New Month || New Topic
FEAR OF GOD
ኢሳይያስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።
² የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
³ እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል።
#Fear_Of_God
#Week_1
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
ዘፍጥረት 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እግዚአብሔርም አለ፦ በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፤
¹³ ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።
¹⁴ በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤
…
¹⁶ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።
#The_Year_Of_Cloud
#Kabod_Verses
#Meditate_The_Word
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
ሉቃስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት
ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
²⁹ ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።
³⁰ እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤
³¹ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።
³² ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።
³³ ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።
³⁴ ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
³⁵ ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
³⁶ ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።
#The_Year_Of_Cloud
#Kabod_Verses
#Meditate_The_Word
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
🔥🔥🔥 ነገ
🔥🔥🔥በልዩ ፕሮግራም እንጠብቃችኋለን!
ከመንፈስቅዱስ ጋር እንደ አዲስ ለመነካካት ተዘጋጅታችሁ ኑ!
🔴 አዳዲስ ሰዎችን ጋብዘን እንምጣ!
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
🔥🔥🔥Don't Miss It🔥🔥🔥
Tommorow 9 seat we will continue our youth program.
#The_Year_Of_Cloud
#Glorious_Service
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
✨CJY Fam✨
Today was Unforgottable Day.God restored us with his presence...😭😭😭
If you have any kind of testimony....
Please feel free to share it with us on:-
@Cjyouth01
👂We would love to hear from you!👂
#The_Year_Of_Cloud
#week_3
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
☁️ ደመና ☁️
Week 2
ዘጸአት 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ።
²² የደመና ዓምድ በቀን፥ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከሕዝቡ ፊት ከቶ ፈቀቅ አላለም።
☁️ የደመናው የመጀመሪያ አላማ መንገድ ማሳየት ነው። ነገር ግን የመጣው ደመና ሁላቸውንም ውጤታማ አላደረጋቸውም።
☁️ የመጣው የእግዚአብሔር ደመና ለሁሉም ቢሆንም ፤ ሁሉም ግን የመጣውን ደመና አልተጠቀሙበትም።
☁️ ለዚህ ነው የመጣውን ደመና ፣ የታወጀልንን ደመና ስንቀበል ደመናው የመጣበትን አላማ መረዳት አለብን። እንዴት እንደሚሰራ ማወቅ አለብን።
☁️ Season ስለተለወጠ ተለወጥን ማለት አይደለም። ከወቅቱ ጋር እንድንለወጥ የሚያደርገው ለወቅቱ ያለን መረዳት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤
² ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤
³ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ፥ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤
⁴ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።
☁️ ደመናው የመጣው ለሁሉም ነበር ፣ በዚህ ደመና ስር የነበሩት ሁሉም ነበሩ። ነገርግን ደመናው የመጣበትን አላማ ያወቁ ሰዎች ብቻ ነበሩ ያተረፉት።
☁️ ደመናውን ህይወታቸው ያደረጉ ሰዎች አሉ ፤ ደመናውን ለህይወታቸው መጠቀሚያ ያደረጉ ሰዎች አሉ።
☁️ ደመናው ከእኛ የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። እርሱም፦ መማረክ(Surrender)ነው።
☁️ ለደመናው የተማረኩ ሰዎች ደመናው ህይወታቸው የሆነላቸው ሰዎች ናቸው።
☁️ ደመናው የሚፈልገው የተማረከን ህይወት ነው።
☁️ ያልተማረኩ ሰዎች ናቸው ደመናውን ለህይወታቸው መጠቀሚያ የሚያደርጉት።
ዘጸአት 33
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ሙሴም ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ የደመና ዓምድ ይወርድ ነበር፥ በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር።
¹⁰ ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ተነሥቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይሰግድ ነበር።
¹¹ እግዚአብሔርም ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነጋገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመለስ ነበር፤ ነገር ግን ሎሌው ብላቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድንኳኑ አይለይም ነበር።
☁️ ሙሴ ወደ ደመናው ሲገባ አንድም ሰው ወደ ድንኳኑ መጠጋት አይችልም ነበር።
☁️ ነገርግን አንድ ብቸኛ ሰው አለ ደመናውን ህይወቱ ያደረገ ፣ ከደመናው ወጪ ህይወት የሌለው ፣ ህይወቱ ከደመናው ጋር የተሰፋ ኢያሱ የተባለ ሰው ነበር።
☁️ ይህ ሰው ለደመናው የተማረከ ሰው ነው።
☁️ አንተ ህያው ሆነህ ደመናው ከአንተ ጋር ሊንቀሳቀስ አይችልም።
☁️ ደመናው በህይወታችን መስራት እንዲጀምር የግድ ለራሳችን መሞት አለብን።
#The_Year_Of_Cloud
#Week_2
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
✨CJY Fam✨
Today, God has blessed us with His Tangible presence... If you have any kind of testimony....
Please feel free to share it with us on:-
@Cjyouth01
👂We would love to hear from you!👂
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
💥 💥💥💥የ 2016 የመጀመሪያው የወጣቶች ፕሮግራም💥💥💥💥
🕒 ከ 9ሰዓት ጀምሮ 🕒
#The_Year_Of_Cloud
#Glorious_Service
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
https://youtu.be/PkcMom3CGd8?si=tsJA9GSMun3vVMdp
Raise Your Expectations
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
#2_Days_Left
#CJY_Conference_2K21
@CJYouth1
@CJYouth1
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
:+: ሻሎም የሲጄ ወጣቶች:- :+:
ከጳጉሜ 2-5 ለ አራት ተከታታይ ቀናት አዲሱን የአምልኮ አዳራሽ ምረቃ እና አመታዊ የወጣቶች ኮንፈረንስ እንዳለን ይታወቃል። ለዚህም ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት ሲባል ነገ ማለትም እሁድ ነሀሴ 28 የወጣቶች ፕሮግራም አይኖረንም።
:+: :+:
@CJYouth1
@CJYouth1
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ሁላችንም በጉጉት ምንጠባበቀው CJY Conference
!!!!!!እነሆ!!!!!!
❤️🔥With Apostle Tamrat T. And Dr. Rodney H.B
🎉 በፕሮግራሙ አዲሱ የአምልኮ አዳራሻችንን እናስመርቃለን 🎉
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🗓 ጷግሜ 2 - 5
📌CMC branch
👇 Click for direction 👇
--------------------------------------------
Christ Jesus (CJ) International Church (CJTV)
---------------------------------------------
እራት እና መኝታ በነፃ ተዘጋጅቷል!!!
እንዳያመልጣችሁ።
@CJYouth1
@CJYouth1
@CJYouth1
◈ ◈
──•◈•──
#Kabod_Quotes
──•◈•──
✴ It is through the knowledge of Christ that we grow to his knowledge.
.
In order to grow into his knowledge We have to work on our thoughts
-Apostle Tamrat.T
#Renewal_of_mind
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
Tomorrow we will have a glorious service with new topic and new month. Invite your friends and be there on time.
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
Tomorrow 🔥🔥
#Come_With_Higher_Expectation.
#Invite_New_Friends.
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
⚠ ATTENTION ⚠
ሻሎም የሲጄ ዩዝ ቤተሰቦች ነገ በቤተክርስቲያናችን በሚኖረው የፓርትነርስ ፕሮግራም ምክንያት የዩዝ ፕሮግራማችን ከ8:00 ጀምሮ የሚደረግ ይሆናል።
🛑 አዳዲስ ሰዎችን ጋብዘን እንምጣ!
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
✨CJY Fam✨
ዛሬ🔥🔥🔥🔥 አስደናቂ ጊዜ ነበረን🔥🔥🔥🔥 የጌታ ደመና በመካከላችን በሙላት ነበር 🌩🌩🌩
ስለ ደመና ተምረን ብቻ ሳይሆን ደመናው በመካከላችን ተገልጦ ነበር የወጣነው!!!
ማንኛውም አይነት ምስክርነት ካላችሁ @Cjyouth01
ልታካፍሉን ትችላላችሁ👍
👂ከእናንተ መስማት እንወዳለን!👂
#The_Year_Of_Cloud
#week_4
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
☁️ ደመና ☁️
Week 3
ዘጸአት 33
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ሙሴም ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ የደመና ዓምድ ይወርድ ነበር፥ በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር።
¹⁰ ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ተነሥቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይሰግድ ነበር።
¹¹ እግዚአብሔርም ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነጋገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመለስ ነበር፤ ነገር ግን ሎሌው ብላቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድንኳኑ አይለይም ነበር።
☁️ ሙሴ ደመና አይቷል ፤ ህዝቡም ደመና አይቷል።
☁️ ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገረው ግን ሙሴ ነበር።
ዘኍልቁ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ደመናውም በማደሪያው ላይ ብዙ ቀን በተቀመጠ ጊዜ የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር።
²⁰ አንዳንድ ጊዜ ደመናው ጥቂት ቀን በማደሪያው ላይ ይሆን ነበር፤ በዚያን ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፤ እንደ እግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር።
²¹ አንዳንድ ጊዜም ደመናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቀመጥ ነበር፤ በጥዋትም ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር፤ በቀንም በሌሊትም ቢሆን፥ ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።
²² ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም አንድ ዓመት ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።
☁️ ደመና ካለ ቀጥሎ እግዚአብሔር አለ።
☁️ ከደመናው የሚወጣ ድምፅ እንድንኖር ያደርገናል።
☁️ ከእግዚአብሔር ህልውና የሚወጣን ድምፅ ሰምተን ተመሳሳይ መሆን አንችልም።
“ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል፥ ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፤ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል፤ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም።”
— መዝሙር 147፥8
☁️ ለምድር ዝናብ የሚዘጋጀው ሰማይ በደመና ሲሞላ ነው።
☁️ ሰማይ በእግዚአብሔር መገኘት ሲሞላ ያኔ ነው ልምላሜ።
☁️ እግዚአብሔር አግኝቶን የምንለመልመው ልምላሜ ፤ ከእኛ ይልቅ ለሌሎች ይጠቅማል።
#The_Year_Of_Cloud
#Week_3
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
Tomorrow🔥🔥🔥
Tomorrow we will have a glorious service. Invite your friends and be there on time.
9:00LT🕒
#The_Year_Of_Cloud
#Glorious_Service
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
1ኛ ቆሮንቶስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤
² ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤
³ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ፥ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤
⁴ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።
#The_Year_Of_Cloud
#Kabod_Verses
#Meditate_The_Word
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
☁️ ደመና
☁️
☁️ የእግዚአብሔር ደመና የእግዚአብሔር መገኘት ማለት አይደለም።
☁️ የእግዚአብሔር ደመና የእግዚአብሔርን መገኘት የተሸከመ ነገር ነው።
☁️ መፅሀፍ ቅዱሳችን እግዚአብሔር ደመና ሆኖ መጣ አይለንም ፤ እግዚአብሔር በደመና ውስጥ ሆኖ መጣ እንጂ።
☁️ ደመና የሚወክለው የእግዚአብሔርን መገኘት ነው።
☁️ ደመናው አለ ማለት ውስጡ እግዚአብሔር አለ ማለት ነዉ።
☁️ ደመናው ክብርን ይገልፃል እንጂ ፤ ክብር አይደለም።
ዘጸአት 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ።
²² የደመና ዓምድ በቀን፥ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከሕዝቡ ፊት ከቶ ፈቀቅ አላለም።
☁️ ደመናው ወደ ህይወታችን የእግዚአብሔርን መገኘት ይዞ ሲመጣ ከእኛ የሚጠበቀው የመጀመሪያው ነገር ወደ ህይወታችን ለመጣው ደመና መማረክ ነው።
☁️ ለደመናው መማረክ ስንጀምር ደመናው ወደ ወደደው ይመራናል።
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
https://youtu.be/aJl7fcgOtBw?si=KLI4QopdBC_JJqyj
Raise Your Expectations
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
#CJY_Conference_2K21
@CJYouth1
@CJYouth1
https://youtu.be/IEWPgdtvi9E?si=xpuQ98u_F-Bz2HEA
Raise Your Expectations
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
#CJY_Conference_2K18
@CJYouth1
@CJYouth1
https://youtu.be/k8esHoOhco4?si=AVY-107TxHqdBjo1
Raise Your Expectations
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
#4th_Round_CJY_Conference
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
የሲጄ ወጣቶች በትናንትናው እለት ከፊታችን ላለው የወጣቶች ኮንፍረንስ ፀልየዋል!!
🔥We are very eager and expectant
to experience the tangible
presence of God !
#CJY
#CJY_Conference
@CJYouth1
@CJYouth1
ኤፌሶን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥
²³ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥
²⁴ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
#Renewal_of_mind
#Week_2
#Kabod_Verses
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1