#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
†
[ አሮጌውን ሰው አስወግዱ ! ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
" በዕድሜ የሸመገሉ ሰዎች አስቀድመን ከተናገርነው በተጨማሪ ብዙውን ጊዜ ጤና ስለሌላቸው ያስላቸዋል፡፡ ያነጫንጫቸዋል ፤ ትንሽ ነገር ያበሳጫቸዋል፡፡ ትንፋሽ ያጥራቸዋል፡፡ ከእኛ መካከል ምናልባት እንዲህ በጠና የታመመ ሰው ካለ እነዚህን ምልክቶች በቀላሉ ያውቃቸዋል፡፡ እነዚህ ኹሉ በሥጋ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡ ወዮ! የአሮጌው ሰው ነፍስ እንደ ምን ከዚህ የባሰች ትኾን?
በወንጌለ ሉቃስ ላይ የምናገኘው የጠፋው ልጅ እንዲህ ኾኖ ታሞ የገረጣ የከሳ ልጅ ነበር፡፡ ሲወስንና ሲጸጸት ግን ወድያው እንደ ቀድሞ ወጣት ኾነ፡፡ "ተነሥቼ ወደ አባቴ እሔዳለሁ" ባለ ጊዜ አሮጌው ሰውነቱ እየከሰመለት ..... እየጠፋለት ...... አዲሱ ሰውነቱ ደግሞ እየፋፋለት ..... መጣ [ሉቃ.፲፭:፲፯]::
በሐሳቡና በቃሉ ላይ ተግባር እየጨመረበት ሲመጣ ደግሞ የበለጠ እየፈረ.... እያገገመ.... መጣ፡፡ "ተነስቼ ወደ አባቴ እሔዳለሁ፡፡ አባቴ አንተንም ፈጣሪዬንም በደልኩ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይገባኝም፡፡ ከባሮችህ እንደ አንዱ ቁጠረኝ እንጂ እለዋለሁ" ብሎ እዚያ የቆየ አይደለም ፤ ፈጥኖ ድሮ የሔደበትን መንገድ እየተወ ወደ ቤቱ ተመለሰ እንጂ፡፡
ተወዳጆች ሆይ ! ከአባታችን ቤት ብዙ ርቀን በአሕዛብ ሀገር ገብተን ቢኾንም ፀሐይዋ ገና አልጠለቀችምና አሁኑኑ ወስነን እንመለስ፡፡ የመንገዱን ርዝማኔ እየታሰበን በዚያ የምንዘገይ አንሁን፡፡ እኛ ፈቃደኞች ከኾንን የሔድንበት መንገድ ለመመለስ ከቀድሞ ይልቅ ቀላል ደግሞም የፈጠነ ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው የሔድንበትን የእንግድነት ሀገር ወስኖ መልቀቅ ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ከሔድንበት የኃጢአት ሀገር ተመልሰን ከአባታችን ከጽድቅ ቤት እንግባ፡፡ አባታችን እኛን ለመቀበል ፍሪዳውን አርዶ [ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን አዘጋጅቶ] ቤቱንም አሰናድቶ እየጠበቀን ነውና ከዚያ የኃጢአት ሀገር ፈጥነን እንውጣ፡፡ ጤናን ከማጣት የተነሣ የገረጣውን ሰውነታችን በእንግድነት ሀገር ሳይሞት ፈጥነን እንመልሰው፡፡ "
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
† † †
💖 🕊 💖
/channel/dnhayilemikael
"ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ልጠይቃችሁ፦ አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የኾነ ቦታ ላይ ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደዚያ ቦታ ለመሔድ አስፈላጊ ነው የምትሉትን ኹሉ አታደርጉምን? ቀኑን ሙሉም ቢኾን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁምን?
እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያላችሁ ግን አንዲት ወይም ዐሥር ወይም ሃያ ወይም መቶ ወይም አንድ ሺሕ ቅንጣት ወርቅ አይደለም፤ ወይም ምድርን ኹሉ አይደለም፡፡ ከዚህ ኹሉ የምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት እንጂ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ ታዲያ ምን አለ? ይህንን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ ሰዎችስ እንደምን ያሉ ምስኪናን ናቸው?"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
/channel/dnhayilemikael
✝️ #የሕይወት_ምክር
👉ድካማነትህን አስታውስ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም።
👉የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔር ቸርነት አስታውስ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል።በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ በልብህ እያደገ ይመጣል።ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።
👉የሰዎችን ፍቅርና ከአንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል የአንተንም ቁጣ ያበርዳል። ሞት እንዳለ ስታውስ፣ እንዲሁም በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ።"ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው"መክ 1÷14
ማለትን ትረዳለህ።
👉በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ ያኔ ኃጥአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።
👉የእግዚአብሔርን ቃልኪዳን አስታውስ።በዚህ ከጭንቀቶችህ ሁሉ ትጽናናለህ።ከዘነጋሃቸው ግን ልበ
አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ያለውን አስታውስ"
ለባሪያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ። ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።
"መዝ 118÷49-50
👉ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ።በዚህ ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፤ ስለዚህ በከንቱ በመኖር አታጥፋውም፣ "በዋጋ ተገዝግታችኋልና "1ኛ ቆሮ 6÷20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።
👉በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤
ድያብሎስን፣ ስራዎቹን ሁሉ፣ሐሳቦቹንና ጥበቡን ኃይሉንም ትክድ ዘንድ።
👉በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታወስ።ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።
👉በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ። ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው አልፈኸው ሂድ ከእሱም እራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና።
👉ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፣ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ።
👉የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ።
👉እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል።
👉የመንፈስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ በውስጥህም ያለውን ቅዳሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን።ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን።
#ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን🙏
ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 2
#ክፍል 5
#ያላገባ_ወጣት_መቁረብ_ይችላል ?
👉ለዚህ ርዕስ በቂ ማብራሪያ ለአንባብያን ከማቅረቤ በፊት አንድ ነጥብ አስቀድሜ ልገልጽ እወዳለሁ::
👉ይኼውም ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል በራሱ ያገባ ወይም ያላገባ ብሉ እንደ መስፈርት መውሰድ ትልቅ ስህተት መሆኑን።
👉መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተ ለሁሉ ነው ስለዚህ አምነው በተጠመቁና ለቅዱስ ቁርባን በተዘጋጁ መካከል የማግባትና ያለማግባት ፣ የዘርና የቀለም ፣ የጾታና የዕድሜ ልዩነትን
እንደመመዘኛ የሚወስድ ካለ ትልቅ ስህተት ውስጥ ገብቷል::
«በአይሁዳዊና በግሪካዊ ሰው መካከል ልዩነት የለምና
አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና ሮሜ
👉በማለት ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን ክርስቲያኖች የጻፈላቸው ይህን ያረጋግጥልናል።
👉በተረፈ የዚህ ርዕሳችን መሠረታዊ ነጥብ ግን ይህ ነው ማንኛይቱም ኦርቶዶክሳዊት ሴት ከልጅነቷ አንስቶ እስከታገባ ድረስ ካገባችም በኋላ ከሕግ ባሏ ጋር በአንድነት እስከ እለተ ሞቷ ድረስ ስትቀበል መኖር ይገባታል እንደዚሁ ወንዱ ከልጅነት ኣንስቶ የህግ ሚስቱን እስካገባበት ቀን ድረስ ካገባም በኋላ ከህግ
ሚስቱ ጋር እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል
ሊኖር ይገባዋል።
#ምዕራፍ 2
ክፍል 6
❖ቆራቢ የሆነ ሰው የትዳር ጓደኛውን
በሞት ቢያጣ ደግሞ ሌላ ማግባት ይችላል?
ያለፈውን ለማግኘት
/channel/dnhayilemikael/4952
ይቀጥላል .....
👆
ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን ለትንሣኤ ሃያ አምስተኛ (፳፭) ቀን ርክበ ካህናት (ዕለተ ጥብርያዶስ) እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።
❤ ርክበ ካህናት (ዕለተ ጥብርያዶስ)፦ የሀገራችን የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ ቀን ርክበ ካህናት፣ ዕለተ ጥብርያዶስ፣ ዳግሚት ዕለት አግብኦተ ግብር ምንድን ነው?
❤ ርክበ ካህናት የሁለት ቃላት ጥምረት ሲኾን እነዚህም፤
፩ኛ. ረክብ የሚለው ቃል ተራከበ ተገናኘ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጕሙም ማግኛ፣ መገኛ፣ መገናኛ ማለት ነው፡፡ /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፰፴፩/፡፡
፪ኛ. ክህነት የሚለው ቃል ከዲቁና ጀምሮ እስከ ከጵጵስና ድረስ ያሉትን መዓርጋት (በጥቅሉ ዲያቆናትን፣ ቀሳውስትንም ኾነ ጳጳሳትን) የሚያጠቃልል ስያሜ ነው፤ ካህን (ነጠላ ቍጥር) ሲኾን ካህናት ደግሞ (ብዙ ቍጥር) ነው፤ ብዙ ጊዜ ግን ይህን ባለማወቅ ካህናት የሚለውን ለቀሳውስት ብቻ መጠሪያ ሲኾን እናያለን፤ አለማወቅ ነው! (ለምሳሌ በቅዳሴ መጨረሻ ላይ ዲያቆኑ በእደ …… ካህን ይባርከነ ቢል ለኹሉም ያስኬዳል፥ ሰዋስዉም ያዛል፥ ሥርዐቱም ይኸው ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ዛሬ በእደ … ካህን ይባርከነ በማለት ፈንታ በእደ ብፁዕ ፓትርያርክ፣ በእደ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ፣ በእደ ቆሞስ …. ሲባል ይታያል፤ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ነው፡፡)
❤ ርክበ ካህናት ማለትም የአባቶች ካህናት (ማለትም በጵጵስና ማዕረግ ያሉ፦ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ጳጳሳት፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስን ያጠቃለለ (የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት) ጕባኤ፤ የካህናት መገኛ፥ መገናኛ ጉባኤ (መሰባሰቢያ፣ መወያያ) ማለት ነው፡፡
❤ በዓሉ በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን ሁልጊዜ በዕለተ ረቡዕ ይውላል፤ ወሩና የሚውልበት ቀን ግን በኢየዓርግና በኢይወርድ (በባሕረ ሓሳብ የበዓላትንና የአጽዋማትን) ቀመር ተከትሎ የሚወጣ ስለኾነ ከፍና ዝቅ ይላል፡፡ የአጽዋማትና የበዓላት ቀመር በቅዱስ ድሜጥሮስ አማካኝነት ከመዘጋጀቱ በፊት (ዐቢይ ጾም ሰኞ፣ ስቅለት ዓርብ፣ ትንሣኤ እሑድ፣ ርክበ ካህናት ረቡዕ፣ ዕርገት ሐሙስ፣ ጰራቅሊጦስ እሑድ እንዲሆን ከመደረጉ በፊት) ርክበ ካህናት በየዓመቱ ግንቦት ፳፩ ቀን ይውል ነበር /መጽሐፈ ግጻዌ ግንቦት ፳፩/፡፡
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በየጸጋቸው መጠን እየተገለጠ ያጽናናቸው፥ ያጸናቸው፥ ያስተምራቸው፥ ይባርካቸውም ነበር፤ ጌታችን እስከ ዕርገቱ ባሉ ፵ ቀናትም መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትምህርተ ኅቡዓትን፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን አስተምሯቸዋል፤ በልቡናቸውም አሳድርድሮባቸዋል፡፡
❤ በመጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል፤ ከዕርገቱ አስቀድሞ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ፫ ጊዜ በጕባኤ መገለጡ ተዘግቦ ይገኛል፡፡ እነዚህም፤
1ኛ. የትንሣኤ (ዮሐ. 20፥19)
2ኛ. የአግብኦተ ግብር (ዳግም ትንሣኤ) /ዮሐ. 20፥:26/
3ኛ. የጥብርያዶስ፤ (ዮሐ. 21፥1)
ለድንግል ማርያም ግን በኹሉም እለታት መገለጡን አበው ያስተምራሉ፡፡
❤ በጥብርያዶስ ባሕርም ከዐሥራ አንዱ ቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ምሳ በልቷል፡፡ የርክበ ካህናት በዓል መነሻም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከተገለጠበት ከጥብርያዶስ ባሕር ካለው ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
በዚህች ዕለት በቅዱስ ዼጥሮስ መሪነት ሐዋርያቱ ወደ ጥብርያዶስ ባሕር ሔዱ፡፡ አሶችን ሊያጠምዱም በብዙ ደከሙ፤ ነገር ግን ጌታችን በረድኤት አብሯቸው አልነበረምና አንዳች አሣ በመረባቸው ሊገባ አልቻለም፡፡ ማጥመድ (አስተምሮ ከክህደት ወደ ሃይማኖት፤ ከኀጢአት ወደ ጽድቅ መመለስ) የሚቻለው በረድኤተ እግዚአብሔር እንጂ በእውቀት ብዛት ወይም በአንደበተ ርቱዕነት ብቻ አይደለምና፡፡
❤ ሲነጋ ግን መድኀኒታችን ወደ ቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ መጣ፤ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻም ቆሞ ታያቸው፤ ከሚወደው ደቀ መዝሙሩ ከቅዱስ ዮሐንስ በቀር ጌታችን መሆኑን ያወቀው ግን አልነበረም፡፡ ቸሩ አባት "ልጆቼ! አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁ?" ሲል ጠየቀ፤ "ጌታ ሆይ! የለም" አሉት፡፡ "የለንም" ብሎ የሌለንን ነገር በጌታ ፊት ማመኑ እጅግ መልካም ነው፤ ምክንያቱም ያጣነውን ነገር ሊሰጠን፥ የጎደለንን ሊሞላልን፥ የጠፋብንን ሊጠቁመን ቸርነቱ ብዙ ነውና፡፡ ያን ጊዜ ሐዋርያቱን መረባቸው በመርከብ ቀኝ እንዲጥሉ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም በደስታ ጣሉ፤ በአግራሞት እስኪሞሉ ድረስ መረባቸውን መሳብ አቅቷቸው ሊቀደድ እስኪደርስ ድረስ 153 ዓሦች ተያዙላቸው፡፡
❤ ያን ጊዜም የሚወደው ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችን መኾኑን ለቅዱስ ዼጥሮስ "ጌታ እኮ ነው" አለው፤ ሽማግሌው ቅዱስ ግን ራቁቱን ነበርና ወደ ባሕሩ ተወረወረ፡፡ ከአፍታ በኋላም ጌታችን ከሐዋርያቱ ጋር በድጋሚ (ለ፪ኛ ጊዜ) ለምሳ ተቀመጠ፤ ባርኮ ሰጥቶ ልባቸውን ሊያጸና አብሯቸው በላ፡፡
በዚያች ሰዓት ቅዱስ ዼጥሮስን ፫ ጊዜ "ትወደኛለህን?" ሲል ጠየቀው፤ ቅዱሱ አረጋዊም እየደጋገመ "ለሊከ ተአምር ከመ አነ አፈቅረከ (እንድወድህ አንተ ታውቃለህ" ሲል መለሰ፡፡ ጌታም በበጐች ሐዋርያት (ካህናት)፤ በጠቦቶች አርድእት (ዲያቆናት)፤ በአባግዕት ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት (ምዕመናን ወምዕመናት) ላይ ሁሉ እረኛ እንዲሆን ሾመው፡፡
❤ ይህ ምሥጢር ለጊዜው ጌታችን ሐዋርያትን፣ ሰብዐ አርድእትንና ሠላሳ ስድስቱን ቅዱሳት አንስት በአጠቃላይ መቶ ሃያውን ቤተሰብእ እንዲጠብቅና እንዲከባከብ ቅዱስ ጴጥሮስን ማስጠንቀቁን፤ ፍጻሜው ግን የቤተ ክርስቲያን አባቶች (ጳጳሳት) መምህራንንና መላው ሕዝበ ክርስቲያንን እንዲጠብቁና እንዲያስተዳድሩ በእግዚአብሔር መሾማቸውን የሚያስረዳ ትርጕም አለው ዮሐ.፳፩፥፩-፲፯ (አንድምታ ትርጓሜ)፡፡ ቀጥሎም የቅዱስ ጴጥሮስን የሰማዕትነቱን ምሥጢር ገልጦለት "ተከተለኝ" (ለጊዜው በእግር፤ በኋላ ግን በግብር ምሰለኝ) ብሎታል፡፡ ወልደ ነጐድጓድ ወፍቊረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስም ሞትን እንደማይቀምስ እንዲሁ ተናግሮለታል።
❤ ጌታ ለሐዋርያት በአንድነት የተገለጠባትን ይህች ቀን እነዚህ ሁሉ ተግባራት የተከናወኑባት ናትና (የትንሣኤ በዓል ፳፭ኛ ቀን) መሠረት በማድረግ፤ የኋላ ሊቃውንት በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን ዐራቱ ሊቃነ ጳጳሳት የሚሰበሰቡበት የካህናት መገናኛ ቀን ርክበ ካህናት ይሁን ብለው ወስነዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ርክበ ካህናት በዓለ ትንሣኤ በዋለ በ፳፭ኛው ቀን፣ በበዓለ ሃምሳ እኩሌታ በዕለተ ረቡዕ ይዘከራል፤ በያዝነው ዓመት በ፳፻፲፭ (2015) ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ከተከበረበት ዕለት (ሚያዝያ ፰ (8) ቀን) ጀምሮ ብንቈጥር ፳፭ (25) ኛው ቀን ግንቦት ፲ (10) ቀን ይኾናል፡፡ በመኾኑም የዘንድሮው ርክበ ካህናት ግንቦት ፪ (2) ቀን በዕለተ ረቡዕ ይውላል ማለት ነው፡፡
❤ ይህ በዓል ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የቆዩ አባቶቻችን ጌታንና ደቀ መዛሙርቱን አብነት በማድረግ በጋራ በመሰባሰብ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተቀላጠፈ አገልግሎት እንደዚሁም ለምእመናን አንድነትና መንፈሳዊ ዕድገት የሚበጁ መንፈሳውያን መመሪያዎችን የሚያስተላልፉበት እለት ነው፡፡
❤ ይህንን የጌታችን ትእዛዝና የሐዋርያትን ሥልጣነ ክህነት መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ጉባኤ ያደርጋል፤
❤ ፩ኛ. የመጀመሪያው ጉባኤ ጥቅምት ፲፪ ቀን (የቅዱስ ማቴዎስ በዓለ ዕረፍት) ሲሆን፣
❤ ፪ኛ. የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን የሚደረ
#ግንቦት_ልደታ
#ክፍል_፪
#የድንግል_ማርያም_ልደት_በነቢያት_አንደበት
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡ መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ መዝ 86፡1-7
💠እግዚአብሔር የዝማሬና የትንቢት ጸጋን ያበዛለት ክቡር ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥርወ ልደት አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት ተገልጾለት ‹‹መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን /መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው/›› በማለት ትንቢት ተናግሯል፡፡
💠‹‹የተቀደሱ ተራሮች›› ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡
💠ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን ‹‹የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ ባባቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው፤ በናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው፤ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው፤ የእናቷም ስም ሐና ነው፡፡›› ብላ ታስተምራለች፡፡
💠ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡ ኢሳ 11፡1
💠ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት ‹‹ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ /ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል/›› በማለት ታላቅ ትንቢትን ተናግሮ ነበር፡፡
💠ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡
💠ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከእሴይ ሥር የተገኘሽ መዓዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ›› በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡
💠‹‹በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ (መዝ 131፡13)›› የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡
💠ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡ መኃ 4፡8
💠በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡
💠በሊባኖስ ስለመሆኑ አስቀድሞ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት /ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች/›› በማለት ተናግሮ ነበር፡፡
💠 የዚህ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡
💠 ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በ15 ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡
💠ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረው ቃልም መፈጸሙን ሲገልጽ ‹‹….የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል እንደተናገረ፡- ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡›› በማለት አመስጥሮታል፡፡
💠 እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡
#ለሃሳብ_አስተያየት
@DnIsraelYeArsemaLije
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
ግንቦት ልደታ
#በዚህ_እለት_በማወቅ_ወይም_ባለማወቅ_ሲደረጉ_የሚታዩ_የባዕድ_አምልኮ_ና_ማድረግ_የሌለብን_ነገሮች_ምን ም_ ናቸው ????
#ነገር ግን በበጎ ነገሮች #ሰበብ_ክፉ_ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ #የግንቦት_ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡
#በዚህ ዕለት አንዳንዶች #ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ #በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡
#እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡
#እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ በምሕረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡
#ለሃሳብ_አስተያየት
@DnIsraelYeArsemaLije
ለመቀላቀል
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 2
#ክፍል 3
#ቅዱስ_ቁርባን_መቀበል_የማይገባቸው_እነማን_ናቸው?
👉ይህን ርዕስ ሥጋ ወደሙ ለማን? የሚለው ርዕስ በከፊሉ የሚዳስሰው ቢሆንም በራሱ ቁም ነገር
የሚያስጨብጥ ሆኖ ስላገኘሁት በአጭሩ ከዚህ በታች ማብራሪያ አቅርቤበታለሁ::
👉በመሠረቱ ቅዱስ ቁርባን ለሰው ልጆች መዳን የተሰጠ ጸጋ ቢሆንም ወደዚህ የሕይወት እንጀራ መቅረብ የማይገባቸው አሉ።
👉ክርስቶስን በወቅቱ ማን እንደሆነ ያላወቁና የተቃወሙ እንዳሉ ሁሉ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ያልገባቸውና ለቅዱስ ቁርባን ተቀራኒ ሕይወት ያላቸው ናቸው እነዚህም፣
👉ሀ/ በልዩ ልዩ የክህደት ጐራ የተሰማሩና ወንጌል ያልደረሳቸው በክርስቶስ የማያምኑ አምነውም ያልተጠመቁ::
«ኢየሱስም መለሰ እንዲህ ሲል እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም::» (ዮሐ 3÷5
👉ለ/ ሕብስቱ ተለውጦ ሥጋ አምላክ ወይኑ ተለውጦ ደመ አምላክ መሆኑን ያላመኑ አምነው የሚጠራጠሩ፡፡
«ኢየሱስም ስለ አየኸኝ አምነሃል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁእን ናቸው» አለው:: / ዮሐ 20:29/
👉ሐ/ ቅዱስ ቁርባን ኃጢአትን የሚያስተስርይ መሆኑን ያልተረዱና በተለይ ቅዱስ ቁርባን የሚዘጋጀው ለጻድቃን ሳይሆን ለኃጥአን እንደሆነ ያልገባቸው::
«የሰውን ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና አለው» ሉቃ 19: 10/
👉መ/ በቅዱስ ቁርባን የዘላለም ሕይወት የሚገኝ መሆኑን ተምረው ያላወቁ አውቀውም ለዚህ ጸጋ መንፈሳዊ ፍላጐት ጉጉት ለሌላቸው
«ኢየሱስም እንዲህ አላቸው የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም፡፡» /ዮሐ 6:35/
«በእውነት አምነው ከርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት ማስተስርያም ሊሆን የሚሰጥ የጌታችንና
የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ «እማሬ>>ነው። /ቅዳሴ ሐዋርያት
👉ሠ/ ከኃጢአታቸው ያልተመለሱ ያልተጸጸቱ ያልተናዘዙ በማን አለብኝነት ለመቀበል የሚፈለጉ በሰሩት ኃጢአት ንስሀ ያልገቡ
«አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ት ኢዩ 2 : 12 /
«ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሀ ግቡ ተመለሱም»
ሐዋ. 3፥20/
👉ረ/ ቆራቢ ለመባል ለታይታ ለከንቱ ውዳሴ ሰው ይየኝ ብለው ለመቁረብ የሚፈልጉ ግብዞች
«ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው
እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም» /ማቴ. 6: 17
👉ሰ/ የቅዱስ ቁርባን ጸጋና ምስጢር ሳይገባቸው ባልንጀሮቻችውን አይተው እንመሳሰል ብለው ለመቀበል የሚፈልጉ
👉ሸ/ የመናፍቃን ትምህርት የበረዛቸው የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት ቅዱስ ቁርባን አማናዊ /እውነተኛ/ አይደለም መታሰቢያ ነው እንጂ የሚሉ
👉ቀ/ መስለው ገብተው የክርስትናን ኃይማኖት የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን እናፈርሳለን ብለው ቅዱስ ቁረባንን እንይ ምስጠጕሩንም እናውጣ ብለው ለመቀበል የሚፈልጉ
«ከውሾች ተጠበቁ ከክፉዎች ሠራተኞችም መገረዝ ተጠበቁ / ፊልጵ 3:2/
👉በ/ ያለ እምነት በድፍረት ያለ ንስሀ በኃጢአት በመናቅ እንደ ምድራዊ ማዕድ በመቁጠር ለሚደፍሩ
እግዚብሔርን መፍራት በሕይወታቸው ለሌላ
«የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው
1 71
እንግዲህ በነዚህ በተዘረዘሩና በሌሎች ምክንያት
ቁርባንን ሳይገባቸው በድፍረት የሚቀበሉ ስለ በረከት
ፈንታ መርገምን ስለ ሥርየት ኃጢአት ፈንታ ገሃነመ እሳት ከክርስቶስ ዘንድ ይቀበላሉ።
ቃለ እግዚአብሔር ከመማር ከንስሐና ስጋውና ደሙን ከመቀበል ጋር ያልተባበረ አገልግሎት ምግባር ትሩፋት ...ሕይወት ??????
#ምዕራፍ 2
ክፍል 4
❖ባልና ሚስት ተነጣጥለው ብቆርቡስ??
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት
👉 @DnIsraelYeArsemaLije 👈
ያለፈውን ክፍል ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/dnhayilemikael/4948
ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 2
#ክፍል 2
#ቅዱስ_ቁርባን_ለመቀበል_የተወሰነ_ዕድሜ_አለን??
👉ብዙ ጊዜ #ህፃናት እስከ ሰባት ዓመት ሲያቆርቡ ኖረው ከዚህ እድሜ ሲገፋ ወንዱን «ለአቅመ አዳም» ደርሰሀል መቁረብ አይገባህም ሴቷን «ለአቅመ
ሔዋንን ደርሰሻል>> ደርሰሻል መቁረብ አይገባሽም የሚለውን አባባል በአንዳንዶች ዘንድ ከአባበል አልፎ
እንደ ቀኖና /ህግ/ ተወስዷል።
👉#ወጣቶች በእድሜያቸው /በወጣትነታቸውን/ ምክንያት ብቻ ወደ ቁርባን መቅረብ እንደሌለበት
ሲነገርባቸው እንሰማለን፡፡
👉ራሳቸው ወጣቶች በዚህ ሰው ሰራሽ ትምህርትና ተራ አባባል ታምነው «ለአቅመ አዳም» «ለአቅመ ሔዋን>> ደርሻለሁ ወደ ቁርባን መቅረብ አይገባኝም ሲሉ ይደመጣሉ።
🙏👉#የሚገርመው ወጣትነትን በራሱ ብቻ እንደ #ኃጢአተኝነት ወይም ለቅዱስ ቁርባን ብቃት የሌለው ሕይወት አድርጐ መውሰድበራሱ ትልቅ ስህተት ነው:: 👉እንዲህ አይነቱን አባባል የሚቀበሉና
እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ወጣቶች ወደ ሥጋ ወደሙ መመለስ የሚገባቸው በስተርጅና አይን ሲፋዝ ጉልበት /ሲደነዝዝ/ እንደሆነ ይስማማሉ፡፡
👉ይህንም ኣስተሳሰብና አባባላቸውንለማጠናከር የሚጠቀሙበት ቢሂል አለ እርሱም <<ጣጣውን ሲጨርስ /ስትጨርስ />> የሚሉት ነው:
👉እዚህ ላይ ለአንባብያን ላስገነዝብ የምወደው እነዚህ ሰዎች በራሱ ኃጢአት «ጣጣ መሆኑን>> መመስከራቸውን ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳስመሰከራቸው ልብ እንድትሉት ነው.
👉ታዲያ በዚህ አባባል ሰው ኃጢአትን ሲሠራ እንዲኖር ወይም ኃጢአት ለመሥራት ተስማሚው እድሜ ይህን ወጣትነት አድርጐ እንደ መመደብ የሚቆጠር አባባል ነው::
👉ለሁሉም #መልሱን የሚሰጠው የወንጌሉ ቃልና የቤተ ክርስቲያኒቱ ህግና ሥርዓት ስለሆነ ከዚህ በታች
በአጭሩ እንመልከት፡፡
👉ታላቁ ሰው ንጉሱና ነብዩ ሰሎሞን « #በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» (መክ 12 1/ በማለት ሰው በጉብዝናው እድሜ ራሱን ለአምላኩ እንዲያቀርብ በቅዱስ ቃሉ ይጣራል ቤተ ክርስቲያኒቱም ብትሆን መሥዋዕቱ በሚለወጥበት በታላቁ ጸሎት
በጸሎተ ቅዳሴው/ ለተዘጋጀውና ለቀረበው የሕይወት ማዕድ ምዕምናኗን ስታዘጋጅ ካህኑ የሚለው
« #በወጣትነት_እድሜ_ያላችሁ_አትቅረቡ_ሳይሆን
« #ንጹህ _ያልሆነ_ግን_አይቅረብ/ ነው
👉 እንግዲህ #ባጠቃላይ ከነቢያት ወገን ወጣቶች አሉ እግዚአብሔር እነ #ሶምሶንን እነ #ጌድዩንን ለሚፈልገው አምላካዊ ዓላማው የጠራቸው
#በጉብዝና እድሚያቸው ነው፡፡
👉ጌታ የቁርባንን ሥርዓት ሲሠራ ከነበሩት ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት #ወጣቶች ነበሩበት
👉በየትኛውም እድሜ_ለሚገኙ ክርስቲያኖች ኃጢአት የሚሰሩበት እድሜ ስ#ላልተመደበላቸው
ወደ ቅዱስ ቁርባን #ለመቅረብና #ላለመቅረብ የተመደበም እድሜ የለም ወደ ሕይወት እንጀራ ወደ ሥጋ ወደሙ ወደሙ ለመቅረብ መስፈርቱም እድሜ ሆነ መወሰድ የለበትም::
#ምዕራፍ 2
ክፍል 3
❖ ቅዱስ ቁርባን መቀበል የማይግባቸው
እነማን ናቸው?
ይቀጥላል .....
ያለፈውን ለማግኘት ክፍል ለመግኘት 👇👇👇👇👇
/channel/dnhayilemikael/4946
ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 2
#ክፍል 1
#ቅዱስ_ቁርባን_ለማን???
«ኢየሱስም መልሶ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች
መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ልጠራ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው /ሉቃ 5:31
ይህን ቃል መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው።ከኃጢያተኞች ጋር በማዕድ በመቀመጡ ፈሪሳውያን ለምን ከኃያተኞች ጋር ይበላል በማዕድ ይቀመጣል ብለው በማንጌራራቸው የተነሳ ነው ::
ለነዚያ ኃጢአተኞች የሚያስፈልጋቸው መድኃኒት ወነፍስ እርሱ እንደሆነ መለሰላቸው እንጂ ያመጣው ለጻድቃን ለንጹሀን እንደሆነ አይደለም የተናገረው::
👉ቅዱስ ቁርባን ለማን የሚለው ጥያቄ በእያንዳንዱ ሕይወት የራሱ የሆነ አንድምታ ትርጉም የሚሰጠው
የአብዛኛው አመለካከት አማኙን ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቅና የወንጌሉ ቃል ተቃራኑ ሆኖ እናገኘዋለን ::
👉ይሁንና በዚህ ምዕራፍ ቅዱስ ቁርባን የሚገባቸው እነማን
እንደሆኑ በዝርዝር ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
#ቅዱስ_ቁርባን_የሚግባቸው ።
👉ሀ/ #የመሥዋዕቱን_መለወጥ_ለሚያምኑ ሕብስቱ ተለውጦ ሥጋ አምላክ ወይኑ ተለውጦ ደመ አምላክ መሆኑን ከልብ ያለ ጥርጥር አምነው ለሚኖሩ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸውን ቃል በእምነት ተቀብለው ለሚከተሉ::
«ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን ኣንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ብሉ ይህ ስጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋንአንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእር
ጠጡ ይህ ደሜ ይህ ነው» /ማቴ 26.26/
👉 ለ/ ይህ ቅዱስ ቁርባን ለኃጢአት እድፍ መንጺሒ ለኃጢአት ቁስል ፈውስ የተሰጠ መሆኑን ላመነ ባጠቃላይ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ መሆኑንና የዕለት የዕለት የኃጢአት በሽታ መድኃኒትነቱን ለተቀበለ
በተለይ የሚዘጋጀው ለፃድቃን ሳይሆን ለኃጥአን መሆኑን ከልብ ላመኑ ለተቀበሉ «በእውነት አምነው ከእርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት የኃጢአት ማስተስረያም ሊሆን የሚሰጥ የጌታችንና የአምላካችንየኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ «እማሬ ነው ቅዳሴ ሐዋርያት«እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢ ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው »
/ማቴ. 26 27
👉ሐ/ የዘለዓለም ሕይወትን የሚያስገኝ መሆኑን አምነው የዘላለም
ሕይወት ያሰጠኛል ብለው ለሚቀርቡ፣
«ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት
አለው እኔም በመጨረሻ ቀን አስነሳዋለሁ» ዮሐ 6:53/
👉መ/በሚቀበሉት ቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ ከእርሱ ጋር እነርሱ
ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነው እንደሚኖሩ ሥጋው ከሥጋቸው ደሙ ከደማቸው ተዋህዶ አምላካቸው ከእነርሱ ጋር በጸጋ ተዋህዷቸው እንደሚኖር ለሚያምኑ።
«ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ (ዮሐ 6:56/
👉ሠ/ በተጨማሪ በቀደመ ኃጢአታቸው ለተፀፀቲ ለተናዘዙ
ለተመለሱ ከሚመጣው ኃጢአት ለሚጠበቁ ነው::
«ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል
እየሰበከና ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ፡» /ማር |: | 4.
ይህን ሁሉ እውነትና የወንጌሉን ቃል በተረትና በጌታ ባሕል እየሸፈኑ የራሳቸውን አስተሳሰብ ያስተጋቡ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህንን ጸጋ የተጋፉ ናቸው።
#ምዕራፍ 2
ክፍል 2
፨ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተወሰነ ዕድሜ አለን???
ይቀጥላል .....
ጥያቄ ሃሳብ በዚህ አድርሱን👇👇👇 @Dnzearsema
ያለፈውን ለማግኘት
ምዕራፍ አንድ ክፍል 2 ለማግኘት👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 /channel/dnhayilemikael/4941
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆
#ከፖርኖግራፊ_ሱስ_መውጫ_መንገዶች
🥀ፖርኖግራፊ የሞራል ችግር ውድቀት ተብሎ በአብዛኛው ቢታይም ከዛ ባለፈ በዋነኝነት ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ችግር ነው።
🥀ስለ ፖርኖግራፊ ስንነጋገር ከላይ እንደተጠቀሰው አይምሮአችን እንዴት እንደሚሰራ መረዳቱ አስፋላጊ ነው። ለምሳሌ አንዲት እናት ልጅዋን በደረትዋ አስደግፋ በምታጠባበት ጊዜ አዕምሮዋ ‘ኦክሲቶሲን’ የሚል ‘ኒውሮኬሚካል’ ይፈጥራል።
🥀ይህም ኬሚካል አንዲት እናት በውስጣዊ ስሜትዋ ከልጅዋ ጋር እንድትተሳሰር የሚያደርግ ሲሆን፣ በሩካቤ ጊዜ ሰውነታችን የሚኖረው የኬሚካል ሁደትም ይህን ይመስላል።
🥀ፈጣሪ በሰውነታችን የሚለቀቀውን ይህን የኬሚካል ሁደት፣ በባለትዳሮች መካከል የሚደረግ ወሲብን ተከትሎ ስሜታዊ ትስስር የመፍጠር አላማ ቢኖረውም፤ ከትዳር ውጭ በሚኖር ሩካቤ ድርጊት ውስጥ ደግሞ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል።
🥀ሰዎች ፖርኖግራፊ በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚለቀቁት እነዚሁ የ‘ኦክሲቶሲን’ ‘ኬሚካሎች’ ተመልካቹ ከሚመለከተው ምስል ጋር ስሜታዊ ትስስር እንዲኖረው ያደርጋል። በግለ ሩካቤ ሱስም ውስጥ ያሉ ሰዎችም በእነዚህ ኬሚካሎች ከራሳቸው ጋር ትስስር ይፈጥራሉ።
🥀በተደጋጋሚ የሚደረግ ማናቸውም ነገር በአይምሮ ላይ እንዳላቸው ተፅህኖ ሁሉ ፖርኖግራፊም የአይምሮአችንን ቅርፅ በመቀየር በፖርኖግራፊ እስራት ውስጥ መውደቅ ያስከትላል። ስለዚህ ስለፖርኖግራፊ እስራት መውጫ መንገዶች ስናወራ ወደ ሱሱ ሊመሩ የሚችሉ ነገሮችን፣ ተያያዥ ባህሪዎችን እና አመለካከቶችን አብረን ማንሳት ይኖርብናል። ከሁሉ ቀዳሚው ነገር ከላይ እንደጠቀስነው ችግሩ እንዳለ ማመን ነው።
🥀እንግዲህ ከፖርኖግራፊ ሱስ ለመውጣት የምትፈልጉ ወገኖች ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡትን ተግባራዊ ነጥቦች ብትከተሉ ከእግዚአብሔር ፀጋ ጋር 100% ልትወጡ እንደምትችሉ አረጋግጥላችኋለው። ይሄን ጽሁፍ ስታነቡ ወረቀትና እስኪብርቶ ይዛችሁ ለተቀመጡት ጥያቄዎች በፅሁፍ መልስ እየሰጣችሁ እለፊ..
1 #ልዑል_እግዚአብሔር_እንደሚወዳችሁ_ #አውቃችሁ_ንሰሐ_ግቡ
🥀በዚህ ሱስ ውስጥ የገቡ ሰዎች እግዚአብሔር እንደሚጠላቸውና እንደሚጸየፋቸው ያስባሉ። እንዲህ አይነቱ ሃሳብ ሰዎችን የሱሱ ባሪያ አድርጎ ለማኖር ሰይጣን ይጠቀምበታል።
🥀በፖርኖግራፊ ሀጢያት መውደቅን ተከትሎ ሰይጣን ሁልጊዜ እዛው ተብትቦ ሊያስቀረን ይጥራል። ይህም ራሳችንን እንድንጠላ፣ እግዚአብሔር ለእኛ ግድ እንደማይለውና ሩቅ እንደሆነ እንድናስብ እና ተስፋ ቢስነት እንዲሰማን ሀሳባችንን በመያዝ ይተጋል። ሁሌም ቢሆን ውድቀትን ተከትሎ ዋና ጠላታችን ማን እንደሆነ ማወቁ ተገቢ ነው።
🥀በጥፋታችን ማዘናችን ተገቢ ቢሆንም እንደ ይሁዳ ወደ ከፋ እርምጃ የሚወስድ መሆን የለበትም። (ማቴ 27:4-5) ራሳችንን በመጥላት ውስጥ ዋዥቀን ራሳችንን የመቅጣት አዝማሚያው ቢኖረንም መውሰድ ያለብን እርምጃ በእግዚአብሄር ፊት እንደ ዳዊት በንስሃ መደፋት ነው (መዝ 51:1- 10) በእኛ እና በኃጢያታችን መካከል ልዩነት አለ።
🥀እግዚአብሔር ኃጢአትን ይጠላል፤ ኃጢያተኛውን ግን ይወዳል። እናት የልጅዋ ልብስ ቢቆሽሽ ለልጅዋ ያላት ፍቅር እንደማይቀየር እግዚአብሔርም ለእኛ ያለው ፍቅር አይቀየርም። ከዚህ ህይወት ወጥታችሁ ወደ እርሱ ለመምጣት ብትወስኑ እጆቹን ዘርግቶ ይቀበላችኋል።
🥀በቀራንዮ ላይ የፈሰሰው የኢየሱስ ደም ከኃጢያታችሁ ሁሉ እንደሚያነጻችሁ አምናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ ግቡ። “የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ዮሐ 1:7) የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለ ዓለም ሁሉ ስለፈሰሰ በእግዚአብሔር ፊት ይቅር የማይባል ኃጢያት የለም።
2. #አምናችሁ_ጸልዩ
🥀የሰው ልጅ በራሱ ጥረት ከኃጢአት መውጣት አይችልም። የእግዚአብሔር ጸጋ ሲያግዘው ግን የማይቻለውን ችሎ በቅድስና አሸብርቆ መኖር ይቻላል።
🥀እስከ ዛሬ በግል ጥረታችሁ ከዚህ ሱስ
መውጣት ስላልቻላችሁ ተስፋ ቆርጣችሁ ሊሆን ይችላል። ጸጋው ግን ጣልቃ ገብቶ አዲስ ህይወት ሊሰጣችሁ ይችላል። ይህ ደግሞ የሚሆነው “እኔ ደካማ ስለሆንኩ የሚረዳኝ ጸጋ ይሰጠኝ” ብሎ በጸሎት እግዚአብሔርን በመለመን ነው። በፀሎት ትጉ (ኤፍ 6:18)።
🥀መውጣት እንደሚቻል አለማመን በራሱ ሰንሰለት ነው። የእግዚአብሔር ፀጋ ታሪክን እንደሚቀይር ከዚህ ህይወት መውጣት እንደሚቻል እመኑ። ምክንያቱም ከኃጢያት አስወጥቶ ቅዱስ የሚያደርግ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጧልና። (ቲቶ 2:11-13)
3. #ሀሳብን_በሀሳብ_ተዋጉ
የፖርኖግራፊ ኃጢያት ስርወ-መሰረቱ ሀሳብ አንደመሆኑ ሀሳብን ልንዋጋው የምንችለው በሌላ ሀሳብ በመተካት ብቻ ነው። አዕምሮእችንን በእግዚብሄር ሀሳብ ለመሙላት ደግሞ ዕለት ዕለት የእግዚአብሄርን ቃል በማንበብ እና በፀሎት ጊዜ ማሳለፍ ያስፈልጋል። ደስታችንን በእግዚአብሄር ስናገኝ በሀጢአት የምናገኘውን ጊዜያዊ ደስታ እየተፀየፍን እንሄዳለን።
4. #ለምን_እንደምታዩ_እወቁ
አንዲት እህት ከ 4ዓመት በፊት አስገድዶ መደፈር ደርሶባት ነበር። ሌሊት ስትተኛ ያለፈችበት እየታወሳት ትጨነቅ ነበር። ከዚህ ስቃይ ማምለጫ ያደረገችው ፖርኖግራፊ መመልከት ነበር።
🥀ለዚህች እህት ፖርኖግራፊ መመልከት የችግሩ መገለጫ እንጂ ዋናው ችግሩ እንዳልነበር ነው። ከዚህች እህቴ ጋር ጊዜ ወስደንም ስናወራ አሰቃቂ ከሆነ ጉዳት በኋላ ሰዎች የሚኖራቸው የስነ ልቦና መቃወስ /Post Traumatic Stress Disorder/ እንዳለባት ማረጋገጥ ችያለሁ።
🥀ፖርኖግራፊ መመልከት ሰዎች በህይወታቸው ያልፈቱት የውስጣዊ ችግር መገለጫ ሊሆን ይችላል። ጊዜ ወስዳችሁ በሕይወታችሁ የሚያስጨንቃችሁን ነገር፤ ያለፋችሁበትን ታሪክ ለመለየት ሞክሩ። ችግሩን በውስጣችንን ተጭኖ ለማስቀረት (repress) ለማድረግ መሞከር ወደ ባሰ ችግር ይወስዳልና ችግሩን ተጋፍጣችሁ መፍትሄ ለመስጠት ሞክሩ።
5. #ቀስቃሽ_ነገሮችን_ለዩ
ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች ለራሳችሁ መልሱ።
• በብዛት ፖርኖግራፊ የምታዩት የትኛው ሰአት ላይ ነው?
• ለመጨረሻ ጊዜ ፖርኖግራፊ ያያችሁት መቼ ነው?
• ፖርኖግራፊ ከመመልከታችሁ በፊት ምን አይነት ስሜት (mood) ላይ ነበራችሁ?
🥀ቀስቃሽ ነገሮቻችሁ ምንድን ናቸው ስሜትን የሚያነሳሱ የሙዚቃ ክሊፖች ወይንስ ፊልሞች? አንዲት እህቴ ፖርኖግራፊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች የምታገኘው ከፌስ ቡክ ላይ ነበር። ከዚህ ህይወትም ሙሉ ለሙሉ መውጣቷን እስክታረጋግጥ ድረስ ፌስቡክ መጠቀሟን አቆመች።
🥀ከዚህ በፊት የሰበሰባችሁት ፊልምና ማንኛውም ነገር አሁኑኑ አስወግዱ። ለዚህ ዓላማ የምታገኙአቸው ሰዎች ካሉ ግንኙነታችሁን አቋርጡ። ኢንተርኔት መጠቀም ማቆም ካለባችሁ አድርጉት። ግድ መጠቀም ካለባችሁም ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ተጠቀሙ። ወይም እንደ ‘Covenant eyes’ ወይም ‘X3watch’ ያሉ ፕሮግራሞችን ተጠቀሙ ከሕይወታችሁ የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና!
🥀ወደ ፖርኖግራፊ የሚገፋፋችሁ ጭንቀት ከሆነ ከጭንቀት መውጫ ሌሎች መንገዶችን ፍጠሩ። ስሙን ሳልጠቅስ ታሪኩን እንዳጋራ የፈቀደልኝን የአንድነትና ወንድምን ሕይወትም ላንሳ፤ “ከሚስቴ ጋር ባለን ህይወት ደስተኛ አይደለሁም።
🥀እቤት መሄዴን ሳስብ ጭንቀት ይወረኛል። መደበሪያዬ ፖርኖግራፊ ሆኖ ለዘመናት ኖርኩኝ። የትዳሬን ችግር መፍታቴ ከፖርኖግራፊ ሱስ አስመለጠኝ”።
የእናንተን ቀስቃሽ ነገርን ጻፉት።
6. #ታገሉ!
🥀ከዚህ ሱስ መውጣት ሂደት ነው። ለማቆም ከወሰናችሁ በኋላ እንኳን መ
+ አትክልተኛ መስሏት ነበር +
መግደላዊት ማርያም በዕለተ እሑድ ገና ጨለማ ሳለ ወደ ጌታ መቃብር ልትሔድ ተነሣች፡፡ እርግጥ ነው በጨለማ መውጣት ያውም ለሴት ልጅ የሚያስፈራት ቢሆንም ለዚህች ቅድስት ግን ከክርስቶስ ሞት በላይ ሌላ ጨለማ ገዝፎ ሊታያት አልቻለም፡፡ የሕይወትዋ ብርሃን በመቃብር ውስጥ አድሮአልና ሌላ ብርሃን ነግቶ መንገድ እንዲያሳያት አልጠበቀችም፡፡ ለሰው ሁሉ የሚያበራውን መብራት ክርስቶስን ከመቃብር ዕንቅብ በታች ካኖሩት ሦስት ቀን መሆኑ እንጂ የቀንና ሌሊቱ ልዩነት አልታወቃትም፡፡
በእርግጥም ሰባት አጋንንት ከላይዋ ላይ አውጥቶላት የነበረችን ሴት የቱ ጨለማ የቱ ጋኔን ሊያስፈራት ይችላል? ‹‹ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል››ና ጨለማውን ሳትፈራ ይህች ሴት እስኪነጋ ልቆይ ሳትል ወደ ጌታችን መቃብር ገሰገሰች፡፡
እንደጠበቀችው ግን ጌታችንን በመቃብር አላገኘችውም፡፡ በዚያ የለም፡፡ በመቃብር አለመገኘቱ ለእርስዋም ሆነ ለደቀ መዛሙርቱ ተስፋ የሚያስቆርጥ ኀዘን ላይ የሚጥላቸው ነገር ሆነ እንጂ ‹‹እነሣለሁ›› ማለቱን እንዲያስታውሱ ምክንያት አልሆናቸውም፡፡ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን እንኳን ጲላጦስ ፊት ቀርበው ‹‹ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ፡- ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን›› ብለው ነበር፡፡ (ማቴ. 27፡63) ሐዋርያቱና ማርያም መግደላዊት ግን መቃብሩ ባዶ ሆኖ ሲያዩ እንኳን ‹እነሣለሁ› እንዳለ ትዝ አላላቸውም፡፡ ስለዚህ የእምነት ጉድለታቸውም ደቀ መዛሙርቱን ‹‹እናንተ የማታስተውሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ›› ብሎ ፤ እርስዋን ደግሞ ‹‹አትንኪኝ›› ብሎ ገሠፆአቸዋል፡፡ (ሉቃ. 24፡25፣ ዮሐ. 20፡ 17)
መግደላዊትዋ ጌታችንን በመቃብር ብታጣውም ‹በዚህ ከሌለማ ወደ ቤቴ ልሒድና ልረፍ› ከማለት ይልቅ በዚያው ቆማ ታለቅስ ጀመር፡፡ ከዚህ በኋላ በዕንባ በፈዘዙ ዓይኖችዋ ሁለት መላእክት ከመቃብሩ ግራና ቀኝ ሆነው ተቀምጠው አየች፡፡ ሳታስተውልም ‹‹ጌታዬን ወስደውታል›› አለቻቸው፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳብራራው) መላእክቱ ወደ ውጪ ሲያዩ ዓይናቸውን ተከትላ ዘወር ስትል ጌታችንን ቆሞ አየችው፡፡ ሆኖም አላወቀችውም፡፡
‹‹ኢየሱስም አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሻለሽ ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት፡፡ እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሏት ፡- ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው›› (ዮሐ. 20፡15)
ይህንን ተከትሎ ጌታችን ስላለማመንዋ ገሥፆአት ማንነቱን ገለጸላት፡፡ በዚህም ይህች ቅድስት ትንሣኤውን ከሰበኩ የጽዮን ልጆች አንዲትዋ ሆነች፡፡ የእስራኤልን ነጻ መውጣት የሙሴ እኅት ማርያም በከበሮ እንዳበሠረች ማርያምም የሰው ልጅን ነጻ መውጣት ያለ ከበሮ አወጀች፡፡ እርስዋን ብቻም ሳይሆን ሌሎች ሴቶችንም ዓርብ ዕለት እያለቀሱ ደረት እየመቱ ሞቱን በዕንባ አጅበዋልና እሑድ ዕለት የትንሣኤው ዜና አብሣሪዎች ለመሆን አበቃቸው፡፡ ሴት ልጅን ‹‹ደስ ይበልሽ›› በማለት የተጀመረው የአምላክ የማዳን ሥራም ሴት ልጅ ራስዋ ለሌሎች ‹‹ደስ ይበላችሁ›› ባይ እንድትሆን በማድረግ ተጠናቀቀ፡፡
ማርያም መግደላዊት ‹‹የአትክልት ጠባቂ መስሏት ነበርና ፡- ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው›› የሚለው ንግግር እንዲሁ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን ይህንን ቃል የተናገረችው ሳታውቀው ቢሆንም ንግግርዋ ግን ከስኅተትነቱ ይልቅ ቅኔነቱ የሚበልጥ ንግግር ነው፡፡ ‹‹አትክልተኛ መስሏት ነበር›› የሚለው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው? አበው በትንቢተ ሕዝቅኤል 44ን ሲተረጉሙ ‹ከእውነት የሚሻል ስኅተት ከመግደል የሚሻል መሳት አለና›› ያሉት ይህንን ዓይነቱን ሳይሆን አይቀርም፡፡
ለመግደላዊት ማርያም ክርስቶስ አትክልተኛ መስሏት ነበር፡፡ ወይ ግሩም! ክርስቶስ በምድር በተመላለሰ ጊዜ ለሰዎች ‹ያልመሰላቸው› ምን ነገር አለ? እንደተወለደ ለአይሁድ ‹የዮሴፍ ልጅ መስሏቸው ነበር› ፣ ለሔሮድስ ደግሞ መንግሥቱን የሚቀናቀን ምድራዊ ንጉሥ መስሎት ነበር፡፡ ለኒቆዲሞስ ነቢይ መስሎት ነበር ፣ ለሳምራዊቷ ሴት ደግሞ መጀመሪያ ውኃ የሚለምን ተራ ሰው መሰላት ፣ በኋላ ደግሞ ነቢይ መስሎ ታይቷት ነበር፡፡ ክርስቶስ ለብዙዎ ያልመሰላቸው ምን አለ? ለግማሹ ኤልያስ ፣ ለአንዳንዱ ሙሴ ለሌላው ኢያሱ መሰለው፡፡ ለኤማሁስ ተጓዦች ‹መንገደኛ› ፣ ለሮም ወታደሮች ‹ወንጀለኛ› ፣ ለሔሮድስ መኳንንት ‹አስማተኛ› መስሏቸው ነበር፡፡ እኛ እርሱን እንድንመስል እርሱ እያንዳንዳችንን መስሎ ተሰደበ ተወቀሰ በመከራ ተሰቅሎ ሞተ፡፡ ዛሬ ደግሞ ለመግደላዊት ማርያም ‹‹አትክልተኛ›› መሰላት፡፡
ማርያም ሆይ በአንድ በኩልስ ልክ ብለሻል፡፡ ያየሽው እርሱ አትክልተኛ ነው፡፡ በእውነትስ አትክልተኛ ካልሆነ ‹‹አዳም ሆይ ወዴት ነህ›› እያለ በገነት ዛፎች መካከል ምን አመላለሰው? አንቺ አልተሳሳትሽም ‹‹ወይንን ተከልሁ አላፈራም ፣ ለወይኔ ያላደረግሁት ምን አለ? በእኔና በወይኔ መካከል ፍረዱ›› ብሎ የጠራን እርሱ አይደለምን? ‹‹ዘር ዘሪ ሊዘራ ወጣ ፣ ዘር ዘሪው እኔ ነኝ ፤ አጫጆቹ መላእክት ናቸው›› ብሎ በምሳሌ ያስተማረ እርሱ አይደለምን? ከዚህ በላይ አትክልተኛ ከየት ሊመጣ?
‹የወይን ሥፍራን ነበረችው ቅጥርም ቀጠረላት› በተባለችዋ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁላችንን ከአብ ጋር ላንነቀል የተከለን ፣ የጎኑን ውኃ እያጠጣን ፣ በመስቀሉ እየኮተኮተ የሚያሳድገን ‹‹ጳውሎስ ሲተክል አጵሎስ ሲያጠጣ ጌታ ያሳድግ ነበረ›› የተባለለት አትክልተኛ እርሱ አይደለምን? ሦስት ዓመት ተመላልሶ ፍሬ እያጣብን አዘነ እንጂ ፣ እሾኽና አሜከላ እያበቀልን አስመረርነው እንጂ እርሱስ ብርቱ አትክልተኛ ነበር ፤ ስለዚህ መግደላዊት ማርያም ሆይ አትክልተኛ ቢመስልሽም አልተሳሳትሽም፡፡
‹‹ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ›› የሚለው ጥያቄም ቢሆን ከእውነታው አንጻር እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ጌታን በእርግጥ ከመቃብር ማን ወሰደው? ማንስ አስነሣው? ራሱ አይደለምን፡፡ ማርያም ‹አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ› አለችው፡፡ ማርያም ሆይ ጥያቄሽ ተገቢ ነው ፤ ብቻ አጥብቀሽ ጠይቂው ፤ የወሰደው እርሱ ራሱ ነው፡፡ ሥጋውን ከመቃብር ሕያው አድርጎ ነስነሥቶ የወሰደው ከፊትሽ ቆሟል፡፡ ማስረጃ ከፈለግሽ ‹‹ነፍሴን ደግሞ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ፤ ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ›› ብሎ ሲናገር ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ሰምቶ ማስረጃ መዝግቦ ይዞበታል፡፡ አጥብቀሽ ያዢው! እንዳትለቂው! በፈቃዱ እንደሞተ ነፍሱንም ሊያኖራት ሥልጣን ያለው ከመቃብርም በሥልጣኑ የተነሣው እርሱ ነው፡፡ ማንም ወሰደው ሲሉ ብትሰሚ አትመኚ ፤ ኢየሱስን ከሙታን መካከል ወስዶ ሕያው ያደረገው ይኸው ከፊትሽ የቆመው አትክልተኛ ራሱ ኢየሱስ ነው፡፡
እግሮቹን ወድቀሽ ያዢ እንዳትለቂው ፤ ይህ አትክልተኛ ባዶ ያደረገው መቃብርን ብቻ እንዳይመስልሽ፡፡ ሲኦልን ብታዪ ምን ልትይ ነው? በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የራሱን መቃብር ባዶ ከማድረጉ በፊት የሲኦልን የብረት መወርወሪያ ሰባብሮ አእላፋት ነፍሳትን ዘርፎ ወደ ገነቱ ወርዶ ነበር፡፡ በዚያም ምርኮውን ሸሸገ፡፡ አሁን ደግሞ የቀረውን መቃብር ባዶ አድርጎት ቆሟልና እንዳትለቂው፡፡
መግደላዊት ማርያም ሆይ ‹‹አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋ
#ለቅዱስ_እዲንበቃ_ምን_እናድርግ
ስለቅዱስ ቁርባን ተከታታይ ትምህርት
በ @dnhayilemikael 👈 በዚህ ቻነል ተጀመረ
#ምዕራፍ_አንድ
#ቅዱስ_ቁርባን_ስለፈለጉ_ብቻ_የሚገቡበት_ሕይወት_አይደለም
❖ ምክረ ካህን
❖ ሰው ግን ራሱን ይፈትን
#ምዕራፍ_ሁለት
#ቅዱስ_ቁርባን_ለማን
❖ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተወሰነ
እድሜ አለን
❖ ቅዱስ ቁርባን መቀበል የማይግባቸው
እነማን ናቸው?
❖ ባልና ሚስት ተለያይተው ቢቆርቡስ?
❖ ያላገባ ወጣት መቁረብ ይችላልን?
❖ ቆራቢ የሆነ ሰው የትዳር ጓደኛውን በሞት
ቢያጣ ደግሞ ሌላ ማግባት ይችላል?
❖ ሕጻናትን ማቁረብ
#ምዕራፍ_ሶስት
#ቅዱስ_ቁርባን ለመቀበል የሚደረግ ዝግጅት
❖ ከመቁረብ በፊት
❖ ሰመቁረብ ጊዜ
❖ ከመቁረብ በኋላ
#ምዕራፍ_አራት
#ከቅዱስ-ቁርባን_የሚያርቁ
❖ ስለ እምነት ምንነት አለመረዳት
❖ እምነት ምንድን ነው?
❖ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ
ማሰኘት አይቻልም
#ምዕራፍ_አምስት
#ንጹህ_ያልሆነ_ቢኖር_አይቅረብ
❖ ሳይገባው ማለቱ ምን ማለቱ ነው?
❖ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት
#ምዕራፍ_ስድስት
#የተሣሣቱ _አባባሎችና_የመንደር_ወሬ
❖ የታመመን ሰው ቢያቆርቡት ቶሎ ይሞታል
❖ የቆረበ ሰው ብቻውን ቢሆን ሰይጣን ያገኘዋል
❖ ያላገባ ሰው መቁረብ አይገባውም
❖ ነፍሰ ጡር ሴት መቁረብ አይገባትም
❖ ጋብቻቸውን በሥርዓተ ተክሊል ያልፈጸሙ
ሰዎች መቁረብ አይችሉም
❖ ፍቅረኛሽ እንዳይክድሽ ተያይዛችሁ ቁረቡ
#ምዕራፍ_ሰባት #ቅዱስ_ቁርባንን_እንደ_ጐጂ_መቁጠርና_ሸሽቶ_መኖር
❖ ትዕግሥቱን መናቅ ነው
❖ ቸርነቱን አለመታመን ነው
❖ ፍቅሩን አለመረዳት ነው
❖ መድኃኒትነቱን አለማወቅ ነው
#ምዕራፍ_ስምንት
#የቅዱስ_ቁርባን_ጥቅም
❖ ዘላለማዊ ድህነት እንቀበልበታለን
❖ ኃጢአታችን ይሰረይበታል
❖ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት ይኖረናል
ኃይል መንፈሳዊ አንቀበልበታለን
❖ ክርስቲያኖችን ሁሉ እንደ አንድ አካል ያደርገናል
❖ በሥጋ ወደሙ እንማጸንበታለን
#ምዕራፍ_ዘጠኝ
#የቅዱስ_ቁርባን_ስጦታ_በኛ_ላይ_ያለው_የፍቅሩ_ማረጋገጫ_ነው
❖ በሥጋ ወደሙ ተወስነው ለሚኖሩ
❖ በሥጋ ወደሙ ለመወሰን ለተነሱ
❖ ከሥጋ ወደሙ ርቀው ለሚኖሩ
❖ ቅዱስ ቁርባን የምንቀበልባቸው ዕለታት
❖ ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት
የሚጸለይ ጸሎት
ትምህርቶቹን በተከታታይ መርሐ ግብር እንከታተል አንድ ክርስቲያን ሥጋውንና ደሙን ካልተቀበለ ወይም የማይቀበል ከሆነ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት የለውም
#ትምህርቱን_ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#ቅዱስ_ቁርባን
👉 #ማሳሰቢያ_ላትጨርሱ_አትጀምሩ
#ምዕራፍ_አንድ
#ቅዱስ_ቁርባን_ስለ_ፈሰጉ_ብቻ_የሚገቡበት_ሕይወት_ይደሰም
#መግብያ
«ሰው ግን እራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ
ከጽዋውም ይጠጣ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ
ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ይጠጣልምና /1ቆሮ 1: 27/
በዚህ ርዕሳችን በሰፊው የምንመለከተው ተያይዞ የተጠቀሰውን የሐዋርያውን መልዕት ተንተርሰን ሲሆን በዚህ ሥር ከ2 ያላነሱ ነጥቦችን ጨምረን እንመለከታለን፡፡
ማንኛውም አማኝ ስለፈለገ ብቻ ተንደርድሮ የሚገባበት ሕይወት ሳይሆን ቅዱስ ቁርባን አስቀድሞ ወደ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት ሲገባ የሚከተለውን ነገር ጠንቅቆ ማወቅና ወድዶና ፈቅዶ ስለ ቅዱስ ቁርባን የሚደርስበትን መከራና ፈተና ለመቀበል መወሰንና መዘጋጀት ይኖርበታል. ለዚህም ደግሞ ወሳኙ ምክረ
ካህን ነው።
#ምዕራፍ_አንድ
#ክፍል 1
: 🙏 #ምክረ_ካህን🙏
ምክረ ካህን ማለት አማኙ በኃጢአቱ ከተናዘዘ በኋላ ቀኖና መስጠት ማለት ብቻ ሳይሆን ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ሆኖ #ቅዱስ_ቁርባን ለመቀበል ጥያቄ ላቀረበው ወይም ለተዘጋጀው አማኝ
ከካህኑ ጥልቅ ምክርና የተብራራ ምሪት ሊሰጠው ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ የእርሱ በመሆናቸው የሚገጥማቸውን አስቀድሞ
እንዲያስተውሉ አድርጎ እንዳዘጋጃቸው ካህኑም አማኙን ሊያዘጋጀው ይገባል፡፡
👉ምክረ ካህን ማለት በአጠቃላይ መልኩ አማኙን ከመቁረቡ በፊትና ከመቁረቡ በኋላ ያለውን ሕይወት ሁሉ ያጠቃልላል እንጂ ኃጢአትን መናዘዝ የመስዋዕቱን መለወጥ እንዲያምን ማስተማር
ብቻ ማለታችን አይደለም፡፡ አብነት እንዲሆን ከዚህ በታችእንደጠቀስነው ሊሆን ይገባል።
👉አንድ አማኝ ወደ ቅዱስ ቁርባን ከቀረበ በኋላ ስለሚጠብቀውና ስለሚመራው ሕይወት ካህኑ በዝርዝር ይግለጽለት።
👉ክርስቶስን መከተል ማለት ወደዚህ ሕይወት መግባት ማለት ባለቤቱ እንደተናገረው መስቀሉን መሸከም ማለት ስለመሆነ ይግለጽለት፡፡
🙏ምን አልባትም አማኙ በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ ሲኖር በዓለሙ ዘንድ የተጠላና የተተቸ ሊሆን ይችላል:: ይህን ነገር ክርስቶስ እንዲህ በማለት ተናግሮታል፡- « ስለእኔ በዓለም ውስጥ
የተጠላችሁ ትሆናላችሁ» /ዮሐ 15 -23/ ምክንያቱም የዓለምን ሥራ ስለምናልክስበትና ስለ ምንንቅበት አለም ሊጠላን ሊተቸን ምክንያት ሊፈልግብን ይችላል ሁሉም የሚወደው ወገን ወገኑን
ነውና
👉 ደቀመዛሙርቱ እርሱን በመከተላቸው ዓለም የአበባ ምንጣፍ አንጥፎ አዘጋጅቶ አይደለም የተቀበላቸው ለአንገታቸው ሰይፍ ለሰውነታቸው እሳት እንጂ /ማቴ. 24÷9/
ስለዚህ አንተም መሰል መከራዎች በደረሰብህ ጊዜ የተቀበልከውን ታውቀዋለህና ስለ እርሱ ራስህን ክደሃልና ስለሥሙና ስለ ቅዱስ ቁርባን በሚደርስብህ ደስ ሊልህ ይገባል ምርጫህ ሕይወት
በመሆኑ ሰይጣን መሸነፉንና ባንተ መቅናቱን እወቅ ስለዚህ ካህኑ ይህንና መሰል ጉዳዮችን ሊያሳውቀው ይገባል እንዲህ እያለ ልጄ በርታ አይዞህ ዓለም ቢጠላህ አትደነቅ ደግሞም የገዛ ሃሳብህ ዕር ይሆንብሃል ይህንን አይነቱን ፈተና በዚህ በዚህ መልክ ተቋቁመው ቢገጥምህ እንዲህ ተወጣ የሰዎች ባንተ አይደነቅህ ምክንያቱም ሰይጣን አንተን ለመፈተን ሊጠቀምባቸው ይችላል የሰይጣንን የውጊያ ባህርያት እወቅ ሊለው ይገባል፡፡
👉በሌላ መንገድ ሰይጣን እራስህን በማይገባ ክስ እንድትከስና በጀመርከው ሕይወት እንዳትገፋበት በአሉባልታዎች ሊያውክህትም ይችላል፡፡ አንተ ግን ስለተቀበልከው በቂ ዝግጅትና እውቀት ካለህ
መልስ ትሰጥበታለህ:: «በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ» /1ጴጥ. 3፥15/
👉ይሔውም «አንተ ቆርበህ እንዲህ ትሆናለህ» «ይህ ሰው ከቆረበ ጀምሮ አቅበዘበዘው» «መቁረብ በማይገባት ጊዜ ቆርባ አደብ አጣች» የመሳሰሉትን ይህ አይነት አሉባልታ ሌሎችን በአንተ ላይ
አነሳስቶ የመክሰስ የዲያቢሎስ ውጊያ ነገ ደግሞ ራስህን በራስህ ላይ አነሳስቶ ለመክሰስ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት መሆኑን ልብ
በልና ለአሉባልታ ሳትገዛና እነርሱ ባሉህ /ባሙህ/ ነገር ሳትገኝ ተገቢውን መልስ በትህትና መስጠት ይገባል:: 👉ይኸውም እኔ የተቀበልኩት ሰላም ነሺውን ሳይሆን ፣ አደብ የሚያሳጣውን፣ ሳይሆን የሚያቅበዘብዘውን ሳይሆን፣ #የሰላሙን_አምላክና ሕይወትን
#የሚቀድሰውን_ጌታ ነው ኢሳ 9:6/ በማለት ደግሞ::
👉አንተ ወገኔ የምትናገረውንና እንዲህ የምትተቸውን
ታውቃለህ ሰላም ነሺ አቅበዝባዥ፣ የምትለውን ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስ ለዓለም ሰላም የሰጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው
እኮ ልክ እንደ አይሁድ ሕዝቡን ሰላም ነሳ ብለው ለቄሳር እንደከሰሱት በማለት ምስጢሩ ያልገባውን ወገንህን ማስተማርና
ሰይጣንን ማሳፈር ይገባሀል።
#ምዕራፍ_አንድ
* #ክፍል 2
#ሰው_ግን_ራሱን_ይፈትን
ይቀጥላል ......
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉@dnhayilemikael 👈
👉@dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች
➛ ትዕቢተኛ ዓይን፥
➛ ሐሰተኛ ምላስ፥
➛ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
➛ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
➛ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
➛ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
➛ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
ምሳሌ 6፥16-19
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 2
#ክፍል 7
#ህፃናትን_ማቅረብ
«ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው [መዝ. 23/
👉ቤተ ክርስቲያን ህፃናትን:ካጠመቀች በኋላ እንደሌሎች ወደ ቤታቸው እንዲሔዱ አታደርግም ወዲያውኑ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ታቀብላቸዋለች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር ዘንድ እነዚህን ታላቅ ስጦታዎች ልጆች የተቀበሉ
ወላጆች እየተከታተሉ በማቁረብ ያሳድጓቸዋል ሲሉም
እያስተማሩም እንዲቀበሉ ያደርጓቸዋል።
👉#ሕፃናትን_በማጥመቅና_በማጥመቅ_ዙርያ ጌታችን «ያመነ የተጠመቀ ይድናል» በማለት የተናገረውን በመንተራስ ፕሮቴስታንቶች ከማጥመቅ ይልቅ እምነት ይቀድማል በማለት ሕፃናትን
ማጥመቃችን ስህተት እንደሆነ ይናገራሉ በማቁረባችንም አንዳንዶች ይህንን ይጠቅሳሉ ብዙዎችም መሰረታዊ ጥያቄ የሚያደርጉት
ጥምቀት ቁርባን ያለ እምነትና እውቀት እንዴት ይከናወናል?
ህፃኑ እምነትም ሆነ እውቀት ሊኖረው አይችልም የሚል ነው::
👉እኛ ግን የምናስበው ስለ ሕፃናት ሰማያዊ ሕይወት ነው ይኸውም ጌታችን
👉 «ከውሃና ከመንፈስ ያልተወለደ የእግዚአሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም» /ዮሐ
👉«ያላመነ ያልተጠመቀ አይድንም»ግር 161 6. 👉«ሥጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘላለም ሕይወት የለውም /ዮሐ 653/ በማለት ለሰው
ልጅ ድህነትን ሊያስገኙ ወይም ድህነቱን ሊያሳጡ የሚችሉ ነገሮችን ስለተናገረ ነው።
👉 እንዲህ ከሆነ ስለምን ሕፃናትን አናጠምቅም አናቆርብም?
👉 ስለምንስ ለእግዚአብሔር ፍርድ አሳልፈየን
እንሰጣቸ ዋለን?
👉 ጌታችን የጠቀስኳቸውን ኃይለ ቃላት ሲናገርሕፃናትን አልተዋቸውም ወይም በሌላ አባባል «ከህፃናት በቀር አላለም አልያም ህፃናት ስለሆኑ ለእግዚአብሔር ማንንታቸው አይጠፋም ነቢዩ ኤርሚያስን ለአገልግሎት ሲጠራው ዛሬ ሳይ ሆን
በእናትህ ማህፀን ሳልሰራህ አውቅሀለሁ አለው ይህንንም ነገር ነቢዩ
ሲመሰክር «የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ በሆድ ሳልሠራህ አውቄአለሁ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ።
👉ለአሕዛብም ነብይ አድርጌአለሁ» ኤር 1፡4-5 ብሏል።
👉ሕፃናት ባጠመቃቸው የቤተክርስቲያንን ሕይወት ይለማመዳሉ በቅዱስ ቁርባንም መንፈሳዊ ጥቅምና የሰማያዊውን ምስጢር በረከት ያገኛሉ ከቤተክርስቲያን ካገለልናቸውና ከሚስጢራት
ከከለከልናቸው እምነትንና የጸጋ ምክንያቶችንም መከልከላችን ነው::
👉 ጌታችን ስለ ሕፃናት እንዲህ አለ «ሕፃናትን ተውአቸው ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና» /ማቴ. 19 ፥ 14/
👉ህፃናትን ከማጥመቅም ሆነ ከሌሎች ከሚገባቸው ምስጢራት የሚከለክል አንድ ጥቅስ እንኳን በመጽሐፍ ቅዱስ የለም እንጂ
ያውም በመጽሐፍ ቅዱስ የሙሉ ቤተሰብን መጠመቅ ወይም አንድ ሰው ራሱን ቤተሰቡን ሁሉ ሲጠመቁ ተጽፏል፡፡
👉ቤተሰቦች ሕፃናት እንደነበሩ ምንም ጥርጥር የለውም
➕1. የወህኒ ጠባቂው ከነቤተሰቡ ተጠመቀ
/ሐዋ 16÷32/
➕2 ቀይ ሐር ሻጭዋ #ሊዲያ ከነቤተሰቧ ተጠመቀች /ሐዋ 16÷1 5|
➕3 የእስጢፋኖስ ቤተሰብ ተጠመቁ 1ኛቆሮ.1 : 1 6/
➕4 በዕለተ ጴንጤ ቆስጤ ብዙዎች ተጠመቁ
እንደዚህ ከነቤተሰቦቻቸው ስለተጠመቁ ሰዎች በተፃፈው በጠቀስኳቸው ጥቅሶች «ከህፃናት በቀር» አልተባለም ቤተሰብም የሚለው ቃል ልጆችን ሁሉ ሊያጠቃልል እንደሚችል የሚያጠራጥር አይደለም ወይም ህፃናት አለመኖራቸው ተለይቶ አልተጠቀሰም
በታሪክም ህፃናትን ማጥመቅ ተጽፎ ይገኛል፡፡
👉የኦሪት ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ ነው የተገረዘው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ይቆጠሩ ነበር ኪዳኑ ግን የተሰጠው ለአብርሃም ነው /ዘፍ 7: 1 1/
👉➕#ግዝረት ግን የሚደረገው ህፃኑ ከተወለደ በ80 ቀን መሆኑ የታወቀ ነው ታዲያ በአብርሃምና በእግዚአብሔር መካከል ስላለው ኪዳን የ80 ቀን ህፃን ምን ያውቃል? ከእግዚአብሔር ሕዝብ
ጋር አንድነት መደመሩንስ ያውቃልን? ስለተሰጠው ተስፋ ምን;ያውቃል?
👉እንደደመና ዙሪያችንን የከበበን ምስክር ካልሆንን ህፃኑን በማቁረባችን መች አመነና ምኑን ያውቀዋል የሚለው ጥያቄ ከሰዎች የሥጋ አስተሳሰብ የሚፈልቅ ጥያቄና ፍልስፍና ስለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡
👉ስለዚህ ህፃኑን ለቅዱስ ቁርባን ማዘጋጀቱና ከቆረበም በኋላ አስፈላጊውን ክትትል ጥበቃ ማድረግ የወላጆቹና የመንፈሳውያን አገልጋዮች ግዴታ ነው::
👉ብዙ ጊዜ ወላጆች ክትትል ባለማድረጋቸው ልጆች ከቅዱስ ቁርባን እርቀው ሲያድጉና እያደጉም ሲሔዱ በንጹህ አእምሮአቸው ላይ የሚቀበሉት ምን እንደሆነና ስለ መንፈሳዊ ጥቅሙ ሊቀርጹባቸው ሲገባ ማቁረቡን እንጂ ማስተማሩን ችላ ሲሉት ይስተዋላል ይህ
ደግሞ ህፃኑ ካደገ በኋላ በራሱ ለቅዱስ ቁርባን ፍቅር እንዳይኖረውና ማድረግ ያለበትን እንዲያውቅ ስለሚያደርግ
👉;#ስለዚህ_በሚገባው_እያስተማሩ_ማቁረብንና_ማሳደጉን_መዘንጋት_የለበትም፡፡
#ምዕራፍ 3
ክፍል 1
❖ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የሚደረግ ዝግጅት
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት
ምዕራፍ አንድ ክፍል 1 ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 2
#ክፍል 6
#ቆራቢ_የሆነ_ሰው_የትዳር_ጓደኛውን_በሞት_ቢያጣ_ደግሞ_ሌላ_ማግባት_ይችላል?
👉️በሥጋ ወደሙ /በቅዱስ ቁርባን/ ተወስነው ከሚኖሩ ባልና ሚስት መካከል አንዱ በሞት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ ቀሪው ሊያገባ አይችልምና የሚል አባባል የተለመደ ሲሆን ከዚህ የተን በአማኙ መካከል ብዙ ጥያቄ ያስነሳል፡፡
✝️✝️✝️በቅድሚያ በዚህ ውስጥ ሊገለጥ የሚገባው ስለሟች ድህነት ሲሆን ሟቹ ከህግ የትዳር ጓደኛው ጋር ጸንቶ የክርስቶስን ሥጋን ደም ሲበላና ሲጠጣ /በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ/ በመኖር ለድህነቱ
ዋስትና ይዟልና የዘላለም ሕይወት ባለቤት ነው «ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻ ቀን
አስነሳዋለሁ» /
ዮሐ 6፥53/
👉ጌታችን ይህን የጠቀስነውን ቃል የተናግረውም ይህንኑ ለማረጋገጥ ነው። በክርስቶስ ወንጌል ለሚያምንና የተናገረውን እንደማያስቀር ተስፋ ለሚያደርግ ይህንን እውነት ሊቃወምና በዚህ
ቃል ሊጠራጠር አይገባውም «የዘላለም ሕይወት አለው» የሚለው ቃል የእራሱ ሁሉን ማድረግ የሚችለው የክርስቶስ ቃልና ቃሉም
የሚፈጸምና ነብዩ ኢሳይያስ እንደተናገረው ሥራ ሳይሰራ
የማይመለስ ቃል ነው፡፡ /ኢሳ 55÷11/
👉 ፈይሁንና የትዳር ጓደኛው የሞተበትን ሰው ከሟች የትዳር ጓደኛው ጋር ሲቆርብ በመኖሩ ብቻ ሊያገባ አይችልም ብለው መወሰን አይቻልም በቤተ ክርስቲያንም እንደ ህግ ወይም እንደ ሥርዓት በዚህ ጉዳይ የሚከለክል ትምህርት የለም::
👉የትዳር ጓደኛው የሞተበት ቆራቢ ምዕመን ከሆነ በፈቃድ «ወንዱ ከሴት እርቆ ንጽህ ጠብቆ»፣ «ሴቷ ከወንድ እርቃ ንጽህ
ጠብቃ»፣ ለመኖር እንጂ ለማግባት ባይፈልጉ ፈቃዳቸው አይከለከልም መልካምም አድርገዋል ቅዱስ ጳውሎስ «ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል» በማለት ለቆሮንቶስ ምዕመን ጽፎላቸዋል
/1ቆሮ 7÷32/
👉በሌላ መልኩ ግን ቀሪው ማግባት ቢፈልግ አይከለከልም ወንዱ ቆራቢዋን ፈልጐ ወይም በድንግልና የኖረችዉን በንጽህና የምትመላለሰውን አጭቶ ወደ ቆራቢነት ሕይወት አድርሶ ሊያገባ
ይችላል ሴቷም እንዲሁ ልታገባ ትችላለች በዚህ ዙሪያ ሐዋርያው ጳውሎስ የተብራራ መልዕክት ጽፎልናል እንዲህ በማለት ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት፡። እንደ ምክሬ ግን እንዳለች ብትኖር ደስተኛ ናት እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር
መንፈስ በእኔ ያለ ይመስለኛል:: 1ቆሮ 7:39-40/ ይህ ቃል ለወንዱም እንዲሁን ነው
#ምዕራፍ 2
ክፍል 7
❖❖ #ህፃናትን ማቁረብ
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት
ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
☦️በዕለተ አርብ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል ጌታ ውሃ ተጠማ፡፡ለአንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በዓርብ ጠዋት ቁርስ ቢቀርብለህ በስመ አብ --በዓርቡ ምድር እንዴ ይባላል
☦️ጾም ለንፍስ ምግብ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በተለይ በዓርብ እንዴት በጠዋት ይበላል
☦️ጌታ ሐሙስ ማታ ከተያዘባት ሰዓት ጀምሮ ለ18 ሰዓት ያህል በባዶ ሆዱ እህልነ ውኃ በአፋ ሳይገባ ሲንገላታ እሰከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ውሎ በተሰቀለበት በዓርቡ ምድር እንዴት በጠዋት ይበላል
☦️የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ በጎዳና ላይ ወድቆ ሲረገጥ በዋለበት ደሙ እንደ ውኃ በፈሰሰበት ማለዳ ምን እንጀራ ይበላል?
☦️ይህን እያሰቡ ቢበሉስ እንዴት ከሆድ ጋር ይሰማማል?ተጠማሁ ብሎ በጮኸበት ዓርብ ማለዳ የሚጠጣ መጠጥስ እንዴት ከጉሮሮ ይወርዳል፡፡
☦️እንደ ጻድቁ አባታችን እንደ መባዓ ጽዮን የቀመሰውን ሐሞትና የጠጣውን ሆምጣጤ እየሰብን በየሳምንቱ ዓርብ መራራ ኮሶ መጠጣት ቢያቅተን፤ እንደ እናቶቻችን መከራውን በስግደት ማሰብ ቢያቅተን በመጾም የጌታችንን ረሃብና ጥሙን እናስባለን እንጂ ኦርቶዶክስ በዓርብ ቀን በጠዋት አይበላም፡፡
☦️ለአርባ ቀንና ሌሊት የጾመው ጌታችን በዚያች በዕለተ ዕለት 18 ሰዓታት መቆየቱ ምናልባት ለሰሚው ትልቅ ነገር አይመስልም ይሆናል፡፡☞ሆኖም ጌታችን ከረሃቡ ይልቅ ትልቁ ሥቃዩ የውኃ ጥም ነበር፡፡ከማታ ጀምር ሲንገላታና ሲደበደብ አድሮ፤ ያ ሁ ግርፋት ከዘነበበት በኃላ እጅግ ከባድ መስቀል ተሸክሞ እየወደቀ እየተነሣ ወደ ቀራንዩ ወጥቷል፡፡
☦️"ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፤ በጉሮሮዬ ምላሴ ተጣጋ"ተብሎ እንደተነገረ ከደሙ መፍሰስና ከድካሙ ብዛት የተነሣ እጅግ የሚቃጥል ትኩሳትና የውኃ ጥም ያሰቃየው ነበር፡፡ ☞ሥቃዩን አደንዝዞ ሊያስታግሥለት የሚችለውን የወይን ጠጅ ሲያቀርቡለት ሊጠጣ ያልወደደው ጌታ የውኃ ጠሙን ለእኛ ሲል ታግሦ በመስቀል ላይ ለሦስት ሰዓታት ቆይቷል፡፡
☦️በመጨረሻ ግን"አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፋ ቃል ይፈጸም ዘንድ ተጠማሁ አለ"(ዮሐ )
☦️የመጽሐፍ ቃሎ "ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፤ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ የሚል ሲሆን ስለ ሐሞቱ የተነገረው ትንቢት በረጡት ጊዜ ቀምሶ በመተው የተፈጸመ ሲሆን የቀረው የሆምጣጤ ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ተጠማሁ አለ፡፡
☦️ጌታችን በመስቀል ላይ"ተጠማሁ"ሲል መሰማት ምነኛ ያስጨንቃል?በሀገራችን "የአባይን ልጅ ውኃ ጠማው"የሚል ብሂል አለ በዕለ ዓርብ ግን የአባይን ፈጣሪ ብቻም አይደለም፤ የውኃ ፈጣሪ እንጂ፡፡
☦️ውኃን ፈጥሮለሦስት የከፈለ ውኃዎችን በእፍኙ የሰፈረ፤ የባሕር ውኃዎች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈሳቸው፤ የባሕርን ጥልቀትና ደርቻ የወሰነ፤ የኤርትራን ባሕር እንደ ግድግዳ ያቆማ አምላክ"ተጠማሁ" ብሎ ጮኸ፡፡
☦️ውኃን በደመና ውስጥ አስሮ፤ዝናምን አውርዶ ምድርን የሚያረካት አምላክ በውኃ ጥም ተቃጥሎ"ተጠማሁ" ብሎ ጮኸ፤
☦️እግዜር "የእግዜር ውኃ አጥቶ ጮኸ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ ብሎ የጮኸው ሕይወት ውኃ ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ግን ተጠማሁ ብሎ ጮኸ፡፡
☦️ራሱ ውኃ ሆኖ ሳለም ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል በውኃ ጥም ተሰቃየ፡፡
☦️ጌታችን ተጠማሁ ብሎ ሲጠይቅ የመጀመሪያው አይደለም ሳምራዊቷ ሴት ውኃ እድትሰጠው በጠቃት ጊዜ "አንተ አይሁዳዊ ሰትሆን ሣምራዊ ከምሆን ከእኔ እንዴት ውኃ ትለምናለህ ብላው ነበር፡፡
☦️ከዚያም በመሲሕነቱ አስካመነችበት እሰከመጨረረሻው ቅጽበት ድረስ እንዲጠጣ ውኃ ቀድታ አልሰጠችውም፡፡ እንዳመነችም ትታው ሔደች እንጂ ውኃን አላቀረበችለትም፡፡
☦️እግዚአብሔር የሚጠማው ውኃን ሳይሆን የሰው ልጅ በንስሓ የሚያነባውን ዕንባ ነው፡፡
☦️ለሳምራዊትዋ ሴት "ውኃ አጠጪኝ ሲላትም የተጠማው ውኃን ሳይሆን የእርስዋን ነፍስ ነበር፡፡ እርሰዋ ግን የተጠማው ምን እንደሆነ ሳታውቅ ስለ ዘር ልዩነት ለመከራከር ተነሣች፡፡
☦️ጌታችን ከውኃ ጥም በላይ ሕመም ሆነ ደሚሰማው የሰዎ ልጅ መጥፋት ሲሆኖ ከውኃ በላይ ጥሙን የሚቆርጥለት የሰው ልጅ በንሓ ወደ አርሱ መመለስ ነውና፡፡
☦️(ከ "ሕማማት" መጽሐፍ የተወሰደ
☦️እኛም ንሰሃ ገብን የጌታን የውሃ ጥመቱን እንጠጣው ዘንድ የእሱ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡ አሜን።፡🤲
ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ገው ይህ ርክበ ካህናት ነው፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በዋዜማው ሁሉም ጳጳሳት ከየሀገረ ስብከታቸው በመንበረ ፓትርያርኩ በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው የመሐረነ አብ ጸሎት ይደርሳል በነጋታው ጕባኤው ይካሄዳል፡፡
በእነዚህ ዕለታት ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያደርገው ጕባኤ የሚተላለፉ መመሪያዎችና የሚጸድቁ ውሳኔዎች ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት፣ ለምእመናን አንድነት፣ ለአገር ሰላምና ደኅንነት የሚጠቅሙ ይሆኑ ዘንድ ሁላችንም በጾም በጸሎት እግዚአብሔርን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ አምላካችን ቤተ ክርስቲያናችንንና አባቶቻችንን ይጠብቅልን፤ እኛንም ለአባቶች የሚታዘዝ ልቡና፣ ሓላፊነታችንን የምንወጣበትን ጥበብና ማስተዋሉን ያድለን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ይህንን ታላቅ ጕባኤ ይባርክ ይመራ፤ እኛንም ይጎብኘን፡፡
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦፦ "ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ። ወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ። በእንተ ዳዊት ገብርከ"። መዝ 131፥9-10 የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 5፥1-ፍ.ም፣ 3ኛ ዮሐ 1፥8-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 15፥22-37። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ወይም የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዐል ሰሞንና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
#ግንቦት ልደታ
#ክፍል_፫
#የእመቤታችን_የልደት_በዓል_አከባበር
💠አባታችን አዳም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ንስሃ በገባ ጊዜ አምላካችን ጌታ እግዚአብሔር የድህነት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡
💠ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚል ነበር፡፡
💠ስለሆነም አዳም 5500 ዘመን የሕይወት ምክንያት የሆነች የልጅ ልጁ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአብራኩ ከተከፈሉ ቅዱሳን ልጆቹ የምትወለድበትን ቀን ተስፋ እያደረገ ኖረ፡፡
💠የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የመወለዷን ዜና ተስፋ በማድረግ “ሴት” ይላት የነበረውን ሚስቱን ሔዋንን በእመቤታችን ምሳሌነት “ሔዋን”፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ብሎ ሰየማት፡፡ (ዘፍ. 3፡20)
💠ዳግማዊ አዳም የተባለ ክርስቶስም የአዳምን ተስፋ በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ እውነተኛዋን ሔዋን (ዳግሚት፣ አማናዊት ሔዋንን) ድንግል ማርያምን በዮሐንስ ወንጌላዊ በኩል ለሕያዋን ምዕመናን ሁሉ እናት አድርጎ ሰጠ፡፡ (ዮሐ. 19፡26)
💠ይህን የከበረ ምስጢር የማይረዳ “ክርስቲያን” እንዴት ያሳዝናል!? እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን የቀዳማዊ አባታችንን የአዳምን፣ እንዲሁም በዳግም ተፈጥሮ ያከበረንን ዳግማዊ አዳም የተባለ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ተቀብለን “የሕያዋን ሁሉ እናት” ድንግል ማርያምን ልደቷን በፍፁም ደስታ እናከብራለን፣ ከተወደደ ልጇ ምሕረትን ትለምንልን ዘንድም ወደ እርሷ እናንጋጥጣለን፡፡
💠በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለን ምዕመናን ከጌታችን ልደት ቀጥሎ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የልደት በዓል የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ነው፡፡
💠 ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል (ሉቃ 1፡14)›› ከተባለ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን?!
💠👉የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት፣
👉የታየው ራዕይም በገሀድ የተከናወነበት፣
👉 የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ (ለሕያዋን ሁሉ) ታላቅ የደስታ ቀን ነው፡፡
💠 ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም በንጽህናዋ በቅድስናዋ ተደንቀው “እህትነ ነያ/እህታችን እነኋት” ብለው ያመሰግኗታል፡፡
#በዘመናችን ያሉ የሰዎች ልደት በድምቀት የሚከበር ከሆነ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባው ይሆን?!
#ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ከዚህ ታላቅ በዓል በረከት ረድኤትን እንድናገኝበት ነው፡፡ የሕይወት ክርስቶስ እናት ዛሬ ተወልዳለችና፡፡
❤በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ #በአድባረ ሊባኖስ ስር ❤እመቤታችንን ወለዱ፡፡
❤ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ #ንፍሮና_ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ #በዓሉ_ከቤት_ዉጭ_ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡
በረከቶ ይደርብን
#ለሃሳብ_አስተያየት
@DnIsraelYeArsemaLije
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
#ግንቦት #ልደታ
ክፍል ፩
❤በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡
❤ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡
💠 ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች (ኢሳ 7፡14)›› ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡
💠ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ‹‹ የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች (መዝ 44፡9)›› ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡
💠ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት (ራዕ 12፡1)›› ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡
💠የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡
ይቀጥላል
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 2
#ክፍል 4
#ባልና_ሚስት_ተነጣጥሰው_ቢቆርቡስ?
«ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነይ /ዮሐ 1-16/
👉ይህንን የጌታችንን ቃል አስተውላችሁት ታውቃላችሁ?
👉ውሃ ለመቅዳት የመጣችው ሳምራዊቷ ሴት «ጌታ ሆይ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውሃ ስጠኝ ባለች ጊዜ «ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ነይ ብሎ መለሰላት፡፡ በዚህ ቃል መሠረትነት ነው ቤተ ክርስቲያን ባልና ሚስት ተነጣጥለው
መቁረብ የለባቸውም የምትለው::
👉ለዚህ ጥያቄ በቂ መልስ ለማግኘት ለአንባብያን ተጨባጭ ማስረጃ ለማቅረብ በጋብቻ ዙሪያ የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል መመልከት ኣስፈላጊ ሆኖ አግንቼዋለሁ፡፡
« ..ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው አለም
ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም እግ
ዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው»
/ማቴ 19:4-6/
👉በዚህ አምላካዊ ቃል መሰረት ባልና ሚስት አንድ ሥጋ ናቸው::
👉ጋብቻ ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ልጆች ከተሰጡ ታላላቅ ስጦታዎችና በረከቶች አንዱና የመጀመሪያው ነው::
👉ገና መጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ ከምድር አፈር አዳምን አበጅቶ በአፍንጫው የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ህያው ካደረገው በኋላ ስለ አዳም አስቦ ያለው እንዲህ ነበር።
👉«አዳም ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም የምትረዳውን እንፍጠርለት» /ዘፍ 2፥18/ በዚህ መሰረት ከአዳም አጥንት ነስቶ ሔዋንን ፈጠረለት አዳምም ከአካሉ የተፈጠረችውን ሴት ተመልክቶ እንዲህ አለ፣
«ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት
እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል» /ዘፍ. 2:23-25/
👉ደግሞም ጋብቻ በረከት ሆኖ ለሰው ልጆች እንደተሰጠ እንዲህ ተፅፏል «እግዚአብሔር እምላክ ሰውን በመልኩ ፈጠረ ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው፡፡
👉ከዚያም እንዲህ ብሎ ባረካቸው «ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ግዙአትም የባሕርን
ዓሶችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው» /ዘፍ 1: 26-31/
👉መድኃኒተዓለም ኢየሱስ ክረስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ በዚህች ዓለም ወንጌለ መንግስቱን በሚሰብክበት ጊዜ ጋብቻ እጅግ የተቀደሰ ባልና ሚስትም አንድ ሥጋ መሆናቸውን አስተምሯል እንዲህ ብሎ፣
🤚«እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው .
/ማቴ. 19:6/
👉አምላካዊ ቃሉ እንዲህ እያለ ኣንድ ሥጋ በሆኑ ባልና
ሚስት መካከል ተነጣጠሉ መቁረብ ለምን ታስቦ?
👉ለመቁረብ እንቢ በሚለው ሰው ውስጥ ያለው ምክንያት ምንድን ነው የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እንድናነሳ ያደርገናል በቅድሚያ አልቆርብም ባዩ ሰው በኃጢአት የመኖር እቅድ እንዳለውና የሚያስጠይቀውም መሆኑ ግልጽ ሲሆን በቃሉ መሠረት ግን ተነጣጥሎ መቁረብ ተገቢ አይደለም የቤተ ክርስቲያን ህግና
ሥርዓትም አይፈቅደውም ምክንያቱም አንዱ ሲቆርብ ሌላው ሲቀር አንድ ሥጋ ተለያየ ማለት ነው::
👉ሌላው በቅዱስ ቁርባን የአንዱ ሕይወት የተቀደሰ ከቅዱስ ቁርባን የራቀው የአንዱ ሕይወት ያልተቀደሰ በመሆኑ በግንኙነት ጊዜ የተቀደሰው ሕይወት ይረክሳል ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ እንዲህ አለ፤ ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና» /1ቆሮ 6፥15-16
👉ይሁንና ሁለቱም በመስማማት በመምህረ ንስሐቸው ምክር በመመራት አንዴ ከቆረቡ በኋላ ቆራቢ ከሆኑ በኋላ ግን በተለያየ ምክንያት ለምሳሌ በሥራ ጉዳይ በመራራቅ፣ ሴቷ ሚስቲቱ
ሥርዓተ አንስት ላይ በመሆን በወር አበባዋ
ጊዜ ፣ ወልዳ በምትታረስበት ጊዜ ወንዱ/አንዱ መቁረብ ቢፈልግ ቢቆርብ እንደመለያየት የሚቆጠር ኣይደለም ምክንያቱም ሁለቱም ቆራቢዎች ናቸው ይህ የመነጣጠል ጉዳይ ሳይሆን በቀን ልዩነት
የመቀበል ሁኔታ ነው ነገር ግን በተቀበሉ ቀን አብሮ መተኛት የተከለከለ ሲሆን ከዚያም በኋላ በልዩ ምክንያት ሳይቀበል የቀረው
ሁኔታዎች ሲስተካከሉ ተዘጋጅቶ በመቀበል ሊቀጥሉ ይችላሉ በተረፈ እንዲህ አይነት ምክንያቶች ካላጋጠሙ በስተቀር የመጀመሪያ ቀን በአንድነት በአንድ ቀን እንደተቀበሉ ሁል ጊዜ በአንድ
ቀን መቀበላቸው ለፈተና ከመጋለጥ ይጠብቃቸዋል:: /1ቆሮ 7:5/
#ምዕራፍ 2
ክፍል 5
❖ያላገባ_ወጣት1መቁረብ_ይችላል ??
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት
/channel/dnhayilemikael/4951
ቻየሉን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ከሰማያዊው ማዕድ የማትሳተፉት ለምንድን ነው?
🥀💠ተወዳጆች ሆይ! ትዘምራላችሁ፡፡ 💠[ከጸሎታቱ ትሳተፋላችሁ፡፡ ቅዳሴውን አስቀድሳችሁ] እምነታችሁን ትመሰክራላችሁ፡፡
💠 ይህን ኹሉ አድርጋችሁ ስታበቁ ግን አትቆርቡም፡፡ ለምን? ከሰማያዊው ማዕድ የማትሳተፉት ለምንድን ነው?
💠 አንዳንዶቻችሁ፡- “እኔ ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ ልቆርብ አይገባኝም” ብላችኋል፡፡ እንዴ! እንደዚህ’ማ ካላችሁ ከመዝሙሩም፣ ከጸሎታቱም፣ ከቅዳሴውም ልትሳተፉ አይገባችሁማ!
💠እስኪ ንገሩኝ! የንጉሥ ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ መላእክት “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” እያሉ የሚያመሰግኑት የሚያገለግሉትም ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ ንጉሡ በፊታችሁ አለ፡፡
💠ታዲያ እናንተ እንዲሁ ቁልጭልጭ እያላችሁ ትቆማላችሁን? ልብሳችሁ አድፎ ተዳድፎም ሳለ ምንም እንዳልተፈጠረ ኾናችሁ ወደ ቤታችሁ ትመለሳላችሁን?
💠ወደ መንግሥተ ሰማያት፣ ወደ ሰማያዊው ንጉሥ ማዕድ ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠርቶን ሳለ ተዘጋጅተን እንደ መቅረብ ወደ ኋላ እንላለንን? 💠እንደዚህ የምናደርግ ከኾነ ታዲያ ተስፋ ድኅነታችን ምንድን ነው?
💠መቅረብ ያልቻልኩት’ኮ” ብለን ደካማ መኾናችንን እንደ ሰበብ ማቅረብ አንችልም፡፡ ተፈጥሮአችንን እንደ ምክንያት ማቅረብ አንችልም፡፡
💠እንዳንቀርብ የሚያደርገን ደካማ መኾናችን አይደለም፡፡ አዎን ከሰማያዊው ማዕድ እንዳንሳተፍ የሚያደርገን እንዲሁ ሳንዘጋጅ ልል ዘሊላን ኾነን መቅረባችን እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት አይደለም፡፡
💠ስለዚህ እማልዳችኋለሁ! [ንስሐ ገብተን እንደ ቸርነቱም ተዘጋጅተን] በፍርሐትና በረዓድ ኾነን [በግድ] እንቅረብ እንጂ “ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ” ብለን አንራቅ፡፡
💠 [ከኃጢአት ኹሉ የሚያነጻን የክርስቶስ ደም እንጂ ኃጢአተኛ ነኝና አይገባኝም ብለን መራቃችን አይደለምና፡፡] ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ በድፍረት ወደ እርሱ መቅረብ ይቻለን ዘንድ ዛሬ በፍርሐትና በረዓድ ኾነን ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡ ያኔ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” ከሚላቸው ጋር ዕድል ፈንታችን ፅዋ ተርታችን በመንግሥተ ሰማያት ይኾን ዘንድ ዛሬ ወደ ሰማያዊው ማዕድ እንቅረብ፡፡
(በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)
#ይቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael
❖❖❖❖ መስቀሉን እሸከማለሁ የሚል የመድኃኔ ዓለም ወዳጅ ?????????????????????????
አንተ ሰው እስኪ ልጠይቅህ? :ጌታ የተሰቀለ ዕለት ዕርጥብ መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ ሲሄድ ብትኖር ኖሮ ታግዘው ነበርን ? ወይስ አብረህ ትገፋው ነበር ? ወይስ በርቀት ሆነህ ይገባዋል እያልክ ትደነፋ ነበር ? ወይስ አላውቀውም ብለህ ትክድ ነበር ? ወይስ ጥለኸው ትጠፋ ነበር ? ወይስ በልብህ አምነህ አብረህ ከጠላቶቹ ጋር ታመዋለህ ? ወይስ ራቅ ብለህ ትከተለው ይሆን ? እስኪ ዛሬ የደመራ ነጭ ልብስህን እንደለበስህ ይህንን አስብና ምን እንደምታደርግ እርግጡን ለልብህና ለራሱ ለመድኀኔዓለም ንገረው !
አይ ጌታዬ ተሸክሞ እየደከመማ አግዘዋለሁ እንጅ አልክደውም ትለኝ ይሆናል ። እኔም እንዲህ እልሃለሁ ።
አንተ ሰው ! አሕዛብ ቤቱን በማቃጠል ፥ ልጆቹን በማረድ እያሳደዱት በአንተ ዘንድ በልጅነት ያድር ዘንድ በመጣ ጊዜ ሰውነትህን በዝሙትና በበደል አርክሰህ በንስሐ ሳትታጠብ ከቆየኸው ማደሪያ እየነሣኸው አይደለምን ? አብረህ እየገፋኸው አይደለምን ? እርሱ ስለአንተ ርጥብ መስቀል ተሸክሞ አንተ የወንድም እኅቶችህን አመል የማትታገሥ ከሆነ ምኑን መስቀሉን አገዝኸው ? እርሱ ለጠላቶቹ መስቀል ከተሸከመ የእኅት ወንድሞቻችን ሸክም የማንሸከም እኛ ምን እዳ ይጠብቀን ይሆን ? ወዳጄ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ሲል የተሸከመውን መስቀል አግዘዋለሁ ካልክ አንተ ለምን ለሚስትህ ብለህ ድካሟን አትሸከምም ? እጠቀም የማይል ጌታ የአይሁድን መስቀል ከተሸከመ መንግሥተ ሰማያት ትወርስ ዘንድ ለምን መከራ አትቀበልም ?
ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ! አንዳንዶቻችን በልብ አምነን በአፍ ዝም ያልን ነን ! አንዳንዶቻችን ገብቶንም ሳይገባንም መስቀሉን ከሚገፉ ጋር ተባባሪዎች ነን ! አንዳንዶቻችን ራቅ ብለን እሰይ ይበላቸው እያልን በአባቶቻችን ውርደት የምንሳለቅ ነን ! አንዳንዷቻችን ደግሞ ቀርቦ ከመቃጠል ራቅ ብሎ መጠቅለል እያልን ከባድ ነገር መስማትን የማንወድ ሲነሣ ንገሩኝ አይነት ሰዎች ነን ! አንዳንዶቻችን እንደ ቀንድ አውጣ ደስታ ሲሆን ብቅ መከራ ሲመጣ በኑሯችን ሸማ ጥልቅ የምንል ነን ! አንዳንዶቻችን ጭራሽ ምን እየሆነ እያለ እንኳ የማይገባን አመት በዓል ሲመጣ ለምግብ ብቻ አለሁ ባዮች ጥለን የጠፋን የበረከተ ኅብስትና የድግሥ ክርስቲያኖች እንጅ ቀራንዮ ላይ የለንም ! የመጥፋታችን ምልክቱማ የመስቀል ዕለት መዝፈናችን
አይደል !
መስቀሉን እሸከማለሁ የሚል የመድኃኔ ዓለም ወዳጅ ?????????????????????????
መልስ ፦ እኔ አለሁ የመድኃኔዓለም ወዳጅ ኃይል ባገኝ የቤተክርስቲያናችን ፈተናዎች ለማሳለፍ እተጋለሁ ። ባይቻለኝ ግን የራሴን ፦
1. የራሴን ሥጋዊ የፍትወት መከራ መስቀል እሸከማለሁ እንጅ የፈቃዴ ባርያ አልሆንም ።
2. ዘወትር የዕለት ዳዊትና ውዳሴ ማርያም በመጸለይ ያለ ማቋረጥ አምላኬን እመገባለሁ ።
3. በሠራኋቸው በደሎች ከነገ ጀምሮ ለንስሐ አባቴ እናዘዛለሁ ።
4. ጌታዬ በመስቀል የተሰቀለው ለእኔ ምግብ ሆኖ ሊፈተት ፥ መጠጥ ሆኖ ሊቀዳ ነውና ለእኔ ሲል መሞቱን ቅዱሥ ሥጋውን በመቀበል እመሠክራለሁ ።
5. ምንም ቢሆን ጌታዬ እኔን ፍለጋ ከሰማይ ወደ ምድር ወርዷልና እኔም እርሱን ፍለጋ ቤተክርስቲያን ኪዳን ሳላስደርስ አልውልም ።
6. እርሱ የእኔን ደዌ በመስቀል እንደተሸከመ እኔም የባልንጀራዬን ድካም ታግሼ ማንንም ሆነ ማንን ይቅር እላለሁ ።
8. በመከራዬም ሆነ በደስታየ ከመስቀሉ ሥር እገኛለሁ እንጅ ራበኝ ብየም አልጠፋም ጠገብሁ ብየም አልርቅም !
9. ቢቻለኝ የቤተክርስቲያንን ችግር እፈታለሁ መስቀሉን እሸከማለሁ እንጅ አባቶችን አልተችም ከገፊዎች ጋር አልቆምም ።
10. ጊዜየን በማይረባና ርብሐ ቢስ በሆነ አላባክንም ፤ በየጊዜው ና በየሰዓቱ ስለቤተክርስቲያን ባልናገር እንኳ ቢያን ጆሮየ ለቤተክርስቲያን የተከፈተ አደርጋለሁ ።
11. ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት ሀሰጠኝ ጌታ ከጠፊ ገንዘቤ ከአሥር አንዱን በታማኝነት አወጣለሁ ።
12. ለተጠራሁበት የጸጋ ሥጦታ እታመናለሁ ። ድንግል የሆነ ለድንግልና ፣ ባለትዳር እንደሁ ለትዳር ፥ ዲያቆን እንደሁ ለዲቁና ፤ መነኩሴ እንደሁ ለምንኩስና ፣ ጳጳስ እንደሁ ለጵጵስና ፥ ሊቀ ጳጳስ እንደሁ ለሊቀጵጵስና ፥ ለመታመን በቆመበት ቁርጥ ሕሊና የሚከፈትበትን ሁለንተናዊ የአጋንንት ጦርነት የሚታገሥ እርሱ ጌታን በቀራንዮ ያገዘው የቀራንዮ ሰው ነው ! ወዳጄ ሆይ ባለህባት የመንፈሳዊነት ደረጃ የምትገጥምህ መሰናክል ያቺ ለአንተ መስቀልህ ። ከመልካምነትህ ያልተናወጽህ እንደሆነ በእውነት ግርማ አይሁድን ታግሠህ ከክርስቶስ ጋር የቆምክ የመስቀሉ ሰው ነህ !
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
@dnhayilemikael
ላልሳችሁ ልትወድቁ ወይም እስከ ዛሬ ያያችሁት ምስል ሀሳባችሁ ላይ እየመጣ ልትጨነቁ ትችላላችሁ። ይሄ ማለት ከዚህ ህይወት አልተላቀቃችሁም ማለት አይደለም። ቡና ለረጅም ጊዜ ጠዋት መጠጣት የለመደ ሰው እንደሚያዛጋው ማለት ነው እንጂ! አዕምሮአችን ወደ ቀደመው ቦታ እስኪመለስ ከማንኛውም ሱስ ስንወጣ የምናልፍበት ጤናማ ሂደት ነው።
ዋናው በጦርነቱ ተሸንፎ እጅ አለመስጠት ነው። ፀንታችሁ ከታገላችሁና የሚፈልገውን እስከነሳችሁት ድረስ ሱሱ በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል። ከመገባችሁት ግን ያድግና ይውጣችኋል።
7. #ስሜቶቻችሁን_ተቆጣጣሩ
🥀ፖርኖግራፊ ማየት ሶስት ደረጃዎች አሉት። እነሱም ስሜት /Emotion/፣ ሐሳብ/Thought/ እና ተግባር/Action/ ናቸው።
🥀ስሜት የምንለው የመጀመሪያው ደረጃ ጭንቀት፣ መከፋት ወይንም ፖርኖግራፊ
የማየት ፍላጎት ሊሆን ይችላል። ይህን ተከትሎ ነው ፖርኖግራፊ የማየት ሐሳብ የሚመጣው።
🥀መጨረሻ ላይ ሁሉም ወደ ተግባር ይቀየራል። ስለዚህ ራሳችሁን መቆጣጠር የምትችሉት በሃሳብ ደረጃ ሳለ ሳይሆን ገና ስሜት ሲሰማችሁ ነው።
🥀አንዲት እህቴ ‘እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማኝ ከቤት ወጥቼ መዝሙር እየሰማሁ የእግር ጉዞ ማድረግ እጀምራለሁ፤ ይህም በጣም ጠቅሞኛል’ ስትል ልምዷን አጋርታኛለች። አንድ ወንድሜ ደግሞ እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማው ስፖርት እንደሚሰራ አጫውቶኛል።
🥀ይህ ስሜት ሲሰማችሁ ምን ብታደርጉ ጥሩ ነው የምትሉትን 3 ነገሮችን ጻፉና የሚስማማችሁን ነገር አድርጉ።
8. #ብቸኝነትን_አስወግዱ
ለረጅም ሰአት ብቻችሁን ላለመሆንና ጊዜያችሁን ከቤተሰብና ከወዳጆቻችሁ ጋር ለማሳለፍ ሞክሩ። በተቻለ መጠን ቀናችሁን በተሻለና ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ነገር ላይ አውሉት።
🥀ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ እንደ ስፖርት መስራት መጽሐፍትን ማንበብ ያሉ ልምዶችን አዳብሩ። እስኪ ከዛሬ ጀምሮ ልታዳብሩት የምትችሉት 5 ልምምዶችን ፃፉ።
9. #ተስፋ_አትቁረጡ
ከዚህ ህይወት ለመውጣት በምታደርጉት ጥረት ውስጥ መውደቅና መነሳት ሊያጋጥማችሁ ይችላል። ተስፋ ሳትቆርጡ ከስህተታችሁ ተምራችሁ እንደ አዲስ በብሩህ ተስፋ ነገን አሻግራችሁ ተመልክቱ።
10. #ግልጽ_ሁኑ
🥀ይሄን ጽሁፍ ሳዘጋጅ እስከዛሬ ድረስ በዚህ ሱስ የተጠቁና ያማከርኳቸውን ሰዎች ከዚህ ሱስ እንድትወጡ ያስቻላችሁን ነገር ግለፁልኝ ስል ጠይቄ ነበር። በሁሉም ውስጥ ያገኘሁት 2 ሀሳብ ነው።
🥀አንደኛው የእግዚአብሔር እርዳታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በችግሩ ላይ በግልጽነት ማውራቴ የሚል ነበር። ብዙ ሰው በጉዳዩ ላይ ማውራት ስለሚያሳፍረው እርዳታም ለማግኘት ይቸገራል።
🥀ከዚህ ህይወት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት ከፈለጋችሁ ሊረዳችሁ ለሚችል ለአንድ ሰው በግልጽ ችግራችሁን መናገር ይኖርባችኋል። በመናገራችሁ ብቻ፤ ሚስጥር ያደረጋችሁትን ነገር ወደ ብርሃን በማውጣታችሁ ይህ ኃጢያት በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል።
🥀ስትደክሙ የሚያማክራችሁ፤ መቆማችሁን ሁሌ የሚከታተል አንድ ሰው ማድረጋችሁ ፀንታችሁ እንድትቆሙ ብርታት ይሰጣችኋል። ይህንን ምክር ሰጥቼው የተቀበለ አንድ ወንድም ችግሩን ለጓደኛው አካፈለው። መጥፎ ስሜት ሲሰማው ይደውልና 'እባክህን እየተቸገርኩ ስለሆነ ጸልይልኝ' ይለዋል።
ልታማክሯቸው የምትችሉ ሶስት ሰዎችን ጻፉና በማስተዋል እና በፀሎት ታግዛችሁ አንዱን ምረጡ።
ፅሁፌን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ልደምድም።
“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ”። ማቴ 11:28
በተረፈ በፆም በፆሎት በስግደት መበርታትን ነው🥰
ተፈጸመ!
=======//////////////==========
ቴሌግራም ተቀላቀሉ ተዋህዶ
@dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael
ለሁ›› ያልሽው ንግግርሽ እንዴት ያለ ጸሎት ነው? ይኼንን እንኳን ለእኛም ጭምር አጥብቀሽ ጠይቂልን፡፡ ከልባችን መቃብር ውስጥ ጌታችንን ካጣነው ቆይተናል፡፡ ክቡር ሥጋውን ተቀብለን በውስጣችን ከያዝን ከሦስት ቀንም በላይ ብዙ ዘመን አልፎናል፡፡ ነገር ግን እርሱ እንደተለየን እየተሰማን ፣ ባዶነት እያስጨነቀን ነው፡፡ ከጲላጦስ ማኅተም የበለጠ የመስቀል ማዕተብ የታተመበት ሰውነታችን የጌታን ሥጋ ተቀብሎ ቢይዝም አሁን ግን ባዶነት እየተሰማን ፣ እርሱም ከእኛ እንደተለየን እየመሰለን ነው፡፡ በመቃብሩ ጠባቂዎች በካህናት ማሳበብ ፣ ‹እነርሱ ስላንቀላፉ ነው ጌታ ከእኛ ተወስዶ ባዶ ሆነን የቀረነው› ማለት ጲላጦስን እንኳን ማሳመን ያልቻለ ተራ ምክንያት ነውና ልናቀርበው አንደፍርም፡፡ ብቻ ባዶነት ሲበዛብን ‹አዳም ወዴት ነህ› ያለውን አትክልተኛ ጌታ ከሰውነታችን ጫካ ውስጥ ገብተን ‹‹ጌታ ሆይ ወዴት ነህ› እያልነው ነውና እባክሽን ጠይቂልን፡፡ እርሱ ወስዶብን ከሆነም ይንገረን፡፡ እንደ ዳዊት ‹መንፈስህን አትውሰድብኝ› እያልነው ጨክኖብን ከሆነም ይንገረን፡፡
ያኖረበትን የነገረሽ እንደሆን ግን እኛም እንዳንቺ እንድንወስደው ወደ ልባችን እንድናስገባው ንገሪን፡፡ ከዚያ በኋላ አውቀነው ‹ረቡኒ› (መምህር ሆይ) እንለዋለን፡፡ አትንኩኝ ቢለንም አናዝንም ‹‹ጌታ ሆይ አንተው በእጆችን ዳስሰን እንጂ አንዳስስህም ፣ ባዶነት ላስጨነቀው ውስጣችን ያለህበትን ንገረን እንጂ በረከሱ እጆቻችን ልንነካህ አንደፍርም፡፡ አንተን ዳስሶ እንደቶማስ ተቃጥሎ ከመጮኽ በአንተ ተዳስሶ መንጻትን እንመርጣለን›› ብለውሃል በይልን፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
@dnhayilemikael
#ቅዱስ_ቁርባን
(ምዕራፍ አንድ ክፍል 1 ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 /channel/dnhayilemikael/4939
#ምዕራፍ 1 #ክፍል 2
#ሰው_ግን_ራሱን_ይፈትን
ሐዋርያው ይህን ኃይል ቃል የተናገረበትን ቁም ነገር
ስንመረምር ፈታኝና ኋለኛ ሕይወታችንን አጢነን የምናስተካክልበት በሁለት ክፍል የምንመለከተው ጉዳይ እንዳለ ያመለክተናል
እነርሱም፣
👉ሀ. #ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል እስከተነሣንበት ጊዜ ድረስ ያለውን
ሕይወትትንን እንዴት እንዳሳለፍን
👉ለ/ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያደረግነው ዝግጅት ምን እንደሚመስልና ስለተቀበልነው ምስጢር ያለንን እውቀት እንድንመረምር የሚያደርገን ነጥብና ስለ ሕይወታችን ትኩረት እንድንሰጥ የሚያደርግ ኃያል ቃል ነው::
.
ሀ. የመጀመሪያውን ነጥብ ስንመለከት ወደ እግዚአብሔ እስከተጠራንበት ለቅዱስ ቁርባን ዝግጅት እስከጀመርንበት ድረስ ሕይወታችንን እንዴት እንዳሳለፍነው ልንመረምር ይገባል
የሐዋርያውም ቃል «በሃይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ>> [2ቆሮ. 13 : 5/ ነው የሚለው ምክንያቱም ቀድሞ የተበላሸ ያልተስተካከለ፣ እግዚአብሔር የማይፈቅደውና ያዘነበት ሕይወት
ሊኖረን ይችላል::
🙏ስለዚህ በዚህ ደረጃ የምናደርገው አትኩሮት ይህ ሕይወት እግዚአብሔር እንደሚወደው፣ እንደሚፈቅደው ሆኖ ሊስተካከል
እንደሚችል ትምህርት የምንወስድበትና በወሰድነው ትምህርት ራሳችንን ልናስተካክልበት ነው::
🙏በሌላ መልኩ ሕይወታችንን በማስተካከልና ንስሐ በመግባት የተውናቸው የራቅናቸው ክፉ ሥራዎች ምን ያሕል ከሕይወታችን እንደራቁና በፊታችን እንደተጠሉ በፈተና መልክ ወደ ፊት በሚቀርብልንና በሚያጋጥሙን ጊዜ ምን ያህል የመቋቋሙ ብቃት
እንዳለንና የዚህ ብቃት ምስጢሩ ዓለምን ያሸነፈውንና ሁሉን ሊያስችለን የሚችለውን አምላክ ምን ያሕል በፍጹም እምነት እንደተከተልነው ልናረጋግጥ ይገበናል ምክንያቱም ያለ እርሱ አንዳች ማድረግ እንዳይቻለን ተጽፏልና:: <<ያለ እኔ ምንም
ልታደርጉ አትችሉም» /ዮሐ15: 5.
👉ለ/ሁለተኛው ደረጃ ቁርባን ለመቀበል ያደረግነውን
ዝግጅት የምንፈተንበት ክፍል ነው ምክንያቱም ያደረግነው ዝግጅት ቅዱስ ቁርባንን ለምንቀበልበት በሰዓት ለተወሰነ ጊዜ ከኛ ጋር የሚቆይ ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ቁርባን ለተቀደሰውና ለተወሰነው ሕይወታችን ዋስትናነት ያለውን እስከ ሕይወታችን ፍፃሜ ድረስ ልንጸናበት የሚገባ ነው ክርስቶስ ከዓለም መርጦ
እርሱን እንዲከተሉት ያደረጋቸውን ደቀ መዛሙርቱን እርሱን በመቀበላቸው ወደ ፊት በዓለሙ ውስጥ ከሚደርስባቸው መከራ መንገድ ላይ እንዳይቀሩ
ሲያስጠነቅቃቸው«እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል፡፡ » /ማቴ. 24:13/ ብሏቸዋል::
ብዙ ሰዎች ለጊዜው በግብታዊነት ተነሣስተው ይህንን ኃጢአት ደግሜ አላደርገውም ስላሉ ብቻ በቂ ዝግጅት አድርገው ይወስዱታል ወይም በዚያን ወቅት ኃይል የሆናቸው ከራሳቸው ጉልበት ከመነጨ ብርታት የወሰኑት ውሳኔ ዘላቂ ይመስላቸውና ወደ ቅዱስ ቁርባን የሚያደርጉትን ግስጋሴ «ይበል በለው »
ያደርጉታል ነገር ግን ወደ ጠባብ ደጅ ከተገባ በኋላና ለጊዜው የታገሰው ጦር መልኩን ቀይሮ ሲመጣ በቀላሉ መዛልና አልፎም ውድቀት ይከተላል ይህ ሁሉ ሊመጣ የሚችለው ቃሉን ስለማናሰተውል ነው ቃሉን ደግሞ የማናስተውለው ቃሉን
ስለማንሰማ ሊሆን ይችላል ጌታችንም ለአይሁድ
«ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ
ነው» /ዮሐ. 8፥43/ ብሏቸዋል::
#ምዕራፍ 2
ቅዱስ ቁርባን ለማን
ይቀጥላል .........
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#ቅዱስ_ቁርባን
👉 #ማሳሰቢያ_ላትጨርሱ_አትጀምሩ
#ምዕራፍ_አንድ
#ቅዱስ_ቁርባን_ስለ_ፈሰጉ_ብቻ_የሚገቡበት_ሕይወት_ይደሰም
#መግብያ
«ሰው ግን እራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ
ከጽዋውም ይጠጣ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ
ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ይጠጣልምና /1ቆሮ 1: 27/
በዚህ ርዕሳችን በሰፊው የምንመለከተው ተያይዞ የተጠቀሰውን የሐዋርያውን መልዕት ተንተርሰን ሲሆን በዚህ ሥር ከ2 ያላነሱ ነጥቦችን ጨምረን እንመለከታለን፡፡
ማንኛውም አማኝ ስለፈለገ ብቻ ተንደርድሮ የሚገባበት ሕይወት ሳይሆን ቅዱስ ቁርባን አስቀድሞ ወደ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት ሲገባ የሚከተለውን ነገር ጠንቅቆ ማወቅና ወድዶና ፈቅዶ ስለ ቅዱስ ቁርባን የሚደርስበትን መከራና ፈተና ለመቀበል መወሰንና መዘጋጀት ይኖርበታል. ለዚህም ደግሞ ወሳኙ ምክረ
ካህን ነው።
#ምዕራፍ_አንድ
#ክፍል 1
: 🙏 #ምክረ_ካህን🙏
ምክረ ካህን ማለት አማኙ በኃጢአቱ ከተናዘዘ በኋላ ቀኖና መስጠት ማለት ብቻ ሳይሆን ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ሆኖ #ቅዱስ_ቁርባን ለመቀበል ጥያቄ ላቀረበው ወይም ለተዘጋጀው አማኝ
ከካህኑ ጥልቅ ምክርና የተብራራ ምሪት ሊሰጠው ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ የእርሱ በመሆናቸው የሚገጥማቸውን አስቀድሞ
እንዲያስተውሉ አድርጎ እንዳዘጋጃቸው ካህኑም አማኙን ሊያዘጋጀው ይገባል፡፡
👉ምክረ ካህን ማለት በአጠቃላይ መልኩ አማኙን ከመቁረቡ በፊትና ከመቁረቡ በኋላ ያለውን ሕይወት ሁሉ ያጠቃልላል እንጂ ኃጢአትን መናዘዝ የመስዋዕቱን መለወጥ እንዲያምን ማስተማር
ብቻ ማለታችን አይደለም፡፡ አብነት እንዲሆን ከዚህ በታችእንደጠቀስነው ሊሆን ይገባል።
👉አንድ አማኝ ወደ ቅዱስ ቁርባን ከቀረበ በኋላ ስለሚጠብቀውና ስለሚመራው ሕይወት ካህኑ በዝርዝር ይግለጽለት።
👉ክርስቶስን መከተል ማለት ወደዚህ ሕይወት መግባት ማለት ባለቤቱ እንደተናገረው መስቀሉን መሸከም ማለት ስለመሆነ ይግለጽለት፡፡
🙏ምን አልባትም አማኙ በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ ሲኖር በዓለሙ ዘንድ የተጠላና የተተቸ ሊሆን ይችላል:: ይህን ነገር ክርስቶስ እንዲህ በማለት ተናግሮታል፡- « ስለእኔ በዓለም ውስጥ
የተጠላችሁ ትሆናላችሁ» /ዮሐ 15 -23/ ምክንያቱም የዓለምን ሥራ ስለምናልክስበትና ስለ ምንንቅበት አለም ሊጠላን ሊተቸን ምክንያት ሊፈልግብን ይችላል ሁሉም የሚወደው ወገን ወገኑን
ነውና
👉 ደቀመዛሙርቱ እርሱን በመከተላቸው ዓለም የአበባ ምንጣፍ አንጥፎ አዘጋጅቶ አይደለም የተቀበላቸው ለአንገታቸው ሰይፍ ለሰውነታቸው እሳት እንጂ /ማቴ. 24÷9/
ስለዚህ አንተም መሰል መከራዎች በደረሰብህ ጊዜ የተቀበልከውን ታውቀዋለህና ስለ እርሱ ራስህን ክደሃልና ስለሥሙና ስለ ቅዱስ ቁርባን በሚደርስብህ ደስ ሊልህ ይገባል ምርጫህ ሕይወት
በመሆኑ ሰይጣን መሸነፉንና ባንተ መቅናቱን እወቅ ስለዚህ ካህኑ ይህንና መሰል ጉዳዮችን ሊያሳውቀው ይገባል እንዲህ እያለ ልጄ በርታ አይዞህ ዓለም ቢጠላህ አትደነቅ ደግሞም የገዛ ሃሳብህ ዕር ይሆንብሃል ይህንን አይነቱን ፈተና በዚህ በዚህ መልክ ተቋቁመው ቢገጥምህ እንዲህ ተወጣ የሰዎች ባንተ አይደነቅህ ምክንያቱም ሰይጣን አንተን ለመፈተን ሊጠቀምባቸው ይችላል የሰይጣንን የውጊያ ባህርያት እወቅ ሊለው ይገባል፡፡
👉በሌላ መንገድ ሰይጣን እራስህን በማይገባ ክስ እንድትከስና በጀመርከው ሕይወት እንዳትገፋበት በአሉባልታዎች ሊያውክህትም ይችላል፡፡ አንተ ግን ስለተቀበልከው በቂ ዝግጅትና እውቀት ካለህ
መልስ ትሰጥበታለህ:: «በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ» /1ጴጥ. 3፥15/
👉ይሔውም «አንተ ቆርበህ እንዲህ ትሆናለህ» «ይህ ሰው ከቆረበ ጀምሮ አቅበዘበዘው» «መቁረብ በማይገባት ጊዜ ቆርባ አደብ አጣች» የመሳሰሉትን ይህ አይነት አሉባልታ ሌሎችን በአንተ ላይ
አነሳስቶ የመክሰስ የዲያቢሎስ ውጊያ ነገ ደግሞ ራስህን በራስህ ላይ አነሳስቶ ለመክሰስ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት መሆኑን ልብ
በልና ለአሉባልታ ሳትገዛና እነርሱ ባሉህ /ባሙህ/ ነገር ሳትገኝ ተገቢውን መልስ በትህትና መስጠት ይገባል:: 👉ይኸውም እኔ የተቀበልኩት ሰላም ነሺውን ሳይሆን ፣ አደብ የሚያሳጣውን፣ ሳይሆን የሚያቅበዘብዘውን ሳይሆን፣ #የሰላሙን_አምላክና ሕይወትን
#የሚቀድሰውን_ጌታ ነው ኢሳ 9:6/ በማለት ደግሞ::
👉አንተ ወገኔ የምትናገረውንና እንዲህ የምትተቸውን
ታውቃለህ ሰላም ነሺ አቅበዝባዥ፣ የምትለውን ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስ ለዓለም ሰላም የሰጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው
እኮ ልክ እንደ አይሁድ ሕዝቡን ሰላም ነሳ ብለው ለቄሳር እንደከሰሱት በማለት ምስጢሩ ያልገባውን ወገንህን ማስተማርና
ሰይጣንን ማሳፈር ይገባሀል።
#ምዕራፍ_አንድ
* #ክፍል 2
#ሰው_ግን_ራሱን_ይፈትን
ይቀጥላል ......
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉@dnhayilemikael 👈
👉@dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ፖርኖግራፊ
ክፍል 4
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፖርኖግራፊ ምን ይላል?
🥀በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሩካቤ ብዙ የተፃፉ ክፍሎች ቢኖሩትም ስለፖርኖግራፊ ይህ ነው ተብሎ በግልፅ የተፃፈ ነገር አናገኝም። ሆኖም ግን ክርስትና በአካል ከሚደረጉ ሃጢያቶች ከመራቅ ባለፈ የአይምሮ ንፅህናን የመጠበቅ ጉዳይ እንደሆነ ያትትልናል።
🥀በዘፀአት 20 :17 ላይ “የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ” ሲል ሆነ፤ ክርስቶስ በማቴዎስ 5:27-29 “ሴትን በምኞት አይን የተመለከተ ሁሉ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሯል’’ ሲል፤ እንዲሁም በተለያዩ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች የስጋ ምኞት ‘ነፍስንም የሚወጋ’ ኃጢት (1ጴጥ 2:11) ተብሎ ሲጠቀስ እነዚህን ክፍሎች ከፖርኖግራፊ ጋር አያይዘን ልንማርባቸው እንችላለን።
🥀የስጋም ምኞት ኃጢያትን እንደምትወልድ ፤ ኃጢያትም ሞትን እንደሚወልድ ይናገራል። (ያቆ 1:14-15) የፖርኖግራፊ ዋና ግብ የስጋን ምኞት መፍጠር ሲሆን ያም ሀጢያትን ይወልዳል፤ ኃጢያት ደግሞ ሞትን! ፖርኖግራፊ በክፉ የጠላት ሃሳብ የተመረዘ የሰው የሃሳብ ውጤት ነው።
🥀ጠላት ዲያቢሎስ ሁሌም ቢሆን ለጦርነት የሚጠቀመው መሳሪያ ሀሳብን ነው። ጥንት ሔዋንና አዳምን ከገነት ያስኮበለላቸውም የተመረዘ ሐሳብ ነው።
🥀“እባብም ለሴቲቱ አላት፦ ሞትን አትሞቱም፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ ” (ዘፍ3:4:5) ዲያብሎስ አሁንም እየተዋጋን እና እየጣለን ያለው ሄዋንን በጣለበት መሣሪያ ይህም በተመረዘ ሃሳብ ነው።
🥀አሁን ላለንበት ዘመን ደግሞ በኢንተርኔት ፣ በዘፈን፣ በፊልም፣ በመጽሐፍ፣ በጌም በመሳሰሉት ይህን ሀሳብ እያቀበለን ነው። ወዳጄ መምሕር ነቢዩ ተስፋ እንዳለው “በዚህ ዘመን የሰይጣን ተቀዳሚ አላማ ኃጢያትን ተደራሽ ማድረግ ነው”።
መጽሐፍ ቅዱስ አዕምሮአችንን በላይ ባሉ ነገሮች ላይ እንድናደርግ ያዘናል። (ቆላ 3:2) በስጋ ስላለው ነገር ከማሰብ ይልቅ መንፈሳዊውን ነገር እንድናስብም ያሳስበናል። (ሮሜ 8:8) ፖርኖግራፊን የሚመለከት ሰው አይምሮውን በስጋ ምኞት ላይ እንጂ በእግዚአብሔር ሀሳብ ላይ ሊያደርግ አይችልም።
🥀የአንድ ክርስቲያን ግብ መሆን ያለበት በአዕምሮ መታደስ መለወጥ ነው። (ሮሜ 12:2)
የክርስቲያን ሰውነት የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ቤተመቅደስ እንደመሆኑ ማናቸውንም በስጋ የሚደረግ ኃጢያት ማስወገድ ይኖርበታል። (1ቆሮ 5:9-11፤ ገላ 5:19-21፤ ኤፌ 5:1-5፤ ቆላ 3:5- 6 ፤ ዕብ 12:15- 17) ስለዚህ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደምናየው በፖርኖግራፊ ሱስ የተያዘ ሰው በንስሃ እስካልተመለሰ ከእግዚአብሄር እንደተለየና የእግዚአብሄርንም ርስት እንደማይወርስ ማየት እንችላለን።
ክፍል 4
#ከፖርኖግራፊ_ሱስ_እንዴት_መውጣት_ይቻላል? ይቀጥላል ......
/channel/dnhayilemikael
ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት?
እናት ብቻ ብሌን እንዳንጠራት ድንግል ሆና አገኘናት !
ድንግል ብቻ ብሌን እንዳንጠራት ልጅ ታቅፋ አየናት !
ጌታ ሆይ እናትህን መጥራት እንድህ የሚያስቸግር ከሆነ
አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራለን ?
ቅዱስ ኤፍሬም
/channel/dnhayilemikael