danahiking1 | Unsorted

Telegram-канал danahiking1 - Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

717

Subscribe to a channel

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

Day trip to Wenchi Crater Lake!
ሽርሽር ወደ ወንጪ ሀይቅ!

📅 ህዳር 08 - Nov 17
💸 ሂሳብ 2900 ብር - Cost 2900 Birr
⏰ Meeting Time - 12:00  LT
📍 Meeting Place - Mexico In front of Wabi Shebela Hotel

The package Includes; Transportation, Lunch, snack,  water, entrance, and Local Guide.

For reservation call at
☎️ 0932230111 & 0900090002

Or DM us @Yalitamaa or @khelludi

/channel/danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

Day trip to Wenchi Crater Lake!
ሽርሽር ወደ ወንጪ ሀይቅ!

📅 ታህሳስ 21 - Dec 31
💸 ሂሳብ 2200 ብር - Cost 2200 Birr
⏰ Meeting Time - 12:00  LT
📍 Meeting Place - Mexico In front of Wabi Shebela Hotel

The package Includes; Transportation, Lunch, snack,  water, entrance, and Local Guide.

For reservation call at
☎️ 0985410593  & 0960008400

Or DM us @Yalitamaa or @khelludi

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ባሳለፍነው እሁድ በ ወንጪ ያደረግነው ቆይታ መልካም ነበር። ውብ የሆነውን የወንጪ ምድር ጎብኝተናል ፏፏቴውን፣mud bath፣ሀይቁን መመልከት ችለናል። ጉዞውን በስኬት ላጠናቀቁ ቤተሰቦቻችን በሌላ አስደሳች ጉዞ በቀጣይ ሳምንት እንገናኛለን።

አብራችሁን ለነበራችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን። በቀጣይ ሳምንት የሚኖረንን ጉዞ ዝርዝር መረጃ በቀጣይ ቀናት እንለቃልን።

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

Come and Visit Wenchi with @danahiking

Hiking Date Sunday, January 29, 2023
⏰ Meeting Time - 12:00  LT
 📍 Meeting Place - Mexico In front of Wabi Shebela Hotel

💵 Price; 1550 Brr

For reservation call at
☎️ 0927710221 & 0985410593 

Or DM us @Xotillweoverdosee or @khelludi

ወንጪ ሀይቅን ከ @danahiking ጋር ይጎብኙ!

ከወዳጅ ጓደኞቻችሁ ጋር ዘና ይበሉ!

የጉዞ ቀን እሁድ ጥር 21
የጉዞ ሂሳብ 1550

ለመመዝገብ በ 0921710221 ወይም 0985410593 ይደውሉ!

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

እየመጣን ነው!
ለአስደናቂ ጉዞዎች ዝግጁ ናችሁ?

ውድ የ ዳና ሀይኪንግ ቤተሰቦች ዳና ሀይኪንግ እንደተለመደው አስደሳች እና አስገራሚ ጉዞዎችን ይዞ እየመጣ ነው።

እንደተለመደው ሁሉ ከእናንተው ጋር አዳዲስ የጉዞ መዳረሻዎችን እንፈልጋለን። ጋራ እና ዱሩን እናስሳለን። ከራስ ዳሽን እስከ ደናኪል እንከትማለን።

ተዘጋጁ!

@danahiking

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

የደርሶ መልስ ሽርሽር ወደ ቡልጋ!

እሁድ ህዳር 18
የጉዞ ሂሳብ 1000 ብር

ለመመዝገብ በ ቴሌግራም @Xotillweoverdosee እና @khelludi ላይ ያዋሩን ካልሆነም በ 0927710221 ይደውሉ።

Hiking to Bulga
Sunday, Nov 27
Hiking cost - 1000 Birr

For registration Dm us @Xotillweoverdosee or @khelludi

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

Something is cooking. 😁😁

Ready to join the adventures?

@danahiking

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ውድ የ @danahiking ቤተሰቦች የቀጣይ ጉዟችን መዳረሻ ነሀሴ 15 ወደ ፖርቹጊዝ ድልድልይ ይሆባክ። በጉዟችን ውቡ የሆነውን ፏፏቴ እና ውብ መልክአ ምድር የምንመለከት ይሆናል። ታላቁን የጀማ ወንዝ፣ ብርቅዬዎቹን ጭላዳ ዝንጀሮዎች እና ሌሎችም አስደሳች ነገሮችን እንመለከታለን። አብሮን ለመጓዝ ዝግጁ የሆነው ማነው?
የጉዞ ሂሳብ 800 ብር
ለመመዝገብ በ @Xotillweoverdosee ወይም @Jooooooooj ላይ አለሁ ይበሉን!
ካልሆነም በ 0911282876 ወይም በ 0927710221 ይደውሉልን!

Dear Dana Hiking Families, We are back with a new hiking destination to Derba waterfall. The hiking is scheduled for Aug 21.
Hiking cost is 800 Birr
For registaration DM us @Xotillweoverdosee or call 0927710221

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ውድ የ @danahiking ቤተሰቦች ዳና ሀይኪንግ ሐምሌ 24 ወደ ውቡ ሰሜን ሸዋ እንሳሮ ጉዞ ለማድረግ ተዘጋጅቷል።

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ወደተጓዝንበት እና ቦታውን ለሀይኪንግ ምቹ እንዲሆን ከመፈለግ እና ከማግኘት ጀምሮ ውብ መልክአ ምድሩ እንዲታወቅ ያቅማችንን ወዳበረከትንበት የእንሳሮ ምድር እና ፏፏቴዎች በቀጣይ ሳምንት እሁድ እንጓዛለን። በጉዟችን ፏፏቴዎች፣ ውብ መልክአ ምድር፣ ዋሻ እና ሌሎች አስደሳች መስህቦችን እንመለከታለን።

አብረውን ይጓዙ! የጉዞ ሂሳቡ 800 ብር ሲሆን ሙሉ ወጪን የሸፈነ ነው።

ለመመዝገብ በ @Xotillweoverdosee ወይም @Jooooooooj ላይ አለሁ ይበሉን!
ካልሆነም በ 0911282876 ወይም በ 0927710221 ይደውሉልን!

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ለ መላው የዳና ሀይኪንግ ቤተሰቦች እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ዳና ሀይኪንግ መልካም የ ዒድ አል-ፊጥር በአል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ እንስላስ ችኩል ተራራ!

የጉዞ ቀን እሁድ መጋቢት 18!

የጉዞ ወጪው 850 ብር !

📍 መገናኛ ቦታ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል

⏰ መነሻ ሰአት : 12 ሰአት ጠዋት

ለመመዝገብ በ ቴሌግራም @Xotillweoverdosee ወይም @Jooooooooj ላይ አለሁ ይበሉን።
ካልሆነም በ 0927710221 ወይም በ 0911282876 ይደውሉ።

Come let's Explore Mount Enselas!

Hiking date March 27

Hiking cost 850 Birr

For registration DM us @Xotillweoverdosee or @Jooooooooj
Recommended for intermediate hikers!
°°°
@danahiking @danahiking1 @danahikingphotos

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ እንስላስ ችኩል ተራራ!

እንስላስ ችኩል በስልጤ ዞን የሚገኝ እጅግ ውብ መልክኣ ምድር ያለው አካባቢ ነው። አካባቢው ዘውትር ለም እና አረንጓዴ ከመሆኑ ባሻገር የአካባቢው ማህበረሰብ ነፍስን በሀሴት የሚይዝ ውብ መስተንግዶ አለው። ዳና ሀይኪንግ ወደዚህ ውብ አካባቢ የደርሶ መልስ ጉዞ አዘጋጅቷል። አብረውን ተጉዘው መንፈስዎን ያድሱ።

የጉዞ ቀን እሁድ መጋቢት 18!

የጉዞ ወጪው 850 ብር !

ለመመዝገብ በ ቴሌግራም @Xotillweoverdosee ወይም @Jooooooooj ላይ አለሁ ይበሉን።
ካልሆነም በ 0927710221 ወይም በ 0911282876 ይደውሉ።

Come let's Explore Mount Enselas!

#danahiking is back with a day hike to the beautiful Mount Enselas. This gorgeous place is located in Site Zone. Besides the stunning landscape and evergreen surrounding the warm greeting of the community is incredible.

Hiking date March 27

Hiking cost 850 Birr

For registration DM us @Xotillweoverdosee or @Jooooooooj

Especially recommended for intermediate hikers!

°°°
@danahiking @danahiking1 @danahikingphotos

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ኑ የሚኒልክ መስኮትን በጋራ እንጎብኝ!

ዳና ሀይኪንግ(@danahiking) የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ ውቡ መልክኣ ምድር የሚኒልክ መስኮት(ገማሳ ገደል) አዘጋጅቷል። በዚህ ሀይኪንግ ላይ ውብ መልክኣ ምድርን ከመመልከት ባሻገር ብርቅዬውን ጭላዳ ዝንጀሮ እንመለከታለን።

የጉዞ ቀን እሁድ መጋቢት 4!

የጉዞ ወጪው 850 ብር

ለመመዝገብ በ ቴሌግራም @Xotillweoverdosee ወይም @Jooooooooj ላይ አለሁ ይበሉን።
ካልሆነም በ 0927710221 ወይም በ 0911282876 ይደውሉ።

Come let's visit Minilks window!

#danahiking is back with a day hike to the beautiful Miniliks windows(Genasa gorge) Besides the stunning gorge, we will have the chance to see the endemic Chilada Baboons.

Hiking date March 13

Hiking cost 850 Birr

For registration DM us @Xotillweoverdosee or @Jooooooooj

Specially recommended for beginners!

°°°
@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ቀጣይ ሳምንት ስለምንሄድበት የሚኒልክ መስኮት ምን ያህል ያውቃሉ?

የሚኒሊክ መስኮት ከደብረብርሀን 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ውብ መልክኣ ምድር ነው። ይህ ውብ አካባቢ ገማሳ ገደል በመባልም ይጠራል። አካባቢው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚገኝ በመሆኑ አመቱን ሙሉ ልምላሜ የማይለየው በአረንጓዴ ሸማ የተሽፈነ ጌጥ ነው።

በጉም ከተሸመነ ውብ ተራራው እና የሚያማምሩ ሳሮች አሻግረው ሲመለከቱ ይፋት ቆላማ መንደሮች፣ ኢትዮጵያን ለሁለት ከፍሎ የሚያልፈው ትልቁ ስምጥ ሸለቆ ፣ የአፋር ክልል በርሃማ ቦታዎችና የአዋሽ ወንዝ በሰልፍ ተኝተው በአግራሞት ለመመልከት ያስችልዎታል።

ይህ ውብ ቦታ ስያሜውን ያገኘው አፄ ሚኒልክ ወደ አያታቸው ንጉስ ሣህለ ስላሴ የትውልድ መንደር ሳላድንጋይ ሲጓዙ በግርምት በተደጋጋሚ ተቀምጠው በውብ ስፍራው አሻግረው ስለሚመለከቱ ነው። ቦታው የወፍ ዋሻን ደን ከፊል ገጽታ ከስሩ የያዘ ሁልጊዜ ለምለም የማይለየው በመሆኑ በርካታ ዝንጀሮዎች፣ ሺኮኮዎችና ገደሉን እንደመጠለያ አድርገው የሚኖሩ በርካታ የአእዋፍ ዝርያዎች የሚገኙበት መሆኑ ደግሞ የቱሪስት መስህብነቱን ይበልጥ ማራኪና አስደናቂ ያደርገዋል፡፡

እርሶውም ይህንን ውብ ቦታ ከዳና ሀይኪንግ ጋር በመሆን እሁድ መጋቢት 4 ይጎብኙት።

የጉዞ ወጪው 850 ብር ሲሆን ሙሉ ወጪዎን ያካተተ መሆንን ልንገልፅልዎት እንወዳለን!

ለመመዝገብ በ 0927710221 ወይም በ 0911282876 ይደውሉ።
°°°
Dana Hiking
@danahiking @danahiking1 @danahikingphotos
°°°

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ውድ የዳና ሀይኪንግ ቤተሰቦች ለነገ ጉዟችን እንደተዘጋጃሁ ተስፋ እናደርጋለን። ለጉዞ ሲመጡ እነዚህን ነጥቦች ልብ ይበሉ ፦

1. መታወቅያ መያዝዎን አይዘንጉ። መታወቅያ ያልያዘ ሰው በጉዞው ላይ የማናስተናግድ ሲሆን መታወቅያ ሳይዙ መተው ለሚፈጠረው መጉላላት ሀላፊነት አንወስድም።

2. ከቤትዎ ሲወጡ ምቾት የማይነሳዎትን ቀለለ ያለ ምግብ ይመገቡ።

3. የጉዞ ሰአታችን 12 ከ 15 ሲሆን ሊፈጠሩ ለሚችሉ አንዳንድ ችግሮች ተጨማሪ 15 ደቂቃ ይዘናል። 12 ከ 30 ሲሆን ጉዟችንን ሜክሲኮ ከ ሸበሌ ሆቴል እንጀምራለን። ከዚህ ሰአት ኋላ ለሚመጡ ቤተሰቦቻችን ሀላፊነት ስለማንወስድ ሰአትዎን ያክብሩ።

4. ለጉዞዎ አመቺ የሆኑ ልብስ ያድርጉ፤ ለእንቅስቃሴ አመቺ የሆነ መጫምያ ማድረግዎንም ልብ ይበሉ።

5. በጉዞዎ ላይ ለትውስታ ፎቶ ያንሱና ያጋሩን!

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በ

0911282876 - ጆ
0927710221 - ቢኪ
ጋር ይደውሉ።

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ዳና ሀይኪንግ እጅግ አስደሳች ቆይታ በወንጪ ሀይኪንግ አድርጎ ተመልሷል። ጉዟችን እጅግ አስደሳች እና አዝናኝ ነበር። በ ጉዟችን ላይ ያጋጠመን ክስተት ደግሞ የበለጠ ጉዟችንን አይረሴ አድርጎታል።

አብራችሁን የነበራችሁን ቤተሰቦች ለነበረን ቆይታ ከልብ እናመሰግናለን! በቀጣይ ጉዞዎች እንገናኛለን።

የ ኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ላደረገልን ትብብር ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

የ ቤተሰብ እንዲሁም የ ግል ጉዞ ከፈለጉም በ ቴሌግራም በ @Khelludi ወይም @Yalitamaa ላይ ያናግሩን! 0960008400 ወይም 0985410593 ይደውሉልን።

Dana Hiking had a breathtaking adventure at the stunning Creator Lake, Wenchi. Our experience was beyond perfect, and the unexpected events that unfolded along the way made the hike all the more captivating.

To all those who joined us on this memorable journey, we extend our heartfelt gratitude. We can't wait to embark on our next hiking adventure together!

We are grateful for OTC and their support.

If you're looking for a unique family or private tour, simply DM us @Khelludi or @Yalitamaa. Get ready for an unforgettable experience!
/channel/danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ባሳለፍነው ማክሰኞ እጅግ አስደሳች የሆነ የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ ወንጪ አድርገን ነበር። በዚህ ጉዞ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ እንግዶች ነበሩን። ከ ቺሊ፣ ቱርክ፣ ቱኒዚያ፣ አልጄሪያ፣ ጋና እና ኬንያ የመጡ የጉዞው ተሳታፊዎች በነበራቸው ቆይታ እጅግ ደስተኛ ነበሩ።

ውድ የዳና ሀይኪንግ ቤተሰቦቻችን ወንጪ ሀይቅ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እጅግ ዘምኖ ተሰርቷል። እኛም ዳግም ወደዚህ ተወዳጅ መዳረሻ ይዘናችሁ ልንሄድ ጓጉተናል። ዝግጁ ናችሁ?

We had an incredible hiking trip to Wenchi Crater Lake last Tuesday. Our visitors were from Chile, Turkey, Tunisia, Algeria, Ghana, and Kenya. They were absolutely amazed by the beautiful lake.

Dear Dana Hiking Families, Wenchi looks absolutely stunning after its renovation by the Gebeta Lehager project. We are already planning our next trip to this amazing destination. Are you ready?

/channel/danahiking1
@danahiking

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

የ ወንጪ ጉዟችን አራት ቀናት ይቀሩታል!

ጥቂት ቦታዎች ይቀሩናል። ከጓደኞችዎ ጋር ይመዝገቡና ይዝናኑ!

📅 የጉዞ ቀን እሁድ ጥር 21
💰 የጉዞ ሂሳብ 1550

ለመመዝገብ በ @Xotillweoverdosee ወይም  @khelludi ላይ ያዋሩን። መደወል ቢሹ በ 0921710221 ወይም 0985410593 ይደውሉ!

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

DAY TRIP TO Wenchi Crater Lake!

Hiking Date Sunday, January 29, 2023
⏰ Meeting Time - 12:00  LT
 📍 Meeting Place - Mexico In front of Wabi Shebela Hotel

💵 Price; 1550 Brr
 
The package Includes; Transportation, Lunch, snack,  water, entrance, and Local Guide (Boat travel and horse riding are not included in the package.)

For reservation call at
☎️ 0927710221 & 0985410593 

Or DM us @Xotillweoverdosee or @khelludi

የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ ወንጪ ሀይቅ

የጉዞ ቀን እሁድ ጥር 21
የጉዞ ሂሳብ 1550

ለመመዝገብ በ 0921710221 ወይም 0985410593 ይደውሉ!

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ታላቁ አባት አርበኛ ጋሽ በቀለ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

ዳና ሀይኪንግ ወደ ቡልጋ ኢላኒ ጋዝማት የለኝ ገደል ጉዞውን ሲያደርግ ከአካባቢው መልክአ-ምድር ባሻገር ከ ፊታውራሪ ቁንጬ ስር ሆነው ከታላቁ አርበኛ ራስ አበበ አረጋዊ ጎን ለሀገራችን ሰላም እና ነፃነት የታገሉትን ጋሽ በቀለ በመጠየቅ እንዲሁም የአባት አርበኛ መስዋዕትነታቸውን ባይመጥንም ለክብራቸው ምስጋና በተደጋጋሚ አቅርቧል።

እኒህ አባት ከ 114+ አመት በላይ በህይወት የኖሩ ጀግና ሲሆኑ የሰገሌ ጦርነት በተደረገ በሁለተኛው አመት እንደተወለዱም ይናገራሉ። እኒህ ታላቅ አባት አርበኛ ቡልጋን እንድንናፍቅ ያደረጉን ታላቅ ሰው ነበሩ።

ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለዳና ሀይኪንግ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።

እሁድ ወደ ቡልጋ ልናደርገው የነበረውን ጉዞም በዚህ የተነሳ ለመሰረዝ መገደዳችንን እንገልፃለን።

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ውድ የዳና ሀይኪንግ ቤተሰቦች ዳና ሀይኪንግ ባለፉት አመታት በሀይኪንግ ዘርፍ ውጤታማ ክንውኖችን ሲያደርግ ቆይቷል።

1. ዛሬ ላይ የተለመዱ ከ ስድስት በላይ አዳዲስ የሀይኪንግ መዳረሻዎችን ዳና ሀይኪንግ ፈልጎ አግኝቷል፤ በተገቢው መልኩ እንዲታወቁ አድርጓል።

2. ባልተለመደ መልኩ በአዲስ መዳረሻ ላይ የ ሳይክል ሀይኪንግ አዘጋጅቷል።

3. የ መጀመርያውን የባክ ፓክ ትሪፕ አዘጋጅቷል።

4. በምንጓዝባቸው ቦታዎች የማህበረሰብ ግንባታ ላይ ትላልቅ ስራዎችን ሰርቷል። የቤተ መፅሐፍት ማሟላት፣ የተማሪዎች የትምህርት መሳርያ ማመቻቸት፣ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ሟሟላት እና የመሳሰሉት።

5. ከ 5 ሺህ በላይ ተጓዦች በተለያዩ የሀይኪንግ መዳረሻዎች ይዘን ተጉዘናል።

6.  ከ 10 የሚበልጡ አዳዲስ የሀይኪንግ ቡድኖች ምስረታ ላይ ከሙያዊ እስከ ሞራል ድጋፍ አድርገናል። ከዚህ በዘለለም ከአዲስ አበባ ውጪ በ ሀዋሳ እና በ አዳማ የሀይኪንግ ዘርፉ እንዲንቀሳቀስ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ አድርጓል።

7. በየአመቱ መዝግያ ማህበረሰብ ተኮር ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ለካንሰር ህሙማን ህፃናት እንዲሁም ለአረጋውያን ወንድማዊ ድጋፍ አድርጓል።

ሌላም! ሌላም!

በሀገራችን በነበረው አለመረጋጋት እና ተደራራቢ ምክንያቶች ዘለግ ላለ ግዜያት ጉዞ ማዘጋጀት አቁመን የነበረ ቢሆንም አሁን ዳግመኛ ኢትዮጵያን ለማሰስ እየመጣን ነው።

አብራችሁን ለቆያችሁ ቤተሰቦቻችን ሁሉ እናመሰግናለን።

ለሀሳብ አስተያየታችሁ በ @khelludi ላይ ያዋሩን!

#እየመጣንነው!

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ለመላው የ @danahiking ቤተሰቦች ዳና ሀይኪንግ አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።

ቀጣዩን አመት በአዲስ የጉዞ ፕሮግራሞች እና መዳረሻዎች እንገናኛለን።

በድጋሜ መልካም አዲስ አመት!

@danahiking

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ባሳለፍነው እሁድ በ እንሳሮ ያደረግነው ቆይታ መልካም ነበር። ውብ የሆነውን የእንሳሮ ምድር ጎብኝተናል ፏፏቴዎቹን እና የአባሪኮ ዋሻ መመልከት ችለናል። በጉዟችን ያጋጠመን ጭቃ ጉዟችንን አስደሳች ካደረጉ ነገሮች መሀከል አንደኛው ነው! ይኽን ሁሉ አልፈው ጉዞውን በስኬት ላጠናቀቁ ቤተሰቦቻችን በሌላ አስደሳች ጉዞ በቀጣይ ሳምንት እንገናኛለን።

አብራችሁን ለነበራችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን። በቀጣይ ሳምንት የሚኖረንን ጉዞ ዝርዝር መረጃ በቀጣይ ቀናት እንለቃልን።

የእንሳሮ ጉዞ ፎቶዎቻችንን በ @danahikingphotos ላይ እናጋራችኋለን።

@danahiking @fanahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ሽርሽር ከ ዳና ጋር!

ውድ የ @danahiking ቤተሰቦች ዳና ሀይኪንግ በአዲስ ሽርሽር እና በአዳዲስ መዳረሻዎች ተመልሷል።

የክረምቱን ወቅት በተለያዩ ጉዞዎች እናደምቀዋለን! ከሚገማሸር ወንዝ ስር የሚፈሱ ፏፏቴቼውን እየጎበኘን ለነፍሳችን ሀሴት እንሸምታለን። እንደ አምናው ሁሉ ለአዲሱ አመት ለተማሪዎች የመማርያ ቁሳቁስ እንለግሳለን፤ ቤተ መፅሐፍት እናደራጃለን።

Dear Dana Hiking families, we are back with new destinations and hiking plans.

Just like we did last year, We will donate educational materials for students located in our hiking destination places and we will build libraries.

Keep updated. We will post the details soon.

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ለ መላው የዳና ሀይኪንግ ቤተሰቦች እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ዳና ሀይኪንግ መልካም የ ፋሲካ በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ እንስላስ ችኩል ተራራ!

የጉዞ ቀን እሁድ መጋቢት 18!

የጉዞ ወጪው 850 ብር !

📍 መገናኛ ቦታ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል

⏰ መነሻ ሰአት : 12 ሰአት ጠዋት

ለመመዝገብ በ ቴሌግራም @Xotillweoverdosee ወይም @Jooooooooj ላይ አለሁ ይበሉን።
ካልሆነም በ 0927710221 ወይም በ 0911282876 ይደውሉ።

Come let's Explore Mount Enselas!

Hiking date March 27

Hiking cost 850 Birr


For registration DM us @Xotillweoverdosee or @Jooooooooj

Recommended for intermediate hikers!

°°°
@danahiking @danahiking1 @danahikingphotos

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ዳና ሀይኪንግ አፍሪካውያን ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የዳበሩ እና በትላልቅ ድርጅቶች ተወዳዳሪ ሰራተኛ እንዲሆኑ ማብቃት ላይ ትኩረቱን ካደረገውድ A2SV ጋር ባሳለፍነው ቅዳሜ ወደ ወንጪ ተጉዞ አሪፍ ግዜን አሳልፏል።

አብረውን ለነበሩት ሁሉ እናመሰግናለን!

A2SV in collaboration with Dana hiking had an amazing day hiking at wenchi crater lake on March 13/2022.

We would like to thank all A2SV members.

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

Follow us on Twitter ~ በትዊተር ይወዳጁን!

https://twitter.com/DanaHiking/status/1500839540843589644?t=5XzjeCrD1qxfNduzZl3SvQ&s=19

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

#DanaHiking is back with a day hike to the Miniliks window, a historical place with a mesmerizing landscape. Located in Amhara Region, Debre Sina, Ethiopia.
For Registration Call - 0927710221 or 0911282876 or Dm us through telegram @Xotillweoverdosee & @Jooooooooj
Hiking Cost - 850 birr
Hiking Date - March 13
Meet up point - Mexic In front of Wabi Shbelle Hotel
Time - 11:50 LT in the morning (bus will leave after 30 minutes)

#ዳናሀይኪንግ በአዲስ ጉዞ መቷል። የፊታችን እሁድ መጋቢት 4 ወደ ሚኒልክ መስኮት የምንጓዝ ይሆናል።
የጉዞ ሂሳብ 850 ብር! ሲሆን ለመመዝገብ በ 0927710221 ወይም በ 0911282876 ይደውሉ። ካልሆነም በ ቴሌግራም @Xotillweoverdosee እና @Jooooooooj ይመዝገቡ!

@danahiking @danahiking1

Читать полностью…

Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

Dear Dana Hiking family plz be sure to fulfil the following tips to enjoy and have a safe, comfortable and pleasurable hike.

1. Bring your ID card. It's Mandatory if you don't bring an ID card we won't let take the responsibility.

2. Eat light carbs for breakfast and drink plenty of water to help you stay hydrated. Avoid eating fats and proteins, they take longer to digest and could make you feel sluggish

3. Plz be punctual. The Time of Departure is 12:15 Local time, we may have an extra 15 min in case unexpected things happen. If you are getting late will not be held responsible. be punctual!

4. Dress a comfortable cloth, the weather may change but we recommend you to have extra cloth in ur bag to keep warm. and wear good hiking shoes.

5. Have a Backpack to Pack extra food, water, fruits and extra cloth.

6. Plz follow the local guides and the organizers don't use a shortcut.

7. Take your own and group photos and don't forget to share with us.

📱📱📱📱📱📱📱


Jo - 0911282876
Biki - 0927710221


See you, don't be late!
🙏🙏

Читать полностью…
Subscribe to a channel