Good News !!
ለሁሉም የኤሌክትሪክ መኪና ባለንብረቶች ማለትም Volkswagen Id4, Id6 , Hybrid Toyota, Hyundai, KN እና ሌሎች የአሜሪካ እና የአውሮፓ መኪና ምርቶች ማለትም BMW,Chevrolet, Ford,Mercedes እና የትኛውም አይነት መኪና ተጠቃሚ የሆናችሁ ባለመኪናዎች የፍሬን ሸራ በማጣት መኪናችሁን መጠቀም ላልቻላችሁ በ48 ሰዓታት ውስጥ ሰርተን የምናስረክብ መሆኑን እንገልጻለን ::
For all Electrical Volkswagen Id4, Id6 , Hybrid Toyota, Hyundai, KN & other unlisted American & Europe like BMW,Chevrolet, Ford,Mercedes and other unlisted vehice users those you didn't get the brake materials please contact us.
We will offer high-quality Brake pads in 48 hours.
ASKEMA ENGINEERING.
.................🏎Daily Auto Contest🚗..............
..........Win cards.........
፩.Share for ur friends [Minimum 10 ]
፪.Share and make sure they joined [Minimum 5 ]
Send us the screenshoot
@DAcommentsbot
@dailyautomotive
Vehicle Lighting System Problems
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
#የቀጠለ..
የመኪናችን የመብራት ስርዓት(vehicle lighting system) ሊበላሽ የሚችልባቸው ምክንያቶች:
✔️ከደረጃ በታች የሆነ እንፖል መጠቀም(using bad bulb)
✔️ዝገት መፈጠር(corrosion)፦ የኤሌክትሪክ መስመሮች እርጥበት ካገኛቸው ሊዝጉ ይችላሉ። ይህም ዝገት ተገቢውን ሃይል እንዳያስተላልፉ ያግዳል።
✔️ገመዶች መላቀቅ(loosen wires)
✔️የግራውንድ ማነስ(Bad ground)
✔️የኤሌክትሪክ መስመር መቃጠል(electrical short or open)
✔️ሪሌይ እና ማብሪያ ማጥፊያ መስራት ማቆም(failed switch or relay)
ከላይ በጥቂቱም ቢሆን የተነሱትን ምክንያቶች በባለሙያ ማስፈተሽ ችግሩን በቀላሉ እንዲፈታ ያግዛል።
@dailyautomotive
BMW stands for Bayerische Motoren Werke GmbH, which roughly translates to the Bavarian Engine Works Company.
The name harks back to the company’s origin in the German state of Bavaria. It also indicates BMW's original product range: engines for various applications.
@dailyautomotive
Waxing our vehicle body #CarTips🚙
*************************
✔️የመኪናዎን ቦዲ ቢያንስ በአመት ሁለት ጊዜ በቅባት ማለስለስ ተገቢ ነው። ይህም ቀለምዎ ቶሎ እንዳይደበዝዝ ያግዛል...መኪናዎን ፀሃይ በመታው ቁጥር በUV ጨረር ምክንያት ቀለሙ እየደበዘዘ እየነጣ ይመጣል..ስለዚህ ዋክስ መጠቀሙ አስፈላጊ ነው።
✔️መኪናዎ አንፀባራቂ፣አዲስ እና ንጹህ እንዲሆን ከፈለጉ በየጊዘው አለስላሽ ቅባት የመኪናዎን ቦዲ መቀባት ተገቢ ነው። ይህ ቅባት መኪናዎን ከጭረት የመከላከል አቅምም አለው።
❕❕እንደየ አጠቃቀምዎ የመኪናዎ ቦዲ የቆይታ ጊዜ ይወሰናል። ስለዚህ ሳይዘነጉ የመኪናዎን ቦዲ ቢንከባከቡ ካላስፈላጊ ወጪ ይተርፋሉ።
@dailyautomotive
1600 እና 2000cc
የቀኑ የመጨረሻ ውድድር ሁለት ተወዳዳሪዎች ብቻ የነበሩበትን የ2000cc ፉክክር ከ7 ባለ1600cc ጉልበት መኪኖች ጋር በማቀላቀል ተደርጓል። ውድድሩ ሲጀምር በ1600cc የብዙዎችን ቀልብ ስባ የነበረው ባለ5 ቁጥሯ የኤሚሊዮ መኪና ፈጣን አነሳስ በማሳየት መምራትና ልዩነቷን ማስፋት ጀመረች። ነገር ግን የደጋፊዎችን ልብ የገዛች ሌላ መኪና ከበስተኋላዋ ድምጿን እያሰማች ነበር። የሮቤል 11 ቁጥር ቮልስዋገን ተወዳዳሪዎቿን አንድ በአንድ እያለፈች በፍጥነት ወደ3ተኝነት ተሸጋገረች። በተለይም የሮቤልን የአነዳድ ችሎታ በግልፅ ያሳዩ ሁለት በቀኝ መታጠፊያው የዙር ክፍል ያደረጋቸው አቀዳደሞች (Overtakes) ከደጋፊዎች አድናቆትን ያስገኙ ነበሩ። በዚህ ጊዜ ቮልሷ ከፊቷ በሁለተኛ ደረጃ ከተቀመጠው የአንቶኒዮ ሰባት ቁጥር ቶዮታ ላይ በፍጥነት ተጠግታ ነበር። የሁለቱ ተወዳዳሪዎች የመጨረሻ ሶስት ዙሮች ፉክክር የቀኑ ምርጥ ክስተት ከመሆንም አልፎ በስፍራው የነበሩ ታዳሚያንን እጅግ ያጓጓና ያስደሰተ ነበር። ሮቤል በመጨረሻዎቹ ዙሮች ቶዮታዋን ለማለፍ የተቻለውን ያህል ቢጥርም የአንቶኒዮ የመታጠፊያ ቦታዎቹን የመከላከልና የመንጃ መስመሩን የመጠበቅ አስገራሚ ችሎታ ከኤሚሊዮ በመከተል ሁለተኝነቱን ለማረጋገጥ በቂ ነበር። ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላም ደጋፊዎች በሮቤል እና ቮልስዋገኗ ትዕይንት ደስታቸውን ገልፀዋል። ከሁለቱ የ2000cc መኪኖች የሰሚር መወዳደሪያዋ ቶዮታ አሸናፊ ሆና ጨርሳለች።
ምርጥ ተወዳዳሪ:ሮቤል
ምንም እንኳ አንቶኒዮ ከቮልሷ ሲደርስበት የነበረውን ጫና ያለምንም ስህተት መመከት ቢችልም ሮቤል በአስደናቂ አስተላለፎች እንዲሁም ተስፋ ባለመቁረጥ እስከመጨረሻው በ100% ትኩረት ሁለተኝነትን ለማግኘት ያደረገው እጅግ አጓጊ ፉክክር ለደጋፊዎች የማይረሳ ነበር።
@dailyautomotive
1000cc
የቀኑ የመጀመሪያ ውድድር በ11 ሹፌሮች መሀል የተደረገው የባለ1000cc ጉልበት መኪኖች ዙር ነበር። ከሶስተኛ ስፍራ የተነሳው ሉካስ ከውድድሩ መጀመር አንስቶ በፍጥነት የመሪነቱን ቦታ በመያዝ ከሌሎቹ መኪኖች መራቁን ተያያዘው። ነገር ግን በቅርብ ርቀት ከዘጠነኛ ስፍራ ተነስቶ አስደናቂ የመንዳት ፍጥነቱን በቶዮታ መኪናው እያሳየን ወደ ሁለተኛ ደረጃ የመጣው ናሆም ሉካስን እየተከተለ ነበር። ነገር ግን ሉካስ በ23 ቁጥሯ ፊያት እንከን አልባ ዙሮችን በመንዳት የናሆምን ወደመሪነት የመጠጋት እድል አምክኖ የውድድሩ አሸናፊ ለመሆን በቅቷል። ሌሎቹ መኪኖች በዙሮቹ መሀል በነበሩ ግጭቶችና ብልሽቶች ምክንያት ከመጀመሪያዎቹ ሶስት መኪኖች ራቅ ብለው ውድድሩን ለመጨረስ ተገደዋል።
ምርጥ ተወዳዳሪ: ናሆም ደመረ
ከዘጠነኛ ስፍራ የጀመረው ናሆም ወደሁለተኛ ቦታ ለመምጣት ያደረገው ፉክክር እጅግ ማራኪና የተወዳዳሪውን የአነዳድ ችሎታ በሚገባ ያሳየ ነበር።
@dailyautomotive
Report on last week car race is ready
........................Stay tuned......................
The look of a winner, Anteneh (LALI) at the testing stage.
📸Adam Mengistu
@driveaddis
Tesla cybertrukሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ በቴስላ ካምፓኒ(Tesla lnc) እየተሰራ ያለ እጅግ የረቀቀ እንዲሁም መነጋገርያ የሆነ መኪና ነው። ካምፓኒው እስካሁን ቀለል ያሉ መኪኖች ናቸው ያላቸውን ሶስት ሞዴሎች ለዓለም ያስተዋቀ ሲሆን ሞዴሎቹ እውን የመሆናቸው ነገር ግን ሲያነጋግር ቆይቷል። ለዚህ እንደመነሻነት ምርቶቹ 2020 ይጀምራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች ካምፓኒው የመጀመርያው ምርት 2022 መገባደጃ ላይ እንደሚወጣ መረጃዎች ያመለክታሉ።።።
for more 👇👇👇
/channel/dailyautomotive
MEXICO // CITY CIRCUIT
The largest motorsport governing body of the land has organized a city circuit race at the heart of Addis Ababa. The fierce competition will be held this Sunday, March 7 2021 at Mexico Square.
Keep it locked on @DriveAddis
🏎Vehicle Lighting System🏎
**********************************
የመኪና መብራት💡 ስርዓት(vehicle lighting system) በውስጡ ለአሽከርካሪው እይታ የሚያግዙ መብራቶችን እንዲሁም አቅጣጫ መጠቆሚያዎችን ይይዛል። በመኪናዎ ፊት ፣ከውስጥ፣ ከውሃላ እና ከጎን በመገጠም ለአሽከርካሪው በቂ እይታን መፍጠር እንዲሁም ከተቃራኒ አሽከርካሪ ጋር ተግባብቶ ለማሽከርከር ጠቃሚ ነው።
የመኪና መብራት አይነቶች
▪️Head Light(ዋናው የፊት መብራት) ፦ይህ መብራት በሁለት ይከፈላል 🔺እረጅም እና 🔺አጭር..
እነዚህ መብራቶች አሽከርካሪው በጨለማ ውስጥ በቂ እይታ እንዲኖ ረው ይረዳሉ።
🔺አጭር መብራት፦ የምንጠቀመው ቅርብ እርቀቶችን ለመመልከት በተለይም ከተማ ውስጥ በብዛት እንጠቀመዋለን ይህም መብራት የተቃራኒ መኪና አሽከርካሪን እይታ አይረብሽም።
🔺እረጅም መብራት ፦ እረጅም እርቀት ለመመልከት ይጠቅማ። የምንጠቀመውም ከፊታችን መኪና በማይኖርበት ሰዓት ብቻ መሆን አለበት።
▪️Tail light(የውሃላ መብራት) ፦ የፊት መብራታችንን ስናበራ ከውሃላ የሚበራ ቀይ መብራት ነው። ይህም ከውሃላ ለሚመጣ ተሽከርካሪ እንደምልክት(ከፊቱ መኪና እንዳለ እንዲያውቅ) ያገለግላል። የፊት መብራት እስካልጠፋ ድረት እንደበራ ይቆያል።
▪️Day time running light(የቀን መብራት) ፦ ይህ መብራት የመኪናችንን ቁልፍ ስንከፍት(on position) አብሮ የሚበራ መብራት ነው።
▪️Fog light(የጉም መብራት) ፦ ከዋናው የፊት መብራት ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን መንገዳችን በጊም በሚሸፈንበት ጊዜ የምንጠቀመው መብራት ነው።
▪️Signal Lights( አቅጣጫ መጠቆሚያ መብራት) ፦ ከመኪናችን ፊት እና ውሃል ይገኛሉ..አቅጣጫ መቀየር ስንፈልግ ከፊት ወይም ከውሃላ ላለው አሽከርካሪ ምልክት የምንሰትበት ጠቃሚ እና ወሳኝ መብራት ነው።
▪️Braking Light(የፍሬን መብራት)፦ ከመኪናችን ውሃላ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፍሬን ስንረግጥ መኪናው ፍጥነት እየቀነሰ መሆኑን ከጀርባው ላለው አሽከርካሪ የሚያሳይበት ቀይ መብራት ነው።
▪️Hazard Light( የአደጋ ጊዜ መብራት)፦ ከፊትም ከውሃላም የሚገኙ ሲሆኑ አደጋ ሲያጋትመን ወይም ከፊት አደጋ እንዳለ ለማሳወቅ ስንፈልግ እንጠቀመዋለን። ቶልቶሎ ብርት ጥፍት በማለት አደጋ መኖሩን ያመለክታል።
@dailyautomotive
Different Forms of Car Wax
#ከላይ_የቀጠለ
*************************
በአይነት እና በይዘት የተለያዩ የቦዲ ቅባቶች(Wax) ይገኛሉ
✔️Paste Wax ፦ ይህ ዋክስ የመጀመሪያው ዋክስ አይነት ሲሆን የሚዘጋጀውም ከተፈጥሮ ቅመማት ነው። ይህም መኪናዎ አንጸባራቂ በማድረግ የቀለምዎን እድሜ ያራዝማል። በዋጋውም ከሌሎቹ አይነቶች ውድ ነው።
✔️Liquid Wax ፦ ይህ ከ paste wax በአይነቱ ለስለስ ያለ ሲሆን በቆይታ ጊዛው ይተሻለ ነው። ቶሎ የመድረቅ ባህሪው ላጠቃቀም ቢያስቸግርም ብዙዎች የሚጠቀሙት የዋክስ አይነት ነው።
✔️Spray Wax ፦ ለፈጣን አጠቃቀም የሚመረጥ የዋክስ አይነት ሲሆን በጥሩ ሁኔታ ላለቁ የመኪና ቦዲዎች ላይ እንደተጨማሪ ማሳመሪያ ይጠቅማል
❗በባለሙያ ምክር ገስቶ መጠቀም ተገቢ ነው
@dailyautomotive
1300cc
ቀጥሎ የተደረገው ውድድር በስድስት ባለ1300 cc ጉልበት መኪኖች መሀል የነበረው ፉክክር ነበር። በበርካታ ደጋፊዎቹ ታጅቦ ውድድሩን ከመጀመሪያ ስፍራ የጀመረውና በቅፅል ስሙ ላሊ የሚሰኘው አንተነህ በፊያት መኪናው በመታገዝ ከሌሎቹ ተወዳዳሪዎች መራቅ የጀመረው ገና በመጀመሪያዎቹ ዙሮች ነበር። ከተከታዮቹ የነበረውን የሰአት ልዩነት ሲያሰፋም ያን ያህል የተጋነነ የአነዳድ risk ሳይወስድ ነው። ከሱ በተቃራኒው በወቅቱ ተከታዩ የነበረው እውቀት ወደ አንተነህ ለመድረስ ባደረገው ጥረት መሀል ያለመጠን ዘግይቶ ፍሬን ለመያዝ መሞከሩ በአንደኛው የቀኝ ዙር መታጠፊያ ላይ መኪናዋን ከመንገዱ ተቃራኒ እንድትዞር ከማድረጉም በላይ ወደ5ተኛ ቦታ እንዲወርድ አስገድዶታል። የውድድሩ መሪ ዙሮቹ በቀጠሉ ቁጥር የሚደርባቸው መኪኖች ሲጨምሩ ውድድሩንም ያለማንም ተቀናቃኝ አሳማኝ በሆነ ችሎታ ለማሸነፍ ችሏል። በ15 ቁጥሯ ቶዮታ የተወዳደረው ግሩም 2ተኛ ሆኖ ሲጨርስ እውቀትም በኦፔል መኪናው እንደገና በማንሰራራት ከነበረበት 5ተኛ በመጨረሻ ላይ 3ተኝነትን አሳክቷል። ባለድሉ ላሊም ውጤቱን ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን አክብሯል።
ምርጥ ተወዳዳሪ: አንተነህ በላቸው
ከዙሩ መነሻ እስከማብቂያው ያለምንም እንከን በመንዳት እንዲሁም ከግሩምና እውቀት መኪኖች ውጪ ሌሎችን በመደረብ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ከፍ ያለ ብቃቱን አስመስክሯል።
@dailyautomotive
Race Report
ለዚህ አመት የመጀመሪያ የሆነው የሞተር ስፖርት ውድድር ያለፈው እሁድ በደማቅ ሁኔታ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ተካሂዷል። ውድድሩ በአዲስ አበባ የሞተር ስፖርት አሶሴሽን አዘጋጅነት እንዲሁም በድራይቭ አዲስ፣ ሊንክአፕ አዲስ እና ሌሎች ተባባሪ አካላት ድጋፍ እውን ሊሆን በቅቷል። ከአምናው የኮቪድ ወረርሽኝ መነሳትና የህዝብ መሰባሰቢያ ዝግጅቶች መከልከል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ እንደመሆኑ በርካታ የስፖርቱ ተከታታዮች በጉጉት ጠብቀውትም ነበር።
የእሁዱ ዝግጅት እንደየፈረስ ጉልበት መጠናቸው በተደለደሉ አራት የመኪና ካቴጎሪዎች ማለትም 1000cc፣ 1300cc፣ 1600cc እና 2000cc መሀከል ውድድሮችን አሳይቶናል። ቅዳሜ ከሰአት የተወሰኑት ተወዳዳሪ መኪኖች ለቅድመፍተሻ የተገኙ የነበረ ሲሆን የቀሩት ደግሞ እሁድ ጠዋት ላይ ዝግጅታቸውን ጨርሰው ለመወዳደሪያነት በተመረጠው የብሄራዊ-ዋቢ ሸበሌ-ሜክሲኮ ላይ ተገኝተዋል። ውድድሩ ከተባለው ሰአት ዘግየት ብሎ ጠዋት አራት ሰአት ሲጀመር እኔም በስፍራው ሆኜ ካየሁት የውድድሩን ሂደት እና የእኔን ምርጥ ተወዳዳሪዎች ከዚህ ቀጥሎ አቀርባለሁ።
@dailyautomotive
Super-human Pitstops of Formula One
#ክፍል፩
በርካቶች የፎርሙላ ዋን ውድድርን ሲመለከቱ አይንን ከሚስቡ ሁነቶች ውስጥ አንደኛው ተወዳዳሪዎች አዲስ ጎማ የሚቀይሩበትመንገድ (Pitstop) ዋነኛው ነው። በተለይም ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ክስተት ባስተዋልነው ጊዜ የሚፈጥረው ግርምትና መደነቅ ውድድሩን የበለጠ ለመውደድ ትልቅ በር ይከፍታል።
በዛሬው እለት የምናቀርበውም ስለዚሁ አስገራሚና እጅግ ለማመን የሚከብድ የሰዎችን ክህሎት ወደሌላ ደረጃ ያሻገረ ስራ ይሆናል።
መነሻ
በበርካታ የሞተር ስፖርት ውድድሮች የተወዳዳሪ መኪኖችን አካላት፣ ጎማ እንዲሁም በአንዳንድ ውድድሮች ተወዳዳሪ ሹፌሮችንም ጭምር በውድድሩ መሀል መቀየር የተለመደ ነው። F1ም ከተጀመረበት 1950 እኤአ ጀምሮ ይሄ ልማድ የውድድሩ አካል ነው።
መወዳደሪያ ትራኮችም ለተወዳዳሪ ቡድኖች መካኒኮችና ለመኪኖቻቸው ማቆሚያ ጋራዥና መተላለፊያ መንገድ ያዘጋጃሉ። ይሄ መተላለፊያ (Pitlane) ከ Pitstop በተጨማሪ ተወዳዳሪዎች የሰአት ቅጣት በሚሰጣቸው ጊዜ ለማቆም ይጠቀሙበታል።
እንዴት ይሄንን መተላለፊያ ቡድኖችና ሹፌሮች በአግባቡ እንደሚጠቀሙበት በርካታ ህግጋት ከመውጣታቸው በፊት ሹፌሮችበከፍተኛ ፍጥነት መጓዝና አደገኛ በሆነ መንገድ ለመሽቀዳደም ይጠቀሙበት ነበር።
ተወዳዳሪ መኪኖችም በርካታ ደቂቃዎችን ሰርቪስ እየተደረጉ ይቆዩ ነበር። የሚፈጀው ሰአት በጊዜ ሂደት እየቀነሰ ቢመጣም F1 ከሌሎች ተመሳሳይ ውድድሮች ብዙም የተለየ የPitstop አሰራር አልነበረውም።
በ1994 እኤአ ተግባራዊ መሆን የጀመረ አዲስ ህግ ግን የድሮውን አካሄድ ላይመለስ ቀየረው።
ይቀጥላል......
@dailyautomotive