dehninet | Unsorted

Telegram-канал dehninet - 🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

-

እንዴት ዳግም መወለድ ይቻላል? እንዴት የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ይቻላል? ጽድቅ፣ቅድስና የኃጢአት ስርየት የሚገኘው በሂደት ነው ወይስ አንድ ጊዜ?

Subscribe to a channel

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

"#የሠርግ #ልብስ #ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?" (ክፍል 1)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ኢየሱስ በማቴዎስ 22 ላይ ያስተማረው ምሳሌያዊ ትምህርት ግሩም ያለው መንፈሳዊ እውነት ይዞዋል። ይህ ምሳሌያዊ ትምህርት አስረግጦ የሚናገረው ትልቁ ቁምነገር "የሠርግ ልብስ ሳይለብሱ" ወደ ንጉሱ ሠርግ መግባት መጨረሻው "በውጭ ወዳለው ጨለማ" መጣል ነው።

"መንግሥተ ሰማያት #ለልጁ #ሰርግ ያደረገ #ንጉሥን ትመስላለች።" (ማቴዎስ 22:2) በዚህ ምሳሌ ውስጥ ሰርጉን የደገሰው ንጉስ እግዚአብሔር ሲሆን ሰርጉ የተደገሰለት "ልጅ" ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሠርጉ "መንግስተ ሠማይ" ነው።

"የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ ሊመጡም አልወደዱም። ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ። የታደሙትን። እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፥ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፥ #ሁሉም #ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ በሉአቸው አለ።" (ማቴዎስ 22:3-4) ንጉሱ እግዚአብሔር ለልጁ ኢየሱስ ባዘጋጀው ሰርግ ላይ የሰው ዘር ሁሉ እንዲገኝ አድሞዋል። ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት የሚያስችለው ጥሪ (መታደም) ለሰው ሁሉ የተሰጠ ነው።

ንጉሱ እግዚአብሔር የልጁን የኢየሱስ ክርስቶስን ሠርግ በሚመለከት "ሁሉ ተዘጋጅቶአል" በማለት ከሰው የሚጠበቀው ጥሪውን መቀበልና በድግሱ ላይ መገኘት ብቻ ነው። እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ መንግስቱ የሚያስገባው ራሱ ባዘጋጀው ድግስ ብቻ ነው። "ሁሉ ተዘጋጅቶአል" ማለት ከእድምተኞቹ የሚፈለግ ምንም ስጦታ የለም ማለት ነው። እግዚአብሔር ወደ መንግስቱ የሚያስገባውን ደህንነት፣ ጽድቅ፣ ቅድስና፣ መንጻትና የመሳሰሉትን "ሁሉ አዘጋጅቶአል።" እግዚአብሔር አዘጋጅቶ ባጠናቀቀው ነገር ላይ መጨመር የንጉሱን የሠርግ ድግስ ከመናቅ አይተናነስም።

ሆኖም የታደሙት የራሳቸውን የተለያዩ ምክንያቶች በማቅረብ በድግሱ ላይ ለመገኘት አልወደዱም።
"እነርሱ ግን ቸል ብለው #አንዱ ወደ #እርሻው፥ ሌላውም ወደ #ንግዱ ሄደ፤ የቀሩትም #ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው #ገደሉአቸውም።" (ማቴዎስ 22:5-6) በንጉሱ ሠርግ ላይ ከመገኘት የበለጠባቸው የራሳቸው "ስራ" ነበር። ከዚያ አለፍ ሲልም ለንጉሱና ለሠርጉ ድግስ ያላቸውን ጥላቻ ለመግለጥ የንጉሱን "ባሮች" መግደል ነበር።

ወደ "እርሻቸውና" ወደ "ንግዳቸው" የሄዱት ታዳሚዎች በራሳቸው ጽድቅ የሚታመኑ የዘመኑን ሃይማኖተኞች ይጠቁማሉ። "ሁሉ ተዘጋጅቶ" በሚጠብቃቸው የንጉሱ ሰርግ ላይ መገኘትን የተጠየፉት "እርሻቸው" እና "ንግዳቸው" (የራስ ጽድቅ) ስለበለጠባቸው ነው።

እንቀጥላለን

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

"በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?" (ኤርምያስ 13:23)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

እንዲህ ያለ ነገር ታይቶ አይታወቅም። ኢትዮጵያዊ መልኩን የቀየረበት ነብርም ዝንጉርጉርነቱን የለወጠበት ታሪክ አላነበብኩም። የዘመኑ የፕላስቲክ ሰርጀሪ ቴክኖሎጂ ምናልባት ውጫዊ ገጽታን ይለውጥ እንደሆነ እንጂ ተፈጥሮን አይቀይርም። እግዚአብሔር ይህንን ማነጻጸሪያ ያቀረበው ምንን ለመግለጥ ነው? መልሱ በዚያው ቃለ ጥቅስ ውስጥ ተሠጥቶዋል። " በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ #ክፋትን #የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ #በጎ #ለማድረግ #ትችላላችሁ። " (ኤርምያስ 13:23

የሰው ዘር "በጎ ለማድረግ" የሚችለው "ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይም ነብር ዝንጉርጉርነቱን" መለወጥ ከቻለ ብቻ ነው። የሰው ዘር በተፈጥሮው "ክፉ" ስለሆነ (ኢሳይያስ 1:4፤ ማቴዎስ 7:11) ክፋትን ማድረግ ልምዱ ነው። ክፋትን ለማድረግ ትምህርት አያስፈልገውም። ጥናት ማድረግ አይጠበቅበትም። ልቡ በደርዘን ሐጢአት የተሞላ ነው። (ማርቆስ 7:21-23) ክፉ ከማሰብ ጀምሮ እስከ መግደል ድረስ የተካነ ነው።

"እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች
ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፤ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር ፤ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ። " (ምሳሌ 6:16-19) እነዚህ "እግዚአብሔር የሚጠላቸው" ሰባት ነገሮች የሰውን ተፈጥሮ ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው። ሰው ከላይ የተዘረዘረውን ከማድረግ አይቦዝንም። የስጋ ተፈጥሮውን በማቀብ፤ በመለጎም ወይም የስነ ምግባር ስልጠና በመውሰድ ከእነዚህ ሐጢአቶች ራሱን ነጻ ማድረግ አይችልም።

ሰው ከልብ ሐጢአት ነጻ መውጣት የሚችለው መጀመሪያ "ሐጢአተኛ" መሆኑን ሲያምና "በውሃና በደም" ወደመጣው (1ኛ ዮሐንስ 5:6) ኢየሱስ ዘወር ሲል ነው። ኢየሱስ ሐጢአቱን በሙሉ በጥምቀቱ እንደተሸከመለትና (ኢሳይያሰ 53:11-12፤ ማቴዎስ 3:15) በመስቀል ላይ የሐጢአቱን ዋጋ እንደከፈለለት ያመነ ያ ሰው "በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከሐጢአትና ከሞት ሕግ አርነት" ያወጣው ሰው ነው። (ሮሜ 8:2) "ኩነኔ" የለበትም። (ሮሜ 8:1) መንፈሱ ድኖዋል። የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ተቀብሎዋል። ሐጢአተኛ መሆኑን አምኖ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የተራበና የተጠማ ያ ሰው ኢየሱስ በሰራው የጽድቅ ስራ "ጸድቆ ወደ ቤቱ" ይገባል። (ሉቃስ 18:13-14)

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

ታጥባችኋል፥ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።" (ክፍል 3)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በክፍል 2 ላይ ከኤፌሶን 5:25-26 እና ከቲቶ 3:5 ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ላይ በመንተራስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 6:11 ላይ የተጠቀሰውን "ታጥባችኋል" የሚለውን ቃል ለማብራራት ሞክረናል። በኤፌሶን 5:25-26 ላይ የኢየሱስ ቤተክርስቲያን "#በውሃ #መታጠብና ከቃሉ ጋር" እንድትቀደስ ኢየሱስ ራሱን ስለ እርስዋ አሳልፎ እንደሰጠ አይተናል። በቲቶ 3:5 ላይ ደግሞ "ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በሚሆን መታደስ" እንደዳንን አይተናል። እዚህ ላይ "አዳነን" የሚለው ቃል "ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በሚሆን መታደስ" ውስጥ ያለ ደህንነት ሆኖ ቀርቦዋል። ከዚህ በመነሳት "ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብ" የማያምን ሰው ከደህንነት ውጪ መሆኑን መደምደም እንችላለን።

ዋናው ርዕሰ ጉዳያችን "ታጥባችኋል" የሚለው በመሆኑ "በውሃ መታጠብና" "ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብ" ትልቅ ከመዳን ጋር ትልቅ ቁርኝት እንዳላቸው መዘንጋት አያስፈልግም። ኢየሱስ "በውሃና በደም" የመጣው ለዚህ ነው። (1ኛ ዮሐንስ 5:6) በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ መሠረት "ውሃ" የሚጠቁመው የኢየሱስን ጥምቀት ነው። "ይህም #ውሃ #ማለት #ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ #አሁን #ያድነናል።" (1ኛ ጴጥሮስ ቁጥር 3:21) እዚህ ላይ "ጥምቀት" የሚለው የሚያሳየው የኢየሱስ ጥምቀት መሆኑን ለመረዳት ቁጥር 19 እና 22ን ማንበብ በቂ ነው። አውዱ የሚያወራው ስለ ኢየሱስ አገልግሎት ነው።

ጴጥሮስ "ውሃ" ማለት የኢየሱስ "#ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ #አሁን #ያድነናል" ሲል ጳውሎስ ለቲቶ በጻፈለት መልዕክቱ ደግሞ "#ለአዲስ ልደት በሚሆን #መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ #አዳነን" ይላል። ለኤፌሶን በጻፈላቸው መልዕክቱም "ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት በውሃ መታጠብና ከቃሉ ጋር እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።" ይላል። (ኤፌሶን 5:25-26) እነዚህን ሶስት ጥቅሶች ስናቆራኛቸው የምናገኘው የእውነት ስዕል የኢየሱስ ጥምቀት ቤተክርስቲያንን ከሐጢአት ቆሻሻ በማንጻትና ለአዲስ ልደት ብቁ አድርጎ በማጠብ ትልቅ ሚና መጫወቱን ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ ኢየሱስ "በውሃና በደም" መምጣቱን ሲናገር "ውሃው" የሚጠቁመው የኢየሱስን "ጥምቀት" መሆኑን ማሳየቱ ነበር።

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሞተ ጊዜ ሮማዊው መቶ አለቃ የኢየሱስ ሞት ለማረጋገጥ ጎኑን በጦር ሲወጋው የወጣው "ደምና ውሃ" ነበር። (ዮሐንስ 19:34) ይህም የሚያሳየው በኢየሱስ የቤዛነት ስራ ውስጥ "ደም" ብቻ ሳይሆን "ውሃም" (የኢየሱስ ጥምቀት) አስፈላጊ መሆኑን ነው።

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!

ከነገ ሐሙስ ጀምሮ እስከ አርብ አብራችሁን የጌታን ጸጋ እና ቅባት በህያው ቃሉ እና በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እንድትለማመዱ ጋብዘናችኋል!

#ENCOUNTER_for_Change በሚል ርዕስ round two ተዘጋጅቷል።

👑የእግዚአብሔርን የክብር አካሄድ በህይወታችሁ ተመልከቱ!

💎“አምላክ ሆይ፤ የክብር አካሄድህ ታየ፤
ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ
የሚያደርገው የክብር አካሄድ ነው።” 📖
— መዝሙር 68፥24 (አዲሱ መ.ት)

ከጠዋቱ 04:00-08:00 ሰዓት
በእግዚአብሔር ቤተሰብ ቤተክርስቲያን

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

"ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።" (ክፍል 1)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ በጻፈላቸው መልዕክቱ ውስጥ አሮጌውን ማንነትና አዲሱስ ማንጀት በንጽጽር አቅርቦዋል። አሮጌው ሚንነት የቆሸሸ፥ ያልተቀደሰና ያልጸደቀ ማንነት ነው። በአሮጌው ማንነት ውስጥ ያሉትንም "አመጸኞች" ብሎ በመጥራት መለያቸውንም በዝርዝር አቅርቦዋል። አክሎም እነዚህ "አመጸኞች" "የእግዚአብሔርን መንግስት" እንደማይወርሱ አስምሮበታል።

"ወይስ #አመጸኞች #የእግዚአብሔርን #መንግስት #እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፥ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች #የእግዚአብሔርን #መንግስት #አይወርሱም።" (1ኛ ቆሮንቶስ 6:9-10) የእግዚአብሔር መንግስት "ለአመጸኞች" ዝግ ነው። ከላይ በተዘረዘሩት አስር የሐጢአት ባህሪዎች ውስጥ የሚገኙ ሁሉ በጥቅሉ "አመጸኞች" ተብለዋል።

"አመጸኞች" ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዳይገቡ የተከለከሉት በውስጣቸው አመጻ ስላለ ነው። ከዚህ የተነሳ ወደ እግዚብሔር መንግስት ለመግባት ሶስት ነገሮች ያስፈልጉዋቸዋል። እነርሱም፦ 1. መታጠብ 2. መቀደስና 3. መጽደቅ። የማጠብ፥ የመቀደስና የማጽደቅ ችሎታም የሌላ እንጂ የእነርሱ አይደለም። አመጸኞች ራሳቸውን ማጠብም ሆነ መቀደስ እንደዚሁም ማጽደቅ አይችሉም።

"ከእናንተም #አንዳንዶቹ እንደ #እነዚህ #ነበራችሁ፥ ነገር ግን በጌታ #በኢየሱስ ክርስቶስ #ስም #በአምላካችንም #መንፈስ #ታጥባችኋል፥ #ተቀድሳችኋል፥ #ጸድቃችኋል።" (1ኛ ቆሮንቶስ 6:11) የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ትርጓሜ "ሕዝቡን ከሐጢአት ያድናቸዋል" ማለት ነው (ማቴዎስ 1:21) "የአምላካችን መንፈስ" ሌላ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ነው። ኢየሱስ ሰዎችን ከሐጢአት ለማዳን ሁለት ታላላቅ ስራዎችን በስሙ አድርጓል። የመጀመሪያው "#ጽድቅን #ሁሉ #ለመፈጸም" በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቁ ሲሆን (ማቴዎስ 3:15) ሁለተኛው "#በገዛ #ደሙ ሕዝቡን #እንዲቀድስ" በመስቀል ላይ ደሙን ማፍሰሱ ነው።

ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀት በመቀበል "ጽድቅን ሁሉ" በመፈጸሙ አመጸኞችን ለማጽደቅ የሚችለውን "ጽድቅ" ተግባራዊ አደረገ። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ "በገዛ ደሙ" ሕዝቡን በመቀደሱ (ዕብራውያን 10:10,14) የሚቀድሰውን "ቅድስና" ተግባራዊ አደረገ። "መጽደቅና መቀደስ" በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ተሰጥተዋል። "አመጸኞች" ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገቡ የሚችሉት ኢየሱስ በጥምቀቱና በሞቱ የሰራላቸውን "ጽድቅና ቅድስና" በእምነት ተቀብለው "ጻድቃንና ቅዱሳን" ሲሆኑ ነው።

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

መዝሙር 103 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝³ ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣
⁴ ሕይወትሽን ከጥፋት ጒድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣
⁵ ጐልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።


⁸ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፣ ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩም የበዛ ነው።
⁹ እርሱ ሁል ጊዜ በደልን አይከታተልም፤ ለዘላለምም አይቈጣም።
¹⁰ እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
¹¹ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።
¹² ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣ መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ።
¹³ አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።


¹⁵ ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤
¹⁶ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤ ምልክቱም በቦታው አይገኝም።
¹⁷ የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤
¹⁸ ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጉት ላይ ይሆናል።
¹⁹ እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል፤ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።


²² እናንተ በግዛቱ ሁሉ የምትኖሩ፣ ፍጥረቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ፤ ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።❞

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

ቅዱሳን እነማናቸው? (ክፍል 3)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ሐጢአት በልባቸው ውስጥ ያለባቸውን ወይም ከሐጢአት ያልዳኑ ሰዎችን "ቅዱሳን" ብሎ የጠራበት አንድም ቦታ የለም። በሐዋርያት መልዕክቶች ሁሉ ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በመስቀል ላይ ሞቱና በትንሳኤው ያመኑ ሁሉ "ቅዱሳን" ተብለዋል። አንዳንድ ማስረጃዎችን እንመልከት። "በእግዚአብሄር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ በአካይያ አገር ሁሉ ከሚኖሩ #ቅዱሳን ሁሉ በቆሮንቶስ ላለች የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን።" (2ኛ ቆሮንቶስ 1:1)

"አለም ሳይፈጠር በፊቱ #ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።" (ኤፌሶን 1:4) "ቅዱሳንና ነውር የሌለን" የሚለው ሐረግ ተዛማጅነት ያለው ሆኖ ቀርቦዊል። "ቅዱሳን መሆን" "ነውር አልባ" ከመሆን ጋር የተያያዘ ነው። ይህንን ይበልጥ የሚያብራራው ዕብራውያን 7:26 ነው። "#ቅዱስና ያለ ተንኮል #ነውርም #የሌለበት ከሐጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀካህናት ይገባናልና።"

ኢየሱስ "ቅዱስ ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከሐጢአተኞችም የተለየ" አምላክ ነው። እኛን ቅዱሳንና ነውር የሌለብን ያደረገን "ቅዱስና ነውር የሌለበት" ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ ይህንን ያደረገው አዋጅ አውጆ ሳይሆን "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" ተጠምቆና በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ የሐጢአትን ቅጣትና ፍርድ ለእኛ ተቀብሎ በመሞት ነው። (ማቴዎስ 3:15፤ማቴዎስ 26:28፤ ኤፌሶን 1:7) ኢየሱስ "ቅዱሳንና ነውር የሌለን" ያደረገን "#ሐጢአታችንን #በራሱ #ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ" ተቀምጦ ነው። (ዕብራውያን 1:3) ኢየሱስ በሰራው የጽድቅ ስራ አምናለሁ የሚል ነገር ግን አሁንም "ነውር (ሐጢአት)" ያለበት ሰው ሐጢአተኛ እንጂ "ቅዱስ" አይደለም።

"የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዮስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር #በክርስቶስ #ኢየሱስ ላሉት #ቅዱሳን ሁሉ።" (ፊልጵስዩስ 1:1) በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ ያሉ "ቅዱሳን" እንጂ ሐጢአተኞች አይደሉም። በኢየሱስ ወይም በጌታ ነኝ እያሉ አሁንም ሐጢአተኝነታቸውን የሚያውጁ ሁሉ የኢየሱስን የማዳን ስራ ያመከኑ አንቱዎች ናቸው። በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ "ቅዱሳን" እንጂ "ሐጢአተኞች" ስፍራ የላቸውም።

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

እውነተኛ ታሪክ ነው።
በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ። አንድ ሙስሊም የሆነ ወዳጅ ነበረኝ። እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በጣም ያሾፍና ይሳደብ ነበር። በልቶ የሚያራ አምላክ እያመለክ እያለኝ ይሰድበኝ ነበር። ሲደጋገምብኝ ምርር ብዬ አለቀስኩ፣ በማግስቱ ወዳጄ በአፍና በአፍንጫው ደም በጆክ መቅዳት ጀመረ፣ ለሰባት ቀናት ደም መፍሰስ አላቆመመ፣ ሁሉም ተደናገጡ። እኔም ደንግጫለሁ ብሃላ አጠገቡ ቁጭ ብዬ ሳስታውስ ወደ አእምሮዬ ይህንን የእኔን ጌታ ኢየሱስን በመሳደቡ ምክንያት በማምረሬ ምክንያት የደረሰበት እንደሆነ ተረዳሁ፣ ይበልጥ ተረበሽኩ ደነገጥኩኝ። ገዚያም እጄን ጭኝ በልቤ እግዚአብሔርን በቃ ይህንን እንዲያነሳለት ጠየኩት። ከዚያ ቀን ጀምሮ የደም መፍሰስ አቆመ። ሙሉ በሙሉ ጤንነቱ ተመለሰ። ከጥቂት ቀናት ብሃላ ከጓደኞቹ ጋር ሰብሰብ ብለው ክብ ሰርተው ጫት እየቃሙ ሳለ ለሰላምታ ወደ እነርሱ ቀረብ ስል ከተቀመጡት መካከል አንዱ በኢየሱስ ላይ ማሾፍ ሲጀምር ጓደኛዬ ከአፉ ቀምቶ ከዚህ ብሃላ በዚህ አምላክ ኢየሱስ እንድታሾፍ አልፈቅድም። የእርሱ አምላክ እውነተኛ አምላክ ነው ብሎ ማስጠንቀቂያ ሰጣቸው።
በሁኔታው አግራሞት ቢጭርብኝም እርሱ ግን ይህንን ኢየሱስን ለምን ማመን አልቻለም ነው። በእርግጥ ኢየሱስ የእኔን መራርነት ተመልክቶ እኔን እያስተማረኝ ይሆንን ብዬ እስከ ዛሬ ድረስ በአግራሞት እኖራለሁ።
ይሄ እውነተኛ ታሪክ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ድንቅ አምላክ ነው።

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

ኢየሱስ ተጠምቆ በመስቀል ላይ ከሞተ እና ለሦስት ቀናት ከተቀበረ ይህ ማለት እግዚአብሔር ለሦስት ቀናት ሞቷል ማለት ነው?
ትልቅ ጥያቄ ፡፡ አንድ ምሳሌ ለመመለስ ይረዳል ፡፡
የአበባ ማስቀመጫ አለን እንበል ፡፡ አበባ የለውም ፣ በውስጡም ውሃ የለውም ፡፡ በቃ በአየር የተሞላ ነው። ከአበባው ውጭ ባለው አየር እና በአበባው ውስጥ ባለው አየር መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? በአበባው ውስጥ ያለው አየር ቅርፅ አለው ፣ አይደል? በአቀማመጥ ተመሳሳይ አየር ነው ፣ ነገር ግን በአበባው ውስጥ ያለው አየር ቅርፅ አለው።
ያንን የአበባ ማስቀመጫ ወስደን በቅጥሩ ላይ ብናፈርስ በውስጧ ያለው አየር ምን ይሆናል? ይሞታል? አይ አየር ሊሞት አይችልም ፡፡ ማስቀመጫው በሺዎች ቁርጥራጭ ሊሆን ይችላል ፣ ግን ቅርፁን ከማጣት በስተቀር በአየር ላይ ምንም የሚከሰት ነገር የለም ፡፡
ኢየሱስ ተጠምቆ በመስቀል ላይ ሲሞት አካሉ ሞተ ፣ ግን የኢየሱስ መንፈስ ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በጭራሽ አይሞትም ፡፡ እግዚአብሄር የሰውን መልክ በኢየሱስ አድርጎ ወሰደ ፡፡ እሱ የሰው ቅርፅን ይዞ ነበር ፣ ግን ኢየሱስ በጭራሽ ሰው ብቻ አልነበረም ፡፡
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለኃጢአታችን ከፍሎ በእኛ እና በእሱ መካከል የቆመውን መሰናክል አስወግዷል ፡፡ በሞቱ ምክንያት ፣ ከእግዚአብሄር ጋር በሰላም መኖር እንችላለን ፡፡ እኛ ጥፋተኞች ብንሆንም ፣ የእግዚአብሔር ፍትሕ ለእኛ የተሠቃየውን የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስን ሙሉ በሙሉ አገኘ ፡፡ የእግዚአብሔርም ፍቅር ኢየሱስ ለእኛ ሲል ራሱን በፈቃደኝነት አሳልፎ በመስጠት ሙሉ በሙሉ ተገልጧል ፡፡
“ያ አግባብ አይደለም” ትል ይሆናል ፡፡ እና ልክ ነህ የኢየሱስ ሞት ለእኛ አይገባንም ፡፡ ግን ይህ ለእኛ የእግዚአብሔር መፍትሔ ነበር ፡፡ እንዴት መሆን እንዳለበት ለእግዚአብሄር እንነግራለን?
ስለ ኃጢአታችን መሞት እንዳያስፈልገን ኢየሱስ የሞት ቅጣታችንን ከፍሏል ፡፡ ከእርሱ ጋር ወደ ግንኙነቶች እንድንመጣ ፣ ፍቅሩን እንድናውቅ እና የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ ይፈልጋል ፡፡
አንድ ተጨማሪ ታሪክ ፡፡ እውነተኛ ታሪክ ፣ ኢየሱስ ለእኛ ያደረገልንን እንዲገነዘቡ ለማገዝ ፡፡
ጉቦ የማይወስድ ጻድቅ ዳኛ ነበረ ፡፡ እሱ ብቻ ነበር ታማኝ። አንዲት ሴት ተይዛ ወደ እርሱ ቀረበች ፡፡ ልትከፍለው የምትችለው ቅጣት የእድሜ ልክ እስራት ወይም እሷ የሌላት ከፍተኛ ገንዘብ ነበር ፡፡
ዳኛው “ጥፋተኛ ነሽ ወይስ አይደለሽም?” ሲል ጠየቃት ፡፡
እርሷም ጮኸች ፣ “ክቡር ፍርድቤት ፣ ፍርዱን መክፈል አልችልም ፣ ገንዘቡን መክፈል አልችልም ፣ እባክህ ማረኝ” አለች ፡፡
ዳኛው “እኔ እየጠየቅኩሽ ነው ጥፋተኛ ነሽ ወይስ አልሆንሽም? ተናዘዥ?” አሉት ፡፡
በመጨረሻም ወጣቷ “ክቡር ፍርድ ቤት አዎ እኔ ጥፋተኛ ነኝ” አለች ፡፡
እሱ “ከዚያ ዋጋውን ትከፍያለሽ። የሕይወት እስራት ወይም የገንዘብ ድምር” አላት ፡፡ እናም ክሱን ዘግቶታል ፡፡
መጮህ እና ማልቀስ ትጀምራለች እና ከፍርድ ቤት ውስጥ ወደ እስር ቤት አስወጡዋት ፡፡ ዳኛው ልብሱን አውልቀው ከፍርድ ቤቱ ወጣ ፡፡ ከዚያ ወደ ግምጃ ቤቱ ሄደ ፡፡ እዚያም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ሁሉ ከፍሎ ለዚያች ልጅ ቤዛ ከፍሏል ፡፡ እንዴት? ምክንያቱም ልጅቷን በጣም ይወዳት ነበር ፡፡ እርሷ ሴት ልጅ ነበረች ፡፡ እናም ሴት ልጁን ራሱ በነበረው ሁሉ ዋጀ ፡፡
ዳኛው ልብሱን ሲያወልቅ እንደማንኛውም ሰው ሆነ ፡፡ ኢየሱስ ያደረገውም ያንን ነው ፡፡ ከሰማይ ትቶ የክብርን ካባ አውልቆ እንደማንኛውም ሰው ሆነ ፡፡ እርሱ ደግሞ ስለ እኛ ሞተ ፣ ስለሆነም ኃጢአታችን ከእንግዲህ እኛን አይኮነንና ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም እንድንለያይ አያደርገንም ፡፡
ሁሉም ነቢያት ኢየሱስ ስለ ዓለም ኃጢአት እንደሚመጣና እንደሚሞት ተናግረዋል ፡፡ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ለሰው ልጆች ብቸኛው ተስፋ ኢየሱስ ነው።
በመጀመሪያ ከአዳምና ከሔዋን ጋር ፣ እግዚአብሔር የሰይጣንን ራስ እንደሚደቅ ፣ የሰው ልጆችም እንደሚቤዥ ለእባቡ ለሰይጣን ነግሮታል ፡፡ የኢየሱስ ጥምቀት ሞትና ትንሣኤ የሰይጣንን ኃይል አሸነፈ ፡፡ ኢየሱስ ኃጢአትን ፣ ሞትን እና ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን መለያየትን አሸነፈ ... ለሰይጣን ከባድ ድብደባ አደረሰ ፡፡
አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው ያለው ፡፡ ስለ እግዚአብሔር እውነት የምናውቀው እዚህ አለ-
እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው - ሁልጊዜም የነበረ ፣ አሁን ያለ ፣ እና ወደፊትም ይኖራል።
እግዚአብሔር ቅዱስ ነው - ያለ ስህተት ፣ ፍጹም ነው።
እግዚአብሔር እውነት ነው - ቃሉ ሁል ጊዜም የማይለወጥ ፣ በአስተማማኝ እውነት ነው ፡፡
እግዚአብሔር ይገኛል - በሁሉም ቦታ ፣ በማንኛውም ጊዜ ፡፡
እግዚአብሔር ኃያል ነው - ለኃይሉ ወሰን የለውም ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው - እሱ ሁል ጊዜም ለሁሉም ነገር ሙሉ እውቀት አለው።
እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው - በእርሱ ያልተፈጠረ የለም ፡፡
አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው ያለው ፡፡ እና ከላይ ያሉት ሁሉ ለእርሱ እውነት ናቸው ፡፡ ይህንን እናውቃለን ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ይህ የእግዚአብሔር እውነት መሆኑን ያሳያል ፡፡ እርሱ ስለሰው ልጆች ይህንን ለማሳወቅ መርጧል ፣ ይህንን ስለራሱ እንዲገልጽልን ፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት በተጨማሪም ኢየሱስ እነዚህን ትክክለኛ የእግዚአብሔር ባሕሪዎች እንዳሉት ያሳያል ፡፡ እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ፡፡ ለምሳሌ ዘላለማዊ እንውሰድ ፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ኢየሱስ ሲናገሩ “እርሱ በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበር ፤ እግዚአብሔር ሁሉን በእርሱ ፈጠረ ፣ በእርሱም በቀር ምንም አልተፈጠረም ፡፡” 12
ደግሞም ፣ “እርሱ የማይታይ አምላክ አምሳል ነው ፣ ከፍጥረት ሁሉ በኩር ነው። በእርሱ ዙፋን ወይም ግዛት ፣ ገዥዎች ወይም ገዥዎች ወይም ባለ ሥልጣናት - ሁሉም ነገሮች በእርሱ የተፈጠሩ ናቸው ፣ በሰማይና በምድር ፣ የሚታዩና የማይታዩ ፣ የተፈጠሩ ሁሉ ናቸው። በእርሱ እና ለእርሱ
ግን ፣ አንድ አምላክ ብቻ ከሆነ ፣ ኢየሱስ እንዴት አምላክ ሊሆን ይችላል?
በምድር ላይ የምንኖረው ባለ ሶስት አቅጣጫዊ ዓለም ውስጥ ነው ፡፡ እያንዳንዱ ሰው ቁመት ፣ ስፋትና ጥልቀት አለው ፡፡ ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው የሚመስል ነገር ሊመስሉ ይችላሉ ፡፡ እነሱ ተመሳሳይ ፍላጎቶች ፣ ተመሳሳይ ስራዎች ሊኖራቸው ይችላል። ግን አንድ ሰው በእውነቱ ከሌላው ሰው ጋር አንድ አይነት ሊሆን አይችልም ፡፡ እነሱ የተለዩ ግለሰቦች ናቸው ፡፡
እግዚአብሔር ግን ፣ ባለሦስት ልኬት አጽናፈ ሰማይ ውስንነቶች ውስጥ አይኖሩም። እሱ መንፈስ ነው ፡፡ እና እሱ ከእኛ የበለጠ እጅግ የተወሳሰበ ነው። ለዚህም ነው ኢየሱስ ወልድ ከአብ የተለየ ሊሆን የሚችለው ፡፡ ግን ተመሳሳይ የሆነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል-እግዚአብሔር ወልድ ፣ እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፡፡ ግን ደግሞ አንድ እግዚአብሔር ብቻ እንዳለ በግልፅ ይነግረናል ፡፡ እግዚአብሔር ን በሂሳብ የምንጠቀም ከሆነ 1 + 1 + 1 = 3 አይሆንም። 1x1x1 = 1 ይሆናል። እግዚአብሔር አንድ ነው ፡፡

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

@Lydia_rahab [1200348601] used a banned word.
Warns now: (3/3) ❕
Action: Muted 🔇

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

💪❤️❤️❤️ልበ ሙሉ ነኝ!❤️❤️❤️💪

📖 “ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤
ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ።” 💎
— መዝሙር 27፥3 (አዲሱ መ.ት)

የአማኝ ሕይወት ከሁኔታው አንጻር አይተረጎምም።
የክርስቲያን የህይወት መሰረት የልቡ ሁኔታ ነው!

ህይወታችሁ የሚናወጠው ልባችሁ ሲከፈል እና ሲረበሽ ነው እንጂ የኑሮ ሁኔታችሁ ከፍ እና ዝቅ ሲል አይደለም።

በጠላት እና ጥሩ ባልሆኑ ሁኔታዎች ተከባችሁ ያለፍርሃት እና ያለመናወጥ ለመኖር ሚስጥሩ የህይወታችሁን መታመኛ ለይቶ ማወቅ ነው!

💎 “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?” 📖
— መዝሙር 27፥1
❤️ "ልቤ ሙሉ ነው፤" ምክንያቱም
"እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው!"🙏

👉 ከከበባችሁ ሁኔታ ይልቅ አብሯችሁ ያለ
አስተማማኝ የህይወት ዋስትና አለ:
🕎እግዚአብሔር🕎

💎 “በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤
በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤” 📖
(መዝሙር 27፥5)

ሰላማችሁ ይብዛ!!!

ጥር15-2013
ወንድማችሁ ዳዊት አለሙ
#ከእግዚአብሔር_ቤተሰብ_ቤተክርስቲያን

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

🙏🙏🙏🙏🙏🙏
አሸናፊነት💪

በዙሪያህ ያሉ ሁኔታዎች የማይመቹ ሊመስሉ ይችላሉ 👈ማንነትህን የሚቀበል አንተ ላለህ አቅም ግድ የሚሠጠው ሠው ላይኖር ይችላል😵🤷‍♂🤷‍♀ ከነመፈጠሩም ብትታመም ብትወድቅ ብትራብ ቢከፋህ ብትጨነቅ ግራ ቢገባህ ብቸኝነት ሲሠማህ በዚ ጊዜ አጠገብህ ሊኖሩ የሚገባቸው እናት አባት ዘመድ ጓደኛህ የሠው ዘር ሁሉ ቢጥልህ አልፎ ተርፎ የእግዚአብሔር ሠዎች የምትላቸው እንኳን እንደማትጠቅም አልፎ ተርፎ መሞትህና መኖርህ ግድ ባይሠጣቸው🙅🙅‍♂ በዚ ሁሉ አይንህን ከሁኔታዎቹ ከደረሠብህ ችግር እየሆነ ካለው ጊዜያዊ ድካም ከተውህ ሠዎች ከጣሉህና አንተነትህን ከረሱ ግፍ እንኳን ከሠሩብህ ሁሉ አይንህን አንሥተህ 🙇‍♀🙇ነገ ሊሆን ያለውን ተሰፋ በልብህ ሠንቀህ 🙋‍♂🙋በራስህ ላይ ያለህን እምነት ከፍ አድርገህ ተጓዝ እነዚህ በአንተ ላይ እየሆኑ ያሉ ነገሮች በሠዎች ድጋፍ እንዳትቆምና በሁኔታዎች ምቾት እንዳትቀመጥ እንድታልፍባቸው የተፈጠሩ መንገዶች ናቸው ሁል ጊዜ ከአሸናፊነት በስተጀርባ ትንቅንቅና ትግል አለ🏃🏃‍♀ ያለትግል አሸናፊነት የለም ትግል የሌለው አሸናፊነት የለም ስታሸነፍ ግን የታገሉህ እነሱ ያሸናፊነትህ ተገዢ ናቸው አሸናፊነት የሚጣፍጠው ብርቱ ፉክክርና ትግል ሲኖረው ነው።በጣም አጣብቂኝ የሚመስልና ብርቱ ትግል ውስጥ ካለህ እመነኝ ስታሸንፍ ድልክ አለምን ሁሉ የሚገዛና የሚቆጣጠር ይሆናል 👑የረሱህ የተቹህ የናቁህ ያዋረዱህ የጣሉህ እንደምናምንቴ የቆጠሩህ ተስፋ ያስቆረጡህ እነሡ የክብርህ የምሥራች ተናጋሪ ናቸው ተሸናፊነት ያለው በሁኔታው ላይ ትኩረት ስታደርግ ነውና ሁኔታዎቹን አትይ ካየሃቸው ቂመኛነት💆‍♂ ተበዳይነት💆 እየተሠማህ ይመጣል የዛኔ መቁሠል ትጀምራለህ ተስፋ ትቆርጣለህ መኖርህን ትጠላለህ ማነስ ይሠማሃል 🙇‍♀🙇የዛኔ ሽንፈት ይጀምራል ትኩረት ልታደርግ የሚገባው አላማህን ነው አሸናፊ ሆይ አሸናፊነትህን እያየህ ተራመድ🚶🚶‍♀ ትደርሳለህ ያየኧውን ትወርሣለህ አሸናፊነት ልብህ ላይ እንጂ አቅምህ ላይ አይደለም ያለው ❤️

📜አለምን የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።
1ዮሐ 5:4
🙌🙌🙌🙌🙌🙌
@prophetyohannesalemayehu
@prophet_yohannes_alemayehu
@prophet_yohannesalemayehu

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

☁️☁️☁️ከደመና በታች☁️☁️☁️

ዘወትር እሁድ "እጆቼን በመጫን..." ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔርን ጸጋ የመካፈል ጊዜ እየሆነልን ነው።

👉 ኑ በግል ህይወታችሁ የእግዚአብሔርን ህያውነት ተለማመዱ!

💎 “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።” 📖
— ዕብራውያን 13፥8

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

Everything the light touches... Is Our Kingdom.
THE LION KING

Everybody/Everything from the light has overcomer name.
Genesis1:5,26

YOU ARE FROM THE LIGHT!
THE LIGHT inside of your heart were THE LIGHT for THE WHOLE WORLD.
Genesis1:3 & 2Cor4:3-6

You were DARK, NOW YOU are THE LIGHT IN CHRIST! This LIGHT is IDENTITY CHANGER!
Ephesians 5:8

“But thanks be to God, Who in Christ always leads us in triumph and through us spreads and makes evident the fragrance of the knowledge of God everywhere,”
— 2Cor 2:14 (AMP)

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

4 ተከታታይ እሁዶች #ከደመና_በታች በሚል የተዘጋጀ የክብር ኮንፍረንስ

💎 “ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።” 📖
— ዘዳግም 33፥26

🔥እግዚአብሔር እናንተን ለመርዳት በደመናት ላይ ይራመዳል!

"ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።”
— ናሆም 1፥3
#CloudsAreTheDustOfHisFeet!!!

ዘወትር እሁድ እና ሐሙስ ከጠዋቱ 04:00 - 08:00

👉 ኑ አብራችሁን ሕያው እግዚአብሔርን በማምለክ እና በህያው ቃል፣ በጸሎት፣ በትንቢት፣ በፈውስ እና በነጻ መውጣት በግል ህይወታችሁ ክብሩን ተለማመዱ!

👑 የእግዚአብሔር ቅባት: የክርስቶስን ስራ በህይወታችን የሚገልጥ የእግዚአብሔር አቅም ነው!!!

በእግዚአብሔር ቤተሰብ ቤተክርስቲያን!

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

#በድጋሜ የወጣ
#አስቸኳይ የክፍት ስራ ማስታወቂያ#
በእርግጥ ስራ ለፈለጉ ብቻ
#ክፍት_የስራ_ቦታ 👉 22/05/2013 የወጣ.
👉 የስልክ ኦፕሬተር
👉 ፆታ. አይለይም.
👉 ብዛት:- 8
👉 የት/ት ደረጃ:- 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ
👉 እድሜ:- ከ23-30 ድረስ ብቻ
👉 መደበኛ ሠራተኝነት
👉ደሞዝ:- በድርጅቱ የደሞዝ ስኬል መሠረት
👉የምዝገባ ጊዜ ከ22/05/ - 23/06/2013
👉የስራ መጀመሪያ ጊዜ:- አስቸኳይ
👉አድራሻ:- ቦሌ ዲኤች ገዳ ህንፃ ጀርባ ዶ/ር አበበ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
👉ሴቶች ስርአት ያለው የሴት ቀሚስ የሚለብሱና በንፅህና አጠባበቅና ስርአት ያላቸው ብቻ።
👉ለምዝገባም ሲመጡ አለባበስ ንፅህናና የአነጋገር ስርአት ይታያል::
👉የትምህርት ማሰረጃዎች በሙሉ ፎቶ ኮፒና ኦሪጂናል ይዘው ይምጡ
👉 መስፈርቱን የምታሟሉ ማመልከትና መወዳደር ትችላላችሁ።
👉ትክክለኛ ስራ ፈላጊ ማሟላት ያለበትን ሁሉ አሟልቶ በተባለበት ቦታ ይገኛል።
📞📱0930 - 00 60 10.
በቅንነት ለሌሎች ሼር አድርጉ
👉 ብሉ-ስካይ ኢኖቬሽን
🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

(አስባቹታል ግን)

~ፍቅር በነፃ
~አየር በነፃ
~ንስሀ በነፃ
~የዘላለም_ህይወት በነፃ


~መጠጥ በክፍያ
~ዝሙት በክፍያ
~ጭፈራ_ቤት በክፍያ
~ሺሻ_ጫት በክፍያ

እንዴት ከፍለን ገሐነም እንገባለን
እናስብ ወገን🔥🤔

(ዛሬን የመድረሳችን ሚስጥር ኢየሱስ ነው)

Ameseginhalewu yene wudi yene Nigusi Yene hiwet tebareklign ejig betam ewedhalewu

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መጽሐፎችን በpdf በነፃ ማግኘት የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ።

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

"ታጥባችኋል፥ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።" (ክፍል 2)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።


በክፍል 1 ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምዕመናን በጻፈላቸው መልዕክቱ "አመጸኞች" የእግዚአብሔርን መንግስት እንደማይወርሱ ከተናገረ በኋላ "አመጸኞች" ራሳቸውን የሚገልጡባቸውን አስር መተላለፎች ዘርዝርዋል። የቆሮንቶስ ምዕመናን "ቀድሞ እንደዚህ" እንደነበሩ ከነገራቸው በኋላ "በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል" (1ኛ ቆሮንቶስ 6:9-11) በማለት "አመጸኞች" የሚለው የቆሸሸ ማንነት እንደተቀየረላቸው ነገራቸው።

በዚህ ክፍል "ታጥባችኋል" በሚለው ቃል ላይ ትኩረት እናደርጋለን። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መታጠብን በሚመለከት ጥቅም ላይ የዋሉት ውሃና ደም መሆናቸውን በግልጽ ያስቀምጣል። "ባሎች ሆይ ክርስቶስ ደግሞ #ቤተክርስቲያንን #እንደወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ #በውሃ #መታጠብና ከቃሉ ጋር እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።" (ኤፌሶን 5:25-26) ኢየሱስ "ቤተክርስቲያንን" "በውሃ መታጠብ" እንዳጠባት ከዚህ ጥቅስ መረዳት ይቻላል። በውሃ የሚታጠብ ማንኛውም ነገር አስቀድሞ የቆሸሸ ነገር ነው።

ኢየሱስ በሐጢአት የቆሸሽነውን ሰዎች ለማጠብ "ውሃን" ተጠቅሞዋል። ኢየሱስ ይህንን ያደረገው "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" (ማቴዎስ 3:15) በአጥማቂው ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በተጠመቀ ጊዜ ነበር። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰው ስለ ሐጢአተኞች እንደሆነ ሁሉ በዮርዳኖስ ወንዝ "ውሃ" ውስጥ የተጠመቀውም ስለ ሐጢአተኞች ነው። ኢየሱስ ሲጠመቅ ሐጢአተኞች ከነሐጢአታቸው ከኢየሱስ ጋር አብረው ተጠምቀዋል። (ሮሜ 6:3-5፤ ገላትያ 3:27 ቆላስያስ 2:12) ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሲሰቀል አብሮ ያልተሰቀለ በአሮጌው ማንነቱ ውስጥ እንዳለ ሁሉ (ገላትያ 2:19-20) ኢየሱስ ሲጠመቅ አብሮ መጠመቁን የማያምን ሁሉ "በውሃ መታጠብ" ውስጥ አያልፍም።

"እንደ ምህረቱ መጠን #ለአዲስ ልደት በሚሆነው #መታጠብና #በመንፈስ #ቅዱስ በመታደስ #አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ስራ አይደለም።" (ቲቶ 3:5) "ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ" የማዳንን ስራ ሰርተዋል። "አዳነን" የሚለው ቃል "ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ" ከሚለው ጋር የተያያዘ ነው። መጀመሪያ መታጠብ ይቀድማል። ቀጥሎ በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ይመጣል። ይህ ምን ማለት እንደሆነ በክፍል 3 ይተነተናል።

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

💪❤️❤️❤️ልበ ሙሉ ነኝ!❤️❤️❤️💪

📖 “ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤
ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ።” 💎
— መዝሙር 27፥3 (አዲሱ መ.ት)

የአማኝ ሕይወት ከሁኔታው አንጻር አይተረጎምም።
የክርስቲያን የህይወት መሰረት የልቡ ሁኔታ ነው!

ህይወታችሁ የሚናወጠው ልባችሁ ሲከፈል እና ሲረበሽ ነው እንጂ የኑሮ ሁኔታችሁ ከፍ እና ዝቅ ሲል አይደለም።

በጠላት እና ጥሩ ባልሆኑ ሁኔታዎች ተከባችሁ ያለፍርሃት እና ያለመናወጥ ለመኖር ሚስጥሩ የህይወታችሁን መታመኛ ለይቶ ማወቅ ነው!

💎 “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?” 📖
— መዝሙር 27፥1
❤️ "ልቤ ሙሉ ነው፤" ምክንያቱም
"እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው!"🙏

👉 ከከበባችሁ ሁኔታ ይልቅ አብሯችሁ ያለ
አስተማማኝ የህይወት ዋስትና አለ:
🕎እግዚአብሔር🕎

💎 “በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤
በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤” 📖
(መዝሙር 27፥5)

ሰላማችሁ ይብዛ!!!

ጥር15-2013
ወንድማችሁ ዳዊት አለሙ
#ከእግዚአብሔር_ቤተሰብ_ቤተክርስቲያን

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

💪❤️❤️❤️ልበ ሙሉ ነኝ!❤️❤️❤️💪

📖 “ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤
ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ።” 💎
— መዝሙር 27፥3 (አዲሱ መ.ት)

የአማኝ ሕይወት ከሁኔታው አንጻር አይተረጎምም።
የክርስቲያን የህይወት መሰረት የልቡ ሁኔታ ነው!

ህይወታችሁ የሚናወጠው ልባችሁ ሲከፈል እና ሲረበሽ ነው እንጂ የኑሮ ሁኔታችሁ ከፍ እና ዝቅ ሲል አይደለም።

በጠላት እና ጥሩ ባልሆኑ ሁኔታዎች ተከባችሁ ያለፍርሃት እና ያለመናወጥ ለመኖር ሚስጥሩ የህይወታችሁን መታመኛ ለይቶ ማወቅ ነው!

💎 “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?” 📖
— መዝሙር 27፥1
❤️ "ልቤ ሙሉ ነው፤" ምክንያቱም
"እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው!"🙏

👉 ከከበባችሁ ሁኔታ ይልቅ አብሯችሁ ያለ
አስተማማኝ የህይወት ዋስትና አለ:
🕎እግዚአብሔር🕎

💎 “በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤
በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤” 📖
(መዝሙር 27፥5)

ሰላማችሁ ይብዛ!!!

ጥር15-2013
ወንድማችሁ ዳዊት አለሙ
#ከእግዚአብሔር_ቤተሰብ_ቤተክርስቲያን

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

💪❤️❤️❤️ልበ ሙሉ ነኝ!❤️❤️❤️💪

📖 “ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤
ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ።” 💎
— መዝሙር 27፥3 (አዲሱ መ.ት)

የአማኝ ሕይወት ከሁኔታው አንጻር አይተረጎምም።
የክርስቲያን የህይወት መሰረት የልቡ ሁኔታ ነው!

ህይወታችሁ የሚናወጠው ልባችሁ ሲከፈል እና ሲረበሽ ነው እንጂ የኑሮ ሁኔታችሁ ከፍ እና ዝቅ ሲል አይደለም።

በጠላት እና ጥሩ ባልሆኑ ሁኔታዎች ተከባችሁ ያለፍርሃት እና ያለመናወጥ ለመኖር ሚስጥሩ የህይወታችሁን መታመኛ ለይቶ ማወቅ ነው!

💎 “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?” 📖
— መዝሙር 27፥1
❤️ "ልቤ ሙሉ ነው፤" ምክንያቱም
"እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው!"🙏

👉 ከከበባችሁ ሁኔታ ይልቅ አብሯችሁ ያለ
አስተማማኝ የህይወት ዋስትና አለ:
🕎እግዚአብሔር🕎

💎 “በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤
በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤” 📖
(መዝሙር 27፥5)

ሰላማችሁ ይብዛ!!!

ጥር15-2013
ወንድማችሁ ዳዊት አለሙ
#ከእግዚአብሔር_ቤተሰብ_ቤተክርስቲያን

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

getan becha meketel yhun ye hul gize alamachen

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

አይመለከተንም፣ የዚህ ግሩፕ አላማ የገባህ አልመሰለኝም። ይሄ ግሩፕ አላማው ፖለቲካ አይደለም፣ የእስራኤልን አምላክ የሆነውን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ማወቅ ነው። Banned ትደረጋለህ።

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

ቅዱሳን እነማናቸው? (ክፍል 1)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ይህ ጥያቄ መልስ የሚሻው ጥያቄ ነው። የክርስትናው አለም "ቅዱሳንን" በሚመለከት በርካታ የተዛቡ ትርክቶችን ተቀብሎዋል። የሐይማኖትን ወግና ስርአት የተቀበሉ ሐይማኖተኞች ራሳቸው "ቅዱሳን" ብለው በሾሙቸው ሰዎች ይህንን ስያሜ የለገሱዋቸው በርካቶች ናቸው። "ብጹዕ" ወይም "ቅዱስ" የሚለውን የከበረ ስያሜ የያዙ ነገር ግን ከሐጢአት ያልዳኑና በልብቻቸው ውስጥ ሐጢአት የተከመረባቸው በርካቶች ናቸው።

"ቅዱሳን እነማናቸው?" የሚለውን ጥያቄ በትክክል የሚመልሰው ግን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። "በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን፥ በክርስቶስ #ኢየሱስ #ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን #የኢየሱስ ክርስቶስን #ስም በየስፍራው #ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት።" 1ኛ ቆሮንቶስ 1:2) ሐዋርያው ጳውሎስ "ቅዱሳን" ብሎ የጠራቸው 1. "በክርስቶስ ኢየሱስ የተቀደሱ 2. "የኢየሱስን ስም በየስፍራው የሚጠሩ" ናቸው።

የኢየሱስን ስም መጥራት ማለት ከሐጢአት መዳንን ማወጅ ማለት ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የሚለው ስም ትርጓሜ "#ሕዝቡን #ከሐጢአታቸው #ያድናቸዋልና" ማለት ነው። (ማቴዎስ 1:21) የኢየሱስን ስም እየጠሩ አሁንም ሐጢአተኞች እንደሆኑ የሚናገሩ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ስም በከንቱ እየጠሩ በመሆኑ እግዚአብሔር ከበደል አያነጻቸውም። (ዘጸአት 20:7)

"ቅዱሳን" የመሆን ስያሜ በሐይማኖት አባቶች ሐይማኖታዊ ውሳኔ ወይም በመጋቢዎችና አቡኖች ደንብና ስርአት ወይም በቤተክርስቲያን ዶግማዊ መስፈረት አይገኝም። መስፈርቱ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም "በክርስቶስ ኢየሱስ መቀደስ" ነው። "በዚህም ፈቃድ #የኢየሱስ ክርስቶስን #ስጋ #አንድ #ጊዜ #በማቅረብ #ተቀድሰናል።" (ዕብራውያን 10:10) ኢየሱስ እኛን ለማዳን የሰጠው ደሙን ብቻ ሳይሆን ስጋውንም ጭምር ነው። ኢየሱስ "ስጋውን" ሲሰጠን "#በስጋው #ሐጢአታችንን በእንጨት ላይ #ተሸከመ።" (1ኛ ጴጥሮስ 2:24) ኢየሱስ "በስጋው ሐጢአታችንን" ባይሸከም ኖሮ በመስቀል ላይ ባልተሰቀለም ነበር። እኛ ይህንን የኢየሱስን ስጋ አንድ ጊዜ በማቅረብ ተቀድሰናል። ከዚህ ውጪ ቅድስና የሚገኝበት ወይም ቅዱሳን የመሆኛ ሌላ መንገድ በጭራሽ የለም።

ጥናታችን ይቀጥላል።

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

አለምን የሚያሸንፈው ያ እምነት ምንድን ነው?

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

ክርስቶስ ጽድቃችን--ከሕግ የሚገኝ ጽድቅና አደጋው (ክፍል 7)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሐዋርያው ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናን በጻፈላቸው መልዕክቱ ውስጥ ‹‹#ከሕግ--#ሥራ--#የሆኑት ሁሉ #በእርግማን--#በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎዋልና›› (ገላትያ 3፡10) በማለት ‹‹በሕግ ሥራ›› ውስጥ የሚርመጠመጡትን ሁሉ ‹‹ከእርግማን በታች›› እንደሆኑ አስረግጦ ይነግራቸዋል፡፡ ‹‹የሕግ ሥራ›› ምን ማለት ነው? በአጭሩ ‹‹ሕግን በመጠበቅ›› የሚገኝ ጽድቅ ነው፡፡ ሕግን በመጠበቅ የሚገኝ ጽድቅ እርግማን ነው፡፡

ብዙ ክርስቲያኖች ሕጉን እንዴት እንደሚያነቡ ስለማያውቁ ሕግን ከልጅነቱ ጀምሮ ሲጠብቅ እንደነበር በኩራት ለኢየሱስ መልስ ከሰጠው ‹‹የሕግ አዋቂ›› ብዙም አይለዩም፡፡ ይሕ የሕግ አዋቂ ወደ ኢየሱስ የመጣው ኢየሱስ ‹‹ሐጢያትን የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› መሆኑን (ዮሐንስ 1፡29፤1ኛ ዮሐንስ 3፡5) አምኖ ለዚህ ምስጋናን ለማቅረብ ሳይሆን ሕግን በመጠበቁ ጻድቅ መሆኑን ለኢየሱስ ለማሳየት ነበር፡፡ ኢየሱስ ለዚህ የሕግ አዋቂ የጠየቀው ጥያቄ ዛሬም ብዙዎች ሊጠየቁት የሚገባ ጥያቄ ነው፡፡ ‹‹በሕግ የተጻፈው ምንድነው? እንዴትስ ታነባለህ?›› (ሉቃስ 10፡25) ሕጉ ትክክል ነው፤ ነገር ግን ችግሩ ሰዎች ሕጉን የሚያነቡበት መንገድ ነው፡፡ እምነታቸውን በሕግ ላይ የመሰረቱ ሰዎች ‹‹እንዴት ታነባለህ?›› ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጡት በሕጉ ላይ ባላቸው እምነት ላይ ተመስርተው ነው፡፡ ሕጉ ሐጢያትን ያሳያል እንጂ ሐጢያት አያስወግድም፡፡ ሕጉ ሐጢያትን ወደሚያስወግደው ኢየሱስ ይመራል እንጂ አያድንም፡፡

ሰዎች ሕግን በመጠበቅ የራሳቸውን ጽድቅ ለማፍለቅ የሚሞክሩት ስለ ሕግ ያላቸው እውቀት የተሳሳተ ስለሆነ ነው፡፡ አንድ ሰው ከሐጢያት ሳይድን ሐጢያት ላለመስራት ቢታገል በሐጢአት ውስጥ መውደቁን ይቀጥላል፡፡ ሕግን እየጠበቀ ለመኖር የሚሞክር ሰው በመጨረሻ የሚተርፈው ነገር ቢኖር የሐጢያት ቁስል፥ ስቃይና መንፈሳዊ ድህነት ብቻ ነው፡፡ ይህ ሰው የእግዚአብሄርን ጽድቅ አያገኝም፡፡ ‹‹#ሕጉ--#መቅሰፍትን--#ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም፡፡›› (ሮሜ 4፡15)
የብዙ ክርስቲያኖች ትልቁ ስህተት ከሕግ ጋር በመጋባት የጽድቅ ፍሬን ለማፍራት መሞከራቸው ነው፡፡

‹‹እንዲሁ ወንድሞቼ ሆይ እናንተ ደግሞ #በክርስቶስ--#ሥጋ--#ለሕግ--#ተገድላችኋል፡፡ ለእግዚአብሄር ፍሬ እንድናፈራ እናንተ ለሌላው ከሙታን ለተነሣው ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ፡፡ በሥጋ ሳለን #በሕግ የሚሆን #የሐጢአት--#መሻት--#ለሞት--#ፍሬ--#ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሰራ ነበርና፡፡ አሁን ግን ለእርሱ #ለታሰርንበት--#ስለሞትን--#ከሕግ--#ተፈትተናል፡፡ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም፡፡›› (ሮሜ 7፡4-6)

1. በክርስቶስ ስጋ ለሕግ ተተገድለናል፡፡
2. ለእግዚአብሄር ፍሬ ማፍራት የምንችለው ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን ከሙታን ለተነሳው ለኢየሱስ በመኖር ነው፡፡
3. ሕግ አስሮን ነበር አሁን ግን ተፈትተናል፡፡
4. በሥጋ ያሉ ሰዎች አሁንም ሕጉን ለመጠበቅ የሚሞክሩ ከሆነ የሚያፈሩት የሞት ፍሬ ነው፡፡
5. ከዚህ በኋላ የምንኖረው በአዲሱ የመንፈስ ኑሮ እንጂ በበአሮጌው በፊደል (ሕግን በመጠበቅ) ኑሮ አይደለም፡፡

ከዚህ የተነሳ ከሕግ የሚገኘውን ጽድቅ ለማግኘት የሚፍጨረጨሩ ሁሉ ከላይ የተዘረዘሩት እውነቶች ወይ አልገባቸውም አለበለዚያም ግራ ተጋብተዋል፡፡

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

የወንጌል አደራ
በመጋቢ ሰለሞን ወ/አምላክ

የወንጌል አደራ ቸል የምንለው ጉዳይ አይደለም
ክፍል - 1
✍አደራ ተቀባይ ካለ አደራ ሰጪ አለ ። አደራ ሰጪውን የሚያከብር ባለአደራ የሆነ ሰው ታማኝ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል ። አደራ ተጠያቂነትም አለበትና ።
✍በዚሁ ረገድ ክርስቶስ ለአማኞች ሁሉ ከትህዛዝ ጋር የሰጠው አደራ አለ ። እርሱም ወንጌልን ለአለም ሁሉ ማደረስ ነው ።

✍የወንጌል መልዕክት ያው አንድ ሆኖ ሳለ፤ አደራ ሰጪው ክርስቶስ ሕያው ሳለ የወንጌል መልዕክት ለምን እንደ ጅማሬው ዘመን አልሆነም የሚል ጥያቄ ቢነሳ ልዩነቱ የመጣው አደራ ተቀባዮቹ ጋር ሆኖ እናገኘዋለን ።

✍የቤተ - ክርስቲያን መሪዎች የክርስቶስ ልብ ሲኖራቸው ቅድሚያ የሚሰጡት አጀንዳ ወንጌል ነው ። የክርስቶስ አጀንዳ ወንጌል ስለሆነ ። መሪዎች ልባቸውን ሌላ ነገር ሲሞላው አጀንዳቸው በሚታይ ነገር ላይ መሆኑ የማይቀር ነው ። ይህን ለማረጋገጥ ቅድሚያ የሰጠናቸውን ጉዳዩች ማየት በቂ ነው ። በዚህ ዙሪያ ሁሉም አንድ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ልዩነት የሚያመጣው የአደራ ሰጪውን ማንነት ማወቅና የተሰጠንን አደረ ምን እንደሆነ የመረዳት ደረጃችን ነው ። ይህን በጥብቅ ከተገነዘብን የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጠው አጀንዳችን የወንጌል ስርጭት ይሆናል ። ምክንያቱም የወንጌል ስርጭት የእግዚአብሔር አጀንዳ ነውና ።
✍ስለሆነም ክርስቶስ ዛሬ በመካከላችን ሆኖ "ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ " ሊለን ይወዳል ። እስከ አለም ፍፃሜ ወንጌል ለአለም መሰበክ እንዳለበት የሰጠው ትህዛዝ ዛሬም ትኩስ ነው ። ስለዚህ የወንጌል አደራ ዛሬም ቸል የምንለው ጉዳይ አይደለም ።

ለወዳጆ share ማረግ አይርሱ 🙏

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

#ክርስቶስ #ጽድቃችን--‹‹#አስቀድማችሁ #የእግዚአብሄርን #መንግስት #ጽድቁንም #ፈልጉ›› (#ማቴዎስ 6፡33) (#ክፍል 5)
-----------------------------------------------------------------------------

የእግዚአብሄር መንግስትና የእርሱ ጽድቅ የተቆራኙ መሆናቸውን የማያውቁ ሰዎች እነዚህን ሁለት ቁም ነገሮች አያስተውሉም፡፡ የዘመኑ ቤተክርስቲያኖች ‹‹የእግዚአብሄርን መንግስት›› እና ‹‹ጽድቁን›› ርቆ እንደተሰቀለ ዳቦ እየተመለከቱ እነዚህን እውነቶች ከመስበክ ጎድለዋል፡፡ ኢየሱስና የእርሱ ሐዋርያት መከራን የተቀበሉት የእግዚአብሄርን መንግስትና ጽድቁን በመስበካቸው ነበር፡፡ ሰይጣን የሲዖል ሐይሎቹን በሙሉ የሚያሰልፈው ‹‹የእግዚአብሄርን መንግስትና ጽድቁን›› በምትሰብክ ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄር ጽድቅ መሰረታዊ እውነት ነው፡፡ ኢየሱስ ‹‹ከእግዚአብሄር መንግስት›› ጋር በጋራ ‹‹ጽድቁንም›› እንድንፈልግ መናገሩን ልብ ይሏል፡፡ የቤተክርስቲያን መሰረት የተመሰረተው ኢየሱስ በገለጠው በዚህ የእግዚአብሄር ጽድቅ ላይ ነው፡፡ ‹‹ጽድቁን›› መፈለግ ማለት ምንድነው? የምንፈልገውስ የት ነው? ‹‹አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት #የእግዚአብሄር--#ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦዋል፡፡ እርሱም #ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ #በኢየሱስ--#ክርስቶስ--#በማመን-- #የሚገኘው--#የእግዚአብሄር--#ጽድቅ ነው፡፡›› (ሮሜ 3፡22-23) ‹‹ጽድቁን›› መፈለግ ‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ›› ማመን ነው፡፡ ይህንን የእግዚአብሄር ጽድቅ የምናገኘው በኢየሱስ ውስጥ ነው፡፡ ኢየሱስ ይህን ጽድቅ በይፋ የገለጠው ደግሞ ‹‹ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም›› በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ነው፡፡

‹‹#እኛ--#በእርሱ--#ሆነን--#የእግዚአብሄር--#ጽድቅ እንሆን ዘንድ #ሐጢአት--#ያላወቀውን እርሱን #ስለ--#እኛ--#ሐጢአት አደረገው፡፡›› (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21) ኢየሱስ ‹‹ሐጢአት ያላወቀው›› ሆኖ ሳለ ‹‹እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሄር ጽድቅ እንሆን ዘንድ›› ‹‹ስለ እኛ ሐጢአት›› ተደረገ፡፡ ይህ የጳውሎስ ጥልቅ መልዕክት ኢየሱስ ‹‹ስለ እኛ ሐጢአት›› የተደረገው በምትኩ እኛን ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ›› ለማድረግ እንደሆነ ይገለጣል፡፡ ኢየሱስ ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ›› ሆኖ ሳለ ‹‹ስለ እኛ›› ግን ‹‹ሐጢአት›› ተደረገ ማለት እርሱ የእኛን የሐጢያተኞቹን ሐጢያት በራሱ ላይ በመውሰድ እኛን በልዋጩ የእግዚአብሄር ጽድቅ አደረገን ማለት፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ መፈለግ ያለባቸው ‹‹ሐጢያተኞች›› እንጂ ‹‹ጻድቃን›› አይደሉም፡፡

ብዙውን ጊዜ ክርስቲያኖች ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ›› ተጨባጭ እውነት አይመስላቸውም፡፡ ከዚህ የተነሳ ‹‹የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከመፈለግ›› ይልቅ ሕግን በመጠበቅ የሚገኘውን ጽድቅ የሙጥኝ ይላሉ፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስን ወደ ምድር የላከውና በአጥማቂው ዮሐንስ እንዲጠመቅ ያደረገው ‹‹ጽድቁ›› ተጨባጭ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ኢየሱስ ለአጥማቂው ዮሐንስ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› (ማቴዎስ 3፡15) ያለው ለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስ እፈጽመዋለሁ ያለው ‹‹ጽድቅ ሁሉ›› የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡ ያ ጽድቅ ከኢየሱስ ጥምቀት በኋላ ‹‹የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ›› ተብሎ ተጠራ፡፡ (2ኛ ጴጥሮስ 1፡1) በመሆኑም የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተክርስቲያን በብዙ መሻት ያለባት ‹‹የእግዚአብሄርን መንግስትና ጽድቁን›› ነው፡፡

ይቀጥላል

Читать полностью…

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

#ክርስቶስ #ጽድቃችን--‹‹#አስቀድማችሁ #የእግዚአብሄርን #መንግስት #ጽድቁንም #ፈልጉ›› (#ማቴዎስ 6፡33) (#ክፍል 4)
-----------------------------------------------------------------------------

ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹የእግዚአብሄርን መንግስት›› እና ‹‹ጽድቁን›› በማዛመድ እነዚህን ሁለት ነገሮች እንድንሻ ነግሮናል፡፡ በሌላ አነጋገር የእግዚአብሄር መንግስትና ጽድቁ የሚነጣጠሉ አይደሉም፡፡ በመሰረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ የአደባባይ አገልግሎቱን ሲጀምር መልዕክቱ ‹‹ዘመኑ ተፈጸመ፡፡ #የእግዚአብሄርም--#መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ›› (ማርቆስ 1፡15) የሚል ነበር፡፡ ሰዎችን ለእግዚአብሄር መንግስት የሚያበቃቸው የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡

አሁን እነዚህን ሁለቱን ኩነቶች ነጣጥለን እንመልከት፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ምንድነች? ሐዋርያት በእግዚአብሄር መንግስት ላይ የነበራቸውን እምነት ማየት የመልዕክታቸውን ቁም ነገር መረዳት ያስችላል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሄርን መንግስት በሚመለከት በርካታ መልዕክቶችን ጽፎዋል፡፡ አሁን እነርሱን ማየት እንጀምር፡፡ ‹‹እርሱ ከጨለማ ሥልጣን #አዳነን፡፡ ቤዛነቱንም እርሱንም #የሐጢአትን--#ስርየት ወዳገኘንበት ወደ #ፍቅሩ--#ልጅ--#መንግሥት--#አፈለሰን፡፡›› (ቆላስያስ 1፡13-14) ‹‹ነገር ግን ስለ እግዚአብሄር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ፡፡›› (የሐዋርያት ስራ 8፡12) ‹‹ወደ ምኩራብም ገብቶ ስለ #እግዚአብሄር--#መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል በግልጥ ይናገር ነበር፡፡›› (የሐዋርያት ስራ 19፡8) ‹‹አሁንም እነሆ እኔ #የእግዚአብሄርን--#መንግስት--#እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳታዩ አውቃለሁ፡፡›› (የሐዋርያት ስራ 20፡25) ‹‹ማንም ሳይከለክለው #የእግዚአብሄርን--#መንግስት--#እየሰበከ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እጅግ ገልጦ ያስተምር ነበር፡፡›› (የሐዋርያት ስራ 28፡31)

ሐዋርያው ጳውሎስ ልክ እንደ አጥማቂው ዮሐንስና ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉ ‹‹የእግዚአብሄርን መንግስት›› ይሰብክ እንደነበረ ከላይ ያሉት ምንባቦች በግልጽ ያሳያሉ፡፡ ይህም የጥንቷ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን የመልዕክትዋ ዋና ቁልፍ የእግዚአብሄር መንግስትና ኢየሱስ ክርስቶስ እንደነበር ያሳያል፡፡ ጳውሎስ ለቆላስያስ ምዕመናን በጻፈው መልዕክቱ ከጨለማው ስልጣን በመዳን ቤዛነት የሆነውን የሐጢያት ስርየት ያገኙ ሰዎች ብቻ ወደ ‹‹ፍቅሩ ልጅ መንግስት›› እንደፈለሱ ግልጽ አድርጓል፡፡ በዚህም ኢየሱስ ‹‹አስቀድማችሁ የእግዚአብሄርን መንግስት…ፈልጉ›› (ማቴዎስ 6፡33) በማለት የሰጠውን መለኮታዊ ምክር ተግባራዊ አድርጓል፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ‹‹ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ›› (ሮሜ 14፡17) መሆንዋን መርሳት አይገባም፡፡ ‹‹ጽድቅ፣ ሰላምና በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታ›› ‹‹ከእግዚአብሄር መንግስት›› ጋር የተቆራኙ ናቸው፡፡

ይቀጥላል…

Читать полностью…
Subscribe to a channel