠረ›› (ዜማ)
16. ለይርዳው ጤናው፡- ‹‹ላፍ አርጋት›› ሙሉ ካሴት (ሶስና ታደሠ ደግሞ ሙሉ ግጥም)
17. ለጸደኒያ ገ/ማርቆስ ሙሉ ካሴት፡- ከ‹‹ላፍ አርጋት›› ካሴት ዕኩል (ሶስና ታደሠ ደግሞ ሙሉ ግጥም)
18. ለይሁኔ በላይ፡- ‹‹የሰው ሐገር›› (ግጥምና ዜማ)
19. አሁንም ለባለቤቱ፡- ‹‹ምስክር›› - ካሴት፤ ይልማ ገ/አብ እና ቢኒአሚር አሕመድ ታክለውበታል
20. ለዳዊት ጽጌ፡- ‹‹እትቱ›› (ዜማ) - ግጥም፡- ናትናኤል ግርማቸው
21. ለተመስገን ተስፋዬ፡- ‹‹ሳቢዬ›› (ዜማ) - ግጥም፡- ናትናኤል ግርማቸው

እና ሌሎች ተጠቃሾች ናቸው። ለዛሬ የሰርጉዓለም ተገኝን

‹‹ሳላያት አመሸሁ፣ ሳላያት፤
እመጣለሁ እያልኩ - እየዋሸሁ፤
ነገር አበላሸሁ - እያመሸሁ፤›› ተጋበዙልኝ።

አቤ ዕድሜና ጤና ይስጥህ፤ አመሰግናለሁ!
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ከእርጋታውዋ ጋር በፍቅር ወድቄያለሁ ! ድምጿን እወደዋለሁ ። መቀራረባችን ባህርያችንን አሳስቦታል ።

በተደጋጋሚ ስንገናኝ ረጅም ሰዓት ተቃቅፈን ፤ ትከሻችንን ተነካክሰን ፤ እጆቼን ስማ ፂሜን በጣቶቿ አበላሽታ ነው ሰላምታችን፤

አረፍ ስንል ነው እንዴት ነሽ ? እንዴት አለህ ? የምንባባለው በዕይታችን ውስጥ መነፋፈቅ አለ ! በዕይታችን ውስጥ መፈላለግ አለ ! መሸነፋችንን ግን ማሳበቅ አንፈልግም ስንገናኝ ተፈጥሮ ሚዛን ይስታል መሰለኝ ሰዓቱ አይበረክትም።  ከሷ ጋ ስሆን ምቾት ይሰማኛል ። ከኔ ጋ ስትሆን ደስ እንደሚላት አውቃለሁ። ምን እንደተሰማኝ አልነገርኳትም ።

ለሁኔታዎች እድል መስጠት ፈልገናል ድልድዩን ስንደርስ እንሻገረዋለን አይነት ድፍረት ….. በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ሰባት ወራት አለፉ፡፡  ባሉን የእረፍት ጊዜያት ሁሉ  መገናኘት ግድ ሆነ ካልሆነ ሁለታችንም መነጫነጭ ይታይብናል ግን ማመን አንፈልግም፤

ሁላችንም ድክመታችን ይለያይ የለ...

የተገናኘን ሰሞን የምንግባባ አይነት ሰዎች አንመስልም…. ዝምታ የምታበዛና እርጋታዋ ትዕግስት የሚያስጨርስ አይነት… ሴት ነች እሷ፤

እሷ ግልፅነት የህይወት መርኋ የሆነ። የማታወሳስብ ያየችውን ፣ያስተዋለችውን ቀለል አርጋ የምታጋራ አይነት ሴት ነች።

መላመድ ያሳስብ የለ....ማንነታችን እየተወራረሰ ነበር ።

ያገናኘን የአንድ ወቅት ስራ ነበር ስራውን ማዕከል አድርገን ዘለግ ያለ ጊዜ አብረን እናሳልፋለን.. ከስራው አረፍ ስንል ስለ ህይወት እናወራለን፡፡ ጠንከር ባሉ የተለያዩ ሀሳቦች ላይ ስንሟገት ላየን አንዳች የምንፈታው ችግር ከፊት ያለ ያስመስልብናል፡፡

ስብዕናዋ ደስ ይላል አዲስ አይነት ባህሪን የምታለማምድ አይነት ሰው ነች፡፡ የተገናኘንበት ስራ ተጠናቀቀ፡፡ አልፎ አልፎ መደዋወል እና ስለሰሞነኛ ጉዳይ መጠያየቅ ጀምረናል፡፡

ሁለታችንም ጋር መገናኘትን መፈለጋችን በብዙ መንገድ ያስታውቅ ነበር የምንደዋወልበት ድግግሞች ከሁለትና ከሶስት ጊዜ አለፈ፡፡ አንዴ ስንደዋወል የወሬያችን የቆይታ ጊዜ ከደቂቃዎች ለሰዓት እየተጠጋ ሆነ…. ሳይደዋወሉ መዋል የማይታሰብ ነው፡፡ ጠዋት በሷ ድምፅ መቀስቀስ ማታ በኔ ድምፅ መተኛት የተፈጥሮ ህግ  እስኪመስል….

በእንዲ ያለ ስሜት ውስጥ ሆኖ መገናኘት ያስፈራል..

በተደጋጋሚ እየተገናኘን እናወጋለን፡፡ የምንወዳቸው ቦታዎች አብረን እንሄዳለን በስራ እየተደጋገፍን የአንዳችንን ሸክም አንዳችን እናቀላለን፡፡ በጣም እየተቀራረብን እየተላመድን ሆነ... እንደ ሱስ አይነት ነገር  ...

አንዳንዴ እንዳናጣቸው የምንፈራቸው ሰዎች አሉ ሁሉን በአንድ የያዙ ልክ ጓደኛ ፤ቤተሰብ፤ ሚስጥረኛ ባልደረባ ፍቅረኛ አይነት የሆኑ … ግን ደግሞ ሁሉንም በአንዴ ማድረግም መፈለግም ይከብዳል፡፡ ከነዚህ ሁሉ የአንዱን መስመር ለመምረጥ ያለ ትግል …… ፈታኝ ጉዳይ ነው፡፡

ግን አሁንም ለግንኙነታችን ስምም፤ መልክም፤ ቅርፅም ፤ አልሰጠነውም እንዲሁ መዋደድ ብቻ መራራቅን መፍራት ብቻ፤

የኔ ሴት እሷ ነበረች ... ያሳለፍነው የህይወት ምልልስ ያቀራረበን የልቤ ሰው…

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

Dear girls❤️

Never remove your clothes to prove your love.

Get a boy who can buy safety pads for you, not condoms. Get a boy who can take you to his home, not to the hotels. Get a boy who ask about your period pain, not for nudes. Get a boy who choosed your soul & heart, not the body.

Respect is one of the greatest expression of love. A real man never hurt a woman. She isn't just a housewife who cooks your meal & washes clothes. She is a homemaker who holds together the family & make sure that everything is as perfect as it can be once you get home. Respect for women is one of the greatest gift a man can show.

Be a real man & respect women.

Happy International Woman's Day!

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ቀና በል አትበሉት!!!
:
የዛለ መዳፉ
ሰውኛ ተስፋውን መሸከም ያቃተው
ማጣት ይሉት ህመም ቃሉ እያቃተተው
አሻግሮ ለማየት
ባልታደሉ አይኖቹ ጎንብሶ ቢማትር
ለካስ ቀን ሲያጎድል
በጠራራ ጠሀይ ይጨልማል ቀትር።

ከመረገም ይሁን ወይ ካለመታደል
ህሊና ሲደማ
ልብ እያለቀሰ ባልፈፀመው በደል
በየ ጥርጊያው ጥጋት
በየጎዳናው ዳር መሄጃው የጠፋው
ከሱነቱ ጎጆ
ይህ ስግብግብ አለም አርቆ የገፋው
እልፍ ሰው ይታያል በኑረት የከፋው።

ተመልከት ቀዬውን
ያዘኔታን ከንፈር ከሚመጠው እኩል
እልፍ አሳዛኝ አለ ባ'ሳዛኞች በኩል።

አጋድሏል ሚዛኑ
ቀን እየፈረደ ተ'በዳይ ይቀጣል
በተራማጅ እግሮች
የተሻለው ሲሄድ የባሰው ይመጣል
ምንም የሌለው ሰው የሌለውን ያጣል።

እንዲህ ናት ሀገሬ
በማለዳ ጀንበር የምትታይ መሽታ
ክርስቶስን አስራ በርባንን ምትፈታ።

እንዲህ ነው የኛ ቤት
አእላፉን ምስኪን ከኑሮ ሚያኳርፍ
በሁሉም ጎዳና
ተመፅዋች አይሄድም መፅዋች ነው የሚያልፍ።
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ወላይታም አለኝ እንደ ካኦ ጦና
ደፍረው በነኩኝ ላይ የሚሆን ፈተና!
ንጉስ ካኦ ጦና የወላይታን ጦር አስከትለው በአደዋ ድል ታላቅ ጀብድ የፈፀሙ ጀግና ናቸው። ብልሀት እንደ ጦና እንዲሉ ታሪክ አዋቂዎች። ኢትዮጵያ ከንጉስ ጦና ብልሀት ብብዙ እንደተጠቀመች ጳውሎስ ኞኞ "ሚኒሊክና ወላይታ" በሚል ባሰፈሩት ፅሑፍ ላይ ተገልጿል።
#አደዋ
#ክብር_ለጀግኖቻችን

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ንጉስ ሚካኤል መክተው በጋሻ
ለጠላት አታጣም ጥጋብ ማስታገሻ!
ንጉስ ሚካኤል የአጤ ሚኒሊክን የክተት አዋጅ ተቀብለው የወሎን ጦር ይዘው ወደ አደዋ ዘምተው ታላቅ ጀብድ የፈፀዉ የጦር መሪ ናቸው።
#አደዋ
#ክብር_ለጀግኖቻችን

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ተኩሶ የሚጥል ጠላት ማርከሻ
የዩሐንስ ልጅ እራስ መንገሻ
ራስ መንገሻ ዩሐንስ የአፄ ዮሐንስ ልጅ ሲሆኑ በአደዋ ጦርነት ታላቅ ጀብዱ የፈፀሙ የጦር መሪ ናቸው።
#አደዋ
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

#አደዋ
ጣሊያን ሰሓቲ ላይ እግሩን ቢዘረጋ
በብረት ምጣዱ በሰሓቲ ኣደጋ
አንገርግቦ ቆላው አሉላ አባነጋ
አውሮፓውያን "The Garibaldi of Abyssinia" በማለት ከታላቁ የጦር አበጋዝ ጋር ያወዳድሩታል።
አሉላ አባነጋ ለሀገሩ ያለውን ታማኝነት በተግባር ኖሮ በአንደበቱም ሲመሰክር እንዲህ ነበር ያለው "ጣሊያን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው እኔ የሮማ ገዢ ሆኜ ስሾም ብቻ ነው"።
ጀግኖቻችንን እናክብር!
ሳይለያዩ ያኖቆዩልንን ሀገር ተለያይተን ልንኖርበት አንችልም!
#አደዋ

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

አንድ ቀን፤ ሁሉም ነገር ተጠቅልሎ የእውነት እና የህሊና ጥያቄ ብቻ ይሆናል፡፡ ትርጉም ያለው ነገር እንፈልጋለን፡፡ ምን አይነት ሰው ልሁን? እንዴት ያለ ኑሮ ልክ ያደርገኛል ማለታችን የነፍሳችን ዓላማ ነው፡፡ ምዕመኑ አምልኮውን፣ መሪዎችም አገዛዛቸውን ይጠይቃሉ፡፡ መምህራን ከሚናገሩት፣ ነጋዴዎችም ከትርፋቸው ወዲያ ስላለው ነገር ማሰባቸው አይቀርም፡፡ ሁላችንም የገዛ ራሳችንን ጽድቅ ለመፈጸም የማንሻገረው ወንዝ አጠገብ እንቆማለን፡፡ ዳሩ ግን ብልጠት የመሰለን ስግብግብነት ከላያችን እስኪራገፍ ድረስ ብዙ ነፍስ [ነፍሶች] ሸቀጥ ሆነው ያልፋሉ፡፡ ደግሞ ከበሰለው ኋላ፣ ካለፈው ያልተማረ፣ ጥሬ ትውልድ ከማሕፀን በር ላይ ይገኛል፡፡
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

" በድሮ ጊዜ ---- ድሮ ሩቅ የሚመስላቸው የዋሃን ናቸው ፣ ትውልድ በተስፋ መቁረጥ ሲመክን የጊዜም ስፍር ይዛነቃልና ÷ ለመኮኑ የዋህነት ምንድነው ? ደርባባ አስተዋይነት የሌለው ÷ ግልብ ፈጣንነት አይደለም ወይ ? ... " የቸኮለ አፍስሶ ለቀመ " ፣ " የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል " ፤ " የእነ ቶሎቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ " ፤ " ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል " ... የፈጠኑ የት ይደርሳሉ ?

የማያልቅ ዘላለማዊ ህዋ ውስጥ በሚያበቃ ታሪክና በሚያከትም ኑባሬ የተወሰንን ፍጡራን ነን :: ፈጣሪም ይሰስታል --- ካልጎደለበት ሺህ አመት ፣ ካላጣው አፈርና ሰማይ በስድሳ ሶስት ዓመት የሚፈራርስ ገላና የሚሸመግል መንፈስ እንደአሻቦ ሰፍሮ ያከፋፍለናል :: ከየት ፈጥነን የት ደርሰናል ?

አድበን ፣ ስሜታችንና መርማሪ ጠያቂ ያልተቀጣ አሳባችንን በአንዳንች ልጓም ገትተን በብዙኃኑ መንገድ " ብቸኛው ተኩላ ይሞታል " ይላሉና አዋቂዎች ከአዳም ጀምረን ብንቆጥር የምንደርሰው አሸብር ዘንድ ነው :: ተመሳሳይነታቸው እስኪያስደንግ ድረስ ነው :: አዳም በሔዋን ሳተ ፤ አሸብር በሔለን ወይ በአንቺናሉ አይተነው ዳምጤ ሳተ :: ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥፍ :: ለመሆኑ አሸብር ማነው ? አናውቅም :: ሕይወቱም እንደህልውናው የሚመረመር ያልሆነ ልሙጥ ተረክ ይሆናል :: ታሪክ ግን መርጦ ያነሳል መርጦ ይጥላል :: ታሪክ ጉልበት የሌለው የሚመስላቸው አሉ :: እኔ ግን እላቹሃለሁ ታሪክን በዕውቀት ለሚጠቀመው የእግዜር እጅ ነው ... በድሮ ጊዜ .... "

ስለትናንሽ አለላዎች
ዮናስ . አ
ሁለተኛ ዕትም
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ለመላው የክርስትና እምነት የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አንቺ ቤተልሔም፥የይሁዳ ምድር፥ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና፥ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፏልና፥በይሁዳ ቤተልሔም የአለም መድሀኒት ፣ የፍጥረታት ጌታ ፣ የሀያላን ሀያል ፣ የጌቶች ጌታ ፣ የንጉሶች ንጉስ የስጋም የነፍስም ፈጣሪ እርሱ መድሐኒት እየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዷል።
የገና በዓል አምላክ በፈጠራት ምድር አንድያ ልጁን ለአዳም መድሀኒት እንዲሆን ስጋ ለብሶ የተወለደበት እንደመሆኑ በልባችን ፍቅር  ፣ ሰላም  ፣ ቅንነት ፣ ምክንያታዊነት እና በጎነትን በልባችን ፀንሰን እንድንወልድ እድል የተሰጠን ነው።
በዓሉን ስናከብር በቅንነት ስራ ፣ በበጎ ተግባር መሆን ይገባዋል። የፍቅርና የይቅርታ አምላክ የተወለደበት ቀን ነውና ሁላችንም ልባችንን በፍቅር ህይወታችንን በይቅርታ እንመራ ዘንድ አደራ እያልን ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሳችሁ በመላት መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ያለንን ማወቅ ... ራስን መሆን ..... ለሁኔታዎች ሚዛናዊ ምላሽ መስጠት...

መቻል መታገስ ለኮሽታዎች ሁሉ አለመገረም....

በስሜት ብልህነት ከፍ እያሉ መምጣት .....

ልምድ ይባላል።

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

(ምናብ)

መስሎ እንደሚጓዝ ወንዝ
ፈልቆ ከአንድ ቦታ
በነገሰ ድባብ
በሃሳብ ከፍታ

መወለድ አይደለም
መፀነስ ያልቻሉ

ረቂቅ ሀሳቦች
ከብሩኽ አዕምሮ
ከንፁህ ልቦና ሁሌም ያደባሉ ።

ብ.አ.ከ.

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

#ከስላንች እስከ #ወሬ ነጋሪ

ያላለቀ የጥበብ ጉዞ ተገታ !☺☺☺
ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ)
#ነፍስህ በሰላም ትርፍ

@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ለአንድ ሴት በተለይ "ቆንጆ ሴት ነን" ብለን ለምናስብ ሴቶች ፥ አቅማችንን እንዳንጠቀም እስር ቤት የሚሆንብን፤ የራሳችን ቁንጅና ነው። የራሳችን ቆዳ የራሳችን እስር ቤት ነው።

በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሴትነት እና ቁንጅና የሚባል የእስር ፍርግርጋችንን እያስዋብን ፥ ተሟሙቀን የወንዶችን ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሆነናል።

ማኅብረሰቡ አንዲትን ሴት "የብረት መዝጊያ" የሚሆን አማች የምትመጣ እንጂ ፥ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም፤ ስለዚህ የነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት ፥ አንዲት ሴት ዓይኗን፤ አዕምሮዋን፤ ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከህፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል።

እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ ፥ በስነ-ጽሁፍ፣ በፊልሙ፤ አዕምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኖሯል።

ከመራመዷ በላይ የአረማመዷን እና የእግሯን ውበት ፥ እንድታስብ ስትሰበክ ኖራለች። ለዚህም ነው ከፊትሽ የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ፥ ረግጠውና ዋጋ ከፍለው አዳሰቡበት ከሚራመዱ ሴቶች ይልቅ፤ ከየትም ባገኟት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው ፥ እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት። እግራቸው ከለሰለሰ በኃላ ፥ አዝሎ የሚያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ።

ገጽ 182-183
(ከእለታት ግማሽ ቀን)
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

#ባለውለታ

"ሰውነት አልሞተም"

በዚህ ግዜ እኛ ኢትዮጵያውያን ብሎም በአለም ላይ የሚታየው የሚሰማው ሁሉ ሰው ሰውነቱን በቃ አጣ? ዓለም ለመኖር አስፈሪ እየሆነች ይሆን? የሚያስብሉ ሰው የሰው ስጋት እየሆነ የመጣበት አስከፊ ነገሮች ተከስተዋል እየተከሰቱም ሰብዓዊነትም እየተሸረሸረ የመጣበት ጊዜ ነው።
ነገር ግን አሁንም በጨለማ ውስጥ ብርሃን የሆኑ እና ለመኖር እንድንጓጓ የሚያደርጉን ጥቂት የማይባሉ ለነብሳቸው ያደሩ ልበ ብሩሃን❤ መልካም ሰዎች ዛሬም አሉ።
👉ለአብነት ያህል ከሰሞኑ በልበ ብሩሁ ቢኒያም አማካኝነት ለተቋቋመው መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የማስፋፊያ ህንፃ ግንባታው ተጠናቆ ነገር ግን ያላለቁ የበር እና የመስኮት እንዲሁም አንዳንድ የፊኒሺንግ ስራዎች ለማጠናቀቅ የሚውል ገንዘብ አሰባስቤ ሳልጨርስ ከዚች ወንበር ንቅንቅ አልልም ብሎ ራሱን ለመልካምነት አሳልፎ የሰጠውን በበጎ ስራዎቹ የምናውቀው ኮሜድያን ዕሸቱ መለሰን መጥቀስ ይቻላል። እንደዚህ ያሉ መልካም ሰዎች ያብዛልን እያልን ፤
ለዚህ በጎ ዓላማ መሳካት ከጎኑ የሆኑ ቅን ልብ ያላቸው መልካም ሰዎች ሁሉ ክብር ይገባቸዋል።

👉የሀገር ባለውለታው ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ላደረከው፤እያደረክ ላለኸው እና ወደፊት ለምታደርገው ሁሉ ክብር ይገባሃል❤❤❤

"ሰውነት!ሰብዐዊነት አሁንም አልሞተም"
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ወላይታም አለኝ እንደ ካኦ ጦና
ደፍረው በነኩኝ ላይ የሚሆን ፈተና!
ንጉስ ካኦ ጦና የወላይታን ጦር አስከትለው በአደዋ ድል ታላቅ ጀብድ የፈፀሙ ጀግና ናቸው። ብልሀት እንደ ጦና እንዲሉ ታሪክ አዋቂዎች። ኢትዮጵያ ከንጉስ ጦና ብልሀት ብብዙ እንደተጠቀመች ጳውሎስ ኞኞ "ሚኒሊክና ወላይታ" በሚል ባሰፈሩት ፅሑፍ ላይ ተገልጿል።
#አደዋ
#ክብር_ለጀግኖቻችን
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ንጉሱ ሲጠሩት መጣ በፈረሱ
ለራስ መኮንን ኢትዮጵያ ናት ነፍሱ!
ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ጉግሳ የአፄ ሀይለ ስላሴ አባት በኢትዮጵያ ታሪክ ከታዩ ሩሩህ ፣ ብልህ ፣ አስተዋይ እና ታማኝ መሪ ነበሩ። በአደዋ ጦርነት ታላቅ ጀብድ የፈፀሙ የጦር መሪ ነበሩ።
#አደዋ

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ንጉስ ተክለሃይማኖት ወዴት ይሆን ድርሻ
ጀግናው ሰው ናጣቸው በጦር በጎራዴ መክቶ በጋሻ
ንጉስ ተክለሀይማኖት ዘ ጎጃም በአደዋ ድል በሀገር ፍቅር ፣ በወኔ ፣ በጦር ጥበብ ፊት ከነበሩ ጀግኖች መካከል ይጠራሉ።
#ክብር_ለጀግኖቻችን
#አደዋ
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

አሻግሮ ገዳይ ዲብ አንተርሶ
የዳኘው አሸብር ባልቻ አባነፍሶ
ብልህነት ፣ ታማኝነት ፣ ሀገር ፍቅርና ጀግንነት ባንድ ላይ ቢሰደሩ ባልቻ ሳፎን ይመስላሉ ይላሉ ታሪክ ነጋሪዎች። አደዋ ላይ ታሪክን በደማቁ ከከተቡ ጀብደኞች አንዱ ናቸው። በግዜ ሒደት በስርዓት መለወጥ ያልተቀየረው ሀገር ፍቅር በ80 አመታቸው ዳግም የጣልያንን ጦር አሳፍረዋል። በወቅቱም ለምን ይዘምታሉ በስተርጅና ሲሏቸው "ሸምግያለሁ መሞት እንደሆነ አይቀር በሰማይ ላይ ጌታዬ ሚኒሊክ በኢትዮጲያ ዙፍኔ ላይ ማነው ያለው ቢሉኝ ምን እመልሳለሁ" ብለው መልሰዋል።
#አደዋ
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

በጋራ ካኖርናቸው ታሪኮቻችን ግንባር ቀደም የዓድዋ ድል ነው፡፡
ዓድዋ ዛሬ ላይ አላሻግር፣ ነገን አላሳይ ያለንን የልዩነት አጥር ለመጣስ የምንማርበት የአንድነት፣
የልዩነት እና የመቻቻል ጥበብ ማስተማሪያ ፊደል ነው።
እስቲ የጥቁር ድል የሆነውን አደዋ የሰጡን የኢትዮጵያ ጀግኖች እናውሳ።
ንጉሱ ተጠርተው ማን ይምጣ ቢሏቸው
ከዚህ ሁሉ ጀግና መሾም አቃታቸው
#አደዋ
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

◉◉◉

...ምናልባት፥ቀና ስንል...
...ሊያየን ካቀረቀዉ ጋር እንተያይ ይሆናል...!!

◉◉◉


@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ማፍቀር መቻል ለአንድ ሰው የመኖር ፣ ተስፋ የማድረግ እና አምነትንና ብርታትን የሚሰጥ ይመስለኛል፡፡ ማፍቅር ለዚህች ቁራጭ ሕይወት ትርጉም ይሰጣል ብዬ አስባለሁ ፡፡ አንድ ጊዜ ከታላላቆቹ የኢትዮጵያ ልብ ወለድ ጸሐፊዎች መካከል በአሉ ግርማ በአንድ ወቅት አንዲ ብሎ ነበር “እኔ ደደብ ነኝ ፤ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ፣ በአለም ላይ ሲኖሩ በሁሉም ነገር ላይ እምነት ከማጣት የበለጠ ሀገርን የሚያፈርስ ነገር የለም” ብሎ ነበር፡፡ እና ለእኔ ማፍቀር መቻል ማለት አንድ ሰው በህይወቱ ትርጉም እና እምነትና ተስፋ እንዲኖረው ሊያደርግ የሚችለው ብቸኛውና ዘላለማዊ ነገር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለነገሩስ ፊዮዶር ዶስቶቭስኪን "እውነተኛ ገሃነብ ምንድ ነው?" ቢሉት "ማፍቀር አለመቻል ነው "ብሎ መልሶ ነበር፡፡"
@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

ታዋቂዋ የሙዚቃ ንግስት ድምፃዊ አስቴር አወቀ ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር መፈራረሟ ይፋ ተደርጓል።

ድምፃዊቷ ቀጣይ አልበሟን በዚሁ በሰዋሰው መተግበሪያ በጥምቀት ዋዜማ ለአድማጭ የምታቀርብ ይሆናል።

@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

.....
" ያልነገሩኝማ ብዙ ታሪክ አለ። በዚህ ብቻ አያልቅም!.... ባይሆንማ መልካቸው የዚህን ያህል ከግድግዳው ጋር ባልተመሳሰለ ነበር! "
.....

@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

+ ያላለቀው ሰፌድ +

ዓሥር ብር ኖት ላይ የነበረችው የዚህች ሴት ነገር አንጀት ይበላል:: ሰፌድዋን ሠርታ ሳትጨርስ ጊዜዋን ጨረሰች:: ቀና ብዬ ወሬ ልይ ሳትል አቅርቅራ ሥራዋ ላይ እንዳተኮረች ኖረች:: ትዳር ልያዝ ሳትል የየሰዉን ኪስ ለመሙላት እንዳቀረቀረች ኖረች::

መልእክቱ ይኼ መሰለኝ :-

ወዳጄ ነገሮች መቼ እንደሚለወጡ አታውቅም:: እጅህ ላይ ያለውን ሥራ ሁሉ በቶሎ ጨርስ:: ማንም ሊሠራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ በፊት ሥራህን አከናውን::

ብዙዎቻችን ከአጭሩ ዘመናችን ብዙ እናባክናለን:: ምንም ያላደረግንባቸው ባዶ ጊዜያትና ያልተኖሩ ብዙ ቀናት አሉ:: ከገንዘብ በላይ የማይተካው ብክነት የጊዜ ብክነት ነው:: ሰዎች ጊዜያቸውን ተጠቅመው የሠሩትን ክፋት ማውራት ትተን ጊዜያችንን መጠቀም ይኖርብናል::

በጊዜህ በአግባቡ ተጠቀም:: የማትጨርሰው ለዓመታት የማያልቅ ሰፌድ አትጀምር:: ለነገሮች ቅደም ተከተል ሥጣቸው:: አንዱን ሳትጨርስ ሌላ አትጀምር:: ቁምነገሩ በነገሮች መወጣጠርና ቢዚ መሆን አይደለም:: ጉንዳኖችም ቢዚ ናቸው:: ቁምነገሩ ጊዜ የምታጠፋው ምን ላይ ነው የሚለው ላይ ነው:: እነርሱ ቢያንስ ለገብረ ጉንዳን ይተርፋሉ:: ያንተ ቢዚነት ለማን ይተርፋል?

ስልክህ ውስጥ ባለ ጌም ላይ ያሉ ግንቦችን ለማፍረስ አለዚያም ለመገንባት ጊዜ የምታጠፋ ከሆነ ድንገት ብትሞት እንኳን በጣም ታሳዝናለህ:: ምድር ካንተ ብዙ ትጠብቃለች:: ሰዎች ገንዘብ እንዲያገኙ አንተ ገንዘብ የማታገኝበት ነገር ላይ ትሰቃያለህ::

የምትሰፋውን ሰፌድ አሁኑኑ ወስን:: ነገ ዓለም ሳትቀይርህ በፊት ሥራህን ወስን:: ጊዜህን ተጠቀምበት:: ባላስፈላጊ ነገር ላይ ጊዜ አትውሰድ:: መጽሐፍ ቅዱስ "ለሚጠፋ መብል አትሥሩ ለዘላለም ሕይወት ሥሩ" ይልሃል::
ከቻልክ ትውልድ የሚጠቅም ለአንተም ለነፍስህ የሚበጅ ነገር ሥራ:: ብቻ እየሰፋኸው ያለኸውን ሰፌድ ቆም አድርገህ ምን እያደረግኩ ነው? ብለህ ራስህን መጠየቂያህ ጊዜ አሁን ነው:: አለዚያ ግን ድንገት ሕልውናህ አብቅቶ ሰዎች ባዩህ ቁጥር እንደዚህች ሴትዮ "ውይይይይ ይቺ ሴትዮ አሥር ብር ላይ የነበረችው እኮ ናት" እያሉ ከንፈር ይመጡብሃል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 11 2013 ዓ ም

@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

በ አጸደ ስጋ
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰው ሟች መሆኑን መርሳት የሚፈልግ ፍጡር ነው፤ ስልጣኔ ደግሞ ለጊዜውም ቢሆን ሞትን ያስረሳል፤ በአውሮፓ በአሜሪካ በጃፓን ኮረና እስኪመጣ ድረስ ሞትን የሚያሳስብ ነገር አልነበረም፤ የመቃብር አጸዶች እንኳ እጀግ ውበ ከመሆናቸው የተነሳ የፍርሀት እና የተስፋ መቁረጥ ስሜት አይቀሰቅሱም፤ ስልጡን ማህበረሰብ ሞትን ማስቀረት ባይችል እንኳ ማዘግይት ችሏል፤
በአገራችን የተለየ ነው፤ ሞት የማይንጸባረቅበት የኑሮ ዘርፍ የለም፤ ስንምል “ አባቴ ይሙት ፤ እናቴ ትሙት “ እንላለን፤ ስናጋብዝ “ በሞቴ ! አፈር ስሆን “ ብለን እንለማመጣለን፤ ራሳችንን ስንወቅስ “ ሞት ይርሳኝ “ እንላለን፤ ስንጸልይ ፤ “ አሟሟቴን አሳምርልኝ” እንላለን፤ አኗኗሬን አሳምርልኝ ሲባል ሰምቼ አላውቀም፤ ከልደታችን እና ከሰርጋችን ቀብራችን ይደምቃል፤ አንድ ሰው በሕይወት ያለን ሰው ካሞገሰ ወይም ካመሰገነ ድሮ “ እበላ ባይ “ ይባል ነበር፤ ዘንድሮ “ አሽቃባጭ “ የሚል ስም ይቀዳጃል፤ የሞተውን ማወደስ ግን የዜግነት ግዴታ መስሏል፤ በሕይወት መወደስ ፐርሰናሊቲ ከልት “ አሰኝቶ ያስወነጅላል፤ በሕይወት ዘመኑ ሀውልት የተሰራለት፤ መንገድ የተሰየመለት ትልቅ ሰው አይታችሁ ታውቃላችሁ? መንገደኞቻችን ረጃጅም መካነ መቃብሮች ሆነዋል፤
የፖለቲካ አስተዳደሮቻችን ለህይወት ያበረከቱት ነገር ጥቂት ነው፤ ባንጻሩ የሞት ፋብሪካ መሆናቸውን ታዝበናል፤ የመስዋአት አምልኮ ተነስራፍቷል፤ የአገረሰቡም ሆነ የብሄረሰቡ መዝሙር “ ስለ ደም ማፍሰስ እንጂ ስለ ደም መለገስ “ አይደለም፤ የሚሞት እና የሚገድል እንጂ፥ የሚኖርና የሚያኖር እንደ ጀግና አይታይም፤
በሀኪም ስተት ከሞተው ይልቅ በአስተዳደር ስህተት የሚያልቀው ይበልጣል፤ ያም ሆኖ ፥ ቆም ብሎ የመጣንበት መንገድ አያዋጣም ለማረም የሞከረ የለም፤

ባጭሩ፥ የሞት አገር ነው በውቄ! በዚህ ሁኔታ ውስጥ፥ ሕይወትህን መንዘንጋት ቀላል ነው፤ ጌታ ኢየሱስ ፥ ነቢዩ መሀመድ ሀዋርያው ጳውሎስ እንደነገሩን ከዚህ የተሻለ አለም አለ፤ ጌታ ኤፌቅሮስ እንደ ነገረን ደግሞ ይህ አለም የመጀመርያውም የመጨረሻውም እድላችን ሊሆን ይችላል ፤ እና በተቻለህ መጠን፤ ለመኖር ተፍጨርጨር፤ ለበጎ ምግባርህ ምድራዊውም ሆነ ሰማያዊ ሽልማት ሳትጠብቅ በጎ ሁን! ከቅኔ ከተረት፥ ከሙዚቃ፤ ከእውቀት ከሚገኘው ፍስሀ ተሳተፍ! ቢሰምርልህ ተቃቀፍ! እንደ ራስ አዳል እና እንደ አቤቶ ምኒልክ አብረህ ብላ! አብረህ አጭስ፥ እንደ ጌቶች ረዳና እንደ ብሬ ጁላ ፤ ከህይወት ጸጋዎች አብረህ ባትሳተፍ ከሞት እዳዎች አብረህ መሳተፍህ አይቀርም፤ ሻምበል ፍቅረስላስላሴ ወግደረስና ገለሳ ዲልቦ በህይወት ዘመናቸው የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ያላቸው “ተጻራሪዎች “ ነበሩ፤ አሁን ስላሴ ቤተክርስትያን ጎን ለጎን ተኝተዋል ፤ እንደዚያ ነው!

@Bookfor
@Bookfor

Читать полностью…

@Book for all

...
"ማነሽ? ተናገሪ!"
"ፍቅር!"
"የት አገኘሽው?"
"እግሬ ሥር?"
"ምን እያ'ረገ?"
"ሲቆፍር።"
"ትለቂያለሽ?"
"አለቅ'ም!"
"ትለቂያለሽ?"
"አለቅ'ም!"
"አትለቂም?!"
"እለቃለሁ!"
(ይኸኔ እስቃለሁ)
አንቺን ሲጠይቁሽ እኔ እመልሳለሁ።

"ምሱን ተናግረሽ አሁን ልቀቂ!"
"በመጀመሪያ አረቂ"
"ከዚያስ?"
"ጠላ፣ ጠጅ - - እንጀራ ጋር"
"ከዚያስ"
"እኔና እሱን መዳር!"

ቂቂቂቂ!

ለቅምሻ የተሰፈረ ነው። ሙሉውን አንብቡት። ብትጠሉት? ጆሮ ልይዝ። ብትወዱት? ድገሙት ልል። ለምንም ለማንም ግን ሰኞ እንድንገናኝ ይሁን። ጊዮን ግሮቭ ጋርደን
ምሽት 11:30
@Bookfor

Читать полностью…
Subscribe to a channel