dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ጥቁር #ልብስ

ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ልዩ_መረጃ
በ"አባ" ሳዊሮስ አማካይነት ከታች የተዘረዘሩት አህጉረ ስብከት ላይ የስም ዝርዝራቸው የሚገኘው መነኮሳት የአህጉረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና ከቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድና እውቅና ውጭ ወረራ እንዲፈጸምበት ስምሪት የተሰጠ በመሆኑ በየአካባቢው የምትገኙ ካህናትና ምዕመናን መንበረ ጵጵስና አህጉረ ስብከቱን እንድትጠብቁ ጥሪ ቀርቧል !

1."አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
2."አባ" ተ/ሃይማኖት ወልዱ - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
3."አባ" ገብርኤል ወ/ዮሐንስ - ጉራጌ ሶዶ ሀገረ ስብከት
4."አባ" ገ/እግዚአብሔር ታደለ - ምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት
5."አባ" ሚካኤል ገ/ማርያም - ከምባታ ሀገረ ስብከት
6."አባ" ኃይሉ እንዳለ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
7."አባ" ተ/ማርያም ስሜ - ጉጂ ሊበን ሀገረ ስብከት
8."አባ" ኃ/ኢየሱስ መንግስቱ - ከፋ ሀገረ ስብከት
9."አባ" ወ/ኢየሱስ ኢፋ - ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት
10."አባ" ጳውሎስ ከበደ - ሀዲያ ሀገረ ስብከት
11."አባ" ኃ/ኢየሱስ ተስፋዬ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
12."አባ" ገ/ኢየሱስ ገለታ - ሆሮ ጉዱሩ ሀገረ ስብከት
13."አባ" ጸጋዘአብ አዱኛ - ምሁር ኢየሱስ ገዳም "የበላይ ጠባቂ"
14."አባ" ኃ/ማርያም ጌታቸው - ምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
15."አባ" ወ/ጊዮርጊስ ኃ/ሚካኤል - ከሚሴ ሀገረ ስብከት
16."አባ" እስጢፋኖስ ገብሬ - ባሌ ሀገረ ስብከት ረዳት
17."አባ" ገ/መድኅን ገ/ማርያም - ጎፋ ባስኬቶ ሀገረ ስብከት
18."አባ" ኃ/ሚካኤል ንጉሤ - ጊኒር ሀገረ ስብከት
19."አባ" አብርሃም መስቀሌ - ዳውሮ,ኮንታ ሀገረ ስብከት
20."አባ" ንዋየ ሥላሴ አክሊሉ - ምዕራብ ጉጂ ሀገረ ስብከት
21.አባ ኪ/ማርያም ቶሎሳ - ጅማና የም ሀገረ ስብከት
22."አባ" ወ/ማርያም ጸጋ - ቦረና ሀገረ ስብከት
23."አባ" አምደሚካኤል ኃይሌ - አርሲ (አሰላ) ሀገረ ስብከት
24."አባ" መርሐጽድቅ ኃ/ማርያም - ጌዴኦ,ቡርጁ,አማሮ ሀገረ ስብከት
25."አባ" ሞገስ ኃ/ማርያም - መናገሻ አምባ ቅድስት ማርያም ፣ ጋራ መ/ዓለምና ደ/ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ "የበላይ ጠባቂ"
26."አባ" ገ/ኢየሱስ ንጉሤ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa



ምንጭ =ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ነገ ጥር 10 የገሃድ ጾም ነው !!!!!!

ገሃድ/ ጾመ ድራረ ጥምቀት
ይህ ጾም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ መጾም ነው፡፡

ይህም ማለት በጥምቀት ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው፡፡ የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነም የጥምቀትን ድራር መጾም ነው፡፡ ሐዋርያት «ልደት ጥምቀት ዓርብ ረቡዕ ቢውል በሌሊት ቀድሰው ሥጋውን ደሙን ይቀበሉ፤ ከሌሊቱ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጹሙ ብለው አይፍረዱ» ብለዋል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/፡፡ የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ሃምሳ የሚበላውን የጥሉላት ምግብ በጠዋት በመብላት ምእመናን በዓሉን እንዲያከብሩ ታዟል፡፡ ይህም እነዚህ ሁለቱ ታላላቅ የእግዚአብሔር በዓላት በመሆናቸው ነው፡፡ የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማክሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል፡፡ በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ሥራ ይከናወናል፡፡ የጥምቀትን ዋዜማ ጥሉላት መባልዕትን መተው ነው፡፡ ይህንንም እንደ ዘይቤው ገሀድ ይለዋል፣ መገለጫ፣ ግልጥ፣ ይፋ መሆን ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ጋድ ይለዋል፣ ለውጥ፣ ልዋጭ ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ረቡዕ ዓርብ ሲውል በዚያ ለውጥ ማክሰኞ ሐሙስ ይጾማልና ጋድ አለው፡፡ እንዲሁም አንድ ጊዜ ሲጾም አንድ ጊዜ ሲቀር እንዳይረሳና ቅዳሜ ወይም እሑድ በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ አይቻልም፣ ነገር ግን እህል ውኃ እንጂ ጥሉላት ከመብላት መጠበቅ ይገባል፡፡ ልደት የሚውልባቸው ረቡዕና ዓርብ ቢሆኑ የፍሥክ /የሚበላባቸው/ ቀናት ሆነው እንዲከበሩ ሐዋርያት ያዘዙ ቢሆንም በዋዜማው የሚገኙት ማክሰኞና ሐሙስ ከጾመ ነቢያት ጋር የተያያዙ ስለሆኑ መጾማቸው ግድ ነው፡፡
የገሃድ ጾም እስከ ማታ ድረስ ቀኑን ሙሉ ነው የሚጾመው
ሆኖም የነቢያትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች በመላው የጾሙ ቀናት ሲበሉ ቆይተው በዋዜማው ብቻ ገሀድ ነው ብለው ይጾማሉ፡፡ ነገር ግን ለጾመ ነቢያት ገሀድ የለውም፡፡ ጾሙ የጥምቀት ብቻ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ለጾመ ነቢያት ገሀድ እንዳለው የሚናገሩም አሉ፡፡ ለዚህም የሚያቀርቡት ማስረጃ እስከ ምሽት መጾሙን ነው፡፡ ይህም «አድልው ለጾም፤ ለጾም አድሉ፡፡» እንዲሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ቢጾም የሚያከራክር ወይንም ስህተት ነው የሚያሰኝ አለመሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ነቢያት ይወርዳል፣ ይወለዳል ብለው የተናገሩት ቃል ይፈጸም ዘንድ የሰው ልጆችም ድኅነት ማረጋገጫ እውን ይሆን ዘንድ እንደ ጾሙ እንደ ጸለዩ በልደቱም እንስሳት፣ ሰዎች እንዲሁም መላእክት በአንድነት በደስታ እንደዘመሩ የእኛም ደስታ የተረጋገጠበት ነው፡፡ በመሆኑም በፍቅር፣ በጾም በጸሎት ዛሬም እናስበዋለን፡፡ ነቢያት በረከት እንዳገኙ እኛም ከእግዚአብሔር በረከት እናገኛለን፡፡ ለዚህም አምላካችን ይርዳን

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ልባም ሴት

#ዜሮን_ፃፉ_አሁንም_ድጋሚ_ዜሮን_ፃፉ.......
ደስ የሚል መልእክት ነው አንብቡት
ጋብቻ ለመመስረት ያሰበ አንድ ወጣት ከቤተሰብና ከጓደኞቹ ጋር ተማክሮ ከጨረሰ በኋላ የንስሀ አባቱ ዘንድ በመሔድ ይህንን ውሳኔውን አስረዳቸው፡፡
#ጥበበኛውም_አባት ለማግባት ያለውን ጉጉት በልጁ ፊት ላይ እያስተዋሉ አሳቡ መልካም እንደሆነ ገልጸው ማስታወሻና ብዕራቸውን በማውጣት “ስለ ልጅቷ ትንሽ ነገር ንገረኝ” በማለት ጥያቄ አቀረቡለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ “ትውልዷ ከነገስታት ዘር እድገቷም በምቾት መሐል ነው” አለ፡፡ እኚህም አባት በሙሉ ልብ ሆነው በያዙት ማስታወሻ ላይ ዜሮ ጻፉ፡፡
ወጣቱም ስለ ልጅቷ ማብራራቱን ቀጠለ፡- “በጣም ውብ ናት” አለ፡፡ እርሳቸውም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ “በጣም ዝነኛ ናት” አለ፡፡ ደግመው ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ “በጣም ሀብታም ናት” አለ፡፡ ጥበበኛውም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡
“በጣም ምሁር ናት” አለ፡፡ አሁንም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡
“በጣም ዘመናዊ ናት” አለ፡፡ ተጨማሪ ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ በመጨረሻ ግን የረሳውን አንድ ነገር ነገራቸው “ልባም እንዲሁም ሕይወቷ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና የተሰጠ ነው” አላቸው፡፡ ጥበበኛውም አባት ፊታቸው ላይ ፈገግታ እየተነበበባቸው አስቀድሞ ከጻፉአቸው ስድስት ዜሮዎች ፊት አንድ ቁጥርን ጽፈው “በል ሂድና አግባት” አሉት፡፡ ወጣቱም በደስታ ከፊታቸው ሄደ፡፡ በደስታም ልጅቷን አገባት♥♥♥
ጋብቻ ብዙ ጊዜም በሌላው ሰው አካላዊ ገጽታና ውጫዊ አቋም ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ምንም እንኳን በአካላዊ ውበት መማረክ ወደ ፍቅር የሚመራ አንደኛው መንገድ ቢሆን እውነተኛ ፍቅር ግን በአካላዊ ውበት፣ በአፋዊ መስፈርት ከመሸነፍ ያለፈ ነው፡፡ አካላዊ ውበት የጊዜያዊ ጉጉት መገለጫ ሲሆን ፍቅር ግን በሌላው ውስጥ ያለውን መልካሙን ነገር በመሻት ትዕግስትን መሰረት የሚያደረግ ነው፡፡ይህም የትኛውንም ልብ የመንካት፣ በላቀና በጠለቀ መንገድ የመግዛት ጉልበት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው በዘመኑ የሚያሳልፋቸው ትልልቅም ይሁን ትንን ውሳኔዎች አሉ፡፡ ሕይወትም በዚህ የዕለት ተዕለት ቋሚ የመምረጥና የመወሰን ተግባር ላይ የተመሰረተች ናት፡፡ ጋብቻ የእኛን ትልልቅ ውሳኔ ከሚፈልጉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡
የምናመልከውን እንመርጣለን፣ የምንኖርበትን አካባቢ እንመርጣለን፣ የልባችንን የምናካፍለው ባልንጀራ እንመርጣለን፣በትዳር አጋር የሚሆነንን እንመርጣለን፣ በአጠቃላይ መሆን የምንፈልገውን እንመርጣለን፡፡ በእርግጥ ምርጫችንን ከምንኖረው በላይ ተጽእኖ ወደ ኑሮአችን የሚያመጣውን መኖራችን ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህም ውስጥ ከእውነት ጋር ያለን ትስስር ሊደበዝዝ አይገባም፡፡ ምርጫችን ውስጥ ሞትም ሕይወትም፣ ደስታም ሀዘንም፣ ክብርም ውርደትም አለ፡፡ መርጠን ዘመናችንን የእንባ ልናደርገው መብቱ የእኛ ነው፡፡
እግዚአብሔር እውነተኛ ፍቅር ሰጥቷችሁ
ለዚህ ክብር ያብቃችሁ አሜንንን🙏🙏🙏🙏


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

👑 በቀራኒዮ መስቀል ስር እናት የተሰጠው ታማኝ ሐዋርያ👑

🌹ጥር 4, ቀን ቅዱስ ዮሐንስን አምላክ ሞትን እንዳያይ የሰወረው እለት ነውና እንኳን አደረሰን| አደረሳችሁ!!!🌹

🌿🌿🌿
🍇 " ቤተሳይዳ " በምትባል የገሊላ አውራጃ ነው የተወለደው! " ዮሐንስ" ማለት የእግዚአብሔር ጸጋ, ሓሴት ማለት ነው🙏

🌿 አባቱ ዘብዴዎስ (ቅለዮጳ), እናቱ ደግሞ ማርያም ሰሎሜ (ማርያም ባውፍሊያ) ከእመቤታችን ጋር በመስቀል ስር የተገኘች ታላቅ እናት ናት!!! ወንድሙ ከ12 ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ነው🙏❣️🙏

🍇አምላክ ሲመርጥ እንዲህ ነው! ከዓሣ አጥማጅነት አንስቶ ለክብር የተጠራ ሐዋርያ፣ ወንጌላዊ፣ ታማኝ አገልጋይ ነው🙏

🌿 ከሐዋርያት ሁሉ እስከ መስቀል ስር ድረስ የተከተለ፣ የታመነ ፣ እነሆ እናትህ የተባለ፣ እመቤታችንን በቤቱ ለ15 ዓመታት ፍቅሯን ፣ ጣዕሟን ፣ በረከቷን እያገኘ በክብር ያኖራት ታላቅ ሐዋርያ ነው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ🙏👑🙏

🍇 📌. ዮሐንስ ሐዋርያ 📌. ታኦሎጎስ
| ወንጌላዊ|

📌. ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ 📌. ንባቤ መለኮት

📌. ፍቁረ እግዚእ 📌. አቡቀለምሲስ

📌. ዮሐንስ ዘንስር 📌. አማናዊ ወዳጅ
ይባላል!!!

🌿 ቅዱስ ዮሐንስ በራእይ መንፈስ ተመርቶ 3ቱን ወንጌሎች የጻፈ ነው :-
✍️.የዮሐንስ ወንጌልን
✍️. የዮሐንስ መልእክትን
✍️. የዮሐንስ ራእይን የጻፈ ታላቅ ወንጌላዊ ነው🙏

👑🌿 . በመጨረሻም ስለክብሩ, ስለፍቅሩ ጥር 4 , ቀን በ90 ዓመቱ ሞትን ሳያይ ልክ እንደ ኤልያስ አምላክ የሰወረው ታላቅ ሐዋርያ ነውና ክብር እና ምስጋና ይገባዋል🙏❣️🙏

✝️🌿 በረከቱ ፣ ፍቅሩ ፣ አማላጅነቱ አይለየን💚💛❤️
🇪🇹ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን🙏

🍇 👇👇👇 🍇
ይከታተሉን

ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇
@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ጾሙስ_አበቃ.....?✝
አንብቡት
😌

🥀ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!

🥀አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?

🥀 የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!

🥀ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግባር ብንወለድ!

🥀የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!

መጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረኪዳን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን
ተቀላቀሉ ቴሌግራም ተዋህዶ አሜን
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ፈተና በክርስቲያናዊ የአገልግሎት ሕይወት



ክርስትና የተግባር ሕይወት ነዉ ፡፡ የክርስትና ሕይወት ተራ ኑሮ ብቻም ሳይሆን ዘለዓለማዊ ዓላማ ያለው ሕይወትም ጭምር ነዉ፡፡ በተጨማሪም የክርስትና ሕይወት እግዚአብሔርን እና ቅዱሳንን የምንመስልበት ሕይወት እንዲሁም ቅዱስ የምንሆንበት ሕይወት ነዉ፡፡ ቅዱሳንን እንድንመሰል የሚያደርገን የክርስትና ሕይወትን በሕይወት፣ በፍቅር፣ በቅድስና፣ በትዕግስት፣ በታማኝነት፣ በንጽህና መኖር እና መግለጥ ሲቻል ብቻ  ነዉ፡፡  ለዚህ ነዉ ሐዋርያው ቅዱስ ጰዉሎስ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን  ምሰሉ ያለን፡፡

የክርስትና ሕይወት  በመንፈሳዊነት ይገለጣል፡፡ ቃሉን በመማር፣ በመስማት፣ በሕይወትም በመግለጥ (በመኖር) ይገለጣል፡፡ “የክርስትና ሕይወት የቅድስና ሕይወት ነዉ”  ስንል ቅድስናዉ የሚገለጠዉ በአገልግሎት ሕይወት፣ ትጋት እና ፍቅር ነዉ፡፡ ክርሰትና አገልጋይነት ነዉ፤ ያዉም በታማኝነት እና በመንፈሳዊነት የምናከናውነው፡፡

አገልግሎት ለቅድስና ሕይወት ያበቃል፡፡ ከኃጢአት፣ ከክፋት፣ ከበደል፣ ከክፉ ምኞት ሐሳብ እና ተግባርም ይሠዉራል፡፡ ለፀጋ እግዚአብሔር፣ ለመንግሥቱና ለርሰቱም ያበቃል፡፡ ለበለጠ ፀጋ እና ክብርም ያደርሳል፡፡ ሰማያዊና ምድራዊ፣ መንፈሳዊ ሀብትን እና ክብርንም ያሰጣል፡፡ ማቴ ፡25፡ 14-30. መንፈሳዊ አገልግሎት፣ መንፈሳዊነት እና ክርሰትና ራስን መካድን፣ ራስን ማሸነፍን፣ ዓለምን መጥላትን/መተዉን፣ ለእግዚአብሔር ራስን አሳልፎ ማስገዛትን/መስጠትን ይፈልጋል፡፡ ‹‹ኑሮዬ ይበቃኛል›› ማለትን ይፈልጋል፡፡ ምክንያትን ማሸነፍን፣ ትዕግሰትን እና ማስተዋል ይጠይቃል ፡፡

የክርስትና ሕይወት በአገልግሎት ይገለጣል ስንል አገልግሎት ፈተና እንዳለዉም ደግሞ መርሳት የለብንም፡፡  መንፈሳዊ አገልግሎት መከራ ይበዛበታል፣ መዉጣት እና መዉረድ መዉደቅ እና መነሳትም አለው፡፡ ያለ ክርስትና ሕይወት መንፈሳዊነት የለም፤ የእግዚአብሔር ሰውም መሆን አይቻልም፡፡

እዉነተኛ አገልገሎት፣ የክርስትና ሕይወት እና  መንፈሳዊነት  ባለበት ቦታ ሁሉ መከራ እና ፈተና አለ፤ ያለ ፈተናም ጸጋን መቀበል አይቻልም፡፡ ለዚህም ነዉ ሐዋርያት በራሳቸው የተፈተነ ሕይወት ተግባራዊ ማሳያነት “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” እያሉ ያስተማሩት (የሐዋ.14፡21-22)፡፡ ይህም መከራ የደረሰባቸው በደስታ የሚቀበሉትና በመንፈስ የሚበለጽጉበት ሆኖላቸዋል፤ “… ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ  ደስታ ጋር ተቀብላችሁ እኛና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፡” (1ተሰ. 1፡6) እንዲል፡፡

ቅዱስ ጳዉሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈዉ መልእክቱ በመከራ ስለሚገኝ በረከት እንዲህ ያስተምረናል። “በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸዉ ብዛትና የድኅነታቸው ጥልቀት የልግስናቸው ባለጠግንት አብዝቶአል።” (2ኛ ቆሮ.8፡2)፡፡ ፈተና በተለያዩ መንገዶች በተለያዩ ምክንያቶችም ሊመጣብን ይችላል፡፡  ለመባረክና  ለመዳንም በፈተና መጽናት ያስፈልጋል፡፡  ለዚህ ነዉ መጽሐፍ ቅዱሰ በተደጋጋሚ ‹‹እሰከ መጨረሻዉ የሚጸና እርሱ ግን ይድናል›› በማለት አጽንቶ የሚመክረን (ማቴ 10፡ ማቴ 24፡ ማር 13)፡፡

ፈተና የክርሰትያናዊ ሕይወት አንዱ መገላጫ ነዉ ፡፡ ያለፈተና በአገልግሎት እና በመንፈሳዊ ሕይወት ያለፉ ቅዱሳን የሉም፡፡ ይህን ሲያስረዳ ቅዱስ ጰዉሎስ 2ኛቆሮ. 11፡22-29 ላይ፡- “—–በድካም አብዝቼ፣ በመገረፍ አብዝቼ፣ በመታሰር አትርፌ፣ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ፡፡ አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ፡፡ ሦስት ጊዜ  በበትር ተመታሁ፤  አንድ  ጊዜ  በድንጋይ  ተወገርሁ፤  መርከቤ ሦስት  ጊዜ  ተሰበረ፤  ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ  ኖርሁ። ብዙ ጊዜ  በመንገድ ሄድሁ፤ በወንዝ  ፍርሃት፣ በወንበዴዎች  ፍርሃት፣  በወገኔ በኩል ፍርሃት፣  በአሕዛብ  በኩል  ፍርሃት፣  በከተማ ፍርሃት፣  በምድረ በዳ ፍርሃት፣  በባሕር ፍርሃት፣  በውሸተኞች  ወንድሞች በኩል ፍርሃት  ነበረብኝ፡፡ በድካምና በጥረት፣  ብዙ ጊዜም  እንቅልፍ  በማጣት፣  በረሀብና  በራቁትነት ነበርሁ። የቀረዉንም  ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት  የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው”  በማለት ስለ ክርሰቲያናዊ የአገልግት ሕይወት እና የመከራን ጥብቅ ቁርኝት ያስረዳናል ፡፡

የክርስቲያን  መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ  በድሎት እና በምቾት የተሞላ አይደለም፡፡ ይልቁንም በማያቋርጡ ተጋድሎዎች የተሞሸረ ነዉ እንጂ፡፡ ክርሰቲያናዊ ሕይወት ቅዱሳንን የምንመሰልበት እና ቅዱስ የምንሆንበት ሕይወት ነዉ፡፡ መከራ እና ፈተና የክርሰትና  የሕይወት ቅመም ነዉ፡፡ ከጸጋ ወደ ጸጋ ያሳድጋል፣ ያተጋል፣ ያበረታል፣ ለንሰሐ ሕይወት ያበቃል፣ ወደ ጾም እና ጸሎት ይመራል፡፡ ሁል ጊዜ ወደ ቤተ እግዚአብሔርም እንድንሄድ ሕይወታችንን በእርሱ ፍቃድ፣ ትእዛዝ እና ሀሳብም እንድንመራ ያደርጋል፡፡  ያለ ፈተናና  መከራ የክርስትና ሕይወት፣ ድኅነት እና ጽድቅ አይገኝም፡፡ መከራ ሲባል ደግሞ ልንችለዉና ልናሸንፈዉ ከምንችለዉ በላይ እንደማንፈተን መጽሐፍ እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነዉ፤ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናዉ ጋር መዉጫዉን ደግሞ ያደርግላችኋል፡፡” (1ኛ ቆሮ እግዚአብሔር
ክርስቲያን ለማመን ብቻ አልተጠራም፡፡ ለማገልገል፣ የቅድስና ሕይወትንም ለመኖር፣ ለመልካም ሥራ እና የእግዚአብሔርንም መንግሥት ለመዉረስ ጭምር ነዉ እንጂ፡፡ ለዚህ ነዉ መጽሐፍ ‹‹እግዚአብሔር ለቅድስና ጠርቶናል›› የሚለን (1ኛ ተሰ.4፡7)፡፡

ዳግመኛም የተጠራነው በስሙም መከራን ለመቀበል እና ለመፈተንም ጭምር ነው፡- ቅዱስ ጰዉሎስ ‹‹ስለ እርሱ መከራን ደግሞ ልትቀበሉ እንጅ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አልተጠራችሁም››  በማለት ያሰተማረንም ይህንን ያስረዳል፡፡ ፊልጵ.(1፡29)

ሁሉም የሚደርስብን ፈተና ግን  በእግዚአብሔር ሰለአመንን በመልካም ሥራችን ነዉ ብሎ መዉሰድ ደግሞ አግባብነት የለውም፡፡ ከእግዚአብሔር የሚመጣብን ፈተና ከእምነታችን ጽናት፣ ከፍቅሩ  ጥልቀት እና ስፋት፣ ለበለጠ ፀጋ  እና ክብር እንበቃ ዘንድ በመንፈሳዊ ሕይወታችን  ጥንካሬ  ደረጃ የሚመጣብን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የአባታችን የአብርሃም  ፈተና እና የትዕግስተኛዉ አባታቸን ኢዮብ ዓይነት ፈተና ማለት ነዉ ፡፡

ግን በእኛ ስህተት፣ በኃጢአታችን ብዛት፣ ለትምህርት እና ለቅጣትም ጭምር  የሚመጣም ፈተና አለ፡፡  በዚህ ጊዜ ከኃጢአት መመለስ፣ ማዘንና ማልቀስ፣ ንሰሐም መግባት፣ መጾም እና መጸለይም  ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ቅዱስ ያዕቆብ፡- ‹‹ማንም ሲፈተን በእግዚዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና፡፡ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብ እና ሲታለል ይፈተናል ፡፡ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፣ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወለዳለች›› በማለት ይመክረናል፡፡ ያዕ. 1፡13.

ስለዚህ ክርስቲያን ሲኖር እንዴት መኖር አለበት? ስንል፡- ‹‹ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፡፡ በበጎነትም እዉቀትን፣ በእዉቀትም ራስን መግዛትን፣ ራስንም በመግዛት መጽናትን፣ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰልን፣ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማች መዋደድ፣ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ›› የሚለንን ቃሉን መሠረት እና የሕይወታችን መመርያ በማድረግ መኖር አለብን፡፡ (2ኛ ጴጥ ፡ 1፡5-8)

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነኝ›› እንዲል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ማለቱ ለእግዚአብሔር የተወሰነ ፊት ኖሮት ማለትም እንደ ንጉሥ ወታደር በእግዚአብሔር ፊት ተገትሮ የሚቆም መሆኑን  ለመግለጽ አይደለም፡፡ ምንጊዜም ከእግዚአብሔር የማይለይ መሆኑን እና አማላጅነቱን ለመግለጽ ነው እንጅ፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፱)

ቅዱስ ገብርኤል  ምእመናንን የሚጠብቅ ጠባቂ መልአክ ነው፤  ስለዚህም ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት፤ ‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል››እንዲል (መዝ.፺፩፥፲፩)፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል​››​(መዝ.፴፬፥፩)፤ ‹‹በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ፡፡​››​(ዘጸ.፳፫፥፳)

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብረ በዓሉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓላቸውን በጸሎት እና በምስጋና ታከብራለች፡፡ በተለይም ታኅሣሥ ፲፱ ቀን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በዓል የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አግብርተ እግዚአብሔር አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከእቶነ እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በግእዝ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ትማልም አሲረነ ሠለስተ እደወ ወደይነ ውስተ እቶነ እሳት  ዮምሰ እሬኢ አርባዕተ እደወ እንዘ ያንሶሰዉ ማዕከለ እሳት ፍቱሐኒሆሙ ወገጹ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብሔር ይመስል››፤ ትናንት ሦስት ሰዎች አስረን ከእሳቱ እቶን ጥለን ነበር፤ ዛሬ ግን ዐራት ሆነው ከእሥራታቸው ተፈትተው በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ አያለሁ፤ ዐራተኛውም የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል፤ በማለት ይገልጸዋ፡፡ (ወዲያውም ከእቶኑ ሂዶ‹‹ አንትሙ ሲድራቅ ወሚሳቅ ወአብድናጎ አግብርተ እግዚአብሔር ንዑ ፃዑ ዝየ፤ ኑ ውጡ›› አላቸው ብር ብር እያሉ ከእሳቱ ውስጥ ወጥተዋል፤ በልብሳቸው ላይም ጥላሸት እንኳን አልተገኘም፤ ናቡከደነጾርም ይህን አይቶ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን አለ፤ ንጉሡም አዋጁን በአዋጅ መልሶ ለሕጻናቱ በሹመት ላይ ሹመት በክብር ላይ ክብር ጨምሮላቸዋል)፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት እና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር፤ አሜን፡፡

@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

📌 ወደ ሕይወት የምትወስደዋ ጎዳና....

❖ ወደ ሕይወት የምትወስደዋ ጎዳና ጠባብ ናት ወደ ጥፋት የምትወስደዋ ጎዳና ሰፊ ናት፡፡

❖ ጸሎት አንድን ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገባ የማብቃት አቅም ያላት ጠባቧ ጎዳና ናት፤ ከኃጢአት ንጹሕ ሆነው የሚያቀርቧት ጸሎት ፍጹም ሥራን ትሠራለች።

❖ ንጹሐ ባሕርይ የሆነውን ክርስቶስን የመሰለ ክርስቲያን በጨለማ የነቃና ለጸሎት የሚተጋ ሰውን ይመስላል፤ ይህ ሰው በጨለማ ውስጥ ቢሆንም በዓይን በማይታይ ብርሃን የተከበበ ነው፡፡

❖ ክፉውንም የሆነ ሰው ግን በሚታየው ብርሃን ውስጥ ሆኖ የጨለማው ልጅ እንደ መሆኑ መጠን የእርሱን ግብር ይፈጽማል፤ ስለዚህ ይህ ሰው በውጭ ሲታይ በብርሃን ውስጥ ነው ፤ በውስጥ ግን የሚዳሰስው ጨለማ አሳውሮታል፡፡

❖ ተወዳጆች ሆይ ! እንደዚህ ዓለም ልጆች ዓይኖቻችሁ በዚህ ዓለም ብርሃን ድጋፍ ብቻ የሚመለከቱ እንዳይሆኑ ተጠንቀቁ፤ በዚህ ዓለም ዓይናማ መሆን ወደ ቅድስና የሚያመጣ ዓይናማነት አይደለምና፤ በዚህ ዓለም ብርሃን የሚመላስ ሰው ይመለከታል ግን አንቀላፍቶአል፤ ምልከታው ጤናማ አይደለም እይታውም ሁሉ ምድራዊ ነው፡፡

📌 ምንጭ
✍️ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር  

ክፍል ሦስት
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
      ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር  
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥  


📌 ጊዜን በአግባቡ መጠቀምና ሰዓትን ማክበር

❓ጊዜ ማለት ምን ማለት ነው

❖ በዚህ ዓለም ስንኖር ለምናከናውናቸው ተግባራት የምንወስደው ሠዓት ጊዜ ይባላል፡፡ 

ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ለምን አስፈለገ

❖ ጊዜያችንን የምናሳለፈው በተለያዩ ነገሮች ነው፡፡

🔔ለምሳሌ
❖ በትምህርት ቤት በክፍል፣ 
❖ በቤተ መፃህፍትና በጨዋታ፣
❖ ከጓዶኞቻችን ጋር፣ 
❖ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት መማር፣ 
❖ ቅዳሴ ማስቀደስ ወ.ዘ.ተ)

❖ በእነዚህ ነገሮች ጊዜያችንን መጠቀም ይኖርብናል፤ ምክንያቱም ጊዜያችንን በአግባቡ ካልተጠቀምን እድሜያችን ጠቃሚ ነገር ሳንሰራበት ሊያልፍ ስለሚችል ነው።

📌 ጊዜያችንን በአግባቡ መጠቀማችን የሚታወቀው

❖ ትምህርት ቤት ውስጥ ሳያረፍዱ በሰዓት ትምህርት ቤት መገኘት

❖ ስራ ቦታ ሳናረፍድ በመገኘት

❖ ቤተ መፃህፍት ልናጠና ያሰብንበትን ሰዓት በማጥናት ማሳለፍ

❖ በቤት ውስጥ
ቤተሰቦቻችንን በመርዳት ስናሳልፈው  

❖ ከጓደኞቻችን ጋር በጥናት ሆነ በጨዋታ የምናሳልፋቸው ጊዜያት 

❖ በቤተ ክርስቲያን 
በሠንበት ትምህርት ቤት ባሉን መርሐግብራት ላይ በሰዓት መገኘት 

❖ ወደ ቅዳሴ ለፀሎት ወይም ለሌላ መርሐ ግብር ስንመጣ መርሃ ግብሩ ሳይጀምር መድረስ

በነዚህ ነገሮች ሁሉ በሰዓት እየተገኘን መፈፀም ያለብንን በሰዓቱ በመፈጸም ሊሆን ይገባል

❖ እግዚአብሔር አምላካችን እኛን ለማዳን ከእመቤታችን በነሳው ስጋ በዚህ አለም ሲመላለስ የመጣበት ጊዜ ለአዳም በሠጠው ቀጠሮ ከቆጠሮው(ከወሰነው ጊዜ) ሳይቀድም ሳያልፍ ነው። 

❖ ከዚህ የምንረዳው ሰዓት ማክበርን የሚያስተምረን ጌታችን ራሱ ነው።

❗️አስተውል

❖ የቤተክርስቲያን ልጆች ሁልጊዜም ጊዜያቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙ ና ሰዓት የሚያከብሩ ናቸው።

📌 አዘጋጅ ዲ/ን ዘአርሴማ

✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

        
           ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                  ይቆየን 

ይቀጥላል 
           🙏 ሼር ማድረግ አይርሱ 🙏

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11

           ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

        ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
ማሰብና ማድረግ እኩል ናቸው
        ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥


➯ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመን የኖሩ እጅግ ለእምነታቸው የሚቀኑ ጽኑዕ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ታዲያ በአንድ ወቅት ኃጢአትን በማሰብ እና በማድረግ መካከል ስላለው ልዩነት አንሥተው ይከራከሩ ጀመር ብዙዎቹም "ማሰብና ማድረግ ምንም ልዩነት የላቸውም" የሚል የሚል አቋም ነበራቸው፤ በስተመጨረሻም ይህን ጥያቄ እንዲመልስላቸው ወደ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይዘው ቀረቡ።

➯ ቅዱሱ በምሳሌ ሊያስተምራቸው ስለ ፈለገ አንድ ቀን ሙሉ ምንም ምግብ ሳይቀምሱ ቆይተው ማታ ለእራት እርሱ ዘንድ እንዲመጡ ጠራቸው፤ በቤቱም ለዓይን ያማረ ለመብላት ደስ የሚያሰኝ ፈታኝ ማዕድ እንዲያዘጋጁ ለአርድእቱ ተናገረ፤ እነርሱም እንዳላቸው አዘጋጁ።

➯ እንግዶቹም በመጡ ጊዜ በየቦታቸው ተቀመጡ፤ የተዘጋጀውም መዓድ ከፊት ቀረበ የምግቡ መዓዛ የምግብ ፍላጎት የሚከፍት ብቻ ሳይሆን የሰዎቹን ረሃብ የሚያባብስም ጭምር ነበር፤ ከዚያም ቅዱስ ዮሐንስ በቤቱ የሚያገለግለውን ዲያቆን ከመዝሙራት እያወጣ እንዲያነብ አዘዘው፤ ዲያቆኑም ረዘም ላሉ ሰዓታት ማንበቡን ቀጠለ እንግዶቹ ግን ከመጎምዠት ብዛት በአፎቻቸው ምራቅ ሞላ፤ ጸሎቱ አልቆ እስኪመገቡ መቆየት ጣር ሆነባቸው።

➯ አሁን ጸሎቱ ተጠናቋል፤ ይሁን እንጂ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ግን እንግዶቹን ለመዓዱ እንዲቀመጡ በመጋበዝ ፈንታ "በቃ ወደየቤታችሁ በሰላም ግቡ" ብሎ አሰናበታቸው፤ ወደ ቤቱ ተጠርተው የመጡት እንግዶችም ደነገጡ፤ ይህን ያየው ቅዱሱ "ምነው ግራ የገባችሁ ትመስላላችሁ? ምግቡን በደንብ አላያችሁትም? ልትበሉስ እጅግ ተመኝታችሁ አልነበረም?" ሲል ጠየቃቸው፤ እነርሱም "አዎን" አሉት።

➯ አፈወርቅም "ጥሩ፤ እንግዲያውስ እንደ በላችሁ ይቆጠራላ" ቢላቸው ሁሉም ፈገግ አሉ፤ በዚህ ጨዋታ መካከል የእነዚያ ክርስቲያኖች ጥያቄ በሚገባ ተመለሰላቸው።

➯ ክፉን ነገር በማሰብና በማድረግ መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ በዚህ ታሪክ ውስጥ ግልጽ ሆኖ ይታያል፤ ክርስትና ሐሳብ እና ሥራን መቀደስ ነው፤ ነገር ግን የሐሳብ ንጽሕና ባይኖርህ "ማሰብ ከማድረግ ጋር እኩል አይደል!" ብለህ በኅሊናህ የቋጠርከውን ክፋት ለማድረግ ራስህን አታደፋፍር፤ ያሰብከውን እስካልፈጸምህ ድረስ አሁንም ከኃጢአት ወጥመድ የማምለጥ እድሉ በእጅህ ነው።

✍️"ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት"
📖ዘፍ 4፥7

✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

📌 ምንጭ
✍️ዲያቆን አቤል ካሳሁን

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
 🧲  /channel/dnhayilemikael
 ───────────

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

*~የትዕቢት ታማኝ ልጅ ማን ነው ?~*

በወንድሞች ላይ መፍረድ የእግዚአብሔር የሆነውን የጌትነቱን ንብረት እንደ መስረቅ፣ በክርስቶስም የፍርድ ዙፋን ላይ ራስን እንደማስቀመጥ ይቆጠራል፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ድፍረት፣ ከዚህ የሚበልጥ ኃጢአትስ ከየት ይገኛል? አበው ‹ሌሎች ላይ መፍረድ› የትዕቢት ታማኝ ልጅ ሲሆን፣ መጋቢና አሳዳጊውም እርሱው (ትዕቢት) እንደ ሆነ ይናገራሉ፡፡

***
የሥነ ልቡና ሳይንሱም እንደሚናገረው አንዳንድ ጊዜ በራስ ውስጥ ያለ የዕውቀት እና የልምድ ክምችት እያነሰ ሲመጣ፣ በሰው ፊት ዝቅ ብሎ ላለመታየት ሲባል በሁሉን ፈራጅና ነቃፊነት መጋረጃ ራሳችንን ልንከልል እንሞክራለን። ይህም አንዱ የሰብዕና መቃወስ (personality disorder) ምልክት ነው።

+++እግዚአብሔር በሰው ያልፈረዱ ቅዱሳን ካሉበት ገነት በቸርነቱ ያግባን!+++

+++‹‹አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም›› ሉቃ 6፡37+++ በሚል እስተማሪ ፁሑፍ የተወሰደ ።

~ዲያቆን አቤል ካሳሁን~


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#የብሔር_ብሔረሰቦች_ቀን

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሁለት ጊዜ ተከስቶአል::

አንደኛው በቋንቋ ልዩነት ተደበላልቀው በተበታተኑበትና አብረው መገንባት በተዉበት #በባቢሎን_ሜዳ ላይ ነበር:: ያን ቀን የቋንቋ ልዩነት ለመለያየትና ለመበታተን ሰበብ ሆነ::

ሁለተኛው ቀን ደግሞ በባቢሎን የተበተነው ቋንቋ የተሰበሰበበት #የጰራቅሊጦስ_ዕለት ነበር:: ያን ቀን ሐዋርያት የተለያየ ቋንቋ ቢናገሩም ልባቸው አንድ የሆነበት ቀን ነበር:: ከየሥፍራው የመጡ ብሔር ብሔረሰቦች ተሰብስበው አንዱ የሌላውን ቋንቋ በፍቅር የተናገረበት ዕለት ነበር:: የቋንቋ ልዩነት ለአንድነትና ፍቅር የዋለበት ቀን ሆነ::

ወዳጄ ልብ አንድ ከሆነ የቋንቋህ ልዩነት አይገድብህም:: የኢትዮጵያን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን #የባቢሎኑ_ሳይሆን #የጰራቅሊጦሱን_ቀን_ያድርግልን:: የቋንቋ ልዩነታችን እንደ ባቢሎን የምንበተንበት መገንባት የጀመርናትን ሀገር የምንተውበት ሳይሆን እንደ ጰራቅሊጦስ የምንሰባሰብበት ይሁንልን::

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
               አሜን
ክፍል ሁለት
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
      ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

📌የአነጋገር ስነምግባር

❓አነጋገር ማለት ምን ማለት ነው

❖ አነጋገር ማለት አንድ ሠው ያለውን ሃሣብ የሚገልጽበት መንገድ ማለት ነው፡፡


✅መልካም አነጋገር ❖ በሠዎች ዘንድ ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚወደድና በአክብሮት ሀሳባችንን     የምንገልፅበት መንገድ ነው፡፡
 

❖ ቤተሰቦቻችን ጥያቄ ሲጠይቁን በእርጋታ መልስ መስጠት፡፡

✅ጥሩ ያልሆነ አነጋገር

❖ ለታላቅ ሆነ ለታናናሾቻችን የምናሳየው እነርሱን ሊያበሳጭና  እግዚአብሔርም እንዲያዝንብን የሚያደርግ ንግግር ነው፡፡ 

🔔ለምሣሌ

❖ ጓደኛችን አበበን አይተኀዋል ሲለን እኔ የአበበ ጠባቂ ነኝ ብሎ መመለስ የቃየን ዓይነት መልስ  ነው፡፡
  
አነጋገራችን መልካም መሆን ለምን አሰፈለገ

❖ በቤተክርስቲያን ትምህርት አንድ ክርስቲያን ክርስቲያን መሆኑ የሚታወቀው በአነጋገሩና በአኗኗሩ ነው፤ ቢሰድቡት እንኳን እርሱ የማይሳደብ፣ ለሚጠይቁት ጥያቄ ሁሉ በአግባቡ ለመመለስ ሁሉጊዜ የሚተጋ ነው፤ ስለዚህ ክርስቲያን ስለሆንን አነጋገራችን ጥሩ እና ያመረ መሆን አስፈላጊ ነው እግዚአብሔር የሚወደው ይህንን ነውና፡፡ 

❖ እኛ ጥሩ (መልካም) አነጋገር ካለን ሠዎች ይወዱናል ለኛ የተለየ ፍቅር ይኖረቸዋል ስለዚህ ስንነጋገር በአክብሮት መሆን አለበት ጥሩ ካልሆኑ አነጋገሮች መሳደብ (ሌሎችን በቁጣ መናገር) ሌሎችን መስደብ እግዚአብሔር የማይወደው ብሎም እኛንም ሊያስቀጣን እንደሚችል ማወቅ ይገባናል፡፡
         
🔔ለምሳሌ

❖ ነቢዩን ኤልሳዕን የሠደቡ ሕፃናት በእግዚያብሔር ስም እንደተረገሙና ጅቦች እንደበላቸው፡፡ 

❖ ስለዚህ እግዚአብሔር መሳደብን እንደሚጠላ ሁሉ እኛም ሰዎች ይጠሉናል ስለዚህ መሳደብ አያስፈለግም ፡፡

📌 ለመናገር ሰንዘጋጅ የሚያስፈልጉን ነገሮች

❖ በመርሐግብራት፣ በትምህርት ቤትና በክፍል ውስጥ እጃችንን በማውጣት እድል ሲሠጠን ብቻ መናገር አለብን የተጠየቅነውን ነገር መረዳታችንን እርግጠኛ መሆን አለብን፤ የምንናገረውን ማወቅ አለብን፡፡ 
❖ የቤተክርስቲያን ልጆች ንግግራቸው የተቆጠበ እና ያልተንዛዛ መሆን አለበት።


® ዲ/ን ዘአርሴማ
 
✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
                   ይቆየን 

           🙏 ሼር ማድረግ አይርሱ 🙏

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር

✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
                አሜን

ክፍል አንድ
  
   ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
      ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••
✥  

❓ክርስቲያን ምን ማለት ነው

❖ የክርስቶስ የሚመስል፣ ተከታይ ማለት ነው፡፡ 
📖ሮሜ 13፥14

ሥነ ምግባር ምን ማለት
 
❖ አንድ በክርስቶስ የሚያምን ሠው ሊኖረው የሚገባው ያማረ ጠባይ ማለት ነው፡፡

ሥነ ምግባር ለምን አስፈለገ
❖ ሃይማኖት ማመን መታመን ማለት ነው፤ ስለሆነም መታመናችን የሚገለጠው በምግባር በመሆኑ ከሠዎች ጋር በፍቅርና በሠላም ለመኖር ጥሩ ምግባር ስለሚያስፈልግ ነው፡

📌 ሥነ ምግባር የሚገለጽባቸው ክፍሎች

🔻አመጋገብ
♦️አነጋገር
♦️ጊዜን በአግባቡ መጠቀምና
♦️ሠዓት ማክበር
♦️መታዘዝ (ታዛዥነት)
♦️አለባበስ
♦️እናትና አባትን ማክበር
♦️መልካም ስነምግባር በትምህርት ቤት
♦️መልካም ስነምግባር በመኖሪያ አካባቢ
🔺አርአያ ማድረግ 

📌 አመጋገብ

❓ምግብ ምንድ ነው


❖ ሁላችንም ሠው ስለሆንን ምግብ ያስፈልገናል፤ ስለሆነም ሠው ቆሞ እንዲኖር ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ምግብ ነው፡፡

❖ ምግብ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች እንደሚያስፈልግ አውቆ ከፍጥረት (የሠውን ልጅ) ከመፍጠሩ በፊት ያዘጋጀው ነው፡፡

❖ ከዚህ የምንረዳው ለኛ ምግብ ያዘጋጀውን አምላክ ከኛ ለልጆቹ የሚፈልገው እርሱን ማመስገን እንዳለብን ነው፡፡

❓ምግብ ስንመገብ ምን ማድረግ አለብን



❖ ይህን ምግብ ስላዘጋጀህልን እናመሰግንሃለን ስምህን አባታችን ሆይ ብለን እንጠራሃለን።
🙏አባታችን ሆይ፤ ይህ ጸሎት ከበላን በኋላም መደገም አለበት፡፡

🔔ለምሳሌ

📌ስብሐት ለአብ  
📌ስብሐት ለወልድ
📌ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ       

ከምግብ በኋላ የሚጸለየው ጸሎት የዘውትር ጸሎት ገና ካልተማሩ አባታችን ሆይ እንዲሆን ያድርግ በምንበላበት ጊዜ ደግሞ በጸሎት የጀመርነው ምግብ እንደ መሆኑ በእርጋታ ቀስ ብለን መብላት ይጠበቅብናል።

ይህን ስንል እየተሻሙ መመገብ የማይፈቀድና እግዚአብሔር የማይወደው ነው ከዚህ በተጨማሪም ሊያንቀንም ስለሚችል በእርጋታ መመገብ አስፈላጊ ነው፤ በምንመገብበት ሰዓት እንግዳ ቢመጣብን አብሮን እንዲመገብ መጋበዝ መልካም ስነምግባር ነው።

❖ ምግብን ከሌሎች ወንድሞች ጋር በጋራ መብላት የክርስቲያን ስነምግባር ነው፤ እኛ የምንመገበው ኖሮን ሌሎች ግን ምንም ባይኖራቸው ወይም ቢያንሳቸው ለእነርሱ ማካፈል አስፈላጊ ነው፤ ከመጠን በላይ መመገብ የጥሩ ክርስቲያን ባህሪ አይደለም።

ለመመገብ በምንዘጋጅበት ጊዜ በቦታው #ካህን ወይም #ዲያቆን ካለ ማዕዱን እነሱ ቢባርኩልን መልካም ነው፤ እነሱ ከሌሉም በእድሜ ከእኛ የሚበልጥ ሰው ማዕዱን ቢባርኩልን ይመረጣል።

❖ አጣዳፊ ሁኔታ ካልመጣ በቀር ማዕድ ትቶ መነሳት ተገቢ አይደለም፤ የተመገቡትን ሳያነሱ ጥሎ መሄድም መጥፎ ስነምግባር ነው፤ ከማዕድ በፊትም ሆነ በኋላ የታላላቆችን እጅ ማስታጠብ የክርስቲያን ባህሪ ነው።



📌 በምግብ ሰዓት  

❖ አፍን ከፍቶ ማኘክ፣ ማንጠባጠብ፣ ማውራት፣ መሳሳቅ፣ ከሰው ፊት ሄዶ መቁረስ መልካም ያልሆኑ ምግባሮች ናቸው።


® ዲ/ን ዘአርሴማ

✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
        
           ወስብሐት ለእግዚአብሔር

                  ይቀጥላል 
           🙏 ሼር ማድረግ አይርሱ 🙏
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

📍📍 ሰበር📍📍

ከደቂቃዎች በፊት የተሰበሰበው አስተዳደራዊ ጉባኤ ከዚህ በታች ያሉት ውሳኔ አስቀምጧል።

ኤጲስ ቆጶሳት ነን ብለው በተገኙ ፳፮ መኖከሳት ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላለፈ
***

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት የአስተዳደር ጉባኤ ዛሬ ማለዳ ላይ በዋለው ስብስባ ትላንት ጥር 14 በወሊሶ ከተማ በተደረገው ህገ ወጥ ሲመት

እራሳቸውን ኤጴስ ቆጶሳት ብለው የገለጡ ከተለያዩ አድባራት እና ገዳማት የተውጣጡ ፳፮ መኖኮሳት ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላልፏል።

በእዚህ መሰረት

፩ኛ .ሁሉም መኖከሳት ከደምወዝ ታግደው እንዲቆዩ
**

፪ኛ. የሚያንቀሳቅሱት የገዳማት እና አድባራት ሂሳብ ካለ እንዲታገዱ
**

፫ኛ. ከእዚህ በፊት ወደሚያገለግሉት የአገልግሎት መዋቅር እንዳይመለሱ
**

፬ኛ.በየትኛው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት እንዳይገኙ ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍትሕ መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀጣይ በሚያደርገው ስብሰባ ይወስናል ተብሎ ይጠብቃል።

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ባልንና ሚስትን አንድ የሚያደርገው እግዚአብሔር ነው። አንድ የሚያደርገውም በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚከናወነው ሥርዓት ነው። ሥርዓቱም ሥርዓተ ተክሊሉ ብሎም ሥርዓተ ቁርባኑ ነው።

ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በመጋባት ግን ባልና ሚስት አንድ አይኾኑም። መኝታ ተጋርተው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።

ስለዚህም፦

☝አንደኛ፥ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን አንድ የኾኑበትን ምሥጢር በተግባር መካድ ነው።

☝ ኹለተኛ፥ የተባረከ ትዳር አይደለም፤ የበረከት ምንጭ የኾነው እግዚአብሔር የለበትምና።

☝ ሦስተኛ፥ በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን መቋቋም አይችልም። መቋቋም የሚችልበትን ጸጋ አልተቀበለምና።

☝ አራተኛ፥ ዝሙት ነው። ለምን ሲባል ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ የሚኾነው ቤተክርስቲያን ስትፈቅድ ብቻ ነውና።
------
ሼር ብታደርጉት መልእክቱ ለብዙ ሰው ይደርሳል!
------
© /channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

መልእክት ለሚጋቡት ሼር አድርጉት።

✅ሐሙስ በሥርዓተ ተክሊል በቅዱስ ቁርባን ጋብቻችሁን ከፈጸማችሁ በኋላ እሁድ እንደገና በቤሎ የምታገቡ ሰዎች እባካችሁ ሁሉም አይቅርብኝ አትሁኑ

✍ቤተ ክርስቲያን ✅በካባዋ ሸልማ ✅በካህናቶቿ ቅኔ ተቀኝታ ወረብ አሰምታ
✅በሰንበት ተማሪዎቿ መዝሙር አዘምራ በልዩ መንፈሳዊ ስርዓት ካጋባቻችሁ በኋላ እንደገና ዓለማዊ ነገር ፈልጋችሁ በቤሎ የምትመነቃቀሩ በባንድ የምትጨፍሩ በዘፈን የምትዳሩ አካላችሁን የምታራቁቱ ሙሽሮች አምላካችሁን ፍሩ

✍በዝማሬ አግብታችው በዘፈን አጨርሱት
✍በካባ በተክሊል አግብታችሁ በቤሎ አትፈጽሙት
✍በቅዱስ ቁርባን አግብታችሁ በስካር አትፈጽሙት
✍በወረብ አግብታችው በዳንኪራ አትደምድሙት
✍በሸብሸቦ ተድራችው በጭፈራ አትፈጽሙት
✍በቤተ ክርስቲያን ተጋብታችሁ በሆቴል አትጨርሱት
✍ቤተ ክርስቲያን ካከበረቻችው ክብር በላይ የትም አታገኙም
✍በጥቅሉ በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ አትጨርሱት
በዚህ ወቅት በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የምትጋቡ መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ተዘክሮ ሞት

ሦስቱ መነኰሳት
ሦስት መነኰሳት ወደ አንድ ታላቅ አባት ምክር ፈልገው ሔደው እንዲህ በማለት ጠየቁት። አንደኛው መነኵሴ “የሲዖል ቁልቁለት፣ ጽንዓተ ጽልመት” ሲባል እየሰማሁ ከዚያ አስጨናቂ መከራ እንዴት ለመዳን ይቻለኛል በማለት እጨነቃለሁና ምን ባደርግ ይሻለኛል በማለት ጠየቃቸው።
ሌላኛው መነኵሴ ደግሞ “ሐቍየ አስናን፡- ጥርስ ማፋጨት ያለበት አስፈሪ ቦታ አለ” ሲባል እሰማለሁና ከዚያ ለመዳን ምን ላድርግ አለው? ሦስተኛው እና የመጨረሻው መነኰሴ ደግሞ “እሳቱ የማይጠፋበት፣ ትሉ የማያንቀላፋበት ቦታ አለ” ሲባል እሰማለሁና ከዚያ ለመዳን ምን ባደርግ ይሻለኛል? ብሎ ጠየቀው። የተጠየቀው አባትም ዝም ብሎ ሲያዳምጣቸው ቆየና “ልጆቼ ቀናሁባችሁ፤ እኔ ይህን ያህል ዘመን ስኖር የእናንተን ያህል ተዘክሮ ሞት አስቤ አላውቅም” አላቸው።
@dnhayilemikael

ሦስቱ መነኰሳትም የታላቁን አባት መልስ ሰምተው “ይህ አባት እውነትም ፍጹም ነው። ለወጣኒነት እንኳ ያልደረስነውን እኛን እንዴት ቀናሁባችሁ ይለናል” ተባባሉ። ታላቁ አባትም “እኔ ኃጢአቴ ብዙ ስለሆነ እራሴ ላይ እየተንጫጫብኝ እናንተ የምታስቡትን ተዘክሮተ ሞት ለማሰብ አልደረስኩም። እናንተስ አንዳንድ ትሩፋት ይዛችኋል።እኔ ግን ምንም ትሩፋት የለኝም” አላቸው። ለጀማሪዎቹ መነኰሳት አንዳንድ ትሩፋት ይዛችኋል ያላቸው ሞትን ማሰብ፣ ኃጢአትን ማሰብ፣ ጥርስ ማፋጨት ያለበት ቦታ መኖሩን ማሰብ ትሩፋት በመሆኑ ነው። በማስከተል ሞትን ማሰብ፣ ኃጢአትን ማዘከር፣ ጥርስ ማፋጨት ያለበትን ቦታ ማሰብ ትሩፋት መሆኑን ተርጕሞላቸው እናንተስ አንዳንድ ትሩፋት ይዛችኋል። እኔማ ኃጢአቴ በዝቶ በአእምሮዬ ይንጫጫብኛል። እናንተ የምታስቡትን ለማሰብ አልደረስኩም አላቸው።

🥀ታላቁ መነኩሴ ለጠየቁት ወጣንያን መነኰሳት እንደዚያ ብሎ የመለሰላቸው ትሕትና ያለው አባት በመሆኑ ነው። ሰዎቹ ምን ብለው ተናገሩ ትሉኝ እንደሆነ “ትሕትናው ከመነገር በላይ ነው ሲሉ ሰምተን ነበር። አሁን ግን በጆሯችን የሰማነውን በዓይናችን አየነው” እያሉ ወደ ገዳማቸው ተመለሱ በማለት አስተማሩ። እግዚአብሔር የሚወደው በጠባብ መንገድ መሔድ ነው። ጠባብ መንገድ ማለት ድሃን መጽውት፣ ሀብታምን ጹም ማለት ነው በማለት ተረጕመው አብራሩልን። ሀብታም እንዴት አድርጎ ይጾማል፤ ድሃስ ከምን አምጥቶ ይመጸውታል? ይህ ችግር ነውና አባቶቻችን ጠባብ መንገድ ብለውታል።

“🥀ሐቁዬ ስን፡- ጥርስ ማፋጨት” ያለበትን የመከራ ቦታ መፍራት ከሲዖል ለመዳን ነው። እሳቱ የማይጠፋ፣ ትሉ የማያንቀላፋ ያለበትን የስቃይ ቦታ መፍራትም ከስቃይ ለማዳን ነውና አንዳንድ ትሩፋት ይዛችኋል ብሎ አመሰገናቸው።

ያአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን።
@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ጥር_1_ቅዱስ_እስጢፋኖስ_የተወለደበት_እና_የሰማዕትነት_አክሊል_የተቀበለበት_ዕለት_ነው

#እስጢፋኖስ፦የስሙ ትርጉም በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡

አባቱ ስምኦን፣ እናቱ ሃና ይባላሉ፡፡ የተወለደው - ጥር 1 ቀን በእስራኤል ሃገር ውስጥ በብፅዓት / በስለት/ ነው፡፡ ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለ ቦት ተወለደ ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡

በደሙ የመሠረታት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በጽርሐ-ጽዮን ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከተቀበለች በኋላ የትንሣኤውን ወንጌል ለትውልድ ማድረስ ጀመረች፡፡ ወንጌል እየተስፋፋ አማኞች እየበዙ መጡ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት የሚያግዟቸው ሰባት ጠቢባን ወጣቶችን መርጠው የዲቁና ሥልጣን ሰጡአቸው፡፡
ከተሾሙት ዲያቆናት መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ነው፡፡ ሐዋ. 6÷5. ቅዱስ እስጢፋኖስ ጥቅምት 17 ቀን የዲያቆናት አለቃ ሆኖ ሊቀ ዲያቆናት ተብሏል፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ ከግሪክ አገር የመጡ አይሁድ በተከራከሩት ጊዜ በመንፈስና በጥበብ መለሰላቸው፡፡ አይሁድም ዳኞች በተሰየሙበት ሸንጎ ፊት አቅርበው በሐሰት ከሰሱት፤ ሸንጎውም በድንጋይ እንዲወገር ፈረደበት፡፡ እስጢፋኖስ ግን በታላቅ ኃይልና በብዙ መረዳት ከአባቶቻቸው ታሪክ ተነሥቶ የዓለም መድኃኒት የሆነውን ክርስቶስን ሰበከላቸው፡፡ ጥላውን ከአካሉ ጋር እያጋጠመ ወደ ፍጹማን ጥበብ በጽድቅ ቃል መራቸው፡፡ አይሁድ በጣም ተቆጡ፤ ሁሉም በአንድነት ሆነው በድንጋይ ወገሩት፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰውነቱ ቆስሎና ዝሎ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ባነሣ ጊዜ የልዑልን ክብር ተመለከተ፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቱ ቀኝ ቆሞ አየ፡፡ ሐዋ. 7÷55፡፡

ቅዱስ አሰስጢፋኖስ “እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) በአባቱ ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አላቸው፡፡ አይሁድ ግን ልበ-ደንዳኖች (የማይራራ ጨካኝ ልብ ያላቸው) ስለሆኑ እስጢፋኖስን ከከተማ ወደ ውጭ አውጥተው ደበደቡት፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰውነቱ ደከመ፤ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በደረሰች ጊዜ በሞት ጣር ሆኖ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው፤ ነፍሴን ተቀበል” ብሎ ጸለየ፡፡ ነፍሱንም ለታመነው ፈጣሪ አደራ ሰጥቶ ጥር 1 ቀን በ34 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡

የሰማዕትነት ሕይወትን በመጀመሩ ስለ ክርስቶስ ፍቅር መራራ ሞትን በመታገሡ ቀዳሜ ሰማዕት ተብሏል፤ የቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ሰማዕት ነውና፡፡

ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን አሜን !!!



@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የክርስትና ሕይወት  ማስተዋል፣ እምነት እና ትእግስትን ይጠይቃል፡፡ ዝም ብሎ በሰዉ ከመነዳት መጠበቅ አለብን፡፡ የዓላማ ሰዉ መሆን ይኖርብናል ፡፡ የተፈጠርንበትን ዓላማ እና ክብርንም መርሳት የለብንም፡፡ የስም ሳይሆን የተግባር እና የሕይወት ክርሰቲያን ሆነን  ክርስትናንም በሕይወት ገልጠን  ለመንግሥቱ እና ለክብሩ እንዲያበቃን የእርሱ የአምላካችን መልካም ፍቃድ ይሁንልን፤ አሜን ፡፡


የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ(አጋሩ)

ዲን ዘአርሴማ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት እንጸልይ?

ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ማለት ነው። 🙏ጸሎት ልመናም ምስጋናም ነው


🛐ሰባቱ የጸሎት ጊዜያት

✅1 ጸሎተ ነግህ (የጠዋት ጸሎት )

✅2 ጸሎተ ሠለስት (3 ሰዓት ጸሎት )

✅3  ቀትር(6 ሰዓት)

✅4  ቀትር(6 ሰዓት)

✅5 ጸሎተ  ሰርክ (11 ሰዓት)

✅6 ጸሎተ  ንዋም (የመኝታ  ጊዜ  ጸሎት)

✅7 መንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት)

አንድ ክርስቶስ በነዚህ ሰአታት እንድጸልይ ቤተክርስቲያን ታዛለች ሌላ ሰፍ ጸሎት መጸለይ ባይችል ግን ጊዜውን አስታውሶ አቡነ ዘበሰማያት ሊጸልይ ይገባል

በተለያየ ምክንያት በቀን ሰባት ጊዜ መጸለይ ባይቻል ማንኛውም ሰው የግድ ጠዋት በማለዳና ማታ ከመተኛታችን በፊት ልንጸልይ ይገባል

የቱን ጸሎት እንጸልይ

ሁሉም ክርስቲያን ልጸልይ የሚገባና እንድንጸልይ አባቶች ያዘዙት የህግ ጸሎት እነዚህ ናቸው

1/ 🛐መዝሙረ ዳዊት

መዝሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት  ባህታውያን ጀምሮ  በካህናት፣ምእመናን በሁሉም ዘንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው።

✅አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዚህ ጊዜ ጀምረው እየደገሙት፣እየጸለዩበት ይኖራሉ ።
✅ዳዊት  ሳይደግሙ  ወደ  ዕለታዊ  ተግባራቸው አይሰማሩም።
✅መዝሙረ ዳዊት  እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው።
🛐ቀጥለን እንመልከት
✅ሰኞ ከመዝሙር 1  – 30፣
✅ማክሰኞ ከ 31 – 60፣
✅ረቡዕ ከ  61 – 80፣
✅ሐሙስ ከ 81 – 110፣
✅አርብ  ከ 111 – 130፣
✅ቅዳሜ  ከ 131 – 150
✅እሁድ- ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ይጸለያል፡፡
 
🛐አንድ ንጉሥ
መዝሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታዘዘውን ሃያ እና ሰላሳ መዝሙር ማድረስ ባንችል እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ  ይገባናል።
አንድ  ንጉሥ  የሚባለው፡-አስር መዝሙር  ነው፡፡ለምሳሌ ሰከኞ አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ 1 – 10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ 30 -40 ያውን የመጀመሪያውን አስር መዝሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡

🛐ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው
ግን የተወሰኑ መዝሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡


🛐2/ውዳሴ ማርያም

✅ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው።
✅የዘወትር ጸሎት ካደረስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን  ደግመን ከእመቤታችን  በረከት ተሳታፊ መሆን ተገቢ ነው፡፡
✅በየአብነት ትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎች እና በየገዳማት ያሉ መነኮሳት ሁሉ ውዳሴ ማርያምን በየዕለቱ ያደርሳሉ፡፡
✅እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡

እነዚህ ሁለቱ የህግ ጸሎት ናቸው እነዚህን ለየቀኑ የታዘዙትን በአግባቡ መጸለይ ሳይችል ሌላ ጸሎት የሚጸልይ ሰው በህግ የታዘዙትን የአዋጅ ጾም ሳይጾም የፈቃድ ጾም ልጾም የምል ሰው ይመስላል
ስለዚህ በእነዚህ ጸሎት በርትተን በአግባቡ መጸለይ ስንችል እንደየ አቅማችን ሌሎች ጸሎቶችን

ለምሳሌ

ወንጌል ዘዮሐንስ

የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው  ጸሎት ነው፡፡
 4.ሌሎች ጸሎታት
ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም ፣ በመዝገበ ጸሎት እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣እንዲሁም ገድላት፣ተአምራትን፣እንደ ችሎታችን በየዕለቱ እናደርሳለን፡፡

✅ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን  የመዝሙረ  ዳዊትና ፣ውዳሴ ማርያምን  ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር በጸሎት እንድንበረታ የእርሱ መልካም ፈቃዱ ይሁንልን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

አዘጋጅ ዲ/ን ዘአርሴማ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)

ዲያቆን ዘአማኑኤል አንተነህ

ታኅሣሥ ፲፰ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ሆይ ተመራምሮ ለማይደረስበት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል›› እንዲል፡፡ (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)

ቅዱስ ገብርኤል የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት እና ሰው መሆን ለመናገር ተልኮ የምሥራች ዜናን ያበሠረ፤ በዲያቢሎስ የተንኮል ወጥመድ ገብተው ለተሰናከሉት ፈጥኖ ለርዳታ የሚደርስ፣ በጨለማ እና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ የብርሃን ፋና ያበራ፣ ሰብአ ሰገልን የመራ መልአክ ነው፡፡ ከቀድሞ ጀምሮ ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገራቸው ዓለምን ስለማዳን ከጽዮን የሚወጣ ከያዕቆብ በደልን የሚያርቅ ጌታ ‹‹ይወርዳል ይወለዳል›› በማለት በየወገናቸው እና በየዘመናቸው የተናገሩትን የነቢያትን ትንቢት ያስፈጸመና የምሥራችን ቃል የተናገር፣ የጨለማ አበጋዝ በሆነ በሰይጣን ተንኮል ከእፉኝት መርዝ የከፋ በሰው ልቦና ውስጥ አድሮ የነበረውን የኀዘን ስሜት ያጠፋ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብሩ

ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሁል ጊዜም ለደስታና ለምሥራች የሚላክ መልአክ ነው፤ በተለይም ስለ ልደተ ክርስቶስ ለድንግል ማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋና እና  የክብር ሰላምታ ያበሠረ በመሆኑ ‹‹አብሳሬ ትስብእት (መልአከ ብሥራት) መጋቤ ሐዲስ›› ተብሎ ይጠራል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ መላእክት ከተፈጠሩ በኋላ አምላካቸውን ለማወቅ ‹‹መኑ ፈጠረነ›› እያሉ ሲባዝኑ ሳጥናኤል ‹‹እኔ ፈጠርኳችሁ›› ሲል ቅዱስ ገብርኤል ግን የፈጠረንን አምላክ እስክናውቅ ድረስ በያለንበት እንቁም እንጽና፤ ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ አምላክነ›› በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ (አክሲማሮስ. ገጽ.፴፭) በዚህም አባቶቻችን እንደሚሉት መልአኩን የመጀመሪያው የተዋሕዶ ሰባኪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከፍጥረታት አስቀድሞ አምላኩን ዐውቆ ስብከት የጀመረ መልአክ ነውና፡፡ በዚህም ምክንያት ጌታ ‹‹ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም፤ድንግል ማርያምን ያበስር ዘንድ የተገባው ሆነ›› እንዲል፤ ነገረ ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበሥር አድሎታል፤ ከዚህ በኋላም ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው ጸሎቶች ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ይኸውም በዘወትር ጸሎቶች በአቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ በውዳሴ ማርያም፣ በይዌድስዋ መላእክት እና በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ካህናት አባቶች እንደሚሉት ስእለት ሰሚ እንዲሁም ፈጥኖ ደራሽ መልአክ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መልአክ ነው፡፡ ስለዚህም ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይባላል፡፡ በሀገራችንም ክብረ በዓሉ በቁልቢ ገብርኤል እና በተለያዩ ቦታዎች እጅግ በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት ይከበራል፡፡

የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች መላእክት ሁሉ በይበልጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንደ ምትወደው በድርሳነ ገብርኤል ላይ ተጽፏል፤ ‹‹ርእዩኬ አኃዊነ ዘከመ ታፈቅሮ እግዝእትነ ማርያም ለቅዱስ ገብርኤል እምኲሎሙ መላእክት እስመ አብሠራ ልደተ ወልድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወውእቱ ከመ ያፈቅራ ወይረድኣ በጊዜ ምንዳቤሃ ለነኒ ይርድአነ በጊዜ ምንዳቤነ፣ ወንድሞቻችን ሆይ፥ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና›› እንዲል፡፡ (ድርሳነ ገብርኤል ዘኅዳር ምዕራፍ ፪፥ ቁጥር ፲፫)

ቅዱስ ገብርኤል ብርሃናዊ መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በራእዩ እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች፡፡›› (ራእ.፲፰፥፩)

ነቢዩ ዳዊት ‹‹መላእክቱን የእሳት ነበልባል የሚያደርግ›› እንዳለው ቅዱስ ገብርኤል ነበልባላዊ መልአክ ነው፡፡ (መዝ.፻፫፥፬)

ቅዱስ ገብርኤል ኃያል መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤ የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ፤ ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሳም አንበሳ በታላቅ ድምጽ ጮኸ›› በማለት መስክሯል፡፡ (ራእ.፲፥፩)

ቅዱስ ገብርኤል የመላእክት አለቃ ነው፤ በራማ በሠፈሩት ዐሥሩ የነገድ ሠራዊት ላይ የአርባብ አለቃ ነው፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ‹‹በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው››  ይላል፡፡ በዚህም ምክንያት የራማው መልአክ ተብሎ ይጠራል፡፡ (ሄኖክ.፲፥፲፬)

ቅዱስ ገብርኤል ፈጣን መልአክ ነው፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሉት በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥነ ስቅለት ጊዜ በመስቀል ላይ የደረሰበትን መከራ አይቶ አላስችለው ቢል ሰይፍ ወርውሯል፤ ‹‹ዓለምም የሚያልፈው ቅዱስ ገብርኤል የወረወረው ሰይፍ ሲያርፍ ነው›› ይላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መልኩም ሰይፍ እንደወረወረ ከዚህ በታች በተጻፈው መልኩ እንገነዘባለን ይኸውም፡-

ሰላም ለሰኰናከ ወለመከየድከ ክልኤ

ታሕተ ዐውደ መስቀል ዘቆማ በዕለተ ድልቅልቅ መውዋዔ

ሰይፈ ቁጥዓ ገብርኤል ዘመላኅከ ቅድመ ጉባኤ

አንስትሰ ሶበ ሰምዓ ቃለ ዚኣከ በቋዔ

ኀበ ሐዋርያት ሖራ ይንግራ ትንሣኤ

ትርጉም፡- ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ›› እንዲል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል ከዓለም በፊት አምላኩን ያወቀ ዓለም ልታልፍ ስትልም የወረወረው ሰይፍ እንደሚያርፍ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡

በሀገራችን በተለምዶም ‹‹ሚካኤል እንደአየህ ገብርኤል እንዳያይህ›› የሚባል አባባል አለ፤ ይኸውም የመልአኩ ተራዳኢነት እንዳለ ሁኖ ተነግሮ ለማይሰማ አካል ግን መልአኩ ፈጣን እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም የቅዱስ ገብርኤልን ቁጣ የምንሰማ እና የምናይ ሲሆን ለምሳሌም ካህኑ ዘካርያስ የመልአኩን ቃል ባለመስማቱ (ባለመቀበሉ) ዲዳ ሁኗል፡፡በተጨማሪም በኢ-አማንያንም ዘንድ ሳይቀር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይፈራል፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፩)

ቅዱስ ገብርኤል እና ተራዳኢነቱ

ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታትን ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደኋላ እንዳይመለሱ ተጋድሏቸውን እንዲጨርሱ ይረበተጨማ (ዳን.፫፥፳፭) ክርስቶስ በስደት ሲሰደድም ሲመለስም እንዲናገር የተላከ መልአክ ነው፡፡ (ማቴ.፪፥፲፱፣ሉቃ.፪፥፰)

ቅዱስ ገብርኤል የእግዚአብሔር ባለሟል ነው፤ ‹‹

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋን በነቀፉና የጥላቻ ንግግር ባስተላለፉ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ ክስ መሠረተች።

ታኅሣሥ 12 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክብሯን በነኩ ሥርዓተ አምልኮዋን ባንቋሸሹ እንዲሁም የሐሰተኛ ንግግር ባስተላለፉ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ታኅሣሥ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ክሷን አቅርባለች።

የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽኝ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት በጻፈው ደብዳቤ ፓስተር ዮናታን አክሊሉ ፣ የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን ፣ ነቢይ ኢዩ ጩፋ እና ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ጠይቋል።

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

📌 ልብህ ሞልቷል

➯ አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ክርስትናን ማወቅ እፈልጋለው ስለ ክርስትና ንገሩኝ አላቸው ና ልጄ ውስጥ ሻይ እየጠጣን እናውራ ብለው ወደ ባዕታቸው ይዘውት ገቡ፤ ከዛ ማንቆርቆሪያቸውን ጥደው ሻዩ እስኪፈላ መጠበቅ ጀመሩ ።

➯ ልጁም በሚገርም የወሬ ፍጥነት አባ ክርስትና እንዲ ነው አይደል፤ አባ ክርስትና እንደዛ ነው አይደል ? ሰዎች እኮ ነግረውኛል እያለ ከሰዎች የሰማውን ይቀባጥራል።

➯ መነኩሴውም ዝም ብለው ሲሰሙት ቆዩና ሻዩ ሲፈላ ብርጭቆ አምጥተው ይቀዱለት ጀመረ፤ ብርጭቆው ሞልቶ እየፈሰሰም ዝም ብለው ይቀዳሉ፤ ከዛ ልጁም አንተ መነኩሴ ያምሀል እንዴ ? ብርጭቆውኮ ሞልቷል ።

➯ አንተ ለምትጨምርበት ሻይ ቦታ የለውም አላቸው፤ መነኩሴውም አየህ ልጄ አንተም እንደዚ ብርጭቆ ነህ፣ ስለ ክርስትና ማወቅ ትፈልጋለህ ነገር ግን ልብህ ሌሎች በነገሩህ አሉባልታ ተሞልቷል እኔ የምነግርህን ነገር የምትቀበልበት ቦታ በልብህ ውስጥ የለም፤ ብነግርህም ታፈሰዋለህ፤ ስለዚህ አሁን ሂድ ልብህ ባዶ ሲሆን ተመልሰህ ና ያኔ እነግርሃለው አሉት።

➯ እኛስ ዛሬ ልባችንን የሞላው ምንድነው❓
➯ ፍቅር❓
➯ ሰላም ❓
➯ መቻቻል  ታማኝነት ፣ ህብረት አንድነት ነው ❓ ወይስ አስቀድሞ ልባችን በተንኮል ፣ በሟርት ፣ በቅናት፣ በሴሰኝነት፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት ስለተሞላ ለመልካም ነገሮች ቦታ የለውም❓

➯ ዛሬ ሰይጣናዊ በሆነ ነገር ልባችንን ስለሞላነው መንፈሳዊ ለሆነ እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ነገር ቦታ የለንም እስቲ ራሳችንን እንፈትሽ ልባችንን ሞልቶት እየፈሰሰ ያለው ምንድነው ❓

📌 ምንጭ
✍️ ሰናይ ሚዲያ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11

           ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

        ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
ስለ ታሰሩ ሰዎች
        ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

➯ አንዳንድ ነገሮች አሉ፤ እንዴት እንደምንጀምር እንጂ እንዴት እንደምናቆም ጨርሶ የማናውቃቸው አጀማመሩን ስላወቅን እና ስለቀለለን ብቻ አቋቋሙም የዚያኑ ያህል ቀላል የሚመስለን እውነታውስ? በነጻ ፈቃዳችን መርጠን እንጀምራለን፤ ነገር ግን ያ የተሳሳተውን ነገር መምረጥ በመቀጠላችን የመረጥነው እርሱን ያለመምረጥ ነጻነታችንን እስኪነጥቀንና ጌታ እስኪሆንብን እንደርሳለን።

➯ በሱስ የተያዘ ሰው ከዚያ ነጻ ለመሆን ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ ደስ ይለዋል ግን ሱሱ ልማድ ሆኖበት አንቆ ይይዘዋል፤ በዚህ ከቀጠለ መጨረሻው ሞት እንደ ሆነ ቢያውቀውም፣ ራሱ በፈጠረው ነገር እንዲህ በመሰቃየቱ ምክንያት መልሶ ራሱን ቢጠላውም በእጁ የያዘውን የመጠጥ ብርጭቆ ግን ወርውሮ መስበር አይችልም፤ መላ ሰውነቱን ስለተቆጣጠረው እርሱ የጨበጠው ጠርሙስ እስረኛ ነው።

➯ ይህን ግን ስለ መጠጥ ብቻ የምንናገር አይደለም፤ በጥቂቱ ብንጀምራቸውም በኋላ ግን አርቀን መጣል ያልቻልናቸው እና ሱስ ስለሆኑብንን ኃጢአቶች ሁሉ ይመለከታል። 

➯ እንዲህ በራሳችን ወህኒ ለታሰርን ምስኪኖች ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ በቅዳሴዋ "እግዚአብሔር ከእስራታቸው ይፈታቸው ዘንድ ስለ ታሰሩ ሰዎች እንማልዳለን" ስትል ትማልዳለች፤ እኛም ከመዝሙረኛ ጋር
✍️ "አቤቱ ስምህን አመሰግን ዘንድ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት" እያልን ልንማጸነው ይገባል።
📖መዝ 142፥7

➯ እኛ በራሳችን ላይ ያደረግነው የትኛውም ዓይነት እስራት የሲኦልን ደጆች ከሰባበረው የብረቱንም መወርወሪያ ከቆረጠው ከክርስቶስ ኃይል አይበልጥም፤ ስለዚህ ከፈቀድንለትና አብረነው ሠራተኛ ለመሆን ከወሰንን ዛሬም ከገባንበት ሲኦል ሊያወጣን የታመነ አምላክ ነው።

➯ ሰው በራሱ ፍላጎት ብቻ ወደ ኃጢአት ጉድጓድ መግባት ቢችልም ያለ እግዚአብሔር ረድኤት ግን ከገባበት መውጣት አይችልም፤ ስለዚህ "እንዴት ከገባኹበት ጉድጓድ በራሴ መውጣት አልቻልኩም?!" እያልህ አትበሳጭ፤ ይልቅ ረድኤተ እግዚአብሔርን እየለመንህ በምትችለው ሁሉ ታገል።

✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

📌 ምንጭ
ዲያቆን አቤል ካሳሁን

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
 🧲  /channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

📌 የተስፋ ቃላት

❖ እኛ ዛሬ ወደፊት የምንኖርባት የእግዚአብሔር ሀገር በተስፋ ዓይኖቻችን ልንመለከት እንጂ ሁካታና ግርግር የበዛበት ዓለም ልንመለከት አይገባም።

❖ ለእኛ በጣም አስቸጋሪ መስሎ የሚታየን ችግር በእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ አሉት፤ ማንኛውም የተዘጋ በር ለመክፈት በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ቁልፍ አንድ ብቻ ሳይሆን ብዙ ቁልፎች ናቸው፤ በእንደዚህ ዓይነት መንገድ የተከፈተውን ማንም ሊዘጋው አይችልም ፡፡
📖ራዕ 3፥7

❖ ተስፋ ፍርሀትን ጭንቀትን ግራ መጋባትን በመከላከል ዕረፍትን ይሰጣል፤ ተስፋ ዕረፍትን ከመጠቱ በላይ በተስፋ ደስ እንዲለን ተነግሮናል። 📖ሮሜ 12፥2

❖ መጥፎውን ወደ በጎ መቀየር የሚቻለውን የእግዚአብሔር አሠራር ሳትይዝ ወደ ችግሮችህ ብቻ አትመልከት።

❖ እግዚአብሔር ሁሉም አጋጣሚዎች እርሱ በወደድው መንገድ ማስኬድ ይቻለዋል።

❖ በሰዎች ድካም ሊደረግ የማይቻለው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል፤ የሰዎች ጥበብ ሊወጣው ያልቻለውንም የእግዚአብሔር ጥበብ ያመጣዋል።

❖ ምንጊዜም በመለኮታዊ ዕርዳታ የተከበብክ ስለሆንህ ብቻህን ላለመሆንህ እርግጠኛ ሁን፤ የሰማያት ወዳጆቻችንና ቅዱሳን ሁሉ በአንተ ዙርያ ሁነው ስለ አንተ እንደሚማልዱም እወቅ።

📌ምንጭ
✍️አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#የአለባበስ #ሥርዓት


በነገራችን ላይ ለምን እንደምትለብሱ አስባችሁት ታውቃላችሁ? ብዙ ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ራስን ከፀሐይ፣ ከውርጭ እና ከመሳሰሉት ራስን ለመከላከል ነው።

ነገር ግን የአለባበስ ሥርዓት ላይ የምናጠብቅበት ዋናው ፍሬ ምክንያት ከዝሙት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው። በአለባበስ ዙሪያ ቅዱስ መጽሐፍ በተለያዩ ቦታዎች ተናግሯል። የካህናት አለባበስ፣ የሴቶች አለባበስ ተገልጿል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች ግን ራሳቸውን ይከናነቡ ለምን አለ? ሙሴስ ሴት የወንድን ወንድ የሴትን ልብስ አይልበስ ለምን አለ።

የወንድ ልብስ ምንድን ነው? የሴት ልብስስ ምንድን ነው? የሚለውን እንመልከት።
                           ።

በማየት የሚመጣ ፍትወት ከሴት ይልቅ በወንድ ይጸናል። በመስማት የሚመጣ ፍትወት ደግሞ ከወንድ ይልቅ በሴት ይጸናል። ወንድ ልጅ የሴትን ገላ ካየ ፍትወት ይነሳበታል። ፍትወት ከተነሳበት ደግሞ "ወደ ሴት አይቶ የተመኘ አመነዘረ" የሚለውን የፈጣሪ ሕግ ይሽራል። ሕግ ከሻረ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት አይገባም።

በነገራችን ላይ ይህን ሰው መንግሥተ ሰማያት እንዳይገባ መሠናክል የሆነችው ሴትም መሰናክል ስለሆነች መንግሥተ ሰማያት አትገባም። ከታናናሾቹ ያሰናከለ ወዮለት ብሎ ጌታ የተናገረው ለዚያ ነው። ስለዚህ ብፁዕ ጳውሎስ ሴቶች ራሳቸውን ይከናነቡ አለ።

ከዚህ ላይ ሴቶች የወንዶችን ልብስ አይልበሱ ሲል ሴቶች ሊለብሱት የሚገባ ልብስ ተብሎ የተዘረዘረ ነገር የለም። ነገር ግን ከሐዋርያው ጳውሎስ ንግግር እንደተረዳነው ተገልብቦ "መከናነብ" ራስን ላለማሳየት ነው። ስለዚህ ሴቶች በየትኛውም መስፈርት አካላቸውን የሚያንጸባርቅ ልብስ መልበስ የለባቸውም። ሰፋ ያለ ከአካላቸው ያልተጠበቀ ልብስ ሊለብሱ ይገባል። ወንድ ልጅም እንዲሁ ሴቶችን ለፍትወት የማይጋብዝ ልብስ ሊለብስ ይገባል። ልብስ የምንለብሰው እንዲያምርብን እና ሌሎችን በፍትወት ለመሳብ ብለን ከሆነ ልብሱ ምንም ይሁን ምን ሥርዓት አልባ አለባበስ ይባላል። በዋናነት ልብሱን የለበስንበትን ምክንያት እንመርምረው።
                            ።
ሌላው የወንድ ልብስ እና የሴት ልብስ የሚለውን በትውፊት እናውቀዋለን። እንደ ኢትዮጵያ ባህል ሴት ልጅ ዘረፍረፍ ያለ ሰፋ ያለ ቀሚስ ነው የምትለብስ "ቀሚስ በመልበሷም የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን ቃል ትፈጽማለች"።

በነገራችን ላይ ጥብቅ ያለ ቀሚስም ያው ሥርዓት አልባ አለባበስ ነው። ምክንያቱም የአካልን ቅርጽ ያሳያልና። ሌላው የካህናት አለባበስ በኦሪት ዘሌዋውያን በሰፊው ተገልጿል። ካህናት ጠምጥመው ልዩ ልብስ የሚለብሱት ስለ ክብረ ወንጌል ነው። እንጂ ካህናትም ይህንን አለባበሳቸውን ለተርእዮ ካዋሉት እንዲለብሱ አይፈቀድም።

ቅዱስ መጽሐፍ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ይላልና። በእኛ አለባበስ ምክንያት በሌላው ፈተና ከሆንን ሌላውንም ራሳችንንም ወደ ገሐነም የምንልክ ስለምንሆን ወዮልን።

ኢትዮጵያዊ መጽሐፋዊ ትውፊታዊ አለባበስ ይኑረን። የባዕድ ሀገር አለባበስ ተገዥ አንሁን። የእኛ ባህል አብዛኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ።ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከጉልበቱ በላይ ጸምር ወይም አጎዛ ብቻ ይለብስ ነበር።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በዚህ ምድር ስትኖር ሁለት ቀሚስ ልብስ ብቻ ነው የነበራት። ዮሐንስ ወንጌላዊውን ስታርፍ በአንዱ ቀሚሴ ገንዘኝ።አንዱን ቀሚሴን ደግሞ ለአንዲት ድሃ ሥጥልኝ ብለዋለች። ልብስ ለከዲነ ዕርቃን ነው። ታላላቁ ቅዱሳንም መንገድ ላይ የሆነ ልብስ ይጥሉና ሰው ንቆ ከተወው አንስተው ይለብሱታል። አንስቶ ይዞት ከሄደ ግን ለሰው ይማርካል ማለት ነው ስለዚህ ፈጣሪየ ከመልበስ አዳነኝ ብለው ይደሰቱ ነበር። ሥለዚህ ዕርቃናችንን የሚሸፍን ጥብቅ ያላለ ሰፋ ያለ ልብስ እንልበስ።ይህ ነው ኢትዮጵያዊው አለባበስ።



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት   

✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
        አሜን

ክፍል አንድ
በቃል ያለ ይረሳል፤ በጽሁፍ ያለ ይወረሳል
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
     ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት   
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥  
✍መግቢያ

📌 የጾታ አጠቃላይ ትርጉም


❖ ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት ሲባል፣ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስለ ጾታ የሚሰጠውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት፣ ስለ ጾታ ያላትን አመለካከት፣ ቀኖናዊ ሥርዓትና ባህላዊ ትውፊት የሚያመለክት ትምህርት ማለት ነው ። 

❖ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ጾታ የሚለው ቃል በአርአያ እግዚአብሔር ከተፈጠረው የሰው ዘር ጀምሮ፣ በመውለድ መዋለድ፣ የመብዛትንና የመባዛትን ተፈጥሮአዊ ጸጋ ከእግዚአብሔር አምላክ ያገኘ ፍጡር ሁሉ "ተባዕታይ አንስታይ " ወይም "ወንዴና ሴቴ " እየተባለ የሚጠራበት በተፈጥሮ አካል የሚለይበት ስያሜ ነው። 

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ስለ ጾታ ምን ታስተምራለች

❖ የጾታ ነገር ሲነሳ የነፃነትና የእኩልነት ጥያቄ ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ የሚታይ የዘመኑ ዐብይ ጉዳይ ነው፤ ይሁንና ሃይማኖትን ከልማድ መለየት የተሳነው፣ የአዲሱ ዓለም አይዲዮሎጂ አራማጅ ትውልድ፣ ለጾታ ልዩነት፣ በተለይም ለሴት የመብት፣ የነፃነትና የእኩልነት መጓደል ተጠያቂ ሃይማኖት እንደሆነ ይናገራሉ።

❖ ሃይማኖት ሴትን ከሰብአዊነት በታች አድርጎ ይመለከታል፣ የሴትን ሰብአዊ ክብር ይቀንሳል እያለ ዘመናዊ ሳይንስ መስበክ ከጀመረ ሰነባብቷል፤ እውነቱና የእነሱ ፈሊጥ ፈፅሞ የተለያየ ነው።

📌 እነዚ ወገኖች ለምን በሃይማኖት ላይ መዝመትን መረጡ ቢባል



1ኛ ሰው በእንስሳዊ ባሕርዩ ልጓም በሌለበት የፍትወት ሜዳ ሽምጥ መጋለብን ይፈልጋል፤ ሃይማኖት ግን ልቅነትን ስለማይፈቅድ ሰው እንስሳዊ ባህሪውን አስወግዶ ለመንፈሳዊ ስርዓት እንዲገዛ ስለሚያስተምር ሃይማኖት አልባ ሰው በመፍጠር ዓለምን በልቅነት ለመፈንጨት እንዲመቻቸው ሲሉ 

2ኛ ሃይማኖት በተለይም ለሴት ልጅ መብትና ነፃነትና እኩልነት አያስተምርም፣ የእኩልነት ጠበቃችሁ እኔ ነኝ ብሎ ሴቶችን ሃይማኖትን እንዲጠሉ ለማድረግ

3ኛ ይህን መሰል ፈሊጥ የሚከተሉ ግለሰቦች ከሚኖራቸው አናሳ የሃይማኖት እውቀት ሌላ የመጻሕፍትን ጥሬ ቃል እንዳሻቸው በመተርጎም የተዛባ አመለካከታቸውን በቀላሉ በሚማረክ አይምሮ ላይ ያሰርፃሉ፤ ይህ ግን ስህተት ነው
✍" ... ወንድ የለም ሴት የለም ሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ናችሁ እንጂ " ብሎ የጾታ እኩልነትን ያስተምራል።


✍"ሴት በፀጥታ ትማር ፣ በፍፁም ቅንነትም ትታዘዝ፣ ሴት እንድታስተምር አንፈቅድም በወንድ ላይም አትሰልጥን በፀጥታ ትኑር እንጂ " ብሏልና ሴትን መጨቆን ነው ሲሉ ይሰማሉ።
📖1ኛ ጢሞ 2፥11

📌 በመሰረቱ ሴት በአደባባይ ወጥታ እንዳታስተምር የመባሉ ነገር

1ኛ አዳም እንዳይበላ የተከለከለውን ፍሬ በለስ እንዲበላ በማድረግ ሔዋን ምክንያተ ስህተት በመሆንዋ፣ አሁንም ምክንያተ ስህተት እንዳትሆን፣ የሴት የሥራ ድርሻ /በመንፈሳዊ ዘርፍ / ተለይቶ ተቀምጧል።
2ኛ ከሴት በፊት የተፈጠረው ወንድ በመሆኑ ባል በሚስቱ እንዲከበር የሆነው በአፈጣጠር ቀዳሚነት ስላለው ነው። 

📌 ሴቶች በቅድስና ሕይወት

❖ ቅድስና ከማንኛውም ክብር የላቀ። የቤተክርስቲያናችን የክብር ሁሉ ጉልላትና ራስ ነው።

❖ በቤተክርስቲያናችን እምነትና ሥርዓት ቅድስና ለወንድ ብቻ እንጂ ለሴት አይገባም አልተባለም፤ ቅዱሳን ወንዶች የመኖራቸውን ያህል ቅዱሳን አንስት /ሴቶች አሉ፤ ይልቁንም የቅድስተ ቅዱሳንን ድንግል ማርያምን ክብርና ቅድስና ስንመለከትማ " በወንድ ምን ቅድስና አለና ነው " ወደሚል አቅጣጫ ያመጣናል።
❖ የድንግልን ያህል ባይሆንም ሌሎችም ቅዱሳን ሴቶችን ገድል ፅፋ ቤተክርስቲያን አንጻ ታከብራለች፤ በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግስት ምትባለው ቤተክርስቲያን የጾታን እኩልነት ምትሰብክና ምትቀበል መሆኗን አውቀው የተሳሳተ አስተሳሰብ የያዙ ሰዎች አመለካከታቸውን ያስተካክሉ ዘንድ መልእክታችን ይድረሳቸው ።

® ዲ/ን ዘአርሴማ

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
        
           ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                  ይቆየን 


                  ይቀጥላል 

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን





✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
        አሜን

ክፍል አንድ
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
       ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥  

❓ሥርዓት ማለት


❖ ሠርዐ ሠራ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደምብ አሠራር መርሀ ግብር ማለት ነው።

❓ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ማለት

❖ የቤተክርስቲያን ዕቅድ፣ የቤተክርስቲያን አሠራር መርሃ ግብር ወይም ደምብ ማለትነው፡፡

❓ለምን ይጠቅማል
❖ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ምሥጢራትን ጥምቀት፣ ቁርባን…. እና አገልግሎቶች ፆም፣ ፀሎት፣ ስግደት…/ እንዴት እንደምንፈፀም ያሣየናል፣ ይጠቁማል፡፡

📌 የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ምንጮች ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ምንጮች አሉት። እነሱም 
📗መጻህፍተ ብሉያት
📙መጻህፍተ ሐዲሳት
📕የሐዋርያት ሲኖዶስ
📘ሥርዓተ ጽዮን
📔አብጥሊስ
📓ትዕዛዝ
📚ዲድስቅልያ
📚ፍትሕ መንፈሳዊ
📚የሶስቱ ጉባኤያት ውሳኔዎች ኒቂያ፣ ቁስጥንጥንያና ኤፌሶን ሌሎችም ከ አራተኛው ክፍለ ዘመን በኋላ የተነሱ ሊቃውንት

የቤተክርስቲያን አሠራር

❖ ሶስት አይነነት የቤተክርስቲያን አሠራር አለ፡፡ እነሱም

1📌 ሰቀላ (ሞላላ )

❖ እንደ ብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደስ (ምኩራብ) ቅርጽ ያለው ነው፤ ውስጡ በመጋረጃ ወይም በአእማድ እንጂ በግንብ የተከፈለ አይደለም።

❖ የዚህ ዓይነት ቤተክርስቲያን ቅርጽ የተወረሰው ከሰሎሞን ቤተመቅደስና ኋላም በዘመነ ክርስትና ታላቁ ቆስጠንጢኖስና እናቱ ዕሌኒ በኢየሩሳሌም በቤተልሔም ካሰሩዋቸው የተወሰደ ነው።

❖ የሰቀላ ቤተክርስቲያን በሩ የተወሰነ አይደለም ሶስትም አራትም ከዚያም በላይ ሊሆን ይችላል።
❖ የሰቀላ ቤተክርስቲያን ጉልላቱ እንደ ቤተክርስቲያኑ ትልቀት ከአንድ በላይ ሊሆን ይችላል

2📌 ቤተ ንጉስ (ክብ)

❖ ዙሪያው ክብ የሆነና በግድግዳ ከሶስት ይከፈላል።

2. ክፍል ቅድስት፤
3. ክፍል መቅደስ ይባላል።

❖ የዚህ አይነት ቤተክርስቲያን አንድ ጉልላት ብቻ ይኖረዋል።


3📌 ዋሻ

❖ በሩ አንድ ብቻ ነው ክፍሎቹ
🔘ቅኔ ማህሌት፣
🔘ቅድስት ፣
🔘መቅደስ) የሚለዩት በመጋረጃ ነው።

🔹የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ምሳሌ ይሆናሉ፤ ጉልላት የለውም።

ይቀጥላል .....


✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

        
           ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                   ይቆየን 

                  ይቀጥላል 
           🙏 ሼር ማድረግ አይርሱ 🙏
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…
Subscribe to a channel