dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት

"ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?"
ቅዱሱ አባት መለሰለት

"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው

ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው

ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል

ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው
በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

⛪️⛪️⛪️⛪️

ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል።

⛪️⛪️⛪️⛪️

"ፍቅር እንዴት መቆጣት እንዳለበት አያውቅም"
ቅዱስ ማር ይስሐቅ

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም ይፈርዱበታል።
⛪️⛪️⛪️⛪️

“የሚጾሙ የሚጸልዩና የሚተጉ ድቃቂ ሳንቲም እስካላስወጣቸው ድረስ በምንም ነገር ላይ የሚገኙ በችግር ላይ የሚሰቃዩትን ግን ዞር ብለው የማያዩ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ" ቅዱስ ባስልዮስ

⛪️⛪️⛪️⛪️

"እኛ መነኮሳት ነን:: እኛ የሠለጠንነው ሰዎችን ለመግደል ሳይሆን ምኞታችንን ለመግደል ነው" አባ ጴኤሜን

★ ★ ★
አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?
ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?
ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?
ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?
ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?
መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?
ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?
በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?
የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?
ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"እንግዲህ
💠 ከሀሜት፣
💠 ከሀሰት ጓደኝነት፣
💠የጌታን ስም በግብዝነት ከሚጠሩ፣ 💠ምንም የማያውቁትን ከሚያታልሉ 👉👉👉በመራቅ ለጥሩ ነገር እንቅና።

💠ማንም ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ
👉የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው።

💠 ማንኛውም በመስቀል ላይ መከራ መቀበሉን የማያምን
👉ዲያብሎስ ነው።

💠 ማንም የክርስቶስን ትምህርት ለራሱ እንደሚመቸው የሚያጣምም እና ትንሳኤና የመጨረሻ ፍርድ የለም የሚል
👉 ይህም የሰይጣን የበኩር ልጅ ነው።"

ቅዱስ ፖሊካርፐስ

   /channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

💒🌾❖ #ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ❖💒🌾

👉 በሃይማኖት መጽናት
👉 ወድቆ መነሳት ~ ንስሓ መግባት
👉 ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ
👉 በእግዚአብሔርም ሕግ መጽናት
👉 #ለእግዚአብሔር ሕግ መታመን
👉 ስንፍናን ማሸነፍ በጸሎት መትጋት
(ስንፍና ወደ ክህደት ይመራል) መዝ 13÷1
👉 በማየት በመስማት ከሚመጡ ነፍስን ከሚወጉ ዓለማውያን ነገሮች መራቅ
👉 ከቅዱሳን ሕይወት መማር በቃል ኪዳናቸውም መማጸን የጠላት ዲያብሎስንም የውጊያ ስልት ማወቅ
👉 ተስፋ ወደ መቁረጥ እንዳያደርስ ያለውን መንፈሳዊ ጸጋ ማወቅ ማክበር መጠበቅ " ከመንፈሳዊ ሀብት ባዶ ነኝ አለማለት " #እግዚአብሔር አለኝ ማለት
👉 ጥቂትም ቢሆን በየጊዜው ከበጎ ሥራ አለመለየት
👉 በፈተና መጽናት ትዕግሥትን መልበስ
👉 #እግዚአብሔርን /ሃይማኖትን/ በሥጋዊ ውጤት አለመመዘን
👉 ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ
👉 በቅዱስ ቁርባን ነፍስን መቀደስ
👉 የገሃነመ እሳትን መራራነት አለመዘንጋት
👉 የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም እያሰቡ መኖር
👉 #በእግዚአብሔር ቸርነት መታመን

🌾ቸርነትህና ምህረትህ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል #በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ
መዝሙር 23፡6

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ድንግልናቸውን እንደ ዐይን ብሌን ይጠብቁ ዘንድ ላላገቡ ደናግል ምከራቸው፣አስተምራቸው።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+++ መጻሕፍትን መስማት +++
.....
ብዙ በማዜም የምትታወቀው ቤተክርስቲያን የዜማዋ ያህል ብዙ መጻሕፍትን በንባብ ለምዕመናኗ በማሰማት ትታወቃለች፡፡ በተለምዶ ብዙ የሚዜም ስለሚመስለን ነው እንጂ ብዙ ለነፍስም ለሕይወትም የሚሆኑ ምክሮችን ተግሳጾችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ትምሕርቶችን በተለያዩ መንገድ ቀንብባ ታቀርባለች፡፡ በዚህ በኩል ግን ከማኅበረ ካህናት ጀምሮ እስከ ምዕመኑ ድረስ ይሄንን የመጻሕፍት ንባብ ያለመስማት ችግር አለ፡፡ ምክንያቶቹ ምን ምን ናቸው??
......
1ኛ ... በቅዳሴው ይሁን በሰዓታቱ ፥ በማኅሌቱም ሆነ በግብረ ሕማማቱ ፥ በስንክሳሩም ሆነ በድርሳኑ የሚነበቡ መጻሕፍትን እንደ እረፍት መስወጃ መቁጠር ነው፡፡ ተዚሞ ተዚሞ ንባቡ መቀመጫና ማረፊያ ሆነ ፤ ብዙ የቆመና የጮኸ ሰው ቢቀመጥና ቢያርፍ ባይገርምም ... አርፎና ተረጋግቶ መጻሕፍቱን ከመስማት ይልቅ ወሬ ማውሪያና መቦዘኛ መሆኑ የተለመደ ነው፡፡ በካህናቱና ሊቃውንቱ ላይ ይሔ ጠባይ መታየቱ ብዙ ባይገርምም ከምዕመናኑም ዘንድ እየተለመደ መምጣቱ አሳሳቢ ነው፡፡ እንደምሳሌ በጾመ ማርያም በሚቀደሰው ቅዳሴ ማርያም የንባብ ጊዜ ብዙ ሰዎች ሲቀመጡ ማየት እየተስተዋለ ነው፡፡
....
2ኛ የመጻሕፍቱ ንባብ ሳያልቅ አቋርጦ የዜማውን ክፍል መጀመር ፡፡ ይሄ በብዛት በቅዳሴ ሰአት የሚታይ ሲሆን በተለይ ዲያቆናቱና ንፍቁ ካህን የሚያነቧቸው በዕለቱ በግጻዌው በታዘዙት የጳውሎስ ፣ የሐዋርያት መልዕክታት እና ግብረ ሐዋርያት የንባብ ክፍሎች ላይ የተጀመረው ንባብ ሳይጠናቀቅ ወደቅዳሴው የዜማ ክፍል የመሸጋገር ነገር በብዛት ይስተዋላል፡፡ ይሄ የመጣው ሽርፍራፊ ደቂቃዎችን ለመቆጠብ ተብሎ ነው ፥ ነገር ግን ዕለቱን የተመለከተው የእግዚአብሔር መልዕክት እና ሐሳብ ተቀባዮቹ ጋር ሳይደርስ ይቋረጣል፡፡ መፍትሔውም ከልክ በላይ የተቅለጸለጹ ዜማዎችን ትቶ በምልክቱ መጮህ ቅዳሴው በተፈለገው ሰአት እንዲያልቅና ንባባቱ ለሰሚው ሳይቆራረጡ እንዲደርሱ ይሆናል፡፡
......
ሌላው ትልቅ ችግር አለማስተዋል ሲሆን ... ውዳሴ ማርያም ሲተረጎም ፣ የፍሬ ቅዳሴ ንባባት ላይ በተመስጦ ካለማዳመጥ የተነሳ የተፈለገውን መልዕክት ምዕመናን ጋር ሳይደርስ ይቀራል

መፍትሔው ... ለሰዉ ስለሚነበቡት ምንባባት አስፈላጊነት በመንገር ለዚህ የተዘጋጀ ንቃተ ሕሊና መፍጠር ነው፡፡፡ /channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ማርያማዊ ብሶት +

"ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?"

ድንግል ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ የተናገረችው የብሶት ንግግር ይኼ ብቻ ነው:: "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?"

ድንግሊቱ እንዲህ ያለችው ምን ቢደርስባት ነው?

ጌዴዎን እስራኤል መከራ ሲጸናባቸው "ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን?" ብሎ ነበር:: መሳ. 6:13

ኢያሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ :- ዋይ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ በአሞራውያን እጅ አሳልፈህ ትሰጠን ታጠፋንም ዘንድ ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? ብሎ በብሶት አልቅሶ ነበር:: ኢያሱ 7:7

ሙሴም የሕዝቡ አመፅ ሲያስጨንቀው ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፦ ለምን በባሪያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? ብሎ ተማርሮ ነበር:: ዘኍ. 11:11

ድንግል ማርያም "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ብላ የብሶት ቃል የተናገረችው ግን መከራ ሲደርስባት አልነበረም::

ወደ ግብፅ ስደት እንድትወጣ ሲነገራት "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" አላለችም:: ግርፋቱንና ሕማሙን ስታይም ኀዘንዋን ዋጥ አድርጋ ቆመች እንጂ "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" አላለችም::

ድንግል ማርያም "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ያለችው ልጅዋ ለሦስት ቀናት ከዓይንዋ በራቀበት ወቅት ነበረ:: "እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን፡ አለችው" ሉቃ. 2:48

ድንግሊቱ ለምን እንዲህ አደረግህብኝ ያለችው ስለ ሌላው መከራዋ ጊዜ ሳይሆን ክርስቶስ ከእርስዋ ዘንድ ስላልነበረባቸው ቀናት ነበር:: እንደርስዋ መንፈሳዊ ስትሆን "ጌታ ሆይ ለምን አስጨነቅኸኝ?" የምትለው እርሱ ከአንተ የራቀ መሆኑ ሲሰማህ ብቻ ነው:: "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ" "አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ?" እያልክ የምትጮኸው እግዚአብሔር ከአንተ የራቀ ሲመስልህና የተቀደሰው ማርያማዊ ብሶት ሲሰማህ ነው:: መዝ. 21:1፤10:1

እርሱ ከአንተ ጋር ከሆነ "በሞት ጥላ መካከል እንኩዋን ብትሔድ ክፉውን አትፈራም" ከአንተ የተለየ ሲመስልህ ግን "ጌታ ሆይ ምን አደረግህብኝ" ብለህ በማርያማዊ ብሶት ትጮኻለህ::

ከእርሱ ጋር ሆነህ መከራን መቀበል አይከብድህም:: መሰደድም አያስጨንቅህም:: እርሱ ከአንተ ዘንድ ከጠፋ ግን ብርሃንህ ምርኩዝህ ኃይልህ ጉልበትህ ሁሉ ከአንተ ዘንድ የሉምና ልትጸና አትችልም::

ዝምተኛዋን ድንግል ማርያም በብሶት ማናገር የቻለ አንዳች መከራ አልነበረም:: በበረሃ ከልጅዋ ጋር ከተንከራተተችበት ጊዜ ይልቅ ግን ያለ ልጅዋ ያሳለፈቻቸው ሦስት ቀናት "ልጄ ሆይ ለምን ይሄን አደረግህብኝ" ብላ እንድትጮህ አደረጓት::

ድንግል ሆይ ከአንቺ ዘንድ ለሦስት ቀን የተሰወረው ጌታ ከእኔ ሕይወት ከራቀ ዓመታት እንዳለፉ እያየሽ ይሆን? "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህበት? ነፍሱ ተጨንቃ እየፈለገችህ አይደለምን?" የማትይው ስለምንድን ነው?

ለሌላው መከራዬ የምጮኸውን ያህል ከልጅሽ መለየቴ ተሰምቶኝ በማርያማዊ ብሶት እንዳልጮህ በኃጢአት ብርድ ተይዤ መንፈሳዊ ሙቀት በእኔ ዘንድ የለም:: የምበላው የምለብሰው ሲጎድል እንጂ አምላኬን ሳጣ የሚሰማኝ ሰው አይደለሁም:: እኔ ባልጠይቅሽ እንኳን እንደ ቃና ሙሽሮች ጉድለቴን አይተሽ የማትለምኚልኝ ለምንድን ነው? ልጅሽ ወደ ወይን እንዲለውጠው ከእኔ ሕይወት በላይ ውኃ ውኃ ያለ ነገር ከወዴት ሊመጣ? ከልቤስ በላይ የድንጋይ ጋን ከየት ይገኛል?

"ንዒ ማርያም ለዕውር ብርሃኑ
ወንዒ ድንግል ለጽሙዕ አንቅዕተ ወይኑ
ኦ ኦ ትኃድግኒኑ ኦ ኦ ትመንንኒኑ
ኀዘነ ልብየ እነግር ለመኑ"
"የዕውር ብርሃኑ ማርያም ሆይ ነይ
ለተጠማው ወይን የምታፈልቂለት ማርያም ሆይ ነይ
ወዮ ትተዪኝ ይሆንን? ወዮ ትንቂኝ ይሆንን?
የልቤን ኀዘን ለማን እነግራለሁ? (መልክአ ኤዶም)

ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪ ተክለ ማርያም

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 7 2015 ዓ.ም.

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ፍልሰታ"
"ሕጻኑም ወጣቱም ወንዱም ሴቱም ዕድሜው የገፋውም ሁሉም በፍቅር የሚጾሟት፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔትና በረከት የሚታፈስባት፡ ፍቅረ እግዚአብሔር በሰው ልቡና የሚሰለጥንባት ፈሪሃ እግዚአብሔር የሚያይልባት፡ የንሰሐና የምህረት ጾም ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡ በዓለም ያሉ ወደ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ያሉ ወደ ገዳማት የሚገሰግሱባት ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡"

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸
🔸🔹🔸
     🔸
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ወልድኪ መድኃኔዓለም ሥጋ ዚኣኪ ዘለብሰ።
በዐውደ ጲላጦስ ተወቅሰ መድኃኔዓለም።

ሊቃውንት ፍቅሩን የማዳን ሥራውን ቸርነቱን በቅኔያቸው በትርጓሜያቸው በማኅሌታቸው ይገልጻሉ። ሊቁ በሞት የተገለጠ ፍቅር እንዳሉት። ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ተሰቀለ። እውነት በአደባባይ ተሰቅሎ ሁሉ አየው።

ጌታችን ሆይ በቸርነትህ በቀኝህ ከሚቆሙት ደምረን።

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+• የሕይወት ስንክሳር •+

የሕይወት ስንክሳር ሦስት ታላላቅ ክፍሎች አሏት:- ትላንት፥ ዛሬ እና ነገ::


1/ ትላንት
ትላንት ስንል የምናወራው ታሪክን ነው:: ትላንትን ከትውስታ ወይም ከማኅደር እየመዘዝን "እንዲህ ሆኖ ነበር" እንላለን:: ከዚያ ባለፈ ግን ትላንት የተባለው የሕይወት ክፍል ላይ የተጻፈው አንዴ ሆኗልና ሊቀየር የማይችል ነው:: መለስ ብለን ልንፍቀው እና እንደ አዲስ ልንጽፈውም አይቻለንም:: ብልህ ከሆንን ተምረንበት ዛሬያችንን ያማረ፤ ነጋችንን የሠመረ እናድርግበታለን::

2/ ዛሬ

ዛሬ ደግሞ ከትላንት እና ከነገ መካከል ያለ እንቆቅልሽ ነው:: ዛሬን እንደ ትላንት ታሪክ ልንለው አንችልም:: አሁን ያለ ስጦታ ነው:: ዛሬን ጣፋጭ እንዳየ ሕጻን ልጅ ፈንድቀን መጠቀም ነው:: ዛሬያችን ነገ ላይ "ትላንት" ስለሚባል አሳምረን መጻፍ ነው:: ዛሬያችን የመዳን ቀን ነው:: ኃጢያታችንን አስፍቀን፥ ክርስቶስን እንደ ሸማ ለብሰን አጊጠን "ድሮ እንዲህ ነበሩ፤ ዛሬ ግን እንዲህ ሆኑ!" መባል የምንችልበት ገጸ በረከት ነው::

2/ ነገ

ነገ ግን ምስጢር ናት:: የነገው ገጾች ገና አልተጻፈባቸውም:: ነገን "እንዲህ ነው" ብለን በእርግጠኛነት አንናገረውም:: ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል? ማን ሞቶ ማንስ ተወልዶ እንደሚያድር በእርግጠኛነት ሊናገር የሚችለው ማን ነው? የዓለም ታሪክ አይወድቁም የተባሉ ሲወድቁ፥ ብርቱ ናቸው የተባሉ ሲደቅቁ፥ ሺህ ዓመት ይንገሱ የተባሉ ሺህ ሰዓታት ሳይሞላቸው ከንግሥና ሲወርዱ፥ ይደልዎ ተብለው የተሾሙ ሲዋረዱ፥ ተወርውረው የተጣሉ ተፈልገው ሲከብሩ አሳይቷል:: ትላንት በታሪክ ልሳን ውስጥ ሕያው ናት፤ ዛሬ ደግሞ ስጦታችን ነች:: ነገ ግን ያለችው በፈጣሪ መዳፍ ብቻ ነው:: ትላንት በማለፏ ትነገራለች፥ ዛሬን እንኖራለን (ወይም እንሞታለን - ማን ያውቃል?) ነገ ግን ወደ ቀኝ ትታጠፍ ወደ ግራ ከፈጣሪ ውጪ የሚያውቅ ማንም የለም::

ይህ ሁሉ የጊዜ ግስጋሴ ግን ማብቃቱ አይቀርም:: ሊቃውንት "ጊዜ ሁሉን ያስረጃል፥ አምላክ ግን ጊዜን ያስረጃል" የሚሉት ለዚሁ ነው:: ትላንትን እያስቆጠረ፥ ዛሬን እያሳለፈ፥ ነገን ተስፋ እያስደረገ የሚነጉደው ጊዜም ተራው ሲደርስ በተራው ያረጃል:: ይህ ሲሆን የሕይወት ስንክሳራችንም ያበቃል፤ መጽሐፉም ይዘጋል::

ትላንታችን ላይ ምን ተጽፏል? ዛሬያችን ላይ ምን ለመጻፍ ተዘጋጅተናል? ነጋችንስ ምን ይል ይሆን? የሕይወታችን ስንክሳር ተጠናቅቆ በፈጣሪ ፊት ሲነበብ ምን ይናገር ይሆን?

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

​​እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!

መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤልና አገልግሎቱ በጥቂቱ

✍ ዑራኤል የሚለው ስም "ዑር"እና ኤል ከሚለው ሁለት ቃላት የተመሰረተ ነው ። ትርጉሙም ብርሃነ ጌታ አምላክ  ብርሃን ነው። ማለት ነው።

✍ ቅዱስ ዑራኤል ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ መብረቅና ነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበቁ ነጓድጓድ ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። (መጽሐፈ ሄኖክ ፮፥፪)

✍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ እየመራ፤ ከእስራኤል ወደ ግብጽ ከዚያም ከእመቤታችን ጋር በሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው።

✍ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለበት ጊዜ፥ክቡር ደሙ በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን ነሳንስ የረጨው እሱ ነው።

✍ ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ልቦና ያጠጣው፥ጥበብን ማስተዋልን የሰጠው የጠፉ መጽሓፍት በቃሉ አስታውሶ እንደገና ያጻፈው የረዳው መልአክ ነው።(ዕዝ፲፫፥፴፱)

✍ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ትዕዛዝ ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ህይወት ስላጠጣቸው ነው።

✍ በዓላቱም በዓመት 3ናቸው።
፩...ጥር። 22 በዓለ ሲመቱ፤
፪....መጋቢት 27 የጌታችንን ደም በዓለም የረጨበት፤
፫...ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ።

✍ በጸሎቱ የተማጸነ ከእግዚአብሔር አምላክ በረከትን ፣ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ ጠባቂ ና የዋህ መልአክ ነው።በተለይም ህጻናትን የሚጠብቅ የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ ፥ኃጢአተኞች ካሉበት ቦታ እኔን ላከኝ እያለ አምላኩን የሚማጸን አዛኝ የዋህ መልአክ ነው።

✍ ይህ አለም በአማላጅነቱ አምኖ በእምነት ጸበሉን ቢጠጣ ፥ዝክሩንም ቢዘክር ከክፉ በሽታው እንደሚድን፤ እንደሚፈውሰው ቃል ኪዳን ተሰጥቶታል ።

✍ ቅዱሳን መላዕክት እግዚአብሔርን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራሉ ከመከራም ያድኑዋቸዋል።(መዝ ፴፫÷፯) የአባታችን የጠባቂያችን የአማላጃችን የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል ቃል ኪዳን አይለየን።

   ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
  ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✔️ #_የጽዋ_ማኅበር_ምንድነው???

#ለምንድነው_ከቤተ_ወደ_ቤት_እያዘዋወሩ_የሚያደረጉ ??
✔️ #የመሶበ_ወርቅና_የጽዋው_ምስጥር_ምንድነው???

#_የጽዋ_ማኅበር_ምንድነው???

✔️👉➕ #የጽዋ_ማኅበር ፡"ክርስቲያኖች በእግዚአብሔርና በቅዱሳን ሰዎች ስም
እየተስበስቡ በቤተክርስቲያን ወይም በየቤታቸው
የሚፈጽሙት የቅድስና ሥራ ነው።
✔️ይህም እግዚአብሔር
በመካከሌቸው እንዳለ በማመን የሚከውኑት የመንፈሳዊ በረከት ነው፡፤ ይህንንም ከአንድ ከርስቲያን ቤት ወደhላኛው አያዘዋወሩ ያደርጉታል።

#ለምንድነው_ከቤተ_ወደ_ቤት_እያዘዋወሩ_የሚያደረጉ??

✔️#መነሻውም 👉አንደኛ #በዘመነ_ብሉይ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በደጉ አባት አብርሃም ቤት
ተገኝቶ ሣራ የሠራችውን ተመግቦ ቤታቸውንም ባርኮ
የተዘጋውን በር ከፍቶ የሣራን ማኅፀን ከፍሬ አብቅቶ ከዚ 👉ቀጥሎ ደግሞ በመላእክቱ አድሮ በኰጥ ቤት ተገኘ፡ ሎጥንህ ከታካቅ መከራ መላእክቱ አጁን ይዘው አወጡት።

✔️👉ዛሬም ክርስቲያኖች መሶቡንና ጽዋውን በመያዝ በየወሩ በየቤቱ አየተሰበሰቡ ይህንን ያስባሉ ፡፤ {ዘፍ ፲፰ (18)

✔️👉 ✔#የመሶበ_ወርቁና_የጽዋው_መግባት የእግዚአብሔር መግባት ምሳሌ ነው
✔️ምሥጢሩን አንመከከተዋከን።👇
ሐእብርሃምና ለሣራ አንዲሁም ለሎጥ የተደረገው የአግዚአብሐርን ቸርነት ጽዋው በገባበት ቤትም ይደረግ ዘንድ የምእመናን ምኞትና ጸሎት ነው።

#✔️👉 #ሁለተኛ_በዘመነ_ሐዲስ_በወንጌልም_ተጽፎ_እንደምናገኘው
✔️ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው በሚያምኑት ቤት እየገባ እየተመገበ ቤታቸውንም ይባርክላቸው ኃጢአታቸውንም ይደመስስላቸው ነበር፡
👉 #ለምሳሌ
✔️በቢታንያ ሀገር በለምጻሙ በስምዖን ቤት (ማቴ ፳፰፡፮ (26፡6)
✔️በኢያሪኮ አገር በቀራጩ በዘኬዎስ ቤት (ሉቃ ፲፱፡፩-፲( 19፡1 - 10)
✔️የማርያምና የማርታ ወንድም በሆነው በአልአዛር
ቤት (ሊቃ ፲፡፴፰-፵፪ ( 10፡38-42)

👉✔️➕ #ዛሬም ምእመናን ኃጢእተኞችን የማይጸየፍ ጌታ በቤታቸው ይገባ ዘንድ መሶበ ወርቁንና ጽዋውን ይዘው ባሉበት ቤት ሁሉ በረከት
ይገባበታል ፡፡

👉"እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳኳሁ ማንም ድምፄን ቢስማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱ ጋር እራት እበካhሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል ።” ራዕ ፫፡፳ (3:20)

👉➕✔️እንዲህ ያለን ጌታ ምእመናን ይህን ምሥጢር በሚገልጽ የጽዋ ማኅበር ይዘክሩታል።

➕👉 #ዘከረ የሚከው የግእዝ ቃል
#አሰበ ማለት ነው።
✔️በዚህም ረቂቅ ምሥጢር የሚታሰበው ቀጥሎ ያለው ነው።

#የመሶበ_ወርቅና_የጽዋው_ምስጥር_ምንድነው???

✔️👉➕ #መሶበ ወርቅ፡- መሶበ ወርቅ በውስጡ ኅብስት ይደረግበታል👉 የዚህ ምሥጢሩ መሶበወርቅ የእመቤታችን ምሳሌ ፡
👉 መሶቡ የወርቅ መሆኑ የእመቤታችን ንጽሕናን የሚያመከት ነው።
✔️ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር ፴፬ ቁጥር ፪
( 44፡9) እመቤታችንን ንግሥቲቱ ብሎ የወርቅ ክብሰ
ተጎናጽፋና ተሸፋፍና በቀኝህ ትቆማለች ብሎ
እንደመሰከረው።

👉✔️✔️ #ክርስቲያኖች መሶባቸውን አጎናጽፈው
ሽፍንፍን አድርገው ይይዙታል፡፤
✔️ምክንያቱም ቅድስት
የሆነች እመቤታችን ክብር ይገባታል።
✔️በመሶበ ወርቁ ውስጥ የሚደረገው ኅብስት “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ " ያለ
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስ ምሳሌ ነው። (
ዮሐ፡፮÷፴፭) ይህንንም አክብሮ መያዝ ብቻ ሳይሆን ይሳለሙታል ይስሙታል ክብሩ ለእግዚአብሔር ነው።

✔️✔️✔️✔️✔️ #ጽዋ ✔️✔️✔️✔️😘
ጽዋ፡- የጽዋውም ምሥጢር እንደ መሶበ ወርቁ አንድ ነው።
✔️ #ጽዋው የእመቤታችን ምሳኤ ነው፡፡
✔️ በውስጡ ያለው ጸበል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የደሙ ምሳሌ ነው።

👉 ከብር ይግባውና መሶበ ወርቁና ጽዋው
የኅብስቱና የጸበሉ መያዣ የእመቤታችን መሆኑ ጌታችን ሥጋንም ደምንም የተዋሐደው ከእርሷ ብቻ ነውና።

✔️ምእመናንም ይህን በመረዳት በጽዋ ማኅበራችን የጌታችን መከራውን በቀራንዮ ያደረገውንም ሞቱን እያሰብን ይህን ዴግ ሥራ እናደርጋለን ፡፤

👉➕✔️ዋና ዓላማው ይህ ሆኖ ሳለ
በመሰባሰባችንም የተቸገሩ፣የተራቡ፣ የተጠሙ ነዳያንን እናስባከን፡፤

✔️ #ይህም_ሊሆን_እንደሚገባ_ቅዱስ_ጳውሎስ_በመክእከቱ_የሥጋ_ወደሙንና_የጽዋ_ማኅበር1መሰባሰብ_እንዳስተማረን_ልናደርገው_ይገባል።

✔️፩. #የእግዚእብሔርን_ማኅበር_እንዳንንቅ፡- ማኅበሩ እግዚእብሔር የሚገኝበት መሆኑን እንድናውቅ፡ ስዚህም ነው የእግራችንን ጫማ የምናወhቀው።

✔️፪. በማኅበራችን ጊዜ ከልክ ያለፈ ድግስ እንዳናደርግ የሌላቸውንም ሰዎች እንዳናሳፍር።

✔️፫. ከተቸገሩ ከተራቡ እንድናስብ፤

✔️፬.ከልክ በላይ እንዳንበላና እንዳንጠጣ። በተለይ
ስካር ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
ሌሎችም ብዙ መልእክቶች ያስተምረናል።

✔️የሥጋ ወደሙን
መክእከት ከጽዋ ማኅበሩ በመለየት ፩ቆሮ ምዕራፍ ፲፩
ከቁጥር ፲፯ ጀምሮ እስከ ፴፬ ያከውን (1ቆሮ 11፡17-34)
ጠንቅቆ ማንበብ ያስፈልጋል።

የጽዋው በታችን መግባት የእግዚአብሔር ቤታችን መግባት ከሆነ በተቻለን መጠን የጽዋ ማህበር እንግባ መልእክቴ ነው

ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✝ ምክረ አበው ✝

#ተግሳጽ ነፍስን በመልካም ምግባር ለማጠናከር ምክንያቷ ነውና ተግሳጽን ውደድ።
#በሌሎች ላይ እርማትን ከመሰንዘር በፊት የራሳችንን ስህተት ማረም ይጠቅማል ።
#አንዳንድ ስዎች ነጻነት የሚለውን ቃል የሚረዱት የወደዱትን ሁሉ የመፈጸም ፈቃድ አድርገው ነው። ሰዎች አብዝተው ራሳቸውን የኃጢአት ባሪያ እያደረጉ በመጡ መጠን ህጉን ለራሳቸው እንዲስማማ አድርገው ሊተረጉሙ ይዳዳቸዋል። እንዲህ አይነት ሰዎች ውጫዊ ነጻነትን የሚጠቀሙበት በተሳሳተ መንገድ ነው።
(ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ)

#ሞትን አትፍራ ሀጢአትን ፍራ።
#ስለ መተላለፋችን ምንም አይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር።
#አለም አንተን ሳትንቅህ አስቀድመህ ናቃት።
(ቅዱስ አትናቴዎስ)


please share✝✝✝@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን
ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ።


💠#በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

💠በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

💠ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ  በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ዝምታ

አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከቃላት ይልቅ ውጤታማ፣ ይበልጥ ተገቢና እጅግ ጠቃሚም ነው። ወይም ደግሞ ቢያንስ - ቢያንስ ተናግሮ ከሚመጣ ጉዳት ይልቅ ሳይናገሩ የሚመጣ ጉዳት ይሻላል። በዝምታ ውስጥ ጥበብና ጥንካሬ ከመኖራቸው በተጨማሪ ክብርና ሞገስም አሉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ይናገር ዘንድ እኛ ዝም እንላለን፣እኛ ልንናገር ከምንወደው ከማንኛውም ነገር የበለጠ የእግዚአብሔር ቃል እጅግ ኃያል ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ የተናገረው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው! «እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤እናንተም ዝም ትላላችሁ. . » ዘጸ 14፥14።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በዝምታ ቆይቷል። በዚያን ጊዜ እርሱ  አፉን አልከፈተም ራሱንም አልተከላከለም። ጌታ ዝምታን በመረጠ ጊዜ ጲላጦስ «ይህን ጻድቅ ሰው የምወነጅልበት ምንም ዓይነት ምክንያት አላገኘሁም» በማለት ተናግሮ ነበር፡፡

ዝምታ ትርፍ አስገኚ ይሁን እንጂ የተወሰነ መመሪያ አይደለም፡፡ ወርቃማው መመሪያ፡- ሰው ሊናገር የሚገባው በትክክለኛው ጊዜ መሆኑና ዝም ማለት የሚገባውም ዝም ማለት በሚገባው ትክክለኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

ሰው ዝም ሲል ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲነጋገር ስለሚፈቅድ በእርሱ ፈንታ ጌታው እንዲናገር ይጠይቃል ማለት ነው፡፡

(አቡነ ሽኖዳ ሣልሳዊ - የሕይወት ልምድ ገጽ 14 - በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)
                  ⌲        ♡   
               ˢʰᵃʳᵉ       ˡᶦᵏᵉ  
@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? +

(ጊዜ ወስደው ያንብቡት አያጥር ነገር ታሪክ ሆኖ ነው)

አንድ ግብፃዊ መነኩሴ ለገዳሙ መርጃ የእጃቸው ሥራ የሆኑትን ቅርጫቶች ሊሸጡ ወደ እስክንድርያ ለመጓዝ በጠዋት ተነሡ፡፡

በመንገድ ላይ ታዲያ ትልቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማድረግ የሚጓዝ ሕዝብ ገጠማቸው፡፡ ሟቹ ዝነኛ አረማዊ ገዢ ሲሆን በዘመነ ሰማዕታት በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለ ሰው ነበር፡፡ አሁን ዕድሜ ጠግቦ ሞቶ ነው፡፡ ቀኑ ውብ ፀሐያማ ቀን ነበርና የሀገሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ገዢያቸውን እየቀበሩ ነው፡፡

ይህንን ያዩት መነኩሴ ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ ገዳም ሲመለሱ አሳዛኝ ዜና ሰሙ፡፡ ለስድሳ ዓመታት በበረሃ በብሕትውና ቅጠልና የበረሃ ፍሬ ብቻ እየበላ የኖረ ባሕታዊ በዚያች ዕለት በጅብ ተበልቶ ሞቶ ነበር፡፡
መነኩሴው እጅግ ጥልቅ ኀዘን ውስጥ ሆነው እንዲህ ሲሉ አሰቡ ፦

‘በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለው አረማዊ ሰው በታላቅ ክብር ታጅቦ ሲቀበር ሕይወቱን ሙሉ በጾምና በጸሎት ፈጣሪውን ያገለገለው ባሕታዊ በጅብ ተበልቶ የተዋረደ አሟሟት ሞተ፡፡ይህ እንዴት ዓይነት ፍርድ ነው? እግዚአብሔር ከመልካምነቱ ሁሉ ጋር ኢፍትሐዊ ነገሮች ሲሆኑ ዝም ብሎ ይፈቅዳል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች የፈጣሪን መኖር ይጠራጠራሉ፡፡ እኔም ፍርዱን እንዲገልጽልኝ መጸለይ ይኖርብኛል’ አሉ፡፡

ከዚያች ቀን ጀምሮ መላልሰው ወደ ፈጣሪ ‘’ፍርድህን ግለጽልኝ’ ብለው ደጋግመው ጸለዩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ እግዚአብሔር ፍርዱን እንዲህ ገለጠላቸው፡፡

ከሳምንታት በኋላ እንደተለመደው ወደ እስክንድርያ የሦስት ቀን ጉዞ ሊሔዱና ቅርጫታቸውን ሊሸጡ ተነሡ፡፡መንገዱን እንደጀመሩ ድንገት አንድ ወጣት መነኩሴ ወደ እርሳቸው ሲመጣ ተመለከቱ፡፡

‘’አባቴ ይባርኩኝ’

‘እግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ’

‘አባቴ ወዴት ይሔዳሉ?’ አለ ወጣቱ መነኩሴ

‘ወደ እስክንድርያ ቅርጫቴን ልሸጥ እየሔድኩ ነው’ አሉት

‘ጥሩ አጋጣሚ ነው አባ እኔም ወደዛ እየሔድኩ ነው’ አለ በትሕትና

‘ጎሽ አብረን እንጓዛለና’ አሉ አባ፡፡ ወጣቱ መነኩሴ ከእጃቸው ሸክማቸውን ተቀበለ፡፡ ጥቂት እንደሔዱ እንዲህ አላቸው፡፡

‘አባ ያው እንደሚያውቁት እንደ መነኮሳት ሥርዓት ጉዞ ስንጓዝ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር አለብን አይደል?’’ አላቸው፡፡

‘ልክ ነው ልጄ’ አሉት

‘እንግዲያውስ ለሦስት ቀን አብረን ስንጓዝ እስክንድርያ እስክንደርስ ድረስ አንዲትም ቃል አንነጋገር ፤ ምናልባት በሦስቱ ቀን ጉዞአችን ለማየት የሚከብድ ነገር እንኳን ሳደርግ ቢያዩኝ ላይናገሩኝ ላይፈርዱብኝና የአርምሞ ቃልኪዳንዎን ላያፈርሱ ቃል ይግቡልኝ’ አላቸው፡፡

አባ እየተገረሙ ‘እሺ በሕያው አምላክ እምላለሁ ልጄ አንዲትም ቃል አልተነፍስም’ አሉት፡፡
ሁለቱ አባቶች በጠዋቱ የአርምሞ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ቀትር ላይ ወደ አንዲት መንደር ደረሱ፡፡

ሁለት ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት አዩአቸው፡፡ ከሁለቱ አንዱ ‘ቅዱሳን አባቶች’ እያለ ወደ እነርሱ ሮጠ ‘ቅዱሳን አባቶቼ ፀሐዩ እስኪበርድ ድረስ እባካችሁን እኛ ቤት አረፍ በሉ’ አላቸው፡፡ ፀሐይዋ እየከረረች ስትመጣ በበረሃማዋ ግብፅ ጉዞ በጠዋትና ማታ እንጂ በቀትር ስለማይታሰብ ጉዞአቸውን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት በክብር ተቀብለው ከቤታቸው አስገቧቸው፡፡እግራቸውን አጠቧቸው፡፡ በቤታቸው ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ የከበረ እጅግ ውድ የብር ሰሐን ላይ ምግብ አቀረቡላቸው፡፡ መነኮሳቱ በዝምታ ተመገቡ፡፡ ከዚያም ትንሽ አረፍ የሚሉበት ክፍል ተሠጣቸው፡፡

ትንሽ እንደቆዩ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ወደ ምግብ ማብሰያው ክፍል ገብቶ ይበሉበትን ውድ የብር ሳህን በልብሱ ደብቆ ይዞት መጣና አባን ጠቅሶ ጠራቸው፡፡ ተሰናብተው ከወጡ በኋላ አባ በቀሚሱ ውስጥ የደበቀውን የብር ሳህን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ መናገር ባይችሉም በልባቸው እንዲህ አሉ ፦

‘እነዚያ ደግ ወጣቶች በክብር ተቀበሉን ፤ እግራችንን አጥበው መገቡን፡፡ እውነት ለውለታቸው ምላሹ ውዱን ንብረታቸውን መስረቅ ነው?’’ ብለው አዘኑ፡፡

ጥቂት እንደተጓዙ የመስኖ ውኃ ወደተከማቸበት አንድ ድልድይ ጋር ደረሱ፡፡ ውኃውን ሲሻገሩ ታዲያ ወጣቱ መነኩሴ በብር ሳህኑ ላይ ካማተበበት በኋላ ወደ ወንዙ ወረወረው፡፡

አባ እንዲህ ብለው አልጎመጎሙ ፦
‘’እንዴት ያለ ነገር ነው? ሳህኑን የሰረቀው ሊወረውረው ነው? እዚያው አይተውላቸውም ነበር?’’ አሉ አርምሞአቸውን ሊያፈርሱ አይችሉምና ዝም አሉ፡፡

ሲመሽ ወደ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ቤት ደረሱ፡፡ እንደ ቀኖቹ ወጣቶች እነዚህም በክብር እግር አጥበው አስተናገዷቸውና ማረፊያ ሠጧቸው፡፡ ባልና ሚስቱ የሁለት ወር ሕፃን ልጅ ነበራቸው፡፡ በጠዋት ሲነሡ ወላጆች ሳይነሡ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ሔዶ የተኛውን ሕፃን ገደለው፡፡ አባ ሊያስጥሉት ቢሉም አልቻሉም፡፡ እየጎተተ ይዞአቸው ወጣ፡፡ ‘ጌታ ሆይ ምን ዓይነት ርጉም ነው ንጹሑን ሕፃን ገደለው እኮ’ እያሉ እንባቸው ወረደ፡፡ ምንም እንኳን አንጀታቸው በኀዘን ቢኮማተርም በመሓላ የገቡበትን አርምሞ አፍርሰው ከግዝት ላለመግባት አንዲት ቃል ግን አልተናገሩም፡፡

በቀጣዩ ቀን ሁለቱ መነኮሳት ወደ አንድ መጠጥ ቤት ደጅ ደረሱ ፤ የጭፈራው ድምፅ ከሩቅ ይሰማል ፤ ሰካራሞቹ መነኮሳቱን ሲያዩ ‘ቅዱሳን’ እያሉ ተሳለቁ፡፡ በሰካራም አንደበት የሚናገረው ዲያቢሎስ ነው ብለው ዝም አሉ፡፡

ወጣቱ መነኩሴ ግን ወደ መጠጥ ቤቱ አቅጣጫ በግንባሩ ተደፋና ሦስት ጊዜ ሰግዶ ተሳለመው፡፡
ጥቂት እንደሔዱ አንድ ያረጀ ፤ መስቀሉ ከጉልላቱ የተነቀለ በርና መስኮት የሌለው ቤተ ክርስቲያን አዩ
ወጣቱ መነኩሴ ድንጋዮች ለቀመና አማተበባቸው ወደ ፈረሰው መቅደስም ወረወረው

አባ ይሄን ጊዜ ፦ መጠጥ ቤቱን ተደፍቶ ተሳለመ ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ ድንጋይ ወረወረ ! ብለው በዝምታ ተንጨረጨሩ ::

አሁን ሦስተኛው ቀን ሞላ በጠዋቱ ወደ አንድ በሸንበቆ የተሠራ ቤት ደረሱ እናታቸው የሞተችባቸውና በአጎታቸው እርዳታ ብቻ የሚኖሩ አምስት ሕፃናት ተቀምጠው ያለቅሳሉ፡፡ አባ በርኅራኄ ለሕፃናቱ ምግብ ሠጧቸው፡፡ እሳቸው ከሕፃናቱ ጋር ሲነጋገሩ ወጣቱ መነኩሴ ደሞ የሸንበቆውን ቤት በእሳት እያያያዘ ነበር፡፡ ሕፃናቱ ከሚነደው ቤት ሮጠው አመለጡ፡፡

‘ይህን ነፍሰ ገዳይ እስከመቼ እታገሰዋለሁ’ ሲሉ የቆዩት አባ እስክንድርያ ደርሰዋልና በምሬት መናገር ጀመሩ
‘’እስቲ ንገረኝ ከዚህ በኋላ ዝም ልልህ አልችልም፡፡ መልስልኝ አንተ ሰው ነው ወይስ ሰይጣን ነህ?’

‘ምነው አባ ምን አጠፋሁ?’ አለ መነኩሴው
‘በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ ምን ያላደረግከው ነገር አለ? በበረሃ አክብረው የተቀበሉንን ሰዎች የብር ሳህን ሰርቀህ ወንዝ ውስጥ አልጨመርህም? እነርሱም መነኩሳት በቤታችን ተቀብለን ሰርቀውን ሄዱ እያሉ ይሆናል’

መነኩሴው መለሰ :- ‘አባ ትልቅ ነገር ነው እኮ ነው ያደረግሁላቸው፡፡ ያቀረቡልን የብር ሳህን ቅድም አያታቸው ከጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን የሰረቀው ጻህል /የቅዱስ ቁርባን ማቅረቢያ/ ነበር፡፡ መላው ቤተሰብ ይህንን ሳያውቅ በዚያ ቤት ለብዙ ዘመን ሲቀባበሉት ነበር፡፡በላዩ ላይም በላቲን ቋንቋ ይህ ጻህል ለቅዱስ ኒቆላዎስ ቤተ ክርስቲያን የተሠጠ የሚል ጽሑፍ አለበት፡፡ በዚህ ምክንያት ያንን ቅዱስ ንዋይ የሚጠቀሙ ሁሉ እስካልተመለሰ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ድፍረት ይሆንባቸዋል፡፡ የሞቱት ወላጆቻቸውም በዚያ ቅዱስ ንዋይ የተነሣ ነፍሳቸው ትታወካለች፡፡ እነዚያም ወጣቶች በጻሕሉ እኛን በማስተናገዳቸው ነፍሳቸው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የመጪው የ10 ዓመታት የመሪ እቅድ ሥልጠና በብፁዕ ቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ቃለ በረከት ተከፈተ::


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመሪ እቅድ መምሪያ አሰናጅነት የ10 ዓመታት መንፈሳዊና ዘላቂ የልማት ግቦች ጉባኤ በእግዚአብሔር ኃይል ጠንካራና ሁለገብ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብን ለመገንባት እንተጋለን ! በሚል ርዕስ ለአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ውይይትና ምክክር እየተሰጠ ነው፡፡

በመሪ ዕቅድ መምሪያ በተዘጋጀውና ለአንድ ቀን በሚቆየው የሥልጠና መክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን በመሪ ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ በንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ ገለጻ ተደረጓል ፣ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልእክት ከተለላልፈ በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሰፊ ትምህርት ቃለ በረከትና ቡረኬ ከሰጡ በኋላ የጉባኤው መከፈት አብስረዋል ::
EOTC TV

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🥀💠በአጠገብህ ላለዉ ወንድምህ መልካም ሰዉ ሁን።

💠በፍፁም መልሶ ሊከፍልህ ለማይችል ዉለታ ዋልለት።

💠 ፍቅርን የሚተካዉ ምን አለ?

💠 ለደከመዉ፣ በኑሮዉ ተስፋ ለቆረጠዉ ብርታት ሁንለት።

💠በመንገድ ዳር ላሉ ፍቅርና ርህራሄን አሳይ።

💠ከአንተ ለማይጠብቁ ሰዎች በጎ ነገርን አድርግላቸዉ።
💠 መልካምነት ክፍያዉ ገንዘብ አይደለም።

💠መልካምነት ወጪዉ ገንዘብ አይደለም። ልብ ነዉ።

💠 ልብህን አካፍላቸዉ።
💠ቅረባቸዉ።
💠ዉደዳቸዉ።
💠ሀዘናቸዉን ተካፈል።
💠በደስታቸዉ ደስ ይበልህ።
💠ሲያለቅሱ አልቅስ።
💠 ሲስቁ ሳቅላቸዉ።
💠በአንተ ምክንያት ደስ የሚላቸዉ ይብዙ።
💠ህይወት ትርጉም የሚኖራት ያኔ ነዉ፤ እኛ በመኖራችን ሌሎች ሰዎች ሲደሰቱ።

•••#ሰናይ ቀን😊
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የሊቀ ዲ /ን ቅ/እስጢፋኖስ
🕊1️⃣7⃣    🕯🕯🕯🕯
(""የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ወራዊ 💠 መታሰቢያ በዓል  ሰማዕቱ
ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን"")🤲
      💚💛❤️
እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ ተነስተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::" [ ሐዋ.፮፥፰-፲፭ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር  †
#ሼር
━━━━━✦✿✦━━━━━
     ◦◦✧join 👇👇
  🔔🔔ተቀላቀሉን 🔔🔔

/channel/dnhayilemikael
💠Tewahdotisfafaa🕊🕊

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#እርሷ_ከታቦር_ተራራ_ትልቃለች

ደብረ ታቦረ የእግዚአብሔር ምሥጢር የተገለጠበት ብርሃነ መለኮት የታየበት የምሥጢር ቦታ ነው። ብርሀነ መለኮቱ በተራራው ሲገለጥ ዓለም ሁሉ ብርሀን ሆኗል ይህ ብርሀን ከእርሷ የተገኘ ነው። ይህ የመገለጥ ምሥጢር አስቀድሞ የእግዚአብሔር ማድርያ ንጹሕ አዳራሽ በተሰኘች በድንግል ማርያም ተገልጧል። በደብረ ታቦር የታየውን ምሥጢር ያደነቅን እንደሆነ በእርሷ ማኅጸን የተደረገውን ነገር ስለምን አናደንቅ?። ልባሙ ዳዊት በአንቺ የተደረገ ድንቅ ነው ማለቱ ለዚህም አይደል።

በታቦር ተራራ ሐዲስና ብሉይ በሐዋርያትና በነቢያት አንድ ሆነው ታይተዋል እንዲሁ ሁሉ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ነቢያት ትንቢት የተናገሩለትን ሐዋርያት የሰበኩለትን ወልዳ በእጆቿ ታቅፉለች። ይህ ምሥጢር ግሩም ነው። ያ በታቦር የተገለጠው እሳታዊ መለኮት በእርሷ ማኅጸን በድንቅ ጥበብ ተገለጠ። ኤልያስ ሙሴ ያዕቆብና ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ አገልጋይ ሆነው ለዚህ ምሥጢር መመረጣቸው ካሰገረመክ እናትም አገልጋይም ሆና በተገኘች የምሥራቅ ደጃፍ በተባለች በእርሷ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተደረገው እንዴት አያስገርም?።

በደብረ ታቦር የተገለጠው ጌትነቱ በእርሷ በነሳው ሥጋ ነው። እርሷ ከታቦር ትበልጣለች በእርሷ የተደረገ በማንም አልተደረገም። ለእሷ የተነገረ ለማንም አልተነገረም። ለእሷ የተሰጣት ጸጋ ለማንም አልተሰጠም። ይህ ታቦር ትንቢት የተነገረለት ምሳሌ የተሰየመለት መሆኑን ካሰብክ ከውልደቷ እስከ እርገቷ በብዙ ኅብርና አምሳል የተገለጠችውን የምስጢር ቦታ እርሷን ማሰብህ ግድ ነው። ከደብረ ታቦር በፊት የሥላሴ ምሥጢር የተገለጠባት ብርሀን ሆና ብርሀንን የወለደች እርሷ ናት።

የደብተራ ኦሪት የሕግ ምስክር ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ድንቅ ነገር ያደረገባት ተራራ ናት።  ተመለከት በታቦር ተራራ በአንድ ቀን እንዲህ ያለውን ምሥጢር  ከገለጠ ዘጠኝ ወር በማኅጸኗ  በተሸከመችው በእሷ ደግሞ ከሰው የተሰወረ ስንት ምሥጢር ፈጽሞ ይሆን። መለአኩ ለሐዋርያት "ለእሷ የገለጠ ምሥጢር ለናተ የተገባ አይደለም" ያላቸውን ቃል ሳስብ ሁል ጊዜ እደነቃለው። በታቦር ተራራ ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን አይተዋል እሳተ መለኮት በእርሷ ማኅፀን እንዴት እንዳደረ ግን ማን ይመረምረዋል። በታቦር የታየውን ወንጌላውያን ገልጸውልናል በእርሷ የተደረገውን ግን እንደ አባ ሕርያቆስ"ሰባቱ የእሳት መጋረጃዎች ወዴት ተከለሉ" ብሎ ከመገረም ውጪ ምን ቃል አለ።

እርሷ ብርሃነ መለኮት የታየባት ብቻ ሳትሆን ሥጋ የሆነባት በጸጋ ሳይሆን በአካል የታየባት ነች። በእውነት ታቦርን ሚተካከል ምሥጢር የገለጠበት ተራራ አይኖር ይሆናል እርሷ ግን ከታቦር ተራራ ትብልጣለች። በታቦር ተራራ የተደረገውን ለማድነቅ ከበቃህ በእርሷ የተደረገውንም ታደንቃለህ።

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እየጾሙ አለመጾም

ተወዳጆች ሆይ! እየጾሙ የጾምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦

✔ ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣

✔ ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
✔ ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ፣

✔ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትዕይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ እየጾሙ እንዲህ አለመጾም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

      አምላከ ቅዱሳን እየጾሙ ካለመጾም ይሰውረን!

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ማርያማዊ ደስታ +

ድንግል ማርያም ‘መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል’ አለች፡፡ የድንግሊቱን ጥበብ ተመልከቱ፡፡ ‘በመልአክ በመመስገኔ ደስ ይለኛል ፣ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመባሌ ደስ ይለኛል ፣ አምላክን ለመውለድ በመመረጤ ደስ ይለኛል’ አላለችም፡፡ የእርስዋ የደስታ ምንጭ ከእግዚአብሔር የተሠጣት ነገር ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡

እግዚአብሔር የደስታህ ምንጭ ከሆነ በሕይወትህ ምንም ነገር ቢከሰት ደስታህን አይነካብህም፡፡ ድንግሊቱ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመሆንዋ ደስ ያላት ብትሆን ኖሮ ከዚያ በኋላ ከሴቶች ሁሉ የተንከራተተች ፣ ከሴቶች ሁሉ ያዘነች ፣ ከሴቶች ሁሉ በዲያብሎስና ጭፍሮቹ የተጠላች ፣ በሔሮድስ በአይሁድ የተነቀፈች መሆንዋን ስታይ ደስታዋ በጠፋ ነበር፡፡

እርስዋ ግን ደስታዋ የመነጨው ከአምላክዋ ብቻ ነበር፡፡ ፍጹም የሆነ ውስጣዊ ደስታን ማግኘት የሰው ልጅ ትልቅ ምኞቱ ነው፡፡ ሰዎች ደስታን ፍለጋ ብዙ ይደክማሉ፡፡ ድንግሊቱ ግን የደስታ ሁሉ ምንጭ የሆነው አምላክ ከእርስዋ ጋር ነውና በፍጹም ደስታ ደስ ይላታል፡፡ የድንግል ማርያም ደስታ ልጅዋ ‘ደስታችሁን የሚወስድባችሁ የለም’ ያለው ዓይነት ደስታ ነበር፡፡ ዮሐ. ፲፮፥፳፪

‘ተፈሥሒ ፍስሕት’ (ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ) ፤ ሙኃዘ
ፍሥሓ (የደስታ መፍሰሻ ሆይ) ብለን የምናመሰግናት እመቤታችን ከማንም የሚበልጥ ደስታ በእርስዋ ዘንድ ነበረ፡፡ ደስተኛ የነበረችው በምድር በነበራት ቆይታ የሚያስደስት ኑሮ ስለነበራት አይደለም፡፡ እንደ እርስዋ የተሰደደ ፣ ያለቀሰ ፣ የተጨነቀ ፍጡር የለም፡፡ እንደ ክርስቶስ መከራ የተቀበለ እንደሌለ እንደ ድንግል ማርያምም ያዘነ የለም፡፡ እርስዋ ግን ለሌሎች የሚተርፍ ወደ ኤልሳቤጥ የሚሸጋገር ፣ ሆድ ውስጥ ወዳለ
ፅንስ የሚጋባ ጥልቅ ደስታ ነበራት፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‘ተፈሢሓ በነፍሳ ፆረቶ በከርሣ’ ‘በነፍስዋ ደስ ተሰኝታ በሆድዋ ተሸከመችው’ እንዳለ እርስዋ የተደሰተችው ሥጋዊ ደስታን አልነበረም፡፡ (ድጓ ዘቅዱስ ገብርኤል )ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች አንዱ ደስታ ነውና ቅድስቲቱ ማንም ጋር ያልነበረ ደስታ ነበራት፡፡ ገላ. ፭፥፳፪

በእርግጥም ደስታን ወልዳ ደስ ባይላት ይደንቅ ነበር፡፡ እርስዋ የወለደችው ‘የመላእክት ተድላ ደስታቸው’ ነው ፤ እርስዋ የወለደችው መወለዱ ‘ለሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች’ የሚሆን ልጅን አይደለምን?

እግዚአብሔር አብ ‘በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው’ ያለውን አንድያ ልጁን ልጅዋ እንዲሆን ሠጥቶአታልና እርስዋም በምትወደው በልጅዋ ደስ ይላታል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ’ ካለ እግዚአብሔር የዘጠኝ ወር ቤቱ አድርጎ ያደረባት ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? መወለዱ ሰውና መላእክትን በደስታ እንዲዘምሩ ካደረገ የወለደችው ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን?

ጌታ ለሐዋርያቱ ‘ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ’ ካላቸው እግዚአብሔር ሁለተኛ ሰማዩ አድርጎ ዙፋን ያደረጋት በምድር ያለች የጠፈር ባልንጀራ ፣ የአርያም እኅት ማርያም ምንኛ ደስ ይላት ይሆን?

እመቤታችን ሆይ እባክሽን በአንቺ ላይ ከፈሰሰው ደስታ ቀድተሽ ወደ እኛ ወደ ኀዘንተኞቹ አፍስሺ፡፡ ኖኅ እንደ ላካት ርግብ የመከራችን ውኃ ጎደለ ብለሽ ታበሥሪን ዘንድ ወደ እኛ ነይ ‘ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ኀዘነ ልብየ’ ‘ርግቤ ሆይ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ’ እንዳለ ሊቁ፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 7 2015 ዓ.ም.
ለበዓለ ጽንሰታ ዝክር
ከብርሃን እናት ገጾች የተቆረሰ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የማይቀርበት ልዩ መንፈሳዊ ዝግጅት !!!

ሁላችንም ተጋብዛችኋል !!!!

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

#መጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ_ገብረ_ኪዳን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 /channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አንዳንድ ሰዎች እጅግ የጠለቀ ኀዘንና መቆርቆር ውስጥ ሲገቡ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ረስቶኛል” ብለው ሲያማርሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ነቢዩ እንዲህ ከሚሉ ሰዎች ጋር ክርክር አለው፡፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀኗ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃኗን ትረሳ ትችላለችን?” በማለትም ይጠይቃቸዋል (ኢሳ.49፡14)፡፡ ይህም ማለት ሴቷ ከማኅፀኗ የተወለደው ልጇን ልትረሳ ዘንድ እንደማይቻላት እግዚአብሔርም ሰውን ይረሳ ዘንድ ባሕርይ አይደለም እያላቸው ነው፡፡

ነቢዩ ይህን ምሳሌና ማነጻጸርያ አንሥቶ ክርክር መግጠም የፈለገው እያንዳንዷ እናት ለልጇ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኾኖም ይህን ያህል የምናንቆለጳጵሰው የእናት ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው “አዎን እርሷ ትረሳ ይኾናል፤ እኔ ግን አልረሳሽም… ይላል እግዚአብሔር” በማለት የሚቀጥለው፡፡ እንግዲህ የአምላካችን ፍቅር እንደምን የበዛ እንደ ኾነ ታስተውላላችሁን?

እንግዲያውስ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አባት ለልጆቹ እንዲያዝን እንዲራራ እንደዚህም ኹሉ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይራራለቸዋል” ብሎ እንደተናገረ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ትቶኛል” የሚል ማንም አይገኝ (መዝ.102፡13)፡፡ ጆሮን የፈጠረ እርሱ ይሰማል፤ ዐይንን የፈጠረ እርሱ ያያል፡፡ እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ የቀረጻቸው ልጆቹን አይረሳም፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🥀እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ወርሃዊ በአል አደረሳቹሁ 

💠ቅዱስ እስጢፋኖስ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በህዝብ ድንጋይ እየተደበደበ ሳለ ለጸሎት ተንበረከከ።
💠ይህ ሁኔታ እንኳን ለመንበርከክ በስርዓት ለመሞትም ፋታ አይሰጠም ነበር።
💠ግን ጌታው ፊት ምን ያህን በአክብሮት መጸለይ እንዳለበት እየሞተም አልረሳም።                                       

🥀በአስቸጋሪ  ሁኔታም ውስጥ እምላኩን በአክብሮት አከበረ።
💠እኛ እየኖርን ምን ያህል ለክብሩ የሚገባ ስግደት እንሰጣለን?
💠ስንቶቻችን ለጸሎት ከመቀመጫችን እንነሳለን? በሰላም የምኖነረው እኛ ለጌታ ሰዓት አጥሮን ምክንያት መደርደራችንን እስጢፋኖስ ቢሰማ ምን ይል ይሆን?
💠እርሱ አምኖ ሲሞት አምኖ መኖር ምን ያህል እንደሚያስፈልገን ተረዳችሁ? እግዚአብሔርን ከወደድነው መቸም ቢሆን ለርሱ ጊዜ አለን።
💠ለአምልኮ ጊዜ ያጣነው ሰዓት ስላጣን ሳይሆን ለርሱ ፍቅር ስላጣን ነው። ይህን ማንም እንዳይረሳ።
💠ተሰብስበን ወደማይቀረው ዓለም መጠራታችን አይቀርም። ወደ ዘላለሙ ስፍራ መድረሳችን አይቀርም። ስለዚህ ቀን ሳለ ጌታችንን ማክበር ወደ ፍለጋው መመልከት እንጀምር።
💠 ማንም የማይሰራበት ሌሊት ይመጣልና።
💠የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በረከቱ እረድኤቱ ይደርብን /አይለየን አሜን

ተቀላቀሉ ቴሌግራም ቻናል
 /channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንዲህ አሉ፦
💠ማንም ቢሰድብህ
ስለ መሰደብህ ሳይሆን ስለ ሰደበህ ሰው አስብ።
💠 ያ ሰው ወንድምህ ነው። በፍቅር የተሞላህ መንፈሳዊ ሰው እንደመሆንህ መጠን አንተን በመስደብ ኃጢአት ላደረገው ወንድምህ ምን ልታደርግለት እንደምትችል ታስብ ዘንድ ይገባሃል።
💠በእርግጥ አንተን የተሳደበበት ስድብ በድኅነቱ መግቢያ ላይ ቆሞ ይከለክለውና በዚሁ ሳቢያ ውድ ነፍሱ ወደ ሲዖል ትወርድ ዘንድ አትሻም።
💠በመሆኑም ያንን ኃጢአት ቆጥሮ እንዳይቀጣው ይልቁንም ይቅር እንዲለው እግዚአብሔርን ትጠይቅለታለህ ከዚህ በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ካለው ኃጢአት እንዲያወጣውና ዳግመኛ አንተን ሆነ ሌሎችን በመስደብ እንዳይበድል ልትጸልይለት ይገባል።
@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ወር በገባ በ11 በወርሐዊ በዓላቸው ታስበው ለሚውሉት አቡነ ሐራ ድንግል መድኃኔዓለም ክረስቶስ የሰጣቸው ቃልኪዳን፤-
“በእጅህ የተባረከውን፤ ለተራቡና ለተጠሙ እህልና ውኃን በመስጠት በዓልህን ያከበረውን ሰው ሁሉ ኃጢአተኛና በደለኛ ሆኖ ሳለ በጸሎትህና በቃልኪዳንህ የታመነውን፤ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈውንና ያጻፈውን፤ ያነበበውንና
የተረጎመውን፤ የሰማውንና ያሰማውን፤ አጽምህንም እየጠበቀ በገዳምህ የተቀመጠውን አንተንም ሰለወደደ ከሩቅም ከቅርብም መጥቶ ገዳምህን የተሳለመውን ወንድ ልጁንና ሴት ልጁንም በስምህ የጠራውን እነዚህን ሁሉ በየወገናቸው ከሥጋና ከነፍስ አገዛዝ ነጻ የወጡ ይሁኑ ዘንድ እስከ ሰባተ ትውልድ ምሬልሃለሁ፡፡”
የአቡነ ሐራ ድንግል ረድኤት በረከት አይለየን በጸሎታቸው ይማረን።
ምንጭ ከገድላት አንደበት
@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"አለሙም ምኞቱም ያልፋል"

ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ፤ ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።

ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ፤ ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም፤ በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ፤ መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም።

ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን፤ ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ።

ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው።

"ዓለም ሳትንቅህ በፊት ናቃት!!!"

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንዳትጎዳ አዘንኩላቸው፡፡ ስለዚህም ሰረቅኋቸው፡፡ የሰረቅሁት ፈልጌው አይደለምና ውኃው ውስጥ ወረወርሁት፡፡

በማግሥቱ የደብሩ ዘበኛ ሊታጠብ ወደ ውኃው ይመጣል፡፡ በውኃው ውስጥም ያገኘዋል፡፡ የላቲን ቋንቋ ስለሚያውቅ የተጻፈውን ያነበዋል፡፡ ወስዶም ለካህኑ ይሠጠዋል፡፡ ፃህሉ ከብሮ ድጋሚ ሲቀደስበት የሞቱትም ያርፋሉ የቆሙትም ከጥፋት ይድናሉ፡፡ ’ አላቸው፡፡
አባ ተደነቁ ፤ ‘እሺ ሕፃኑንስ የገደልከው ለመልካም ብለህ ነው?’

‘አባ የእግዚአብሔርን ፍርድ አይመዝኑ ፤ ሕፃኑ የተፀነሰው በኃጢአት ነው ፤ ለወደፊት ደግሞ እጅግ ጨካኝ ወንጀለኛ ሆኖ ወላጆቹን የሚገድል ብዙዎችን የሚያሰቃይ ነው፡፡ ስለዚህ ልጁን በመግደሌ ሦስት መልካም ነገሮች አደረግሁ፡፡ ሕፃኑ ከንጽሕናው ጋር ወደ ሰማይ እንዲሔድ አደረግሁት ፤ ወላጆቹንም በልጃቸው እጅ ከመሞት አዳንኋቸው፡፡በዚህ ልጅ ኀዘን ምክንያት ወላጆቹም ልባቸው በመሰበሩ የቀደመ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል’

‘እሺ መጠጥ ቤቱ ደጃፍ ላይ የሰገድከው ምን ሆነህ ነው?’
‘ሦስት ሰዎች በዚያ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው የፈረሰውን የከተማችንን ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንሥራ እያሉ እየተጨነቁ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ምንም እንኳን የተሰበሰቡበት ቦታ መጥፎ ቢሆንም በልባቸው ያለው ሃሳብ ቅን ስለሆነ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ወድቄ ሰግጄ ለመንሁት’’

‘ታዲያ ወደ ፈረሰው ቤተ መቅደስ ድንጋይ ለምን ወረወርህ?’
‘በፈረሰው መቅደስ ላይ እየተሳለቁ አጋንንት ሲጨፍሩ አየሁ፡፡ በመስቀል ምልክት አማትቤ ድንጋይ ወረወርሁ ፤ በዚህም ምክንያት አጋንንቱ በንነው ሸሹ’ አለ መነኩሴው፡፡

አባ ቀጠሉ ‘የእነዛን የሙት ልጅ የሆኑ ሕፃናት ቤትስ ለምን አቃጠልከው?’
‘’እነዚያ ሕፃናት እንደሚያውቁት ወላጆቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ የቀራቸው ንብረትም ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ቅድመ አያታቸው የቀብሩት እጅግ ብዙ ሀብት ግን ከዚያ ቤት በታች አለ፡፡ ከቃጠሎው በኋላ በቀረው ክፍል ለማደር ልጆቹ ሲገቡ የተቀበረውን ሀብት ያዩታል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት ለሚያገለግል አጎታቸውም ሔደው ይነግሩታል፡፡ በረሃብ መሞታቸው ቀርቶ በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ’’ አለ መነኩሴው፡፡

አባ ምንም እንኳን ነገሩ ቢያስደንቃቸውም አንድ ወጣት መነኩሴ ይህንን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አደረባቸውና ‘አንተ ማን ነህ?’ አሉት፡፡
‘የእኔ ማንነት ይቆይና እርስዎ በዚህ ሰሞን መላልሰው ፈጣሪን የጠየቁት ነገር ካለ ይንገሩኝ’ አላቸው
‘እኔማ እግዚአብሔር ሆይ ፍርድህን አሳየኝ ብዬ በምድር ላይ ስለሚደረጉ ኢፍትሐዊ ነገሮች ጠይቄው ነበር’ አሉት፡፡

‘እግዚአብሔር ‘ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ መንገዴ ከመንገዳችሁ ሃሳቤም ከሃሳባችሁ የራቀ ነው’ ብሏልና ፍርዱ አይመረመርም፡፡ ለመላእክት እንኳን ያልተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዴት እርስዎ በሰው አቅም ሊመረምሩ ይፈልጋሉ፡፡ ጸሎትዎን ሰምቶ እግዚአብሔር ያዩትን ሁሉ እንዳደርግና ፍርዱን እንዳሳይዎት ላከኝ’’ አላቸው፡፡

ቅዱስ ዑርኤል ለዕዝራ እንዲህ አለው፦
‘የምትፈርስ የምበሰብስ አንተ የማይፈርስ የማይበሰብስ የሕያው እግዚአብሔርን ፍርዱን ልትመረምር አትችልም’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 24/ 2012 ዓ ም

/How God Judges People – The patristic heritage book 2 – /Elder Cleopa/ ከሚለው የዜና አበው መጽሐፍ የተተረጎመ/

ማስታወሻ ፦ ይህንን ታሪክ ትንሽ የሚመስለው ታሪክ በ1747 የተጻፈው የቮልቴር ዛዲግ ላይ አንብቤ የታሪኩ ሞራል ደስ ቢለኝም የዞራስትራኒዝም ነበርና ለቤተ ክርስቲያን አይሆንም ብዬ ነበር፡፡ ለካንስ ይህ ታሪክ አስቀድሞ በመነኮሳት ታሪክ የተመዘገበ ነበርና በዚህ መልኩ ከአራተኛውና አምስተኛው ክፍለ ዘመን ወርቃማ የምንኩስና ታሪኮች በአንዱ ተመዝግቦ አገኘሁት፡፡ ባየነውና በምናየው ሁሉ እንዳሻን የእግዚአብሔርን ፍርድ በምንደመድምና በምናብራራበት በዚህ የደፋር ዘመን እንዲህ ያሉ ታሪኮች ልጉዋም ቢሆኑ በሚል ተርጉሜዋለሁ/

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም Like እና Share

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ይህም ምእመናንን እያወከ ያለ አጭበርባሪ ድርጅት ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናን በእነዚህ የከሓድያን ድርጅት ምክንያት እንዳይነጠቁ። ድርጅቱን አውግዞ መለየት አለባት። ባለማወቅ ከዚህ ድርጅት የገቡትንም ጠንቅቆ አስተምሮ ወደ ቤተክርስቲያን ቢመልሳቸው መልካም ነው።

ንቀን ዝም ያልናቸው ችግሮች ወደፊት ታላላቅ መከራ ውስጥ ይከቱናል። አጭባርባሪ ባሕታውያን ነን ባዮችን፣ አጥማቂ ነን ባይ ሌቦችን ዝም ማለት ተገቢ አይደለም። የሊቃውንት ጉባኤውም እነዚህ አካላት ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እያዘጋጀ ምእመናንን ከወጥመድ ቢያድን መልካም ነው።

ባለማወቅ ተታላችሁ የዚህ አባል የሆናችሁ ምእመናን ራሳችሁን ከሲኦል አድኑ። ይህ ክፉ ሥራ ወደሲኦል የሚሸኝ ነውና። ነፍሳችሁ እንዳትጎዳ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ተመለሱ።

መ/ር በትረ ማርያም



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…
Subscribe to a channel