🗣እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብከዋለን! ትክክለኛ የሆኑ የወንጌል አስተምህሮዎችን መሰረት ያደረጉ፦ ዝማሬዎች፣ ትምህርቶች፣ ስብከቶች፣ ምስክርነቶች፣ የሪቫይቫል ታሪኮች፣ መንፈሳዊ ዜናዎች፣ እንዲሁም መንፈሳዊነታቸውን የያዙ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ! ለወዳጅ ጋደኞቻቹ #ሼር በማድረግ ይጋብዙ! አስተያየት @ChristianMezmur_bot ላይ ፃፉልን✍ ሁሌም ከኛ ጋር ስለሆናቹ እናመሰግናለን!
ዝማሬ🎙"ኢየሱስ ሰላሜ ነው"
ዘማሪ👥 Mesay ft Kingdom Sound
Size💾 14MB
የተለቀቀው📅 Aug 2023
ርዝመት⏰ 14፡56
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል አስራ ሁለት(ሜርሲ✍️)
"እሷ አልነገረችኝም እኔ ነኝ ፈጣሪ ሲወደኝ የደረስኩባት::አንተ ግን እንዴት ትደብቀኛለህ!?... ከእኔ ከወንድምህ ይልቅ እሷ በለጠችብህ?"
"ማቲ... አሁን ግራ አጋባሀኝ ምንድነው የደረስክበት!?"
ማቲያስ እጁን አጣጥፎ ተመቻችቶ በመቀመጥ አተኩሮ ሲመለከተው ቆይቶ:-
"ሶስና የሆነ የደበቀችኝ ነገር እንዳለ አውቅ ነበር ግን ምን እንደሆነ ልደርስባት አልቻልኩም::ከአንተ ጋር የሆነ ችግር እንዳለ እንደዛው::ያን ቀን ሁለታችሁ ስትጨቃጨቁ እንደድንገት እያለፍኩ ያወራችሁትን ሰማሁ እና ይበልጥ ጥርጣሬዬ ከፍ አለ::ያኔ በእራሴ መንገድ እሷንም አንተንም መከታተል ጀመርኩ::እናም ደረስኩበት::" ሚልኪያስ እንደተመታ ሰው በድንጋጤ ውስጥ ሆኖ ይመለከተዋል::ማቲያስ ውሃውን ተጎንጭቶ ከጠረጴዛው በመመለስ::
"እናም መጀመሪያ ላይ ስሰማ..."
"ማቲ ልነግርህ ብዙ ጊዜ ፈለግኩ ግን..."
"አስጨርሰኝ::ሁሉንም ነገር አውቃለሁ::አንተም የማታውቀውን እሷ ጋር ያለውን ሚስጥርም እንደዛው::ስልኳ ላይ ከጓደኛዋ ጋር የተፃፃፈቻቸውን ሁሉንም ነገር አይቻለሁ::አንተ እሷን ከእኔ ለመለየት ምን ያህል ትለፋ እንደነበር::በምን ታስፈራራህ እንደነበር::እኔን ያጠመደችኝ ካናዳ ለመሄድ እና ለገንዘብ እንደሆነ... ፍቅረኛ እዛው ድሬ እንዳላት... የማያልቅ ጉድ...." በእረጅሙ ተነፈሰ::ሚልኪያስ ሊመጣ ያለውን ነገር ለመቀበል እራሱን አዘጋጀ::
"እንደዛ ከሆነ ሁሉን ደርሰህበታል::የሰራሁት ኃጢያት እስካሁን የህሊና እረፍት ነስቶኝ ብዙ ሲሰቃይ ነበር::እናም ይቅርታ ልጠይቅህ እንደማልችል አውቃለሁ::እንደፈለግክ አድርገኝ አውቄ እንዳላደረግኩት ብቻ እወቅልኝ::አንድ አንድ ቀን መልሰን ማጥፋት ብንችል ያንን ቀን ከሕይወቴ በሰረዝኩት ነበር..." እንባው ከዓይኑ ሲፈስ በእጁ በመጥረግ ተደግፎ ተቀምጦ ዓይኑን ወደ ሌላ አቅጣጫ አሸሸ::
"አሁንም የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ::ጥፋትህን ለመሸፋፈን አለመሞከርህ::ምን አይነት ጠንካራ ሰው ብትሆን ነው ይሄን ሁሉ ስታደርግህ ችለህ የቆየሐው ብዬ እያሰብኩ ነበር::እና አንተ ቀድመህ ብትነግረኝ ብዙ ነገር ይበላሹም ነበር::እግዚአብሔር ምን ያህል ቤተሰባችንንም እንደሚወድ ያወኩት በዛ ነው::" ሚልኪያስ ግራ በመጋባት ዓይኑን ወደ እሱ አደረገ::
ማቲያስ ስልኩን አውጥቶ በመክፈት በጠረጴዛው ገፋ አደረገለት::ሚልኪያስ ግራ እንደተጋባ ተመለከተው::
"አንብበው ሶስና ከጓደኛዋ ጋር የተፃፃፈችው ነው::ወደ ስልኬ አስተላልፌው ነው::" ሚልኪያስ ስልኩን አነሳ::
* * *
#ከወራት በፊት
"መጠጥ እንደምትጠጣ አላውቅም ነበር::" ሚልኪያስ ከቆመበት ዘወር ብሎ አያት እና ዓይኑን ወደ ውጪው መለሰ::
ሶስና የወይን ብርጭቆ በእጇ እንደያዘች ወደ እሱ በመቅረብ ከጎኑ ቆመች::
"ለምን ክፍሌ ገባሽ!?"
"አሁን ግን ክፍልህን ተሻግሬ በረንዳው ላይ ነው ያለሁት::" አለች ፈገግ ብላ::
"ሁሌም ቤታችሁ ላይ እንደዚህ አይነት ድግስ ይኖራል?"
"በዓመት አንዴ... የቤተዘመድ ፕሮግራም አለን::አሁን ግን ወደመጣሽበት ትመለሺ!"
"ለምንድነው የምትጠላኝ ግን?"
"የሚወደድ ነገር ስለሌለሽ::ሥራሽ ሁሉ ክፉ ስለሆነ::"
"እ.... እናም ለወንድሜ ሲመጣ እነግረዋለሁ::ያኔ ከእኛ ሕይወት ትወጪያለሽ::"
ጥርሶችዋን ብልጭ አድርጋለት ዝም ብላ ከቆየች በኋላ::
"ወይን ክፍልህ ላይ አስቀምጬልሃለሁ::ዘና በልበት::" ብላ በክፍሉ በኩል አድርጋ ወጣች::ቆይቶ ወደ ውስጥ ሲገባ ግማሽ የደረሰ ወይን ከነጠርሙሱ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጦ አየ::ብርጭቆውን ሲያይ አልቆበት ነበር::ካቅማማ በኋላ ብርጭቆው ላይ እየቀዳ አልጋው ላይ በመቀመጥ መጠጣት ጀመረ::ቆይቶ ሁሉም ነገር ብዥ አለበት እና አልጋው ላይ በመጋደም ዓይኑን ጨፈነ::
* * *
"ከዛ በኋላ ሶስና እንዳትናገር ወጥመድህ ውስጥ ከተተችህ::ጠዋት ስትነሳ ከጎንህ አገኘሃት::" ሚልኪያስ ስልኩን ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ::
"እና.... ምንም አልተፈጠረም?"
"ምንም አልተፈጠረም::ያነበብከው ነው የሆነው::እዛ ቤተሰቦቿ ፊት ስጠይቃት ሁሉንም በአንደበቷ ነው የተናገረችው::"
"ቤተሰቦቿ!?"
"አዎ... እሷን ለመሸኘት ቤተዘመድ ሁሉም ተሰብስቦ ነበር::ያኔ ፍቅረኛዋን ጠርቼ ሁሉንም ነገር ስነግራቸው በእነርሱ ፊት አመነች::ገንዘብ ስለሆነ የምትፈልገው እዛው ገንዘቧን ሰጥቼ ጥዬ መጣሁ::"
ሚልኪያስ ባለማመን እና በመገረም እየተመለከተው:-
"የምርህን ነው ወንድሜ!?"
"አዎ... ሰው ሁሉ የዘራውን ነው የሚያጭደው::አሁን እሷ የምታጭድበት ጊዜ ነው::እና ለምን አልነገርከኝም ያልኩህ ከምን እንደምጀምር ግራ ስለገባኝ ነበር::እንጂ እንኳንም አልነገርከኝ::
አሁን ግን ሌላ የቤት ሥራ አለብኝ::ወንድሜ ለምን መጠጥ መጠጣት እንደጀመረ ማወቅ እፈልጋለሁ::"
* * *
"በክርስቶስ... እና ያ ሁሉ ድራማ ነበር!?" አለ ሚኪያስ የተፃፃፉትን አንብቦ እንደጨረሰ::
ሚልኪያስ አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀለት::
"ና እስኪ እቀፈኝ::" አለው እጁን እየዘረጋ::ሚልኪያስ ከአልጋው ተነስቶ አቀፈው::
"አሁን ምን ያህል ሸክም እንደቀለለኝ::"
"ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ወንድሜ::እግዚአብሔር ዛሬም ለአንተ እየተዋጋልህ ነው::" አለው እንዳቀፈው::
* * *
"....ምን አይነት ልጅ ልበልሽ.... ከእራሱ አስበልጦ ለእኛ የሚኖር::ለቤተሰቡ ለውጊያው ከፊት የተሰለፈ ሰው ነው::የሚመጣው ነገር ሁሉ እሱ ላይ ነው የሚያርፈው::ቃሉ ላይ እንደሚለው የምርም የክርስቶስ ልብ ያለው ሰው ነው::"
ሰሎሜ ስታዳምጠው ቆይታ ፈገግ ብላ:-
"እንደዚህ አይነት ሰው እዚህ ምድር ላይ እንዳለ አላውቅም ነበር::የምር እድለኛ ነህ::እና ለምን ከጌታ ቤት እንደወጣ ጠይቀሀው ታውቃለህ?"
"ብዙ ጊዜ::ግን ሊነግረኝ ፍቃደኛ አይደለም"
"ከመጠየቅ በዘለለስ?"
"ማለት?"
"ማለትማ ብዙ ጊዜ ከቤተክርስቲያን ሰዎች ሲቀሩ ዛሬ ቸርች አንሄድም?... ከቤተክርቲያን እየጠፋህ ነው... ክርስቲያን አይደለህ?" የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቀን የውስጣቸውን ቁስል ቀስቅሰን እልህ ውስጥ ከተናቸው የሆነ ጊዜ ላይ ደግሞ ሰልችቶን እንተዋቸዋለን::ግን ለምን እንደማይሄዱ ለመጠየቅ ትዕግስቱ የለንም::እሁድ ቀን ሲደርስ 'ለምን ዛሬ አትሄድም?' ከማለት ውጭ ሌሎች ቀናት ላይ አንጠይቃቸውም::አንዴ እኮ ነው ከቤቱ የወጡት... ከወጡ ቆይተው እኛ እሁድ እሁድ ላይ ደጋግመን እንጠይቃቸዋለን::እነርሱም' አይ ዛሬ አልሄድም' ይሉንና ይተዉናል::እና እሁድን ጠብቀህ ሳይሆን መነሻውን እንዲነግርህ ሥራዬ ብለው አውራው::ያለበለዚያ ወንድምህን ታጣዋለህ::"
ሚኪያስ ተደንቆ ሲሰማት ቆይቶ ከወንበሩ ተነሳ የውስጡ መረበሽ ፊቱ ላይ ይነበባል::
"ወንድሜን ማናገር አለብኝ ይሄ ከእኔ እንዴት ተሰወረ!?" ፊቱን አዙሮ ከቢሮዋ ሲወጣ ከወንበሯ ተደግፋ ትመለከተዋለች::
ይቀጥላል...
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙" በህልውናህ"
ዘማሪት 👥 Kenean Abiy
Size💾 5MB
የተለቀቀው📅 Sep 2023
ርዝመት⏰ 5:22min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
"አንተስ ምን አለበት ትንሽ እንኳ ብትነካው ልጄ::" ስልኩ ሲጠራ አየውና የጠቀለለውን ምግብ ከሳህኑ እየመለሰ ወደ ጆሮው አደረገ::
"ዛሬ ከባንዳ ጋር አየኋችሁ..ጥሩ ጊዜ አሳልፋችኋል መችም::"
"ምንድነው የምትቀባጥረው!?"
"አረ አትቀልድ ከእኔ ጋር ድብብቆሽ ባይሆን ምን ምን አወራችሁ?... ተስማማህላቸው!?"
"አንተ ልጅ... እኔ ዛሬ ማንንም አላገኘሁም::ከእንቅልፍህ ስትነቃ ደውልልኝ::" ስልኩን ጆሮው ላይ ዘግቶት ከጠረጴዛው በማስቀመጥ መመገቡን ቀጠለ:-
"ሰላም አይደለም?" አለች አስቴር::
"ሰላም ነው እማ... ባይሆን እራትሽን ብትበይ ይሻላል::" ስልኩ ላይ መልእክት ሲገባ በአንድ እጁ ከፍቶ አየው::
"እኔ ላይ ስልክ መዝጋት!?..ባይሆን የሆነ ነገር ካደረገህ ብዬ ፎቶ አንስቼ ነበር ቴሌግራም ላይ ገብተህ እየው::" ይላል::ግራ እንደተጋባ ወደ ቴሌግራም ገብቶ የተላከለትን ፎቶ በመጫን ውሃውን ተጎንጭቶ ዝቅ ሲል የጠጣው ውሀ ትን አደረገው አስቴር ተደናግጣ ከአጠገቡ ደረሰች::ዓይኑን ማመን አቅቶት ፎቶዎቹን ደጋግሞ ተመለከተ::ቀን ሚኪያስ የለበሰው ልብስ ትዝ ሲለው ብድግ አለ::
"አይሆንም... ይሄ ቀልድ ነው::"
"ምንድነው ልጄ ምን ሆንክብኝ?"
"እማዬ መጣሁ::" ከቤቱ እየወጣ ወደ ሚኪያስ ደወለ ስልኩ ዝግ ነበር::
"አታደርገውም ሚኪ... አታደርገውም::" መኪና ውስጥ ከፍቶ በመግባት ገብሬ በሩን ሲከፍትለት ከግቢው እየነዳ ወጣ::
ይቀጥላል...
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
. ልዩ የትምህርት ጊዜ
| እውነተኛ መስዋዕት |
Revealed Gospel
With Seifu Zerihun
Season -01 EPISODE 07
Amazing Preaching Program
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
( ለፕሮፋይላችሁ እና ለወዳጆቻችሁ ለመላክ ) HD
🌼እንኳን ለ2016 አመተ ምህረት በእግዚአብሔር ቸርነት በሰላም አደረሳችሁ።
ከፊታችን ያለው አመት በእግዚአብሔር ቃል በኑሮ በምልልሳችሁ ሁሉ ከፍ የምትሉበት እንደ ሊባኖስ በእግዚአብሔር ላይ ስር የምትሰዱበት ፤ መልካም መአዛችሁ ገኖ የሚወጣበት ፤ በአለም ላሉትና ለጠፉት መፍትሄ የምትሆኑበት እግዚአብሔርን ደስ የምታሰኙበት ፤ አቅዳችሁ የሚሳካላችሁ ፤ ፀሎታችሁ የሚመለስበት የደስታ አመት ይሁንላችሁ።
#QouteVerse #Bduvlm #HappyNewYear #2016
መልካም አዲስ አመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Faithful Witness of the Kingdom
ታማኝ የመንግሥቱ ምስክሮች
እናያለን | እንመሠክራለን | እንጸናለን
Follow Us On INSTAGRAM YOUTUBE
( ለፕሮፋይላችሁ እና ለወዳጆቻችሁ ለመላክ ) HD
“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።”
መዝሙር 65፥11
“You crown the year with Your bounty and goodness, and the tracks of Your drip with fatness.”
Ps 65፥11
#QouteVerse #Bduvlm #HappyNewYear #2016
መልካም አዲስ አመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Faithful Witness of the Kingdom
ታማኝ የመንግሥቱ ምስክሮች
እናያለን | እንመሠክራለን | እንጸናለን
Follow Us On INSTAGRAM YOUTUBE
ዝማሬ🎙" መመኪያዬ"
ዘማሪ 👥 መስፍን ጉቱ
Size💾 6.4MB
የተለቀቀው📅 Sep 2023
ርዝመት⏰ 7:30min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"ፀናው"
ዘማሪት 👥 ዝናሽ ታያቸው
Size💾 5.4MB
የተለቀቀው📅 Sep 2023
ርዝመት⏰ 5:54min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል ስድስት(ሜርሲ✍️)
"ስማኝ አንተ ጥሩ ክርስቲያን እንደሆንክ አውቃለሁ::እና ይቅርታን በነፃ እንጂ...." ሳቁ ንግግሯን እንድተገታው አደረጋት::ግራ በመጋባት ተመለከተችው::
"ጥሩ ክርስቲያን!?" አለ ሳቁን እንደገታ::
"ባይገባሽ እንጂ ክርስቲያን ላይ ቅጥያ አያስፈልገውም ነበር::ጥሩ ክርስቲያን.. በጣም ጥሩ ክርስቲያን.... መጥፎ ክርስቲያን.. ብላ ብላ በጣም ይደንቁኛል ክርስትና ላይ ቅጥያን የሚጨምሩ ሰዎች::ክርስትና አንድ ትርጉም ብቻ ነው ያለው::የሆነ ሆኖ እግዚአብሔር ለፈተናችን መውጫ በር ያዘጋጅልናል እናም ለወንድሜም የሆነው ይሄ ነው::ማነው ንገሪኝ?"
"ይቅርብህ... ወንድምህን ግን አስፈታዋለሁ::"
"ወንድሜን አንቺ ባታስወጪውም.." ከጠረጴዛው ስልኩን እያነሳ:-
"እስካሁን ያወራነው አንቺን በእሱ ቦታ ለመተካት በቂ ማስረጃ ነው::"
"ወይኔ ማኪ.." ጠረጴዛውን በእጇ ደበደበችው::ፈገግ ብሎ ይመለከታታል::
"እናንተ ቤት ሁላችሁም ጌም ትወዳላችሁ ልበል?"
"እንዴት!?"
"አባትህ ከሌሎች ሴቶች ጋር እያደረ ልጁ ሲነቃባት ልጁን ለማሳሰር እኔን ይጠቀማል.... እህትህ ቤተክርስቲያን እያለች ጭፈራ ቤት ቤቷ አድርጋለች... ወንድምህ በአባቱ ምክንያት ሴቶችን ለመበቀል እራሱን ያጣል... እሱ ሞቶ ቤቱን ለመታደግ ላይ ታች ይላል::ምን አይነት እንቆቅልሽ የሆናችሁ ሰዎች ናችሁ!?"
ሚኪያስ የሰማውን ማመን አቅቶት ብዙ ሊጠይቅ አስቦ አፉ ግን አልታዘዝ አለው::
"አባትህ የተጫወተብኝ ይበቃል::ከፈለግክ የድምፁን ቅጂ ለፍርድ ቤቱ መስጠት ትችላለህ::የእኔ ሕይወት ከዚህ በላይ እንዲመሰቃቀል የምትፈልግ ከሆነ::" ቦርሳዋን ይዛ ተነሳች::
"አንድ ነገር ማወቅ ያለብህ::" ቀና ብሎ አያት:-
"ሚልኪ ቢፈታ እንኳ አባትህ ያስገድለዋል::" ስትሄድ ዓይኑ እሷ ላይ ነበር::ምንም ማድረግ አቅቶት ነበር::
* * *
ሚኪያስ ቀና ብሎ ማክዳን ወደ መኪናዋ ውስጥ ስትገባ ተመለከታት::
"ክሱን ለምን እንዳነሳችው ባውቅ ጥሩ ነበር::" አለች ሕይወት ከኋላው ቆማ::ዘወር ብሎ ሲያያት ማክዳ ያለችው ጆሮው ላይ አቃጨለ::ምንም ሳይላት ወደ መኪናው ገባ ።ሕይወት ልትገባ ስትል በሩን ዘጋው::መስታወቱን ዝቅ አድርጎ:-
"ከነ እማዬ ጋር ሕጂ!... እኛ የሆነ ቦታ ደርሰን እንመጣለን::" ፊቱን ስታየው አስፈራት::
"እሺ ግን አትቆዩ... ይጠብቋችኋል::"
አንገቱን በእሽታ ነቅንቆ መስታወቱን በመዝጋት መኪናውን አስነስቶ በመንገዱ ነዳው::
"ደህና ነህ ግን?" አለው ሚልኪያስ በጥርጣሬ በመስታወቱ በኩል እያየው::
"ደህና ነኝ::"
"ደህና ነህ.... መዋሸት ተጀመረ... ጥሩ ለውጥ ነው::"
"ሚልኪ.. እባክህ ምንም አትበለኝ::"
ሚልኪያስ ትከሻውን ሰብቆ ዝም አለ::ትንሽ ከሄዱ በኋላ ሚልኪያስ ከተደገፈበት ቀና ብሎ::
"መኪናውን አቁመው!" ድምፁ ትእዛዝ የተቀላቀለበት ነበር::
"ምን እያልክ ነው!?"
"መኪናውን አቁመው አልኩህ እኮ!" ጮሀበት::ተደናግጦ ከመንገዱ ዳር አቆመው::በሩን ከፍቶ በመውረድ ወደ ፊተኛው በር በመሄድ በሩን ከፈተው::
"ምን እየሆንክ ነው!?" ሚኪያስ ግራ ተጋብቶ ያየዋል::
"ወደዛኛው ወንበር ተጠጋ!" ጮሀበት::
"ለምን!?"
"ያልኩህን አድርግ ሚኪ... ይቆጭሃል በኋላ::"ወንበሩን ቀይሮ ተቀመጠ::ሚልኪያስ ገብቶ በሩን በመዝጋት መኪናውን አስነስቶ ጥቂት ከነዳ ባኋላ ድምፁን አውጥቶ መሳቅ ጀመረ::ሚኪያስ ጤንነቱ አጠራጥሮት ይመለከተዋል::
ሚልኪያስ ከሳቁ ጋር እየታገለ ይመለከተዋል::
"ጤነኛ ነህ አንተ ልጅ?"
"ወንድሜን አንድ ቀን ከጎኑ ብጠፋ ሁሉ ነገሩ ተቀያይሮ ሳገኛው ምን ላድርግ?... ምን እንደሰማህ ባላውቅም በዚህች ነገር ብቻ እንዲህ ከተረበሽክ ትልቁን እውነት ብትሰማ ምን ልትሆን ነው!?... ወንድሜ ያለነው አባት ልጁን አሳልፎ የሚሰጥበት ዘመን ላይ ነው... ለዚህች ዓለም እንኳን ደንግጠህላት ተጀንነህባትም የምትሸነፍልህ አይነት አይደለችም::" ሚኪያስ ወንድሙን አስተውሎ ተመለከተው::ፅናቱን ሲመለከት ሰው መሆኑን ተጠራጠረ::
"ታውቅ ነበር?" አለው በተረጋጋ ድምፅ::
"እኔ ከማውቀው ኢምንቷን ነው የምታውቀው ወንድሜ.... ኢምንቷን ብቻ::"
"እና ምን ልታደርግ አሰብክ?"
"አሁን አንተም ተቀላቅለሃል እኮ::ቤታችንን ለመታደግ ምን እናድርግ ነው የሚባለው::"
"አንተ ልጅ ግን ያምሃል?... እኔ ስለአንተ ነው እያወራሁ ያለሁት::አንተ ስለ ቤት ታወራለህ::"
"እኔስ የቤቱ አንድ አካል አይደለሁ?.... ግን የምንወስነው ውሳኔ እኔን ተኮር ሳይሆን ቤቱን ተኮር መሆን አለበት::አንድ ማክልልህ ነገር አባዬ ኮንትሮባንድ ንግድ ላይ አለበት::እና ህብረት አላቸው::የዚህ ሁሉ መነሻ ያለው እዛ ቦታ ነው::"
* * *
"እኔን ግራ የገባኝ እንዴት ክሱን ልታነሳልህ ቻለች?"
"መፈታቴ ያሳሰበሽ ይመስላል::" ሶስና ልትጎርሰው የነበረውን ወደ ሳህኑ መለሰች::
"እንዴት እንዴት ነው የምትናገራት አንተ ልጅ?" ማቲያስ ነበር::
"መች ነው የምትመለሱት ወንድሜ?" ማቲያስ ከተቀመጠበት ተነሳ ::
"የእኛ እዚህ መሆን ይሄን ያህል አስጠልቶሃል ማለት ነው!?"
"እሱን አንተ አልህ::" ሚኪያስ ተደናግጦ ተመለከተው::አስቴር ግራ በመጋባት ሁለቱንም አፈራርቃ ትመለከታለች::እጁን በሶፍት በመጠራረግ ከጠረጴዛው እየጣለ:-
"እኔ ላይ ቅኔ!?"
"ቅኔውማ አልገባህ ሲልህ እኮ ነው በግልፅ መናገር የጀመርኩት::"
ማቲያስ ሲሄድ ሶስና ተከተለችው:-
"ማቲ.." አስቴር ከተቀመጠችበታ ተነሳች::
"እማዬ ተያቸው ይሂዱ እውነቱ እስኪገባው ነው::ከዚህ በኋላ እነርሱ ይነሳሉ እንጂ እኔ አልነሳም::" አለ ኤሊያስን እየተመለከተ::
* * *
"ቆይ ምን እያደረግክ ነው?" አለው ከክፍሉ እንደገባ::
"እየሳልኩ::" አለ ሚልኪያስ ግማሽ ካደረሰው ስዕል ላይ ዓይኑን አድርጎ::
"በእግዚአብሔር ሚልኪ ትዕግስቴን እየተፈታተንክ ነው::" አለ አንድ እጁን ወገቡ ላይ በማድረግ::መሳሉን አቁሞ ብሩሹን በማስቀመጥ ወደ እሱ ከነወንበሩ ዞረ::
"ከዚህ በኋላ ድብብቆሹ ከቀጠለ ስትነቃ እኔን ጨምሮ ሁላችንንም አጥተሀን ታገኛለህ::ከአንተ ውጭ ሁሉም ሰንሰለቱ ላይ አሉ::መጨረሻ ላይ ሰይጣን ሁሉን ካሳጣህ በኋላ ወደ ነብስህ ይመጣል::እመነኝ አንድ እርምጃ ባልሄድን ቁጥር ሞት አንድ እርምጃ ወደ እኛ ይጠጋል::እኛ ጋር ለመድረስ ደግሞ ስንት እርምጃ እንደቀረው አናውቅም::" ሚኪያስ ከአልጋው ጫፍ ተቀመጠ::
"ይሄ ሁሉ ለምን ግን?"
"ወንድሜ ይሄን ጥያቄ አትጠይቅ::እኔም ደጋግሜ ጠይቄ ነው ከቤቱ የወጣሁት::እዚህ ቤት አንተ እና እማዬ ብርታታችሁ ከተወሰደ ይሄ ቤት መጨረሻው ይሆናል::"
በሩ ሲንኳኳ ሚኪያስ ሄዶ ከፈተ ሶስና ነበረች::
ይቀጥላል..
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"ስዕለቴን እከፍላለሁ "
ዘማሪ👥 እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ
Size💾 90MB
የተለቀቀው📅 Sep 2023
ርዝመት⏰ 8min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል አምስት
"ወንድሜ ይሄን እንደማያደርግ ልቦናሽ ያውቀዋል::"
"ወንድምሽን አታውቂውም ማለት ነው::ታዲያ ቦርሳው እሱ ክፍል ውስጥ ምን ይሰራል!?"
"ሰው ይሆናላ... እሱን ሊጎዳው የሚፈልገው ሰው::"
"ህ... ቀልደኛ::" መኪናዋ ውስጥ በመግባት ከፊቷ ስትሄድ ተመለከተቻት::
"ማናት ይቺ ሴት!?" አለ ሚኪያስ ከአጠገቧ ቆሞ መኪናው ላይ ዓይኑን አድርጎ::
"ጓደኛዬ ናት::"
"ለሚልኪስ?"
"አላውቅም::በየት እንደተገናኙ እራሱ አላውቅም::እንዴት ሆነ... ምን አሉት?" አለች ፊቷን ወደ እሱ አዙሯ::
"ፍርድ ቤት ይቀርብና የሚሉትን እንሰማለን::" አስቴር ከእስር ቤቱ ቅጥር ግቢ በመውጣት እነርሱ ወዳሉበት ቀረበች::ድንጋጤዋ ፊቷ ላይ ይነበብ ነበር::ኤሊያስም ተከትሎ ወጥቶ ፈጠን ብሎ ከአጠገባቸው በመድረስ:-
"እዚህ ብርድ ላይ ምንም አንሰራም::ጠበቃውን አናግሬለታለሁ::ነገ እንደሚሆን ይሆናል::"
"ልጄን ጥዬማ እኔ ቤቴ አላድርም::"
"ለሌባ ልጅሽ ነው ብርድ ላይ የምታድሪው!?"
"አባዬ..." አስቴር ከአፏ ልታወጣው የነበረውን ቃል መለሰችው::
"ልጅህን ነው ሌባ የምትለው!?" ሚኪያስ በመገረም እና በቁጣ ተመለከተው::
"ታዲያ እጁ ላይ የተገኘው ወርቅ በስጦታ ተሰጥቶት ነው::"
"ይሆናል.... እንጂ ወንድሜ ወርቅ እና ብር አጥቶ ሰው ጋር አይሄድም::ሞልቶ የተረፈው ሰው ነው::አንተ ግን ታሳዝናለህ::እማዬ እንሂድ::"ሚኪያስ ከፊት ሲገባ ሕይወት እና አስቴር ደግሞ ከኋላው ገቡ::መኪናዋን በዓይኑ ከሸኛት በኋላ ኤሊያስ ስልኩን ሊደውል አወጣ::
* * *
ሚልኪያስ ከሰጠው የስጦታ ስዕል ላይ ዓይኑን ሳይነቅል ለደቂቃዎች ቆሞ ተመለከተ::ወገቡን እንደያዘ በእረጅሙ ተንፍሶ ወደ አልጋው ተመልሱ ከጫፉ ተቀመጠበት::አይኖቹን ጨፍኖ ከቆየ በኋላ ስልኩን ይዞ ከክፍሉ በመውጣት ወደ ቀጣዩ ክፍል አመራ::በሩን ከፍቶ ሲገባ አስቴር ለፀሎት ተብሎ ከተዘጋጀው ምንጣፍ ላይ ተንበርክካ አገኛት::ሊመለስ ካለ በኋላ ሀሳቡን በመቀየር በሩን ከኋላው በመዝጋት ከአጠገቧ ሄዶ ተንበረከከ::
* * *
ሚኪያስ ዓይኑን ሲገልጥ አስቴር ከሶፋው ሥር በጉልበቷ ተንበርክካ ፀጉሩን ስትዳብሰው አገኛት::
"ክፍሉ የተለየ ሰላም አለው::ፊትሽ ከትላንትናው ፈክቷል::" አለ ፈገግ ብሎ የእጇን መዳፎች እየሳመ::
"ይሄን ቤት ሳሰራው ይሄ ክፍል የፀሎት ክፍል እንዲሆን የወሰንኩትም ለዛ ነው::አባቴ ፊት ካለቀስኩ እና ከነገርኩት ሌላ የሚያስጨንቀኝ ነገር አይኖርም::አሁን ሚልኪ የሚወደውን ቁርስ ልስራለትና አብረን እንሄዳለን::"
"ሰራተኛዋ የለችም!?"
"አይ.... በእጄ የሰራሁትን ነው እንዲበላልኝ የሚፈልገው::"
"እንደዛ ከሆነ እኔም ላግዝሻ::"
* * *
"እማዬ ይሄ ልጅ እዚህ መሆኑ መልካም ይመስለኛል::እኔ አልቅሶ ያባበጠ ፊት እየሳልኩ ነበር የመጣሁት::"
"ለምኑ ነው የማዝነው!?.... የወደቅኩበትን ሳላውቀው ነው የነጋው::" አለ ፈገግ ብሎ::
"ፀሎቴ ተሰምቶልኛላ::" አለች አስቴር እየሳቀች::
"አሃ... እዛች ክፍል ላይ ነው እማዬ ያደርሽው መችም::"
"ወንድምህ አብሮኝ ሲፀልይ ነበር::" ወደ ሚልኪያስ ተደንቆ እየዞረ::
"ምን ብለህ እንደፀለይክ መስማት አለብኝ::"
"ሰዓት አልቋል::"
"የነዚህ ሰዓት ደግሞ ደቂቃም እንኳ መች አወራን::" የተቋጠረለትን ምግብ እየወሰደ:-
"በሉ ነገ እራት ከእናንተ ጋር ነኝ::" ሕይወት እና አስቴር ተሰናብተውት ሲሄዱ ሚኪያስ ወደ ኋላ ቀርቶ በአትኩሮት ተመለከተውና:-
"እንላደረግከው አውቃለሁ::ልጅቷን ግን ማግኘት እፈልጋለሁ::"
"ስልኬ እኮ ክፍሌ ላይ ነው ያለው::"
"እና ያለፍቃድህ!?"
"ስልኳን ብቻ ውሰድና መልሰህ ዝጋው::" አለው ፈገግ ብሎ::
"እስኪ ከፍርድ ቤቱ በፊት ቀድመህ ደውልልኝ... መስማት ያለብኝ ነገር አለ መሰለኝ::"
"ሰዓት አልቁአል::"
"እደውልልሃለሁ::"
* * *
የሚልኪያስ ክፍል በመግባት አልጋው ላይ የተቀመጠውን ስልክ አንስቶ(ፓተርኑን) በመክፈት ወደ ስልክ ቁጥር ማውጫው ገባ::በሩ ሲከፈት ስልኩን እንደያዘ ቀና አለ::ሶስና ስታየው ደንገጣ ልትወጣ ስትል:-
"ሚኪ ነኝ ሶሲ::" አላት:: ሶስና እራሷን ለማረጋጋት እየሞከረች:-
"ደሕና ነህ ሚኪ.... እኔ እኮ... ሚልኪ መስሎኝ::መች እንደምለያችሁ እኮ::"
"አልፈርድብሽም::እዚህ ስልኩን አስቀምጦ ስለሆነ የሄደው ልወስድ ብዬ ገብቼ ነው::"
"እ..... አስቲ እኮ እንድጠራህ ልካኝ ክፍልህ ላይ ሳጣህ ጊዜ ነው ወደ እዚህ የመጣሁት::ምሳ ስለቀረበ...."
"እሺ መጣሁ..." አለ::ስትሄድ ግራ ተጋብቶ ከቆየ በኋላ ወደ ስልኩ ዝቅ አለ::መልእክት ማስቀመጫው ላይ ሶስና የሚለውን ፈለገ::
* * *
"ስንት ዓመት ነው እንድታሰር የምትፈልገው?.... አራት ዓመት አምስት...."
"ከማስገድልህ ይሻልሃል::ይሄ የመጨረሻህ ማስጠንቀቂያህ ይሆንሃል::"
ሚልኪያስ ኤሊያስን እያየ ፈገግ አለ:-
"ባይሆን እኔን እና ሂዊን ለገንዘብ ብላ ከምትሸጠን ሴት አድነሀናል::እኔን ለማስተማር ልጅነቴ ተሰጥቶህ ነበር::አሁን የምማርበት ጊዜ ላይ አይደለሁም::አባዬ እንኳን በስርቆት ነብስ በማጥፋት ወንጀል ብታሰር በፈለግኩት ሰዓት መለቀቅ እችላለሁ አሁንም እዚህ ያሉት ልጆች ስለወደድኳቸው አብሬ ልሁን ብዬ ነው::እጄ ከአንተ እጥፍ ይረዝማል::" ተመልሶ ሲገባ ኤሊያስ በቁጣ እና በመገረም ተመለከተው::
* * *
ማክዳ ሰላም ብላው ከአጠገቡ ተቀመጠች::
"የሳለሽን ወረቀት እኔ ክፍል ላይ ጥሎት ነበር... አሁን ነው በደንብ ያስተዋልኩት::"
"ወንድምህ ጥሩ ሰዓሊ ነው::"
"ልክ ነሽ.... እእ..... ቤተሰቦችሽ እዚህ ናቸው?"
ያልጠበቀችው ጥያቄ ስለሆነ ደንገጥ አለች:-
"አዎ... ምነው!?"
"አይ የልጃቸው ሰርግ ሲበላሽ ምን ሊሰማቸው እንደሚችል እያሰብኩ::" ድንጋጤዋ ከፍ አለ::
"አልገባኝም...."
ከጠረጴዛው ደገፍ እያለ:-
"ፍቅረኛሽ ቢኒያም የአንቺን ሌላኛውን ማንነትሽን ቢያውቅ... ዛሬ ሽማግሌዎችን የሚልክ ይመስልሻል?.... ማለቴ ከአሜሪካ የመጣው ምንም የማታውቀውን ጨዋዋን ፍቅረኛውን ሊያገባ ነው ብዬ ነው::"
"ምንድነው የምትፈልገው ከእኔ!?"
"ጥሩ ጥያቄ...ወንድሜ ሰረቀ ስለተባለው ወርቅ እናወራለን::"
ይቀጥላል......
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"ሠንበትበት አለ"
ዘማሪ👥 Biniyam Ayele
Size💾 32MB
የተለቀቀው📅 Aug 2023
ርዝመት⏰ 7:41min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"Praise "
ዘማሪ👥 Brandon Lake ft Elevation Worship
Size💾 4.7MB
የተለቀቀው📅 Aug 2023
ርዝመት⏰ 5min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል ሶስት(ሜርሲ✍️)
"ሚልኪ አልጨረስክም?" ሚክያስ ከበሩ ሲገባ ሶስቱም ዞረው ተመለከቱት::ሙሉ ነጭ ሱፍ ለብሶ ነበር::"
"በፈጣሪ እንዴት ነው ያማረብህ!?" አለው ማቲያስ ኮሌታውን እያስተካከለለት::
"አመሰግናለሁ ወንድሜ::ግን ተሰብስባችሁ ምን እያደረጋችሁ ነው?"
"አስቲ እንድጠራችሁ ነግራኝ መጥቼ ነው::" አለች ሶስና ቅልስልስ ብላ::
"እኔ ደግሞ እልፍ ስል የጭቅጭቅ ድምፅ ሰምቼ::" አለ ማቲያስ እጁን እያነሳ::
"ሸሚዚህን ልቆልፍልህ ወይስ?" ሚልኪያስ ዝቅ ብሎ ሸሚዙን ተመለከተ እና ወደ ቀልቡ ተመልሶ መቆለፍ ጀመረ::
"በሉ ኑ!" ብለው እንደወጡ ሚኪያስ ቀረብ አለና ጃኬቱን እያለበሰው:-
"ምን ተፈጥሮ ነው?" አለው::
"ምንም..." አለው ዝቅ እንዳለ::
"ምንም.... መርሳት አለብህ ሚልኪ::"
"እሷ እዚህ እያለች ነው የምረሳው!?..... ስማኝ ኃጢያትን ለምጄዋለሁ::ወንድሜ ላይ ግን..."
"የአንተ ጥፋት አልነበረም::እሱን ህሊናህም ያውቀዋል::እዛ ምሽት የተፈጠረው የአንተ ጥፋት አይደለም::ስንቴ ልንገርህ ጠጥተህ ነበር::"
"እሷ ግን አልጠጣችም::ሆም ብላ ነበር ከባሏ ወንድም ጋር ለመተኛት አቅዳ የተነሳችው::ያ ማለት እኔ ላይ ያንን ለማድረግ ካልፈራች ሌሎቹ ላይስ.... ወንድሜ ግን ንፁህ ሴት እንደሆነች በልቡ አምኖ ተቀብሏል::"
"እንሂድ.... እየጠበቁን ነው::" ተከታትለው ሲወርዱ ሁሉም ቀና ብለው ተመለከቷቸው::
"ማነው ሚኪ ማነው ሚልኪ::" አለች ሕይወት ሁለቱንም እያፈራረቀች::
ሁለቱም ተያይተው ተሳሳቁ::
"ፀጉሬን ማሳደጌ እና ጆሮዬ ላይ ጌጥ ማድረጌ አሁን ምክንያቴ ተዋጠልህ?"
"የማይሆነውን..."
"እስኪ ባላችሁበት አንዴ ፈገግ::" አለ ካሜራ ማኑ ከደረጃው ሥር ቆሞ::
* * *
"ያቺ ማናት?"
"የቷ" አለ ሚልኪያስ ቀና ብሎ::
"ከአባዬ ጋር::" ሚኪያስ ፈገግ አለና:-
"የሥራ ባልደረባው ትሆናለች::"
"ትሆናለች?.... አንተ እዛ አይደል የምትሰራው... እንዴት አታውቃትም?"
"እኔንጃ.... እዛ አይቻት አላውቅም::" ከአፉ ያደረሰውን የእንጀራ ጥቅልል ከሳህኑ እየመለሰ ሚልኪያስን በጥርጣሬ ተመለከተው::
"ለምንድነው እንደዚህ የምትመለከተኝ?"
"የት ነው የምታውቃት?"
"ማንን?" ደንገጥ አለ::
ሚኪያስ እጁን ያዘውና ከወንበሩ ጎትቶ በማስነሳት ሰፊውን ሳሎን እያቆራረጡ ወደ ደረጃው መውጣት ሲጀምሩ አስቴር ከፊታቸው ቆመች::
"ገበታ እረግጣችሁ የት ነው የምትሄዱት?... ሰዉ እኮ የመጣው..."
"እንመለሳለን እማዬ::" ብሏት ሚልኪን እንደያዘው ወደ ክፍሉ በመሄድ በሩን ከኋላቸው ዘጋ::
"ያምሃል ሚኪ?"
የምልኪያስ ፊቱ ተቀያይሮ ነበር::
"የት ነው የምታውቃት?"
"ሚኪ... እኔ እኮ ነኝ የጠየኩህ::"
"ምክንያቱም የጠየከኝ ስለምታውቃት ነው::አይደለ..."
"ምን እያወራህ...."
"ሚኪ ነኝ እሺ... እኔ ሚኪ ነኝ::" ጩሀቱ ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ አደረገው::
"የሆነ ሆቴል ላይ ማታ ላይ አይቻቸው ነበር ከአባዬ ጋር::"
"ምን እያደረጉ::"
"እራት እየበሉ.... ከዛ የስራ ባልደረባው ትሆናለች ብዬ ተውኩት::"
ሚኪያስ ግንባሩን አከክ አከክ አድርጎ:-
"ታውቆሃል ግን ሚልኪ.... እንደዚህ አይነት ጥያቄ ስትጠይቀኝ ዛሬ ሶስተኛህ ጊዜ ነው::"
"እኔም ግራ ስለገባኝ ነው የጠየኩህ::በተደጋጋሚ ነው የተለያየ ቦታ ከተለያዩ ሴቶች ጋር የማየው::እኔ ከዛ ድርጅት ከወጣሁ በኋላ አዳዲስ ሰዎች ተጨምረው ይሆን ብዬ አስቤ ነበር ግን በጣም ሲደጋገምብኝ አንተን መጠየቅ ጀመርኩ::"
"ለምንድነው የሆነ ነገር እንደደበቅከኝ እየተሰማኝ ያለው::"
"አይ እንግዲህ... የተሰማህ ሁሉ እውነት አይደለም::ኬኩን አብረሀኝ ትቆርሳለህ ወይስ ብቻዬን ልቁረሰው!?.. እየጠበቁን ነው::"
* * *
"አባዬ አንዴ ላናግርህ?"አለው ሚኪያስ ከኋላው ቆሞ::ኤሊያስ የመኪናውን በር ይዞ ቆመ::
"ምንድነው ሚልኪ .. ችግር አለ?"
"አይ...." መኪናው ውስጥ አስቴርን ሲመለከታት ቀና ብሎ:-
"ማታ አናግርሃለሁ::መልካም ቀን ይሁንላችሁ::" መኪናው ከግቢው ሲወጣ በዓይኑ ተከተለ::
"ማናቸው ልትለው ነው?" ሚኪያስ ከአጠገቡ ቆሞ::
ዞሮም ሳይመለከተው ወደ መኪናው በመሄድ ገብቶ መኪናዋ ከግቢው ወጣ::
"ሚልኪ ግን ደህና ነው!?"
"ምን አውቄ እህቴ... አሁን ወደ መኪናው ግቢ ክላስ እንዳታረፍጂ::"
"ተመራቂ እኮ ነኝ::"
"የሆንሽ እንደሆን... በይ ግቢ..."
* * *
ሚኪያስ ከቤተክርስቲያኑ አዳራሽ ላይ ከመሃል አንዱ ወንበር ላይ ተቀምጦ ከሚልኪያስ ጋር አብረው ያገለገሉበትን ጊዜ ያስባል::
ስልኩ ሲጠራ ከሀሳብ አለም ወጥቶ ከኪሱ ውስጥ በማውጣት ተመለከተው::ሚኪ ይላል::አንስቶ ወደ ጆሮው አስጠጋ::
"የት ሆነህ ነው?"
"ቤተክርስቲያን::" አለው ዝግ ባለ ድምፅ::
"እንዴ ዛሬ ፕሮግራም አለህ?"
"አይ... ዝም ብዬ ልቀመጥ ብዬ..."
"ደሕና ነህ ግን::"
"ከአካሉ ውስጥ አንድ ብልቱ የተቆረጠበት ሰው እንዴት ደህና ይሆናል::"
"ወንድሜ..."
"ባይሆን አንተ ያልከኝን ሳስብ ነበር::ትዝ ይልሃል የፋስኪ ምሽት አድረን እዚህ ወደ ቤት ስንመለስ... እኔ ከእግዚአብሔር ቤት እግሬ ቢወጣ እንኳ ልቤ ይሄን ፍቅር ሊክደው አይችልም ብለሀኝ ነበር::"
"ነበር....."
"ነበር ብቻ አይደለም::ልብህ ሳይሆን እግርህ ነው የሸፈተብህ::እና ከብዙ ጊዜ በኋላ የምፅናናበትን ነገር አገኘሁ::አሁን የት ሆነህ ነው?"
"ሆስፒታል.... ማለቴ... የሆነ ቦታ::እራት አብረሀኝ አትበላም?... ሂዊም አለች::"
"ሆስፒታል ምን ታደርጋለህ?"
"ኡፍፍፍፍ አንተ ደግሞ..... ጨጓራዬን ያመኝ የለ::መድሃኒት አልቆብኝ ልገዛ ገብቼ ነው::"
"ፋርማሲ የለም ታዲያ?"
"ነበር::ግን ሀኪሜንም ማግኘት ነበረብኝ::መድሃኒቱ ብዙም እየተስማማኝ ስላልሆነ::"
"ይሄን ጭንቀትህ ሳታቆም እንዴት ሆኖ መድሃኒቱ ይስራ?"
"እራቱን ተስማማህ?...."
"እንዴታ::"
* * *
"ከእማዬ ምን አጥተህ ነው ግን!?"
"በማያገባህ ነገር ጥልቅ አትበል አንተ ልጅ::አርፈህ ኑሮህን ኑር!" አለ ከሚልኪያስ በላይ ስሜታዊ ሆኖ::
ከጠረጴዛው በእጁ ደገፍ ብሎ:-
"ሚኪያስ ነገሩን ቢደርስበት ምን ሊፈጠር እንዳለ አስበሀዋል ግን!?.."
"እንደዛ አታደርግም::" ድምፁ ወደ ድንጋጤ ተቀየረ::
"ለምንድነው የማላደርገው?... እንዳቆምክ ነበር የነገርከኝ አንተ ግን ከዚያም ከዚህም ማለቱን አልተውክም::እናም ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለመላው ቤተሰቡ ነግሬ የሚሆነውን እናያለን::"
"አንተ ልጅ..."
ከወንበሩ ደገፍ አለና:-
"ይሐው መጡ::" አሉ በፊቱ ወደ ሆቴሉ መግቢያ እየጠቆመ::ኤልያስ ዞሮ ተመለከተ::ሕይወት እና ሚኪያስ አስቴርን አስከትለው እየገቡ ነበር::
ይቀጥላል.......
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"ኢየሱስ ሰላሜ ነው"
ዘማሪ👥 Mesay ft Kingdom Sound
Size💾 14MB
የተለቀቀው📅 Aug 2023
ርዝመት⏰ 14፡56
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል አስራ አንድ(ሜርሲ✍️)
.......
"ቸርች!?... ምን ብሎህ ነው የወጣው?"
"ከእሱ ጋር አታያይዘው.. እኔ ነኝ የጋበዝኩህ::"
ሚልኪያስ ከተቀመጠበት ተነስቶ እጁን የሱሪው ኪሱ ውስጥ ከቶ ጀነን ብሎ ቆሞ ሲመለከተው ቆይቶ:-
"ልቡ ተሰብሮ ለሄደው ሰው... ዴማስን አንስቶ የሚሰብክ እረኛ ባለበት ቤተክርስቲያን ትንሽ ተስፋ ያለበትን ሰው አትጋብዘው::ባይሆን ልቡ ተመልሶ ሰውን ከማየት ኢየሱስን የማየት አቅም ላይ እስኪደርስ ፀልይለት::" ብሎት ወደ በሩ አመራ ሚልኪያስ ከበሩ ደርሶ ዘወር ብሎ:-
"ይቅርታ ተደርጎልኛል አይደል?"
ሚኪያስ ፈገግ ብሎ አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀለት::
"በል ደህና እደር::" በሩን ከፍቶ እንደወጣ ሚኪያስ ስልኩን አንስቶ ቁልፎቹን በመጫን ወደ ጆሮው አስጠጋ:-
"ሄለው ፓስተር.."
* * *
ከቤተክርስቲያኑ መናፈሻ ላይ ሚኪያስ እና የቤተክርስቲያኑ መጋቢ ጎን ለጎን ተቀምጠው ያወጋሉ::
"ይሄን ያለው ሌላ ሰው ቢሆን ለእራሱ ሰበብ እየፈጠረ እንደሆነ አስብ ነበር::ግን ሚልኪያስ ነው::ከእግሬ ሥር ነው ያደገው::ለክርስቶስ የነበረው ልብ በዚህ አንድ ሁለት ዓመት ይለወጣል ብዬ አላስብም::"
"አዎ ፓስተር... እኔም እሺ እንደማይለኝ አውቀው ነበር ግን ይሄን መልስ ከእሱ አልጠበኩም ነበር::እናም ቆም ብዬ እንዳስብ ነው ያደረገኝ::ፓስተር... በዚህ ሰዓት ወንድሜን አባቴን መላው ቤተሰቤን እያጣሁ እንደሆነ ነው እየተሰማኝ ያለው::ብዙ ነገር ተጋርዶብኝ አሁን ሁሉም ነገር ግልጥልጥ እያለልኝ ያለው ለምን እንደሆነ አልገባኝም::"
"ምን አልባት የእግዚአብሔር ጊዜ አሁን ስለሆነ ይሆናል::ኢዮብን አስታውሰው ሁሉም ነገር የመጣበት አንድ ላይ ነበር::እና እግዚአብሔር ለዚህ ጊዜ ሲያዘጋጅህ ቆይቶ አሁን ሁኔታዎችን እየገለጠልህ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ እና ለስጋህ ፋንታ እንዳትሰጠው እባክህን::እያንዳንዱ እንቅስቃሴህ ላይ ክርስቶስን አስገባበት::ምን አልባት እየሰጠመች ያለችውን መርከብ አንተን ተጠቅሞ ሊታደግ ፈልጎ ይሆናል::የሚልኪን ጉዳይ የወጣቶች መሪዎችን አናግራቸዋለሁ... እኔም ከዚህ በኋላ ሥራዬ ቢዬ እይዘዋለሁ::"
"አመሰግናለሁ ፓስተር::"
መጋቢው እጁን ከትከሻው ጣል አድርጎ:-
"እኔ ነኝ የማመሰግንህ::አንተ ባትነግረኝ ቤተክርስቲያኗ ማስተካከል ያለባትን ነገር ዘንግታ ብዙ ሚልኪያሶችን ታጣ ነበር::እስካሁንስ ቀርበን ሳንጠይቃቸው የጠፉብን ስንት በጎች በክርስቶስ አይን ተቆጠሩ::"
* * *
"ምንድነው እማዬ በጣም ደስ ያለሽ ትመስያለሽ!?" አለ ሚልኪያስ ቡናውን እየተቀበላት::
"እማዬ ሁሌ ደስ እንዳላት አይደል?" አለ ሚኪያስ ከፋንዲሻው እየዘገነ::
"አይ.. የዛሬው ለየት አለብኝ::"
"አዎ ደስ ብሎኝ ነው የዋልኩት::ዛሬ የፀሎት ሕብረት ላይ አንተን እያነሱ ሲፀልዩ ነበር::" ሚልኪያስ የፌዝ ፈገግታ አሳይቶ:-
"ዛሬ ከየት ትዝ አልኳቸው ባክሽ!?"
"ለምን ነገ አብረሀን አትሄድም?"
ሚኪያስ ግር ብሎት:-
"ቆይ ይሄን ሰሞን ምን ተገኝቶ ነው ቸርች ቸርች የምትሉብኝ... ወይስ ሚልኪያስ ሊሞት ነው አሏችሁ!?" አስቴር አነሳስታ ልትወስድ የያዘችውን ሳህን ከመሬቱ ጣለች::ሚኪያስ ሮጦ ከአጠገቧ ደርሶ ያዛት::ሁለቱም ደግፈዋት ከሶፋው አስቀምጠው ከአጠገቧ ቁጭ አሉ::ሰራተኛዋ የሳህኖቹን ስብርባሪ እያነሳሳች ሚኪያስ እሷን እያየ:-
"ቆይ እሷ አታነሳሳውም ነበር!?..ሁሉን ነገር ካልሰራሁ የምትይው ነገር አለ::" አለ ቆጣ ብሎ::
"አንተ ደግሞ አትጩህባት!..እማዬ ደህና ነሽ?"
"ደሕና ነኝ... ከእጄ አምልጦኝ ነው::" አለች እራሷን እያረጋጋች::ወደ ሚልኪያስ ዞራ:-
"ሁለተኛ እንደዛ ስትል እንዳልሰማ::"
"እማዬ... ቀልዴን እኮ ነው::"
"ለቀልድም ቢሆን::"
ሚኪያስ ግራ ተጋብቶ ሁለቱንም እያፈራረቀ ተመለከተ::
* * *
ሚልኪያስ ቀለሙን ቀብቶ ሲጨርስ ብሩሹን እንደያዘ ከጀርባው ደገፍ ብሎ ተመለከተ::ሚኪያስ በሩን ከፍቶ በመግባት ከኋላው ሆኖ ይመለከታል::
"የምትስለው ጠፍቶህ ነው?"
ሚልኪያስ ፈገግ ብሎ:-
"ሳልኩኝ እኮ::" አለ::
"ምኑን... እንዳለ ጥቁር ቀለም እኮ ነው የቀባሀው::"
ሚኪያስ ብሩሹን አንስቶ ነጭ ቀለም ላይ በመንከር ከመሀሉ ጠቅ አደረገ::
"ምንድነው ደግሞ እሱ!?"
"ነጥብ::" አለ ከተቀመጠበት እየተነሳ::
"እናንተ ሰዓሊዎች ስትባሉ እኮ::እሺ ምንድነው ትርጉሙ!?"
"እኛ ሰዓሊዎች ለሁሉም ሰው የሳልነውን የማስረዳት ግዴታ የለብንም::" ፎጣውን ይዞ ወደመታጠቢያ ክፍል ገባ::
ሚኪያስ ነጥቡ ላይ ዓይኑን ተክሎ ቀረ:-
"ጥቁር ላይ አንድ ትንሽ ነጥብ... ምን ሊሆን ይቻላል?" አለ ለእራሱ::
* * *
"አዎ በጣም ደህና ናቸው::"
"ማነው?" አለ ሚኪያስ ከደረጃው እየወረደ::
"ወንድምህ.." ከማለቱ ስልኩን ከጆሮው ነጥቆት ወደ ጆሮው አደረገ:-
"አንተ.... እኔም እኮ ድሬ ሄጄ አውቃለሁ::"
"ሚልኪዬ.... በጣም በጣም ይቅርታ ወንድሜ::የምር በእራሴ አፍሬያለሁ::"
"እፈር እንጂ... በጣም ልታፍር ይገባል::"
"አይ እንግዲህ... ሁለታችንም ነው ልናፍርማ የሚገባን::አንተስ መች ደወልክልኝ!?"
ሚኪያስ አይቶት ሳቀ:-
"የማኪ ጉዳይ ትንሽ እረብሾን..."
"እ..ሰማሁ እኮ በጣም ያሳዝናል::"
"ተወው ባክህ.... ሶስና እንዴት ናት?"
"ደህና ናት.... "
"እ... ድምፅህ ልክ አይደለም::ደህና አይደላችሁም?"
"ደህና ነን... ዛሬ ስለምመጣ እናወራለን::"
"ዛሬ?"
"አዎ... ስድስት ሰዓት አካባቢ::እና እነርሱ..."
"እ... እነርሱ ቤተክስቲያን ስለሚሆኑ እኔ እቀበልሃለሁ::ስትደርስ ደውልልኝ::"
"ምንድነው?" አለች አስቴር ነጠላዋን እያስተካከለች::
"ምንም እማ... ማቲ ዛሬ ይመጣል እና ተቀበለኝ ነው ያለኝ::"
"ዛሬ!?... ገና ሳምንት መች ሞላቸው!?"
"እኔንጃ... ምን አልባት እዚህ መጨረስ ያለበት ነገር ሳይኖርበት አይቀርም::"
ሚኪያስ ስልኩን ሲቀበለው ሚልኪያስ ኮሌታውን እያስተካከለለት:-
"አምሮብሃል::እና እንደወጣህ ደውልልኝ::"
"ምን አለበት የጌታ እራት እንኳ ብትገኝ::" አለው ኤሊያስ ወደ እነርሱ እየተቀላቀለ::
"ሰዎች ሌላውን ጊዜ ትዝም ሳይላቸው የጌታ እራት ጊዜ ቤተክርስቲያኗን የሚያጣቡት ነገር ነው የማይገባኝ::የጌታ እራት ትርጉሙ ቢገባቸው በተቃራኒው ይሆን ነበር::ስጋና ደሙ እዳ እንደሚሆንብን የዘነጋነው መሰለኝ::" ኤሊያስ ተረባው ለእሱ መሆኑ ገብቶት በቁጣ ሲመለከተው::ሚኪያስ እና አስቴር በመልሱ ተደንቀው ይመለከቱታል::
* * *
ከሆቴሉ አንድ ጥግ ላይ ማቲያስ እና ሚልኪያስ ተቀምጠዋል።
"ለምንድነው የደበቅከኝ!?" ጩሀቱ አስደንግጦት ከተደገፈበት ቀና አለ::
"ምኑን ወንድሜ!?"
"ስለ ሶስና::" ሚልኪያስ ተደናግጦ አፍጦ ይመለከተዋል::
"ነገረችህ!?" አለው ብዙ ነገር እንደተበላሸ እያሰበ::
ይቀጥላል..
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል አስር(ሜርሲ✍️)
ከመኪናው ውስጥ ሁለቱም ወጡ::ሚልኪያስ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳገኘው ሰው ወንድሙን ከበሩ ጋር ቆሞ ተመለከተው::እራሱን ከፊቱ ያየ እስኪመስል ድረስ ፍፁም ተመሳሳይ ነበሩ::ከጆሮው ላይ የእራሱን ጌጥ ሲመለከት ፀጉሩ እንደእራሱ አድጎ ሲመለከት::ጓደኛው ያለው ነገር እውነት እንደሆነ አመነ::ሚኪያስ ባለበት ሚልኪያስ ተንደርድሮ ሄዶ ቀኝ ጉንጩ ላይ መዳፉን አሳረፈበት::ከአንገቱ ዘንበል ብሎ ከቆየ በኋላ ሳይመለከተው ወደ መኪናው ውስጥ ገባ::ሚልኪያስም ተከትሎት ገባ::ከላይ የተደረበለትን ፀጉር በማውጣት ከኋላ ወንበሩ በመወርወር የጆሮውንም ጌጥ ከተለጠፈበት በማላቀቅ አስቀምጦ መኪናውን አስነሳ::
* * *
ኤሊያስ ሲገባ አስቴር እየሮጠች ወደ እሱ ሄደች::
"ምን ሆነሻል?"
"ልጆቼ ልጆቼ የት ናቸው!?"
"ሚልኪያስ እራት ከሚኪያስ ጋር እንደሚበላ ነግሮኝ ነበር::አብረው ይሆናሉ::"
"እራት!?....እየበላ አልነበር?"
"ማ!?"
ስልኳ መልእክት ሲገባ ሄዳ ከጠረጴዛው በማንሳት ከፍታ አየችው::
"እማ አብረን ነን::ትንሽ ቆይተን እንመጣለን አታስቢ::" ከሚልኪያስ ነበር::በእፎይታ ተንፍሳ ከወንበሩ ተቀመጠች:-
"ችግር አለ?" አለ ጃኬቱን አስቀምጦ ወንበሩን ስቦ እየተቀመጠ::
"አይ አብረው ናቸው::ህዊ.."
"ግቢ አድራለች... ፈተና ደርሶባት የለ::"
* * *
"አዎ አንተ ጋር ውሰደው..."
"እና አሁንስ ትደብቀኛለህ ከባንዳ ጋር እንደነበርክ?"
"ዳጊ.... አሁን መኪናውን አንተ ጋር ውሰድ.. ከዘገየህ እንዳልነበረች ያደርጓታል::መጥፎ ቦታ ነው ያቆምኩት.. ሌላውን ስንገናኝ እነግርሃለሁ::" ስልኩን ዘግቶ ወደ ሚኪያስ ዞሮ አየው ዝም ብሎ ይነዳ ነበር::
"አቁም መኪናውን!" አለው ወደ ሰፈራቸው ሲጠጉ:: ሚኪያስ ዝም ብሎ ይነዳል::
"ሚኪ መኪናውን አቁመው እያልኩህ እኮ ነው::" ጮሀበት::መኪናውን ከአንድ ጥግ በማቆም ዞሮ ተመለከተው::
"ሁል ጊዜ ነገሮችን በጩሀት ብቻ የምታስቆም ነው አይደል የሚመስልህ?"
"አሁን ተናድጃለሁ ትርፍ ቃል አታውራ::"
"የምር ተናደድክ!?"
"ሚኪ"
"በእግዚአብሔር... በጣም ደክሞኛል ሄጄ ማረፍ እፈልጋለሁ::ልትል የፈለግከውን በል እና እንግባ::"
ሚልኪያስ ወንድሙ በአንዴ እንደዚህ መቀየሩ አስገርሞት ግራ ተጋብቶ እጁን አጣምሮ ሲመለከተው ቆይቶ:-
"ለምን እንደዚህ አደረግክ!?.... ቆይ ለምን?.... ሕይወትህን አደጋ ውስጥ እንደከተትከው ታውቆሃል ግን?" ዝግ ባለ ድምፅ ተናገረው::
"ይሄን ሁሉ ጊዜ የማውቅህ ነበር የሚመስለኝ::መንታዬ ስለሆንክ... ተመሳሳይ ልብ ያለን ምናምን... እንጂ ከሁለት ሰው ጋር እንደምኖር እኔ በምን አውቄ::እዛ ስፍራ ሲያወሩ አቅሌን ስቼ ልወድቅ ምንም አልቀረኝ::"
"ምንድነው ያወራችሁት!?"
"አንተ የምታውቀውን ሁሉ አውጣጥቼ ማወቅ ያለብኝን አውቄያለሁ::አባዬም አንተም ምን አይነት ሰዎች እንደሆናችሁ ምን እንደምትሰሩም ጭምር::"
ሚልኪያስ ፈገግ ብሎ ከወንበሩ ተደገፈ::
"ይሄን ቀን ነበር እንዳይመጣ የፈለግኩት::አሁን አንተ ልትነግረኝ ፍቃድህ ካልሆነ ሄጄ የምጠይቃቸው ይሆናል::"
"የምር!?.... ወንድሜ እኔን መስሎ ገብቶ አውርቷችሁ ነበር ነው የምትላቸው?... "
"ፈጣሪዬ..."
"ከዚህ በኋላ ከእኔ እውቅና ውጭ የምታደርገው አንዳች ነገር አይኖርህም::ትነግረኛለህ እነግርሃለሁ::" መኪናውን አስነሳ::
* * *
ሚኪያስ ክፍሉ እንደገባ ወደ መስኮቱ በኩል አቅጣጫውን አድርጎ ወደ ተቀመጠው ወንበር ሄዶ በመቀመጠ ከጀርባው ደገፍ ብሎ አይኖቹን ጨፈነ::ንግግራቸው ከጭንቅላቱ ውስጥ ይመላለሳል።
አራት ሰዎች ከፊቱ በጠረጴዛው ዙሪያ ተቀምጠው አይናቸውን እሱ ላይ አድርገዋል::ሚኪያስ የውስጡን ፍርሃት.. ንዴት.. ግራ መጋባት ለመቆጣጠር እየታገለ እጆቹን ይፈትጋል::ኤሊያስ ሲንጎራደድ ቆይቶ ወንበሩ ላይ በመቀመጥ:-
"ሚልኪ ልጄ... እባክህን ብዙ አታስጠብቀን::እኔ ከእናንተ ውጭ ማንም ወራሽ የለኝም::"
"ወራሽ!?..... ለእኛ ስትል ይሄን እንዳላደረግክ ልቦናህ ያውቀዋል::አሁን እንደልጅ እና አባት ሳይሆን እንደማንኛውም ሰው ጠላትህም ሊሆን ይቻላል እንደዛ አስበኝ::ነገ አሳውቃችኋለሁ::" በሩን ከፍቶ ወጣ::ሚኪያስ በሩ የተከፈተ ስለመሰለው አይኖቹን ገልጦ ወደ ኋላ ዞሮ ተመለከተ::ኤሊያስን ከኋላው ቆሞ ሲያየው በድንጋጤ ከፊቱ ቆመ::
"ይቅርታ አስደነገጥኩህ::"
"አይ አባዬ... በሰላም ነው?"
"አዎ...." ከፊቱ ባለው ወንበር ተቀመጠ::ሚኪያስ ወንበሩን አዙሮ ተቀመጠ::
"ሰሞኑን ግን ደሕና ነህ?.... ማለት ሥራ እየበዛብኝም እየጠየኳችሁም አይደለም::"
"አይ... ደህና ነኝ አባዬ::ትንሽ የማክዳ ጉዳይ እረብሾን ስለነበር ነው::"
"እ.... የእሷ ሞት ሁላችንንም እረብሾናል::ያው የሚፈጠር ጉዳይ ነው::ግን ከሚልኪ ጋርስ ሰላም ናችሁ?"
ሚኪያስ አሰብ አድርጎ በአዎንታ አንገቱን በመነቅነቅ::
"ደሕና ነን አባዬ አታስብ::ባይሆን አንተ በጣም ዝምታ እያበዛህ ነው::ቢሮም ሥራው ላይ ቀንሰሃል?... ደሕና ነህ አባዬ? የተፈጠረ ችግር ካለም እባክህን አካፍለን አባዬ... አንተ ላይ የሚከሰት ነገር ሁሉ እኛም ላይ ነው የሚከሰተው::" ኤሊያስ ፈገግ ብሎ:-
"የኔ አሳቢ ልጅ... ምንም አልተፈጠረም::ትንሽ የወንድምህ ድርጅታችንን ለቆ መውጣት አሳስቦኛል::"
"እም... እሱ የሚሻለውን ያውቃል::"
"አይ ልጄ.... ከአንተ መራቁ በጣም ጎድቶታል::ቤተክርስቲያን እንኳ ሄዶ አያውቅም::እኔንም ማናገር ሙሉ ለሙሉ ትቷል::እና ደሕና አልመሰለኝም::እስኪ ጠይቀው... ወደ ድርጅቱ እንዲመለስ::"
ሚኪያስ አባቱን አተኩሮ አየው::
"እ... አባዬ..." በሩ ተከፍቶ ሚልኪያስ ገባ:: ኤሊያስ ዞሮ አይቶት ከተቀመጠበት ተነስቶ:-
"ደሕና እደሩ::" ብሎ ወጣ::ሚልኪያስ በሩ ላይ ዓይኑን አድርጎ ቆይቶ በመመለስ:-
"ስለ እኔ ነው መችም::" ብሎ ኤሊያስ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ተቀመጠ::
"አልመሸም?" አለ ከተቀመጠበት እየተነሳ::
"እሁድ የጌታ እራት ነው አይደል?"
ሚኪያስ ቆም ብሎ ፈገግ አለ::
"እና እኔ ላይ ቂም ይዘህ የጌታ እራት ልትወስድ አትችልም::ዛሬ በጥፊ ስለመታሁ ይቅርታ::በጣም ደንግጬ ስለነበር ነው::"ሚኪያስ ከአልጋው ጠርዝ ተቀምጦ ቀና ብሎ አየው::ዓይኑ ላይ እንባው ግጥም ብሎ ነበር::ፈገግ ብሎ አይቶት:-
"ልጅ እያለን ቅዳሜ ትበድለኝ እና እሁድ በጠዋቱ ተነስተህ ዛሬ የጌታ እራት አይደል ትል ነበር::" ሚልኪያስ ፈገግታውን እየተጋራ:-
"የጌታ እራቱ አጋጣሚ ነበር::እኔ ልብህን ስለማውቀው ነው እጠይቅህ የነበረው::"
"እሺ ይቅርታ ላድርግልህ... ግን አንድ ውለታ ዋልልኝ"
"ምን?"
"እሁድ ቸርች አብረን እንሂድ::"
ይቀጥላል...
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል ዘጠኝ(ሜርሲ✍️)
ሚልኪያስ መኪናውን በማቆም ከመኪናው የሚወጣው ሰው ላይ ዓይኑን አደረገ::
"ስሙ ግን ማነው?"
"ባንዳ::" ሚክያስ ዘወር ብሎ:-
"የሰው ስም ነው?"
"ቢሆን ነዋ::" ሚኪያስ አንገቱን ወደ ፊት ሲመልስ ከፊተኛው መኪና ውስጥ የሚወጣውን ሰው ተመለከተ:-
"ይሄ ሰው... ባለፈው ከአባዬ ጋር ሆቴል ውስጥ ያየነው አይደለ?"
ሚልኪያስ ፈገግ ብሎ አይቶት:-
"ጥሩ ታስታውሳለህ::ከትንሽ ቀናት በኋላ ለምን ያን ቀን እዛ ቦታ እንደተገኘህ ምክንያቱ በግልፅ የሚታይህ ይሆናል::"
"ተስፋ ላድርግ.... አሁን ግን ለምን እዚህ ተገኘን?"
"ቦታውን እስኪ በደንብ ቃኘው::እናም የማይረሳህን ምልክት ጭንቅላትህ ውስጥ አስቀምጥ::" ባንዳ እና ሰውየው ግንባታው ካላለቀለት ህንፃው ውስጥ ገቡ::ሚኪያስ በጫካ የተከበበውን ስፍራ በዓይኑ ከቃኘ በኋላ:-
"ይሄ ስፍራ መችም አይጠፋኝም... ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ቦታ በአስፈሪ ፊልሞች እንጂ በእውነተኛ ዓለም አይቼው ስለማላውቅ::"
"መልካም... አሁን መሄድ አለብን::" የሚኪያስ ስልክ ሲጠራ ከኪሱ ውስጥ አወጣ ቁጥሩን ሲመለከተው ፈገግ ብሎ አንስቶት ወደ ጆሮው አስጠጋ:-
"ሄይ ሰሎሜ እንዴት ነሽ?" ሚልኪያስ በመገረም ተመልክቶት መኪናውን አስነሳው::
"ባለቤትነቱ የኔ ነው ተብሎ ሶስት ቀን ከሥራ ገበታ መጥፋት?" አለች የቢሮውን መጋረጃ እየገለጠች::
"ይቅርታ ሶሊ... የምር ለማሳወቅ እንኳ ፋታ አላገኘሁም::"
"አይ... አይ... አቶ ኤሊያስ ነግረውኝ ነበር::እኔም ቀብሩን ብደርስ ደስ ባለኝ ግን እዚህ ያለው ሥራ::"
"ሁላችንም ሥራውን ከተውንማ ድርጅቱ ከሰረ ማለት ነው::ዛሬ አርብ ነው ሰኞ ስመጣ እናወራለን::"
"መልካም... ደሕና ሁን::"
ስልኩ ሲዘጋ ሚልኪያስ ድምፁን ሳያሰማ ይስቃል:-
"ምን ሆንክ!?"
"አይ ምንም... እንዲሁ ገርሞኝ::አዲስ ሰራተኛ ገብቷል ማለት ነው::"
"የድርጅታችን ምክትል ማኔጀር ናት::"
"አረ ባክህ!.... ኦውው በጣም ጥሩ ነዋ::እና አቶ ኤሊያስ መች ሊያባራት አሰበ?"
"አንተ... ጤናህን አጥተሃል::"
"የምሬን እኮ ነው በየወሩ ማኔጀር የሚቀያየርበት ቢሮ የእኛ ድርጅት ብቻ ነው::"
"አይ እሷ እንኳ ትቆያለች::ገና ከመግባቷ ድርጅቱን ቀጥ ለጥ አድርጋ እያስተዳደረችው ነው::እማዬም በጣም ወዳታለች::"
"አንተም እንደዛው::" ሚኪያስ ገፋ አድርጎት ሳቀ::
"እና ቀጣይ ወዴት ነን?"
"እስር ቤት::"
"አታደርገውም::ባለፈው እኮ ሊያወራን ፍቃደኛ አልነበረም::"
"እስኪ አንዳንዴም የሳይኮሎጂ መፅሐፎችን አንብብ ወንድሜ::"
* * *
ሁለቱንም በዓይኑ እያፈራረቀ ተመልክቶ ሲያበቃ::
"እኔም መንታ ልጅ ቢኖረኝ ደስ ይለኝ ነበር::" አለ::
"የፈጣሪ ፍቃድ ይሁን እንጂ ይኖርሃል ገና ወጣት አይደለህ?"አለው ሚልኪያስ::
የጃኬቱን ኮፊያ ከጭንቅላቱ ላይ በማድረግ እጁን አጣምሮ ከወንበሩ ደገፍ አለ::
"ወጣት!?.... ከዚህ በኋላ እንኳን ልጅ የመኖሬም ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የገባ ሰው ነኝ::የሚያሳዝኑኝ የኔን ደስታ ለማየት የቋመጡት ቤተሰቦቼ ናቸው::"
"እናም አንተም አልረፈደብህም እኮ::አስራ አራት ቀን በጣም ብዙ ነው::" ቢኒያም ድጋሚ ትክ ብሎ አይቷቸው:-
"መጀመሪያ እየለየኋችሁ እንዳወራ ሚኪያስ እና ሚልኪያስ::"
ሚኪያስ የሚልኪያስን ጆሮ ይዞ:-
"በዚህ ለየን::እሱ ሚልኪያስ ነው::እናም ፀጉሩ ከእኔ ትንሽ አደግ ይላል::" ቢኒያም ፈገግ ብሎ:-
"እንዴት አላስተዋልኩም::እሺ ሚልኪያስ አንተ ነህ እስካሁን ስታወራኝ የነበረው::ማኪ ለአንተ ምንህ ነበረች::"
"ጓደኛዬ.... እናም ትንሽም ነገር ቢሆን አውቃታለሁ::"
"እና ጓደኛህን የገደለብህን ሰው ልትረዳው ለምን ፈለግክ?" ሚልኪያስ ከጠረጴዛው ደገፍ ብሎ ክፍሉን በዓይኑ ቃኘ::ውጭ ላይ ከቆመው ፖሊስ ውጭ ምንም አይነት ምስል መቅረጫ አልነበረም::ዓይኑ ወደ እሱ መልሶ:-
"ምክንያቱም አንተ ጓደኛዬን ስላልገደልክ::" ቢኒያም የስላቅ ፈገግታ አሳይቶት:-
"ጌም ትወዳለህ መሰለኝ?"
"እህም.... ለዛም ነው እዚህ ድረስ ላወራህ የመጣሁት::ጌምን በጌም ማሸነፍ ደስ ይለኛል::"
"በማይገባኝ አማርኛ ባታወሩ እና... ያኔ እጅህ ላይ ሽጉጥ ይዘህ ነበር?" ቢኒያም ዓይኑን ወደ ሚኪያስ አደረገ::
* * *
"ይሄ ልጅ ግን ምኑም ነው ያላማረኝ::አሁን ደግሞ ሚኪያስም ከስር ስሩ እያለ ነው::
"ሚኪያስ!?..... አገልጋዩ ልጅህ::" ሁለቱም ተሳሳቁ::
"ከመቅሰፍቱ የዳንነው በእሱ እና በእናቱ በኩል እንጂ እንደኛ ቢሆንማ::" ኤሊያስ ብርጭቆ ላይ የቀረውን ጭላጭ ጠጥቶ ከጠረጴዛው ላይ በማድረግ ውስኪውን ከጠርሙሱ ለሁለቱም ቀድቶ አስቀመጠው::
"ከዛ ሁሉ የዋህ ሰው እሱ እንዴት እንደዚህ እንደጠመመ ነው ያልገባኝ::ደግሞ በጣም የምትወደው እሱን ነበር አይደል?"
"አሁንም እንደዛው::ግን በመንገዴ ከገባ እያዘንኩም ቢሆን..."
"አይ.. አይ... ትንሽ ዕድል ስጠው::እኔም ልጆች አሉኝ ክፉ ነገር እንዲያገኛቸው አልፈልግም::"
"እኔም እንደዛው::አንድ ነገር አስቤያለሁ ጎይቶም::"
"ምን?"
"ሚልኪያስን ወደ ቡዱኑ መልሶ መቀላቀል::"
* * *
"ማመን ነው ያቃተኝ::አልጠበኩም ጌታን::"
"ነግሬህ ነበር::አሁን መረጃ ሳይሆን ማስረጃ ነው የሚያስፈልገን ይሄ የሰንሰለቱ ጫፍ ከተገኘ ሁሉንም በየተራ የምንደርስባቸው ይሆናል::"
ሚልኪያስ አንድ ሰው ከመንገዱ አየና መኪናውን አቆመው::
"ምነው?"
"መጣሁ ጓደኛዬ ነው::ባለፈው በስልክ ያወራሁት::" እሱ ሲወጣ በመስታወቱ ውስጥ አተኩሮ ልጁን ተመለከተው::ሁለቱ ቆመው እያወሩ ሳለ ስልክ ሲጠራ ወደ ኋላ ወንበር ዞረ::ከወንበሩ ስልኩን አንስቶ ተመለከተው::
"ጎይቶም::" ይላል:: ሲያየው ቆይቶ ሊዘጋ ሲል አንስቶ ወደ ጆሮው አደረገ::
* * *
"ፀጉሩን ያንጨባረረ::አንዱ ጆሮው ላይ ጆሮ ጌጥ ይጠቀማል::እና ሁለቱ አብረው ከሆኑ.."
"ጌታዬ..."
"ምንድነው?" አለ ከስልኩ ውስጥ
"ሚልኪያስ ብቻውን መጥቷል::"
"ጥሩ.... እኔ እስክመጣ ምንም ነገር እንዳታደርጉት::" ባንዳ ስልኩን በመዝጋት ከመኪናው ላይ ተደግፎ እየጠበቀ ወዳለው ሰው አመራ::
"ሚልኪያስ?"
አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀለት::
"እባክህን ወደዛኛው መኪና አብረሀኝ ትሄድ::" አለው::
"እሺ ይቻላል::"
* * *
"አባትህ እና ሚኪ የት ሄደው ነው?" ሚልኪያስ ትከሻውን ሰበቀ::
"ሚኪ አብሮኝ ነበር ፀጉር ቤት ብሎኝ ነው የተለየኝ::"
#ነጥብ
ክፍል ስምንት(ሜርሲ✍️)
ስልኩ እንደተነሳ ሚልኪያስ መሪውን ባልያዘበት እጁ ነጥቆት ወደ ጆሮው አደረገ::
"ሄለው ሚኪ::"
"ምን ሆነሽ ነው ስልክ የማታነሺው!?" አንባረቀባት::
"እ... አላየሁትም ነበር::ሚልኪ ነህ?... ደህና ናችሁ!?"
"አላየሽውም ነበር!?... የት ነሽ አሁን!?"
"ቤት... ማለቴ..."
"መደባበቁን አቁሚ ሂዊ.... ዛሬ ማክዳን አይተሻት ነበር!?"
"እ.. አዎ.... አሁን ወጣች::"
"አብሯት ነበር ሰው?"
"አሁን እያየኋት ነበር... ስልክ እያናገረች ወጣች::" አለች::
"ስልክ!?... ስልኳ ዝግ አይደል!?"
"የትኛው?... ማለቴ ብዙ ነው ያላት::"
"ወይኔ ሚልኪ... እሺ ሌላውን ስልኳን ላኪልኝ::"
"ቆይ...." አለች ከግቢው ስትወጣ የተሰበሰቡ ሰዎችን ተመልክታ::
"ምንድነው ህዊ::"
"እኔንጃ... የተሰበሰቡ ሰዎች::"
"የት ነሽ?"
"ውጭ... ማለቴ ባለፈው ያገኘሀኝ ቦታ::" አለች ወደ ተሰበሰቡት ሰዎች ጠጋ እያለች::ሰዎቹን አልፋ ከመሃል ስትደርስ ስልኳን ከጆሮዋ ለቀቀችው::
"ሄለው ሂዊ... ሂዊ..." በስልኩ ውስጥ የሕይወት የጩሀት ድምፅ ተሰማ::ሚልኪያስ ከመንገዱ ዳር መኪናውን አቆመው::
"ምንድነው?... ምን ተፈጠረ?"አለ ተደናግጦ እያየው::ሚልኪያስ ምንም ምላሽ ሳይሰጠው ከመሪው ላይ ዝቅ አለ::
* * *
አስቴር ሰዓቱን ቀና ብላ ተመለከተች ከምሽቱ አራት ሰዓት ይላል::ገበታውን ሰራተኛዋ እያቀራረበች እሷንም ግራ ገብቷት በየ መሀሉ በሩን ትመለከታለች::
"ቆይ ምን ገጠማቸው ይባላል!?.... እንዴት ነው የአንዳቸውም ስልክ የማይነሳው!?"
"ምን አልባት አብረው የሆነ ቦታ ሄደው ሊሆን ይቻላል::" አለች ቀና ብላ ተመልክታት::
የመኪና ድምፅ ሲሰሙ ተከታትለው ወጡ::ገብሬ በሩን ከፍቶ የሚልኪያስ እና የኤሊያስ መኪና ተከታትሎ ሲገባ በእፎይታ ተነፈሰች::ከመኪና ውስጥ ኤሊያስ እና ሕይወት ቀድመው ወጡ::የሕይወት ዓይን አባብጦ ስታይ ከበረንዳው ፈጠን ብላ ወረደች::ሕይወት አቅፋት ስታለቅስባት አስቴር ግራ ተጋብታ ፀጉሯን እየዳበሰች ኤሊያስን እየተመለከተች::
"ምንድነው... ምን ሆናችሁብኝ... ምን ተፈጥሮ ነው!?"
"ጓደኛዋ ማክዳ በፍቅረኛዋ ተገድላ ነው::እሷም በቦታው ስለነበረች ለጥያቄ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋት ትንሽ በዛ ተጨንቀን ነው ስልክሽንም ያላነሳነው::"
"በኢየሱስ ስም::ምን አይነት ነገር ነው የምሰማው!?" በዛ መሃል ሚልኪያስ እና ሚኪያስ ከአጠገባቸው ደርሰው ነበር::ሕይወት ከእ
ቅፉአ ወጥታ ወደ ቤት ገባች::አስቴር የሁለቱንም ጉንጭ ተራ በተራ በመሳም በስስት እያየቻቸው:-
"በምትሰሙት ነገር አትረበሹ::ይሄ ዘመን አባት በልጁ ላይ ወንድም በወንድሙ ላይ እጁን የሚያነሳበት ዘመን ነው::የትንቢቱ መፈፀሚያዎች እንዳንሆን መፀለይ ነው መፍትሄው::" ሚኪያስ ወደ ኤሊያስ ዞሮ ተመለከተ::
* * *
ሚኪያስ በሩን ከፍቶ ገብቶ ወንድሙን በዓይኑ ፈለገው::ሲያጣው በሩን ዘግቶ ወደ ውስጥ በመዝለቅ ከክፍሉ በስተኋላ ያለውን በር ሲመለከት ገርበብ ተብሎ ስለተከፈተ ከፍቶት ወጣ::ሚልኪያስን ከተደጋፊ ወንበር ላይ ተቀምቶ የከተማው ማብራት ላይ ዓይኑን ተክሎ አገኘው::ተመልሶ በመግባት ጋቢ ይዞ ወጥቶ ከአጠገቡ ቆሞ ሲመለከተው ቆይቶ ከጀርባው አልብሶት ከጎኑ ባለው ወንበር ተቀመጠ::
"አንድ ቀን ንጉስ ዳዊት በሰገነት ላይ ሲመላለስ ሳለ የሆነች ቆንጆ ሴት ሰውነቷን ስትታጠብ ይመለከታታል..ከዛ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ታስታውሳለህ መችም::" ሚልኪያስ አንገቱን ወደ እሱ አዙሮ በትንሹም ፈገግ ብሎ:-
"ሰንደይ ስኩል ላይ ስንማር አንድን የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ ወደዚህ ዘመን በማምጣት እና በማገናኘት ተወዳዳሪ እንደሌለህ አስታውሳለሁ::እና በዛም ምክንያት አስተማሪዎቻችን ትልቅ ወንጌላው እንደምትሆን ይናገሩልህ ነበር::"
"ደመናን አይቶ ዝናብ::" አለ እሱም ፈገግ ብሎ::
"እህም... እና የዳዊትን ታሪክ ለምን አነሳሀው?"
"ዳዊት ሀገሩ ጦርነት ላይ ሆና እሱ ግን ሰገነቱ ላይ ይመላለስ ነበር::ኃጢያቱ የሚጀምረው ከዛ ነው::ያለ ሰዓት ያለ ቦታ መገኘት::አንተም በዚህ ውድቅት ለሊት በዚህ ብርድ ብቻህን ተኮራምተህ የአዲስአበባ መብራቶች ላይ አይንህን ተክለሃል::
ዳዊትን እዛ ስፍራ የሚያስቆመው አልነበረም::እኔ ግን ወንድሜን ላስቆመው እዚህ ተገኝቻለሁ::ያ ማለት ወደ ቀጣዩ ሃሳብ ከመሸጋገርህ በፊት ማለቴ ነው::"
"አድክም::" አለውና ከወንበሩ ደገፍ አለ::
"እንዴት እጮኛዋን እዚህ ውስጥ እንደከተቱት ነው ሊገባኝ ያልቻለው::አንተ ባታቋርጠኝ አባቴ ላይ ክፉ ነገር እያሰብኩበት ነበር::"
"አየህ ልክ ነበርኩ::ይሄን ሃሳብህን አቁመው::ሲመስለኝ በጣም ብዙ ነገር አልገባንም::በዚህኛው ነገር ውስጥ እራስህን አትክተት ወንድሜ::ለአንተም ጥሩ አይሆንም::"
"ማክዳን እነርሱ እንዳስገደሉ ግልፅ ነው::እናም የምርም ጓደኛዋ ገድሏት ካልሆነ እድሜ ልኩን ሁለት ነገር አጥቶ ሲሰቃይ ይኖራል::"
"እሱ እንደገደላት እኮ ወዲያው ነው ያመነው::"
"ሁሉም እንደዛው ነበር ያመኑት::"
"ሁሉም!?"
"ነገ እሥር ቤት አብረሀኝ ትሄዳለህ::"
"አንተ ልጅ.... ቆይ አንድ ነገር ቢያደርጉህስ?'
"መግደሉን ነው?...." ከተቀመጠበት ተነስቶ ትክ ብሎ ተመልክቶት:-
"ሚልኪያስን ከገደሉት እኮ ቆዩ::አሁን ከገደሉም የሚገድሉት እነርሱ የፈጠሩትን ሚልኪያስ ነው::እሱንም ተፈጥሮ ካልቀደማቸው::" ትቶት ሲገባ ሚኪያስ ንግግሩን እያሰላሰለ ባለበት ቆየ::
* * *
የቀብሩ ስነስርዓት አልቆ ሰዉ ወደ ቤት መመለስ ሲጀምር ሕይወት ሚልኪያስ እና ሚኪያስ ወደ ቆሙበት በማምራት ከፊታቸው ቆመች::
"አንተ ነበርክ አይደል ለፍቅረኛው ከአንተ ጋር ስለነበራችሁ ግንኙነት የነገርከው!?" ግራ ተጋብተው አዪአት::
"ምንድነው የምታወሪው እህቴ?" አለ ሚልኪያስ::
"አሁን ነው ሁሉም ነገር ግልፅ የሆነልኝ::ግን አታፍርም እዚህ ልታስቀብራት የምትመጣው!?... ለአንተ ይሄ በቀል በጣም ቀላል ነው::" አስቴር ከአጠገባቸው ስትደርስ ልናገር የነበረውን ከአፉ መለሰው::
"እማዬ ይዘሻት ሂጂ.. እኛ እንመጣለን::ቤት እንነጋገራለን::ሌላ ነገር አትቀባጥሪ!" ከአጠገባቸው እንደሄዱ ሚልኪያስ ወንድሙን እያየ:-
"ምን ሆናለች ልጅቷ!?"
"ድንጋጤው ነው::በሽጉጥ ተመታ የሞተችዋን ጓደኛዋን ነው በዓ ኗ ያየችው::" እሱ እየተናገረ አሻግሮ የዛን ምሽት ከኤሊያስ ጋር የነበረውን ሰው ወደ መኪናው ሲገባ ተመለከተ::
ሚኪያስ ግራ ተጋብቶ እሱ ወደሚያይበት አቅጣጫ ተመለከተ::ማንም አልነበረም::ዘወር ሲል ሚልኪያስ መኪናው ውስጥ ገብቶ በሩን ከፍቶለት ሲጠብቀው አገኘው::ፈጠን ብሎ መኪና ውስጥ ገብቶ አፉን ከማላቀቁ ሚልኪያስ በሩን ዘግቶ መኪናውን አስነስቶ ነበር::
"ምንድነው?"
"ገዳዩ::"
"የት?"
ከፊቱ ያለውን መኪና በዓይኑ አሳየው::
ይቀጥላል...
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
( ለፕሮፋይላችሁ እና ለወዳጆቻችሁ ለመላክ ) HD
አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።
መዝሙር 102÷27
“But You remain the same, and Your years shall have no end.”
Ps 102፥27
#QouteVerse #Bduvlm #HappyNewYear #2016
መልካም አዲስ አመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Faithful Witness of the Kingdom
ታማኝ የመንግሥቱ ምስክሮች
እናያለን | እንመሠክራለን | እንጸናለን
Follow Us On INSTAGRAM YOUTUBE
#ነጥብ
ክፍል ሰባት (ሜርሲ✍️)
ሚኪያስ ሁለቱን እያፈራረቀ ሲመለከት ቆይቶ:-
"ብቻችሁን ብታወሩ ይሻላል መሰለኝ::" ሲነሳ ሚልኪያስ እጁን ይዞ አስቀመጠው::
"ከዚህ በኋላ ብቻዬን የምወስነው ነገር አይኖርም::"
"ሚልኪ" አለች ግራ ተጋብታ::
"የተፃፃፍነውን አይቷል::ከእሱ የተደበቀ ነገር የለም::"
"ካናዳ መች ልትሄዱ አሰባችሁ?" አለ ሚኪያስ ረጋ ባለ ድምፅ::
"በዚህ ሁለት ሳምንት::ቪዛው መጥቷል::ትላንት እሱን ሊነግራችሁ ነበር ሚልኪ የማይሆን ነገር ተናግሮ..."
"የማይሆን ነገር አልተናገርኩም ነበር::"
"ሚልኪ ግን ታውቆኋል የዚህን ቤት ሰላም እያደፈረስክ ነው::"
"ሰላም ነው ያልሽው!?.... ሊፈነዳ የደረሰ እሳተጎሞራ ላይ ያለን ቤት ነው ሰላም ብለሽ የምትጠሪው!?"
"እባካችሁ ድምፅ ቀንሱ!... አሁን መፍትሄው ላይ ነው ማውራት ያለብን::ወንድሜ ያደረጋችሁትን ነገር ካወቀ ብዙ ነገር ይበላሻል::በዚህ አካሄዳችሁ ከቀጠላችሁ እራሱ ይደርስባችኋል::ያኔ ፀፀቱን መሸከም አትችሉም::"
"ስለዚህ ወንድምህ አጉል የጀመረውን ነገር ያቆማል::" አለች እጇን አጣጥፋ ከወንበሩ ደገፍ አለች::ሚኪያስ ተገርሞ ተመለከታት::
"አንቺስ... አንቺስ ማስተካከል ያለብሽ ነገር ያለ አይመስልሽም?"
"ምን?... ማለቴ እኔ ምን አደረግኩ?" ሚልኪያስ ፈገግ ብሎ አየው::
"ብዬህ ነበር"
ፀጉሯን ወደ ኋላ እያደረገች በመጠቅለል ተመቻችታ እየተቀመጠች:-
"ምኑን ነው ያልከው?"
"እሺ ከዚህ በኋላ አልደርስባችሁም::አሁን መሄድ ትቺያለሽ::" አለ እጁን ከፍ ዝቅ እያደረገ::
"አልጨረስንም እኮ ባለቤቴን ይቅርታ ልትለው ይገባል::በጣም አዝኖብሃል::"
"እሺ... ነገ እጠይቀዋለሁ::አሁን መሄድ ትቺያለሽ::" አለ በተሰላቸ ድምፅ:: ከወጣች በኋላ ሚኪያስ በመገረም ይመለከተዋል::
"የሆነ ነገር አስበሃል አይደል?"
"አይ... ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኜ ይቅርታ ጠይቄው ወደ ካናዳ እልካቸዋለሁ::በሄዱ በወሩ ነው ወንድሜ እራሱን አጥፍቶ እዚህ እሬሳው የሚላከው::"
"በስመአብ በል አንተ::" ሚኪያስ ተደናግጦ ቆመ::
"በስመአብ::" አለና ወንበሩን አዙሮ ቀለሙን እና ብሩሹን አነሳ::
"ሌላ የማላውቀው ነገር አለ ስለ ሶስና?"
ሚልኪያስ ትከሻውን ሰብቆ:-
"ደሕና እደር ወንድሜ::" አለው::
* * *
ሚኪያስ ክፍሉ ሲገባ ሰውነቱ ብዙ ሥራ ሰርቶ እንደዋለ ዝሎ ከአልጋው ላይ ከነልብሱ ዘፍ አለበት::በጀርባው ተንጋሎ ጣሪያ ጣሪያውን ሲመለከት ቆይቶ ስልኩ ላይ መልእክት ሲገባለት አንስቶ አየው::ማክዳ ነበረች:-
"ዛሬ ሽማግሌ መጥቶ ነበር እና ቤተሰብ እሺ ብሎ ነበር የሄደው::የምር ነገሮችን የምታበላሽ መስሎኝ በጣም ሰግቼ ነበር::ጥሩ ልብ አለህ::እግዚአብሔር ለቤታችሁ መልካሙን ነገር ያምጣ::አመሰግናለሁ::" ይላል::ደግሞ አንብቦት ወደ ድምፅ ማስቀመጫው በመሄድ የቀዳውን አጠፍው::
"ከዚህ በኋላ ሕይወታችን ላይ ጣልቃ እንደማትገቢ ተስፋ አለኝ::አንቺ ላይስ አባቴ ምን አድርሶብሽ ይሆን?" አለ በልቡ::ስልኩን መልሶ አስቀመጠው::
* * *
ሚልኪያስ ከማቲያስ እግር ሥር እንደተደፋ ምላሹን ይጠብቃል::
"አረ ልጄ ይቅርታ እያለህ እኮ ነው::" አለች አስቴር ማቲያስን እያየችው::
"እኔን ሳይሆን ይቅርታ መጠየቅ ያለበት ሶሲን ነው::እሷን ነው የበደላት::"
"እኔን ማታውኑ ነበር ይቅርታ የጠየቀኝ::እባክህ ውዱ ባለቤቴ ይቅር በለው::ልጅነት ይዞት ነው እንጂ ልቡ ንፁህ ነው::"ሚልኪያስ ንዴቱን እንደምንም እየተቆጣጠረ ከእግሩ ስር ቆየ::
"ተነስ በቃ::" ከእግሩ ሥር ሲነሳ ተቃቀፉ::
ሁለቱም ወንበር ስበው ጎን ለጎን ተቀመጡ::
"የሆነው ሆኖ... ዛሬ እንሄዳለን::"
"እንዴ ይቅርታ አላደረግክልኝም ማለት ነው!?"
"በፍፁም ወንድሜ... ድሬ እናቷ ጋር ነው የምንሄደው ቤተሰብ መሰናበት አለባት::"
"እንደዛ ከሆነ ይሁን::"
"እንፀልይ::" አለች አስቴር::ሁሉም እጅ ለእጅ ሲያያዙ ሚልኪያስም የማቲያስ እና ከጎኑ የነበረውን ሚልኪያስ እጅ ይዞ ዝቅ አለ::ሁሉም እሱ ላይ ዓይናቸውን በመገረም አደረጉ::አብሯቸው ከፀለየ ዓመት አለፎት ነበር::
* * *
"ዛሬ በመኪናሽ ሂጂ... እኔ አስቸኳይ መሄድ ያለብኝ ቦታ አለ::" አለ ኤሊያስ አስቴርን ሚኪያስ እና ሚልኪያስ እርስ በእርስ ተያዩ::
"እማዬ በዛው ሕይወትን ሸኛት::እኔና ወንድሜ ደረስ ብለን የምንመለስበት ቦታ አለን::"ሚኪያስ ግራ ተጋብቶ አየው::ሕይወት እና አስቴር ቀድመው ሲወጡ የኤሊያስ መኪና ስትወጣ ሚኪያስ እና ሚልኪያስ ግቢው ላይ ቀሩ::
"የት ልንሄድ ነው!?"
"ና ግባ::"
* * *
"ቀኑን ሙሉ እሱን ስንከተለው ዋልን::በጣም ውድ ጊዜዬን ነው ያጠፋህብኝ ጌታን::" አለ እየተነጫነጨ::
"ጌታን አትበል አንተ ልጅ::ጊዜህ እንደባከነ በምን እርግጠኛ ሆንክ!?.... ቤታችንን ለመታደግ ነው አይደል የተነሳነው!?.... ስለዚህ ጥቂቷ ነገር ለእኛ ዋጋ አላት::"
"እሺ ይሁን ዛሬ ምን አገኘን!?... አባዬ ከሆነ ሰው ጋር ይገናኛል ሌላ ያገኛል::በቃ ሥራ ትቶ ይሄን ነው ሲከውን የሚውለው::ሆቴል እየቀያየረ ከሰው ጋር ቁርስ ምሳ እራት መብላት::" ሚልኪያስ ንግግሩ ቢያስቀውም ከመሳቅ የሚያግተው ነገር ከፊቱ እየተከናወነ ስለነበር ትኩረቱን ወደ እዛ አደረገ::ሰአቱን ሲመለከት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ሆኗል::ከመኪናቸው እራቅ ብሎ ኤሊያስ እና አንድ ገዘፍ ያለ ጎልማሳ ከሆቴሉ እያወሩ ወጥተው ከመኪናው ማቆሚያው ጋር ቆሙ::
"ምን ሆነሃል!?" አለው ሚኪያስ የሚልኪያስ የፊቱ መቀያየር ግራ አጋብቶት::
"ምን ይሰራል እዚህ!?..... ዛሬ ምን ተፈጥሮ ነው!?"
"ምንድነው የምታወራው!?" ምላሽ ሳይሰጠው ስልኩን አንስቶ ደወለ::
"ስማ የት ነህ?"
"ቤቴ... ምነው?" አለ ከስልኩ ውስጥ አንድ የወንድ ድምፅ::
"የተፈጠረ ነገር ነበር ዛሬ?" ስልኩ ማጉያ ላይ ስለነበር ለሚኪያስም ይሰማው ነበር::" በዛ መሃል ኤሊያስ ወደ መኪናው ገብቶ ሁለቱም በተለያየ አቅጣጫ ሄዱ::
"አዎ... አይጠቅምህም ብዬ ነው::የሆነች ልጅ ዛሬ ያስወግዷታል::ብዙም አልሰማኋቸውም ግን የከዳቻቸው ነገር አለ መሰለኝ::"
"ስሟ ማነው!?"
"ማን ነበር..... እ.... ማ... ማኪ... ማክዳ::" ሚልኪያስ ስልኩን ለቀቀው::ሚኪያስ የሰማውን ማመን አቅቶት የወደቀው ስልክ ላይ ዓይኑን አድርጓል::
"ሄለው... ሄለው ሚልኪ...."ሚኪያስ ፈጥኖ የወደቀውን ስልክ አነሳ::
"የት ናት አሁን እሷ!?" ሚልኪያስ ስልኩን ነጥቆት በመዝጋት ወደ ኋላ ወንበር ወርውሮ መኪናውን አስነሳ::
"ሚልኪ.."
"አሁን ጥያቄ የምትጠይቅበት ሰዓት አይደለም ለማኪ ደውልላት::" ጮሀበት::
ስልኩን ወደ ማክዳ በመደወል ወደ ጆሮው አስጠጋው::
"ስልኳ ዝግ ነው::"
ሚልኪያስ መሪውን በቡጥ ነረተው::
ይቀጥላል....
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙" መመኪያዬ"
ዘማሪ 👥 መስፍን ጉቱ
Size💾 54.1MB
የተለቀቀው📅 Sep 2023
ርዝመት⏰ 7:30min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"ፀናው "
ዘማሪት 👥 ዝናሽ ታያቸው
Size💾 41.4MB
የተለቀቀው📅 Sep 2023
ርዝመት⏰ 5:54min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"ስዕለቴን እከፍላለሁ "
ዘማሪ👥 እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ
Size💾 8MB
የተለቀቀው📅 Sep 2023
ርዝመት⏰ 8min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዛሬ ምሽት 3ሰዓት ላይ ልዩ የበዓል ዝግጅት ተዘጋጅቷል እንዲሁም አሸላሚ ዝግጅቶች ይኖሩናል ይቀላቀላሉን👇
t.me/KALTUBE
t.me/KALTUBE
ዝማሬ🎙"ሠንበትበት አለ"
ዘማሪ👥 Biniyam Ayele
Size💾 7.1MB
የተለቀቀው📅 Aug 2023
ርዝመት⏰ 7:41min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል አራት(ሜርሲ✍️)
ኤሊያስ ሁሉንም በፍርኃት ውስጥ ሆኖ ይመለከታል::ሚኪያስ ከተናገራቸው በኋላ የሚፈጠረውን አስቦ አይኖቹን ጨፈነ::ሲገልጠው ሚኪያስ አፍጦበት ነበር እና ደንገጥ አለ:-
"አባዬ ደሕና አይደለህም እንዴ?"
"የሆነ ነገር ሰምቶ ትንሽ ተደናግጦ ነው::" አለ ሚልኪያስ ፈጠን ብሎ::ሶስቱም ኤሊያስን ተመለከቱ::
"ምን ገጠመህ!?... የተፈጠረ ችግር አለ?" አለች አስቴር መጨነቋ ድምጿ ላይ ያሳብቅ ነበር::
"እ..."የሚናገረው ጠፋው::
"ምንድነው አንተ?" አለው ሚኪያስ ወደ ወንድሙ ዞሮ::
"አይ.... አንድ ሰው የሆነ ነገር አማከረን እና ትንሽ አስጨንቆት ነው እና እራት እየበላን እናወራበታለን::"
ኤሊያስ ግራ በመጋባት ተመለከተው::ሚልኪያስ ከወንበሩ ደገፍ አለ::ሚኪያስ ሁለቱንም እያፈራረቀ በማስተዋል ተመለከተ::
* * *
ማቲያስ ሲገባ ሶስና ደንገጥ ብላ ስልኳን ከጆሮዋ አወረደችው::
"ምነው ደነገጥሽ?" አለ በሩን እየዘጋ
"ኮቴም የለህ!?"
"በተከፈተ በር ነው የገባሁት... ማንን እያወራሽ ነበር?"
"እማዬ ደውላልኝ ነው.... መች ነው ቤት የምትመጡት እያለች::" ስልኳን ከአልጋው አስቀመጠች::ጉንጯን በመሳም ከአልጋው ላይ ከጎኗ እየተቀመጠ:-
"ድሬ ናፍቃኝ ነበር::ወደ ውጭ ከመመለሳችን በፊት እናያታለን::"
"እዛ የኖርኩ አስመሰለብህ እኮ::"
"ያው እኔ አንቺ አንድ ነን የሚለውን አስቤ ነው::አይዞሽ ካናዳ እንደናፈቀችሽ አይቀርም::ባይሆን ቤት የት ሄደው ነው?... ስገባ ማንንም አላየሁም::"
እግሯን ካጣጠፈችበት በመዘርጋት የስልኳን ሰዓት እያየች:-
"ሚኪያስ እራት ጋብዞናል ስትል ነበር አስቲ::"
"ታዲያ ለምን አልነገርሽኝም?"
"ግብዣው እኛን ስለማያካትት::"
"አልገባኝም... ሁሉም ሄደው ለምን እኛ!?"
ትከሻዋን ሰበቀች::
* * *
"አሁን ይነገረና::" አለ ሚኪያስ ፀልየው መብላት እንደጀመሩ::ኤሊያስ ሚልኪያስን ተመለከተ::
"ዌል እንግዲህ::" ሹካውን እያስቀመጠ ሁሉንም በዓይኑ በመቃኘት ወደ ኤሊያስ እየተመለከተ:-
"ትንሽ ሊያከራክረን ይችላል::የጓደኛዬ አባት ከሚስቱ ውጭ ሌላ ሰው ጋር መሄድ ከጀመረ ትንሽ ቆየና ሚስቱ ባጣም ፍፁም የዋህ... ክርስቲያን.. የፀሎት ሴት... እጅግ ውብ..... ብቻ መልካምነት ሁሉ እሷ ላይ ያለ ሴት ናት::" ይሄን ብሎ አስቴርን ተመለከተ::
"እናም ሃብቱ ሁሉ የእሷ ነው::አንደላቃው የምታኖረው እሷ ናት::ግን ቧለ..... በእሷ ላይ ይዘሙታል::በዚህ መሃል ጓደኛዬ ሁሉንም ነገር ደረሰበት::" ይሄን ብሎ ውሃውን በመጎንጨት ደገፍ አለ::ሁሉም ምግባቸውን አቁመው ያዳምጡት ነበር::
"ይሄ የማይረባ.... እሺ ከዛስ?" አለች ሕይወት::
"ከዛ.... ለመናገር ወስኖ ብዙ ጊዜ ለቤተሰቡ ሲል ያልፈው ነበር::እጅ ከፍንጅም ይዞት አስጠንቅቆት ምሎ ተገዝቶ አቁሞ ነበር::ግን እንደገና ከተለያየ ሴት ጋር ያዘው እና ለመናገር ወሰነ.... ለዛም ይናገር አይናገር የሚለው ላይ ከአባዬ ጋር እየተከራከርን እያለ ነበር የመጣችሁት::"
"ስለምን ቤተሰብ ነው የሚያስበው!?.... ዝም ባለ ቁጥር ቤታቸውን እየፈረሰ ነው የሚሄደው::መናገር ብቻ ሳይሆን ይሄንንማ በአደባባይ ነበር መስቀል::" ኤሊያስ ንግግሯ ሰቅጥጦት በፍርኃት ተመለከታት::
"ትንሽ ብትረጋጊ እህትየዋ::" አለ ሚኪያስ ዘወር ብሎ አይቷት::
"ለምን እየማገጠባት እንዳለ ጠይቆታል ጓደኛህ?" አለው ወደ ሚኪያስ እየተመለሰ::
"ያውም ብዙ ጊዜ.... ግን ምላሹንም እራሱ የሚያውቀው አይመስለኝም::አዋዋሉ ይሆናል::እማዬስ አንቺ ብትሆኝ ምን ታደርጊ ነበር ማለቴ የዛ ሰው ሚስቱ ብትሆኚ?" ኤሊያስ እንደተመታ ሰው ደርቆ ቀረ::
አስቴር በእረጅሙ ተንፍሳ:-
"እግዚአብሔርን ሁሌም የማመሰግነው ንፁህ ባል ስለሰጠኝ እና በዛም ስላልፈተነኝ ነው::እኔ ለዛች ሴት አዝናለሁ... ምን አይነት መከራ ነው የተጋረጠባት::እኔ ብሆን...."
ሚልኪያስ ከተደገፈበት ቀና ብሎ ከጠረጴዛው ደገፍ አለ ልቡ በፍጥነት ሲመታ ይሰማዋል::
"የእግዚአብሔርም ቃል ስለሚፈቅድ እፈታዋለሁ::ከዛ ውጭ ግን ተመልሼ ደህና የምሆን አይመስለኝም::ያውም እኔ የልብ ታማሚ ነኝ እሷም ህመም ቢኖርባት ተመልሳ ሰው የምትሆን አይመስለኝም::ለዛ ልጇ ያናግረው ደጋግሞም ውትወታውን አያቁም ምን አልባት ወደ ልቡ ልመለስ ይቻላል::ያን ጊዜ እራሱ ተፀፅቶ ይቅርታ ይጠይቃታል::"
ሚልኪያስ ከወንበሩ ብድግ ሲል ተደናግጠው ተመለከቱት:-
"አንዴ መታጠቢያ ደርሼ መጣሁ::" በማለት ትቷቸው ሄደ::
"እማዬ ግን ልብሽ.... የምር አባዬ ዕድለኛ ነው አንቺን የመሰለች ሚስት እግዚአብሔር ስለሰጠው::አይደለ አባዬ?" አለች ህይወት ኤሊያስ ከሃሳብ ከሄደበት ብንን ብሎ እራሱን ለማረጋጋት እየሞከረ በአንገቱ አዎንታዊ ምላሽ ሰጠ::
ሚልኪያስ ከመስታወቱ ፊት ቆሞ ዝቅ ብሎ ሲያለቅስ ከነበረበት ትከሻውን የያዘው እጅ ቀና እንዲል አደረገው ሲያየው ደንገጥ ብሎ ፈጠን ብሎ እንባውን በመጠራረግ ፈገግ ብሎ:-
"አይኔ ላይ ትንኝ..." ሚኪያስ አጥብቆ ሲያቅፈው መናገሩን አቁሞ እንባው ከጉንጮቹ ይፈስ ጀመረ::
"ለምን ይሄን ሁሉ ጊዜ ብቻህን ተሸከምከው?.... ወንድምህ አይደለሁም... ሸክምህን እንድጋራህ ለምን ከለከልከኝ?...." ሳጉ አፍኖት ንግግሩን አቆመ::
* * *
ወደ ቤት ሲገቡ ሳሎኑ ላይ ሁለት ወንዶች እና አንዲት ሴት ተቀምጠው ከማቲያስ ጋር ሲነጋገሩ አገኛቸው::ሚልኪያስ ማክዳን ሲያያት ደንገጥ ብሎ ባለበት ቆመ:-
"ማኪ!?" አለ ተደናግሮ:: ሕይወትም ግራ ተጋብታ ፈጠን ብላ ወደ እሷ ሄዳ ጉንጯን በመሳም:-
"ምንድነው እሱ?" አለቻት::
ሁለቱም ሰዎች በመቆም ለኤሊያስ እና ለአስቴር ሰላምታ በመስጠት::ከፖሊስ ጣቢያ መምጣታቸውን መታወቂያውን አውጥተው አሳዩ::ወደ ሚኪያስ እና ሚልኪያስ ግራ በመጋባት እየተመለከቱ:-
"የቱ ነው ሚልኪያስ?" አለ ከሁለቱ በሰውነቱ ገዘፍ ያለው ሳጅን::
ማክዳ ቀረብ ብላ:-
"እሱ" አለች በፊቷ ወደ ሚልኪያስ እያመለከተች::
"ክፍልህን ልንፈትሸው ነበር::እባክህ ታሳየን ክፍልህን?"
ሚልኪያስ ማክዳን ግራ በተጋባ አስተያየት ተመልክቷት እየመራቸው ወደ ክፍሉ አቀኑ::ክፍሉን ሲበረብሩ ሁሉም ከበሩ አቅራቢያ ቆመው ነበር::
"ምንድነው ማኪ!?" አለ ሚልኪያስ ቀረብ ብሏት::
"ማኪ አትበለኝ አሁን ከእኔ ገለል በል!" ፊቷን አዞረችበት::
"ወንድሜን ነው እንደዚህ የምታናግሪው... ቆይ ምን ሆነሻል!?" ሕይወት ቁጣ በተሞላ ንግግር::
"ምንም በማታውቂው ጣልቃ አትግቢ ጓደኛዬ::" የሌዛር ቦርሳ ይዘው ሲወጡ ሁሉም ተደናግጠው አዩ::ውስጡ ላይ ያሉትን ወርቆች የአንገት ጌጥ በማውጣት አንዱ ሳጅን ከፍ አድርጎ::
"ይሄ ነው!?" አላት::ማክዳ አንገቷን በአዎንታ ነቀነቀች::ሳጅኑ ወደ ሚልኪያስ ቀረብ ብሎ ካቴናውን በመዘርጋት:-
"በስርቆት ወንጀል ተጠርጥረህ በቁጥጥር ሥር ውለሃል" አለው::
ይቀጥላል....
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"Praise "
ዘማሪ👥 Brandon Lake ft Elevation Worship
Size💾 40MB
የተለቀቀው📅 Aug 2023
ርዝመት⏰ 5min
Quality🎬 MP3
Genres 🎹 Gospel Song
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
#ነጥብ
ክፍል ሁለት(ሜርሲ✍️)
"ወንድሜ"
"ዝም እንድትይ እየነገርኩሽ ነው!" አንባረቀባት::ኩምሽሽ ብላ ከወንበሩ ላይ ተደግፋ ተቀመጠች::በየ መኋሉ ሰረቅ እያደረገችው ታየዋለች::ፊቱ ላይ ፍፁም መረበሽ እና ንዴት አስተዋለች::
"ከተናገርክ ግን እኔም የማውቀውን መናገሬ አይቀርም::" አለች ወደ ግቢያቸው በር ሲደርሱ::መኪናዋን አቁሞ በጥያቄ ተመለከታት:-
"ምንድነው የምታውቂው!?"
"እሱን ስለ እኔ ስትነግራቸው የምትሰማው ይሆናል::" ከቦርሳዋ ውስጥ ጃኬት በማውጣት ከላይ ደርባ የመኪናውን በር ከፍታ ወጣች::ከበሩ ደርሳ ልታንኳኳ ስትል ተከትሏት ወርዶ ኖሮ እጇን ከአየር ላይ ያዘው::
"ይሄን ከእኔ ጋር ትጨርሺያለሽ::"
ከኋላቸው የመኪና መብራት ሲበራባቸው እጇን እንደያዘ ዘወር አሉ::
መኪናው ቆሞ ሚኪያስ ከመኪናው ውስጥ ወጥቶ እነርሱ ጋር ደረሰ::
"ምን ሆናችሁ ነው::ጥበቃው አልከፍት ብሏችሁ?"
"እእ..." አሉ ሁለቱም አንገታቸውን በአዎንታ እየነቀነቁ::
"ይቅርታ በጣም.... ጋሼ ሱቅ ልከውኝ እኮ::" ገብሬ ከኋላቸው እየሮጠ ደረሰ::እጁ ላይ ፔስታል አንጠልጥሎ በሩን በቁልፉ ከፍቶ ገባ::ሚልኪያስ እና ሕይወት ተንፍሰው ተያዩ::እጇን መንጭቃው አስለቅቃ ወደ ውስጥ ዘለቀች::ሚኪያስ ወንድሙን አተኩሮ ተመለከተው::
"ምን!?" አለው::
"ተናደሃል... ተረብሸሃል::"
"መች ተናደድኩ አልኩህ!?"
"መንታዬ መሆንህን አትርሳ..."
"ጋሼ ዝናብ እየመጣ ነው::" አለ ገብሬ ከበሩ ቆሞ ሚኪያስን::
ሁለቱም ወደየመኪኖቻቸው በመግባት ተከታትለው ገቡ::
ቤት ሲገቡ እራት ቀርቦ እየጠበቋቸው አገኟቸው::ሚኪያስ ሲቀላቀላቸው ሚልኪያስ ደግሞ በደረጃው መውጣት ጀመረ::
"እንዴ እራት ብላ እንጂ" አለች አስቴር::
"በቃኝ::" ብሎ ፊቱን ሳያዞር ወደ ክፍሉ አመራ::
"ምን ሆነዋል ዛሬ!?... ሂዊም በቃኝ ብላ ሄደች::"
"እራት አብረው በልተው ይሆናል እማዬ::" አለ ሚኪያስ እሱም ግራ እየገባው::
"አልመሰለኝም::" አለች ሶስና::
ቀና ብሎ ተመልክቷት:-
"አንቺ በመሰለኝ ነው::እኔ ግን ስለ ቤተሰቤ ሳወራ እርግጠኛ ሆኜ ነው::"አላት።
* * *
ፀጉሩን በፎጣ እየጠራረገ ከመታጠቢያ ክፍሉ ሲወጣ ከአልጋው እራስጌው አጠገብ የስእል መሳያ ሸራ ከነ ቀለሙ ተቀምጦ አየ::
"በፈጣር!" ፈጠን ብሎ በመሄድ እየዞረ ተመለከተው::ከጠረጴዛው ላይ ቁራጭ ወረቀት የተፃፈበትን አነሳ::"የእኔን ድርሻ ተወጥቻለሁ::አሁን ተራው የአንተ ነው::"ይላልፈገግ ብሎ ደግሞት አንብቦት::ከወንበሩ ላይ ተቀመጠ::
* * *
"ምን አውቃለሁ ጓደኛዬ::ቆይ እኔ ያልገባኝ.... ከወንድሜ ጋር ግንኙነት እንዳለሽ አላውቅም ነበር::" በስልኩ ውስጥ ፀጥታ ሰፈነ::
"ገና ግንኙነታችን መስመር አልያዘም::ለዛ ነው ላረጋግጥ እና እነግርሻለሁ ብዬ ዝም ያልኩት::"
"ቆይ ቢኒስ!?"
"ተይው እሱን... በአካል ስንገናኝ በደንብ እናወራለን በቃ... እነ ማሚ እራት እየጠበቁኝ ነው::"
"እም... እሺ ማኪ ... (ናይት)" ስልኩን አልጋው ላይ ወርውራ ወገቧን ይዛ እንደቆመች ቀና ብላ ከግድጊዳው ላይ ወደተሰቀለው ከሁለቱም ጋር አብራ ወደ ተነሳችው ፎቶ እየተመለከተች:-
"ደግሞ ምን ደብቀሀን ነው!?" አለች::
* * *
ሚኪያስ ከአልጋው ላይ በጀርባው ተንጋሎ ኮርኒሱን እየቆጠረ በየ መሃሉ ቤታቸው ውስጥ እየተፈጠረ ስላለው ነገር ያስባል::ስልኩ ሲጠራ ዘወር ብሎ ተመለከተ "ሚልኪ" የሚለውን ሲያይ ደንገጥ ብሎ ከአልጋው አንስቶ ወደ ጆሮው አስጠጋው:-
"በሰላም ነው!?"
"ላናግርህ ፈልጌ ነበር::" ድምፁ ዝግ ያለ ነበር::ከተንጋለለበት ቀና ብሎ እየተቀመጠ:-
"ሰዓቱን አይተሀዋል ግን!?"
"ለስድስት ሁለት ደቂቃ ይቀረዋል::አሁን ትመጣለህ ወይስ..."
"መጣሁ መጣሁ::" ከአልጋው በመነሳት ተጠቅልሎ የተቀመጠውን ጋቢ አንስቶ በመልበስ ወደ ሚልኪያስ ክፍል አመራ::በሩ ጋር ደርሶ ቆም ብሎ ከቆየ በኋላ ገና ከማንኳኳቱ በሩ ተከፈቶ ሙሉ ቀዝቃዛ ውሃ ከላዩ ላይ ተደፋበት::ሚኪያስ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ልብሱን ያራግፋል::ሚልኪያስ ቆሞ እየተፍነከነከ ያየዋል::
"አንተ ህፃን....." ቀና ብሎ ሲመለከተ ቤቱን የሞላ ሻማ በየቦታው በርቶ ከጠረጴዛው ላይ ከአልጋው ፊት ኬክ ተቀምጦ ሲያይ የረሳው ትዝ አለው::
"በጌታ ስም! ዛሬ ቀኑ ስንት ነው!?" አለው ሚልኪያስን እየተመለከተው::
"አየህ ብዙ ነገሮች ልብህ ላይ ዋጋ እያጡ ነው::ለነገሩ የዛሬ ዓመት አንተ ስለነበርክ ያስታወስከው የዘንድሮውን እንዳስታውስ ኃላፊነቱን እኔ ላይ ጥለህብኝ ነበር::ለዛ ይሆናል የእማዬን ስጦታ ግን..." እየተነጫነጨ ከትከሻው ላይ ጣል ያደረገውን ጋቢ አንስቶ ከወንበሩ ላይ ዘረጋው::ሚኪያስ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ በሩን በመዝጋት እግሩን እየጎተተ ወደ አልጋው አመራ::
"ፈጣሪዬ አረ ልብስህን ቀይር ቤቱን አጨቀየሀው::" ፊቱን አዙሮ ልብስ ወደመቀየሪያ ክፍል ገባ::ሲመለስ ልቡ ተመልሶ ክፉሉ ላይ ያሉትን ነገሮች ማስተዋል ጀመረ::
"እንዴ ይሄን ፎቶ ከየት አገኘሀው!?" አለው ከተሰቀሉት የልጅነት ፎቶዎች ወደ አንዱ ቀረብ ብሎ::
"ከፈለግኩ አጣለሁ ብለህ ነው!?..…የምር ግን እራት አልበላሁም::"
"እንዴ ከሂዊ ጋር ምን ስትሰሩ ነበር!?"
"ተወው እሱን.... አሁን ነው (ቴክ) ያስደረግኩት...." አለ የታሸገውን እየፈታ::
ሚኪያስ ፈገግ ብሎ እየተመለከተው:-
"እንደቀልድ አረጀን አይደል!?"
"ሃያ ስድስት ብዙ አይደለም::ገና ወጣት እየሆንኩ እንዳለ ነው የሚሰማኝ::"
"የእናትህን እንጀራ እግርህን አጣጥፈህ እየበላህ እንደዛ ባይሰማህ ነበር የሚገርመኝ::"
"ወይኔ ሚልኪ.... ምስጋና ቢስ ልሁን አአ!?"
ሚኪያስ እየሳቀ:-
"ይሄን እስክትለኝ ነበር ስጠብቅህ የነበረው::ና እስኪ ልቀፍህ ከአዕምሮዬ በላይ ነው የሆነብኝ::" እጁን ሲዘረጋለት ሚልኪያስ አቀፈው::
"እንኳንም ተወለድን::" እንዳቀፈው ቀና ሲል ከአልጋው በስተጀርባ የተደበቀውን የስዕል ሸራ ተመለከተ::ከእቅፉ ወጥቶ ወደ አልጋው በመሄድ እጁን ሰዶ አወጣው::ሚልኪያስ ዘወር ብሎ ተመልክቶ በብስጭት:-
"ይሄ ሰርፕራይዝ የማይሆንልህ ልጅ"አለው:: ሚኪያስ ዓይኑ ላይ እንባው ሞልቶ ስዕሉ ላይ ፈዞ ቀረ አንደኛ ዓመት ሲያከብሩ የተነሱት ነበር::
"በእግዚአብሔር እርቦኛል ሚኪ::" አለው::
* * *
ልደታቸውን በማስመልከት ቤቱ ላይ ሽሩ ጉድ መባል የተጀመረው ገና በማለዳው ነበር::አስቴር ሰዓቱን ተመልክታ:-
"እነዚህ ልጆች ዛሬ በጤናቸው ነው!?"
"እኔ እቀሰቅሳቸዋለሁ::" አለች ሶስና ፈጠን ብላ::አዎንታዋን ስታገኝ ወደ ላይ በመውጣት ወደ ሚልኪያስ ክፍል በመሄድ እጀታውን ስታዞረው ተከፈተ::ወደ ውስጥ ስትዘልቅ ሚልኪያስ ሸሚዙን እየለበሰ ነበር::ዞሮ ሲመለከታት ፊቱ ተቀያየረ::
"አምሮብሃል::" አለች ፈገግ ብላ::
"አይንሽን ሳላጠፋው ከዚህ ውጪ!" ጮሀባት::
"አታስመስል ባክህ::"
"አንቺ..." ተንደርድሮ ተጠጋት በዚህ መሃል ማቲያስ በሩን ከፍቶ ገባ::
"ምንድነው!?"
ሁለቱም ተደናግጠው ዞረው አዩት::