#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።
1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ !!
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ !!
ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።
የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።
" ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ ።
+++ ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ+++
ሥራህን ሥራ፦ ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰቶታል፤ ያንን መሥራት የእሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነው። በርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፤ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል። የሃሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን እንዲጠይቁህ፣ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገርብህ ይጠቀምባቸዋል።
ጲላጦስ፣ ሔሮድስ፣ ሐናንያ፣ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ። ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሰላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል። ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዝብ አትችልምን?
ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ ይጨቃጨቅ፡፡ አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል። የሰይጣን ውሻዎችን ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎቹን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ።
ሥራህን ሥራ፦ ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኅበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ። አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈፀም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።
ሥራህን ሥራ፦ ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልተነገረህም፤ ሰይጣን አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም። እነኚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሠራ አትችልም፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለጌታ አልሠራህም።
ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ዐለት የፀና ይሁን፣ ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፤ ትቆስልና ትናቅ ይሆናል። አንተ ግን በጸና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት እስከ መጨረሻ ጸንተህ “የሰጠኽኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ” ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል።
" ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ !!!
ቻነሉን ለመቀላቀል⤵️⤵️
/channel/dnhayilemikael
🌹እግዚአብሔርን በሰው ተጎዳሁ ብትለው ከእኔ ምን ጎደለ? ይልሀል።
🌹ከዐሥር ወዳጅ እርሱ ይበልጣልና። 🌹እንኳን የተጠላ ሞት የተፈረደበትም እስረኛ ይኖራል።
🌹ሕይወት በእግዚአብሔር እጅ ናትና ማንንም አትፍራ።
🌹 እየወደዱህም ትሞታለህ እየተጠላህም ትኖራለህ።
ሠናይ ሰንበት
/channel/dnhayilemikael
📌 በድያለሁ ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው❓
✍️•• ተስፋ አትቁረጥ! ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሐ ግባ፤ ኃጢአት ሠርተሃልን? እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ የሚጠይቅህ ድካምና ጥረት እንደ ምን ያለ ነው? “በድያለሁ [ይቅር በለኝ]” ለማለት የሚጠይቅህ ዓይነት የሕይወት መንገድ ወይም እንደ ምን ያለ መከራ ነው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት ኃጥእ ነኝ ብለህ ራስህን ባትጠራ፥ ዲያብሎስ በዚህ እንደማይነቅፍህ አስበህ ነውን? በፍጹም! እንዲያውም ንስሐ ባትገባ ይህን ከዲያብሎስ የሚመጣ ነቀፋ እንደሚኖር ጠብቅ፡፡
❖ የከሳሽ ግብሩ ንስሐ እንዳትገባ መከልከል በዚያ ንስሐ ባልገባህበት በደልም አንተን መውቀስ ነውና ንስሐ ባትገባ ይህን ጠብቅ፤ ስለዚህ ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን እንዳይወቅስህ አትከለክለውም? ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?
❖ ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ና “በድያለሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፤ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፤ መጽሐፍ ሲናገር
✍️“ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል
📖ኢሳ 43፥26
❖ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፤ ይህን ለማድረግ ድካም ጥረት አይጠይቅህም፤ አንደበተ ርቱዕ መኾን አያሻህም፤ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፤ አስቀድመህ በደልህን በሰቂለ ሕሊና በነቂሐ ልቡና ኾነህ አስባትና አንዲት ቃል ተናገር “በድያለሁ” ብለህ ተናዘዛት፡፡
📌 ምንጭ
✍️ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚 ንስሐና ምጽዋት (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ) የተተረጎመ
ቻነሉን ለመቀላቀል⤵️⤵️
/channel/dnhayilemikael
[ 🌹 ትእግስትን በተመለከተ !🌹 ]
------------------------------------------------
ምንም በመከራ ውስጥ ብንሆን !
🌹" ጊዜውን አይተህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ጠላት ለጊዜው መልካም መስሎ በሚታይ ነገር እንድትሳብ ይደክማልና፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ሥጋዊ ደስታን ከሚሰጡና ከትይንት ቤቶች ትርቅ ዘንድ ወደ እነርሱም ከመሳብ ራስህን ትጠብቅ ዘንድ እመክርሃለሁ።
ወዳጄ ሆይ ! በእግዚአብሔር ደስ የሚልህ ሰው እንደ መሆንህ መጠን ሐዋርያው “አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል” ብሎአልና የሰው ባሪያ ከመሆን ወጥተህ ለክርስቶስ ባርያ ሁነህ ኑር፡፡
🌹ለዚህም ሕይወት አርአያ ይሆኑ ዘንድ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ቅዱሳን አሉ፡፡ እነርሱ በመከራ ውስጥ ቢያልፉም በሥራቸው ሁሉ ለእግዚአብሔር ታዘው የሚኖሩ ነበሩና ከአምላካቸው ቃል ኪዳንን ተቀበሉ፡፡ ከእግዚአብሔር አምላከ ዘንድ ቃል ኪዳንን የመቀበላቸው ምሥጢርም እርሱን በማምለክ መጽናታቸው ነው፡፡
🌹ስለዚህ እኛም ከእነርሱ ጋር የመንግሥቱ ወራሾች የርስቱ ተሳታፊዎች እንድንሆን ምንም በመከራ ውስጥ ብንሆን እነርሱን አርአያ አድርገን ራሳችንን በቅድስና ሕይወት ልናመላልስ ይገባናል፡፡ "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🌹 🌷 🥀
18/2/2014
/channel/dnhayilemikael
#ክህነት_እሳት_በተባለ_በቃለ_እግዚአብሔር_ነጥሮ_የሚገኝ_ማዕረግ_ነው !!!
༺◉❖═──────◉●◉🌹🌹🌹◉●◉──────═❖◉༻
#ክህነት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርታዊ ፣ መንፈሳዊ ፣ ሐዋርያዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በሚገባ ለመፈጸምንና የዘለዓለም ሕያው ቃል በሆነው በወንጌል ያለሥጋዊ ዋጋና ጥቅም የክህነትን ተልእኮን በብቃት ለመወጣት ነው ።
ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን አሟልቶ በመፈጸም ነፍስና ሥጋን መቀደስ በእግዚብሔርና በሰው ፣ በሰውና በመላእክት ፣ በሰውና በሰው መካከል ያለው ሰላማዊ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ተግቶ ማስተማር ።
በኀጢአት የራቀውን በንስሐ አስታርቆ ቀኖና ሰጥቶ ፣ አንጽቶ እንደ ሕጉ ማቁረብ ነው መሥዋዕት እየሠዉ ጸሎት እያደረሱ አምልኮተ እግዚአብሔርን ማከናወን ነው ።
#የክህነት ምንጩ እግዚአብሔር ሲሆን ክህነትን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጠው ለአባታችን ለአዳም ነው ፤ አዳም ከእግዚአብሔር ያገኘውን ሀብተ ክህነትን ተጠቅሞ በገነት መሥዋዕት ያቀርብ ነበር ኋላም በበደለ ጊዜ ደሙን አፍሶ ከፍሬ በለስ ጋር ለውሶ መሥዋዕት በማቅረብ የእግዚአብሔርን ምሕረት ተማጽኗል ። ( ኩፋ 5 ፥ 1 )
#ክህነት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ሁሉ ልዕልና ዋልታና ምሰሶ ሲሆን ይኸውም በቅዱስ ወንጌል ትእዛዝ መሠረት ዐላማው በትክክል ሲፈጸም በእግዚአብሔር ዘንድም ሆነ በሰው ዘንድ ያሾማል ፣ ያሸልማል ያስመሰግናል ፤ ያስከብራል (ማቴ 25 ፥ 20 ) ባለሟልና ፈራጅ ያደርጋል እጥፍ ዋጋ ያሰጣል ።
#ክህነት ርኩሱን የሚቀድስ ፤ ስደተኛን ባለርስት የሚያደርግ መውረሻ መቀደሻ ነው መክበሪያ ፣ መወደጃ ነው በክርስቶስ የማዳን ሥራ ተሳታፊ ያደርጋል ‹‹ አማልክት ዘበምድር ›› ለመባል ያበቃል ከሕዝባዊነት አውጥቶ ከመላእክት ያስቆጥራል ስለዚህ ካህናት ከሕዝብ መካከል ለሕዝብ ተመርጠው በሕዝብ ላይ የተሾሙ ምድራውያን መላእክት ናቸው ። ( ዮሐ 10 ፥ 34 ) (መዝ 81 ፥ 6) ( ያዕ 60 ፥ 26 )
#ክህነት ከምድራዊ አባር ቸነፈር ከዕታዊ ኀጢአት ከሥጋዊ መቅሰፍት ብቻ የሚያድን አይደለም ሰማያዊ ጸጋ ምድራዊ ክብር የሚያጎናጽፍ የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ የማዕርጋት ሁሉ ጫፍ ነው ለሰዎች ከተሰጡት ምሥጢራት ትልቁ ምስጢር ክህነት ነው ። ስለዚህም
#ክህነት ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ጊዜያዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ሥጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ምሥጢር ነው የድኅነት አገልግሎት የሚረጋገጥበት የአምላክ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚቀርብበት የእሳት ገበታ ፣ የመለኮት ማዕድ የሚስተናገድበት ሰውንና እግዚአብሔርን የሚያገናኝ ትልቅ ሥልጣን ነው በምድርና በሰማይም የማሰርና የመፍታት ሥልጣን ያለው ሰማያዊ ስጦታ ነው ። ( ማቴ 16 ፥ 18 ) ( ማቴ 18 ፥ 18) (1ኛ ቆሮ 4 ፥ 1 ) (1ኛ ቆሮ 5 ፥ 20 )
#ክህነት ምን ያህል ክብር እንዳለው ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሲናገር ፦ ❝ የካህናት የክነታቸው ሹመት ከወርቅና ከብር ይልቅ የተፈተነ የጠራ ነው ወደ መጋረጃ ውስጥ ይገባል ለመላእክት ያልተገለጠ ሥውር ምሥጢር ሰማያዊ ማዕድ ለካህናት ገለጠላቸው ።❞ በማለት ዘምሯል ።
ወርቅ ከማዕድናት ሁሉ እንደሚበልጥ #ክህነትም ከማዕረግ ሁሉ ይበልጣልና #አንድም ወርቅ በእሳት ነጥሮ እንደሚወጣ ክህነት እሳት በተባለ በቃለ እግዚአብሔር ነጥሮ የሚገኝ ነው ። ( ዮሐ 1 ፥ 52 )
/channel/dnhayilemikael
"ጸሎት ለሚወዱ ሰዎች እግዚብሔር ያድርባቸዋል መከራ ከሚመጣባቸው ከሚያሳዝናቸው ከሰይጣን ያሳርፋቸዋል፡፡ "
/አረጋዊ መንፈሳዊ/
/channel/dnhayilemikael
አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።
ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።
(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)
🍀🌹+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ + 🌿🌹
🌹"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው
🌷"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ
🌹"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር
ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ
🌹"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ" አባ ስምዖን
🌹"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
🌹"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን
🌹
"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል" አባ ቴዎዶር
"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው
🌷
"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
🌹
ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::
🌹
"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ [ If you don’t forgive, forget heaven]
🍀🌹
/channel/dnhayilemikael
#ፆመ_ፅጌ / የፅጌ ፆም
የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ
ለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ጽጌ ጾም መቼ ነው የሚገባው እያሉ የሚጠይቁ ስላሉ ከወዲሁ ለማስታወስ ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡
በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡
ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ "አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ"፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡
እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት "ሰቆቃወ ድንግል" በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”
የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡
ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡
ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!!!
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
/channel/dnhayilemikael
🌼🌼🌼🌼🌼💠🌼🌼🌼💠💠🌼
"መለያየትን እና ጥላቻን ልንወርስ እና ልንሰብክ አይገባም" ብፁዕ አቡነ አብርሃም
መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ/ አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመስቀል ደመራ በዓል ምን መምሰል አለበት የሚለውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ እና የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ናቸው።
በመግለጫውም በበዓሉ የምንገኘውም ሆንን ከዚያ ውጪ ያለን አገልጋይ እና ምእመናን ለመስቀል ደመራ በዓል የሚደረገው እና መደረግ ያለበት ነገር ሁሉ በትዕግስት ሊደረግ ይገባል ሲሉ የገለጹት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው።
የደመራ በዓል የሚከበረው በተያዘለት ዕቅድ እና መመሪያ መሠረት ስለሆነ እና የሰዓት እቅድ ስለወጣለት በመርሐ ግብሩ መሠረት ሰዓት መከበር እንዳለበት ፤ አገልጋዮች ከተሰጣቸው የሥራ ዘርፍ ውጪ መገኘት እንደሌለባቸው አሳስበዋል።
በበዓሉ ወቅት ንግግር የሚያደርጉ አካላትም የበዓሉን መንፈሳዊነት የሚገልጹ ንግግሮችን እንዲያደርጉ እና በዓሉ የቤተ ክርስቲያን በዓል እንደመሆኑ ንግግሮቹ ከመንፈሳዊነት እንዳይዘሉ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው እና መከፋፈልን የሚሰብኩ ንግግሮች እንዳይሆኑም አሳስበዋል።
በደመራው ወቅት የሚገኙት አስተባባሪዎች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ ሊቃውንት ፣ መዘምራን እና ምእመናን ስነ ሥርዓትን የጠበቅን እና ያስጠበቅን ልንሆን ይገባልም ነው ያሉት።
ባንዲራን በተመለከተ የቤተክርስቲያኒቱን ባንዲራ እና የሀገሪቱን ባንዲራ ብቻ መያዝ የተፈቀደ በመሆኑ ከሁለቱ ውጪ የሆነ የትኛውንም ዓይነት ባንዲራ ይዞ ለመግባት መሞከር እንደማይገባ እና በቲሸርቶች ላይ መከፋፈልን የሚሰብኩ ጽሑፎችም እንደማያስፈልጉ ፤ የትኛውንም አይነት "እርችት" እና ከቤተክርስቲያን ታሪክ ጋር ግንኙነት የሌለው ቁስም እንደማይፈቀድ ገልጸዋል።
የመስቀል ደመራ በዓል በዩኔስኮ የተመዘገበ ዓለም አቀፍ በዓል ቢሆንም ለእኛ ግን መንፈሳዊ በዓል ነውና የሚታየው ሁሉ መንፈሳዊ የሆነ ተግባር ሊሆን ይገባልና መንፈሳዊ ልንሆን ይገባል ያሉት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ናቸው።
የበዓሉ ባለቤት የሆንን ኦርቶዶክሳውያን በዓሉ መንፈሳዊ መሆኑን በሥራ ልናሳይ ይገባል ፤ የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር በትዕግስት ፤ በመታዘዝ እና በጥንቃቄ ሊሆን ይገባልም ብለዋል ብፁዕነታቸው።
የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )
መሰረተ ሚዲያ
የቴሌግራም አድራሻ/channel/Meseretemedia
🌼🌼🌼🌼🌼💠🌼🌼🌼💠💠🌼
#በአርባዕቱ_ግብራት_ይጸልም_ልብ
በአራት ነገሮች ልብ ይጨልማል (አእምሮ ይጠቁራል)
1. #በጸሊአ_ቢጽ ፦ ባለንጀራን በመጥላት " ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።
1. 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2 : 11።
1.
2. #በአስተሐቅሮ፦ ሰውን በመናቅ/በማቃለል " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል" ማቴ5 : 22።
2.
3. #በቅንዓት፦ በክፉ ቅንዓት/ምቀኝነት "ቅንዓት አጥንትን ያነቅዛል" ምሳ 14፡30።
4. #በአስተአክዮ፦ ሰውን በማክፋፋት/የሰው ስም በማጥፋት "ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል" ማቴ 12 : 35።
የእኛን ልብ ያጠቆረው ፤ አእምሯችንን ያጠቆረው የትኛው ይሆን?
ለጸሎታችን እንዳይሰማ
እንዳንተያይ ፤ እንዳንግባባ የጋረደን ጨለማ
ብርሃናችን በሰው ፊት እንዳይበራ የከለከለን የልብ ጨለማ የአእምሮ የጽልመት የትኛው ይሆን???
ሀገራችን ውስጥ ብዙዎች የአእምሮ (የልብ) ጨለምተኞች አሉ ፤ ሀገር የምትታወከው ሰላም የሚታጣው በነዚህ የአእምሮ ጨለማ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ነው።
አምላካችን ሁላችንንም ከልብ ጨለማ በብርሃኑ ያውጣን!
ንዑ ናንሶሱ በብርሃኑ
ከጨለማ ወጥተን ኑ በትንሣኤው ብርሃን እንመላለስ!
ጌታን መድኃኔ ዓለም ሆይ! በመስቀልህ ወደሚደነቀው ብርሃንህ አሻግረን!
አሜን!!!
ምንጭ፦ ሕንጻ መነኮሳት
የቴሌግራም ቻነላችንን ለመቀላቀል
/channel/dnhayilemikael
አዲስ ዓመት
ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡
ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይኾን መንፈሳዊውን ብርሃን ልናበራ ይገባናል (ማቴ.5፡16)፤ በአዲሱ ዓመት፡፡ ይህም ብርሃን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያስገኝ ነው፡፡
ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ -
/channel/dnhayilemikael
ዘፈን
«ዘፈን ባህላዊ ሲሆን፣ ሀገራዊ ሲሆን፣ መልካም መልዕክት ያለው ሲሆን ችግር የለውም የሚለው በፍፁም የተሳሳተ ነው። ቤተክርስቲያን የምትፈቅደው ዘፈን አንድ ብቻ ነው እሱም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህዝብ መዝሙር ነው። ከዛ ውጪ ስለ መፅሐፍ ቅዱስ ስናወራ ባህላዊ ስለሆነ፣ ጥሩ መልዕክት ስላለው የሚለው ስህተት ነው። ባህላዊ ከተባለ የትኛው አካባቢ ዘፈን ነው ፅድቅ የሚሆነው? ዘፈን ዘፈን ነው! አሜሪካ ለተወለደ ሰው ራፕ እና ሂፕሃፕ ባህሉ ነው፣ ስለዚህ ለእሱም ሊፈቀድ ነው ማለት ነው። በቤተክርስቲያ ትምህርት ሞቅ ያለ መዝሙር ከመንፈሳዊነት ወደ ስጋዊነት ሲይል ቤተክርስቲያን ታስቆማለች፣ ማህሌት እራሱ ሲደምቅ አባቶች ያስቆማሉ! ምክንያቱም ዝማሬ ነፍስ እንጂ ስጋ የምትደሰትበት አይደለም!» መምህር ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌኀ
/channel/dnhayilemikael
ሰላም እንዴት ናችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
ነገ በቀን 28/12/2015 ዓ.ም ዕለተ እሁድ ከ8:30
በሀገረ ማርያም /ቡሌ ሆራ/ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመሠረቱ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት አደራሽ ልዩ የሆነ ስልጠና ተዘጋጅቷል
ሁላችሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ወጣቶች መጥታችሁ ስልጠናው እንድትወስዱ ተጋብዛችኋል ::
በቦታው ተገኝተን ቃሉን ለመማር እንድንበቃ እግዚአብሔር ይርዳን
❗❗🔵#ድንግል_ሆይ❗❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴 ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ።
🔵ድንግል ሆይ በቤተልሔም ካንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም አሳስቢ።
🔴👉 ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋር ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ።
🔵👉 ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መዓትን ያይደለ ምህረትን አሳስቢ
✥ያለ አንቺ ---ብርሃን የለም
✥ያለ አንቺ ----ህይወት የለም
✥ያለ አንቺ ----መኖር የለም
✥ያለ አንቺ ----ብርታት የለም
✥ያለ አንቺ ---- እቅድ የለም
✥ያለ አንቺ ----ስኬት የለም
✥ያለ አንቺ -----ደስታ የለም
✥ያለ አንቺ ------ሰላም የለም
🔵👉 የመስቀል ስር ስጦታዬ እመብርሃን ሆይ የትም ብሆን ከጎኔ ያራቅሽኝ በምሄድበት የጠበቅሽኝ እንዳልሞት ያማልድሽኝ እንዳልወድቅ የደገፍሽኝ እናቴ ጉልበቴ ብርታቴ አማላጄ ወላዲተ አምላክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ሆይ ክብር ምስጋና ይገባሻል አንቺን የሰጠኝ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
/channel/dnhayilemikael
#ወደ_እግዚአብሔር_በመጸለይሽ_ምን_አተረፍሽ?
✍አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች፦
አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይሽ ምን "ትርፍ" ታገኛለሽ?
እሷም መለሰች፦ ብዙውን ጊዜ "ምንም አላገኘሁም" ይልቁንም "ነገሮችን አጣለሁ"
እናም ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፦
"ኩራቴን" አጣሁ።
"ትዕቢቴን" አጣሁ።
"ስግብግብነቴን" አጣሁ።
"ክፉ ፍላጎቴን" አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
"ራስ ወዳድነቴን" አጣሁ።
"ተንኮለኛነቴን" አጣሁ።
"ምቀኝነቴን" አጣሁ።
"ፍትወትን" አጣሁ።
"የመዋሸት ደስታን" አጣሁ።
"የኃጢአትን ጣዕም" አጣሁ።
"ትዕግስት ማጣትን" አጣሁ።
"ተስፋ መቁረጥን" አጣሁ።
✍ አንዳንድ ጊዜ የምንጸልየው አንድን ነገር ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ህይወታችን እንድናድግ የማይፈቅዱልንን ክፉ ነገሮች እንድናጣ ነው።
ጸሎት ያስተምራል፣ ያጠናክራል እናም ይፈውሳል።*ጸሎት መልስ ይዞ ከመምጣቱ በፊት ለጸሎታችን መልስ ምቹ አድርጎ ይሰራናል። ጸሎት በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ነው!
“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18
ቻነሉን ይቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael
"እውነተኛ ክርስቲያን አባቱ ክርስቶስን ይመስላል፡፡ ይሰደዳል እንጂ አያሳድድም፡፡ ይሰደባል እንጂ አይሳደብም፡፡ የጠፉትን ፍለጋ ይደክማል እንጂ ይባስ ብሎ አይገፈትርም፡፡ በወንድሙ ውድቀት ያለቅሳል እንጂ አይደሰትም፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን አባቱ ሌላ ነው፡፡
ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና በጊዜውም ያለ ጊዜውም ሊሆን ይገባል፡፡ ባገኘን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ባጣንም ጊዜ፤ ባለጤና በሆንን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በታመምንም ጊዜ፤ ሲሳካልን ብቻ ሳይሆን ባልተሳካልንም ጊዜ ማመስገን በመለማመድ አለብን፡፡ የምስጋናችን ምንጭ የሁኔታዎች መለዋወጥ ሳይሆን ስለ አምላካችን ብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ ስንለማመድ በክብር ላይ ክብር ይጨመርልናል፤ እንደ አባታችን ኢዮብ የዲያብሎስን አፍ እንዘጋለን፡፡
ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን?” እንኪያስ "በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቻነሉን ለመቀላቀል⤵️⤵️
/channel/dnhayilemikael
🌹እንኳን ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ አመታዊ ለዋዜማ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ
🌹~~~
🌹ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ 🌹 ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ ~~~
🌹የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው 🌹በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ
🌹 ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤
🌹ቅዱስ እስጢፋኖስ መቼ ? እንዴት ዲያቆን ሆኖ ተሾመ?
👉 ዲያቆን ሆኖ የተሾመ፤ ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡
🌹በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ቅዱስ በመጀመሪያ ገማልያል በተባለ መምህር ትውፊትን፣ ኦሪትንና ነቢያቱን ተምሯል፡፡
🌹በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስብከት ወቅትም እርሱ በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ፤
👉ደቀ መዝሙሩም ሆነ፤
👉ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አደረገው፤
👉 አጋንንትም ተገዙለት፡፡ (የሐዋ.፭፥፴፬፣፮፥፭-፲ (5÷34/6÷5-10)
🌹በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት መካከል የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡
👉በመንፈስ ቅዱስ መሪነትም ወንግልን ሰብኳል፡፡
👉በቤተ ክርስቲያንም ፈተና ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰባት ዲያቆናት ሲመርጡ አንዱ እርሱ ነበር፡፡
👉የስድስቱ ዲያቆናት አለቃና የስምንት ሺህ ማኅበር መሪ ሆኗል፡፡
🌹ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህውን ማኅበረ እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት እየጠፋች ወንጌል ደግሞ እየሰፋች ሄደች፡፡ (የሐዋ.፮፥፬)
🌹ቅዱስ እስጢፋኖስም የእግዚአብሔር ጸጋና ኃይል ያደረበትና ታላቅ እንዲሁም ድንቅ ታምራትን የሚያደርግ ሰው ስለነበር በዚያን ጊዜ አይሁድ በምቀኝነት ተነሡበት፤
👉ከእርሱ ጋርም ክርክር ገጠሙ፤ ነገር ግን ሊያሸንፉት አልቻሉም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበታልና በፈጣሪ ኃይል አሸነፋቸው፡፡
🌹ከዚህም በኋላ በሐሰት ምስክር ‹‹ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› በማለት ወነጀሉት፤
👉እርሱ ግን ስለ እውነት መሰከረ እንጂ በጀ አላላቸውም፤ ሊቀ ካህናቱም በጠየቁት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር አምላኩ መሰከረ፤
👉በመጨረሻም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ፡፡ አባቶቻችሁ ከነቢያት ያሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፡፡ በመላእክትም ሥርዐት ኦሪትን ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም፡፡›› (የሐዋ. ፯፥፶፩-፶፫)
🌹በዚህም ተበሳጭተው በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ በዚህም ምስክሩን ፈጽሞ የሰማዕታት አክሊልን በጥር ፩ ቀን ተቀዳጅቷል፤ በዚህም ቀዳሜ ሰማዕታት ይባላል፡፡
🌹አይሁድ ቅዱስ እስጢፋኖስን ለማጥፋት ቀንተው ሲገድሉት ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ክርስትናን ለማጥፋት እነርሱን ሰበብ አድርጎ ለሞቱም ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርጎአቸዋል፡፡
🌹በአሁኑ ጊዜም ክርስትናን ለማጥፋት ጠላት በሰዎች ላይ እያደረ ክርስቲያኖችን ያስገድላል፤ ያስጨፈጭፋል፤ እንዲሁም ያሳድዳል፡፡ በየጊዜውም በተለያዩ ክፍለ ሀገራት በጅምላ የሚጨፈጨፉት ሕፃናት፣ አረጋዊያን እንዲሁም ወጣቶች ምንም በማያውቁት ምክንያት፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በመናገራቸው ሳቢያ፣ ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓላትን በማክበራቸውና ባህላቸውን ለማስጠበቅ በመፈለጋው ብቻ ነው፡፡
🌹 እነዚህ እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች የጠላት ተገዢ ከመሆናቸው ባሻገር ለራሳቸውና ለሌሎች ጥፋት መንሥኤ በመሆናቸው እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሐሰተኞችን በመቃወም ለእውነት መመስከር ይገባናል፡፡
ለዚህም በሃይማኖት ጸንቶ መኖር ይጠበቃልና እንጽና!
የቅዱስ እስጢፋኖስ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን፡
ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )
⬇️
➡️ መሰረተ ሚዲያ ⬅️
⬆️
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia
✝የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጸሎት
“ጌታዬ ሆይ! ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን አትንሣኝ፤ ከምረረ ገሃነምም አድነኝ፡፡ አቤቱ ሆይ! በኀልዮ ወይም በነቢብ ወይም በገቢር ብበድልኽ ይቅር በለኝ፡፡ ከድንቁርና፣ ከዝንጋዔ፣ ልል ዘሊል ከመኾን፣ ክሳደ ልቡናዬንም ከማደንደን ጠብቀኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ወደ ፈተና አታግባኝ፤ ክፉውን በመሻት የታወረውን ዓይነ ልቡናዬንም አብራልኝ፡፡ አቤቱ ሆይ! ሰው ነኝና በድያኻለኹ፤ አንተ ግን ምኅረትኽ የበዛ መዓትኽ የራቀ ጻድቅና ቸር ነኽና የነፍሴን ደካማነት ተመልክተኽ አድነኝ፡፡ ቅዱሱን ስምኽን ከፍ ከፍ አደርገው ዘንድም ረዳት የሚኾነኝ ጸጋኽን ላክልኝ፡፡ ጌታዬና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በመዝገበ ሕይወት ስሜን ጻፍልኝ፤ መጨረሻዬንም አሳምርልኝ፡፡ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ! እስከ ዛሬ ድረስ በፊትኽ ያደረግኩት ምግባር ትሩፋት የለኝም፤ ነገር ግን አኹን መዠመር እችል ዘንድ በርኅራኄኅ ርዳኝ፡፡ የቸርነትኽን ጠል በልቡናዬ ጨምርልኝ፡፡ ንጉሠ ሰማይ ወምድር የኾንክ እግዚአብሔር ሆይ! ኀጥእና ርኵስ የምኾን ባርያኽን በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ፡፡ አሜን በእውነት እንበለ ሐሰት!!!”
#ወደ_እግዚአብሔር_በመጸለይሽ_ምን_አተረፍሽ?
✍አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች፦
አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይሽ ምን "ትርፍ" ታገኛለሽ?
እሷም መለሰች፦ ብዙውን ጊዜ "ምንም አላገኘሁም" ይልቁንም "ነገሮችን አጣለሁ"
እናም ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፦
"ኩራቴን" አጣሁ።
"ትዕቢቴን" አጣሁ።
"ስግብግብነቴን" አጣሁ።
"ክፉ ፍላጎቴን" አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
"ራስ ወዳድነቴን" አጣሁ።
"ተንኮለኛነቴን" አጣሁ።
"ምቀኝነቴን" አጣሁ።
"ፍትወትን" አጣሁ።
"የመዋሸት ደስታን" አጣሁ።
"የኃጢአትን ጣዕም" አጣሁ።
"ትዕግስት ማጣትን" አጣሁ።
"ተስፋ መቁረጥን" አጣሁ።
✍ አንዳንድ ጊዜ የምንጸልየው አንድን ነገር ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ህይወታችን እንድናድግ የማይፈቅዱልንን ክፉ ነገሮች እንድናጣ ነው።
ጸሎት ያስተምራል፣ ያጠናክራል እናም ይፈውሳል።*ጸሎት መልስ ይዞ ከመምጣቱ በፊት ለጸሎታችን መልስ ምቹ አድርጎ ይሰራናል። ጸሎት በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ነው!
“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18
ቻነሉን ይቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael
✍ "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
አመ_፳ወ፯_ለመስከረም_ዘቀዳማይ_ጽጌ_በዓለ_መድኃኔዓለም_ማኅሌት.pdf
የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )
መሰረተ ሚዲያ
የቴሌግራም አድራሻ/channel/Meseretemedia
++ በሰንበት መፍረስ ++
የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡
ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡
ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡
እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ በስካር በዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!
ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 9 /2012 ዓ.ም.
ቪክቶሪያ አውስትራሊያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
/channel/dnhayilemikael
🌼🌼🌼🌼🌼💠🌼🌼🌼💠💠🌼
+++ "እግዚአብሔር የጣላት እሳት" +++
በደብተራ ኦሪት በመሠዊያው ላይ የሚነደውና መሥዋዕቱ ይቃጠልበት የነበረው እሳት ከሰማይ የወረደ ነበር። ይህም እሳት ዘወትር እንዳይጠፋ የአሮን ልጆች (ካህናቱ) ማለዳ ማለዳ እንጨት እየጨመሩ እንዲያቀጣጥሉና እንዲያነዱት እግዚአብሔር አዝዟቸዋል።(ዘሌዋ 6፥12) ከማዕጠንት ጀምሮ እስከ እንስሳት በድንኳኑ የሚቀርቡ ማናቸውም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሁሉ የሚበሉት ከሰማይ በወረደው በዚህ "የእግዚአብሔር እሳት" ነው።
ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እንዲህ አደረጉ። ለእግዚአብሔር የእጣን መሥዋዕት ማቅረብ ፈልገው ለየራሳው ጥናውን (ማዕጠንት) አነሡ። ነገር ግን በጥናው ውስጥ ያደረጉት ከሰማይ የወረደውን "የእግዚአብሔር እሳት" ሳይሆን፣ ከመንደር ጭረው ያመጡትን ወይም ራሳቸው ያቀጣጠሉትን "ሌላ እሳት" ነበር። በዚህም እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት ስላቀረቡ አምላክ ተቆጣ። በፊቱም እሳት ወጥቶ እንዲበላቸው አደረገ። እነርሱም ወዲያው ሞቱ።(ዘሌ 10፥1-3) ሊቀ ካህናቱ አሮንን እየተከተሉ እንዲያገለግሉ የተመረጡት ሁለቱ ልጆቹ ገና አገልግሎታቸውን በቅጡ ሳይጀምሩ ተቀሰፋ። ለመሆኑ እነዚህ ሁለት የኦሪት ወጣት ካህናት የተቀጡበት "የሌላ እሳት" ታሪክ ለሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ምን ምሳሌ ይኖረው ይሆን?
እግዚአብሔር በኦሪቱ ድንኳን እሳትን እንዳወረደ፣ በሐዲስ ኪዳንም የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማይ ሲወርድ ይዞልን የመጣው እሳት አለ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር፤ ወምንተ እፈቅድ ዘእንበለ አንድዶታ" - "በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ?" እንዳለን።(ሉቃ 12፥49) ይህ መድኃኒታችን በምድር ላይ የጣለው እሳት ምንድር ነው? አገልግሎቱስ እንዴት ነው?
ጌታችን በምድር የጣላት እሳት "ወንጌል" ትባላለች። ሰው ሰውነቱን ንጹሕና የተቀደሰ ሕያውም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብባት "የእግዚአብሔር እሳት" ወንጌል ነች። ይህች ወንጌል ጌታ አንድ ጊዜ በምድር የጣላት፣ እኛ ደግሞ ለዘወትር እንዳትጠፉ የምናቀጣጥላትና የምናነዳት እሳት ነች። የማቀጣጠያው እንጨቶችም ቃለ እግዚአብሔርን መስማት እና ማንበብ ናቸው። ያለ ወንጌል እሳትነት ምንም መሥዋዕት እንድናቀርብ አልተፈቀደልንም። ነገር ግን እንደ አሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ ከመንደር ቆስቁሰን ወይም ራሳችን አቀጣጥለን የምናመጣቸው "ሌላ እሳት" የተባሉ ከንቱ ፍልስፍናዎችና እንግዳ ትምህርቶች የእግዚአብሔርን ቁጣ ይቀሰቅሱብናል።
ዳግመኛም እሳት የተባለው በጥምቀት ጊዜ በሁላችንም ላይ የወረደው ጸጋ እግዚአብሔር ነው። ይህም ጸጋ ለመዳናችን ዓይነተኛ ሚና አለው። ይሁን እንጂ ልክ በደብተራ ኦሪት እንደ ወረደው እሳት ካልተንከባከብነው እና ካላቀጣጠልነው ሊዳፈን እና የሌለ ሊመስል ይችላል። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ "እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው...በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ" በማለት የሚመክረው።(2ኛ ጢሞ 1፥6) እግዚአብሔር ለሰጠን ጸጋ ማቀጣጠያዎቹ ደግሞ ጾም፣ ጸሎትና መንፈሳዊ ትሩፋት ሁሉ ናቸው። እርሱ የሰጠንን የጸጋ እሳት ከማቀጣጠል ይልቅ "ሌላ እሳት" እናምጣ ያልን ቀን ግን ታላቅ ጥፋት ያገኘናል።
በዲያቆን አቤል ካሳሁን ተጻፈ
/channel/dnhayilemikael
2016ን
የኪዳነ ምሕረት ዓመት ያድርግልን!
እርስ በእርስ የምንበላላ በላዔ ሰብኦች ነንና እስካሁን ድረስ በግፍ የበላናቸው ነፍሳት በቅተውን በምሕረት ኪዳን ልባችን የሚመለስበት ፤ የሰው ሞት ዜናን ስንሰማ እንደ ቀድሞው ዘመን የምደነግጥበት ዓመት ይሁን:: ንስሓ ከገባን ሊምረን የገባውን ቃል ፈጽመን ምሕረት የምናገኝበት የኪዳነ ምሕረት ዓመት ይሁን::
የአባይን ውኃ መገደብ ችላ የደም ጎርፍን ግን መገደብ ያቃታትን ኢትዮጵያ የሚያሻግር የምሕረት መርከብ ይታዘዝላት:: በኖኅ ዘመን የታየው የኪዳነ ምሕረት ቀስተ ደመና የጥፋት ውኃዋ አላባራ ባለው ሀገራችን ላይ ይታይ::
አድራሻ እየቀያየርን የምንፋጅበትን እሳት ያብርድልን:: አንዱ በላው ሞት የሚስቅበት ፣ አንዱ በሌላው ቁስል እንጨት የሚሰድድበት የመጨካከን ዘመን ይብቃ:: የአባቶቻቸውን ጸሎት አስታውሶ የገባውን ኪዳነ ምሕረት አስቦ እስራኤልን ይቅር ያለ ጌታ ኢትዮጵያውያንም ዛሬ ያወረድነውን እጃችንን ሳይሆን ትናንት ኢትዮጵያ ትዘረጋለች የተባለችውን እጅዋን አስቦ የኪዳነ ምሕረት ዓመት ያድርግልን::
"ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ?
ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤
ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ" ሰ. ኤርምያስ 5:21
/channel/dnhayilemikael
🌼አዲስ ዓሜት🌻
#እግዚአብሔር_የሚወዳችሁ_እናንተም_የምትወዱት_ልጆቼ!
🌻አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡
🌼 አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡
🌻ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ 🌻ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡
🌼 ዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “👉ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ 👉ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡
👉የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡
👉ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡
👉 ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ?
👉በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡
👉 ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ይቀላቀሉ)
/channel/dnhayilemikael
+ አምናለሁ እና አላምንም +
ልጁ የታመመበት አባት ነው:: ጌታን "ቢቻልህስ ልጄን ፈውስልኝ" አለው:: ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡ አለው።
ይህን ጊዜ ሰውዬው "ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው፡ አለ" ማር. 9:24
የዚህ ሰውዬ ንግግር ፍቺ የሚፈልግ ቅኔ ይሆንብኛል "አምናለሁ አለማመኔን እርዳው"
ይኼ ሰውዬ ያምናል ወይንስ አያምንም?
ያምናል እንዳንል "አለማመኔን" ይላል ፤ አያምንም እንዳንል "አምናለሁ" ይላል:: የቸገረ ነገር ነው? ሁሉን አዋቂው መድኃኔዓለም ምን ለማለት እንደፈለገ ገብቶት ልጁን ፈወሰለት:: እኔ አላዋቂው ግን "አምናለሁ አለማመኔን እርዳው" የሚለውን ቃል እየደጋገምኩት ቀረሁ::
እያመኑ አለማመን እንዴት ያለ ነው? ብዬ መላልሼ ሳጤነው ግን ሰውዬው የእኔኑ ድክመት እየተናገረ እንደሆነ ገባኝ::
አምናለሁ እላለሁ:: በእርግጥም በፈጣሪ መኖር አምናለሁ:: ሁሉን እንደሚችልም አምናለሁ::
ግን ደግሞ በእርሱ ታምኜ አላውቅምና በሥራዬ እክደዋለሁ:: ኑሮዬ "በሥራቸው ይክዱታል" ከተባሉት የሚመደብ ነው:: (ቲቶ 1:16) አቅዋሜ የማመን ኑሮዬ ያለማመን ነውና አምናለሁ አለማመኔን እርዳው ብል ለእኔ የሚገባ ጸሎት ነው::
ወረደ ተወለደ ተጠመቀ ተሰቀለ ሞተ ተነሣ ዐረገ ብዬ አምናለሁ:: በትሕትና መውረድን ፣ በንስሓ መወለድን ፣ በታናሽ እጅ ዝቅ ብሎ ጽድቅን መፈጸምን ፣ መከራን በትዕግሥት መቀበልን ፣ ከመከራ ሞት ወዲያ ተነሥቶ በክብር ከፍ ማለትን ግን እኔ ሕይወት ላይ አላውቀውም:: የምተርከው ክርስቶስ እንጂ የሚተረክ ክርስትና የለኝም:: ስለዚህ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው በልኬ የተሰፋ ጸሎት ነው::
መች በዚህ ያበቃል::
እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳው::
ከምግብ እጾማለሁ ከኃጢአት ግን አልጾምም:: ሥጋ መብላት ትቼ የሰው ሥጋ በሐሜት የምበላ ነኝና እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳሁ እላለሁ::
እጸልያለሁ አለመጸለዬን::
ቆሜ የማደርሰው ጸሎትስ አለኝ:: ግን ልቤ ሠላሳ ቦታ ደርሶ ይመለሳል:: የምጸልየው ማናገር የማልፈልገውን ሰው በግድ የማናግር ያህል የግብር ይውጣ እንጂ ነፍሴ እርሱን ሽታ አይደለምና እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው እላለሁ::
እሰግዳለሁ አለመስገዴን እርዳውስ?
ላቤ እስኪወርድ ሰግጄ አውቃለሁ:: ልቤ ግን አንዴ አልሰገደም::
ጌታ ሆይ እመጸውታለሁ አለመመጽወቴን እርዳው:: እዘምራለሁ አለመዘመሬን እርዳው:: አስቀድሳለሁ አለማስቀደሴን እርዳው:: እማራለሁ አለመማሬን እርዳው:: ሆኜ ያልሆንሁትን አድርጌ ያላደርግሁትን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና እርዳኝ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 3 2015 ዓ.ም.
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
/channel/dnhayilemikael
+++ ይህችን ዓመት ተወኝ! +++
ከዓመት እስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ
በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ
አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ
አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ
ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ
ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም
ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም
የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ
የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ!
አውቃለሁ ታውቃለህ - ቀጠሮን ሰጥቼ - እንደማላከብር
ብዙ ጊዜ አቅጄ - ብዙ ጊዜ ዝቼ - በወሬ እንደምቀር
‹ዘንድሮስ…!› እንዳልኩኝ - አምና ይሄን ጊዜ - ሰምተኸኝ ነበረ
ምንም ሳልለወጥ - ‹ዘንድሮዬ› አልፎ - በአዲስ ተቀየረ
ፍሬ የማይወጣኝ - እኔን በመኮትኮት - እጆችህ ደከሙ
እኔ ግን አለሁኝ - ዛሬም አልበቃኝም - በኃጢአት መታመሙ
የቃልህን ውኃ - በድንጋይ ልጅህ ላይ - ሳትታክት ስታፈስስ -
ዘመን ተቆጠረ
ወደ ልቤ ሳይሰርግ - ሕይወቴን ሳይለውጥ - እንዲያው ፈስሶ ቀረ
ቃልህን ጠግቤ - እያገሳሁት ነው - ሌሎች እስኪሰሙ
በቃልህ መኖር ግን - አልያዝህ አለኝ - ከበደኝ ቀለሙ
ብዙ ጥቅስ አገኘሁ - ከቅዱስ መጽሐፍህ - ገልጬ አይቼ
ከራሴ ላይ ብቻ - አንድ ጥቅስ አጣሁኝ - በበደል ተኝቼ
ውጤቴ ደካማ - ትምህርት የማይሠርጸኝ - ተማሪ ብሆንም
ይህችን ዓመት ተወኝ - ደግሞ ትንሽ ልማር - ታገሠኝ አሁንም!
እባክህ አልቆረጥ - በቅዱስ መሬትህ - ልቆይ ፍቀድልኝ
ያፈሩት ቅዱሳን - የፍሬያቸው ሽታ - መዓዛ እንዲደርሰኝ
የተሸከምከኝ ሆይ - ዛሬም ተሸከመኝ - አትሰልቸኝ አደራ
ማን ይታገሠኛል - ጠላት እየሆንኩት - አይሠሩ ስሠራ!
አታውጣኝ ከቤትህ - ብዙ ቦታ አልይዝም - ፍሬ ስለሌለኝ
ስፍራ የማያሻኝ - ቤት የማላጣብብ - ፍሬ አልባ በለስ ነኝ!
ቦታስ የሚይዙት - ባለ ምግባሮቹ - ቅዱሳንህ ናቸው
ልክ እንደ ዘንባባ - የተንዠረገገ - ተጋድሎ ጽድቃቸው!
ከሊባኖስ ዝግባ - እጅጉን የበዛ - ገድል ትሩፋታቸው!
እኔ አይደለሁም - ቦታስ የምትይዘው - የአንተው እናት ናት
ሥሮቿ በምድር - ጫፎቿ በሰማይ - ሲደርሱ ያየናት
ይሀችን ዓመት ተወኝ - ከሥርዋ እሆናለሁ - ባፈራ ምናልባት!..
ይህችን ዓመት ተወኝ - እባክህ አምላኬ - አንድ ዓመት ምንህ ናት
ሺህ ዓመት አንድ ቀን - አይደለም ወይ ለአንተ - ዓመት ኢምንት ናት!
ይሄ ዓመት አልፎ - ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ› - እስከምልህ ድረስ
እባክህን ጌታ - ይህችን ዓመት ተወኝ - የወጉን እንዳደርስ!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 5 ቀን 2001 ዓ.ም.
ሐመር መጽሔት ላይ
የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
/channel/dnhayilemikael
ጽናት!
የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን
...ቀኖና ቤተክርስቲያንን በጣሰ መንገድ የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዲገነጠሉ ከመንግስት የቀረበላቸውን ፖለቲካዊ ጥያቄ አልቀበልም በማለታቸው በዩክሬን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት የአምስት ዓመት እሥር ተፈረደባቸው።
በረከታቸው ይደርብን።
/channel/dnhayilemikael