Miss it Not!
The Coming Sunday🔥
Bring your notebook and bible📖
Invite your Friends🧑🤝🧑
⛔️Share & Repost It.
#CJY
#New_Month
#The_Year_of_Cloud
@CJYouth1
@CJYouth1
This Sunday🔥🔥🔥
We will have Special Youth Service
💥we will Start Our New Month💥
📆 Jan 28 📆
⏰ 9:00LT ⏰
⛪ @CJ Church ⛪
Tomorrow We will Post Our Upcoming Month Topic.
#Invite_and_Share
#CJY
#New_Month
#Special_Youth_Service
#The_Year_of_Cloud
@CJYouth1
@CJYouth1
Let's all attend the service tomorrow!
🔥🔥🔥It Will Be Glorious 🔥🔥🔥
#CJY
#Conference
#The_Year_of_Cloud
@CJYouth1
@CJYouth1
🎄 የፊታችን አርብ 🎄 ታህሳስ 26 🎄
🎄 ልዪ የገና ፕሮግራም 🎄
@CJ Church ⛪
⏰ ከ 10:00 ጀምሮ ⏰
#Christmas_Eve
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
HAPPY BIRTHDAY FATHER😍
____
Today on this Beloved day, we are very proud to have the opportunity to wish a very happy birthday to our father Apostle Tamrat.T
____
Apostle, you are the father of this generation, especially for the youth of CJ, you have become a role model for us. God used you to Change our Lives, to Change our Hunger, and Change Our Destiny. God used you and made us not for anything else but for His glory. We are very Lucky to have you as a father.🤗
____
You are the Best Leader, The Best Father, The Best Teacher in the World. You are a Hero For Our Generation.All CJY Families HONORS AND CELEBRATES YOU.
🫡
❤️We love you❤️
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
#HAPPY_BIRTHDAY
#FATHER
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
🔥🔥🔥የፊታችን እሁድ 🔥🔥🔥
💥 ልዩ የወጣቶች ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።
📌ሁላችንም አዳዲስ ጓደኞቻችንን ጋብዘን እንምጣ!
SHARE SHARE SHARE !!
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
FEAR OF GOD
እግዚአብሔር ምስጢሩን ከሚፈሩት ወዳጆቹ አይሰውርም፤ ኪዳኑንም ይገልጥላቸዋል።
መዝሙር 25:14 NASV
The Lord is a friend to those who fear him. He teaches them his covenant.
Psalms 25:14 NLT
#Kabod_Verses
#Fear_Of_God
#Final_Week
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
. FEAR OF GOD
Final Week
🤔እግዚአብሔርን መፍራት ምን ማለት ነው❓
✨ ባሳለፍናቸው ሳምንታት እግዚአብሔርን መፍራት ብለን የምናስባቸውን ነገር ግን ያልሆኑትን ስናይ ቆይተናል፤ በዚህ ሳምንት ደግሞ ትክክለኛው እግዚአብሔርን መፍራት ምን እንደሆነ የምናይ ይሆናል:-
✨ እግዚአብሔርን መፍራት ማለት :-
1ኛ. በእግዚአብሔር እውቀት ላይ መደገፍ ማለት ነው።
“በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ፤”
— ምሳሌ 3፥7
✨ በራስ ማስተዋል እና እውቀት ላይ መደገፍ በራሱ እግዚአብሔርን አለመፍራት ነው።
✨ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች መገለጫ ሁልጊዜ ከሚያዩት እና እነርሱ ጋር ካለ እውቀት በላይ በእግዚአብሔር እውቀት ላይ ጥገኞች ናቸው።
✨ ኖህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር ፤ ኖህ አከባቢው ላይ ባሉ ሰዎች እውቀት ፣ እራሱ ባለው እውቀት ሳይሆን በእግዚአብሔር እውቀት የተመላለሰ ሰው ነው።
✨ እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ለእግዚአብሔር መንቀጥቀጥ ማለት አይደለም። እግዚአብሔርን መፍራት ማለት በእግዚአብሔር እውቀት ላይ መደገፍ እና በዛ እውቀት መመላለስ ማለት ነው።
............ይቀጥላል !
#Fear_Of_God
#Final_Week
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
✨CJY Fam✨
ዛሬ እግዚአብሔር አስደናቂ ጊዜን ሰጥቶናል። እግዚአብሔርን ስለመፍራት ተምረን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን በፍቅር ለመፍራት ልባችንም ተቀይሮ ነበር የወጣነው!
በእነዚህ ሳምንታት እግዚአብሔርን ስለመፍራት ማንኛውም አይነት ምስክርነት ካላችሁ:-
@Cjyouth01 ልታካፍሉን ትችላላችሁ👍
👂ከእናንተ መስማት እንወዳለን!👂
#Fear_Of_God
#Final_Week
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
. FEAR OF GOD
Week -2
ኤፌሶን 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
³² ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።
³³ ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።
✨ መፅሐፍ ቅዱሳችን በእኛ እና በክርስቶስ መካከል ያለውን ህብረት ከገለፀባቸው ምሳሌዎች መካከል አንዱ የባል እና የሚስት (የክርስቶስ አና የቤተክርስቲያን) ህብረት አንዱ ነው።
✨ የባል ድርሻ ሚስቱን መውደድ ነው።
✨ የሚስት ድርሻ ደግሞ ባልዋን መፍራት ነው።
✨ስለዚህ የክርስቶስ ድርሻ ቤተክርስቲያንን መውደድ ሲሆን እግዚአብሔርን መፍራት ደግሞ የቤተክርስቲያን(የእኛ) ድርሻ ነው።
✨ እግዚአብሔር እኛን በወደደበት በዛው መጠን እኛ ደግሞ እርሱን እንድንፈራው ከእኛ ይጠብቃል።
✨ አንድ ባል ሚስቱ እርሱን መፍራት ባቆመች ጊዜ አይጠላትም ፤ ነገር ግን በእርሷ ደስተኛ አይሆንም።
✨ ልክ እንደዛው እኛም እግዚአብሔርን መፍራት ስናቆም እግዚአብሔር ይጠላናል ማለት አይደለም ፤ ነገርግን የእግዚአብሔርን ደስታ እና ፈገግታ ከህይወታችን ላይ እናጣዋለን።
✨ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ደስታ በህይወታችን ላይ የምናቆይበት ትልቁ ቁልፍ እግዚአብሔርን በፍቅር በመፍራት ነው።
ኢሳይያስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል።
✨ እግዚአብሔር በፍቅር የሚፈራ አምላክ ነው።
✨ ከእግዚአብሔር የሆነ ፍርሀት የሚያሸሽ ፍርሀት አይደለም። እንድንወደውና ለእርሱ ክብር እንድንኖር የሚያደርግ ፍርሀት ነው።
ምሳሌ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፤ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።
²⁹ እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና፤
✨ እግዚአብሔርን መፍራት ምርጫ ነው።
“እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤”
— ዕብራውያን 5፥7
✨ ኢየሱስ ፀሎቱ እንዲሰማለት ካደረጉ ነገሮች አንዱ እና ዋነኛው እግዚአብሔርን መፍራቱ ነው።
✨ ፀሎታችን ቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን እንዲገባ ፤ እንዲሁም ፀሎታችን ከእግዚአብሔር ዙፋን መልስን ይዞ እንዲወጣ የሚያደርገው እግዚአብሔርን መፍራታችን ነው።
#Fear_Of_God
#Week_2
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
ቅዳሜ እና እሁድ 🔥🔥🔥
በቤተክርስቲያናችን በሚኖረው ኮንፍራንስ ላይ ሁላችንም እንገናኝ !
#Conference
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
FEAR OF GOD
እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።
ምሳሌ 15:16 NASV
Better to have little, with fear for the Lord, than to have great treasure and inner turmoil.
Proverbs 15:16 NLT
#Fear_Of_God
#Week_2
#Kabod_Verses
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
ነገ🔥🔥🔥
ከ8:30 ጀምሮ የወጣቶች አገልግሎታችን ይቀጥላል።
📌 አዳዲስ ሰዎችን ጋብዘን እንምጣ!
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
FEAR OF GOD
እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ ምሕረቱንም በሚጠባበቁት ላይ አትኵረዋል።
መዝሙር 33:18 NASV
But the Lord watches over those who fear him, those who rely on his unfailing love.
Psalms 33:18 NLT
#Fear_Of_God
#Week_1
#Kabod_Verses
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
⚠⚠⚠⚠⚠⚠⚠⚠⚠⚠⚠⚠⚠⚠
የተወደዳችሁ የCJY ቤተሰቦች:-
በዚህ ሳምንት የሚኖረን የወጣቶች ፕሮግራም በመንገድ መዘጋጋት ምክንያት አይኖረንም😔
ቀጣይ ሳምንት በልዩ ፕሮግራም እንጠብቃችኋለን👍
እንወዳችኋለን❤
#CJY
#The_Year_of_Cloud
@CJYouth1
@CJYouth1
ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
💥Merry Christmas💥
💥To All CJY Families💥
THE KING IS BORN!
#merry_Christmas
#CJY
#The_Year_of_Cloud
@CJYouth1
@CJYouth1
Leaders Honoring and Appreciation ceremony 🤝
#New_Beginning
#New_Explosion
#New_Era
#CJY
#The_Year_of_Cloud
@CJYouth1
@CJYouth1
. FEAR OF GOD
Final Week
🤔እግዚአብሔርን መፍራት ምን ማለት ነው❓
✨ እግዚአብሔርን መፍራት ማለት :-
3ኛ. ክፉ (Evil) የሆነውን ነገር መጥላት ማለት ነው።
“እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም አፍ እጠላለሁ።”
— ምሳሌ 8፥13
✨ ክፉ የተባለን ነገር እስካልጠላን ድረስ በፍፁም እግዚአብሔርን እየፈራን አይደለም።
✨ እግዚአብሔርን መፍራት መንፈስ ነው። ከራሱ ከእግዚአብሔር የምንቀበለው መንፈስ ነው።
✨ በራሳችን እግዚአብሔርን መፍራት አንችልም ፣ በራሳችን ክፉን ነገር መጥላት አንችልም።
✨ ክፉ (Evil) የሆነውን ነገር ለመጥላት እግዚአብሔርን መፍራት ያስፈልገናል ፤ እግዚአብሔርን ለመፍራት የእግዚአብሔር መንፈስ ያስፈልገናል።
✨ ያለ እግዚአብሔር መንፈስ እግዚአብሔርን መፍራት አይቻልም።
“ሰውንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው።”
— ኢዮብ 28፥28
✨ ሁላችንም የምንፈልገውን ጥበብ የተባለውን ነገር እግዚአብሔር ያስቀመጠው እርሱን በመፍራት ውስጥ ነው።
✨ እግዚአብሔርን ስንፈራ ለጥበብ መፀለይ አይጠበቅብንም ፤ ጥበብ የህይወታችን አካል ይሆናል።
#Fear_Of_God
#Final_Week
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
. FEAR OF GOD
Final Week
🤔እግዚአብሔርን መፍራት ምን ማለት ነው❓
✨ እግዚአብሔርን መፍራት ማለት :-
2ኛ. እግዚአብሔር እንዳለ እና እግዚአብሔር እንደሚያየን መገንዘብ ማለት ነው።
✨ አብዛኞቻችን ጌታ የበራልን የመጀመሪያ ጊዜ ላይ የገባን የመጀመሪያው ነገር እግዚአብሔር እንደሚያየን እና አጠገባችን እንዳለ ነው። ለዛም ነው ፀሎት የማይሰለቸን ፣ ለዛም ነው ሀጢያት የሚባለውን ነገር ለማሰብ እንኳን የምንፀየፈው ፣ ለዛም ነው ለምናስበው ፣ ለምንናገረው ፣ ለምናደርገው ለየትኛውም ነገር የምንጠነቀቀው። እግዚአብሔር እንደሚያየን ስለምናስብ።
✨ አብዛኞቻችን አሁን ላይ ቀድሞ የነበረንን እግዚአብሔርን መፍራት ከህይወታችን ላይ ስላጣን ምንም ስናደርግ ምንም አይመስለንም። ባንፀልይ ምንም አይመስለንም ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ባናነብ ምንም አይመስለንም ፣ ስለ ሀጢያት ስናስብ ምንም አይመስለንም።
✨ የእግዚአብሔርን መገኘት ከህይወታችን ማጣት የምንጀምረው ስንደክም አይደለም ፤ ስንደክም ስንደክም የሚሸሽ ፤ ስንበረታ ደግሞ የሚመጣ የእግዚአብሔር መገኘት የለም። የእግዚአብሔርን መገኘት ከህይወታችን ማጣት የምንጀምረው እግዚአብሔርን መፍራት ማቆም ስንጀምር ነው።
✨ አብዛኞቻችን የማንረዳው ነገር እግዚአብሔርን መፍራት ስናቆም እየወደቅን እንደሆነ አንረዳም።
.......... ይቀጥላል !
#Fear_Of_God
#Final_Week
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
FEAR OF GOD
እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤ ያድናቸዋልም።
መዝሙር 34:7 NASV
For the angel of the Lord is a guard; he surrounds and defends all who fear him.
Psalms 34:7 NLT
#Kabod_Verses
#Fear_Of_God
#Final_Week
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
ነገ🔥🔥🔥እሁድ🔥🔥🔥
💥 ያለፈው ሳምንት በነበረን በኮንፈረንስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የወጣቶች አገልግሎታችን ነገ ከ9:00 ጀምሮ ይቀጥላል።
📌 አዳዲስ ሰዎችን ጋብዘን እንምጣ!
#The_Year_Of_Cloud
#CJY
#Share_And_Invite
@CJYouth1
@CJYouth1
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
በነገው ኮንፍራንስ ምክንያት የነገው ፕሮግራም ስለታጠፈ ሁላችንም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ለኮንፍራንሱ እንገናኝ!
⚠️ አዳዲስ ሰዎችን ጋብዘን እንምጣ!
#Conference
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
FEAR OF GOD
“የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው።”
— ምሳሌ 9፥10
Fear of the Lord is the foundation of wisdom. Knowledge of the Holy One results in good judgment.
Proverbs 9:10 NLT
#Fear_Of_God
#Week_2
#Kabod_Verses
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
👉 እግዚአብሔርን መፍራት ምንድን ነው?🤔
✨ አንዳንድ ሰው እግዚአብሔርን መፍራት ብሎ የሚያስበው የሲኦልን ፍርሀት ነው።
✨ እንደዚ አይነት ሰው እየፈራ ያለው እግዚአብሔርን ሳይሆን ሲኦልን ነው። ከሲኦል ፍርሀት የተነሳ እግዚአብሔርን ያመልከዋል።
✨ አንዳንድ ሰው ደግሞ እየፈራ ያለው ወድቀትን ነው። ውድቀትን ስለሚፈራ ላለመውደቅ ብሎ እግዚአብሔርን ያመልከዋል።
✨ አንዳንድ ሰው ደግሞ እየፈራ ያለው አጋንንትን ነው። አጋንንትን ስለሚፈራ አጋንንት በህይወቱ ላይ እንዳይሰለጥን ሳይወድ በግዱ እግዚአብሔርን ያመልከዋል።
"እግዚአብሔርን በፍርሀት አገልግሉት፤ ለእርሱ መራድም ደስ ያሰኛችሁ።"
መዝሙር 2:11 NASV
💡ትክክለኛው እግዚአብሔርን መፍራት ልብን ከእግዚአብሔር የሚያርቅ ሳይሆን እግዚአብሔርን ወደነው ወይም በእግዚአብሔር ደስተኛ ሆነን እንድንፈራው የሚያደርግ ፍርሀት ነው።
ኢሳይያስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።
² የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
³ እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤
💡እግዚአብሔርን መፍራት ከራሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚገኝ ብቸኛው ነገር ነው።
💡ያለ እግዚአብሔር መንፈስ እግዚአብሔርን መፍራት አይቻልም።
#Fear_Of_God
#Week_1
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1
“እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም።”
— ምሳሌ 19፥23
Fear of the Lord leads to life, bringing security and protection from harm.
Proverbs 19:23 NLT
#Fear_Of_God
#Week_1
#Kabod_Verses
#Meditate_The_Word
#CJY
@CJYouth1
@CJYouth1