dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ቅዱስ_ቁርባን

#ምዕራፍ 2
#ክፍል 4

#ባልና_ሚስት_ተነጣጥሰው_ቢቆርቡስ?

«ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነይ /ዮሐ 1-16/
👉ይህንን የጌታችንን ቃል አስተውላችሁት ታውቃላችሁ?
👉ውሃ ለመቅዳት የመጣችው ሳምራዊቷ ሴት «ጌታ ሆይ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውሃ ስጠኝ ባለች ጊዜ «ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ነይ ብሎ መለሰላት፡፡ በዚህ ቃል መሠረትነት ነው ቤተ ክርስቲያን ባልና ሚስት ተነጣጥለው
መቁረብ የለባቸውም የምትለው::

👉ለዚህ ጥያቄ በቂ መልስ ለማግኘት ለአንባብያን ተጨባጭ ማስረጃ ለማቅረብ በጋብቻ ዙሪያ የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል መመልከት ኣስፈላጊ ሆኖ አግንቼዋለሁ፡፡
« ..ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው አለም
ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም እግ
ዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው»
/ማቴ 19:4-6/

👉በዚህ አምላካዊ ቃል መሰረት ባልና ሚስት አንድ ሥጋ ናቸው::
👉ጋብቻ ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ልጆች ከተሰጡ ታላላቅ ስጦታዎችና በረከቶች አንዱና የመጀመሪያው ነው::
👉ገና መጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ ከምድር አፈር አዳምን አበጅቶ በአፍንጫው የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ህያው ካደረገው በኋላ ስለ አዳም አስቦ ያለው እንዲህ ነበር።

👉«አዳም ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም የምትረዳውን እንፍጠርለት» /ዘፍ 2፥18/ በዚህ መሰረት ከአዳም አጥንት ነስቶ ሔዋንን ፈጠረለት አዳምም ከአካሉ የተፈጠረችውን ሴት ተመልክቶ እንዲህ አለ፣
«ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት
እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል» /ዘፍ. 2:23-25/

👉ደግሞም ጋብቻ በረከት ሆኖ ለሰው ልጆች እንደተሰጠ እንዲህ ተፅፏል «እግዚአብሔር እምላክ ሰውን በመልኩ ፈጠረ ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው፡፡
👉ከዚያም እንዲህ ብሎ ባረካቸው «ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ግዙአትም የባሕርን
ዓሶችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው» /ዘፍ 1: 26-31/

👉መድኃኒተዓለም ኢየሱስ ክረስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ በዚህች ዓለም ወንጌለ መንግስቱን በሚሰብክበት ጊዜ ጋብቻ እጅግ የተቀደሰ ባልና ሚስትም አንድ ሥጋ መሆናቸውን አስተምሯል እንዲህ ብሎ፣
🤚«እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው .
/ማቴ. 19:6/

👉አምላካዊ ቃሉ እንዲህ እያለ ኣንድ ሥጋ በሆኑ ባልና
ሚስት መካከል ተነጣጠሉ መቁረብ ለምን ታስቦ?
👉ለመቁረብ እንቢ በሚለው ሰው ውስጥ ያለው ምክንያት ምንድን ነው የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እንድናነሳ ያደርገናል በቅድሚያ አልቆርብም ባዩ ሰው በኃጢአት የመኖር እቅድ እንዳለውና የሚያስጠይቀውም መሆኑ ግልጽ ሲሆን በቃሉ መሠረት ግን ተነጣጥሎ መቁረብ ተገቢ አይደለም የቤተ ክርስቲያን ህግና
ሥርዓትም አይፈቅደውም ምክንያቱም አንዱ ሲቆርብ ሌላው ሲቀር አንድ ሥጋ ተለያየ ማለት ነው::

👉ሌላው በቅዱስ ቁርባን የአንዱ ሕይወት የተቀደሰ ከቅዱስ ቁርባን የራቀው የአንዱ ሕይወት ያልተቀደሰ በመሆኑ በግንኙነት ጊዜ የተቀደሰው ሕይወት ይረክሳል ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ እንዲህ አለ፤ ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና» /1ቆሮ 6፥15-16

👉ይሁንና ሁለቱም በመስማማት በመምህረ ንስሐቸው ምክር በመመራት አንዴ ከቆረቡ በኋላ ቆራቢ ከሆኑ በኋላ ግን በተለያየ ምክንያት ለምሳሌ በሥራ ጉዳይ በመራራቅ፣ ሴቷ ሚስቲቱ
ሥርዓተ አንስት ላይ በመሆን በወር አበባዋ
ጊዜ ፣ ወልዳ በምትታረስበት ጊዜ ወንዱ/አንዱ መቁረብ ቢፈልግ ቢቆርብ እንደመለያየት የሚቆጠር ኣይደለም ምክንያቱም ሁለቱም ቆራቢዎች ናቸው ይህ የመነጣጠል ጉዳይ ሳይሆን በቀን ልዩነት
የመቀበል ሁኔታ ነው ነገር ግን በተቀበሉ ቀን አብሮ መተኛት የተከለከለ ሲሆን ከዚያም በኋላ በልዩ ምክንያት ሳይቀበል የቀረው
ሁኔታዎች ሲስተካከሉ ተዘጋጅቶ በመቀበል ሊቀጥሉ ይችላሉ በተረፈ እንዲህ አይነት ምክንያቶች ካላጋጠሙ በስተቀር የመጀመሪያ ቀን በአንድነት በአንድ ቀን እንደተቀበሉ ሁል ጊዜ በአንድ
ቀን መቀበላቸው ለፈተና ከመጋለጥ ይጠብቃቸዋል:: /1ቆሮ 7:5/





#ምዕራፍ 2
ክፍል 5
❖ያላገባ_ወጣት1መቁረብ_ይችላል ??

ይቀጥላል .....

#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈

ያለፈውን ለማግኘት
/channel/dnhayilemikael/4951

ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ከሰማያዊው ማዕድ የማትሳተፉት ለምንድን ነው?

🥀💠ተወዳጆች ሆይ! ትዘምራላችሁ፡፡ 💠[ከጸሎታቱ ትሳተፋላችሁ፡፡ ቅዳሴውን አስቀድሳችሁ] እምነታችሁን ትመሰክራላችሁ፡፡
💠 ይህን ኹሉ አድርጋችሁ ስታበቁ ግን አትቆርቡም፡፡ ለምን? ከሰማያዊው ማዕድ የማትሳተፉት ለምንድን ነው?
💠 አንዳንዶቻችሁ፡- “እኔ ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ ልቆርብ አይገባኝም” ብላችኋል፡፡ እንዴ! እንደዚህ’ማ ካላችሁ ከመዝሙሩም፣ ከጸሎታቱም፣ ከቅዳሴውም ልትሳተፉ አይገባችሁማ!

💠እስኪ ንገሩኝ! የንጉሥ ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ መላእክት “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” እያሉ የሚያመሰግኑት የሚያገለግሉትም ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ ንጉሡ በፊታችሁ አለ፡፡
💠ታዲያ እናንተ እንዲሁ ቁልጭልጭ እያላችሁ ትቆማላችሁን? ልብሳችሁ አድፎ ተዳድፎም ሳለ ምንም እንዳልተፈጠረ ኾናችሁ ወደ ቤታችሁ ትመለሳላችሁን?

💠ወደ መንግሥተ ሰማያት፣ ወደ ሰማያዊው ንጉሥ ማዕድ ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠርቶን ሳለ ተዘጋጅተን እንደ መቅረብ ወደ ኋላ እንላለንን? 💠እንደዚህ የምናደርግ ከኾነ ታዲያ ተስፋ ድኅነታችን ምንድን ነው?

💠መቅረብ ያልቻልኩት’ኮ” ብለን ደካማ መኾናችንን እንደ ሰበብ ማቅረብ አንችልም፡፡ ተፈጥሮአችንን እንደ ምክንያት ማቅረብ አንችልም፡፡
💠እንዳንቀርብ የሚያደርገን ደካማ መኾናችን አይደለም፡፡ አዎን ከሰማያዊው ማዕድ እንዳንሳተፍ የሚያደርገን እንዲሁ ሳንዘጋጅ ልል ዘሊላን ኾነን መቅረባችን እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት አይደለም፡፡

💠ስለዚህ እማልዳችኋለሁ! [ንስሐ ገብተን እንደ ቸርነቱም ተዘጋጅተን] በፍርሐትና በረዓድ ኾነን [በግድ] እንቅረብ እንጂ “ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ” ብለን አንራቅ፡፡
💠 [ከኃጢአት ኹሉ የሚያነጻን የክርስቶስ ደም እንጂ ኃጢአተኛ ነኝና አይገባኝም ብለን መራቃችን አይደለምና፡፡] ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ በድፍረት ወደ እርሱ መቅረብ ይቻለን ዘንድ ዛሬ በፍርሐትና በረዓድ ኾነን ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡ ያኔ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” ከሚላቸው ጋር ዕድል ፈንታችን ፅዋ ተርታችን በመንግሥተ ሰማያት ይኾን ዘንድ ዛሬ ወደ ሰማያዊው ማዕድ እንቅረብ፡፡

(በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)

#ይቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

❖❖❖❖ መስቀሉን  እሸከማለሁ የሚል የመድኃኔ ዓለም ወዳጅ ?????????????????????????

  አንተ  ሰው እስኪ ልጠይቅህ? :ጌታ የተሰቀለ ዕለት ዕርጥብ መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ ሲሄድ ብትኖር ኖሮ ታግዘው ነበርን ? ወይስ አብረህ ትገፋው ነበር ? ወይስ በርቀት ሆነህ ይገባዋል እያልክ ትደነፋ ነበር ?  ወይስ አላውቀውም ብለህ ትክድ ነበር ? ወይስ ጥለኸው ትጠፋ  ነበር ? ወይስ በልብህ አምነህ አብረህ ከጠላቶቹ ጋር ታመዋለህ ?  ወይስ ራቅ ብለህ ትከተለው ይሆን ?  እስኪ ዛሬ የደመራ ነጭ ልብስህን እንደለበስህ ይህንን አስብና ምን እንደምታደርግ እርግጡን ለልብህና ለራሱ ለመድኀኔዓለም ንገረው !

አይ ጌታዬ ተሸክሞ እየደከመማ አግዘዋለሁ እንጅ አልክደውም ትለኝ ይሆናል ።  እኔም እንዲህ እልሃለሁ ።

አንተ ሰው !  አሕዛብ ቤቱን በማቃጠል ፥ ልጆቹን በማረድ እያሳደዱት በአንተ ዘንድ በልጅነት ያድር ዘንድ በመጣ ጊዜ ሰውነትህን በዝሙትና በበደል አርክሰህ በንስሐ ሳትታጠብ ከቆየኸው ማደሪያ እየነሣኸው አይደለምን ? አብረህ እየገፋኸው  አይደለምን ? እርሱ ስለአንተ ርጥብ መስቀል ተሸክሞ አንተ የወንድም እኅቶችህን አመል የማትታገሥ ከሆነ ምኑን መስቀሉን አገዝኸው ?  እርሱ ለጠላቶቹ መስቀል ከተሸከመ የእኅት ወንድሞቻችን ሸክም የማንሸከም እኛ ምን እዳ ይጠብቀን ይሆን ?  ወዳጄ  ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ሲል የተሸከመውን መስቀል አግዘዋለሁ ካልክ አንተ ለምን ለሚስትህ ብለህ ድካሟን አትሸከምም ? እጠቀም የማይል ጌታ የአይሁድን መስቀል ከተሸከመ መንግሥተ ሰማያት ትወርስ ዘንድ ለምን መከራ አትቀበልም ?

ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ! አንዳንዶቻችን በልብ አምነን በአፍ ዝም ያልን  ነን ! አንዳንዶቻችን ገብቶንም ሳይገባንም መስቀሉን ከሚገፉ ጋር ተባባሪዎች  ነን ! አንዳንዶቻችን  ራቅ ብለን እሰይ ይበላቸው እያልን በአባቶቻችን ውርደት የምንሳለቅ  ነን !  አንዳንዷቻችን ደግሞ ቀርቦ ከመቃጠል ራቅ ብሎ መጠቅለል እያልን ከባድ ነገር መስማትን የማንወድ ሲነሣ ንገሩኝ አይነት ሰዎች  ነን !  አንዳንዶቻችን እንደ ቀንድ አውጣ ደስታ ሲሆን ብቅ መከራ ሲመጣ በኑሯችን ሸማ ጥልቅ የምንል ነን !  አንዳንዶቻችን ጭራሽ ምን እየሆነ እያለ እንኳ የማይገባን አመት በዓል ሲመጣ  ለምግብ ብቻ አለሁ ባዮች  ጥለን የጠፋን የበረከተ ኅብስትና የድግሥ ክርስቲያኖች እንጅ ቀራንዮ ላይ የለንም !  የመጥፋታችን ምልክቱማ የመስቀል ዕለት መዝፈናችን
አይደል !

  መስቀሉን እሸከማለሁ የሚል የመድኃኔ ዓለም ወዳጅ ?????????????????????????

መልስ ፦ እኔ አለሁ የመድኃኔዓለም ወዳጅ ኃይል ባገኝ የቤተክርስቲያናችን ፈተናዎች ለማሳለፍ እተጋለሁ ። ባይቻለኝ ግን የራሴን ፦

1. የራሴን ሥጋዊ የፍትወት መከራ መስቀል  እሸከማለሁ እንጅ የፈቃዴ ባርያ አልሆንም ።
2. ዘወትር የዕለት ዳዊትና ውዳሴ ማርያም በመጸለይ ያለ ማቋረጥ አምላኬን እመገባለሁ ።
3.  በሠራኋቸው በደሎች ከነገ ጀምሮ ለንስሐ አባቴ እናዘዛለሁ ።
4. ጌታዬ በመስቀል የተሰቀለው ለእኔ ምግብ ሆኖ ሊፈተት ፥ መጠጥ ሆኖ ሊቀዳ ነውና ለእኔ ሲል መሞቱን ቅዱሥ ሥጋውን በመቀበል  እመሠክራለሁ ።
5. ምንም ቢሆን ጌታዬ እኔን ፍለጋ ከሰማይ ወደ ምድር ወርዷልና እኔም እርሱን ፍለጋ ቤተክርስቲያን ኪዳን ሳላስደርስ አልውልም ።
6. እርሱ የእኔን ደዌ በመስቀል እንደተሸከመ እኔም የባልንጀራዬን ድካም ታግሼ ማንንም ሆነ ማንን ይቅር እላለሁ ።
8. በመከራዬም ሆነ በደስታየ ከመስቀሉ ሥር እገኛለሁ እንጅ ራበኝ ብየም አልጠፋም ጠገብሁ ብየም አልርቅም !
9. ቢቻለኝ የቤተክርስቲያንን ችግር እፈታለሁ መስቀሉን እሸከማለሁ እንጅ አባቶችን አልተችም  ከገፊዎች ጋር አልቆምም ።
10. ጊዜየን በማይረባና ርብሐ ቢስ በሆነ አላባክንም ፤ በየጊዜው ና በየሰዓቱ ስለቤተክርስቲያን ባልናገር እንኳ ቢያን ጆሮየ ለቤተክርስቲያን የተከፈተ  አደርጋለሁ ።
11. ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት ሀሰጠኝ ጌታ ከጠፊ ገንዘቤ ከአሥር አንዱን በታማኝነት አወጣለሁ ።
12. ለተጠራሁበት የጸጋ ሥጦታ እታመናለሁ ።  ድንግል የሆነ ለድንግልና ፣ ባለትዳር እንደሁ ለትዳር ፥ ዲያቆን እንደሁ ለዲቁና ፤ መነኩሴ እንደሁ ለምንኩስና ፣  ጳጳስ እንደሁ ለጵጵስና ፥ ሊቀ ጳጳስ እንደሁ ለሊቀጵጵስና ፥ ለመታመን በቆመበት ቁርጥ ሕሊና የሚከፈትበትን ሁለንተናዊ የአጋንንት ጦርነት የሚታገሥ እርሱ ጌታን በቀራንዮ ያገዘው የቀራንዮ ሰው  ነው !   ወዳጄ ሆይ ባለህባት የመንፈሳዊነት ደረጃ የምትገጥምህ መሰናክል ያቺ ለአንተ መስቀልህ ።  ከመልካምነትህ ያልተናወጽህ እንደሆነ በእውነት ግርማ አይሁድን ታግሠህ ከክርስቶስ ጋር የቆምክ የመስቀሉ ሰው  ነህ !

 ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ላልሳችሁ ልትወድቁ ወይም እስከ ዛሬ ያያችሁት ምስል ሀሳባችሁ ላይ እየመጣ ልትጨነቁ ትችላላችሁ። ይሄ ማለት ከዚህ ህይወት አልተላቀቃችሁም ማለት አይደለም። ቡና ለረጅም ጊዜ ጠዋት መጠጣት የለመደ ሰው እንደሚያዛጋው ማለት ነው እንጂ! አዕምሮአችን ወደ ቀደመው ቦታ እስኪመለስ ከማንኛውም ሱስ ስንወጣ የምናልፍበት ጤናማ ሂደት ነው።

ዋናው በጦርነቱ ተሸንፎ እጅ አለመስጠት ነው። ፀንታችሁ ከታገላችሁና የሚፈልገውን እስከነሳችሁት ድረስ ሱሱ በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል። ከመገባችሁት ግን ያድግና ይውጣችኋል።

7. #ስሜቶቻችሁን_ተቆጣጣሩ

🥀ፖርኖግራፊ ማየት ሶስት ደረጃዎች አሉት። እነሱም ስሜት /Emotion/፣ ሐሳብ/Thought/ እና ተግባር/Action/ ናቸው።

🥀ስሜት የምንለው የመጀመሪያው ደረጃ ጭንቀት፣ መከፋት ወይንም ፖርኖግራፊ
የማየት ፍላጎት ሊሆን ይችላል። ይህን ተከትሎ ነው ፖርኖግራፊ የማየት ሐሳብ የሚመጣው።

🥀መጨረሻ ላይ ሁሉም ወደ ተግባር ይቀየራል። ስለዚህ ራሳችሁን መቆጣጠር የምትችሉት በሃሳብ ደረጃ ሳለ ሳይሆን ገና ስሜት ሲሰማችሁ ነው።

🥀አንዲት እህቴ ‘እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማኝ ከቤት ወጥቼ መዝሙር እየሰማሁ የእግር ጉዞ ማድረግ እጀምራለሁ፤ ይህም በጣም ጠቅሞኛል’ ስትል ልምዷን አጋርታኛለች። አንድ ወንድሜ ደግሞ እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማው ስፖርት እንደሚሰራ አጫውቶኛል።

🥀ይህ ስሜት ሲሰማችሁ ምን ብታደርጉ ጥሩ ነው የምትሉትን 3 ነገሮችን ጻፉና የሚስማማችሁን ነገር አድርጉ።

8. #ብቸኝነትን_አስወግዱ

ለረጅም ሰአት ብቻችሁን ላለመሆንና ጊዜያችሁን ከቤተሰብና ከወዳጆቻችሁ ጋር ለማሳለፍ ሞክሩ። በተቻለ መጠን ቀናችሁን በተሻለና ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ነገር ላይ አውሉት።

🥀ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ እንደ ስፖርት መስራት መጽሐፍትን ማንበብ ያሉ ልምዶችን አዳብሩ። እስኪ ከዛሬ ጀምሮ ልታዳብሩት የምትችሉት 5 ልምምዶችን ፃፉ።

9. #ተስፋ_አትቁረጡ

ከዚህ ህይወት ለመውጣት በምታደርጉት ጥረት ውስጥ መውደቅና መነሳት ሊያጋጥማችሁ ይችላል። ተስፋ ሳትቆርጡ ከስህተታችሁ ተምራችሁ እንደ አዲስ በብሩህ ተስፋ ነገን አሻግራችሁ ተመልክቱ።

10. #ግልጽ_ሁኑ

🥀ይሄን ጽሁፍ ሳዘጋጅ እስከዛሬ ድረስ በዚህ ሱስ የተጠቁና ያማከርኳቸውን ሰዎች ከዚህ ሱስ እንድትወጡ ያስቻላችሁን ነገር ግለፁልኝ ስል ጠይቄ ነበር። በሁሉም ውስጥ ያገኘሁት 2 ሀሳብ ነው።

🥀አንደኛው የእግዚአብሔር እርዳታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በችግሩ ላይ በግልጽነት ማውራቴ የሚል ነበር። ብዙ ሰው በጉዳዩ ላይ ማውራት ስለሚያሳፍረው እርዳታም ለማግኘት ይቸገራል።

🥀ከዚህ ህይወት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት ከፈለጋችሁ ሊረዳችሁ ለሚችል ለአንድ ሰው በግልጽ ችግራችሁን መናገር ይኖርባችኋል። በመናገራችሁ ብቻ፤ ሚስጥር ያደረጋችሁትን ነገር ወደ ብርሃን በማውጣታችሁ ይህ ኃጢያት በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል።

🥀ስትደክሙ የሚያማክራችሁ፤ መቆማችሁን ሁሌ የሚከታተል አንድ ሰው ማድረጋችሁ ፀንታችሁ እንድትቆሙ ብርታት ይሰጣችኋል። ይህንን ምክር ሰጥቼው የተቀበለ አንድ ወንድም ችግሩን ለጓደኛው አካፈለው። መጥፎ ስሜት ሲሰማው ይደውልና 'እባክህን እየተቸገርኩ ስለሆነ ጸልይልኝ' ይለዋል።

ልታማክሯቸው የምትችሉ ሶስት ሰዎችን ጻፉና በማስተዋል እና በፀሎት ታግዛችሁ አንዱን ምረጡ።

ፅሁፌን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ልደምድም።
“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ”። ማቴ 11:28
በተረፈ በፆም በፆሎት በስግደት መበርታትን ነው🥰

ተፈጸመ!

=======//////////////==========
ቴሌግራም ተቀላቀሉ ተዋህዶ

@dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ለሁ›› ያልሽው ንግግርሽ እንዴት ያለ ጸሎት ነው? ይኼንን እንኳን ለእኛም ጭምር አጥብቀሽ ጠይቂልን፡፡ ከልባችን መቃብር ውስጥ ጌታችንን ካጣነው ቆይተናል፡፡ ክቡር ሥጋውን ተቀብለን በውስጣችን ከያዝን ከሦስት ቀንም በላይ ብዙ ዘመን አልፎናል፡፡ ነገር ግን እርሱ እንደተለየን እየተሰማን ፣ ባዶነት እያስጨነቀን ነው፡፡ ከጲላጦስ ማኅተም የበለጠ የመስቀል ማዕተብ የታተመበት ሰውነታችን የጌታን ሥጋ ተቀብሎ ቢይዝም አሁን ግን ባዶነት እየተሰማን ፣ እርሱም ከእኛ እንደተለየን እየመሰለን ነው፡፡ በመቃብሩ ጠባቂዎች በካህናት ማሳበብ ፣ ‹እነርሱ ስላንቀላፉ ነው ጌታ ከእኛ ተወስዶ ባዶ ሆነን የቀረነው› ማለት ጲላጦስን እንኳን ማሳመን ያልቻለ ተራ ምክንያት ነውና ልናቀርበው አንደፍርም፡፡ ብቻ ባዶነት ሲበዛብን ‹አዳም ወዴት ነህ› ያለውን አትክልተኛ ጌታ ከሰውነታችን ጫካ ውስጥ ገብተን ‹‹ጌታ ሆይ ወዴት ነህ› እያልነው ነውና እባክሽን ጠይቂልን፡፡ እርሱ ወስዶብን ከሆነም ይንገረን፡፡ እንደ ዳዊት ‹መንፈስህን አትውሰድብኝ› እያልነው ጨክኖብን ከሆነም ይንገረን፡፡

ያኖረበትን የነገረሽ እንደሆን ግን እኛም እንዳንቺ እንድንወስደው ወደ ልባችን እንድናስገባው ንገሪን፡፡ ከዚያ በኋላ አውቀነው ‹ረቡኒ› (መምህር ሆይ) እንለዋለን፡፡ አትንኩኝ ቢለንም አናዝንም ‹‹ጌታ ሆይ አንተው በእጆችን ዳስሰን እንጂ አንዳስስህም ፣ ባዶነት ላስጨነቀው ውስጣችን ያለህበትን ንገረን እንጂ በረከሱ እጆቻችን ልንነካህ አንደፍርም፡፡ አንተን ዳስሶ እንደቶማስ ተቃጥሎ ከመጮኽ በአንተ ተዳስሶ መንጻትን እንመርጣለን›› ብለውሃል በይልን፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ቅዱስ_ቁርባን
(ምዕራፍ አንድ ክፍል 1 ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 /channel/dnhayilemikael/4939

#ምዕራፍ 1 #ክፍል 2
#ሰው_ግን_ራሱን_ይፈትን
ሐዋርያው ይህን ኃይል ቃል የተናገረበትን ቁም ነገር
ስንመረምር ፈታኝና ኋለኛ ሕይወታችንን አጢነን የምናስተካክልበት በሁለት ክፍል የምንመለከተው ጉዳይ እንዳለ ያመለክተናል
እነርሱም፣

👉ሀ. #ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል እስከተነሣንበት ጊዜ ድረስ ያለውን
ሕይወትትንን እንዴት እንዳሳለፍን
👉ለ/ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያደረግነው ዝግጅት ምን እንደሚመስልና ስለተቀበልነው ምስጢር ያለንን እውቀት እንድንመረምር የሚያደርገን ነጥብና ስለ ሕይወታችን ትኩረት እንድንሰጥ የሚያደርግ ኃያል ቃል ነው::
.
ሀ. የመጀመሪያውን ነጥብ ስንመለከት ወደ እግዚአብሔ እስከተጠራንበት ለቅዱስ ቁርባን ዝግጅት እስከጀመርንበት ድረስ ሕይወታችንን እንዴት እንዳሳለፍነው ልንመረምር ይገባል
የሐዋርያውም ቃል «በሃይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ>> [2ቆሮ. 13 : 5/ ነው የሚለው ምክንያቱም ቀድሞ የተበላሸ ያልተስተካከለ፣ እግዚአብሔር የማይፈቅደውና ያዘነበት ሕይወት
ሊኖረን ይችላል::
🙏ስለዚህ በዚህ ደረጃ የምናደርገው አትኩሮት ይህ ሕይወት እግዚአብሔር እንደሚወደው፣ እንደሚፈቅደው ሆኖ ሊስተካከል
እንደሚችል ትምህርት የምንወስድበትና በወሰድነው ትምህርት ራሳችንን ልናስተካክልበት ነው::
🙏በሌላ መልኩ ሕይወታችንን በማስተካከልና ንስሐ በመግባት የተውናቸው የራቅናቸው ክፉ ሥራዎች ምን ያሕል ከሕይወታችን እንደራቁና በፊታችን እንደተጠሉ በፈተና መልክ ወደ ፊት በሚቀርብልንና በሚያጋጥሙን ጊዜ ምን ያህል የመቋቋሙ ብቃት
እንዳለንና የዚህ ብቃት ምስጢሩ ዓለምን ያሸነፈውንና ሁሉን ሊያስችለን የሚችለውን አምላክ ምን ያሕል በፍጹም እምነት እንደተከተልነው ልናረጋግጥ ይገበናል ምክንያቱም ያለ እርሱ አንዳች ማድረግ እንዳይቻለን ተጽፏልና:: <<ያለ እኔ ምንም
ልታደርጉ አትችሉም» /ዮሐ15: 5.


👉ለ/ሁለተኛው ደረጃ ቁርባን ለመቀበል ያደረግነውን
ዝግጅት የምንፈተንበት ክፍል ነው ምክንያቱም ያደረግነው ዝግጅት ቅዱስ ቁርባንን ለምንቀበልበት በሰዓት ለተወሰነ ጊዜ ከኛ ጋር የሚቆይ ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ቁርባን ለተቀደሰውና ለተወሰነው ሕይወታችን ዋስትናነት ያለውን እስከ ሕይወታችን ፍፃሜ ድረስ ልንጸናበት የሚገባ ነው ክርስቶስ ከዓለም መርጦ
እርሱን እንዲከተሉት ያደረጋቸውን ደቀ መዛሙርቱን እርሱን በመቀበላቸው ወደ ፊት በዓለሙ ውስጥ ከሚደርስባቸው መከራ መንገድ ላይ እንዳይቀሩ
ሲያስጠነቅቃቸው«እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል፡፡ » /ማቴ. 24:13/ ብሏቸዋል::
ብዙ ሰዎች ለጊዜው በግብታዊነት ተነሣስተው ይህንን ኃጢአት ደግሜ አላደርገውም ስላሉ ብቻ በቂ ዝግጅት አድርገው ይወስዱታል ወይም በዚያን ወቅት ኃይል የሆናቸው ከራሳቸው ጉልበት ከመነጨ ብርታት የወሰኑት ውሳኔ ዘላቂ ይመስላቸውና ወደ ቅዱስ ቁርባን የሚያደርጉትን ግስጋሴ «ይበል በለው »
ያደርጉታል ነገር ግን ወደ ጠባብ ደጅ ከተገባ በኋላና ለጊዜው የታገሰው ጦር መልኩን ቀይሮ ሲመጣ በቀላሉ መዛልና አልፎም ውድቀት ይከተላል ይህ ሁሉ ሊመጣ የሚችለው ቃሉን ስለማናሰተውል ነው ቃሉን ደግሞ የማናስተውለው ቃሉን
ስለማንሰማ ሊሆን ይችላል ጌታችንም ለአይሁድ
«ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ
ነው» /ዮሐ. 8፥43/ ብሏቸዋል::

#ምዕራፍ 2
ቅዱስ ቁርባን ለማን
ይቀጥላል .........



👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ቅዱስ_ቁርባን

👉 #ማሳሰቢያ_ላትጨርሱ_አትጀምሩ

#ምዕራፍ_አንድ
#ቅዱስ_ቁርባን_ስለ_ፈሰጉ_ብቻ_የሚገቡበት_ሕይወት_ይደሰም

#መግብያ
«ሰው ግን እራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ
ከጽዋውም ይጠጣ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ
ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ይጠጣልምና /1ቆሮ 1: 27/
በዚህ ርዕሳችን በሰፊው የምንመለከተው ተያይዞ የተጠቀሰውን የሐዋርያውን መልዕት ተንተርሰን ሲሆን በዚህ ሥር ከ2 ያላነሱ ነጥቦችን ጨምረን እንመለከታለን፡፡
ማንኛውም አማኝ ስለፈለገ ብቻ ተንደርድሮ የሚገባበት ሕይወት ሳይሆን ቅዱስ ቁርባን አስቀድሞ ወደ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት ሲገባ የሚከተለውን ነገር ጠንቅቆ ማወቅና ወድዶና ፈቅዶ ስለ ቅዱስ ቁርባን የሚደርስበትን መከራና ፈተና ለመቀበል መወሰንና መዘጋጀት ይኖርበታል. ለዚህም ደግሞ ወሳኙ ምክረ
ካህን ነው።


#ምዕራፍ_አንድ
#ክፍል 1
: 🙏 #ምክረ_ካህን🙏

ምክረ ካህን ማለት አማኙ በኃጢአቱ ከተናዘዘ በኋላ ቀኖና መስጠት ማለት ብቻ ሳይሆን ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ሆኖ #ቅዱስ_ቁርባን ለመቀበል ጥያቄ ላቀረበው ወይም ለተዘጋጀው አማኝ
ከካህኑ ጥልቅ ምክርና የተብራራ ምሪት ሊሰጠው ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ የእርሱ በመሆናቸው የሚገጥማቸውን አስቀድሞ
እንዲያስተውሉ አድርጎ እንዳዘጋጃቸው ካህኑም አማኙን ሊያዘጋጀው ይገባል፡፡
👉ምክረ ካህን ማለት በአጠቃላይ መልኩ አማኙን ከመቁረቡ በፊትና ከመቁረቡ በኋላ ያለውን ሕይወት ሁሉ ያጠቃልላል እንጂ ኃጢአትን መናዘዝ የመስዋዕቱን መለወጥ እንዲያምን ማስተማር
ብቻ ማለታችን አይደለም፡፡ አብነት እንዲሆን ከዚህ በታችእንደጠቀስነው ሊሆን ይገባል።

👉አንድ አማኝ ወደ ቅዱስ ቁርባን ከቀረበ በኋላ ስለሚጠብቀውና ስለሚመራው ሕይወት ካህኑ በዝርዝር ይግለጽለት።
👉ክርስቶስን መከተል ማለት ወደዚህ ሕይወት መግባት ማለት ባለቤቱ እንደተናገረው መስቀሉን መሸከም ማለት ስለመሆነ ይግለጽለት፡፡
🙏ምን አልባትም አማኙ በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ ሲኖር በዓለሙ ዘንድ የተጠላና የተተቸ ሊሆን ይችላል:: ይህን ነገር ክርስቶስ እንዲህ በማለት ተናግሮታል፡- « ስለእኔ በዓለም ውስጥ
የተጠላችሁ ትሆናላችሁ» /ዮሐ 15 -23/ ምክንያቱም የዓለምን ሥራ ስለምናልክስበትና ስለ ምንንቅበት አለም ሊጠላን ሊተቸን ምክንያት ሊፈልግብን ይችላል ሁሉም የሚወደው ወገን ወገኑን
ነውና
👉 ደቀመዛሙርቱ እርሱን በመከተላቸው ዓለም የአበባ ምንጣፍ አንጥፎ አዘጋጅቶ አይደለም የተቀበላቸው ለአንገታቸው ሰይፍ ለሰውነታቸው እሳት እንጂ /ማቴ. 24÷9/
ስለዚህ አንተም መሰል መከራዎች በደረሰብህ ጊዜ የተቀበልከውን ታውቀዋለህና ስለ እርሱ ራስህን ክደሃልና ስለሥሙና ስለ ቅዱስ ቁርባን በሚደርስብህ ደስ ሊልህ ይገባል ምርጫህ ሕይወት
በመሆኑ ሰይጣን መሸነፉንና ባንተ መቅናቱን እወቅ ስለዚህ ካህኑ ይህንና መሰል ጉዳዮችን ሊያሳውቀው ይገባል እንዲህ እያለ ልጄ በርታ አይዞህ ዓለም ቢጠላህ አትደነቅ ደግሞም የገዛ ሃሳብህ ዕር ይሆንብሃል ይህንን አይነቱን ፈተና በዚህ በዚህ መልክ ተቋቁመው ቢገጥምህ እንዲህ ተወጣ የሰዎች ባንተ አይደነቅህ ምክንያቱም ሰይጣን አንተን ለመፈተን ሊጠቀምባቸው ይችላል የሰይጣንን የውጊያ ባህርያት እወቅ ሊለው ይገባል፡፡
👉በሌላ መንገድ ሰይጣን እራስህን በማይገባ ክስ እንድትከስና በጀመርከው ሕይወት እንዳትገፋበት በአሉባልታዎች ሊያውክህትም ይችላል፡፡ አንተ ግን ስለተቀበልከው በቂ ዝግጅትና እውቀት ካለህ
መልስ ትሰጥበታለህ:: «በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ» /1ጴጥ. 3፥15/
👉ይሔውም «አንተ ቆርበህ እንዲህ ትሆናለህ» «ይህ ሰው ከቆረበ ጀምሮ አቅበዘበዘው» «መቁረብ በማይገባት ጊዜ ቆርባ አደብ አጣች» የመሳሰሉትን ይህ አይነት አሉባልታ ሌሎችን በአንተ ላይ
አነሳስቶ የመክሰስ የዲያቢሎስ ውጊያ ነገ ደግሞ ራስህን በራስህ ላይ አነሳስቶ ለመክሰስ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት መሆኑን ልብ
በልና ለአሉባልታ ሳትገዛና እነርሱ ባሉህ /ባሙህ/ ነገር ሳትገኝ ተገቢውን መልስ በትህትና መስጠት ይገባል:: 👉ይኸውም እኔ የተቀበልኩት ሰላም ነሺውን ሳይሆን ፣ አደብ የሚያሳጣውን፣ ሳይሆን የሚያቅበዘብዘውን ሳይሆን፣ #የሰላሙን_አምላክና ሕይወትን
#የሚቀድሰውን_ጌታ ነው ኢሳ 9:6/ በማለት ደግሞ::
👉አንተ ወገኔ የምትናገረውንና እንዲህ የምትተቸውን
ታውቃለህ ሰላም ነሺ አቅበዝባዥ፣ የምትለውን ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስ ለዓለም ሰላም የሰጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው
እኮ ልክ እንደ አይሁድ ሕዝቡን ሰላም ነሳ ብለው ለቄሳር እንደከሰሱት በማለት ምስጢሩ ያልገባውን ወገንህን ማስተማርና
ሰይጣንን ማሳፈር ይገባሀል።

#ምዕራፍ_አንድ
* #ክፍል 2
#ሰው_ግን_ራሱን_ይፈትን

ይቀጥላል ......
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉@dnhayilemikael 👈
👉@dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ፖርኖግራፊ

ክፍል 4

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፖርኖግራፊ ምን ይላል?

🥀በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሩካቤ ብዙ የተፃፉ ክፍሎች ቢኖሩትም ስለፖርኖግራፊ ይህ ነው ተብሎ በግልፅ የተፃፈ ነገር አናገኝም። ሆኖም ግን ክርስትና በአካል ከሚደረጉ ሃጢያቶች ከመራቅ ባለፈ የአይምሮ ንፅህናን የመጠበቅ ጉዳይ እንደሆነ ያትትልናል።

🥀በዘፀአት 20 :17 ላይ “የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ” ሲል ሆነ፤ ክርስቶስ በማቴዎስ 5:27-29 “ሴትን በምኞት አይን የተመለከተ ሁሉ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሯል’’ ሲል፤ እንዲሁም በተለያዩ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች የስጋ ምኞት ‘ነፍስንም የሚወጋ’ ኃጢት (1ጴጥ 2:11) ተብሎ ሲጠቀስ እነዚህን ክፍሎች ከፖርኖግራፊ ጋር አያይዘን ልንማርባቸው እንችላለን።

🥀የስጋም ምኞት ኃጢያትን እንደምትወልድ ፤ ኃጢያትም ሞትን እንደሚወልድ ይናገራል። (ያቆ 1:14-15) የፖርኖግራፊ ዋና ግብ የስጋን ምኞት መፍጠር ሲሆን ያም ሀጢያትን ይወልዳል፤ ኃጢያት ደግሞ ሞትን! ፖርኖግራፊ በክፉ የጠላት ሃሳብ የተመረዘ የሰው የሃሳብ ውጤት ነው።

🥀ጠላት ዲያቢሎስ ሁሌም ቢሆን ለጦርነት የሚጠቀመው መሳሪያ ሀሳብን ነው። ጥንት ሔዋንና አዳምን ከገነት ያስኮበለላቸውም የተመረዘ ሐሳብ ነው።

🥀“እባብም ለሴቲቱ አላት፦ ሞትን አትሞቱም፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ ” (ዘፍ3:4:5) ዲያብሎስ አሁንም እየተዋጋን እና እየጣለን ያለው ሄዋንን በጣለበት መሣሪያ ይህም በተመረዘ ሃሳብ ነው።

🥀አሁን ላለንበት ዘመን ደግሞ በኢንተርኔት ፣ በዘፈን፣ በፊልም፣ በመጽሐፍ፣ በጌም በመሳሰሉት ይህን ሀሳብ እያቀበለን ነው። ወዳጄ መምሕር ነቢዩ ተስፋ እንዳለው “በዚህ ዘመን የሰይጣን ተቀዳሚ አላማ ኃጢያትን ተደራሽ ማድረግ ነው”።
መጽሐፍ ቅዱስ አዕምሮአችንን በላይ ባሉ ነገሮች ላይ እንድናደርግ ያዘናል። (ቆላ 3:2) በስጋ ስላለው ነገር ከማሰብ ይልቅ መንፈሳዊውን ነገር እንድናስብም ያሳስበናል። (ሮሜ 8:8) ፖርኖግራፊን የሚመለከት ሰው አይምሮውን በስጋ ምኞት ላይ እንጂ በእግዚአብሔር ሀሳብ ላይ ሊያደርግ አይችልም።

🥀የአንድ ክርስቲያን ግብ መሆን ያለበት በአዕምሮ መታደስ መለወጥ ነው። (ሮሜ 12:2)
የክርስቲያን ሰውነት የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ቤተመቅደስ እንደመሆኑ ማናቸውንም በስጋ የሚደረግ ኃጢያት ማስወገድ ይኖርበታል። (1ቆሮ 5:9-11፤ ገላ 5:19-21፤ ኤፌ 5:1-5፤ ቆላ 3:5- 6 ፤ ዕብ 12:15- 17) ስለዚህ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደምናየው በፖርኖግራፊ ሱስ የተያዘ ሰው በንስሃ እስካልተመለሰ ከእግዚአብሄር እንደተለየና የእግዚአብሄርንም ርስት እንደማይወርስ ማየት እንችላለን።

​​ክፍል 4
#ከፖርኖግራፊ_ሱስ_እንዴት_መውጣት_ይቻላል? ይቀጥላል ......


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር


ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት?
እናት ብቻ ብሌን እንዳንጠራት ድንግል ሆና አገኘናት !
ድንግል ብቻ ብሌን እንዳንጠራት ልጅ ታቅፋ አየናት !
ጌታ ሆይ እናትህን መጥራት እንድህ የሚያስቸግር ከሆነ
አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራለን
?



ቅዱስ ኤፍሬም


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሰላም ለሁላችሁ ፦አንድ ወጣት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው። የጌታዬን ሥጋ በልቼ ደሙንም ጠጥቼ ተመልሼ ደግሜ በኃጢአት ወድቃለሁ ምን ይሻለኛል? አላቸው። እርሳቸውም ሲመልሱ የለም በኃጢአቴ ስወድቅ በሥጋው እነሳለሁ ደግሞ ስወድቅ በደሙ እነሳለሁ ብለህ እመን አሉት።
እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#እኔ_በሕይወት_ዘመኔ_ሦስት ነገሮችን ሳስብ እፈራለሁ።

❶ ነፍስ ከስጋዬ የምትለይበትን ሰዓት ፤
❷ ወደ እግዚአብሔር ፊት እንድቀርብ መላእክት በሚወስዱኝ ሰዓት ፤
❸ ከፈጣሪም አንደበት የፍርድ ቃል ለመስማት በፊቱ የምቆምባትን ሰዓት ፤
/ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ/

🥀†አቤቱ በመንግስት አስበን መልካም ስራ ለመስራት አብቃንአሜን🤲
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ፖርኖግራፊ

ክፍል 3

#የፖርኖግራፊ_መዘዞች

ፖርኖግራፊ መመልከት የሚያስከትለው እጅግ በጣም ብዙ መዘዞች አሉት። ጉዳቶቹም መንፈሳዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ናቸው። እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት።

1. #ከልዑል_እግዚአብሔር_ይለያል

በክርስቶስ የተጠራነው ንፁህ እና ቅዱሳን (1ጴጥ 1:10) እንድንሆን እንደመሆኑ በድብቅ የምንሰራቸው ማናቸውም ኃጢያቶች በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንድንደክም ያደርጉናል።

💠በፖርኖግራፊ ሱስ ላለ ሰው መፀለይ፤ ቃሉን ማንበብ እና ከሌሎች ክርስትያኖች ጋር ህብረት ማድረግ ከባድ ይሆናል። በዚህ ሱስ ከተጠቁ ወገኖቼ በተደጋጋሚ ከሰማዋቸው ድምጾች ዋነኛው፤ “መጸለይ አልቻልኩም፤ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ከበደኝ፤ ምክንያቱም ፊቴ ላይ የሚመጣው የተመለከትኩት ፖርኖግራፊ ነው” የሚል ነው።

💠ሀሳቡ ከሌላው ሰው የተደበቀ ስለሆነ ብዙ ትኩረት ባይሰጠውም ተጨባጭ ሀጢያት ከመሆን አያግደውም። ፖርኖግራፊ መመልከት ኃጢያት መሆኑ ግልፅ ነው። ጌታችን ኢየሱስ “ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል” (ማቴዎስ 5:28) እንዳለ እናስታውስ።

💠እኔ ፖርኖግራፊ አይቼ በፍጹም አልመኝም የሚል ይኖር ይሆን? አንድ ሰው ፖርኖግራፊ እያየ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ተሰጥቻለሁ ማለት አይችልም። ምክንያቱም በማቴ 6:24 ላይ እንደሚናገረው አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች ሊገዛ አይችልም። የስጋን ፈቃድ እየፈፀሙ ክርስቶስን ለማምለክ መሞከር ትርፉ ብቸኝነት፤ ተስፋ መቁረጥ እና ውድቀት ነው።

💠ፖርኖግራፊ መንፈሳዊ ሕይወትን የሚያኮላሽ ነው። ሰው መንፈሳዊነቱን ካጣ ደግሞ ምንም ነገር ቢያገኝ አይረካም። ፖርኖግራፊ ዋና ነገሮቻችንን ያሳጣናል።

2. #ድብርት_ጭንቅት

💠ፖርኖግራፊ ውስጥ የገባ ሰው ያለበት ሕይወት ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል። ስለዚህ ከባድ የሆነ ጭንቀት ይሰማዋል። ብዙ ሰዎች በዚህ ምክንያት ሀፍረት ስለሚሰማቸው በራስ መተማመናቸውን ያጣሉ። ስለዚህ በከባድ የድብርት ስሜት ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ከሰው ያገላሉ።

​​3. #አቅምን_ይገላል

💠በዚህ ሱስ የተያዘ ሰው በቀን ውስጥ በትንሹ 3 ሰዓት ፖርኖግራፊ በመመልከት ሊያጠፋ ይችላል። ምን ያህል የከበረ ጊዜውን እንደሚያጠፋም አስተውሉ! ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ሱስ መጠቃት ኃላፊነትን ቸል ወደማለት ያደርሳል። የፈጠራ ችሎታን ይቀንሳል።

💠በፖርኖግራፊ ምክንያት የአፈጻጸም ብቃታቸው ወርዶ ከስራና ከትምህርት የተባረሩ ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም። አስደናቂና ዕምቅ ችሎታ ያላቸው ስንቶችን በፖርኖግራፊ ምክንያት አጥተናቸዋል?

4. #ላልተፈለገ_ተግባር_ያጋልጣል

💠ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሕጻናትን ከደፈሩ ሰዎች ብዙዎቹ በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቁ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ከማይመለከቱት ጋር ሲነጻጸሩ በ40% ሴተኛ አዳሪዎች ጋር የመሄድ ዝንባሌ አላቸው።

💠የተመሳሳይ ጾታ ፖርኖግራፊ በመመልከታቸው ብቻ ወደ ግብረ ሰዶማዊነት የገቡ ሰዎች እንዳሉም ለማየት ችያለው።

💠ብዙውን ጊዜ በፖርኖግራፊ ምስሎች ላይ ሴቶች የወንዶች የሩካቤ ፍላጎት አገልጋይ ተደርገው የተሳሉ ሲሆን ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ወንዶችም ልክ እንደዛው ሴቶቹን እንደሚመልከቱ ያስባሉ። ሴቶች ደግሞ ሁሉም ወንዶች ለስሜታቸው ብቻ የሚኖሩ እንደሆኑ እንዲያስቡ እንዳደረጋቸው ያምናሉ። በዚህ የተሳሳተ አመለካከት ምክንያት ጤናማ የሆነ የፍቅር ህይወት ለመጀመር የተቸገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

6. #ትዳርን_ይበጠብጣል

💠ከሀገር ውጪ የሚኖር አንድ ሰው ደውሎ እንዲህ አለኝ፣ "እኔ በፖርኖግራፊ ሱስ ከተጠቃሁ አንድ ዓመት ሆኖኛል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ ችግር ገጥሞኛል። በስራ ሰአቴ ላይ ረጅም ጊዜ የማጠፋው ፖርኖግራፊ በመመልከትና ግለ ወሲብ በመፈጸም በመሆኑ እቤት ስገባ ከባለቤቴ ጋር ግንኙነት የማድረግ ፍላጎት የለኝም።”

የዚህ ሰው ችግር የብዙዎችም ነው። ‘ፖርኖግራፊ’ የሚመለከቱ ሰዎች በትዳራቸው ያላቸውን እርካታ ያጡታል። የግንኙነት መቃወስም (Sexual Dysfunction) ሊያጋጥማቸው ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ ፍቺ እና የቤተሰብ መበተን እስከማምራት ይደርሳል።

ክፍል 4 ይቀጥላል
ቴሌግራም ተቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#የፖርኖግራፊ

ክፍል ሁለት


#የፖርኖግራፊ_ሱሰኝነት_ምልክቶች
አንብቡት🗣

1. #ከፍተኛ_ፍላጎት

አንድ ሰው ሱስ ደረጃ ላይ ከደረሰ ለፖርኖግራፊ ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረዋል። በውስጡ የማያቋርጥ ፍላጎት ይቀጣጠላል። በማንኛውም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ በማንኛውም ሰአት ፖርኖግራፊን መመልከት ይፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከትበትን ጊዜ እየጨመረ ይመጣል። በሳምንት ያይ የነበረ በቀን፤ በቀንም አንዴ ያይ የነበረው ሁለቴ ማየት ከጀመረ፣ በፖርኖግራፊም የሚያጠፋውም ጊዜ እያደገ ከመጣ፤ በሚመለከትበት ጊዜ የሚሰማው መነቃቃት እና ደስታ በሀፍረት፤ ጥፋተኝነት ስሜት እና ፀፀት ሲተካ ነገሩ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ይጠቁማል።

2. #ለማቆም_አለመፈለግ / #አለመቻል

ሱስ ውስጥ የገባ አንድ ሰው ፖርኖግራፊ መመልከቱን ማቆም አይፈልግም። ሱስ እንደሆነና ችግር መሆኑን እንኳን መቀበል አይፈልግም። ይህም የሚሆነው ሱስ ውስጥ ስለገባና ከዛ ህይወት ቢወጣ ሌላ የሚያዝናናው ነገር ሊያገኝ እንደሚችል ስለማያምን ነው።

በሌላ መልኩ ደግሞ ለማቆም እየፈለጉ
አለመቻልም የሱሰኝነት ማሳያ ነው። እዚህ ጋር አንድ ወንድም በድምጽ ባስቀመጠልኝ መልዕክት ውስጥ “እኔ ከፖርኖግራፊ ሕይወት ለመውጣት ከ100 ጊዜ በላይ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር፤ ነገር ግን ተመልሼ እዛው ሕይወት ውስጥ እገኛለው” ብሎኛል። ይህ ንግግር የሚያሳየው ከባድ የሆነ ሱስ ውስጥ መግባቱን ሲሆን እየተጸየፍነውም የምናደርገው ነገር ሱስ እንደሆነብን ያሳያል። /channel/dnhayilemikael

3. #በሌላ_ነገር_ደስታ_አለማግኘት

አንድ ሰው ወደዚህ ሱስ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ያስደስቱት የነበሩትን ነገሮች ለምሳሌ ከቤተሰብና ከወዳጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ወደ ኃይማኖት ስፍራ መሄድ፣ ስፖርት መስራት፣ ፊልም ማየት፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወ.ዘ.ተ በመተው ደስታውን ሙሉ ለሙሉ በፖርኖግራፊ ላይ ካስቀመጠ ይህ ሰው የፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ እንደገባ ያሳያል።

​​4. #ከተጽኖው_ጋር_መቀጠል

በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ ሰው በሱሱ ምክንያት ብዙ ነገር እንዳጣ እያወቀ ህይወቱ ወደተሳሳተ አቅጣጫ እያመራ መሆኑን እየተረዳ በዛው ከቀጠለ ሱስ ደረጃ ላይ ለመድረሱን ያሳያል።

5. #ሚስጥራዊነት

በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለ ሰው ህይወቱን አጠገቡ ካሉ እና ከሚወዳቸው ሰዎች ሚስጥር ከማረጉ የተነሳ ድብቅ እና ሁለት ገፅታ ያለው ባይተዋር ሰው እንደሆነ ይሰማዋል።

ሚስጥሩም እንዳይጋለጥ ያያቸውን ድህረ ገፆች በማጥፋት፤ የት እና ምን ያደርግ እንደነበር ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ሰዎችን ይዋሻል። የሚሰማውንም ሀፍረት ለመሸፈን በማስመሰል ህይወት ውስጥ ይዘፈቃል።

#ኃላፊነትን_አለመወጣት

ብዙ ሰዓታትን በፖርኖግራፊ ከማሳለፍ የተነሳ በአግባቡ ስራን አለማከናወን፤ የቤተሰብ፤ የማህበራዊና መንፈሳዊ ሐላፊነቶችን መወጣት አለመቻል እና ገለልተኝነት ሱስ ደረጃ ላይ መደረሱን ያሳያል።

7. #የፀባይ_መቀያየር

በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ባጡ ጊዜ በጣም ብስጩ ፤ ቁጡ እና በጥቂት ነገር የሚናደዱ ይሆናሉ።

ከላይ የጠቀስናቸው ዋና የሚባሉት የሱስ ምልክቶች ሲሆን እነዚህ ምልክቶች የሚታዩባቸው ሰዎች ቆም ብለው ራሳቸውን አይተው ዕርዳታ ካልፈለጉ ለፖርኖግራፊ ሱስ መዘዞች ራሳቸውን ያጋልጣሉ።

ይቀጥላል .....


/channel/dnhayilemikael

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

በእንተ ዲያቆናት

✝️ 📚 @በእንተ ዲያቆናት(ስለ ዲያቆናት) የቅድስትና ሐዋርያዊት ኵላዊት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ይላሉ? ❓

💒 ፩. ዲያቆንም ኾነ ቄስ ሰሞነኛም ይኹን አይኹን፤ ለመቀደስም ኾነ ለጸሎት ቤተ መቅደስ ውስጥ መግባት ያለባቸው ሌሊት ነው። ሥርዐተ ቅዳሴ እንዲህ ይላላል፦

👌 "ሌሊት ለጸሎት ያልመጡ ቀሳውስትና ዲያቆናት ወደ ቤተ መቅደስ ይገቡ ዘንድ ያገለግሉም ዘንድ አይገባቸውም። ይኽን ትእዛዝ ቢደፋፈሩ ግን ከሕግ ትእዛዝ የወጡ ይኾናል።" [ሥርዐተ ቅዳሴ]

💒 ፪. ብዙዎቹ ዲያቆናት ልብሰ ተክህኖ ለብሶ መቀደስ፥ ሰዓታትና ማኅሌት መቆምና በንግሥ ሰዓት መስቀልና ቃጭል ይዘው ቅድመ ታቦት መኼድ እንጂ የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር መረዳት የስብከተ ወንጌል ግብር ብቻ ይመስላቸው። 🙅ፍጹም ስሕተት ነው።

💒 ከመቀደስ ባለፈ እውነተኛውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት መማር፥ መረዳት፤ ከክህደት ትምህርት አንጥሮ መገንዘብም የመለየት ኃላፊነት አለባቸው።

💢 ➺ቅጥረኛ ስለኾንኩ እንጂ...በሚል ሳይፈልገው የሚቀድስ፦ ከታማኝ አገልጋይ ጋር ምን አንድነት አለው? ❓

➾ቅባት ከተዋሕዶ ጋራ፥ ኑፋቄ ከአሚን(ከእምነት) ጋራ፥ ምርግትና ከጥንቆላ ጋራ፥ አውደ ነገሥት ከፍትሐ ነገሥት ጋር፥ ክህደት ከእውነተኛዋ ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ትምህርት ጋር፤ ምንም ኅብረት እንደሌላቸው አንጥሮ፥ ኵልል አድርጎ የመረዳት የማስረዳትም ግዴታ አለባቸው። ለዚኽም ነው፦

💒 "የቤተ ክርስቲያን መብራት አገልጋዮቹዋም የምትኾኑ ዲያቆናት ኾይ ተኵላ ከበግ ጋራ፤ ጭላት(ጭልፊ) ከርግብ ጋራ፤ ክርዳድ ከስንዴ ጋራ እንዳይኖር ከውስጥዋ ንቀሉ፤[ቅዳሴ አትናቴዎስ] እንዲል።

💒 ፫. ደጀ ሰላም፦ የሰላም ደጅ ናት።

የዲያቆናት አብነት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ መጽሐፈ ገድሉ ላይ "የቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ አምላክ እግዚአብሔርም የዚኽን ሰው የንስሓ እንባ ተመልክቶ ይቅር አለው። ይኽ ሰውም በዚያች ቤተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም ተቀምጦ የደረሰበትን ለሚገባውና ለሚወጣው ኹሉ መሰከረ።
" [ገድለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ዘወርኃ መጋቢት]

💢 ✍️ አኹንማ የተጣሉ የሚታረቁባት፦ የሰላም ደጅ የተሰኘችው "ደጀ ሰላም" ድረስ ቢራና ዘር ማንዘሮቹ ገብተው "ምን ይኹንልህ?!" ❓ ብለን ግሮሰሪ አደረግነው። በርግጥ መጠጥ ፈጽሞ የተከለከለ ባይኾንም፤ አብዝቶ መጠጣት ግን የተገባ አለመኾኑ ለኹላችንም ግልጽ ነው። ደጀ ሰላም "የሰላም ደጅ" እንጂ 'የቢራዎች ደጅ' አይደለችምና ባይገባ ይመከራል።

💒 ✍️በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ተፈቅደው ነገር ግን ከማይበረታቱ ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው። ፈጽሞ አይጠጣም፥ ርኵስ ነው ባንልም የማይጠጣ የተሻለ አደረገ።

➣"ከስካር ተጠበቁ ሙሴ በኦሪት ዘሌዋውያን እንዳይሰክሩ አዟቸዋል። እንዲሁ እናንተ ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስትና ዲያቆናት መጠጥን ከማብዛትና ከስካር ተጠበቁ፤ መዳራት፣ ዝሙት፣ ስግብግብነት፣ ሰውን መስደብና ማስቀየም፣ መታበይ፣ በሐሰት መማል፣ ብዙ ቁም ነገሮችን መዘንጋትና ሌሎችም ከስካር የሚመነጩ ናቸው።"[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፲፤ ቍጥር 56]

➛"ከስካርና ወይንን ከማብዛት ተጠበቁ፤ ቃለ እግዚአብሔር የሠፈረባቸውን መጻሕፍት መጠጣትን አዘውትሩ እንጂ።" [ዝኒ ከማሁ(Ibid) ቍጥር 57]

💒❤ ፬. የበቁ ዲያቆናት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅድስና ሥጋወደሙን ለመለወጥ ሲወርድ ማየት ይችላሉ።

➤"ካህን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ ላክ ባለጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመስዋዕትነት በቀረቡ ፅዋዕና ሕብስት ላይ መንፈስ ቅዱስ ይወርዳል፤ ዲያቆናት በቅድስና ሥጋወደሙን ለመለወጥ ሲወርድ ማየት ይችላሉ። የዲያቆናት ክብር በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ቅዱስ እስጢፋኖስ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ የክብር ቦታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሊሠጠው እንደቻለ ለነሱም ይሠጣል።"
[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፲፩፤ ቍጥር 33]

💒 ፭. ዛሬ ላይ ዲያቆናት የት ይገኛሉ? ምን ሲያደርጉ ይገኛሉ? ❓
ክቡር ዲያቆን ሆይ! "ዙረታም" ነኝ ካልክ የት መዞር እንዳለብህ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ይመክሩናል።

➣"ዲያቆናት የክርስቲያኖችን የመኖሪያ ቤት ወዳለበት ኹሉ እየዞሩ የተቸገሩትን ኹሉ ይጎብኙ፤ ችግራቸውንም ይመልከቱ። ጥዋትም ኾነ ማታ ምእመናኑ በስንፍና እንዳይያዙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲተጉ ያነቃቁዋቸዋል። በሠርክ በጧትና በማታም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ እየኼዱ ያመስግኑት፤ እግዚአብሔር የዕለት ብርሃን ነው፤ ኹሉንም ይረዳል።"
[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፱፤ ቍጥር 66]

💒 ፮. ዲያቆናት ምንም ዓይነት ጉቦ መቀበል፥ በደም ግባት ማዳላት፤ ድሀን አይቶ ባላየ ማለፍ፤ ዝም ብሎ ስለ ሴትና ወንድ በማውራት ዋዛ ፈዛዛ በመስማት- ነገረ ዘርቅ መስማት የለባቸውም።

➤ "እናንተም የመንጋዎች ጠባቆችና ዲያቆናት ሆይ መማለጃ በመቀበልና ፊት አይቶ በማድላት ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን ታወጡት ዘንድ በደል በሌለው በንጹህ ሰው ላይ ነገር ሥራንና የሐሰት ነገርን ትሰሙ ዘንድ አይገባም። እንደዚህ ያለ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች የዲያብሎስ ወዳጆች ይኾናሉና።"
[መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፲፥ ቍጥር 55]

➣ "ዲያቆናት ድኆች ሳይለምኗቸው ፈቃዳቸውን ሊያደርጉላቸው አገባብ ነው።"[መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፲፮፥ ቍጥር 55]

💒 ፯. ዲያቆን በድቁና የተካነ ካህን ነው። ቄስም በቅስና የተካነ ካህን ነውና በአጠቃላይ ማኅበረ ካህናት አይደለም በfb በሕዝባውያን መዋኛ ገንዳዎች እንዲዋኙና ለሕዝባውያን ገላቸውን እንዲያሳዩና ተገላልጠው እንዲታዩ፥ ቁንጣ፥ ጃፖኒ፣ ጥብቅብቅ የሚያደርጉ አልባሳት አድርጎ ውጭ መታየት ፈጽሞ አይፈቀድላቸውምና.... ❌

👌ጸጉር አቆራረጥንም በተመለከተ ለምዕመናን ሲገልጽ የቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን የሕግና የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው ፍትሕ መንፈሳዊ ወሥጋዊ "በተፈጠርህ ጊዜ እግዚአብሔር በሰጠህ መልክ ላይ መልክ አትጨምር። ያድግ ዘንድ ፀጉርህን አትከባከበው ተላጨው እንጂ አታሳድገው። ወጥመዳቸው ቅርብ የሆነ ሴቶችን ወደ አንተ ያመጣብህ ዘንድ አታሳምረው።

💢ረቂቅ ልብስ አትልበስ፤ ይህች ስሕተትን ታመጣለችና፤ ቀለም የተቀባ ጫማ አትጫማ፤ በጣቶችህ የወርቅ ቀለበትን አታድርግ፤ ይህ ሁሉ የዝሙት ምልክት ነውና። ጠጉርህን ግልስልስ ብጥር አታድርገው፤ አትሠራው፤ " [ፍትሕ መንፈሳዊ፤ አንቀጽ ፲፩፤ ገጽ. 123]
ፍትሐ ነገሥት ክፍል ፯
አንቀጽ ፯ ስለ ዲያቆናት ይናገራል።
፩) ዲያቆናት ጸጥ ያሉ፣ የሚታዘዙ ይሁኑ። ዲያቆናት ሁለት ሦስት ሰዎች መስክረውላቸው ይሾሙ። በአገልግሎት ሁሉ ይፈተኑ። ለሰው የሚያዝኑ የሚራሩ ይሁኑ። በቀለኞች ሳይሆን በቀልን የሚተው ይሁኑ። ቁጡ ብስጩ አይሁኑ።
_
፪) ዲያቆናት ባለጸጎችን ደስ የሚያሰኙ ነዳያንን የሚያሳዝኑ አይሁኑ። አንድነትን ሦስትነትን (ምስጢረ ሥላሴን) ለመማር ለማስተማር ይትጉ። ምዕመናንን በፍጹም ክብር ያክብሩ። ሰውን በማፈር እግዚአብሔርን በመፍራት ይኑሩ። ዲያቆን በአንብሮተ እድ ይሾማል። ቀሳውስት ዲያቆናትም ቆመው ይጸልዩለት።
_
፫) ሰው ተምሮ ከተገኘ ዲቁና በ7 ዓመት፣ በ12 ዓመት መሾም ይችላል። ሀገሪቱ ሰፊ ካልሆነች ሰባት ዲያቆናት ሊሾሙ ይገባል። ሀገሪቱ ሰፊ ከሆነች ኤጲስ ቆጶሱ እንደወደደ ይሹሙ። ዲያቆናት ከቤተክርስቲያን

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ስለ የፖርኖግራፊ አጭር ተከታታይ ትምህርት ተጀመረ ይከታተሉ


#ሰዎች_ለምን_ፖርኖግራፊ_ይመለከታሉ?

#የፖርኖግራፊ_ሱሰኝነት_ምልክቶች ?

#የፖርኖግራፊ_መዘዞች_ምንድናቸው?


#ከፖርኖግራፊ_ሱስ_እንዴት_መውጣት_ይቻላል?

እነዚህን ትምህርቶች ለማግኘት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠/channel/dnhayilemikael💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ቅዱስ_ቁርባን

#ምዕራፍ 2
#ክፍል 3

#ቅዱስ_ቁርባን_መቀበል_የማይገባቸው_እነማን_ናቸው?

👉ይህን ርዕስ ሥጋ ወደሙ ለማን? የሚለው ርዕስ በከፊሉ የሚዳስሰው ቢሆንም በራሱ ቁም ነገር
የሚያስጨብጥ ሆኖ ስላገኘሁት በአጭሩ ከዚህ በታች ማብራሪያ አቅርቤበታለሁ::

👉በመሠረቱ ቅዱስ ቁርባን ለሰው ልጆች መዳን የተሰጠ ጸጋ ቢሆንም ወደዚህ የሕይወት እንጀራ መቅረብ የማይገባቸው አሉ።

👉ክርስቶስን በወቅቱ ማን እንደሆነ ያላወቁና የተቃወሙ እንዳሉ ሁሉ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ያልገባቸውና ለቅዱስ ቁርባን ተቀራኒ ሕይወት ያላቸው ናቸው እነዚህም፣

👉ሀ/ በልዩ ልዩ የክህደት ጐራ የተሰማሩና ወንጌል ያልደረሳቸው በክርስቶስ የማያምኑ አምነውም ያልተጠመቁ::
«ኢየሱስም መለሰ እንዲህ ሲል እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም::» (ዮሐ 3÷5

👉ለ/ ሕብስቱ ተለውጦ ሥጋ አምላክ ወይኑ ተለውጦ ደመ አምላክ መሆኑን ያላመኑ አምነው የሚጠራጠሩ፡፡
«ኢየሱስም ስለ አየኸኝ አምነሃል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁእን ናቸው» አለው:: / ዮሐ 20:29/

👉ሐ/ ቅዱስ ቁርባን ኃጢአትን የሚያስተስርይ መሆኑን ያልተረዱና በተለይ ቅዱስ ቁርባን የሚዘጋጀው ለጻድቃን ሳይሆን ለኃጥአን እንደሆነ ያልገባቸው::
«የሰውን ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና አለው» ሉቃ 19: 10/

👉መ/ በቅዱስ ቁርባን የዘላለም ሕይወት የሚገኝ መሆኑን ተምረው ያላወቁ አውቀውም ለዚህ ጸጋ መንፈሳዊ ፍላጐት ጉጉት ለሌላቸው
«ኢየሱስም እንዲህ አላቸው የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም፡፡» /ዮሐ 6:35/

«በእውነት አምነው ከርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት ማስተስርያም ሊሆን የሚሰጥ የጌታችንና
የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ «እማሬ>>ነው። /ቅዳሴ ሐዋርያት

👉ሠ/ ከኃጢአታቸው ያልተመለሱ ያልተጸጸቱ ያልተናዘዙ በማን አለብኝነት ለመቀበል የሚፈለጉ በሰሩት ኃጢአት ንስሀ ያልገቡ
«አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ት ኢዩ 2 : 12 /
«ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሀ ግቡ ተመለሱም»
ሐዋ. 3፥20/

👉ረ/ ቆራቢ ለመባል ለታይታ ለከንቱ ውዳሴ ሰው ይየኝ ብለው ለመቁረብ የሚፈልጉ ግብዞች
«ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው
እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም» /ማቴ. 6: 17

👉ሰ/ የቅዱስ ቁርባን ጸጋና ምስጢር ሳይገባቸው ባልንጀሮቻችውን አይተው እንመሳሰል ብለው ለመቀበል የሚፈልጉ

👉ሸ/ የመናፍቃን ትምህርት የበረዛቸው የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት ቅዱስ ቁርባን አማናዊ /እውነተኛ/ አይደለም መታሰቢያ ነው እንጂ የሚሉ

👉ቀ/ መስለው ገብተው የክርስትናን ኃይማኖት የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን እናፈርሳለን ብለው ቅዱስ ቁረባንን እንይ ምስጠጕሩንም እናውጣ ብለው ለመቀበል የሚፈልጉ
«ከውሾች ተጠበቁ ከክፉዎች ሠራተኞችም መገረዝ ተጠበቁ / ፊልጵ 3:2/

👉በ/ ያለ እምነት በድፍረት ያለ ንስሀ በኃጢአት በመናቅ እንደ ምድራዊ ማዕድ በመቁጠር ለሚደፍሩ
እግዚብሔርን መፍራት በሕይወታቸው ለሌላ
«የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው
1 71
እንግዲህ በነዚህ በተዘረዘሩና በሌሎች ምክንያት
ቁርባንን ሳይገባቸው በድፍረት የሚቀበሉ ስለ በረከት
ፈንታ መርገምን ስለ ሥርየት ኃጢአት ፈንታ ገሃነመ እሳት ከክርስቶስ ዘንድ ይቀበላሉ።


ቃለ እግዚአብሔር ከመማር ከንስሐና ስጋውና ደሙን ከመቀበል ጋር ያልተባበረ አገልግሎት ምግባር ትሩፋት ...ሕይወት ??????



#ምዕራፍ 2
ክፍል 4
❖ባልና ሚስት ተነጣጥለው ብቆርቡስ??

ይቀጥላል .....

#ለሃሳብ_አስተያየት
👉 @DnIsraelYeArsemaLije 👈

ያለፈውን ክፍል ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/dnhayilemikael/4948

ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ቅዱስ_ቁርባን

#ምዕራፍ 2
#ክፍል 2

#ቅዱስ_ቁርባን_ለመቀበል_የተወሰነ_ዕድሜ_አለን??


👉ብዙ ጊዜ #ህፃናት እስከ ሰባት ዓመት ሲያቆርቡ ኖረው ከዚህ እድሜ ሲገፋ ወንዱን «ለአቅመ አዳም» ደርሰሀል መቁረብ አይገባህም ሴቷን «ለአቅመ
ሔዋንን ደርሰሻል>> ደርሰሻል መቁረብ አይገባሽም የሚለውን አባባል በአንዳንዶች ዘንድ ከአባበል አልፎ
እንደ ቀኖና /ህግ/ ተወስዷል።

👉#ወጣቶች በእድሜያቸው /በወጣትነታቸውን/ ምክንያት ብቻ ወደ ቁርባን መቅረብ እንደሌለበት
ሲነገርባቸው እንሰማለን፡፡
👉ራሳቸው ወጣቶች በዚህ ሰው ሰራሽ ትምህርትና ተራ አባባል ታምነው «ለአቅመ አዳም» «ለአቅመ ሔዋን>> ደርሻለሁ ወደ ቁርባን መቅረብ አይገባኝም ሲሉ ይደመጣሉ።

🙏👉#የሚገርመው ወጣትነትን በራሱ ብቻ እንደ #ኃጢአተኝነት ወይም ለቅዱስ ቁርባን ብቃት የሌለው ሕይወት አድርጐ መውሰድበራሱ ትልቅ ስህተት ነው:: 👉እንዲህ አይነቱን አባባል የሚቀበሉና
እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ወጣቶች ወደ ሥጋ ወደሙ መመለስ የሚገባቸው በስተርጅና አይን ሲፋዝ ጉልበት /ሲደነዝዝ/ እንደሆነ ይስማማሉ፡፡

👉ይህንም ኣስተሳሰብና አባባላቸውንለማጠናከር የሚጠቀሙበት ቢሂል አለ እርሱም <<ጣጣውን ሲጨርስ /ስትጨርስ />> የሚሉት ነው:

👉እዚህ ላይ ለአንባብያን ላስገነዝብ የምወደው እነዚህ ሰዎች በራሱ ኃጢአት «ጣጣ መሆኑን>> መመስከራቸውን ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳስመሰከራቸው ልብ እንድትሉት ነው.

👉ታዲያ በዚህ አባባል ሰው ኃጢአትን ሲሠራ እንዲኖር ወይም ኃጢአት ለመሥራት ተስማሚው እድሜ ይህን ወጣትነት አድርጐ እንደ መመደብ የሚቆጠር አባባል ነው::

👉ለሁሉም #መልሱን የሚሰጠው የወንጌሉ ቃልና የቤተ ክርስቲያኒቱ ህግና ሥርዓት ስለሆነ ከዚህ በታች
በአጭሩ እንመልከት፡፡

👉ታላቁ ሰው ንጉሱና ነብዩ ሰሎሞን « #በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» (መክ 12 1/ በማለት ሰው በጉብዝናው እድሜ ራሱን ለአምላኩ እንዲያቀርብ በቅዱስ ቃሉ ይጣራል ቤተ ክርስቲያኒቱም ብትሆን መሥዋዕቱ በሚለወጥበት በታላቁ ጸሎት
በጸሎተ ቅዳሴው/ ለተዘጋጀውና ለቀረበው የሕይወት ማዕድ ምዕምናኗን ስታዘጋጅ ካህኑ የሚለው
« #በወጣትነት_እድሜ_ያላችሁ_አትቅረቡ_ሳይሆን
« #ንጹህ _ያልሆነ_ግን_አይቅረብ/ ነው
👉 እንግዲህ #ባጠቃላይ ከነቢያት ወገን ወጣቶች አሉ እግዚአብሔር እነ #ሶምሶንን እነ #ጌድዩንን ለሚፈልገው አምላካዊ ዓላማው የጠራቸው
#በጉብዝና እድሚያቸው ነው፡፡

👉ጌታ የቁርባንን ሥርዓት ሲሠራ ከነበሩት ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት #ወጣቶች ነበሩበት

👉በየትኛውም እድሜ_ለሚገኙ ክርስቲያኖች ኃጢአት የሚሰሩበት እድሜ ስ#ላልተመደበላቸው
ወደ ቅዱስ ቁርባን #ለመቅረብና #ላለመቅረብ የተመደበም እድሜ የለም ወደ ሕይወት እንጀራ ወደ ሥጋ ወደሙ ወደሙ ለመቅረብ መስፈርቱም እድሜ ሆነ መወሰድ የለበትም::


#ምዕራፍ 2
ክፍል 3
❖ ቅዱስ ቁርባን መቀበል የማይግባቸው
እነማን ናቸው?

ይቀጥላል .....

ያለፈውን ለማግኘት ክፍል ለመግኘት 👇👇👇👇👇
/channel/dnhayilemikael/4946

ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ቅዱስ_ቁርባን

#ምዕራፍ 2
#ክፍል 1

#ቅዱስ_ቁርባን_ለማን???

«ኢየሱስም መልሶ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች
መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ልጠራ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው /ሉቃ 5:31
ይህን ቃል መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው።ከኃጢያተኞች ጋር በማዕድ በመቀመጡ ፈሪሳውያን ለምን ከኃያተኞች ጋር ይበላል በማዕድ ይቀመጣል ብለው በማንጌራራቸው የተነሳ ነው ::
ለነዚያ ኃጢአተኞች የሚያስፈልጋቸው መድኃኒት ወነፍስ እርሱ እንደሆነ መለሰላቸው እንጂ ያመጣው ለጻድቃን ለንጹሀን እንደሆነ አይደለም የተናገረው::

👉ቅዱስ ቁርባን ለማን የሚለው ጥያቄ በእያንዳንዱ ሕይወት የራሱ የሆነ አንድምታ ትርጉም የሚሰጠው
የአብዛኛው አመለካከት አማኙን ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቅና የወንጌሉ ቃል ተቃራኑ ሆኖ እናገኘዋለን ::
👉ይሁንና በዚህ ምዕራፍ ቅዱስ ቁርባን የሚገባቸው እነማን
እንደሆኑ በዝርዝር ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

#ቅዱስ_ቁርባን_የሚግባቸው ።

👉ሀ/ #የመሥዋዕቱን_መለወጥ_ለሚያምኑ ሕብስቱ ተለውጦ ሥጋ አምላክ ወይኑ ተለውጦ ደመ አምላክ መሆኑን ከልብ ያለ ጥርጥር አምነው ለሚኖሩ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸውን ቃል በእምነት ተቀብለው ለሚከተሉ::
«ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን ኣንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ብሉ ይህ ስጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋንአንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእር
ጠጡ ይህ ደሜ ይህ ነው»
/ማቴ 26.26/

👉 ለ/ ይህ ቅዱስ ቁርባን ለኃጢአት እድፍ መንጺሒ ለኃጢአት ቁስል ፈውስ የተሰጠ መሆኑን ላመነ ባጠቃላይ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ መሆኑንና የዕለት የዕለት የኃጢአት በሽታ መድኃኒትነቱን ለተቀበለ
በተለይ የሚዘጋጀው ለፃድቃን ሳይሆን ለኃጥአን መሆኑን ከልብ ላመኑ ለተቀበሉ «በእውነት አምነው ከእርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት የኃጢአት ማስተስረያም ሊሆን የሚሰጥ የጌታችንና የአምላካችንየኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ «እማሬ ነው ቅዳሴ ሐዋርያት«እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢ ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው »
/ማቴ. 26 27

👉ሐ/ የዘለዓለም ሕይወትን የሚያስገኝ መሆኑን አምነው የዘላለም
ሕይወት ያሰጠኛል ብለው ለሚቀርቡ

«ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት
አለው እኔም በመጨረሻ ቀን አስነሳዋለሁ»
ዮሐ 6:53/

👉መ/በሚቀበሉት ቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ ከእርሱ ጋር እነርሱ
ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነው እንደሚኖሩ ሥጋው ከሥጋቸው ደሙ ከደማቸው ተዋህዶ አምላካቸው ከእነርሱ ጋር በጸጋ ተዋህዷቸው እንደሚኖር ለሚያምኑ

«ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ (ዮሐ 6:56/

👉ሠ/ በተጨማሪ በቀደመ ኃጢአታቸው ለተፀፀቲ ለተናዘዙ
ለተመለሱ ከሚመጣው ኃጢአት ለሚጠበቁ ነው::

«ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል
እየሰበከና ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ፡» /ማር |: | 4.
ይህን ሁሉ እውነትና የወንጌሉን ቃል በተረትና በጌታ ባሕል እየሸፈኑ የራሳቸውን አስተሳሰብ ያስተጋቡ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህንን ጸጋ የተጋፉ ናቸው።

#ምዕራፍ 2
ክፍል 2
፨ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተወሰነ ዕድሜ አለን???

ይቀጥላል .....

ጥያቄ ሃሳብ በዚህ አድርሱን👇👇👇 @Dnzearsema


ያለፈውን ለማግኘት
ምዕራፍ አንድ ክፍል 2 ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 /channel/dnhayilemikael/4941


👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ከፖርኖግራፊ_ሱስ_መውጫ_መንገዶች

🥀ፖርኖግራፊ የሞራል ችግር ውድቀት ተብሎ በአብዛኛው ቢታይም ከዛ ባለፈ በዋነኝነት ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ችግር ነው።

🥀ስለ ፖርኖግራፊ ስንነጋገር ከላይ እንደተጠቀሰው አይምሮአችን እንዴት እንደሚሰራ መረዳቱ አስፋላጊ ነው። ለምሳሌ አንዲት እናት ልጅዋን በደረትዋ አስደግፋ በምታጠባበት ጊዜ አዕምሮዋ ‘ኦክሲቶሲን’ የሚል ‘ኒውሮኬሚካል’ ይፈጥራል።

🥀ይህም ኬሚካል አንዲት እናት በውስጣዊ ስሜትዋ ከልጅዋ ጋር እንድትተሳሰር የሚያደርግ ሲሆን፣ በሩካቤ ጊዜ ሰውነታችን የሚኖረው የኬሚካል ሁደትም ይህን ይመስላል።

🥀ፈጣሪ በሰውነታችን የሚለቀቀውን ይህን የኬሚካል ሁደት፣ በባለትዳሮች መካከል የሚደረግ ወሲብን ተከትሎ ስሜታዊ ትስስር የመፍጠር አላማ ቢኖረውም፤ ከትዳር ውጭ በሚኖር ሩካቤ ድርጊት ውስጥ ደግሞ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል።

🥀ሰዎች ፖርኖግራፊ በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚለቀቁት እነዚሁ የ‘ኦክሲቶሲን’ ‘ኬሚካሎች’ ተመልካቹ ከሚመለከተው ምስል ጋር ስሜታዊ ትስስር እንዲኖረው ያደርጋል። በግለ ሩካቤ ሱስም ውስጥ ያሉ ሰዎችም በእነዚህ ኬሚካሎች ከራሳቸው ጋር ትስስር ይፈጥራሉ።

🥀በተደጋጋሚ የሚደረግ ማናቸውም ነገር በአይምሮ ላይ እንዳላቸው ተፅህኖ ሁሉ ፖርኖግራፊም የአይምሮአችንን ቅርፅ በመቀየር በፖርኖግራፊ እስራት ውስጥ መውደቅ ያስከትላል። ስለዚህ ስለፖርኖግራፊ እስራት መውጫ መንገዶች ስናወራ ወደ ሱሱ ሊመሩ የሚችሉ ነገሮችን፣ ተያያዥ ባህሪዎችን እና አመለካከቶችን አብረን ማንሳት ይኖርብናል። ከሁሉ ቀዳሚው ነገር ከላይ እንደጠቀስነው ችግሩ እንዳለ ማመን ነው።

🥀እንግዲህ ከፖርኖግራፊ ሱስ ለመውጣት የምትፈልጉ ወገኖች ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡትን ተግባራዊ ነጥቦች ብትከተሉ ከእግዚአብሔር ፀጋ ጋር 100% ልትወጡ እንደምትችሉ አረጋግጥላችኋለው። ይሄን ጽሁፍ ስታነቡ ወረቀትና እስኪብርቶ ይዛችሁ ለተቀመጡት ጥያቄዎች በፅሁፍ መልስ እየሰጣችሁ እለፊ..

1
#ልዑል_እግዚአብሔር_እንደሚወዳችሁ_ #አውቃችሁ_ንሰሐ_ግቡ

🥀በዚህ ሱስ ውስጥ የገቡ ሰዎች እግዚአብሔር እንደሚጠላቸውና እንደሚጸየፋቸው ያስባሉ። እንዲህ አይነቱ ሃሳብ ሰዎችን የሱሱ ባሪያ አድርጎ ለማኖር ሰይጣን ይጠቀምበታል።

🥀በፖርኖግራፊ ሀጢያት መውደቅን ተከትሎ ሰይጣን ሁልጊዜ እዛው ተብትቦ ሊያስቀረን ይጥራል። ይህም ራሳችንን እንድንጠላ፣ እግዚአብሔር ለእኛ ግድ እንደማይለውና ሩቅ እንደሆነ እንድናስብ እና ተስፋ ቢስነት እንዲሰማን ሀሳባችንን በመያዝ ይተጋል። ሁሌም ቢሆን ውድቀትን ተከትሎ ዋና ጠላታችን ማን እንደሆነ ማወቁ ተገቢ ነው።

🥀በጥፋታችን ማዘናችን ተገቢ ቢሆንም እንደ ይሁዳ ወደ ከፋ እርምጃ የሚወስድ መሆን የለበትም። (ማቴ 27:4-5) ራሳችንን በመጥላት ውስጥ ዋዥቀን ራሳችንን የመቅጣት አዝማሚያው ቢኖረንም መውሰድ ያለብን እርምጃ በእግዚአብሄር ፊት እንደ ዳዊት በንስሃ መደፋት ነው (መዝ 51:1- 10) በእኛ እና በኃጢያታችን መካከል ልዩነት አለ።

🥀እግዚአብሔር ኃጢአትን ይጠላል፤ ኃጢያተኛውን ግን ይወዳል። እናት የልጅዋ ልብስ ቢቆሽሽ ለልጅዋ ያላት ፍቅር እንደማይቀየር እግዚአብሔርም ለእኛ ያለው ፍቅር አይቀየርም። ከዚህ ህይወት ወጥታችሁ ወደ እርሱ ለመምጣት ብትወስኑ እጆቹን ዘርግቶ ይቀበላችኋል።

🥀በቀራንዮ ላይ የፈሰሰው የኢየሱስ ደም ከኃጢያታችሁ ሁሉ እንደሚያነጻችሁ አምናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ ግቡ። “የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ዮሐ 1:7) የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለ ዓለም ሁሉ ስለፈሰሰ በእግዚአብሔር ፊት ይቅር የማይባል ኃጢያት የለም።

2. #አምናችሁ_ጸልዩ

🥀የሰው ልጅ በራሱ ጥረት ከኃጢአት መውጣት አይችልም። የእግዚአብሔር ጸጋ ሲያግዘው ግን የማይቻለውን ችሎ በቅድስና አሸብርቆ መኖር ይቻላል።

🥀እስከ ዛሬ በግል ጥረታችሁ ከዚህ ሱስ
መውጣት ስላልቻላችሁ ተስፋ ቆርጣችሁ ሊሆን ይችላል። ጸጋው ግን ጣልቃ ገብቶ አዲስ ህይወት ሊሰጣችሁ ይችላል። ይህ ደግሞ የሚሆነው “እኔ ደካማ ስለሆንኩ የሚረዳኝ ጸጋ ይሰጠኝ” ብሎ በጸሎት እግዚአብሔርን በመለመን ነው። በፀሎት ትጉ (ኤፍ 6:18)።

🥀መውጣት እንደሚቻል አለማመን በራሱ ሰንሰለት ነው። የእግዚአብሔር ፀጋ ታሪክን እንደሚቀይር ከዚህ ህይወት መውጣት እንደሚቻል እመኑ። ምክንያቱም ከኃጢያት አስወጥቶ ቅዱስ የሚያደርግ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጧልና። (ቲቶ 2:11-13)

3. #ሀሳብን_በሀሳብ_ተዋጉ

የፖርኖግራፊ ኃጢያት ስርወ-መሰረቱ ሀሳብ አንደመሆኑ ሀሳብን ልንዋጋው የምንችለው በሌላ ሀሳብ በመተካት ብቻ ነው። አዕምሮእችንን በእግዚብሄር ሀሳብ ለመሙላት ደግሞ ዕለት ዕለት የእግዚአብሄርን ቃል በማንበብ እና በፀሎት ጊዜ ማሳለፍ ያስፈልጋል። ደስታችንን በእግዚአብሄር ስናገኝ በሀጢአት የምናገኘውን ጊዜያዊ ደስታ እየተፀየፍን እንሄዳለን።

4. #ለምን_እንደምታዩ_እወቁ

አንዲት እህት ከ 4ዓመት በፊት አስገድዶ መደፈር ደርሶባት ነበር። ሌሊት ስትተኛ ያለፈችበት እየታወሳት ትጨነቅ ነበር። ከዚህ ስቃይ ማምለጫ ያደረገችው ፖርኖግራፊ መመልከት ነበር።

🥀ለዚህች እህት ፖርኖግራፊ መመልከት የችግሩ መገለጫ እንጂ ዋናው ችግሩ እንዳልነበር ነው። ከዚህች እህቴ ጋር ጊዜ ወስደንም ስናወራ አሰቃቂ ከሆነ ጉዳት በኋላ ሰዎች የሚኖራቸው የስነ ልቦና መቃወስ /Post Traumatic Stress Disorder/ እንዳለባት ማረጋገጥ ችያለሁ።

🥀ፖርኖግራፊ መመልከት ሰዎች በህይወታቸው ያልፈቱት የውስጣዊ ችግር መገለጫ ሊሆን ይችላል። ጊዜ ወስዳችሁ በሕይወታችሁ የሚያስጨንቃችሁን ነገር፤ ያለፋችሁበትን ታሪክ ለመለየት ሞክሩ። ችግሩን በውስጣችንን ተጭኖ ለማስቀረት (repress) ለማድረግ መሞከር ወደ ባሰ ችግር ይወስዳልና ችግሩን ተጋፍጣችሁ መፍትሄ ለመስጠት ሞክሩ።

5. #ቀስቃሽ_ነገሮችን_ለዩ

ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች ለራሳችሁ መልሱ።
• በብዛት ፖርኖግራፊ የምታዩት የትኛው ሰአት ላይ ነው?
• ለመጨረሻ ጊዜ ፖርኖግራፊ ያያችሁት መቼ ነው?
• ፖርኖግራፊ ከመመልከታችሁ በፊት ምን አይነት ስሜት (mood) ላይ ነበራችሁ?

🥀ቀስቃሽ ነገሮቻችሁ ምንድን ናቸው ስሜትን የሚያነሳሱ የሙዚቃ ክሊፖች ወይንስ ፊልሞች? አንዲት እህቴ ፖርኖግራፊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች የምታገኘው ከፌስ ቡክ ላይ ነበር። ከዚህ ህይወትም ሙሉ ለሙሉ መውጣቷን እስክታረጋግጥ ድረስ ፌስቡክ መጠቀሟን አቆመች።

🥀ከዚህ በፊት የሰበሰባችሁት ፊልምና ማንኛውም ነገር አሁኑኑ አስወግዱ። ለዚህ ዓላማ የምታገኙአቸው ሰዎች ካሉ ግንኙነታችሁን አቋርጡ። ኢንተርኔት መጠቀም ማቆም ካለባችሁ አድርጉት። ግድ መጠቀም ካለባችሁም ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ተጠቀሙ። ወይም እንደ ‘Covenant eyes’ ወይም ‘X3watch’ ያሉ ፕሮግራሞችን ተጠቀሙ ከሕይወታችሁ የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና!

🥀ወደ ፖርኖግራፊ የሚገፋፋችሁ ጭንቀት ከሆነ ከጭንቀት መውጫ ሌሎች መንገዶችን ፍጠሩ። ስሙን ሳልጠቅስ ታሪኩን እንዳጋራ የፈቀደልኝን የአንድነትና ወንድምን ሕይወትም ላንሳ፤ “ከሚስቴ ጋር ባለን ህይወት ደስተኛ አይደለሁም።

🥀እቤት መሄዴን ሳስብ ጭንቀት ይወረኛል። መደበሪያዬ ፖርኖግራፊ ሆኖ ለዘመናት ኖርኩኝ። የትዳሬን ችግር መፍታቴ ከፖርኖግራፊ ሱስ አስመለጠኝ”።
የእናንተን ቀስቃሽ ነገርን ጻፉት።

6. #ታገሉ!

🥀ከዚህ ሱስ መውጣት ሂደት ነው። ለማቆም ከወሰናችሁ በኋላ እንኳን መ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ አትክልተኛ መስሏት ነበር +

መግደላዊት ማርያም በዕለተ እሑድ ገና ጨለማ ሳለ ወደ ጌታ መቃብር ልትሔድ ተነሣች፡፡ እርግጥ ነው በጨለማ መውጣት ያውም ለሴት ልጅ የሚያስፈራት ቢሆንም ለዚህች ቅድስት ግን ከክርስቶስ ሞት በላይ ሌላ ጨለማ ገዝፎ ሊታያት አልቻለም፡፡ የሕይወትዋ ብርሃን በመቃብር ውስጥ አድሮአልና ሌላ ብርሃን ነግቶ መንገድ እንዲያሳያት አልጠበቀችም፡፡ ለሰው ሁሉ የሚያበራውን መብራት ክርስቶስን ከመቃብር ዕንቅብ በታች ካኖሩት ሦስት ቀን መሆኑ እንጂ የቀንና ሌሊቱ ልዩነት አልታወቃትም፡፡

በእርግጥም ሰባት አጋንንት ከላይዋ ላይ አውጥቶላት የነበረችን ሴት የቱ ጨለማ የቱ ጋኔን ሊያስፈራት ይችላል? ‹‹ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል››ና ጨለማውን ሳትፈራ ይህች ሴት እስኪነጋ ልቆይ ሳትል ወደ ጌታችን መቃብር ገሰገሰች፡፡

እንደጠበቀችው ግን ጌታችንን በመቃብር አላገኘችውም፡፡ በዚያ የለም፡፡ በመቃብር አለመገኘቱ ለእርስዋም ሆነ ለደቀ መዛሙርቱ ተስፋ የሚያስቆርጥ ኀዘን ላይ የሚጥላቸው ነገር ሆነ እንጂ ‹‹እነሣለሁ›› ማለቱን እንዲያስታውሱ ምክንያት አልሆናቸውም፡፡ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን እንኳን ጲላጦስ ፊት ቀርበው ‹‹ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ፡- ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን›› ብለው ነበር፡፡ (ማቴ. 27፡63) ሐዋርያቱና ማርያም መግደላዊት ግን መቃብሩ ባዶ ሆኖ ሲያዩ እንኳን ‹እነሣለሁ› እንዳለ ትዝ አላላቸውም፡፡ ስለዚህ የእምነት ጉድለታቸውም ደቀ መዛሙርቱን ‹‹እናንተ የማታስተውሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ›› ብሎ ፤ እርስዋን ደግሞ ‹‹አትንኪኝ›› ብሎ ገሠፆአቸዋል፡፡ (ሉቃ. 24፡25፣ ዮሐ. 20፡ 17)

መግደላዊትዋ ጌታችንን በመቃብር ብታጣውም ‹በዚህ ከሌለማ ወደ ቤቴ ልሒድና ልረፍ› ከማለት ይልቅ በዚያው ቆማ ታለቅስ ጀመር፡፡ ከዚህ በኋላ በዕንባ በፈዘዙ ዓይኖችዋ ሁለት መላእክት ከመቃብሩ ግራና ቀኝ ሆነው ተቀምጠው አየች፡፡ ሳታስተውልም ‹‹ጌታዬን ወስደውታል›› አለቻቸው፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳብራራው) መላእክቱ ወደ ውጪ ሲያዩ ዓይናቸውን ተከትላ ዘወር ስትል ጌታችንን ቆሞ አየችው፡፡ ሆኖም አላወቀችውም፡፡

‹‹ኢየሱስም አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሻለሽ ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት፡፡ እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሏት ፡- ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው›› (ዮሐ. 20፡15)

ይህንን ተከትሎ ጌታችን ስላለማመንዋ ገሥፆአት ማንነቱን ገለጸላት፡፡ በዚህም ይህች ቅድስት ትንሣኤውን ከሰበኩ የጽዮን ልጆች አንዲትዋ ሆነች፡፡ የእስራኤልን ነጻ መውጣት የሙሴ እኅት ማርያም በከበሮ እንዳበሠረች ማርያምም የሰው ልጅን ነጻ መውጣት ያለ ከበሮ አወጀች፡፡ እርስዋን ብቻም ሳይሆን ሌሎች ሴቶችንም ዓርብ ዕለት እያለቀሱ ደረት እየመቱ ሞቱን በዕንባ አጅበዋልና እሑድ ዕለት የትንሣኤው ዜና አብሣሪዎች ለመሆን አበቃቸው፡፡ ሴት ልጅን ‹‹ደስ ይበልሽ›› በማለት የተጀመረው የአምላክ የማዳን ሥራም ሴት ልጅ ራስዋ ለሌሎች ‹‹ደስ ይበላችሁ›› ባይ እንድትሆን በማድረግ ተጠናቀቀ፡፡

ማርያም መግደላዊት ‹‹የአትክልት ጠባቂ መስሏት ነበርና ፡- ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው›› የሚለው ንግግር እንዲሁ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን ይህንን ቃል የተናገረችው ሳታውቀው ቢሆንም ንግግርዋ ግን ከስኅተትነቱ ይልቅ ቅኔነቱ የሚበልጥ ንግግር ነው፡፡ ‹‹አትክልተኛ መስሏት ነበር›› የሚለው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው? አበው በትንቢተ ሕዝቅኤል 44ን ሲተረጉሙ ‹ከእውነት የሚሻል ስኅተት ከመግደል የሚሻል መሳት አለና›› ያሉት ይህንን ዓይነቱን ሳይሆን አይቀርም፡፡

ለመግደላዊት ማርያም ክርስቶስ አትክልተኛ መስሏት ነበር፡፡ ወይ ግሩም! ክርስቶስ በምድር በተመላለሰ ጊዜ ለሰዎች ‹ያልመሰላቸው› ምን ነገር አለ? እንደተወለደ ለአይሁድ ‹የዮሴፍ ልጅ መስሏቸው ነበር› ፣ ለሔሮድስ ደግሞ መንግሥቱን የሚቀናቀን ምድራዊ ንጉሥ መስሎት ነበር፡፡ ለኒቆዲሞስ ነቢይ መስሎት ነበር ፣ ለሳምራዊቷ ሴት ደግሞ መጀመሪያ ውኃ የሚለምን ተራ ሰው መሰላት ፣ በኋላ ደግሞ ነቢይ መስሎ ታይቷት ነበር፡፡ ክርስቶስ ለብዙዎ ያልመሰላቸው ምን አለ? ለግማሹ ኤልያስ ፣ ለአንዳንዱ ሙሴ ለሌላው ኢያሱ መሰለው፡፡ ለኤማሁስ ተጓዦች ‹መንገደኛ› ፣ ለሮም ወታደሮች ‹ወንጀለኛ› ፣ ለሔሮድስ መኳንንት ‹አስማተኛ› መስሏቸው ነበር፡፡ እኛ እርሱን እንድንመስል እርሱ እያንዳንዳችንን መስሎ ተሰደበ ተወቀሰ በመከራ ተሰቅሎ ሞተ፡፡ ዛሬ ደግሞ ለመግደላዊት ማርያም ‹‹አትክልተኛ›› መሰላት፡፡
ማርያም ሆይ በአንድ በኩልስ ልክ ብለሻል፡፡ ያየሽው እርሱ አትክልተኛ ነው፡፡ በእውነትስ አትክልተኛ ካልሆነ ‹‹አዳም ሆይ ወዴት ነህ›› እያለ በገነት ዛፎች መካከል ምን አመላለሰው? አንቺ አልተሳሳትሽም ‹‹ወይንን ተከልሁ አላፈራም ፣ ለወይኔ ያላደረግሁት ምን አለ? በእኔና በወይኔ መካከል ፍረዱ›› ብሎ የጠራን እርሱ አይደለምን? ‹‹ዘር ዘሪ ሊዘራ ወጣ ፣ ዘር ዘሪው እኔ ነኝ ፤ አጫጆቹ መላእክት ናቸው›› ብሎ በምሳሌ ያስተማረ እርሱ አይደለምን? ከዚህ በላይ አትክልተኛ ከየት ሊመጣ?

‹የወይን ሥፍራን ነበረችው ቅጥርም ቀጠረላት› በተባለችዋ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁላችንን ከአብ ጋር ላንነቀል የተከለን ፣ የጎኑን ውኃ እያጠጣን ፣ በመስቀሉ እየኮተኮተ የሚያሳድገን ‹‹ጳውሎስ ሲተክል አጵሎስ ሲያጠጣ ጌታ ያሳድግ ነበረ›› የተባለለት አትክልተኛ እርሱ አይደለምን? ሦስት ዓመት ተመላልሶ ፍሬ እያጣብን አዘነ እንጂ ፣ እሾኽና አሜከላ እያበቀልን አስመረርነው እንጂ እርሱስ ብርቱ አትክልተኛ ነበር ፤ ስለዚህ መግደላዊት ማርያም ሆይ አትክልተኛ ቢመስልሽም አልተሳሳትሽም፡፡

‹‹ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ›› የሚለው ጥያቄም ቢሆን ከእውነታው አንጻር እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ጌታን በእርግጥ ከመቃብር ማን ወሰደው? ማንስ አስነሣው? ራሱ አይደለምን፡፡ ማርያም ‹አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ› አለችው፡፡ ማርያም ሆይ ጥያቄሽ ተገቢ ነው ፤ ብቻ አጥብቀሽ ጠይቂው ፤ የወሰደው እርሱ ራሱ ነው፡፡ ሥጋውን ከመቃብር ሕያው አድርጎ ነስነሥቶ የወሰደው ከፊትሽ ቆሟል፡፡ ማስረጃ ከፈለግሽ ‹‹ነፍሴን ደግሞ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ፤ ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ›› ብሎ ሲናገር ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ሰምቶ ማስረጃ መዝግቦ ይዞበታል፡፡ አጥብቀሽ ያዢው! እንዳትለቂው! በፈቃዱ እንደሞተ ነፍሱንም ሊያኖራት ሥልጣን ያለው ከመቃብርም በሥልጣኑ የተነሣው እርሱ ነው፡፡ ማንም ወሰደው ሲሉ ብትሰሚ አትመኚ ፤ ኢየሱስን ከሙታን መካከል ወስዶ ሕያው ያደረገው ይኸው ከፊትሽ የቆመው አትክልተኛ ራሱ ኢየሱስ ነው፡፡

እግሮቹን ወድቀሽ ያዢ እንዳትለቂው ፤ ይህ አትክልተኛ ባዶ ያደረገው መቃብርን ብቻ እንዳይመስልሽ፡፡ ሲኦልን ብታዪ ምን ልትይ ነው? በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የራሱን መቃብር ባዶ ከማድረጉ በፊት የሲኦልን የብረት መወርወሪያ ሰባብሮ አእላፋት ነፍሳትን ዘርፎ ወደ ገነቱ ወርዶ ነበር፡፡ በዚያም ምርኮውን ሸሸገ፡፡ አሁን ደግሞ የቀረውን መቃብር ባዶ አድርጎት ቆሟልና እንዳትለቂው፡፡

መግደላዊት ማርያም ሆይ ‹‹አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ለቅዱስ_እዲንበቃ_ምን_እናድርግ

ስለቅዱስ ቁርባን ተከታታይ ትምህርት
በ @dnhayilemikael 👈 በዚህ ቻነል ተጀመረ

#ምዕራፍ_አንድ

#ቅዱስ_ቁርባን_ስለፈለጉ_ብቻ_የሚገቡበት_ሕይወት_አይደለም
❖ ምክረ ካህን
❖ ሰው ግን ራሱን ይፈትን
#ምዕራፍ_ሁለት
#ቅዱስ_ቁርባን_ለማን
❖ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተወሰነ
እድሜ አለን
❖ ቅዱስ ቁርባን መቀበል የማይግባቸው
እነማን ናቸው?
❖ ባልና ሚስት ተለያይተው ቢቆርቡስ?
❖ ያላገባ ወጣት መቁረብ ይችላልን?
❖ ቆራቢ የሆነ ሰው የትዳር ጓደኛውን በሞት
ቢያጣ ደግሞ ሌላ ማግባት ይችላል?
❖ ሕጻናትን ማቁረብ
#ምዕራፍ_ሶስት
#ቅዱስ_ቁርባን ለመቀበል የሚደረግ ዝግጅት
❖ ከመቁረብ በፊት
❖ ሰመቁረብ ጊዜ
❖ ከመቁረብ በኋላ
#ምዕራፍ_አራት
#ከቅዱስ-ቁርባን_የሚያርቁ
❖ ስለ እምነት ምንነት አለመረዳት
❖ እምነት ምንድን ነው?
❖ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ
ማሰኘት አይቻልም
#ምዕራፍ_አምስት
#ንጹህ_ያልሆነ_ቢኖር_አይቅረብ
❖ ሳይገባው ማለቱ ምን ማለቱ ነው?
❖ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት
#ምዕራፍ_ስድስት
#የተሣሣቱ _አባባሎችና_የመንደር_ወሬ
❖ የታመመን ሰው ቢያቆርቡት ቶሎ ይሞታል
❖ የቆረበ ሰው ብቻውን ቢሆን ሰይጣን ያገኘዋል
❖ ያላገባ ሰው መቁረብ አይገባውም
❖ ነፍሰ ጡር ሴት መቁረብ አይገባትም
❖ ጋብቻቸውን በሥርዓተ ተክሊል ያልፈጸሙ
ሰዎች መቁረብ አይችሉም
❖ ፍቅረኛሽ እንዳይክድሽ ተያይዛችሁ ቁረቡ
#ምዕራፍ_ሰባት #ቅዱስ_ቁርባንን_እንደ_ጐጂ_መቁጠርና_ሸሽቶ_መኖር
❖ ትዕግሥቱን መናቅ ነው
❖ ቸርነቱን አለመታመን ነው
❖ ፍቅሩን አለመረዳት ነው
❖ መድኃኒትነቱን አለማወቅ ነው
#ምዕራፍ_ስምንት
#የቅዱስ_ቁርባን_ጥቅም
❖ ዘላለማዊ ድህነት እንቀበልበታለን
❖ ኃጢአታችን ይሰረይበታል
❖ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት ይኖረናል
ኃይል መንፈሳዊ አንቀበልበታለን
❖ ክርስቲያኖችን ሁሉ እንደ አንድ አካል ያደርገናል
❖ በሥጋ ወደሙ እንማጸንበታለን
#ምዕራፍ_ዘጠኝ
#የቅዱስ_ቁርባን_ስጦታ_በኛ_ላይ_ያለው_የፍቅሩ_ማረጋገጫ_ነው
❖ በሥጋ ወደሙ ተወስነው ለሚኖሩ
❖ በሥጋ ወደሙ ለመወሰን ለተነሱ
❖ ከሥጋ ወደሙ ርቀው ለሚኖሩ
❖ ቅዱስ ቁርባን የምንቀበልባቸው ዕለታት
❖ ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት
የሚጸለይ ጸሎት



ትምህርቶቹን በተከታታይ መርሐ ግብር እንከታተል አንድ ክርስቲያን ሥጋውንና ደሙን ካልተቀበለ ወይም የማይቀበል ከሆነ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት የለውም


#ትምህርቱን_ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ቅዱስ_ቁርባን

👉 #ማሳሰቢያ_ላትጨርሱ_አትጀምሩ

#ምዕራፍ_አንድ
#ቅዱስ_ቁርባን_ስለ_ፈሰጉ_ብቻ_የሚገቡበት_ሕይወት_ይደሰም

#መግብያ
«ሰው ግን እራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ
ከጽዋውም ይጠጣ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ
ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ይጠጣልምና /1ቆሮ 1: 27/
በዚህ ርዕሳችን በሰፊው የምንመለከተው ተያይዞ የተጠቀሰውን የሐዋርያውን መልዕት ተንተርሰን ሲሆን በዚህ ሥር ከ2 ያላነሱ ነጥቦችን ጨምረን እንመለከታለን፡፡
ማንኛውም አማኝ ስለፈለገ ብቻ ተንደርድሮ የሚገባበት ሕይወት ሳይሆን ቅዱስ ቁርባን አስቀድሞ ወደ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት ሲገባ የሚከተለውን ነገር ጠንቅቆ ማወቅና ወድዶና ፈቅዶ ስለ ቅዱስ ቁርባን የሚደርስበትን መከራና ፈተና ለመቀበል መወሰንና መዘጋጀት ይኖርበታል. ለዚህም ደግሞ ወሳኙ ምክረ
ካህን ነው።


#ምዕራፍ_አንድ
#ክፍል 1
: 🙏 #ምክረ_ካህን🙏

ምክረ ካህን ማለት አማኙ በኃጢአቱ ከተናዘዘ በኋላ ቀኖና መስጠት ማለት ብቻ ሳይሆን ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ሆኖ #ቅዱስ_ቁርባን ለመቀበል ጥያቄ ላቀረበው ወይም ለተዘጋጀው አማኝ
ከካህኑ ጥልቅ ምክርና የተብራራ ምሪት ሊሰጠው ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ የእርሱ በመሆናቸው የሚገጥማቸውን አስቀድሞ
እንዲያስተውሉ አድርጎ እንዳዘጋጃቸው ካህኑም አማኙን ሊያዘጋጀው ይገባል፡፡
👉ምክረ ካህን ማለት በአጠቃላይ መልኩ አማኙን ከመቁረቡ በፊትና ከመቁረቡ በኋላ ያለውን ሕይወት ሁሉ ያጠቃልላል እንጂ ኃጢአትን መናዘዝ የመስዋዕቱን መለወጥ እንዲያምን ማስተማር
ብቻ ማለታችን አይደለም፡፡ አብነት እንዲሆን ከዚህ በታችእንደጠቀስነው ሊሆን ይገባል።

👉አንድ አማኝ ወደ ቅዱስ ቁርባን ከቀረበ በኋላ ስለሚጠብቀውና ስለሚመራው ሕይወት ካህኑ በዝርዝር ይግለጽለት።
👉ክርስቶስን መከተል ማለት ወደዚህ ሕይወት መግባት ማለት ባለቤቱ እንደተናገረው መስቀሉን መሸከም ማለት ስለመሆነ ይግለጽለት፡፡
🙏ምን አልባትም አማኙ በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ ሲኖር በዓለሙ ዘንድ የተጠላና የተተቸ ሊሆን ይችላል:: ይህን ነገር ክርስቶስ እንዲህ በማለት ተናግሮታል፡- « ስለእኔ በዓለም ውስጥ
የተጠላችሁ ትሆናላችሁ» /ዮሐ 15 -23/ ምክንያቱም የዓለምን ሥራ ስለምናልክስበትና ስለ ምንንቅበት አለም ሊጠላን ሊተቸን ምክንያት ሊፈልግብን ይችላል ሁሉም የሚወደው ወገን ወገኑን
ነውና
👉 ደቀመዛሙርቱ እርሱን በመከተላቸው ዓለም የአበባ ምንጣፍ አንጥፎ አዘጋጅቶ አይደለም የተቀበላቸው ለአንገታቸው ሰይፍ ለሰውነታቸው እሳት እንጂ /ማቴ. 24÷9/
ስለዚህ አንተም መሰል መከራዎች በደረሰብህ ጊዜ የተቀበልከውን ታውቀዋለህና ስለ እርሱ ራስህን ክደሃልና ስለሥሙና ስለ ቅዱስ ቁርባን በሚደርስብህ ደስ ሊልህ ይገባል ምርጫህ ሕይወት
በመሆኑ ሰይጣን መሸነፉንና ባንተ መቅናቱን እወቅ ስለዚህ ካህኑ ይህንና መሰል ጉዳዮችን ሊያሳውቀው ይገባል እንዲህ እያለ ልጄ በርታ አይዞህ ዓለም ቢጠላህ አትደነቅ ደግሞም የገዛ ሃሳብህ ዕር ይሆንብሃል ይህንን አይነቱን ፈተና በዚህ በዚህ መልክ ተቋቁመው ቢገጥምህ እንዲህ ተወጣ የሰዎች ባንተ አይደነቅህ ምክንያቱም ሰይጣን አንተን ለመፈተን ሊጠቀምባቸው ይችላል የሰይጣንን የውጊያ ባህርያት እወቅ ሊለው ይገባል፡፡
👉በሌላ መንገድ ሰይጣን እራስህን በማይገባ ክስ እንድትከስና በጀመርከው ሕይወት እንዳትገፋበት በአሉባልታዎች ሊያውክህትም ይችላል፡፡ አንተ ግን ስለተቀበልከው በቂ ዝግጅትና እውቀት ካለህ
መልስ ትሰጥበታለህ:: «በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ» /1ጴጥ. 3፥15/
👉ይሔውም «አንተ ቆርበህ እንዲህ ትሆናለህ» «ይህ ሰው ከቆረበ ጀምሮ አቅበዘበዘው» «መቁረብ በማይገባት ጊዜ ቆርባ አደብ አጣች» የመሳሰሉትን ይህ አይነት አሉባልታ ሌሎችን በአንተ ላይ
አነሳስቶ የመክሰስ የዲያቢሎስ ውጊያ ነገ ደግሞ ራስህን በራስህ ላይ አነሳስቶ ለመክሰስ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት መሆኑን ልብ
በልና ለአሉባልታ ሳትገዛና እነርሱ ባሉህ /ባሙህ/ ነገር ሳትገኝ ተገቢውን መልስ በትህትና መስጠት ይገባል:: 👉ይኸውም እኔ የተቀበልኩት ሰላም ነሺውን ሳይሆን ፣ አደብ የሚያሳጣውን፣ ሳይሆን የሚያቅበዘብዘውን ሳይሆን፣ #የሰላሙን_አምላክና ሕይወትን
#የሚቀድሰውን_ጌታ ነው ኢሳ 9:6/ በማለት ደግሞ::
👉አንተ ወገኔ የምትናገረውንና እንዲህ የምትተቸውን
ታውቃለህ ሰላም ነሺ አቅበዝባዥ፣ የምትለውን ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስ ለዓለም ሰላም የሰጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው
እኮ ልክ እንደ አይሁድ ሕዝቡን ሰላም ነሳ ብለው ለቄሳር እንደከሰሱት በማለት ምስጢሩ ያልገባውን ወገንህን ማስተማርና
ሰይጣንን ማሳፈር ይገባሀል።

#ምዕራፍ_አንድ
* #ክፍል 2
#ሰው_ግን_ራሱን_ይፈትን

ይቀጥላል ......
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉@dnhayilemikael 👈
👉@dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች
     ➛ ትዕቢተኛ ዓይን፥
     ➛ ሐሰተኛ ምላስ፥
     ➛ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
     ➛ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
     ➛ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
     ➛ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
     ➛ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

ምሳሌ 6፥16-19

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ንጉሥና ካ ህ ን ሲነጻጸሩ

#በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

💠የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው።

💠ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤ ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው።

💠ንጉሥ ያዝዛል፤ ካህን ግን #ያስተምራል ይዘክራል።

💠ንጉሥ ያስገድዳል፤ ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል።

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ውዳሴ ከንቱን የመሻት መዘዝ !

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ሰው ረስቶ ለትላትል ከመጨነቅ በላይ ምን ከንቱነት አለ ?

" ውዳሴ ከንቱን መሻት የገሃነመ እሳት እናት ናት፡፡ ውዳሴ ከንቱን መሻት እሳቱ ለማይጠፋው ትሉ ለማያንቀላፋው ዓለም መጋቢዋ ናት፡፡ ሌሎች ክፉ ምግባራት በሞት ይገታሉ፡፡ ውዳሴ ከንቱ ግን አንድ ሰው ከሞተ በኋላ እንኳን ሊያደርገው የሚችል የክፉ ክፉ ምግባር ነው፡፡ በመሆኑም ውዳሴ ከንቱ የገሃነመ እሳት እናት ናት እላለሁ፡፡

ሌሎች ክፉ ምግባራት ሰው ሲሞት ይቆማሉ፡፡ ውዳሴ ከንቱ ግን ከሞት በኋላ እንኳ የሚቀጥል ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ የባሰ ምን አለ ልንል እንችላለን? ምን ማለቴ እንደሆነ እነግራችሁ ዘንድ ትሻላችሁን?

እስኪ ወደ መካነ መቃብር ሒዱ፡፡ ቢያንስ አሁን በአካል ባትሔዱ በዓይነ ሕሊናችሁ ሒዱ፡፡ ብዙ የብዙ ብዙ ሐውልቶች አታገኙምን?

አዎ ! እነዚህ ሰዎች ከመሞታቸው በፊት የሚናዘዙት ሀብታቸው ለድኾች እንዲሰጥ አይደለም ፤ ሀብታቸው ብል እንዲበላው ሐውልት እንዲቆምላቸው እንጂ፡፡ በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ለየት ያለ ትርዒት እንዲፈጸምላቸው ነው የሚናዘዙት፡፡

እነዚህ ሰዎች በዘመናቸው ድኾችን ሲሳደቡ የነበሩ ናቸው፡፡ የምድር ትላትል ይበሉት ዘንድ መቃብራቸው እንዲያምር ሲናገሩ ግን ምንም ሐፍረት ቢጤ አይሰማቸውም፡፡ ለሠራተኞቻቸው ደመወዝ ለመጨመር ይንገበገባሉ፡፡ እንዲሁ በከንቱ ለትላትል ለሚያወጡት ገንዘብ ግን እጅግ ይጨነቃሉ፡፡

ወዮ ! በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ሰው ረስቶ ለትላትል ከመጨነቅ በላይ ምን ከንቱነት አለ? ከዚህ የባሰ ክፉ ደዌ ምን አለ?

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

† † †

/channel/dnhayilemikael

💖 🕊

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሰይጣን አንድን ኃጢአት ሊያሠራን ሲፈልግ ቀድሞ ስለ እግዚአብሔር መሐሪነት በሰፊው ይሰብከናል። ያን ኃጢአት ከፈጸምን በኋላ ደግሞ ስለ እውነተኛ ፈራጅነቱና ምንም ቢሆን ከቁጣው የማናመልጥ መሆኑን ከቀድሞው ይልቅ እየጮኸ ይነግረናል። በመጀመሪያው ስብከቱ ኃጢአትን እንዳንቃወም ሰነፎች ያደርገናል። በሁለተኛው ስብከቱ ደግሞ ንስሐ እንዳንገባ ተስፋ ያስቆርጠናል።

ይህ የተገለባበጠ ስብከት "የሰይጣን" ነው። ሰው በኃጢአት ከመውደቁ በፊት ሊያስብ የሚገባው የእግዚአብሔርን ፈታሒነት (ፈራጅነት) ሲሆን በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ግን ማሰብ ያለበት የእግዚአብሔርን መሐሪነት ነው።

ፈታሒነቱ ኃጢአትን እንዳንሠራ ይጠብቀናል፤
መሐሪነቱ ንስሐ እንድንገባ ያቀርበናል፤

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#እግዚአብሔር_ምን-ሰራሽ_እንጂ_ምን_ለበስሽ_አይለኝም


💠ብዙ ጊዜ አንዳድ እህቶቻችን ሱሪ ወይም ቅርፅን የሚያሳይ ወይም ቅዱስ ገላቸዉ የሚያሳይ ልብስ አትልበሱ ሲባሉ
፣የሚመልሱት ነገር ቢኖር ይህ ቃል ይመልሳሉ፦እግዚአብሔር ምን ሰራሽ እንጂ ምን ለበስሽ አይለኝም ይላሉ፣
💠እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል።"እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም እቀጣለዉ።(ትን ሶፎ 1÷18)
ታዲያ አምላካችን እንዲህ ካለን እኛ እራሳችን ተሰናክለን ሌሎችስ በምን ሁኔታ ይሰናከሉ? ዳግም እንዲህም ይላል

💠ከነዚህ ከተናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለዉ ነበር።(ማቴ 16÷8)እንግዲያዉስ የሴቶች ምርጫ ወይስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንቀበል? እንግዲያዉስ ምርጫዉ ያንቺዉ ነዉ

💠ከሰዉ ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።(የሐዋ 5÷29)

💠ሴትም የራስዋ የሆነ ልብስ ልትለብስ ይገባል፣ወንድም የራሱ የሆነ ልብስ ሊለብስ ይገባል።
#ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፣ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህ የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነዉ።(ዘዳ 22÷5)ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት በሚገባ ስረአት ታስተምራለች

💠ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም።(1ኛ ቆሮ 11÷16)

💠ቅዱስ ጳዉሎስ እንዳለዉ ስህተት መሆኑን መናገር እንጂ መከራከር አያስፈልግም ክርስትና በምርጫ ነዉና።

💠በፊትህ እሳትና ዉሃ አኑሬአለሁ ወደ ወደድከዉ እጅህን ክተት
።(ሲራክ 15÷15)

💠ደግሞ ክርስትና እራስን ወዳድነት አብዝታ ትጠላለች ምንም ነገር ስናደርግ ስለ ሌላኛዉ ሰዉ ልናስብ ይገባል እኛስ ሰዉን ወደ ዝሙት ሊያመራዉ ስለሚችል አለባበሳችን እጅግ ተጨንቀን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል ፣ቅዱስ ጳዉሎስ ስለማሰናክል እንዲህ ሲል ተናገረ

💠መብል ወንድሜን የሚያሰናክለዉ ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክለዉ ለዘላለም ሥጋ አልበላም
።(1ኛ ቆሮ 8÷ 13)
💠ስለዚህ ስለ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ልናስብላቸዉ ይገባል ለእነሱ መሰናከያ እንዳንሆን እየተጠነቀቅን እያስታወስን የምናደርጋቸዉ ተግባራት በሥረአት ማደረግ ይኖርብናል

💠የመጨረሻ መልዕክቴ ሱሪ ዉስጤ ነዉ ሱሪ ከልጅነቴ ጀምሮ ነዉ ምለብሰዉ የምትሉ ሴቶች በእዉነት ማስተዋል ሲያቅተን ነዉ የእግዚአብሔር ቃል እያወቅን እንደአላወቀ በድፍረት መጠቀም ምን ይሉታል?

💠 አምላክ እኮ እንደ ሰዉ የዉጪ ዉበት ብቻ ሳይሆን እስከ ልብና ኩላሊት የሚመረምር አምላክ ነዉ ታዲያ አምላክን ማታለል ይቻላልን???
💠 እርሱ አንቺዉ መርምሪዉ ሰዉ ከሞትኩ በዃላ በምን አዉቃለህ ይላል ነገር ግን አስተዉለህ የምታቀዉ ነፍስህ ከሥጋህ ሲለይ እንደሆነ አስተዉል ያኔ ምነዉ ክፉ ባልሰራሁ ምነዉ ትዕዛዙ በጠበኩ ብላ የምትጮኸዉ ነፍሳችን ናት የዛኔ ነፍሳችን በሰማይ በክበር በዙፋን ላይ የተቀመጠዉ አምላክ ሲጠይቃት ነዉ የምናስተዉለዉ ስለዚህ ሥጋ ትሞታለች እንጂ ነፍስ አትሞትምና ነፍስሽን አድኛት አድናት ያለፈዉ ዘመን በቅቶን ወደ ንስሃ እንገስግስ እህት ወንድሞቼ።

በቃሉ የምታምኑ ብቻ አንብባችሁ share♥
ከሰዉ ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባል እንደ ሰዉ ቃል ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል መኖር ተገቢ ነዉ ቸሩ መድኃኒአለም ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይፍጠርልን🙏

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ገንዘብ ይመገቡ። ዲያቆናትን ያክብሯቸው። ዲያቆን ቀሳውስትን ያገልግላቸው። ከሕዝቡ ወገን ጠያቂ የሌላቸውን ድውያንንም በመጠየቅ ያገልግላቸው። ለኤጲስ ቆጶሱም ችግራቸውን ይንገረው።
_
፬) ዲያቆኑ በቤተክርስቲያን ሕዝቡ እንዳይተኙ እንዳይስቁ እንዳይዘባበቱ ይጎብኛቸው። ዲያቆን ደሙን በቄሱ ትእዛዝ ለምእመናን ያቀብል። በመዓርግ ከእርሱ ለሚበልጥ ደሙን አያቀብል። ኤጲስ ቆጶስ ቄስ ባይኖር በምሳ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት ደግሞ ባርኮ ይስጥ። ዲያቆን ያስተምት ያጠምቅ፣ ሥጋውን ደሙን ያቀብል ዘንድ፣ ሕዝብን ይባርክ ዘንድ አይገባውም። ዲያቆን ዓውዱን አይያዝ።
_
፭) ሊቀ ዲያቆን በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ከኤጲስ ቆጶስ ቀጥሎ ይቁም። ከኤጲስ ቆጶሱ ብቻ በቀር ሌላ በበላዩ አይፍረድ አይቀመጥ። እስመ ውእቱ ሊቀ ካህናት። የካህናት አለቃ ነውና።
_
፮) ዲያቆናት ሆይ የተቸገሩትን ልትጎበኟቸውና የተቸገሩበትንም ነገር ለኤጲስ ቆጶሳችሁ መንገር ይገባችኋል።
_
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ነገረ ትንሳኤ ክርስቶስን አስመልክቶ ብዙዎች የሚያነሱት ጥያቄ

#ጥያቄ ክርስቶስ፥ በከርሰ መቃብር፤ ሦስት መአልት ሦስት ሌሊት እንዴት ሊሞላው ቻለ?         ክርስቶስ ሦስት መአልት ሦስት ሌሊት፣ በከርሰ መቃብር አደረ፤ የሚባለው፥ እንዴት ሆኖ ነው? (ለሚለው ጥያቄ፥ ምላሹ በሁለት ዓይነት አረዳድ እንገነዘባለን)

አንደኛው
        1/ ፩፤ ለዚህ ምላሽ የዕብራውያንን አቆጣጠር ማወቅ ያስፈልጋል:: የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢር ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት የዕብራውያንን ሥርዓት ወግና ጂኦግራፊያዊ (መልክአ ምድራዊ) አቀማመጥ ያስፈልጋል።

        👉 ምክንያቱም፥ ጸሐፊዎቹ ባህላቸውንና ሥርዓታቸውን ጠብቀው የጻፉት ስለሆነ ነው
👉 ጌታ ዓርብ ተሰቅሎ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ከተነሳሣ እንዴት ብሎ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይሞላል ሊያሰኝ ይችላል።

      💠   በዕብራውያንን አቆጣጠር ሌሊት የሚቆጠርው በዋዜማው ካለው አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው።
💠 ከአሥራ አንዱ ሰዓት በፊት ያሉት ሰዓቶች ግን አንድ ሰዓትም ቢሆን እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል። ጌታ የተቀበረው ዓርብ ከአሥራ አንድ ሰዓት በፊት ስለሆነ የተቀበረበት ሰዓት የዓርብን መዓልትና ሌሊት ያጠቃልላል።

      💠   አርብ ከሠርክ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ አሥራ አንድ ሰዓት ከሰዓት በዋላ ድረስ ያለው የቅዳሜ መዓልትና ሌሊት ነው።

👉 ቅዳሜ ከአሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ያለው እሑድ ነው። አንዱም ሰዓት ቢሆን ከላይ እንደ ተገለጠው የዕለቱን ሰዓቶችን ያሟላል። ጌታም የተነሣው እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ስለሆነ ሦስት መዓልት ሶስት ሌሊት ይሆናል።


ሁለተኛው
       2/፪፤
በጌታችን ላይ የሞት ፍርድ ከተፈረደበት ጀምሮ እንደ ሞተ በመቁጠር
👉አርብ ጠዋት ከ፲፪ ሰዓት እስከ ፮ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ብርሃን ነበር፤ አንድ ቀን።

        👉 ከ፮ እስከ ፱ ሰዓት በምድር ላይ ጨለማ ሆነ ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፤ ያም፥ ጨለማ እውነተኛ ጨለማ እንጂ በምትሐት የሆነ ስላልሆነ እንደ ሌሊት ይቆጠራል። አንድ ቀን አንድ ሌሊት ይኖረናል።

 👉አርብ ከ፱ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፲፪ ሰዓት እንደገና ቀን ሆኖአል፤ 
👉አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ ያለውን ጨለማ ወይም ሌሊት ስንቆጥር ሁለት ቀን ሁለት ሌሊት ይሆናል።

👉         ቅዳሜ ሙሉ ቀንና ሌሊትን  ለእሁድ አጥቢያ ጌታ እሁድ ሌሊት ተነስቷል፤ አንድ ላይ ሲደመር ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይሆናል።

👉 እንግዲህ በሁለቱም ዓይነት የሚቆጥሩ ስላሉ ሁለቱም ዓይነቶች ቀርበዋል እኛም የገባንና የተረዳንን አቆጣጠር መርጠን ማስረዳትም መረዳትም እንችላለን።

                      <<<<<<<<


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ፖርኖግራፊ አንብቡት🗣 ክፍል አንድ

#ሰዎች_ለምን_ፖርኖግራፊ_ይመለከታሉ?
አንብቡት🗣 ክፍል አንድ


✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታው እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11




🥀ሰዎች ለምን ፖርኖግራፊን አዘውትረው ይመለከታሉ? “ችግሩን መለየት በራሱ የመፍትሄው አንድ አካል ነው” የሚለውን መርህ ይዘን ከብዙዎቹ ምክንያቶች ጥቂቶቹን ለመመልከት እንሞክር።

1. #ደስታን_ፍለጋ

🥀ለዚህ ጥያቄ ግልፅ የሆነውና የመጀመሪያው ምላሽ ሰዎች ማንኛውንም አይነት ፊልም እራሳቸውን ለማዝናናት እንደሚመለከቱት ሁሉ፣ ፖርኖግራፊንም የሚያነቃቃቸው እና ደስ የሚያሰኛቸው ነገር ከመፈለግ አንፃር ማየታቸው ነው።

ከሰው መሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ አንዱ ወሲብ እንደመሆኑ ሰዎች ይህንን ፍላጎት በተገቢው ሆነ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ለማሟላት፣ በገሀዱ አለም እራሳቸው ያላደረጉትን ወይም የማያረጉትን ነገር ግን ስሜታቸው የሚፈልገውን ነገር አይተው በምናባቸው ተሳታፊ ለመሆን ፖርኖግራፊን ይመለከታሉ።

2. #ጭንቀት/#ድብርት

🥀ብዙውን ጊዜ በድብርት እና በጭንቀት ውስጥ ያሉ ሰዎች በፖርኖግራፊ ሱስ የሚጠቁ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ።

በአብዛኛው በፖርኖግራፊ ብቻ ሳይሆን በሌላም የዕፅ ሱሶች የሚያዙ ሰዎች ሱስ የሆነባቸውን ድርጊት ደጋግመው እንዲያረጉ የሚገፋፋቸው ወሲባዊን ደስታን ለማግኘት ያላቸው ፍላጎት ሳይሆን ውስጣቸው ከሚሰማቸው የስሜት መዋዥቅ ማለትም ጭንቀት፣ ድብርት፣ ሀዘን፣ ፍርሃት እና ሀፍረት ለማምለጥ ነው።

🥀ስለዚህ በሕይወታቸው ከባድ ጭንቀት ያለባቸውና ያልፈቱት አስጨናቂ ነገር በልባቸው ያለባቸው ሰዎች ሃዘናቸውን ለመርሳትና ጊዜያዊ ደስታ ለማግኘት ይጠቀሙበታል። በስራ ቦታቸው ላይ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ስራቸውን እየጠሉት የሚሰሩ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል።

3. #ብቸኝነት

🥀ብዙውን ጊዜ ብቸኝነትን የሚያዘወትሩ በተለያየ ምክንያት ከሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ የማይችሉ ሰዎች በዚህ ሱስ ሊጠቁ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ።

​​4. #በጓደኛ_ግፊት

🥀በአብዛኛው ታዳጊዎች እና ወጣቶች ስለ ሩካቤ ስጋ ምንነት ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ወደ ፖርኖግራፊ ሊሳቡ ይችላሉ።

🥀ብዙዎች ወደሚያደርጉት ነገር ወይም ከዚያም ባለፈ በደፈናው ‘አታድርጉ!’ የሚባሉ ነገሮችን የመሞከር ዝንባሌ በወጣቶች ይስተዋላል። ታዳጊዎችና ወጣቶችም በጓደኞቻቸው ግፊት ወደዚህ ህይወት በቀላሉ ሊሳቡ ይችላሉ።

🥀ለ10 አመት ያህል በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለች አንዲት እህት እንዴት ወደዚህ ሱስ እንደገባች እንዲህ ስትል አጫውታኛለች።
አንብቡት🗣

🥀“የዪኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ዶርም ውስጥ ጓደኞቼ ተሰብስበው ፖርን ይመለከቱ ነበር። እኔ ግን ሁሌም እቃወማቸው ነበር። ከሆነ ጊዜ በኋላ ግን ሳላስበው እነሱን መቀላቀል ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ከነሱ የባስኩ ተመልካች ሆንኩኝ።”

5. #ሱስ

🥀አንዳንድ ሰዎች ፖርኖግራፊን በተለያየ ምክንያት አንድ ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ከተመለከቱ በኋላ ሱሰኝነትን ያዳብራሉ። ሱስ ማለት ፈልገን የገባንበት ኋላ ግን እየጠላነውም ቢሆን የምናደርገው ነገር ነው።

🥀ማንኛውም ሱስ ሲጀመር በፍላጎት ሲሆን የሚቀጠለው ግን ያለ ፍላጎት ሊሆን ይችላል። ፖርኖግራፊ ልክ እንደ ማንኛውም አደንዛዥ ዕጽ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከፍተኛ አቅም አለው። በአንድ ወቅት ስለ ፖርኖግራፊ ሱስ ዶክተር ስዩም ያሉትን ልዋስ፤ “ብዙዎች ፖርኖግራፊ ሳያዩ መተኛት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ሱስ አይሆንም ብሎ የመናገር ድፍረት አላቸው::

🥀ነገር ግን ፖርኖግራፊ ከሌሎች ሱሶች ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ መልኩ ወደ ሱስነት ያድጋል። አንድ ሰው ፖርኖግራፊ ሲመለከት ደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች (hormons) አሉ፤ እነዚህ ቅመሞች አንድ ሰው ኮኬንና ሄሮዊን የሚባሉትን አደዛዥ ዕፅ ሲጠቀም በደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች ናቸው።

🥀እኚህን ዕጾች ስንወስድ ደማችን ውስጥ የሚለቀቁት ቅመሞች ፖርኖግራፊ በምናይበት ጊዜ ከተለቀቁ ፖርኖግራፊ ሱስ አይሆንም ማለት አንችልም። ሱስ ለመባል የግድ በአፍ በኩል ወደ ውስጣችን መግባት የለበትም።

🥀አሁን ባለን መረጃ ‘Pornography is not like a drug, it is a drug’ (ፖርኖግራፊ አንደ አደንዛዥ ዕፅ ሳይሆን እራሱ አደንዛዥ ዕፅ ነው) እንዲያውም መልከ ብዙ ዕፅ ነው።

🥀ሰው ፖርኖግራፊ ሲያይ ብዙ ዕፅ በአንድ ላይ እንደወሰደ ይቆጠራል። አንድ የኒዩሮ ሳይንቲስት (neuroscientist) ባለሙያው በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሚፈጅበትን ጊዜ ሲናገሩ አንድን ምስል ለግማሽ ሰከንድ ካየን በኋላ በሚቀጥሉት 5ና 10 ደቂቃ ውስጥ አንጎላችን ውስጥ መሰረታዊ የሆነ የቅርጽ ለውጥ (nerve restriction) ይፈጠራል።

🥀ይሄ አይነት ለውጥ ልክ አንድ ሰው አደጋ ሲደርስበት የሚፈጠረውን የቅርጽ ለውጥና አይነትን ነው። በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሰከንድ 1/3ኛ ይበቃል እንደማለት ነው:: አስተውላችሁ ከሆነ ለሰከንድ ያየነው የፖርኖግራፊክ ምስል ለአመታት ከአይምሮአችን አይወጣም።

🥀ለምን ካላችሁ ‘epimerphine’ በተባለው ‘ሆርሞን’ ምክንያት እንዳይጠፋ ሆኖ ተቀርጿል:: ከዚህም የተነሳ ከአመታት በኋላ እንኳን አይረሳም። በዚህም ምክንያት ‘በቃ አይኔንም ስከድን ስተኛም በመንገድ ላይ ስሄድም የሚመጣብኝ እሱ ነው’ እያሉ በመንፈስ ጭንቀት የሚሰቃዩ ወጣቶች ገጥመውኛል።”

🥀ከዚህ የምንረዳው በቀላሉ የሚጀመር ነገር እንዴት ወደ ትልቅ ሱስ ሊያድግ እንደሚችል ነው።

ይቀጥላል
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
ቴሌግራም ተቀላቀሉ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…
Subscribe to a channel