ለልተደረሰላቸው . . . !
ማህበራችን ካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከሠብዓዊ ድጋፍ ጥምረት ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም በየሺ ደበሌ አካባቢ ለሚገኙ ከ30 በላይ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች የምግብ ፍጆታ እና ለንጽህና መጠበቂያ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ቤት ለቤት በመሄድ የማካፈል ስራውን በተሳካ ሁኔታ ማካሄድ ችሏል፡፡
በዚህም በጎ ተግባር ላይ በቀናነት ያገዙንን #የሠብዓዊ_ድጋፍ_ጥምረት እና ትብብር ሲያደርጉልን የነበሩትን የኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 8 ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊና ሰራተኞችን #በማህበራችን_ስም_ለማመስገን እንወዳለን፡፡
ተባብረን ይሄንን ጊዜ እናልፈዋለን!
#ኢትዮጵያ_ብዙ_ይገባታል !
#ኢትዮጵያ_ብዙ_ይገባታል!
#ኮሮና_ቀልድ_አይደለም_ራስዎን_ይጠብቁ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር
1000293521801
የዳሽን ባንክ የሂሳብ ቁጥር
0026017157011
📞 0972102935
📞 099174 0321
አድራሻ፡- 6 ኪሎ ጃንሜዳ ግቢ የአ.አ ወጣቶች ፌዴሬሽን የሚገኝበት ህንፃ ቢሮ ቁጥር 4
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የማህበራችን አባላትና በመላው አለም ለምትገኙ ሁሉ ይህ የረመዷን ወር መልካም መልካሙን የምንሰማት ደግ ደጉን የምናደርግበት የተቀደሰ ወር እንዲሆን ካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ይመኝላችኋል።
ረመዷን ከሪም !
#ኢትዮጵያ_ብዙ_ይገባታል!
የፌስቡክ ፕሮፋይሎትን በዚህ የአድዋ ማሳመሪያ በማሳመር በዓሉን ያክብሩ!
👇 ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
http://www.facebook.com/profilepicframes/?selected_overlay_id=3009457909106037
ተጀመረ ተጀመረ ተጀመረ ...
አሁንም ደግመን እናስታውሶት...!!!
ያለን ቦታ ውስን ነው ...
ትኬቱ መሸጥ ተጀምሯል..!!
ፈጥነው በእጅዎ ያስገቡ ...!!
በካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር አዘጋጅነት የተሰናዳው "ጥበባዊ በጎነት በአድዋ" የተሰኘው የጥበብ ምሽት የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም በሀገር ፍቅር ቲያትር የሚያካሂድ ሲሆን #ገቢው_የአረጋውያንን_መኖሪያ_ለመጠገን_ይውላል ...!
እርሶም በዚህ የጥበብ ምሽት ላይ በመታደም እየተዝናኑ የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያበረከቱት ዘንድ በክብር ተጠርተዋል....!
የመግቢያ ዋጋ:- 99.99 ብር ብቻ
ትኬቱን
#በዳሽን_ሁሉም ቅርንጫፎች
#በአሞሌ
#በሜዳቻት
#በሸክላ
#በቴሌግራም @AmoleChatBot
እንዲሁም
በተመረጡ ቦታዎች
ተስፉ ቡና (5 ኪሎ)
ኤዞፕ መጽሐፍት መደብር(ፒያሳ)
ጃዕፈር መጽሐፍት መደብር(ሜክሲኮ)
የማርያም የስጦታ እቃ መሸጫ(መገናኛ መተባበር ህንፃ)
ብሔራዊ ዙሪያ በሚገኙ መጽሐፍት መደብሮች ትኬቶች ይገኛሉ።
ያለን ውስን ቦታ ስለሆነ ፈጥነው ትኬቱን በእጅዎ ማስገባትዎን አይዘንጉ...!!
#ኢትዮጵያ_ብዙ_ይገባታል!!
#የአረጋውያን_ቤት_ሲጠገን_ነበርኩበት ይበሉ!
ቀድመው ቦታ ለመያዝ በዚህ ይመዝገቡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdN_huigAv5zt7j4yrcARNRcKfLnu5kSdLLXVSWM0oHrXxmHA/viewform?usp=sf_link
ይደውሉ...
0972102935 / 0922735759 / 0991740321

አዋጅ አዋጅ አዋጅ ..!!!
ደጉ ንጉሳችን እምዬ ሚኒሊክ ይህንን የክተት አዋጅ አውጀዋልና ልብ ብለህ አድምጥ .!
አንተ የሀገሬ ሰው.. ወራሪ ጠላት አይኑን አፍጥጦ ድንበርህን ሰንጥቆ እመሃል ሀገር ለመግባት በገሰገሰ ጊዜ ስጠራህ አሻፈረኝ ሳትል እንደተከተልከኝ.. አሁን ደሞ ለበጎ ስራ አብረኧኝ ትዘምት ዘንድ ጠርቼሀለሁ ...
ልጆቻችን በችግር ምክንያት በብርድ በዝናብ በፀሀይ የሚሰቃዩ አረጋውያንን ቤት ለማደስ ሲሉ ደማቁ ታሪካችን አድዋን በሀገር ፍቅር ቲያትር የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሹማምንት፣ የጥበብ ሰዎች ከያኒያን እና ሀያሲያን በተገኙበት በጠላታችን ኢጣሊያ ላይ የተቀናጀነውን ድል ሊዘክሩ ቆርጠው ተነስተዋል።
እናም .. መልካም ማድረግን የመሰለ ሸጋ ነገር የለምና ይህንን መልካም ተግባር ለማከናወን ሲጠሩህ አትለግም፣ ተገኝላቸው በዛውም አይዟችሁ ከጎናችሁ ነኝ ልትላቸው ይገባል።
ግዴለህም በጀ በል ለመልካም ስራ መቼም ቢሆን አትዘግይ... መቼ አልኩህ? የካቲት 16 በደንብ አድርገህ ጣፈውማህ... ደሞም ሰው መርዳት መረዳዳት ያደግንበት የኖርንበት የአያት ቅድመአያቶቻችን ወግና ባህል ነው።
እነሱም ደግ ናቸው.. ዘመነኛውን ነገር ልብ ብለው ይዘውታልና ለዝግጅቱ ቀን መቀመጫ እንዳታጣ ቀድመህ ልትመዘገብ ትችል ዘንድ ከዚህ በታች ያኖሩልህን ማስፈንጠሪያ ጠቁመህ ተመዝገብ..!
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdN_huigAv5zt7j4yrcARNRcKfLnu5kSdLLXVSWM0oHrXxmHA/viewform?usp=sf_link
ካሻህም ደውለህ ሃሎ በላቸው ካሲዮፒያ ብለው በቀደመች ንግስታችን ስም ይጠራሉ፣ አድራሻቸውን ልስጥህማ 0972102935 አልበያም 0922735759 .. ብትቀር ማርያምን እቀየምሃለው..!!
"ጥበባዊ በጎነት በአድዋ"
የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም
124ኛውን የአድዋ በዓልን በሀገር ፍቅር ቲያትር ከታዋቂ ሰዎች፣ ደራሲያን፣ ገጣሚያን እና ሌሎች የጥበብ ሰዎች ጋር በመሆን እየዘከርን ቁም ነገር እንሰራለን!
👉 ፉከራና ሽለላ
👉 ዲስኩሮች
👉 ግጥሞች
👉 ወጎች
👉 የአንድ ሰው ቲያትር
👉 እና ሌሎችም ....
የእርስዎ በፕሮግራማችን ላይ መታደም የበርካታ አረጋውያንን ቤት በብቃት እንድናድስ ድጋፍ ይሆነናል... መቅረት አይደለም ማርፈድ ያስቆጫል!
በታሪካዊው የጀግንነት እና የድል በዓል ታጅበን ሌላ ድል እናስመዘግባለን!
ቀድመው ቦታ ለማስያዝ እንዲረዳዎት ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ ወይም በምስሉ ላይ የሚገኘው ባርኮድ ስካን በማድረግ ሊመዘገቡ ይችላሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdN_huigAv5zt7j4yrcARNRcKfLnu5kSdLLXVSWM0oHrXxmHA/viewform?usp=sf_link
ካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ሰብዓዊነትን እያስቀደመ ማድረግ በሚችለው አቅም ሁሉ ከሀገራችን ህዝቦች ጎን በመቆም የተለያዩ የበጎ ፈደኝነት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
አሁን ያለንበት ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የደም እጥረት ያጋጠመበት ወቅት በመሆኑ እና የእኛም የ3 ወርሃዊ የደም ልገሳ ቀን የደረሰ ስለሆነ የፊታችን ግንቦት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ #አካላዊ_ርቀትን #የአፍና_አፍንጫ_መሸፈኛ_ጭምብል እና #የእጅ_ጓንት እና ሌሎች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን አጠቃቀም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባደረገ መልኩ ለወገኖቻችን ደም የመለገስ እና ህይወትን የማስቀጠል በጎ ፈቃደኝነቱን በድጋሚ ያካሂዳል።
ስለሆነም በዚህ ዙር ደም መለገስ የምትችሉ እና ፈቃደኛ የሆናችሁ የማህበራችን አባላት እሁድ ግንቦት 2፣2012 ዓ.ም ስታዲየም በሚገኘው ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት እንድትገኙ ጥሪያችንን ከአደራ ጭምር ለማስተላለፍ እንወዳለን።
#ኮሮና_ቀልድ_አይደለም
#ጥንቃቄ_አይለየን!
#ኢትዮጵያ_ብዙ_ይገባታል!
0972102935
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በአብይ ሐይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም!
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።"
የሉቃስ ወንጌል 24 : 5
ለመላው የክርስትና እምነተ ተከታዮች በሙሉ
መልካም የትንሳዔ በዓል እንዲሆን እንመኛለን!
#ካሲዮፒያ_የበጎ_አድራጎት_ማህበር
🔔 በዓሉን ሲያከብሩ ጥንቃቄ እንዳይለየዎት 📣
ካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር 124ኛውን ዓመት የአድዋ የድል በኣል ለመዘከር እና የአረጋውያንን ቤት ለማደስ የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም በሀገር ፍቅር ቲያትር የተደረገው የጥበብ ምሽት ይህንን ይመስላል !
አክብራችሁን ስለተገኛችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን!
አድዋ ይክበር!
አድዋ ይዘከር!
አድዋ ለዘላለም ይኑር !
መልካም በዓል!
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም የሀገሬ ጥቁር ሰማይ... ለዛሬ መቆሜ ግልጽ መስዋዕትነት
የካቲት ሚካኤል መቼ ተከበረ፣
ዶማ ይዞ ዋለ ሰው እየቆፈረ፡፡
በኢጣሊያ ንጉሳዊ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ልዑል መወለዱን አስመልክቶ በግራዚያኒ ትዕዛዝ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በገነተ ልዑል ቤተ መንግሰት እንዲሰባሰቡ ተደረገ።
ግራዚያኒ በዚህ ዕለት በዐዋጅ ለጠራቸው ምንዱባን የሚወረውረው ምፅዋት ኢትዮጵያዊያን "በከባድ ግብር የሚያስጨንቀን ገዢ ሒዶ በስጦታ አንቀባሮ የሚያኖረን መሪ መጣልን" ብለው እልል እንዲሉ ነበር ስሌቱ።
ጀግኖቹ ኢትዮጵያዊያን ሞገስ አስገዶምና አብርሃ ደቦጭ፣ ይሕ የፋሽስት ደባ ተገልፆላቸዋል።በወቅቱ በአስተርጓሚነት ምክንያት ለጣልያኖች የነበራቸውን ቅርበት የአገራቸውን መዋረድ የማይሹ ነዲዶች መሆናቸውን የሚያሳዩበት አጋጣሚ እንዲሆን ወሰኑ።
የነበራቸው የድሎት ኑሮ አላሳሳቸውም። በአፍ የጣልያን ወገን፣ በልባቸው ግን የኢትዮጵያቸው ዐርበኞች ነበሩ። ከሌሎቹ ዐርበኞች ከስምዖን አደፍርስ፣ በጅሮንድ ለጥይበሉና መሰሎቻቸው ጋር በመሆን በምፅዋት የድሃ ኢትዮጵያዊያንን ቀልብ ለመማረክ የሚጥረውን ፋሽስት ድርጊት ለማጨናገፍ ወሰኑ። ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን ግራዚያኒን መገዳደር በሕይወት ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን አላጡትም።ግን ሕይወታቸውን ለአገራቸው ክብር ለመክፈል አልሳሱምና ጀግኖቼን ከልቤ አከብራቸዋለሁ።
የጣልያን ትክክለኛ አረመኔያዊ ገፅታ በዚች ዕለት ይበልጥ ተጋለጠ።ለጥቁር አመፀኛ ጥይት አናባክንም ያሉ ወራሪዎች በርካታ ቤተሰቦችን ቤት እየዘጉ የእሳት እራት አደረጉ።የተረፉትን በአካፋና በዶማ ጨፈጨፋ። ለዚህ ነው ብዙዎች ቀኑን "የአካፋው ሚካኤል" ብለው የሚጠሩት።የተማሩ ኢትዮጵያዊያንና መነኮሳት ዋና ዒላማ ተደርገው በያሉበት ተለቀሙ። ከ2ሺሕ በላይ መነኮሳትን ጨምሮ ከ30ሺሕ በላይ ወገኖቻችን በሰማዕትነት አለፋ። ጭካኔው የዐርበኝነት ትግሉን እንዳይበርድ አድርጎ አጋጋመው።ተዘናግተው የነበሩ ኢትዮጵያዊያን፦
አረ ጥራኝ ጫካው አረ ጥራኝ ዱሩ"፣
ላንተም ይሻልኻል ብቻ ከማደሩ፣
ብለው ጫካ ገቡ። የመጨረሻው ጣልያን ጎንደር ቁልቋል በር አካባቢ ተቀጥቅጦ ድራሹ እስከሚጠፋ ድረስ ኢትዮጵያ ለፋሽስት ሁሉ ቋያ ሆነች።
ከዚህ ጊዜ አንስቶ የካቲት 12 ቀን ለኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያን ለሚወዱ በሀዘን የሚያስታውሱት ቀን ሆነ። በአባት አያቶቻችን ብርቱ ትግል የሀገር ነጻነቷ ከተመለሰ በኃላም እነዚህን በኢጣሊያ የግፍ አገዛዝ የተገደሉ ሰማዕታትን ለማሰብ 6 ኪሎ ገነተ ልዑል ቤተመንግሥት በር ላይ የየካቲት 12 ሆስፒታል እና ከጎኑም የመታሰቢያ ሐውልት ተሰራ።
ክብር ሕይወታቸውን ለሀገራቸው ያለስስት ለሰጡ ሁሉ።
#ኢትዮጵያ_ብዙ_ይገባታል!
#የካቲት_16_በሀገር_ፍቅር_እንገናኝ
"ለራሴ ቢሆንስ...?" ብለው አስበው ያውቃሉ ???
እርግጥ ነው አሁን ፍጹም የጤንነት ስሜት እየተሰማህ ይሆናል ... ፍጹም ሰላምም ሆነህ ይሆናል .. ግን በደቂቃዎች ውስጥ ምን እንደሚከሰት አታውቅም .... ድንገት ባላሰብከው መንገድ #ደም_መውሰድ ቢጠበቅብህና ያንን ደም ለማግኘት ችግር ቢገጥምህ .... ማንን ማማረር የምትችል ይመስልሃል..???
አንተ እንኳን ለጊዜው ባያስፈልግህ በየሆስፒታሉ በርካታ እናቶች፣ አረጋውያን፣ ወጣቶች እና ህፃናት ደም ይፈልጋሉ ...
#ደም_በልግስና የሚገኝ እንጂ የሚሸጥ ባለመሆኑ አሁንም የኔ እና ያንተ ደም ከእነዚህ ወገኖች ያስፈልጋቸዋል።
ና .. ደማችንን ሰጥተን ሕይወት እናድን ...!!
የካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር 3ኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም ከሌሎች ማህበራቶች ጋር በመሆን ዛሬ የካቲት 1 በብሔራዊ የደም ባንክ ግቢ ውስጥ ይደረጋል።
#ኢትዮጵያ_ብዙ_ይገባታል!
አዋጅ አዋጅ አዋጅ ..!!!
ደጉ ንጉሳችን እምዬ ሚኒሊክ ይህንን የክተት አዋጅ አውጀዋልና ልብ ብለህ አድምጥ .!
አንተ የሀገሬ ሰው.. ወራሪ ጠላት አይኑን አፍጥጦ ድንበርህን ሰንጥቆ እመሃል ሀገር ለመግባት በገሰገሰ ጊዜ ስጠራህ አሻፈረኝ ሳትል እንደተከተልከኝ.. አሁን ደሞ ለበጎ ስራ አብረኧኝ ትዘምት ዘንድ ጠርቼሀለሁ ...
ልጆቻችን በችግር ምክንያት በብርድ በዝናብ በፀሀይ የሚሰቃዩ አረጋውያንን ቤት ለማደስ ሲሉ ደማቁ ታሪካችን አድዋን በሀገር ፍቅር ቲያትር የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሹማምንት፣ የጥበብ ሰዎች ከያኒያን እና ሀያሲያን በተገኙበት በጠላታችን ኢጣሊያ ላይ የተቀናጀነውን ድል ሊዘክሩ ቆርጠው ተነስተዋል።
እናም .. መልካም ማድረግን የመሰለ ሸጋ ነገር የለምና ይህንን መልካም ተግባር ለማከናወን ሲጠሩህ አትለግም፣ ተገኝላቸው በዛውም አይዟችሁ ከጎናችሁ ነኝ ልትላቸው ይገባል።
ግዴለህም በጀ በል ለመልካም ስራ መቼም ቢሆን አትዘግይ... መቼ አልኩህ? የካቲት 16 በደንብ አድርገህ ጣፈውማህ... ደሞም ሰው መርዳት መረዳዳት ያደግንበት የኖርንበት የአያት ቅድመአያቶቻችን ወግና ባህል ነው።
እነሱም ደግ ናቸው.. ዘመነኛውን ነገር ልብ ብለው ይዘውታልና ለዝግጅቱ ቀን መቀመጫ እንዳታጣ ቀድመህ ልትመዘገብ ትችል ዘንድ ከዚህ በታች ያኖሩልህን ማስፈንጠሪያ ጠቁመህ ተመዝገብ..!
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdN_huigAv5zt7j4yrcARNRcKfLnu5kSdLLXVSWM0oHrXxmHA/viewform?usp=sf_link
ካሻህም ደውለህ ሃሎ በላቸው ካሲዮፒያ ብለው በቀደመች ንግስታችን ስም ይጠራሉ፣ አድራሻቸውን ልስጥህማ 0972102935 አልበያም 0922735759 .. ብትቀር ማርያምን እቀየምሃለው..!!
ካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር የፊታችን የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም የ124ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ የድል በዓልን በማስመልከት ታላቅ የጥበብ ምሽት በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።
በዚህ ዝግጅት የታዳሚዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት #ማን ቢጋበዝ ይመርጣሉ ስንል ጥያቄ አቅርበናል።
እርስዎ ሊያዩት የሚወዱትን ሰው ከዚህ በታች በሚገኘው የአስተያየት መስጫ ሊያስቀምጡልን ይችላሉ!
@cassiopeiamediabot
@Cassiopeiamediabot
*እናመሰግናለን ! *
ከጥበብ ምሽቱ የሚገኘው ገቢ የአረጋውያንን ቤት ለመጠገን ይውላል!!!