#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
++ በሰንበት መፍረስ ++
የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡
ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡
ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡
እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ በስካር በዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!
ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 9 /2012 ዓ.ም.
ቪክቶሪያ አውስትራሊያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
/channel/dnhayilemikael
🌼🌼🌼🌼🌼💠🌼🌼🌼💠💠🌼
+++ "እግዚአብሔር የጣላት እሳት" +++
በደብተራ ኦሪት በመሠዊያው ላይ የሚነደውና መሥዋዕቱ ይቃጠልበት የነበረው እሳት ከሰማይ የወረደ ነበር። ይህም እሳት ዘወትር እንዳይጠፋ የአሮን ልጆች (ካህናቱ) ማለዳ ማለዳ እንጨት እየጨመሩ እንዲያቀጣጥሉና እንዲያነዱት እግዚአብሔር አዝዟቸዋል።(ዘሌዋ 6፥12) ከማዕጠንት ጀምሮ እስከ እንስሳት በድንኳኑ የሚቀርቡ ማናቸውም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሁሉ የሚበሉት ከሰማይ በወረደው በዚህ "የእግዚአብሔር እሳት" ነው።
ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እንዲህ አደረጉ። ለእግዚአብሔር የእጣን መሥዋዕት ማቅረብ ፈልገው ለየራሳው ጥናውን (ማዕጠንት) አነሡ። ነገር ግን በጥናው ውስጥ ያደረጉት ከሰማይ የወረደውን "የእግዚአብሔር እሳት" ሳይሆን፣ ከመንደር ጭረው ያመጡትን ወይም ራሳቸው ያቀጣጠሉትን "ሌላ እሳት" ነበር። በዚህም እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት ስላቀረቡ አምላክ ተቆጣ። በፊቱም እሳት ወጥቶ እንዲበላቸው አደረገ። እነርሱም ወዲያው ሞቱ።(ዘሌ 10፥1-3) ሊቀ ካህናቱ አሮንን እየተከተሉ እንዲያገለግሉ የተመረጡት ሁለቱ ልጆቹ ገና አገልግሎታቸውን በቅጡ ሳይጀምሩ ተቀሰፋ። ለመሆኑ እነዚህ ሁለት የኦሪት ወጣት ካህናት የተቀጡበት "የሌላ እሳት" ታሪክ ለሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ምን ምሳሌ ይኖረው ይሆን?
እግዚአብሔር በኦሪቱ ድንኳን እሳትን እንዳወረደ፣ በሐዲስ ኪዳንም የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማይ ሲወርድ ይዞልን የመጣው እሳት አለ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር፤ ወምንተ እፈቅድ ዘእንበለ አንድዶታ" - "በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ?" እንዳለን።(ሉቃ 12፥49) ይህ መድኃኒታችን በምድር ላይ የጣለው እሳት ምንድር ነው? አገልግሎቱስ እንዴት ነው?
ጌታችን በምድር የጣላት እሳት "ወንጌል" ትባላለች። ሰው ሰውነቱን ንጹሕና የተቀደሰ ሕያውም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብባት "የእግዚአብሔር እሳት" ወንጌል ነች። ይህች ወንጌል ጌታ አንድ ጊዜ በምድር የጣላት፣ እኛ ደግሞ ለዘወትር እንዳትጠፉ የምናቀጣጥላትና የምናነዳት እሳት ነች። የማቀጣጠያው እንጨቶችም ቃለ እግዚአብሔርን መስማት እና ማንበብ ናቸው። ያለ ወንጌል እሳትነት ምንም መሥዋዕት እንድናቀርብ አልተፈቀደልንም። ነገር ግን እንደ አሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ ከመንደር ቆስቁሰን ወይም ራሳችን አቀጣጥለን የምናመጣቸው "ሌላ እሳት" የተባሉ ከንቱ ፍልስፍናዎችና እንግዳ ትምህርቶች የእግዚአብሔርን ቁጣ ይቀሰቅሱብናል።
ዳግመኛም እሳት የተባለው በጥምቀት ጊዜ በሁላችንም ላይ የወረደው ጸጋ እግዚአብሔር ነው። ይህም ጸጋ ለመዳናችን ዓይነተኛ ሚና አለው። ይሁን እንጂ ልክ በደብተራ ኦሪት እንደ ወረደው እሳት ካልተንከባከብነው እና ካላቀጣጠልነው ሊዳፈን እና የሌለ ሊመስል ይችላል። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ "እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው...በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ" በማለት የሚመክረው።(2ኛ ጢሞ 1፥6) እግዚአብሔር ለሰጠን ጸጋ ማቀጣጠያዎቹ ደግሞ ጾም፣ ጸሎትና መንፈሳዊ ትሩፋት ሁሉ ናቸው። እርሱ የሰጠንን የጸጋ እሳት ከማቀጣጠል ይልቅ "ሌላ እሳት" እናምጣ ያልን ቀን ግን ታላቅ ጥፋት ያገኘናል።
በዲያቆን አቤል ካሳሁን ተጻፈ
/channel/dnhayilemikael
2016ን
የኪዳነ ምሕረት ዓመት ያድርግልን!
እርስ በእርስ የምንበላላ በላዔ ሰብኦች ነንና እስካሁን ድረስ በግፍ የበላናቸው ነፍሳት በቅተውን በምሕረት ኪዳን ልባችን የሚመለስበት ፤ የሰው ሞት ዜናን ስንሰማ እንደ ቀድሞው ዘመን የምደነግጥበት ዓመት ይሁን:: ንስሓ ከገባን ሊምረን የገባውን ቃል ፈጽመን ምሕረት የምናገኝበት የኪዳነ ምሕረት ዓመት ይሁን::
የአባይን ውኃ መገደብ ችላ የደም ጎርፍን ግን መገደብ ያቃታትን ኢትዮጵያ የሚያሻግር የምሕረት መርከብ ይታዘዝላት:: በኖኅ ዘመን የታየው የኪዳነ ምሕረት ቀስተ ደመና የጥፋት ውኃዋ አላባራ ባለው ሀገራችን ላይ ይታይ::
አድራሻ እየቀያየርን የምንፋጅበትን እሳት ያብርድልን:: አንዱ በላው ሞት የሚስቅበት ፣ አንዱ በሌላው ቁስል እንጨት የሚሰድድበት የመጨካከን ዘመን ይብቃ:: የአባቶቻቸውን ጸሎት አስታውሶ የገባውን ኪዳነ ምሕረት አስቦ እስራኤልን ይቅር ያለ ጌታ ኢትዮጵያውያንም ዛሬ ያወረድነውን እጃችንን ሳይሆን ትናንት ኢትዮጵያ ትዘረጋለች የተባለችውን እጅዋን አስቦ የኪዳነ ምሕረት ዓመት ያድርግልን::
"ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ?
ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤
ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ" ሰ. ኤርምያስ 5:21
/channel/dnhayilemikael
🌼አዲስ ዓሜት🌻
#እግዚአብሔር_የሚወዳችሁ_እናንተም_የምትወዱት_ልጆቼ!
🌻አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡
🌼 አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡
🌻ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ 🌻ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡
🌼 ዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “👉ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ 👉ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡
👉የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡
👉ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡
👉 ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ?
👉በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡
👉 ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ይቀላቀሉ)
/channel/dnhayilemikael
+ አምናለሁ እና አላምንም +
ልጁ የታመመበት አባት ነው:: ጌታን "ቢቻልህስ ልጄን ፈውስልኝ" አለው:: ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡ አለው።
ይህን ጊዜ ሰውዬው "ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው፡ አለ" ማር. 9:24
የዚህ ሰውዬ ንግግር ፍቺ የሚፈልግ ቅኔ ይሆንብኛል "አምናለሁ አለማመኔን እርዳው"
ይኼ ሰውዬ ያምናል ወይንስ አያምንም?
ያምናል እንዳንል "አለማመኔን" ይላል ፤ አያምንም እንዳንል "አምናለሁ" ይላል:: የቸገረ ነገር ነው? ሁሉን አዋቂው መድኃኔዓለም ምን ለማለት እንደፈለገ ገብቶት ልጁን ፈወሰለት:: እኔ አላዋቂው ግን "አምናለሁ አለማመኔን እርዳው" የሚለውን ቃል እየደጋገምኩት ቀረሁ::
እያመኑ አለማመን እንዴት ያለ ነው? ብዬ መላልሼ ሳጤነው ግን ሰውዬው የእኔኑ ድክመት እየተናገረ እንደሆነ ገባኝ::
አምናለሁ እላለሁ:: በእርግጥም በፈጣሪ መኖር አምናለሁ:: ሁሉን እንደሚችልም አምናለሁ::
ግን ደግሞ በእርሱ ታምኜ አላውቅምና በሥራዬ እክደዋለሁ:: ኑሮዬ "በሥራቸው ይክዱታል" ከተባሉት የሚመደብ ነው:: (ቲቶ 1:16) አቅዋሜ የማመን ኑሮዬ ያለማመን ነውና አምናለሁ አለማመኔን እርዳው ብል ለእኔ የሚገባ ጸሎት ነው::
ወረደ ተወለደ ተጠመቀ ተሰቀለ ሞተ ተነሣ ዐረገ ብዬ አምናለሁ:: በትሕትና መውረድን ፣ በንስሓ መወለድን ፣ በታናሽ እጅ ዝቅ ብሎ ጽድቅን መፈጸምን ፣ መከራን በትዕግሥት መቀበልን ፣ ከመከራ ሞት ወዲያ ተነሥቶ በክብር ከፍ ማለትን ግን እኔ ሕይወት ላይ አላውቀውም:: የምተርከው ክርስቶስ እንጂ የሚተረክ ክርስትና የለኝም:: ስለዚህ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው በልኬ የተሰፋ ጸሎት ነው::
መች በዚህ ያበቃል::
እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳው::
ከምግብ እጾማለሁ ከኃጢአት ግን አልጾምም:: ሥጋ መብላት ትቼ የሰው ሥጋ በሐሜት የምበላ ነኝና እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳሁ እላለሁ::
እጸልያለሁ አለመጸለዬን::
ቆሜ የማደርሰው ጸሎትስ አለኝ:: ግን ልቤ ሠላሳ ቦታ ደርሶ ይመለሳል:: የምጸልየው ማናገር የማልፈልገውን ሰው በግድ የማናግር ያህል የግብር ይውጣ እንጂ ነፍሴ እርሱን ሽታ አይደለምና እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው እላለሁ::
እሰግዳለሁ አለመስገዴን እርዳውስ?
ላቤ እስኪወርድ ሰግጄ አውቃለሁ:: ልቤ ግን አንዴ አልሰገደም::
ጌታ ሆይ እመጸውታለሁ አለመመጽወቴን እርዳው:: እዘምራለሁ አለመዘመሬን እርዳው:: አስቀድሳለሁ አለማስቀደሴን እርዳው:: እማራለሁ አለመማሬን እርዳው:: ሆኜ ያልሆንሁትን አድርጌ ያላደርግሁትን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና እርዳኝ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 3 2015 ዓ.ም.
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
/channel/dnhayilemikael
+++ ይህችን ዓመት ተወኝ! +++
ከዓመት እስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ
በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ
አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ
አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ
ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ
ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም
ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም
የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ
የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ!
አውቃለሁ ታውቃለህ - ቀጠሮን ሰጥቼ - እንደማላከብር
ብዙ ጊዜ አቅጄ - ብዙ ጊዜ ዝቼ - በወሬ እንደምቀር
‹ዘንድሮስ…!› እንዳልኩኝ - አምና ይሄን ጊዜ - ሰምተኸኝ ነበረ
ምንም ሳልለወጥ - ‹ዘንድሮዬ› አልፎ - በአዲስ ተቀየረ
ፍሬ የማይወጣኝ - እኔን በመኮትኮት - እጆችህ ደከሙ
እኔ ግን አለሁኝ - ዛሬም አልበቃኝም - በኃጢአት መታመሙ
የቃልህን ውኃ - በድንጋይ ልጅህ ላይ - ሳትታክት ስታፈስስ -
ዘመን ተቆጠረ
ወደ ልቤ ሳይሰርግ - ሕይወቴን ሳይለውጥ - እንዲያው ፈስሶ ቀረ
ቃልህን ጠግቤ - እያገሳሁት ነው - ሌሎች እስኪሰሙ
በቃልህ መኖር ግን - አልያዝህ አለኝ - ከበደኝ ቀለሙ
ብዙ ጥቅስ አገኘሁ - ከቅዱስ መጽሐፍህ - ገልጬ አይቼ
ከራሴ ላይ ብቻ - አንድ ጥቅስ አጣሁኝ - በበደል ተኝቼ
ውጤቴ ደካማ - ትምህርት የማይሠርጸኝ - ተማሪ ብሆንም
ይህችን ዓመት ተወኝ - ደግሞ ትንሽ ልማር - ታገሠኝ አሁንም!
እባክህ አልቆረጥ - በቅዱስ መሬትህ - ልቆይ ፍቀድልኝ
ያፈሩት ቅዱሳን - የፍሬያቸው ሽታ - መዓዛ እንዲደርሰኝ
የተሸከምከኝ ሆይ - ዛሬም ተሸከመኝ - አትሰልቸኝ አደራ
ማን ይታገሠኛል - ጠላት እየሆንኩት - አይሠሩ ስሠራ!
አታውጣኝ ከቤትህ - ብዙ ቦታ አልይዝም - ፍሬ ስለሌለኝ
ስፍራ የማያሻኝ - ቤት የማላጣብብ - ፍሬ አልባ በለስ ነኝ!
ቦታስ የሚይዙት - ባለ ምግባሮቹ - ቅዱሳንህ ናቸው
ልክ እንደ ዘንባባ - የተንዠረገገ - ተጋድሎ ጽድቃቸው!
ከሊባኖስ ዝግባ - እጅጉን የበዛ - ገድል ትሩፋታቸው!
እኔ አይደለሁም - ቦታስ የምትይዘው - የአንተው እናት ናት
ሥሮቿ በምድር - ጫፎቿ በሰማይ - ሲደርሱ ያየናት
ይሀችን ዓመት ተወኝ - ከሥርዋ እሆናለሁ - ባፈራ ምናልባት!..
ይህችን ዓመት ተወኝ - እባክህ አምላኬ - አንድ ዓመት ምንህ ናት
ሺህ ዓመት አንድ ቀን - አይደለም ወይ ለአንተ - ዓመት ኢምንት ናት!
ይሄ ዓመት አልፎ - ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ› - እስከምልህ ድረስ
እባክህን ጌታ - ይህችን ዓመት ተወኝ - የወጉን እንዳደርስ!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 5 ቀን 2001 ዓ.ም.
ሐመር መጽሔት ላይ
የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
/channel/dnhayilemikael
ጽናት!
የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን
...ቀኖና ቤተክርስቲያንን በጣሰ መንገድ የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዲገነጠሉ ከመንግስት የቀረበላቸውን ፖለቲካዊ ጥያቄ አልቀበልም በማለታቸው በዩክሬን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት የአምስት ዓመት እሥር ተፈረደባቸው።
በረከታቸው ይደርብን።
/channel/dnhayilemikael
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የመጪው የ10 ዓመታት የመሪ እቅድ ሥልጠና በብፁዕ ቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ቃለ በረከት ተከፈተ::
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመሪ እቅድ መምሪያ አሰናጅነት የ10 ዓመታት መንፈሳዊና ዘላቂ የልማት ግቦች ጉባኤ በእግዚአብሔር ኃይል ጠንካራና ሁለገብ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብን ለመገንባት እንተጋለን ! በሚል ርዕስ ለአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ውይይትና ምክክር እየተሰጠ ነው፡፡
በመሪ ዕቅድ መምሪያ በተዘጋጀውና ለአንድ ቀን በሚቆየው የሥልጠና መክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን በመሪ ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ በንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ ገለጻ ተደረጓል ፣ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልእክት ከተለላልፈ በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሰፊ ትምህርት ቃለ በረከትና ቡረኬ ከሰጡ በኋላ የጉባኤው መከፈት አብስረዋል ::
EOTC TV
🥀💠በአጠገብህ ላለዉ ወንድምህ መልካም ሰዉ ሁን።
💠በፍፁም መልሶ ሊከፍልህ ለማይችል ዉለታ ዋልለት።
💠 ፍቅርን የሚተካዉ ምን አለ?
💠 ለደከመዉ፣ በኑሮዉ ተስፋ ለቆረጠዉ ብርታት ሁንለት።
💠በመንገድ ዳር ላሉ ፍቅርና ርህራሄን አሳይ።
💠ከአንተ ለማይጠብቁ ሰዎች በጎ ነገርን አድርግላቸዉ።
💠 መልካምነት ክፍያዉ ገንዘብ አይደለም።
💠መልካምነት ወጪዉ ገንዘብ አይደለም። ልብ ነዉ።
💠 ልብህን አካፍላቸዉ።
💠ቅረባቸዉ።
💠ዉደዳቸዉ።
💠ሀዘናቸዉን ተካፈል።
💠በደስታቸዉ ደስ ይበልህ።
💠ሲያለቅሱ አልቅስ።
💠 ሲስቁ ሳቅላቸዉ።
💠በአንተ ምክንያት ደስ የሚላቸዉ ይብዙ።
💠ህይወት ትርጉም የሚኖራት ያኔ ነዉ፤ እኛ በመኖራችን ሌሎች ሰዎች ሲደሰቱ።
•••#ሰናይ ቀን😊
/channel/dnhayilemikael
የሊቀ ዲ /ን ቅ/እስጢፋኖስ
🕊1️⃣7⃣ 🕯🕯🕯🕯
(""የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ወራዊ 💠 መታሰቢያ በዓል ሰማዕቱ
ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን"")🤲
💚💛❤️
እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ ተነስተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::" [ ሐዋ.፮፥፰-፲፭ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
#ሼር
━━━━━✦✿✦━━━━━
◦◦✧join 👇👇
🔔🔔ተቀላቀሉን 🔔🔔
/channel/dnhayilemikael
💠Tewahdotisfafaa🕊🕊
#እርሷ_ከታቦር_ተራራ_ትልቃለች
ደብረ ታቦረ የእግዚአብሔር ምሥጢር የተገለጠበት ብርሃነ መለኮት የታየበት የምሥጢር ቦታ ነው። ብርሀነ መለኮቱ በተራራው ሲገለጥ ዓለም ሁሉ ብርሀን ሆኗል ይህ ብርሀን ከእርሷ የተገኘ ነው። ይህ የመገለጥ ምሥጢር አስቀድሞ የእግዚአብሔር ማድርያ ንጹሕ አዳራሽ በተሰኘች በድንግል ማርያም ተገልጧል። በደብረ ታቦር የታየውን ምሥጢር ያደነቅን እንደሆነ በእርሷ ማኅጸን የተደረገውን ነገር ስለምን አናደንቅ?። ልባሙ ዳዊት በአንቺ የተደረገ ድንቅ ነው ማለቱ ለዚህም አይደል።
በታቦር ተራራ ሐዲስና ብሉይ በሐዋርያትና በነቢያት አንድ ሆነው ታይተዋል እንዲሁ ሁሉ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ነቢያት ትንቢት የተናገሩለትን ሐዋርያት የሰበኩለትን ወልዳ በእጆቿ ታቅፉለች። ይህ ምሥጢር ግሩም ነው። ያ በታቦር የተገለጠው እሳታዊ መለኮት በእርሷ ማኅጸን በድንቅ ጥበብ ተገለጠ። ኤልያስ ሙሴ ያዕቆብና ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ አገልጋይ ሆነው ለዚህ ምሥጢር መመረጣቸው ካሰገረመክ እናትም አገልጋይም ሆና በተገኘች የምሥራቅ ደጃፍ በተባለች በእርሷ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተደረገው እንዴት አያስገርም?።
በደብረ ታቦር የተገለጠው ጌትነቱ በእርሷ በነሳው ሥጋ ነው። እርሷ ከታቦር ትበልጣለች በእርሷ የተደረገ በማንም አልተደረገም። ለእሷ የተነገረ ለማንም አልተነገረም። ለእሷ የተሰጣት ጸጋ ለማንም አልተሰጠም። ይህ ታቦር ትንቢት የተነገረለት ምሳሌ የተሰየመለት መሆኑን ካሰብክ ከውልደቷ እስከ እርገቷ በብዙ ኅብርና አምሳል የተገለጠችውን የምስጢር ቦታ እርሷን ማሰብህ ግድ ነው። ከደብረ ታቦር በፊት የሥላሴ ምሥጢር የተገለጠባት ብርሀን ሆና ብርሀንን የወለደች እርሷ ናት።
የደብተራ ኦሪት የሕግ ምስክር ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ድንቅ ነገር ያደረገባት ተራራ ናት። ተመለከት በታቦር ተራራ በአንድ ቀን እንዲህ ያለውን ምሥጢር ከገለጠ ዘጠኝ ወር በማኅጸኗ በተሸከመችው በእሷ ደግሞ ከሰው የተሰወረ ስንት ምሥጢር ፈጽሞ ይሆን። መለአኩ ለሐዋርያት "ለእሷ የገለጠ ምሥጢር ለናተ የተገባ አይደለም" ያላቸውን ቃል ሳስብ ሁል ጊዜ እደነቃለው። በታቦር ተራራ ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን አይተዋል እሳተ መለኮት በእርሷ ማኅፀን እንዴት እንዳደረ ግን ማን ይመረምረዋል። በታቦር የታየውን ወንጌላውያን ገልጸውልናል በእርሷ የተደረገውን ግን እንደ አባ ሕርያቆስ"ሰባቱ የእሳት መጋረጃዎች ወዴት ተከለሉ" ብሎ ከመገረም ውጪ ምን ቃል አለ።
እርሷ ብርሃነ መለኮት የታየባት ብቻ ሳትሆን ሥጋ የሆነባት በጸጋ ሳይሆን በአካል የታየባት ነች። በእውነት ታቦርን ሚተካከል ምሥጢር የገለጠበት ተራራ አይኖር ይሆናል እርሷ ግን ከታቦር ተራራ ትብልጣለች። በታቦር ተራራ የተደረገውን ለማድነቅ ከበቃህ በእርሷ የተደረገውንም ታደንቃለህ።
#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ
/channel/dnhayilemikael
እየጾሙ አለመጾም
ተወዳጆች ሆይ! እየጾሙ የጾምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦
✔ ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣
✔ ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
✔ ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ፣
✔ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትዕይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ እየጾሙ እንዲህ አለመጾም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አምላከ ቅዱሳን እየጾሙ ካለመጾም ይሰውረን!
+ ማርያማዊ ደስታ +
ድንግል ማርያም ‘መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል’ አለች፡፡ የድንግሊቱን ጥበብ ተመልከቱ፡፡ ‘በመልአክ በመመስገኔ ደስ ይለኛል ፣ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመባሌ ደስ ይለኛል ፣ አምላክን ለመውለድ በመመረጤ ደስ ይለኛል’ አላለችም፡፡ የእርስዋ የደስታ ምንጭ ከእግዚአብሔር የተሠጣት ነገር ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
እግዚአብሔር የደስታህ ምንጭ ከሆነ በሕይወትህ ምንም ነገር ቢከሰት ደስታህን አይነካብህም፡፡ ድንግሊቱ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመሆንዋ ደስ ያላት ብትሆን ኖሮ ከዚያ በኋላ ከሴቶች ሁሉ የተንከራተተች ፣ ከሴቶች ሁሉ ያዘነች ፣ ከሴቶች ሁሉ በዲያብሎስና ጭፍሮቹ የተጠላች ፣ በሔሮድስ በአይሁድ የተነቀፈች መሆንዋን ስታይ ደስታዋ በጠፋ ነበር፡፡
እርስዋ ግን ደስታዋ የመነጨው ከአምላክዋ ብቻ ነበር፡፡ ፍጹም የሆነ ውስጣዊ ደስታን ማግኘት የሰው ልጅ ትልቅ ምኞቱ ነው፡፡ ሰዎች ደስታን ፍለጋ ብዙ ይደክማሉ፡፡ ድንግሊቱ ግን የደስታ ሁሉ ምንጭ የሆነው አምላክ ከእርስዋ ጋር ነውና በፍጹም ደስታ ደስ ይላታል፡፡ የድንግል ማርያም ደስታ ልጅዋ ‘ደስታችሁን የሚወስድባችሁ የለም’ ያለው ዓይነት ደስታ ነበር፡፡ ዮሐ. ፲፮፥፳፪
‘ተፈሥሒ ፍስሕት’ (ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ) ፤ ሙኃዘ
ፍሥሓ (የደስታ መፍሰሻ ሆይ) ብለን የምናመሰግናት እመቤታችን ከማንም የሚበልጥ ደስታ በእርስዋ ዘንድ ነበረ፡፡ ደስተኛ የነበረችው በምድር በነበራት ቆይታ የሚያስደስት ኑሮ ስለነበራት አይደለም፡፡ እንደ እርስዋ የተሰደደ ፣ ያለቀሰ ፣ የተጨነቀ ፍጡር የለም፡፡ እንደ ክርስቶስ መከራ የተቀበለ እንደሌለ እንደ ድንግል ማርያምም ያዘነ የለም፡፡ እርስዋ ግን ለሌሎች የሚተርፍ ወደ ኤልሳቤጥ የሚሸጋገር ፣ ሆድ ውስጥ ወዳለ
ፅንስ የሚጋባ ጥልቅ ደስታ ነበራት፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‘ተፈሢሓ በነፍሳ ፆረቶ በከርሣ’ ‘በነፍስዋ ደስ ተሰኝታ በሆድዋ ተሸከመችው’ እንዳለ እርስዋ የተደሰተችው ሥጋዊ ደስታን አልነበረም፡፡ (ድጓ ዘቅዱስ ገብርኤል )ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች አንዱ ደስታ ነውና ቅድስቲቱ ማንም ጋር ያልነበረ ደስታ ነበራት፡፡ ገላ. ፭፥፳፪
በእርግጥም ደስታን ወልዳ ደስ ባይላት ይደንቅ ነበር፡፡ እርስዋ የወለደችው ‘የመላእክት ተድላ ደስታቸው’ ነው ፤ እርስዋ የወለደችው መወለዱ ‘ለሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች’ የሚሆን ልጅን አይደለምን?
እግዚአብሔር አብ ‘በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው’ ያለውን አንድያ ልጁን ልጅዋ እንዲሆን ሠጥቶአታልና እርስዋም በምትወደው በልጅዋ ደስ ይላታል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ’ ካለ እግዚአብሔር የዘጠኝ ወር ቤቱ አድርጎ ያደረባት ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? መወለዱ ሰውና መላእክትን በደስታ እንዲዘምሩ ካደረገ የወለደችው ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን?
ጌታ ለሐዋርያቱ ‘ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ’ ካላቸው እግዚአብሔር ሁለተኛ ሰማዩ አድርጎ ዙፋን ያደረጋት በምድር ያለች የጠፈር ባልንጀራ ፣ የአርያም እኅት ማርያም ምንኛ ደስ ይላት ይሆን?
እመቤታችን ሆይ እባክሽን በአንቺ ላይ ከፈሰሰው ደስታ ቀድተሽ ወደ እኛ ወደ ኀዘንተኞቹ አፍስሺ፡፡ ኖኅ እንደ ላካት ርግብ የመከራችን ውኃ ጎደለ ብለሽ ታበሥሪን ዘንድ ወደ እኛ ነይ ‘ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ኀዘነ ልብየ’ ‘ርግቤ ሆይ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ’ እንዳለ ሊቁ፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 7 2015 ዓ.ም.
ለበዓለ ጽንሰታ ዝክር
ከብርሃን እናት ገጾች የተቆረሰ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
/channel/dnhayilemikael
ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።
በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።
ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!
#መጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ_ገብረ_ኪዳን
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 /channel/dnhayilemikael
"መለያየትን እና ጥላቻን ልንወርስ እና ልንሰብክ አይገባም" ብፁዕ አቡነ አብርሃም
መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ/ አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመስቀል ደመራ በዓል ምን መምሰል አለበት የሚለውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ እና የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ናቸው።
በመግለጫውም በበዓሉ የምንገኘውም ሆንን ከዚያ ውጪ ያለን አገልጋይ እና ምእመናን ለመስቀል ደመራ በዓል የሚደረገው እና መደረግ ያለበት ነገር ሁሉ በትዕግስት ሊደረግ ይገባል ሲሉ የገለጹት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው።
የደመራ በዓል የሚከበረው በተያዘለት ዕቅድ እና መመሪያ መሠረት ስለሆነ እና የሰዓት እቅድ ስለወጣለት በመርሐ ግብሩ መሠረት ሰዓት መከበር እንዳለበት ፤ አገልጋዮች ከተሰጣቸው የሥራ ዘርፍ ውጪ መገኘት እንደሌለባቸው አሳስበዋል።
በበዓሉ ወቅት ንግግር የሚያደርጉ አካላትም የበዓሉን መንፈሳዊነት የሚገልጹ ንግግሮችን እንዲያደርጉ እና በዓሉ የቤተ ክርስቲያን በዓል እንደመሆኑ ንግግሮቹ ከመንፈሳዊነት እንዳይዘሉ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው እና መከፋፈልን የሚሰብኩ ንግግሮች እንዳይሆኑም አሳስበዋል።
በደመራው ወቅት የሚገኙት አስተባባሪዎች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ ሊቃውንት ፣ መዘምራን እና ምእመናን ስነ ሥርዓትን የጠበቅን እና ያስጠበቅን ልንሆን ይገባልም ነው ያሉት።
ባንዲራን በተመለከተ የቤተክርስቲያኒቱን ባንዲራ እና የሀገሪቱን ባንዲራ ብቻ መያዝ የተፈቀደ በመሆኑ ከሁለቱ ውጪ የሆነ የትኛውንም ዓይነት ባንዲራ ይዞ ለመግባት መሞከር እንደማይገባ እና በቲሸርቶች ላይ መከፋፈልን የሚሰብኩ ጽሑፎችም እንደማያስፈልጉ ፤ የትኛውንም አይነት "እርችት" እና ከቤተክርስቲያን ታሪክ ጋር ግንኙነት የሌለው ቁስም እንደማይፈቀድ ገልጸዋል።
የመስቀል ደመራ በዓል በዩኔስኮ የተመዘገበ ዓለም አቀፍ በዓል ቢሆንም ለእኛ ግን መንፈሳዊ በዓል ነውና የሚታየው ሁሉ መንፈሳዊ የሆነ ተግባር ሊሆን ይገባልና መንፈሳዊ ልንሆን ይገባል ያሉት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ናቸው።
የበዓሉ ባለቤት የሆንን ኦርቶዶክሳውያን በዓሉ መንፈሳዊ መሆኑን በሥራ ልናሳይ ይገባል ፤ የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር በትዕግስት ፤ በመታዘዝ እና በጥንቃቄ ሊሆን ይገባልም ብለዋል ብፁዕነታቸው።
የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )
መሰረተ ሚዲያ
የቴሌግራም አድራሻ/channel/Meseretemedia
🌼🌼🌼🌼🌼💠🌼🌼🌼💠💠🌼
#በአርባዕቱ_ግብራት_ይጸልም_ልብ
በአራት ነገሮች ልብ ይጨልማል (አእምሮ ይጠቁራል)
1. #በጸሊአ_ቢጽ ፦ ባለንጀራን በመጥላት " ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።
1. 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2 : 11።
1.
2. #በአስተሐቅሮ፦ ሰውን በመናቅ/በማቃለል " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል" ማቴ5 : 22።
2.
3. #በቅንዓት፦ በክፉ ቅንዓት/ምቀኝነት "ቅንዓት አጥንትን ያነቅዛል" ምሳ 14፡30።
4. #በአስተአክዮ፦ ሰውን በማክፋፋት/የሰው ስም በማጥፋት "ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል" ማቴ 12 : 35።
የእኛን ልብ ያጠቆረው ፤ አእምሯችንን ያጠቆረው የትኛው ይሆን?
ለጸሎታችን እንዳይሰማ
እንዳንተያይ ፤ እንዳንግባባ የጋረደን ጨለማ
ብርሃናችን በሰው ፊት እንዳይበራ የከለከለን የልብ ጨለማ የአእምሮ የጽልመት የትኛው ይሆን???
ሀገራችን ውስጥ ብዙዎች የአእምሮ (የልብ) ጨለምተኞች አሉ ፤ ሀገር የምትታወከው ሰላም የሚታጣው በነዚህ የአእምሮ ጨለማ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ነው።
አምላካችን ሁላችንንም ከልብ ጨለማ በብርሃኑ ያውጣን!
ንዑ ናንሶሱ በብርሃኑ
ከጨለማ ወጥተን ኑ በትንሣኤው ብርሃን እንመላለስ!
ጌታን መድኃኔ ዓለም ሆይ! በመስቀልህ ወደሚደነቀው ብርሃንህ አሻግረን!
አሜን!!!
ምንጭ፦ ሕንጻ መነኮሳት
የቴሌግራም ቻነላችንን ለመቀላቀል
/channel/dnhayilemikael
አዲስ ዓመት
ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡
ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይኾን መንፈሳዊውን ብርሃን ልናበራ ይገባናል (ማቴ.5፡16)፤ በአዲሱ ዓመት፡፡ ይህም ብርሃን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያስገኝ ነው፡፡
ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ -
/channel/dnhayilemikael
ዘፈን
«ዘፈን ባህላዊ ሲሆን፣ ሀገራዊ ሲሆን፣ መልካም መልዕክት ያለው ሲሆን ችግር የለውም የሚለው በፍፁም የተሳሳተ ነው። ቤተክርስቲያን የምትፈቅደው ዘፈን አንድ ብቻ ነው እሱም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህዝብ መዝሙር ነው። ከዛ ውጪ ስለ መፅሐፍ ቅዱስ ስናወራ ባህላዊ ስለሆነ፣ ጥሩ መልዕክት ስላለው የሚለው ስህተት ነው። ባህላዊ ከተባለ የትኛው አካባቢ ዘፈን ነው ፅድቅ የሚሆነው? ዘፈን ዘፈን ነው! አሜሪካ ለተወለደ ሰው ራፕ እና ሂፕሃፕ ባህሉ ነው፣ ስለዚህ ለእሱም ሊፈቀድ ነው ማለት ነው። በቤተክርስቲያ ትምህርት ሞቅ ያለ መዝሙር ከመንፈሳዊነት ወደ ስጋዊነት ሲይል ቤተክርስቲያን ታስቆማለች፣ ማህሌት እራሱ ሲደምቅ አባቶች ያስቆማሉ! ምክንያቱም ዝማሬ ነፍስ እንጂ ስጋ የምትደሰትበት አይደለም!» መምህር ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌኀ
/channel/dnhayilemikael
ሰላም እንዴት ናችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
ነገ በቀን 28/12/2015 ዓ.ም ዕለተ እሁድ ከ8:30
በሀገረ ማርያም /ቡሌ ሆራ/ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመሠረቱ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት አደራሽ ልዩ የሆነ ስልጠና ተዘጋጅቷል
ሁላችሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ወጣቶች መጥታችሁ ስልጠናው እንድትወስዱ ተጋብዛችኋል ::
በቦታው ተገኝተን ቃሉን ለመማር እንድንበቃ እግዚአብሔር ይርዳን
አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት
"ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?"
ቅዱሱ አባት መለሰለት
"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው
ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው
ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል
ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው
በል ሒድና ተአምር ሥራ!"
⛪️⛪️⛪️⛪️
ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል።
⛪️⛪️⛪️⛪️
"ፍቅር እንዴት መቆጣት እንዳለበት አያውቅም"
ቅዱስ ማር ይስሐቅ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም ይፈርዱበታል።
⛪️⛪️⛪️⛪️
“የሚጾሙ የሚጸልዩና የሚተጉ ድቃቂ ሳንቲም እስካላስወጣቸው ድረስ በምንም ነገር ላይ የሚገኙ በችግር ላይ የሚሰቃዩትን ግን ዞር ብለው የማያዩ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ" ቅዱስ ባስልዮስ
⛪️⛪️⛪️⛪️
"እኛ መነኮሳት ነን:: እኛ የሠለጠንነው ሰዎችን ለመግደል ሳይሆን ምኞታችንን ለመግደል ነው" አባ ጴኤሜን
★ ★ ★
አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?
እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?
ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?
ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?
ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?
ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?
መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?
ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?
በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?
የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?
ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?
/channel/dnhayilemikael
"እንግዲህ
💠 ከሀሜት፣
💠 ከሀሰት ጓደኝነት፣
💠የጌታን ስም በግብዝነት ከሚጠሩ፣ 💠ምንም የማያውቁትን ከሚያታልሉ 👉👉👉በመራቅ ለጥሩ ነገር እንቅና።
💠ማንም ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ
👉የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው።
💠 ማንኛውም በመስቀል ላይ መከራ መቀበሉን የማያምን
👉ዲያብሎስ ነው።
💠 ማንም የክርስቶስን ትምህርት ለራሱ እንደሚመቸው የሚያጣምም እና ትንሳኤና የመጨረሻ ፍርድ የለም የሚል
👉 ይህም የሰይጣን የበኩር ልጅ ነው።"
ቅዱስ ፖሊካርፐስ
/channel/dnhayilemikael
💒🌾❖ #ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ❖💒🌾
👉 በሃይማኖት መጽናት
👉 ወድቆ መነሳት ~ ንስሓ መግባት
👉 ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ
👉 በእግዚአብሔርም ሕግ መጽናት
👉 #ለእግዚአብሔር ሕግ መታመን
👉 ስንፍናን ማሸነፍ በጸሎት መትጋት
(ስንፍና ወደ ክህደት ይመራል) መዝ 13÷1
👉 በማየት በመስማት ከሚመጡ ነፍስን ከሚወጉ ዓለማውያን ነገሮች መራቅ
👉 ከቅዱሳን ሕይወት መማር በቃል ኪዳናቸውም መማጸን የጠላት ዲያብሎስንም የውጊያ ስልት ማወቅ
👉 ተስፋ ወደ መቁረጥ እንዳያደርስ ያለውን መንፈሳዊ ጸጋ ማወቅ ማክበር መጠበቅ " ከመንፈሳዊ ሀብት ባዶ ነኝ አለማለት " #እግዚአብሔር አለኝ ማለት
👉 ጥቂትም ቢሆን በየጊዜው ከበጎ ሥራ አለመለየት
👉 በፈተና መጽናት ትዕግሥትን መልበስ
👉 #እግዚአብሔርን /ሃይማኖትን/ በሥጋዊ ውጤት አለመመዘን
👉 ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ
👉 በቅዱስ ቁርባን ነፍስን መቀደስ
👉 የገሃነመ እሳትን መራራነት አለመዘንጋት
👉 የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም እያሰቡ መኖር
👉 #በእግዚአብሔር ቸርነት መታመን
🌾ቸርነትህና ምህረትህ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል #በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ
መዝሙር 23፡6
/channel/dnhayilemikael
"ድንግልናቸውን እንደ ዐይን ብሌን ይጠብቁ ዘንድ ላላገቡ ደናግል ምከራቸው፣አስተምራቸው።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@ortodoxtewahedo
+++ መጻሕፍትን መስማት +++
.....
ብዙ በማዜም የምትታወቀው ቤተክርስቲያን የዜማዋ ያህል ብዙ መጻሕፍትን በንባብ ለምዕመናኗ በማሰማት ትታወቃለች፡፡ በተለምዶ ብዙ የሚዜም ስለሚመስለን ነው እንጂ ብዙ ለነፍስም ለሕይወትም የሚሆኑ ምክሮችን ተግሳጾችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ትምሕርቶችን በተለያዩ መንገድ ቀንብባ ታቀርባለች፡፡ በዚህ በኩል ግን ከማኅበረ ካህናት ጀምሮ እስከ ምዕመኑ ድረስ ይሄንን የመጻሕፍት ንባብ ያለመስማት ችግር አለ፡፡ ምክንያቶቹ ምን ምን ናቸው??
......
1ኛ ... በቅዳሴው ይሁን በሰዓታቱ ፥ በማኅሌቱም ሆነ በግብረ ሕማማቱ ፥ በስንክሳሩም ሆነ በድርሳኑ የሚነበቡ መጻሕፍትን እንደ እረፍት መስወጃ መቁጠር ነው፡፡ ተዚሞ ተዚሞ ንባቡ መቀመጫና ማረፊያ ሆነ ፤ ብዙ የቆመና የጮኸ ሰው ቢቀመጥና ቢያርፍ ባይገርምም ... አርፎና ተረጋግቶ መጻሕፍቱን ከመስማት ይልቅ ወሬ ማውሪያና መቦዘኛ መሆኑ የተለመደ ነው፡፡ በካህናቱና ሊቃውንቱ ላይ ይሔ ጠባይ መታየቱ ብዙ ባይገርምም ከምዕመናኑም ዘንድ እየተለመደ መምጣቱ አሳሳቢ ነው፡፡ እንደምሳሌ በጾመ ማርያም በሚቀደሰው ቅዳሴ ማርያም የንባብ ጊዜ ብዙ ሰዎች ሲቀመጡ ማየት እየተስተዋለ ነው፡፡
....
2ኛ የመጻሕፍቱ ንባብ ሳያልቅ አቋርጦ የዜማውን ክፍል መጀመር ፡፡ ይሄ በብዛት በቅዳሴ ሰአት የሚታይ ሲሆን በተለይ ዲያቆናቱና ንፍቁ ካህን የሚያነቧቸው በዕለቱ በግጻዌው በታዘዙት የጳውሎስ ፣ የሐዋርያት መልዕክታት እና ግብረ ሐዋርያት የንባብ ክፍሎች ላይ የተጀመረው ንባብ ሳይጠናቀቅ ወደቅዳሴው የዜማ ክፍል የመሸጋገር ነገር በብዛት ይስተዋላል፡፡ ይሄ የመጣው ሽርፍራፊ ደቂቃዎችን ለመቆጠብ ተብሎ ነው ፥ ነገር ግን ዕለቱን የተመለከተው የእግዚአብሔር መልዕክት እና ሐሳብ ተቀባዮቹ ጋር ሳይደርስ ይቋረጣል፡፡ መፍትሔውም ከልክ በላይ የተቅለጸለጹ ዜማዎችን ትቶ በምልክቱ መጮህ ቅዳሴው በተፈለገው ሰአት እንዲያልቅና ንባባቱ ለሰሚው ሳይቆራረጡ እንዲደርሱ ይሆናል፡፡
......
ሌላው ትልቅ ችግር አለማስተዋል ሲሆን ... ውዳሴ ማርያም ሲተረጎም ፣ የፍሬ ቅዳሴ ንባባት ላይ በተመስጦ ካለማዳመጥ የተነሳ የተፈለገውን መልዕክት ምዕመናን ጋር ሳይደርስ ይቀራል
መፍትሔው ... ለሰዉ ስለሚነበቡት ምንባባት አስፈላጊነት በመንገር ለዚህ የተዘጋጀ ንቃተ ሕሊና መፍጠር ነው፡፡፡ /channel/dnhayilemikael
+ ማርያማዊ ብሶት +
"ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?"
ድንግል ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ የተናገረችው የብሶት ንግግር ይኼ ብቻ ነው:: "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?"
ድንግሊቱ እንዲህ ያለችው ምን ቢደርስባት ነው?
ጌዴዎን እስራኤል መከራ ሲጸናባቸው "ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን?" ብሎ ነበር:: መሳ. 6:13
ኢያሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ :- ዋይ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ በአሞራውያን እጅ አሳልፈህ ትሰጠን ታጠፋንም ዘንድ ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? ብሎ በብሶት አልቅሶ ነበር:: ኢያሱ 7:7
ሙሴም የሕዝቡ አመፅ ሲያስጨንቀው ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፦ ለምን በባሪያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? ብሎ ተማርሮ ነበር:: ዘኍ. 11:11
ድንግል ማርያም "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ብላ የብሶት ቃል የተናገረችው ግን መከራ ሲደርስባት አልነበረም::
ወደ ግብፅ ስደት እንድትወጣ ሲነገራት "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" አላለችም:: ግርፋቱንና ሕማሙን ስታይም ኀዘንዋን ዋጥ አድርጋ ቆመች እንጂ "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" አላለችም::
ድንግል ማርያም "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ያለችው ልጅዋ ለሦስት ቀናት ከዓይንዋ በራቀበት ወቅት ነበረ:: "እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን፡ አለችው" ሉቃ. 2:48
ድንግሊቱ ለምን እንዲህ አደረግህብኝ ያለችው ስለ ሌላው መከራዋ ጊዜ ሳይሆን ክርስቶስ ከእርስዋ ዘንድ ስላልነበረባቸው ቀናት ነበር:: እንደርስዋ መንፈሳዊ ስትሆን "ጌታ ሆይ ለምን አስጨነቅኸኝ?" የምትለው እርሱ ከአንተ የራቀ መሆኑ ሲሰማህ ብቻ ነው:: "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ" "አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ?" እያልክ የምትጮኸው እግዚአብሔር ከአንተ የራቀ ሲመስልህና የተቀደሰው ማርያማዊ ብሶት ሲሰማህ ነው:: መዝ. 21:1፤10:1
እርሱ ከአንተ ጋር ከሆነ "በሞት ጥላ መካከል እንኩዋን ብትሔድ ክፉውን አትፈራም" ከአንተ የተለየ ሲመስልህ ግን "ጌታ ሆይ ምን አደረግህብኝ" ብለህ በማርያማዊ ብሶት ትጮኻለህ::
ከእርሱ ጋር ሆነህ መከራን መቀበል አይከብድህም:: መሰደድም አያስጨንቅህም:: እርሱ ከአንተ ዘንድ ከጠፋ ግን ብርሃንህ ምርኩዝህ ኃይልህ ጉልበትህ ሁሉ ከአንተ ዘንድ የሉምና ልትጸና አትችልም::
ዝምተኛዋን ድንግል ማርያም በብሶት ማናገር የቻለ አንዳች መከራ አልነበረም:: በበረሃ ከልጅዋ ጋር ከተንከራተተችበት ጊዜ ይልቅ ግን ያለ ልጅዋ ያሳለፈቻቸው ሦስት ቀናት "ልጄ ሆይ ለምን ይሄን አደረግህብኝ" ብላ እንድትጮህ አደረጓት::
ድንግል ሆይ ከአንቺ ዘንድ ለሦስት ቀን የተሰወረው ጌታ ከእኔ ሕይወት ከራቀ ዓመታት እንዳለፉ እያየሽ ይሆን? "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህበት? ነፍሱ ተጨንቃ እየፈለገችህ አይደለምን?" የማትይው ስለምንድን ነው?
ለሌላው መከራዬ የምጮኸውን ያህል ከልጅሽ መለየቴ ተሰምቶኝ በማርያማዊ ብሶት እንዳልጮህ በኃጢአት ብርድ ተይዤ መንፈሳዊ ሙቀት በእኔ ዘንድ የለም:: የምበላው የምለብሰው ሲጎድል እንጂ አምላኬን ሳጣ የሚሰማኝ ሰው አይደለሁም:: እኔ ባልጠይቅሽ እንኳን እንደ ቃና ሙሽሮች ጉድለቴን አይተሽ የማትለምኚልኝ ለምንድን ነው? ልጅሽ ወደ ወይን እንዲለውጠው ከእኔ ሕይወት በላይ ውኃ ውኃ ያለ ነገር ከወዴት ሊመጣ? ከልቤስ በላይ የድንጋይ ጋን ከየት ይገኛል?
"ንዒ ማርያም ለዕውር ብርሃኑ
ወንዒ ድንግል ለጽሙዕ አንቅዕተ ወይኑ
ኦ ኦ ትኃድግኒኑ ኦ ኦ ትመንንኒኑ
ኀዘነ ልብየ እነግር ለመኑ"
"የዕውር ብርሃኑ ማርያም ሆይ ነይ
ለተጠማው ወይን የምታፈልቂለት ማርያም ሆይ ነይ
ወዮ ትተዪኝ ይሆንን? ወዮ ትንቂኝ ይሆንን?
የልቤን ኀዘን ለማን እነግራለሁ? (መልክአ ኤዶም)
ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪ ተክለ ማርያም
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 7 2015 ዓ.ም.
/channel/dnhayilemikael
"ፍልሰታ"
"ሕጻኑም ወጣቱም ወንዱም ሴቱም ዕድሜው የገፋውም ሁሉም በፍቅር የሚጾሟት፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔትና በረከት የሚታፈስባት፡ ፍቅረ እግዚአብሔር በሰው ልቡና የሚሰለጥንባት ፈሪሃ እግዚአብሔር የሚያይልባት፡ የንሰሐና የምህረት ጾም ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡ በዓለም ያሉ ወደ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ያሉ ወደ ገዳማት የሚገሰግሱባት ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡"
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸
🔸🔹🔸
🔸
/channel/dnhayilemikael
ወልድኪ መድኃኔዓለም ሥጋ ዚኣኪ ዘለብሰ።
በዐውደ ጲላጦስ ተወቅሰ መድኃኔዓለም።
ሊቃውንት ፍቅሩን የማዳን ሥራውን ቸርነቱን በቅኔያቸው በትርጓሜያቸው በማኅሌታቸው ይገልጻሉ። ሊቁ በሞት የተገለጠ ፍቅር እንዳሉት። ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ተሰቀለ። እውነት በአደባባይ ተሰቅሎ ሁሉ አየው።
ጌታችን ሆይ በቸርነትህ በቀኝህ ከሚቆሙት ደምረን።
/channel/dnhayilemikael
+• የሕይወት ስንክሳር •+
የሕይወት ስንክሳር ሦስት ታላላቅ ክፍሎች አሏት:- ትላንት፥ ዛሬ እና ነገ::
1/ ትላንት
ትላንት ስንል የምናወራው ታሪክን ነው:: ትላንትን ከትውስታ ወይም ከማኅደር እየመዘዝን "እንዲህ ሆኖ ነበር" እንላለን:: ከዚያ ባለፈ ግን ትላንት የተባለው የሕይወት ክፍል ላይ የተጻፈው አንዴ ሆኗልና ሊቀየር የማይችል ነው:: መለስ ብለን ልንፍቀው እና እንደ አዲስ ልንጽፈውም አይቻለንም:: ብልህ ከሆንን ተምረንበት ዛሬያችንን ያማረ፤ ነጋችንን የሠመረ እናድርግበታለን::
2/ ዛሬ
ዛሬ ደግሞ ከትላንት እና ከነገ መካከል ያለ እንቆቅልሽ ነው:: ዛሬን እንደ ትላንት ታሪክ ልንለው አንችልም:: አሁን ያለ ስጦታ ነው:: ዛሬን ጣፋጭ እንዳየ ሕጻን ልጅ ፈንድቀን መጠቀም ነው:: ዛሬያችን ነገ ላይ "ትላንት" ስለሚባል አሳምረን መጻፍ ነው:: ዛሬያችን የመዳን ቀን ነው:: ኃጢያታችንን አስፍቀን፥ ክርስቶስን እንደ ሸማ ለብሰን አጊጠን "ድሮ እንዲህ ነበሩ፤ ዛሬ ግን እንዲህ ሆኑ!" መባል የምንችልበት ገጸ በረከት ነው::
2/ ነገ
ነገ ግን ምስጢር ናት:: የነገው ገጾች ገና አልተጻፈባቸውም:: ነገን "እንዲህ ነው" ብለን በእርግጠኛነት አንናገረውም:: ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል? ማን ሞቶ ማንስ ተወልዶ እንደሚያድር በእርግጠኛነት ሊናገር የሚችለው ማን ነው? የዓለም ታሪክ አይወድቁም የተባሉ ሲወድቁ፥ ብርቱ ናቸው የተባሉ ሲደቅቁ፥ ሺህ ዓመት ይንገሱ የተባሉ ሺህ ሰዓታት ሳይሞላቸው ከንግሥና ሲወርዱ፥ ይደልዎ ተብለው የተሾሙ ሲዋረዱ፥ ተወርውረው የተጣሉ ተፈልገው ሲከብሩ አሳይቷል:: ትላንት በታሪክ ልሳን ውስጥ ሕያው ናት፤ ዛሬ ደግሞ ስጦታችን ነች:: ነገ ግን ያለችው በፈጣሪ መዳፍ ብቻ ነው:: ትላንት በማለፏ ትነገራለች፥ ዛሬን እንኖራለን (ወይም እንሞታለን - ማን ያውቃል?) ነገ ግን ወደ ቀኝ ትታጠፍ ወደ ግራ ከፈጣሪ ውጪ የሚያውቅ ማንም የለም::
ይህ ሁሉ የጊዜ ግስጋሴ ግን ማብቃቱ አይቀርም:: ሊቃውንት "ጊዜ ሁሉን ያስረጃል፥ አምላክ ግን ጊዜን ያስረጃል" የሚሉት ለዚሁ ነው:: ትላንትን እያስቆጠረ፥ ዛሬን እያሳለፈ፥ ነገን ተስፋ እያስደረገ የሚነጉደው ጊዜም ተራው ሲደርስ በተራው ያረጃል:: ይህ ሲሆን የሕይወት ስንክሳራችንም ያበቃል፤ መጽሐፉም ይዘጋል::
ትላንታችን ላይ ምን ተጽፏል? ዛሬያችን ላይ ምን ለመጻፍ ተዘጋጅተናል? ነጋችንስ ምን ይል ይሆን? የሕይወታችን ስንክሳር ተጠናቅቆ በፈጣሪ ፊት ሲነበብ ምን ይናገር ይሆን?
/channel/dnhayilemikael