#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
" ዳግመ ትንሣኤ"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተጋር ይሁን እንዴት አደራችው እህት ወንድሞች እንኳን አደረሳችው
ዛሬ ስለ ዳግም ትንሳኤ አንበላችሁ
እንኳን ለዳግመ ትንሳኤ አደረሳችሁ
ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
✅ሰሙነ ሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤን እንድናከብር ቀደም ሲል በዲዲስቅልያ ኋላም በፍትሐ ነገሥት ታዝዟል፡፡ “እስመ ሰሙነ ዐብይ ሰሙነ ሕማማት እንተ ትተልዋሄ ሰሙነ ትንሣኤ ወዘይትፈቀድ ከመ ናእምር እስመ ዘሐመ ናሁ ትንሣአ” ሲል ይገኛል፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፱፤
✅ የሰሙነ ትንሣኤ መጨረሻው ስምንተኛው ቀን ዳግም ትንሣኤ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣው አንድ ጊዜ ነው፡፡
🌹ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?🌹
✅ዳግም ትንሣኤ የተባለበት ምክንያት፡- በአከባበር፥ በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡
💠የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤ በሙሉ በዚህ ቀን ይደገማል፡፡
ከዚህም ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡
🛐እነዚህም “ፈጸምን አግብዓተ ግብር” ይባላሉ፡፡
💠“ፈጸምነ” የተባለበትም፤ ሰሙነ ትንሣኤ በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡
“💠አግብዓተ ግብር” የተባለበትም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ… እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ” ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ ዮሐንስ ፯፥፬
✅በተጨማሪም የሐዋርያው ቶማስ ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡
💠ዳግመኛ ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ሳሉ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ሳለ ደጁም ተዘግቶ ሳለ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በመካከላቸው ቁሞ እንዴት ሰነበታችሁ አስታረቅኋችሁ” አላቸው፡፡
💠ሁለት ሰዓት አሳልፎ ስለመጣ “እምድኅረ ሰሙነ” አለ እንጅ፥ በስምንተኛው ቀን ሲል ነው፡፡
💠በመጀመሪያው መገለጡ ያልተገኘው ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤውን አላመነም ነበርና፤ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ እጆቼንም እይ፤ እመን እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው፡፡
💠ቶማስም መለሰ “ጌታዬ አምላኬ ሆይ” አለ፡፡ መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤ መቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ ሆይ “አለ፡፡
💠ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ ሕያዊት ሁና፤ (በሕይወት ትኖራለች) በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ያስቀምጧታል፡፡ በዓመት በዓመት በእምቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ፥ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች፤ ዓመት አገልግሎ ያርፋል፤ እንዲሁ በዓመቱ የሚሾመውን ተራምዳ ትይዘዋለች፤ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡ ይህም የሚያስተምረን የጌታን ተአምራት፤ የሐዋርውን ሥልጣንና ብቃት ነው፡፡ ጌታም ቶማስ ሆይ! ብታየኝ አመንክን? ሳያዩኝ የሚያምንብኝ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡ ዮሐ ፳፩፥፳፬–፳፱
የዋናው ትንሣኤ ሳምንት እሑድ ዳግም ትንሣኤ
🛐በዚች ሰንበት ከላይ እንደተጠቆመው የትንሣኤው ዕለት ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ብሎም ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡
✅ በኋላ ከሔደበት
ሲመጣ የጌታችን መነሣትና እንደተገለጸላቸውም በደስታ ሲነግሩት በኋላ እናንተ አየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን ሰምቼአለሁ ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር?
✅አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ ብሎ አሳየው፡፡
✅እርሱም ምልክቱን በማየቱ፤ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ አመነ፡፡
💠እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ዳግም ትንሣኤ ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡፡ዮሐ. 20-24-30፡፡
💠በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ሁሉ ከቅዳሴው ውጭ ከሚፈጸመው ድኅረ ቁርባን በስተቀር ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ዕለት ሆኖ ይከናወናል፡፡
ለብርሀነ ትንሣኤው ያደረሰን አምላካችን፥ፍጻሜ ሕይወታችን በሃይማኖት የቀናን፤ በምግባር የጸናን ያድርገን! አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
++++++++++++++++++++
/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael
+++++++++++++++++++++
☞"ያኔ ማንም ምንም አይጠቅምህም መልካም ስራህ ብቻ" ::
☞"በምትሞትበት ጊዜ በመጀመሪያ ስምህ ይቀየራል ስምህም ሬሳ ትባላለች" እከሌ/እከሊት ሳይሆን ሬሳዉ አልወጣም ወይ ትባላለህ። የቅርብ ሰዉ እንኳን ቢሆን ከጎንህ ሊሆን ይፈራል"
☞ወደ መቃብር ስፍራ ወስደዉ አጣድፈዉ ከቀበሩህ በሗላ ብቻህን ጥለዉህ ለመሔድ ይቻኮላሉ።
☞ ላይጠቅምህ አብሬህ ካልሔድኩ እያለ የሚያለቅሱልህ እንኳን ቢኖር ቀብሮህ ተሎ ይሸሻል።ቀብረዉህ እደተመለሱ ንብረት ካለህ ለመከፋፈል ይጣደፋሉ ። ከሳምንት በሗላ ጭራሹኑ ከምድር ያልኖርክ እስኪመስል ድረስ በአብዛኞቹ ትረሳለህ ።
☞የቅርብ ወዳጆችህ እንኳን ቢሆኑ ሀዘኑ በልባቸዉ ጥቂት ወራት ያክል ቢቆይ ነዉ ።በቃ ምድር ላይ የነበረህ ቆይታ በዚህ መልኩ ይጠናቀቃል ።ፍራሽህ አፈር ትራስህ ደሞ ድንጋይ ይሆናል ይሔዉ ነዉ ።
☞"ያኔ ማንም ምንም አይጠቅምህም መልካም ስራህ ብቻ" ::
☞''በዚች ዓለም ላይ እድለኛ ሰዉ ማለት በህይወት እያለ ወደ ፈጣሪዉ የተመለሰ ሰዉ ነው።🙏"
ሊቀ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ❤
በእዉነት ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን ያቆይልን♦
/channel/dnhayilemikael
አርብ :-ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል።
በዚህ እለት ቤተ ክርሰቲያን በክርስቶስ ደም መመስረቷ ይነገራል።
✅ክርስቶስ ስለ እርሷ እራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አጽንቶ በትንሳኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል የቤተክርስቲያን እራሷ መሰረቷ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት እና በምልዐት ይሰበካል።
✅ቤተ ክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞቹን ነው ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና።
/channel/dnhayilemikael
በትንሳኤ ማግስት
✍ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመዉን
የዐቢይ ጾምን ጾመን ፣
✅በሰሙነ ሕማማት በጸሎቱ በስግደቱ አሳልፈን ፣
✅የክርስቶስን መከራዉን ሁሉ አስበን ፣ የስቅለቱን ቀን አርብን እንዲሁ የጌታን መከራዉን በማሰብ በመዉደቅ በመነሳት
አሳልፈን ፣
✅ ትንሣኤዉንም እንዲሁ በአክፍሎት በማስቀደስ የክርስቶስን ትንሣኤዉን ካከበርን እና ሰዉነታችን በጾም
በጸሎት አስገዝተን ከቆየን በኃላ ፦
✅በዓለ ሃምሳ ሲደርስ
🛐ብዙዋቻችን ከቤተክርስትያን እንርቃለን
🛐ጸሎቱን እናቋርጣለን
🛐በሰርክ ጉባኤዉም ይቀዛቀዛል
🛐ለብዙዋቻን በኃጢአት ጭምር
የምንወድቅበት ወቅት ይሆናል
🛐 በዚህ ወቅት ጾም
ባለመኖሩ
~ እንደፈለግን እንበላለን
~ እንዳሻን እንጠጣለን
ይኼ ሲሆን ደግሞ አብዝታ የጠገበች ሰዉነት
✅በጸሎት እና ራስን በማስገዛት ዉስጥ የማንኖር ከሆነ ልንወድቅ
እንችላለን ፡፡ ፦ "ማንም ሰው የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ " እንዳይወድቅ ፩ኛ ቆሮ ፲፥፲፪ ነቀርሳ ይጠንቀቅ።" ይላልና
✅ በብዙ በረከት እና ወደ እግዚአብሔር
በመቅረብ ያሳለፍነዉ የጾም ወቅት በዓለ ሃምሳ ሲመጣ
ራሳችንን ከቤተክርስቲያን አርቀን ወደ ቀደመ በደላችን
እንዳንሄድና እንዳንወድቅ በተቻለ መጠን 🛐በጸሎት
እና🛐 በመንፈሳዊ ብርታት እየጨመርን ልንሄድ ይገባል
✅ይሄንን እንድናደርግ ሁሌም በቤተእግዚአብሔር
እንድንገኝ እና እንድንበረታ እና እንድንጸና የቅዱስ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ የቅድስት ድንግል
ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን ፡፡
✞
/channel/dnhayilemikael
⚜️⚜️⚜️ ማክሰኞ ቶማስ ይባላል ⚜️⚜️⚜️
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን በዓላት ቀኖና መሰረት ከትንሣኤ በኋላ ያለችው ዕለተ ማክሰኞ "ቶማስ" በመባል ይጠራል።
⚜️ቶማስ ሐዋርያ ሲሆን፣ ቶማስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው።ከክስቶስ ትንሣኤ በኋላ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል። ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓንስ ናቸው» አለው (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች።
⚜️ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡ ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡
ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)። መለኮቱን የዳሰሰች እጁ በሕይወት ትኖራለች፤ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር በመንበር ላይ ትኖራለች።
⚜️የሐዋርያ ቶማስ መታሰቢያ በዳግመ ትንሣኤ ላይ የሚነሳ ቢሆንም አባቶች በዓል ላይ በዓል እንዳይደራረብ ብሎ ከትንሣኤ በኋላ ባለው በዕለተ ማግሰኞ ቶማስ ተብሎ እንዲጠራ ስርዓት ሰርቶልናሉ። የአባቶቻችን በረከት ይደርብን በእውነት። በዓሉንም በዓለ ደስታና በዓለ ፍስሐ ያድርግልን።
*@dnhayilemikael
+ የተቀደሰው የሩጫ ውድድር +
እንደ ኢትዮጵያ ያለ ሩጫ ብሔራዊ ኩራት በሆነበት ሀገር መቼም የሩጫ ነገር ብናወራ ሰሚ አናጣም:: ሮጦ ሀገር ማስጠራት : ሮጦ ብዙ ሀብት ማፍራትና ለሀገር መትረፍ የቻሉ ውድ አትሌቶቻችንን በፍቅር እናያቸዋለን:: "በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ" የሚለው ቅዱስ ቃል ለነፍስ ቢነገርም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን "ታገኙ ዘንድ ሩጡ" የሚለው መርሕ "ሮጬ ባለፈልኝ" በሚሉ ተስፈኞች ይተገበራል:: (1ቆሮ 9:24)
ዛሬ ግን በሁለት ሰዎች መካከል የተደረገ ቅዱስ ሩጫ ትዝ አለኝ:: በትንሣኤ ዕለት የተደረገ ቅዱስ እሽቅድምድም በዓይነ ሕሊናዬ መጣ::
ከዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል ሁለቱ የተሳተፉበት ዳኛም ተመልካችም የሌለበት የትንሣኤ ዕለት ሩጫ!!!
ሴቶች ወደ ጌታ መቃብር ደርሰው ሲመለሱ ጌታ በመቃብር እንደሌለ ለደቀ መዛሙርቱ ነገሩአቸው::
ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሔዱ::
"ሁለቱም አብረው ሮጡ፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና አስቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ" ዮሐ 20:4
በዚህ ቀን በተደረገው ቅዱስ ሩጫ የ58 ዓመቱ ጎልማሳ ጴጥሮስ ከ28 ዓመቱ ወጣት ዮሐንስ ጋር ወደ ጌታ መቃብር ሮጡ:: ሐሙስ ማታ ጌታውን የካደው ጴጥሮስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታውን ከተከተለው ዮሐንስ ጋር አብሮ ወደ መቃብሩ ሮጠ::
ጴጥሮስ ሆይ ወደ ጌታህ መቃብር በሩጫ ስትገሰግስ ምን እያሰብህ ይሆን? ሐሙስ በካድከው ጊዜ ቀና ብለው ያዩህ ዓይኖቹ በሕሊናህ መጥተው ይሆን?
ወደ መቃብሩ ስትሮጥ "ጌታ ሆይ በአፌ ክጄሃለሁ በእግሮቼ ግን አልክድህም" ብለህ አስበህ ይሆን? "በባሕር ላይ ያራመድኸው እግሬ : አጎንብሰህ ያጠብከው እግሬ ወደ አንተ ለመሮጥ አይደክመውም" ብለህ ይሆን? መቃብሩ ሥር ተደፍተህ ለማልቀስ የሐሙሱን ዕንባህን በመግነዙ ለማበስ አስበህ ይሆን?
ብቻ ጴጥሮስ ከዮሐንስ ጋር ወደ መቃብሩ ሮጠ:: ዮሐንስ በጉልበቱ ገና ወጣት ቢሆንም : እንደ ጴጥሮስ ጸጸት የማይቆጠቁጠው ድል አድራጊ ቢሆንም ጴጥሮስ አብሮ ከመሮጥ አልተመለሰም::
ብቻ መቃብሩ ልድረስ እንጂ ቢቀድመኝም እከተላለሁ:: እንደርሱ እስከ መስቀል ባልጸናም ለመቃብሩ ግን ዳግም እታገላለሁ ብሎ ጴጥሮስ ሮጠ::
በዚህ ቅዱስ ሩጫ አርብ የወንድ ለቅሶን ያፈሰሰው ዮሐንስ በዕንባ በደከሙ ዓይኖቹ በኀዘን በጠቆረ ፊቱ እያማተረ ወደ ጌታ መቃብር ገሠገሠ:: እንዴት እንደ ገረፉት አይቶአል:: እንዴት እንደ ቸነከሩት ተመልክቶአል:: አሁን ደግሞ መስቀል ሥር ቆመው በዋሉ እግሮቹ ወደ መቃብሩ እየሮጠ ነው::
ወንድሜ ሆይ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ጌታ መቃብር ሲሮጡ እያቸው:: አንተና ጉዋደኞችህስ ወዴት ትሮጣላችሁ? የእናንተ እሽቅድምድም ወደ ጌታ መቃብር ነው? የት ለመሔድ ትፎካከራላችሁ? የት እንገስግስ ትባባላላችሁ?
ወጣቱ ዮሐንስ ጎልማሳውን ጴጥሮስን ቀድሞ ከጌታ መቃብር ደረሰ:: የጌታን መግነዝም አየ:: ወደ ውስጥ ግን ሳይገባ ቆሞ ጴጥሮስን ጠበቀው:: ጴጥሮስ ዘግይቶ ቢደርስም ከዮሐንስ ቀድሞ ወደ መቃብሩ ገባ::
ከእኔ የበረታ መንፈሳዊ ጉልበት ያለህ ወንድሜ ሆይ ብትቀድመኝ እንኩዋን አትፍረድብኝ:: ጨክነህ ጥለኸኝ ወደ ጌታ ማረፊያ እንዳትገባ:: የዘገየሁት ኃጢአት እግሬን አስሮት ነውና ብርቱው ወንድሜ ሆይ እባክህን ጠብቀኝ:: ድክመቴን አይተህ አትናቀኝ መጎተቴን አይተህ አትፍረድብኝ:: ብቻህን ወደ ጌታ ደስታ እንዳትገባ:: አደራህን በንስሓ እስክበረታ ጠብቀኝ:: እንኩዋን አንተ አብረኸኝ ሩጫ የጀመርክ ወንድሜ ቀርቶ ከእኔ ቀድመው ሩጫቸውን የጨረሱት እንኩዋን ብቻቸውን ወደ ዘላለማዊ ደስታ እንዳይገቡ ጻድቃን በገነት ሆነው እኔን ይጠብቃሉ:: ነቢዩ እንደተናገረ :-
አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ፤
ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤
ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ፡
ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ። (መዝ 142:7)
@dnhayilemikael
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!
======⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️======
- «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋነው፡፡
- መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለውግሥ ይሆናል፡፡
- «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትንያመለክታል፡፡
- «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንበየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስትክፍል አለው፡፡
1) አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ይህም ማለት ተዘክሮተእግዚአብሔር ነው፡፡
2) ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርንመስማትና በንስሐ እየታደሱበሕይወት መኖር ነው፡፡
3) ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜውየሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡
4) አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስበገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድልአድርጎ መነሣት ነው፡፡
5) ዐምስተኛውና የመጨረሻው«የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይአምላክ የጌታችን የመድኀኒታችንኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ»መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ»ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርናለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔበአንድነት የሚነሣው የዘለዓለምትንሣኤ ይሆናል፡፡
ወደ ተነሣንበት ዐላማ ስንመለስ የትንሣኤበዓል በቃሉም ምስጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ«ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡
«ፋሲካ» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ«ፌሳሕ» በጽርእ በግሪክኛው «ስኻ»ይባላል፡፡ ይህም ወደ እኛው ግእዝና ዐማርኛ ቋንቋችን ሲመለስ ፍሥሕ ዕድወት =ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣እየተቸኮለ የሚበላ መሥዋዕት፣ መሻገር መሸጋገር ማለት ነው፡፡ ነጮቹ በእንግሊዝኛው «ስኦቨር» ይሉታል የዚህም ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነትየተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹምደሰታ፣ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል«ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡
ፋሲካ፣ በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ
እስራኤል ዘነፍስ የሆኑት ምእመናን ክርስቶስ ትንሣኤውን የሚያከብሩበት ዕለት ሆኖ በእርሱ ትንሣኤ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፣ከኃሳር ፤ ከውርደት ወደክብር፣
ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደዘለዓለማዊ ነፃነት፣ከአደፈ፣ ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወትወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገሩበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡
- ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት ያከብሩታል፡፡ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡
- መድኀኒታችን ሞትን በሞቱ ድል መትቶ፣ሙስና መቃብርን አጥፍቶ በሥልጣኑ የተነሣው መጋቢት 29 ቀን በ34 ዓ.ምእንደሆነ ታሪከ ቤተ ከርስቲያን ያስረዳል፡፡
- የትንሣኤ በዓል መከበር የጀመረው በቅዱሳን ሐዋርያትና በሰብዐ አርድእት፣ኋላም በየጊዜው በተነሡት ተከታዮቹምእመናን ነው፡፡ ድምቀቱና የአከባበር ሥርዐቱ ይበዛ ይቀነስ እንደሆን እንጂ መከበሩ ተቋርጦ አያውቅም፡፡
«እንኳንለብርሃነትንሣኤውአደረሰን»
@dnhayilemikael
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ሕማማት ሰሞን ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ ቋንቋዎች ትርጉም
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
❖ በግብረ ሕማማት (በሕማማት ሰሞን) ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ
➊ የዕብራይስጥ(hebrew)
➋ የቅብጥ (ግብጽ) (coptic)
➌ የግሪክ (ጽርዕ) (greek) ቃላት ይገኛሉ፡፡
📌 የእነዚህ ቃላት ትርጉም በጥቂቱ እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡
#ኪርያላይሶን
❖ ቃሉ የግሪክ(ጽርዕ) ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነዉ፡፡
❖ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡
❖ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ፤ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፤ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡
❖ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፤ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡
#ናይናን
❖ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን "መሐረነ / ማረን" ማለት ነዉ፡፡
# አብኖዲ
❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "አብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ ፡፡
#ታኦስ
❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "ጌታ / አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "ታኦስ ናይናን" ሲልም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡
#ማስያስ
❖ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "መሲሕ" ማለት ነዉ።
❖ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡
#ትስቡጣ
❖ "ዴስፓታ" ከሚለዉ የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ደግ ገዢ" ማለት ነዉ፡፡
#ሙዳሱጣ
❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "ነበልባላዊ" ማለት ነዉ፡፡
#መዓግያ
❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "እሳታዊ" ማለት ነዉ፡፡
#አንቲፋሲልያሱ
❖ ቃሉ "በመንግስትከ / በመንግስትህ" ማለት ነዉ፡፡
#አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲፋሲልያሱ
❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚኦ በዉስጠ መንግስትከ / አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነዉ፡፡
#አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በዉስጠ መንግስትከ / ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡
#አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚአ ኲሉ መንግስትከ / የሁሉ የላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡
#ኤልማስ
❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "አምላኪየ / አምላኬ" ማለት ነዉ፡፡
#አህያ ሸራህያ
❖ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "ያለና የሚኖር" ማለት ነዉ፡፡
❖ እነዚህ ከላይ ያሉና ሌሎች ቃላት ከሌሎች ቋንቋዎች በቀጥታ የተወሰዱ ናቸዉ፡፡
መልካም የሰሙነ ሕማማት ወቅት ይሁንልን
ስብሐት ለከ፤
ሰጊድ ለአቡከ፤
ዕበይ ለመንፈስከ፤
ወምህረተ ፈኑ ለሕዝብከ፤
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡፡
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽዐነ በፍሥሐ ወበሰላም
ሙሉዉን ያነበበ ብቻ አሜን ይበል እንዲሁ #ሼር ያድርግ
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
───────────
Channel
@dnhayilemikael
#መቼ #ነው
መቼ ነው እውነተኛ ክርስቲያን የምንሆነው ሼር ሳታነቡ አትለፉ
መቼ ነው እግዚአብሔር በፈጠራቸው ነገሮች የምንረካው?
መቼ ነው እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠረን የምንረዳው?
መቼ ነው እግዚአብሔር እንደፈለገው መኖር የምንጀምረው?
መቼ ነው ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልባችን የምንናገረው?
መቼ ነው እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው?
መቼ ነው ለመልካም ሥራ ምሳሌ የምንሆነው?
መቼ ነው በስግደታችን በፆሎታችን የምንጠቀመው?
መቼ ነው ጸሎታችን ተሰሚነት የሚያገኘው?
መቼ ነው ውሎና አዳራችን በቅዱስ ቃሉ የሚሆነው?
መቼ ነው ሙለ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ የምንመካው?
መቼ ነው የዓለምን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው?
መቼ ነው ቤታችን ውስጥ የተበላሸ ሂወት የሚስተካከለው?
መቼ ነው ቤታችን ውስጥ መጽሀፍ ቅዱስ ውዳሴ ማርያም የሚወራው?
መቼ ነው ውሸት የምናቆመው?
መቼ ነው የእግዚአብሔርን ውሳኔ መቃወም የምናቆመው?
መቼ ነው እኔ እኔ ማለት ትተን ወንድሜ እህቴ ማለት የምንጀምረው?
መቼ ነው ለሰዎች ከክርስቶስ ውጪ ጌታ እንደሌለ የምንናገረው?
መቼ ነው ጥሩና ለጋሽ መልካም ሰው የምንሆነው?
መቼ ነው ክርስቲያንነታችንን የምናስተዋውቀው?
መቼ ነው ለደሃ እምናዝነው?
መቼ ነው ትዳራችን ሰላም የሚያገኘው?
መቼ ነው የጋብቻን ጥቅም ተረድተን ለትዳር የምንቸኩለው?
መቼ ነው ከሀሜት ሰውን ከመበደል ከማስቀየም ከማማት እምንላቀቀው?
መቼ ነው ወላጆቻችንን የምናስደስተው የምንታዘዘው?
መቼ ነው ያልተጣረ ወሬ ከማውራት የምንቆጠበው?
መቼ ነው የምንዋደደው?
መቼ ነው እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ደስተኞች የምንሆነው?
መቼ ነው ስግዴተ ፆም ፀሎት የምንላመደው?
መቼ ነው የበደሉንን ይቅር የምንለው?
መቼ ነው ከራስ ወዳድነት የምንላቀቀው?
መቼ ነው ከሞት በኃላ ላለው ሕይወት ስንቅ የምናዘጋጀው?
መቼ ነው አባቶችን የምናከብረው?
መቼ ነው ለእውቀት ጊዜ የምንሰጠው?
መቼ ነው ክርስትናን የምንኖረው?
ኸረ መቼ ነው ለእነዚህ ተግባራት መልስ የምንመልሰው
እግዚአብሔር ይርዳን
ተራራውን ደልድለህ ሸለቆውን ሞልተህ መንገዴን ያቀናህኝ የማለዳው ድምቀት የቀኑ ውበት ክብሬ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እላለሁ ብቻ ተመስገን። በሕይወቴ ስንት አለፈ
ሞት ለሚገባኝ ምሕረት የሰጠኸኝ ጌታ እባክህ እንዳለፈው ዘመን ጊዜዬ አይለፍብኝ። ፍጻሜዬ በቤትህ ይሁንልኝ። የነዚህ ባሪያዎችህን ፍጻሜ እኔም ተመኘሁ። አምኜህ መሞትህ ናፈቅሁ። ያላንተ ወርቅ ከምደብር ከመስቀልህ ሥር እርቃኔን ልቀመጥ። አንተ የሕይወቴ ተስፋ ያላንተ እንደማይሆንልኝ እንኳን መራራው ጣፋጩ እንደማይጣፍጠኝ ታውቃለህና ዘመኔን በፍቅር ፈጽመው በተወጋው ጎንህ።
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን አሜን፫።
@dnhayilemikael
📍📍 ሰበር📍📍
ከደቂቃዎች በፊት የተሰበሰበው አስተዳደራዊ ጉባኤ ከዚህ በታች ያሉት ውሳኔ አስቀምጧል።
ኤጲስ ቆጶሳት ነን ብለው በተገኙ ፳፮ መኖከሳት ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላለፈ
***
የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት የአስተዳደር ጉባኤ ዛሬ ማለዳ ላይ በዋለው ስብስባ ትላንት ጥር 14 በወሊሶ ከተማ በተደረገው ህገ ወጥ ሲመት
እራሳቸውን ኤጴስ ቆጶሳት ብለው የገለጡ ከተለያዩ አድባራት እና ገዳማት የተውጣጡ ፳፮ መኖኮሳት ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላልፏል።
በእዚህ መሰረት
፩ኛ .ሁሉም መኖከሳት ከደምወዝ ታግደው እንዲቆዩ
**
፪ኛ. የሚያንቀሳቅሱት የገዳማት እና አድባራት ሂሳብ ካለ እንዲታገዱ
**
፫ኛ. ከእዚህ በፊት ወደሚያገለግሉት የአገልግሎት መዋቅር እንዳይመለሱ
**
፬ኛ.በየትኛው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት እንዳይገኙ ውሳኔ አስተላልፏል።
ፍትሕ መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀጣይ በሚያደርገው ስብሰባ ይወስናል ተብሎ ይጠብቃል።
/channel/dnhayilemikael
ባልንና ሚስትን አንድ የሚያደርገው እግዚአብሔር ነው። አንድ የሚያደርገውም በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚከናወነው ሥርዓት ነው። ሥርዓቱም ሥርዓተ ተክሊሉ ብሎም ሥርዓተ ቁርባኑ ነው።
ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በመጋባት ግን ባልና ሚስት አንድ አይኾኑም። መኝታ ተጋርተው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።
ስለዚህም፦
☝አንደኛ፥ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን አንድ የኾኑበትን ምሥጢር በተግባር መካድ ነው።
☝ ኹለተኛ፥ የተባረከ ትዳር አይደለም፤ የበረከት ምንጭ የኾነው እግዚአብሔር የለበትምና።
☝ ሦስተኛ፥ በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን መቋቋም አይችልም። መቋቋም የሚችልበትን ጸጋ አልተቀበለምና።
☝ አራተኛ፥ ዝሙት ነው። ለምን ሲባል ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ የሚኾነው ቤተክርስቲያን ስትፈቅድ ብቻ ነውና።
------
ሼር ብታደርጉት መልእክቱ ለብዙ ሰው ይደርሳል!
------
© /channel/dnhayilemikael
✍መልእክት ለሚጋቡት ሼር አድርጉት።
✅ሐሙስ በሥርዓተ ተክሊል በቅዱስ ቁርባን ጋብቻችሁን ከፈጸማችሁ በኋላ እሁድ እንደገና በቤሎ የምታገቡ ሰዎች እባካችሁ ሁሉም አይቅርብኝ አትሁኑ
✍ቤተ ክርስቲያን ✅በካባዋ ሸልማ ✅በካህናቶቿ ቅኔ ተቀኝታ ወረብ አሰምታ
✅በሰንበት ተማሪዎቿ መዝሙር አዘምራ በልዩ መንፈሳዊ ስርዓት ካጋባቻችሁ በኋላ እንደገና ዓለማዊ ነገር ፈልጋችሁ በቤሎ የምትመነቃቀሩ በባንድ የምትጨፍሩ በዘፈን የምትዳሩ አካላችሁን የምታራቁቱ ሙሽሮች አምላካችሁን ፍሩ
✍በዝማሬ አግብታችው በዘፈን አጨርሱት
✍በካባ በተክሊል አግብታችሁ በቤሎ አትፈጽሙት
✍በቅዱስ ቁርባን አግብታችሁ በስካር አትፈጽሙት
✍በወረብ አግብታችው በዳንኪራ አትደምድሙት
✍በሸብሸቦ ተድራችው በጭፈራ አትፈጽሙት
✍በቤተ ክርስቲያን ተጋብታችሁ በሆቴል አትጨርሱት
✍ቤተ ክርስቲያን ካከበረቻችው ክብር በላይ የትም አታገኙም
✍በጥቅሉ በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ አትጨርሱት
በዚህ ወቅት በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የምትጋቡ መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ
/channel/dnhayilemikael
ተዘክሮ ሞት
ሦስቱ መነኰሳት
ሦስት መነኰሳት ወደ አንድ ታላቅ አባት ምክር ፈልገው ሔደው እንዲህ በማለት ጠየቁት። አንደኛው መነኵሴ “የሲዖል ቁልቁለት፣ ጽንዓተ ጽልመት” ሲባል እየሰማሁ ከዚያ አስጨናቂ መከራ እንዴት ለመዳን ይቻለኛል በማለት እጨነቃለሁና ምን ባደርግ ይሻለኛል በማለት ጠየቃቸው።
ሌላኛው መነኵሴ ደግሞ “ሐቍየ አስናን፡- ጥርስ ማፋጨት ያለበት አስፈሪ ቦታ አለ” ሲባል እሰማለሁና ከዚያ ለመዳን ምን ላድርግ አለው? ሦስተኛው እና የመጨረሻው መነኰሴ ደግሞ “እሳቱ የማይጠፋበት፣ ትሉ የማያንቀላፋበት ቦታ አለ” ሲባል እሰማለሁና ከዚያ ለመዳን ምን ባደርግ ይሻለኛል? ብሎ ጠየቀው። የተጠየቀው አባትም ዝም ብሎ ሲያዳምጣቸው ቆየና “ልጆቼ ቀናሁባችሁ፤ እኔ ይህን ያህል ዘመን ስኖር የእናንተን ያህል ተዘክሮ ሞት አስቤ አላውቅም” አላቸው።
@dnhayilemikael
ሦስቱ መነኰሳትም የታላቁን አባት መልስ ሰምተው “ይህ አባት እውነትም ፍጹም ነው። ለወጣኒነት እንኳ ያልደረስነውን እኛን እንዴት ቀናሁባችሁ ይለናል” ተባባሉ። ታላቁ አባትም “እኔ ኃጢአቴ ብዙ ስለሆነ እራሴ ላይ እየተንጫጫብኝ እናንተ የምታስቡትን ተዘክሮተ ሞት ለማሰብ አልደረስኩም። እናንተስ አንዳንድ ትሩፋት ይዛችኋል።እኔ ግን ምንም ትሩፋት የለኝም” አላቸው። ለጀማሪዎቹ መነኰሳት አንዳንድ ትሩፋት ይዛችኋል ያላቸው ሞትን ማሰብ፣ ኃጢአትን ማሰብ፣ ጥርስ ማፋጨት ያለበት ቦታ መኖሩን ማሰብ ትሩፋት በመሆኑ ነው። በማስከተል ሞትን ማሰብ፣ ኃጢአትን ማዘከር፣ ጥርስ ማፋጨት ያለበትን ቦታ ማሰብ ትሩፋት መሆኑን ተርጕሞላቸው እናንተስ አንዳንድ ትሩፋት ይዛችኋል። እኔማ ኃጢአቴ በዝቶ በአእምሮዬ ይንጫጫብኛል። እናንተ የምታስቡትን ለማሰብ አልደረስኩም አላቸው።
🥀ታላቁ መነኩሴ ለጠየቁት ወጣንያን መነኰሳት እንደዚያ ብሎ የመለሰላቸው ትሕትና ያለው አባት በመሆኑ ነው። ሰዎቹ ምን ብለው ተናገሩ ትሉኝ እንደሆነ “ትሕትናው ከመነገር በላይ ነው ሲሉ ሰምተን ነበር። አሁን ግን በጆሯችን የሰማነውን በዓይናችን አየነው” እያሉ ወደ ገዳማቸው ተመለሱ በማለት አስተማሩ። እግዚአብሔር የሚወደው በጠባብ መንገድ መሔድ ነው። ጠባብ መንገድ ማለት ድሃን መጽውት፣ ሀብታምን ጹም ማለት ነው በማለት ተረጕመው አብራሩልን። ሀብታም እንዴት አድርጎ ይጾማል፤ ድሃስ ከምን አምጥቶ ይመጸውታል? ይህ ችግር ነውና አባቶቻችን ጠባብ መንገድ ብለውታል።
“🥀ሐቁዬ ስን፡- ጥርስ ማፋጨት” ያለበትን የመከራ ቦታ መፍራት ከሲዖል ለመዳን ነው። እሳቱ የማይጠፋ፣ ትሉ የማያንቀላፋ ያለበትን የስቃይ ቦታ መፍራትም ከስቃይ ለማዳን ነውና አንዳንድ ትሩፋት ይዛችኋል ብሎ አመሰገናቸው።
ያአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን።
@dnhayilemikael
#ጥር_1_ቅዱስ_እስጢፋኖስ_የተወለደበት_እና_የሰማዕትነት_አክሊል_የተቀበለበት_ዕለት_ነው ።
#እስጢፋኖስ፦የስሙ ትርጉም በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡
አባቱ ስምኦን፣ እናቱ ሃና ይባላሉ፡፡ የተወለደው - ጥር 1 ቀን በእስራኤል ሃገር ውስጥ በብፅዓት / በስለት/ ነው፡፡ ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለ ቦት ተወለደ ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡
በደሙ የመሠረታት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በጽርሐ-ጽዮን ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከተቀበለች በኋላ የትንሣኤውን ወንጌል ለትውልድ ማድረስ ጀመረች፡፡ ወንጌል እየተስፋፋ አማኞች እየበዙ መጡ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት የሚያግዟቸው ሰባት ጠቢባን ወጣቶችን መርጠው የዲቁና ሥልጣን ሰጡአቸው፡፡
ከተሾሙት ዲያቆናት መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ነው፡፡ ሐዋ. 6÷5. ቅዱስ እስጢፋኖስ ጥቅምት 17 ቀን የዲያቆናት አለቃ ሆኖ ሊቀ ዲያቆናት ተብሏል፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ ከግሪክ አገር የመጡ አይሁድ በተከራከሩት ጊዜ በመንፈስና በጥበብ መለሰላቸው፡፡ አይሁድም ዳኞች በተሰየሙበት ሸንጎ ፊት አቅርበው በሐሰት ከሰሱት፤ ሸንጎውም በድንጋይ እንዲወገር ፈረደበት፡፡ እስጢፋኖስ ግን በታላቅ ኃይልና በብዙ መረዳት ከአባቶቻቸው ታሪክ ተነሥቶ የዓለም መድኃኒት የሆነውን ክርስቶስን ሰበከላቸው፡፡ ጥላውን ከአካሉ ጋር እያጋጠመ ወደ ፍጹማን ጥበብ በጽድቅ ቃል መራቸው፡፡ አይሁድ በጣም ተቆጡ፤ ሁሉም በአንድነት ሆነው በድንጋይ ወገሩት፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰውነቱ ቆስሎና ዝሎ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ባነሣ ጊዜ የልዑልን ክብር ተመለከተ፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቱ ቀኝ ቆሞ አየ፡፡ ሐዋ. 7÷55፡፡
ቅዱስ አሰስጢፋኖስ “እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) በአባቱ ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አላቸው፡፡ አይሁድ ግን ልበ-ደንዳኖች (የማይራራ ጨካኝ ልብ ያላቸው) ስለሆኑ እስጢፋኖስን ከከተማ ወደ ውጭ አውጥተው ደበደቡት፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰውነቱ ደከመ፤ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በደረሰች ጊዜ በሞት ጣር ሆኖ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው፤ ነፍሴን ተቀበል” ብሎ ጸለየ፡፡ ነፍሱንም ለታመነው ፈጣሪ አደራ ሰጥቶ ጥር 1 ቀን በ34 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
የሰማዕትነት ሕይወትን በመጀመሩ ስለ ክርስቶስ ፍቅር መራራ ሞትን በመታገሡ ቀዳሜ ሰማዕት ተብሏል፤ የቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ሰማዕት ነውና፡፡
ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን አሜን !!!
@dnhayilemikael
የክርስትና ሕይወት ማስተዋል፣ እምነት እና ትእግስትን ይጠይቃል፡፡ ዝም ብሎ በሰዉ ከመነዳት መጠበቅ አለብን፡፡ የዓላማ ሰዉ መሆን ይኖርብናል ፡፡ የተፈጠርንበትን ዓላማ እና ክብርንም መርሳት የለብንም፡፡ የስም ሳይሆን የተግባር እና የሕይወት ክርሰቲያን ሆነን ክርስትናንም በሕይወት ገልጠን ለመንግሥቱ እና ለክብሩ እንዲያበቃን የእርሱ የአምላካችን መልካም ፍቃድ ይሁንልን፤ አሜን ፡፡
የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ(አጋሩ)
ዲን ዘአርሴማ
/channel/dnhayilemikael
#እሺ_ምን_እንዳመጣልህ_ነው_የምትፈልገው?
በአንድ ወቅት አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ቆሞ ጌታየ ሆይ! አንተ ከእኔ ምን ትፈልጋለህ? ምንስ ባደርግልህ ደስ ትሰኛለህ?...እስቲ ንገረኝ ረጅምና በቁመቴ ልክ የሆነ ከሰም የተሰራ ሻማ እንዳመጣልህ ትፈልጋለህ? አለው። ጌታም መልሶ "ለሻማው መስሪያ የሚሆነው ሰሙም የእኔ ነው፤ ሰሙ የሚገኝበት የማር እንጀራውም የእኔ እኮ ነው"አለው።
ያም ሰው ቀጥሎ "እንግዲውስ ድሆችን ለመርዳት ይሆን ዘንድ 1000,000 ብር እሰጥሃለሁ አለው። ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "
አንተ አለኝ ያልካቸው ነገሮች ሁሉ የእኔ ናቸው፤ ምድርና መላዋ ለእግዚአብሔር ናት ፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። መዝ.24:1) አለው።
ሰውየውም እንዲህ አለ " ጌታዬ ሆይ እሺ ምን እንዳመጣልህ ነው የምትፈልገው?
ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ፣ ስለአንተ ብየ ተጠምቻለሁ ፣ ስለአንተ ፍቅር መስቀል ላይ ወጥቻለሁ አለው።
እግዚአብሔር ካለን ነገር በፊት እኛን ይፈልገናል። ራሳችንን ሳንሠጠው ብንደክም ብንለፋ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው" (ሉቃ. 10:42) ይለናል ይህም ልባችንን ለእርሱ በቃሉ ለመኖር መሥጠት ነው።
እውቀታችንን ሠጥተን ፣ ገንዘባችንን ሠጥተን ፣ ጉልበታችንን ሠጥተን እኛ የእርሱ ካልሆንን ምን ይጠቅማል? ኃጢአት ከእርሱ ለይታናለችና ፣ በንስሐ ልባችንን እንዲንሠጠው በመንፈሳዊ ምሥጢራት ከእርሱ ጋር አንድን እንድንሆን ይሻል። ራሳችንን በንስሐ አቅርበን ልባችንን ለፈጠረን አምላክ እንስጠው።
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
/channel/dnhayilemikael
ከቤተክርስቲያን ውጭ ጋቢቻ ቢፈጸም ምን ችግር አለው ?
✅በቤተ ክርስቲያን ጋብቻ የሚፈጸመው ድንግልናቸውን ለጠበቁ በተክሊል ስሆን ለሌች ደግሞ በቁርባን ነው
✅ ጋብቻ ፈጻሚዎቹ ደናግል ከሆኑ በተክሊል አንድ ይሆናሉ
ካልሆኑ ደግሞ የመዓስባን ጸሎት ተደርጎላቸው በቅዱስ ቁርባን ይጣመራሉ።
✅#በማለዳ ቤተክርስቲያን ተገኝተው በካህናት ቡራኬ አክሊል ደፍተው፣ ካባ ደርበው፣ ቅብዐ ቅዱስ ተቀብተው የቃል ኪዳን ቀለበታቸውን በቤተክርስቲያን ፊት አሥረው የነገር ሁሉ ማሠሪያ የሆነውን የክርስቶስን ሥጋና ደም ተቀብለው ጋብቻቸውን ይፈጽማሉ።
✅ጋብቻቸው በእግዚአብሔር የተባረከ ቅዱስ፥ መኝታቸውም ንጹሕ ይሆንላቸዋል /ዕብ. ፲፫÷፬
አበው በፍትሐ ነገሥት ስለዚህ ምሥጢር ሲናገሩ - የጋብቻ አንድነት ግን በካህናት መኖር በላያቸው በሚጸልዩት ጸሎት ካልሆነ በቀር አይሆንም አይፈጸምም:
✅ ሁለቱ አንድ በሚሆኑባት በተክሊልም (በቁርባን)
ጊዜ ቅዱስ ቁርባንን ያቀብሏቸዋል
✅ምስጋና ይግባውና ጌታችን እንደተናገረ አንድ አካል ይሆናሉ (ማቴ.፲፱÷፭)
✅ያለዚያ ግን ጋብቻ ተብሎ አይቆጠርላቸውም።
✅ወንዶችን ከሴቶች ሴቶችንም ከወንዶች አንድ የምያደርግ ጸሎት ናትና ብለዋል፡፡
ፍትሐ ነገስት አንቀጽ ፳፬
ስለዚህ ቤተክርስቲያን ያልተፈጸመ ጋቢቻ ተብሎ ካልተጠራ ምን ልባል ይችላል? መልሱን ለእናንተ
/channel/dnhayilemikael
ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም?
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።
ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?
እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል? ይፈልጋል🥰
ዲያቆን አቤል ካሳሁን💖💖💖
/channel/dnhayilemikael
ማክሰኞ † ቶማስ
-----------------------------
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ……… በዓቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን ………….አግአዞ ለአዳም
ሰላም ………………………እም ይእዜሰ
ኮነ………………………………ፍስሐ ወሰላም
••••••••••••••••••• † •••••••••••••••••
እንደ ኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሰረት ከትንሣኤ በኋላ ያለው ሁለተኛው ዕለተ ማክሰኞ "ቶማስ" በመባል ይጠራል።
ቶማስ ሐዋርያ ሲሆን፣ ቶማስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው። ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ ፤ እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል።
ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው» አለው። (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች።
ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡
ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡
ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)።
የሐዋርያ ቶማስ መታሰቢያ በዳግመ ትንሣኤ ላይ የሚነሳ ቢሆንም አባቶች በበዓል ላይ በዓል እንዳይደራረብ ብለው ከትንሣኤ በኋላ ባለው በዕለተ ማግሰኞ ቶማስ ተብሎ እንዲጠራ ስርዓት ሰርተውልናል።
የአባቶቻችን በረከት ይደርብን በእውነት። በዓሉንም በዓለ ደስታና በዓለ ፍስሐ ያድርግልን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም ቀን!!!!
/channel/dnhayilemikael
🤗ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
⚡⚡⚡ሰኞ⚡⚡⚡
👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
@dnhayilemikael
ጾሙስ አበቃ.....?
✅ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን?
✅ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው?
✅ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው?
✅ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው?
✅በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተሰቅሎ ሞቶ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቶ የኃጢአት እዳችን ተወገደ ሰውና እግዚአብሔርና ታረቁ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው?
✅መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው።
✅ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት።
✅ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት?
✅ምን ንብረት ተመደበላት?
✅ምን ሙክት ተገዛላት?
✅ምን ወይን ተጠመቀላት?
✅ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት?
✅ እነማንን ድግሥ ጠራንላት? ✅አጋንንትን ወይስ መላእክትን?
✅ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል።~ የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል ~የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። ~በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ~ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!
✅አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል።
✅ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው።
✅ ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል።
✅ ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?
✅የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው?
✅የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው?
✅መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!
✅ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ ..ተሰቀለ ሞተ ተነሳ አዳነን። ✅የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? ✅በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ!
✅ጸሎቱ ቀጠሮ 🛐ጾሙ ቀጠሮ 🛐ትጋቱ ቀጠሮ 🛐አሥራቱ ቀጠሮ 🛐ኑዛዜው ቀጠሮ🛐 መታረቁ ቀጠሮ
🛐ቁርባኑ ቀጠሮ 🛐ሁሉ ቀጠሮ!
✅ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ
✅የዐቢይ ጾም ፍጻሜ ጌታ ተነሳ። እኛም ከኃጢአት በንስሐ እንድንነሳ ይርዳን።
✅ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከሲኦል አወጣን። ከጾማችን ፍጻሜ እኛም ከኃጢአት እንውጣ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። @dnhayilemikael
👉🏻 ረቡዕ || ሰሞነ ሕማማት
••
1. ምክረ አይሁድ ይባላል
••
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል።
••
የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
••
2. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል ፦
•
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት / ባለ ሽቶዋ ማርያም / « ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ » ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ አልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ / በራሱ / ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመዓዛ ቀን ይባላል።
•••
3. የእንባ ቀን ይባላል
•
ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። ጌታ ሆይ መከራህን ስቃይህን ረሃብ ጥማትህን ሞትህን እያሰብኩ የማነባበት እንባ አብራህ ስለተንከራተተችው በመስቀል ላይ ሳለህም አንዴ ከድንጋይ አንዴም ከእሾህ ላይ እየወደቀች እየተነሳች ወየው አንድ ልጄ እያለች ስታነባ በነበረችው በአዛኝቱ እናትህ ስጠኝ አቤቱ ይቅር በለኝ ኢትዮጵያን ተዋሕዶን አስባት ኪርያላይሶን!
••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
••
👉🏻 @dnhayilemikael
+++"@dnhayilemikael
እጅግ ጥልቅ የጸሎት ሕይወት የነበረው፣ አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ የሚጾመው ተሐራሚው ቅዱስ አባ ጳጉሚስ ከእለታት በአንዱ ቀን ይህን ተመለከተ፡፡ ቅዱሱ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር አብዝቶ ይሰግድ ነበር፡፡ ከዓይኑ የሚወርደው እንባ ከሰውነቱ ወዝ ጋር እየተቀላቀለ ወደ መሬት በመውረዱ ምክንያት የሚሰግድበትን ቦታ አረጠበው፡፡ አባ ጳኩሚስም ይህን ወደ ጌታው እያመለከተ "ይኸው አንተን አገኝ ብዬ እንዲህ እደክማለሁ" ሲል ተናገረ፡፡ በዚህ ጊዜም መድኃኒታችን ለአባ ጳጉሚስ ተገልጦ "እኔም እንጂ ላንተ ብዬ እንዲህ ሆኜ ተሰቅያለሁ" በማለት በእለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሆኖ የተወጋ ጎኑን፣ የፈሰሰ ደሙን አሳየው፡፡ ቅዱሱም የጌታው ሕማም ከሕሊናው በላይ ሆኖበት ወድቆ ምሕረትን ለምኗል፡፡
+++++++++++++
ሕሊናቸው የክርስቶስን ሕማም ከማሰብ አቁሞ የማያውቀው አባ መብዓ ጽዮን መድኃኔዓለምን :- ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፡፡ ስለ ራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ›› ሲሉ ለመኑት፡፡ ጌታም ‹‹መከራ መስቀሌን ለማየት ትፈቅዳለህን?›› ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮንም ‹‹አዎ! አይ ዘንድ እወዳለሁ›› አሉት። ያን ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ታየ፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር። እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ታያቸው። ይህን የመድኃኔዓለም መከራ የተመለከቱ የጻድቁ ዓይኖችም ፈዝዘው እስኪጠፉ ድረስ ትኩስ እንባዎችን ሲያዘንቡ ኖረዋል።
‹‹ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ›› - ‹‹ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው!››
✍🏿 @dnhayilemikael
#ጥቁር #ልብስ
ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
#ልዩ_መረጃ
በ"አባ" ሳዊሮስ አማካይነት ከታች የተዘረዘሩት አህጉረ ስብከት ላይ የስም ዝርዝራቸው የሚገኘው መነኮሳት የአህጉረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና ከቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድና እውቅና ውጭ ወረራ እንዲፈጸምበት ስምሪት የተሰጠ በመሆኑ በየአካባቢው የምትገኙ ካህናትና ምዕመናን መንበረ ጵጵስና አህጉረ ስብከቱን እንድትጠብቁ ጥሪ ቀርቧል !
1."አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
2."አባ" ተ/ሃይማኖት ወልዱ - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
3."አባ" ገብርኤል ወ/ዮሐንስ - ጉራጌ ሶዶ ሀገረ ስብከት
4."አባ" ገ/እግዚአብሔር ታደለ - ምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት
5."አባ" ሚካኤል ገ/ማርያም - ከምባታ ሀገረ ስብከት
6."አባ" ኃይሉ እንዳለ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
7."አባ" ተ/ማርያም ስሜ - ጉጂ ሊበን ሀገረ ስብከት
8."አባ" ኃ/ኢየሱስ መንግስቱ - ከፋ ሀገረ ስብከት
9."አባ" ወ/ኢየሱስ ኢፋ - ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት
10."አባ" ጳውሎስ ከበደ - ሀዲያ ሀገረ ስብከት
11."አባ" ኃ/ኢየሱስ ተስፋዬ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
12."አባ" ገ/ኢየሱስ ገለታ - ሆሮ ጉዱሩ ሀገረ ስብከት
13."አባ" ጸጋዘአብ አዱኛ - ምሁር ኢየሱስ ገዳም "የበላይ ጠባቂ"
14."አባ" ኃ/ማርያም ጌታቸው - ምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
15."አባ" ወ/ጊዮርጊስ ኃ/ሚካኤል - ከሚሴ ሀገረ ስብከት
16."አባ" እስጢፋኖስ ገብሬ - ባሌ ሀገረ ስብከት ረዳት
17."አባ" ገ/መድኅን ገ/ማርያም - ጎፋ ባስኬቶ ሀገረ ስብከት
18."አባ" ኃ/ሚካኤል ንጉሤ - ጊኒር ሀገረ ስብከት
19."አባ" አብርሃም መስቀሌ - ዳውሮ,ኮንታ ሀገረ ስብከት
20."አባ" ንዋየ ሥላሴ አክሊሉ - ምዕራብ ጉጂ ሀገረ ስብከት
21.አባ ኪ/ማርያም ቶሎሳ - ጅማና የም ሀገረ ስብከት
22."አባ" ወ/ማርያም ጸጋ - ቦረና ሀገረ ስብከት
23."አባ" አምደሚካኤል ኃይሌ - አርሲ (አሰላ) ሀገረ ስብከት
24."አባ" መርሐጽድቅ ኃ/ማርያም - ጌዴኦ,ቡርጁ,አማሮ ሀገረ ስብከት
25."አባ" ሞገስ ኃ/ማርያም - መናገሻ አምባ ቅድስት ማርያም ፣ ጋራ መ/ዓለምና ደ/ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ "የበላይ ጠባቂ"
26."አባ" ገ/ኢየሱስ ንጉሤ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa
ምንጭ =ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
ነገ ጥር 10 የገሃድ ጾም ነው !!!!!!
ገሃድ/ ጾመ ድራረ ጥምቀት
ይህ ጾም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ መጾም ነው፡፡
ይህም ማለት በጥምቀት ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው፡፡ የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነም የጥምቀትን ድራር መጾም ነው፡፡ ሐዋርያት «ልደት ጥምቀት ዓርብ ረቡዕ ቢውል በሌሊት ቀድሰው ሥጋውን ደሙን ይቀበሉ፤ ከሌሊቱ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጹሙ ብለው አይፍረዱ» ብለዋል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/፡፡ የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ሃምሳ የሚበላውን የጥሉላት ምግብ በጠዋት በመብላት ምእመናን በዓሉን እንዲያከብሩ ታዟል፡፡ ይህም እነዚህ ሁለቱ ታላላቅ የእግዚአብሔር በዓላት በመሆናቸው ነው፡፡ የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማክሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል፡፡ በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ሥራ ይከናወናል፡፡ የጥምቀትን ዋዜማ ጥሉላት መባልዕትን መተው ነው፡፡ ይህንንም እንደ ዘይቤው ገሀድ ይለዋል፣ መገለጫ፣ ግልጥ፣ ይፋ መሆን ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ጋድ ይለዋል፣ ለውጥ፣ ልዋጭ ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ረቡዕ ዓርብ ሲውል በዚያ ለውጥ ማክሰኞ ሐሙስ ይጾማልና ጋድ አለው፡፡ እንዲሁም አንድ ጊዜ ሲጾም አንድ ጊዜ ሲቀር እንዳይረሳና ቅዳሜ ወይም እሑድ በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ አይቻልም፣ ነገር ግን እህል ውኃ እንጂ ጥሉላት ከመብላት መጠበቅ ይገባል፡፡ ልደት የሚውልባቸው ረቡዕና ዓርብ ቢሆኑ የፍሥክ /የሚበላባቸው/ ቀናት ሆነው እንዲከበሩ ሐዋርያት ያዘዙ ቢሆንም በዋዜማው የሚገኙት ማክሰኞና ሐሙስ ከጾመ ነቢያት ጋር የተያያዙ ስለሆኑ መጾማቸው ግድ ነው፡፡
የገሃድ ጾም እስከ ማታ ድረስ ቀኑን ሙሉ ነው የሚጾመው
ሆኖም የነቢያትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች በመላው የጾሙ ቀናት ሲበሉ ቆይተው በዋዜማው ብቻ ገሀድ ነው ብለው ይጾማሉ፡፡ ነገር ግን ለጾመ ነቢያት ገሀድ የለውም፡፡ ጾሙ የጥምቀት ብቻ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ለጾመ ነቢያት ገሀድ እንዳለው የሚናገሩም አሉ፡፡ ለዚህም የሚያቀርቡት ማስረጃ እስከ ምሽት መጾሙን ነው፡፡ ይህም «አድልው ለጾም፤ ለጾም አድሉ፡፡» እንዲሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ቢጾም የሚያከራክር ወይንም ስህተት ነው የሚያሰኝ አለመሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ነቢያት ይወርዳል፣ ይወለዳል ብለው የተናገሩት ቃል ይፈጸም ዘንድ የሰው ልጆችም ድኅነት ማረጋገጫ እውን ይሆን ዘንድ እንደ ጾሙ እንደ ጸለዩ በልደቱም እንስሳት፣ ሰዎች እንዲሁም መላእክት በአንድነት በደስታ እንደዘመሩ የእኛም ደስታ የተረጋገጠበት ነው፡፡ በመሆኑም በፍቅር፣ በጾም በጸሎት ዛሬም እናስበዋለን፡፡ ነቢያት በረከት እንዳገኙ እኛም ከእግዚአብሔር በረከት እናገኛለን፡፡ ለዚህም አምላካችን ይርዳን
/channel/dnhayilemikael
፡
ልባም ሴት
#ዜሮን_ፃፉ_አሁንም_ድጋሚ_ዜሮን_ፃፉ.......
ደስ የሚል መልእክት ነው አንብቡት
ጋብቻ ለመመስረት ያሰበ አንድ ወጣት ከቤተሰብና ከጓደኞቹ ጋር ተማክሮ ከጨረሰ በኋላ የንስሀ አባቱ ዘንድ በመሔድ ይህንን ውሳኔውን አስረዳቸው፡፡
#ጥበበኛውም_አባት ለማግባት ያለውን ጉጉት በልጁ ፊት ላይ እያስተዋሉ አሳቡ መልካም እንደሆነ ገልጸው ማስታወሻና ብዕራቸውን በማውጣት “ስለ ልጅቷ ትንሽ ነገር ንገረኝ” በማለት ጥያቄ አቀረቡለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ “ትውልዷ ከነገስታት ዘር እድገቷም በምቾት መሐል ነው” አለ፡፡ እኚህም አባት በሙሉ ልብ ሆነው በያዙት ማስታወሻ ላይ ዜሮ ጻፉ፡፡
ወጣቱም ስለ ልጅቷ ማብራራቱን ቀጠለ፡- “በጣም ውብ ናት” አለ፡፡ እርሳቸውም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ “በጣም ዝነኛ ናት” አለ፡፡ ደግመው ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ “በጣም ሀብታም ናት” አለ፡፡ ጥበበኛውም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡
“በጣም ምሁር ናት” አለ፡፡ አሁንም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡
“በጣም ዘመናዊ ናት” አለ፡፡ ተጨማሪ ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ በመጨረሻ ግን የረሳውን አንድ ነገር ነገራቸው “ልባም እንዲሁም ሕይወቷ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና የተሰጠ ነው” አላቸው፡፡ ጥበበኛውም አባት ፊታቸው ላይ ፈገግታ እየተነበበባቸው አስቀድሞ ከጻፉአቸው ስድስት ዜሮዎች ፊት አንድ ቁጥርን ጽፈው “በል ሂድና አግባት” አሉት፡፡ ወጣቱም በደስታ ከፊታቸው ሄደ፡፡ በደስታም ልጅቷን አገባት♥♥♥
ጋብቻ ብዙ ጊዜም በሌላው ሰው አካላዊ ገጽታና ውጫዊ አቋም ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ምንም እንኳን በአካላዊ ውበት መማረክ ወደ ፍቅር የሚመራ አንደኛው መንገድ ቢሆን እውነተኛ ፍቅር ግን በአካላዊ ውበት፣ በአፋዊ መስፈርት ከመሸነፍ ያለፈ ነው፡፡ አካላዊ ውበት የጊዜያዊ ጉጉት መገለጫ ሲሆን ፍቅር ግን በሌላው ውስጥ ያለውን መልካሙን ነገር በመሻት ትዕግስትን መሰረት የሚያደረግ ነው፡፡ይህም የትኛውንም ልብ የመንካት፣ በላቀና በጠለቀ መንገድ የመግዛት ጉልበት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው በዘመኑ የሚያሳልፋቸው ትልልቅም ይሁን ትንን ውሳኔዎች አሉ፡፡ ሕይወትም በዚህ የዕለት ተዕለት ቋሚ የመምረጥና የመወሰን ተግባር ላይ የተመሰረተች ናት፡፡ ጋብቻ የእኛን ትልልቅ ውሳኔ ከሚፈልጉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡
የምናመልከውን እንመርጣለን፣ የምንኖርበትን አካባቢ እንመርጣለን፣ የልባችንን የምናካፍለው ባልንጀራ እንመርጣለን፣በትዳር አጋር የሚሆነንን እንመርጣለን፣ በአጠቃላይ መሆን የምንፈልገውን እንመርጣለን፡፡ በእርግጥ ምርጫችንን ከምንኖረው በላይ ተጽእኖ ወደ ኑሮአችን የሚያመጣውን መኖራችን ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህም ውስጥ ከእውነት ጋር ያለን ትስስር ሊደበዝዝ አይገባም፡፡ ምርጫችን ውስጥ ሞትም ሕይወትም፣ ደስታም ሀዘንም፣ ክብርም ውርደትም አለ፡፡ መርጠን ዘመናችንን የእንባ ልናደርገው መብቱ የእኛ ነው፡፡
እግዚአብሔር እውነተኛ ፍቅር ሰጥቷችሁ
ለዚህ ክብር ያብቃችሁ አሜንንን🙏🙏🙏🙏
/channel/dnhayilemikael
👑 በቀራኒዮ መስቀል ስር እናት የተሰጠው ታማኝ ሐዋርያ👑
🌹ጥር 4, ቀን ቅዱስ ዮሐንስን አምላክ ሞትን እንዳያይ የሰወረው እለት ነውና እንኳን አደረሰን| አደረሳችሁ!!!🌹
🌿🌿🌿
🍇 " ቤተሳይዳ " በምትባል የገሊላ አውራጃ ነው የተወለደው! " ዮሐንስ" ማለት የእግዚአብሔር ጸጋ, ሓሴት ማለት ነው🙏
🌿 አባቱ ዘብዴዎስ (ቅለዮጳ), እናቱ ደግሞ ማርያም ሰሎሜ (ማርያም ባውፍሊያ) ከእመቤታችን ጋር በመስቀል ስር የተገኘች ታላቅ እናት ናት!!! ወንድሙ ከ12 ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ነው🙏❣️🙏
🍇አምላክ ሲመርጥ እንዲህ ነው! ከዓሣ አጥማጅነት አንስቶ ለክብር የተጠራ ሐዋርያ፣ ወንጌላዊ፣ ታማኝ አገልጋይ ነው🙏
🌿 ከሐዋርያት ሁሉ እስከ መስቀል ስር ድረስ የተከተለ፣ የታመነ ፣ እነሆ እናትህ የተባለ፣ እመቤታችንን በቤቱ ለ15 ዓመታት ፍቅሯን ፣ ጣዕሟን ፣ በረከቷን እያገኘ በክብር ያኖራት ታላቅ ሐዋርያ ነው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ🙏👑🙏
🍇 📌. ዮሐንስ ሐዋርያ 📌. ታኦሎጎስ
| ወንጌላዊ|
📌. ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ 📌. ንባቤ መለኮት
📌. ፍቁረ እግዚእ 📌. አቡቀለምሲስ
📌. ዮሐንስ ዘንስር 📌. አማናዊ ወዳጅ
ይባላል!!!
🌿 ቅዱስ ዮሐንስ በራእይ መንፈስ ተመርቶ 3ቱን ወንጌሎች የጻፈ ነው :-
✍️.የዮሐንስ ወንጌልን
✍️. የዮሐንስ መልእክትን
✍️. የዮሐንስ ራእይን የጻፈ ታላቅ ወንጌላዊ ነው🙏
👑🌿 . በመጨረሻም ስለክብሩ, ስለፍቅሩ ጥር 4 , ቀን በ90 ዓመቱ ሞትን ሳያይ ልክ እንደ ኤልያስ አምላክ የሰወረው ታላቅ ሐዋርያ ነውና ክብር እና ምስጋና ይገባዋል🙏❣️🙏
✝️🌿 በረከቱ ፣ ፍቅሩ ፣ አማላጅነቱ አይለየን💚💛❤️
🇪🇹ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን🙏
🍇 👇👇👇 🍇
ይከታተሉን
ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇
@dnhayilemikael
✝#ጾሙስ_አበቃ.....?✝
አንብቡት 😌
🥀ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!
🥀አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?
🥀 የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!
🥀ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግባር ብንወለድ!
🥀የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!
መጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረኪዳን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን
ተቀላቀሉ ቴሌግራም ተዋህዶ አሜን
/channel/dnhayilemikael
ፈተና በክርስቲያናዊ የአገልግሎት ሕይወት
ክርስትና የተግባር ሕይወት ነዉ ፡፡ የክርስትና ሕይወት ተራ ኑሮ ብቻም ሳይሆን ዘለዓለማዊ ዓላማ ያለው ሕይወትም ጭምር ነዉ፡፡ በተጨማሪም የክርስትና ሕይወት እግዚአብሔርን እና ቅዱሳንን የምንመስልበት ሕይወት እንዲሁም ቅዱስ የምንሆንበት ሕይወት ነዉ፡፡ ቅዱሳንን እንድንመሰል የሚያደርገን የክርስትና ሕይወትን በሕይወት፣ በፍቅር፣ በቅድስና፣ በትዕግስት፣ በታማኝነት፣ በንጽህና መኖር እና መግለጥ ሲቻል ብቻ ነዉ፡፡ ለዚህ ነዉ ሐዋርያው ቅዱስ ጰዉሎስ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ ያለን፡፡
የክርስትና ሕይወት በመንፈሳዊነት ይገለጣል፡፡ ቃሉን በመማር፣ በመስማት፣ በሕይወትም በመግለጥ (በመኖር) ይገለጣል፡፡ “የክርስትና ሕይወት የቅድስና ሕይወት ነዉ” ስንል ቅድስናዉ የሚገለጠዉ በአገልግሎት ሕይወት፣ ትጋት እና ፍቅር ነዉ፡፡ ክርሰትና አገልጋይነት ነዉ፤ ያዉም በታማኝነት እና በመንፈሳዊነት የምናከናውነው፡፡
አገልግሎት ለቅድስና ሕይወት ያበቃል፡፡ ከኃጢአት፣ ከክፋት፣ ከበደል፣ ከክፉ ምኞት ሐሳብ እና ተግባርም ይሠዉራል፡፡ ለፀጋ እግዚአብሔር፣ ለመንግሥቱና ለርሰቱም ያበቃል፡፡ ለበለጠ ፀጋ እና ክብርም ያደርሳል፡፡ ሰማያዊና ምድራዊ፣ መንፈሳዊ ሀብትን እና ክብርንም ያሰጣል፡፡ ማቴ ፡25፡ 14-30. መንፈሳዊ አገልግሎት፣ መንፈሳዊነት እና ክርሰትና ራስን መካድን፣ ራስን ማሸነፍን፣ ዓለምን መጥላትን/መተዉን፣ ለእግዚአብሔር ራስን አሳልፎ ማስገዛትን/መስጠትን ይፈልጋል፡፡ ‹‹ኑሮዬ ይበቃኛል›› ማለትን ይፈልጋል፡፡ ምክንያትን ማሸነፍን፣ ትዕግሰትን እና ማስተዋል ይጠይቃል ፡፡
የክርስትና ሕይወት በአገልግሎት ይገለጣል ስንል አገልግሎት ፈተና እንዳለዉም ደግሞ መርሳት የለብንም፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት መከራ ይበዛበታል፣ መዉጣት እና መዉረድ መዉደቅ እና መነሳትም አለው፡፡ ያለ ክርስትና ሕይወት መንፈሳዊነት የለም፤ የእግዚአብሔር ሰውም መሆን አይቻልም፡፡
እዉነተኛ አገልገሎት፣ የክርስትና ሕይወት እና መንፈሳዊነት ባለበት ቦታ ሁሉ መከራ እና ፈተና አለ፤ ያለ ፈተናም ጸጋን መቀበል አይቻልም፡፡ ለዚህም ነዉ ሐዋርያት በራሳቸው የተፈተነ ሕይወት ተግባራዊ ማሳያነት “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” እያሉ ያስተማሩት (የሐዋ.14፡21-22)፡፡ ይህም መከራ የደረሰባቸው በደስታ የሚቀበሉትና በመንፈስ የሚበለጽጉበት ሆኖላቸዋል፤ “… ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ እኛና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፡” (1ተሰ. 1፡6) እንዲል፡፡
ቅዱስ ጳዉሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈዉ መልእክቱ በመከራ ስለሚገኝ በረከት እንዲህ ያስተምረናል። “በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸዉ ብዛትና የድኅነታቸው ጥልቀት የልግስናቸው ባለጠግንት አብዝቶአል።” (2ኛ ቆሮ.8፡2)፡፡ ፈተና በተለያዩ መንገዶች በተለያዩ ምክንያቶችም ሊመጣብን ይችላል፡፡ ለመባረክና ለመዳንም በፈተና መጽናት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ነዉ መጽሐፍ ቅዱሰ በተደጋጋሚ ‹‹እሰከ መጨረሻዉ የሚጸና እርሱ ግን ይድናል›› በማለት አጽንቶ የሚመክረን (ማቴ 10፡ ማቴ 24፡ ማር 13)፡፡
ፈተና የክርሰትያናዊ ሕይወት አንዱ መገላጫ ነዉ ፡፡ ያለፈተና በአገልግሎት እና በመንፈሳዊ ሕይወት ያለፉ ቅዱሳን የሉም፡፡ ይህን ሲያስረዳ ቅዱስ ጰዉሎስ 2ኛቆሮ. 11፡22-29 ላይ፡- “—–በድካም አብዝቼ፣ በመገረፍ አብዝቼ፣ በመታሰር አትርፌ፣ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ፡፡ አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ፡፡ ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ። ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ፤ በወንዝ ፍርሃት፣ በወንበዴዎች ፍርሃት፣ በወገኔ በኩል ፍርሃት፣ በአሕዛብ በኩል ፍርሃት፣ በከተማ ፍርሃት፣ በምድረ በዳ ፍርሃት፣ በባሕር ፍርሃት፣ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ፡፡ በድካምና በጥረት፣ ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፣ በረሀብና በራቁትነት ነበርሁ። የቀረዉንም ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው” በማለት ስለ ክርሰቲያናዊ የአገልግት ሕይወት እና የመከራን ጥብቅ ቁርኝት ያስረዳናል ፡፡
የክርስቲያን መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ በድሎት እና በምቾት የተሞላ አይደለም፡፡ ይልቁንም በማያቋርጡ ተጋድሎዎች የተሞሸረ ነዉ እንጂ፡፡ ክርሰቲያናዊ ሕይወት ቅዱሳንን የምንመሰልበት እና ቅዱስ የምንሆንበት ሕይወት ነዉ፡፡ መከራ እና ፈተና የክርሰትና የሕይወት ቅመም ነዉ፡፡ ከጸጋ ወደ ጸጋ ያሳድጋል፣ ያተጋል፣ ያበረታል፣ ለንሰሐ ሕይወት ያበቃል፣ ወደ ጾም እና ጸሎት ይመራል፡፡ ሁል ጊዜ ወደ ቤተ እግዚአብሔርም እንድንሄድ ሕይወታችንን በእርሱ ፍቃድ፣ ትእዛዝ እና ሀሳብም እንድንመራ ያደርጋል፡፡ ያለ ፈተናና መከራ የክርስትና ሕይወት፣ ድኅነት እና ጽድቅ አይገኝም፡፡ መከራ ሲባል ደግሞ ልንችለዉና ልናሸንፈዉ ከምንችለዉ በላይ እንደማንፈተን መጽሐፍ እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነዉ፤ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናዉ ጋር መዉጫዉን ደግሞ ያደርግላችኋል፡፡” (1ኛ ቆሮ እግዚአብሔር
ክርስቲያን ለማመን ብቻ አልተጠራም፡፡ ለማገልገል፣ የቅድስና ሕይወትንም ለመኖር፣ ለመልካም ሥራ እና የእግዚአብሔርንም መንግሥት ለመዉረስ ጭምር ነዉ እንጂ፡፡ ለዚህ ነዉ መጽሐፍ ‹‹እግዚአብሔር ለቅድስና ጠርቶናል›› የሚለን (1ኛ ተሰ.4፡7)፡፡
ዳግመኛም የተጠራነው በስሙም መከራን ለመቀበል እና ለመፈተንም ጭምር ነው፡- ቅዱስ ጰዉሎስ ‹‹ስለ እርሱ መከራን ደግሞ ልትቀበሉ እንጅ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አልተጠራችሁም›› በማለት ያሰተማረንም ይህንን ያስረዳል፡፡ ፊልጵ.(1፡29)
ሁሉም የሚደርስብን ፈተና ግን በእግዚአብሔር ሰለአመንን በመልካም ሥራችን ነዉ ብሎ መዉሰድ ደግሞ አግባብነት የለውም፡፡ ከእግዚአብሔር የሚመጣብን ፈተና ከእምነታችን ጽናት፣ ከፍቅሩ ጥልቀት እና ስፋት፣ ለበለጠ ፀጋ እና ክብር እንበቃ ዘንድ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ጥንካሬ ደረጃ የሚመጣብን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የአባታችን የአብርሃም ፈተና እና የትዕግስተኛዉ አባታቸን ኢዮብ ዓይነት ፈተና ማለት ነዉ ፡፡
ግን በእኛ ስህተት፣ በኃጢአታችን ብዛት፣ ለትምህርት እና ለቅጣትም ጭምር የሚመጣም ፈተና አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ከኃጢአት መመለስ፣ ማዘንና ማልቀስ፣ ንሰሐም መግባት፣ መጾም እና መጸለይም ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ቅዱስ ያዕቆብ፡- ‹‹ማንም ሲፈተን በእግዚዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና፡፡ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብ እና ሲታለል ይፈተናል ፡፡ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፣ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወለዳለች›› በማለት ይመክረናል፡፡ ያዕ. 1፡13.
ስለዚህ ክርስቲያን ሲኖር እንዴት መኖር አለበት? ስንል፡- ‹‹ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፡፡ በበጎነትም እዉቀትን፣ በእዉቀትም ራስን መግዛትን፣ ራስንም በመግዛት መጽናትን፣ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰልን፣ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማች መዋደድ፣ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ›› የሚለንን ቃሉን መሠረት እና የሕይወታችን መመርያ በማድረግ መኖር አለብን፡፡ (2ኛ ጴጥ ፡ 1፡5-8)