dbustudent | Unsorted

Telegram-канал dbustudent - DBU የተማሪዎች ህብረት!!

2582

የደ/ብ/ዩ የተማሪዎች ህብረት የመረጃ አውታር !!!

Subscribe to a channel

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

እንዴት አመሻችሁ ዉድ ተማሪዎቻችን ዛሬ በግቢያችን የተፈጠረዉን የመብራት መቆራረጥ በሀገር ደረጃ መሆኑን ተገንዝባችሁ የግቢው ጀኔሬተር የሚበራዉ ዶርም ላይ ስለሆነ እራሳችሁን ከተለያዩ ነገሮች ለመጠበቅ በጊዜ ወደ ዶርም እንድትገቡ እናሳስባለን ።

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
/channel/DBUstudent
/channel/DBUstudent

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ማሳሰቢያ
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በቀን 18-19/03/2017 ዓ.ም ለተጠራችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ ዩኒቨርስቲዉ ከዚህ በፊት ሲያደርግ የነበረዉ መነሀሪያ እና ጠባሴ ላይ የነበረ የመኪና ምደባ ባሁኑ ወቅት ባለመመደቡ ሁሉም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ዩኒቨርሰቲው ቅጥር ግቢ እስከምትገቡ ድረስ ምንም አይነት የተመደበ እና ሀላፊነቱን የሚወስድ አካል እንደሌለ ተገንዝባችሁ እራሳችሁን እንዲሁም ንብረታችሁን እንድትጠብቁ ለማሳወቅ እንወዳለን።
የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

Dear Class Representatives,

Attached to this message is the schedule for the Field Choice Orientation. Please share this information with your classmates as soon as possible.

Best regards!

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

የበጎ አድራጎት ጥሪ:-
ለወገን ደራሹ ወገን ነውና
ከዚህ በታች ስሙ የተለጠፈው ተማሪ የኛን እርዳታ ይፈልጋልና እባካችሁ እንድረስለት::

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ማስታዎቂያ
የክረምት በጎ አድራጎት ለመሳተፍ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ሰኞ 03/10/16 ዓ/ም ከተዋቱ 3:00 ሰአት በመመርቂያ አዳረሽ ስልጠናው ስለሚሰጥ በሰአቱ እድትገኙ ስንል እናሳስባለን::

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ውድ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን አንዳንድ መረጃዎችን እንዲሁም መልክትን ለማስተላለፍ እንወዳለን።
1ኛ, ማንኛውም ተማሪ ንብረቱን በጥንቃቄ ሊይዝ ይገበዋል
2ኛ, ዶርም ሳትቆልፉ መውጣት አትርሱ መፀዳጃ ቤት እንኳን ቢሆን የሄዳችሁት
3ኛ, በየኮሪደር እና ሻወር ቤት እንዲሁም ዶርም እና በጀርባ በኩል የሚገኘው መብራቶች በርተው ውለው ሲያድሩ ይታያሉ። በመሆኑም በሃላፊነት ስሜት ሁላችንም ልንቆጣጠራቸው እና ልናጠፋቸው ግድ ይለናል።
4ኛ, ሁሌም እንደምንለው ውጭ የምናመሽ ተማሪዎች በጊዜ እንግባ እንዲሁም የምንወጣ ተመሪዎች በጊዜ እንውጣ ጊዜው አይደለም እንኳንለማታ ለቀንም አስቸግሯል።
5ኛ, ላፕቶፕ በላይብረሪ ለብዙ ሰአት ትታችሁ የምትቆዪ እባካችሁ ንብረታችሁንም ተጠንቀቁለት፣ሃላፊነቱንም የራሳችሁ ነው
6ኛ, ዴስቲቪ በምትመለከቱ ጊዜ ያላግባብ ድምጽ የምታወጡ እንዲሁም በወንበር የምትነጋገሩ ሁላችንም እራሳችንን እንፈትሽ
7ኛ,ውሃን ያላግባብ ተከፍቶ ሲፈስ ካየን መዝጋት የሚያሰቸግር(የተበላሸ) ከሆነ ለሚመለከተው ማሳወቅ,ተከፍተው ያሉ በር እና መስኮትን መዝጋት
8ኛ,ከጊዜ ወደ ጊዜ በከተማችን በግቢ አከባቢም ጭምር አሰቸጋሪ ሌባ ተንሰራፍቶ ይገኛል, የሌቦች ባህርያት በባጃጅ እንሸኛችሁ,ይሄን ጽሁፍ አንብብልኝ,ሎተሪ ደርሶኝ ብሄራዊ ሎተሪ አሳዩኝ ፣እስከዛው ስልካችሁን ይዠልቆይ መታወቂያ የለኝ ሆኖነው እናንተ አውጡልኝ ስልክ ቁጥር ያዝልኝ,አንዴ አስደውለኝ, ገፍቶ ለማለፍ መሞከር, ለማኝ መምሰል,ደካማ መምሰል,የሃይማኖት አባት መምሰል, ፈፅሞ የማይገመት (ሃብታም) ወዘተ በመምሰል........ ብቻ በተለያዪ ዘዴ እየሸወዱ ይገኛል። አንዱም የዩንቨርስቲ ተማሪዎች የዝርፊያው ተጋላጭ ናቸው። ስለዚህ እባካችሁ ተጠንቀቁ።

አብዛኛው መልክት ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ላይ ያተኩራል።

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

Example user name= DBU1600004167( his/her ID number)
current Password= Dbu1234*

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

Dear all representatives,

Please share the following information with your class students regarding the online exam page: The page address is 10.18.3.9. Students should log in using their username, which is their student ID number, and the current password, which is Dbu1234*. After logging in, students must immediately change their password to one that is not easily forgettable and consists of a minimum of 8 characters, including capital letters, small letters, numbers, and special characters (# $ % $#*?/+-)Please note that students can practice with a mock exam using the password 1234. If you encounter any challenges, you can contact us on Saturday, 28/07/2016, at the post-graduate library. Natural science students should come in the morning, while social sciences students should come in the afternoon.

Thank you for your cooperation.

Sincerely,

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

Edited DBU-Dereja Campaign

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

የአዲስ ተማሪዎች ዶርም ድልደላ

/channel/ASRAT_WOLDEYES1

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

የመውጫ ፈተና ተራዘመ።

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ መራዘሙን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ማረጋገጥ ችሏል።

የመውጫ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ይፋ ባደረገው መርሐግብር ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።

ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የተፈታኞች ዝርዝር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚላክም ተገልጿል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻  ቻናል👇
/channel/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ🌷🌹💒✝ ።
በዓሉን የሰላም የፍቅርና የአድነት ያድርግልን!!!🙏🙏🐓🐑🐐🌈🌈🌈

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

እንኳን ደስ አላችሁ!!
Congratulations!!🎓🎓🎓
ሁሉም የ2015 ዓ.ም የደ/ብ/ዩ ተመራቂ ተማሪዎች ሀምሌ 13 በደመቀ ሁኔታ ይመረቃሉ።

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የተሰጠ መግለጫ!

በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ማሟላት የሚጠበቅባችሁን አሟልታችሁ ለዚህ ለበቃችሁ ውድ እጩ ምሩቃን እና ክቡራን የምሩቃን ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በዚህ አመት በሁሉም የትምህርት ክፍሎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና፤ ተመራቂ ተማሪዎች ያላቸውን ብቃት ለመለካት የተዘጋጀ እና ለት/ት ጥራት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ቢሆንም የነበሩ ክፍተቶችን እና በቅድሚያ መሟላት የነበረባቸው ሁኔታዎችን በዝርዝር በማስቀመጥ ቢያንስ ቁጥራቸው በዛ ያሉ ተመራቂዎች በሚገኙባቸው የት/ት ፕሮግራሞች በዚህ አመት እንዲጀመር አልያም በሙከራ ደረጃ እንዲሰጥ ያላሳለሰ ጥረት አድርገናል።

ሆኖም የት/ት ጥራትን ለማምጣት በሁሉም የት/ት ክፍሎች እንዲጀመር በመወሰኑ፤ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት በትግበራው ተማሪው ተጎጂ እንዳይሆን እያደረግን ቆይተናል። በቅርቡ በተሰጡት የመለማመጃ እና የሙከራ ፈተናዎች ወቅት የነበሩ ክፍተቶችን ከየዩኒቨርሲቲው የተማሪ ህብረቶች በመሰብሰብ እና በዋናው ፈተና ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመለየት እንዲስተካከሉ ለት/ት ሚኒስቴር ከወዲሁ አሳውቀናል።

በተጨማሪም ምርቃት እና የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ከት/ት ሚኒስቴር ጋር በነበረን ቅድመ ውይይት የምረቃ መርሀ-ግብር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎችን በተመለከት ዩኒቨርሲቲዎች የቀደመ አሰራራቸውን መከተል እንደሚችሉ ስምምነት ላይ ደርሰን የነበረ ቢሆንም፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “የመውጫ ፈተናን ያላለፉ ተማሪዎች የምርቃት ፕሮግራም ላይ አይሳተፉም” በማለት በድንገት አሳውቆ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

ውሳኔው ከተገለፀበት እለት ጀምሮ እንደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ጉዳዩ አግባብነት የሌለው፣ በህግ ለተቋማት ሴኔት በተሰጠ ስልጣን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያለ አግባብ ጣልቃ መግባቱን እንዲሁም ውሳኔው ከ4-7 አመታት የተማረው ተማሪን ብቻ ሳይሆን የሀገር መሰረት የሆነውን ቤተሰብንም ጭምር የሚጎዳ፤ ለት/ት ጥራቱም ምንም ፋይዳ የሌለው መሆኑን በመግለፅ በተደጋጋሚ ውይይት ያደረግን ሲሆን በዚህም መሰረት ት/ት ሚኒስቴር በግብታዊነት ያስተላለፈውን ውሳኔ በማሻሻል ወደቀድሞ ሀሳብ ተመልሷል። ለዚህም በተመራቂ ተማሪዎች ስም ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በዚህም መሰረት በሀገራችን የሚገኙ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንድ/ሁለት ያልተሟላ ውጤት ኖሯቸው ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት(CGPA>=2.00) ያላቸውን ተማሪዎች የምርቃት መርሀ-ግብር እንዲሳተፉ አድርገው ሲያሟሉ ዲግሪ የሚሰጡ ሲሆን አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፍ ተማሪ ካለ የምርቃት መርሀ-ግብር ላይ በመሳተፍ ለምዘናው ብቁ በሆነ ጊዜ በየሶስት ወሩ በሚሰጠው ፈተና ያለገደብ መመዘን ብሎም ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌለው እጩ ምሩቅ በደረጃ ዝቅ ያለ የት/ት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችል በመመሪያ ተቀምጧል።

በመሆኑም ውድ እጩ ምሩቃን በምርቃት መርሀ-ግብር ዙሪያ ሲነሱ የነበሩ ነገሮችን ታግሳችሁ ከሚመለከታቸው አካላት መልስ እስኪሰጥ በትግስት ስለጠበቃችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ ጥያቄያችን መልስ አግኝቶ ሁሉም ተመራቂ ተማሪ የምርቃት መርሀ-ግብር ላይ የሚሳተፍ በመሆኑን እንገልፃለን።

በተያያዘም የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው(Tempo) ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት ማለትም የወጪ መጋራታቸውን ከፍለው ሲያጠናቅቁ በሚሰጣቸው፤ የወሰዱትን የት/ት አይነቶች ከነውጤታቸው በሚያሳየው ማስረጃ ላይ መሆኑን እየገለፅን መንግስት አዲስ ቅጥር ማቆሙን ካሳወቀ 2 አመታት ያለፉ ቢሆንም በግሉ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በመንግስት መስሪያ ቤቶችም የተለያዩ አዲስ ቅጥሮች ሲፈፀሙ የቆዩ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

በመጨረሻም ክቡራን እጩ ምሩቃን፦
1) የምትፈተኑበት ኮምፒውተር ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ፈትሻችሁ እንድትቀመጡ፤
2) ፈተናውን በምትሰሩበት ወቅት የኮምፒውተር ገመዶች በሰውነታችሁም ሆነ በሌላ ነገሮች እንዳይነኩ እና እንዳይቋረጡ ጥንቃቄ እንድታደርጉ፤
3) ወደ መፈተኛ ክፍሎች ስትገቡ እና ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ መመሪያዎችን እንድታከብሩ፤
4) ምዘናው በበይነመረብ የሚሰጥ እንደመሆኑ በፈተናው ወቅት ችግሮች ካጋጠሙም ወድያው መፍታት ስለሚቻል እንከን ሲያጋጥማችሁ በየመፈተኛ አዳራሹ ለተመደቡ የአይሲቲ ባለሙያዎች በፍጥነት እንድታሳውቁ እንዲሁም የሚያጋጥሟችሁን የትኛውም ተግዳሮቶች በግቢያቹ ላለው ህብረታችሁ በማመልከት ከግቢው ከአቅም በላይ ከሆነ በእኛ በኩል በሚመለከተው አካል እንዲፈታ የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን በቅርቡ በተሰጠው የሙከራ ፈተና ልክ በመዘጋጀት ያለምንም ፍርሀት እና ጭንቀት የፈተና ስነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ እንድትፈተኑ አደራ እያልን መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ስም አብዝተን እንመኛለን።


መልካም እድል!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት



@EHEISUOfficialChannell

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ማስታወቂያ
ለስፖርት አፍቃሪያን በሙሉ ተቋርጦ የነበረው DSTV ዛሬ 5/05/2015 ዓ/ም ከ 9:00 ሰአት ጀምሮ አገልግሎት ስለሚሠጥ በሠአቱና በቦታውና ተገኝታችሁ ተሳታፊ እንድትሆኑ እያልን እናሳስባለን ።
መልካም እድል

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ለመላው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ በቤተ-መፃህፍት (library) ዙሪያ ከሚመለከታቸዉ የሁሉም ቤተ-መፃህፍት ሀላፊዎች እና አስተባባሪዎች ጋር በቀን 12/03/2017 ዓ.ም ባደረግነው ስብሰባ እስካሁን ድረስ በተማሪም ሆነ በሰራተኛ ሲፈጠሩ የነበሩ የቤተ-መፃህፍት ህግና ደንብ የጣሱ ክፍቶች በያዝነው የትምህርት ዘመን እንደማይኖሩ እንዲሁም ለመማር ማስተማር ሂደቱ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ እንደምንወጣ ስምምነት ላይ ደርሰናል ።

የተማሪ ህብረት ጽ/ቤት

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ዉድ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ዛሬ በቀን 12/03/17 ዓ.ም በግቢያችን ውስጥ የውሀ አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል ይህም የተፈጠረው የዩኒቨርስቲው የዉሀ ጉድጓድ ብልሽት ስላጋጠመው በመሆኑ ነዉ ፤ ዉሀዉ ከተቋረጠበት ጊዜ አንስቶ ባለ ሙያዎች የቻሉትን ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ተገንዝባችሁ እስከ ንጋት ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁን እና የተለመደው ትብብራችሁ እንዳይለየን በትህትና እንጠይቃለን።

የተማሪ ህብረት ጽ/ቤት

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

#MoE #Pharmacy

ትናንት የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና "የቴክኒክ ችግር" አጋጥሞት እንደነበር ትምህርት ሚኒስቴር አረጋገጠ።

ስለሆነም ፈተናውን በድጋሜ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ፈተናው በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰአት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል ተብሏል።

ለፈተናው ተቀምጣችሁ የነበራችሁ የፋርማሲ ተማሪዎች በየተፈተናችሁበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንድትወስዱ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻  ቻናል👇
/channel/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

የበጎ አድራጎት ጥሪ:-
ለወገን ደራሹ ወገን ነውና
ከዚህ በታች ስሙ የተለጠፈው ተማሪ የኛን እርዳታ ይፈልጋልና እባካችሁ እንድረስለት::

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ማስታወቂያ
ሰላም ወድ የደብረ ብረሃን ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ ጠዋት ተስተጉጉ ሎ የነበረው ክላስ ከሰዓት ኖርማል በነበረው ክፍለጊዜ ስለሚቀጥ ል ሁሉም ተማሪ ወደ ክላስ አንድትገቡ ስንል አናሳስባለን::

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
⭐️🌙🕍እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ ::
ኢድ ሙባረክ !!!🕌🌠🌃
"የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት "

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ውድ ሁሉም ተወካዮች ፣
ኦንላይን ላይ የፈተና ገጽን በተመለከተ ለክፍል ተማሪዎችዎ የሚከተለውን መረጃ ያካፍሉ፡ የገጹ አድራሻ 10.18.3.9 ነው። ተማሪዎች ስማቸውን ማለትም የተማሪ መታወቂያ ቁጥራቸውን እና የአሁኑን የይለፍ ቃል Dbu1234* በመጠቀም መግባት አለባቸው። ተማሪዎች ከገቡ በኋላ ወዲያውኑ የይለፍ ቃሎቻቸውን በቀላሉ ወደማይረሳው እና ቢያንስ 8 ካራክተር ያካተተ ሲሆን ይህም ትልቅ ፊደላትን, ትናንሽ ፊደላትን, ቁጥሮችን እና ልዩ ካራክተር (# $ % $#*?/+-) መቀየር አለባቸው. ተማሪዎች የይለፍ ቃሉን 1234 በመጠቀም በሞክ ፈተና መለማመድ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ ማንኛውም ችግር ካጋጠማችሁ ቅዳሜ በ28/07/2016 በድህረ ምረቃ ላይብረሪ ሊያገኙን ይችላሉ። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በጠዋት መምጣት አለባቸው፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሰአት በኋላ መምጣት አለባቸው።
ለትብብርዎ እናመሰግናለን.

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ለሁሉም የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ2016ዓ/ም የሰኔ እና 2017ዓ/ም የጥር ተመራቂዎች በሙሉ ሃሙስና ቅዳሜ ከላይ በፎቶ ላይ በምታዩያቸው ፓኬጆች ስልጠና ስለሚሰጥ የስልጠናው ተሳታፊ እድትሆኑ::

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ማሳሰቢያ
ለሁሉም የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ሰዓት ስንት ሰዓት እደሆነ ሁሉም ተማሪ የሚያውቀው ነው ::ቢሆንም ግን አንዳንድ ተማሪዎች ሰዓት አሳልፋችሁ የምትመጡ አላችሁ እናም ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለዚህ ምቹ ስላልሆነ በሰአቱ እድትገቡ ስንል እናሳስባለን :: ከዚህ ውጭ ግን ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን በራሳችሁ የምትወስዱ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን ::

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ማስታወቂያ
ለሁሉም አዲስ 1ኛ አመት ክፍል ተወካዮች ነገ
በ02/06/2016ዓ.ም ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 ድህረ ምረቃ ህንፃ መማሪያ ክፍል ውስጥ የጋራ ኮርሶች ማስተባበሪያ ለአጭር ስብሰባ ስለሚፈልጋችሁ ሁላችሁም እንድትገኙ በአክብሮት እናሳስባለን ።

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

የ2016ዓ/ም የሴት ተማሪዎች ዶርሚተሪ ድልድል

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ሰላም ውድ የ2013 እና 2014 ባች  የDBU ተማሪዎች ሰሜታችሁ ይገባናል የሁላችንም ስሜት ነው ቢሆንም ባሁኑ ሰዓት ምንም አይነት ስለ ጥሪ ቀን የተወሰነ ነገር ስለሌለ ጥሪው እንደተወሰነ እናሳውቃለን እስከዛው በትዕግስት ጠብቁን፡፡

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ሰላም ውድ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተና እደት ነበር ?
የመመረቂያ ቀን መቸ ነው እያላችሁ ለጠየቃችሁን ልጆች ሀምሌ 13 ነው።

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ማስታወቃያ
የተማሪ ህብረት፥ የተማሪ ፖሊስ ፥ የድስፕሊን ኮምቴ ሰኞ የምክክር መድረክ ከፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ጋር በመመረቂያ አዳራሽ ይኖራል ስለተባለ ከወዲሁ እየተዘጋጃችሁ ቆዪ መቅረት ፈፅሞ አይቻልም ።
ሰዓት ከቀኑ 8:00
መሳሰቢ ፦ ተለዋጭ ሀሳብ ካለ እናሳውቃለን

Читать полностью…

DBU የተማሪዎች ህብረት!!

ዓለም ዓቀፍ የፀረ-ኤድስ እና የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መመረቂያ አዳራሽ
ሓሙስ ህዳር 22 /2015 ዓ.ም ከ7፡30 ጀምሮ ይከበራል።
በዕለቱም፡- የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ዝግጅቶች ይቀርባሉ።

ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን በዓሉን በአጃቢነት ያደምቃል።

@DBU11
@dbudailynews

Читать полностью…
Subscribe to a channel