"ኢትዮጵያ ዳግም የህሊና እስረኞች ቤት እንድትሆን መፍቀድ የለብንም" - ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) 'ኢትዮጵያ ዳግም የህሊና እስረኞች ቤት እንድትሆን መፍቀድ የለብንም' በሚል የታሰሩ አመራሮቹ እንዲፈቱ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በዛሬው ዕለት እንደሚያካሂድ አሳውቋል።
ፓርቲው በፌስቡክ እና በትዊተር ዓለም አቀፍ ዘመቻው አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው አመራሮች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ለማድረግ ዘመቻ እንደሚያካሂድ ገልጿል።
በሌላ በኩል ለመጋቢት 28/2013 ዓ.ም ተቀጥረው የነበሩት እነ አቶ እስክንድር ቀጥሮ ተሻሽሎ በመጭው ጥር 5 ቀን 2013 ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
share
join @dailyfeta