dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

‹‹ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ኾኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚኾን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፡፡ ይህን ወዷልና፤›› 

(ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ፷፮፥፲፯)፡፡ 

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ።




#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዋዛ ፈዛዛ ነገር ማውራት


"... ልጆቼ! የሚያሳፍር ነገር፣ የስንፍና ንግግር ወይም ዋዛ ፈዛዛ የማይገቡ ናቸውና በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ ከቶ አይሰሙ፡፡ እስኪ ንገሩኝ! የዋዛ ፈዛዛ ንግግር ጥቅሙ ምንድን ነው? እስኪ ንገሩኝ፤ አንድ ጫማ ሰፊ፣ ጫማ እየሰፋ በአንድ ጊዜ ሌላ ሥራ መሥራት ይችላልን? አይችልም፡፡ ከዋዛ ፈዛዛ የሚያሳፍር ንግግር ይወለዳል፡፡ የአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለእኛ ለክርስቲያኖች ዋዛ ፈዛዛ የምንናገርበት ሳይኾን የንስሐችን ጊዜ ነው፡፡ እስኪ አሁንም ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! አንድ ቦክስ የሚጫወት ሰው ውድድሩን ችላ ብሎ ዋዛ ፈዛዛን ይናገራልን? እንዲህ የሚያደርግ ከኾነስ በተጋጣሚው በቀላሉ የሚሸነፍ አይደለምን? ታዲያ ባለጋራችን ዲያብሎስ‘ኮ የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙርያችን ቁሟል፡፡ ጥርሱን እያንቀጫቀጨብን ነው፡፡ እኛን የሚጥልበት ወጥመድ በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ የደኅንነታችን መንገድ ላይ እሳት እየተነፈሰ ነው፡፡ ታዲያ ዲያብሎስ እንዲህ እኛን ለመጣል ሲተጋ እኛ ዋዛ ፈዛዛን፣ የሚያሳፍር ነገርን፣ የስንፍናንም ንግግር ስንናገር ቁጭ ልንል ይገባናልን?

የምወዳችሁ ልጆቼ! ጊዜው የምንተኛበት ጊዜ አይደለም፡፡ የተጋድሎ ጊዜ ነው እንጂ፡፡ ቅዱሳን ጊዜያቸውን እንደ ምን እንደሚያሳልፉት ማወቅ ትፈልጋላችሁን? እስኪ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን አብረን እንስማው፤ እንዲህ ያለውን፡- “ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ”፤ … “በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችኋለሁ…”፡፡ … “የሚደክም ማን ነው፤ እኔ አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፤ እኔም አልናደድምን?”፤ “… በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን”፡፡ ታዲያ እነ ቅዱስ ጳውሎስ ጊዜያቸውን እንዲህ ካሳለፉ፣ ኃጥአን የምንኾን እኛ ጊዜያችንን በሳቅና ስላቅ ልናጠፋ ይገባናልን? በክርስቶስ ፍቅር የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በንግግሬ አትማረሩ፡፡

ጊዜው የተጋድሎ ጊዜ ነው፤ ታዲያ ስለ ምንድን ነው የዘፋኞችን መሣርያ አንሥተን ከዓለም ጋር የምንዘፍነው? በጦር ግንባር ያለ ወታደር ከጠላት ሊመጣ የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል ከመዘጋጀት ይልቅ ጊዜውን በዋዛ ፈዛዛ ያጠፋልን? አያጠፋም፡፡ ታዲያ እኛም‘ኮ የክርስቶስ በጎ ወታደሮች ነን፡፡ ..."

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

በሁሉም ነገሮች ውስጥ ራሱን የሚወቅስ ሰው ብሩክ ነው እርሱ ስለዘለዓለማዊነቱ ትኩረት ይሰጣል ጂ በሰዎች ላይ ስላለ እፍረት ትኩረት አይሰጥም።

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ፫

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ሥጋዊ_አሳቤ 
            
    #አንብቡት_እስቲ_እራሳችን_እንፈትሽበት

🥀እንደ ሰላይ ወዳጅ መስሎ አቅሜን ይለካኛል ። አብሮኝ እየተጋበዘ መድከሜን ለጠላቴ ሰይጣን ያሳብቅብኛል ። የውጭውን ጠላት ስታገል በውስጤ ሥጋዊ አሳቤ ያደባብኛል ። ስቆጣ ሎሌ ፣ ስበርድ ጌታ እየሆነ ይመጣብኛል ። ክረምት ከበጋ ይተጋብኛል ፣ እኔ ተኝቼ ሥጋዊ አሳቤ ከተማ ያስሳል ። ለማመስገን ስነሣ ጉድለቴን ይቆጥርብኛል ። ለመንፈሳዊ ነገር ስታጠቅ በከንቱ ነገሮች ጊዜዬን ይበላል ። ሥጋዊ አሳቤ እንደ ክፉ ጎረቤት ይነዘንዘኛል ። አብረን ማርጀታችን ፣ ስንጣላ ስንታረቅ ዘመን ማሳለፋችን ይደንቀኛል ። ሥጋዊ አሳቤ አካሌ ደክሞ ሳለ ነፍሴን አባብሎ ይወስድብኛል ። ልብ አይሞትምና ነፍሴ ማድረግ ቢያቅታት በአሳብ ስትዘምት ትውላለች ። ነፍሴ በተመስጦ ወደ ሰማይ ስትሄድ ሥጋዬን ይሻረክብኛል ። ሥጋዬ አገሯ መሬት ነውና ከመሬት ስበት ጋር ወደ ታች ትጎትተኛለች ።

🥀በሁለት አሳብ በደግነትና በክፋት ስንገላታ ሥጋዊ አሳቤ ብዙ መረጃዎችን እየጠቀሰ ክፋት ያስከብርሃል ይለኛል ። ነፍሴም መረጃ ከእምነት አይበልጥም ትለኛለች ። አስታራቂ መስሎ ሥራውን የሚሠራ ፣ ለደግነት ትቶ ለክፋት የሚያደላ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ይሞግተኛል ። መቅዘፊያዋን እንደ ጣለች ጀልባ አቅጣጫ እያሳተ ፣ የአሳብ ሰይፍ ፣ የበቀል ስለት እያስጨበጠ ሥጋዊ አሳቤ በቂም ያዘምተኛል ። ከክርስቶስ መከራ ያንተ ይበልጣል እያለ ያስታብየኛል ። ሥጋዊ አሳቤ ገላጋይ መስሎ የሚያስደበድበኝ ፣ ጠበቃ መስሎ የሚያስረታኝ ፣ ወዳጅ መስሎ ወደ ገደል የሚገፈትረኝ እርሱ ነው ። በዝማሬ ውዬ በልቅሶ እንዳድር ፣ በፍቅር ውዬ በቂም እንድሰክር የሚያደርገኝ ፣ አንዱን ቀን ሁለት የሚያደርግብኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ።

🥀እንደ ማጥ ጉዞ ወጣሁ ስል የሚይዘኝ ፣ ጨረስሁ ስል የሚያስጀምረኝ ፣ ሸመገልሁ ስል ልጅ የሚያደርገኝ ፣ ታጠብሁ ስል መልሶ የሚያቆሽሸኝ ፣ ተፋሁ ስል እንደ ውሻ የሚያስልሰኝ ሥጋዊ አሳቤ በክለሳ ኑሮ የሚያደክመኝ እርሱ ነው ። በእምነት ሰላሜን አገኘሁ ስል በአዳዲስ ጉድ የሚያናውጠኝ ፣ እጆቼን ፣ ዓይኖቼን ፣ ጆሮዎቼን እየኮረኮረ ክፉ ወሬ የሚያስቃኘኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። አዳም ሲወድቅ ውስጤ የገባው ረቂቅ መንግሥት ሥጋዊ አሳቤ ነው ። ሳላውቀው ከእኔ ጋር የኖረው ፣ ተገላገልሁት ለማለት የማልደፍረው ጠላቴ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። አገሬ በሰማይ ነው ስል ጎሣ የሚያስቆጥረኝ ፣ ተበደልሁ እንጂ በደልሁ የማያሰኘኝ ፣ መንግሥተ ሰማያት ላያስገባኝ ትክክል ነህ እያለ የሚያጸድቀኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። አገልግሎት ሕይወትህ ነው እያለ ከሰው የሚያጋድለኝ ፣ ሕይወት ክርስቶስ መሆኑን በዘዴ የሚያስጥለኝ ፤ ከመድረክ አትጉደል እያለኝ ከጽሞና የሚያጎድለኝ ፣ በዘዴ የጠለፈኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ።

🥀ኃጢአትን ጽድቅ ለማድረግ ሱባዔ የሚያስገባኝ ፣ ሃይማኖቴን ለመለወጥ የሚያጸልየኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። እንደ አቡን ሥልጣነ ክህነት የሚሰጠኝ ፣ ሳልሾም የተሾሙትን የሚያስንቀኝ ፣ የሕልም ዓለም የሚያወርሰኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነውና በቁም የሚያቃዠኝ ። ሚስቴን አመንዝራ ፣ ወዳጄን ጉድጓድ ማሽ አድርጎ የሚስልብኝ አእምሮዬን የሚያቆሽሸው ፣ ባልተጨበጠ ነገር የተጨበጠ ጦርነት የሚሰጠኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ።በስግብግብነት ከተማውን ካልገዛህ የሚለኝ ፣ አልጠግብ ብዬ ስተፋ የሚያሳድረኝ ፣ የኪስ ጣዖት የሆነውን ገንዘብ የሚያሳየኝ እርሱ ሥጋዊ አሳቤ ነው ። በአሥራት ታማኝ አድርጎ ለድሀ የሚያስጨክነኝ ፣ ሬሳ እየተራመድሁ እንዳልፍ የሚያደርገኝ እርሱ ነው ፤ ሌላ ጊዜም ለድሀ ቸር አድርጎኝ የእግዚአብሔር ሥራ እንዲበደል አሥራቴን የሚያሰርቀኝ ሥጋዊ አሳቤ ነው ፣ ጎዶሎ ጽድቅ ውስጥ የሚያስዋኘኝ ። ከሥጋው ጦመኛ ነኝ ፣ ከመረቁ አውጡልኝ የሚያሰኘኝ ፣ ከወገብ በላይ ታቦት ፣ ከወገብ በታች ጣዖት የሚያደርገኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው በሁለት ማንነት የሚያኖረኝ ።

🥀ካድሁ እንዳልል በሃይማኖታዊ ፉከራ እየጠመደኝ ፣ ቀጥሎ ሁሉን የሚያስረሳኝ ፣ በስሜት እሳት የሚያሟሙቀኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው እኔን ለእኔ ያስጠፋኝ ። እያደባ የሚይዘኝ አውሬ ፣ እንደ እባብ ለመንደፍ የሚለሰልሰኝ ጠላቴ እርሱ ሥጋዊ አሳቤ ነው ። ሁሉም ሰው ኀጥእ ነው ብሎ ኃጢአት አሠርቶኝ ፣ ቀጥሎ አንተማ ከእንግዲህ ክርስቲያን አይደለህም የሚለኝ ፣ አሳስቶ የሚከሰኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። የሰይጣን ቆንሲል ሁኖ በውስጥ የሚዋጋኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። እንደ ክፉ ጎረቤት የሚነዘንዘኝ ፣ እንደማይሸጡት ልጅ መላቀቂያ ያሳጣኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። እንደ ባሕር ንውጽውጽታ የማያጣው ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። የዘመኑ ሰማዕትነት ሥጋዊ አሳብን ማሸነፍ ነው ። እባክህ ጌታዬ ሥጋዊ አሳቤን አሸንፌ መንፈሳዊ እንድሆን ፣ የጨለማን አሳብ ጥላቻን ድል ነሥቼ ውሉደ ብርሃን እንድሆን እርዳኝ ። ክፉ ከሆንሁት ከራሴ አድነኝ  አሜን።(ፍቅርተ ኢየሱስ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን 🤲

                   
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ዕለታዊ_መልዕክት

አንዳንዶቻችን መንፈሳዊ ጽሁፍ መጻሕፍት ስብከት መዝሙር ጊዜ የለኝም እንጂ ቢያነብ ቢያዳሚጥ ጥሩ ነው እንላለን !!!

። አንዳንዶቻችሁ ደሞ ጊዜ የለንም ትላላችሁ ለማንበብ። ቆይ ከጓደኞቻችን ጋር ለመጫወት፣ ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ facebook , Tik Tok , YouTube እና ሌሎች ማህብረዊ ድህረ ገፆች ላይ የተለቀቁ ቪዲዮዎችን ለማየት፣ ስለ ሰዎች ለማወቅ፣ ዜና ለመስማት፣ ወሬ ለመስማት፣ ለኳስ.... ለብዙ ብዙ ስጋዊ ነገሮች ጊዜ አለን ይሄ ጊዜ ከ24 ⌚ ሰዓት በተጨማሪ ከዬት የመጣ ነው፣ መንፈሳዊ ፅሁፎችን በቀን 5 ደቁቃ እንኳን ለማንበብ ረዘመ እንላለን። በቀን አንድ ምዕራፍ ከመፅሀፍ ቅዱስ ለማንበብ እንኳን በዛ እንላለን። ዘፈን ለማዳመጥ ሲሆን ጊዜ አለን መዝሙር እና ትምህርቶችን ለመስማት ግን ጊዜ የለንም። ለምን??

ሰንበት ትምህርት ተማሩ ስንባል አብዛኞቻችን ጊዜ የለኝም አይመችም እንላለን። በሳምንት 6ቀን የአለማዊ ትምህርት ለመማር እና ስድስት ቀን ለመስራት ጊዜ አለን በሳምንት 1 ቀን ግን ለነፍሳችን ሚጠቅመውን ቃለ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ሄዶ ለመማር ጊዜ የለንም ለምን??

እስኪ ልጠይቃችሁ ሁለት ፍቅረኛሞች በጣም እንዋደዳለን እንፋቀራለን ቢሉ ግን ባይገናኙ፣ ባይደዋወሉ፣ አንዱ ስለ አንዱ ማንነት የማያውቅ ከሆነ፣ ካልተጠያየቁ በችግርም በደስታም አብረው ካልተባበሩ ምኑ ላይ ነው ፍቅራቸው?? እኛም እኮ እንዲው ነን፣ እግዚአብሔርን እንወዳለን እንላለን፣ ለስሙ ክርስቲያን ነን ግን ከእግዚአብሔር ብዙ ርቀናል። በህይወታችን እኮ ቦታ ስንሰጠው ነው መውደዳችን ሚገለጠው። በነገሮች ሁሉ እሱን ስናስቀድም ነው መውደዳችን ሚታወቀው። እንወደዋለን ግን ለሱ ጊዜ የለንም።

ግን እንደው አንዳንዴ ሳስበው ግርም ይለኛል። የሰማይ እና የምድር ንጉስ፣ መላእክት በፊቱ የሚንቀጠቀጡለት፣ ሁሉ የሚታዘዝለት ሁሉን የሚችል አምላክ እኛን ለማናገር ጊዜ የለኝም ሳይለን እኛ ግን እሱን ለማናገር(ለመፀለይ) ጊዜ የለኝም እንላለን። እንደው ምሳሌ ልስጣችሁ አሁን ጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር አብይ ልናገኛቸው ልናወራቸው ብንሄድ እንዴት በአክብሮት እንዴት በስርዓት እንዴት በተጠንቀቅ እና በጉጉት ነው ሚሆነው። እግዚአብሔርንስ ለማናገር ሲሆን ምን ያህል ደስተኞች ነን? ምን ያህል እንደ ትልቅ ነገር እንቆጥረዋለን ከሱ ጋር ማውራታችንን? ምንስ ያህል በስርዓት እና በቁምነገር ነው??

እለት እለት በምናደርጋቸው ነገር ሁሉ እራሳችንን እየመረመርን ከራሳችን ጋር መታገል ያስፈልጋል። አካሄድን መመርመር። ውሳኔያችንን መመርመር። እርምጃችንን መመርመር? አንድ ነገር ከማድረጋችን በፊት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ወይስ ይህ ነገር ሀጥያት ነው ብለን ማስብ አለብን መጀመርያ። ምንም አይነት ነገር ከማድረጋችን አስቀድሞ እኮ ሊታሰብ የሚገባው አምላክ አለን። በስጋዊ ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊውም ጉዳዬች።


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አንዳንድ ሰዎች እጅግ የጠለቀ ሃዘንና መቆርቆር ውስጥ ሲገቡ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ረስቶኛል” ብለው ሲያማርሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ነቢዩ እንዲህ ከሚሉ ሰዎች ጋር ክርክር አለው፡፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀኗ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃኗን ትረሳ ትችላለችን?” በማለትም ይጠይቃቸዋል (ኢሳ.49፥14)፡፡ ይህም ማለት ሴቷ ከማኅፀኗ የተወለደው ልጇን ልትረሳ ዘንድ እንደማይቻላት እግዚአብሔርም ሰውን ይረሳ ዘንድ ባሕርይ አይደለም እያላቸው ነው፡፡

ነቢዩ ይህን ምሳሌና ማነጻጸርያ አንሥቶ ክርክር መግጠም የፈለገው እያንዳንዷ እናት ለልጇ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኾኖም ይህን ያህል የምናንቆለጳጵሰው የእናት ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው “አዎን እርሷ ትረሳ ይኾናል፤ እኔ ግን አልረሳሽም… ይላል እግዚአብሔር” በማለት የሚቀጥለው፡፡ እንግዲህ የአምላካችን ፍቅር እንደምን የበዛ እንደ ኾነ ታስተውላላችሁን?

እንግዲያውስ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አባት ለልጆቹ እንዲያዝን እንዲራራ እንደዚህም ኹሉ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይራራለቸዋል” ብሎ እንደተናገረ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ትቶኛል” የሚል ማንም አይገኝ (መዝ.102፡13)፡፡ ጆሮን የፈጠረ እርሱ ይሰማል፤ ዐይንን የፈጠረ እርሱ ያያል፡፡ እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ የቀረጻቸው ልጆቹን አይረሳም፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✍የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስብከት ይፈልጋሉ ❓

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🙏ጸሎት የተሰኘ አዲስ ግሩም ኦርቶዶክሳዊ 🙏

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🙏ጸሎት የተሰኘ አዲስ ግሩም ኦርቶዶክሳዊ 🙏

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#የመጨረሻ_ክፍል

#ራስን_መግዛት (ክፍል- ፭)

#ምኞትና_የበላይነት

መንፈሳዊው ሰው ምኞቱን፣ ደስታውን መውደዱንና የበላይነቱን አስመልክቶ ራስን መግዛት አለው:: በራሱ ዓይኖች ፊት ራሱን አዋቂ አድርጎ ሲያገኘው ወይም በአመለካከቱ ውስጥ ራሱን አጽድቆ ሲመለከት ወይም ደግሞ ራሱን ከሚያስበው በላይ ከፍ አድርጎ ሲያስብ ራሱን ለመግዛት ይጥራል፡፡ ሮሜ 12፥3

ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔር ከሰጠው ጸጋ በላይ ራሱን ሊያልቅ አይሞክርም፡፡ ዲያብሎስ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ብሎ በትዕቢት የተነሣው ራሱን መግዛት ባለመቻሉ ስለሆነ ወድቋል። ኢሳ. 14፥14

መንፈሳዊው ሰው ራሱን የሚገዛው ውዳሴ ከንቱን አስመልክቶ ብቻ ሳይሆን ስጦታዎችንም በተመለከተ ነው:: ወይም ደግሞ ሰውየው ራሱን ከፍ ከፍ እንዳያደርግ እግዚአብሔር እርሱነቱን የሚገዛበትን መንገድ ያመቻችለታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ የተናገረውን ቃል አትርሱ! «ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።» 2ኛ ቆሮ. 12፥7።

#ወንድሜ_ሆይ! አሳብህ ከፍ ከፍ ባለብህ ጊዜ ሁሉ ተቆጣጠረው። ራስህን ከተሰጠህ በላይ አድርገህ አትገምት፡፡ አንተነትህን ከሌሎች ጋር አነጻጽረህ ወደምትመለከትበት ደረጃ የሚመሩህ ምኞቶችህን ግታቸው፡፡ ራስህን ከፍ ከፍ ብሎ ስታየው ወይም ደግሞ በፊትህ ታላቅ ሆኖ ስታገኘ ው ታዛዥነትህን፣ ትሕትናህን፣ ለሌሎች ያለህን ክብር በማጣት ላይ መሆንህን እወቅ፡፡ በማንኛውም ጊዜ ከፊት ለፊትህ የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አኑር። «ትዕቢት ጥፋትን ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።» ምሳ. 16፥18::

#በሕይወት_ዙሪያ

ራስን መግዛት መላ ሕይወትን ያጠቃልላል፡፡ መንፈሳዊው ሰው ምቾትንና ድሎትን አስመልክቶ ራስን መግዛት አለው፡፡ እርሱ ሰዓቱን በትክክል ይጠቀማል፡፡ በመሆኑም ጊዜውን ለሚሠራው መንፈሳዊ ሥራ ያከፋፍላል። ቀጠሮ ያከብራል:: በተሰደበ ወይም በተጠቃ ጊዜ ሰራሱ ሊበቀል እንዳይነሳሳ ራሱን ይገዛል፡፡ ገንዘብን በተመለከተም ስለሚቀበለውና ስለሚስጠው ገቢና ወጪ ላይ ራሱን ይገዛል። ከሌሎች ጋር የሚያደርገው ግንኙነት እስከ ምን ድረስ መሆን እንዳለበት ይረዳል:: ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ እንዳያጋድል የልቡን ስሜታዊነትና ፍላጎት ይቆጣጠራል:: ሌላው ቢቀር በአምልኮ፣ በአገልግሎት፣ሌሎችን በመቆጣጠርና ሌሎችም ባሉበት ኃላፊነቶች ውስጥ ራሱን ይገዛል::

#ለማጠቃለል
በዚህ ጉዳይ ላይ የምስጠው ጠቃሚ አስተያየት ራሱን ከውስጥ መቆጣጠር የማይችል ስው ከውጪ የሌሎች ቁጥጥር እንደሚያስፈልጉት የሚገልጽ ነው:: እርሱ ራሱን ከውስጥ መቆጣጠር ካልቻለ ቁጥጥሩ ያለ ፈቃዱ ከውጪ ይመጣል። ከውጪ የሚመጡት ኃይላትም አመሉን በቅርብ የሚያውቀውና ኃላፊነቱን የሚጠይቀው ኅብረተሰብ አንዱ ሲሆን የሚመለከቱት ዓይኖችና የሚሰሙት ጆሮዎች ተጠያቂ ያደርጉታል። ከዚህ በኋላ በፍርሃት ይገዛል ወይም በእፍረት ይሸማቀቃል፡፡ በመጨረሻም በሕግና ከበላይ አካላት በሚመጡ ውሳኔዎች እንዲቆጣጠሩት ይሆናል::

ወይም ደግሞ በመንፈሳዊ ምክሮች ከገደቡ እንዳያልፍ አድርገው ያቆሙታል፡፡ ከዚህ ካለፈ ስህተቱን እንዳይደግም በሚያደርጉት ውጪያዊ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ይወድቃል:: ነቢዩ ዳዊት ራሱን ባለመግዛቱ ብቀላ ከመውሰድ ራሱን ሊከለክል አለመቻሉ በጣም ያስደንቀኛል። በዚያን ወቅት ለእርሱ ውጪያዊ ኃይል ስላስፈለገው አቢግያ በጥበብና በእውቀት እንድትገሥጸው ሆኗል። 1ኛ ሳሙ. 25::

አንድ ሰው ያለራሱ ፈቃድ በሌላ ቁጥጥር ውስጥ ከሚገባ ወይም በውጪያዊ ኃይል ከሚገዛ ይልቅ ራሱን በመንፈሳዊነት ገዝቶ መለኮታዊውን ዋጋ ቢያገኝ ይሻለዋል ይበጀዋልም:: መንፈሳዊው ሰው ግን ራሱን የሚገዛው ከውስጥ ነው:: በዚህ ጊዜ ውጊያዎች ከመጡበትም ምንጊዜም ቢሆን የሚፈልገው የልቡን ንጽሕና እና የተቀደሱ ሥራዎቹን ስለሆነ የተለያዩ መንፈሳዊ እርምጃዎችን ይወስዳል::

(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ  ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ራስን_መግዛት  (ክፍል-፫)

#መብላትና_መጠጣትን_መግዛት

ብዙ ሰዎች «ዳይት» በሚለው አካሄድ ምግብን ከወትሮው በመቀነስ ራሳቸውን ተቆጣጥረው ክብደታቸውን ይቀንሳሉ፡፡ ይህን የሚደርጉትም ለስኳር በሽታ፣ ለልብ ሕመም፣ ለደም ብዛትና ስብ (ውፍረት) ለመቀነስ ሲሉ ነው:: መንፈሳዊው ስው ግን ምግቡንና መጠጡን የሚቆጣጠረው ለመንፈሳዊ ምክንያቶች ነው፡፡ ይህም ጾምንና መከልከልን ያካትታል፡፡ እርሱ እዚህ ላይ ራሱን የሚገዛው ሥጋውን አድክሞ ለመንፈሱ የትጋት ጊዜ ለመስጠት ነው::

ምግብን አስመልክተን ስንናገር እናታችን ሔዋን ራስዋን መግዛት እንዳልቻለች እናስታውሳለን። እርሷ ራስዋን መግዛት ስላልቻለች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፍ እንዳትበላ ከተከለከለችው ዛፍ ፍሬዋን ቆርጣ በልታለች:: አባታችን አዳምም እንዲሁ ተቀብሎ በልቷል:: በዚህም የመጀመሪያው ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፡፡

እዚህ ላይ ከውድቀት በፊት ቀድሞ የመጣው ስሜትን ለመቆጣጠር አለመቻል ነው:: በመሆኑም የመጀመሪያው ኃጢአት የተፈጸመው ሔዋን እባቡን በመስማቷ ወይም ደግሞ «ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነና ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ . . » አይታ ስለጎመጀች ነው:: ዘፍ. 3፥5:: በእርግጥም አንዱ ኃጢአት ወደ ሌላኛው ኃጢአት ስለሚመራ በመጀመሪያ ከስሜት ወደ አሳብ፤ ቀጥሎም ወደ ልብ፤ ከዚያም ወደ ድርጊት ያሸጋግራል፡፡

#ቁጣን_በተመለከተ ...

ይኼኛውን «ነርቭን መግዛት» ልንለው እንችላለን፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል መንፈሳዊው ሰው ዘወትር ከቁጣ ለመራቅ ይሞክራል:: «...የሰው ቁጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።» ያዕ. 1፥20:: እርሱ ንዴት በልቡ ውስጥ መንቀሳቀስ መጀመሩን ሲያውቅ ምላሱንና ነርሹን እንዲቆጣጠሩበት አይተዋቸውም:: ስለሆነም በቁጣ ጊዜ ቃላቱን በሚገባ ለመቆጣጠር እንዲችል ወይ ዝም ማለትን ይመርጣል አሊያም ንግግሩ እንዲዋጥ ያደርጋል፡፡

ከሁሉ በላይ ደግሞ ቁጣን ከልቡ ውስጥ ያባርራል:: በዚህም በሚችለው ሁሉ በቁጣ እንዳይቀጣጠልና ድምፁ ከፍ ብሎ እንዳይወጣ ያደርጋል። በተጨማሪም ገጹን አያጨፈግግም:: በዚህ ጊዜ አኳኋኑ ሁሉ የሐዋርያውን ቃል የተከተለ ይሆናል፡፡ «ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ይሁን . . » ያዕ. 1፥19:: ለቁጣ የፈጠነ ሰው በጥድፊያ ስለሚወድቅ ብዙ ኃጢአት ይፈጽማል: በተረጋጋ ጊዜ በወሰደው የተሳሳተ እርምጃው አብዝቶ ይጸጸታል። በመጨረሻም መስኮታዊውን መልክ ስለሚያጣ ለብዙዎች የማሰናከያ በቁጣው ውስጥ ድንጋይ ይሆናል።

መንፈሳዊው ሰው በቁጣ ውስጥ እያለ ደብዳቤ አይጽፍም:: ብስጭት ውስጥ እያለም ውሳኔ አይወስንም:: ምናልባት ግን በቁጣ ውስጥ እያለ ደብዳቤ ከጻፈ ተጣድፎ ወደ ፖስታ ቤት አይልከውም ለአንድ ለሁለት ቀን እንዳለ ያስቀምጠዋል:: ከዚህ በኋላ በድጋሚ ያነበውና ወይ ቀዶ ይጥለዋል አለበለዚያም ሌላ ይጽፋል:: ይህን በማድረጉም ይህ ነገር በእርሱ ላይ የኃጢአት መረጃ እንዳይሆንበትና ውጤቱም የማያስደስት ሆና እንዳይቀር ያደርጋል:: በተናደደ ጊዜ ውሳኔዎቹን የሚወስደውም ባለማስተዋል ነው:: እንደነዚህ ዓይነቶቹ ውሳኔዎች «ስሜታዊ ውሳኔዎች» ተብለው ይጠራሉ:: ብዙዎቹ የተሳሳቱና ተገቢ ያልሆኑ ውሳኔዎች ናቸው:: ከዚህ ጋር በተያያዘ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:: «በነፍስህ ለቁጣ ችኩል አትሁን፤ ቁጣ በሰነፍ ብብት ያድራልና: መክ. 7፥9::

ይቀጥላል....

(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ  ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የስብከተ ወንጌልን ተደራሽነት ለማስፋት 36 ሰባኪያነ ወንጌል ተመረቁ ፡፡

በጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ ፣ ቦረና ፣ ምሥራቅ ቦረና እና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከትና በማኅበረ ቅዱሳን ትብብር  የአገልጋይ እጥረት ካለባቸው ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ  36 ሠልጣኞች ለ 3 ወራት  የተለያዩ ሥልጠናዎችን ሲከታተሉ  ቆይተው  ታኅሣሥ 7 ቀን 2016 ዓ.ም  ሊቀ ማዕምራን ጌታሁን ሞርኪ የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅና የተለያዩ የሀ/ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ምእመናን በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡

     በሀገረ ስብከቱ የሚታየውን የሰባኪያነ ወንጌል እጥረት መቅረፍና ስብከተ ወንጌልን ማስፋት ዓላማውን ያደረገው ሥልጠና  ትምህርተ ወንጌልን በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ ለማድረግ ሠልጣኞቹ የኦሮምኛ፣ጌድዮኛ፣ ኮንሶኛ፣ ሶማልኛና አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ  በመሆናቸው የቤተክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልእኮ ከማስፈጸም አንጻር ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።  

በሥልጠናውም ነገረ ሃይማኖት ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ የስብከት ዘዴ ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ ድኅነት እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች የተካተቱ ሲሆን  ሥልጠናው በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ከ 6 ዓመታት በፊት በነገሌ ቦረና ለሀ/ስብከቱ በተሠራው  አዳሪ አብነት ት/ቤት የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

   አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

የሚያየውን ዓለም ለውጦ ባላየው
ሳሙኤል በትኅርምት ስላገለገለው
የሰማዩን መንግስት አምላክ አወረሰው
ከሀገሩ ወጥቶ ተከዚን መሻገር
ኮሮጆ አልያዘም አልያም ወርቅ ብር
የርሱ ወርቅ እንቁ በገዳሙ ሲኖር
የድንግል ቅዳሴ ውዳሴዋ ነበር
በጽድቅ በትሩፋት ብርሃን ቢሆን ለዓለም
ለእርሱ ተገዙለት አናብስተ ገዳም
አምላኩ በሰጠው ክቡር ቃልኪዳን
ጻድቁ ሳሙኤል እንዲያማልደን
በስሙ እናስብ ችግረኛውን
በጻድቁ ስም በጎ የሠራ በፍቅር
ያገኘዋልና የጻድቁን ክብር




#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ራስን መግዛት (ክፍል -፩)

መንፈሳዊው ሰው ካሉት ብቃቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ራስን መግዛት ነው፡፡ እርሱ ራሱን ለሥጋ ምኞትና ለፍላጎቶቹ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ሕሊናው የኃጢአትን ምኞት ሲናፍቅ ይህን አሳቡን በመቃወም መንፈሱ እንድትመራው በማድረግ ራሱን አጥብቆ ይገዛል:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- «በመንፈሱ ላይ የሚገዛ (መንፈሱን የሚገዛ) ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል፡፡» ምሳ. 16፥32

እንደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ራሱን የሚገዛ ወይም የሚመራ ማለት ሥጋው የጠየቀውን ሁሉ የማይሰጥ ይልቁኑ የሚቃወም ማለት ነው:: «ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፤ነፍሱን በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል፡፡» ዮሐ. 12፥25።

ራስን መግዛት በውስጡ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉት እርግጥ ነው፡፡ እነርሱም፤-

1. #ምላስን_መግዛት፡፡
2. #አሳብን_መግዛት::
3. #ልብን_መግዛት፡፡ (ፍላጎትንና ምኞትን በመግዛት)
4. #ስሜትን_መግዛት::
5. #ሆድን_መግዛት (ምግብን በተመለከተ) ናቸው፡፡

ራሱን የሚመራ ሰው እርሱነቱን ለእሴትና ለዓላማ እንዲሁም ለሕግና ደንብ ያስገዛል፡፡ ራሱን መምራት የማይችል ሰው ግን በእርግጥ እርሱነቱን ለጥፋት ይጋብዛል፡፡ ራሱን የሚገዛ ሰው ነፍሱን በእውነተኛ ፍቅር ይወዳታል:: ራሱን የሚያቀናጣ ግን ነፍሱን ከማጣቱም በላይ ሌሎችም ከእርሱ ጋር አብረው እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ ራሱን አጥብቆ የሚጠብቀው በትጋቱ ነፍሱን ስለሚጠብቃትና በመልካም ሁኔታ ስለሚይዛት ያድናታል፡፡ አልፎ ተርፎም ሌሎችን ለማዳን ምክንያት ይሆናል፡፡ የራሱን አመለካከትና ግንኙነት በቅደም ተከተል ያደራጃል፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ያስቀድማል፤ በመቀጠል ሰዎችን ያስከትላል፤ በመጨረሻም ራሱን።

#ምላስን_መግዛት፡፡

መንፈሳዊው ሰው ቃላት ወይም አሳቦች ያቀበሉትን ወደ አእምሮው የመጡትን ሁሉ በአንደበቱ አይናገራቸውም፡፡ እያንዳንዱን ቃል ከአንደበቱ ከማውጣቱ በፊት ይመዝናል:: የእርሱ ሚዛን የሚለካው የቃሉን ፍሬ ነገር ብቻ ሳይሆን ትክክል መሆኑንና አለመሆኑንም ጭምር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእርሱ ዋና ዓላማው ቃሉ በሌሎች ሰዎች ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ፣አፀፋና ውጤቱን ጭምር ነው::

የምላስ ወይም የአንደበት ስህተት ውጤት ሥጋን ማሳደፉንና የፍጥረትንም ሩጫ ማቃጠሉን የሚያውቅ ሰው ከመናገሩ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል:: ያዕ. 3፥5-6:: ከነቢዩ ከዳዊት ጋር ሆኖም:- «አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ፡፡» ይላል፡፡ እርሱ አንዴ ከአፉ የወጣው ቃል ተመልሶ ሊገባ እንደማይችል ያውቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከአፉ የወጣው ቃል አድማጮቹ ጆሮ ከደረሰ በኋላ የተናገረውን መልሶ ሊውጠው፣ ወይም ይቅርታ ሊያገኝበት እንደማይችል አስቀድሞ ያውቃል:: ከዚህ በኋላ ስህተቱን ለማስተካከል ቢጥርም ጥፋቱ በእርሱ ላይ ዕዳ ሆኖ እንደሚቆጠር አጥብቆ ይረዳል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ጌታ እንደተናገረው እንደሚኮነንበት ያውቃል፡ . . . ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና፤ ከቃልህም የተነሣ ትኮነናለህ፡፡» ማቴ. 12፥37::

#ይቀጥላል...

(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ  ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)



#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ቁጣ_ድል_አይንሣህ
(#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ)

ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር ሰውነትህን አትጋት። ባገኘህውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው፤ በጎ አድርግለት አክብረህ ወደህ እየው፡፡ ሥራው ባይደለ ሥራ አመስግነው፣ ከአንተም በተለየ ጊዜ የእሱን ነገር ተናገር፡፡ ከበጎ ሥራው ወገን መናገር በሚቻልህ ገንዘብ በጎ በጎ አድርግለት፡፡

በጎ ነገር በመናገርህ ወደ በጎ ሥራ ትስበዋለህ ታነቃቀዋለህ፡፡ አንተ ባመሰገንከው ምስጋና፣ አንተ ባከበርከው ክብር የተነሣ ያፍር ዘንድ እንዳመሰገንከው ያልሆነ እንደሆነ ያፍራል፤ እንዲህ የሆነ እንደሆነ ዘርአ ትሩፋትን ትዘራበታለህ፡፡

ነፍስህ ከለመደችው ባልንጀራህን ከማክበር የተነሣ በጎ ነገርን መውደድ በልቡናህ ይቀርጻል፡፡ ፍጹም ትሕትናን ገንዘብ ታደርጋለህ ሳትጥር ብዙ ሥራ ትሠራልህ፡፡ የምታከብረው በጎውን ሰው ብቻ አይደለም ነውር ያለበትም ቢሆን አክብረው እንጂ፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ አንተ ካከበርከው ክብር የተነሣ አፍሮ ካንተ ድኅነትን ያገኛል።

ገንዘብህ የምትሆን ይህችን ጥበብ ለሁሉ አድርጋት፤ ጥበብም የተባለች ሰውን ማክበር ለሰው ማዘን መራራት ናት። አንዱንስ እንኳን አትቈጣ፣ ተቈጥተህ አታሳዝነው፣ ቍጣ ድል አይንሳህ፡፡ ስለ ሃይማኖትም ቢሆን፣ ሥራው ክፉ ስለሆነም ቢሆን ሰው እንዳታማ ተጠበቅ እንጂ አትፍረድበት፡፡ በልዕልና ፊት አይቶ ሳያዳላ የሚፈርድ ዳኛ ክርስቶስ አለንና፡፡ ወደ በጎ ሥራም ልትመልሰውም ብትወድ እዘንለት፤ እያለቀስህ የለዘበ ነገር ንገረው፤ በቍጣ አትናደድበት፤ ጸብ ያለህ ይመስለዋል ፍቅር ውስጣዊ ቍጣን አይሻምና።

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለኢየሱስ ክርስቶስ
እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
በቤተልሔም የተወለደው ጌታ ዛሬ ልባችን እንደ ቤተልሔም ጌታን ለመቀበል ከኃጢአት ከክፋት ተለይቶ በንስሐ ተዘጋጅቶ በቤተልሔም ሰውና መላእክት በአንድነት እንደ ዘመሩ በእኛ መመለስ ቅዱሳን ሰዎችና መላእክት ይደሰቱ ዘንድ በቤተልሔም የተወለደ ጌታ የበቃን ያድርገን

መልካም በዓል ይሁንላችሁ


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አርበኛና ካህን ሞትን የማይፈራ፣ ለሆዱ ሳይሆን ሁልጊዜም ለእውነት የሚኖር መሆን ይገባዋል። በዚህ ምድር የምንኖረው ለአጭር ጊዜ ነው። ስለዚህ ለዚህች አጭር ሕይወት ብሎ ዘለዓለማዊውን ሕይወት የሚያሳጣ ድርጊት ማድረግ አይገባም። መፍራት ያለብን እግዚአብሔርን ብቻ ነው። አድርባይነት፣ ዘረኝነት፣ የሥልጣን ጥማት፣ ግላዊ ክብርና የመሳሰሉ ጉዳዮች ፍጻሜያቸው ውርደት ነው። እውነትን ይዘን ውሸትን እስከሞት ድረስ መታገል ያጸድቃል እንጂ አያስወግዝም። እውነትን ይዘው ለሚታገሉ ጀግኖች እግዚአብሔር እድሜንና ጤናን ይስጥልን።

ከእውነተኞች ጋር እውነት የሆነው መድኃኔ ዓለም ሁልጊዜም ከእነርሱ ጋር አለ። ከሐሰተኞች ጋር ደግሞ የውሸት አባት ዲያብሎስ ከዚያ አለ። ሰይጣን ቢረዳህ እስኪያዋርድህ ድረስ ብቻ ነው። የእግዚአብሔር እርዳታ ግን ዘለዓለማዊ ሕይወትን እስከማግኘት ያደርሳል።

የሚዲያ ጋጋታ መሬት ላይ ያለውን እውነታ አይቀይረውም። ነጩን ጥቁር ቢሉት ነጭነቱን አይቀይረውም። ጥቁሩን ነጭ ቢሉትም ጥቁርነቱን አይለውጠውም።


መ/ር በትረ ማርያም

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ለሥጋም ለነፍስም የማይጠቅም መልካም ሐሳብ የለም። እንዲሁ በሥጋም በነፍስም ጉዳትን የማያመጣ ክፉ ሐሳብም የለም። ሐሳብ ሲቀደስ ንግግርና ተግባርም ይቀደሳሉ። ሐሳብ ሲረክስ ደግሞ ንግግርና ተግባርም ይረክሳሉ። ሰው ልዑል ኅሊና ሲኖረው በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል። ትምክህቱም፣ ደስታውም እግዚአብሔር ይሆናል።

በሥጋዊ ጥቅም የማይታለል፣ ሥጋዊ መከራን የማይሰቀቅ፣ ለእውነት ያደላ ንጹሕና ልዑል ኅሊና ሊኖረን ይገባል


(መምህር በትረ ማርያም አበባው)

#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+++የማይተወን እረኛችን! ኖላዊ ዘበአማን!+++

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ‹‹እረኞች ያመሰገኑት በግ እና እረኛ›› ብሎ ክርስቶስን ይጠራዋል (Select Orations of Saint Gregory Nazianzen, Nicene and Post Nicene Fathers Series II, Volume 7, 1893; Page 436) ፤ እርሱ ስለ እኛ ስለበጎቹ መዳን የሚሰዋ በግ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ፤ በሌላ በኩል ስለ በጎቹ ነፍሱን የሠጠ ቸር እረኛም ነው ፤ በወንጌል ‹‹ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል” ካለ በኋላ “እንደ ገና አስነሣት ዘንድ እኔ ነፍሴን እሰጣለሁና” (ዮሐ. 10፡17) ይላል፡፡ “እርሱ ሞቶ በጎቹን የሚያድን ከሞት የሚያስነሣ እንዲህ ያለ እረኛ ከወዴት ይገኛል? የበጎቹን ሕመም ሕመሙ አድርጎ መድኃኒቱን ቀምሶ የሚያቀምስ እረኛ እንደምን ያለ እረኛ ነው?”

+++

አቤቱ መልካሙ እረኛዬ ሆይ! እኔ ለዐይኖቼ የቀረበውን ለጊዜው የታየኝን አረንጓዴውን ለምለም መስክ እያየሁ ከፊት ያለው ገደል ተዘንግቶኛል ፤ ጤና ፤ ትዳር ፤ ልጅ ፤ ገንዘብ ፤ ጊዜያዊ የሕሊና ዕረፍት ፤ እንዲሁም ምኞትና መሻቴን የማገኝበትን የትኛውንም ፈጣንና አቋራጭ መንገድ ስለመጠቀም እንጂ ፤ ከበስተኋላው ያለውን ጥፋት አስቀድሞ ማስተዋል ተስኖኛል ፤ ቸሩ እረኛዬን አንተን መከተል ከተውኹኝ ሰነባበትኹኝ፡፡

የጨበጥኹትና ያገኘሁ የመሰለኝ ነገር ፤ አንተንና ቅዱሱ በረትህን አስረስቶኛል ፤ ጌታ ሆይ የአንተ እረኝነት ልክ እንደ ትላንቱ ዛሬም አልተለወጠም በትዕግሥት ለሚጠብቁህ ፤ ቃልህን ጠብቀህ እንደምትሠጣቸው እንደምታድናቸው ፤ ከሚያስጨንቃቸውም እንደምታሳርፋቸው ፤ ሕይወትህን ስለ በጎችህ የምትሠጥ ቸር እረኛ መሆንህን አውቃለሁ፡፡

የማውቀውን መኖር በሕይወት መተርጎም ግን እጅጉን ከብዶኛል ፤ እኔ ደካማ በግህ የጊዜ ሠሪና ፈጣሪ አንተ መሆንህ ከልቡናዬ እየተሰወረብኝ ፤ አንተን በመጠበቅ ከነገሮች የዘገየሁ ይመስለኛልና ማስተዋልን አድለኝ!!! በማይጠቅም ሀሳብ የሞተው ልቤን ፤ በቅዱስ ቃልህ ትንሣኤውን አውጅለት ፤ በልቤ የመላውን አንደበቴ እንዲህ እያለ ይመስክር “እርሱ ሞቶ በጎቹን የሚያድን ከሞት የሚያስነሣ እንዲህ ያለ እረኛ ከወዴት ይገኛል? የበጎቹን ሕመም ሕመሙ አድርጎ መድኃኒቱን ቀምሶ የሚያቀምስ እረኛ እንደምን ያለ እረኛ ነው?”

+++

Image Credit: monasteryicons (Pinterest)

ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ታኅሣሥ 20 2016 ዓ.ም ምሽት



#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"አሁን እየጾምክ ነው?

እስቲ ጾምህን በተግባር አሳየኝ?

         የቱን ሰራህ?


💠 ድሃውን ባየህ ጊዜ ምህረትን አሳየው።
💠 ጠላትህን ስታየው ታረቀው።
💠 ስኬታማ የሆነ ወንድምህን ስታየው አትቅናበት በመንገድ የምትሔድ ሴትን ስታይ ዝም በለህ እለፋት።

🛐በአጠቃላይ አፍህ ብቻ አይጹም ነገር 👉ግን ዓይንህ፣
👉 እግርህ፣
👉እጅህ ሁሉም አካልህ ይጹም።

💠 እጅህ ከመስረቅና ከስስት ይጹም፣ 💠እግሮችህ ወደ ኃጢአት ከመጓዝ ይከልከሉ፣
💠 አይኖችህም በሌሎች ሰዎች ውበት ላይ ተተክለው ከመዋል ይጹሙ።

❤💠አሁን ስጋ እየበላህ አይደለም አይደል?
👉በዓይንህም መጥፎ ነገር አትመልከት፤ 👉መስማትንም ጹም።
💠የፈውስ ጾም ክፉን አለመስማት የሌሎችንም ስም አለማጥፋት ነው።

💠 አንደበትም ከክፉና ከአጸያፊ ንግግር ይጹም።
🛐 የዶሮና የአሳ ስጋ ከመብላት እንከለከላለን ነገር ግን የወንድማችንን ስጋ ስናኝክና ስንበላ እንውላለን።

💠የወንድሙን ስጋ የሚበላ ደግሞ የተረገመና አሳች ነው።👉 ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ” እንዳለን። ገላ.5:15

💠ሆዳችንን ከምግብ ብቻ ባዶ ማድረግ አይደለም። ነገር ግን ሁለንተና ሕይወታችንን ራሳችንንም የምንቆጣጠር እኛ ወደ መንፈሳዊ ነገሮች የምንመራ መሆን አለብን።"

የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን ውርስ ትርጉም #መምህር_ንዋይ_ካሳሁን


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

♡YAHWEH PROMOTION♡

↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
              ➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel      :- +251943686155
  :- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ወደ እስራኤል ለሥራ ወይም ለትምህርት መሄድ ይፈልጋሉ⁉️

👇👇
@Hebrewethio
@Hebrewethio

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🙏ጸሎት የተሰኘ አዲስ ግሩም ኦርቶዶክሳዊ 🙏

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🙏ጸሎት የተሰኘ አዲስ ግሩም ኦርቶዶክሳዊ 🙏

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ራስን_መግዛት (ክፍል - ፬)

#ዶግማና_ትምህርት

💠መንፈሳዊው ሰው በዶግማና በትምህርት ላይ ራሱን ይገዛል፡፡

❤እርሱ አዘውትሮ ስለሚያነብ ወደ አእምሮው የገባውን ማንኛውንም ዓይነት አሳብ ለማስፋፋት አይጣደፍም:: ለምሳሌ፦ ቀስ ብሎ ሊያስተምረው ወይም አሳጥሮ ሊጽፈው ወይም ደግሞ መጽሐፍ አድርጎ ሊያሳትመው ይችላል፡፡ አንድ ሰው አንድን አሳብ ከመስጠቱም ሆነ ከመቀበሉ በፊት ወይም ጉዳዩን ለሌሎች ሕሊና ከማስተዋወቁ በፊት ለረዥም ጊዜ ሊያብላላውና ከገዛ ራሱ ሕሊና ጋር ሊወያይበት ይገባል፡፡

❤በልብህ ውስጥ ያለው አሳብ በአንተ ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ ካወጣኸው ወይም ካስፋፋኸው ግን በሌሎች ሰዎች ቁጥጥር ሥር ነው::
❤ታላቁ አባት ቅዱስ መቃርስ «ወንድሜ ሆይ! ሰዎች በአንተ ላይ ከመፍረዳቸው በፊት በራስህ ላይ ፍረድ!›› ብሎ መናገሩ ምንኛ ትክክል ነው! ምናልባት ይህንን አባባሉን ያገኘው ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ሊሆን ይችላል፡፡ «ራሳችንን ብንመረምር ባልተፈረደብንም ነበር . . » 1ኛ ቆሮ. 11፥31።
❤ይህም ማለት መንፈሳዊው ሰው በሌሎች ቁጥጥር ሥር ከመውደቅ ይልቅ ራሱን መቆጣጠር ይመርጣል ማለት ነው፡፡

#ታዛዥነትና_ቃል_መግባት

❤ራሱ ቃል በመግባት፣ በታዛዥነትና በተሸናፊነት ውስጥ ራሱን ይገዛል፡፡
❤ምክንያቱም ዛሬ አንዳንድ ሰዎች በነፃነት፣በግል ክብርና በራስ መተማመን ስም ስለ ሥነ ሥርዓት፣ ስለ ወግና ስለ ሕግ ሳይጨነቁ የወደዱትን ስለሚያደርጉ ነው፡፡
❤በዲሞክራሲ ብናምንም የምናምነው በገደብ ውስጥ ባለ ዲሞክራሲ ነው::
❤ለዚህ አባባል ወንዝ ጥሩ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል፡፡ ወንዝ ከግራና ከቀኙ ባሉት ሁለት ከፍ ያሉ የምድር አካላት ተገድቦ ይፈሳል፡፡ ሰዎች ወንዙን ከሚፈስበት አቅጣጫ በማስቆም ነጻነቱን ሊነፍጉት ባይችሉም አፍሳሹ ወጥቶ የጎርፍ አደጋ እንዳያስከትልና አካባቢውን ረግረግ እንዳያደርግ ግን ሊቆጣጠሩት ይችላሉ፡፡

💠መንፈሳዊው ሰው
❤ ቃሉን ይጠብቃል

❤ግብረገብነትን ያከብራል!
❤ሕግጋትን ያጤናል፡፡
❤ሌሎች ሰዎችንም እንዲሁ ያከብራል፡፡ ሐዋርያው የተናገረውን ቃል ሳያንገራግር ይቀበላል:: «ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ግብር ለሚገባው ግብርን፣ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።» ሮሜ 13፥7: የራሱን ምኞትና አስተሳሰብ የሚከተለውና ለሥነ ሥርዓት፣ ለበላዩና ለማንም የማይገዛው ሰው ግን መንፈሳዊ ሰው አይደለም፡፡ እርሱ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ስለማይቀበል ምንም ዓይነት ነገር አይቀበልም።

❤ታዛዥነትን አስመልክቶ መንፈሳዊው ሰው ራሱን ይገዛል፡፡ እርሱ ለወላጆቹ፣ ለንሥሐ አባቱ፤ ለሥነ ሥርዓት ከመታዘዙም በላይ ለእግዚአብሔርም ፍጹም ታዛዥ ነው::
💠መታዘዝ ክብሩን እንደማይቀንሰው ይረዳል:: መታዘዝ የትሕትና ምልክት ሲሆን ትሕትና ደግሞ መልካም ባሕርይ ነው፡፡ ለማንም የማይታዘዝ ሰው ሙሉ ለሙሉ የሚታዘዘው ለትዕቢቱና ለአሳቡ መሆኑ እርግጥ ነው፡፡

ይቀጥላል......

(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ  ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)



#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

MK TV || ዕለታዊ መረጃዎች || የስብከተ ወንጌል ተደራሽነትን ለማስፋት 36 ሰባክያነ ወንጌል ተመሩቁ
https://youtube.com/watch?v=n49JSiqTE-o&feature=shared

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ታኅሣሥ 12
ዕረፍቱ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

💠ታኅሣሥ ፲፪ የከበረ ገድለኛ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም ደግሞ ዓመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጋግ ናቸው፤ እነርሱም በአክሱም ሀገር ሲኖሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ። አንደኛው ስሙ ገብረ ክርስቶስ ሲሆን ይህ ሁለተኛው ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው አባ ሳሙኤል ነው። እርሱንም ለመምህር ሰጥተውት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እየተማረ በትጋት ኖረ። ከዚህ በኋላም ያስተምረው የነበረ መምህሩ ስለ አባ ሳሙኤል ታላቅነት ትንቢት ተናገረና በመቶ ዓመቱ ዐረፈ።

💠አባ ሳሙኤልም አባትና እናቱ እንዳረፉ ተነሥቶ ወደ አባ መድኃኒነ እግዚእ (አባ አድኃኒ) በመሄድ በደብረ በንኰል መኖር ጀመረ። በዚያም ትጋቱን ያዩ የአባ መድኃኒነ እግዚእ ደቀ መዛሙርት አባ ምንኲስና አስኬማ የሚገባው ደገ’ኛ ነውና እንዲያመነኩሱት ነገሩት። አባ አድኃኒም ትጋቱንና ተአዛዚነቱን ተመልክቶ አመነኰሰው። በዚያም ለሁላቸውም እየታዘዘ እንደመንኰራኲር በመፋጠን ያገለግል ነበር። የራሱን ሥራ ጨርሶ የደከማቸው ካለ ፈጥኖ መሄድ የነርሱንም ሥራ በመሥራት ያግዛቸው ነበር። በዚህም አፍቅሮ ቢጽን በግብር በግልጥ አሳያት። አባ መድኃኒነ እግዚእም በእጅጉ ወደደው። ነገር ግን በዚህ ገዳም ሲቆይ የሻገተ ጎመንና ጥቂት ውኃ ካልሆነ በቀር ምንም ምን ሌላ እህል አይቀምስም። እንዲህ ራሱን ሥጋውን በገድል እየቀጠቀጠ ቢኖርም ዘመዶቹ ግን እየመጡ ስላወኩት ለአባ መድኃኒነ እግዚእ አስፈቅዶ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ እግሮቹ እስኪያብጡ ድረስ እንደመንኰራኲር ይሰግድ፣ እጅግም ብዙ ጊዜ ይጸልይ ነበር። ከዚህም የተነሣ ሊቁ አባታችን ማር አባ ጊዮርጊስ ሲያመሰግነው ‹‹ሰአል ለነ ሳሙኤል አቡነ ሠረገላ ጸሎት፤ የፈጣን የጸሎት ሠረገላ የሆንክ ሳሙኤል ሆይ ለምንልን›› በማለት ተማጽኖታል።

💠ከዚያም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ በረኃ ወጥቶ ሲጋደል አናብርትና አናብስት ይሰግዱለትና ይገዙለትም ነበር። አንድ ዕለት አንዲት ለመውለድ የደረሰች አንበሳ ከበዓቱ መጣች። እርሱም ነገሩን አውቆ ቦታ ካስተካከለላት በኋላ መንታ የሆኑ ወንድና ሴት ደቦሎችን ወለደች። ወንዱም ሴቷን እየተጋፋ ሲጠባ አባ ሳሙኤል ግን ተራ በተራ እንዲጠቡ ያደርጋቸው ነበር። በሌላም ጊዜ አንድ አንበሳ እግሩ በእሾህ ተወግቶ አቂሞበት በጽኑዕ ታሞ ከውኃ ዳር ሁኖ ከደቀ መዝሙሩ ጋራ ሲጓዙ አዩት። ደቀ መዝሙሩም ውኃ ጠጥቶ ደክሞት የተኛ መስሎት ነበር። በኋላም ቀረቡና አባ ሳሙኤል ወስፌ አምጥቶ እሾሁን አወጣለት፤ ቂሙንም አፈረጠለት። ያም አንበሳ ከዚያ ልክ እንደእምቦሳ በአባ ሳሙኤል ፊት ይዘል ነበር።

💠አንድ ቀንም መጽሐፉን ሸክፎና የእሳት ማኅቶት ይዞ ሲጓዝ ታላቅ ወንዝ ውኃው እስከ አፉ መልቶ ገጠመው። አባታችንም በእምነት በውስጡ ገብቶ ተጓዘ። ሲገባበትም ውኃው ከራሱም በላይ ሞልቶበት ነበር። ተሻግሮ ሲወጣ ግን የእግዚአብሔር ድንቅ ቅዱስ ክብሩ እንዲገለጽ የቸሩ አምላክ ፈቃዱ ስለነበር እሳቱም አልጠፋ፣ ከመጻሕፍቱም አንዲቱ ቅጠን ስንኳ የውኃ ጠል አላገኛትም።

💠ጸላኤ ሠናያትም እጅግ ብዙ ጊዜ ይፈታተነው ነበር። አባ ሳሙኤል ግን በጸሎቱ ኃይል ድል ያደርገዋል። አንድ ዕለትም ጥልቅ ጉድጓድ አስቆፍሮ ለዐራት ወራት እህል ውኃ ሳይቀምስ ቆዳው ከአጥንቱ እስኪጣበቅ ሥጋውን አስጨንቆ ሲጋደል ከቆየ በኋላ ጌታችን ከአእላፍ መላእክት ከእመቤታችን እና ከቅዱሳን ጋር መጥቶ ባረከው፤ በምራቁም መላ ሰውነቱን ቀብቶ ኃይልን አሳደረበት። እንዲሁ ጣቱንም ሦስት ጊዜ ቢያጠባው ረኃብ የሚባል ነገር ሁሉ እልም ብሎ ጠፋለት። ከዚያችም ዕለት አንሥቶ እግሮቹን እያሠረ ማቅንም ለብሶ በየዕለቱ ከባሕር እየሰጠመ መዝሙረ ዳዊትን አምስት ጊዜ እየመላለሰ ቁጥር በሌለውም ግርፋት ራሱን ሥጋውን ይቀጣ ነበር። አናብስቱንም ልክ እንደፈረስ ለዕቃም ለመጓጓዝም ይገለገላቸው ነበር። እነርሱም እጅጉን ይታዘዙለታል።

💠ብዙ ደቀ መዛሙርትም ወደርሱ መጥተው የርሱ ልጆች ሆኖ። አንድ ዕለትም አባ ገብረ መስቀል ከሚባል ደገ’ኛ ጻድቅ አባት ጋር ተገናኝየው ሲጨዋወቱ አመሹ። ከዚያም በፊት ተያይተው አያውቁም ነበር። የእራትም ሰዓት ሲደርስ ተነሥተው በጸሎት ቢተጉ ከሰማይ የተዘጋጀ ማዕድ ወርዶላቸው አብረው ተመግበዋል። በሌላም ጊዜ ከአንድ ገዳማዊ አባት ሲነጋገሩ አባ ሳሙኤል ለዚያ ደግ ሰው ሲናገር ‹‹እነሆ እኔ በአርያም ቁሜ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የአምላክን መንበር ሳጥን ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነኝ›› አለው። ጻድቁ አባ ሳሙኤል አባታችን ለመቀደስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ የሚቀድስበት ጽዋዕ እና ኅብስት ከሰማይ የሚወርድለት ነበር።

💠ከዚህ ሁሉ ላይ ከዚህ ደገ’ኛ ጻድቅ የምናነሳለት ነገር ለንጽሕት የአምላክ እናት ለእመቤታችን ያለውን ጽኑዕ ፍቅር ነው። እርሱም ውዳሴዋን ከቅዳሴዋ አስተባብሮ የሚደግም ነበር። በሚጸልይበትም ጊዜ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ይል ነበር። እመቤታችንም በእጅጉ የምትወደው ንጹሕ ድንግል ተጋዳይ መነኰስ አባት ነው። ተያይዞም የሚነሣው አባታችን ምግብ ባሻቸው ጊዜ በውኃው ላይ ውዳሴዋን ከቅዳሴዋ አድርጎ ቢጸልይ ኅብስት ሁኖላቸው ይመገቡት ነበር። ንጽሕት እመቤታችንም አንድ ዕለት ተገልጻለት በክብር ታየችውና ንጹሕ ዕጣንን ከሚያበራ ዕንቊ ጋራ ሰጥታዋለች።

💠ዕረፍቱ በደረሰ ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናውያን አክናሱ ተሸክሞ ኢየሩሳሌም ሰማያዊትን አሳየውና ወደ ልዑል እግዚአብሔር አቀረበው። ቸሩ አምላካችንም በማይታበለው ቃሉ ጽኑዕ ቃልኪዳንን ሰጠው። ወደ ቀደመ አኗኗሩም በተመለሰ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው፤ ከዚህም ሁሉ በኋላ በሰላም ዐረፈ።

💠እግዚአብሔር አምላካችን በዚህ ኃያል ገድለኛ ጻድቅ ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ትደርብን፤ ለዘላለሙ አሜን።


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🥀በሰው ልጅ አፈጣጠር ትልቁ የማይዳሰስና ዋጋ የሚሰጠው አካል ህሊና ነው ። 💝
ቴሌግራም ቻናል⤵️

➯ ህሊና የአምላክ መቀመጫ ነው
➯ ህሊና ልክ እንደ አምላክ ነው
➯ ህሊና የሌለው ሰው አምላክ የሌለው ሰው ነው
➯በህሊናችን በኩል የሚያነጋግረን አምላክ ነው
መልካሙንና ክፉውን ሁሉ ይነግረናልና

💝ስንዋሽ
💝ውሸታምነታችንን
💝አድርባይነታችንን
💝ስግብግብነታችንን
💝ጨካኝ መሆናችችን
💝ኀጢያታችንን
💝 አስመሳይነታችንን ..... ሁሉ ሁልጊዜ ዝክዝክ አድርጎ ይነግረናል ።

💝ጥሩ ከሠራንም በዛውል ልክ መልካም መስራታችን ይመሰክርልናል ሀሴትም ያደርጋል ።
ህሊናችንን ብንሰማው መልካሙን መንገድ ይመራናል ። ባልሰማነው መጠን ደግሞ እየደከሞ ሂዶ መልካም ማድረግ ይሳነዋል የሰይጣን መጫወቻም ሆኖ ይኖራል ።

💝የህሊና ወቀሳ ከሰዎች ወቀሳ በእጅጉን ይለያል
ሰው ቢወቅስህ ለጊዜው ነው ህሊና ግን እረፍት የለሽ ነው ።

💝ህሊና ሲኖረን የኛ ምርጥ ጠላቶች
ውሸት ፣ ክፋት ፣ ማታለል ፣ ስግብግብነት ...... ይሆናሉ ።

💝ህሊና ሲኖረን በሰዎች ውስጥ ለመቀመጥ ማስመሰልንንና በሰዎች እንባ መደሰትን እንጠየፋለን ።

💝ህሊና ሲኖረን በሰዎች መቸገር ፣ መውደቅና መንከራተት ተባባሪ መሆንን አንጠላለን

💝ህሊና ቢስነት በየዋህ ሰዎች መጫወትን ፣  በተቸገሩ መጠቀምን ፣ በፈሪ ሰዎች መዘባበትን.....የምንወድ ለሆድ ያደርን ክፉ ሰው ያደረገናል ።

🥀አስተሳሰባችን ከአለባበሳችን ሲያምር
መልካምነታችን ከምንቀባው ሽቶ በላይ ሲያውድ
ምግባራችን በተግባር ሲገለጥ በሰብአዊነትና በህሊና መንገድ ስንሄድ
ለሰው ምናወራውን መልካም ነገር ስንኖረው ያኔ ህሊናችን ለራሳችን ምቹ ትራስ ሆኖ ያገለግለናል ። /ፍቅርተ ኢየሱስ /
            አምላከ ቅዱሳን ማስተዋልን ይስጠን🙏
     ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
   


#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ለሦስት ወራት ትምርህታቸውን በሀገረ ስብከቱ የካህናት ማሠልጠኛ ስከታተሉ የነበሩ የመጀመሪያ ዙሪ ደቀመዛሙርት ተመረቁ

መሠረተ ሚዲያ

በጉጂ ምዕራብ ጉጂ ቦረና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከት ከሀገረ ስብከቱ ከተለያየ 13 ወረዳ ቤተ ክህነት የተወጣጡ ቤተ ክርስቲያንን በተለያየ ቋንቋ (አፋን ኦሮሞ ፣ አማርኛ ፣ ኮንሰኛ ፣ገደኤኛ፣ እና ሱማለኛ)
የሚያገለግሉ
ከመስከረም 12 እስከ ታኅሣሥ 7  ትምህርታቸውን በሀገረ ስብከቱ የካህናት ማሠልጠኛ ስማሩ የነበሩ  35 ደቀመዛሙርት በዛሬ ዕለት ተመርቀዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በተመራቅ ደቀ መዛሙርቱ የተለያየ ወረብ ዝማረ እንድሁ የዕለቱ ወንጌል ተሰብኳል

መምህር አለምቀር ማኅበረ ቅዱን የነጌሌ ማዕከል ሰብሳቢ ለተመራቂ ተማርዎች መልእክት አስተላልፎ በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ለደቀመዛሙርቱ የምስክር ወረቀት በመስጠት
ምክር መልእከት በማስተላለፍና ቃለ ቡራከ በመስጠት መርሐ ግብሩ ተፈጽሟል


መርሐ ግብሩ የተካሄደው የነጌሌ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጠዋት በሰንበት መርሃ ግብር ላይ ነው ።



╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )
➡️      መሰረተ ሚዲያ


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ


👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia

   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ዕለታዊ_መልዕክት

“አንድ ገበሬ ዘር መዝራት ስላለበት ብቻ እንዲሁ አይዘራም፡፡ አስቀድሞ መሬቱን ማረስ፣ ማለስለስ አለበት፡፡ ካረሰ ካለሰለሰ በኋላ ዘሩን ይዘራዋል፡፡ አሁንም ግን መዝራቱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የዘራውን ዘር አፈር ሊያለብሰው ይገባዋል፡፡ እንዲያ ካላደረገ ወፎች መጥተው ይለቅሙታልና፡፡ ልክ እንደዚሁ እኛ ክርስቲያኖችም በእኛ ላይ የተዘራውን ዘር (ቃለ እግዚአብሔር) በየጊዜው እንደ ገበሬው የማንከታተለው ከሆነ በአየር ላይ እንደተዘራ ዘር ይሆንብናል፡፡ ሰይጣን ይለቅምብናል፤ የራሳችን ስንፍና እንዲጠወልግ ያደርጓል፤ ፀሐይ ያደርቋል፤ ጐርፍ ይወስዷል፤ እሾክ አንቆ ይይዟል፡፡

ስለዚህ ዘር ዘርቶ ዞር ማለት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ በየጊዜው መኮትኮት፣ ወፎችን ማባረር፣ የበቀለ አረም ካለ ማረም፣ ጭንጫ የበዛበት አከባቢ ካለ የለሰለሰ አፈር መጨመር፣ በየጊዜው መከታተል፣ አጥር ማጠር፣ እንዲሁም ማንኛውም የተዘራውን እህል ሊያበላሹ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ምናልባት በሰብሉ እርሻ የገበሬው ትጋት ብቻ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም መሬቱ ግዑዝ ነገር ስለሆነ፡፡ በመንፈሳዊው እርሻ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ኃላፊነቱ የገበሬው ማለትም የመምህሩ ብቻ አይደለም፡፡ ከግማሽ ወይም ከዚያ በላይ የደቀመዝሙሩ (የምእመኑ) ኃላፊነት ነው፡፡ በርግጥ መምህሩ ዘሩን መዝራት አለበት፡፡ ነገር ግን ደቀ መዝሙሩ የተነገረውን ቃል ሁል ጊዜ መስማት ብቻ ሳይሆን ማድረግም አለበት፤ በግብር ፍሬ ማፍራት አለበት፤ የበቀሉ አረሞች ካሉ በየጊዜው መንቀል አለበት፡፡

የገበሬ ልጆች በሰብሉ መካከል የበቀለ አረም ካለ እንዲሁ ጫፍ ጫፉን ብቻ አይቈርጡትም፡፡ ከሥር ይነቅሉትና በመጨረሻም በእሳት ያቃጥሉታል እንጂ፡፡ በእኛ ላይ የበቀሉ አረሞችም (ጥርጥሮች፣ ክሕደቶች፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ማነቆ የሆኑብንን ነገሮች…) ከሥራቸው ነቅለን ልናቃጥላቸው ይገባናል፡፡”

#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ

 
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !

   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
     /channel/dnhayilemikael
   ╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ═══╯

Читать полностью…
Subscribe to a channel