dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ድነኀል_ወይስ_አልዳንክም?

◦ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በአንድ መጽሐፋቸዉ እንዲህ ይላሉ። አንድ ወጣት ልጅ እንዲህ ብሎ ጠይቆኛል “አንድ ሰው ድነኀል ወይስ አልዳንኽም?” ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድ ነው?

◦ መጀመሪያ ይሄ ሰዉ እዉነተኛ ኦርቶዶክስ እንዳልሆነ ማወቅ አለብህ። በእርግጠኝነት ይሄ ሰዉ ፕሮቴስታንት ነዉ ወይንም ቢያንስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ውስጥ ነዉ የሚኖረዉ፣ ባህሉም የፕሮቴስታንት ነው። ከዚህ በፊት የተቀበልካቸዉን ምስጢራትንና ጥምቀትን እንደ ምንም ቆጥሮ፣ በሃይማኖትህ ላይ ጥርጥር ለመሙላት በመሞከር፣ ባለፈዉ የሕይወት ዘመንህ ሁሉ አሕዛብ እንደነበርክ አድርጎ እንደ ገና እመንና ዳን ሊልህ ነው። ይሄ ሰዉ በፍጹም ኦርቶዶክስ ሊሆን አይችልም አነጋገሩም ይገልጠዋል።

◦ ለማንኛዉም እንዲህ ብለህ ልትመልስለት ትችላለህ “በጥምቀት ከአዳም የውርስ ኀጢአት ድኜያለሁ፤ ይሄ ድኅነት የሚገኛዉ በደመ ክርስቶስ የቤዛነትንና የድኅነት ኀይል ነው። ነገር ግን የመጨረሻዉ ድኅነት በስጋ ስንለይ የሚገኝ ነው። አሁንም በውጊያ ላይ ነን “መጋዳላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፣ ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር እንጂ።” (ኤፌ. 6፥12)። ይሄንን ውጊያ ድል ስናደርግና ስናሸንፍ ድኅነትን እናገኛለን…”

◦ በስጋ እስካለን ድረስ “ድል ነስተናል፤ ድኅነትን አግኝተናል” ልንል አንችልም። ስለዚህ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት አታከብርም ወይም የተጠመቁበትን ዕለት፤ ይልቁንም ከዚህ ዓለም የተለዩበትን ወይንም መስዋዕት የሆኑበትን ቀን ታከብራለች እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና “ዋነኞቻችሁን አስቡ፣ የኑሮአቸዉንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸዉ ምሰሉአቸዉ።” (ዕብ. 13፥7)። ስለዚህ በቅዳሴ ላይ የቅዱሳንን መታሰቢያ እናደርጋለን፤ በእምነት ፍጹማን የሆኑትንና ሕይወታቸውን በእምነት የፈጸሙትን፣ በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ እናስባለን።

◦ ይሄም የታላቁ አባ መቃርስን ከዚህ ዓለም መለየት እንዳስታውስ ያደርገኛል። ነፍሱ ከስጋው ተለይታ ስትሄድ “መቃርስ አንተ ድነኸል” እያሉ አጋንንት ነፍሱን አሳደዷት፤ ነገር ግን ገነት እስከሚገባ ድረስ “በጌታ ጸጋ ድኜያለኹ” አላላቸዉም ነበር…!
.
.
ምንጭ ፦ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ነገረ ድኅነትን አስመልክቶ ለፕሮቴስታንቶች መልስ ከሰጡበት “Salvation in the Orthodox Concept” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ ነዉ።

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ከሀቢብ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ራስን መስጠትና እውነተኛ
          አገልግሎት እንማር

‹‹... በዚያን ጊዜ የነበረው አገልግሎት ብዛት ያላቸው ችግሮች ነበሩበት፡፡

💠ሰባኪያንና የተማሩ ካህናት  አልነበሩም፡፡
💠በመሆኑም በቤተ ክርስቲያን ድካም ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች ያድጉ ጀመር፡፡
👉በዚህ ጊዜ መለያየትና ውስጣዊ ጠብ ተስፋፋ፡፡

💠ጥቂት ሰዎች👉 ስድብን ፣ 👉ነቀፌታንና👉 ማጎሳቆልን በይፋ ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ👉 በፍርድ ቤት ለሕግ ጉዳዮች ከፍተኛ ገንዘብ በማባከን ቤተ ክርስቲያንን ይዋጓት ጀመር፡፡

💠ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ምንም ዓይነት ጥቅም አልነበራቸውም፡፡ 💠ቤተ ክርስቲያን ከስድብ ፣ከትችት ፣ ከማጎሳቆል ፣ ከመከፋፈል ፣ከፍርድ ቤት ወይም ከለቅሶ የተጠቀመችው ነገር አልነበራትም፡፡ ታዲያ ለውጥ እንዴት ሊመጣ ቻለ?

ለውጥ የመጣው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን የአገልግሎት መሪ በነበረው በሀቢብ ጊዮርጊስ መልካም ሥራ አማካኝነት ነው፡፡

👉እርሱ በዘመኑ በነበሩት ስኅተቶች ውስጥ ራሱን ሳያስገባ ሥራ ጀመረ፡፡

💠በወቅቱ ሁለት ወሳኝ የመሠረት ድንጋዮችን በዚያ ጣለ ፤ ለሰ/ት/ቤትና ለመንፈሳዊ ኮሌጅ፡፡
👉እነዚህን ነገሮች መመሥረት እንደጀመረ መሠረቶቹ በየዕለቱ ያድጉ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ፣ በየማኅበረሰቡ ፣ በየሰንበት ትምህርት ቤቱና በየመንደሩ መስበክ የጀመሩ ብዙ ቁጥር ያላቸው አገልጋዮች ታዩ፡፡
💠 ሀቢብ ጊዮርጊስም ይህን እየተመለከተ ፡-
‹‹ሕዝብህ ፈቃድህን በመፈጸም በበረከትህ እልፍ አእላፋት ይሁኑ!›› እያለ ይዘምር ነበር፡፡

💠እርሱ በጉድለቶች ላይ ነቀፌታ አልሰነዘረም ቤተ ክርስቲያን የሚጎድሏትን ነገሮች ለማቅረብ ሥራ ሠራ እንጂ፡፡
👉 ቤተ ክርስቲያን ሰባኪያን ይጎድሏት ነበር ፣ አብዛኞቹ ካህናት አባቶች የቅዳሴና የሥርዓት መጻሕፍትን ብቻ የሚያነብቡ ስለነበሩ የመስበክ ችሎታ አልነበራቸውም፡፡

👉 ሀቢብ ጊዮርጊስ ግን ይህን ዓለም በቤተ ክርስቲያን ዕንባ አልሞላውም ፤ ይልቁንስ ሰባኪያንና አገልጋዮችን ማደራጀት ጀመረ እንጂ፡፡
💠 የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የሰባኪያን ማኅበር እንዲያቋሙ አድርጓቸዋል ፤
💠 እነዚህ ተማሪዎች ደግሞ በካይሮ ፣ በጊዛ እና በሌሎች ከከተማው ወጣ ባሉ ቦታዎች ላይ ሰማንያ አራት ቅርንጫፎችን ሊያቋቁሙ ችለዋል፡፡

💠 ሀቢብ ጊዮርጊስ ሕጻናትና ወጣቶች አንድ እንኳን የሚያስተምራቸው ሰው ማጣታቸውን ሲመለከትም ከዚያ ተነሥቶ ቤተ ክርስቲያንን ለመተቸት ወይም ለመውቀስ አልወደደም፤ ዛሬ በሁሉም ሥፍራ ለመስፋፋት የቻሉትን ሰንበት ትምህርት ቤቶች አቋቋመ እንጂ፡፡

💠 ከዚህ ሌላ ለትምህርት ቤቶችንና ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤቶች መጻሕፍትን አዘጋጅቷል፡፡

💠 በአንዳንድ ጉባኤዎች የፕሮቴስታንቶች መዝሙር ቦታ እየያዘ ሲመጣ በቤተ ክርስቲያን ዜማ የተቃኙ መዝሙራትን ያዘጋጅ ጀመር፡፡
💠 የእርሱ አገልግሎት በሁሉም መስክ የተስፋፋ ነበር፡፡ በሀቢብ ጊዮርጊስ የተመራው ይህ የማነቃቃት ሥራ ታላቅ ትምህርትን ሰጥቶን አልፏል፡፡››

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 117ኛፓትርያርክ

<<የሀቢብ ጊዮርጊስ ሕይወቱና ትምህርቱ >> የሚል መጽሐፍ ከታች ያለውን ❤ 15 ሰው ከተጫነ በpdf እናደርሳችኋለን

     

የቴሌግራም አድራሻ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ካህኑን እንደ መንፈሳዊ አባትነቱ እየው፤ ልክ በሽተኛ የተሸፈኑ ቁስሎችን ለሐኪም እንደሚያሳይና እንደሚፈውስ ምስጢሮችህን በግልጽ ንገረው”

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ።

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጾም

ጾም እጅግ ግሩም የሆነ ነገር ነው፡፡ ኃጢአታችንን እንደማይጠቅም አረም ከውስጣችን ይነቅለዋል፡፡ እውነተኛው የጽድቅ ተክልም በውስጣችን ልክ እንደ አበባ እንዲያብብ ይረዳዋል፡፡  (ቅዱስ ባስልዮስ)

ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጾም ነው፡፡ የምንጾምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጾም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡ (ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ)




የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ለጽዮን ማርያም አደረሳችሁ

         ኀዳር ጽዮን


💠ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፡-
👉1.በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ
👉2.ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ
👉3.በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት
👉4.ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
👉5.ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
👉6.ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት
👉7.አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት
👉8.በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን እና ታቦተ ማርያም ባለበት ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል ይከበራል

💠ከዚህ  ጋር የመመኪያችን ዘውድ፣ የመዳናችን ምክንያት፣
💠የንጽሕናችን መሠረት ስለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያልተነበየ ነቢይ፣ ያልሰበከ ሐዋርያ፣ ያልተቀኘ ባለቅኔ ከቶ የለም፡፡
💠ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፣ በቤዛነቱ ዓለምን አዳነ፣ ዳግመኛም በክበበ ትስብእት፣ በግርማ መለኮት ለፍርድ ይመለሳል ብንል
👉ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በመሆኑ ያለ ወላዲተ አምላክ ምስጢረ ሥጋዌን፣ ነገረ ድኅነትን፣ ነገረ ምጽአትን ማሰብ ከቶ የማይቻል ነው፡፡

💠«ዕግትዋ ለጽዮን፤ ጽዮንን ክበቧት» እንዳለ ነቢዩ፤ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈባትን የእስራኤል አምባና መጠጊያ የሆነችውን ታቦተ ጽዮንን ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ ያቀርቡላት እንደነበረው፤
👉 ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል ፡፡

💠በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምስጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡

💠 👉ይህቺ የቃል ኪዳን ታቦት በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች፣ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያ. 3÷14-17/፤
👉ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያ 6÷1-21/፤
👉ዳጎን የተባለ የፍልስጥኤማውያንን 👉ጣዖት የቆራረጠች /1ሳሙ 5÷1-5/፤ 👉በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ሳሙ 6÷6/፤
👉በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/፣ 👉ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/፤ 👉ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት/1ነገ 8÷1/፤
👉የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡

በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለውን ረቂቅ እና ድንቅ ምስጢራዊ ንጽጽር አስመልክቶ ሶርያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም፤ «ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሔ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ፤
👉ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በውስጥ በአፍአ በወርቅ የተለበጠ»ያለው።
💠እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሐ ጠባይ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት በንጽሕናና በቅድስና ጸንታ በኃጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡
👉ጠቢቡ ሰሎሞንም፤ «አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ 👉ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኃጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» /መኃ 4÷7/ ሲል ተናግሯል፡፡

👉ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች
💠 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች መሆኗን ያጠይቃል፡፡

👉ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነችው
💠ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ሆናለች፡፡
ይኽንንም ቅዱስ ኤፍሬም ሲያስረዳ፤ «ኮንኪ ታቦቶ ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ፆርኪዮ በከርስኪ ተሰዓተ አውርኃ አንቲ ማእምንት ለዘኢያገምርዎ ሰማያት ወምድር፤ ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ  ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» ብሎ ተቀኝቶላታል፡፡

ስለሆነም ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትን የቸርነት በዓል እግዚአብሔር በፈቀደልን ቦታ ሆነን ስናከብር ከእኛ የሚጠበቀውን በጎ ነገር እያሰብን በተግባርም እየገለጥን ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ተሳታፊ እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን



           
👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ከአፍ የሚወጣ እሳት +

"አፌ ይለፈልፋል እንጂ ውስጤ እኮ ንጹሕ ነው"
አለች አባ ፊት ቀርባ - በክፉ ንግግርዋ ብዙ ሰው ያስቀየመች ሴት::

አባ መለሱላት :-
ልክ ነሽ ልጄ እባብም እኮ መርዙን ከተፋ በኁዋላ ውስጡ ንጹሕ ነው!

ምላስ አጥንት የለውም ነገር ግን አጥንት ይሰብራል:: እግዚአብሔር ምላስን እንደጆሮ ክፍት አላደረገም:: በከንፈርና በጥርስ ሸፍኖታል:: ትንሽ አሰብ አድርገን እንድናወራ ነው:: "ሰው ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን" የሚለው ቅዱስ ያዕቆብ ስለ አንደበት ሲናገር "ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል" እንዳለ የምላስ ኃይል እጅግ ከባድ ነው:: ከአፍ የሚወጣ እሳት ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል::

ሰው በዱላ ቢደበደብ ታክሞ ቁስሉ ያገግማል:: ክፉ ንግግር የሚያቆስለው ቁስል ግን በቀላሉ አይሽርም:: ዱላ የሚያርፈው ሥጋ ላይ ሲሆን መጥፎ ንግግር ግን ነፍስ ላይ ነው:: ክፉ ንግግሮች ሰውን ለጊዜው ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ሊያመርሩት ይችላሉ::

(ሌላ ነገርዋን ትተነው) ሚሼል ኦባማ በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ በጣም ልብ የሚነካ ነገር ስትናገር ሰማሁ:: ስለወረደባት ስድብ ስታስታውስ "አንዳንድ ክፉ ቃላት የነፍስን ቅርፅ ይቀይራሉ" ብላ ነበር::

እውነት ነው በመራር ቃላት የነፍሳቸው ቅርፅ ከተቀየረ ስንቶች ናቸው:: የማይዘነጉት ንግግር እድሜ ልክ የሚያቆስላቸው : የአንድ ሰው ከባድ ስድብ በራስ መተማመናቸውን የነጠቃቸው : የአንድ ሰው "አትችልም" የሚል ድምፅ እጅና እግራቸውን ያሰራቸው እጅግ ብዙ ናቸው:: ሰው ለማሳቅ ተብለው የተሰነዘሩ "ትረባዎች"ና አጥንት ሰባሪ ቀልዶች ቂመኛ ያደረጉዋቸው ሰውን ሁሉ ያስጠሉአቸው ስንት ናቸው?  በስድብ ብቻ የፈረሱ ቤቶች አሉ:: ስለተሰደቡ ብቻ በሕዝብ ላይ የሚፈርዱ ዘር እስከማጥፋት የተነሡ አሉ:: ተናጋሪው በጥፋታቸው ውስጥ ትልቅ ድርሻ እና ተጠያቂነት እንዳለው ግን ይዘነጋል::

እግዚአብሔርም "እንደ ዋዛ ለተናገራችሁት ቃል በፍርድ ቀን መልስ ትሠጡበታላችሁ" ብሎአልና ለሰዎች የምንሰነዝረው እያንዳንዱ ቃል ያስጠይቀናል::

በተቃራኒው ለሰዎች ጥሩ ቃል መናገርን ብዙ ዋጋ አንሠጠውም:: ለስድብ የማናቅማማ ሰዎች ለምስጋና ሲሆን ግን እንሽኮረመማለን::
ፊት ለፊት አሳምረን የምንሳደብ ሰዎች ለማመስገን ሲሆን "በፊትህ ማመስገን እንዳይሆንብኝ" እንላለን::

ሆኖም ብናወጣው ሰዎች የሚነገራቸው ጥቂት በጎ ቃል ሰብእናቸውን ይገነባል:: ፈጣሪ "ብርሃን ይሁን" ብሎ በቃሉ እንዳበራው ማድረግ ባይቻልህ እንኩዋን በጥቂት በጎ ቃላት የአንድን ሰው ቀን ማብራት ትችላለህ::
ከምንም ሥጦታ በላይ መልካም የምስጋና ቃላት በሰው ልብ የሚቀር ውድ ሥጦታ ነው::

ባል ለሚስቱ ከሚገዛው ሥጦታ በላይ "ባልዋም ያመሰግናታል" የሚለውን ቃል ቢፈጽምላት ደስታ ይሆንላታል:: ልጆች ከብዙ ሥጦታዎች በላይ ከወላጆቻቸው የሚሰሙት የፍቅር ቃል ይሠራቸዋል::

የእስክንድርያው ፊሎ ለልጅ አባትና እናቱ ከሀገሪቱ ንጉሥና ንግሥት በላይ ናቸው ይላል:: የንጉሥ ቃል የሹመት ቃል ነውና ልጆች በወላጆቻቸው የሚሰሙት "ጎሽ" የሚል ቃል ከፍ ያደርጋቸዋል::

"ልጅሽ ትምህርት የማይገባው ደደብ ስለሆነ ትምህርት ቤት አትላኪው" የሚልን ደብዳቤ "ልጅሽ በጣም ጎበዝ ስለሆነ እሱን ማስተማር ስለማንችል በቤት አስተምሪው" ብላ ያነበበች እናት ትልቅ ሳይንቲስት አፍርታለች::

ብርሃን ይሁን ! ምድር ታብቅል! ብሎ የፈጠረን አምላክ በአርኣያው ፈጥሮናልና በቃላችን የምናሳምም ሳይሆን የምንፈውስ እንሁን::

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ "ወንድሙን የሚሰድብ ነፍሰ ገዳይ ነው" ብሎአል:: ስድብ ከመግደል እኩል ነው ሲል ነገሩን ለማግነን የተጠቀመው አገላለጽ ሳይሆን በእርግጥም መሳደብ ከመግደል ብዙም ስለማይለይ ነው:: ሀገራችን ላይ ያንዣበበው የዘር ጭፍጨፋ ብዙዎቻችንን ያሳስበናል:: እንደ ሩዋንዳ ልንሆን ነው? እንላለን:: ወዳጄ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት መነሻው እኮ የሚዲያ የጥላቻ ንግግር ነበር:: እውነት ለመናገር ዘር ነክ ስድቦችና በቀልድ መልክ የሚነገሩ የንቀት ንግግሮች ሁሉ የዘር ማጥፋት ዋዜማ ናቸው:: የጥላቻ ንግግር (hate speech) የዘር ማጥፋት እጅግ ወሳኙ መቆስቆሻ ነው:: ስለዚህ "በለው በለው" ብለህ በምትጽፈው comment ወንድሙን ከገደለው እኩል በፈጣሪ ፊት ትጠየቃለህ:: ቅዱሱ እንዲህ ይላል  "እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል" ማቴ 5:22

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 11 2012 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ!
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ቅድስት ቤተክርስቲያን:-
-ጥንቆላን
-ሙስናን
-ዘረኝነትን
አምርራ ትጠላለች። በውስጧ የሚኖሩ አንዳንድ ቄሶች፣ ዲያቆናት፣ መምህራን፣ ጳጳሳት፣ ምእመናን ወዘተ እኒህን ነገሮች ሲያደርጉ ቢገኙ በሕግ አፍራሽነት እንዳደረጉት ማስተዋል ይገባል። በእነርሱ ምክንያት ክርስቶስ ራሷ የሆነላትን ቤተክርስቲያን መሳደብ አላዋቂነት ነው።

የቤተክርስቲያን ልኳ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ ሁልጊዜም ትክክል የሆነውንና የሕይወት አባት እርሱ ጌታን ማሰብና በፍጹም ልቡና መከተል ይገባል



።/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እኛ ስለምን እንጾማለን?

🛐 ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ::
💠 እኛ ስለምን እንጾማለን?

💠ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን?
👉አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::

🛐 ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን?
💠እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? 💠ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?

💠የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ?
💠የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ?
💠 የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?

💠ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን::

🛐 ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው::
🛐 ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ:: 

💠 የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣
💠የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣
💠የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣
💠 ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ::

💠 ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ?

🛐የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር? 

💠ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ?
💠 ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም?
💠 ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ?

ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው::

💠ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ::




ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጾመ ነቢያት 2015 ዓ.ም. የተጻፈ



የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
እኛ ስለምን እንጾማለን?

🛐 ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ::
💠 እኛ ስለምን እንጾማለን?

💠ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን?
👉አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::

🛐 ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን?
💠እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? 💠ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?

💠የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ?
💠የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ?
💠 የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?

💠ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን::

🛐 ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው::
🛐 ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ:: 

💠 የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣
💠የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣
💠የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣
💠 ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ::

💠 ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ?

🛐የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር? 

💠ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ?
💠 ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም?
💠 ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ?

ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው::

💠ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ::




ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጾመ ነቢያት 2015 ዓ.ም. የተጻፈ



የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመላው ዓለም ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን የታወጀውን አዋጅ አስተላልፈዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ያለፈውን በይቅርታና በምህረት ዘግተን በእውነተኛ ንሥሓ ልቅሶና በምህላ፣ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንድንቀርብ፣ በመካከላችንም ፍቅርና አንድነት እንዲመጣ ይኽንን ጾመ ነቢያት ወይም የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንድንጾም መንፈሳዊ አዋጅ ተላልፏል፡፡ 


አፈጻጸሙ


፩ኛ. የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር ፲፭ እስከ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ፣ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን፤

 
፪ኛ. በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ መነኰሳት፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ፤ 

፫ኛ. በላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ፣ በፍቅርና በአንድነት፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ፤

፬ኛ. በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር ፲፭ ቀንና፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር ፳፩ ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

፭ኛ. በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም፣ ስለንሥሓና ጸጸት፣ ስለ ፍቅርና አንድነት፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን፤

፮ኛ. በሰፊህና በአንቀዓድዎ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ፣ ምኅላው ከደረሰና፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ፤

፯ኛ. ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም፤ 
 
፰ኛ. አስቀድሞ የደረሰውንና፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም፤   

፱ኛ. ይኽንኑ መልእክት መላው ዓለም እንዲውቀው፣ በተለይም የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጸሎት እንዲያስቡን፣ የጸሎታችንና የምኅላችን መነሻ ምክንያቱ የሀገራችን ወቅታዊ ችግር ቢሆንም የምንጸልየው ለመላው ዓለም መሆኑ ተገልጾ በደብዳቤ እንዲላክ እንዲደረግ፣ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል፡፡ 

እግዚአብሔር አምላካችን በእንባና በንሥሓ የምናቀርበውን ጸሎተ ምኅላችንን በምህረቱ ተቀብሎ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፣ ሕዝባችንን ይጠብቅልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 
ቅዱስ ሲኖዶስ

ኅዳር ፲፩ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም፡ 
አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ልጆቼ፦ እግዚአብሔርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ልናቀርብ ይገባናል፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን?

እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሔርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እግዚአብሔርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

                          †                          

🌼  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  🌼

   ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !
                              
🕊

[ “ ቅዱሳንን ትመስላቸው ዘንድ ! " ]

------------------------------------------------

" ወዳጄ ሆይ ! ፍቅርንና ራስን መግዛትን ገንዘብህ አድርገህ ተመላለስ፡፡ ምክንያቱም ትልቅ ዋጋ አላቸውና፡፡ እነዚህ ካሉህ እግዚአብሔር ሰውነትህን ማደሪያው ያደርገዋል። አንተም የእውነተኛ ተሐራሚ ጠባይን ገንዘብህ ታደርጋለህ፡፡ ስለዚህም ቅብዝብዝና በአንድ ቦታ ረግቶ የማይቀመጥ ሰው እንዳትሆን አንተን ከወንድሞች ኅብረት ሊነጥሉህ የሚያስቡትን ሰዎች ምክር አትስማ፡፡

በወጣኒነት ሳለህ የነበረህን ትጋት እንዳታጣ ተጠንቀቅ፡፡ ነገር ግን ይህን ትጋትህን እስከ መጨረሻው ጠብቅ፡፡ ክፉ ንግግር ወይም መሓላ ከከፈርህ አይገኝ፡፡ ቅዱሳንን ትመስላቸው ዘንድ ትሕትናን ገንዘብህ አድርግ፡፡

በንግግርህ ሁሉ “ይቅር በሉኝ” ማለትን ልመድ፡፡ ይህ ከዚህ ዓለም ተግባር ፈጽሞ እንድትርቅ በማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋናን የምታገኝበት ሕይወት እንዲኖርህ ያግዝሃል፡፡ ወደ ትሕርምት ሕይወት በመጣህ ጊዜ ወርቅ ወይም ብር ወይም ልብስ ይዘህ አትምጣ [ወይም የአንተ እንዳልሆኑ ከእግዚአብሔር ያገኘሃቸው እንደሆኑ አስብ]

በፊትህ እግዚአብሔርን አድርግ እንጂ ፤ እንደ ጌታችን እንደ መድኀኒታችን አስተምህሮ እነዚህ ከአንተ ዘንድ እንዲኖሩ ፈልግ፡፡

እነዚህም እምነት ፣ ራስን መግዛት ፣ ትዕግሥት ፣ ትሕትናና እነዚህን የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ከእግዚአብሔር የምናገኛቸው የእርሱ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ለእርሱ ክብር ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡"

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]

†                       †                        †
🌼                    🍒                     🌼


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"አምስቱ የንሰሃ መንገዶች"

ቅዱስ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው

💠የንሳሃን መንገዶች ልዘርዝር?
💠 የንስሃ መንገዶች ብዙ ናቸው ሁሉም ወደ መንገስተ ሰማያት ይመራሉ፡

💠1/ የመጀመሪያው መንገድ ኃጢአትን መንቀፍ (መለየት-condemnation) ነው።

⛪️ ኃጢአታችሁን ከእናነተ አውግዙ ይህንን ማድረጋችሁ ጌታ ፊት ይቅርታን ያሰጣችኋል። ኃጢአቱን አንድ ጊዜ ያወገዘ ሰው እነዛን ኃጢአቶች ድጋሚ የመስራት እድሉ ይቀንሳል።
🛐ህሊናህ ከሳሽህ እንዲሆን አነሳሳው (Stir up your own conscience) ይህን ካደረክ በጌታ የፍርድ ዙፋን ፊት ስትቆም የሚከስህ አይኖርም። 

🛐ይህ የመጀመሪያው የንሳሃ መንገድ ነው ነገር ግን ቀጥለን የምናየው ሁለተኛ መንገድ ከመጀመሪያው መንገድ ያነሰ ወይም ዝቅ ያለ አይደለም።

💠💠💠2/ሁለተኛው መንገድ በሰዎች የደረሰብንን በደል መርሳት፤ ንዴታችንን መቆጣጠርና ከእኛ ጋር አብረው የእግዚአብሔር ባሪያ የሚሆኑትን ሰዎች ኃጢአት ይቅር ማለት ነው።
🛐 ይህንን በደንብ ካደረግን እኛም እግዚአብሔር ላይ ያደረግናቸው ኃጢአቶች ይሰረዩልናል። ጌታም በማቴዎስ ወንጌል ላይ እንዲህ ይላል “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና” (ማቴ 6፥14)። ይህ ንሳሃን የምናገኝበት ሁለተኛ መንገድ ነው።

💠💠💠3/ ሦስተኛውን የንስሃ መንገድ ማወቅ ትፈልጋላችሁ?👉 ጸሎት ነው። ይህ ጸሎት ከልብ የሆነ፤ በተመስጦ፤ በትኩረት የሆነ እና ከልብ የሚመነጭ ጸሎት ነው።


💠💠🛐4/ አራተኛውን የንሰሃ መንገድ ማወቅ ከፈለጋችሁ እነግራችኋለው ይህም ምጽዋት ነው። ምጽዋት እጅግ በጣም ኃይል አለው።

5/የመጨረሻው መንገድ ትህትና ነው። ይህ መንገድ እንደሌሎቹ መንገዶች ኃጢአትን የማሸነፍ ኃይል አለው። በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 18 ላይ ያለውን ቀራጭ ተመልከቱ ስለራሱ እሚናገረው አንዳች ጥሩ ምግባር የለውም። በጥሩ ምግባር ቦታ ትህታናን አቀረበ በዚህም ኃጢአቱ ተሰረየለት።
💠ስለዚህ እስካሁን አምስቱን የንስሃ መንገዶች አሳየኋችሁ እነሱም ኃጢአትን ማውገዝ፤ የሌሎችን ኃጢአት ይቅር ማለት፤ ጸሎት፤ ምጽዋት እና ትህትና ናቸው።


💠ስለዚህ ስራ ፈት አትሁኑ ሁሉንም መንገዶች በየቀኑ አተግብሯቸው።
💠 እነዚህ መንገዶች ከባዶች አይደሉም ድህነትም እንደ ምክንያት ሊሆን አይችልም። እጅግ በጣም ድሃ ብትሆኑም እነዚህን ሁሉ ነገሮች ማድረግ ትችላላችሁ ቁጣን አስወግዳችሁ ትህትናን ልበሱ፤ ጠንክራችሁ ጸልዩ፤ ኃጢአታችሁን አውግዙ።
👉ድህነት እነዚህን የንስሃ መንገዶች እንዳንለማመድ መሰናክል ሊሆን አይችልም።
👉አይደለም ሌሎቹን ብር የሚያስፈልገውን ምጸዋትን እንኳን እንዳንሰጥ አይከለክለንም።
👉በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21 ቁጥር 2 ላይ ያለው የድሃዋ መበለት ታሪክ ትዝ ይላችኋል? አሁን ቁስላችንን ማከም የምንችልባቸውን መንገዶች ተምረናል እነዚህን መንገዶች እናተግብራቸው። በንስሃው መንገድ ጤንነትን አግኝተን ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል እንብቃ። በክርስቶስ መንግስት ያለውን ክብር ተሞልተን በጸጋው፤ በርህራሔውና በምህረቱ ዘላለማዊውን ሃሴት እናገኛለን።


የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን
ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ።


💠#በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

💠በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

💠ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ  በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🌹 #ተፈጸመ_ማህሌተ_ጽጌ.. ✝️👏❤️💒

🌹ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ማህሌተ ጽጌ  ስሙር  ተፈጸመ ናሁ አክሊል አክሊል  ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግስቱ!

🌹እነሆ በእመቤታችን ስም ተሰባስበን 🌹አበባ🌹 ይዘን
🌹 ልጅዋን  በአበባ
🌹እርስዋን በጽጌረዳ እየመሰልን የምንዘምርበት ያ የተወደደው የምስጋና የዝማሬ ወር አለፈ
🌹 እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ የጊዮርጊስ የክብር ዘውድ ነሽ! እያሉ በተመስጦ እንደ ቅዱስ ያሬድ የቅዱስ ያሬድ ልጆች ሊቃውንቱ  እናታቸውን ሲያመሰግኑ  የሚያሳይ ግሩም (ማህሌተ ጽጌ)

🌹እመቤታችን ዘውድነቷ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን  ውዳሴዋን ቅዳሴዋን እየደገመ ስሟን እየጠራ ለሚማጸን በአማላጅነቷ በቃል ኪዳኗ ለሚያምን ሁሉ ዘውድ ናት!

🌹ምዕመናንም ትምክህተ ዘመድነ! እያሉ ይዘምሩላታል፤ ያመስግኗታል!
🌹ድንግል ሆይ የባህርያችን መመኪያ ነሽ!
🌹ተስፋችን ነሽ!
🌹የድህነታችን ምልክታችን ነሽ! እያሉ በእናትነቷ ጥላ ስር ያሉ ምዕመናን ይዘምሩላታል!
🌹እርስዋም እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ትባርካቸዋለች! 
🌹ሁላችንም እናታችን ትባርከን!

ለእኛም ለልጆችሽ ሞገስ ሁኝን  አማላጅነትሽ ቃልኪዳንሽ አይለየን!!✝️👏


ዲ/ን እስራኤል 2/3/2016




የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን ለሰማዕታት ጽድቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ

ስለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምን እንላለን ?
💠በመልአከ ብስራት የተጸነሰው
💠በማህጸን ሳለ ለእመቤታችንን ለአምላኩ የሰገደ
💠ስጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ስወለድ የአባቱን አንደበት የዘጋ
💠በበረሃ ያደገ
💠ልብሱ የግመል
💠ምግቡም አንበጣና የበረሐ ማር የሆነ
💠በበረሐ የሚጮህ አዋጅ ነጋር(መምህረ ንስሐ )
💠ጥምቀተ ንስሐ ያጠምቅ የነበረ
💠መንገድ ጠራግ (የሰዎችን ልቡና ከክፋት እንዲመለሱ ጌታችን ከማስተማሩ አስቀድሞ የሰበከ)

🌹መምህረ ትህትና
💠የጫማውን ማሰሪያ ልፈታ የመይገባኝ ስል ጌታውን አምላኩን መለኮትን ለማጥመቅ የበቃ
💠መለኮትን ያጠመቀው
💠 ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ ተብሎ የተነገረለት
💠ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰከረ


💠ንጉስን ጭምር ሳይፈራ ከክፋት እንድመለስ የሚገስጽ (ሰማዕተ ጽድቅ )

💠ስለ እውነት ስለ ሕገ እግዚአብሔር ሰማዕትነትን የቀበለ

ማቴ 3÷1-ፍጸሜ   /11÷11/
ማቴ 14÷1-ፍጸሜ
ማር 1÷1_ፍጻሜ
ሉቃ 1÷5-25
ዮሐ 1÷6-10/1÷19-34

ጸሎቱ በረከቱ ጸጋው አይለየን
አምላከ ዮሐንስ ሀገራችን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን
ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን ይጠብቅልን እኛ ክርስቲያኖችን በአምነ ሥላሴ በተዋህዶ ሃይማኖት በምግባር በትሩፋት ምስጢራትን በመቀበል አጽንቶ ያኑረን !አሜን

  ዲ/ን እስራኤል 30/2/2016 መሠረተ ሚዲያ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

መድኃኔዓለም

💠«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት  ማለት ነው።
💠ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።

ምን ዓይነት ፍቅር ነው?????
👉 ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው።
💠ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው።
👉 በፈጠራቸው ፍጥረታት ተሰቃየ ተተፋበት መከራ ጸናበት ሰቀሉት ።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር።
💠ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።
ታድያ
💠 እኛ ደግሞ መንግሥቱን ለመውረስ ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።

💠ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን። በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ።
አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።

መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ካህኑን እንደ መንፈሳዊ አባትነቱ እየው፤ ልክ በሽተኛ የተሸፈኑ ቁስሎችን ለሐኪም እንደሚያሳይና እንደሚፈውስ ምስጢሮችህን በግልጽ ንገረው”

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ።




የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ጾም

*"#እውነቱን_ስለተናገረ_ግን_ተጠቀመ_ወይስ_ተጎዳ ?❓ "*

" ከእናንተ መካከል ፦ " ዋሽቼ ስለ ወንድሜ ክፉ ነገርን ካልተናገርኩ ፥ ነገር ግን እውነት የኾነውን ነገር ብናገር [የሠራው ኃጢአትም ቢኾን] ምን ነውር አለው? የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፡፡

ግድ የላችሁም ! የምታወሩት ነገር እውነት ቢኾንም እንኳን አሁንም ንግግራችሁ ከነቀፋ አያመልጥም፡፡ "እንዴት ኾኖ?" ብላችሁ ልትጠይቁኝ ስለምትችሉ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌ ልስጣችሁና ንግግራችሁ እንዴት ብሎ ክፉ እንደ ኾነ ይገባችኋል፡፡

በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አሥራ ስምንት ላይ የምናገኘው አንድ ፈሪሳዊ አለ፡፡ ይህ ፈሪሳዊ ስለ ቀራጩ ወንድሙ የተናገረው ነገር እውነት ነው፡፡

"ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ። እግዚአብሔር ሆይ ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም ፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤" [ሉቃ.፲፰:፲፩] እንዲህ እውነቱን ስለተናገረ ግን ተጠቀመ ወይስ ተጎዳ? ፍጹም አልተጠቀመም! እንዲህ በማለቱ ባዶ እጁን አልተመለሰምን? በመጸለዩና በመጾሙስ ምን ጥቅም አገኘ?

እስኪ አሁን ልጠይቃችሁ ፤ እናንተም መልሱልኝ፡፡ ቀራጩ ኃጢአተኛ አልነበረምን? ከወንጌሉ እንደምናነበው ያ ቀራጭ ኃጢአተኛ እንደ ነበር ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ፈሪሳዊው በጸሎቱና በጾሙ መካከል የራሱን ኃጢአት ከማሰብና ከማሳሰብ ይልቅ ወንድሙን እያማ ስለነበረ ወደ ቤቱ የተመለሰው የጾምን ዋጋ ሳያገኝ ባዶውን ነበር፡፡ "

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]


የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

💠 ጽዮን የሚለው ቃል ለአምስት ነገሮች መጠርያ ሆኗል

1/ ሙሴ በደብረ ሲና የተቀበለው ጽላተ ሕግ ታቦተ ጽዮን ትባላለች 1ሳሙ 2:19

2/ የአብርሃም ርስት የሆነችው ኢየሩሳሌም ጽዮን ትባላለች 2ሳሙ 5:6

3/ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጽዮን ቅድስት ትባላለች (ቅ.ያሬድ )

4/ መንግሥተ ሰማያት ደብረ ጽዮን ትባላለች ዕብ12:22

5/ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ቅ.ያሬድ )



👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#የሰናፍጭ_ቅንጣት_ምሳሌነት

የሰናፍጭ ዘር ስትዘራ መጠኗ ከዘር ሁሉ ያንሳል፤ በአደገች ጊዜ ግን ከአታክልቶች ትበልጣለች፤ የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች፡፡ ምሳሌነቷም ለመንግሥተ ሰማያት መሆኑ ተገልጧል፡፡ እዚህ ላይ መንግሥተ ሰማያት የተባለች ወንጌል ናት፡፡ ምክንያቱም በሕገ ወንጌል ጸንቶ የኖረ መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳልና፡፡
በዚህም መሠረት ሰናፍጭ ለወንጌል ምሳሌ የሆነችበት ምክንያት ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡
➛ ሰናፍጭ ፍጽምት ናት፣ ነቅ የለባትም፤ ወንጌልም ነቅዓ ኑፋቄ የሌለባት ፍጽምት ናት፡፡
➛ ሰናፍጭ ላይዋ ቀይ ውስጧ ነጭ ነው፤ ወንጌልም በላይ ደማችሁን አፍስሱ ትላለች በውስጥ ግን ሕገ ተስፋ ናት፡፡ ይህም ተስፋ መንግሥተ ሰማያት ነው፡፡
➛ ሰናፍጭ ጣዕሟ ምሬቷን ያስረሳል፤ ወንጌልም ተስፋዋ መከራን ያስረሳል፡፡
➛ ሰናፍጭ ቁስለ ሥጋን ታደርጋለች፣ ወንጌልም ቁስለ ነፍስ ታደርቃለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ደም ትበትናለች፤ ወንጌልም አጋንንትን፣ መናፍቃንን ትበትናለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ከምትደቆስበት ተሐዋስያን አይቀርቡም፤ ወንጌልም በእውነት ከምትነገርበት አጋንንት መናፍቃን አይቀርቡም፡፡
➛ ሰናፍጭ ስትደቆስም ስትበላም ታስለቅሳለች፤ ወንጌልም ሲማሯትም፣ ሲያስትምሯትም ታሳዝናለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ከበታቿ ያሉትን አታክልት ታመነምናለች፤ ወንጌልም የመናፍቃንን ጉባኤ ታጠፋለች፡፡
➛ ሰናፍጭ አንድ ጊዜ የዘሯት እንደሆነ ባመት ባመት ዝሩኝ አትልም፤ ተያይዞ ስትበቅል ትኖራለች፡፡ ወንጌልም አንድ ጊዜ ተዘርታ ማለትም በመቶ ሃያው ቤተሰብ ተጀምራ እስከ ምጽአት ድረስ ስትነገር ትኖራለች፡፡
➛ ሰናፍጭ የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ እንድትሆን፣ ወንጌልም ሕዝብም አሕዛብም ተሰብስበው መጥተው እስኪያምኑባት ድረስ ደግ ሕግ ትሆናለች፡፡


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ለምንድን ነው የምንጾመው?

💠እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡
👉 ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው?

👉 በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን?
👉በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡
👉ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

💠በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡
👉ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡

ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-

#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡
💠በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡
👉በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡
👉ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ 👉ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

#ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡
💠ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ 👉እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡
👉አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡
👉በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

👉ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡

(#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 71-72 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ እንደተረጎመው)

/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )

                  ⬇️

➡️      መሰረተ ሚዲያ   ⬅️

                  ⬆️


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ


👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጾም በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ

🛐 ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡
💠ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡
  💠እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡
👉❤ልቡናችንን በማንጻት፣
👉 ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣
👉 የክፋት እርሾን በማስወገድ፣
👉ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት

💠የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡
ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

🛐🛐🛐  በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ   ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡
💠ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡

🛐እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡
💠ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ



የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🍀🌹አስተውል!🍀🌹

ትላንትና የሞቱት ሰዎች ለዛሬ ጠዋት እቅድ ነበራቸው፤ ዛሬ ጠዋት የሞቱት ሰዎች ለዛሬ ምሽት እቅድ ነበራቸው።

ህይወትን እንደ ተራ ነገር አትውሰድ። በሰከንዶች ውስጥ ሁሉም ነገር ሊለወጥ ይችላል።

ምንጊዜም ይቅር በል!

በሙሉ ልብህ ለሌሎች ፍቅርን ስጥ፡፡

ይህን እድል እንደገና ላታገኘው ትችላለህና!

ማስተዋሉን ያድለን

/channel/dnhayilemikael  መልካም ምሽት❤️

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🕯የአባ እንጦንስ ምክሮች💠

✞⛪️ ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ አባ እንጦስን "ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል።

👉አባ እንጦስም እንዲህ ሲል መለሰለት
💠"በራስህ ጽድቅ አትታመን፤
💠ላለፈው አትጨነቅ
💠፤ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ።"


⛪️⛪️✞ አባ እንጦስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፦
💠"በዚች ምድር ላይ ስንኖር ህይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልጀራችን ጋር ነው።
💠ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው እግዚአብሔርን ገንዘብ እናደርጋለን፤ 💠ወንድማችንን ካስቀየምነው ግን በክርስቶስ ላይ ኃጢአትን እናመጣለን።"

⛪️⛪️⛪️✞ በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ እንጦስን "ጸልይልኝ" በማለት ይጠይቃል።
💠አባ እንጦስም "አንተ ራስህ ጥረት የማታደርግና ወደ እግዚአብሔር የማትጸልይ ከሆነ እኔም ሆንሁ እግዚአብሔር ምህረት ልናደርግልህ አንችም" አለው።

⛪️⛪️💠⛪️⛪️✞ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ፦ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።


👉 “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።”
  — ማቴዎስ 6፥33


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ህዳር_8 #አርባዕቱ_እንስሳ❗❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ህዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣

🔵👉 እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

🔶👉 የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

🔷👉 የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

🔴👉 ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

🔵👉 የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

❗👉 ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

🔵👉 በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

🔴👉 እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

🔷👉 ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

🔷👉 ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

🔵👉 በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

🔴👉 ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው።

🔷👉 ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

🔵👉 ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።

❗መንፈሳውያን አመስጋኞችና መዘምራን የምትሆኑ አራቱ እንስሳት ስለ አኛ ለምኑ❗
 
❗አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን ሰዐሉ በእንቲአነ❗
( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት )  

🔷👉 ቅዱስ ጄሮም እንዲህ አለ ፦
     አርባዕቱ እንስሳት የድኅነታችን ምሥጢር የሆኑትን አራት ደረጀዋች ያስረዳሉ ።

🔷👉ገጸ ሰብእ ፦ ሥጋዌውን ( ቃል ስጋ መሆኑን )
🔷ገጸ አንበሳ ፦ ትንሣኤውን
🔷ገጸ ላህም ፦ ንጹሕ መሥዋዕት ( ቤዛ ) መሆኑን
🔷ገጸ ንሥር ፦ ዕርገቱን

🔴የእግዚአብሔርን ባሕርያት ያመለክታሉ።
ገጸ ሰብእ ፦ ጥበቡንና ዕውቀቱን
ገጸ አንበሳ ፦ ግርማውንና ኃይሉን
ገጸ ላህም ፦ ትዕግስቱን ፈታሒነቱን
ገጸ ንሥር ፦ ክብሩን ልዕልናውን

🔴አንድም አርባዕቱ እንስሳት
በአራቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ።
    
          🔵#አርባዕቱ_እንስሳት #በእመቤታችን_ድንግል_ማርያም_ይመሰላሉ። እነሱ መንበሩን ለመሸከም እንደተመረጡ ፤  ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለችና ።

፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+++ ምክር እና ቡጢ... +++

አንዳንዴ ሰው ተቸግሮ ወደ እኛ መጥቶ ሲያወያየን ከግለሰቡ በላይ የምንሰጠውን ምክር የምንወድ ሰዎች አለን። ያ ሰው ምን ሁኔታ ላይ ነው? ምን ይሰማዋል? ብሎ ለመረዳት ከመጣር ይልቅ ልንነግረው ባሰብነው ምክር ቀድሞ ደስ መሰኘት። አውርቶ እስኪጨርስ ትዕግሥት ማጣት። እንዴት ሰምቼ ላሳርፈው ከማለት ይልቅ ከመቼው ነግሬው ላስደንቀው (ይደነቅብኝ) የሚል ጉጉት። 

መፍትሔ ብለን የምንነግረው ደግሞ ሸክም ያደከመው ሰውነቱን ጨርሶ ያላገናዘበ የሚሆንበት አጋጣሚ በጣም ብዙ ነው።

አንድ በchildhood psychology የተመረቀ አንድ ወጣት ሰው ነው አሉ። ወላጆች በተሰበሰቡበት የመጀመሪያውን ሥልጠና ሲሰጥ ለጥናቱ የመረጠው ርእስ "ዐሥርቱ ትእዛዛት ለወላጆች"/"Ten commandments for parent" በሚል ነበር። ታዲያ እርሱም እንደ ሌሎች የትዳር ወጉ ደርሶት ልክ አንድ ልጅ ወልዶ ማሳደግ እንደ ጀመረ ያ ይሰጠው የነበረውን የሥልጠና ርእስ መቀየር እንዳለበት ተሰማውና "ዐሥር ማሳሰቢያ ለወላጆች" አለው። ቀጥሎ ሁለተኛ ልጅ ወልዶ ሲያሳድግ አሁንም የቀየረው የሥልጠና ርእስ ድጋሚ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ተረዳ። ስለዚህ በስተመጨረሻ ርእሱን "ዐሥር ጥቆማ ለወላጆች" አለው ይባላል። አንዳንዴ ለሰዎች የምንሰጠው ምክር ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ሕይወት እስክታስተምረን ድረስ የምንጨክን እንኖራለን።

አንዳንድ ጊዜ ሰው ጨንቆት ወደ አንተ ሲመጣ ግዴታ የሆነ ወርቃማ አባባል እንድትነግረው ወይም በአነቃቂ ቃላት እንድታግለው ላይሆን ይችላል። ያን ሰው በዝምታ መስማት እና የተዘበራረቀው ሐሳቡን ጊዜ ወስዶ ለአንተ በመናገር እንዲያጠራ ማድረግም ትልቅ እርዳታ ነው።

@dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

💒🌾❖ #ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ❖💒🌾

👉 በሃይማኖት መጽናት
👉 ወድቆ መነሳት ~ ንስሓ መግባት
👉 ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ
👉 በእግዚአብሔርም ሕግ መጽናት
👉 #ለእግዚአብሔር ሕግ መታመን
👉 ስንፍናን ማሸነፍ በጸሎት መትጋት
(ስንፍና ወደ ክህደት ይመራል) መዝ 13÷1
👉 በማየት በመስማት ከሚመጡ ነፍስን ከሚወጉ ዓለማውያን ነገሮች መራቅ
👉 ከቅዱሳን ሕይወት መማር በቃል ኪዳናቸውም መማጸን የጠላት ዲያብሎስንም የውጊያ ስልት ማወቅ
👉 ተስፋ ወደ መቁረጥ እንዳያደርስ ያለውን መንፈሳዊ ጸጋ ማወቅ ማክበር መጠበቅ " ከመንፈሳዊ ሀብት ባዶ ነኝ አለማለት " #እግዚአብሔር አለኝ ማለት
👉 ጥቂትም ቢሆን በየጊዜው ከበጎ ሥራ አለመለየት
👉 በፈተና መጽናት ትዕግሥትን መልበስ
👉 #እግዚአብሔርን /ሃይማኖትን/ በሥጋዊ ውጤት አለመመዘን
👉 ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ
👉 በቅዱስ ቁርባን ነፍስን መቀደስ
👉 የገሃነመ እሳትን መራራነት አለመዘንጋት
👉 የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም እያሰቡ መኖር
👉 #በእግዚአብሔር ቸርነት መታመን

🌾ቸርነትህና ምህረትህ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል #በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ
መዝሙር 23፡6

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጆሮህ መስማት የለመደው
          ምንድን ነው

........................................................
🌹በተጓዳኝ በቤቱ አንድ ንብ የሚያንብ ደራሲ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ከጓደኛው ጋር በሞቀ በደራው የመርካቶ ገበያ ውስጥ እየተጓዙ ሳሉ ድንገት፥ « የንብ ድምጽ ይሰማሃል?»  አለው ጓደኛውን፤ ጓደኛውም « አብደሃል እንዴ? ሕዝብ በሚተራመስበት በዚህ ሁሉ ጩኸት መካከል እንዴት የንብ ድምጽ ይሰማሃል?» አለው። ደራሲውም፥ ሳንቲሞች አውጥቶ መንገዱ ላይ በተነው፤ የዚያን ጊዜ የሚተራመሰው ሰው ሁሉ የሳንቲሙን ድምጽ ሰምቶ ፊቱን ወደ እነርሱ አዞረ።  የዚያን ጊዜ ደራሲውም ለባልንጀራው፥ አየህ ተመልከት « ጆሮአችን የሚሰማው ያስለመድነውን ነው።» አለው።

አንተስ ጆሮህ መስማት የለመደው ምንድን ነው?

👉በዕለተ ሰንበት የሚሰማውን የቅዳሴ ድምፅ 📢 ነው?
👉ወይስ በየዳንኪራቤቱ  የሚሰማው የሙዚቃ ጩኸት?
👉የእመቤቴ ምስጋና የጽጌው ማኅሌት ?
ወይስ የዓለም ሁካታና ጫጫታ?

🌹🌹የእኛ ጆሮ የሚያደምጠው፣ የለመደውስ ምንድ ነው?

👉በየሚዲያው ጸብ ክርክርን የሚፈጥሩ  ተሳዳቢዎችን ?
👉እውነትን በአደባባይ ሰቅለው የእውነትን ልብስ ለብሰው ለራሳቸው
👉ጥቅም የቆሙ ሌቦችና ሐሰተኞችን ?
ጆሯችን የሚሰማው ማንን ነው?

🌹ጆሮአችንን ስብከት ማድመጥን እናስለምደው
🌹ጆሮአችንን ቅዳሴና መዝሙር መስማትን እናለማምደው።
🌹ጆሮአችንን የሚያንጹ ፣የሚሰሩ በጎና ውብ ቃላት መስማትንን እናስለምደው።

🌹ጆሮአችንን ቃለ እግዚአብሔር መማርን እናስለምደው። ምክንናቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ

«ጆሮአችን የሚያዳምጠው ያስለመድነውን ስለ ሆነ » 

💠አንድ የዋልድባ መነኩሴ ለገዳማዊ አገልግሎት አራት ኪሎ ቢመጣ አንተም እርሱም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ብትጓዙ የእርሱ ጆሮ የለመደው የጸሎት ድምጽ ስለሆነ የሚሰማው ጫጫታ የሚያደምጠውም የሙዚቃ ድምጽ የለም።
💠ዋልድባ የሚሰማው የማኅበር ጸሎት ጣዕመ ዜማ ካልሆነ በቀር።እየጸለየ ይጓዛልና።

🌹ጆሮአችን ሁልጊዜ ሊያደምጠው የሚገባው በጎ ቃላትን ብቻ ነው።ሁካታና ጩኸት በበዛበት ዓለም ላይም ቢሆን መልካም ነገርን ለመስማት ጆሮአችንን እናስለምደው።

👉ፌዝና ቧልት ማድመጥ የለመደ ጆሮ ቁም ነገር ይሰለቸዋል።
👉ዘፈን ማድመጥ የለመደ ጆሮ መዝሙር ይደብረዋል።
👇👇⤵️⤵️⤵️
ስብከትና መዝሙር፤ ማኅሌትና ቅዳሴ ማድመጥን ለጆሮህ አስለምደው።


ቻነሉን የቀላቀሉ

⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

/channel/dnhayilemikael

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

💠💠💠 መስቀል 💠💠💠

💠💞የመስቀሉ ኃይል እንደ ምን ይደንቅ?
💠በሰው ልጆች ዘንድ በመስቀሉ ኃይል የኾነው የተደረገው ለውጥ እንደ ምን ይረቅ?
💠ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን አውጥቶናልና፤ ከሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት መልሶናልና፤ ከዘለዓለም ጥፋት ወደ ዘለዓለም ልማት አሸጋግሮናልና፡፡

💠💞በመስቀሉ ያልተደረገልን በጎ ነገርስ ምን አለ?
💠ምክንያቱም በመስቀሉ ርትዕት ሃይማኖትን ዐወቅን፤ የእግዚአብሔር የጸጋውን ብዛት ተረዳን፡፡
💠በመስቀሉ ስለ እግዚአብሔር እውነት የኾነውን ዐወቅን፡፡
💠በመስቀሉ፥ ርቀን የነበርን እኛ ሕዋሳተ ክርስቶስ እስከ መኾን ደርሰን የቀረብን ኾንን፡፡
💠 በመስቀሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተካፋይ የመኾን መብት (ሥልጣን) አገኘን፡፡

💠💞በመስቀሉ የፍቅርን ኃያልነት ዐወቅን፡፡
💠 በመስቀሉ ለሌሎች መሞትን ተማርን፡፡
💠በመስቀሉ ንቀት፣ ውርደት፣ መከራ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ ዐወቅን፡፡
💠ጊዜያዊ ያይደለ የዘለዓለም በረከት ምንጭ መኾኑን ተረዳን፤ የማይታየውን እንደሚታይ አድርገን ተቀበልን፡፡

💠በመስቀሉ የተሰቀለው ይሰበካል፤ በእግዚአብሔር ማመንን እውነትም ለዓለም ኹሉ ይነገራል፡፡
💠በመስቀሉ የተሰቀለው ክርስቶስ ይሰበካል፤ በትንሣኤ ማመንንና በላይ በሰማያት ያለችውንም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትም በእውነት ያለ ሐሰት ያለ ጥርጥር ይሰበካል፡፡

💠💞ከመስቀሉ በላይ የከበረ፣ ለነፍስም ድኅነትን የሚሰጣት ምን አለ?

💠መስቀል አጋንንት ድል የተነሡበት ነው፡፡
💠መስቀል የኃጢአት ድል መንሻ የጦር ዕቃ ነው፡፡
💠መስቀል ጌታችን እባቡን የመታበት ሰይፍ ነው፡፡

💠💞መስቀል የአብ ፈቃድ፣
💠የወልድ ክብር፣
💠የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣
💠የመላእክት ጌጥ፣
💠የቤተ ክርስቲያን አጥር፣
💠የቅዱስ ጳውሎስ ውዳሴ፣ የቅዱሳን ጋሻ፣ የዓለምም ብርሃን ነው፡፡


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…
Subscribe to a channel