🗣እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብከዋለን! ትክክለኛ የሆኑ የወንጌል አስተምህሮዎችን መሰረት ያደረጉ፦ ዝማሬዎች፣ ትምህርቶች፣ ስብከቶች፣ ምስክርነቶች፣ የሪቫይቫል ታሪኮች፣ መንፈሳዊ ዜናዎች፣ እንዲሁም መንፈሳዊነታቸውን የያዙ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ! ለወዳጅ ጋደኞቻቹ #ሼር በማድረግ ይጋብዙ! አስተያየት @ChristianMezmur_bot ላይ ፃፉልን✍ ሁሌም ከኛ ጋር ስለሆናቹ እናመሰግናለን!
ዐብይ ጾም የሚጀምረው መቼ ነው? ጾሙስ ስንት ቀን ነው ❓
ጾም ዛሬ ገባ፤ ዐቢይ ጾም የሚጀምረው ግን በሚቀጥለው ሰኞ ዕለት ነው። (ዝርዝሩን ዝቅ ብዬ አስረዳለሁ።) የካቶሊክ፣ የአንግሊካን፣ የምስራቅ ኦርቶዶክስ እና የተለያዩ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ይህን የ40 ቀናት ጾም (Lent) ያካሄዳሉ። (የኢትዮጵያ ፕሬቴስታንቶች ግን ከኦርቶዶክሳዊነት ጋር የተለያዩ መሆናቸው እንዲያሳይላቸው ነው መሰለኝ ይህን ትውፊት አይከተሉም።) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ይህን “ጾመ አርብዓ” (ሁዳዴ) እንዲጾሙ ታዛለች፤ ይህንን ቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጓ አድርጋ በተቀበለችው መጽሐፈ ሲኖዶስ (ዘሐዋርያት ተደንግጓል)። 40 ቀናት የተመረጡት ጌታ "በገዳመ ቆሮንቶስ" ለአርባ ቀናት መጾሙንና በብሉይ ኪዳንም ሙሴና ኤልያስ የጾሙት በመሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጾም በተግባር ሲታይ ግን የአርባ ቀን ጾም ሳይሆን፣ የ54 ቀናት ነው። (አንዳንዶች 55 ያደርጉታል።) ለምን?
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በግለ ታሪካቸው እንዳሰፈሩት ከሆነ፣ ይህ የሆነበት ምክንያት በ40 ቀናቱ ጾም ላይ “ሁለት ባለሰባት ቀን ጾሞች፣ አንዱ ጾመ አርባ ከመጀመሩ በፊት፣ አንዱ ካለቀ በኋላ ተጨምረው፣ እነዚህ ሦስት ጾሞች ተርታውን ስለሚመጡ ነው። ከጾመ አርባ በፊት የሚመጣው (የመጀመሪያው) ጾም “ጾመ ሕርቃል” ይባላል። ጾመ ሕርቃልና ጾመ አርባ እንዳለቁ የሚመጣው (የመጨረሻው) ጾም ደግሞ “ጾመ ሕማማት” ይባላል። ሦስቱ ጾሞች በተለያየ ጊዜ ከመምጣት ይልቅ ተከታትለው የመጡት በአበው ውሳኔ እንጂ፣ ታሪካቸው ተከታታይ ሆኖ አይደለም። ጾመ አርባ የሚጾመው የጌታን ጾም ለማስታወስና ከጌታ ጋር ተባባሪ ለመሆን ነው፤ ጾመ ሕማማት የሚጾመውና የሚሰገደው የጌታን ሥቃይ ለማስታወስና ስርየት ኀጢአት ለማግኘት ነው። ጾመ ሕርቃል የሚጾመው ሕርቃል ላፈረሰው መሐላ ፍዳ ለመክፈል ነው።”
ሕርቃል ማነው?
ሕርቃል (Heraclius) ከ610-641 ባይዛንታይንን የገዛ ንጉሠ ነገሥት ነው። ዋና ከተማው ቁስጥንጥንያ ነበረች። በግዛቱም ውስጥ ኦርቶዶክሳውያን፣ ካቶሊኮች እና አይሁድ ነበሩ። እነዚህም ሦስት ወገኖች በየጊዜው ጠብ የሚፈጥሩና አዲስ ወራሪ በመጣ ቁጥር ከመካከላቸው አንዱ ወራሪውን አስቀድሞ በመቀበል ሌሎቹን ለማስመታት የሚጥሩ ነበሩ። ሕርቃል በፊት የነበረው ንጉሥ ፎቃ በሚገዛበት ጊዜ የፋርስ ንጉሥ ቁስጥንጥንያን ከብቦ ማስጨነቅ ጀመሩ። ያኔ ክርስቲያኖቹ የፋሲካን በዓል በሚያደርጉበት ጊዜ በየአገሩ ያሉ አይሁድ ተጠራርተው ወረሯቸውና አብያተ ክርስቲያናትን ዘረፉ። መዘበሩ።
ወዲያው ሕርቃል የጦር መኮንን ነበረና የፋርስን ንጉሥ አሸንፎ ሕዝቡን ነጻ ሲያወጣ የቁስጥንጥንያ ነዋሪዎች የገዛ ንጉሣቸውን ገድለው እርሱን አነገሡት። እርሱም ከአገር አገር በውጊያ እየዞረ ኢየሩሳሌም ሲደርስ በዚያን ወቅት አይሁድም ብዙ እጅ መንሻ አመጡለትና እንዳይገድላቸው ቃል አስገቡት፤ አይሁድ ያደረጉት የማያውቀው ሕርቃልም ቃል ኪዳን ገባላቸው። ኢየሩሳሌም ሲገባ ደግሞ የክርስቲያኖቹ ካህናት በዝማሬ ተቀበሉት። የፈራረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ያየው ሕርቃል የሆነውን ነገር ቢጠይቅ የአይሁድን ክፋት አጫወቱትና እንዲበቀልላቸው ጥያቄ አቀረቡለት።
እርሱ ግን ለአይሁድ ቃል ኪዳን እንደገባላቸውና ቃል ኪዳኑን ቢያፈርስ እግዚአብሔር እንደሚቀጣው ነገራቸው። ካህናቱ ግን “አይሁድን ተበቀልልን እንጂ ቃል ኪዳኑ አያሳስብህ፤ ንስሓ እንዲሆንህ እኛ ክርስቲያኖቹ ዓለም እስክታልፍ ድረስ ስላንተ በየዓመቱ አንድ ሳምንት እንጾምልሃለን” አሉት። በዚያ ጊዜ ሠራዊቱ አይሁድን እንዲገድሏቸው ትእዛዝ ሰጠ። ብዙዎቹን ፈጇቸው። እነዚያም ኤጴስ ቆጶሳት ስለ ሕርቃል መሓላ መጣስ በየዓመቱ አንድ ሳምንት የንስሓ ጾም እንዲጾሙ ለክርስቲያኖች ሁሉ ላኩባቸው።
እናም “ጾመ ሕርቃል” የንሥሐ ጾም ነው። Encyclopaedia Aethiopica ይህን አሳምሮ ይገልጸዋል፤ “Heraclius was also the Emperor whose repentance for the massacre of Jews in Jerusalem in 630/31 became the alleged reason for adding an (eighth) extra week to the Lent.” በማለት። ጾሙ ራሱን የቻለ ሳምንት ስላስፈለገው፣ በሰባቱ ሳምንታት ጾም ላይ ተጨምሮ ጾሙን የስምንት ሳምንታት አድርጎታል። “ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው” የሚለውን ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍም፣ “ከዐቢይ ጾም አስቀድማ የምትሆን የሕርቃል ጾም ናት” ይላል (ገጽ 150)።
እናላችሁ የዚህ ሳምንት ጾም ከዐቢይ ጾም ቀድማ የምትመጣ ጾመ ሕርቃል ናት። ጾመ ሕርቃልን ፍትሓ ነግሥቱ ቢጠቅሰውም ዝርዝሩን አይናገርም። ትርጓሜ ፍትሐ ነገሥትም መንፈሳዊ አንድምታው ላይ ያተኩራል እንጂ ታሪኩን አይናገርም፤ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው አገላለጽ። እሳቸውም ታሪኩን ያገኙት አባቶች ወደ ግዕዝ ከተተረጎመው የጊዮርጊስ ወልደ ዓሚድ የዓለም ታሪክ መጽሐፍ ላይ ነው። ስለዚህም አብዛኛው ጿሚ የዐቢይ ጾምን የመጀመሪያ ሳምንት ጾም ታሪክ ሳያውቅ ነው የሚጾመው። ለኢትዮጵያ ጾሙን የሰጠችው የግብፅ ቤ/ክ ታሪኩ በሕይወት ያሉ ወገኖችን የሚያቃቅር ሆኖ ስላገኘችው ታሪኩን መካድ ወይም ለጾሙ ሌላ ምክንያት መስጠትን የተሻለ ሆና ያገኘችው ይመስላል። በእኔ ውስን ንባብ መሠረት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን የዚህን ሳምንት ጾም “የዝግጅት ሳምንት” በሚል ስያሜ ነው የምትጾመው፤ የዐቢይ ጾም ዝግጅት መሆኑ ነው። በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደ ታዘብሁት ከሆነ ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ግን ይህ ታሪክ በቅጡ የሚታወቅ አይመስለኝም።
ጾመ ሕርቃል የአንድ ሳምንት ጾም ነው፤ ከዚያ የ40 ቀን ዐቢይ ጾም ይቀጥላል። ከዚያም የጌታን ሕማማት መነሻው የሚያደርገው የሐዋርያት ጾም ለአንድ ሳምንት ይቀጥላል። ስለዚህ 7 + 40 + 7 = 54። ከዚያም ይፈሰካል!
ዛሬ ዛሬ ዐቢይ ጾምን የሚጾሙ ጥቂት ወንጌላውያን ክርስቲያኖችን ዐውቃለሁ፤ እኔም ስተባበራቸው ነበር። ታዲያ ከአርባው ቀን በፊት (በዚህ ሳምንት) የሚካሄደውን “ጾመ ሕርቃል” መጾም አለባቸው? ይህስ ምን ያህል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?
© ጳውሎስ ፈቃዱ
@christian_mezmur🤔
ዝማሬ🎙"ይህም ያንስሃል"
ዘማሪ 👤 Tsega Tesfaye
Size💾 12.2 MB
የተለቀቀው📆 2022
ርዝመት⏰ 5:15
Quality😀 320 kbps
Genres 🎼 Gospel Song ✝️
ለሌሎችም እንዲደርስ #share📱✅
🔥🔽ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔽🔥
@christian_mezmur✅
@christian_mezmur✅
ዝማሬ🎙"ይለፈኝ"
ዘማሪ 👤 Aster Abebe
Size💾 18.7 MB
የተለቀቀው📆 Sep 2024
ርዝመት⏰ 8:07
Quality😀 320 kbps
Genres 🎼 Gospel Song ✝️
ለሌሎችም እንዲደርስ #share📱✅
🔥🔽ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔽🔥
@christian_mezmur✅
@christian_mezmur✅
▶️ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስራቸውን በፀሎት ጀመሩ! 🇺🇸
አዲሱ ተመራጭ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት Donald Trumpና ምክትል ፕሬዝዳንት JD Vance ወደ ነጩ ቤቱ ከመግባታቸው በፊት በSt. John ቤተክርስቲያን የፀሎት ስነስርዓት አድርገዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ታዋቂ ባለሃብቶችና ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች እንደነ Elon Musk, Mark Zuckerberg, Tim Cook, Jeff Bezos, Sundar Pichai, Joe Roganና ሌሎች ሰዎችም ተገኝተዋል።
ወደ ቤተመንግስት ከመመለሳቸው በፊት የእስራኤልና ሃማስን ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲስማሙ በማድረጋቸው ከብዙዎች አድናቆትና የመልካም እድል ምኞት የጎረፈላቸው ትራምፕ፣ ጦርነት ይቁም የሚለውን አቋመቸው ከምርጫው በፊት ሲያንፀባርቁ በብዛት ተስተውለዋል።
ብዙዎች አለም በእሳቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ጊዜ ለውጥ ታሳየለች ብለው በተስፋ እየጠበቁ ነው።
መልካም የስራ ዘመን Mr President! 🇺🇸
@christian_mezmur
ልዩ የበዓል ቆይታ ከ ዘማሪት መስከረም ጌቱ ጋር
ከማለዳ እስከ ምሽት የገና ዋዜማ ውሎዋን ከ ተስፋ ቲቪ ጋር ሙሉውን ፕሮግራም ከ ዩቲዩባችን ላይ ያገኙታል።
https://youtu.be/7hYNny7d-NI?si=7AWtJK4WhXj20rqi
Follow tesfa on
Facebook | tbn_et?_t=ZM-8sqJGx1EMrO&_r=1">Tik tok | Telegram | Instagram
👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿
( ለፕሮፋይላችሁ እና ለወዳጆቻችሁ ለመላክ ) HD
#QouteVerse #Bduvlm #Jesus
#Jesusbirth #holynight
#Jesusislove#Joytotheworld . .
የጠፋው ሊፈለግ ቃል ስጋ ለበሰ“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
ጨለማን ሊያጠፋ ብርሃን ተወለደ
ሞትን ሊየሳፍር ህይወት ተጀመረ
በእርሱ ላመኑቱ ድነትን ለገሰ
በዳግም ውልደት የሰው ልጅ ተረፈ
በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም የተኛው፤ ስጦታ፤
ስጦታው ለማን ይሆን?
ስጦታው የስጦታ መታሰቢያ ነው፡፡
ህጻኑ የተወለደው ነብሱን #ለዓለም ሁሉ ሊሰጥ ነው፡፡
ለዓለም?
አዎ ለዓለም ፤ለነጭ ለጥቁሩ፣ለሀብታም ለደሃ፣ለሁሉም ዘርና ጎሳ፡፡ለ..... ሀይማኖት ሳይሆን #ስጦታው_ለሚቀበል_ሁሉ፣
ከርቤ እና እጣን ሳይሆን ራሱን በስጦታ ለተሰጠው ስጦታ ሲሰጥ ነው፡፡
ምን ያክል ራስህን/ሽን ለዚህ ጌታ ለመስጠት ዝግጁ ነህ/ሽ የምንሰጠው ስጦታ ለተሰጠን ምላሽ ባይሆንም ለተሰጠን ትልቅ ስጦታ ምልክት ነው፡፡
የዮሐንስ ወንጌል 3 : 16የሰላሙ ንጉስ
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
❌የሉም ሲባል ይኖራሉ
🫢ጠፉ ሲባሉ ይበዛሉ
🤱ሲዋለዱ ብዙ መንታ
⚡️🐆ሩጫቸውን ማን ሊገታ !
@christian_mezmur🌱
ዝማሬ🎙 “ ስጋት አይገባኝም "
ዘማሪ ተስፋዬ ጫላ
የተለቀቀው📅 August , 2022
Size💾 5MB
ርዝመት⏰ 5Min
Quality🔊 128 kbps(High Quality)
Genres 🎹 Gospel Song
ገራሚ ዝማሬ ነው ሰምታቹ ተባረኩበት😱
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻
🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
✅ @christian_mezmur✅
✅ @christian_mezmur✅
በኛ ቤት ግን ዛሬም ኢየሱስ ሲመሽም ሲነጋም ብቻውን ጌታ ነው! 🙌🏾🥰
@christian_mezmur🧡
ከማላ ሃሪስ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገች እያለች ከኋላ የኮሌጅ ተማሪዎች Jesus is King Jesus is Lord የሚል ድምፅን ሲያሰሙ የካማላ መልስ ግን ልጆቹን ለማሸማቀቅ መሞከር ነበር። የተሳሳተ ቦታ ናቹ አይነት ስላቅ።
በአንፃሩ የትራምፕ ምክትል ፕሬዝዳንት ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የሪፐብሊካኑ ሴናተር አንደበተ ርቱው JD Vance በተመሳሳይ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያለ ከታዳሚዎች Jesus is King የሚል ድምፅ ሲሰማ እሱም መልሶ that's right JESUS IS KING ብሎ አስተጋባ! 🥰
እንደ ኢትዮጵያዊ ማንም የምረጥ ማን ምንም ልዩነት ላያመጣ ይችል ይሆናል። የአሜሪካ የውጪ ፖሊሲ መንግስት ቢቀያየርም በአብዛኛው ወጥ ስለሆነ። እንደ ክርስቲያን፣ የኢየሱስ ሲም ሱጠራ ደስ እንደሚለው ሰው፣ ለሰው አእምሮ የሚከብድን ነገር ሲፈፅሙ የኖሩትን ዲሞክራቶችን ማየት እንደማይፈልግ ሰው ሪፓብሊካን ነጩን ቤት ስለመረከባቸው እግዚአብሔር ይመስገን !
JESUS IS THE KING!
@christian_mezmur
የእገዛ ጥሪ 🤲🏾
ለዚህች ጨቅላ እንድረስላት ሁላችሁም ሼር አድርጉ !
ከእናቴ ማህፀን ከወጣሁ ጥቂት ወራቶች ናቸው የሆኑኝ። ለመንተባተብ እንኳን ያልታደልኩት እኔ ሳሙኤል የ 4 ወር እድሜ ላይ የምገኝ ትንሽዬ እንባቀቅላ ነኝ።
ባጋጠመኝ የልብ ህመም የልቤ ውስጥ ክፍል 10 inch መጠን ተሰንጥቋል። ወደዚህች ምድር ከመጣውባት ለ4 ወራት ያክል በጂንካ ዞናል ሆስፒታል ለውጥ አገኝ ብዬ ህክምና ስከታተል ነበር።
ነገር ግን የተሻለ ህክምና እንደሚያስፈልገኝ ይሄም እንዲሆን 1.2 ሚልየን ብር የተጠየኩ ሲሆን በወላጆቼ የመምህርነት ደሞዝ አቅም ሊታደጉኝ አልቻሉም።
በእናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን በቸርነት እጆች ካላችሁ ሣንቲም ቆንጥራችሁልኝ ህክምና እንዳገኝ ትታደጉኝ ዘንድ በአንደበቴ መማፀን ባልታደል እንኳን በልቤ ጩኸቴን እያሰማሁ እየተማፀንኩ እገኛለሁ💔🙏
CBE
1000453403541 (Asfawu Dessalegn)
1000453401859 (Genet Kebede )
@christian_mezmur⭐️
#Update
" እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።
ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።
ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።
በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።
ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።
በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ።
ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።
ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።
ለመረጃ ያህል 4.9 ሬክተር ስኬል ምን ያህል ነው ?
➡️ Micro: ከ3.0 ሬክተር ስኬል በታች: በጣም ትንሽ በሰዎች ሊታወቁ የሚችሉ
➡️Minor: ከ3.0 እስከ 3.9; ጉዳት የሌለው ለሰዎች በደንብ የሚታወቅ
➡️Light: ከ4.0 እስከ 4.9; ቀለል ያለ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል
➡️ Moderate: ከ5.0 እስከ 5.9; መጠነኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል
➡️Strong: ከ6.0 እስከ 6.9; ከበድ ያለ ጉዳት ሊያስከት የሚችል
➡️Major: ከ7.0 እስከ 7.9; በጣም ከባድ አደጋ ሊያደርስ የሚችል
➡️Great: ከ8.0 ሬክተር ስኬል በላይ; በጣም አስከፊ አደጋ ሊያደርስ የሚችል
Full Album Playlist Aster Abebe
https://youtube.com/playlist?list=PLKNx68410nPXKxLqRbQ5FWHte-cOCN1Lg&si=5N4U74j1eFUW3iBq
የማወራችሁ ስለ ኃይል ነው! ኃይል ያስፈልገናል!
ኃይል ስል፡ የማወራው፡ መሬት ላይ ጥሎ እንደ ትል ስለሚያንፈራፍረው ኃይል አይደለም፤ የማወራው መርሴዲስ ቤንዝ (Mercedes benz) ለመንዳት አዋጅ እንድናውጅ ስለሚያደርገን ኃይል አይደለም፤ የማወራው፡ ያልተፈወሰውን ተፈወሰ ስለሚያስብለው የውሸት ኃይል አይደለም። የማወራው፡ የክርስትናን ሕይወት በሚገባ እንድትኖሩ ስለሚያስችለው ኃይል፤ እውነተኛ በሆነ ፍቅር ስለሚያራምድ ኃይል፤ ስለ ጸሎት ኃይል፤ ወንጌል-መስካሪ ስለሚያደርግ ኃይል ነው። ይህ ኃይል ነው የሚያስፈልገን።
መጋቢ ፖል ዎሸር
(Paul Washer)
("Empowered by the holy spirit" ከሚለው ስብከት የተቀነጨበ)
@christian_mezmur⭐️
የልጆቼ አባት በክርስቶስ ፍቅር ሁልግዜ የምወደዉ ዶክተር ወዳጄነህ ወደ አገልግሎቱ ቢመለስ መልካም እንደሆነ ይሰማኛል፣ በተለይ እጅግ ብዙ ነፍሳት ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደሚጨምር አምናለሁ!
የእግዚአብሔር ፀጋ አሁንም በእሱ እየሰራ እንዳለ አዉቃለሁ።
አይ በዚህና በዚያ ምክንያት ማገልገል የለበትም የሚል ካለ በደሉን ሁሉ አንድ ሳይቀር በእኔ ላይ ቁጠሩት! እዉነት ለመናገር ይሄ ሁሉ አገልጋይ ፍፁም ሆኖ ነዉ የሚያገለግለዉ? ስንተዋወቅ አንተናነቅ እንደተባለዉ ነዉ! የእግዚአብሔር ምህረት ሸፍኖለት ነዉ በአብዛኛዉ አገልጋይ መድረክ ላይ የሚቆመዉ እንጂ ብዙ ነዉ ጉዱ። በእሱ ላይ ያላችሁን የትኛዉንም ቅሬታ በእኔ ላይ ቁጠሩት ወይም ጨርሳችሁ ምህረት አድርጉለትና እግዚአብሔር በእርሱ የሚሰራዉን ተመልከቱ!
በሁለታችንም ማንም ባይፈርድብን በጣም ደስ ይለኛል ያሳለፍነዉን የሚያዉቅ የለምና!ነገር ግን የግድ በአንዳችሁ መፍረድ አለብን አንዳችሁ ከአገልግሎት መገለል አለባችሁ ከተባለ በእኔ ላይ ፍረዱ እኔን ከአገልግሎት አግልሉኝ እሱ ያገልግል።
ፈፅማችሁ ምህረት አድርጉና በክብር ወደ አገልግሎቱ መልሱት ያገልግል!
መከሩን ወደጎተራዉ ያስገባ።
@christian_mezmur⭐️
https://www.youtube.com/live/ZDp2JTWXwiU?si=J0Dz_6HT8hNwBEr8
Читать полностью…ዝማሬ🎙"ምህረትህ"
ዘማሪ 👤 Henok Addis
Size💾 11.0 MB
የተለቀቀው📆 2011
ርዝመት⏰ 04:45
Quality😀 320 kbps
Genres 🎼 Gospel Song ✝️
ለሌሎችም እንዲደርስ #share📱✅
🔥🔽ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔽🔥
@christian_mezmur✅
@christian_mezmur✅
“በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።”
ኢሳ 26:3
©Fenan Befikadu
@christian_mezmur⭐️
''እርሱ የሰው ልጅ ወደመባል ዝቅታ ወረደና እኔን የእግዚአብሔር ልጅ ወደመባል ከፍታ ወሰደኝ።''
የንጉሡ ግብዣ
“እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀላል ነውና።”
ማቴዎስ 11:28-30
ያያ ዘ ልደታ: "ግፋ ቢል ከ5 እስከ 7 ዓመት በሗላ የፕሮቴስታንት እምነት ያከትምለታል!::"
"ተማር ይጠቅምሃል እንደምንም ቢያንስ ሚኒስትሪ ተፈተን" ሲባል ለክፋት የመከሩት መስሎት እኮ ነው እንዲህ ጋዜጣ አንብቦ የመረዳት አቅም እንኳን የሌለው ሁኖ የቀረው 🤦🏽♂️😂🤷🏾♂️
Btw በቀሀስ ዘመን <5% ነበርን፣ ደርግ እንደዚያ አሳዶን አስሮ እና ገድሎን በዛን እንጂ ከቁጥር እልጎደልንም! አሁንማ ሀገር ምድሩን በዝተንበታል! ዘንበንበታል!
"የሰናፍጯን ቅንጣት ቢዘራት
ጌታ በምድር እንድትበዛ
ያ ጉልበተኛ መጥቶ ረገጣት
የማትበቅል መስላው ፈዛዛ
ግን አልተሳካም አምልጣ ወጣች
ሄደች አደገች
ጌታ ይመስገን ድምበሯ ሰፋ
ለደካከሙት መጠለያ ሆነች
ህዝብህን.... "
©️Ebenezer F. Zeleke
@christian_mezmur
📺አንጋፋዋ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ታላቅ የወንጌል ጀማ ስብከት በአዲስ አበባ ስታዲየም አድርጋለች! 👏🏾
ጅማሮውን ከትናንት በስትያ ያደረገው ይህ ፕሮግራም በብዙ ድል በዛሬው ዕለት ተጠናቋል 🥰
#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል😍
@christian_mezmur🧡
የአግዙኝ ጥሪ!
ፌኔት ቱሉ እባላለሁ የ18 አመት ወጣት ነኝ በነበረብኝ የደም ግፊት የተነሳ ሁለቱ ኩላሊቶቼ ስራ አቁመዋለወ። የህክምናው ወጪ ከቤተሰቦቼ አቅም በላይ ስለሆነ እንድታጉዙኝ ደግም እንደቆም እንድትረዱኝ በጌታ ስም እጠይቃቹሃለሁ! 😪
🏦1000611589712
Fenet Tulu Worku (CBE)
🏦1000247849185
Abel Tulu Worku (CBE)
🏦01320444559000
Abel Tulu Worku (Awash)
📞 0927876182
@christian_mezmur🧡
ያልተጠበቀው የዲያቆን ሐዋዝ ውሳኔ 🥹
@christian_mezmur
▶️ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ! 🇺🇸
የሪፐብሊካን ተወካይ የሆኑት ትራምፕ፣ ዲሞክራቷን ካማላ ሃሪስን አሸንፈው በድጋሚ ወደ ነጩ ቤት ተመልሰዋል። ከዚህ በፊት 2016 ላይ ሂላሪ ክሊንተንን በማሸነፍ መንበሩን መጨበጣቸው አይዘነጋም።
ትራምፕ ክርስትና ላይ ያላቸው አቋም፣ ድምፅ አጣለው ብለው ሳይፈሩ በድፍረት ሁለት ፆታ ብቻ ነው ያለው የሚሉ፣ ግብረሰዶማዊነትን የሚቃወሙ፣ የመመረጥ እድሉን ካገኙ ውርጃን በህግ ሊከለክሉ የዘጋጁ፣ ጦርነት መፍትሄ አይደለም ብለው የሚያምኑና ፅንፍ ለፅንፍ ከሆኑ ሃገራት ጋር መወያየትን ሚመርጡ (ከሰሜን ኮሪያ መሪ ጋር በአካል የገናኙ የመጀመሪያው የአሜሪካ መሪ ናቸው)፣ በእስራኤል የአሜሪካን ኤምባሲ ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም የመለሱ እና በሌሎችም ምክንያቶች አሜሪከሰ በመገኙ ትላልቅ አገልጋዮችና ፓስተሮች ትራምፕን እንዲመረጡ ሰዎችን ሲያበረታቱ ነበር።
እንደ አንድ ክርስቲያንና አሜሪካ የአለምን ቅርፅ የመቀየር አቅም አላት ብሎ እንደሚያምን ሰው፣ ሃሪስና ዲሞክራቶች የያዙትን ሰይጣናዊ ሃሳብ ትራምፕ ማሸነፉ አስድስቶኛል!
God Bless You President !
@christian_mezmur
ዝማሬ🎙"ሳሙኤልን እንካ"
ዘማሪ 👤 Aster Abebe
Size💾 8.5 MB
የተለቀቀው📆 Sep 2024
ርዝመት⏰ 9:14
Quality😀 128 kbps
Genres 🎼 Gospel Song ✝️
ለሌሎችም እንዲደርስ #share📱✅
🔥🔽ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔽🔥
@christian_mezmur✅
@christian_mezmur✅
#ሃገራዊ #Ethiopia🇪🇹
በአዲስ አበባና በአከባቢዋ በበርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል!
ከምሽት 2:10 አከባቢ በርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር።
በአዲስ አበባ ህንፃዎች ላይ የነበሩ ሰዎችም በደንብ ንዝረቱ የተሰማቸው ሲሆን በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ከስጋት አንጻር ወደ መሬት ወርደው ተሰባስበው ነው የሚገኙት።
the end is near ንስሃ ንስሃ ንስሃ!
26 tracks 😍
አዎ 26 ትራኮች ያሉት የዘማሪት አስቴር አበበ ሃሌሉያ አልበም ተለቀቀ!
በ apple music🎵, Spotify🎵, i tunes እና በተለያዩ የonline ገበያዎች ተለቋል!
Youtube📹 ላይ ስለሌለ ለጊዜው በውጭ ያሉ ወገኖች በኢትዮጵያ ያለነውን እንቁልልጭ እያሉን ነው 😂
ከApple music የአስቴርን አልበም መግዛት የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ተጠቀሙ።
➡️https://music.apple.com/ca/album/hallelujah/1771682841
@christian_mezmur⭐️