#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
አንዳንድ ሰዎች እጅግ የጠለቀ ኀዘንና መቆርቆር ውስጥ ሲገቡ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ረስቶኛል” ብለው ሲያማርሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ነቢዩ እንዲህ ከሚሉ ሰዎች ጋር ክርክር አለው፡፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀኗ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃኗን ትረሳ ትችላለችን?” በማለትም ይጠይቃቸዋል (ኢሳ.49፡14)፡፡ ይህም ማለት ሴቷ ከማኅፀኗ የተወለደው ልጇን ልትረሳ ዘንድ እንደማይቻላት እግዚአብሔርም ሰውን ይረሳ ዘንድ ባሕርይ አይደለም እያላቸው ነው፡፡
ነቢዩ ይህን ምሳሌና ማነጻጸርያ አንሥቶ ክርክር መግጠም የፈለገው እያንዳንዷ እናት ለልጇ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኾኖም ይህን ያህል የምናንቆለጳጵሰው የእናት ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው “አዎን እርሷ ትረሳ ይኾናል፤ እኔ ግን አልረሳሽም… ይላል እግዚአብሔር” በማለት የሚቀጥለው፡፡ እንግዲህ የአምላካችን ፍቅር እንደምን የበዛ እንደ ኾነ ታስተውላላችሁን?
እንግዲያውስ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አባት ለልጆቹ እንዲያዝን እንዲራራ እንደዚህም ኹሉ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይራራለቸዋል” ብሎ እንደተናገረ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ትቶኛል” የሚል ማንም አይገኝ (መዝ.102፡13)፡፡ ጆሮን የፈጠረ እርሱ ይሰማል፤ ዐይንን የፈጠረ እርሱ ያያል፡፡ እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ የቀረጻቸው ልጆቹን አይረሳም፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
/channel/dnhayilemikael
🥀እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ወርሃዊ በአል አደረሳቹሁ
💠ቅዱስ እስጢፋኖስ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በህዝብ ድንጋይ እየተደበደበ ሳለ ለጸሎት ተንበረከከ።
💠ይህ ሁኔታ እንኳን ለመንበርከክ በስርዓት ለመሞትም ፋታ አይሰጠም ነበር።
💠ግን ጌታው ፊት ምን ያህን በአክብሮት መጸለይ እንዳለበት እየሞተም አልረሳም።
🥀በአስቸጋሪ ሁኔታም ውስጥ እምላኩን በአክብሮት አከበረ።
💠እኛ እየኖርን ምን ያህል ለክብሩ የሚገባ ስግደት እንሰጣለን?
💠ስንቶቻችን ለጸሎት ከመቀመጫችን እንነሳለን? በሰላም የምኖነረው እኛ ለጌታ ሰዓት አጥሮን ምክንያት መደርደራችንን እስጢፋኖስ ቢሰማ ምን ይል ይሆን?
💠እርሱ አምኖ ሲሞት አምኖ መኖር ምን ያህል እንደሚያስፈልገን ተረዳችሁ? እግዚአብሔርን ከወደድነው መቸም ቢሆን ለርሱ ጊዜ አለን።
💠ለአምልኮ ጊዜ ያጣነው ሰዓት ስላጣን ሳይሆን ለርሱ ፍቅር ስላጣን ነው። ይህን ማንም እንዳይረሳ።
💠ተሰብስበን ወደማይቀረው ዓለም መጠራታችን አይቀርም። ወደ ዘላለሙ ስፍራ መድረሳችን አይቀርም። ስለዚህ ቀን ሳለ ጌታችንን ማክበር ወደ ፍለጋው መመልከት እንጀምር።
💠 ማንም የማይሰራበት ሌሊት ይመጣልና።
💠የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በረከቱ እረድኤቱ ይደርብን /አይለየን አሜን
ተቀላቀሉ ቴሌግራም ቻናል
/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንዲህ አሉ፦
💠ማንም ቢሰድብህ ስለ መሰደብህ ሳይሆን ስለ ሰደበህ ሰው አስብ።
💠 ያ ሰው ወንድምህ ነው። በፍቅር የተሞላህ መንፈሳዊ ሰው እንደመሆንህ መጠን አንተን በመስደብ ኃጢአት ላደረገው ወንድምህ ምን ልታደርግለት እንደምትችል ታስብ ዘንድ ይገባሃል።
💠በእርግጥ አንተን የተሳደበበት ስድብ በድኅነቱ መግቢያ ላይ ቆሞ ይከለክለውና በዚሁ ሳቢያ ውድ ነፍሱ ወደ ሲዖል ትወርድ ዘንድ አትሻም።
💠በመሆኑም ያንን ኃጢአት ቆጥሮ እንዳይቀጣው ይልቁንም ይቅር እንዲለው እግዚአብሔርን ትጠይቅለታለህ ከዚህ በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ካለው ኃጢአት እንዲያወጣውና ዳግመኛ አንተን ሆነ ሌሎችን በመስደብ እንዳይበድል ልትጸልይለት ይገባል።
@dnhayilemikael
ወር በገባ በ11 በወርሐዊ በዓላቸው ታስበው ለሚውሉት አቡነ ሐራ ድንግል መድኃኔዓለም ክረስቶስ የሰጣቸው ቃልኪዳን፤-
“በእጅህ የተባረከውን፤ ለተራቡና ለተጠሙ እህልና ውኃን በመስጠት በዓልህን ያከበረውን ሰው ሁሉ ኃጢአተኛና በደለኛ ሆኖ ሳለ በጸሎትህና በቃልኪዳንህ የታመነውን፤ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈውንና ያጻፈውን፤ ያነበበውንና
የተረጎመውን፤ የሰማውንና ያሰማውን፤ አጽምህንም እየጠበቀ በገዳምህ የተቀመጠውን አንተንም ሰለወደደ ከሩቅም ከቅርብም መጥቶ ገዳምህን የተሳለመውን ወንድ ልጁንና ሴት ልጁንም በስምህ የጠራውን እነዚህን ሁሉ በየወገናቸው ከሥጋና ከነፍስ አገዛዝ ነጻ የወጡ ይሁኑ ዘንድ እስከ ሰባተ ትውልድ ምሬልሃለሁ፡፡”
የአቡነ ሐራ ድንግል ረድኤት በረከት አይለየን በጸሎታቸው ይማረን።
ምንጭ ከገድላት አንደበት
@dnhayilemikael
"አለሙም ምኞቱም ያልፋል"
ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ፤ ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።
ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ፤ ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም፤ በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ፤ መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም።
ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን፤ ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ።
ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው።
"ዓለም ሳትንቅህ በፊት ናቃት!!!"
እንዳትጎዳ አዘንኩላቸው፡፡ ስለዚህም ሰረቅኋቸው፡፡ የሰረቅሁት ፈልጌው አይደለምና ውኃው ውስጥ ወረወርሁት፡፡
በማግሥቱ የደብሩ ዘበኛ ሊታጠብ ወደ ውኃው ይመጣል፡፡ በውኃው ውስጥም ያገኘዋል፡፡ የላቲን ቋንቋ ስለሚያውቅ የተጻፈውን ያነበዋል፡፡ ወስዶም ለካህኑ ይሠጠዋል፡፡ ፃህሉ ከብሮ ድጋሚ ሲቀደስበት የሞቱትም ያርፋሉ የቆሙትም ከጥፋት ይድናሉ፡፡ ’ አላቸው፡፡
አባ ተደነቁ ፤ ‘እሺ ሕፃኑንስ የገደልከው ለመልካም ብለህ ነው?’
‘አባ የእግዚአብሔርን ፍርድ አይመዝኑ ፤ ሕፃኑ የተፀነሰው በኃጢአት ነው ፤ ለወደፊት ደግሞ እጅግ ጨካኝ ወንጀለኛ ሆኖ ወላጆቹን የሚገድል ብዙዎችን የሚያሰቃይ ነው፡፡ ስለዚህ ልጁን በመግደሌ ሦስት መልካም ነገሮች አደረግሁ፡፡ ሕፃኑ ከንጽሕናው ጋር ወደ ሰማይ እንዲሔድ አደረግሁት ፤ ወላጆቹንም በልጃቸው እጅ ከመሞት አዳንኋቸው፡፡በዚህ ልጅ ኀዘን ምክንያት ወላጆቹም ልባቸው በመሰበሩ የቀደመ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል’
‘እሺ መጠጥ ቤቱ ደጃፍ ላይ የሰገድከው ምን ሆነህ ነው?’
‘ሦስት ሰዎች በዚያ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው የፈረሰውን የከተማችንን ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንሥራ እያሉ እየተጨነቁ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ምንም እንኳን የተሰበሰቡበት ቦታ መጥፎ ቢሆንም በልባቸው ያለው ሃሳብ ቅን ስለሆነ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ወድቄ ሰግጄ ለመንሁት’’
‘ታዲያ ወደ ፈረሰው ቤተ መቅደስ ድንጋይ ለምን ወረወርህ?’
‘በፈረሰው መቅደስ ላይ እየተሳለቁ አጋንንት ሲጨፍሩ አየሁ፡፡ በመስቀል ምልክት አማትቤ ድንጋይ ወረወርሁ ፤ በዚህም ምክንያት አጋንንቱ በንነው ሸሹ’ አለ መነኩሴው፡፡
አባ ቀጠሉ ‘የእነዛን የሙት ልጅ የሆኑ ሕፃናት ቤትስ ለምን አቃጠልከው?’
‘’እነዚያ ሕፃናት እንደሚያውቁት ወላጆቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ የቀራቸው ንብረትም ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ቅድመ አያታቸው የቀብሩት እጅግ ብዙ ሀብት ግን ከዚያ ቤት በታች አለ፡፡ ከቃጠሎው በኋላ በቀረው ክፍል ለማደር ልጆቹ ሲገቡ የተቀበረውን ሀብት ያዩታል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት ለሚያገለግል አጎታቸውም ሔደው ይነግሩታል፡፡ በረሃብ መሞታቸው ቀርቶ በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ’’ አለ መነኩሴው፡፡
አባ ምንም እንኳን ነገሩ ቢያስደንቃቸውም አንድ ወጣት መነኩሴ ይህንን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አደረባቸውና ‘አንተ ማን ነህ?’ አሉት፡፡
‘የእኔ ማንነት ይቆይና እርስዎ በዚህ ሰሞን መላልሰው ፈጣሪን የጠየቁት ነገር ካለ ይንገሩኝ’ አላቸው
‘እኔማ እግዚአብሔር ሆይ ፍርድህን አሳየኝ ብዬ በምድር ላይ ስለሚደረጉ ኢፍትሐዊ ነገሮች ጠይቄው ነበር’ አሉት፡፡
‘እግዚአብሔር ‘ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ መንገዴ ከመንገዳችሁ ሃሳቤም ከሃሳባችሁ የራቀ ነው’ ብሏልና ፍርዱ አይመረመርም፡፡ ለመላእክት እንኳን ያልተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዴት እርስዎ በሰው አቅም ሊመረምሩ ይፈልጋሉ፡፡ ጸሎትዎን ሰምቶ እግዚአብሔር ያዩትን ሁሉ እንዳደርግና ፍርዱን እንዳሳይዎት ላከኝ’’ አላቸው፡፡
ቅዱስ ዑርኤል ለዕዝራ እንዲህ አለው፦
‘የምትፈርስ የምበሰብስ አንተ የማይፈርስ የማይበሰብስ የሕያው እግዚአብሔርን ፍርዱን ልትመረምር አትችልም’
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 24/ 2012 ዓ ም
/How God Judges People – The patristic heritage book 2 – /Elder Cleopa/ ከሚለው የዜና አበው መጽሐፍ የተተረጎመ/
ማስታወሻ ፦ ይህንን ታሪክ ትንሽ የሚመስለው ታሪክ በ1747 የተጻፈው የቮልቴር ዛዲግ ላይ አንብቤ የታሪኩ ሞራል ደስ ቢለኝም የዞራስትራኒዝም ነበርና ለቤተ ክርስቲያን አይሆንም ብዬ ነበር፡፡ ለካንስ ይህ ታሪክ አስቀድሞ በመነኮሳት ታሪክ የተመዘገበ ነበርና በዚህ መልኩ ከአራተኛውና አምስተኛው ክፍለ ዘመን ወርቃማ የምንኩስና ታሪኮች በአንዱ ተመዝግቦ አገኘሁት፡፡ ባየነውና በምናየው ሁሉ እንዳሻን የእግዚአብሔርን ፍርድ በምንደመድምና በምናብራራበት በዚህ የደፋር ዘመን እንዲህ ያሉ ታሪኮች ልጉዋም ቢሆኑ በሚል ተርጉሜዋለሁ/
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም Like እና Share
ይህም ምእመናንን እያወከ ያለ አጭበርባሪ ድርጅት ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናን በእነዚህ የከሓድያን ድርጅት ምክንያት እንዳይነጠቁ። ድርጅቱን አውግዞ መለየት አለባት። ባለማወቅ ከዚህ ድርጅት የገቡትንም ጠንቅቆ አስተምሮ ወደ ቤተክርስቲያን ቢመልሳቸው መልካም ነው።
።
ንቀን ዝም ያልናቸው ችግሮች ወደፊት ታላላቅ መከራ ውስጥ ይከቱናል። አጭባርባሪ ባሕታውያን ነን ባዮችን፣ አጥማቂ ነን ባይ ሌቦችን ዝም ማለት ተገቢ አይደለም። የሊቃውንት ጉባኤውም እነዚህ አካላት ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እያዘጋጀ ምእመናንን ከወጥመድ ቢያድን መልካም ነው።
።
ባለማወቅ ተታላችሁ የዚህ አባል የሆናችሁ ምእመናን ራሳችሁን ከሲኦል አድኑ። ይህ ክፉ ሥራ ወደሲኦል የሚሸኝ ነውና። ነፍሳችሁ እንዳትጎዳ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ተመለሱ።
መ/ር በትረ ማርያም
/channel/dnhayilemikael
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 4
#ከቅዱስ_ቁርባን_የሚያርቁ_ስለ_እምነት_ምንነት_አለመረዳት_እምነት_ምንድነው ???
#ክፍል 2
#እምነት ብርሃን ነው
✔️✔️ተአማኒው ሰው እግዚአብሔርን ካለማወቅ ጨለማ የሚወጣ በት እምነት ብርሃን ነው::
✔️ ስለዚህ ተአማኒው ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚደረስበት መንገድ እምነት ሲሆን እምነቱ ደግሞ
የብርሃን ሕይወት ስለሆነ እምነት ብርሃን ነው::
✔️ ከላይ እንደገለፅነው ተአማኒው እምነቱን የጣለበት እምነቱን የመሠረተበት እግዚአብሔር ብርሃን ነው:: [መዝ 26 : 1/
✔️አባታችን ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ላይ «ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኩሉ ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም» በማለት ይህን ይመሰክራል
ትርጓሜውም አማናዊ ብርሃን ጠፈር የማይከለክለው የሌሊት ጨለማ የማይሽፍነው በዓለም ላሉት ሁሉ የሚያበራ ማለት ነው::
✔️ሐዋርያው በመልእክቱ እንዲህ ጽፏል «ከእርሱ የሰማናት ለእናንተ የምናወራላችሁ መልእክት እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት 1ዮሐ 1:5
✔️ወደዚህዘለዓለማዊ ብርሃን የሚጓዙበትና የሚደርሱበት ከእርሱም ጋር ሕብረት የሚያደርጉበት የሰው ልጅ የአእምሮ ብርሃን እምነቱ ነው
✔️ጨለማ በማያሸንፈው «ብርሃን ዘዘልፈ ያበርህ» ዘወትር የሚያበራ በተባለው አምላክ በመድኃኒት ዓለም በኢየሱስ ክርስቶስ ማመኑ::
✔️ዮሐንስ በመልእክቱ «ኅብረት አለን ብለን በጨለማ
ብንመላለስ እንዋሻለን፡፡ እውነትም አናደርግም ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት ኣለን» /ዮሐ 1፥6/ በማለት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ቅዱስ ቁርባን/ በሰጠን በሕይወት ብርሃን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል
አምነን ብርሃን ለብሰን ብርሃን ተጎናፅፈን ከወሉደ ብርሃን ጻድቃን ጋር በእግዚአብሔር ቀኝ ለመቆም እንድንተጋ ያስጠነቅቀናል::
✔እንግዲህ እምነት ከብርሃናዊ አምላክ ጋር ኅብረት
የምናደርግበት እንደሆነ በወንጌል ተረጋግጦልናል::
✔️በእምነት ሕይወት የሚመላለሱ ሰዎች በብርሃን የሚመላለሱ ሰዎች ናቸው::
✔️የእግዚአብሔርን ሕልውና በእምነት የተረዱና ያወቁ በርሱም የተገኙትን ምሥጢራት ለመቀበል የሚተጉ የእግዚአብሔር ብርሃንነት የተገለጠላቸው ናቸው።
መዝሙረኛው<<አቤቱ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ>>መዝ 4:6 ይላል።
✔️«እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው >>መዝ 27÷1 ያለው የራሳቸው የሆነውን ነገር ትተው በስብከት ሞኝነት ማማ እግዚአብሔርን በእምነት የሚከተሉት አማኞች እግዚአብሔር የሕይወት ብርሃን እንደሆነ እምነታቸው የብርን እንደሆነ የተረዱ ናቸው::
✔️በእርሱ የሚታመኑ በእምነት የሚገሰግሱ ፈጽሞ
ወደማይደርስበት ዓለም ለመግባት በዓለም ብርሀን
ክርስቶስ አምላክነት አምነው ቅዱስ ቁርባን የተቀበሉ
ሊመሰክር ዮሐንስ ተላከ ሲመሰክርም<< ለሰው ሁሉ የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ>> ብሎ መሰከረ ይኸም ብርሀን በልቦናችን ውስጥ የሚያበራ ነው።
✔️2ጴጥ.1÷19 ስለዚህ የዓለም ብርሃን በእምነት ለሚከተሉት ብርሃን ይሆንላቸዋል እርሱንም የሚከተሉበት ብቸኛው መንገድ እምነት ነው::
✔️ዮሐንስ በወንጌል የጻፈው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ይህን ያረጋግጣል
«ደግሞም ኢየሱስ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለሱምን ተናገራቸው /ዮሐ 8፥12/
✔️በእምነት ብርሃን የሕይወት ብርሃን የሆነውን አምላክ የተመለከቱ ባለማመን ጨለማ የማይመሳለሁ
እውነተኛ ምእመናን ናቸው::
✔️በመዝሙር «በብርሃንህ ብርሃን እናያለን» መዝ. 36 : 9 እንደተባለ ሕዝቡን ከባርነት በሙሴ እና
ነጻ ያደረገው የእስራኤል አምላክ በጉዞ ላይ የነበረውን የእስራኤልን ሕዝብ ሌሊት በብርሃን ይመራቸው ነበር በእርሱ የሚታመኑት ጨለማ እያሽንፋቸውምና በብርሃን ያመላልሳቸዋል በብርሃን የሚመላለሱ ብቻ ሳይሆኑ መድኃኒታችን ክርስቶስ እንደተናገረው ለሌሎች የሚያበሩ ብርሃኖች ናቸው ።
✔️እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ» /ማቴ 5 : 14/ ብርሃንነታቸውም እርሱን ከማመንና በእምነት ብርሃንነት በመመላለሳቸው ወይም
በሃይማኖት ጸሎት ላይ የተደነገገውን የሃይማኖት
መግለጫ ከማወቃቸው ብቻ የመነጨ ሳይሆን ሐዋርያው እንደተናገረው ከእርሱ ከብርሃናት አባት ስለተወለዱ ጭምር ነው
«ከብርሃናት አባት ይወለዳሉ» (ያዕ. 1 : 17/
✔️በተጨማሪም ቅዱስ
ዮሐንስ «እነርሱ ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም ዮሐ 1 ፥ 13/ ይላል፡፡
✔️እነዚህ በትክክል የእግዚአብሔር ጥሪ የደረሳቸውና
ወደ ዓለም በላከው ልጁ አንቀጸ ብርሃን ከተባለች ከእመቤታችን ድንግል ማርያም በተወለደው አማናዊ ብርሃን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት ያለ መጠራጠር የሚያምኑ ቅዱስ ጴጥሮስ
እንደፃፈው ወደ ሚያስደንቅ ብርሃን የተጠሩ ናቸው: 1ጴጥ.2፡9/
✔️ይህም እምነት ደግሞ የዘላለም ሕይወት የሚያስገኘውን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ ለመብላት ክቡር ደሙን ለመጠጣት ዝግጁ ያደርጋቸዋል።
✔️ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ለያዕቆብ ቤት ያቀረበው ጥሪ በእግዚአብሔር ብርሃንነት እንመላለስ የሚል ነው:: «እናንተ የያዕቆብ ቤት ኑ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ>> ኢሳ 2:5
✔️ነቢያት የሕይወት ብርሃን የኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ዓለም መምጣት ይጠባበቁ እንደነበረ ያረጋግጥልናል ልበ አምላክ ዳዊት
«ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቅከ /ብርሃንህንና እውነትህን ላክ መዝ. 42:3/ በማለት በትንቢቱ ተማጽኗል።
✔️በትንቢት መጽሐፍ ስለፅዮን «ብርሃንሽ መጥቷልና የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ ኣብሪ» ኢሳ 60:1
✔️ይህ ቃል አማናዊቷን ፅዮን የፀሐየ ጽድቅ
የኢየሱስ ክርስቶስን መገኛ እመቤታችን ድንግል ማርያምን የሚመለከት ነው:: በተጨማሪም የሰው የሕይወት ብርሃን እግዚአብሔር እንደሆነ ምእመናንም ከእርሱ የተነሣ የሚያበሩ የብርሃን ልጆች መሆናቸውን
ያረጋግጥልናል።
✔️ጨለማ የሚያሽንፈው አሕዛብን ነው::
👉✔️️ በእምነት ብርሃን የማይመላለሱ ስለሆኑ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል:
✔️ እነሆ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አህዛብን ይሽፍናል ኢሳ 60: 2
✔️በዚህ ጽሑፍ መግለጽ የፈለግነው እግዚአብሔር ብርሃን ነው አማኞቹም የክብሩ ብርሃን የሚገለጽባቸው ብርሃናት ናችሁ
ስለዚህም የእግዚአብሔር ነቢይ በትንቢቱ <<ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም የጨረቃም ብርሃን በሌሊት
አያበራልሽም እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናል ኢሳ 60:19/ እንግዲህ ወደዚህ የዘላለም ብርም የሚደርስበት
የሕይወት መንገድ ምን ሊባል ይችላል ጥበብ እንጂ።
ምዕራፍ 4
ክፍል 3
(1) እምነት ጥበብ ነው
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት
/channel/dnhayilemikael/4982
ሰንበት ተማሪነት!
......
ከላይም ከታችም ልትሰደብ ትችላለህ ... መሳሳት በፍጹም አይፈቀድልህም ... ምናልባት ከታናሽ እህትህ ጋር ሊሆን ይችላል ከጉባኤ አምሽተህ ወደቤት እየገባህ ያለኸው ... ነገር ግን የሚያየው ሁሉ ሰው ስም ያወጣልሃል ... ባለጌዎች ናቸው ልትባል ትችላለህ ፡፡፡ ሕጉን ስርአቱን የሚያውቀውም ... ዛሬ ቤተክርስቲያን የመጣውም ሊቆጣህ ሊያዝህ ይችላል፡፡፡ አንተ ግን ምንም አትልም ... በፍጹም ትህትና አገልግሎትህን ታገለግላለህ ... ምክንያቱም አንተ ሰንበት ተማሪ ነህ!! ሰንበት ተማሪ!
.........
የጥምቀት ዕለት ጸሐይ ከልጅ ልጇ ጋር ልትወርድብህ ትችላለች ... ውሃ ጠምቶ ጠምቶ ሊያምርህ፡፡፡ በዚህም በዚያም በስራ የተወጠሩ ወጣቶች እየገፈተሩህ ምንጣፍ ይዘው ሊያነጥፉ ይችላሉ .... በዚህም መሀል መዝሙር ክፍሉ መጥቶ ሊጮህብህ ይችላል ፡፡፡ በስርዓት ዘምር! ድምጽህ አይሰማም ይልሃል .... አንተ ግን አስፓልቱን ሙሉ እየዘለልክ የዘመርኸው ውልብ ይልብህና እምባ ባይንህ ግጥም ይላል፡፡፡፡ ግን ምንም ማለት አይጠበቅብህም ... ለምንስ ታኮርፍና ... ምክንያቱም አንተ ሰንበት ተማሪ ነህና !
........
የሆነ ችግር ሊፈጠር ይችላል ... ከተማ ይበጠበጣል ... አንተ አጣናህን ይዘህ ቤተክርስቲያን ትውላለህ ታድራለህ ... በለስ ከቀናህ ትፈነከታለህ፣ ትታሰራለህ ... የግንባር ስጋ ነህ ቤተክርስቲያን ላይ የሚወረወሩ ድንጋዮች በቀጥታ አንተን ነው የሚያገኙት ... ምክንያቱም አንተ ሰን.....
..........
ወረብ ጥናት ፣ መዝሙር ጥናት ፣ ኮርስ ፣ አዳር መርሐ ግብር ... የገጠር አገልግሎት እያልክ መሄድ ነው ፡፡፡ በዚ መሀል ትምህርትህ ይከዳሃል ፤ ውጤት አይጠጋህም ፤ በትምህርትህ ላይ ትኩረት አድርግ ተብለህ ከማዘርህ ጋር ዱላ ቀረሽ ግብ ግብ ትለማመዳለህ ፤ አባትህ ማውራት አለብን ይልሃል፡፡፡ በዚ ሁሉ መሀል የእናንተ ደብር ንግስ ይመጣል ... ክላስ መሄድ አይታሰብም ፤ በማግስቱ እግርስ ሰንበት ትምህርት ቤት እንዳይደርስ የሚል እገዳ ይወጣብሃል ፤ በማግስቱ ማግስት ግን ነጠላህን በአጥር ወርውረህ ሰንበት ትምህርት ቤት ትገኛለህ!!
ምክንያቱን ከላይ ነግሬሃለሁ፡፡፡
.......
ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ አንዱ አባል እንኳን አንተ እሱም በውሉ በማያውቀው ምክንያት ይጠላሃል፡፡ ጓደኞቹ ይደረባሉ ... ሕይወት ሊያስጠላህ ይችላል ፤ ከበሮም ላይሰጡህ ይችላሉ ... ፊትም ልትነሳ ትችላህ፤ ደግነቱ አንዱ እሁድ ለት ባለው መርሐ ግብር የታጣላ ሰው አለ ብሎ ይገላግልህንና ሰላምህን ታገኛለህ፡፡፡፡
.......
እንደኔ ደግሞ ዲቁና ከሞካከርክ ... ይሄ ይከተላል ፡፡፡ በመቅደስ አገልግሎት አንድ ቀለም ሳት ካለህ ... ድሮስ ከሰንበት ተማሪ የሚል ጽርፈት ከሽማግሎቹ ቄሶች ትሰማለህ .... ትሸማቀቃለህ ... ቅስምህ ሊሰበርም ይችላል፡፡፡
......
በሁሉም ፈተናዎች ግን ... ጸጥ ብለህ ታገለግለህ ... ደስ ቢልህ .. ደስ ባይልህ .. ተሰሚነት ቢኖሮህ .. ባይኖርህ ... ያላንተ አይደምቅም ቢባልም ... ይሄን ልጅ ባናየው ቢባልም ፥
በዚሁ ሁሉ መሀል አንተ በትጋት፣ በታማኝነት ፣ በንጹህ ልብህ ታገለግላለህ ...
ምክንያቱም አንተ ሰንበት ተማሪ ነህና!!
ምንጭ fb
Kallkidann Genetu
@dnhayilemikael
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዲህ አለ:-
በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት
መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡
የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡
እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ! ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!
ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ
ይሻለኛል? ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳልሆንሁ
በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ
መናገር ያምረኛል፡፡...
ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን ከንፈሮች በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት! ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች’
(የብርሃን እናት ገፅ 352)
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 3
#ክፍል 3
#በ_መቁረብ_ጊዜ
👉ሀ/ ሃሳብን በአንድ ሰብስቦ በፈሪያ እግዚአብሔር ሆኖ መድኃኒት ሥጋ ወነፍስ አድርግልኝ እያሉ ወደ እርሱ በመቅረቤ እድናለሁ ብለው አምነው መቀበል ያስፈልጋል፡፡
👉ለ/ በሚቀበሉበት ጊዜ የሚደርስና የሚጸለየውን ጸሎት በልብ እየደገሙ መቀበል ይገባል። እንደዚሁ በመቀበል ጊዜ
«በሥጋው ላይ አንድ ጊዜ አሜን በደሙ ላይ ሁለት ጊዜ አሜን» እያሉ መቀበል ይገባል፡፡ /ቅዳሴ ሐዋርያት
👉ሐ/ እንደ ቤተክርስቲያን ሥርዓት የወጣውን ተራ ጠብቆ ከሊቃነ ጳጳሳት አንስቶ እስከ ዲያቆናት በማዕረጋቸው ደረጃ ይቀበላሉ ምዕምናንም እንደ ደረጃቸው ይቀበላሉ፡፡
👉መ/ ተቀብሎ ሲያበቁ ጠበል [መካረር መጠጣት ተሐዋስያን ወደ አፍ ገብተው እንዳያውኩ አፍን መሽፈን ይግባል
Iፍት መን13 ክርስጣ 65/
➕➕➕➕ #ሐ_ከቀረቡ_በኋላ➕➕➕➕
👉ከመቁረብ በፊትና በመቁረብ ጊዜ እንደወሰዱት ዓይነት መንፈሳዊ ጥንቃቄ ከቆረቡም በኋላ መወሰድ ተገቢ ነው እነዚህም።
👉ሀ ቆራቢው ሰው በጋብቻ ሥርዓት የሚኖር ከሆነ ከቁርባን በኋላ ሁለት ቀን ከሩካቤ ሥጋ መከልከል ይገባዋል::
👉የቆረበ ሰው ካለመጠንቀቅ ነስር ትዉኪያ የአካል መድማ መቁሰል ወደ አፍ የሚገባ እንደ ትንኝ ዝምብ ቢያጋጥመው ንስሐ ሊሰጠው ስለሚገባ ለንስሐ ንስሐውንም አባቱ መናገር ይኖርበታል ሳይፈጽም እንደገና መቁረብ አይችልም::
👉ሐ/ ከቆረቡ በኋላ በዚያው ዕለት ወደ ፍርድ ቤት መሔድ መመገት ክልክል ነው ጉባኤ ኒቂያ
👉መ/ከቆረቡ በኋላ በቆረቡበት ቀን ከሚስት መገናኘት፣ አብዝ.. መብላት፣ መጠጣት፣ ጥፍርን መቁረጥ፣ ጠጉር መላጨ. መስገድና መንበርከክ ፣ ምራቅን መትፋት፣ በውሀ መታጠብ ከልብስ መራቆት፣ ክልክል ነው:: |ሥርዓተ ቅዳሴ ብ166/
👉ሠ/ ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር ወደሚቃረን ቦታ ከዚህ በኋላ መሐድና ለኃጢአት ከሚያጋልጥ ሁኔታ ጋር መወዳጀት ፈጽሞ ተገቢ አለመሆኑን ማወቅና ክፉውን ሁሉ መቋቋም ተገቢ ነው::
➕ይሁንና በዘልማድ በአባባልና አማኙ በግምት የሚጨምራችውን ነገር ግን ስህተት የሆኑ ነገሮች መኖራቸው የማይካድ ሀቅነው::
👉ለምሳሌ የቆረበ ሰው የቀረበለትን ማስትረፍ የለበትም ጨርሶ መብላት፣ ጨርሶ መጠጣት አለበት እያሉ ማስጨነቅና ሳያውቁት አብዝቶ አይብላ መጥኖ ይብላ የሚለውን ሥርዓትና ትዓዛዝ መጋፋታቸው
👉በተጨማሪ ከሰው አይበላም እርሱ በበላበት
ሌላ አይብላ አይጠጣ የሚሉትና የመሳሰሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
👉ይህን ነጥብ በዚህ እያጠቃለልኩ ለአንባቢያን ለማስገንዘብ የምፈልጋቸው በሥርዓተ ቤተክርስቲያን የታዘዘ ምክንያቶች መቀበል የሚፈቀድላቸውና መቀበል የሚከለከሉትን ቀጥዬ እገልጻለሁ።
👉ሀ/ ቅዳሴ ሲጀመር ያልነበረ ሰው ቅዳሴ ሲጀመር ያልነበረ ካህን እነዚህ ሁለቱ ሥ ጋ ወደመ ሊቀበለ ሊያቀብሉ አልተፈቀደላቸውም፡፡ /ፍት መን 12 በስ 97
👉ለ/ ያላመኑ ሰዎች ሥጋ ወደሙ እንዳይ በሉ መጠበቅና መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡/ፍት መን 23 ረስጠብ 44
👉ሐ በንስሐ ላይ ያለ ሰው የንስሐ ጊዜውን ሳይፈጽም ለሞት የሚያበቃ ደዌ ቢታመም ሥጋ ወደሙ ከመቀበል አይከለከልም፡፡
ሥጋ ወደሙ ተቀብሎ ከዳነም _ከምዕመናን ጋር በጸሎት ይሳተፋል በንስሐ ወደ ተለዩ ሰዎች አይመለስም:: [ፍት መን.
13 ዕንቁ 15/
👉መ/ ካልታመመ በቀር በንስሐ ላይ ያለ ሰው የተቀበለውን ቀኖና ሳይጨርስ መቀበል አይችልም::
👉ሠ/ ጋኔን የሚጥለው ሕመም ያለበት ሰው አረፋ የሚያስደፍቀው የሚያስተፋው ከሆነ ሥጋ ወደሙ ከመቀበል አይከለከልም፡፡
/ፍት. መን 13/
#ምዕራፍ 4
ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቁ ስለ እምነት ምንነት አለመረዳት እምነት ምንድነው ???
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት
ምዕራፍ አንድ ክፍል 1 ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
❖ ዮሴፍ ጭንቀት አልነበረውም ብለህ ታስባለህ❓
❖ ሙሴ ጭንቀት አልነበረውም ብለህ ታስባለህ❓
❖ ዳዊት ሐዋርያት አባቶቻችን ቅዱሳኑ❓
❖ ሰማዕታቱ❓
❖ ትጉሀኑ ❓
❖ ሁሉም ጭንቀት ነበረባቸው፤ በእነርሱና በእኛ መካከል ያለው ልዩነት እኛ ጭንቀታችንን መፍታት የምንፈልገው በራሳችን፤ በገንዘባችን፣ በዘመዳችን፣ በጉልበታችን ወዘተ ...ነው ።
❖ እግዚአብሔር መፍትሔ አለው፤ ስለሆነም ራሳችንን ለእግዚአብሔር ሰጥተን እንዲህ እንላለን "እግዚአብሔር ሆይ ህይወቴን ምራው፤ አንተ በአስቀመጥክልኝ መንገድ መጓዝ እፈልጋለሁ፤ አንተ ለእኔ የተሻለውን መንገድ እንደምትመራኝ አውቃለሁ፤ ስለሆነም በእውነተኛው መንገድ ምራኝ፤ የሕይወቴን አቅጣጫ ወስንልኝ ።
❖ እግዚአብሔር ሕይወታችን ሁሉ መቆጣጠር እንደሚችል ማመን ያስፈልጋል፤ እኛ ውጥረትና ጭንቀት እንደፈለገው የሚያደርገን ግዑዝ ወይም ቁስ ነገር አይደለንም ዕቃ ወስዳችሁ ክብደት ወይም ግፊት ያለውን ነገር ብትከቱበት ይሠበራል፤ እኛ ግን የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆን ውጥረት፤ ጫና ወይም ጭንቀት ውስጥ ስንሆን ብንገላታም አንሰበርም እግዚአብሔር ያወጣናል፤ አንዳንድ ጊዜ ልንፈተን እንችላለን፤ እግዚአብሔር ሰይጣን እንዲፈትነን ሊፈቅድ ይችላል፤ ነገር ግን ብዙ መከራ ወይም ስቃይ እንዲያመጣብን አይፈቅድለትም፤ የእግዚአብሔር እጆች ሁል ጊዜ ይጠብቁናል፤ አይተወንም ችላም አይለንም፤ ጭንቀታችንን ሁሉ ያስወግድልናል፤ መልካም ህይወትን ይሰጠናል፤ ሠላምን ያጎናጽፈናል ዘላለማዊ በሆነ ፍቅሩ፤ ትምህርቱ መስዋዕትነቱ ማረጋገጫ ሰጥቶናል፤ ኃያላን እጆቹም ሁል ጊዜም ይጠብቀናል፤ በዕውነት ይህ እንዲሆን እንደ ቅዱሳኑ በእምነት ከፍ ልንል ያስፈልጋል ።
📌 ምንጭ
✍️ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 3
#ክፍል 2(፪)
#ቅዱስ_ቁርባን_ለመቀበል_የሚያስፈልግ_ግዴታና_ጥንቃቄ
👉አማኙ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የሚያስፈልገው ግዴታ ሕይወተ ሥጋ ወነፍስ አገኝበታለሁ ብሎ እስከ መጣና የሚቀበለው አማናዊውን የክርስቶስን ሥጋና ደም እንደሆነ እስካመነ ድረስ መሥዋዕቱን ሰውታ በማቅረብ ወደ ሕይወት ግብዣ የጠራችውን ቤተክርስቲያን ትዕዛዝ መስማትና የደነገገችውን መንፈሳዊ ሥርዓት መጠበቅና ማክበር ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ የሚያስፈልገው እምነታዊ ግዴታው ነው::
👉 ከምን አለበትን ከግዴለሽነት እንዲርቅ መንፈሳዊ ግዴታውን መወጣቱ የሚቀበለው የክርስቶስ ሥጋና ደም እንደሆነ እንዲለይና ለፍርድ ከመብላትና
ከመጠጣት እንዲድን ያደርገዋል ቅዱስ ጳውሎስ «ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ይጠጣልምና» /1ቆሮ 11 ፥26/ በማለት ይህን ታላቅ
መልዕክት ጽፏል፡፡
👉ሌላው ነጥብ ደግሞ አማኙ ለመቀበል የሚወስደው ጥንቃቄ ሲሆን ይህ ከላይ አፍአዊ ዝግጅት ብለን እየተንደረደርን ያለንበት
ነጥብ ነው።
👉 ይህንን ለመቀበል የሚደረግ ጥንቃቄ ወይም ዝግጅት ከተቀበሉ በኋላ እስካለው ሕይወት ድረስ በሦስት ክፍል ከፋፍዬ አቀርበዋለሁ።
ሀ. #ከመቁረብ_በፊት
👉አማኙ ወደ ቅዱስ ቁርባን ከመቅረብ በፊት ሊያደርጋቸው የሚገቡ ዝግጅቶች መንፈሳዊ ጥንቃቄዎች ይባላሉ እነዚህም ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርበዋል።
➕ሀ/ የሚቆርቡ ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉ ሰዎች በጋብቻ ሥርዓት የሚኖሩ ከሆኑ ከመቁረባቸው በፊት 3ቀን ከሩካቤ ሥጋ መከልከል ይገባቸዋል። ይህ ግንኙነት ኃጢአት ሆኖ ሳይሆን ግብረ ሥጋ /የሥጋ ሥራ ስለሆነ ለተቀበሉት ክብር ነው.
➕ለ/ ማንኛውም ሰው ስለሚያውቀው ኃጢአት ተናዝዞ ስለማያውቀው ይቅር በለኝ እያለ ከኃጢአቱ ነጽቶ ልቡን ከቂም በቀል ሰውነቱን ከበደል ማራቅ ይገባቸዋል::
➕ሐ/ ሥጋ ወደሙ ለመቀበል 18 ሰዓት ከእህል ከውሃ ተከል በመጾም አፍን ምሬት እስኪሰማው የበሉት ከሆድ እስኪጠፋ መቁየት ይገባል /ፍት መን 13 ረስጠብ 46.
➕መ/ ጰወንድ ዝንየት ርስሐት/ /ህልመ ሌሊት ካገኘው በዚያ ቀን
አይቆርብም ካህን ቢሆን እንኳ በሚቀድስበት ቀን እንእንቅፋት ቢያገኘው ማለት ነስር፣ ትውኪያ፣ ብስና፣ ማንኛውም የአካል መድማት መቁሰል ወደ አፍ የሚገባ እንደ ትንኝ ዝምብ ይህን የመሰለ ሁሉ ቢያጋጥመው በዚያን ዕለት መቀደስ
መቁረብ አይገባውም ይህ ለካህን ብቻ ሳይሆን ምዕመናንንም የሚመለከት ነው።
➕ሠ/ በመቁረብ ዋዜማ ገላን መታጠብ የሚለብሱትን ንጹህ አድርጎ ማዘጋጀት ይገባል፡፡
➕ረ/ ቅዳሴ ከመገባቱ አስቀድሞ ከቤተክርስቲያን መገኘትና በሚገባ
ሆኖ ቅዳሴውን ማስቀደስ ቅዳሴ ሲገባ ያልነበረ በመሃል የመጣ ሰው መቁረብ አይገባውም::
➕ሰ/ ሴት በወር አበባ ላይ እስከ 7 ቀን መቁረብ አይገባም ከዚያ ሰውነቷን ታጥባ ትቀበላለች፣ በወሊድ ጊዜ ደግሞ የመታረስ ጊዜዋ እስኪፈጸም
ድረስ እስከ እሰከ ህጻኑ ክርስትና ድረስ አትቀበልም ።
«ሴት ከወለደች 80 ቀን ወንድ ከወለደች 40
ቀን ማለት ነው» /ዘሌ 12 : 1-5/
#ምዕራፍ 3
ክፍል 3
❖❖#በመቁረብ_ጊዜ
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
✍ "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
ግንቦት 11 የዜማው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ወደ ብሔረ ህያዋን የተሰወረበት ዕለት ነው
በዚህች ዕለት የምስጋናችን ውበት፣ የድምፃችን ፊደል፣ የዜማችን አርማ እንዲሁም የዜማ አባት፣ የቅኔ ሊቅ፣ አሠረ ሊቃውንት ያሬድ ማሕሌታይ ተሰወረ
❤❶❶እንኳን አደረሳችሁ❶❶❤
/channel/dnhayilemikael
እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!
መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤልና አገልግሎቱ በጥቂቱ
✍ ዑራኤል የሚለው ስም "ዑር"እና ኤል ከሚለው ሁለት ቃላት የተመሰረተ ነው ። ትርጉሙም ብርሃነ ጌታ አምላክ ብርሃን ነው። ማለት ነው።
✍ ቅዱስ ዑራኤል ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ መብረቅና ነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበቁ ነጓድጓድ ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። (መጽሐፈ ሄኖክ ፮፥፪)
✍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ እየመራ፤ ከእስራኤል ወደ ግብጽ ከዚያም ከእመቤታችን ጋር በሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው።
✍ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለበት ጊዜ፥ክቡር ደሙ በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን ነሳንስ የረጨው እሱ ነው።
✍ ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ልቦና ያጠጣው፥ጥበብን ማስተዋልን የሰጠው የጠፉ መጽሓፍት በቃሉ አስታውሶ እንደገና ያጻፈው የረዳው መልአክ ነው።(ዕዝ፲፫፥፴፱)
✍ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ትዕዛዝ ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ህይወት ስላጠጣቸው ነው።
✍ በዓላቱም በዓመት 3ናቸው።
፩...ጥር። 22 በዓለ ሲመቱ፤
፪....መጋቢት 27 የጌታችንን ደም በዓለም የረጨበት፤
፫...ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ።
✍ በጸሎቱ የተማጸነ ከእግዚአብሔር አምላክ በረከትን ፣ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ ጠባቂ ና የዋህ መልአክ ነው።በተለይም ህጻናትን የሚጠብቅ የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ ፥ኃጢአተኞች ካሉበት ቦታ እኔን ላከኝ እያለ አምላኩን የሚማጸን አዛኝ የዋህ መልአክ ነው።
✍ ይህ አለም በአማላጅነቱ አምኖ በእምነት ጸበሉን ቢጠጣ ፥ዝክሩንም ቢዘክር ከክፉ በሽታው እንደሚድን፤ እንደሚፈውሰው ቃል ኪዳን ተሰጥቶታል ።
✍ ቅዱሳን መላዕክት እግዚአብሔርን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራሉ ከመከራም ያድኑዋቸዋል።(መዝ ፴፫÷፯) የአባታችን የጠባቂያችን የአማላጃችን የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል ቃል ኪዳን አይለየን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael
✔️ #_የጽዋ_ማኅበር_ምንድነው???
#ለምንድነው_ከቤተ_ወደ_ቤት_እያዘዋወሩ_የሚያደረጉ ??
✔️ #የመሶበ_ወርቅና_የጽዋው_ምስጥር_ምንድነው???
#_የጽዋ_ማኅበር_ምንድነው???
✔️👉➕ #የጽዋ_ማኅበር ፡"ክርስቲያኖች በእግዚአብሔርና በቅዱሳን ሰዎች ስም
እየተስበስቡ በቤተክርስቲያን ወይም በየቤታቸው
የሚፈጽሙት የቅድስና ሥራ ነው።
✔️ይህም እግዚአብሔር
በመካከሌቸው እንዳለ በማመን የሚከውኑት የመንፈሳዊ በረከት ነው፡፤ ይህንንም ከአንድ ከርስቲያን ቤት ወደhላኛው አያዘዋወሩ ያደርጉታል።
#ለምንድነው_ከቤተ_ወደ_ቤት_እያዘዋወሩ_የሚያደረጉ??
✔️#መነሻውም 👉አንደኛ #በዘመነ_ብሉይ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በደጉ አባት አብርሃም ቤት
ተገኝቶ ሣራ የሠራችውን ተመግቦ ቤታቸውንም ባርኮ
የተዘጋውን በር ከፍቶ የሣራን ማኅፀን ከፍሬ አብቅቶ ከዚ 👉ቀጥሎ ደግሞ በመላእክቱ አድሮ በኰጥ ቤት ተገኘ፡ ሎጥንህ ከታካቅ መከራ መላእክቱ አጁን ይዘው አወጡት።
✔️👉ዛሬም ክርስቲያኖች መሶቡንና ጽዋውን በመያዝ በየወሩ በየቤቱ አየተሰበሰቡ ይህንን ያስባሉ ፡፤ {ዘፍ ፲፰ (18)
✔️👉 ✔#የመሶበ_ወርቁና_የጽዋው_መግባት የእግዚአብሔር መግባት ምሳሌ ነው
✔️ምሥጢሩን አንመከከተዋከን።👇
ሐእብርሃምና ለሣራ አንዲሁም ለሎጥ የተደረገው የአግዚአብሐርን ቸርነት ጽዋው በገባበት ቤትም ይደረግ ዘንድ የምእመናን ምኞትና ጸሎት ነው።
#✔️👉 #ሁለተኛ_በዘመነ_ሐዲስ_በወንጌልም_ተጽፎ_እንደምናገኘው
✔️ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው በሚያምኑት ቤት እየገባ እየተመገበ ቤታቸውንም ይባርክላቸው ኃጢአታቸውንም ይደመስስላቸው ነበር፡
👉 #ለምሳሌ
✔️በቢታንያ ሀገር በለምጻሙ በስምዖን ቤት (ማቴ ፳፰፡፮ (26፡6)
✔️በኢያሪኮ አገር በቀራጩ በዘኬዎስ ቤት (ሉቃ ፲፱፡፩-፲( 19፡1 - 10)
✔️የማርያምና የማርታ ወንድም በሆነው በአልአዛር
ቤት (ሊቃ ፲፡፴፰-፵፪ ( 10፡38-42)
👉✔️➕ #ዛሬም ምእመናን ኃጢእተኞችን የማይጸየፍ ጌታ በቤታቸው ይገባ ዘንድ መሶበ ወርቁንና ጽዋውን ይዘው ባሉበት ቤት ሁሉ በረከት
ይገባበታል ፡፡
👉"እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳኳሁ ማንም ድምፄን ቢስማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱ ጋር እራት እበካhሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል ።” ራዕ ፫፡፳ (3:20)
👉➕✔️እንዲህ ያለን ጌታ ምእመናን ይህን ምሥጢር በሚገልጽ የጽዋ ማኅበር ይዘክሩታል።
➕👉 #ዘከረ የሚከው የግእዝ ቃል
#አሰበ ማለት ነው።
✔️በዚህም ረቂቅ ምሥጢር የሚታሰበው ቀጥሎ ያለው ነው።
#የመሶበ_ወርቅና_የጽዋው_ምስጥር_ምንድነው???
✔️👉➕ #መሶበ ወርቅ፡- መሶበ ወርቅ በውስጡ ኅብስት ይደረግበታል👉 የዚህ ምሥጢሩ መሶበወርቅ የእመቤታችን ምሳሌ ፡
👉 መሶቡ የወርቅ መሆኑ የእመቤታችን ንጽሕናን የሚያመከት ነው።
✔️ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር ፴፬ ቁጥር ፪
( 44፡9) እመቤታችንን ንግሥቲቱ ብሎ የወርቅ ክብሰ
ተጎናጽፋና ተሸፋፍና በቀኝህ ትቆማለች ብሎ
እንደመሰከረው።
👉✔️✔️ #ክርስቲያኖች መሶባቸውን አጎናጽፈው
ሽፍንፍን አድርገው ይይዙታል፡፤
✔️ምክንያቱም ቅድስት
የሆነች እመቤታችን ክብር ይገባታል።
✔️በመሶበ ወርቁ ውስጥ የሚደረገው ኅብስት “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ " ያለ
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስ ምሳሌ ነው። (
ዮሐ፡፮÷፴፭) ይህንንም አክብሮ መያዝ ብቻ ሳይሆን ይሳለሙታል ይስሙታል ክብሩ ለእግዚአብሔር ነው።
✔️✔️✔️✔️✔️ #ጽዋ ✔️✔️✔️✔️😘
ጽዋ፡- የጽዋውም ምሥጢር እንደ መሶበ ወርቁ አንድ ነው።
✔️ #ጽዋው የእመቤታችን ምሳኤ ነው፡፡
✔️ በውስጡ ያለው ጸበል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የደሙ ምሳሌ ነው።
👉 ከብር ይግባውና መሶበ ወርቁና ጽዋው
የኅብስቱና የጸበሉ መያዣ የእመቤታችን መሆኑ ጌታችን ሥጋንም ደምንም የተዋሐደው ከእርሷ ብቻ ነውና።
✔️ምእመናንም ይህን በመረዳት በጽዋ ማኅበራችን የጌታችን መከራውን በቀራንዮ ያደረገውንም ሞቱን እያሰብን ይህን ዴግ ሥራ እናደርጋለን ፡፤
👉➕✔️ዋና ዓላማው ይህ ሆኖ ሳለ
በመሰባሰባችንም የተቸገሩ፣የተራቡ፣ የተጠሙ ነዳያንን እናስባከን፡፤
✔️ #ይህም_ሊሆን_እንደሚገባ_ቅዱስ_ጳውሎስ_በመክእከቱ_የሥጋ_ወደሙንና_የጽዋ_ማኅበር1መሰባሰብ_እንዳስተማረን_ልናደርገው_ይገባል።
✔️፩. #የእግዚእብሔርን_ማኅበር_እንዳንንቅ፡- ማኅበሩ እግዚእብሔር የሚገኝበት መሆኑን እንድናውቅ፡ ስዚህም ነው የእግራችንን ጫማ የምናወhቀው።
✔️፪. በማኅበራችን ጊዜ ከልክ ያለፈ ድግስ እንዳናደርግ የሌላቸውንም ሰዎች እንዳናሳፍር።
✔️፫. ከተቸገሩ ከተራቡ እንድናስብ፤
✔️፬.ከልክ በላይ እንዳንበላና እንዳንጠጣ። በተለይ
ስካር ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
ሌሎችም ብዙ መልእክቶች ያስተምረናል።
✔️የሥጋ ወደሙን
መክእከት ከጽዋ ማኅበሩ በመለየት ፩ቆሮ ምዕራፍ ፲፩
ከቁጥር ፲፯ ጀምሮ እስከ ፴፬ ያከውን (1ቆሮ 11፡17-34)
ጠንቅቆ ማንበብ ያስፈልጋል።
የጽዋው በታችን መግባት የእግዚአብሔር ቤታችን መግባት ከሆነ በተቻለን መጠን የጽዋ ማህበር እንግባ መልእክቴ ነው
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
@dnhayilemikael
✝ ምክረ አበው ✝
#ተግሳጽ ነፍስን በመልካም ምግባር ለማጠናከር ምክንያቷ ነውና ተግሳጽን ውደድ።
#በሌሎች ላይ እርማትን ከመሰንዘር በፊት የራሳችንን ስህተት ማረም ይጠቅማል ።
#አንዳንድ ስዎች ነጻነት የሚለውን ቃል የሚረዱት የወደዱትን ሁሉ የመፈጸም ፈቃድ አድርገው ነው። ሰዎች አብዝተው ራሳቸውን የኃጢአት ባሪያ እያደረጉ በመጡ መጠን ህጉን ለራሳቸው እንዲስማማ አድርገው ሊተረጉሙ ይዳዳቸዋል። እንዲህ አይነት ሰዎች ውጫዊ ነጻነትን የሚጠቀሙበት በተሳሳተ መንገድ ነው።
(ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ)
#ሞትን አትፍራ ሀጢአትን ፍራ።
#ስለ መተላለፋችን ምንም አይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር።
#አለም አንተን ሳትንቅህ አስቀድመህ ናቃት።
(ቅዱስ አትናቴዎስ)
please share✝✝✝@dnhayilemikael
እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን
ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ።
💠#በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።
💠በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።
💠ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!
#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
@dnhayilemikael
#ዝምታ
አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከቃላት ይልቅ ውጤታማ፣ ይበልጥ ተገቢና እጅግ ጠቃሚም ነው። ወይም ደግሞ ቢያንስ - ቢያንስ ተናግሮ ከሚመጣ ጉዳት ይልቅ ሳይናገሩ የሚመጣ ጉዳት ይሻላል። በዝምታ ውስጥ ጥበብና ጥንካሬ ከመኖራቸው በተጨማሪ ክብርና ሞገስም አሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ይናገር ዘንድ እኛ ዝም እንላለን፣እኛ ልንናገር ከምንወደው ከማንኛውም ነገር የበለጠ የእግዚአብሔር ቃል እጅግ ኃያል ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ የተናገረው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው! «እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤እናንተም ዝም ትላላችሁ. . » ዘጸ 14፥14።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በዝምታ ቆይቷል። በዚያን ጊዜ እርሱ አፉን አልከፈተም ራሱንም አልተከላከለም። ጌታ ዝምታን በመረጠ ጊዜ ጲላጦስ «ይህን ጻድቅ ሰው የምወነጅልበት ምንም ዓይነት ምክንያት አላገኘሁም» በማለት ተናግሮ ነበር፡፡
ዝምታ ትርፍ አስገኚ ይሁን እንጂ የተወሰነ መመሪያ አይደለም፡፡ ወርቃማው መመሪያ፡- ሰው ሊናገር የሚገባው በትክክለኛው ጊዜ መሆኑና ዝም ማለት የሚገባውም ዝም ማለት በሚገባው ትክክለኛ ጊዜ መሆኑ ነው።
ሰው ዝም ሲል ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲነጋገር ስለሚፈቅድ በእርሱ ፈንታ ጌታው እንዲናገር ይጠይቃል ማለት ነው፡፡
(አቡነ ሽኖዳ ሣልሳዊ - የሕይወት ልምድ ገጽ 14 - በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)
⌲ ♡
ˢʰᵃʳᵉ ˡᶦᵏᵉ
@dnhayilemikael
+ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? +
(ጊዜ ወስደው ያንብቡት አያጥር ነገር ታሪክ ሆኖ ነው)
አንድ ግብፃዊ መነኩሴ ለገዳሙ መርጃ የእጃቸው ሥራ የሆኑትን ቅርጫቶች ሊሸጡ ወደ እስክንድርያ ለመጓዝ በጠዋት ተነሡ፡፡
በመንገድ ላይ ታዲያ ትልቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማድረግ የሚጓዝ ሕዝብ ገጠማቸው፡፡ ሟቹ ዝነኛ አረማዊ ገዢ ሲሆን በዘመነ ሰማዕታት በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለ ሰው ነበር፡፡ አሁን ዕድሜ ጠግቦ ሞቶ ነው፡፡ ቀኑ ውብ ፀሐያማ ቀን ነበርና የሀገሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ገዢያቸውን እየቀበሩ ነው፡፡
ይህንን ያዩት መነኩሴ ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ ገዳም ሲመለሱ አሳዛኝ ዜና ሰሙ፡፡ ለስድሳ ዓመታት በበረሃ በብሕትውና ቅጠልና የበረሃ ፍሬ ብቻ እየበላ የኖረ ባሕታዊ በዚያች ዕለት በጅብ ተበልቶ ሞቶ ነበር፡፡
መነኩሴው እጅግ ጥልቅ ኀዘን ውስጥ ሆነው እንዲህ ሲሉ አሰቡ ፦
‘በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለው አረማዊ ሰው በታላቅ ክብር ታጅቦ ሲቀበር ሕይወቱን ሙሉ በጾምና በጸሎት ፈጣሪውን ያገለገለው ባሕታዊ በጅብ ተበልቶ የተዋረደ አሟሟት ሞተ፡፡ይህ እንዴት ዓይነት ፍርድ ነው? እግዚአብሔር ከመልካምነቱ ሁሉ ጋር ኢፍትሐዊ ነገሮች ሲሆኑ ዝም ብሎ ይፈቅዳል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች የፈጣሪን መኖር ይጠራጠራሉ፡፡ እኔም ፍርዱን እንዲገልጽልኝ መጸለይ ይኖርብኛል’ አሉ፡፡
ከዚያች ቀን ጀምሮ መላልሰው ወደ ፈጣሪ ‘’ፍርድህን ግለጽልኝ’ ብለው ደጋግመው ጸለዩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ እግዚአብሔር ፍርዱን እንዲህ ገለጠላቸው፡፡
ከሳምንታት በኋላ እንደተለመደው ወደ እስክንድርያ የሦስት ቀን ጉዞ ሊሔዱና ቅርጫታቸውን ሊሸጡ ተነሡ፡፡መንገዱን እንደጀመሩ ድንገት አንድ ወጣት መነኩሴ ወደ እርሳቸው ሲመጣ ተመለከቱ፡፡
‘’አባቴ ይባርኩኝ’
‘እግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ’
‘አባቴ ወዴት ይሔዳሉ?’ አለ ወጣቱ መነኩሴ
‘ወደ እስክንድርያ ቅርጫቴን ልሸጥ እየሔድኩ ነው’ አሉት
‘ጥሩ አጋጣሚ ነው አባ እኔም ወደዛ እየሔድኩ ነው’ አለ በትሕትና
‘ጎሽ አብረን እንጓዛለና’ አሉ አባ፡፡ ወጣቱ መነኩሴ ከእጃቸው ሸክማቸውን ተቀበለ፡፡ ጥቂት እንደሔዱ እንዲህ አላቸው፡፡
‘አባ ያው እንደሚያውቁት እንደ መነኮሳት ሥርዓት ጉዞ ስንጓዝ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር አለብን አይደል?’’ አላቸው፡፡
‘ልክ ነው ልጄ’ አሉት
‘እንግዲያውስ ለሦስት ቀን አብረን ስንጓዝ እስክንድርያ እስክንደርስ ድረስ አንዲትም ቃል አንነጋገር ፤ ምናልባት በሦስቱ ቀን ጉዞአችን ለማየት የሚከብድ ነገር እንኳን ሳደርግ ቢያዩኝ ላይናገሩኝ ላይፈርዱብኝና የአርምሞ ቃልኪዳንዎን ላያፈርሱ ቃል ይግቡልኝ’ አላቸው፡፡
አባ እየተገረሙ ‘እሺ በሕያው አምላክ እምላለሁ ልጄ አንዲትም ቃል አልተነፍስም’ አሉት፡፡
ሁለቱ አባቶች በጠዋቱ የአርምሞ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ቀትር ላይ ወደ አንዲት መንደር ደረሱ፡፡
ሁለት ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት አዩአቸው፡፡ ከሁለቱ አንዱ ‘ቅዱሳን አባቶች’ እያለ ወደ እነርሱ ሮጠ ‘ቅዱሳን አባቶቼ ፀሐዩ እስኪበርድ ድረስ እባካችሁን እኛ ቤት አረፍ በሉ’ አላቸው፡፡ ፀሐይዋ እየከረረች ስትመጣ በበረሃማዋ ግብፅ ጉዞ በጠዋትና ማታ እንጂ በቀትር ስለማይታሰብ ጉዞአቸውን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት በክብር ተቀብለው ከቤታቸው አስገቧቸው፡፡እግራቸውን አጠቧቸው፡፡ በቤታቸው ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ የከበረ እጅግ ውድ የብር ሰሐን ላይ ምግብ አቀረቡላቸው፡፡ መነኮሳቱ በዝምታ ተመገቡ፡፡ ከዚያም ትንሽ አረፍ የሚሉበት ክፍል ተሠጣቸው፡፡
ትንሽ እንደቆዩ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ወደ ምግብ ማብሰያው ክፍል ገብቶ ይበሉበትን ውድ የብር ሳህን በልብሱ ደብቆ ይዞት መጣና አባን ጠቅሶ ጠራቸው፡፡ ተሰናብተው ከወጡ በኋላ አባ በቀሚሱ ውስጥ የደበቀውን የብር ሳህን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ መናገር ባይችሉም በልባቸው እንዲህ አሉ ፦
‘እነዚያ ደግ ወጣቶች በክብር ተቀበሉን ፤ እግራችንን አጥበው መገቡን፡፡ እውነት ለውለታቸው ምላሹ ውዱን ንብረታቸውን መስረቅ ነው?’’ ብለው አዘኑ፡፡
ጥቂት እንደተጓዙ የመስኖ ውኃ ወደተከማቸበት አንድ ድልድይ ጋር ደረሱ፡፡ ውኃውን ሲሻገሩ ታዲያ ወጣቱ መነኩሴ በብር ሳህኑ ላይ ካማተበበት በኋላ ወደ ወንዙ ወረወረው፡፡
አባ እንዲህ ብለው አልጎመጎሙ ፦
‘’እንዴት ያለ ነገር ነው? ሳህኑን የሰረቀው ሊወረውረው ነው? እዚያው አይተውላቸውም ነበር?’’ አሉ አርምሞአቸውን ሊያፈርሱ አይችሉምና ዝም አሉ፡፡
ሲመሽ ወደ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ቤት ደረሱ፡፡ እንደ ቀኖቹ ወጣቶች እነዚህም በክብር እግር አጥበው አስተናገዷቸውና ማረፊያ ሠጧቸው፡፡ ባልና ሚስቱ የሁለት ወር ሕፃን ልጅ ነበራቸው፡፡ በጠዋት ሲነሡ ወላጆች ሳይነሡ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ሔዶ የተኛውን ሕፃን ገደለው፡፡ አባ ሊያስጥሉት ቢሉም አልቻሉም፡፡ እየጎተተ ይዞአቸው ወጣ፡፡ ‘ጌታ ሆይ ምን ዓይነት ርጉም ነው ንጹሑን ሕፃን ገደለው እኮ’ እያሉ እንባቸው ወረደ፡፡ ምንም እንኳን አንጀታቸው በኀዘን ቢኮማተርም በመሓላ የገቡበትን አርምሞ አፍርሰው ከግዝት ላለመግባት አንዲት ቃል ግን አልተናገሩም፡፡
በቀጣዩ ቀን ሁለቱ መነኮሳት ወደ አንድ መጠጥ ቤት ደጅ ደረሱ ፤ የጭፈራው ድምፅ ከሩቅ ይሰማል ፤ ሰካራሞቹ መነኮሳቱን ሲያዩ ‘ቅዱሳን’ እያሉ ተሳለቁ፡፡ በሰካራም አንደበት የሚናገረው ዲያቢሎስ ነው ብለው ዝም አሉ፡፡
ወጣቱ መነኩሴ ግን ወደ መጠጥ ቤቱ አቅጣጫ በግንባሩ ተደፋና ሦስት ጊዜ ሰግዶ ተሳለመው፡፡
ጥቂት እንደሔዱ አንድ ያረጀ ፤ መስቀሉ ከጉልላቱ የተነቀለ በርና መስኮት የሌለው ቤተ ክርስቲያን አዩ
ወጣቱ መነኩሴ ድንጋዮች ለቀመና አማተበባቸው ወደ ፈረሰው መቅደስም ወረወረው
አባ ይሄን ጊዜ ፦ መጠጥ ቤቱን ተደፍቶ ተሳለመ ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ ድንጋይ ወረወረ ! ብለው በዝምታ ተንጨረጨሩ ::
አሁን ሦስተኛው ቀን ሞላ በጠዋቱ ወደ አንድ በሸንበቆ የተሠራ ቤት ደረሱ እናታቸው የሞተችባቸውና በአጎታቸው እርዳታ ብቻ የሚኖሩ አምስት ሕፃናት ተቀምጠው ያለቅሳሉ፡፡ አባ በርኅራኄ ለሕፃናቱ ምግብ ሠጧቸው፡፡ እሳቸው ከሕፃናቱ ጋር ሲነጋገሩ ወጣቱ መነኩሴ ደሞ የሸንበቆውን ቤት በእሳት እያያያዘ ነበር፡፡ ሕፃናቱ ከሚነደው ቤት ሮጠው አመለጡ፡፡
‘ይህን ነፍሰ ገዳይ እስከመቼ እታገሰዋለሁ’ ሲሉ የቆዩት አባ እስክንድርያ ደርሰዋልና በምሬት መናገር ጀመሩ
‘’እስቲ ንገረኝ ከዚህ በኋላ ዝም ልልህ አልችልም፡፡ መልስልኝ አንተ ሰው ነው ወይስ ሰይጣን ነህ?’
‘ምነው አባ ምን አጠፋሁ?’ አለ መነኩሴው
‘በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ ምን ያላደረግከው ነገር አለ? በበረሃ አክብረው የተቀበሉንን ሰዎች የብር ሳህን ሰርቀህ ወንዝ ውስጥ አልጨመርህም? እነርሱም መነኩሳት በቤታችን ተቀብለን ሰርቀውን ሄዱ እያሉ ይሆናል’
መነኩሴው መለሰ :- ‘አባ ትልቅ ነገር ነው እኮ ነው ያደረግሁላቸው፡፡ ያቀረቡልን የብር ሳህን ቅድም አያታቸው ከጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን የሰረቀው ጻህል /የቅዱስ ቁርባን ማቅረቢያ/ ነበር፡፡ መላው ቤተሰብ ይህንን ሳያውቅ በዚያ ቤት ለብዙ ዘመን ሲቀባበሉት ነበር፡፡በላዩ ላይም በላቲን ቋንቋ ይህ ጻህል ለቅዱስ ኒቆላዎስ ቤተ ክርስቲያን የተሠጠ የሚል ጽሑፍ አለበት፡፡ በዚህ ምክንያት ያንን ቅዱስ ንዋይ የሚጠቀሙ ሁሉ እስካልተመለሰ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ድፍረት ይሆንባቸዋል፡፡ የሞቱት ወላጆቻቸውም በዚያ ቅዱስ ንዋይ የተነሣ ነፍሳቸው ትታወካለች፡፡ እነዚያም ወጣቶች በጻሕሉ እኛን በማስተናገዳቸው ነፍሳቸው
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 4
#ከቅዱስ_ቁርባን_የሚያርቁ_ስለ_እምነት_ምንነት_አለመረዳት_እምነት_ምንድነው ???
#ክፍል 3
#እምነት_ጥበብ_ነው
«ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያየውም አይችልም [1ጢሞ 6 : 1 6/
✔️በእርግጥ ተሰውሮና ማንም ሊያየው ሊደርስበትም የማይችለውን አምላክ በእምነት መከተል ጥበብ ነው:: ማንም ሊቀርበው በሃይችል ብርሃን ተሰውሮ ወደሚኖር ከሰው አእምሮ በላይ ወደ
ሆነ አምላክ የሚደርሱበትና ከእርሱም ጋራ የሚኖሩበት ይህ የእምነት ሕይወት ጥበብ ነው:: ✔️ስለዚህ በእምነት የሚመላለሱ
በማያምኑት ዘንድ በጥበብ የሚመላለሱ ናቸው::
✔️የጥበብ ሁሉ መገኛ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ዓለም ሳይፈጠር ጥበብ በእርሱ ዘንድ ነበረች/ ሲራክ1÷1/ እግዚአብሔርን በእምነት ሕይወት መከተል ደግሞ የጥበብ ለመጀመሪያ*ነው አባታችን ✔️ኢዮብ እንዲህ አለ «ሰውንም እነሆ እግዚአብሔርን
መፍራት ጥበብ ነው ከኃጢአት መራቅ ማስተዋልነው አለ። ኢዮብ 28 ፡ 28/ ከዓለም የተሰወረችን እግዚአብሔርን ማወቅና መፍራት የተገኘችው የእምነት ሕይወት ባላቸው ሰዎች ልብ ነው።
✔️ይህ ደግሞ የዓለምን ጥበብ ከንቱ የሚያደርግበት ነው ሐዋርያው « ዘመኑን እየዋጃችሁ በውጭ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ >>
በተጨማሪ ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ሲጽፍ
<<እንግዲህ እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ >>ኤፌ 5÷15 ይላታል። ይኸውም እግዚአብሔር በማመንና በመፍራት
ጥበብ ተመላለሱ ሲል ነው፡፡
✔️ጠቢቡ ሰለሞን «የጥበብ መጀመሪያ
እግዚአብሔርን መፍራት ነው ምሳ.1÷7 በማለት የተናገረው ይህን ያረጋግጥልናል፡፡
✔️እውነተኛ ምዕመናን የሚያምኑትን እግዚአብሔርን ከፍቅር በመነጨ ይታዘዙታል ይፈሩታልም፡፡ ተመልሰን የሐዋርያውን መልእክት እንድንመለከት የሚጋብዘን አንድ ቃል አለ «በውጭ ባሉት ዘንድ የሚለው ኃይለ ቃል ከእምነት ሕይወት ውጪ ከብርሃን ተለይተው ባለማወቅ ጨለማ_በሚመላለሱት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ የሚለው ይህም በቀናች ሃይማኖት ጸንታችሁ ኑሩ ሲለን ነው።
✔️በብርሃን ተሰውሮና ከፍጥረታት እውቀት በላይ የሆነውን አምላክ በእምነት አግኝተዋልና እነዚህ የጥበብ ሰዎች ናቸው፡፡
✔️ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍ በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን ስላላወቀው በስብከት ሞኝነት
የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኗልና 1ቆሮ ብሏቸዋል።
እግዚአብሔርን የሚያውቁበትንና የሚያገኙበትን በስብከት ሞኝነት ያመኑ እነዚህ እግዚአብሔር የዓለምን ጥበብ ከንቱ ወዳደረግበት ጥበብ የአምላክ ሰው የመሆን ምስጢር የደረሱና ያመኑ የጥበብ ልጆች ናቸው።
✔️ይኸውም የእግዚአብሔር ጥበብ
ቅዱስ ጳውሎስ እንደመሰከረው በሐዋርያት በተሰበከው ከድንግል ✔️ማርያም በተወለደው ✔️በክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት ማመን ነው።
የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው ይላል ቆሮንቶስ 1÷24 ተብሎ ተጽፏልና።
✔️ሌላው በእምነት የሚመላለሱ ሰዎች የዓለም ጥበብ ተመራምሮ የማይደረስበት የሰማያዊው ጸጋ ባለቤቶች ናቸው
✔️በእምነት ሀይልና ከእግዚአብሔር በተቀበሉት ጸጋ ዓለሙን ወደ እምነት የሚስቡበት ታላላቅ ድንቆች ያደርጋሉ የሐሰተኞችንም ድንቅ ማደረግ ያዋርዳሉ።
✔️እግዚአብሔር ያዘዘውን ተቀብሎ ወደ ፈርዖን ቤተ
መንግሥት የገባው ሙሴ በትሩን በመጣል በንጉሥ ፊት ወደ እባብነት ለወጠው ይህን ነገር የንጉሥ ጠንቋዮችና ሟርተኞች አድርገውታል ።
✔️ ነግር ግን የሙሴ በትር የሟርተኞችን በትር
በመዋጥ አሳፈራችው የሙሴ ተዓምራት በእምነትና በእግዚአብሔር ዘንድ የሆነች ነበረችና ሙሴም በፈርኦን ፊት በጥበብ ተገለጠ ።
✔️ሐዋርያው <<እርሱን በማወቅ የጥበብ መገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ>>/ኤፌ1÷ 17 በማለት ያስረዳናል ።
✔️ስለዚህ ሕይወትን መምረጥ ጥበብ ነው።
✔️ሕይወትን የሚመርጥ ደግሞ እራሱን ወደ ክርስቶስ #ሥጋና #ደም ያቀርባል ።
✔️የዘላለማዊ አምላክ አምላክ በማመን የሚገኘው የዘላለም ሕይወት ነው
✔️እውነተኛ አማኝ ደግሞ የዘላለም ሕይወት ወራሽ ነው ። ስለዚህ ደግሞ እምነት ህይወት ነው ።
ምዕራፍ 4
ክፍል 4
(1) እምነት ህይወት ነው
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት /channel/dnhayilemikael/4985
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ግንቦት 28/2015 ዓ.ም
ይገባል!
የንስሐ፣የሰላምና የፍቅር ጾም ይሁንልን!
#ፆመ_ሐዋርያት #ሰኔ_ፆም
መቼ_ይገባል?ለምንስ_ይፆማል‼
2015'ዓ'ም ግንቦት 28 ሰኞ ይጀመራል።👉ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ፆም ነው።
🌿💒 የሰኔ ፆም :- ይህ ፆም የሀዋርያት ፆም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ፆም ተባለ ቢሉ በበአለ ጴራቅሪጦስ ሀዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በዉሀላ የፆሙት ፆም ስለሆነ ነው።
👉የሰኔ ዖም የሚፆምበት ጊዜያት
የሰኔ ፆም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይፆማል የሰኔ ፆምን እስከ 9 ሰአት እንድንፆም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።
🌿💒 የሚገባበት ቀን በየአመቱ የተለያየ ቢሆንም የፆሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ። ሐምሌ 5 ሁለቱ ሀዋርያት ጴጥሮስ እና ጳዉሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉበት እለት ነው ።
🌿💒 ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡
👉ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16
🌿💒 እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው። አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሰላም ያድርሰን!!!
@dnhayilemikael
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 4
#ክፍል 1
#ከቅዱስ_ቁርባን_የሚያርቁ_ስለ_እምነት_ምንነት_አለመረዳት_እምነት_ምንድነው ???
👉እምነት የሚለው መሠረታዊ ቃሉ ግዕዝ ሲሆን የቃሉ ፍቺ✔️ #ማመን✔️ #መታመን✔️ #ተስፋ✔️ #ሐሴት ማድረግ ማለት ነው::
👉 #ማመን ደግሞ ✔️ስለ እግዚአብሔር ✔️#የሰሙትን✔️ #የተረዱትን እንዲሁም የተቀበሉትን ትምህርት እውነት ነው ብሎ በልብ መቀበል ነው።
👉✔️ #መታመን ደግሞ #ያመኑትን✔️ #የተቀበሉትን በሰው ፊት ሳይፈሩ መመስከር ነው::
/ማቴ. 10፥23/ «በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እመሰክ
ርለታለሁ» እንዳለ
👉✔️ #በተጨማሪም ሰው እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረጉ በእርሱም መደሰቱ በማያወላውል ጽኑ ውሳኔው ሲከተለው የማመኑም ✔️ውሳኔ ለሚጠይቀው 👉ግዴታ ሲገዛና የሚጠይቀውን
✔️መሥዋዕትነት 👉በመክፈል ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ፈጥሮ በመታዘዝ ሲኖር እምነቱ ተመሰከረ ተገለጸ ማለት ነው::
👉✔️ #በአጠቃላይ መልኩ እምነት የሰውን የውስጥ መንፈሳዊ ሕልውና የሚዳስስና የሚቆጣጠር ስሜትን የሚቀሰቅስና ሕይወትን የሚመራ ታላቅ ኃይል ነው::
👉✔️ #እምነት ለሰው ልጆች ከተሰጡት ታላላቅ በረከቶች መሐል አንዱና ዋናው ለሌሎችም በረከቶችና ጸጋዎች መገኘት መሠረት ነው::
እንግዲህ እምነት ከላይ ከፍ ብሎ የተጠቀሰው ትርጉም ሲኖረው እምነት በተአማኒው ሕይወት ውስጥ
ተግባራዊ የሕይወት ትርጉም ከዚህ በታች የሚከተሉት ፍቺዎች
የሚኖረው
ይዞ ይገኛል::
፩(1) እምነት ብርሃን ነው
ምዕራፍ 4
ክፍል 2
(1) እምነት ብርሃን ነው
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት
/channel/dnhayilemikael/4979
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
❖ ስብከት ወይም መንፈሳዊ ንባብ የእግዚአብሔርን ድምፅ የሚተላለፊበት መንገድ ሊሆን ይችላል፤ አንድ የወንጌል ጥቅስ ስታነብ ወይም ሲነበብ ስትሰማ እግዚአብሔር ለአንተ እና ለአንተ ብቻ በግልህ እንደተናገረው ሆኖ ይሰማሃል፤ ይህ ጥቅስ ለአንተ የሆነ ትርጉምና ጥቅም እንዳለው ሆኖ ይሰማሃል፤ ይሁን እንጂ ይኼኛው ጥቅስ በተለየ ሁኔታ #በአሳብህ_በልብህ_በስሜቶችህና_በእምነትህ_ውስጥ_ተጽዕኖ_ያሳድርብሃል በውስጡ የእግዚአብሔርን ድምፅ ትሰማለህ፤ ስብከት ስትሰማም ተመሳሳይ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፤ የምትሰማው ስብከት ለአንተ የተነገረ ሆኖ ይሰማሃል፤ በዚህ ጊዜ
✍️ " ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት በማስመረር እንደ ሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አስታውሱ ቃሉ ምንም ዓይነት አሻራ ሳይጥል እንዲያልፍህ አትተውት ።
📖 ዕብ 3፥15
📌ምንጭ
✍አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
አንተ ነህ ያመምከኝ
*****
በተኩላ ያስበላህ በጎቼን ያልጠበክ
የሰቡትን አርደህ የተሰበሩትን የበተንክ
ክህነቴን በገንዘብ ቸርችረህ ያረከስክ
ቀድሰህ የከሰርክ ሰብከህም የከሰርክ
ሺ በደል በድለህ በሌሎች ያላከክ
አንተ ነህ ያመምከኝ
ከሃይማኖት ይልቅ ዘርህን ያደመክ
በጎጥ ተደራጅተህ በመቅደስ የቀደስክ
ደሙን በእጅህ ይዘህ በዘዉጌ ዛር ልክፍት የሰዉ ደም የፈለክ
ወንጌሉን ረግጠህ በመንደር የወረድክ
አንተ ነህ ያመምከኝ ..........
ግጥም ዲ/ን መኩሪያ ጉግሳ
የቆየ ግጥም ነዉ !
@dnhayilemikael
ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ
ለቃ 21:34
፤
ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ናት። ለሰማይ አገልጋዮችን ገና ሳይሞቱ የምትልክ፣ ከተዋጊዎች መካከል ወደ ድል ነሺዎች መልእክተኛ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት?
ቅዱስ ያሬድ በትሕትናው ከትል ተማረ። ትሑታንን ከፍ የሚያደርግ ፈጣሪም ከፍ አደረገውና ከመላእክት ጋር ዘመረ። ከትል ለመማር ፈቃደኛ ከሆንክ ከመላእክት ለመማር ትመረጣለህ::
ያሬድ ትልዋን ከዛፍ አውርዶ ቢጨፈልቃት ኖሮ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያልነጠፈው የምስጋና ጅረት በሀገራችን ባልፈሰሰ ነበር። ኃይል አለኝ ብለህ የምትጨፈልቃቸው ትሎች ሰማይ የሚያደርሱህ መምህራኖችህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ ይላል የታሪኩ ተግሣፅ።
ቅዱስ ያሬድ እግሩን በጦር እየተወጋ እንኩዋን ዝማሬው ሰማያት ወስዶት አልተሰማውም ነበር። የእኛው ሲላስ የእኛው ጳውሎስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በዘመርክባት ሀገርህ ዛሬ ብዙ ጦር ተሰክቶባታል። ከአንተ ዜማ በቀር ዛሬም መጽናኛ የለንምና በምልጃህ አስበን።
ጥዑመ ልሳን ያሬድ: ሊቀ ጠበብት ያሬድ: ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ!!
ምንጭ =ከዲያቆን ሄኖክ ሃይለ fb ገጽ ነው
/channel/dnhayilemikael
◈ግንቦት 11 የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል◈
♥♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ (ይሥሐቅ) እናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻፭ ዓ.ም. በአክሱም ነው፡፡ ሰባት ዓመት ሲመላው አባቱ ስላረፈ፤ እናቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲያስተምረው ለአባ ጌዴዎን ሰጠችው፡፡
♥♥ ነገር ግን ማጥናት ስላልቻለ አባ ጌዴዎን ይቈጣው ነበርና ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ፤ ከዐዘኑም ብዛት የተነሣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንዲት ታናሽ ትል ከዛፍ እኩሌታ ደርሶ ሲወድቅ ሲነሣ በመጨረሻም በጭንቅ ከዛፉ ላይ ሲወጣ በማየቱ እግዚአብሔር በዚኽች ታናሽ ፍጥረት እንዳስተማረው በመረዳት ይቅርታ ጠይቆ ወደ መምህሩ ተመልሷል፡፡
♥ “ወእምዝ ሶበ ሰአለ ኀበ እግዚአብሔር በብካይ ብዙኅ ተርኅወ ልቡናሁ ወተምህረ በሐጺር ዕለት መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ” ይላል ከዚኽ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ኾኖለት በዐጭር ጊዜ ውስጥ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተምሮ በመጨረስ ዲቁናን ተሾመ፤ እስከ ርሱ ዘመን በማነብነብ እንጂ በከፍተኛ ድምፅ የመዝሙር ማሕሌት አልነበረም፤ እግዚአብሔርም ለዚኽ አባት የመላእክትን ዝማሬ ሊያሳየው ስለወደደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ እንደተነጠቀ ኹሉ ሊቁም ተነጥቆ የኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይን የምስጋና ዝማሬ ሰምቶ ተመለሰ፡፡
♥ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር እንደ ደረሰ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ፡- ✍ “ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ” (ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ለሙሴ የድንኳኑን ሥራ እንዴት እንደሚሠራ አሳየው) ሲል ዘምሮ ይቺኑ መዝሙር ከሰማይ መላእክት አገኘኹት፣ በማለት አርያም በሚል ሥያሜ ጠርቷታል፡፡
♥ይኽነኑ ድርሳነ ዜማ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል በሰማ ጊዜ ጫማውን ሳይጫማ ንግሥቲቱም ደንገጡሮቿን አጃቢዎቿን ሳታስከትል መኳንንቱ፣ ካህናቱና መምህራኑ እነሱን ተከትለው እየተጣደፉ ወደ ዐደባባዩ በመኼድ በተመስጦ ሲሰሙት ውለዋል፡፡
♥ ቅዱስ ያሬድ ዐምስት የዜማ መጻሕፍትን የደረሰ ሲኾን እነርሱም
፩ኛ) ድጓ
፪ኛ) ጾመ ድጓ
፫ኛ) ምዕራፍ
፬ኛ) ዝማሬ
፭ኛ)መዋሥዕት ናቸው፡፡
♥ እነዚኽንም ታላላቅ ድርሰቶቹን በሦስት የዜማ ስልቶች ማለት በግእዝ፣ በዕዝል፣ በአራራይ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ “ወአሐተ ዕለተ እንዘ ይዜምር ያሬድ ቀዊሞ ታሕተ እገሪሁ ለንጉሥ ገብረ መስቀል ወእንዘ ያጸምዕ ንጉሥ ቃሎ ለያሬድ ተከለ በትረ ኀጺን ውስተ መከየደ እግሩ ለያሬድ” ይላል፤ ከዕለታት ባንዳቸው ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ ልዑል እግዚብሔርን በዝማሬ ሲያመሰግን ንጉሥ ገብረ መስቀል ሳያውቁት ልባቸው በጣዕመ ዜማው በመመሰጡ የብረት ዘንጉን በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተክለውታል፤ ከእግሩም ብዙ ደም ቢፈስስም ቅዱስ ያሬድ ግን ማሕሌቱን እስከሚፈጽም ድረስ ምንም አልሰማውም ነበር፡፡
♥ንጉሡም የደሙን መፍሰስ አይቶ ደንግጦ ቅዱስ ያሬድን “የደምኽ ዋጋ የፈለግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ቅዱስ ያሬድም ተምኔቱ ወደ ገዳም መኼድ እንደኾነ ነገረው፤ ያን ጊዜ ንጉሡ እያዘነ አሰናብቶታል፡፡
♥ “ወእምዝ ቦአ ያሬድ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወቆመ ቅድመ ታቦተ ጽዮን” ይላል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት በመቆም የአንቀጸ ብርሃንን ምስጋና ከመዠመሪያው እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ በእግዚአብሔር ኀይል ክንድ ያኽል ከምድር ከፍ ከፍ አለ፤ ከዚኽ በኋላ ወደ ሰሜን ተራራዎች ወደ ገዳም ሲኼድ የአኲስም ጽዮን ካህናት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት ርሱም እጅግ ባማረ ጣዕመ ዜማ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ሰላም እግዚአብሔር ኲሉ ባቲ ተሃሉ ወትረ ምስለ ኲልክሙ” (በኹሉ ላይ ጸንታ የምትኖር የእግዚአብሔር ሰላም ዘወትር ከኹላችኊ ጋር ትኑር) ብሎ የስንብት መዝሙርን ዘመረ፤ ካህናቱም ይኽነን ቃል ሰምተው መሪር እንባን አለቀሱና ተሰነባበቱ፡፡
♥ በትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም መቅድም ላይ እንደምናነብበው ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ በተባለው ቦታ ተሰውሮ ጸዋትወ ዜማን ሲያስተምር እመቤታችን ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምን የብህንሳውን አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ እንዲመጡ አድርጋ ኤፍሬም ውዳሴዬን፤ ሕርያቆስ ቅዳሴዬን ነግራችኹት ቅዱስ ያሬድ በዜማ ይድረስልኝ ብላ ነግረውት በዜማ ደርሶታል፤ ይኽም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡
♥ ርሱም ጸዋትወ ዜማን ለደቀ መዛሙርቱ እያስተማረ መላእክት ዘወትር እየጐበኙት በጾም በጸሎት ተወስኖ በተጋድሎ ለኻያ ኹለት ዓመት ጸንቶ ኖረ፤ በመጨረሻም ጌታችንም ለቅዱስ ያሬድ ተገልጾለት:-
♥ “ኦ ፍቁርየ ቀዳሚኒ በከመ ሰመርኩ ትርአይ ሥርዐተ ስብሐተ መላእክት ዘበሰማያት ወአስተኀለፍከ ዘንተ ማሕሌተ ዲበ ምድር...” (ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዐተ ማሕሌት እንድታይና ወደ ምድርም አስተላልፈኽ ይኽነኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኊ ኹሉ እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሰው ሕፃናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊልና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልኻል” ብሎት ቃል ኪዳንን ሰጥቶት በክብር ዐረገ፡፡ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያውም ግንቦት ዐሥራ አንድ ነው፡፡
♥ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ያሬድን ነገር በአርኬው ላይ፦
“ሰላም ለያሬድ ስብሐተ መላእክት ለሕዋጼ
እንተ አዕረገ በልቡ ኅሊና መንፈስ ረዋጼ
ለትምህርተ መጽሐፍ ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ
በብዙኅ ጻማ ዘአልቦ ሑጻጼ
መልዕልተ ጒንደ ዖም ነጺሮ እንዘ የዐርግ ዕጼ”
(የመላእክትን ምስጋና ለመጐብኘት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ፈጣን ዐሳብን ወደ ልቡናው ያሳረገ ለኾነ፤ ጒድለት በሌለበት በብዙ ድካምም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ፤ ኰብልሎ ከኼደበት መጻሕፍትን ለመማር የተመለሰ ለኾነ ለያሬድ ሰላምታ ይገባል) በማለት ሊቁ ማሕሌታይን አመስግኖታል፡፡
♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሲያወድስ፡-
“ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤
ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት
ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት
ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ
ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ
ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ”፡፡
(የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡
የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን፤ እናንተም ይኽነን ሊቅ አወድሱት
እንኳን አደረሳችሁ ❤️
/channel/dnhayilemikael
#ቅዱስ_ቁርባን
#ምዕራፍ 3
#ክፍል 1
#ቅዱስ_ቁርባን_ለመቀበል_የሚደረግ_ዝግጅት
«ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል የሚደረገውን ዝግጅት በሁለቱ ከፍለን እንመለከተዋለን>>
👉ሀ/ ውሳጣዊ ዝግጅት /የመንፈስ ዝግጅት
👉ለ/ አፍአዊ ዝግጅት /የሚታይ ውጫዊ ዝግጅት
.
👉ሀ. #ውሳጣዊ_ዝግጅት:-የምንለው ቆራቢው ያለውን እምነት የመንፈሱን ዝግጅት ያመለክታል በቅዱስ ወንጌል ወደ ክርስቶስ ቀርበው በፊቱ ለቀረበለት የእምነት ልመና «እምነትሽ ታላቅ ነን
እንደወደድሽ ይደረግልሽ» /ማቴ 15-28/ የሚል መልስ ደጋግሞ ይመልስ እንደነበር ተጽፎ እናገኛለን፡፡
👉ስለዚህ አማኙ ወደ ቅዱስ ቁርባን ሲቀርብ በውስጡ የተዛባ እምነት እንዳይኖረው ሊጠነቀቅ ይገባዋል የምቀበለው አማናዊውን
በዕለተ ሐሙስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸውን በዕለተ አርብ በቀራንዬ መስቀል ላይ ለድህነተ ዓለም የቆረሰውን ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን ነው።
👉 በዚህ ለሠራሁትና ንስሐ ለገባሁበት ኃጢአት
ስርየት አገኛለሁ፣ ከሚመጣ ኃጢአት የምጠበቅበት ኃይል አገኛለሁ፣ ክርስቶስ በእኔ እኔ በክርስቶስ እኖራለሁ፣ የዘላለምን ድህነት አገኛለሁ፣ ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ እጠበቃለሁ፣ እያለ በፍጹም እምነት ሊዘጋጅና የተቀበለውን ከኃጢአት ርቆ በንጽህና
ሊጠብቅ በእምነት መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
👉 #አፍአዊ_ዝግጅት:- ይህ አይነት ዝግጅት መሠረቱና ምንጩ ከላይ የጠቀስነው እምነት ሆኖ አማኙ ለሚቀበለው መለኮታዊ ሥጋና ደም ያለውን እምነት አክብሮት የሚገልጽበትና እንደ ማንኛዉም ምድራዊ ማዕድ እንዳልቆጠረው ጭምር ነው ይህም በቤተክርስቲያኗ የሥርዓት የሚመሠክርበት ለምእመናኗ ተደንግጐ የምናገኘው ሲሆን አልፎ አልፎ አንዳንድ ሰዎች በዘልማድ የሚናገሩት ነገር እንደ ህግ ተወስዶ ተደባልቆ አማኙን ግራ ሲያጋባው ይስተዋላል በዚህ ክፍል ይህንን ለይተን በመግለጽ ለማሳወቅ እንወዳለን፡።
#ምዕራፍ 3
ክፍል 2
❖❖#ቅዱስ_ቁርባን_ለመቀበል_የሚያስፈግ_ግዴታና_ጥንቃቄ
ይቀጥላል .....
#ለሃሳብ_አስተያየት 👇👇
👉 @DnIsraelYeArsemaLije👈
ያለፈውን ለማግኘት
ምዕራፍ አንድ ክፍል 1 ለማግኘት
/channel/dnhayilemikael/4966
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👉 @dnhayilemikael 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆