ያልተበረዘውን ያልተቀየጠውን የጥንቱን ወንጌል የሚያስተምሩ ተከታታይ የክርስቲያን መፅሐፍት አሉን!!! ሁሉም ያለምንም ክፊያ በነፃ ናቸው!!!
nlmethiopia.com
👉0910555190
👉0910367615
/channel/dehnenet
Coworker Daniel Tesfaye sharing the primitive gospel at funeral
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በፃድቁ ወንድማችን ደጉ ቀብር ስነስርዓት ላይ ሲሰበክ!!!
በርካታ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ጥምቀት አሽቀንጥሮ ጥለው ፣ ደሙ ላይ ብቻ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ደሙ ደሙ ደሙ ደሙ ደሙ ብቻ ነው፡፡ ስለ ደሙ ብዙ ተሰብኳል፣ ስለ ደሙ ብዙ ተዘምሯል፣ ስለ ደሙ ብዙ ተጽፏል፡፡ ስለ ክርስቶስ ጥምቀት ግን ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ ለምን የክርስቶስ ጥምቀት ተሸፈነ? ለምን የክርስቶስ ጥምቀት ተደበስብሶ ታለፈ ? ልምን የክርስቶስ ጥምቀት ችላ ተባለ? መጥምቁ የሐንስና ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ የፈጽሙት የጽድቅ ስራ ለምን ተሰወረ? ትኩረት ወደ ውሃው (ወደ ኢየሱስ ጥምቀት)! www.nlmethiopia.com
Читать полностью…አጋር ምዕመናኖቼ አምላካችን በትንሽ የዝምታ ድምጽ በውሃውና በመንፈሱ
ቃል አማካይነት ይሰራል፡፡ አንዳንድ ክርስቲያኖች በመነቃቃት ጉባኤ ላይ
የእንቅጥቃጤ ስሜት ከላይ እስከ ታች እንደተሰማቸውና ሰዎች በልሳናት ሲናገሩና
በሐሴት በጀርባቸው ሲወድቁ፣ ሁሉም ዓይነት ተዓምራዊ ነገሮች ሲከሰቱ እንዳዩ
ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች የእግዚአብሄር ሥራ አይደሉም፡፡ አንዳንድ
መጋቢዎች በክፍላቸው ውስጥ ሳሉ እንግዳ የሆነ ስሜት እንደተሰማቸው፣
በድንገትም ሰውነታቸው በሙሉ ከላይ እስከ ታች እንደተርገፈገፈና አፍንጫቸውም
የሚያነቃቃ መዓዛ እንዳሸተተ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህም ቢሆኑ የመንፈስ ቅዱስ
ሥራዎች አይደሉም፡፡ የዲያብሎስ ሥራዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በውሃውና
በመንፈሱ ወንጌል አምነው የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ሳይቀበሉ እንዴት
የእግዚአብሄርን ሥራ የሚያዋቅር አንዳች ነገር በእነርሱ ላይ ሊከሰት ይችላል? በሌላ
አነጋገር መንፈስ ቅዱሰ በጭራሽ በሐጢያተኞች መካከል አይሰራም፡፡ ይህ የመንፈስ
ቅዱስ ሥራ ሳይሆን የዲያብሎስ ሥራ ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሚመጣው
ሰው በተብራራው የእግዚአብሄር ቃል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ቃል ሲያምን
ነው፡፡
ያለን አንድ ምርጫ ነው። በዮርዳኖስ ወንዝ የተከናወነውን ጥምቀት በማመን ወደ ተስፋይቱ ምድር መሻገር ወይም ወደ ሙት ባህር መፈሰስ። ~~~
“እንዲህም ይሆናል፤ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ ከላይ የሚወርደው የዮርዳኖስ ውኃ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።” (ኢያሱ 3፥13)
በነዌ ልጅ በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን ወተትና ማር ወደ ምታፈስ ከነዓን ለመግባት እየገሰገሱ ነበር።ይህን ሲሰሙ ከናአዓውያን በታላቅ ፍርሃት እየተዋጡ መጡ። እስራኤልውያን ከናዓን እንዳይገቡ የሚከለክል ትልቅ እንቅፋት ከፍታቸው ገጠመ። እርሱም እጅግ የሞላው የዮርዳኖስ ወንዝ ነው። የዮርዳኖሰን ወንዝ ሳይሻገሩ ከናዓንን መውረስ አይችሉም። ታላቅ ድልድይ በመገንባት የዮርዳኖስ ወንዝን ለመሻገር አልሞከሩም። የሞላው የዮርዳኖስ ወንዝ እስኪቀንስ ድረስ እዚያ ለመቆየትም አላሰቡም። በሌላ መንገድ ወደ ከናዓን ለመግባት ጥረት አላደረጉም። ዮርዳኖስን ወንዝ ለማቋረጥ ማንኛውም ሰብአዊ መንገድ አልተጠቀሙም። ታዲያ ምን አደረጉ? የእግዚአብሔር ቃል ሰሙ። የሰሙትን አደረጉ። እግዘመአብሔር ድንቅ ነገር አደረገ።
ኢያሱ እግዚአብሔር ድንቅ ነገር እንደሚያደርግ አሰማቸው። ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት እግሮቻቸውን በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ዳር ሲያጠልቁ ወደ ሙት ባህር የሚፈሰው እጅግ የሞላው የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክምር እንደሚቆም ተናገረ። የእስራኤል ሕዝብ በደረቀ ምድር ተሻገረ።
ኢያሱ ማለት የስሙ ትርጉም አዳኝ ማለት ነው። የእስራኤል ሕዝብ እጅግ የሞላውን ዮርዳኖስን ተሻገረው የተስፋይቱን ምድር የወረሱት በሙሴ መሪነት ሳይሆን በኢያሱ መሪነት ነው። ወደ ሞት ባህር ማለት ወደ ሲኦል ከሚወስደን ኃጢአቶቻን አሻግሮን ወደ መንግስተ ሰማያት ሊያስገባን የሚችለው ሕግ ሳይሆን ጸጋ ነው። ሙሴ ሳይሆን ኢያሱ ነው። ሕግን መጠበቅ ሳይሆን በውሃና በደም ውስጥ የተገለጠውን ጸጋ ማመን ነው። ኢያሱና ኢየሱስ የስማቸው ትርጉም አንድ ነው። አዳኝ ማለት ነው። ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀው ምሳሌ ለመሆን አይደለም። ትሑት መሆኑን ለማሳየትም አይደለም።
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀው የዓለምን ሕዝብ ሁሉ ወደ ተስፋይቱ ምድር ማለትም ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊያሻግር ነው። ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ወደ ተስፋይቱ ምድር መሻገር አይቻልም። ሁላችንም ከልባችን ከሚፈሱ ኃጢአቶቻችን የተነሳ ወደ ሙት ባህር የምንሄድ ሰዎች ነን። ኢየሱስ ግን በዮሐንስ እጅ ዝቅ ብሎ በመጠመቅ መተላለፎቻችን፣ ድከመቶቻችንን፣ኃጢአቶቻችንን፣ ነውሮቻችንን ሁሉ ወሰደ። ጽድቅን ሁሉ ፈጸመ። ወደ ከናዓን አሻገረን። ለዚያ ነው ኢየሱስ ሲጠመቅ እንዲህ ያለው "አሁንስ ፍቀድልኝ ጽድቅ ሁሉ እንዲህ መፈጸም ይገባናል (ማቴ 3:15)። ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ደህንነት የለም። ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ጽድቅ የለም። ያለ ኢየሱስ ጥምቀት መሻገር የለም። ሊቀ ካህኑ አሮን እጆቹን ጭኖ የእስራልን ኃጢአት ሁሉ፣ በደል ሁሉ፣መተላለፍ ሁሉ ወደ ሕያው ፍየል እንዳስተላለፈ ሁሉ፣ ከሊቀ ካህኑ አሮን ዘር ግንድ የመጣው አጥማቂው ዮሐንስ እጆቹን ኢየሱስ ላይ በማኖር ሲያጠቅ የዓለም ኃጢአት ሁሉ፣ መተላለፍ ሁሉ፣ በደል ሁሉ ወደ ኢየሱስ እንደ ተሻገረ ማመን አለብን። ይህን ካመንን ድንቅ ነገር ይሆናል። ዮርዳኖስን እንሻገራለን። የተስፋይቱን ምድር መንግስተ ሰማያትን እንወርሳለን። ይህ ካለመንን የዮርዳኖስን ወንዝ አንሻገርም። ወደ ሙት ባህር እንገባለን። እርሱም የዘላለም ሞት ነው። ስለዚህ ሞትና ሕይወት ከፊታችን አለ። ምርጫው የእኛ ነው።
መልካም የጥምቀት በአል!
በነፃ የሚታደሉ ተከታታይ የክርስቲያን መጽሐፍት አሉን።
@dehnenet
@dehnenet
@dehnenet
ከተቆለለ የምስጋና መስዋዕት የስናፍጭ ቅንጣት እምነት ዳግመኛ ያልተወለዱ ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስን በቃላቸው ያሸሞነሙናሉ። ኢየሱስዬ፣ ውዴ፣ የልቤ ወዳጅ፣ ምስጢረኛዬ፣.አባብዬ...ይላሉ። ወደ እግዚአብሔር ፊት ሲቀርቡም፣ ትሩፋቶቻቸውን፣ ጥረቶቻቸውን፣ ታማኝነታቸውን፣ ጽድቃቸውን፣ መልካምነታቸውን...ይቆልላሉ። ለእግዚአብሔር ይህንና ያንን እንዳደረጉ ይናገራሉ። መድረካቸውን ያስገጣሉ። አዳራሻቸውን ያሳምራሉ። ንግግራቸውን ያስውባሉ። በውድ ዋጋ በተገዙ በተላያዩ ዓይነት የሙዝቃ መሳሪያ ታጅቦ ይቦርቃሉ። ለእ/ር ምስጋና ይሰዋሉ። እግዚአብሔር ግን ወደ እነሱ አይመለከትም። መስዋዕታቸውንም አይቀበልም። ለምን? የሚያቀርቡት የቃየን ዓይነት መስዋዕት ስለሆነ። ለምን? ለእግዚአብሔር የሚሠውት መስዋዕት የምድር ፍሬ ስለሆነ። ለምን? የምድር ፍሬ የሚያምር ቢሆንም እ/ር ስለማይደሰትበት። ለምን? ምክንያቱም ደም የሌለበት መስዋዕት ስለሆነ። ለምን? የኃጢአትን ስርየት የማያስገኝ መስዋዕት ስለሆነ።ለምን? ደም ሳይፈስ የኃጢአት ስርየት የማይገኝ ስለሆነ ።
~~~~~~~~~~~~~~~~
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤.... ("እግዚአብሔር) ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። ቃየንም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ።"(ኦሪት ዘፍጥረት 4: 3 ፤5)"
በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች ለእ/ር የሚያቀርቡት መስዋዕት እንደ ቃየን አይነት ነው። የምድርን ፍሬ ያቀርባሉ። የምድርን ፍሬ ይዞ በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርብ ማንም ቢኖር፣ ተቀባይነት አያገኝም። የምድር ፍሬ የሚያመለክተው ጥረታችንን፣ታመኝነታችንን፣ ትሩፋቶቻችንን፣ ጽድቃችንን፣ መልካምነታችንን... ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ " አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤" (ኦሪት ዘፍጥረት 4:4)
በእግዚአብሔር ፊት ይዘን መቅረብ የሚገባን እንደ አቤል ዓይነት መስዋዕት ነው። በኩር ጠቦት ስብ ያለበት። ያም ኃጢአቶቻችንን በጥምቀቱ ተሸክሞ በጵላጦስ ችሎት ተፈርዶበት በመስቀል ላይ የሞተው ኢየሱስ ነው። እግዚአብሔር የሚፈልገው ይህን መስዋዕት ይዘን በፊቱ እንድንቀርብ ነው። ከዚህ ውጪ የሆነ መስዋዕት እግዚአብሔርን አያስደስተውም። ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት በዮሐንስ ሲጠመቅ ወስዶ በመስቀል ላይ ሞቶ የነፍሳችን ቤዛ እንደሆነ አምነን ለእግዚአበሐር የምንሠዋ ምስጋና እግዚአብሔርን ያስደስታል። እግዚአብሔር ወደ እኛና ወደ መስዋዕታችን ይመልከታል። በእኛም ምስጋና ይደሰታል ። ለምን? ምክንያቱም መስዋዕትታችን ደም የሌለበት የብርትኳን ወይም የማንጎ ወይም የአናናስ ወይም የፓፓያ ክምር ሳይሆን ኃጢአቶቻችንን ተሸክሞ ደሙን ያፈሰሰልን በኩር ጠቦት ነው። ይህ በኩር ጠቦት በመንፈስ ቅዱስ የተጸነሰ የዓለምን ኃጢአት ያሰወገደው የእግዚአብሔር በግ ነው።
የተወደዳችሁ ጻድቃን፤ ተቆልሎ ተራራ ከሚያኽል እጅግ ከሚያምር ከምድር ፍሬ መስዋዕት ይልቅ በውኃ ጥምቀቱ ኃጢአቶቻችንን ወስዶ በመስቀል ላይ ደሙን ባፈሰሰልን በእግዚአብሔር በግ ላይ ያለን የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክል እምነት እግዚአብሔርን ታስደስተዋለች።
ወድ ጻድቃን፣ ዛሬም ይህን የማይሻር የማይለወጠውን የደህንነት እውነት አምነን፣ ለእግዚአብሔር እንደ አቤል ዓይነት መስዋዕት የምናቀርበው እኛ ጻድቃን ነን። ሃሌሉያ! ሃሌሉያ! ሃሌሉያ! በማንኛውም ዓይት የሃይማኖት ተቋም ውስጥ የሚገኙ ኃጢአተኞች ወደ እግዚአበሐር ሲቀርቡ የቃየን ዓይንት መስዋዕት ይዞ ነው የሚቀርቡት። እግዚአብሔር ወደ እነሱና ወደ መስዋዕታቸው አይመለከት። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር የሚደሰትበትን ትክክለኛውን መስዋዕት ማቅረብ የሚችሉት እኛ ጻድቃን የምንሰብከውን የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል ሰምተው በልባቸው ሲያምኑ ብቻ ነው።
መልካም ቀን!
18/01/2014
ወንድም ዮሐንስ
🙏🙏🙏
ሁለት አይነት ክርስቲያኖች አሉ። ከአጋር የተወለዱና ከሳራ የተወለዱ። የባሪይቱ ልጆችና የጨዋይቱ ልጆች። እንደ ስጋ ፈቃድ የተወለዱና እንደ መንፈስ ፈቃድ የተወለዱ። የባሪይቱ ልጆች ከጨዋይቱ ልጆች ጋር አይወርሱም። አሁን ምድርቷን ያጥለቀለቁ የባሪይቱ ልጆች ናቸው። ሃጢአት ያለባቸው ክርስቲያኖች በሙሉ የባሪይቱ ልጆች ናቸው። የጨዋይቱ ልጆች ጥቂቶች ናቸው። እነሱም በክረስቶስ ውሃ ጥምቀትና በመስቀል ላይ በተፈመው የደህንነት ስራ በማመን ዳግመኛ የተወለዱ አማኞች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በመሆኔ ሁሌም ክብር ይሰማኛል።
ዳግመኛ ልደትን ወደ ሚስጠው ወደ ጥንቱ ወንጌል ተመለሱ!
በነፃ የሚሰጡ ተከታታይ መንፈሳዊ መፅሐፍት አሉን!
#ደህንነት
በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርስ መመካከር~~
መጽሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ ከሚነግረን ነገሮች ውስጥ አንዱ የጻድቃን ኀብረት ነው። እግዚአብሔር በተናጥል በሚናደርገው ነገር ፈጽሞ አይደሰትም። እግዚአብሔር አንድ አካል ነው ማየት የሚሻው። በእርግጥ የተለያዩ ብልቶች ነን ግን አንድ አካል ነን። እያንዳንዱ ብልቶች በጅማት የተጋጠሙ፣ በጥብቅ የተቆራኙ ናቸው። አንድ ብልት ከአካል ቢቆርጥ፣ በራሱ ሕይወት ሊኖሮው አይችልም። functional አይደለም። እጃችን ከአካላችን ቢቆረጥ፣ ብቻውን መስራት አይችልም። እግራችን ከሰውነታችን ተቆሮጦ ቢወጣ፣ በራሱ መሮጥ አይችልም። መሮጥ የሚችለው ከአካል ጋር ሲቆራኝ ብቻ ነው። ጠንካራ፣ ብርቱ፣ ቆራጥ ብንሆንም፣ ከአካል ከተገነጠልን፣ ምንም ማድረግ አንችልም። ለጊዜው ልንፍጨረጨር እንችላለን። ነገር ግን በጊዜ ሂደት እንሞታለን።
ዶሮ ሲታረድ አይታችሁ ታውቃላችሁ? አባቴ ቤት ከሌለ፣ ዶሮ የማርደው እኔ ነኝ። አንገቱን በቢላዋ እቆርጥና ቅርጫት ወይም ሳፋ እደፋበታለሁ። ከዚያም አንዱን እግሬን አሳርፍበታለሁ። ዶሮው ቢታረድም ወዲያውኑ አይሞትም። ይፈጨረጨራል። ተነስቶ ለመሮጥም ይሞክራል። መፍጨርጨሩ ሲበዛ አንዳንዴ በደምብ ጉሮሮውን አልቆርጥክም አባላለሁ። የዶሮው መፍጨርጨር ግን ጊዝያዊ ነው። ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ይሞታል።
ከአካል ከተገነጠልን፣ ለጊዜው ልንፍጨረጨር እንችላለን። አልሞቱኩም አለው አለው ልንል እንችላለን። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ በሂደት መሞታችን አይቀሬ ነው። የአካላችን ማዘዣ ጣቢያ ጭንቅላታችን ነው። አካላችን ማንኛውንም ትዕዛዝ የሚቀበለው ከጭንቅላታችን ነው። አንድ ብልት ከአካል ከተገነጠለ፣ ከጭንቅላት የሚላከውን ትዕዛዝ መቀበል አይችልም።
ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት። ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው። ቤተክርስቲያንን ዓለም ላይ እንዳሉ ተራ ተቋማት ማየት የለብንም። ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት። ለዚያ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ከቤተክርስቲያን መጣበቅ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ የሚነግረን። ይህን ቀለል አድርጎ ማየት አያስፈልግም።
ስለዚህ እኛ በውኃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምን ጻድቃን ሁልጊዜ መሰባሰብ፣ እርስ በርስ መመካከር፣ በሕብረት የእግዚአብሔርን ሥራ መስራት ያስፈልጋል። ይህን ስናደርግ ከቤተክርስቲያን ጋር እንቆራኛለን። ከቤተክርስቲያን ያልተቆራኘ፣ ከዓለም ጋር መቆራኘቱ አይቀርም። ከቤተክርስቲያን ጋር ያለው ቁርኝት ሲላላ፣ ልቡ ይደነድናል። መንፈሱም ይበከላል። በመጨረሻም ይሞታል። የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፦
📌“ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤” (ዕብራውያን 3፥13)
📌“በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።” (ዕብራውያን 10፥25)
📌"ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤ በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።" (ሐዋርያት 2:41-42)
ጸጋ ይብዛችሁ!
(ወንድም ዮሐንስ)
ሐምሌ 23-2014
በእምነት ዳግም ተወልደናል፤በእምነት እንኖራለን፤ በእምነት እንሞታለን።~~
የዕብራውያን መልዕክት ጻሐፊው መጀመሪያ እምነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ዕብራውያን ምዕራፍ 11 ላይ ያብራራልናል። ከዚያም በእምነት የኖሩ አባቶቻችንን ይዘረዝርልናል። የእነሱን ፈለግ እንድንከተልም ይመከረናል። የእምነት ቀድምቶችን ሽማግሌዎች (elders) ብሎ ይጠራቸዋል። እነሱ እንዴት በእምነት እንደኖሩና የደረሰባቸውን ማንኛውንም መከራ እንዴት በእምነት ድል እንደነሱ ይናገራል።
📌"እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና" (ዕብራውያን 11:1-2)
ከአቤል ይጀምራል። አቤል በምንድን ነው የኖረው? በእምነት። ቀጥሎ ሄኖክን ያነሳል። ሄኖክ በምንድን ነው የኖረው? በእምነት። ከዚያም ኖኀን ያነሳል።ኖኅ በምንድን ነው የኖረው? በእምነት።
📌"አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል። ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና" (ዕብራውያን 11፡4-6)።
አብርሃምን ያነሳል። ሣራን ያነሳል። ይስሐቅን ያነሳል። ያዕቆብን ያነሳል። ዮሴፍን ያነሳል። ሙሴን ያነሳል። ጋለሞታይቱ ረዓብን ያነሳል። ጌዴዎንን፣ ሶምሶንን፣ ባርቅን፣ ዮፍታሔን፣ ዳዊትን፣ ሳሙኤልን፣ ነቢያትን ያነሳል። አብርሃም በምንድን ነው የኖረው? ሣራ በምንድን ነው የኖረችው? ይስሐቅ፣ያዕቆብ፣ዮሴፍ፣ ሙሴ፣ ጋለሞታይቱ ረዓብ፣ ጌዴዎን፣ ሶምሶን፣ ባርቅ፣ዮፍታሔ፣ዳዊት፣ ሳሙኤል፣ነቢያት....በምንድን ነው የኖሩት? በእምነት።
መንግስታትን ድል የነሱት በእምነት ነው። ጽድቅን ያደረጉት በእምነት ነው። የተሰጣቸውን የተሰፋ ቃል ያገኙት በእምነት ነው።የአንበሶችን አፍ የዘጉት በእምነት ነው። የእሳትን ኃይል ያጠፉት በእምነት ነው።ከሰይፍ ስለት ያመለጡት፣ከድካማቸው የበረቱት፣በጦርነት ኃይለኞች የሆኑት፣ የባዕድ ጭፍሮችን ያባረሩት በእምነት ነው።..........ሁሉንም ነገር በእምነት ነው ያደረጉት።
በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ከእምነት ውጭ የሆነ ነገር አይሰራም። ዳግም የተወለድነው በእምነት ነው። የምንኖረው በእምነት ነው። የምንሞተውም በእምነት ነው። የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፦ 📌“ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።” (ፊልጵስዩስ 1፥21)
ያለ እምነት ምንም ነገር ብናደርግ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። እግዚአብሔርን ደስ ልናሰኝ አንችልም። የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል ከልባችን እንዳመንን ሁሉ፣ እያንዳንዱን የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል በልባችን ማመን ያስፈልጋል። ልባችንን የእግዚአብሔር ቃል የተከማቸበት ግምጃ ቤት ማድረግ ያስፈልጋል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈው ገጽ ለመሙላት ሳይሆን እንድናመነው ነው። እግዚአብሔር አምላክ በእምነት ድል ነሺ ሕይወት እንድንኖር ይርዳን!
አብረን እንደ ሐዋርያት ይህን ጸሎት እንጸልይ፦ "ጌታ ሆይ እምነትን ጨምርልን!"
📌“ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት።”(ሉቃስ 17፥5)
(ወንድም ዮሐንስ)
ሐምሌ 22፣ 2014
ያልተበረዘውን የጥንቱን ወንጌል የሚያስተምሩ በነፃ የሚታደሉ ተከታታይ የክርስቲያን መፅሐፍት አሉን!!!
nlmethiopia.com
0910367615
0910555190
/channel/dehnenet
በነጻ የሚታደሉ አስገራሚ ተከታታይ የክርስቲያን መጽሐፍት አሉን፡፡ ለማግኘት ከፈለጋችሁ በዚህ ስልክ ቁጥር መደወል ትችላላችሁ፡፡ 0910555190 0910367615
Читать полностью…በነጻ የሚታደሉ አስገራሚ ተከታታይ የክርስቲያን መጽሐፍት አሉን፡፡ ለማግኘት ከፈለጋችሁ በዚህ ስልክ ቁጥር መደወል ትችላላችሁ፡፡ 0910555190 0910367615
Читать полностью…እግዚአብሔር ኖህ መርከቡን እንዴት መስራት እንዳለበት ዝርዝር መረጃን ሰጥቶታል። ኖህ በራሱ ሃሳብ ተመርቶ ዝምብሎ መርከብን አልሰራም። እንዴት በክርስቶስ ማመን እንዳለብህ ዝርዝሩ በቃሉ ውስጥ ተፅፏል። በደፈናው በጭፍኑ በክርስቶስ ማመን ካለማመን የሚለየው ነገር የለም። እንደ ተፃፈው ያለመኑም ሙሉ በሙሉ ያላመኑም ተመሳሳይ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
#ደህንነት
አሁን በዓለም ላይ ኃጢአት የለም!
********
እንዴት? መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ ‹‹የዓለምን ኃጢአት›› የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።”(ዮሐ 1፥29) ይላል፤
ቀጥሎም
“ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና። ‹‹መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና›› በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል።”(ሮሜ 6፥9-10)
ይላል።
ስለዚህ ከእንግዲህ በኋላ ኢየሱስ እንደገና ይሞታል? አይሞትም። ለምን? ኃጢአት ስለሌለ።
ኢየሱስ በመጀመሪያም እንዲሞት ያበቃው ኃጢአት መኖር ነበረ።
መጽሐፉ “#መሞትን_አንድ_ጊዜ_ፈጽሞ #ለኃጢአት_ሞቶአልና” ያለው ለዚህ ነው።
ስለዚህ አሁንም ‹‹በዓለም ላይ ኃጢአት አለ›› የሚሉ ሰዎች በፍጹም የኢየሱስን ኃጢአትን የማስወገዱን ኃይሉን አላመኑም ማለት ነው።
ይኼውላችሁ ሰዎች፣ እናንተ ማየት ያለባችሁ፦ ኃጢአት መሥራታችሁንና አለመሥራታችሁን ወይም በዓለም ላይ ያለውን የኃጢአት ብዛቱንና ክብደቱን ሳይሆን ‹‹የኢየሱስን ሞቱን›› ነው።
የኢየሱስ ሞቱና ትንሳኤው የተገለጠው ኢየሱስ ገና በሞተ ሰዓትና በተነሳ ሰዓት ሳይሆን በኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በጥምቀቱ ሰዓት ነው።(ማቴ 3፥13-17፣ ሮሜ 6፥3-6) የኢየሱስ ሞት ማለት የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል ማለት ነው።(ዮሐ 3፥5)
እናንተ ‹‹ኃጢአት አሁንም በዓለም አለ›› የሚትሉ ሰዎች የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል በትክክል ከአለማወቃችሁና ከአለማመናችሁ የመነጨ የአለማወቃችሁ ንግግር ነው።
እርግጥ ነው አዳምና ሔዋን ኃጢአት መሥራትን ከጀመሩበት ሰዓት አንስቶ እስከዚህች ሰዓት ድረስ ሰዎች ኃጢአት በመሥራት አሉ። አሁንም ይህ ዓለም እስኪጠፋ ድረስ ሰዎች ኃጢአትን በማድረግ ይቀጥላሉ።
ይህ ዓለም ሊጠፋ የተወሰነው የኃጢአት ዓለም በመሆኑ ማለትም ሰዎች ኃጢአት መሥራት የማያቆሙ በመሆኑ ነው። እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን(ዓለምን) አጥፍቶ ኃጢአተኛ ያልህኑትን(ጻድቃንን) ለዘላለም ሊያኖር ወስኖ አለ።
ነገር ግን መጽሐፉ ምን አለ?
- ኢየሱስ ‹‹ዓለም እንዳይጠፋ ዓለምን ሊያጸድቅ›› መጥቷል።
- የተሸከመው ‹‹የዓለምን ኃጢአት›› ነው።
- የሞተው ‹‹ለዓለም ኃጢአት›› ነው።
- ከሞትም የተነሳው ‹‹ዓለምን ሁሉ አዲስ ፍጥረት ለማድረግ ነው›› አለ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ዓለም›› የሚያመለክተው ‹‹ሰዎችን ሁሉ›› ማለት ነው።
ስለዚህ አሁን ጻድቅ ያልሆነ ሰው የኢየሱስን ሥጋ ያልበላና ደሙን ያልጠጣ ወይም በኢየሱስ ውኃና ደም ያልታጠበ ሰው ነው ማለት ነው።(1ዮሐ 5፥6፣ ሐዋ 22፥16፣ ኤፌ 5፥26፣ 1ዮሐ 1፥7፣ ራእ 1፥5)
ኢየሱስ በማንነቱ አልፋና ዖሜጋ ፍጹም የሆነ አምላክ ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ ፍጹም እንደመሆኑ ከዓለም መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የተሰራውን የሰውን ዘር ኃጢአት በአንዴ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ በሥጋው ተሸከሞ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ በሥጋው የተሸከማቸውን ኃጢአት በደሙ ደምስሷል ማለት ነው።
በዚህ እምነት ዓለምን የምንመለከት ከሆነ በዓለም ምንም ኃጢአት የለም ማለት ነው። ይህ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነ እምነት ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚያውቀው ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት ተሸክሞ መደምሰሱን ነው።
ሁሉም ሰው ይህንን ቢያምን ሁሉም በዳነ ነበረ። ስለዚህ አሁን ሰው ፍርድን የሚያገኘው በሰራው ኃጢአቱ ሳይሆን ይህንን ታላቁን የኢየሱስን የማዳኑን ኃይሉን በአለማመኑ ጠንቅ ብቻ ነው። በዓለም ላይ በኃጢአቱ የሚፈርድ ማንም ሰው የለም። በአለማመኑ ግን ወደ ፍርድ ይመጣል።(ዮሐ 3፥16-18)
‹‹አሁንም ኃጢአት በዓለም አለ›› ብለን የሚናምን ከሆነ ኢየሱስ እንደገና ይሞታል ማለታችን ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከእንግዲህ ወዲህ ኢየሱስ አይሞትም፣ ምክንያቱም እርሱ በመጀመሪያም አንድ ጊዜ የሞተው ለኃጢአት ነበርና ማለትም ኃጢአትን ለማስወገድ ነበርና አስወግዷል፤
ከዚህ በኋላ እርሱ የሚያስወግደው ወይም የሚሞትለት ሌላ ኃጢአት የለምና ብሏል።(ሮሜ 6፥9-10)
‹‹ኃጢአት አለ›› የሚትሉ ሰዎች እናንተ ኢየሱስን በትክክል አላመናችሁም ከማለት ውጭ ሌላ የምንለው የለም።
ሰዎች በአዳም ምክንያት ኃጢአትን የሚሰሩ ፍጥረቶች ሆነዋል፣ ማንም ኃጢአትን እንዳይሰሩ ማገድ አይችልምና ከሰው ላይ አይናችሁን አንስታችሁ በኢየሱስ ላይ አይናችሁን አስቀምጡ፣ ያን ጊዜ ኃጢአት በዓለም የሌለው መሆኑን ታዩታላችሁ።
ኃጢአት የለም ማለት የምንችለው ሰዎች ኃጢአት መሥራትን ሲያቆሙ ሳይሆን የኢየሱስን መጠመቁን፣ በመስቀል ላይ መሞቱና መነሳቱን በማመናችን ነው።
ስለዚህ እኛ የምናምን ሰዎች በዓለም ኃጢአት የለም እንላለን።
በመጀመሪያ ኃጢአት ወደ ዓለም የገባው በአንድ ሰው በአዳም ነበረ፣ እንደዚሁም ደግሞ ከዓለም የተወገደው በአንድ ሰው በኢየሱስ ነው።(ሮሜ 5፥12-19)
ኃጢአት በአዳም ወደ ዓለም ገባ፣ ኢየሱስ ደግሞ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ ሆኖ መጣ። ስለዚህ በአዳም የገባው ኃጢአት እንዳለ በኢየሱስ ተወግዷል ማለት ነው።
ሰዎች እስከ ዕለተ ሞታቸው በሥጋቸው የሚሰሩት ኃጢአት በአዳም የገባውን ኃጢአት ነው። ነገር ግን በኢየሱስ ጥምቀትና ሞት ከዓለም ጠፍቷል። ይህ የእምነት ቃል ነው። ይህ የመንፈሳዊ ንግግር ነው።
ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ይህንን ሊያስተውልና ሊረዳ አይችልም።
t.me/tobebornagain / nlmethiopia.com
ጌታን ተቀብያለሁ ብሎ ነገር ግን ዳግመኛ ላልተወለደ ሰው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ስመሰክር የተቀዳ ንግግር። ይህን መልዕከት ያዳመጠ ሰው እውነኛውን ወንጌልና እንክርዳዱን ወንጌል ይለያል።
@dehnenet
@dehnenet
@dehnenet
📌"በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ማለት ምን ማለት ነው❓"በመጀመሪያ እነዚህን ሁለቱን የወንድማችን ሐዋርያው ጴጥሮስ መልዕክቶች እናንበብ።
✍ “ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።” (1ጴጥሮስ 2፥24)
✍ “ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤” (1ጴጥሮስ 3፥21)
እግዚአብሔር በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት አዕምሯችን ካልከፈተ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እጅግ ከባድ ነው። ሰው በራሱ መረዳት መጽሐፍ ቅዱስን ሊተነትን ቢሞክር፣ ለተሳሳተ መረዳት ይጋለጣል። ለዚያ ነው ጳውሎስ ለጢሞትዎስ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ ያለው (2ጢሞ 2:7)። ኢየሱስ ክርስቶስም ሰዱቃውያንን መጽሐፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ ብሏቸዋል (ማቴ 22:29)። ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያንን ቅዱሳን መጽሐፍትን እያነበቡ ለምን ይስታሉ? በራሳቸው አሳብ ላይ ተመርኩዞ ስለሚረዱ። ስለዚህ ማስተዋል የላቸውም። ይስታሉ። ያስታሉም።
በዓለም ላይ እጅግ በጣም የተነበበ መጽሐፍ ቢኖር፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የዚያን ያህል እጅግ ብዙ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ የተረዱት መጽሐፍ ቢኖር፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ለዚያ ነው በክርስቲና ስም ብዙ የስህተት ትምህርቶች የተንሰራፉት።
ከላይ ያነበብነው ጥቅስም ብዙ ክርስቲያኖች በተሳሳተ መንገድ ከሚረዱት ጥቅሶች ውስጥ አንዱ ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ ኢየሱስ ራሱ በሥጋው ኃጢአቶቻችንን በእንጨት ላይ እንደተሸከመና በመገረፉ ቁስል እንደፈወሰን ይናገራል። በሌላ ሥፍራ ደግሞ ራሱ ጴጥሮስ ይህ ውኃ አሁን ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ያድነናል ብሎ ይመሰክራል። እግዚአብሔር በሚሰጠን ማስታዋል ካልተረዳን በስተቀር፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ የተናገረው ነገር እርስ በርስ የሚጣረስ ይመስላል። በአንድ በኩል ውሃው (የክርስቶስ ጥምቀት) ያድነናል ይላል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኃጢአቶቻችን በሥጋው በእንጨት ላይ ተሸከመ ይላል።
ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት የተሸከመው በብሉይ ኪዳን የመስዋዕት ስርዓት መሠረት ከአሮን ዘር በመጣው በሊቀ ካህኑ በዮሐንስ አማካኝነት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ቢናገርም፣ ብዙ ክርስቲያኖች ይህ የእውነት እውቀት የላቸውም። ስለሆነም ኢየስሱ በሥጋው ኃጢአቶቻችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ የሚለውን የሐዋርያው ጴጥሮስን መልዕክት በትክክል አይረዱም (1ጴጥሮስ 2: 24)። ኃጢአት ወደ ኢየሱስ የተላለፈው በእንጨት ላይ ሲሰቀል ነው ብሎ ያስባሉ። ይህ ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት አይደለም። የዓለም ኃጢአት ወደ ኢየሱስ የተላለፈው ሲሰቀል አይደልም። ኢየሱስ በእንጨት ላይ የተሰቀለው የዓለምን ኃጢአት ሊሸከም አይደለም። ኢየሱስ በመስቀል የተሰቀለው ኃጢአትን ስለ ተሸከመ ነው። እደግመዋለሁ ሊሸከም ሳይሆን ስለ ተሸከመ ነው። በኦሪት ኪዳን ለኃጢአት የሚቀርብ መስዋዕት ከመታረዱ በፊት፣ እጅ ተጭኖ መስዋዕቱ ላይ ኃጢአት መተላለፍ ነበረበት። መስዋዕቱ የሚታረደው ኃጢአት ከተላለፈበት በኋላ ነው እንጂ ሲታረድ አይደለም ኃጢአት የሚተላለፍበት። ልክ እንደዚያው ኢየሱስ በእንጨት ላይ ከመስቀሉ በፊት የዓለምን ኃጢአት በጥምቀቱ አስቀድሞ መሸከም ነበረበት። ሳይሸከም ቢሰቀል ኖሮ፣ ሞቱ ከንቱ ይሆን ነበር። የመስዋት በግ ኃጢአት ሳይተላለፍበት ቢታረድ ፣ ደሙ ኃጢአተኛውን አያነፃም። በከንቱ የፈሰሰ ደም ይሆናል። ምክንያቱም ኃጢአት አልተላለፈበትማ።
ስለዚህ ሐዋርያው ጴጥሮስ ኢየሱስ በሥጋው ኃጢአቶቻችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ሲል ምን ማለቱ ነው? ኢየሱስ በእንጨት ሲሰቀል የዓለም ኃጢአት ወደ ኢየሱስ ተላልፏል እያለ አይደለም። እንደዛ ቢሆንማ፣ ይህ ውሃ አሁን ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ያድነናል ብሎ ባልተናገረ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ በስጋው ኃጢአቶቻችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ማለት ኢየሱስ በጥምቀቱ የተላለፈበትን ኃጢአት በእንጨት እስኪ ሰቀል ድረስ በሥጋው ተሸክሞት ነበር ማለት ነው። ለዚያ ነው በመገረፉ ቁስል ከኃጢአት ዴዌ ተፈውሰን ጻድቅ የሆንነው!!!
ኃጢአቶቻችንን በጥምቀቱ ተሸክሞ፣ እስከ መስቀል ሞት ድረስ በመታዘዝ የኃጢአታችንን ዕዳ ክፍሎ ለዋጀን ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይግባው!
ሰኔ 09- 2014
ወንድም ዮሐንስ
(Brother John)