የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል ኃጢአት አልባ አድርጎኛል
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የአንደኛ ዓመት የዩኒቨረስቲ ተማሪ ሳለሁ፣ አንድ ቀን ከጓደኛዬ ጋር መንገድ ላይ እየተራመድኩ የፖውል ሲ ጆንግ መጽሐፎችን በሰው እጅ ላይ አገኘሁ። ከመጽሐፎቹ አንዱ "በውኑ ከውኃና ከመንፈስ ዳግም ተወልዳችኋልን?" የሚል ነው።
ይህን መጽሐፍ ከማንበቤ በፊት ዳግም እንደተወለድኩ አስብ ነበር። ዳግም መወለድ የሚመስለኝ ጌታን እንደ ግል አዳኝ አድርጎ መቀበልና መጠመቅ ነበር። እንዲያውም ብዙም ጠለቅ ብዬ ከውኃና ከመንፈስ መወለድ ምን እንደሆነም ጠይቄ አላውቅም። ምንም እንኳን ኃጢአተኛ ክርስቲያን ብሆንም፣ ራሴን እንደ ዳንኩና ዳግም እንደተወለድኩ ክርስቲያን እቆጥር ነበር።
ነገር ግን ይህን መጽሐፍ ሳነብ ፈጽሞ ሰምቼም አንብቤም የማላቀውን ሰማያዊ እውነት አገኘሁ። ጌታችን ኢየሱስ "እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል" እንዳለው፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያላው የደህንነት እውነት ከኃጢአትና ከሞት አርነት አውጥቶኛል። ጻድቅ አድርጎኛል። ልክ እንደማንኛውም ክርስቲያን፣ ቀስ በቀስ በመቀደሰ፣ የንስሐ ጸሎት በመጸለይና በመልካም ምግባር ከኃጢአት ነፃ መውጣት የሚቻል ይመስለኝ ነበር። ጊዜው ሲሄድና ዕድሜዬም እየጨመረ ሲሄድ፣ በኃጢአቶቼ መሰቃየትና መጨነቅ ጀመርኩ። ሕይወትም አስለቺና አስጠሊታ ሆኖብኝ ነበር።
ይህ መጽሐፍ ከእድሜ ልክ ኃጢአቶቼና ከሞት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በውኃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ነፃ መውጣት እንደሚቻል አሳይቶኛል። የዳግም ልደት መንፈሳዊ በረከት እንዳገኝም ረድቶኛል። በሚያሳዝን ሁኔታ በርካታ ክርስቲያኖች በክርስቶስ በጭፍኑ ቢያምኑም፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ካለው ከደህንነት እውነት ጋር ባለመገናኘታቸው በኃጢአት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። የደህንነት እውነትን የሚጠማ ማንም ቢኖር ይህን መጽሐፍ እንዲያነብና ዳግም የመወለድን ሰማያዊ በረከት እንዲያገኝ ምኞቴና ጸሎቴ ነው።
ዮሐንስ ማኬ
#ክርስቶስ #ጽድቃችን--#የጽድቅና #የደህንነት #ዝምድና (#ክፍል 2)
-----------------------------------------------------------------------------------
ጽድቅና ደህንነት የሚባሉት ቃሎች በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ውስ ጥቅብ በሆነ ዝምድና ተቆራኝተዋል፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን እንይ፡፡
‹‹#ጽድቄ ፈጥኖ #ቀርቦአል፡፡ #ማዳኔም ወጥቶአል፡፡ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፡፡ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፡፡ በክንዴም ይታመናሉ፡፡›› (ኢሳይያስ 51፡5) ‹‹#ጽድቅን እንደ ጥሩር #ለበሰ፡፡ በራሱም ላይ #የማዳንን #ራስ #ቁር አደረገ፡፡ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፡፡ በቅንዓትም መጎናጸፊያ ተጎናጸፈ፡፡›› (ኢሳይያስ 59፡17) ‹‹እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- #ማዳኔ ሊመጣ #ጽድቄም ሊገለጥ ቀርቦአልና ፍርድን ጠብቁ ጽድቅንም አድርጉ፡፡›› (ኢሳይያስ 56፡1) ‹‹በወንጌል አላፍርምና አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሄር ሐይል #ለማዳን ነውና፡፡ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደተጻፈ #የእግዚአብሄር #ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት #በእርሱ ይገለጣልና፡፡›› (ሮሜ 1፡16-17) ‹‹ሰው በልቡ አምኖ #ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ #ይድናልና፡፡›› (ሮሜ 10፡10)
ከጽድቅ ጋር ቁርኝት የሌለውና ስለ ደህንነት የሚስተማር ማንኛውም ትምህርት የተሳሳተ ነው፡፡ ጽድቅንና ደህንነትን መነጣጠል መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት መሻር ነው፡፡ በብዙ የአዲስ ኪዳን ምንባቦች ውስጥ ደህንነት ከዘላለም ሕይወት ጋር ጉድኝት ያለው ሆኖ ተገልጦዋል፡፡ (ሮሜ 1፡16-17፤5፡18,21፤6፡23፤ማቴዎስ 19፡17-25) በጽድቅና በደህንነት መካከል ያለው ቁርኝት በአጭሩ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ጽድቅ የደህንነት ቅድመ መጠይቅ ነው፡፡ ሰው ያለ ጽድቅ ደህንነትን ሊያገኝ አይችልም፡፡ ደህንነት በጽድቅ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የጽድቅን መጠይቅ የማያከብር ደህንነት እግዚአብሄርን ሊያከብርም ሆነ የሐጢያተኛውን ሕሊና ሊያረጋጋ አይችልም፡፡
በጽድቅ ላይ ያልተመሰረተ ደህንነት የምታሰተምር ቤተክርስቲያን ‹‹ሌላ ወንጌል›› እየሰበከች ነው፡፡ ይህንን ጽድቅ ያቀረበው የእግዚአብሄር ጸጋ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ›› ተብሎ ተጠራ፡፡ (ሮሜ 1፡17፤3፡21፤10፡3፤ፊልጵስዩስ 3፡9) ኢየሱስ ይህንን ጽድቅ ለመፈጸም ተጠመቀ፡፡ (ማተዎስ 3፡15) ይህንን በማድረጉም ‹‹የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ›› ተብሎ ተጠራ፡፡ (2ኛ ጴጥሮስ 1፡1) ይህ ‹‹የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ›› የሆነው ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ›› ለሰዎች ሊሰጥ የሚችለው በአንድ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ያም በ2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21 ላይ እንደተጻፈው ‹‹እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሄር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ሐጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ሐጢአት በማድረግ›› ነው፡፡ ኢየሱስ ‹‹የእግዚአብሄርን ጽድቅ›› ለእኛ የሰጠን እርሱ ‹‹ስለ እኛ ሐጢአት እንዲሆን ተደርጎ›› ነው፡፡ ያኔ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ ሊጠመቅ በመጣ ጊዜ ‹‹ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› ብሎ ሲናገር የሰውን ዘር ሐጢያት በራሱ ላይ ወስዶ ስለ እኛ ሐጢአት በመሆን በምትኩ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሊሰጠን መወሰኑ ነበር፡፡
ይቀጥላል…
#ክርስቶስ #ጽድቃችን (#ክፍል 1)
--------------------------------------
እግዚአብሄር በክርስቶስ በኩል በሰራው የቤዛነት ስራ ውስጥ የተቆራኙ ሁለት ስረ ነገሮች ያሉ ሲሆን እነርሱም ጽድቅና ደም ናቸው፡፡ ጳውሎስ ደህንነትን ያቆራኘው ከደም ጋር ብቻ ሳይሆን ከጽድቅም ጋር ነው፡፡ በሮሜ 3፡22 ላይ ጳውሎስ ጽድቅ ‹‹#ለሚያምኑ #ሁሉ የሆነ #በኢየሱስ #ክርስቶስ #በማመን የሚገኘው #የእግዚአብሄር #ጽድቅ›› መሆኑን ይነግረናል፡፡ ‹‹እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሄር #ያለ #ሥራ #ጽድቅን #ስለሚቆጥርለት ስለ ሰው ብጽዕና ይናገራል እንዲህ ሲል፡- #ዓመፃቸው #የተሰረየላቸው #ሐጢአታቸውም #የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፡፡ ጌታ #ሐጢአቱን #የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው፡፡›› (ሮሜ 4፡6-8)
‹‹ያለ ሥራ ጽድቅ የሚቆጠርለት ሰው ብጽዕና›› ‹‹የአመጽ ስርየትና የሐጢያት መከደን›› ከማግኘት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ጌታ ሐጢያቱን የማይቆጥርበት ሰው ቀድሞውኑም ‹‹ያለ ሥራ ጽድቅ›› የተቆጠረለት ሰው ነው፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ ይህንን ጽድቅ ‹‹የኢየሱስ ጽድቅ›› በማለት ጠርቶታል፡፡ ‹‹በአምላካችንና በመድሃኒታችን #በኢየሱስ #ክርስቶስ #ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፡፡›› (2ኛ ጴጥሮስ 1፡1) ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያወራ ነው ሲባል (ሮሜ 1፡3) ስለ ጽድቁና ደሙ የሚያወራ ነው ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ ደሙን ያፈሰሰው በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር፡፡ ኢየሱስ ጽድቁን የገለጠው በዮርዳኖስ ወንዝ ተጥምቆ ነበር፡፡ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ #ጽድቅን ሁሉ #መፈጸም ይገባናልና፡፡›› (ማቴዎስ 3፡15) ኢየሱስ ደሙን ለማፍሰስ መስቀል እንዳስፈለገው ሁሉ ጽድቁን ለመግለጥም የዮርዳኖስ ጥምቀት አስፈለገው፡፡ ከዚህ የተነሳ በኢየሱስ የቤዛነት ስራ ውስጥ የተቆራኙት ‹‹ጽድቅና ደም›› ‹‹የዮርዳኖስ ጥምቀትን›› እና ‹‹የጎልጎታን መስቀል›› የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ብሉይ ኪዳን የኢየሱስን ጽድቅ ይመሰክራል፡፡ ‹‹#የወገቡም #መታጠቂያ #ጽድቅ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል፡፡›› (ኢሳይያስ 11፡5) ኤርምያሥም ክርስቶስ ‹‹ጻድቅ ቁጥቋጥ›› መሆኑን አስመልክቶ እንዲህ ተንብዮአል፡፡ ‹‹እነሆ ለዳዊት #ጻድቅ #ቁጥቋጥ የማስነሳበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሄር፡፡ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፡፡ ይከናወንለታልም፤ #በምድርም ፍርድንና #ጽድቅን ያደርጋል፡፡›› (ኤርምያስ 23፡5) እዚህ ላይ ለዳዊት የሚነሳለት ‹‹ጻድቅ ቁጥቋጥ›› ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ አያከራክርም፡፡ (ማቴዎስ 22፤41-46) ኢየሱስ በምድር ላይ ‹‹ፍርድንና ጽድቅን›› እንደሚያደርግ ተተንብዮአል፡፡ ይህ ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው ኢየሱስ ‹‹#ጽድቅን ሁሉ #ለመፈጸም›› (ማቴዎስ 3፡13) በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ነበር፡፡
ይቀጥላል…
"ከተራ"
።።።።።።።።።።።።።
"ከተራ የግዕዝ ቃል ሲሆን ከተረ. ወይም አቆመ ማለት ነው።" ብሎ የኢያሱን መጽሐፍ በመጥቀስ አንድ መ/ር ሲያብራራ ሰማውት።
የእውነት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከተራን ስታከብር በከተራ እለት የሚካሄደውን "የታቦታት መውጣት መግባት" ጭፈራ እና ዳንስ፣መጠጥ፣ደፈራ. . .ወዘተ ያሉትን ነገሮች ብቻ በማየት በተለያየ ጊዜ ተችቼ አውቃለው።
ትችት ግን ፍሬ እንደማያፈራ ገብቶኛል። በመሠረቱ በመሠረታዊ አስተምህሮቷ "ቤተክርስቲያኒቱ" ጨፍሩ ጠጡ ደንሱ ድፈሩ ወዘተ ብላ አታስተምርም። ግና አይማኖትና ባህል ሲቀላቀል እንዲ አይነቱ ነገር የሚጠበቅ ነው።
የሆነው ሆኖ አሁን እኔ ወደ ዋናው ነጥቤ ልምጣላችሁ።
በእውነቱ የሆነው ሆኖ ካህናቱና ታቦቱ ሲገቡበት የዮርዳኖስ ወንዝ መገደቡን ማሰቡ ግን ለእኔ አስደሳች ነው። አድራጊዎቹ በጊዜ ብዛት ባህል አድርገውት ይሆናል። በተለይ ለጻድቃን በዮርዳኖስ ወንዝ የተከናወነውን ነገር ጠንቅቀን ለምናውቅ ይህ
ጆሮ ለሚሰጠን ወንጌልን ለማስተማር ምቹ ጊዜያችን ነው።
ስለጥምቀት ሁሉ በሚያስብበት ወቅት ጥምቀቱን እንስበክ።እኔ የመምህሩን ንግግር ከሰማው በኋላ
ብዙ አሳቦችን ከቃሉ አንጻር ቃኘው።
በዚያውም ስለጥምቀት ስለከተራ አንድ እውነት ብንካፈልስ ስል አሰብኩ። እነሆ፦
የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ከባርነት ቤት ወጥቶ ወደ ከነሃን እንዳይገባ ከፊቱ ጋሬጣ ከሆኑበት ነገሮች
አንዱ የዮርዳኖስ ወንዝ ሙላት ነበር።
ዮርዳኖስ እስከገደፉ ሞልቶ ነበር። እስራኤል ከነሃን ይገባ ዘንድ የግድ ይህን ወንዝ ማቋረጥ ነበረበት።
ዝም ብሎ ዘሎ መግባት አደጋ አለው። የሞላ ወንዝ ነውና። ወንዝ ደሞ እያካለበ እያጋጨ ወዳሻው ቦታ የማድረስ ባህሪ አለው።
ከኢያሱ መጽሐፍ ገራሚ ቃል ላካፍላችሁ፦
(መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ ምዕራፍ 3)
14፤ እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።
15፤ እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ ነበርና ታቦት ተሸካሚዎቹ ወደ ዮርዳኖስ ሲደርሱ፥ ታቦቱንም የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ፥
16፤ ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።
17፤ የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፥ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ።"
የዮርዳኖስ ወንዝ እጅግ ሞልቶ ወደ ወደ ሙት ባህር የሚፈስ ወንዝ ነው። በሙት ባህር ውስጥ ሕይወት ያለው ነገር የለም። ይህ ወደ ሙት ባህር የሚፈሰው ውኃ ካህናቱ እና ታቦቱ ሲገባበት ቆመ። ህዝቡ ሁሉ በደረቅ መሬት ይሻገሩ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ተአምር የግድ አስፈላጊ ነበር። ካህናቱና ታቦቱ ባይገቡና ውኃው ባይገደብ፣መረረቱም ባይደርቅ ህዝቡ በፍጹም
ከነሃን አይገቡም ነበር።
ይህ ኩነት ስለክርስቶስ የሚነግረን አስገራሚ የጽድቅ ቃል አለው። ጌታ ኢየሱስ " እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤" (ዮሐ 5:39) ብሎናል።
በአዲስ ኪዳንም ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ይገቡ ዘንድ ካህናት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መግባት ነበረባቸው። ሰው ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዳይገባ እስከገደፉ የሞላው የምድራችን ኃጢአት መገደብ፣ መድረቅ ነበረበት።ይህ የሚሆነው ደግሞ በካህናቱ ወደ ዮርዳኖስ መግባት ነው።
ኢየሱስ ሹመቱ እንደ መልከ ጸዴቅ የሆነ ሰማያዊ ሊቀ ካህን ነው። አጥማቂው ዮሐንስ ደግሞ እንደ አሮን ክህነት የተካነ፣ ለእግዚአብሔር የተለየ፣ህግና ነብያት እስከ ዮሐንስ ብለው የተነበዩለት የሰው ልጆች ሁሉ ወኪል የሆነ የመጨረሻው ምድራዊ ሊቀካህን ነው። እነዚህ ካህናት ወደ ዮርዳኖስ ገቡ።
የያኔው በስጋ ዓይን የሚታይ የውኃ መገደብ ነበረ።
የአዲስ ካዳኑ ዮርዳኖስ ጋ ግን በመንፈስ የሚታይ የኃጢአት ገደብ ተደረሰጓል።ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዳይገባ ኃጢአት ዘግቶ ነበር። ኢየሱስ ይንን ኃጢአት በዮርዳኖስ ወንዝ በተቀበለው ጥምቀት አስወግዶታል። በታቦት ውስጥ መና አለ። በታቦት ውስህ ህግ አለ።በታቦት ውስጥ የለመለመችው የአሮን በትር አለች። ታቦቱ ክርስቶስን እና የማዳኑን ስራ የሚገልጥ ነው።
ሰው በክርስቶስ እና አጥማቂው ዮሐንስ እና ኢየሱስ በፈጸሙት የጽድቅ ስራ ሲያምን ብቻ ዮርዳኖስን በእምነት ይሻገራል። ከነአን ይገባል።
የአዳም ኃጢአት(በዘር የወረስነውም ሆነ እኛ ሰዎች በሕይወት ዘመናችን የምንሰራው ኃጢአት) ከእኛ ርቆ እንዲገደብ ያደረገው የኢየሱስ ጥምቀት ነው።
ኃጢአት በዮርዳኖስ ወንዝ ከተራውን አግኝቷል።
ኢየሱስ ስለሰው ልጆች ኃጢአት ሙሉ አላፊነትን በጥምቀቱ ወስዶ በመስቀል ላይ ጨርሶታል።
ከክርስቶስ ጋር በእምነት ስንጠመቅ ከእርሱ ጋር አንድ እንሆናለን(ሮሜ6:3)
ከክርስቶስ ጋር ስንጠመቅ ክርስቶስን እንለብሳለን (ገላ3:27)
ያመነ የተጠመቀ ሁሉ ይድናል!
ያላመነ(ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ የዓለምን ኃጢአት በስጋው መሸከሙን አውቆ በልቡ ያልተቀበለ)
ይፈረድበታል።
ምኞቴ ከተራ በዚህ መረዳት ውስጥ ይከበር ዘንድ ነው። ጸሎቴ በመንፈስ ደሃ የሆነ ሁሉ በእግዚአብሔር ጽድቅ ዮርዳኖስን ይሻገር የሚል ነው።
ሻሎም!
4 ተከታታይ እሁዶች #ከደመና_በታች በሚል የተዘጋጀ የክብር ኮንፍረንስ
💎 “ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።” 📖
— ዘዳግም 33፥26
🔥እግዚአብሔር እናንተን ለመርዳት በደመናት ላይ ይራመዳል!
"ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።”
— ናሆም 1፥3
#CloudsAreTheDustOfHisFeet!!!
ዘወትር እሁድ እና ሐሙስ ከጠዋቱ 04:00 - 08:00
👉 ኑ አብራችሁን ሕያው እግዚአብሔርን በማምለክ እና በህያው ቃል፣ በጸሎት፣ በትንቢት፣ በፈውስ እና በነጻ መውጣት በግል ህይወታችሁ ክብሩን ተለማመዱ!
👑 የእግዚአብሔር ቅባት: የክርስቶስን ስራ በህይወታችን የሚገልጥ የእግዚአብሔር አቅም ነው!!!
በእግዚአብሔር ቤተሰብ ቤተክርስቲያን!
ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንዲህ አይነት ጥያቄ አትጠይቁ ይሉናል። የዘመኑ ሐይማኖተኞች ይህንን ጥያቄ ለምን እንደሚፈሩት እናውቃለን። ጥያቄው እየገፋ ሲሄድ አድበስብሰው ለመመለስ ይሞክራሉ። የተድበሰበሰው መልሳቸው ይበልጥ ሌሎች ጥያቄዎችን ይፈጥራል።
አንዱ ተነስቶ ኢየሱስ የተጠመቀው ትህትና ሊያስተምረን ነው ይላል። በመስቀል ላይ የተሰቀለውስ ምን ሊያስተምረን ነው? ተሰቅሎ መሞትን?
ሌላው ተነስቶ ኢየሱስ የተጠመቀው ምሳሌ ሊሆንልን ነው ይላል። በመስቀል ላይ የተሰቀለውስ ተሰቅሎ የመሞትን ምሳሌ ሊያሳየን ነው? ግራ የተጋቡ መልሶች የሚያሳዩት ግራ የተጋቡ ጭንቅላቶችን ነው።
ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? የሚለውን ጥያቄ ራሱ ጥምቀቱን የተቀበለው ባለቤት ሲመልስው ሌሎች መልሶች ሁሉ ውሸት እንጂ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም። ኢየሱስ ለምን እንደተጠመቀ ሲናገር እንዲህ አለ፦ " ኢየሱስም መልሶ:- አሁንስ ፍቀድልኝ፤ #እንዲህ #ጽድቅን #ሁሉ #መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።" (ማቴዎስ 3:15) ኢየሱስ ስለ ጥምቀቱ ከሰጠው ከዚህ ትክክለኛ መልስ በስተቀር ሌላው መልስ ሁለ በትልቁ ❌ ነው።
ኢየሱስ የተጠመቀው "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" ነው። ኢየሱስ የጽድቅ ሁሉ ምንጭ መሆኑን ያሳየው በጥምቀቱ ነው። የአዳም ዘር ያጣው "ጽድቅ" ነው። ምክንያቱም "በአመጻ ተጸንሶ በሐጢአት የተወለደው" (መዝሙረ ዳዊት 51:5) የአዳም ዘር ሁሉ ነው። "እናንተ #ከጽድቅ #የራቃችሁ እልከኞች፥ ስሙኝ፤ #ጽድቄን #አቀርባለሁ፥ አይርቅም #መድኃኒቴም #አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።" (ኢሳይያስ 46:12-13)
የሰው ዘር "ከጽድቅ በመራቁ" እግዚአብሔር ሁለት ነገሮችን እንደሚያደርግ በኢሳይያስ በኩል ተነበየ። የመጀመሪያው "ጽድቄን አቀርባለሁ" የሚለው ሲሆን ሁለተኛው "መድሃኒቴም አይዘገይም" የሚለው ነው። በዚህ መሠረት እግዚአብሔር "መድሃኒቴ" ያለው ኢየሱስ በድንግል ማርያም በኩል እንዲወለድ አደረገ። "ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድኃኒት እርሱም #ክርስቶስ #ጌታ የሆነ #ተወልዶላችኋልና።"
(ሉቃስ 2:11) ኢየሱስ "መድሃኒት" ሆኖ የተወለደው "ሕዝቡን ከሐጢአት ስለሚያድን" ነው። (ማቴዎስ 1:21)
ኢየሱስ 30 አመት ሲሆነው "ጽድቄን አቀርባለሁ" በተባለው መሠረት "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" ተጠመቀ። ሕዝብ ከሐጢአት የሚድነው በጽድቅ ነው። "ንጉሥ ሆይ፥ ስለዚህ ምናልባት የደኅንነትህ ዘመን ይረዝም እንደ ሆነ ምክሬ ደስ ያሰኝህ፤ #ኃጢአትህንም #በጽድቅ፥ በደልህንም ለድሆች በመመጽወት #አስቀር። " (ዳንኤል 4:27) ኢየሱስ በፈጸመው "ጽድቅ ሁሉ" የሰውን ዘር "ሐጢአት አስቀርቶዋል።"
"እግዚአብሔር ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ።" (ክፍል 2)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በክፍል 1 ዳዊት በመዝሙሩ "እግዚአብሔር #ማዳኑን አስታወቀ..." (መዝሙረ ዳዊት 98:2) ብሎ ሲናገር በትንቢታዊ መልክ ስለ ኢየሱስ መናገሩ እንደነበር አይተናል። በአዲስ ኪዳን ስምዖን የተባለ ጻድቅና ትጉህ ሰው ኢየሱስን ተቀብሎ ካቀፈው በኋላ እግዚአብሔርን እየባረከ "ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት #ያዘጋጀኸውን #ማዳንህን አይተዋልና" (ሉቃስ 2:30-31) በሐሴት ተሞልቶ አወጀ። በእርግጥም ኢየሱስ እግዚአብሔር "በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀው ማዳን" ነበር። እግዚአብሔር ኢየሱስ የእርሱ "ማዳን" እንደሆነ አስታውቆዋል።
እግዚአብሔር "ለሰው ሁሉ ያዘጋጀው ማዳን" ኢየሱስ መሆኑን በማስታወቅ ብቻ አላበቃም "ጽድቁንም በአሕዛብ ፊት ገለጠ።" ይህ የሆነው መቼ ነበር? " ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን። እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።
ኢየሱስም መልሶ። አሁንስ ፍቀድልኝ፤ #እንዲህ #ጽድቅን #ሁሉ #መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።" (ማቴዎስ 3:13-15)
ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቅ የፈለገበት ምክንያት "ጽድቅን ሁሉ መፈጸም" እንደሆነ ተናግሯል። ኢየሱስ "ጻድቅ" ስለሆነ ጽድቅ አያስፈልገውም። (1ኛ ዮሐንስ 1:9፤ 1ኛ ዮሐንስ 3:7) ጽድቅ የሚያስፈልጋቸው ሐጢአተኞች ናቸው። "ለማይሰራ #ሐጢአተኛውንም #በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።" (ሮሜ 4:5) ኢየሱስ "ጽድቅን ሁሉ" የፈጸመው ለሐጢአተኞች ነው። እግዚአብሔር "በአሕዛብ ፊት ጽድቁን ገለጠ" የተባለው የመዝሙረ ዳዊት ትንቢት የተፈጸመው ኢየሱስ "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" በተጠመቀ ጊዜ ነበር። ያኔ ሰማያት ተከፈቱ፤ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ ወረደ፤ እግዚአብሔርም ኢየሱስ "ደስ የሚሰኝበት የሚወደው ልጁ" መሆኑን አወጀ። (ማቴዎስ 3:16-17)
"አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት #የእግዚአብሔር #ጽድቅ ያለ ሕግ #ተገልጦአል"
(ሮሜ 3:21) ይህ የእግዚአብሔር "ጽድቅ" ሌላ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (1ኛ ቆሮንቶስ 1:30-31) የተገለጠውም መስቀል ላይ ሳይሆን "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" በተጠመቀ ጊዜ ነበር። በዚህም እኛ ሐጢአተኞች በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ሐጢአት ያላወቀው እርሱ ስለ እኛ ሐጢአት ሆነ። (2 ቆሮ: 5:21) ኢየሱስ በጥምቀቱ "ጽድቅን ሁሉ መፈጸሙ" የእግዚአብሔር የደህንነት ዕቅድ ክፍል ነው። የእግዚአብሔርን "ማዳንና ጽድቅ" ሳያምኑ ደህንነት አይኖርም።
ኢሳይያስ 45 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝¹⁴ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የግብፅ ሀብትና የኢትዮጵያ ንግድ፣ ቁመተ ረጃጅሞቹ የሳባ ሰዎች፣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ የአንተ ይሆናሉ፤ ከኋላ ይከተሉሃል፤ በሰንሰለትም ታስረው ወደ አንተ በመምጣት፣ በፊትህ እየሰገዱ፣ ‘በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ብለው ይለምኑሃል።”
…
¹⁶ ጣዖት ሠሪዎች ሁሉ ያፍራሉ፤ ይቀላሉ፤ በአንድነት ይዋረዳሉ።
…
¹⁹ በጨለማ ምድር፣ በምስጢር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብም ዘር፣ “በከንቱ ፈልጉኝ” አላልሁም። እኔ እግዚአብሔር እውነትን እናገራለሁ፤ ትክክለኛውንም ነገር ዐውጃለው።’
²⁰ “በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንት ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።
²¹ ጒዳያችሁን ተናገሩ፤ አቅርቡ፤ ተሰብስበውም ይማከሩ። ይህን አስቀድሞ ማን ዐወጀ? ከጥንትስ ማን ተናገረ? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ጻድቅና አዳኝ የሆነ አምላክ፣ ከእኔ በቀር ማንም የለም፤ ከእኔ ሌላ አምላክ የለም።
²² “እናንት የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔ አምላክ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና፤ ትድኑ ዘንድ ወደ እኔ ተመለሱ።
²³ ጒልበት ሁሉ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ አንደበትም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ ብዬ በራሴ ምያለሁ፤ የማይታጠፍ ቃል፣ ከአፌ በጽድቅ ወጥቶአል።❞
ፍቅር ማለት ለኔ ኢየሱስ የሰው ልጆችን ከሐጢአት ለማዳን በዮርዳኖስ ወንዝ የፈጸመው ጽድቅና በመስቀል ላይ በመሞት የሰራው የደህንነት ስራ ነው። ይህ ፍቅር ነው እኔን የእግዚአብሔር ልጅ ያደረገኝ። ለዘለዓለም ጻድቅ እንድሆን በጽድቁ የለወጠኝ።
@jonahnlm
ነገ እሁድ ጥር 09 , ከጠዋቱ 04:00 - 08:00
☁️☁️☁️ከደመናው በታች☁️☁️☁️
👑👑👑👑የክብር ወቅት👑👑👑👑👑
💎 “ወንድሞች ሆይ፤ አባቶቻችን ሁሉ
ከደመናው በታች
እንደ ነበሩና በባሕሩ ውስጥ እንደ ተሻገሩ
ታውቁ ዘንድ እፈልጋለሁ።” 📖
(1ቆሮ10፥1)
ኑ የእግዚአብሔርን ክብር የመለማመድ (Experience) እና የመግለጥ ተከታታይ ፕሮግራም አለንና ጋብዘናችኋል!
👉 Come and Share
LIFE UNDER THE CLOUD OF GLORY!
አድራሻ: አዲስ አበባ 22
ለበለጠ መረጃ +251920340130
#የእግዚአብሔር_ቤተሰብ_ቤተክርስቲያን
"እግዚአብሔር ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ።" (ክፍል 1)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የእግዚአብሔር ማዳንና ጽድቁ የመዝሙረኛው ተደጋጋሚ ርዕሰ ጉዳይ መሆኑን ለማወቅ የጻፋቸውን ሌሎች መዝሙሮች መመልከት በቂ ነው። እንደ ዳዊት ያሉ እግዚአብሔር በደምብ የገባቸው የእምነት ባለቤቶች መፈ"ማዳኑንና ጽድቁን" ለአፍታም አልዘነጉም። የእምነታቸው መሠረት ይህ ነበር። ተስፋቸው በዚህ እውነት ላይ የተመሠረተ ነበር። መልዕክታቸው ይኸው ነበር።
ዳዊት ያጣጣመው ይህ የእግዚአብሔር "ማዳንና ጽድቅ" ሌሎች እንዲታወቅና እንዲገለጥ ተመኝቷል። አርቆ በመመልከትም እንዲህ አለ። "እግዚአብሔር #ማዳኑን #አስታወቀ፤ በአሕዛብም ፊት #ጽድቁን #ገለጠ።" (መዝሙረ ዳዊት 98:2) ይህ ትንቢት በአዲስ ኪዳን ሳይዛነፍ ፍጻሜውን ማግኘቱ አስገራሚ ነው። እግዚአብሔር በመጀመሪያ በአዲስ ኪዳን ያስታወቀው "ማዳኑን" ነበር። ከዚያ አስከትሎ ደግሞ "ጽድቁን "ገለጠ።"
"ዓይኖቼ #በሰዎች #ሁሉ ፊት #ያዘጋጀኸውን #ማዳንህን አይተዋልና።" (ሉቃስ 2:30-31) ይህንን የተናገረው "ጻድቁ ትጉሁና መንፈስ ቅዱስ የሞላበት" ስምዖን ነበር። (ሉቃስ 2:25) አጥማቂው ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀት እያጠመቀ በመጣ ጊዜ አስቀድሞ በኢሳይያስ የተጻፈው ትንቢት ወደ ፍጻሜ መምጣቱን ሉቃስ እንዲህ በማለት አረጋግጦ ነበር። "...ስጋን የለበሰ ሁሉ #የእግዚአብሄርን #ማዳን #ይይ ተብሎ እንደተጻፈ..." (ሉቃስ 3:6)
ከእነዚህ ሁለት ጥቅሶች መረዳት እንደሚቻለው "የእግዚአብሔር ማዳን" ሌላ ሳይሆን "ሕዝቡን ከሐጢአታቸው ለማዳን" የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (ማቴዎስ 1:21) እግዚአብሔር "ማዳኑን" በሌሊት መንጎቻቸውን ይጠብቁ ለነበሩት እረኞች "ሲያስታውቃቸው" የምስራቹ የተበሰረላቸው እንዲህ ነበር። "ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድሃኒት እርሱም #ክርስቶስ #ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል።" (ሉቃስ 2:11) ከዚህም መረዳት የሚቻለው "የእግዚአብሔር ማዳን" "መድሃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ ነው"
ኢየሱስ "የእግዚአብሔር ማዳን" ሆኖ በመወለድ "#ሐጢአተኞችን #ሊያድን ወደ አለም መጣ" (1ኛ ጢሞቴዎስ 15) ኢየሱስ የመጣበት ዋናውና ብቸኛው አላማ "#የጠፋውን #ሊፈልግና #ሊያድን" ነው። (ሉቃስ 19:10) የሰው ዘር በሐጢአት ምክንያት ጠፍቶዋል። የሐጢአት ባርያ ሆኖዋል። ራሱን ፈልጎ ማግኘትም ሆነ ማዳን አልቻለም። እግዚአብሔር "ማዳኑን" ኢየሱስን ወደዚህ አለም የላከው በሐጢአት ምክንያት የጠፋውን ለመፈለግና ለማዳን ነው።
እግዚአብሔር "ማዳኑን" አስታውቆዋል። ያም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እግዚአብሔር ካስታወቀው ከዚህ "ማዳኑ" ውጪ ሌላው "ማዳን" ሁሉ የተጭበረበረና የሰይጣን ማታለያ ነው።
ይቀጥላል....
የክርስቶስ ተቃዋሚ ማለት ምን ማለት ነው?
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ኢየሱስ የተናገራቸውን ቃሎችና ያደረጋቸውን የጽድቅ ስራዎች በሙሉ የሚቃወም ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው?
👉ኢየሱስ "ሐጢአትን ለማስወገድ መገለጡን" (1ኛ ዮሐ፡ 3:5;ማቴ፡ 1:21) የሚቃወም ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
👉ኢየሱስ "ጽድቅን ሁሉ ለመፈፀም" መጠመቁን (ማቴ፡ 3:15) የሚቃወም ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
👉 ኢየሱስ የሐጢአት ይቅርታን ወይም የሐጢአት ስርየትን ለመስጠት ደሙን ማፍሰሱን (ማቴ፡ 26:28;ኤፌ፡ 1:7;1ኛ ዮሐ፡ 2:2) የሚቃወም የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
👉 ኢየሱስ አዲስ ህይወትን ለመስጠት ከሙታን እንደተነሳ የሚቃወም ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡ (ሮሜ 6:5)
👉 ኢየሱስ በውሃ÷በደምና በመንፈስ እንደመጣ የሚቃወም ሰው (1ኛ ዮሐ፡ 5:6-10) የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
👉 ኢየሱስ ሰው ዳግመኛ የሚወለደው "ከውሃና ከመንፈስ" መሆኑን መናገሩን (ዮሐ፡ 3:3,5) የሚቃወም ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
👉 ኢየሱስ "ሐጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኃላ" በግርማው ቀኝ መቀመጡን (ዕብ፡ 1:3) እየካደ ሐጢአትን በንስሐ ጸሎት ለማስወገድ የሚጥር ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
👉 ኢየሱስ "ጥበብ ቅድስና ቤዛነትና ጽድቅ" ሆኖ ሳለ (1ኛ ቆሮ፡ 1:31) ሕግን በመጠበቅ ለመጽደቅና ለመቀደስ የሚጥር ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
👉 ኢየሱስ በስጋ እንደመጣ የማያምን ሰው (1ኛ ዮሐ፡ 4:3) የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
👉 ኢየሱስ ስለ ሰው ሐጢአተኛ ማንነት የተናገረውን የማያምን (ማር፡ 7:21-23) ነገር ግን ራሱን ጻድቅ አድርጎ የሚቆጥር ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
ን ሲትገነባ ኃጢአት አልሰራም ዝሙት አይመጥነኝም ስርቆት ንክኪ የለብኝም እያልክ ራስህን ታስታለህ❓
👉 እውነት እውነት እልሃለሁ፦ የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል ካላገኘህና ካላመንክ ከዘላለም እስከ ለዘላለም በገሃነም እሳት ትቃጠላለህ፤ወደ ሲኦል ትጣላለህ። ቶሎ ሳይረፍድብህ የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማመን ዳን‼ አዋጅ❗
በኢየሱስ ስም
~~~~~~~
"በኢየሱስ ስም" ማለት ምን ማለት ነው❓ ይህ ትርጉምና መገለጥ ያለው ቃል መሆኑን ያስተዋለው ስንቱ ነው? የዓለማውያን ክርስቲያኖች በሁሉም ነገሮቻቸው በኢየሱስ ስም ሲሉ አዘውትረን የሚንሰማው ነው።
ግን በኢየሱስ ስም የሚሉት ገብቷቸው ይሆን? ብለን ሲንመለከት፣ ፈጽሞ ገብቷቸው እንዳልሆነ እናያለን። ይልቁንም ሁላቸውም በሰይጣን ፍርሃት ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ስላሉ ቦቅቧቃነታቸውን መግለጻቸውን ወይም ሰይጣን በእርግጠኝነት በተጨባጭ ገዝቷቸው እየተጫወተ መሆኑን እናያለን።
.
በርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ፦ “እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ #በኢየሱስ_ስም አድርጉት።”(ቆላ3፥17) ይላል። እርሱም ኢየሱስም በአፉ፦ "እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር #በስሜ_የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። #ማናቸውንም_ነገር #በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።(ዮሐ14፥13-14) “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።”(ዮሐ16፥23) አለ። እነኚህ ቃሎች የታመኑና እውነት ናቸው።
ነገር ግን ይህ ቃል እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና በቃ በኢየሱስ ስም፣ በየሱስ ስም፣ ስስስስስም . . . እያሉ መንቀጥቀጥ፣ መጮህ፣ መወራጨት ማለት ነው ብሎ ማመን በቃሉ መሰናከል ነው።
.
ክርስትና መገለጥ ነው‼
የእግዚአብሔር ቃል በሙሉ የመገለጥ ቃል ነው።
እግዚአብሔር ከአንድ ሰው የሚሻው፦ አንድ ሰው የቃሉን መገለጥ ይረዳና ያገኝ ዘንድ ነው። ምክንያቱም፦ “የእግዚአብሔር ክብር ነገርን መሰወር ነው፤ የነገሥታት ክብር ግን ነገርን መመርመር ነው።” ተብሎ ተጽፏልና(ምሳ25፥2)።
.
ስለዚህ <<በኢየሱስ ስም>> ማለት ምን ማለት ነው? የሚለውን ለመረዳት <<ኢየሱስ>> የሚለውን የስሙን ትርጉም ማወቁ ለጥያቄው በቂ ምላሽ ይሆናል።
<<ኢየሱስ>> የሚለው ቃል የግርክ ቃል ነው። ወደ አማርኛው ሲናመጣው <<አዳኝ>> ማለት ነው።
<<ኢየሱስ>> የሚለውን ስም ያወጣው የጌታ መልአክ እንዲህ ብሎ ነው፦ “ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን #ከኃጢአታቸው_ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” ብሎ ነው ያወጣው(ማቴ1፥21)።
በዚህ ቃል መሰረት <<ኢየሱስ>> ማለት ምን ማለት እንደሆነ? በግልጽ እየታየ ነው። ስለዚህም "ኢየሱስ" ማለት ትክክለኛው የስሙ ትርጉም <<ሰውን ከኃጢአት የሚያድን>> ማለት ነው። ኢየሱስ ማለት <<እግዚአብሔር መድኃኒት/አዳኝ>> ማለት ነው። ኢየሱስ ሰውን የሚያድነው #ከኃጢአት ነው‼ አንድ ሰው ይህንን እውነት በትክክል ሳያስተውልና ሳያውቅ <<በኢየሱስ ስም>> እያለ ምንም ያህል ቢጠራውም #ስሙን_በከንቱ_ጠራው እንጂ ሌላ ምንም አላደረገም። በሌላ በኩልም <<የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አትጥራ!>> የሚለውን ትዕዛዝ እንደመጣስም ይሆናል።
በላይኛው፦ “አብም ስለ #ወልድ_እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።”(ዮሐ14፥13) "እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ . . . "(ቆላ3፥17) ተብሏል።
እግዚአብሔር አብ ከአንድ ሰው ክብርን የሚያገኘው መቼ ነው❓ አንድ ሰው ከኃጢአቱ ሲድን ነው።
አንድ ሰው ከኃጢአቱ የሚድነው መቼ ነው? ኢየሱስን ባመነበት ቅጽበቱ ነው።
አንድ ሰው ሲድን ከመች መች ኃጢአቱ ይድናል❓ ከውርስ ኃጢአቱ፣ ካለፈው ኃጢአቱና ገና ወደፊትም እስከለተ ሞቱ ከሚሰራው ኃጢአቱ ሁሉ አንድ ጊዜ ድኖ ለዘለዓለም ይቀራል ማለት ነው።
አብ በወልድ የተከበረው ለዚህ ነው። አብ ወልድን ወደ ዓለም የላከው ሰዎችን በሙሉ በአንድ ጊዜ ከኃጢአታቸው ለማዳን ነው።(ዮሐ3፥16)
እግዚአብሔርና ሰው በኃጢአት ምክንያት ተጣልተው ነበረ፤ ይህንን ጥላቸውን ከመሀላቸው ለማስወገድ ከዘላለም እስከዘላለሙ ቃል ሆኖ የነበረው አምላክ(ዮሐ1፥1) በሥጋ መጣና(ዮሐ1፥14፤ 1ዮሐ4፥2) የጥል ግድግዳን በሥጋው አፈረሰ።(ኤፌ2፥15)
እግዚአብሔርና ሰው በኃጢአት ምክንያት ለዘላለሙ ላይገናኝ ተቋርጦና ተለያይቶ ነበረ፤ነገር ግን በሰው ላይ ለእግዚአብሔር ጥልቅ ፍቅር ስለነበረው እግዚአብሔር የገዛ ልጁን ለዓለም(ለህዝቡ) ኃጢአት አሳልፎ ሰጠና እርቅን ፈጸመ።
“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤”(1ኛጢሞ2፥5) ተብሎ እንደተጻፈ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል አስታራቂ ሆኖ በመገኘት ሰውንና እግዚአብሔርን አስታረቀ።
.
ስለዚህ <<በኢየሱስ ስም>> ማለት ወይም <<በስሙ እግዚአብሔርን መለመን>> ማለት ትክክለኛው ትርጉሙ፦ #በእግዚአብሔር_ፊት_ጻድቅ_ሆኖ_ተገኝቶ_መጸለይ_ማለት_ነው። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚችለው ኃጢአተኛ ሰው ሳይሆን ጻድቅ ሰው ነው። የእግዚአብሔርን ስም መጥራት የሚችለው እርኩስ ሰው ሳይሆን ቅዱስ ሰው ነው።
ታዲያ ሰው መጽደቅና መቀደስ የሚችለው ኃጢአት ባለመሥራት ነውን❓ አይደለም! ኢየሱስን በማመን ብቻ ነው።
አንድ ሰው በኢየሱስ አምኗል ማለት ጻድቅ ሆኗል፤ኃጢአት የለውም ማለት ነው።
አንድ ሰው በኢየሱስ አምኗል ማለት ቅዱስ ሆኗል ማለት ነው።
አንድ ሰው በኢየሱስ አምኗል ማለት በቀጥታ የራሱ የገዛው የእግዚአብሔር ልጅ ሆኗል ማለት ነው።
ስለዚህ በስሙ መለመን ሲባል፦ እዚህ ላይ ልመና ማለት አስፈላጊውን ነገር ጥየቃ ማለት ነው። አንድ ሰው ኢየሱስን ከማመኑ በፊት የእግዚአብሔር ልጅ አልነበረም። ኢየሱስን በሚያምንበት ጊዜ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ተወልዶ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል።(ዮሐ1፥12) ከዚህ በኋላ ይህ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነ ለሥጋውና ለነፍሱ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ነገር አባቱን መጠየቅ ይችላል፤ እርዳታን መጠየቅ ይችላል። በመሐላቸው አንዳች የሚለያቸው ነገር የለም ማለት ነው። ቀድሞ ለይቷቸው የነበረው ኃጢአት ነበረና ኢየሱስ አስወግደው።
.
ስለዚህ ኢየሱስ አብን በስሜ ለምኑት ማለቱ፦ በቀጥታ <<እግዚአብሔር አብ ሆይ በኢየሱስ ስም ስማን! ብላችሁ ጸልዩ>> ማለቱ ብቻ አይደለም። ዋናው ንግግሩ ይህ አይደለም።
<<ኢየሱስ>> የሚለው ስም ለሰው የተሰጠው፦ ሰዎች በእርሱ ከኃጢአታቸው ይፈወሱና ይድኑ ዘንድ ነው እንጂ ሰዎች በእርሱ ድግምት ጥንቆላ ይሰሩበት ዘንድ አይደለም።
ዛሬ ብዙ ክርስቲያን ተብየዎች፦ የኢየሱስን ስም ለዓለማዊ ክብር ስስታቸው መነገጃ አድርገው መጮሃቸውን በማየቴ በጣም አዝናለሁ። መንገድ ላይ፦ መኪና ፎቅ ሲያገኙ፣ ሚስት ባል ልጅ ሲመኙ፣ ሱሪ ጫማ ኮት መብል መጠጥና ማንኛውንም የሥጋዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሲሉ፣ በዓለም ላይ በሁሉም ነገር ታዋቂና ዝነኛ ለመሆን ሲሹ . . . . በኢየሱስ ስም እያሉ ይደጋግማሉ ይጠነቁላሉ።
ቃሉ ግን ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም የመጣበት ዓለማ ወይም የኢየሱስ ስም ተብሎ ስሙ የወጣበት ዓለማ ለዚህ ለምድራዊ ጉዳይ እንዳልነበረ እየተናገረ ነው። ነገር ግን እነዚህ አውቀው ይሁን ሳያውቁ የኢየሱስ ወዳጅ መስለው ጠላቱ የሆኑ ሰዎች ለምድራዊ ስስታቸው ብቻ ኢየሱስን ይከተሉታል።
ኢየሱስ የሚባለው ስም ለሰዎች የተሰጠው ሰዎች በእርሱ #የኃጢአታቸውን_ስርየት_ያገኙ_ዘንድ_ነው። ቃሉም በግልጽ፦ “ #በስሙም ንስሐና #የኃጢአት_ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።”(ሉቃስ 24፥47) “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።”(ሐዋ10፥43) የሚለው ለዚህ ነው። አንድ ሰው የኃጢአትን ስርየት ማግኘት የሚችለው ኢየሱስን
#ክርስቶስ #ጽድቃችን--#የክርስቶስ #ጽድቅ #ጠቀሜታዎች (#ክፍል 3)
-----------------------------------------------------------------------------------
ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ ‹‹ጽድቅን ሁሉ መፈጸሙን›› ተመልክተናል፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) ኢየሱስ ‹‹ጽድቅን ሁሉ›› ከፈጸመ ያ ጽድቅ የራሱ የኢየሱስ ጽድቅ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ሁሉ ሐጢአትን ሰርተዋልና፤ የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎዋቸዋል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ›› (ሮሜ 6፡23-24) ይላል፡፡ ሐጢያትን የሰሩ ሁሉ በጸጋው መጽደቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሐጢያተኛው ጻድቅ መሆን የሚችለው ‹‹በክርስቶስ ቤዛነት በኩል በጸጋው›› በመጽደቅ ብቻ ነው፡፡
አሁን የክርስቶስን ጽድቅ ጠቀሜታዎች በዝርዝር እንመመልከት፡፡
1. የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ የሚያጸድቀው ጻድቃንን ሳይሆን ሐጢያተኞችን ነው፡፡ ይህ ጽድቅ ‹‹ሐጢአትን›› የሰሩትንና ‹‹የእግዚአብሄር ክብር›› የጎደላቸውን ሰዎች ‹‹በጸጋው በማጽደቅ›› ወደ እግዚአብሄር ክብር ይመልሳል፡፡
2. የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ‹‹በፊት የተደረገውን ሐጢአት በእግዚአብሄር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን›› የገለጠበት ነው፡፡ (ሮሜ 3፡25) ሐጢያትን የመተው የእግዚአብሄር ችሎታ የተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ነው፡፡ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ እግዚአብሄር ሐጢአትን የሚተውበት ችሎታ የለውም፡፡ ኢየሱስ ‹‹ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም›› በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲጠመቅ የተፈለገው እግዚአብሄር ሐጢያትን የመተው ችሎታ እንዳለው ለማሳየት ነው፡፡
3. የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ከቁጣ የምንድንበት ጽድቅ ነወ፡፡ ‹‹ይልቁንስ እንግዲህ አሁን #በደሙ #ከጸደቅን በእርሱ #ከቁጣው #እንድናለን፡፡›› (ሮሜ 5፡9) የእግዚአብሄር ቁጣ የሚወርደው በሐጢያተኞች ላይ ነው፡፡ ‹‹እውነትን በዓመጻ በሚከለክሉ ሰዎች #በሐጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ #የእግዚአብሄር #ቁጣ ከሰማይ #ይገለጣልና፡፡›› (ሮሜ 1፡18) ከእግዚአብሄር ቁጣ ለመዳን ‹‹መጽደቅ›› (ሐጢአት አልባ) መሆን ያስፈልጋል፡፡
4. የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ሕይወትን ያጸድቃል፡፡ ‹‹እንዲሁም #በአንድ #ጽድቅ ምክንያት ስጦታው #ሕይወትን #ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ፡፡›› (ሮሜ 5፡18) ‹‹አንድ ጽድቅ›› የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥማቂው ዮሐንስ ሲጠመቅ ‹‹ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› (ማቴዎስ 3፡15) በማለት የፈጸመው ጽድቅ ነው፡፡ ሕይወትን የሚያጸድቀውም ጽድቅ ይህ ነው፡፡
ኢየሱስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡31 ላይ ከተሰጡት ማዕረጎች አንዱ ለእኛ ከእግዚአብሄር ዘንድ ‹‹ጽድቅ›› የተደረገልን መሆኑ ነው፡፡ ከእነዚህ የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ጠቀሜታዎች መጉደል ሐጢያተኛ ሆኖ ኖሮ ሐጢያተኛ ሆኖ መሞት ነው፡፡ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ደህንነት የለም፡፡
ይቀጥላል…
4 ተከታታይ እሁዶች #ከደመና_በታች በሚል የተዘጋጀ የክብር ኮንፍረንስ
💎 “ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።” 📖
— ዘዳግም 33፥26
🔥እግዚአብሔር እናንተን ለመርዳት በደመናት ላይ ይራመዳል!
"ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።”
— ናሆም 1፥3
#CloudsAreTheDustOfHisFeet!!!
ዘወትር እሁድ እና ሐሙስ ከጠዋቱ 04:00 - 08:00
👉 ኑ አብራችሁን ሕያው እግዚአብሔርን በማምለክ እና በህያው ቃል፣ በጸሎት፣ በትንቢት፣ በፈውስ እና በነጻ መውጣት በግል ህይወታችሁ ክብሩን ተለማመዱ!
👑 የእግዚአብሔር ቅባት: የክርስቶስን ስራ በህይወታችን የሚገልጥ የእግዚአብሔር አቅም ነው!!!
በእግዚአብሔር ቤተሰብ ቤተክርስቲያን!
ሰላም ሰላም የተወደዳችው የጌታ ቤተሰቦች 👋👋👋 ሰላማችው ይብዛ!! በአዳማ አማኑኤል ባፕቲስት ቤተክርስቲያንነገ በ11,5,2013ዓ,ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ የወጣቶች የፀሎት ጊዜ ስለሚኖረን ትካፈሉ ዘንድ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን። እንዳያመልጦት
መቅረት አይቻልም😐
ኢየሱስ የተጠመቀው ለትዕትና አይደለም።
ኢየሱስ የተጠመቀው ሰዎችን ከኃጢአት ለማዳን ነው።
"ጥምቀትና ከኃጢአት መዳንን ምን አገናኘው?"
ትለኝ ይሆናል።
ወዳጄ የገዛ ሃሳብህን በቃሉ እንድትፈትሽ መክርሃለው።
ቃሉ እንዲህ ይላል:- " ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥"(1ኛጴጥ3:21)
ስለዚህ የሚያድን ጥምቀት አለ ማለት ነው።
ሰው በማንኛውም ተግባሩ ከኃጢአት መዳን እንደማይችል መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
( ኤፌሶን 2)
"8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9፣ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።"
ስለዚህ ይህ የያድናል የተባልነው ጥምቀት አማኞች በስመአብ ወ ወልድ ወመንፈስቅዱስ ብለው የሚጠመቁበት ወይም በኢየሱስ ስም ብለው የሚጠመቁበት ጥምቀት አይደለም ማለት ነው።
አንድ ሰው እኔ በምጠመቀው ጥምቀት ከኃጢአት ድናለሁ ካለ በስራዬ ድናለው እያለ ነው። ሰው ደግሞ በስራው እንደማይድን ቃሉ ግልጽ አድርጓል።
ታዲያ ይህ የሚያድነው ጥምቀት የማን ጥምቀት ነው?
የኢየሱስ ጥምቀት ነው። አዎ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት በእርግጥም ከኃጢአት ሁሉ ያድናል።
ኢየሱስ ለመሰንድነው የተጠመቀው? የዮሐንስ ጥምቀት ዓላማውስ ምንድነው?
የዮሐንስ ጥምቀት የንስሀ ጥምቀት ነው።ሲጠመቁ የነበሩትም ኃጢአተኞች ለንስሃ ነበር። ሁሉም ከተጠመቁ በኋላ ግን ኃጢአት የሌለበት ኢየሱስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።
ይህንን ያየው አጥማቂው ዮሐንስም ንስሃ የማያስፈልገው ኢየሱስ ሊጠመቅ መምጣቱን አይቶ ይከለክለው ጀመር። ያኔ ጌታ ኢየሱስ እርሱ የሚጠመቀው ለሰው ዘር ሁሉ ጽድቅን ለመፈጸም እንደሆነ ተናገረ።
(የማቴዎስ ወንጌል 3)
"13፤ ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።14፤ ዮሐንስ ግን። እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።15፤ ኢየሱስም መልሶ። አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።"
ኢየሱስ ጻድቅ አምላክ ነው። ጽድቅን የፈጸመው ለራሱ ሳይሆን ለሰው ዘር ሁሉ ነው። ጽድቅን መፈጸም ማለት ሰዎች ጻድቅ የሚሆኑበትን(ከኃጢአት የሚነጹቀትን) ስራ መስራት ማለት ነው።
ኢየሱስ የተጠመቀው የሊቀ ካህኑ የአሮን ዘር በሆነው በአጥማቂው በዮሐንስ እጆችን በመጫን ስርዓት ነው።
ዓለምን ከኃጢአት ለማዳን ሊሰዋ የመጣውና
የእግዚአብሔር በግ የሆነው ኢየሱስ በራሱ ላይ እጆች የተጫኑበት ለምንድነው?
በመሥዋህቱ እንስሳ ላይ በብሉይ ኪዳን ጊዜ እጆች የሚጫኑት ለምንድነው?
please visit www.bjnewlife.org
ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ❓
-----------------------------------------------------------------------------------------------
ከዓለም ሰዎች ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ትርጉምና ምስጢር ተሰውሮባቸዋል። ፈጽሞ አያውቁም። በዚህ በኢየሱስ ጥምቀት የማያምን ማንም ሰው ወደ ገሃነም እሳት ይጣላል።
ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ❓ መልሱን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ኢየሱስም መልሶ፦ #አሁንስ_ፍቀድልኝ_እንዲህ_ጽድቅን_ሁሉ_መፈጸም #ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።"
(የማቴዎስ ወንጌል 3: 15)
👉 ኢየሱስ በጥምቀቱ የፈጸመው ጽድቅ ምንድነው❓ " #በሕግና_በነቢያት_የተመሰከረለት #የእግዚአብሔርን_ጽድቅ" ፈጸመ ማለት ነው።(ሮሜ 3:21)
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ "በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦአል"(ሮሜ3:21)
.
በሕግና በነብያት ማለት ምን ማለት ነው❓
ሕግ ማለት የሙሴ መጽሐፍት ማለት ነው። ማለትም ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም ድረስ ያሉ ቃሎች።
ነብያት ጠቅላላው የትንቢት ቃሎች ማለት ነው።
.
ሕግና ነብያት ማለት ባጭሩ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ማለት ነው።
.
በሕግ መጽሐፍ ስርየት የሚፈጸመው
1ኛ. ነውር የለሽ እንስሳ ማዘጋጀት።
2ኛ. እጆችን በመጫን ኃጢአትን ማሸከም።
3ኛ. እንስሳውን መግደልና ደሙን ማፍሰስ ናቸው። (ዘሌዋውያን 1:1-4, 4:1-4, 16:21-22)
.
ኢየሱስ #ጽድቅን_ሁሉ ማለቱ፦
1ኛ. ዮሐንስ ራሱን ሲይዝ(ሲጭን) የዓለምን ኃጢአት ተቀበለ።
2ኛ. ውኃ ውስጥ ሲገባ ለዓለም ኃጢአት ሞተ(የመስቀል ሞቱን ገለጠ)።
3ኛ. ከውኃ መውጣቱ እሱ ከሞት መነሳቱን ገላጭ ነው።
ይህ ማለት ነው ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ማለት። በሕግና በነቢያት ተብሎ እንደተጻፈው ከነቢያቱ ባንዱ በኢሳይያስ መጽሐፍ እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖሬ ተብሎ የተጻፈው በጥምቀቱ ተፈጸመ። እግዚአብሔር በዮሐንስ አማካኝነት ኃጢአታችንን በሙሉ በልጁ ላይ አኑሯል። ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ እኛና ኢየሱስ ተለዋውጠናል፤እርሱ የእኛን ኃጢአት ወስዶ ኃጢአት ሲሆንብን እኛ የእርሱ ጽድቅ ሆነናል።(2ኛቆሮ5:21)
.
ብሉይ ኪዳን ለአዲስ ኪዳን ጥላ ስለሆነ(ዕብ10:1) በኢየሱስ ጥምቀት በኢየሱስ ስቅለትና በኢየሱስ ትንሳኤ ተፈጸመ ማለት ነው።
.
ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ❓ ለሚለው ጥያቄ ዋና መልሱ #የዓለምን_ኃጢአት_ሙሉ_በሙሉ_በሥጋው_ለመሸከም_ተጠመቀ ማለት ነው። ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የእኛ ኃጢአት ሁሉ ወደ ኢየሱስ ሄዷል፤በኢየሱስ ሥጋ ላይ ተጭኗል ማለት ነው።
ኢየሱስ ለምን ሞተ❓ ኃጢአታችንን በሥጋው ስለተሸከመ የኃጢአትን ደመወዝ ለመክፈል ነው።
ኢየሱስ ለምን ከሞት ተነሳ❓ ለእኛ አዲስ ሕይወት ለመስጠት ነው። So we have got new life Hallelujah.
ስለዚህ ለእኛ አሁን ኃጢአት የለም፤ዕዳም የለም፤ ነጻ ነን። ጻድቅ ነን። ቅዱስ ነን። ፍጹም ነን። የእግዚአብሔር ልጅ ነን ማለት ነው።
ሃሌሉያ!!!
.
ስለዚህ በኢየሱስ ጥምቀት የማያምን ማንም ሰው ኃጢአቱ በእርሱ ላይ ይቀራል እንጂ ከኃጢአቱ አይላቀቅም። ከኃጢአቱ አልተላቀቀም ማለት ወደ ሲኦል ይገባል ማለት ነው።
.
ይህንን ምስጢር ላስወቀንና እውነቱን ለገለጠን ላዳነን ላጸደቀንና ወደ እውነቱ መንገድ ለመራን ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን። ሃሌሉያ!!!
.
የኢየሱስን ጥምቀት የሚያሰረዱ በተከታታይ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መጽሐፍትን ለማግኘት፦
👉 Join t.me/tobebornagain
Or
👉 Visit www.bjnewlife.org
የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው። ሁለም ያወራኛል። ይመክረኛል። ያጽናናኛል። ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭ ይመራኛል ምክንያቱም በኢየሱስ ጥምቀትና ሞት የሐጢአትን ስርየት ለአንደ ተቀብያለሁና።
@jonahnlm
በኢየሱስ ማመን ማለት ለዘለዓለም ጻድቅ መሆን ማለት ነው። በኢየሱስ እያመንኩንም ሐጢአት ካለብኝ ገና አልዳንኩም ማለት ነው። ስለዚህ ሐጢአት ያለበት ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት አይቻለውም።
@jonahnlm
hello everyone!!
👩💻1k direct YouTube subscribers 500 br
🧑💻2.5k direct YouTube subscribers 1200br
👨💻4k direct YouTube subscribers 2000br
🧣Free bonus
1k sub 200 free bonus
2.5k sub 400 free bonus
4k sub 600 free bonus
All subscription takes 1 week.
Contact us @sutafee
#እንደተናገራችሁ_ይሆናልና_በእግዚአብሔር_ላይ_ባላችሁ_እምነት_በርቱ!
📖 “ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ፥ አይዞአችሁ፤
እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን
እግዚአብሔርን አምናለሁና።” 💎
ሐዋርያት 27፥25
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
የኢየሱስ ጥያቄ
==========
ኢየሱስ የመጨረሻውን የኢየሩሳሌም ጉዞ ካደረገ በኋላ እውርና አንካሶችን ሲፈውስ፤ቤተ መቅደሱን ሲያጠራ፣ እንደ ባለ ስልጣን ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች አይተው
በምን ሥልጣን እየሰራ እንዳለ ጠየቁት። ክፍሉን እናንብብ።
(የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 11)
----------
27፤ ደግሞም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። እርሱም በመቅደስ ሲመላለስ፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጥተው።
28፤ እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ወይስ እነዚህን ለማድረግ ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።
29፤ ኢየሱስም። እኔም አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፥ እናንተም መልሱልኝ፥ እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ።
30፤ የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው? መልሱልኝ አላቸው።
31፤ እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ። ከሰማይ ነው ብንል። እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤
32፤ ነገር ግን። ከሰው ነው እንበልን? አሉ፤ ሁሉ ዮሐንስን በእውነት እንደ ነቢይ ያዩት ነበርና ሕዝቡን ፈሩ።
33፤ ለኢየሱስም መልሰው። አናውቅም አሉት ኢየሱስም። እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው።"
ከላይ በርዕሴ የኢየሱስ ጥያቄ ብዬ ያልኩት፤ኢየሱስ ለተነሳበት የሥልጣን ምንጭህን ንገረን ጥያቄ፣ምላሽ ለመስጠት ያነሳውን ጥያቄ ነው።
"የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረች ወይስ ከሰው?"
ጌታ ኢየሱስ የስልጣን ምንጭህ ማን ነው? ከየት ነው?
ለሚለው ጥያቄ በቀጥታ "ከእግዚአብሔር ነው" ብሎ ከመመለስ ይልቅ የዮሐንስን ጥምቀት የጠቀሰው ለምንድነው?
ከላይ እንዳነበብነው እነዚህ ሰዎች በዮሐንስ ጥምቀት አያምኑም። ተመሳሳይ ሃሳብ በተነሳበት በማቴዎስ ወንጌል ላይ ጌታ ኢየሱስ የዮሐንስ ጥምቀት ሰዎች የሚጸድቁበት መንገድ መሆኑን በግልጽ ጠቅሶ፤ አይማኖተኞችን ባለማመናቸው ሲወቅሳቸው እናነባለን።
" ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ መጥቶላችሁ ነበርና፥ አላመናችሁበትም፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች ግን አመኑበት፤ እናንተም ይህን አይታችሁ ታምኑበት ዘንድ በኋላ ንስሐ አልገባችሁም።" (ማቴ 21:32)
የዮሐንስ ጥምቀት ዓላማ ምንድን ነው?
1.የዮሐንስ ጥምቀት የንስሃ ጥምቀት ነው።(ማቴ3:11)
2.የዮሐንስ ጥምቀት #ጽድቅ_ሁሉ የተፈጸመበት ጥምቀት ነው።(ማቴ3:15)
በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት የሰው ልጅ ሁሉ፣ከእግዚአብሔር መንገድ የራቀ፣ የክፉ ዘር፣የኃጢአት ምንጭና ለሞትና ለገሃነም የታጨ ነው።
ይህ በክፉ መንጠድ ላይ ሆኖ ወደ ሲኦል እየገሰገሰ ያለ ሰው ስለኃጢአትና ስለኃጢአት ፍርድ ትክክለኛ ግንዛቤ በማግኘት ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለበት።
ንስሃ የሚባለው ይህ ነው። ከእግዚአብሔር የራቅን፣ዳግመኛ ያልተወለድን፣ በራሳችን ጎዳና እግዚአብሔር ያውቀናል ብለን ስንኳትን የኖርን ሰዎች መሆናችንን መቀበል እና ወደ እግዚአብሔር መመለስ። ወደ እግዚአብሔር የምንመለሰው እንዴት ነው? በእግዚአብሔር ጽድቅ በማመን ነው።
የእግዚአብሔር ጽድቅ ምንድነው?
መልሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት ውስጥ አለ።
ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ እጆችን በመጫን ስርዓት በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀው ለምንድነው?
ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ነው።
ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ማለት ምን ማለት ነው?
ልክ በብሉይ ኪዳን ጊዜ ሊቀ ካህኑ አሮን በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን የእስራኤልን ህዝብ ወክሎ በመስዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ሁለቱንም እጆቹን በመጫን የእስራኤልን የአመቱን በደል፣ኃጢአት እና መተላለፋቸውን በጠቦቱ ራስ ላይ እንደሚያሸክመው ሁሉ(ዘሌ16:21) የአሮን ዘርና የመጨረሻው ምድራዊው ሊቀ ካህን የሆነው አጥማቂው ዮሐንስ በእግዚአብሔር በግ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሁለቱንም እጆቹን ጭኖ በማጥመቅ የዓለምን ኃጢአት ወደ ክርስቶስ ሥጋ አስተላልፏል።
እግዚአብሔር በኢሳይያስ 53:6 ላይ የተናገረው የትንቢት ቃል በዮርዳኖሱ ወንዝ በዮሐንስ ጥምቀት ተፈጽሟል። ይህንን ያመነ(ጌታ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቅ የዓለምን ኃጢአት በሙሉ በስጋው መሸከሙን ያመነ) የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ መሆኑን አምኗል።
ይህን የማያውቅና የማያምን በጽድቅ መንገድ ላይ አይደለም። ስለዚህ ቶሎ በጽድቅ መንገድ የመጣውን ዮሐንስን እና የጽድቅ አገልግሎቱን ተረድተን በኢየሱስ በማመን ዳግመኛ እንወለድ።
እግዚአብሔርን እናክብር። ከጥፋት እንዳን።
ሻሎም!
በማመን ብቻ ነው። አንድ ሰው ኢየሱስን አምኗል ማለት ንስሐ ገብቷል ማለት ነው።
.
ኢየሱስ በስሜ እያለ ያለው የኃጢአትን ስርየት ማለቱ ነው። አንድ ሰው የኃጢአቱን ስርየት ካገኘ ያለምንም መሸማቀቅና ፍርሃት ወደ እግዚአብሔር ቀርቦ የፈለገውን ነገር ስጠኝ ብሎ ጠይቆ መውሰድ ይችላል ማለት ነው። ነገር ግን የኃጢአቱን ስርየት ያላገኘ ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ አንዳች ነገር አያገኝም። ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር ጥለኛ ነውና።
.
ለክርስቶስ፦ <<ኢየሱስ>> የሚባለው ስሙ የሰብዓዊው ስሙ ነው። ክርሰቶስ የሚለው ደግሞ የአገልግሎት ማዕረግ ስሙ ነው። "ኢየሱስ" ማለት "ከኃጢአት የሚያድን" ማለት ሲሆን <ክርስቶስ> ማለት ደግሞ <ነብይ ካህን ንጉስ> ማለት ነው። ባጭሩ <<ክርስቶስ>> ማለት የግርክ ቃል ሲሆን ወደ አማርኛው ሲንገለብጠው <<የተቀባው>> ማለት ነው። ኢየሱስ ለዚህ ዓለም ሕዝብ ነብይ ሆኖ፣ ካህን ሆኖና ንጉስ ሆኖ በእግዚአብሔር የተሾመ የተቀባ ነው። የሚገርመው፦ ኢየሱስን እግዚአብሔር የቀባው እርሱ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ከውኃ ከወጣ በኋላ ነው።(ማቴ3፥16፣ ሉቃ4፥1:18፣ ሐዋ10፥38) በኢየሱስ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ የወረደው ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ከወጣ በኋላ ነው። በኢየሱስ ላይ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል መውረዱና ኢየሱስ በኃይል መሞላቱ የሚያሳየው እርሱ መቀባቱን ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስን ቀባው ማለት እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ዓለምን ለማዳን ወስኗል ማለት ነው። ሰዎች ሁሉ ኢየሱስን በማመን ከአዳም ዝሪያነት ወደ ኢየሱስ ዝሪያነት ያልፋሉ።
.
ኢየሱስ ራሱ በማንነቱ እግዚአብሔር ነው። ኢየሱስ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከዘላለም እስከ ዘላለም ነበረ። አሁን ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ለማዳን ስለፈለገ ኢየሱስ የሚለውን ስያሜ ይዞ ሰው ሆኖ ተወለዶ ተገለጠና ኢየሱስ ተባለ። ኢየሱስ ከመወለዱ አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ክርሰቶስ ማለትም እስራኤልን የሚበዥ የእስራኤል ንጉሥ ይወለዳል ተብሎ ሲጠባበቅ ነበረና ኢየሱስ ሰው ሆኖ በተገለጠ ጊዜ ተፈጸመ።
.
ሐዋርያውያ ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች ሲጽፍላቸው፦ “እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።”(ቆላ3፥17) ሲል እዚህ ላይ በነ ጳውሎስ ዘመን አህዛቦች ማለትም አይሁድ ወይም እስራኤል ያልሆኑ ሕዝቦች ያን ያህል ብዙ ስለእግዚአብሔር ምስጢር ባያውቁም በተለይም የእግዚአብሔርን ምስጢር የሚያውቁ(የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆኑ) እስራኤላውያን ኢየሱስን እነርሱ ሲጠባበቁ የነበረው ክርስቶስ(መሲሑ) እርሱ እንደሆነ አልተቀበሉትም አላመኑትምም። ስለዚህ የዛነ የነበሩት ክርስቲያኖች፦ ማናቸውንም ነገር ሲያደርጉ በኢየሱስ ስም እያሉ ከአፋቸው ሲጠሩ ብዙ ድንቅና ተአምራቶች ሲደረግና ሲታይ ነበረ። የዚህ ምክንያቱ፦ የዛነ የነበሩት አይሁድ ኢየሱስን እርሱ ክርስቶስ ነው ብለው ስላልተቀበሉ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ለማሳመን በእርሱ ስም ብዙ ታምራትና ምልክት ማሳየት አስፈላጊ ነው።
እግዚአብሔር አብን በእርሱ ማመስገን ማለት፦ እግዚአብሔር አብ የአንድን ሰው ኃጢአቱን በእርሱ ስላስወገደ ዘወትር ለእርሱ ክብርን መስጠት ይገባል ማለት ነው። እውነተኛው ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን ዘውትር የሚያመሰግኑት ከእግዚአብሔር ዘንድ የኃጢአታቸውን ስርየት በማግኘታቸው ነው።
"በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ #በጌታ_በኢየሱስ_ስም አድርጉት።”(ቆላ3፥17) ለሚለው ዋናው መገለጥ ቃሉ፦ እዚህ ዓለም ላይ የመኖራችሁ ዓለማ ለዓለም ኢየሱስን ለመግለጥ ነው ማለት ነው። ኢየሱስን መግለጥ ማለት ለሰዎች የኃጢአትን ስርየት ወንጌል መስበክ ማለት ነው።
.
አሁን ዋናውና የዚህ ርዕስ መቋጫ የሆነው ጥያቄ፦ ኢየሱስን መቀበልና ማመን እርሱን መስበክ ማለት ምን ማለት ነው❓ የሚለው ነው።
ኢየሱስን መቀበል ማለት ኢየሱስን ተራ ሰው አድርጎ መመልከት ሳይሆን አምላክ አድርጎ ማመን ወይም ኢየሱስን አምላክ አድርጎ መቀበል ማለት ነው።
ኢየሱስን ማመን ማለት እርሱ ኢየሱስ ለኃጢአት የሚታረድ በግ ሆኖ መቅረቡን፣ በመጥምቁ ዮሐንስ ሲጠመቅ የዓለምን(የሕዝቡን) ኃጢአት በሙሉ መሸከሙን፣ በመስቀል ላይ ሲሞት የዓለምን ኃጢአት ኩነኔን መቀበሉንና ከሞትም በመነሳት ለሕዝቡ አዲስ ሕይወትን መስጠቱን ማመን ማለት ነው። በኢየሱስ ስም ማመን ማለት የኃጢአትን ስርየት መቀበል ማለት ነው።
ኢየሱስን ማመን ማለት እርሱ ኢየሱስ የሰራውንና የፈጸማቸውን የደኅንነቱን ሥራ ማመን ማለት ነው። እዚህ ጋር የደኅንነቱ ሥራ በተለይም #ጥምቀቱ #ሞቱና #ትንሳኤው ነው።(1ኛዮሐ5፥6-8) ከደኅንነቱ ሥራ አንዱን አጉድሎ ወይም ጨምሮ ማመን ከደኅንነት ውጭ መሆን ነው።
.
የዛሬይቱ ክርስትና ዓለም #የኢየሱስ_ክርስቶስን_ጥምቀት አያምንም። ኢየሱስ በጥምቀቱ ጽድቅን ሁሉ እንደፈጸመ(ማቴ3፥15) አያውቁም አያምኑምም።
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በተጠመቀ ጊዜ የዓለምን ኃጢአት እንደተሸከመ አያውቁም። ዮሐንስ የኢየሱስን ራስ በሁለቱ እጆቹ ጭኖ የዓለምን ኃጢአት ወደ ኢየሱስ ክርሰቶስ ሥጋ አስተላልፏል። የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በብሉይ ኪዳን ጊዜ ለኃጢአት ስርየት የሚታረደውን እንስሳ ራስ በሁለት እጆች ጭኖ ኃጢአትን በእንስሳው ራስ ላይ የማሸከሙ ጥላ ነበረ።(ዘሌ16፥21፣ ዕብ6፥1) ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ በራሱ ላይ ተሸክሟል።(ዮሐ1፥29) ይህንን የሚያምን ሰው ከእንግዲህ ወዲህ ጻድቅ ሰው ነው ኃጢአት አይኖረውም። ምክንያቱም ሁሉንም ኃጢአቱን ኢየሱስ ወስዶታልና። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተው በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ የዓለምን ኃጢአት በሥጋው ስለተሸከመ የዓለም ኃጢአት ደመወዝ ነው።
.
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ተገልጦ የፈጸመው #የውኃውንና_የመንፈሱን_ወንጌል ነው። ኢየሱስ ይህንን እውነት እንዲህ ብሎ መስክሯል፦ “ሰው #ከውኃና_ከመንፈስ_ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” በማለት(ዮሐ3፥5)። <<ውኃ>> የእርሱ <<ጥምቀቱ>> ሲሆን <<መንፈስ>> የእርሱ <<አምላክነቱ>> ነው። ስለዚህ አንድ ሰው በኢየሱስ ጥምቀትና በእርሱ አምላክነት ማለትም በእርሱ #አዳኝነትና_አምላክነት_ሲያምን #ዳግመኛ_ይወለዳል ማለት ነው። ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በማመን ብቻ ዳግም ይወለዳል የተባለው ለዚህ ነው።(1ኛጴጥ1፥23) (ያዕ1፥18) (ኤፌ5፥26) የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል ያላወቀ ማናቸውም ሰው እውነተኛውን የእግዚአብሔር የደኅንነቱን ወንጌል አላገኘም። የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል ይበልጥኑ ለመረዳት www.bjnewlife.org ን
ወይም
t.me/tobebornagain ንን ይጫኑ/ይጎበኙ። ወይም በ0926467275 / በ0916552361 ደውለው ነጻ የክርስቲያን መጽሐፍቶችን ማግኘት ይችላሉ።
.
ዛሬ ብዙ ሰዎች "በኢየሱስ ስም" ቢሉም #በስሙ_አያምኑም። የዚህ መግለጫቸው፦ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ሲሞክሩ አቤቱ ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ! ይቅር በለኝ! ማለታቸው ገና ያልዳኑና የኃጢአታቸውን ስርየት ያልተቀበሉ ስለመሆናቸው በቂ ማሳያ ነው። የኃጢአቱን ስርየት ያልተቀበለ ማናቸውም ሰው የኃጢአቱን ደመወዝ ይቀበላል።
በውኑ የኃጢአትህን ስርየት ተቀብለሃል❓
በትክክል በኢየሱስ ስም አምነሃል❓
አሁን ኃጢአተኛ ነህ ወይስ ጻድቅ ነህ❓
አሁን ምንም አንዳች ኃጢአት የለብህም❓
ወይስ ኃጢአት ስላልሰራህ ኃጢአት እንደሌለብህ ይሰማሃል❓
ወይስ የራስህን ግብዝነትህ
መዝሙር 112 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝¹ ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ የተባረከ ነው።
² ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
³ ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።❞