#life_Style_Fashion
በጥራታቸውና በአይነታቸው የተመሰከራለችው የተለያዩ የሴቶች አልባሳትን በልዩነት ይዘን ቀርበናል።
ይዘዙን ባሉበት ይዘን እንቀርባለን!
Life Style Fashion ለዘመናዊነት የተመረጠ!
Join የሚለውን በመጫን የሚፈልጉትን ይምረጡ።
/channel/+ilLeD1LYh9U3NjQ0
አራዳ ነው። ሕይወትን በመሠለውና በወደደው መንገድ ኖሯል።
ባላገር ነው። ሀገር ፍቅሯ ልቡ ውስጥ አለ።
ዕድለኛ ነው። ባህር ማዶ እያለ ደጋግሞ የሎተሪ እጣ ያሸንፍ ነበር። ጌቾ ምን አደረክበት ስትለው " ምን አደርገዋለሁ? Dance and Music ነዋ! " ይልሀል።
ሙዚቃ ነው። ከሁሉ የሚልቀው ይሄ ነው። ጌታቸው ሙዚቃን ራሱን ነው ወይም አንዳች አይነት ሚውዚክል Note። የማይጠፋ ግን የማይተካ።
ሞተ አንልም።
ሙዚቃ አይሞትም።
—
@Bookfor
@Bookfor
የአስቻለው ፈጠነ አልበም ተለቀቀ!
#Ethiopia | የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) "አስቻለ" የሙዚቃ አልበም ዛሬ አርብ ጥር 3 2016 ዓ.ም በብርቧክስ ሪከርድስ በኩል ተለቋል።
እናትዋ ጎንደር እና ካሲናው ጎጃም በሚሉት ነጠላ ዜማዎቹ ተወዳጅነትን ያተረፈው አስቻለው ፈጠነ ( Aschalew Fetene Ardi ) "አስቻለ" የተሰኘውን የመጀመሪያውን አልበም ለህዝብ ደርሷል።
እመት ሸዋ እና ወሎ የሚሉትን ትራኮች ለቅምሻ ያሰማን ሲሆን ጣፋጭ ጠላ ተገፈቱ እንደሚያስታውቀው ሁሉ አልበሙም የተዋጣለት እንደሚሆን ያሳብቃል።
አስቼ ትክክለኛ መንገዱን ይዞ እየተጓዘ የሚገኝ ባለ ተሰጥኦ ህልመኛ ነው ።
"እናትዋ ጎንደር" በሚለው ስራው አስደምሞኛል።
"እነ እቴቴ ጉርሻ ኧረ እንደምን ናችሁ
ጉብ ጉብ አለብኝ አፈር ልብላላችሁ " ብሎ አንጀትን ሰፍፍፍ የሚያደርግ ስራ ሰርቷል ።
ቃላት እርሷን ለመግለፅ ለሚሽመደመዱላት ሙሽራዋ ጎንደር
"እናትዋ ጎንደር
ትንፋሽዋ ጎንደር
እህልዋ ጎንደር " እያለ በሚያስገመግም ድምፁ ተቀኝቶላታል ።
"እናትዋ ጎንደር" አዕምሮዬ ላይ ላይወርድ ተቀርፆ የተቀመጠ ድንቅ ስራ ነው።
ከግጥም እስከ ዜማ ፣ ከአጀማመር እስከ ፍፃሜው ከሲኒማቶግራፊ እስከ ክሊፕ ትወናው ጥንቅቅ ያለ ስራ ነው።
በ "ካሲናው ጎጃም"
"ድግሱን ደግሶ አይነግሩም አዋጅ
መንገደኛው ሁሉ ሰተት ነው እንጅ " እያለ
መሬት ላይ በአይኔ ያየሁትን ሃቅ በጥበቡ ከፍ አድርጎ አሳይቶኛል።
"የነካኸው ይጣፍጥልህ" ተብሎ የተመረቀው ሰው መሆን ይስማው ሰርቶት ደግሞ እንዴትስ የተዋጣለት ላይሆን ይችላል ?
እንኳን ደስ አለህ ወንድሜ አስቼ😍
ብራቮ ሶሚክ Sewmehon Yismaw
Aschalew Fetene Ardi እንኳን ደስ አለህ!
https://youtube.com/BirbauxRecord
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ።
በአሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ በቻነላችን ስም ከልብ እንመኛለን !!
@Bookfor
@Bookfor
"ወንጌለ ውዴ፣ አንድን ቦታ እንዲናፍቅሽ ወይም ደግመሽ ለማየት የሚያጓጓሽ የቦታው ውበትና ድምቀት ብቻ ይመስለኝ ነበር። ግና ከቦታው ውበት በላይ የሚናፍቀው ጊዜ ነው፤ ያውም ያውም ያጊዜ መስፈርት ሣናወጣ የተዋደድንበት ዘመን።
@Bookfor
@Bookfor
ያልተሰሙ ሙዚቃዎች ፤ ያልተገለጡ የመፅሀፍ ገፆች ፤ ከኮመዲና ጀርባ የተጣሉ ያረጁ ጋዜጦች፤ ዝም ያሉ ግን ዝምታቸው የሚከነክናቸው ሰዎች ፤ figure የሌለው ሀይማኖት፤ ብዙ ሰው የማይወዳቸው ሰዎች፤ 8 ወይም 9 reaction ያላቸው የfacebook ልጥፎች ፤ ባዶ ቤት ፤ የተሰቀለ ስዕል ለማየት ጀርባዋን የሰጠች ሴት ፤ በአንድ እጇ መፅሀፍ በሌላው ቁራሽ ሲጋራ የያዘች ፀሀፊ ሴት ፤ ይቅር ማለት ፤ ጥሩ ጥሩ የሚሸት ረጅም እና ኪሱ ባዶ የሆነ ወንድ
አዎ እነዚህም ደግሞ ውብ ናቸው ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
©newal
@Bookfor
@Bookfor
Description
ካሲናው ጎጃም | አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video)
BirbauxRecords.SewMehonFilms">
Birbaux Records. SewMehon Films
7.3KLikes
200,789Views
12 May2023
#kasinawugojam
#BirbauxRecords
#SewMehonFilms
ካሲናው ጎጃም ______ ግጥም: አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ሐይለ እየሱስ ደርብ የህዝብ ዜማ: የህዝብ ዋሽንት: አይችሉህም መንግስቴ ከበሮ: ሐገረሰላም ሻፊ መሰንቆ: እንድሪስ ሐሰን አረሒት : እየሩስ መለሰ አድማቂ: መላኩ ታረቀኝ ተቀባይ: አማኑኤል አሊ: አሳየ ፈንቴ: ክንፈገብርኤል ክንዱ :ተፈሪ አሰፋ ጋፈርና ግሪፕ: አበበ ከፈለኝ፣ ዳግማው አበበ ረዳት ካሜራ: የአብስራ ደሳለኝ ፕሮዳክሽን ዲዛይነር: ሄለን ብዙነህ ፕሮዳክሽን አስተባባሪ: አከለ መሰለ ፕሮዳክሽን ማናጀር: ዮናስ አብርሀም ሲኒማቶግራፈር: ፍስሀፅዮን ንብረት ከለር: ሮሀ ስቱዲዬ ኤዲተርና ዳይሬክተር: ሰውመሆን ይስማው ፕሮዲዩሰር: ብርቧክስ ሪከርድስ ---------------------- ልዩ ምስጋና ለዲማ እና አካባቢው ነዋሪዎች ግንቦት 4/2015 ዓ/ም -------------------- ካሲናው ጎጃም ግጥም ---------------------------- መላየ ነይ መላ አለው መላ መላ (3) አቴ መላ ዘውዴ ዘውዴ (3) የአንችው ማሽላ ነው ዘውዴ የእኔ አዝመራ ስንዴ ዘውዴ እቴ መላ ዘውዴ ሐገራችን ጎጃም ዘወዴ (ወንዛችን አባይ)2 እንደመስቀሏ ወፍ ዘውዴ (ብቅ አትይም ወይ) ግምባሯን ቶ መስቀል ዘወዴ (የተነቀሰችው )2 ያያ ወንድአለን ልጅ ዘውዴ (ነብሮን አገባችው የዳጉሳ ጠላ የለውም ዘውዴ( የለውም ቅራሪ) አሁን ገና መጣች ዘውዴ (አስኳላ ተማሪ)2 ዳማይ አንችን ነው ዳማየ (2) እናት ወልዳ ወልዳ ዳማየ ስም ማውጣት ታውቃለች ዳማየ የመጀመሪያውን ዳማየ በላይ ትለዋለች ዳማየ ደግሞም አስቀጥላ ዳማየ ሽፈራው ትላለች ዳማየ ደሞም አስቀጥላ ዳማየ ባንችዋ ትላለች ዳማየ የማሳረጊያዋን ዳማየ ይጋርዱሽ ትላለች ዳማየ ዳማይ አንችን ነው ዳማየ (2) ሎሚተራ ተራ ዎ (4) እናቴን አደራ አሸበል ገዳየ አሐው ገዳየ አይናማው ገዳየ አሐው ገዳየ ሻየ ገዳየ አሐው ገዳየ አታሞው ሲመታ አሐው ገዳየ መሬቱ አረገደ አሐው ገዳየ (2) ያያ ኩታ ለብሶ አሐው ገዳየ ዝናብ አወረደ አሐው ገዳየ(2) ድግሱ አማረላት አሐው ገዳየ እመ ተመናሸች አሐው ገዳየ ታተይ ተመናሸች አሐው ገዳየ መቀነቷን ታትቃ አሐው ገዳየ ዋንጫ ለቀለቀች አሐው ገዳየ(2) ያዋልዳል በሬ( ያዋልዳል ላም)2 የእናጅሬው አገር እንዴት ነው ጎጃም ድግሱን ደግሶ( አይነግርም አዋጅ)2 መንገደኛው ሁሉ ሰተት ነው እንጅ ምንኛ ደግ ነው( የእዜሩ በረከት)2 በውሀም አይደለ በቅምጫና ወተት ጋኑን እጠኝና (በጋምቢሎ ጭስ)2 በጥብጠሽ ጠብቂኝ ገምበሀ ስደርስ ኩራትሽ (5)ራትሽ ዶቅማ መቅመስሽን አወቅሁ በምላስሽ ደልቂ (6) እኔ እያለሁልሽ እንደ ፀሐይ ሳቂ ደልቂ(6) አማቶችሽ ዘንዳ መጠሽ ተመረቂ ያለ ዛሬ ቤቴን (አታውቀውም ብሎ)2 ጠሪ አክባሪ ድሷል አቆልቋይ አክሎ ባለጌታው ባይሸሽ አብየ ሰንደቁ አርበኛው ሰንደቁ ገና እንደፎከረ ጠላጦች ወደቁ ፍጥረት መጀመሪያው የአፍላጋት መፍለቂያ የዬቶር ሞገድ ካሲናው ጎጃም ነው ምድሪቱ ምጣድ ደልቂ (6) ከሽማግሌ እግር ወድቀሽ ተመረቂ ደልቂ (6) እኔ እያለሁልሽ እንደ ፀሐይ ሳቂ
https://youtu.be/dSh0jJXCd_E
እንዳይሆን በጽኑ የምመኘው ፥ ግን ከመሆን የሚቀር የማይመስለው የዚህ አገር የእለት ከእለት ሀቅ
ከሆነው በላይ ሊሆን ያ'ለው ያስፈራል💔
¤¤¤
አገር በሚያልፍበት ባዘቦት መንገዱ
በ.ስ
አገር በሚያልፍበት ፥ ባዘቦት ጎዳና
በሁሉም ሰው ፊት ላይ ፥ትካዜ ተስሎ
ሲመስል ደመና
ማን ከማን ተሽሎ
ማን ማንን ሊያጽናና?
በዕንባ ስፍር እንጂ የምንለያየው
ክንብንቡን ገልጦ፥ ቀረብ ብሎ ላየው
ሁሉም ልቅሶ ላይ ነው።
በየትኛው ዘመን ፥ ይፈርሳል ድንኳኑ
የምስራች መምጫው መቼ ይሆን ቀኑ?
ብየ ብጠይቅም
መልሱን ግን አላውቅም።
አገር በሚያልፍበት፥ ባዘቦት መንገዱ
ባስፋልት በሐዲዱ
መርዶ እየዘለለ
ብስራት ግን ይድሀል
በዚህ ሁሉ መሀል
እኔን ስታስቢ
ፈገግታሽ ፤ ከናደው
ፊትሽ አካባቢ
ያንዣበበውን ጉም
በሕይወት መኖሬ፥ አለው ትልቅ ትርጉም።
@Bookfor
@Bookfor
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ኢድ ሙባረክ!
@Bookfor
@Bookfor
ታላቁ ሰው አረፉ !
ለሃገር ትልቅ ባለ ውለታ የነበሩት ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።
ዶክተር ተወልደ ለሃገራቸው ሲደክሙ ከኖሩ ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነበሩ ።
ደራሲ ዘነበ ወላ "የምድራችን ጀግና" በሚለው መፅሃፉ የዶክተር ተወልደን ንግግር እንዲህ ሲል አስፍሮታል ።
“ሰው ሁሉ ሰው ነው። ሰው ሁሉ የትም ይፈጠር እኩል ነው የሚለውን እምነት … በተጨባጭ እያሳዩ ነው ወላጆቼ ያሳደጉኝ።
አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሕይወቴን ሳስበውና የተጓዝኩበትን መንገድ ዞሬ ሳየው የቤተሰቦቼ አመራር የምወደውና የምቀበለው ነው። የሰው ልጆች እምነት እምነቴ ነው። የሕዝቦች ሁሉ ተፈጥሮአዊ ዕውቀትን የገበየሁት በዚህ ዓይነት መንገድ ነው። ማንንም ሰው በእኔ ሕይወት ውስጥ እምነቱን አከብርለታለሁ። እኔም እንዲሁ አመለካከቴን እንዲያከብሩልኝ እፈልጋለሁ። በዚህም አመለካከት ዓለምን ሀገሬ አድርጌያለሁ። ”
ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር
ነፍስዎ በሰላም ትረፍ🙏
@Bookfor
@Bookfor
''.....ሰው ሲታመም የምንጠይቀው ከቋጠሮ ሰሐን ጋር ነው... ሰው ሲታሰር ' እግዚአብሔር ያውጣህ ' የምንለው ከፍትፍት አገልግል ጋር ነው ....አራስ የምትጠይቀው ከፔርሙዝ አጥሚት ጋር ነው ... የክርስትና አባታችን ለፋሲካ አክፋዩን የሚጠብቀው ድፎ ዳቦ ና አረቄ ነው ...እዝንተኛ የምናስተዛዝነው ሰባት እንጀራ ከአንድ ሰሐን ወጥ ጋር ነው ...ሟች የምንሸኘው ከገንቦ ጠላና ከለምለም እንጀራ ጋር ነው ...የቅዱሳንና የመልአክታት ተራዳኢነት የሚጎበኘን በስማቸው ከዘከርን ነው...ሰዕለታችን በሬ ወይም በግ ነው ...ሰርጋችን ፣ ልደታችን፣ እርቃችን፣ ሹመታችን፣ አምልኳችን፣ የሚበላ ነገርን ሙጥኝ ያሉ ናቸው ... ...ሌላው ቀርቶ አንድ ሰው ተምሮ ሲመረቅ ይዘን የምንሄደለት ስጦታ ብዕር ወይንም መጽሐፍ አይደለም ፤ ኬክ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ...ነው ። በሽተኛ ስትጠይቅ ከብርቱካንና ከሙዝ ይልቅ መጽሐፍ መውሰድ እንደማላገጥ ይቆጠራል ። ጊዜውን ይገፋበት ዘንድ መጽሐፍ ማበርከት በሽተኛው እንዳይድን ከመመኘት እኩል ነው ። ለኛ ለኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ከባዶ ገበታችን በስተዚያ የተቀመጡ ትርፍ ነገሮች ናቸው ። መጻሕፍት የሚያስፈልጉት ገበታችን ሞልቶ ከገነፈለ በኃላ ነው ብለን በይነናል። ገበታችንም አይሞላ ፤ መጻሕፍቱም አይነሱም ። ያልተረዳነው ቢኖር ለገበታ መትረፍረፍ ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ መጻሕፍት አቋራጭ መንገድ መሆናቸውን ነው ።እንዴት ታዲያ ማንበብ መብላትን ይቅደም ? መቼ ይሆን ከምንኮራባቸው ባህሎቻችን በላይ ማንበብ ባህላችን ሆኖ የምንታወቅበት ናየምንኮራበት?......'''''
አለማየሁ ገላጋይ
@Bookfor
@Bookfor
ይሔ ስራ ንግድ አይደለም!
ይሔ ስራ ስም ሸመታ አይደለም!!
ይሔ ስራ ማንገቻም ሆነ መንጠላጠያ አይደለም!!!
💧ሀውልት እድሳት ነው!
💧አንድ ጨዋ ልጅ ለአባቱ መንፈስ ማረፍ የሚያደርገው የነብስ ይማር መታሰቢያ ነው!!
ደሞ ደሞ.....
💧ተዘግቶ የከረመን እልፍኝ ከፋፍቶ እንደማናፈስ ያለ ነገር ፤ አቧራ የለበሱ የሳሎን ጌጦችን እንደመወልወል ያለ ነገር ፤ ርጥብ ቀጤማ ጎዝዝዝጎዝዝዝዝ አድርጎ በጠጅ ሳርና አደስ ሽታ መሀል በእጣን ጢስ ስር ደጅ ደጁን በስስ ፈገግታ እንደመመልከት ያለ ነገር......!!!
እንደዚያ ያለ ነገር🖐🍻
ዋሸሁ?
© ጋሽ ናደው
Thank You Dawit Tsige!
@Bookfor
@Bookfor
Am I the tree? Am I the river?
፟ዛፍን ነው ወይ የኔ ህይወት? ግንዱን ነች ወይ እቺ ነፍሴ? አዲስ ፍሬ አዲስ ቅጠል ይበቅላል ብስል ጥሬው በገላዬ። በጋ ክረምት ደግሞ ይረግፋል ቀን ጠብቆ ። ሰው ይመጣል ሰው ይሄዳል በእድሜዬ።
ዛፉን ነሽ ካልከኝ አደራ፦ ከጎኔ የበቀለ ሁሉ ሳያብብ አይክሰም ። እስኪረግፍ ፀደይ መጥቶ ይፍካ ይመርበት አብሮኝ ሲኖር። ላካፍለው ካለኝ ሁሉ። እሱ እንጂ የኔ እንግዳ እኔ መሄዱን አውቃለሁና። ሲረግፍም ቀን ጠብቆ ‘ሂድ መጣሁ’ ልበለው ። እኔስ ብሆን ከመሬት ጎን የበቀልኩ ቅርንጫፍ አይደለሁ?
ምን ቢራራቅ ፍጠረተ አለሙ ሁሉ መርገፍ በሚሉት የጋራ ሃቅ የቆመ አይደለ?
፟ወንዙን ነው ወይ ይሄ ልቤ? የጠለቀኝ የጠለቅኩት ይሰራኛል ያለድካም ።የነካሁት የታከከኝ መልኬ ይሆናል ።
ወንዝ ነሽም ካልከኝ አደራ ፦ የሰው ልጅ ንፅህና እንደውሃ ብዙ ባለመፍሰስ አይለካምና በወንዝነት ትርምስ ውስጥ ስፈስ በመንገዴ ከምገጨው ተራራ ስር የምንጭነትን ንፅህና አቅምሰኝ። የወደደኝ ሁሉ ሊጠጣኝ አይጠየፈኝ። ከመቀመስ ኋላ የምጠላ የምተፋ አታድርገኝ።
ዛፍን ነው ወይ የኔ ህይወት? ወንዙን ነው ወይ ይሄ ልቤ?
إن معي ربي سيهدين
©Newal Abubeker
@Bookfor
@Bookfor
ቅዳሜን በአዲስ መጽሐፍ የመምጣት ብሥራት መጀመር መልካም ዜና ነው። ጋዜጠኛው ታምሩ ከፈለኝ Tamiru Kefelegn አዲስ መጽሐፌ መንገድ ላይ ነው ብሎናል።
@Bookfor
@Bookfor
የቱ ጋ ነው ጫፉ?
(በእውቀቱ ስዩም Bewketu Seyoum )
አየሩን ሲሞላው፤ ድቀት እና ሽንፈት
እንኳን ባጭር ታጥቆ፥ ዱር ጥሶ መሸፈት
ጉልበት ይፈትናል ፤ አይንን ከድኖ መክፈት ::
በውሀካታው መሀል፥ አንቀላፋን ቆመን
ሳንለፋ ደከመን፤
የት ጋ ነው ምእራፉ
የቱ ጋ ነው ጫፉ ?
-ይሄ ዳገት ዘመን ::
@Bookfor
@Bookfor
"እድሜ መገስገሱን ከንቱ ሰው ዘንግቶት፣
ነገ አልፎልኝ ይላል ማለፉን ረስቶት፣
አይቀር መንፈራገጥ ያሆድ እስኪሞላ፣
ወድቃ እስክትሰበር ህይወት እንደሸክላ
ጣራና ግድግዳው በወርቅ ቢሰራ፣
ገንዘብ ተቆልሎ ቢመስል ተራራ፣
በከፋው ጨለማ በዚያ በሞት መንገድ፣
ተከትሎ አይሄድም ሃብት ስጋ ዘመድ፣
ያለው ከሌለው ጋር ተካፍሎ እንደመብላት፣
ለምን ይሰስታል እድሜ አይለውጥም ሃብት፣
የሌለው ዘመዱን ሸኝቶት በጥርሱ ፣
ችጋር ይዞት ሲሞትው ማልቀሱ።"
ነፍስ ይማር
@Bookfor
@Bookfor
#ካሲናው_ጎጃም .... Coming Soon...🎶 💚‼️
"ድግሱን ደግሶ አይነግርም አዋጅ
አልፎ ሒያጁ ሁሉ ሰተት ነው እጅ
ደልቂ...ደልቂ...ደልቂ...ደልቂ...
እኔ እያለሁልሽ እንደ ፀሐይ ሳቂ"
ካሲና ~ምንም እንኳን የገጣሚውና ሚዚቀኛው የሰጠው ትርጉም ቢኖርም ካሲና የተለያየ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን፣ ለምሳሌ፡- ጅምር ፣ የመጀመሪያ፣ መሞከሪያ ..አንዳንዴም የማሳረጊያ ፣ የመጨረሻ ... ወዘተ ሊሆንም ይችላል .!
"ካሲና" ..
"የፍጥረት ጅምር
የአፍላጋት መፍለቂያ
የዮቶር ሞገድ፤
ካሲናው ጎጃም ነው
ምድሪቱ ምጣድ።"
ሲል ይጀምራል፣ ካሲና የመጀመሪያ የሚል ትርጉም አለው። የብዙ ነገር መጀመሪያ፣ የጥበብ፣ የፍጥረት፣ የጀግንነት፣ የእውቀት፣ የፈጠራ መጀመሪያ.....፣ የነገሮች ሁሉ ማሳረጊያ...ሲሆን ፥ በሁለቱም አምድ ስናየው ደግሞ "አልፋና እና ኦሜጋ" የሚል ትርጉም ይኖረዋል..! አስቻለው ስለጎጃም በትክክል በመዝፈን "ካሲና" መሆንክን እንደምታሳየኝ እምነቴ ነው።"
Aschalew Fetene Ardi
©Getu Temesegen
@Bookfor
@Bookfor
ለመላው የክርስትና እምነት የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን እና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የልባችሁ መሻት የሚሞላበት የፍቅርና የፀጋ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን::
መልካም በዓል!
@Bookfor
@Bookfor
sometimes later became never! አንዳድ ግዜ ቦሀላ ወይም ነገ መቼም ላይሆን ይችላል!
ብዙ የሰው ልጅ በኪሱና በባንክ አካውንቱ ካለው ገንዘብ ምን ያክል እንደቀረው ያውቃል ነገር ግን ከህይወት አካውንቱ የቀረውን ግዜ ማንም አያቅም፡፡ ለዚህም ነው መልካም ትሩፋቶችን ለመተው ቀጠሮ መስጠት የሌለብን ይቅር ማለት ካለብን ዛሬ እንባባል ፣ መርዳት ካሰብን ዛሬ እናድርገው ፣ ሰውን መውደድም ዛሬ ላይ ሆኖ ነው፡፡ ይህንን ስናረግ ብቻ ነው ከጸጸት የምንድነው አለበለዛ የቢሆንስ ኖሮ እስረኞች እንሆናል፡፡
መባ
@Bookfor
@Bookfor
ዒላማህን ምታ
__________________
ውሃ በተሞላ ድስት አንዲት እንቁራሪት ብንጨምር እና ከዛም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር ፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች።
የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች። የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ደረጃ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል ማትችልበት ደረጃ ስለሚደርስ እራሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ፤ ትሞክራለችም ፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም። ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና ወድያው ትሞታለች፡፡
እንቁራሪቷን ምን ገደላት ???
አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል ፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም። እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን እቅም ማጣቷ ነው።
አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል፤ ግን እስከ መች ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማውቅ ይሳነናል።
አንዳንዴ ነገሮችን እንለምዳቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታዩናል፤ በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳለመድናቸው ቢገባንም ማመልጥና መውጣት የማይቻለን ሰአት ይሆናል።
በጥፋት/ወንጀል መንገድ ውሰጥም ስንሆን እንዲሁ ነው፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡
ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን ፍፃሜው ግልፅ ነው፡፡ ከሙቀቱ መውጣት ካልቻልን ከእሳት እንደማንወጣ ግልፅ ነው። እናም ለውሳኔ አንዘግይ !!!
ምንጭ | ከመጻሕፍት ዓለም ገጽ