dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጾም ቅድስት ናት ጥቅም አላት፤
የበረከት ፍሬ ታፈራልናለች፤
ለቅዱሳንም ጽድቅን ትከፍላቸዋለች።

ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጾም፦
🍂ጾሞ የመልአካዊነት ግብራችን መገለጫ ናት።
🍂ጾም የነፍስ ምግብ የሥጋ ደግሞ መስልብ ናት።
🍂 ጾሞ የመንግሥተ ሰማያት ኑሮን በምድር ላይ መጀመሪያ ናት።
ጾም የተዐቅቦ መለማመጂያ፣የቅድስና መሰላል ናት።
🍂 ጾም የፍትዎት ማጥፊያ የተስፋ ወንጌል ግን ማለምለሚያ ናት።
🍂ጾም የጸሎት እናት የአርምሞ እኅት የዕንባም ነቅዕ ናት
🍂ጾም የኃይለ ነፍስ የተፈጥሮ ነፍስ መገለጫ ናት
🍂ጾም የደፈረሰ ህሊና ማጥሪያ ናት።
🍂ጾም የቃለ መጽሐፍ መፈጸሚያ ናት
"ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም።"ማቴ.፬፥፬ እንዲል።
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ስለ ሰርግ ቀን" የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ወጣቶች ትዳራቸው፥ ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንዲኾንላቸው ከፈለጉ ከኹሉም አስቀድመው ሊያደርጉት የሚገባቸው ልክ እንደ ቃና ዘገሊላው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጋቸው ዕለት እንዲገኝ ማድረግ ነው፡፡ ይኸውም ሰርጋቸውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያን ማከናወን ማለት ነው፡፡

ሊቁም ይህን አስመልከቶ ሲናገር እንደዚህ ይላል፡- “ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በመገኘትና ጸጋውን በመስጠት ሰርግን ቀድሷል፡፡ ሌሎች ይረባል ይጠቅማል ብለው ካመጡት ስጦታ ይልቅ ከፍ ያለ ስጦታ ይዞ በመምጣት ይኸውም ውኃውን ወደ ወይን በመለወጥ ሰርግን አክብሯል፡፡ … ስለዚህ የዲያብሎስ ትርኢትን በማምጣት ጌታችን ያከበረውን ሰርግ አናቃልል፡፡ ወደ ትዳር የሚገቡ ሰዎችም በቃና ዘገሊላ በተደረገው መልኩ ያግቡ፡፡ በመካከላቸው ክርስቶስ እንዲገኝ ያድርጉ፡፡ ‘ይህንንስ እንዴት ሊያደርጉ ይችላሉ? ጌታችን ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በአካል እንደ ተገኘ ዛሬም መገኘት ይችላልን?’ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ አዎ! ካህናትን ይጥሩ፡፡ ጌታችን ‘እናንተን የተቀበለ እኔን ይቀበላል’ በማለት ተናግሯልና (ማቴ 10፥40)፡፡

እንደዚህ በማድረግ ዲያብሎስን ያርቁት፦
  ➛ ጸያፍ ዘፈኖችን፣
  ➛ ርኵሳን ሙዚቃዎችን፣
  ➛ ሥርዐት የለሽ ውዝዋዜዎችን፣
  ➛ አሳፋሪ ንግግሮችን፣
  ➛ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣
  ➛ ወሰን የለሽ ሁካታዎችንና ሳቆችን፣
እንደዚሁም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነውርን የተሞሉ ድርጊቶችን ያርቁ፡፡ ከእነዚህ ይልቅ የክርስቶስ አገልጋዮችን ይጥሩ፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋቸው ይገኛል፤ ይታደማልም፡፡”

(ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መጽሐፍ የተወሰደ)

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

❖ ወዳጄ እስኪ ልጠይቅህ፤ አንተም አንቺም መልሱልኝ!

❓ጌታችን ዛሬ ቢመጣ የምትመልሰው የምትመልሺው መልስ ምንድን ነው

✍️"ንስሐ ያልገባሁት፣ ሥጋ ወደሙን ያልተቀበልሁት፣ ምግባር ትሩፋት ያልያዝሁት ዕድሜዬ ገና ነው ብዬ አስቤ ነው፤ ሥራ በጣም በዝቶብኝ ስለ ነበረ ጊዜ አጥቼ ነው፤ ዛሬ ነገ እያልኩ እየረሳሁት እንጂ እንደዚያ ማድረግ አቅቶኝ አልነበረም"

❓ምክንያትህ እነዚህ ናቸው
❓እኅቴ! ሰበቦችሽ እነዚህ ናቸው

❖ በዚያ ሰዓት ግን እነዚህ ኹሉ ጥቅም የላቸውም፤ እናት ልጇን በማታድንበት ሰዓት እነዚህ ምክንያቶች ምንም አይረቡም፡፡

❓ ታዲያ ለምን ትዘገያለህ
❓ እኮ ለምን ትዘገያለሽ
❓ያኔ ዋይ ዋይ ከምትዪ... ያኔ የማይጠቅም ጸጸት ከምትጸጸት ለምን ዛሬ አትጠቀምበትም
❓ለምን ራስህን አታድንም

📌 ምንጭ
✍️ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ
https://youtube.com/watch?v=ZlJmiQKQAN4&feature=shared

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን ለአባ ሳሙኤል ዓመታዊ እረፍት በዓል ለዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ ።

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ከፈሪ ሰው ጋር ስለ ጦርነት አትማከር መጋቤ ሐዲስ ፍሬስብሐት ይርጋ የቅኔና የመጽሐፍት መምህር
https://youtube.com/watch?v=Q9RDoxL4bqQ&feature=shared

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዝጎራ ገፅ 315

" የምሥጢር ሙዳይ ሁን እንጂ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን ። ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ችሎታቸውና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር ፣ ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን ። ለዕውቀት ትጋ ። በከፊል በተረዳኸው ነገር ራስክን እንደ አዋቂ አትቁጠር ። በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል ። ሥራ ስትሠራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው ። ትጋት ጥሩ ነው ። ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፣ በችኮላ መሥራትና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው ። ርኩሰት የዕውቀትና ስልጣኔ መገለጫ አይደለምና ማንነትንና ሰብዓዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ አድርግ ። "

" እናም በየዕለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን ። ያለጸጸት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ ፤ ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር ፤ ልክ እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውንና ለማከናዎን የምትመርጠውን ዐይነት ሕይወት ለመኖር ሞክር ። .... "

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የክርስትና አባትና እናት

✝️ በቤተክርስቲያናችን ወንዶች በ፵ ቀናቸው ሴቶች በ፹ ቀናቸው በተጠመቁ ጊዜ የክርስትና አባት ወይም እናት ይኖራቸዋል

✝️ የክርስትና አባትና እናት ማለት ደግሞ ልጆች በሚጠመቁ ጊዜ ስለ እምነታቸው ባለው ነገር ሁሉ ሀላፊነት ወስደው አስፈላጊውን ትምህርት የሚሰጡ፣ የሚደግፉ ማለት ነው
➻ በጥምቀታቸው ወቅትም ስለ ልጆቹ በእምነታቸው ለለመስከር ቃል የሚገቡ፣ ሀላፊነት የሚወስዱ ናቸው

✝️ ይህ ስርዓት በቤተክርስቲያናችን የተጀመሪያው በ፬ኛው ክፍለ ዘመን በመጀመሪያው የሀገራችን ኢጲስ ቆጶስ በአቡነ ሰላም ከሳቴ ብርሃን ነው

✝️ የመንፈሳዊ ትምህርት ከመስጠትም በዘለለ መንፈሳዊ ዝምድናን (አበ ልጅነትን) ማጠናከሪያ መንገድ ነው

⛪️ ከክርስትና አባትነትና እናትነት የሚከለክሉ ነገሮች፦

➻ የሥጋ ዝምድና መኖር
➻ የጋብቻ ዝምድና ያላቸው መሆን
➻ ዕድሜያቸው ለማስተማር፣ ለማሳመን አለመድረስ
➻ በቂ እምነት፣ መልካም መንፈሳዊ ሕይወት አለመኖር
➻ ሃይማኖታቸው ከተጠማቂው ጋር የተለየ መሆን

✝️ ጾታን ስናይ ወንድ ወንድን ሴት ሴትን ያነሳሉ እንጂ ወንድ ሴትን ሴት ወንድን ክርስትና ማንሳት አይፈቀድም

✝️ የክርስትና አባትና እናት ክርስትና ያነሷቸውን ልጆች በሥጋ ከወለዷቸው ልጆች ሳይለዩ አስፈላጊውን የክርስትና ትምህርት፣ ድጋፍና ክብካቤ ለማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ይገባሉ

✝️ ይህንን ቃልም በተግባር የመተርጎም ሀላፊነትን እንዲወጡ ቤተክርስቲያን በሚገባ ታስተምራለች

✝️ የክርስትና አባትነትና እናትነት የተዛመዱ ክርስቲያኖች በፍጹም መጋባት አይችሉም
➻ ይህም በሥጋ ከመዛመድ በላይ መንፈሳዊ ዝምድና ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ያሳየናል

ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን። ሀገራችንና ሃይማኖታችንን ይባርክ።

#

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እመኑ ብየ
https://youtube.com/watch?v=8NxHAUlTxDg&feature=shared

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
መስከረም 21-ብዙኃን ማርያም (የእመቤታችን የበዓሏ መታሰቢያ ነው፡፡)
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አስቀድሞ ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው ቅዱስ ቆጵርያኖስ በሰማዕትነት ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
+ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ በነው የጠፉት ድንግሊቱ ዮስቴናም በሰማዕትነት ያረፈችው በዚሁ ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም ይህች ዕለት የከበሩ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ አበው ሊቃውንት በ325 ዓ.ም አርዮስን አስተምለው ለመመለስ በኒቅያ የተሰበሰቡባት ዕለት ናት፡፡ የጉባኤውም ፍጻሜ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ኅዳር ዘጠኝ ነው፡፡
+ የጌታችን ቅዱስ መስቀል ግሸን ደብረ ከርቤ የገባበት ዕለት ነው፡፡ (የመስከረም ዓሥራ ሰባቱን ይመለከቷል፡፡)
+ ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጢባርዮስ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"የክርስቶስ መስቀል ታላቅ በረከትንና ድኅነትን እንድናገኝ ምክንያት እንደ ሆነ እናስተውላለን፡፡ የክርስቶስ መስቀል ስናስበው ሐዘንና ምሬት ነው ነገር ግን እውነታው ደስታና ሐሴትን የሚሞላ ነው፡፡ መስቀል ለቤተ-ክርስቲያን ድኅነት ነው መስቀል ተስፋ ለሚያደርጉት መመኪያ ነው መስቀል የእግዚአብሔር ጠላቶች የነበሩት የታረቁበትና ኃጢአን ወደ ክርስቶስ የቀረቡበት ነው፡፡ በመስቀል ከጠላትነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ተሸጋግረናል በመስቀል ከዲያብሎስ ቀንበር ወጥተናል ከሞት ወደ ሕይወት መጥተናል፡፡ ስለ መስቀል የማንሰብክ ከሆነ አሁንም በሞትና በፍዳ እንደ ተያዝን ነው ማለት ነው፡፡
            ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ልብሰ ተክህኖን ክህነት የሌለው ሰው መንካትና ማጠብ አይችልም። ሥርዓት አይደለም። በቅንነት አንዳንድ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት አድርጋችሁት ከነበረ ከእንግዲህ እንዳታደርጉ ትምህርት ይሁናችሁ። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፰ ላይ ከዲያቆናት፣ ከቀሳውስትና፣ ከዚያ በላይ ከሆኑት በስተቀር ንዋየ ቅድሳትን እንዲነኩ አልተፈቀደም። ስለዚህ ካህናት ሆይ ክህነት የሌላቸው ሰዎች ንዋየ ቅድሳትን እንዲነኩና እንዲያጥቡ አታድርጉ።

መ/ር በትረ ማርያም አበባው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✓•ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?

✓•ተወዳጆች_ሆይ!
አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡

✓•ልብ_በሉ!
ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

✓•ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን?
እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና።

ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ይብሰተ_አእምሮ
#የአእምሮ_ድርቀት

የወንጌል አንድምታ ትርጓሜያችን እንዲህ ይላል 👇
"አሥራ ሁለት መሳክወ ነፋሳት አሉ
አራቱ መሳክው (መስኮቶች) የአራት
#ነፋሳተ_ምሕረት መውጫ ሲሆኑ
ስምንቱ መሳክው ደግሞ የስምንቱ ነፋሳተ መዓት መውጫ ናቸው
#ስምንቱ ነፋሳተ መዓት ሲታዘዙ በዓለም ላይ አምስት ዓይነት መቅሠፍት ይወርዳል
ከነዚያ ውስጥ አንዱ
#ይብሰት/ድርቅ ነው ይልና ይብሰት በሁለት እንደሚከፈል ይናገራል
የመጀመሪያው የእህል የውሃ መታጣት ሲሆን
ሁለተኛው ግን
#ይብሰተ_አእምሮ (የአእምሮ ድርቀት) ነው
👉በዚህ ዘመን የገጠመን ዋና በሽታ ይህ ይመስለኛል
በዓለም ላይ እየከተሠቱ የምናያቸውና የምንሰማቸው ችግሮች ሁሉ
#በይብሰተ_አእምሮ የተቀደሙ ናቸው
• የእርስ በእርስ ጦርነት
• የሀገራት ጦርነት
• የኅፃናት መደፈርና መገደል
• የታላላቅ ሰዎች አለመከበር
• የሙስና መስፋፋት
• የተመሳሳይ ፆታ መጋባት
• መተሳሰብና መተዛዘን መጥፋት ...እነዚህ ሁሉ የ
#ይብሰተ_አእምሮ ውጤቶች ናቸው

የሰውነት ልክ የደረቀበት
እውነት የማይታመንበት
እውነት ተናጋሪ የሚሰቀልበት
ውሸት የለመለመበት
ጩኸት የሚቀማበት
ዕውቀትና አዋቂዎች የሚገፉበት ይህ ዘመን ነው
ይኸውም ይብሰተ አእምሮ ነው
ይብሰተ አእምሮ ሲከሠት በሁሉም ቦታ
#ደህና_ሰው ይታጣል
ጽኑ ተስፋ በሚጣልባቸው በሃይማኖት ቦታዎች ሳይቀር
#ደግ_ሰው ይታጣል
ፍርድ ይዛባል፤ ድሃ ይገፋል....መደማመጥ የለም ...ሁሉም አውቃለሁ ይላል...ጫጫታ እንጂ ንግግር የለም!!!
ይህ
#ይብሰተ_አእምሮ ይባላል

መፍትሔው በሃይማኖትና በምግባር መታነጽ ዕውቀት ንባብና መደማመጥ ነው !!!!!

የራስ ቅል ድርቀት በቅባት እንደሚርስ
የዕውቀት ማጣትም በንባብ ይርሳል ይታደሳል!

መጪውን ዘመን የደረቀውን አእምሯችንን በንስሐ አለምልመን
በሥጋ ወደሙ አፍርተን
በንባብና በዕውቀት ታድሰን የምንኖርበት ያድርግልን !!!

ለሀገራችን ሰላምን ይስጥልን!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🙏🙏🙏🙏ለሎት ተነሱ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ጸሎት መጸለይ ለምን እንደሚከብድህ ታውቃለህ?

ወንድሞች በአንድ ወቅት አባ አጋቶንን ጠየቁት፤ “ከመልካም ሥራ ሁሉ የትኛው በጎ ሥራ ከሁሉ የበለጠ ጥረት (ድካም) ይጠይቃል?”። እርሱም መለሰ “ይቅርታ አድርጉልኝ፣ እኔ ወደ እግዚአብሔር ከመጸለይ የበለጠ ከባድ ሥራ ያለ አይመስለኝም። አንድ ሰው ለመጸለይ በፈለገ ጊዜ ሁሉ፣ ጠላቶቹ አጋንንት እንዳይጸልይ ሊከለክሉት ይሻሉ፤ ከመንገዱ ሊያደናቅፉት የሚችሉት ከጸሎት እንዲርቅ ሲያደርጉት ብቻ መሆኑን ያውቃሉና። ሰው ማንኛውንም ዓይነት በጎ ሥራ ቢሠራ፣ በሥራውም ቢጸና እረፍትን ያገኛል። ጸሎት ግን እስከ መጨረሻ ህቅታ ድረስ [እረፍት የሌለበት] ውጊያ ነው።

ስለዚህ ወዳጄ ውጊያ ከሰው ሳይሆን ከአጋንንት ነው እና ሁላችሁንም የሱን ጦር ሚያርቁልንን ጾም ጸሎት በማድረግ ሚከላከሉልንን መላእክት ማቅረብ አለብን ።

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ማን ያስተምር? አንበቡት ታተርፉበታላችሁ።

መምህራን በ3 ይከፈላሉ

ኀጥአን መምህራን ፣ከሀድያን መምህራንና ደጋግ መምህራን ይባላሉ። የመጀመሪያዎቹ ኀጥአን መምህራን በሥጋ የደከሙ በኀጢአት የዛሉ ከጸሎት የሰነፉ ከአርዓያነት የራቁ ናቸው። እምነትና እውቀት ግን ያልተወሰደባቸው ማለት ነው። ፈጽሞ አይጸልዩም አይጾምም ማለታችን ግን አይደለም። በአዋጅ ሕግ ይገዛሉ በዶግማ በቀኖና ጸንተው ቢኖሩም በሕይወት ምሳሌ መሆን በአርዓያነት መጠቀስ ግን አይችሉም።

እነዚህ መምህራን ኀጠአን ቢሆኑም።ሰው ኀጢአት እንዲሰራ በአደባባይ አይሰብኩም በእግዚአብሔር ፊት ቢወድቁም ፈጽሞ ሕዝብ አያሰናክሉም።

በዓርዓያነት የሚጠቀስ ግብር ባይኖራቸውም ኀጢአትን አያደፋፍሩም።በድካማቸው ይሰቀቃሉ።

ያስተማሩትን ባለመኖራቸው ይጨነቃሉ።

ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከነዚህ መምህራን ቃሉን እንድንማር ከሕይወታቸው ደግሞ እንዳንማር አዞናል።

ስለምን ቢሉ

ለሰው የሚተርፍ ሕይወት የላቸውምና።

ቃሉን ግን እንዳያስተምሩ አልከለከላቸውም። ጸጋቸው ጨረሶ አልተገፈፈም። በጊዜው ለራሳቸው የማይጠቀሙ ቢሆኑም ሕዝቡን ለማዳን የቃሉ ማስተላለፊያ ያደርጋቸዋል። ከበሽተኛ ዶክተር መታክም እንደማይከለከል የዶክተሩም በሽታም መድኀኒቱ እንደማይበክለው ሁሉ ድክመታቸው ቅዱስ ቃሉን አያረክሰውም።

ባይመለሱ ጸጋቸውን ገፎ ከአገልግሎት ያርቃቸዋል።

እግዚአብሔር እስከተጠቀመባቸው ድረስ ግን እኛም እንጠቀምባቸዋለን። እግዚአብሔር ሲከለክላቸው ደግሞ እንከለከላለን።

እነርሱ የግል ኀጢአተኛ ስለሆኑ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ አይረክስም።እግዚአብሔር የዓለምን ድኅነት በቀያፋ በበለዐም አድሮ የእስራኤል ተስፋ ሲናገር እንደሰማነው ሁሉ።

አገልጋዩ የበቃ ባይሆን ራሱ ይከስማበል እንጅ የሌላውን መዳን አይከለክልም።

2ኛዎቹ ከሐዲያን መምህራን ይባላሉ።

እነዚህ በራሳቸው ማስተዋል የተደገፉ በራሳቸው መጠበብ የእግዚአብሔርን ቃል ያለአግባብ ተርጉመው የሚያስተምሩ ነውራቸውን እንደወንጌል የሚሰብኩ ቃሉን በአደባባይ የሚክዱ ናቸው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ሐዋርያትን ሰብስቦ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ ሲላቸው ከትምህርታቸው ራቁ ማለቱ ነው። ዛሬ ዛሬ ከንፉቃን መምህራን ሕይወትን ከክሀድያን መምህር እውቀትን ለመሸመት መጣጣር መርዝ በማር በጥበጦ መጠጣት ለጤና ተስማሚ ነው እንደማለት ይቆጠራል።

በታጠበ ትሪ በተቀመመ ወጥ በተዋበ እንጀራ ቢቀርብም መርዝ መድኀኒት አይሆንምና።ከጥርጥር ሐሳባቸው ከሚበርዝ ተልኳቸው መጠበቅ የክርስቲያን ሁሉ ግዴታ ነው።

3ኛዎቹ እንደወርቅ የተፈተኑት ደግሞ ደጋግ መምህራን ይባላሉ።እነዚህ ደጋግ መምህራን እውቀታቸው እውቀትን ሕይወታየው ሕይወትን እየወለደ በእልፍ የሚባዙ የቃሉ ምሥክር ገድላት ናቸው። ከሚያስተምሩት የሚኖሩት ይበልጣልና ብዙውን በሕይወታየው ጥቂቱን በቃላቸው ያስተምራሉ። እነዚህን መምህራን ፈልጎ ያገኘ ነፍሱ ትረካለች ሕይወቱ ትቀደሳለችና ከሚኖሩበት ገዳም ከሚያስተምሩበት ጉባዔ ድረስ ተጉዞ በረከታቸውን መቀበል ምርቃታቸውን ማግኘት ያስፈልጋል።
ቅዱስ እግዚአብሔር ደጋግ መምህራን አያርቅብን።በያሉበት በረከታየው ይድረሰን።

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር


ራስን ዝቅ ስለማድረግ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

እጅግ የምወዳችኁ ልጆቼ! ምንም ያኽል የምግባር ማማ ላይ ብንወጣም ከኹሉም ይልቅ ጐስቋሎች እንደኾንን ልናስብ ይገባናል፡፡ ትዕቢትን ከልቡናችን ነቅለን ካልጣልን በቀር ምንም መንበረ ጸባዖትን ብንደርስም ጠልፎ እንጦርጦስ ይወረውረናል ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለኁ፡፡

ዳግመኛም ትሕትናን በልቡናችን ውሳጤ የምናኖር ከኾነ ምንም ያኽል በኃጢአት ሸለቆ ብንወድቅም መንበረ ጸባዖትን ታደርሰናለች ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለኁ፡፡ ከፈሪሳውያን ይልቅ ቀራጮች በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ያገኙት ልበ ትሑታን ስለነበሩ ነው፡፡ ትዕቢት፣ ልቡናንም ከፍ ከፍ ማድረግ ከዲያብሎስ ይልቅ የከፋን እንኾን ታደርገናለች፡፡ ፈያታዊ ዘየማን ከሐዋርያት አስቀድሞ ገነት የገባው ልበ ትሑት፣ ኃጢአቱን ዐውቋት ይናዘዛት ስለነበር ነው፡፡ ኃጢአታቸውን ዘወትር የሚያስቡ ደግሞም የሚናዘዝዋት ሰዎች ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡

ምንም ያኽል በጐ ምግባር እንደሠሩ የሚያውቁ፥ ነገር ግን ምንም በጐ ምግባር እንዳልሠሩ ኾነው ልቡናቸውን ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉ ሰዎች ሹመት ሽልማታቸው እንዴት የበዛ ይኾን? ኃጢአተኛ ኾኖ ሳለ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ሰው በትዕቢት ከተያዘ ጻድቅ ሰው ይልቅ ንዑድ ክቡር ነው፡፡ እንግዲኽ ኃጢአተኛ ኾኖ ሳለ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ሰው ይኽን ያኽል ንዑድ ክቡር ከኾነ፥ ጻድቅ ኾኖ ሳለ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ሰው ደግሞ ከዚኽ ይልቅ እንዴት ይከብር ይኾን? የምግባሩ መዓዛ፣ የትሩፋቱ በጐ ጠረን እስከየትኛው ሰማይ ይወጣ ይኾን? አዎ! የዚኽ ሰው የምግባሩ ዕጣን መንበረ ጸባዖት ይደርሳል፡፡ በእውነት ያለ ጥርጥር በማዕከለ ሠራዊተ መላእክት ይገባል፡፡

ከዚኹ በተቃራኒ በበጐ ምግባር ያጌጠ ሰው ትዕቢተኛ በመኾኑ ብቻ ይኽን ያኽል ጉዳት የሚያመጣበት ከኾነ፥ በኃጢአት ዐዘቅት ተዘፍቀው ሳሉ ትዕቢትን የሚጨምሩ ሰዎች እንደምን ይዋረዱ ይኾን?

የምወዳችኁ ልጆቼ! ይኽን ኹሉ የምላችኁ በጐ ማድረግን ቸል እንል ዘንድ አይደለም፤ ከኹሉም አስቀድመን ልቡናን ከፍ ከፍ ማድረግ አስወግደን ልበ ትሑታን እንኾን ዘንድ ስለምሻ ነው እንጂ፡፡ ትሕትና የጥበብ ኹሉ መሠረት ናት፡፡ ምንም ያኽል በጐ ምግባር ቢኖረን፣ ምጽዋትም ቢኾን፣ ጸሎትም ቢኾን፣ ጾምም ቢኾን፣ ሌላም ብዙ የብዙ ብዙ ምግባር ቢኖረን የእነዚኽ ምግባራት መሠረት የሚኾን ትሕትናን ካልያዝን ቤታችን በአሸዋ እንደተሠራ ቤት ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ እነዚኽ በጐ ምግባራቶቻችን ያለ ትሕትና ብቻቸውን መቆም አይችሉም፡፡ ምንም ያኽል ትዕግሥተኞች ብንኾን፣ ደናግላን ብንኾን፣ ፍቅረ ንዋይ የጠፋልን ብንኾን፣ ሌላም እናንተ የምትጠቅሱት በጐ ነገር ቢኖረን ትሕትና ግን ከሌለን እነዚኽ ኹሉ ጥቅም የላቸውም፤ በእግዚአብሔር ዘንድም ንጹሐን መሥዋዕቶች አይደሉም፡፡

ስለዚኽ እጅግ የምወዳችኁ ልጆቼ! በቃላችንም፣ በግብራችንም፣ በሐሳባችንም ትሕትናን ገንዘብ እናድርግና ከላይ የጠቀስናቸውን በጐ ምግባራት በርሷ መሠረትነት እናንፃቸው (እንገንባቸው) ብዬ እማልዳችኋለኁ፡፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ክቡር የሚሆን የወንጌል ቃል እንሰማ ዘንድ እንሳለመው ዘንድ በእርሱም ደስ ይለን ዘንድ በዚህ የበቃን ያድርገን  ሁሉን የያዘ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ለአንተ ምስጋና ይገባል ዳግመኛም ክቡር የሚሆንን የወንጌልን ቃል በልቦናችን ትጽፍ ዘንድ እንለምንሃለን እንማልድሃለንም

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ዕለታዊ_መልዕክት

1, ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!
2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!
3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!
4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ፣ አልተናደድክም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ ነው እንጂ!
6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ ነው እንጂ!
7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ምን አይጉደልብህ ማለት አይደለም ባለህ ትንሽ ነገር ቢሆን ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!
8. ሥራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ሥራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ሥራ እንዲኖርህ ዛሬ ላይ የምትሰራውን ሥራ ውደድ ማለት እንጂ!


እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን !


[ወልደ ሚካኤል]


#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ

JOIN /channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

“አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል" / ኤፌ 5÷14/

ወዳጆቼ ብዙዎቻችን ስልክ ስናወራ ሳንቲሜ ቆጠረ እንጂ ዕድሜዬ ቆጠረ አንልም ከዕድሜው ይልቅ ለሳንቲም ዋጋ እንሰጣለን። በስልክ ከወዳጆቻችን ጋር የምናወራውን ያክል እንኳ ከፈጣሪያችን ጋር ማውራት ሸክም ሆኖብናል።

በመንፈሳዊ ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት በፕሮግራም ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው መኋዝ ያለብን።  ነገ እጀምራለው ነገ ይህን አደርጋለው እያልን ቆጠሮ ብንሰጥ ትርፉ መሰላቸት ነው ማድረግ ያለብንን ዛሬ አሁኑን እንጀምረው። የእግዚአብሔር ፈቃዱም አሁኑኑ እንድንድን ነው።

ነቢያት ስላልመጣው ዘመን ያውቁ ነበር ፤ እኛ ግን የምንኖርበት ዘመን ምንነት እንኳ ተሰውሮብናል። ሐዋርያት ሄደው ዓለምን ዞረው ይሰብኩ ነበር ፣ እኛ ግን በተመቻቸ ቦታ መጥታችሁ ተሰበኩ እንላለን። ሰማዕታት ለክርስቶስ ፍቅር ሞቱ ፣ እኛ ግን ለጥቅማችን ፣ ለምኞታችን ፣ ለኃጢያታችን እንሞታለን። ጻድቃን የዚህን ዓለምን ጣዕም ንቀው መነኑ ፣ እኛ ግን ዓለም መራራ ሆናብንም እንኳ ደግመን ደጋግመን እንፈልጋታለን።

ቅዱሳን አባቶቻችን ከሕግ አልፈው በትሩፋት ኖሩ ፣ እኛ ልጆቻቸው ግን የታዘዝነውን እንኳ መፈጸም ተስኖናል። ደናግል መነኮሳት የክርስቶስ ሙሽሮች ሆኑ ፣ እኛ ግን በአንድ ሃይማኖታችን ጸንተን ክርስቶስን መከተል (ማምለክ) አቅቶናል። ሊቃውንት አባቶቻችን አህያ እንኳ የማትሸከመውን መጽሐፍ በቃላቸው አጠኑ ፣ እኛ ግን አንድ ጥቅስ ለማጥናት ያዙኝ ልቀቁኝ እንላለን።

ጌታ ሆይ እባክህን እኛን እንቅልፋሞቹን ከእንቅፋችን አንቃን !


ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  /channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
ነገ ኅዳር 15/2017 ዓ.ም
(Nov 24/2024 G.C) ይገባል፡፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:- የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም

ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።

ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።

ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።

እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።

መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።

ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡

ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።

(ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ገጽ 334 - 336  በዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው የተተረጎመ)


የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )

                  ⬇️

➡️      መሰረተ ሚዲያ   ⬅️

                  ⬆️

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መጽሐፍ_ቅዱስን_የሚያነቡ_ሰዎች_በ፭ ይመደባሉ

በ፭ የመደብኳቸው እራሴ በተለያየ ምክንያት ያገኘኋቸውን ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ያላቸውን ልምድ በመጠየቅ ካገኘሁት መልስ የተነሳ ነው።

አጭር ስለሆነ እስከ መጨረሻ አንብባችሁ ሐሳብ ስጡበት።

በዚህ አጋጣሚ የመምህር #በትረ_ማርያምን ምክረ ሐሳብ እንከተል እላለሁ።
የእኔም ልምዴ ሁሌም ጧት ጧት ከጸሎት በኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ከብሉይ ኪዳን ፫ ምዕራፍ ፣ ከሐዲስ ኪዳን ፪ ምዕራፍ ከዚያ ቀጥሎ የዕለት ስንክሳር ሳላነብ አልወጣም።
ምናልባት ልምዱ ከጠቀማችሁ ብየ ነው እንጂ ይህን ማውራት ፈልጌ አይደለም ።
ግን ማልዶ መነሣትን ይጠይቃል።

✝️፩ኛ, በአጋጣሚ የሚያነቡ፦ እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡት እንደ ማንኛውም መጽሐፍ በአጋጣሚ ካገኙትና እጃቸው ከገባ ምን እንደሚል ሳያስተውሉ የሚያነቡ ናቸው።
ለምሳሌ፦አንዱ ጓደኛው ጋዜጣ ሲያነብ ሲያየው ቀበል ብሎ አንዳንድ ነገሮችን አንብቦና ፎቶ አይቶ ጋዜጣውን እንደሚመልስ ሰው ናቸው።
በአጋጣሚ ስለሚያነቡትም አይጠቀሙበትም።

✝️፪ኛ, ለጥናትና ለዕውቀት የሚያነቡ፦ እነዚህ ሃይማኖት ከየት መጣ? ማን ጀመረው? ወዘተ የሚለውንና ሌሎች ተዛማጅ ነገሮችን ለማጥናትና ለማወቅ የሚያነቡ ናቸው።
ስለሆነም ለጥናትና ለዕውቀት ብቻ ስለሚያነቡት አይጠቀሙበትም።

✝️፫ኛ, ለትችት የሚያነቡ ፦ እነዚህ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሕይወት እንደሆነ ለማወቅና እንደ ቃሉ ለመኖር ሳይሆን ለመተቸትና የሚቀበሉትን ሰዎች ለማወናበድ የሚያነቡ ናቸው።
ለትችት ስለሆነ የሚያነቡት በቃሉ አማካኝነት በእግዚአብሔር አምነው ወደ ሕይወት አይደርሱም።

✝️፬ኛ, በመስማት የሚያነቡ፦ እነዚህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ሲባል ይሰሙና ውይ ደስ ሲል ብለው ማንበብ ብቻ ስለሚወዱ ያነቡታል።
ነገር ግን የማይገባቸውና ለሕይወት የማይበቁ ናቸው።
ተግተውና ደጋግመው ቢያነቡት ልባቸው ተለውጦ ሊድኑ ይችላሉ።

✝️፭ኛ, ለሕይወት የሚያነቡ ፦ እነዚህ የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት እንደሆነና ቃሉን በመስማት ድኅነት እንደሚገኝና ወደ ድኅነት እንደሚያደርስ በማመን የሚያነቡ ናቸው።
"ወዝኒ ቃል ዘአነ ነገርኩክሙ መንፈስ ውእቱ ወሕይወት ውእቱ = ይኽ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወት ነው" እንዲል (ዮሐ፮፥፷፫)።
✔️እነዚህ አንባቢዎች ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ
"ዘዳዕሙ ሕገ እግዚአብሔር ሥምረቱ
ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ
ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ
እን ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ
ወቈጽላኒ ኢይትነገፍ
ወኵሎ ዘገብረ ይፌጽም (መዝ፩፥፪-፫) በማለት እንደነገረን ነው የሚሆኑት።

እኛስ መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበው ለምን ዐላማ ነው❓
✔️በአጋጣሚ
✔️ለጥናትና ለዕውቀት ብቻ
✔️ለትችት
✔️በመስማትና ጥቅሱ ደስ ስላለን
✔️ለሕይወት
ወይስ ሰባኪና አስተማሪ ለመሆንና ተቀጥሮ ደሞዝ ለማግኘት ለምን❓

እንደእኔ ፭ኛውን ብንመርጥ በነፍስም በሥጋም ተጠቃሚዎች እንሆናለን።
እናንተስ❓
ሌላም ከአምስቱ ውጪ ቢጨመሩ የምትሉትን መጨመር ትችላላችሁ እኔ ግን አንዳንድ ሰዎችን ስጠይቅ ያገኘሁት መልስ ባብዛኛው በአምስቱ የሚጠቃለል ነው።

መልካም ንባብ።

ወጣቱን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነብ እያበረታቱ ለሚገኙት ለመምህር #በትረ_ማርያም እድሜና ጤና ይስጥልን።

@መምህር ዳንኤል አለባቸው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ቅዱስ መስቀል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በመስቀል ከጠላትነት ድነናል፤ በመስቀል ወደ እግዚአብሔር አንድነት ተመልሰናል፡፡ በመስቀል ዲያብሎስ አርነት ወጥተናል፤ በመስቀል ከሞትና ከጥፋት ድነናል፡፡

ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን በሞት ጥላ ሥር ተይዘን ነበር፤ አሁን ብሥራተ መስቀል በተገለጠበት ጊዜ ግን ህልውና እንኳን እንደሌለው አድርገን ቈጥረን የዘለዓለም ሕይወትን እየናፈቅን ሞትን ንቀነዋል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን ለገነት እንግዶች ነበርን፤ መስቀል በተገለጠ ጊዜ ግን ወንበዴስ እንኳን ለገነት የተገባ ሆኖ ተገኘ፡፡

የሰው ልጅ እንደዚህ ካለ ጨለማ መጠን ወደ ሌለው ብርሃን፣ ከሞት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት፣ ከመዋቲነት ወደ ኢመዋቲነት ታድሶ ተሸጋገረ፡፡ ዓይነ ልቡና ባለማወቅ ጽልመት ከመታወር ድኖ በመስቀል የዕውቀት ብርሃን ተጥለቀለቀ፡፡ እዝነ ልቡና ካለማመን ድንቁርና ወጥቶ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ መስማት ተመለሰ፤ ዕውራንም ብርሃናቸው ተመልሶላቸው የእግዚአብሔርን ክብር ማየት ተችሎአቸዋል፡፡ በቅዱስ መስቀሉ የተሰጡን ሀብታት እነዚህ ናቸው፡፡ በቅዱስ መስቀሉ ያልተሰጡን በረከቶችስ ምን አሉ?

እነሆ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእግዚአብሔር ማመንም ተመልሷል፤ የእውነት ወንጌልም ወደ ዓለም ሁሉ ደርሷል፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ ሰማዕታትም ከመስቀል በኋላ ሞት ሞት መኾኑ እንደ ቀረና የሹመት የሽልማት ማሳ መኾኑን ዐውቀው አብረው ተገልጠዋል፤ በክርስቶስ ማመንም በሁሉም ዘንድ ተሰራጭቷል፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእርሱም ሞት ራሱ ሞቷልና ትንሣኤ ሙታንም ተገልጧል፤ ሕይወትም ታይታለች፤ መንግሥተ እግዚአብሔርም እንደዚሁ እርግጥ ኾናለች፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ለእነዚህ ኹሉ ነገሮች ምክንያት ኾኗል፡፡ በመስቀሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ተማርን፡፡ እንግዲህ ከቅዱስ መስቀሉ ይልቅ ሌላ የተወደደ ምን አለ? እኮ ከቅዱስ መስቀሉ በላይ ለነፍሳችን የሚረባት ወይም የረባትና የጠቀማት ሌላ ምን አለ? ስለዚህ በሙሉ ልባችን ይህን እንመስክር እንጂ ስለ ቅዱስ መስቀሉ ለመናገር ቅንጣት ታህልስ እንኳን አንፈር፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"የክርስቶስ መስቀል ታላቅ በረከትንና ድኅነትን እንድናገኝ ምክንያት እንደ ሆነ እናስተውላለን፡፡ የክርስቶስ መስቀል ስናስበው ሐዘንና ምሬት ነው ነገር ግን እውነታው ደስታና ሐሴትን የሚሞላ ነው፡፡ መስቀል ለቤተ-ክርስቲያን ድኅነት ነው መስቀል ተስፋ ለሚያደርጉት መመኪያ ነው መስቀል የእግዚአብሔር ጠላቶች የነበሩት የታረቁበትና ኃጢአን ወደ ክርስቶስ የቀረቡበት ነው፡፡ በመስቀል ከጠላትነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ተሸጋግረናል በመስቀል ከዲያብሎስ ቀንበር ወጥተናል ከሞት ወደ ሕይወት መጥተናል፡፡ ስለ መስቀል የማንሰብክ ከሆነ አሁንም በሞትና በፍዳ እንደ ተያዝን ነው ማለት ነው፡፡
            ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"አቤቱ ጥበብንና ኃይልን ልብንና እና ልቡናን ዕውቀትንም ስጠን። እንግዲህ ከሚፈታተነን ከሰይጣን ሥራ ሁሉ እስከ ዘላለሙ እንርቅ እንሸሽም ዘንድ። አቤቱ ሁልጊዜ ፈቃድህን ውድህንም እንሠራ ዘንድ ስጠን።"
   ሥርዓተ ቅዳሴ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ምቹ ቀን ሆነላት +
ማር 6:21
ብዙ ጊዜ ክፉ ሰዎች የሚጠሉትን ሰው ለማጥቃት ምቹ ጊዜ ይጠብቃሉ።መጽሐፍ ቅዱስ ይሁዳ ጌታውን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ ጊዜ ይጠብቅ ነበር ይላል።"ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።"(ማቴ 26:16 ) ስለዚህ ወዳጄ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ስትስቅ የሚስቁት እንቅፋት ሲመታህ እኔን የሚሉ ሁሉ ይወዱሃል ማለት አይደለም አንተ የምትወድቅበትን ምቹ ቀን እየጠበቁ ነው።ጠላት ሁልጊዜም አንተን ለማጥቃት ወደ አንተ የሚቀርበው ደካማ ጎንህን አይቶ ነው።ይህን ያነሳሁበት ያለ ምክንያት አይደለም የጌታ መንገድ ጠራጊ ባሕታዊ መናኝ ካህን የሆነውን የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን ራስ ያስቆረጠችው የሄሮዳዳ ልጅ የዚህን ቅዱስ ራስ ለማስቆረጥ መጽሐፍ እንደሚናገር ራሱን የምታስቆርጥበት ምቹ ቀን ትጠብቅ ነበር። ለንጉሡና ለእርሷ ምቹ ቀን ሆነላትና የቅዱሱን ራስ አስቆረጠችው።ሁልጊዜም አምነኸው የማይከዳህ ተደግፈኸው የማይጥልህ ለምነኸው ፊቱን የማያዞርብህ ቀን አይቶ ብቻህን የማይተውህ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
አዲሱ ዓመት የሰላም የጤና ይሁንልን።
Dn Sintayehu Emagnu
መስከረም 01/01/2017 ዓ.ም

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

“ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንደሚሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋል” ዕብ 11፥6 እንዲል!
@ ጃንደረባው ሚዲያ

Читать полностью…
Subscribe to a channel