#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
🍀🌹አስተውል!🍀🌹
ትላንትና የሞቱት ሰዎች ለዛሬ ጠዋት እቅድ ነበራቸው፤ ዛሬ ጠዋት የሞቱት ሰዎች ለዛሬ ምሽት እቅድ ነበራቸው።
ህይወትን እንደ ተራ ነገር አትውሰድ። በሰከንዶች ውስጥ ሁሉም ነገር ሊለወጥ ይችላል።
ምንጊዜም ይቅር በል!
በሙሉ ልብህ ለሌሎች ፍቅርን ስጥ፡፡
ይህን እድል እንደገና ላታገኘው ትችላለህና!
ማስተዋሉን ያድለን
/channel/dnhayilemikael መልካም ምሽት❤️
🕯የአባ እንጦንስ ምክሮች💠
✞⛪️ ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ አባ እንጦስን "ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል።
👉አባ እንጦስም እንዲህ ሲል መለሰለት
💠"በራስህ ጽድቅ አትታመን፤
💠ላለፈው አትጨነቅ
💠፤ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ።"
⛪️⛪️✞ አባ እንጦስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፦
💠"በዚች ምድር ላይ ስንኖር ህይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልጀራችን ጋር ነው።
💠ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው እግዚአብሔርን ገንዘብ እናደርጋለን፤ 💠ወንድማችንን ካስቀየምነው ግን በክርስቶስ ላይ ኃጢአትን እናመጣለን።"
⛪️⛪️⛪️✞ በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ እንጦስን "ጸልይልኝ" በማለት ይጠይቃል።
💠አባ እንጦስም "አንተ ራስህ ጥረት የማታደርግና ወደ እግዚአብሔር የማትጸልይ ከሆነ እኔም ሆንሁ እግዚአብሔር ምህረት ልናደርግልህ አንችም" አለው።
⛪️⛪️💠⛪️⛪️✞ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ፦ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።
👉 “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።”
— ማቴዎስ 6፥33
/channel/dnhayilemikael
❗❗#ህዳር_8 #አርባዕቱ_እንስሳ❗❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ህዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣
🔵👉 እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።
🔶👉 የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።
🔷👉 የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
🔴👉 ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።
🔵👉 የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።
❗👉 ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።
🔵👉 በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።
🔴👉 እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።
🔷👉 ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።
🔷👉 ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።
🔵👉 በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።
🔴👉 ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው።
🔷👉 ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።
🔵👉 ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።
❗መንፈሳውያን አመስጋኞችና መዘምራን የምትሆኑ አራቱ እንስሳት ስለ አኛ ለምኑ❗
❗አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን ሰዐሉ በእንቲአነ❗
( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት )
🔷👉 ቅዱስ ጄሮም እንዲህ አለ ፦
አርባዕቱ እንስሳት የድኅነታችን ምሥጢር የሆኑትን አራት ደረጀዋች ያስረዳሉ ።
🔷👉ገጸ ሰብእ ፦ ሥጋዌውን ( ቃል ስጋ መሆኑን )
🔷ገጸ አንበሳ ፦ ትንሣኤውን
🔷ገጸ ላህም ፦ ንጹሕ መሥዋዕት ( ቤዛ ) መሆኑን
🔷ገጸ ንሥር ፦ ዕርገቱን
🔴የእግዚአብሔርን ባሕርያት ያመለክታሉ።
ገጸ ሰብእ ፦ ጥበቡንና ዕውቀቱን
ገጸ አንበሳ ፦ ግርማውንና ኃይሉን
ገጸ ላህም ፦ ትዕግስቱን ፈታሒነቱን
ገጸ ንሥር ፦ ክብሩን ልዕልናውን
🔴አንድም አርባዕቱ እንስሳት
በአራቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ።
🔵#አርባዕቱ_እንስሳት #በእመቤታችን_ድንግል_ማርያም_ይመሰላሉ። እነሱ መንበሩን ለመሸከም እንደተመረጡ ፤ ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለችና ።
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
/channel/dnhayilemikael
+++ ምክር እና ቡጢ... +++
አንዳንዴ ሰው ተቸግሮ ወደ እኛ መጥቶ ሲያወያየን ከግለሰቡ በላይ የምንሰጠውን ምክር የምንወድ ሰዎች አለን። ያ ሰው ምን ሁኔታ ላይ ነው? ምን ይሰማዋል? ብሎ ለመረዳት ከመጣር ይልቅ ልንነግረው ባሰብነው ምክር ቀድሞ ደስ መሰኘት። አውርቶ እስኪጨርስ ትዕግሥት ማጣት። እንዴት ሰምቼ ላሳርፈው ከማለት ይልቅ ከመቼው ነግሬው ላስደንቀው (ይደነቅብኝ) የሚል ጉጉት።
መፍትሔ ብለን የምንነግረው ደግሞ ሸክም ያደከመው ሰውነቱን ጨርሶ ያላገናዘበ የሚሆንበት አጋጣሚ በጣም ብዙ ነው።
አንድ በchildhood psychology የተመረቀ አንድ ወጣት ሰው ነው አሉ። ወላጆች በተሰበሰቡበት የመጀመሪያውን ሥልጠና ሲሰጥ ለጥናቱ የመረጠው ርእስ "ዐሥርቱ ትእዛዛት ለወላጆች"/"Ten commandments for parent" በሚል ነበር። ታዲያ እርሱም እንደ ሌሎች የትዳር ወጉ ደርሶት ልክ አንድ ልጅ ወልዶ ማሳደግ እንደ ጀመረ ያ ይሰጠው የነበረውን የሥልጠና ርእስ መቀየር እንዳለበት ተሰማውና "ዐሥር ማሳሰቢያ ለወላጆች" አለው። ቀጥሎ ሁለተኛ ልጅ ወልዶ ሲያሳድግ አሁንም የቀየረው የሥልጠና ርእስ ድጋሚ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ተረዳ። ስለዚህ በስተመጨረሻ ርእሱን "ዐሥር ጥቆማ ለወላጆች" አለው ይባላል። አንዳንዴ ለሰዎች የምንሰጠው ምክር ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ሕይወት እስክታስተምረን ድረስ የምንጨክን እንኖራለን።
አንዳንድ ጊዜ ሰው ጨንቆት ወደ አንተ ሲመጣ ግዴታ የሆነ ወርቃማ አባባል እንድትነግረው ወይም በአነቃቂ ቃላት እንድታግለው ላይሆን ይችላል። ያን ሰው በዝምታ መስማት እና የተዘበራረቀው ሐሳቡን ጊዜ ወስዶ ለአንተ በመናገር እንዲያጠራ ማድረግም ትልቅ እርዳታ ነው።
@dnhayilemikael
💒🌾❖ #ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ❖💒🌾
👉 በሃይማኖት መጽናት
👉 ወድቆ መነሳት ~ ንስሓ መግባት
👉 ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ
👉 በእግዚአብሔርም ሕግ መጽናት
👉 #ለእግዚአብሔር ሕግ መታመን
👉 ስንፍናን ማሸነፍ በጸሎት መትጋት
(ስንፍና ወደ ክህደት ይመራል) መዝ 13÷1
👉 በማየት በመስማት ከሚመጡ ነፍስን ከሚወጉ ዓለማውያን ነገሮች መራቅ
👉 ከቅዱሳን ሕይወት መማር በቃል ኪዳናቸውም መማጸን የጠላት ዲያብሎስንም የውጊያ ስልት ማወቅ
👉 ተስፋ ወደ መቁረጥ እንዳያደርስ ያለውን መንፈሳዊ ጸጋ ማወቅ ማክበር መጠበቅ " ከመንፈሳዊ ሀብት ባዶ ነኝ አለማለት " #እግዚአብሔር አለኝ ማለት
👉 ጥቂትም ቢሆን በየጊዜው ከበጎ ሥራ አለመለየት
👉 በፈተና መጽናት ትዕግሥትን መልበስ
👉 #እግዚአብሔርን /ሃይማኖትን/ በሥጋዊ ውጤት አለመመዘን
👉 ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ
👉 በቅዱስ ቁርባን ነፍስን መቀደስ
👉 የገሃነመ እሳትን መራራነት አለመዘንጋት
👉 የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም እያሰቡ መኖር
👉 #በእግዚአብሔር ቸርነት መታመን
🌾ቸርነትህና ምህረትህ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል #በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ
መዝሙር 23፡6
/channel/dnhayilemikael
ጆሮህ መስማት የለመደው
ምንድን ነው?
........................................................
🌹በተጓዳኝ በቤቱ አንድ ንብ የሚያንብ ደራሲ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ከጓደኛው ጋር በሞቀ በደራው የመርካቶ ገበያ ውስጥ እየተጓዙ ሳሉ ድንገት፥ « የንብ ድምጽ ይሰማሃል?» አለው ጓደኛውን፤ ጓደኛውም « አብደሃል እንዴ? ሕዝብ በሚተራመስበት በዚህ ሁሉ ጩኸት መካከል እንዴት የንብ ድምጽ ይሰማሃል?» አለው። ደራሲውም፥ ሳንቲሞች አውጥቶ መንገዱ ላይ በተነው፤ የዚያን ጊዜ የሚተራመሰው ሰው ሁሉ የሳንቲሙን ድምጽ ሰምቶ ፊቱን ወደ እነርሱ አዞረ። የዚያን ጊዜ ደራሲውም ለባልንጀራው፥ አየህ ተመልከት « ጆሮአችን የሚሰማው ያስለመድነውን ነው።» አለው።
አንተስ ጆሮህ መስማት የለመደው ምንድን ነው?
👉በዕለተ ሰንበት የሚሰማውን የቅዳሴ ድምፅ 📢 ነው?
👉ወይስ በየዳንኪራቤቱ የሚሰማው የሙዚቃ ጩኸት?
👉የእመቤቴ ምስጋና የጽጌው ማኅሌት ?
ወይስ የዓለም ሁካታና ጫጫታ?
🌹🌹የእኛ ጆሮ የሚያደምጠው፣ የለመደውስ ምንድ ነው?
👉በየሚዲያው ጸብ ክርክርን የሚፈጥሩ ተሳዳቢዎችን ?
👉እውነትን በአደባባይ ሰቅለው የእውነትን ልብስ ለብሰው ለራሳቸው
👉ጥቅም የቆሙ ሌቦችና ሐሰተኞችን ?
ጆሯችን የሚሰማው ማንን ነው?
🌹ጆሮአችንን ስብከት ማድመጥን እናስለምደው።
🌹ጆሮአችንን ቅዳሴና መዝሙር መስማትን እናለማምደው።
🌹ጆሮአችንን የሚያንጹ ፣የሚሰሩ በጎና ውብ ቃላት መስማትንን እናስለምደው።
🌹ጆሮአችንን ቃለ እግዚአብሔር መማርን እናስለምደው። ምክንናቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ
«ጆሮአችን የሚያዳምጠው ያስለመድነውን ስለ ሆነ »
💠አንድ የዋልድባ መነኩሴ ለገዳማዊ አገልግሎት አራት ኪሎ ቢመጣ አንተም እርሱም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ብትጓዙ የእርሱ ጆሮ የለመደው የጸሎት ድምጽ ስለሆነ የሚሰማው ጫጫታ የሚያደምጠውም የሙዚቃ ድምጽ የለም።
💠ዋልድባ የሚሰማው የማኅበር ጸሎት ጣዕመ ዜማ ካልሆነ በቀር።እየጸለየ ይጓዛልና።
🌹ጆሮአችን ሁልጊዜ ሊያደምጠው የሚገባው በጎ ቃላትን ብቻ ነው።ሁካታና ጩኸት በበዛበት ዓለም ላይም ቢሆን መልካም ነገርን ለመስማት ጆሮአችንን እናስለምደው።
👉ፌዝና ቧልት ማድመጥ የለመደ ጆሮ ቁም ነገር ይሰለቸዋል።
👉ዘፈን ማድመጥ የለመደ ጆሮ መዝሙር ይደብረዋል።
👇👇⤵️⤵️⤵️
ስብከትና መዝሙር፤ ማኅሌትና ቅዳሴ ማድመጥን ለጆሮህ አስለምደው።
ቻነሉን የቀላቀሉ
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
/channel/dnhayilemikael
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
💠💠💠 መስቀል 💠💠💠
💠💞የመስቀሉ ኃይል እንደ ምን ይደንቅ?
💠በሰው ልጆች ዘንድ በመስቀሉ ኃይል የኾነው የተደረገው ለውጥ እንደ ምን ይረቅ?
💠ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን አውጥቶናልና፤ ከሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት መልሶናልና፤ ከዘለዓለም ጥፋት ወደ ዘለዓለም ልማት አሸጋግሮናልና፡፡
💠💞በመስቀሉ ያልተደረገልን በጎ ነገርስ ምን አለ?
💠ምክንያቱም በመስቀሉ ርትዕት ሃይማኖትን ዐወቅን፤ የእግዚአብሔር የጸጋውን ብዛት ተረዳን፡፡
💠በመስቀሉ ስለ እግዚአብሔር እውነት የኾነውን ዐወቅን፡፡
💠በመስቀሉ፥ ርቀን የነበርን እኛ ሕዋሳተ ክርስቶስ እስከ መኾን ደርሰን የቀረብን ኾንን፡፡
💠 በመስቀሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተካፋይ የመኾን መብት (ሥልጣን) አገኘን፡፡
💠💞በመስቀሉ የፍቅርን ኃያልነት ዐወቅን፡፡
💠 በመስቀሉ ለሌሎች መሞትን ተማርን፡፡
💠በመስቀሉ ንቀት፣ ውርደት፣ መከራ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ ዐወቅን፡፡
💠ጊዜያዊ ያይደለ የዘለዓለም በረከት ምንጭ መኾኑን ተረዳን፤ የማይታየውን እንደሚታይ አድርገን ተቀበልን፡፡
💠በመስቀሉ የተሰቀለው ይሰበካል፤ በእግዚአብሔር ማመንን እውነትም ለዓለም ኹሉ ይነገራል፡፡
💠በመስቀሉ የተሰቀለው ክርስቶስ ይሰበካል፤ በትንሣኤ ማመንንና በላይ በሰማያት ያለችውንም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትም በእውነት ያለ ሐሰት ያለ ጥርጥር ይሰበካል፡፡
💠💞ከመስቀሉ በላይ የከበረ፣ ለነፍስም ድኅነትን የሚሰጣት ምን አለ?
💠መስቀል አጋንንት ድል የተነሡበት ነው፡፡
💠መስቀል የኃጢአት ድል መንሻ የጦር ዕቃ ነው፡፡
💠መስቀል ጌታችን እባቡን የመታበት ሰይፍ ነው፡፡
💠💞መስቀል የአብ ፈቃድ፣
💠የወልድ ክብር፣
💠የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣
💠የመላእክት ጌጥ፣
💠የቤተ ክርስቲያን አጥር፣
💠የቅዱስ ጳውሎስ ውዳሴ፣ የቅዱሳን ጋሻ፣ የዓለምም ብርሃን ነው፡፡
/channel/dnhayilemikael
❗❗🔵#ድንግል_ሆይ❗❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴 ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ።
🔵ድንግል ሆይ በቤተልሔም ካንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም አሳስቢ።
🔴👉 ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋር ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ።
🔵👉 ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መዓትን ያይደለ ምህረትን አሳስቢ
✥ያለ አንቺ ---ብርሃን የለም
✥ያለ አንቺ ----ህይወት የለም
✥ያለ አንቺ ----መኖር የለም
✥ያለ አንቺ ----ብርታት የለም
✥ያለ አንቺ ---- እቅድ የለም
✥ያለ አንቺ ----ስኬት የለም
✥ያለ አንቺ -----ደስታ የለም
✥ያለ አንቺ ------ሰላም የለም
🔵👉 የመስቀል ስር ስጦታዬ እመብርሃን ሆይ የትም ብሆን ከጎኔ ያራቅሽኝ በምሄድበት የጠበቅሽኝ እንዳልሞት ያማልድሽኝ እንዳልወድቅ የደገፍሽኝ እናቴ ጉልበቴ ብርታቴ አማላጄ ወላዲተ አምላክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ሆይ ክብር ምስጋና ይገባሻል አንቺን የሰጠኝ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
/channel/dnhayilemikael
#ወደ_እግዚአብሔር_በመጸለይሽ_ምን_አተረፍሽ?
✍አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች፦
አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይሽ ምን "ትርፍ" ታገኛለሽ?
እሷም መለሰች፦ ብዙውን ጊዜ "ምንም አላገኘሁም" ይልቁንም "ነገሮችን አጣለሁ"
እናም ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፦
"ኩራቴን" አጣሁ።
"ትዕቢቴን" አጣሁ።
"ስግብግብነቴን" አጣሁ።
"ክፉ ፍላጎቴን" አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
"ራስ ወዳድነቴን" አጣሁ።
"ተንኮለኛነቴን" አጣሁ።
"ምቀኝነቴን" አጣሁ።
"ፍትወትን" አጣሁ።
"የመዋሸት ደስታን" አጣሁ።
"የኃጢአትን ጣዕም" አጣሁ።
"ትዕግስት ማጣትን" አጣሁ።
"ተስፋ መቁረጥን" አጣሁ።
✍ አንዳንድ ጊዜ የምንጸልየው አንድን ነገር ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ህይወታችን እንድናድግ የማይፈቅዱልንን ክፉ ነገሮች እንድናጣ ነው።
ጸሎት ያስተምራል፣ ያጠናክራል እናም ይፈውሳል።*ጸሎት መልስ ይዞ ከመምጣቱ በፊት ለጸሎታችን መልስ ምቹ አድርጎ ይሰራናል። ጸሎት በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ነው!
“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18
ቻነሉን ይቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael
"እውነተኛ ክርስቲያን አባቱ ክርስቶስን ይመስላል፡፡ ይሰደዳል እንጂ አያሳድድም፡፡ ይሰደባል እንጂ አይሳደብም፡፡ የጠፉትን ፍለጋ ይደክማል እንጂ ይባስ ብሎ አይገፈትርም፡፡ በወንድሙ ውድቀት ያለቅሳል እንጂ አይደሰትም፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን አባቱ ሌላ ነው፡፡
ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና በጊዜውም ያለ ጊዜውም ሊሆን ይገባል፡፡ ባገኘን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ባጣንም ጊዜ፤ ባለጤና በሆንን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በታመምንም ጊዜ፤ ሲሳካልን ብቻ ሳይሆን ባልተሳካልንም ጊዜ ማመስገን በመለማመድ አለብን፡፡ የምስጋናችን ምንጭ የሁኔታዎች መለዋወጥ ሳይሆን ስለ አምላካችን ብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ ስንለማመድ በክብር ላይ ክብር ይጨመርልናል፤ እንደ አባታችን ኢዮብ የዲያብሎስን አፍ እንዘጋለን፡፡
ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን?” እንኪያስ "በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቻነሉን ለመቀላቀል⤵️⤵️
/channel/dnhayilemikael
🌹እንኳን ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ አመታዊ ለዋዜማ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ
🌹~~~
🌹ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ 🌹 ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ ~~~
🌹የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው 🌹በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ
🌹 ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤
🌹ቅዱስ እስጢፋኖስ መቼ ? እንዴት ዲያቆን ሆኖ ተሾመ?
👉 ዲያቆን ሆኖ የተሾመ፤ ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡
🌹በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ቅዱስ በመጀመሪያ ገማልያል በተባለ መምህር ትውፊትን፣ ኦሪትንና ነቢያቱን ተምሯል፡፡
🌹በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስብከት ወቅትም እርሱ በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ፤
👉ደቀ መዝሙሩም ሆነ፤
👉ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አደረገው፤
👉 አጋንንትም ተገዙለት፡፡ (የሐዋ.፭፥፴፬፣፮፥፭-፲ (5÷34/6÷5-10)
🌹በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት መካከል የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡
👉በመንፈስ ቅዱስ መሪነትም ወንግልን ሰብኳል፡፡
👉በቤተ ክርስቲያንም ፈተና ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰባት ዲያቆናት ሲመርጡ አንዱ እርሱ ነበር፡፡
👉የስድስቱ ዲያቆናት አለቃና የስምንት ሺህ ማኅበር መሪ ሆኗል፡፡
🌹ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህውን ማኅበረ እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት እየጠፋች ወንጌል ደግሞ እየሰፋች ሄደች፡፡ (የሐዋ.፮፥፬)
🌹ቅዱስ እስጢፋኖስም የእግዚአብሔር ጸጋና ኃይል ያደረበትና ታላቅ እንዲሁም ድንቅ ታምራትን የሚያደርግ ሰው ስለነበር በዚያን ጊዜ አይሁድ በምቀኝነት ተነሡበት፤
👉ከእርሱ ጋርም ክርክር ገጠሙ፤ ነገር ግን ሊያሸንፉት አልቻሉም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበታልና በፈጣሪ ኃይል አሸነፋቸው፡፡
🌹ከዚህም በኋላ በሐሰት ምስክር ‹‹ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› በማለት ወነጀሉት፤
👉እርሱ ግን ስለ እውነት መሰከረ እንጂ በጀ አላላቸውም፤ ሊቀ ካህናቱም በጠየቁት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር አምላኩ መሰከረ፤
👉በመጨረሻም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ፡፡ አባቶቻችሁ ከነቢያት ያሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፡፡ በመላእክትም ሥርዐት ኦሪትን ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም፡፡›› (የሐዋ. ፯፥፶፩-፶፫)
🌹በዚህም ተበሳጭተው በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ በዚህም ምስክሩን ፈጽሞ የሰማዕታት አክሊልን በጥር ፩ ቀን ተቀዳጅቷል፤ በዚህም ቀዳሜ ሰማዕታት ይባላል፡፡
🌹አይሁድ ቅዱስ እስጢፋኖስን ለማጥፋት ቀንተው ሲገድሉት ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ክርስትናን ለማጥፋት እነርሱን ሰበብ አድርጎ ለሞቱም ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርጎአቸዋል፡፡
🌹በአሁኑ ጊዜም ክርስትናን ለማጥፋት ጠላት በሰዎች ላይ እያደረ ክርስቲያኖችን ያስገድላል፤ ያስጨፈጭፋል፤ እንዲሁም ያሳድዳል፡፡ በየጊዜውም በተለያዩ ክፍለ ሀገራት በጅምላ የሚጨፈጨፉት ሕፃናት፣ አረጋዊያን እንዲሁም ወጣቶች ምንም በማያውቁት ምክንያት፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በመናገራቸው ሳቢያ፣ ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓላትን በማክበራቸውና ባህላቸውን ለማስጠበቅ በመፈለጋው ብቻ ነው፡፡
🌹 እነዚህ እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች የጠላት ተገዢ ከመሆናቸው ባሻገር ለራሳቸውና ለሌሎች ጥፋት መንሥኤ በመሆናቸው እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሐሰተኞችን በመቃወም ለእውነት መመስከር ይገባናል፡፡
ለዚህም በሃይማኖት ጸንቶ መኖር ይጠበቃልና እንጽና!
የቅዱስ እስጢፋኖስ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን፡
ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )
⬇️
➡️ መሰረተ ሚዲያ ⬅️
⬆️
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia
✝የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጸሎት
“ጌታዬ ሆይ! ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን አትንሣኝ፤ ከምረረ ገሃነምም አድነኝ፡፡ አቤቱ ሆይ! በኀልዮ ወይም በነቢብ ወይም በገቢር ብበድልኽ ይቅር በለኝ፡፡ ከድንቁርና፣ ከዝንጋዔ፣ ልል ዘሊል ከመኾን፣ ክሳደ ልቡናዬንም ከማደንደን ጠብቀኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ወደ ፈተና አታግባኝ፤ ክፉውን በመሻት የታወረውን ዓይነ ልቡናዬንም አብራልኝ፡፡ አቤቱ ሆይ! ሰው ነኝና በድያኻለኹ፤ አንተ ግን ምኅረትኽ የበዛ መዓትኽ የራቀ ጻድቅና ቸር ነኽና የነፍሴን ደካማነት ተመልክተኽ አድነኝ፡፡ ቅዱሱን ስምኽን ከፍ ከፍ አደርገው ዘንድም ረዳት የሚኾነኝ ጸጋኽን ላክልኝ፡፡ ጌታዬና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በመዝገበ ሕይወት ስሜን ጻፍልኝ፤ መጨረሻዬንም አሳምርልኝ፡፡ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ! እስከ ዛሬ ድረስ በፊትኽ ያደረግኩት ምግባር ትሩፋት የለኝም፤ ነገር ግን አኹን መዠመር እችል ዘንድ በርኅራኄኅ ርዳኝ፡፡ የቸርነትኽን ጠል በልቡናዬ ጨምርልኝ፡፡ ንጉሠ ሰማይ ወምድር የኾንክ እግዚአብሔር ሆይ! ኀጥእና ርኵስ የምኾን ባርያኽን በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ፡፡ አሜን በእውነት እንበለ ሐሰት!!!”
#ወደ_እግዚአብሔር_በመጸለይሽ_ምን_አተረፍሽ?
✍አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች፦
አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይሽ ምን "ትርፍ" ታገኛለሽ?
እሷም መለሰች፦ ብዙውን ጊዜ "ምንም አላገኘሁም" ይልቁንም "ነገሮችን አጣለሁ"
እናም ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፦
"ኩራቴን" አጣሁ።
"ትዕቢቴን" አጣሁ።
"ስግብግብነቴን" አጣሁ።
"ክፉ ፍላጎቴን" አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
"ራስ ወዳድነቴን" አጣሁ።
"ተንኮለኛነቴን" አጣሁ።
"ምቀኝነቴን" አጣሁ።
"ፍትወትን" አጣሁ።
"የመዋሸት ደስታን" አጣሁ።
"የኃጢአትን ጣዕም" አጣሁ።
"ትዕግስት ማጣትን" አጣሁ።
"ተስፋ መቁረጥን" አጣሁ።
✍ አንዳንድ ጊዜ የምንጸልየው አንድን ነገር ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ህይወታችን እንድናድግ የማይፈቅዱልንን ክፉ ነገሮች እንድናጣ ነው።
ጸሎት ያስተምራል፣ ያጠናክራል እናም ይፈውሳል።*ጸሎት መልስ ይዞ ከመምጣቱ በፊት ለጸሎታችን መልስ ምቹ አድርጎ ይሰራናል። ጸሎት በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ነው!
“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18
ቻነሉን ይቀላቀሉ
/channel/dnhayilemikael
✍ "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
አመ_፳ወ፯_ለመስከረም_ዘቀዳማይ_ጽጌ_በዓለ_መድኃኔዓለም_ማኅሌት.pdf
የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )
መሰረተ ሚዲያ
የቴሌግራም አድራሻ/channel/Meseretemedia
ልጆቼ፦ እግዚአብሔርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ልናቀርብ ይገባናል፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን?
እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሔርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እግዚአብሔርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
/channel/dnhayilemikael
†
🌼 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 🌼
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !
🕊
[ “ ቅዱሳንን ትመስላቸው ዘንድ ! " ]
------------------------------------------------
" ወዳጄ ሆይ ! ፍቅርንና ራስን መግዛትን ገንዘብህ አድርገህ ተመላለስ፡፡ ምክንያቱም ትልቅ ዋጋ አላቸውና፡፡ እነዚህ ካሉህ እግዚአብሔር ሰውነትህን ማደሪያው ያደርገዋል። አንተም የእውነተኛ ተሐራሚ ጠባይን ገንዘብህ ታደርጋለህ፡፡ ስለዚህም ቅብዝብዝና በአንድ ቦታ ረግቶ የማይቀመጥ ሰው እንዳትሆን አንተን ከወንድሞች ኅብረት ሊነጥሉህ የሚያስቡትን ሰዎች ምክር አትስማ፡፡
በወጣኒነት ሳለህ የነበረህን ትጋት እንዳታጣ ተጠንቀቅ፡፡ ነገር ግን ይህን ትጋትህን እስከ መጨረሻው ጠብቅ፡፡ ክፉ ንግግር ወይም መሓላ ከከፈርህ አይገኝ፡፡ ቅዱሳንን ትመስላቸው ዘንድ ትሕትናን ገንዘብህ አድርግ፡፡
በንግግርህ ሁሉ “ይቅር በሉኝ” ማለትን ልመድ፡፡ ይህ ከዚህ ዓለም ተግባር ፈጽሞ እንድትርቅ በማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋናን የምታገኝበት ሕይወት እንዲኖርህ ያግዝሃል፡፡ ወደ ትሕርምት ሕይወት በመጣህ ጊዜ ወርቅ ወይም ብር ወይም ልብስ ይዘህ አትምጣ [ወይም የአንተ እንዳልሆኑ ከእግዚአብሔር ያገኘሃቸው እንደሆኑ አስብ]
በፊትህ እግዚአብሔርን አድርግ እንጂ ፤ እንደ ጌታችን እንደ መድኀኒታችን አስተምህሮ እነዚህ ከአንተ ዘንድ እንዲኖሩ ፈልግ፡፡
እነዚህም እምነት ፣ ራስን መግዛት ፣ ትዕግሥት ፣ ትሕትናና እነዚህን የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ከእግዚአብሔር የምናገኛቸው የእርሱ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ለእርሱ ክብር ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡"
🕊
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
† † †
🌼 🍒 🌼
/channel/dnhayilemikael
"አምስቱ የንሰሃ መንገዶች"
ቅዱስ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው
💠የንሳሃን መንገዶች ልዘርዝር?
💠 የንስሃ መንገዶች ብዙ ናቸው ሁሉም ወደ መንገስተ ሰማያት ይመራሉ፡
💠1/ የመጀመሪያው መንገድ ኃጢአትን መንቀፍ (መለየት-condemnation) ነው።
⛪️ ኃጢአታችሁን ከእናነተ አውግዙ ይህንን ማድረጋችሁ ጌታ ፊት ይቅርታን ያሰጣችኋል። ኃጢአቱን አንድ ጊዜ ያወገዘ ሰው እነዛን ኃጢአቶች ድጋሚ የመስራት እድሉ ይቀንሳል።
🛐ህሊናህ ከሳሽህ እንዲሆን አነሳሳው (Stir up your own conscience) ይህን ካደረክ በጌታ የፍርድ ዙፋን ፊት ስትቆም የሚከስህ አይኖርም።
🛐ይህ የመጀመሪያው የንሳሃ መንገድ ነው ነገር ግን ቀጥለን የምናየው ሁለተኛ መንገድ ከመጀመሪያው መንገድ ያነሰ ወይም ዝቅ ያለ አይደለም።
💠💠💠2/ሁለተኛው መንገድ በሰዎች የደረሰብንን በደል መርሳት፤ ንዴታችንን መቆጣጠርና ከእኛ ጋር አብረው የእግዚአብሔር ባሪያ የሚሆኑትን ሰዎች ኃጢአት ይቅር ማለት ነው።
🛐 ይህንን በደንብ ካደረግን እኛም እግዚአብሔር ላይ ያደረግናቸው ኃጢአቶች ይሰረዩልናል። ጌታም በማቴዎስ ወንጌል ላይ እንዲህ ይላል “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና” (ማቴ 6፥14)። ይህ ንሳሃን የምናገኝበት ሁለተኛ መንገድ ነው።
💠💠💠3/ ሦስተኛውን የንስሃ መንገድ ማወቅ ትፈልጋላችሁ?👉 ጸሎት ነው። ይህ ጸሎት ከልብ የሆነ፤ በተመስጦ፤ በትኩረት የሆነ እና ከልብ የሚመነጭ ጸሎት ነው።
💠💠🛐4/ አራተኛውን የንሰሃ መንገድ ማወቅ ከፈለጋችሁ እነግራችኋለው ይህም ምጽዋት ነው። ምጽዋት እጅግ በጣም ኃይል አለው።
5/የመጨረሻው መንገድ ትህትና ነው። ይህ መንገድ እንደሌሎቹ መንገዶች ኃጢአትን የማሸነፍ ኃይል አለው። በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 18 ላይ ያለውን ቀራጭ ተመልከቱ ስለራሱ እሚናገረው አንዳች ጥሩ ምግባር የለውም። በጥሩ ምግባር ቦታ ትህታናን አቀረበ በዚህም ኃጢአቱ ተሰረየለት።
💠ስለዚህ እስካሁን አምስቱን የንስሃ መንገዶች አሳየኋችሁ እነሱም ኃጢአትን ማውገዝ፤ የሌሎችን ኃጢአት ይቅር ማለት፤ ጸሎት፤ ምጽዋት እና ትህትና ናቸው።
💠ስለዚህ ስራ ፈት አትሁኑ ሁሉንም መንገዶች በየቀኑ አተግብሯቸው።
💠 እነዚህ መንገዶች ከባዶች አይደሉም ድህነትም እንደ ምክንያት ሊሆን አይችልም። እጅግ በጣም ድሃ ብትሆኑም እነዚህን ሁሉ ነገሮች ማድረግ ትችላላችሁ ቁጣን አስወግዳችሁ ትህትናን ልበሱ፤ ጠንክራችሁ ጸልዩ፤ ኃጢአታችሁን አውግዙ።
👉ድህነት እነዚህን የንስሃ መንገዶች እንዳንለማመድ መሰናክል ሊሆን አይችልም።
👉አይደለም ሌሎቹን ብር የሚያስፈልገውን ምጸዋትን እንኳን እንዳንሰጥ አይከለክለንም።
👉በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21 ቁጥር 2 ላይ ያለው የድሃዋ መበለት ታሪክ ትዝ ይላችኋል? አሁን ቁስላችንን ማከም የምንችልባቸውን መንገዶች ተምረናል እነዚህን መንገዶች እናተግብራቸው። በንስሃው መንገድ ጤንነትን አግኝተን ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል እንብቃ። በክርስቶስ መንግስት ያለውን ክብር ተሞልተን በጸጋው፤ በርህራሔውና በምህረቱ ዘላለማዊውን ሃሴት እናገኛለን።
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael
እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን
ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ።
💠#በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።
💠በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።
💠ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!
#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
@dnhayilemikael
🌹 #ተፈጸመ_ማህሌተ_ጽጌ.. ✝️👏❤️💒
🌹ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ማህሌተ ጽጌ ስሙር ተፈጸመ ናሁ አክሊል አክሊል ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግስቱ!
🌹እነሆ በእመቤታችን ስም ተሰባስበን 🌹አበባ🌹 ይዘን
🌹 ልጅዋን በአበባ
🌹እርስዋን በጽጌረዳ እየመሰልን የምንዘምርበት ያ የተወደደው የምስጋና የዝማሬ ወር አለፈ
🌹 እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ የጊዮርጊስ የክብር ዘውድ ነሽ! እያሉ በተመስጦ እንደ ቅዱስ ያሬድ የቅዱስ ያሬድ ልጆች ሊቃውንቱ እናታቸውን ሲያመሰግኑ የሚያሳይ ግሩም (ማህሌተ ጽጌ)
🌹እመቤታችን ዘውድነቷ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን ውዳሴዋን ቅዳሴዋን እየደገመ ስሟን እየጠራ ለሚማጸን በአማላጅነቷ በቃል ኪዳኗ ለሚያምን ሁሉ ዘውድ ናት!
🌹ምዕመናንም ትምክህተ ዘመድነ! እያሉ ይዘምሩላታል፤ ያመስግኗታል!
🌹ድንግል ሆይ የባህርያችን መመኪያ ነሽ!
🌹ተስፋችን ነሽ!
🌹የድህነታችን ምልክታችን ነሽ! እያሉ በእናትነቷ ጥላ ስር ያሉ ምዕመናን ይዘምሩላታል!
🌹እርስዋም እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ትባርካቸዋለች!
🌹ሁላችንም እናታችን ትባርከን!
ለእኛም ለልጆችሽ ሞገስ ሁኝን አማላጅነትሽ ቃልኪዳንሽ አይለየን!!✝️👏
ዲ/ን እስራኤል 2/3/2016
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael
እንኳን ለሰማዕታት ጽድቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ
ስለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምን እንላለን ?
💠በመልአከ ብስራት የተጸነሰው
💠በማህጸን ሳለ ለእመቤታችንን ለአምላኩ የሰገደ
💠ስጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ስወለድ የአባቱን አንደበት የዘጋ
💠በበረሃ ያደገ
💠ልብሱ የግመል
💠ምግቡም አንበጣና የበረሐ ማር የሆነ
💠በበረሐ የሚጮህ አዋጅ ነጋር(መምህረ ንስሐ )
💠ጥምቀተ ንስሐ ያጠምቅ የነበረ
💠መንገድ ጠራግ (የሰዎችን ልቡና ከክፋት እንዲመለሱ ጌታችን ከማስተማሩ አስቀድሞ የሰበከ)
🌹መምህረ ትህትና
💠የጫማውን ማሰሪያ ልፈታ የመይገባኝ ስል ጌታውን አምላኩን መለኮትን ለማጥመቅ የበቃ
💠መለኮትን ያጠመቀው
💠 ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ ተብሎ የተነገረለት
💠ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰከረ
💠ንጉስን ጭምር ሳይፈራ ከክፋት እንድመለስ የሚገስጽ (ሰማዕተ ጽድቅ )
💠ስለ እውነት ስለ ሕገ እግዚአብሔር ሰማዕትነትን የቀበለ
ማቴ 3÷1-ፍጸሜ /11÷11/
ማቴ 14÷1-ፍጸሜ
ማር 1÷1_ፍጻሜ
ሉቃ 1÷5-25
ዮሐ 1÷6-10/1÷19-34
ጸሎቱ በረከቱ ጸጋው አይለየን
አምላከ ዮሐንስ ሀገራችን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን
ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን ይጠብቅልን እኛ ክርስቲያኖችን በአምነ ሥላሴ በተዋህዶ ሃይማኖት በምግባር በትሩፋት ምስጢራትን በመቀበል አጽንቶ ያኑረን !አሜን
ዲ/ን እስራኤል 30/2/2016 መሠረተ ሚዲያ
/channel/dnhayilemikael
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።
1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ !!
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ !!
ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።
የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።
" ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ ።
+++ ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ+++
ሥራህን ሥራ፦ ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰቶታል፤ ያንን መሥራት የእሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነው። በርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፤ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል። የሃሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን እንዲጠይቁህ፣ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገርብህ ይጠቀምባቸዋል።
ጲላጦስ፣ ሔሮድስ፣ ሐናንያ፣ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ። ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሰላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል። ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዝብ አትችልምን?
ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ ይጨቃጨቅ፡፡ አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል። የሰይጣን ውሻዎችን ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎቹን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ።
ሥራህን ሥራ፦ ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኅበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ። አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈፀም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።
ሥራህን ሥራ፦ ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልተነገረህም፤ ሰይጣን አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም። እነኚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሠራ አትችልም፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለጌታ አልሠራህም።
ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ዐለት የፀና ይሁን፣ ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፤ ትቆስልና ትናቅ ይሆናል። አንተ ግን በጸና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት እስከ መጨረሻ ጸንተህ “የሰጠኽኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ” ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል።
" ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ !!!
ቻነሉን ለመቀላቀል⤵️⤵️
/channel/dnhayilemikael
🌹እግዚአብሔርን በሰው ተጎዳሁ ብትለው ከእኔ ምን ጎደለ? ይልሀል።
🌹ከዐሥር ወዳጅ እርሱ ይበልጣልና። 🌹እንኳን የተጠላ ሞት የተፈረደበትም እስረኛ ይኖራል።
🌹ሕይወት በእግዚአብሔር እጅ ናትና ማንንም አትፍራ።
🌹 እየወደዱህም ትሞታለህ እየተጠላህም ትኖራለህ።
ሠናይ ሰንበት
/channel/dnhayilemikael
📌 በድያለሁ ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው❓
✍️•• ተስፋ አትቁረጥ! ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሐ ግባ፤ ኃጢአት ሠርተሃልን? እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ የሚጠይቅህ ድካምና ጥረት እንደ ምን ያለ ነው? “በድያለሁ [ይቅር በለኝ]” ለማለት የሚጠይቅህ ዓይነት የሕይወት መንገድ ወይም እንደ ምን ያለ መከራ ነው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት ኃጥእ ነኝ ብለህ ራስህን ባትጠራ፥ ዲያብሎስ በዚህ እንደማይነቅፍህ አስበህ ነውን? በፍጹም! እንዲያውም ንስሐ ባትገባ ይህን ከዲያብሎስ የሚመጣ ነቀፋ እንደሚኖር ጠብቅ፡፡
❖ የከሳሽ ግብሩ ንስሐ እንዳትገባ መከልከል በዚያ ንስሐ ባልገባህበት በደልም አንተን መውቀስ ነውና ንስሐ ባትገባ ይህን ጠብቅ፤ ስለዚህ ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን እንዳይወቅስህ አትከለክለውም? ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?
❖ ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ና “በድያለሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፤ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፤ መጽሐፍ ሲናገር
✍️“ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል
📖ኢሳ 43፥26
❖ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፤ ይህን ለማድረግ ድካም ጥረት አይጠይቅህም፤ አንደበተ ርቱዕ መኾን አያሻህም፤ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፤ አስቀድመህ በደልህን በሰቂለ ሕሊና በነቂሐ ልቡና ኾነህ አስባትና አንዲት ቃል ተናገር “በድያለሁ” ብለህ ተናዘዛት፡፡
📌 ምንጭ
✍️ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚 ንስሐና ምጽዋት (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ) የተተረጎመ
ቻነሉን ለመቀላቀል⤵️⤵️
/channel/dnhayilemikael
[ 🌹 ትእግስትን በተመለከተ !🌹 ]
------------------------------------------------
ምንም በመከራ ውስጥ ብንሆን !
🌹" ጊዜውን አይተህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ጠላት ለጊዜው መልካም መስሎ በሚታይ ነገር እንድትሳብ ይደክማልና፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ሥጋዊ ደስታን ከሚሰጡና ከትይንት ቤቶች ትርቅ ዘንድ ወደ እነርሱም ከመሳብ ራስህን ትጠብቅ ዘንድ እመክርሃለሁ።
ወዳጄ ሆይ ! በእግዚአብሔር ደስ የሚልህ ሰው እንደ መሆንህ መጠን ሐዋርያው “አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል” ብሎአልና የሰው ባሪያ ከመሆን ወጥተህ ለክርስቶስ ባርያ ሁነህ ኑር፡፡
🌹ለዚህም ሕይወት አርአያ ይሆኑ ዘንድ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ቅዱሳን አሉ፡፡ እነርሱ በመከራ ውስጥ ቢያልፉም በሥራቸው ሁሉ ለእግዚአብሔር ታዘው የሚኖሩ ነበሩና ከአምላካቸው ቃል ኪዳንን ተቀበሉ፡፡ ከእግዚአብሔር አምላከ ዘንድ ቃል ኪዳንን የመቀበላቸው ምሥጢርም እርሱን በማምለክ መጽናታቸው ነው፡፡
🌹ስለዚህ እኛም ከእነርሱ ጋር የመንግሥቱ ወራሾች የርስቱ ተሳታፊዎች እንድንሆን ምንም በመከራ ውስጥ ብንሆን እነርሱን አርአያ አድርገን ራሳችንን በቅድስና ሕይወት ልናመላልስ ይገባናል፡፡ "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🌹 🌷 🥀
18/2/2014
/channel/dnhayilemikael
#ክህነት_እሳት_በተባለ_በቃለ_እግዚአብሔር_ነጥሮ_የሚገኝ_ማዕረግ_ነው !!!
༺◉❖═──────◉●◉🌹🌹🌹◉●◉──────═❖◉༻
#ክህነት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርታዊ ፣ መንፈሳዊ ፣ ሐዋርያዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በሚገባ ለመፈጸምንና የዘለዓለም ሕያው ቃል በሆነው በወንጌል ያለሥጋዊ ዋጋና ጥቅም የክህነትን ተልእኮን በብቃት ለመወጣት ነው ።
ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን አሟልቶ በመፈጸም ነፍስና ሥጋን መቀደስ በእግዚብሔርና በሰው ፣ በሰውና በመላእክት ፣ በሰውና በሰው መካከል ያለው ሰላማዊ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ተግቶ ማስተማር ።
በኀጢአት የራቀውን በንስሐ አስታርቆ ቀኖና ሰጥቶ ፣ አንጽቶ እንደ ሕጉ ማቁረብ ነው መሥዋዕት እየሠዉ ጸሎት እያደረሱ አምልኮተ እግዚአብሔርን ማከናወን ነው ።
#የክህነት ምንጩ እግዚአብሔር ሲሆን ክህነትን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጠው ለአባታችን ለአዳም ነው ፤ አዳም ከእግዚአብሔር ያገኘውን ሀብተ ክህነትን ተጠቅሞ በገነት መሥዋዕት ያቀርብ ነበር ኋላም በበደለ ጊዜ ደሙን አፍሶ ከፍሬ በለስ ጋር ለውሶ መሥዋዕት በማቅረብ የእግዚአብሔርን ምሕረት ተማጽኗል ። ( ኩፋ 5 ፥ 1 )
#ክህነት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ሁሉ ልዕልና ዋልታና ምሰሶ ሲሆን ይኸውም በቅዱስ ወንጌል ትእዛዝ መሠረት ዐላማው በትክክል ሲፈጸም በእግዚአብሔር ዘንድም ሆነ በሰው ዘንድ ያሾማል ፣ ያሸልማል ያስመሰግናል ፤ ያስከብራል (ማቴ 25 ፥ 20 ) ባለሟልና ፈራጅ ያደርጋል እጥፍ ዋጋ ያሰጣል ።
#ክህነት ርኩሱን የሚቀድስ ፤ ስደተኛን ባለርስት የሚያደርግ መውረሻ መቀደሻ ነው መክበሪያ ፣ መወደጃ ነው በክርስቶስ የማዳን ሥራ ተሳታፊ ያደርጋል ‹‹ አማልክት ዘበምድር ›› ለመባል ያበቃል ከሕዝባዊነት አውጥቶ ከመላእክት ያስቆጥራል ስለዚህ ካህናት ከሕዝብ መካከል ለሕዝብ ተመርጠው በሕዝብ ላይ የተሾሙ ምድራውያን መላእክት ናቸው ። ( ዮሐ 10 ፥ 34 ) (መዝ 81 ፥ 6) ( ያዕ 60 ፥ 26 )
#ክህነት ከምድራዊ አባር ቸነፈር ከዕታዊ ኀጢአት ከሥጋዊ መቅሰፍት ብቻ የሚያድን አይደለም ሰማያዊ ጸጋ ምድራዊ ክብር የሚያጎናጽፍ የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ የማዕርጋት ሁሉ ጫፍ ነው ለሰዎች ከተሰጡት ምሥጢራት ትልቁ ምስጢር ክህነት ነው ። ስለዚህም
#ክህነት ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ጊዜያዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ሥጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ምሥጢር ነው የድኅነት አገልግሎት የሚረጋገጥበት የአምላክ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚቀርብበት የእሳት ገበታ ፣ የመለኮት ማዕድ የሚስተናገድበት ሰውንና እግዚአብሔርን የሚያገናኝ ትልቅ ሥልጣን ነው በምድርና በሰማይም የማሰርና የመፍታት ሥልጣን ያለው ሰማያዊ ስጦታ ነው ። ( ማቴ 16 ፥ 18 ) ( ማቴ 18 ፥ 18) (1ኛ ቆሮ 4 ፥ 1 ) (1ኛ ቆሮ 5 ፥ 20 )
#ክህነት ምን ያህል ክብር እንዳለው ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሲናገር ፦ ❝ የካህናት የክነታቸው ሹመት ከወርቅና ከብር ይልቅ የተፈተነ የጠራ ነው ወደ መጋረጃ ውስጥ ይገባል ለመላእክት ያልተገለጠ ሥውር ምሥጢር ሰማያዊ ማዕድ ለካህናት ገለጠላቸው ።❞ በማለት ዘምሯል ።
ወርቅ ከማዕድናት ሁሉ እንደሚበልጥ #ክህነትም ከማዕረግ ሁሉ ይበልጣልና #አንድም ወርቅ በእሳት ነጥሮ እንደሚወጣ ክህነት እሳት በተባለ በቃለ እግዚአብሔር ነጥሮ የሚገኝ ነው ። ( ዮሐ 1 ፥ 52 )
/channel/dnhayilemikael
"ጸሎት ለሚወዱ ሰዎች እግዚብሔር ያድርባቸዋል መከራ ከሚመጣባቸው ከሚያሳዝናቸው ከሰይጣን ያሳርፋቸዋል፡፡ "
/አረጋዊ መንፈሳዊ/
/channel/dnhayilemikael
አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።
ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።
(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)
🍀🌹+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ + 🌿🌹
🌹"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው
🌷"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ
🌹"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር
ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ
🌹"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ" አባ ስምዖን
🌹"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
🌹"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን
🌹
"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል" አባ ቴዎዶር
"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው
🌷
"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
🌹
ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::
🌹
"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ [ If you don’t forgive, forget heaven]
🍀🌹
/channel/dnhayilemikael
#ፆመ_ፅጌ / የፅጌ ፆም
የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ
ለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ጽጌ ጾም መቼ ነው የሚገባው እያሉ የሚጠይቁ ስላሉ ከወዲሁ ለማስታወስ ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡
በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡
ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ "አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ"፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡
እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት "ሰቆቃወ ድንግል" በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”
የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡
ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡
ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!!!
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
/channel/dnhayilemikael
🌼🌼🌼🌼🌼💠🌼🌼🌼💠💠🌼