dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ንጉሥና ካ ህ ን ሲነጻጸሩ

#በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

💠የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው።

💠ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤ ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው።

💠ንጉሥ ያዝዛል፤ ካህን ግን #ያስተምራል ይዘክራል።

💠ንጉሥ ያስገድዳል፤ ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል።

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ውዳሴ ከንቱን የመሻት መዘዝ !

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ሰው ረስቶ ለትላትል ከመጨነቅ በላይ ምን ከንቱነት አለ ?

" ውዳሴ ከንቱን መሻት የገሃነመ እሳት እናት ናት፡፡ ውዳሴ ከንቱን መሻት እሳቱ ለማይጠፋው ትሉ ለማያንቀላፋው ዓለም መጋቢዋ ናት፡፡ ሌሎች ክፉ ምግባራት በሞት ይገታሉ፡፡ ውዳሴ ከንቱ ግን አንድ ሰው ከሞተ በኋላ እንኳን ሊያደርገው የሚችል የክፉ ክፉ ምግባር ነው፡፡ በመሆኑም ውዳሴ ከንቱ የገሃነመ እሳት እናት ናት እላለሁ፡፡

ሌሎች ክፉ ምግባራት ሰው ሲሞት ይቆማሉ፡፡ ውዳሴ ከንቱ ግን ከሞት በኋላ እንኳ የሚቀጥል ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ የባሰ ምን አለ ልንል እንችላለን? ምን ማለቴ እንደሆነ እነግራችሁ ዘንድ ትሻላችሁን?

እስኪ ወደ መካነ መቃብር ሒዱ፡፡ ቢያንስ አሁን በአካል ባትሔዱ በዓይነ ሕሊናችሁ ሒዱ፡፡ ብዙ የብዙ ብዙ ሐውልቶች አታገኙምን?

አዎ ! እነዚህ ሰዎች ከመሞታቸው በፊት የሚናዘዙት ሀብታቸው ለድኾች እንዲሰጥ አይደለም ፤ ሀብታቸው ብል እንዲበላው ሐውልት እንዲቆምላቸው እንጂ፡፡ በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ለየት ያለ ትርዒት እንዲፈጸምላቸው ነው የሚናዘዙት፡፡

እነዚህ ሰዎች በዘመናቸው ድኾችን ሲሳደቡ የነበሩ ናቸው፡፡ የምድር ትላትል ይበሉት ዘንድ መቃብራቸው እንዲያምር ሲናገሩ ግን ምንም ሐፍረት ቢጤ አይሰማቸውም፡፡ ለሠራተኞቻቸው ደመወዝ ለመጨመር ይንገበገባሉ፡፡ እንዲሁ በከንቱ ለትላትል ለሚያወጡት ገንዘብ ግን እጅግ ይጨነቃሉ፡፡

ወዮ ! በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ሰው ረስቶ ለትላትል ከመጨነቅ በላይ ምን ከንቱነት አለ? ከዚህ የባሰ ክፉ ደዌ ምን አለ?

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

† † †

/channel/dnhayilemikael

💖 🕊

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሰይጣን አንድን ኃጢአት ሊያሠራን ሲፈልግ ቀድሞ ስለ እግዚአብሔር መሐሪነት በሰፊው ይሰብከናል። ያን ኃጢአት ከፈጸምን በኋላ ደግሞ ስለ እውነተኛ ፈራጅነቱና ምንም ቢሆን ከቁጣው የማናመልጥ መሆኑን ከቀድሞው ይልቅ እየጮኸ ይነግረናል። በመጀመሪያው ስብከቱ ኃጢአትን እንዳንቃወም ሰነፎች ያደርገናል። በሁለተኛው ስብከቱ ደግሞ ንስሐ እንዳንገባ ተስፋ ያስቆርጠናል።

ይህ የተገለባበጠ ስብከት "የሰይጣን" ነው። ሰው በኃጢአት ከመውደቁ በፊት ሊያስብ የሚገባው የእግዚአብሔርን ፈታሒነት (ፈራጅነት) ሲሆን በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ግን ማሰብ ያለበት የእግዚአብሔርን መሐሪነት ነው።

ፈታሒነቱ ኃጢአትን እንዳንሠራ ይጠብቀናል፤
መሐሪነቱ ንስሐ እንድንገባ ያቀርበናል፤

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#እግዚአብሔር_ምን-ሰራሽ_እንጂ_ምን_ለበስሽ_አይለኝም


💠ብዙ ጊዜ አንዳድ እህቶቻችን ሱሪ ወይም ቅርፅን የሚያሳይ ወይም ቅዱስ ገላቸዉ የሚያሳይ ልብስ አትልበሱ ሲባሉ
፣የሚመልሱት ነገር ቢኖር ይህ ቃል ይመልሳሉ፦እግዚአብሔር ምን ሰራሽ እንጂ ምን ለበስሽ አይለኝም ይላሉ፣
💠እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል።"እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም እቀጣለዉ።(ትን ሶፎ 1÷18)
ታዲያ አምላካችን እንዲህ ካለን እኛ እራሳችን ተሰናክለን ሌሎችስ በምን ሁኔታ ይሰናከሉ? ዳግም እንዲህም ይላል

💠ከነዚህ ከተናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለዉ ነበር።(ማቴ 16÷8)እንግዲያዉስ የሴቶች ምርጫ ወይስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንቀበል? እንግዲያዉስ ምርጫዉ ያንቺዉ ነዉ

💠ከሰዉ ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።(የሐዋ 5÷29)

💠ሴትም የራስዋ የሆነ ልብስ ልትለብስ ይገባል፣ወንድም የራሱ የሆነ ልብስ ሊለብስ ይገባል።
#ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፣ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህ የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነዉ።(ዘዳ 22÷5)ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት በሚገባ ስረአት ታስተምራለች

💠ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም።(1ኛ ቆሮ 11÷16)

💠ቅዱስ ጳዉሎስ እንዳለዉ ስህተት መሆኑን መናገር እንጂ መከራከር አያስፈልግም ክርስትና በምርጫ ነዉና።

💠በፊትህ እሳትና ዉሃ አኑሬአለሁ ወደ ወደድከዉ እጅህን ክተት
።(ሲራክ 15÷15)

💠ደግሞ ክርስትና እራስን ወዳድነት አብዝታ ትጠላለች ምንም ነገር ስናደርግ ስለ ሌላኛዉ ሰዉ ልናስብ ይገባል እኛስ ሰዉን ወደ ዝሙት ሊያመራዉ ስለሚችል አለባበሳችን እጅግ ተጨንቀን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል ፣ቅዱስ ጳዉሎስ ስለማሰናክል እንዲህ ሲል ተናገረ

💠መብል ወንድሜን የሚያሰናክለዉ ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክለዉ ለዘላለም ሥጋ አልበላም
።(1ኛ ቆሮ 8÷ 13)
💠ስለዚህ ስለ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ልናስብላቸዉ ይገባል ለእነሱ መሰናከያ እንዳንሆን እየተጠነቀቅን እያስታወስን የምናደርጋቸዉ ተግባራት በሥረአት ማደረግ ይኖርብናል

💠የመጨረሻ መልዕክቴ ሱሪ ዉስጤ ነዉ ሱሪ ከልጅነቴ ጀምሮ ነዉ ምለብሰዉ የምትሉ ሴቶች በእዉነት ማስተዋል ሲያቅተን ነዉ የእግዚአብሔር ቃል እያወቅን እንደአላወቀ በድፍረት መጠቀም ምን ይሉታል?

💠 አምላክ እኮ እንደ ሰዉ የዉጪ ዉበት ብቻ ሳይሆን እስከ ልብና ኩላሊት የሚመረምር አምላክ ነዉ ታዲያ አምላክን ማታለል ይቻላልን???
💠 እርሱ አንቺዉ መርምሪዉ ሰዉ ከሞትኩ በዃላ በምን አዉቃለህ ይላል ነገር ግን አስተዉለህ የምታቀዉ ነፍስህ ከሥጋህ ሲለይ እንደሆነ አስተዉል ያኔ ምነዉ ክፉ ባልሰራሁ ምነዉ ትዕዛዙ በጠበኩ ብላ የምትጮኸዉ ነፍሳችን ናት የዛኔ ነፍሳችን በሰማይ በክበር በዙፋን ላይ የተቀመጠዉ አምላክ ሲጠይቃት ነዉ የምናስተዉለዉ ስለዚህ ሥጋ ትሞታለች እንጂ ነፍስ አትሞትምና ነፍስሽን አድኛት አድናት ያለፈዉ ዘመን በቅቶን ወደ ንስሃ እንገስግስ እህት ወንድሞቼ።

በቃሉ የምታምኑ ብቻ አንብባችሁ share♥
ከሰዉ ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባል እንደ ሰዉ ቃል ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል መኖር ተገቢ ነዉ ቸሩ መድኃኒአለም ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይፍጠርልን🙏

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ገንዘብ ይመገቡ። ዲያቆናትን ያክብሯቸው። ዲያቆን ቀሳውስትን ያገልግላቸው። ከሕዝቡ ወገን ጠያቂ የሌላቸውን ድውያንንም በመጠየቅ ያገልግላቸው። ለኤጲስ ቆጶሱም ችግራቸውን ይንገረው።
_
፬) ዲያቆኑ በቤተክርስቲያን ሕዝቡ እንዳይተኙ እንዳይስቁ እንዳይዘባበቱ ይጎብኛቸው። ዲያቆን ደሙን በቄሱ ትእዛዝ ለምእመናን ያቀብል። በመዓርግ ከእርሱ ለሚበልጥ ደሙን አያቀብል። ኤጲስ ቆጶስ ቄስ ባይኖር በምሳ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት ደግሞ ባርኮ ይስጥ። ዲያቆን ያስተምት ያጠምቅ፣ ሥጋውን ደሙን ያቀብል ዘንድ፣ ሕዝብን ይባርክ ዘንድ አይገባውም። ዲያቆን ዓውዱን አይያዝ።
_
፭) ሊቀ ዲያቆን በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ከኤጲስ ቆጶስ ቀጥሎ ይቁም። ከኤጲስ ቆጶሱ ብቻ በቀር ሌላ በበላዩ አይፍረድ አይቀመጥ። እስመ ውእቱ ሊቀ ካህናት። የካህናት አለቃ ነውና።
_
፮) ዲያቆናት ሆይ የተቸገሩትን ልትጎበኟቸውና የተቸገሩበትንም ነገር ለኤጲስ ቆጶሳችሁ መንገር ይገባችኋል።
_
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ነገረ ትንሳኤ ክርስቶስን አስመልክቶ ብዙዎች የሚያነሱት ጥያቄ

#ጥያቄ ክርስቶስ፥ በከርሰ መቃብር፤ ሦስት መአልት ሦስት ሌሊት እንዴት ሊሞላው ቻለ?         ክርስቶስ ሦስት መአልት ሦስት ሌሊት፣ በከርሰ መቃብር አደረ፤ የሚባለው፥ እንዴት ሆኖ ነው? (ለሚለው ጥያቄ፥ ምላሹ በሁለት ዓይነት አረዳድ እንገነዘባለን)

አንደኛው
        1/ ፩፤ ለዚህ ምላሽ የዕብራውያንን አቆጣጠር ማወቅ ያስፈልጋል:: የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢር ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት የዕብራውያንን ሥርዓት ወግና ጂኦግራፊያዊ (መልክአ ምድራዊ) አቀማመጥ ያስፈልጋል።

        👉 ምክንያቱም፥ ጸሐፊዎቹ ባህላቸውንና ሥርዓታቸውን ጠብቀው የጻፉት ስለሆነ ነው
👉 ጌታ ዓርብ ተሰቅሎ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ከተነሳሣ እንዴት ብሎ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይሞላል ሊያሰኝ ይችላል።

      💠   በዕብራውያንን አቆጣጠር ሌሊት የሚቆጠርው በዋዜማው ካለው አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው።
💠 ከአሥራ አንዱ ሰዓት በፊት ያሉት ሰዓቶች ግን አንድ ሰዓትም ቢሆን እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል። ጌታ የተቀበረው ዓርብ ከአሥራ አንድ ሰዓት በፊት ስለሆነ የተቀበረበት ሰዓት የዓርብን መዓልትና ሌሊት ያጠቃልላል።

      💠   አርብ ከሠርክ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ አሥራ አንድ ሰዓት ከሰዓት በዋላ ድረስ ያለው የቅዳሜ መዓልትና ሌሊት ነው።

👉 ቅዳሜ ከአሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ያለው እሑድ ነው። አንዱም ሰዓት ቢሆን ከላይ እንደ ተገለጠው የዕለቱን ሰዓቶችን ያሟላል። ጌታም የተነሣው እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ስለሆነ ሦስት መዓልት ሶስት ሌሊት ይሆናል።


ሁለተኛው
       2/፪፤
በጌታችን ላይ የሞት ፍርድ ከተፈረደበት ጀምሮ እንደ ሞተ በመቁጠር
👉አርብ ጠዋት ከ፲፪ ሰዓት እስከ ፮ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ብርሃን ነበር፤ አንድ ቀን።

        👉 ከ፮ እስከ ፱ ሰዓት በምድር ላይ ጨለማ ሆነ ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፤ ያም፥ ጨለማ እውነተኛ ጨለማ እንጂ በምትሐት የሆነ ስላልሆነ እንደ ሌሊት ይቆጠራል። አንድ ቀን አንድ ሌሊት ይኖረናል።

 👉አርብ ከ፱ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፲፪ ሰዓት እንደገና ቀን ሆኖአል፤ 
👉አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ ያለውን ጨለማ ወይም ሌሊት ስንቆጥር ሁለት ቀን ሁለት ሌሊት ይሆናል።

👉         ቅዳሜ ሙሉ ቀንና ሌሊትን  ለእሁድ አጥቢያ ጌታ እሁድ ሌሊት ተነስቷል፤ አንድ ላይ ሲደመር ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይሆናል።

👉 እንግዲህ በሁለቱም ዓይነት የሚቆጥሩ ስላሉ ሁለቱም ዓይነቶች ቀርበዋል እኛም የገባንና የተረዳንን አቆጣጠር መርጠን ማስረዳትም መረዳትም እንችላለን።

                      <<<<<<<<


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ፖርኖግራፊ አንብቡት🗣 ክፍል አንድ

#ሰዎች_ለምን_ፖርኖግራፊ_ይመለከታሉ?
አንብቡት🗣 ክፍል አንድ


✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታው እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11




🥀ሰዎች ለምን ፖርኖግራፊን አዘውትረው ይመለከታሉ? “ችግሩን መለየት በራሱ የመፍትሄው አንድ አካል ነው” የሚለውን መርህ ይዘን ከብዙዎቹ ምክንያቶች ጥቂቶቹን ለመመልከት እንሞክር።

1. #ደስታን_ፍለጋ

🥀ለዚህ ጥያቄ ግልፅ የሆነውና የመጀመሪያው ምላሽ ሰዎች ማንኛውንም አይነት ፊልም እራሳቸውን ለማዝናናት እንደሚመለከቱት ሁሉ፣ ፖርኖግራፊንም የሚያነቃቃቸው እና ደስ የሚያሰኛቸው ነገር ከመፈለግ አንፃር ማየታቸው ነው።

ከሰው መሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ አንዱ ወሲብ እንደመሆኑ ሰዎች ይህንን ፍላጎት በተገቢው ሆነ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ለማሟላት፣ በገሀዱ አለም እራሳቸው ያላደረጉትን ወይም የማያረጉትን ነገር ግን ስሜታቸው የሚፈልገውን ነገር አይተው በምናባቸው ተሳታፊ ለመሆን ፖርኖግራፊን ይመለከታሉ።

2. #ጭንቀት/#ድብርት

🥀ብዙውን ጊዜ በድብርት እና በጭንቀት ውስጥ ያሉ ሰዎች በፖርኖግራፊ ሱስ የሚጠቁ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ።

በአብዛኛው በፖርኖግራፊ ብቻ ሳይሆን በሌላም የዕፅ ሱሶች የሚያዙ ሰዎች ሱስ የሆነባቸውን ድርጊት ደጋግመው እንዲያረጉ የሚገፋፋቸው ወሲባዊን ደስታን ለማግኘት ያላቸው ፍላጎት ሳይሆን ውስጣቸው ከሚሰማቸው የስሜት መዋዥቅ ማለትም ጭንቀት፣ ድብርት፣ ሀዘን፣ ፍርሃት እና ሀፍረት ለማምለጥ ነው።

🥀ስለዚህ በሕይወታቸው ከባድ ጭንቀት ያለባቸውና ያልፈቱት አስጨናቂ ነገር በልባቸው ያለባቸው ሰዎች ሃዘናቸውን ለመርሳትና ጊዜያዊ ደስታ ለማግኘት ይጠቀሙበታል። በስራ ቦታቸው ላይ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ስራቸውን እየጠሉት የሚሰሩ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል።

3. #ብቸኝነት

🥀ብዙውን ጊዜ ብቸኝነትን የሚያዘወትሩ በተለያየ ምክንያት ከሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ የማይችሉ ሰዎች በዚህ ሱስ ሊጠቁ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ።

​​4. #በጓደኛ_ግፊት

🥀በአብዛኛው ታዳጊዎች እና ወጣቶች ስለ ሩካቤ ስጋ ምንነት ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ወደ ፖርኖግራፊ ሊሳቡ ይችላሉ።

🥀ብዙዎች ወደሚያደርጉት ነገር ወይም ከዚያም ባለፈ በደፈናው ‘አታድርጉ!’ የሚባሉ ነገሮችን የመሞከር ዝንባሌ በወጣቶች ይስተዋላል። ታዳጊዎችና ወጣቶችም በጓደኞቻቸው ግፊት ወደዚህ ህይወት በቀላሉ ሊሳቡ ይችላሉ።

🥀ለ10 አመት ያህል በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለች አንዲት እህት እንዴት ወደዚህ ሱስ እንደገባች እንዲህ ስትል አጫውታኛለች።
አንብቡት🗣

🥀“የዪኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ዶርም ውስጥ ጓደኞቼ ተሰብስበው ፖርን ይመለከቱ ነበር። እኔ ግን ሁሌም እቃወማቸው ነበር። ከሆነ ጊዜ በኋላ ግን ሳላስበው እነሱን መቀላቀል ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ከነሱ የባስኩ ተመልካች ሆንኩኝ።”

5. #ሱስ

🥀አንዳንድ ሰዎች ፖርኖግራፊን በተለያየ ምክንያት አንድ ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ከተመለከቱ በኋላ ሱሰኝነትን ያዳብራሉ። ሱስ ማለት ፈልገን የገባንበት ኋላ ግን እየጠላነውም ቢሆን የምናደርገው ነገር ነው።

🥀ማንኛውም ሱስ ሲጀመር በፍላጎት ሲሆን የሚቀጠለው ግን ያለ ፍላጎት ሊሆን ይችላል። ፖርኖግራፊ ልክ እንደ ማንኛውም አደንዛዥ ዕጽ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከፍተኛ አቅም አለው። በአንድ ወቅት ስለ ፖርኖግራፊ ሱስ ዶክተር ስዩም ያሉትን ልዋስ፤ “ብዙዎች ፖርኖግራፊ ሳያዩ መተኛት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ሱስ አይሆንም ብሎ የመናገር ድፍረት አላቸው::

🥀ነገር ግን ፖርኖግራፊ ከሌሎች ሱሶች ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ መልኩ ወደ ሱስነት ያድጋል። አንድ ሰው ፖርኖግራፊ ሲመለከት ደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች (hormons) አሉ፤ እነዚህ ቅመሞች አንድ ሰው ኮኬንና ሄሮዊን የሚባሉትን አደዛዥ ዕፅ ሲጠቀም በደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች ናቸው።

🥀እኚህን ዕጾች ስንወስድ ደማችን ውስጥ የሚለቀቁት ቅመሞች ፖርኖግራፊ በምናይበት ጊዜ ከተለቀቁ ፖርኖግራፊ ሱስ አይሆንም ማለት አንችልም። ሱስ ለመባል የግድ በአፍ በኩል ወደ ውስጣችን መግባት የለበትም።

🥀አሁን ባለን መረጃ ‘Pornography is not like a drug, it is a drug’ (ፖርኖግራፊ አንደ አደንዛዥ ዕፅ ሳይሆን እራሱ አደንዛዥ ዕፅ ነው) እንዲያውም መልከ ብዙ ዕፅ ነው።

🥀ሰው ፖርኖግራፊ ሲያይ ብዙ ዕፅ በአንድ ላይ እንደወሰደ ይቆጠራል። አንድ የኒዩሮ ሳይንቲስት (neuroscientist) ባለሙያው በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሚፈጅበትን ጊዜ ሲናገሩ አንድን ምስል ለግማሽ ሰከንድ ካየን በኋላ በሚቀጥሉት 5ና 10 ደቂቃ ውስጥ አንጎላችን ውስጥ መሰረታዊ የሆነ የቅርጽ ለውጥ (nerve restriction) ይፈጠራል።

🥀ይሄ አይነት ለውጥ ልክ አንድ ሰው አደጋ ሲደርስበት የሚፈጠረውን የቅርጽ ለውጥና አይነትን ነው። በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሰከንድ 1/3ኛ ይበቃል እንደማለት ነው:: አስተውላችሁ ከሆነ ለሰከንድ ያየነው የፖርኖግራፊክ ምስል ለአመታት ከአይምሮአችን አይወጣም።

🥀ለምን ካላችሁ ‘epimerphine’ በተባለው ‘ሆርሞን’ ምክንያት እንዳይጠፋ ሆኖ ተቀርጿል:: ከዚህም የተነሳ ከአመታት በኋላ እንኳን አይረሳም። በዚህም ምክንያት ‘በቃ አይኔንም ስከድን ስተኛም በመንገድ ላይ ስሄድም የሚመጣብኝ እሱ ነው’ እያሉ በመንፈስ ጭንቀት የሚሰቃዩ ወጣቶች ገጥመውኛል።”

🥀ከዚህ የምንረዳው በቀላሉ የሚጀመር ነገር እንዴት ወደ ትልቅ ሱስ ሊያድግ እንደሚችል ነው።

ይቀጥላል
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
ቴሌግራም ተቀላቀሉ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#እሺ_ምን_እንዳመጣልህ_ነው_የምትፈልገው?


በአንድ ወቅት አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ቆሞ ጌታየ ሆይ! አንተ ከእኔ ምን ትፈልጋለህ? ምንስ ባደርግልህ ደስ ትሰኛለህ?...እስቲ ንገረኝ ረጅምና በቁመቴ ልክ የሆነ ከሰም የተሰራ ሻማ እንዳመጣልህ ትፈልጋለህ? አለው። ጌታም መልሶ "ለሻማው መስሪያ የሚሆነው ሰሙም የእኔ ነው፤ ሰሙ የሚገኝበት የማር እንጀራውም የእኔ እኮ ነው"አለው።



ያም ሰው ቀጥሎ "እንግዲውስ ድሆችን ለመርዳት ይሆን ዘንድ 1000,000 ብር እሰጥሃለሁ አለው። ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "
አንተ አለኝ ያልካቸው ነገሮች ሁሉ የእኔ ናቸው፤ ምድርና መላዋ ለእግዚአብሔር ናት ፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። መዝ.24:1) አለው።

ሰውየውም እንዲህ አለ " ጌታዬ ሆይ እሺ ምን እንዳመጣልህ ነው የምትፈልገው?

ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ፣ ስለአንተ ብየ ተጠምቻለሁ ፣ ስለአንተ ፍቅር መስቀል ላይ ወጥቻለሁ አለው።

እግዚአብሔር ካለን ነገር በፊት እኛን ይፈልገናል። ራሳችንን ሳንሠጠው ብንደክም ብንለፋ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው" (ሉቃ. 10:42) ይለናል ይህም ልባችንን ለእርሱ በቃሉ ለመኖር መሥጠት ነው።

እውቀታችንን ሠጥተን ፣ ገንዘባችንን ሠጥተን ፣ ጉልበታችንን ሠጥተን እኛ የእርሱ ካልሆንን ምን ይጠቅማል? ኃጢአት ከእርሱ ለይታናለችና ፣ በንስሐ ልባችንን እንዲንሠጠው በመንፈሳዊ ምሥጢራት ከእርሱ ጋር አንድን እንድንሆን ይሻል። ራሳችንን በንስሐ አቅርበን ልባችንን ለፈጠረን አምላክ እንስጠው።
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ከቤተክርስቲያን ውጭ ጋቢቻ ቢፈጸም ምን ችግር አለው ?

✅በቤተ ክርስቲያን ጋብቻ የሚፈጸመው ድንግልናቸውን ለጠበቁ በተክሊል ስሆን ለሌች ደግሞ በቁርባን ነው

✅ ጋብቻ ፈጻሚዎቹ ደናግል ከሆኑ በተክሊል አንድ ይሆናሉ
ካልሆኑ ደግሞ የመዓስባን ጸሎት ተደርጎላቸው በቅዱስ ቁርባን ይጣመራሉ።
✅#በማለዳ ቤተክርስቲያን ተገኝተው በካህናት ቡራኬ አክሊል ደፍተው፣ ካባ ደርበው፣ ቅብዐ ቅዱስ ተቀብተው የቃል ኪዳን ቀለበታቸውን በቤተክርስቲያን ፊት አሥረው የነገር ሁሉ ማሠሪያ የሆነውን የክርስቶስን ሥጋና ደም ተቀብለው ጋብቻቸውን ይፈጽማሉ።

✅ጋብቻቸው በእግዚአብሔር የተባረከ ቅዱስ፥ መኝታቸውም ንጹሕ ይሆንላቸዋል /ዕብ. ፲፫÷፬

አበው በፍትሐ ነገሥት ስለዚህ ምሥጢር ሲናገሩ - የጋብቻ አንድነት ግን በካህናት መኖር በላያቸው በሚጸልዩት ጸሎት ካልሆነ በቀር አይሆንም አይፈጸምም:

✅ ሁለቱ አንድ በሚሆኑባት በተክሊልም (በቁርባን)
ጊዜ ቅዱስ ቁርባንን ያቀብሏቸዋል

✅ምስጋና ይግባውና ጌታችን እንደተናገረ አንድ አካል ይሆናሉ (ማቴ.፲፱÷፭)

✅ያለዚያ ግን ጋብቻ ተብሎ አይቆጠርላቸውም።

✅ወንዶችን ከሴቶች ሴቶችንም ከወንዶች አንድ የምያደርግ ጸሎት ናትና ብለዋል፡፡
ፍትሐ ነገስት አንቀጽ ፳፬

ስለዚህ ቤተክርስቲያን ያልተፈጸመ ጋቢቻ ተብሎ ካልተጠራ ምን ልባል ይችላል? መልሱን ለእናንተ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም?

አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል? ይፈልጋል🥰
ዲያቆን አቤል ካሳሁን💖💖💖

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ማክሰኞ † ቶማስ
-----------------------------
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ……… በዓቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን ………….አግአዞ ለአዳም
ሰላም ………………………እም ይእዜሰ
ኮነ………………………………ፍስሐ ወሰላም
••••••••••••••••••• † •••••••••••••••••
እንደ ኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሰረት ከትንሣኤ በኋላ ያለው ሁለተኛው ዕለተ ማክሰኞ "ቶማስ" በመባል ይጠራል።

ቶማስ ሐዋርያ ሲሆን፣ ቶማስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው። ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ ፤ እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል።

ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው» አለው። (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች።

ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡

ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡

ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)።

የሐዋርያ ቶማስ መታሰቢያ በዳግመ ትንሣኤ ላይ የሚነሳ ቢሆንም አባቶች በበዓል ላይ በዓል እንዳይደራረብ ብለው ከትንሣኤ በኋላ ባለው በዕለተ ማግሰኞ ቶማስ ተብሎ እንዲጠራ ስርዓት ሰርተውልናል።

የአባቶቻችን በረከት ይደርብን በእውነት። በዓሉንም በዓለ ደስታና በዓለ ፍስሐ ያድርግልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም ቀን!!!!

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

​​🤗ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

⚡⚡⚡ሰኞ
⚡⚡⚡

👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጾሙስ አበቃ.....?


✅ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን?
ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው?
✅ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው?
✅ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው?
✅በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተሰቅሎ ሞቶ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቶ የኃጢአት እዳችን ተወገደ ሰውና እግዚአብሔርና ታረቁ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው?
✅መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው።
✅ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት።
✅ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት?
✅ምን ንብረት ተመደበላት?
✅ምን ሙክት ተገዛላት?
✅ምን ወይን ተጠመቀላት?
✅ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት?
✅ እነማንን ድግሥ ጠራንላት? ✅አጋንንትን ወይስ መላእክትን?

ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል።~ የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል ~የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። ~በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ~ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!

አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል።
✅ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው።
✅ ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል።
✅ ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?

✅የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው?
✅የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው?
✅መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!

✅ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ ..ተሰቀለ ሞተ ተነሳ አዳነን። ✅የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? ✅በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ!

✅ጸሎቱ ቀጠሮ 🛐ጾሙ ቀጠሮ 🛐ትጋቱ ቀጠሮ 🛐አሥራቱ ቀጠሮ 🛐ኑዛዜው ቀጠሮ🛐 መታረቁ ቀጠሮ
🛐ቁርባኑ ቀጠሮ 🛐ሁሉ ቀጠሮ!
✅ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ

✅የዐቢይ ጾም ፍጻሜ ጌታ ተነሳ። እኛም ከኃጢአት በንስሐ እንድንነሳ ይርዳን።
✅ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከሲኦል አወጣን። ከጾማችን ፍጻሜ እኛም ከኃጢአት እንውጣ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። @dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

👉🏻 ረቡዕ || ሰሞነ ሕማማት
••
1. ምክረ አይሁድ ይባላል
••
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል።
••
የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
••
2. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል ፦

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት / ባለ ሽቶዋ ማርያም / « ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ » ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ አልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ / በራሱ / ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመዓዛ ቀን ይባላል።
•••
3. የእንባ ቀን ይባላል

ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። ጌታ ሆይ መከራህን ስቃይህን ረሃብ ጥማትህን ሞትህን እያሰብኩ የማነባበት እንባ አብራህ ስለተንከራተተችው በመስቀል ላይ ሳለህም አንዴ ከድንጋይ አንዴም ከእሾህ ላይ እየወደቀች እየተነሳች ወየው አንድ ልጄ እያለች ስታነባ በነበረችው በአዛኝቱ እናትህ ስጠኝ አቤቱ ይቅር በለኝ ኢትዮጵያን ተዋሕዶን አስባት ኪርያላይሶን!
••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
••
👉🏻 @dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+++"@dnhayilemikael
እጅግ ጥልቅ የጸሎት ሕይወት የነበረው፣ አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ የሚጾመው ተሐራሚው ቅዱስ አባ ጳጉሚስ ከእለታት በአንዱ ቀን ይህን ተመለከተ፡፡ ቅዱሱ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር አብዝቶ ይሰግድ ነበር፡፡ ከዓይኑ የሚወርደው እንባ ከሰውነቱ ወዝ ጋር እየተቀላቀለ ወደ መሬት በመውረዱ ምክንያት የሚሰግድበትን ቦታ አረጠበው፡፡ አባ ጳኩሚስም ይህን ወደ ጌታው እያመለከተ "ይኸው አንተን አገኝ ብዬ እንዲህ እደክማለሁ" ሲል ተናገረ፡፡ በዚህ ጊዜም መድኃኒታችን ለአባ ጳጉሚስ ተገልጦ "እኔም እንጂ ላንተ ብዬ እንዲህ ሆኜ ተሰቅያለሁ" በማለት በእለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሆኖ የተወጋ ጎኑን፣ የፈሰሰ ደሙን አሳየው፡፡ ቅዱሱም የጌታው ሕማም ከሕሊናው በላይ ሆኖበት ወድቆ ምሕረትን ለምኗል፡፡

+++++++++++++

ሕሊናቸው የክርስቶስን ሕማም ከማሰብ አቁሞ የማያውቀው አባ መብዓ ጽዮን መድኃኔዓለምን :- ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፡፡ ስለ ራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ›› ሲሉ ለመኑት፡፡ ጌታም ‹‹መከራ መስቀሌን ለማየት ትፈቅዳለህን?›› ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮንም ‹‹አዎ! አይ ዘንድ እወዳለሁ›› አሉት። ያን ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ታየ፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር። እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ታያቸው። ይህን የመድኃኔዓለም መከራ የተመለከቱ የጻድቁ ዓይኖችም ፈዝዘው እስኪጠፉ ድረስ ትኩስ እንባዎችን ሲያዘንቡ ኖረዋል።

‹‹ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ›› - ‹‹ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው!››

✍🏿 @dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሰላም ለሁላችሁ ፦አንድ ወጣት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው። የጌታዬን ሥጋ በልቼ ደሙንም ጠጥቼ ተመልሼ ደግሜ በኃጢአት ወድቃለሁ ምን ይሻለኛል? አላቸው። እርሳቸውም ሲመልሱ የለም በኃጢአቴ ስወድቅ በሥጋው እነሳለሁ ደግሞ ስወድቅ በደሙ እነሳለሁ ብለህ እመን አሉት።
እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#እኔ_በሕይወት_ዘመኔ_ሦስት ነገሮችን ሳስብ እፈራለሁ።

❶ ነፍስ ከስጋዬ የምትለይበትን ሰዓት ፤
❷ ወደ እግዚአብሔር ፊት እንድቀርብ መላእክት በሚወስዱኝ ሰዓት ፤
❸ ከፈጣሪም አንደበት የፍርድ ቃል ለመስማት በፊቱ የምቆምባትን ሰዓት ፤
/ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ/

🥀†አቤቱ በመንግስት አስበን መልካም ስራ ለመስራት አብቃንአሜን🤲
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ፖርኖግራፊ

ክፍል 3

#የፖርኖግራፊ_መዘዞች

ፖርኖግራፊ መመልከት የሚያስከትለው እጅግ በጣም ብዙ መዘዞች አሉት። ጉዳቶቹም መንፈሳዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ናቸው። እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት።

1. #ከልዑል_እግዚአብሔር_ይለያል

በክርስቶስ የተጠራነው ንፁህ እና ቅዱሳን (1ጴጥ 1:10) እንድንሆን እንደመሆኑ በድብቅ የምንሰራቸው ማናቸውም ኃጢያቶች በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንድንደክም ያደርጉናል።

💠በፖርኖግራፊ ሱስ ላለ ሰው መፀለይ፤ ቃሉን ማንበብ እና ከሌሎች ክርስትያኖች ጋር ህብረት ማድረግ ከባድ ይሆናል። በዚህ ሱስ ከተጠቁ ወገኖቼ በተደጋጋሚ ከሰማዋቸው ድምጾች ዋነኛው፤ “መጸለይ አልቻልኩም፤ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ከበደኝ፤ ምክንያቱም ፊቴ ላይ የሚመጣው የተመለከትኩት ፖርኖግራፊ ነው” የሚል ነው።

💠ሀሳቡ ከሌላው ሰው የተደበቀ ስለሆነ ብዙ ትኩረት ባይሰጠውም ተጨባጭ ሀጢያት ከመሆን አያግደውም። ፖርኖግራፊ መመልከት ኃጢያት መሆኑ ግልፅ ነው። ጌታችን ኢየሱስ “ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል” (ማቴዎስ 5:28) እንዳለ እናስታውስ።

💠እኔ ፖርኖግራፊ አይቼ በፍጹም አልመኝም የሚል ይኖር ይሆን? አንድ ሰው ፖርኖግራፊ እያየ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ተሰጥቻለሁ ማለት አይችልም። ምክንያቱም በማቴ 6:24 ላይ እንደሚናገረው አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች ሊገዛ አይችልም። የስጋን ፈቃድ እየፈፀሙ ክርስቶስን ለማምለክ መሞከር ትርፉ ብቸኝነት፤ ተስፋ መቁረጥ እና ውድቀት ነው።

💠ፖርኖግራፊ መንፈሳዊ ሕይወትን የሚያኮላሽ ነው። ሰው መንፈሳዊነቱን ካጣ ደግሞ ምንም ነገር ቢያገኝ አይረካም። ፖርኖግራፊ ዋና ነገሮቻችንን ያሳጣናል።

2. #ድብርት_ጭንቅት

💠ፖርኖግራፊ ውስጥ የገባ ሰው ያለበት ሕይወት ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል። ስለዚህ ከባድ የሆነ ጭንቀት ይሰማዋል። ብዙ ሰዎች በዚህ ምክንያት ሀፍረት ስለሚሰማቸው በራስ መተማመናቸውን ያጣሉ። ስለዚህ በከባድ የድብርት ስሜት ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ከሰው ያገላሉ።

​​3. #አቅምን_ይገላል

💠በዚህ ሱስ የተያዘ ሰው በቀን ውስጥ በትንሹ 3 ሰዓት ፖርኖግራፊ በመመልከት ሊያጠፋ ይችላል። ምን ያህል የከበረ ጊዜውን እንደሚያጠፋም አስተውሉ! ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ሱስ መጠቃት ኃላፊነትን ቸል ወደማለት ያደርሳል። የፈጠራ ችሎታን ይቀንሳል።

💠በፖርኖግራፊ ምክንያት የአፈጻጸም ብቃታቸው ወርዶ ከስራና ከትምህርት የተባረሩ ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም። አስደናቂና ዕምቅ ችሎታ ያላቸው ስንቶችን በፖርኖግራፊ ምክንያት አጥተናቸዋል?

4. #ላልተፈለገ_ተግባር_ያጋልጣል

💠ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሕጻናትን ከደፈሩ ሰዎች ብዙዎቹ በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቁ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ከማይመለከቱት ጋር ሲነጻጸሩ በ40% ሴተኛ አዳሪዎች ጋር የመሄድ ዝንባሌ አላቸው።

💠የተመሳሳይ ጾታ ፖርኖግራፊ በመመልከታቸው ብቻ ወደ ግብረ ሰዶማዊነት የገቡ ሰዎች እንዳሉም ለማየት ችያለው።

💠ብዙውን ጊዜ በፖርኖግራፊ ምስሎች ላይ ሴቶች የወንዶች የሩካቤ ፍላጎት አገልጋይ ተደርገው የተሳሉ ሲሆን ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ወንዶችም ልክ እንደዛው ሴቶቹን እንደሚመልከቱ ያስባሉ። ሴቶች ደግሞ ሁሉም ወንዶች ለስሜታቸው ብቻ የሚኖሩ እንደሆኑ እንዲያስቡ እንዳደረጋቸው ያምናሉ። በዚህ የተሳሳተ አመለካከት ምክንያት ጤናማ የሆነ የፍቅር ህይወት ለመጀመር የተቸገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

6. #ትዳርን_ይበጠብጣል

💠ከሀገር ውጪ የሚኖር አንድ ሰው ደውሎ እንዲህ አለኝ፣ "እኔ በፖርኖግራፊ ሱስ ከተጠቃሁ አንድ ዓመት ሆኖኛል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ ችግር ገጥሞኛል። በስራ ሰአቴ ላይ ረጅም ጊዜ የማጠፋው ፖርኖግራፊ በመመልከትና ግለ ወሲብ በመፈጸም በመሆኑ እቤት ስገባ ከባለቤቴ ጋር ግንኙነት የማድረግ ፍላጎት የለኝም።”

የዚህ ሰው ችግር የብዙዎችም ነው። ‘ፖርኖግራፊ’ የሚመለከቱ ሰዎች በትዳራቸው ያላቸውን እርካታ ያጡታል። የግንኙነት መቃወስም (Sexual Dysfunction) ሊያጋጥማቸው ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ ፍቺ እና የቤተሰብ መበተን እስከማምራት ይደርሳል።

ክፍል 4 ይቀጥላል
ቴሌግራም ተቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#የፖርኖግራፊ

ክፍል ሁለት


#የፖርኖግራፊ_ሱሰኝነት_ምልክቶች
አንብቡት🗣

1. #ከፍተኛ_ፍላጎት

አንድ ሰው ሱስ ደረጃ ላይ ከደረሰ ለፖርኖግራፊ ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረዋል። በውስጡ የማያቋርጥ ፍላጎት ይቀጣጠላል። በማንኛውም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ በማንኛውም ሰአት ፖርኖግራፊን መመልከት ይፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከትበትን ጊዜ እየጨመረ ይመጣል። በሳምንት ያይ የነበረ በቀን፤ በቀንም አንዴ ያይ የነበረው ሁለቴ ማየት ከጀመረ፣ በፖርኖግራፊም የሚያጠፋውም ጊዜ እያደገ ከመጣ፤ በሚመለከትበት ጊዜ የሚሰማው መነቃቃት እና ደስታ በሀፍረት፤ ጥፋተኝነት ስሜት እና ፀፀት ሲተካ ነገሩ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ይጠቁማል።

2. #ለማቆም_አለመፈለግ / #አለመቻል

ሱስ ውስጥ የገባ አንድ ሰው ፖርኖግራፊ መመልከቱን ማቆም አይፈልግም። ሱስ እንደሆነና ችግር መሆኑን እንኳን መቀበል አይፈልግም። ይህም የሚሆነው ሱስ ውስጥ ስለገባና ከዛ ህይወት ቢወጣ ሌላ የሚያዝናናው ነገር ሊያገኝ እንደሚችል ስለማያምን ነው።

በሌላ መልኩ ደግሞ ለማቆም እየፈለጉ
አለመቻልም የሱሰኝነት ማሳያ ነው። እዚህ ጋር አንድ ወንድም በድምጽ ባስቀመጠልኝ መልዕክት ውስጥ “እኔ ከፖርኖግራፊ ሕይወት ለመውጣት ከ100 ጊዜ በላይ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር፤ ነገር ግን ተመልሼ እዛው ሕይወት ውስጥ እገኛለው” ብሎኛል። ይህ ንግግር የሚያሳየው ከባድ የሆነ ሱስ ውስጥ መግባቱን ሲሆን እየተጸየፍነውም የምናደርገው ነገር ሱስ እንደሆነብን ያሳያል። /channel/dnhayilemikael

3. #በሌላ_ነገር_ደስታ_አለማግኘት

አንድ ሰው ወደዚህ ሱስ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ያስደስቱት የነበሩትን ነገሮች ለምሳሌ ከቤተሰብና ከወዳጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ወደ ኃይማኖት ስፍራ መሄድ፣ ስፖርት መስራት፣ ፊልም ማየት፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወ.ዘ.ተ በመተው ደስታውን ሙሉ ለሙሉ በፖርኖግራፊ ላይ ካስቀመጠ ይህ ሰው የፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ እንደገባ ያሳያል።

​​4. #ከተጽኖው_ጋር_መቀጠል

በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ ሰው በሱሱ ምክንያት ብዙ ነገር እንዳጣ እያወቀ ህይወቱ ወደተሳሳተ አቅጣጫ እያመራ መሆኑን እየተረዳ በዛው ከቀጠለ ሱስ ደረጃ ላይ ለመድረሱን ያሳያል።

5. #ሚስጥራዊነት

በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለ ሰው ህይወቱን አጠገቡ ካሉ እና ከሚወዳቸው ሰዎች ሚስጥር ከማረጉ የተነሳ ድብቅ እና ሁለት ገፅታ ያለው ባይተዋር ሰው እንደሆነ ይሰማዋል።

ሚስጥሩም እንዳይጋለጥ ያያቸውን ድህረ ገፆች በማጥፋት፤ የት እና ምን ያደርግ እንደነበር ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ሰዎችን ይዋሻል። የሚሰማውንም ሀፍረት ለመሸፈን በማስመሰል ህይወት ውስጥ ይዘፈቃል።

#ኃላፊነትን_አለመወጣት

ብዙ ሰዓታትን በፖርኖግራፊ ከማሳለፍ የተነሳ በአግባቡ ስራን አለማከናወን፤ የቤተሰብ፤ የማህበራዊና መንፈሳዊ ሐላፊነቶችን መወጣት አለመቻል እና ገለልተኝነት ሱስ ደረጃ ላይ መደረሱን ያሳያል።

7. #የፀባይ_መቀያየር

በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ባጡ ጊዜ በጣም ብስጩ ፤ ቁጡ እና በጥቂት ነገር የሚናደዱ ይሆናሉ።

ከላይ የጠቀስናቸው ዋና የሚባሉት የሱስ ምልክቶች ሲሆን እነዚህ ምልክቶች የሚታዩባቸው ሰዎች ቆም ብለው ራሳቸውን አይተው ዕርዳታ ካልፈለጉ ለፖርኖግራፊ ሱስ መዘዞች ራሳቸውን ያጋልጣሉ።

ይቀጥላል .....


/channel/dnhayilemikael

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

በእንተ ዲያቆናት

✝️ 📚 @በእንተ ዲያቆናት(ስለ ዲያቆናት) የቅድስትና ሐዋርያዊት ኵላዊት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ይላሉ? ❓

💒 ፩. ዲያቆንም ኾነ ቄስ ሰሞነኛም ይኹን አይኹን፤ ለመቀደስም ኾነ ለጸሎት ቤተ መቅደስ ውስጥ መግባት ያለባቸው ሌሊት ነው። ሥርዐተ ቅዳሴ እንዲህ ይላላል፦

👌 "ሌሊት ለጸሎት ያልመጡ ቀሳውስትና ዲያቆናት ወደ ቤተ መቅደስ ይገቡ ዘንድ ያገለግሉም ዘንድ አይገባቸውም። ይኽን ትእዛዝ ቢደፋፈሩ ግን ከሕግ ትእዛዝ የወጡ ይኾናል።" [ሥርዐተ ቅዳሴ]

💒 ፪. ብዙዎቹ ዲያቆናት ልብሰ ተክህኖ ለብሶ መቀደስ፥ ሰዓታትና ማኅሌት መቆምና በንግሥ ሰዓት መስቀልና ቃጭል ይዘው ቅድመ ታቦት መኼድ እንጂ የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር መረዳት የስብከተ ወንጌል ግብር ብቻ ይመስላቸው። 🙅ፍጹም ስሕተት ነው።

💒 ከመቀደስ ባለፈ እውነተኛውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት መማር፥ መረዳት፤ ከክህደት ትምህርት አንጥሮ መገንዘብም የመለየት ኃላፊነት አለባቸው።

💢 ➺ቅጥረኛ ስለኾንኩ እንጂ...በሚል ሳይፈልገው የሚቀድስ፦ ከታማኝ አገልጋይ ጋር ምን አንድነት አለው? ❓

➾ቅባት ከተዋሕዶ ጋራ፥ ኑፋቄ ከአሚን(ከእምነት) ጋራ፥ ምርግትና ከጥንቆላ ጋራ፥ አውደ ነገሥት ከፍትሐ ነገሥት ጋር፥ ክህደት ከእውነተኛዋ ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ትምህርት ጋር፤ ምንም ኅብረት እንደሌላቸው አንጥሮ፥ ኵልል አድርጎ የመረዳት የማስረዳትም ግዴታ አለባቸው። ለዚኽም ነው፦

💒 "የቤተ ክርስቲያን መብራት አገልጋዮቹዋም የምትኾኑ ዲያቆናት ኾይ ተኵላ ከበግ ጋራ፤ ጭላት(ጭልፊ) ከርግብ ጋራ፤ ክርዳድ ከስንዴ ጋራ እንዳይኖር ከውስጥዋ ንቀሉ፤[ቅዳሴ አትናቴዎስ] እንዲል።

💒 ፫. ደጀ ሰላም፦ የሰላም ደጅ ናት።

የዲያቆናት አብነት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ መጽሐፈ ገድሉ ላይ "የቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ አምላክ እግዚአብሔርም የዚኽን ሰው የንስሓ እንባ ተመልክቶ ይቅር አለው። ይኽ ሰውም በዚያች ቤተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም ተቀምጦ የደረሰበትን ለሚገባውና ለሚወጣው ኹሉ መሰከረ።
" [ገድለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ዘወርኃ መጋቢት]

💢 ✍️ አኹንማ የተጣሉ የሚታረቁባት፦ የሰላም ደጅ የተሰኘችው "ደጀ ሰላም" ድረስ ቢራና ዘር ማንዘሮቹ ገብተው "ምን ይኹንልህ?!" ❓ ብለን ግሮሰሪ አደረግነው። በርግጥ መጠጥ ፈጽሞ የተከለከለ ባይኾንም፤ አብዝቶ መጠጣት ግን የተገባ አለመኾኑ ለኹላችንም ግልጽ ነው። ደጀ ሰላም "የሰላም ደጅ" እንጂ 'የቢራዎች ደጅ' አይደለችምና ባይገባ ይመከራል።

💒 ✍️በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ተፈቅደው ነገር ግን ከማይበረታቱ ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው። ፈጽሞ አይጠጣም፥ ርኵስ ነው ባንልም የማይጠጣ የተሻለ አደረገ።

➣"ከስካር ተጠበቁ ሙሴ በኦሪት ዘሌዋውያን እንዳይሰክሩ አዟቸዋል። እንዲሁ እናንተ ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስትና ዲያቆናት መጠጥን ከማብዛትና ከስካር ተጠበቁ፤ መዳራት፣ ዝሙት፣ ስግብግብነት፣ ሰውን መስደብና ማስቀየም፣ መታበይ፣ በሐሰት መማል፣ ብዙ ቁም ነገሮችን መዘንጋትና ሌሎችም ከስካር የሚመነጩ ናቸው።"[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፲፤ ቍጥር 56]

➛"ከስካርና ወይንን ከማብዛት ተጠበቁ፤ ቃለ እግዚአብሔር የሠፈረባቸውን መጻሕፍት መጠጣትን አዘውትሩ እንጂ።" [ዝኒ ከማሁ(Ibid) ቍጥር 57]

💒❤ ፬. የበቁ ዲያቆናት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅድስና ሥጋወደሙን ለመለወጥ ሲወርድ ማየት ይችላሉ።

➤"ካህን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ ላክ ባለጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመስዋዕትነት በቀረቡ ፅዋዕና ሕብስት ላይ መንፈስ ቅዱስ ይወርዳል፤ ዲያቆናት በቅድስና ሥጋወደሙን ለመለወጥ ሲወርድ ማየት ይችላሉ። የዲያቆናት ክብር በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ቅዱስ እስጢፋኖስ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ የክብር ቦታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሊሠጠው እንደቻለ ለነሱም ይሠጣል።"
[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፲፩፤ ቍጥር 33]

💒 ፭. ዛሬ ላይ ዲያቆናት የት ይገኛሉ? ምን ሲያደርጉ ይገኛሉ? ❓
ክቡር ዲያቆን ሆይ! "ዙረታም" ነኝ ካልክ የት መዞር እንዳለብህ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ይመክሩናል።

➣"ዲያቆናት የክርስቲያኖችን የመኖሪያ ቤት ወዳለበት ኹሉ እየዞሩ የተቸገሩትን ኹሉ ይጎብኙ፤ ችግራቸውንም ይመልከቱ። ጥዋትም ኾነ ማታ ምእመናኑ በስንፍና እንዳይያዙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲተጉ ያነቃቁዋቸዋል። በሠርክ በጧትና በማታም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ እየኼዱ ያመስግኑት፤ እግዚአብሔር የዕለት ብርሃን ነው፤ ኹሉንም ይረዳል።"
[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፱፤ ቍጥር 66]

💒 ፮. ዲያቆናት ምንም ዓይነት ጉቦ መቀበል፥ በደም ግባት ማዳላት፤ ድሀን አይቶ ባላየ ማለፍ፤ ዝም ብሎ ስለ ሴትና ወንድ በማውራት ዋዛ ፈዛዛ በመስማት- ነገረ ዘርቅ መስማት የለባቸውም።

➤ "እናንተም የመንጋዎች ጠባቆችና ዲያቆናት ሆይ መማለጃ በመቀበልና ፊት አይቶ በማድላት ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን ታወጡት ዘንድ በደል በሌለው በንጹህ ሰው ላይ ነገር ሥራንና የሐሰት ነገርን ትሰሙ ዘንድ አይገባም። እንደዚህ ያለ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች የዲያብሎስ ወዳጆች ይኾናሉና።"
[መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፲፥ ቍጥር 55]

➣ "ዲያቆናት ድኆች ሳይለምኗቸው ፈቃዳቸውን ሊያደርጉላቸው አገባብ ነው።"[መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፲፮፥ ቍጥር 55]

💒 ፯. ዲያቆን በድቁና የተካነ ካህን ነው። ቄስም በቅስና የተካነ ካህን ነውና በአጠቃላይ ማኅበረ ካህናት አይደለም በfb በሕዝባውያን መዋኛ ገንዳዎች እንዲዋኙና ለሕዝባውያን ገላቸውን እንዲያሳዩና ተገላልጠው እንዲታዩ፥ ቁንጣ፥ ጃፖኒ፣ ጥብቅብቅ የሚያደርጉ አልባሳት አድርጎ ውጭ መታየት ፈጽሞ አይፈቀድላቸውምና.... ❌

👌ጸጉር አቆራረጥንም በተመለከተ ለምዕመናን ሲገልጽ የቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን የሕግና የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው ፍትሕ መንፈሳዊ ወሥጋዊ "በተፈጠርህ ጊዜ እግዚአብሔር በሰጠህ መልክ ላይ መልክ አትጨምር። ያድግ ዘንድ ፀጉርህን አትከባከበው ተላጨው እንጂ አታሳድገው። ወጥመዳቸው ቅርብ የሆነ ሴቶችን ወደ አንተ ያመጣብህ ዘንድ አታሳምረው።

💢ረቂቅ ልብስ አትልበስ፤ ይህች ስሕተትን ታመጣለችና፤ ቀለም የተቀባ ጫማ አትጫማ፤ በጣቶችህ የወርቅ ቀለበትን አታድርግ፤ ይህ ሁሉ የዝሙት ምልክት ነውና። ጠጉርህን ግልስልስ ብጥር አታድርገው፤ አትሠራው፤ " [ፍትሕ መንፈሳዊ፤ አንቀጽ ፲፩፤ ገጽ. 123]
ፍትሐ ነገሥት ክፍል ፯
አንቀጽ ፯ ስለ ዲያቆናት ይናገራል።
፩) ዲያቆናት ጸጥ ያሉ፣ የሚታዘዙ ይሁኑ። ዲያቆናት ሁለት ሦስት ሰዎች መስክረውላቸው ይሾሙ። በአገልግሎት ሁሉ ይፈተኑ። ለሰው የሚያዝኑ የሚራሩ ይሁኑ። በቀለኞች ሳይሆን በቀልን የሚተው ይሁኑ። ቁጡ ብስጩ አይሁኑ።
_
፪) ዲያቆናት ባለጸጎችን ደስ የሚያሰኙ ነዳያንን የሚያሳዝኑ አይሁኑ። አንድነትን ሦስትነትን (ምስጢረ ሥላሴን) ለመማር ለማስተማር ይትጉ። ምዕመናንን በፍጹም ክብር ያክብሩ። ሰውን በማፈር እግዚአብሔርን በመፍራት ይኑሩ። ዲያቆን በአንብሮተ እድ ይሾማል። ቀሳውስት ዲያቆናትም ቆመው ይጸልዩለት።
_
፫) ሰው ተምሮ ከተገኘ ዲቁና በ7 ዓመት፣ በ12 ዓመት መሾም ይችላል። ሀገሪቱ ሰፊ ካልሆነች ሰባት ዲያቆናት ሊሾሙ ይገባል። ሀገሪቱ ሰፊ ከሆነች ኤጲስ ቆጶሱ እንደወደደ ይሹሙ። ዲያቆናት ከቤተክርስቲያን

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ስለ የፖርኖግራፊ አጭር ተከታታይ ትምህርት ተጀመረ ይከታተሉ


#ሰዎች_ለምን_ፖርኖግራፊ_ይመለከታሉ?

#የፖርኖግራፊ_ሱሰኝነት_ምልክቶች ?

#የፖርኖግራፊ_መዘዞች_ምንድናቸው?


#ከፖርኖግራፊ_ሱስ_እንዴት_መውጣት_ይቻላል?

እነዚህን ትምህርቶች ለማግኘት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠/channel/dnhayilemikael💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

" ዳግመ ትንሣኤ"

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተጋር ይሁን እንዴት አደራችው እህት ወንድሞች እንኳን አደረሳችው
ዛሬ ስለ ዳግም ትንሳኤ አንበላችሁ
እንኳን ለዳግመ ትንሳኤ አደረሳችሁ



ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

✅ሰሙነ ሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤን እንድናከብር ቀደም ሲል በዲዲስቅልያ ኋላም በፍትሐ ነገሥት ታዝዟል፡፡ “እስመ ሰሙነ ዐብይ ሰሙነ ሕማማት እንተ ትተልዋሄ ሰሙነ ትንሣኤ ወዘይትፈቀድ ከመ ናእምር እስመ ዘሐመ ናሁ ትንሣአ” ሲል ይገኛል፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፱፤
የሰሙነ ትንሣኤ መጨረሻው ስምንተኛው ቀን ዳግም ትንሣኤ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣው አንድ ጊዜ ነው፡፡

🌹ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?🌹

ዳግም ትንሣኤ የተባለበት ምክንያት፡- በአከባበር፥ በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡
💠የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤ በሙሉ በዚህ ቀን ይደገማል፡፡
ከዚህም ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡
🛐እነዚህም “ፈጸምን አግብዓተ ግብር” ይባላሉ፡፡
💠“ፈጸምነ” የተባለበትም፤ ሰሙነ ትንሣኤ በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡
“💠አግብዓተ ግብር” የተባለበትም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ… እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ” ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ ዮሐንስ ፯፥፬


በተጨማሪም የሐዋርያው ቶማስ ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡
💠ዳግመኛ ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ሳሉ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ሳለ ደጁም ተዘግቶ ሳለ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በመካከላቸው ቁሞ እንዴት ሰነበታችሁ አስታረቅኋችሁ” አላቸው፡፡

💠ሁለት ሰዓት አሳልፎ ስለመጣ “እምድኅረ ሰሙነ” አለ እንጅ፥ በስምንተኛው ቀን ሲል ነው፡፡
💠በመጀመሪያው መገለጡ ያልተገኘው ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤውን አላመነም ነበርና፤ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ እጆቼንም እይ፤ እመን እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው፡፡
💠ቶማስም መለሰ “ጌታዬ አምላኬ ሆይ” አለ፡፡ መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤ መቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ ሆይ “አለ፡፡

💠ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ ሕያዊት ሁና፤ (በሕይወት ትኖራለች) በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ያስቀምጧታል፡፡ በዓመት በዓመት በእምቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ፥ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች፤ ዓመት አገልግሎ ያርፋል፤ እንዲሁ በዓመቱ የሚሾመውን ተራምዳ ትይዘዋለች፤ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡ ይህም የሚያስተምረን የጌታን ተአምራት፤ የሐዋርውን ሥልጣንና ብቃት ነው፡፡ ጌታም ቶማስ ሆይ! ብታየኝ አመንክን? ሳያዩኝ የሚያምንብኝ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡ ዮሐ ፳፩፥፳፬–፳፱

የዋናው ትንሣኤ ሳምንት እሑድ ዳግም ትንሣኤ


🛐በዚች ሰንበት ከላይ እንደተጠቆመው የትንሣኤው ዕለት ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ብሎም ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡
✅ በኋላ ከሔደበት
ሲመጣ የጌታችን መነሣትና እንደተገለጸላቸውም በደስታ ሲነግሩት በኋላ እናንተ አየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን ሰምቼአለሁ ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር?
✅አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ ብሎ አሳየው፡፡
✅እርሱም ምልክቱን በማየቱ፤ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ አመነ፡፡

💠እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ዳግም ትንሣኤ ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል
፡፡ዮሐ. 20-24-30፡፡

💠በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ሁሉ ከቅዳሴው ውጭ ከሚፈጸመው ድኅረ ቁርባን በስተቀር ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ዕለት ሆኖ ይከናወናል፡፡
ለብርሀነ ትንሣኤው ያደረሰን አምላካችን፥ፍጻሜ ሕይወታችን በሃይማኖት የቀናን፤ በምግባር የጸናን ያድርገን! አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

++++++++++++++++++++

/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael

+++++++++++++++++++++

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

☞"ያኔ ማንም ምንም አይጠቅምህም መልካም ስራህ ብቻ" ::



☞"በምትሞትበት ጊዜ በመጀመሪያ ስምህ ይቀየራል ስምህም ሬሳ ትባላለች" እከሌ/እከሊት ሳይሆን ሬሳዉ አልወጣም ወይ ትባላለህ። የቅርብ ሰዉ እንኳን ቢሆን ከጎንህ ሊሆን ይፈራል"

☞ወደ መቃብር ስፍራ ወስደዉ አጣድፈዉ ከቀበሩህ በሗላ ብቻህን ጥለዉህ ለመሔድ ይቻኮላሉ።

☞ ላይጠቅምህ አብሬህ ካልሔድኩ እያለ የሚያለቅሱልህ እንኳን ቢኖር ቀብሮህ ተሎ ይሸሻል።ቀብረዉህ እደተመለሱ ንብረት ካለህ ለመከፋፈል ይጣደፋሉ ። ከሳምንት በሗላ ጭራሹኑ ከምድር ያልኖርክ እስኪመስል ድረስ በአብዛኞቹ ትረሳለህ ።

☞የቅርብ ወዳጆችህ እንኳን ቢሆኑ ሀዘኑ በልባቸዉ ጥቂት ወራት ያክል ቢቆይ ነዉ ።በቃ ምድር ላይ የነበረህ ቆይታ በዚህ መልኩ ይጠናቀቃል ።ፍራሽህ አፈር ትራስህ ደሞ ድንጋይ ይሆናል ይሔዉ ነዉ ።

☞"ያኔ ማንም ምንም አይጠቅምህም መልካም ስራህ ብቻ" ::

☞''በዚች ዓለም ላይ እድለኛ ሰዉ ማለት በህይወት እያለ ወደ ፈጣሪዉ የተመለሰ ሰዉ ነው።🙏"

ሊቀ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ❤
በእዉነት ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን ያቆይልን♦
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አርብ :-ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል።

በዚህ እለት ቤተ ክርሰቲያን በክርስቶስ ደም መመስረቷ ይነገራል።
✅ክርስቶስ ስለ እርሷ እራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አጽንቶ በትንሳኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል የቤተክርስቲያን እራሷ መሰረቷ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት እና በምልዐት ይሰበካል።
✅ቤተ ክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞቹን ነው ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና።



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

በትንሳኤ ማግስት

✍ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመዉን
የዐቢይ ጾምን ጾመን ፣
✅በሰሙነ ሕማማት በጸሎቱ በስግደቱ አሳልፈን ፣
✅የክርስቶስን መከራዉን ሁሉ አስበን ፣ የስቅለቱን ቀን አርብን እንዲሁ የጌታን መከራዉን በማሰብ በመዉደቅ በመነሳት
አሳልፈን ፣
✅ ትንሣኤዉንም እንዲሁ በአክፍሎት በማስቀደስ የክርስቶስን ትንሣኤዉን ካከበርን እና ሰዉነታችን በጾም
በጸሎት አስገዝተን ከቆየን በኃላ ፦
በዓለ ሃምሳ ሲደርስ
🛐ብዙዋቻችን ከቤተክርስትያን እንርቃለን
🛐ጸሎቱን እናቋርጣለን
🛐በሰርክ ጉባኤዉም ይቀዛቀዛል
🛐ለብዙዋቻን በኃጢአት ጭምር
የምንወድቅበት ወቅት ይሆናል
🛐 በዚህ ወቅት ጾም
ባለመኖሩ

~ እንደፈለግን እንበላለን
~ እንዳሻን እንጠጣለን
ይኼ ሲሆን ደግሞ አብዝታ የጠገበች ሰዉነት
✅በጸሎት እና ራስን በማስገዛት ዉስጥ የማንኖር ከሆነ ልንወድቅ
እንችላለን ፡፡ ፦ "ማንም ሰው የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ " እንዳይወድቅ ፩ኛ ቆሮ ፲፥፲፪ ነቀርሳ ይጠንቀቅ።" ይላልና

✅ በብዙ በረከት እና ወደ እግዚአብሔር
በመቅረብ ያሳለፍነዉ የጾም ወቅት በዓለ ሃምሳ ሲመጣ
ራሳችንን ከቤተክርስቲያን አርቀን ወደ ቀደመ በደላችን
እንዳንሄድና እንዳንወድቅ በተቻለ
መጠን 🛐በጸሎት
እና🛐 በመንፈሳዊ ብርታት እየጨመርን ልንሄድ ይገባል
✅ይሄንን እንድናደርግ ሁሌም በቤተእግዚአብሔር
እንድንገኝ እና እንድንበረታ እና እንድንጸና የቅዱስ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ የቅድስት ድንግል
ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን ፡፡

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

⚜️⚜️⚜️ ማክሰኞ ቶማስ ይባላል ⚜️⚜️⚜️

እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን በዓላት ቀኖና መሰረት ከትንሣኤ በኋላ ያለችው ዕለተ ማክሰኞ "ቶማስ" በመባል ይጠራል።

⚜️ቶማስ ሐዋርያ ሲሆን፣ ቶማስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው።ከክስቶስ ትንሣኤ በኋላ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል። ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓንስ ናቸው» አለው (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች።

⚜️ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡ ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡
ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)። መለኮቱን የዳሰሰች እጁ በሕይወት ትኖራለች፤ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር በመንበር ላይ ትኖራለች።

⚜️የሐዋርያ ቶማስ መታሰቢያ በዳግመ ትንሣኤ ላይ የሚነሳ ቢሆንም አባቶች በዓል ላይ በዓል እንዳይደራረብ ብሎ ከትንሣኤ በኋላ ባለው በዕለተ ማግሰኞ ቶማስ ተብሎ እንዲጠራ ስርዓት ሰርቶልናሉ። የአባቶቻችን በረከት ይደርብን በእውነት። በዓሉንም በዓለ ደስታና በዓለ ፍስሐ ያድርግልን።
*@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ የተቀደሰው የሩጫ ውድድር +

እንደ ኢትዮጵያ ያለ ሩጫ ብሔራዊ ኩራት በሆነበት ሀገር መቼም የሩጫ ነገር ብናወራ ሰሚ አናጣም:: ሮጦ ሀገር ማስጠራት : ሮጦ ብዙ ሀብት ማፍራትና ለሀገር መትረፍ የቻሉ ውድ አትሌቶቻችንን በፍቅር እናያቸዋለን:: "በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ" የሚለው ቅዱስ ቃል ለነፍስ ቢነገርም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን "ታገኙ ዘንድ ሩጡ" የሚለው መርሕ "ሮጬ ባለፈልኝ" በሚሉ ተስፈኞች ይተገበራል:: (1ቆሮ 9:24)

ዛሬ ግን በሁለት ሰዎች መካከል የተደረገ ቅዱስ ሩጫ ትዝ አለኝ:: በትንሣኤ ዕለት የተደረገ ቅዱስ እሽቅድምድም በዓይነ ሕሊናዬ መጣ::
ከዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል ሁለቱ የተሳተፉበት ዳኛም ተመልካችም የሌለበት የትንሣኤ ዕለት ሩጫ!!!

ሴቶች ወደ ጌታ መቃብር ደርሰው ሲመለሱ ጌታ በመቃብር እንደሌለ ለደቀ መዛሙርቱ ነገሩአቸው::
ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሔዱ::

"ሁለቱም አብረው ሮጡ፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና አስቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ" ዮሐ 20:4

በዚህ ቀን በተደረገው ቅዱስ ሩጫ የ58 ዓመቱ ጎልማሳ ጴጥሮስ ከ28 ዓመቱ ወጣት ዮሐንስ ጋር ወደ ጌታ መቃብር ሮጡ:: ሐሙስ ማታ ጌታውን የካደው ጴጥሮስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታውን ከተከተለው ዮሐንስ ጋር አብሮ ወደ መቃብሩ ሮጠ::

ጴጥሮስ ሆይ ወደ ጌታህ መቃብር በሩጫ ስትገሰግስ ምን እያሰብህ ይሆን? ሐሙስ በካድከው ጊዜ ቀና ብለው ያዩህ ዓይኖቹ በሕሊናህ መጥተው ይሆን?
ወደ መቃብሩ ስትሮጥ "ጌታ ሆይ በአፌ ክጄሃለሁ በእግሮቼ ግን አልክድህም" ብለህ አስበህ ይሆን? "በባሕር ላይ ያራመድኸው እግሬ : አጎንብሰህ ያጠብከው እግሬ ወደ አንተ ለመሮጥ አይደክመውም" ብለህ ይሆን? መቃብሩ ሥር ተደፍተህ ለማልቀስ የሐሙሱን ዕንባህን በመግነዙ ለማበስ አስበህ ይሆን?

ብቻ ጴጥሮስ ከዮሐንስ ጋር ወደ መቃብሩ ሮጠ:: ዮሐንስ በጉልበቱ ገና ወጣት ቢሆንም : እንደ ጴጥሮስ ጸጸት የማይቆጠቁጠው ድል አድራጊ ቢሆንም ጴጥሮስ አብሮ ከመሮጥ አልተመለሰም::
ብቻ መቃብሩ ልድረስ እንጂ ቢቀድመኝም እከተላለሁ:: እንደርሱ እስከ መስቀል ባልጸናም ለመቃብሩ ግን ዳግም እታገላለሁ ብሎ ጴጥሮስ ሮጠ::

በዚህ ቅዱስ ሩጫ አርብ የወንድ ለቅሶን ያፈሰሰው ዮሐንስ በዕንባ በደከሙ ዓይኖቹ በኀዘን በጠቆረ ፊቱ እያማተረ ወደ ጌታ መቃብር ገሠገሠ:: እንዴት እንደ ገረፉት አይቶአል:: እንዴት እንደ ቸነከሩት ተመልክቶአል:: አሁን ደግሞ መስቀል ሥር ቆመው በዋሉ እግሮቹ ወደ መቃብሩ እየሮጠ ነው::

ወንድሜ ሆይ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ጌታ መቃብር ሲሮጡ እያቸው:: አንተና ጉዋደኞችህስ ወዴት ትሮጣላችሁ? የእናንተ እሽቅድምድም ወደ ጌታ መቃብር ነው? የት ለመሔድ ትፎካከራላችሁ? የት እንገስግስ ትባባላላችሁ?

ወጣቱ ዮሐንስ ጎልማሳውን ጴጥሮስን ቀድሞ ከጌታ መቃብር ደረሰ:: የጌታን መግነዝም አየ:: ወደ ውስጥ ግን ሳይገባ ቆሞ ጴጥሮስን ጠበቀው:: ጴጥሮስ ዘግይቶ ቢደርስም ከዮሐንስ ቀድሞ ወደ መቃብሩ ገባ::

ከእኔ የበረታ መንፈሳዊ ጉልበት ያለህ ወንድሜ ሆይ ብትቀድመኝ እንኩዋን አትፍረድብኝ:: ጨክነህ ጥለኸኝ ወደ ጌታ ማረፊያ እንዳትገባ:: የዘገየሁት ኃጢአት እግሬን አስሮት ነውና ብርቱው ወንድሜ ሆይ እባክህን ጠብቀኝ:: ድክመቴን አይተህ አትናቀኝ መጎተቴን አይተህ አትፍረድብኝ:: ብቻህን ወደ ጌታ ደስታ እንዳትገባ:: አደራህን በንስሓ እስክበረታ ጠብቀኝ:: እንኩዋን አንተ አብረኸኝ ሩጫ የጀመርክ ወንድሜ ቀርቶ ከእኔ ቀድመው ሩጫቸውን የጨረሱት እንኩዋን ብቻቸውን ወደ ዘላለማዊ ደስታ እንዳይገቡ ጻድቃን በገነት ሆነው እኔን ይጠብቃሉ:: ነቢዩ እንደተናገረ :-
አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ፤
ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤
ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ፡
ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ። (መዝ 142:7)



@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!
======⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️======

- «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋነው፡፡

- መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለውግሥ ይሆናል፡፡

- «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትንያመለክታል፡፡

- «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንበየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስትክፍል አለው፡፡

1) አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ይህም ማለት ተዘክሮተእግዚአብሔር ነው፡፡

2) ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርንመስማትና በንስሐ እየታደሱበሕይወት መኖር ነው፡፡

3) ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜውየሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡

4) አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስበገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድልአድርጎ መነሣት ነው፡፡

5) ዐምስተኛውና የመጨረሻው«የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይአምላክ የጌታችን የመድኀኒታችንኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ»መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ»ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርናለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔበአንድነት የሚነሣው የዘለዓለምትንሣኤ ይሆናል፡፡

ወደ ተነሣንበት ዐላማ ስንመለስ የትንሣኤበዓል በቃሉም ምስጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ«ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡



«ፋሲካ» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ«ፌሳሕ» በጽርእ በግሪክኛው «ስኻ»ይባላል፡፡ ይህም ወደ እኛው ግእዝና ዐማርኛ ቋንቋችን ሲመለስ ፍሥሕ ዕድወት =ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣እየተቸኮለ የሚበላ መሥዋዕት፣ መሻገር መሸጋገር ማለት ነው፡፡ ነጮቹ በእንግሊዝኛው «ስኦቨር» ይሉታል የዚህም ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነትየተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹምደሰታ፣ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል«ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡

ፋሲካ፣ በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ
እስራኤል ዘነፍስ የሆኑት ምእመናን ክርስቶስ ትንሣኤውን የሚያከብሩበት ዕለት ሆኖ በእርሱ ትንሣኤ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፣ከኃሳር ፤ ከውርደት ወደክብር፣
ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደዘለዓለማዊ ነፃነት፣ከአደፈ፣ ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወትወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገሩበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡

- ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት ያከብሩታል፡፡ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡

- መድኀኒታችን ሞትን በሞቱ ድል መትቶ፣ሙስና መቃብርን አጥፍቶ በሥልጣኑ የተነሣው መጋቢት 29 ቀን በ34 ዓ.ምእንደሆነ ታሪከ ቤተ ከርስቲያን ያስረዳል፡፡

- የትንሣኤ በዓል መከበር የጀመረው በቅዱሳን ሐዋርያትና በሰብዐ አርድእት፣ኋላም በየጊዜው በተነሡት ተከታዮቹምእመናን ነው፡፡ ድምቀቱና የአከባበር ሥርዐቱ ይበዛ ይቀነስ እንደሆን እንጂ መከበሩ ተቋርጦ አያውቅም፡፡

«እንኳንለብርሃነትንሣኤውአደረሰን»


@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11

           ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

      ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ሕማማት ሰሞን ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ ቋንቋዎች ትርጉም
       ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

❖ በግብረ ሕማማት (በሕማማት ሰሞን) ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ

➊ የዕብራይስጥ(hebrew)
➋ የቅብጥ (ግብጽ) (coptic)
➌ የግሪክ (ጽርዕ) (greek) ቃላት ይገኛሉ፡፡

📌 የእነዚህ ቃላት ትርጉም በጥቂቱ እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡

#ኪርያላይሶን

❖ ቃሉ የግሪክ(ጽርዕ) ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነዉ፡፡
❖ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡
❖ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ፤ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፤ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡
❖ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፤ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

#ናይናን

❖ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን "መሐረነ / ማረን" ማለት ነዉ፡፡

# አብኖዲ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "አብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ ፡፡

#ታኦስ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "ጌታ / አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "ታኦስ ናይናን" ሲልም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡

#ማስያስ

❖ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "መሲሕ" ማለት ነዉ።
❖ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡

#ትስቡጣ

❖ "ዴስፓታ" ከሚለዉ የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ደግ ገዢ" ማለት ነዉ፡፡

#ሙዳሱጣ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "ነበልባላዊ" ማለት ነዉ፡፡

#መዓግያ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "እሳታዊ" ማለት ነዉ፡፡

#አንቲፋሲልያሱ

❖ ቃሉ "በመንግስትከ / በመንግስትህ" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚኦ በዉስጠ መንግስትከ / አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በዉስጠ መንግስትከ / ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚአ ኲሉ መንግስትከ / የሁሉ የላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡

#ኤልማስ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "አምላኪየ / አምላኬ" ማለት ነዉ፡፡

#አህያ ሸራህያ

❖ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "ያለና የሚኖር" ማለት ነዉ፡፡

❖ እነዚህ ከላይ ያሉና ሌሎች ቃላት ከሌሎች ቋንቋዎች በቀጥታ የተወሰዱ ናቸዉ፡፡

መልካም የሰሙነ ሕማማት ወቅት ይሁንልን

ስብሐት ለከ፤
ሰጊድ ለአቡከ፤
ዕበይ ለመንፈስከ፤
ወምህረተ ፈኑ ለሕዝብከ፤
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡፡    

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽዐነ በፍሥሐ ወበሰላም

ሙሉዉን ያነበበ ብቻ አሜን ይበል እንዲሁ #ሼር ያድርግ

✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
 @dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መቼ #ነው

መቼ ነው እውነተኛ ክርስቲያን የምንሆነው ሼር ሳታነቡ አትለፉ
መቼ ነው እግዚአብሔር በፈጠራቸው ነገሮች የምንረካው?
መቼ ነው እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠረን የምንረዳው?
መቼ ነው እግዚአብሔር እንደፈለገው መኖር የምንጀምረው?
መቼ ነው ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልባችን የምንናገረው?
መቼ ነው እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው?
መቼ ነው ለመልካም ሥራ ምሳሌ የምንሆነው?
መቼ ነው በስግደታችን በፆሎታችን የምንጠቀመው?
መቼ ነው ጸሎታችን ተሰሚነት የሚያገኘው?
መቼ ነው ውሎና አዳራችን በቅዱስ ቃሉ የሚሆነው?
መቼ ነው ሙለ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ የምንመካው?
መቼ ነው የዓለምን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው?
መቼ ነው ቤታችን ውስጥ የተበላሸ ሂወት የሚስተካከለው?
መቼ ነው ቤታችን ውስጥ መጽሀፍ ቅዱስ ውዳሴ ማርያም የሚወራው?
መቼ ነው ውሸት የምናቆመው?
መቼ ነው የእግዚአብሔርን ውሳኔ መቃወም የምናቆመው?
መቼ ነው እኔ እኔ ማለት ትተን ወንድሜ እህቴ ማለት የምንጀምረው?
መቼ ነው ለሰዎች ከክርስቶስ ውጪ ጌታ እንደሌለ የምንናገረው?
መቼ ነው ጥሩና ለጋሽ መልካም ሰው የምንሆነው?
መቼ ነው ክርስቲያንነታችንን የምናስተዋውቀው?
መቼ ነው ለደሃ እምናዝነው?
መቼ ነው ትዳራችን ሰላም የሚያገኘው?
መቼ ነው የጋብቻን ጥቅም ተረድተን ለትዳር የምንቸኩለው?
መቼ ነው ከሀሜት ሰውን ከመበደል ከማስቀየም ከማማት እምንላቀቀው?
መቼ ነው ወላጆቻችንን የምናስደስተው የምንታዘዘው?
መቼ ነው ያልተጣረ ወሬ ከማውራት የምንቆጠበው?
መቼ ነው የምንዋደደው?
መቼ ነው እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ደስተኞች የምንሆነው?
መቼ ነው ስግዴተ ፆም ፀሎት የምንላመደው?
መቼ ነው የበደሉንን ይቅር የምንለው?
መቼ ነው ከራስ ወዳድነት የምንላቀቀው?
መቼ ነው ከሞት በኃላ ላለው ሕይወት ስንቅ የምናዘጋጀው?
መቼ ነው አባቶችን የምናከብረው?
መቼ ነው ለእውቀት ጊዜ የምንሰጠው?
መቼ ነው ክርስትናን የምንኖረው?
ኸረ መቼ ነው ለእነዚህ ተግባራት መልስ የምንመልሰው
እግዚአብሔር ይርዳን
ተራራውን ደልድለህ ሸለቆውን ሞልተህ መንገዴን ያቀናህኝ የማለዳው ድምቀት የቀኑ ውበት ክብሬ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እላለሁ ብቻ ተመስገን። በሕይወቴ ስንት አለፈ
ሞት ለሚገባኝ ምሕረት የሰጠኸኝ ጌታ እባክህ እንዳለፈው ዘመን ጊዜዬ አይለፍብኝ። ፍጻሜዬ በቤትህ ይሁንልኝ። የነዚህ ባሪያዎችህን ፍጻሜ እኔም ተመኘሁ። አምኜህ መሞትህ ናፈቅሁ። ያላንተ ወርቅ ከምደብር ከመስቀልህ ሥር እርቃኔን ልቀመጥ። አንተ የሕይወቴ ተስፋ ያላንተ እንደማይሆንልኝ እንኳን መራራው ጣፋጩ እንደማይጣፍጠኝ ታውቃለህና ዘመኔን በፍቅር ፈጽመው በተወጋው ጎንህ።
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን አሜን፫።




@dnhayilemikael

Читать полностью…
Subscribe to a channel