#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
+++ የአንድ ኃጢአተኛ ሰው ጸሎት ++
ይህሄን ድንቅ ምክር ትምህርት እና ጸሎት በትእግስት ከቻላችሁ ደጋግማችሁ አንብቡ ባይቻላችሁ አንደ ታነቡ ዘንድ አደራ እላችኋለሁ
( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ )
አቤቱ “በጎውን ነገር ማን ያሳየናል?” የምንልበት ዘመን አይደለም፤ እንኳን በእኛ ዘንድ ይቅርና ወንጌል በአሕዛብ ዘንድ ሳይቀር የተሰበከበት ዘመን ነውና። ነገር ግን የተሰበከውን ቃል በልቤ አኑሬ ሕይወቴን ሳልለውጥበት ብዙ ዘመናትና ዓመታት አለፉ። ቃልህን ሰምቶ አለማድረግ በአንተ መዘባበት መሆኑን አውቃለሁ፤ ቃልህን የምሰማ እንጅ የምፈጽም ባለመሆኔም ምክንያት በድቡሽት ላይ እንደተሠራ ቤት ሆኛለሁ። ጥልቀት በሌለው አኗኗር ላይ የተገነባው መንፈሳዊነቴ ጎርፍ በጎረፈ፣ ነፋስ ባለፈ ጊዜ የሚናወጥ ደካማ ሆኖብኛል።
ዓለምን ለማሳለፍ ዳግመኛ መምጣትህን ባሰብሁ ጊዜ እደነግጣለሁ። ጻድቃን “አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና” እያሉ የምትመጣበትን ቀን ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ ሴት በተስፋ ይጠባበቃሉ፤ እኔ ግን አሁንም ለንስሐ ዕድሜ እንድትጨምርልኝ እለምናለሁ። ለንስሐ ብየ የለመንሁትን ዕድሜ አሁንም ማለቂያ ለሌለው ፍላጎቴ ባውለውም አንተ ግን የለመንሁትን ዕድሜ ሰጥተህ አጠገብኸኝ። ሰው ምን ቢቸግረው ነው የሠርጉን ቀን የሚያራዝመው? የደስታ ቀኑ እንዳትደርስ የሚከላከል ሰው ማለት እኔ ነኝ። አንተ የምትመጣበት ቀን ከዓለም አስቀድሞ ያጨኻትን የጻድቃንን ነፍስ እንደ ሴት ሙሽራ በአፍህ መሳም ስመህ መኃ 1፥2 የምትቀበልበት ቀን ነው።
ፀሐይና ጨረቃ በማያስፈልጓት ከተማ ለመኖር ጻድቃን ራሳቸው እንደ ፀሐይና ጨረቃ የሚያበሩበትን ያንን ቀን በቶሎ እንዲመጣ አለመለመን እንዴት ያለ ሞኝነት ነው? ያንጊዜ ታላቅ ደስታ ይደረጋል፤ ሙታንን የሚያነቃቸው ታላቁ ዝማሬ በሰማያውያን መላእክት ይጀመራል፤ መላእክት “ቅዱስ እግዚአብሔር” ሲሉ ምድራውያን ጻድቃንም “ቅዱስ ኃያል.......” እያሉ ያንን ዝማሬ ሊቀበሉ ከመቃብራቸው ይወጣሉ። ሞት ያንን ምስጋና ሰምቶ ይደነግጣል። ዲያብሎስ ይገሠጻል።
በእውነት የዚያን ቀን የሚደረገው ተድላ ደስታ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስካሁን አልተደረገም። እመቤታችን “ተፈሥሒ” የሚለውን የምስጋና ቃል በሰማች ጊዜ ያገኘችውን ደስታ ጻድቃን ያንጊዜ ያገኙታል። ያችን የደስታ ቀን ባለመዘጋጀቴ መድረሷን እየቸኮሉ ከሚጠባበቁት ውስጥ አይደለሁምና አዝናለሁ።
ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ያንን ቀን በደስታ እንድጠብቅ እንጅ ባሰብሁት ጊዜ ከመደንገጥ አውጣኝ። አውቃለሁ ጌታዬ ዛሬ ቃልህን ሰምተው ደስ የማይላቸው ሰዎች ያንጌዜ “ንዑ ኀቤዬ” የሚለውን ቃልህን ሰምተው ደስ አይላቸውም። ያንጊዜም ደስታን የሚሰጠን ዛሬ የምንሰማው ቃልህ ነው።
ይህንንማ በመካከላችን ስብከትን በጀመርህባት ቀን “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ባልኸን ጊዜ ገልጠህልን ነበር። መንግሥተ ሰማያት ብለህ የጠራሃት ቃልህን መሆኑን መምህራኖቻችን፥ “መንግሥተ ሰማያት፡− ሕገ ወንጌል፣ ሕገ ወንጌል፡− ተስፋ፣ ተስፋ፡− እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ብለው ተርጉመው ነግረውን ተረድተን ነበር። መንግሥተ ሰማያትን በመካከላችን ያኖርህልን ሆይ! ቃልህን በሰሙ ጊዜ የማር ወለላ እንዳቀረቡላቸው ሕጻናት ሳስተው እንደሚሰሙህ ወዳጆችህ እንድሆን እርዳኝ።
ደፍሬ ስምህን መጥራቴን ሳስብ አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ይይዘኛል፤ ደግሞ “ሰውን የምትወድ ሆይ” ብለው ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ ሲጠሩህ ስሰማ ፍርሀቴን ያርቅልኛል። አንተ በምትከብርበት መቅደስ ውስጥ ገብቼ መቆሜንም ሳስብ በቅዱሳን ጉባኤ መካከል የአንድ ኃጢአተኛ የእኔ መገኘት ያስጨንቀኛል፤ ነገር ግን ካህኑ በቅዳሴው መካከል “ወንጌል” ብለው ወጥተው “ኃጥአንን ለንስሐ እንጅ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም” የሚለውን ቃልህን ሲያነቡ በሰማሁ ጊዜ በሰጠኸኝ ዕድል ድምጼን ከፍ አድርጌ አመሰገንሁህ።
ሰዎች እስኪገርማቸው ድረስ በእኔ በቀራጩ ቤት መዋልህ ለምንድነው? በፊትህ በድለው ከማያውቁ መላእክት ይልቅ የእኔን ምስጋና ለመስማት መምጣትህ ለምንድነው? ሰውን መውደድህ ያስደንቃል!
ከተግሣጽህ ይልቅ ፍቅርህ ማርኮኝ መጥቻለሁ። ደዌ ከጸናበት ሰው በቀር ሀኪሙን በብርቱ ፍለጋ ማን ይፈልገዋል? እኔም ደዌ ነፍስ ቢጸናብኝ ኃጢአት ቢያስጨንቀኝ መጥቻለሁና ፈውሰኝ። ላገለግልህ ብወድም እንደ ሐማተ ጴጥሮስ ሳልፈወስ ላገለግልህ አልፈቀድሁም። ለአንተ ምን ይሳንሃል? ከለምጼ ልታነጻኝ ብትወድ ይቻልሃል።
ከአልጋዬ ልታነሣኝ ብትወድስ ማን ይከለክልሃል? ፈውሰኝና ዕድሜዬን በሙሉ አገልጋይህ አድርገኝ። ሳልፈወስ ባገለግል ደዌዬ ወደ ሌሎችም እየተዛመተ ብዙዎችን ይበክላል። ይሁዳ ባዛመተው ገንዘብ መውደድ፣ አፍኒንና ፊንሐስ በጀመሩት የመቅደስ ውስጥ ድፍረት፣ ዳታንና አቤሮን ባቀጣጠሉት ዘረኝነት፣ ሲሞናውያን ባሳዩት ጉቦኛነት ተይዘው ያልተፈወሱ ብዙ ናቸው፤ የእኔም ተጨምሮ የፈውስ ጊዜአችንን እንዳያርቅብን ስለምፈራ ፈውሰኝና አገልጋይህ ልሁን።
እኔ ሥጋህንና ደምህን የምቀበለው ዝቅ ብለህ አጥበህ እንዳነጻሓቸው እንደ ሐዋርያት ንጹሕ ሆኜ አይደለም፤ እንዲያውም ስቆርብ ያዩኝ ሰዎች ገርሟቸው “ይሄ ኃጢአተኛ ሰው ቆራቢ ለመባል ብሎ ነው እንጅ አምኖበት ነው?” ብለው ተሳለቁብኝ። በሽታ የጸናበት ሰው መድኃኒቱን የሚወስደው ደዌው እንዲለቀው እንጅ ደዌው ከለቀቀው በኋላ ነውን? እኔስ ይህ ቍርባን ፈራጅ እንደሆነ ባውቅም ማኅየዊ እንደሆነም አምናለሁ።
ሐዋርያት “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” 1ዮሐ 1፥7 ብለው ያስተማሩት ትዝ ይለኛል። የምትፈርድብኝ ፍርድ ሳይሆን “እንካችሁ ብሉ ሥጋዬን፣ እንካችሁ ጠጡ ደሜን” ብለህ ወደ እኔ የዘረጋሃት እጅህን አያታለሁ። ስለዚህም አፌን ከፍቼ እቀበልሃለሁ።
ዛሬ “በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ አንተን በመፍራትም ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ” ዳግመኛ በምትመጣ ጊዜም በምሕረትህ ብዛት በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ ዙፋንህ ፊት እቆማለሁ። ጭብጥ አፈር ወደ ባሕሩ ቢወረወር ባሕሩን ያደፈርሰዋልን? የእኔ የኃጢአተኛው ወደ መቅደስህ መግባትስ ያንተን ባሕርይ ያሳድፈዋልን? በእውነት በስምዖን ቤት መዋልህ ስምዖንን ያነጻዋል እንጅ አንተን አያረክስህም። ማርያም ኃጥዕት እግርህን ያጠበችበት እንባ እሷን አነጻት እንጅ አንተን አላረከሰህም። ደም የሚፈሳት ሴት ልብስህን በመንካቷ ካንተ የወጣው ኃይል እሷን ጎበኛት እንጅ አንተን አልለወጠኸም። እኔም ወደ ቤትህ የምገባው ይህንን እያሰብሁ ነው።
በተራራው ስብከት ጊዜ ተገኝቼ ስታስተምር ባልሰማህም፤ በደብረ ታቦር በተገለጥህ ጊዜ ክብርህን ካዩት መካከል ባልሆንም፤ በደብረ ዘይት እጅህን ጭነህ ከሾምኻቸው ውስጥ ባልመደብም አንተ ግን ለእኔ ምሕረት ማድረግን አትሰለችም። ወደ አንተ ባልመጣ እንኳን በተኛሁበት መጥተህ “ልትድን ትወዳለህ?” ማለትህ አይቀርም።
ከሰማይ የወረድህልኝ ሆይ! ኢያሱ ለእስራኤል ርስታቸውን እስኪያወርሳቸው ፀሐይን እንዳቆምህለት በምድር ላይ ያለን ኃጥአን ልጆችህ ሰማያዊት ርስትህን ሳንወርሳት ፀሐይ አትጥለቅብን፤ ዕድሜአችን አይለቅብን። አሜን!
@ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
[
የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
♥❖♥ ኢያቄምና ሐና ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ዘመዶቻቸውን ባልንጀሮቻቸውን ከነልጆቻቸው በመጥራት ሕፃን ልጃቸውን እመቤታችንን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ ያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በካህናቱ ታጅቦ የምስጋና ዝማሬን ከልኡካኑ ጋር እያሰማ እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ።
♥❖♥ በዚያም ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወደሚገባበት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ሲኖሩ በየደረጃዎቹም መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ ሲደረስባቸው ከሚጸለዩት የዳዊት መዝሙራት ውስጥ መዝ ፻፲፰(፻፲፱)-፻፴፪ (፻፴፫) የሚገኙ ሲኾኑ እነዚኽንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አጥኚዎች “Psalms of Ascent” (የመውጣት መዝሙራት) ይሏቸዋል::
♥❖♥ እናትና አባቷም ሊቀ ካህናቱን ካለበት ቅዱስ ቦታ ወደነርሱ እስኪመጣ ለመቆየት ልጃቸው ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯትም ርሷ ግን በድንቅ አምላካዊ ሥራ መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ የሦስት ዓመቷ እመቤታችን ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት በእጅጉ ወደተቀደሰው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወዳለበት ስፍራ ኼደች ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት፤ ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሊቀ ካህናቱ የሰው ዘርን በመላ ወደ ገነት የሚያስገባ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የእግዚአብሔር ልጅን የምትወልደው ርሷ እንደኾነች ገልጾለት ቦታዋም በጣም የተቀደሰውና ርሱ መሥዋዕት ለማቅረብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገባበት ከርሱ በቀር ማንም ሰው የማይገባበት ቅድስት ቅዱሳን ውስጥ መኾኑን ገልጾለታል ፡፡
♥❖♥ ርሱም ይኽነን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ይኽቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ብሎ ሲጨነቅ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብስት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ ፲፮፥፴፩፤ ፩ነገ ፲፱፥፮፤ ዕዝ. ሱቱ. ፲፫፥፴፰-፵፩)::
♥❖♥ ከዚያም “ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሀባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ” ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊን፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡
♥❖♥ ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላክ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ ታኅሣሥ ፫ በ፭ሺሕ ፬፻፹፰ (5488) ዓመተ ዓለም በሦስት ዓመቷ አስገብተዋታል፤ ከዚያም ኢያቄምና ሐና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡
♥♥♥ የቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ መቅደስ ሕይወት በእጅጉ አስደናቂ ሲኾን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት (Holy Tradition) እንደሚያስረዳን ቤተ መቅደስ በኖረችባቸው 12 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለቤተ መቅደስ የሚያስፈልገውን ነገር በእጆቿ እየሠራች በፍጹም ንጽሕና ቅድስና ኾና እግዚአብሔርን በማመስገን መላእክት እያገለገሏት ኖራለች፡፡
ይኽነን በቤተ መቅደስ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል እነሆ የሊቃውንቱ ቃል፦
፩) [አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ]
“የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና
ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስና
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”
(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል)♥
♥“ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስ
በድንግልና ማርያም ስርጉተ ሥጋ ወነፍስ
ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ
ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ
እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ”
(በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ)
++++++++++++++
፪) [ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም]
♥♥♥ “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ…” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ)
+++++++++++++++++++
፫) [በ፭፻፭ (505) ዓ.ም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን]
♥“አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ…” (ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ፤ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ እንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቊ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ፤ እንዲኽ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ፤ መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤ መላእክት እየጐበኙሽ እንዲኽ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር፤ ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር)
♥ “መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት) (ቅዱስ ያሬድ፤ መጽሐፈ ድጓ)
♥ ጌታ የመረጠሽ ማርያም ሆይ ለምኝልን፤ ዕፀ ጳጦስ ተብላ የተጠራችውን እመቤታችን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ተቀበላት፤ ኹላቸውም ቅዱሳን ዐዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል)
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
💧💦💧💦💧💦💧💦💧💦💧💦
ጾምና ጸሎት በአበው አንደበት
👉 "ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ጸሎትን የማታደርግ ነፍስ ሕይወት የላትም።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👉 "ጾም የነፍስን ቁስል ትፈውሳለች ፣ የሥጋ ምኞትንም ታሥታግሳለች ለወጣቶች ትዕግሥትን ታስተምራቸዋለች።" ቅዱስ ያሬድ
👉 "ጾም ጸሎት ከስግደትና ከምጽዋት ጋር ከሆነ የጦር ዕቃ ነው።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
👉 "ጸሎት የእኛን ፈቃድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር አስማምተን የምንመራበት ነው።"
ቅዱስ ኤፍሬም
👉 "የማይጸልይ ሰው ቅጽር የሌላትን ሀገር ይመስላል ያን ማንም እየገባ እንዲዘርፈው እርሱም የተሰጠውን ጸጋ ያጣል።"
ማር ይስሐቅ
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
እንኳን ለነቢየ ልዑል ለቅዱስ አልያስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ! አደረሰን!
💠ቅዱስ አልያስ ማለት በአጭሩ፦
አክአብና ኤልዛቤል ጣዖት በማምለከታቸው ኤልያስ 3 ዓመት ከ6 ወር ዝናብን እንዳይዘንብ በጸሎቱ ያቆመ፤
💠የሰራጵታዋን መበለት የሞተ ልጇን ከሞት ያስነሣ፤
💠 የአቀረበውን መሥዋዕት እሳት ከሰማይ ወርዶ0 ስለበላለት መሥዋዕቱን እግዚአብሔር የተቀበለለት፤
💠ከ3 ዓመት ከ6 ወር በኋላ ቀርሜሎስ ወጥቶ በመጸለይ ዝናብ እንዲዘንብ ያደረገ፤
💠አካዝያስ የላካቸውን 50 አለቃዎችን እሳት ከሰማይ አውርዶ ያቃጠለ፤
💠በመጐናጸፊያው የዮርዳኖስን ወንዝ የከፈለ፤
💠በእሳት ሠረገላ በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የዐረገ፤
በደብረ ታቦር ጌታ ምሥጢረ መንግሥቱን ሲገልጽ ከሙሴ ጋር አብሮ የተገኘ፤
💠ዳግመኛ በመምጣት በሐሳዌ መሲሕ ጊዜ መጥቶ ሰማዕትነትን የሚቀበል እጅግ ክቡር ነቢይ ነው።
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ "ቴስቢያዊ፣ ኮሬባዊ (ወደ ኮሬብ ተራራ የወጣ)፤ ታቦራዊ (በታቦር ተራራ የተገኘ)፤ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የለጐመ ለኾነ፤ የጸሎቱ ቃልም በአዶናይ ጆሮ ውስጥ ለተሰማ፤ ውኃውን እስኪበላ ደርሶ እሳትን ከሰማይ ያወረደ ለኾነ፤ በእሳት ሠረገላ ተጭኖ ወደ ተድላ ደስታ ቦታ ለገባ ለነቢዩ ለኤልያስ ሰላምታ ይገባል) ሲል አወድሶታል።
ሊቁ አርከ ሥሉስም በአርኬ መጽሐፉ ላይ፦ "ምድራዊ የሆነ የዓም ሕይወትን አራግፈህ ለማረፍ ወደ ሰማያት ያረግህ ለሆንክ ለአንተ ለኤልያስ ሰላም እላለሁ፡፡ አክአብን ለተናቀ ሥራው እየዘለፍከው ጣዖታትን የቀጠቀጥክ ማምለኪያዎቹን ያፈረስክ በምስጋናህ ምንኛ ተመሰገንህ) ብሎ አመስግኖታል።
የነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን።
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
💠ጊዜ ለመቆጠብ የሚባክን ጊዜ!💠
................. ......................
🛐ብዙ ጊዜ በአገልግሎት የምናውቃቸው፣ነግህ ለኪዳን ሠርክ ለጸሎት ከአውደ ምሕረቱ የማይጠፉ። በጎደለው በኩል ቆመው የሚሞሉ፣ ለአገልግሎት የማይታክቱ ብዙ እህትና ወንድሞች ከሆነ ጊዜ በሗላ ሥራ ጀምረው፣ትዳር መስርተው...ወዘተ በአጋጣሚ አግኝታችሁ "ምነው ጠፋችሁ ከቤተክርስቲያን ?" ብላችሁ ስትጠይቋቸው። መልሳቸው ጊዜ አጣሁ ነው።
👉ብዙዎቻችን ለእግዚአብሔር ጊዜ የምንሰጠው በችግር ጊዜ፣ባጣን ጊዜ፣ተስፋ በቆረጥን ጊዜ፣ በጎደለብን ጊዜ እንጂ በበረታን፣ በተሳካልን፣ በሆነልን ጊዜ አይደለም። የሚገርመው ለጸሎት ጊዜ፣ለቤተክርስቲያን ጊዜ መስጠት በማቆማችን ባናውቅም ፣ባይገባንም ጊዜ ለመቆጠብ ብለን ከእግዚአብሔር ቤት በመራቃችን በሕይወታችን ብዙ ነገር ይባክናል። ጥቂት ጊዜ ከአምላክ ፊት በመቆም የምናገኘው መልስ በአቅም ስንደክም ዘመናትን እናስቆጥራለን።
አንድ ታሪክ አለ ማሳያ የሚሆን" በአንድ ወቅት ሰውየው በደነዘ መጥረቢያ የዛፉን ግንድ ለመቁረጥ ይታገላል። መጥረቢያው እየነጠረ ከመመለስ ውጪ የተፈጠረ ነገር የለም። ይህን ሁኔታ ያስተዋለ አንድ መንገደኛ ሰው ጠጋ ይልና << ወንድሜ መጥረቢያዉ እኮ ደንዟል አንድ ጊዜ አረፍ ብለህ ሳል ሳል ብታደርገው ጥሩ ነው " አለው። በደነዘ መጥረቢያ እየታገለ ያለው ምስኪን ሠው መንገደኛውን ዞር ብሎ አየውና "እርሱን የምስልበት ጊዜ የለኝም" በማለት በደነዘው መጥረቢያ መደብደቡን ቀጠለ ይባላል፡፡
💠ይኼ ሰው እኛን ይመስላል። መጥረቢያ ለመሳል የቆጠበውን ጊዜ ግንዱን ለመቁረጥ የወሰደበትን ጊዜ ተመልከቱ። 👉መጥረቢያውን ለመሳል የሚወስድበት ጊዜ 10 ደቂቃ ሊሆን ይችላል።👉 ባልተሳለ መጥረቢያ ቢቆርጥ ግን ሰዓታትን ይፈጅበታል።ጊዜውንም ጉልበቱንም ያባክናል።
💠ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ፣በመጸለይ፣ቅዱሳት መጻሕፍን በማንበብ፣ በማገልገል የምናባክነው ጊዜ የለንም።
💠በቀናችን ውሎ ካለን ጊዜ በቤተክርስቲያን የሚኖረን ቆይታችንም ጥቂት ጊዜ ነው።ያውም በብዙ የምናተርፍበት።
💠ለጸሎትና ለአገልግሎት
የምናውለውን ጊዜ እንደባከነ ልንቆጥረው አይገባም። ምክንያቱም በዓለም ሀሳብ እንዳንባክን፤የተሰጠን ነገር እንዲባረክ፣ በስራና በትዳር ሕይወታችን እንዳንዝል፤እግዚአብሔር ካዘጋጀልን መልካም ስጦታ እንዳንዘገይ ይረዳናል ይረዳናልና።
ጊዜ ለመቆጠብ ብለን ከሕይወት ምእራፍ እንዳናረፍድ እንጠንቀቅ። ጊዜ የእግዚአብሔር ነውና
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
#ዕለታዊ_መልዕክት
"አንተ በየዕለቱ ጠዋት ጠዋት ከእንቀልፍ ስትነቃ የምትጨነቀው ስለ ምንድርን ነው፣ የምትጨነቀው ፊትህን መታጠብህ፣ ቁርስህን መብላትህ፣ ልብስህን መልበስህና ለመሄድ መዘጋጀትህ የቀን ተቀን ሕይወትህ ነውን ወይስ የመጀመሪያ ጉዳይህ ዕለቱን በጸሎት በንባብና በተመስጦ ከእግዚአብሔር ጋር መጀመር ነው... እንደዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ላይ አንዳንዶች 'ለመጸለይ ጊዜ የለኝም' ይላሉ። እኔ ግን እውነተኛ ምክንያት ነው ብዬ አልቀበለውም። አንተ ግን ጸሎትህንና ተመስጦህን ካስቀደምክ ያ አጣሁት የምትለው ጊዜህን ታገኘዋለህ። ስለሆነም በሁሉም ነገር ላይ ለእግዚአብሔር ቅድሚያ ስጥ።
🙏 የጸሎት ህይወት ይኑረን 🙏
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
ብዙዎቻችን ለምን እንደምንኖር አላወቅንም። በዚህ ምድር ሳለን የምንናገረው፣ የምናስበው፣ የምናደርገው ነገር ሁሉ ከሞት በኋላ ለምንኖረው ዘለዓለማዊ ሕይወት ግብዓት የሚሆን መሆን ሲገባው በቀልድ፣ ለማንም በማይጠቅም ንግግር፣ ጊዜያችንን ስናባክን ይስተዋላል። እያንዳንዱ ድርጊታችን ከፈጣሪ ዘንድ እንጠይቅበታለን። መልካም ከሆነ እንሸለምበታለን። ክፉ ከሆነ ለዘለዓለም እንሰቃይበታለን።
ስለዚህ ያለንበትን ሁኔታ ቆም ብለን አስበን በክፉ መንገድ ካለን ንስሓ ገብተን ወደ መልካም መመለስና በመልካም መንገድ ካለን ደግሞ በዚሁ ለመጽናት መጣር አለብን።
© በትረ ማርያም አበባው
/channel/dnhayilemikael
♥ መድኃኔዓለም ♥
💠«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው።
💠ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?????
👉 ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው።
💠ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው።
👉 በፈጠራቸው ፍጥረታት ተሰቃየ ተተፋበት መከራ ጸናበት ሰቀሉት ።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር።
💠ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።
ታድያ
💠 እኛ ደግሞ መንግሥቱን ለመውረስ ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።
💠ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን። በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ።
አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።
።
መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።
/channel/dnhayilemikael
"ካህኑን እንደ መንፈሳዊ አባትነቱ እየው፤ ልክ በሽተኛ የተሸፈኑ ቁስሎችን ለሐኪም እንደሚያሳይና እንደሚፈውስ ምስጢሮችህን በግልጽ ንገረው”
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ።
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael
#ጾም
*"#እውነቱን_ስለተናገረ_ግን_ተጠቀመ_ወይስ_ተጎዳ ?❓ "*
" ከእናንተ መካከል ፦ " ዋሽቼ ስለ ወንድሜ ክፉ ነገርን ካልተናገርኩ ፥ ነገር ግን እውነት የኾነውን ነገር ብናገር [የሠራው ኃጢአትም ቢኾን] ምን ነውር አለው? የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፡፡
ግድ የላችሁም ! የምታወሩት ነገር እውነት ቢኾንም እንኳን አሁንም ንግግራችሁ ከነቀፋ አያመልጥም፡፡ "እንዴት ኾኖ?" ብላችሁ ልትጠይቁኝ ስለምትችሉ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌ ልስጣችሁና ንግግራችሁ እንዴት ብሎ ክፉ እንደ ኾነ ይገባችኋል፡፡
በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አሥራ ስምንት ላይ የምናገኘው አንድ ፈሪሳዊ አለ፡፡ ይህ ፈሪሳዊ ስለ ቀራጩ ወንድሙ የተናገረው ነገር እውነት ነው፡፡
"ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ። እግዚአብሔር ሆይ ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም ፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤" [ሉቃ.፲፰:፲፩] እንዲህ እውነቱን ስለተናገረ ግን ተጠቀመ ወይስ ተጎዳ? ፍጹም አልተጠቀመም! እንዲህ በማለቱ ባዶ እጁን አልተመለሰምን? በመጸለዩና በመጾሙስ ምን ጥቅም አገኘ?
እስኪ አሁን ልጠይቃችሁ ፤ እናንተም መልሱልኝ፡፡ ቀራጩ ኃጢአተኛ አልነበረምን? ከወንጌሉ እንደምናነበው ያ ቀራጭ ኃጢአተኛ እንደ ነበር ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ፈሪሳዊው በጸሎቱና በጾሙ መካከል የራሱን ኃጢአት ከማሰብና ከማሳሰብ ይልቅ ወንድሙን እያማ ስለነበረ ወደ ቤቱ የተመለሰው የጾምን ዋጋ ሳያገኝ ባዶውን ነበር፡፡ "
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael
💠 ጽዮን የሚለው ቃል ለአምስት ነገሮች መጠርያ ሆኗል
1/ ሙሴ በደብረ ሲና የተቀበለው ጽላተ ሕግ ታቦተ ጽዮን ትባላለች 1ሳሙ 2:19
2/ የአብርሃም ርስት የሆነችው ኢየሩሳሌም ጽዮን ትባላለች 2ሳሙ 5:6
3/ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጽዮን ቅድስት ትባላለች (ቅ.ያሬድ )
4/ መንግሥተ ሰማያት ደብረ ጽዮን ትባላለች ዕብ12:22
5/ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ቅ.ያሬድ )
👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia
#የሰናፍጭ_ቅንጣት_ምሳሌነት
የሰናፍጭ ዘር ስትዘራ መጠኗ ከዘር ሁሉ ያንሳል፤ በአደገች ጊዜ ግን ከአታክልቶች ትበልጣለች፤ የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች፡፡ ምሳሌነቷም ለመንግሥተ ሰማያት መሆኑ ተገልጧል፡፡ እዚህ ላይ መንግሥተ ሰማያት የተባለች ወንጌል ናት፡፡ ምክንያቱም በሕገ ወንጌል ጸንቶ የኖረ መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳልና፡፡
በዚህም መሠረት ሰናፍጭ ለወንጌል ምሳሌ የሆነችበት ምክንያት ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡
➛ ሰናፍጭ ፍጽምት ናት፣ ነቅ የለባትም፤ ወንጌልም ነቅዓ ኑፋቄ የሌለባት ፍጽምት ናት፡፡
➛ ሰናፍጭ ላይዋ ቀይ ውስጧ ነጭ ነው፤ ወንጌልም በላይ ደማችሁን አፍስሱ ትላለች በውስጥ ግን ሕገ ተስፋ ናት፡፡ ይህም ተስፋ መንግሥተ ሰማያት ነው፡፡
➛ ሰናፍጭ ጣዕሟ ምሬቷን ያስረሳል፤ ወንጌልም ተስፋዋ መከራን ያስረሳል፡፡
➛ ሰናፍጭ ቁስለ ሥጋን ታደርጋለች፣ ወንጌልም ቁስለ ነፍስ ታደርቃለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ደም ትበትናለች፤ ወንጌልም አጋንንትን፣ መናፍቃንን ትበትናለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ከምትደቆስበት ተሐዋስያን አይቀርቡም፤ ወንጌልም በእውነት ከምትነገርበት አጋንንት መናፍቃን አይቀርቡም፡፡
➛ ሰናፍጭ ስትደቆስም ስትበላም ታስለቅሳለች፤ ወንጌልም ሲማሯትም፣ ሲያስትምሯትም ታሳዝናለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ከበታቿ ያሉትን አታክልት ታመነምናለች፤ ወንጌልም የመናፍቃንን ጉባኤ ታጠፋለች፡፡
➛ ሰናፍጭ አንድ ጊዜ የዘሯት እንደሆነ ባመት ባመት ዝሩኝ አትልም፤ ተያይዞ ስትበቅል ትኖራለች፡፡ ወንጌልም አንድ ጊዜ ተዘርታ ማለትም በመቶ ሃያው ቤተሰብ ተጀምራ እስከ ምጽአት ድረስ ስትነገር ትኖራለች፡፡
➛ ሰናፍጭ የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ እንድትሆን፣ ወንጌልም ሕዝብም አሕዛብም ተሰብስበው መጥተው እስኪያምኑባት ድረስ ደግ ሕግ ትሆናለች፡፡
/channel/dnhayilemikael
ለምንድን ነው የምንጾመው?
💠እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡
👉 ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው?
👉 በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን?
👉በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡
👉ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?
💠በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡
👉ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-
#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡
💠በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡
👉በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡
👉ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ 👉ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡
#ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡
💠ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ 👉እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡
👉አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡
👉በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡
👉ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡
(#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 71-72 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ እንደተረጎመው)
/channel/Meseretemedia
የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )
⬇️
➡️ መሰረተ ሚዲያ ⬅️
⬆️
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ
👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia
ጾም በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
🛐 ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡
💠ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡
💠እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡
👉❤ልቡናችንን በማንጻት፣
👉 ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣
👉 የክፋት እርሾን በማስወገድ፣
👉ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት
💠የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡
ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡
🛐🛐🛐 በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡
💠ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡
🛐እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡
💠ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia
#ዕለታዊ_መልዕክት
ሕፃናት የእናታቸውን ጡት ለመጥባት ምን ያህል እንደሚጓጉ አስተውላችኋልን? እኛም ወደ ቅዱሱ ማዕድ መቅረብ ያለብን፣ ከመንፈሳዊው ጽዋ ጡትም ለመጠጣት መጓጓት ያለብን እንደዚህ ነው፡፡
ሕፃናቱ የእናታቸውን ጡት ሲያዩ እንዴት ደስ እንደሚሰኙም ተመልክታችኋል! እኛም የመንፈስ ቅዱስን ፍቅር ስንመለከት ደስ ሊለን የሚገባው እንደዚህ ነው፡፡
ሕፃናቱ የእናታቸው ጡት ሲከለከሉ ምርር ብለው እንደሚያለቅሱ ኹሉ፥ እኛም ከዚህ ማዕድ (ከቅዱስ ቁርባን) ስንርቅ ምርር ብለን ልናለቅስ ይገባናል::
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
"እነሆ መቅደሱ ይቀደስ ዘንድ አማናዊቷ ቤተመቅደስ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባች"
🌹🌹🌹ባዕታ ለማርያም❤🌹🌹🌹
እንኳን (ለባዕታ ለማርያም) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ ለገባችበት አመታዊ የንግስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏🙏
ነገ ታህሳስ 3 /4/2016 በዓሉ በደማቁ ይከበራል
❤️ዓመ ሰሉሱ ለታህሳስ በአታ ለማርያም ውስተቤተ መቅደስ❤
መልካም በዓለ ማርያም🙏
የባዕታ ማርያም ምልጃዋ አይለየን
መልካም በዓለ ዋዜማ ይሁንላቸሁ።🙏
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
++++እናስተውል በድጋሜ የዘላለም ቁጣ ሳይመጣ++++
ልጄ ሆይ ዛሬን ብትወድቅ ተስፋ አትቁረጥ ተነስ እንጂ ዛሬ እንደ ቃሉ በፍቅር መኖር ቢያቅትህ መፍትሔው ተስፋ መቁረጥ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ እንጂ ዛሬ በአገልግሎትህ ብትደክም ተስፋ ቆርጠህ ከቤቱ ከቶ አትውጣ፡፡ ከሐዋርያት ጋር ሆነህ ጌታ ሆይ ወደ ማን እሄዳለሁ? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ በለው፡፡ ዮሐ 6፡68 ከዳዊት ጋርም ሆነህ አሁንስ ተስፋዬ ማነው አንተ እግዚአብሔር አይደለህምን በለው መዝ 38፡7 ፍሬ ለማፍራትም በእርሱ ተስፋ አድርግ፡፡ በተስፋ ለምትጠባበቀው ለምትሻውም ነፍስ ጌታ ቸር የሚራራም ነውና፡፡ ልጄ ሆይ አዳም ከገነት ቢሰደድ ይዞ የወጣው ሌላ አይደለም ተስፋን ነው፡፡ በጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ እድሜ ልኩን በክፉ ስራ ቢኖርም ተስፋን ግን አልጣለም በመጨረሻ ትንፋሽ ላይ ሳለ ወደ ሕይወት ያደረሰችው ይህች ተስፋ አለመቁረጥ ናት፡፡ በግራ ያለውማ ተስፋ በመቁረጡ የእምነትና የፍቅር ሻማዎቹ ሊበሩለት አልቻሉም፡፡ እንግዲህ ልጄ ሆይ በጊዜውም ያለጊዜውም እርሱን ተስፋ አድርገህ ኑር፡፡ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ።
:ምናልባት ለመፆም፣ ለመፀለይ፣ ለማስቀደስ፣ ለመስገድ፣ የተለያዩ መንፈሳዊ ተግባራትን ለማከናወን ፍላጎታችን ፍቅራችን ጠፍቶ ይሆናል። እነዚህን መንፈሳዊ ተግባራትን ለማከናወንም እምነት አጥተን ይሆናል ግን ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም በእግዚአብሔር። ፍቅር እንዲጨምርልን እንለምነው። አለማመኔን እርዳው እምነትን ጨምርልኝ፣ ትእዛዛቶችህን ለመፈፀም እምነት ይጎድለኛል። በመፆም በመፀለይ የሚገኘውን በረከት አላስብም እንዲሁ ለማድረግ ያክል ብቻ ነው። ዋጋም ያለው አይመስለኝም። አምላኬ ፍቅርህን አብዛልኝ አንተን ማመንንም ጨምርልኝ ብለን እንለምነው። የመበለቲቱን ሁለት ዲናር ሳይንቅ አክብሮ የተቀበለ አምላካችን ይለመነናል።
‹‹እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ›› መዝ 36፡9
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
#ሆድ_አምላክ_ይሆናልን?
የሰው ልጅ ወደድኳቸው በሚላቸው ነገሮች ሕይወቱ ይወሰናል። ሰይጣንም በምንወዳቸው ነገሮች ቀዳዳ በኩል ገብቶ ነው በውንብድና የጸጋችንን መዝገብ የሚበረብር።
ለእግዚአብሔርም ያለንን ፍቅር የምንገልጠው በምንወዳቸው ነገሮች ነው። እርሱ አንድ ልጁን በመስጠት ፍቅሩን እንደገለጠልን እኛም የምንወዳቸውን ለእግዚአብሔር ብለን ይቅርብን ብለን በመተው በዚህ ፍቅራችንን እንገልጣለን።
የምንወዳቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ፋንታ ከገቡብን፥ እነዚያ በእርግጥ የምንወዳቸው ነገር ግን በፍቅረ እግዚአብሔር የተካናቸው የወዳጅ ጠላት የሆኑበትን ጠዖታት ናቸው። ከእነዚህም ሳይገባን ጣዖታት አደርገን ከምናመልካቸው መካከል አንዱ ሆድ ነው።
እግዚአብሔር አትብሉ ብሎ የከለከለንን ነገርና አትብሉ ባለን ሰአት የምንበላ ከሆነ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሆዳችንን እየወደድን ስለሆነ ሆዳችንን አመለክን ማለት ነው።
ይህ ብቻ አይደለም፤ እግዚአብሔር እውነት ነው እቸገራለሁ ብሎ አስቦ መዋሸትም ጣዖት ማምለክ ነው። ለሆዱ ብሎ የሚዋሽ ሰው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር ይቃረናልና። የእግዚአብሔር ባሕርይው እውነት ነው።
ድኻ እየተቸገረ እያዩ ለነገ በማሰብ የማይመጸውቱ ሰዎችም በሁለት መንገድ ጣዖት አምልከዋል፦
#አንደኛ አስቀድመን እንደ ገለጥነው ከፍቅር ይልቅ ገንዘብን በማስቀደም፤
#ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ራሳቸውን ለራሳቸው ጠባቂ መጋቢ አድርጎ በመሾም መግቦተ እግዚአብሔርን በመካድ ነው።
እንግዲህ እናስተውል ሆድ በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ጣዖት ሊሆንብን እንደሚችል፦
#መጀመሪያ እግዚአብሔር የከለከለንን በመመገብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ይልቅ መብልን በመውደድ፤
#ሁለተኛ ለቅዳሴ መላእክት የተፈጠርን ክቡራን አገልጋዮቹ ስንሆን መላ ዘመናችን ሆዳችንን በማገልገል ራሳችንን የራሳችን ባርያዎች በማድረግ፤
#ሦስተኛ እግዚአብሔር እንደፈጠረኝ ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ለነገ በመስገብገብ ለድኾች አለመራራት ናቸው።
ጾም ፍቅር እንጅ ቀመር አይደለም። የምንጾመው ከምንወደው መብል መጠጥ በመከልከል ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ለመግለጥ እንጅ ሰባት ጾም የጾምን ሰዎች ነን የሚል መስፈርት ለማሟላት አይደለም።
የሰው ልጆች ሁሉ እናትና አባት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዲት የእንጨት ፍሬ የተከለከሉት ያችን በመተው ፍቅረ እግዚአብሔርን እንዲገልጡ እንጅ ለአንዲት እንጨት ፍሬ ነፍጓቸው አይደለም። እርሱማ እንኳን የበለስ ፍሬ ሊነፍገን ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት የሰጠ የባሕርይ ቸር አይደለምን?
ክርስትና የፍቅር ሃይማኖት ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ስለ ፍቅር ትጾማለህ፤ ስለ ፍቅር ትጸልያለህ፤ ሰለ ፍቅር ትሰደዳለህ፤ ስለ ፍቅር ትታሰራለህ፤ ስለ ፍቅር ትናቃለህ፤ ስለ ፍቅር ግፍን ሁሉ ተቀብለህ ትሞታለህ፤ በፍቅር ብርሃን ደምቀህ ትነሣለህ።
ፍቅር ደግሞ ስለ ፍቅር በመማር የምታውቃት አይደለችም ስለ ፍቅር በመኖር እንጂ። ፍቅር በልቡናህ ዛፍ ሆኖ የተተከለ እንደሆነ ሥሩ እስከ ተረከዝህ ይወርዳል፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ራስህ ያድጋሉ፤ አበባቸው በአንደበትህ ይፈነድቃሉ፤ የፍቅር ፍሬዎችም እነ ጾምና ጸሎት ምጽዋት ከአንተ በመላእክት እጅ እየተለቀሙ በሰማይ ጎተራ ይከማቻሉ፤ የፍቅርን ፍሬ እየበላህም ለዘለዓለም ትኖራለህ።
እግዚአብሔርን የምትወደው ከሆነ እንኳን ሰባቱን አጽዋማትን ሁሉንም ቀን ትጾማለህ። ፍቅረ እግዚአብሔር ያነሰህ ፍቅረ መብልዕ የበዛልህ ስትሆን ደግሞ ጾም ይቀነስልኝ ብለህ ክተት ሠራዊት ትወጣለህ፤ ነጋሪት ትጎስማለህ። እንዳትጾም የሚረዱህ የሚመስልህን ጥቅሶችም በመብራት እየፈለግህ ትለኩሳለህ። በጅብ ቆዳ የተለጎመ ከበሮ ሲመቱት 'እንብላው' ብሎ ይጮኻል እንዲሉ አበው፤ የሆድ ጠበቃ የሆኑ የጅብ ስብከት የሚያመሰጥሩ የእንብላው መጽሐፍ ሊቃውንትንም አታጣም።
እናም ወዳጄ ሆይ "እለ ከርሦሙ ያመልኩ" "ሆዳቸው አምላካቸው ነው" እንደለ ቅዱስ ጳውሎስ (ፊልጵ. ፫፥፲፰ )የምትወደው ሆድህ ጠላት ሆኖ በግራ እንዳያቆምህ በእግዚአብሔር ፍቅር ሰይፍነት የስስትን ገመድ ቆርጠህ ጥለህ ከምጽዋትና ከተገራ ሰውነት ጋር ጹም!
#መጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ_ገብረ_ኪዳን
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
አንድ ሰው መጥቶ እናንተ የምትለብሱትን አንዲት ቁራጭ ልብስ እንኳ ሳይሰጣችሁና ሰውነታችሁ በብርድና በዋዕየ ፀሐይ እየተቆራመደ ሳለ ቤታችሁን በወርቅና በተንቆጠቆጠ የመጋረጃ ዓይነት ቢያስጌጥላችሁ ምን ጥቅም አለው? እኛስ ነፍሳችን ዕራቁቷን ሳለች ሥጋችንን ወርቅ ብናለብሰው በወርቅ ብናስተኛው ምን ትርጉም አለው? ነፍሳችን በመሬት ላይ እየተንፏቀቀች ሳለ ሥጋችን በከበሩ ሠረገላዎችና የተለያዩ ማጓጓዣዎች ብትንፈላሰስ ምን ጥቅም አለው?
ልጆቼ ! እውነተኛውን ልብስ ልበሱ ብዬ እመክራችኋለሁ። እዚህ የሚቀረውን ሳይኾን ዘለዓማዊውን ልብስ ልበሱ። የሰርጉን ልብስ ልበሱ።
እስኪ በየገዳማቱ ሒዱና ይህን ከቅዱሳን አበው ወእማት ተማሩ። እነዚህ ቅዱሳን በእልፍ ወትእልፊት ዕንቁ የተሽቆጠቆጠ ልብስ ብትሰጥዋቸው አይቀበሏችሁም። ለምን? እነርሱ ጋር ያለው ልብስ እናንተ ይዛችሁት ከሔዳችሁት ይልቅ በእጅጉ እንደሚበልጥ ስለሚያውቁ! ይኸውም የነፍሳቸው ልብስ ማለቴ ነው።
ለእነርሱ ይዛችሁት የሔዳችሁት ልብስ ለአንድ ምድራዊ ንጉሥ ብትሰጡት እጅግ ያመሰግናችኋል። እነርሱ ግን ከዚህ ንጉሥ በላይ በከበረ ልብሱ ያጌጡ ናቸውና አይቀበሏችሁም። ወርቃቸውን ወደሚያስቀምጡበት መዝገብ (ልቡናቸው) ገብታችሁ ስታዩ'ማ ራሳችሁን ስታችሁ ትወድቃላችሁ ። የሀብታቸውን (ምግባር ትሩፋታቸውን) ብዛት የወርቃቸውን ንጻት እንዲህ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም ። እናንተም ከእነርሱ ተማሩና እውነተኛውን ልብስ ለመልበስ ተሽቀዳደሙ ።
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ)
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
♥ መድኃኔዓለም ♥
💠«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው።
💠ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?????
👉 ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው።
💠ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው።
👉 በፈጠራቸው ፍጥረታት ተሰቃየ ተተፋበት መከራ ጸናበት ሰቀሉት ።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር።
💠ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።
ታድያ
💠 እኛ ደግሞ መንግሥቱን ለመውረስ ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።
💠ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን። በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ።
አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።
።
መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።
/channel/dnhayilemikael
#ድነኀል_ወይስ_አልዳንክም?
◦ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በአንድ መጽሐፋቸዉ እንዲህ ይላሉ። አንድ ወጣት ልጅ እንዲህ ብሎ ጠይቆኛል “አንድ ሰው ድነኀል ወይስ አልዳንኽም?” ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድ ነው?
◦ መጀመሪያ ይሄ ሰዉ እዉነተኛ ኦርቶዶክስ እንዳልሆነ ማወቅ አለብህ። በእርግጠኝነት ይሄ ሰዉ ፕሮቴስታንት ነዉ ወይንም ቢያንስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ውስጥ ነዉ የሚኖረዉ፣ ባህሉም የፕሮቴስታንት ነው። ከዚህ በፊት የተቀበልካቸዉን ምስጢራትንና ጥምቀትን እንደ ምንም ቆጥሮ፣ በሃይማኖትህ ላይ ጥርጥር ለመሙላት በመሞከር፣ ባለፈዉ የሕይወት ዘመንህ ሁሉ አሕዛብ እንደነበርክ አድርጎ እንደ ገና እመንና ዳን ሊልህ ነው። ይሄ ሰዉ በፍጹም ኦርቶዶክስ ሊሆን አይችልም አነጋገሩም ይገልጠዋል።
◦ ለማንኛዉም እንዲህ ብለህ ልትመልስለት ትችላለህ “በጥምቀት ከአዳም የውርስ ኀጢአት ድኜያለሁ፤ ይሄ ድኅነት የሚገኛዉ በደመ ክርስቶስ የቤዛነትንና የድኅነት ኀይል ነው። ነገር ግን የመጨረሻዉ ድኅነት በስጋ ስንለይ የሚገኝ ነው። አሁንም በውጊያ ላይ ነን “መጋዳላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፣ ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር እንጂ።” (ኤፌ. 6፥12)። ይሄንን ውጊያ ድል ስናደርግና ስናሸንፍ ድኅነትን እናገኛለን…”
◦ በስጋ እስካለን ድረስ “ድል ነስተናል፤ ድኅነትን አግኝተናል” ልንል አንችልም። ስለዚህ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት አታከብርም ወይም የተጠመቁበትን ዕለት፤ ይልቁንም ከዚህ ዓለም የተለዩበትን ወይንም መስዋዕት የሆኑበትን ቀን ታከብራለች እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና “ዋነኞቻችሁን አስቡ፣ የኑሮአቸዉንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸዉ ምሰሉአቸዉ።” (ዕብ. 13፥7)። ስለዚህ በቅዳሴ ላይ የቅዱሳንን መታሰቢያ እናደርጋለን፤ በእምነት ፍጹማን የሆኑትንና ሕይወታቸውን በእምነት የፈጸሙትን፣ በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ እናስባለን።
◦ ይሄም የታላቁ አባ መቃርስን ከዚህ ዓለም መለየት እንዳስታውስ ያደርገኛል። ነፍሱ ከስጋው ተለይታ ስትሄድ “መቃርስ አንተ ድነኸል” እያሉ አጋንንት ነፍሱን አሳደዷት፤ ነገር ግን ገነት እስከሚገባ ድረስ “በጌታ ጸጋ ድኜያለኹ” አላላቸዉም ነበር…!
.
.
ምንጭ ፦ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ነገረ ድኅነትን አስመልክቶ ለፕሮቴስታንቶች መልስ ከሰጡበት “Salvation in the Orthodox Concept” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ ነዉ።
/channel/dnhayilemikael
ከሀቢብ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ራስን መስጠትና እውነተኛ
አገልግሎት እንማር
‹‹... በዚያን ጊዜ የነበረው አገልግሎት ብዛት ያላቸው ችግሮች ነበሩበት፡፡
💠ሰባኪያንና የተማሩ ካህናት አልነበሩም፡፡
💠በመሆኑም በቤተ ክርስቲያን ድካም ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች ያድጉ ጀመር፡፡
👉በዚህ ጊዜ መለያየትና ውስጣዊ ጠብ ተስፋፋ፡፡
💠ጥቂት ሰዎች👉 ስድብን ፣ 👉ነቀፌታንና👉 ማጎሳቆልን በይፋ ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ👉 በፍርድ ቤት ለሕግ ጉዳዮች ከፍተኛ ገንዘብ በማባከን ቤተ ክርስቲያንን ይዋጓት ጀመር፡፡
💠ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ምንም ዓይነት ጥቅም አልነበራቸውም፡፡ 💠ቤተ ክርስቲያን ከስድብ ፣ከትችት ፣ ከማጎሳቆል ፣ ከመከፋፈል ፣ከፍርድ ቤት ወይም ከለቅሶ የተጠቀመችው ነገር አልነበራትም፡፡ ታዲያ ለውጥ እንዴት ሊመጣ ቻለ?
ለውጥ የመጣው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን የአገልግሎት መሪ በነበረው በሀቢብ ጊዮርጊስ መልካም ሥራ አማካኝነት ነው፡፡
👉እርሱ በዘመኑ በነበሩት ስኅተቶች ውስጥ ራሱን ሳያስገባ ሥራ ጀመረ፡፡
💠በወቅቱ ሁለት ወሳኝ የመሠረት ድንጋዮችን በዚያ ጣለ ፤ ለሰ/ት/ቤትና ለመንፈሳዊ ኮሌጅ፡፡
👉እነዚህን ነገሮች መመሥረት እንደጀመረ መሠረቶቹ በየዕለቱ ያድጉ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ፣ በየማኅበረሰቡ ፣ በየሰንበት ትምህርት ቤቱና በየመንደሩ መስበክ የጀመሩ ብዙ ቁጥር ያላቸው አገልጋዮች ታዩ፡፡
💠 ሀቢብ ጊዮርጊስም ይህን እየተመለከተ ፡-
‹‹ሕዝብህ ፈቃድህን በመፈጸም በበረከትህ እልፍ አእላፋት ይሁኑ!›› እያለ ይዘምር ነበር፡፡
💠እርሱ በጉድለቶች ላይ ነቀፌታ አልሰነዘረም ቤተ ክርስቲያን የሚጎድሏትን ነገሮች ለማቅረብ ሥራ ሠራ እንጂ፡፡
👉 ቤተ ክርስቲያን ሰባኪያን ይጎድሏት ነበር ፣ አብዛኞቹ ካህናት አባቶች የቅዳሴና የሥርዓት መጻሕፍትን ብቻ የሚያነብቡ ስለነበሩ የመስበክ ችሎታ አልነበራቸውም፡፡
👉 ሀቢብ ጊዮርጊስ ግን ይህን ዓለም በቤተ ክርስቲያን ዕንባ አልሞላውም ፤ ይልቁንስ ሰባኪያንና አገልጋዮችን ማደራጀት ጀመረ እንጂ፡፡
💠 የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የሰባኪያን ማኅበር እንዲያቋሙ አድርጓቸዋል ፤
💠 እነዚህ ተማሪዎች ደግሞ በካይሮ ፣ በጊዛ እና በሌሎች ከከተማው ወጣ ባሉ ቦታዎች ላይ ሰማንያ አራት ቅርንጫፎችን ሊያቋቁሙ ችለዋል፡፡
💠 ሀቢብ ጊዮርጊስ ሕጻናትና ወጣቶች አንድ እንኳን የሚያስተምራቸው ሰው ማጣታቸውን ሲመለከትም ከዚያ ተነሥቶ ቤተ ክርስቲያንን ለመተቸት ወይም ለመውቀስ አልወደደም፤ ዛሬ በሁሉም ሥፍራ ለመስፋፋት የቻሉትን ሰንበት ትምህርት ቤቶች አቋቋመ እንጂ፡፡
💠 ከዚህ ሌላ ለትምህርት ቤቶችንና ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤቶች መጻሕፍትን አዘጋጅቷል፡፡
💠 በአንዳንድ ጉባኤዎች የፕሮቴስታንቶች መዝሙር ቦታ እየያዘ ሲመጣ በቤተ ክርስቲያን ዜማ የተቃኙ መዝሙራትን ያዘጋጅ ጀመር፡፡
💠 የእርሱ አገልግሎት በሁሉም መስክ የተስፋፋ ነበር፡፡ በሀቢብ ጊዮርጊስ የተመራው ይህ የማነቃቃት ሥራ ታላቅ ትምህርትን ሰጥቶን አልፏል፡፡››
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 117ኛፓትርያርክ
<<የሀቢብ ጊዮርጊስ ሕይወቱና ትምህርቱ >> የሚል መጽሐፍ ከታች ያለውን ❤ 15 ሰው ከተጫነ በpdf እናደርሳችኋለን
የቴሌግራም አድራሻ
/channel/dnhayilemikael
"ካህኑን እንደ መንፈሳዊ አባትነቱ እየው፤ ልክ በሽተኛ የተሸፈኑ ቁስሎችን ለሐኪም እንደሚያሳይና እንደሚፈውስ ምስጢሮችህን በግልጽ ንገረው”
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ።
ጾም
ጾም እጅግ ግሩም የሆነ ነገር ነው፡፡ ኃጢአታችንን እንደማይጠቅም አረም ከውስጣችን ይነቅለዋል፡፡ እውነተኛው የጽድቅ ተክልም በውስጣችን ልክ እንደ አበባ እንዲያብብ ይረዳዋል፡፡ (ቅዱስ ባስልዮስ)
ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጾም ነው፡፡ የምንጾምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጾም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡ (ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ)
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ለጽዮን ማርያም አደረሳችሁ
ኀዳር ጽዮን
💠ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፡-
👉1.በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ
👉2.ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ
👉3.በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት
👉4.ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
👉5.ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
👉6.ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት
👉7.አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት
👉8.በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን እና ታቦተ ማርያም ባለበት ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል ይከበራል
💠ከዚህ ጋር የመመኪያችን ዘውድ፣ የመዳናችን ምክንያት፣
💠የንጽሕናችን መሠረት ስለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያልተነበየ ነቢይ፣ ያልሰበከ ሐዋርያ፣ ያልተቀኘ ባለቅኔ ከቶ የለም፡፡
💠ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፣ በቤዛነቱ ዓለምን አዳነ፣ ዳግመኛም በክበበ ትስብእት፣ በግርማ መለኮት ለፍርድ ይመለሳል ብንል
👉ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በመሆኑ ያለ ወላዲተ አምላክ ምስጢረ ሥጋዌን፣ ነገረ ድኅነትን፣ ነገረ ምጽአትን ማሰብ ከቶ የማይቻል ነው፡፡
💠«ዕግትዋ ለጽዮን፤ ጽዮንን ክበቧት» እንዳለ ነቢዩ፤ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈባትን የእስራኤል አምባና መጠጊያ የሆነችውን ታቦተ ጽዮንን ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ ያቀርቡላት እንደነበረው፤
👉 ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል ፡፡
💠በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምስጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡
💠 👉ይህቺ የቃል ኪዳን ታቦት በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች፣ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያ. 3÷14-17/፤
👉ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያ 6÷1-21/፤
👉ዳጎን የተባለ የፍልስጥኤማውያንን 👉ጣዖት የቆራረጠች /1ሳሙ 5÷1-5/፤ 👉በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ሳሙ 6÷6/፤
👉በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/፣ 👉ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/፤ 👉ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት/1ነገ 8÷1/፤
👉የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡
በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለውን ረቂቅ እና ድንቅ ምስጢራዊ ንጽጽር አስመልክቶ ሶርያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም፤ «ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሔ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ፤
👉ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በውስጥ በአፍአ በወርቅ የተለበጠ»ያለው።
💠እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሐ ጠባይ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት በንጽሕናና በቅድስና ጸንታ በኃጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡
👉ጠቢቡ ሰሎሞንም፤ «አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ 👉ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኃጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» /መኃ 4÷7/ ሲል ተናግሯል፡፡
👉ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች
💠 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች መሆኗን ያጠይቃል፡፡
👉ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነችው
💠ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ሆናለች፡፡
ይኽንንም ቅዱስ ኤፍሬም ሲያስረዳ፤ «ኮንኪ ታቦቶ ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ፆርኪዮ በከርስኪ ተሰዓተ አውርኃ አንቲ ማእምንት ለዘኢያገምርዎ ሰማያት ወምድር፤ ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» ብሎ ተቀኝቶላታል፡፡
ስለሆነም ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትን የቸርነት በዓል እግዚአብሔር በፈቀደልን ቦታ ሆነን ስናከብር ከእኛ የሚጠበቀውን በጎ ነገር እያሰብን በተግባርም እየገለጥን ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ተሳታፊ እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን
👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia
+ ከአፍ የሚወጣ እሳት +
"አፌ ይለፈልፋል እንጂ ውስጤ እኮ ንጹሕ ነው"
አለች አባ ፊት ቀርባ - በክፉ ንግግርዋ ብዙ ሰው ያስቀየመች ሴት::
አባ መለሱላት :-
ልክ ነሽ ልጄ እባብም እኮ መርዙን ከተፋ በኁዋላ ውስጡ ንጹሕ ነው!
ምላስ አጥንት የለውም ነገር ግን አጥንት ይሰብራል:: እግዚአብሔር ምላስን እንደጆሮ ክፍት አላደረገም:: በከንፈርና በጥርስ ሸፍኖታል:: ትንሽ አሰብ አድርገን እንድናወራ ነው:: "ሰው ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን" የሚለው ቅዱስ ያዕቆብ ስለ አንደበት ሲናገር "ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል" እንዳለ የምላስ ኃይል እጅግ ከባድ ነው:: ከአፍ የሚወጣ እሳት ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል::
ሰው በዱላ ቢደበደብ ታክሞ ቁስሉ ያገግማል:: ክፉ ንግግር የሚያቆስለው ቁስል ግን በቀላሉ አይሽርም:: ዱላ የሚያርፈው ሥጋ ላይ ሲሆን መጥፎ ንግግር ግን ነፍስ ላይ ነው:: ክፉ ንግግሮች ሰውን ለጊዜው ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ሊያመርሩት ይችላሉ::
(ሌላ ነገርዋን ትተነው) ሚሼል ኦባማ በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ በጣም ልብ የሚነካ ነገር ስትናገር ሰማሁ:: ስለወረደባት ስድብ ስታስታውስ "አንዳንድ ክፉ ቃላት የነፍስን ቅርፅ ይቀይራሉ" ብላ ነበር::
እውነት ነው በመራር ቃላት የነፍሳቸው ቅርፅ ከተቀየረ ስንቶች ናቸው:: የማይዘነጉት ንግግር እድሜ ልክ የሚያቆስላቸው : የአንድ ሰው ከባድ ስድብ በራስ መተማመናቸውን የነጠቃቸው : የአንድ ሰው "አትችልም" የሚል ድምፅ እጅና እግራቸውን ያሰራቸው እጅግ ብዙ ናቸው:: ሰው ለማሳቅ ተብለው የተሰነዘሩ "ትረባዎች"ና አጥንት ሰባሪ ቀልዶች ቂመኛ ያደረጉዋቸው ሰውን ሁሉ ያስጠሉአቸው ስንት ናቸው? በስድብ ብቻ የፈረሱ ቤቶች አሉ:: ስለተሰደቡ ብቻ በሕዝብ ላይ የሚፈርዱ ዘር እስከማጥፋት የተነሡ አሉ:: ተናጋሪው በጥፋታቸው ውስጥ ትልቅ ድርሻ እና ተጠያቂነት እንዳለው ግን ይዘነጋል::
እግዚአብሔርም "እንደ ዋዛ ለተናገራችሁት ቃል በፍርድ ቀን መልስ ትሠጡበታላችሁ" ብሎአልና ለሰዎች የምንሰነዝረው እያንዳንዱ ቃል ያስጠይቀናል::
በተቃራኒው ለሰዎች ጥሩ ቃል መናገርን ብዙ ዋጋ አንሠጠውም:: ለስድብ የማናቅማማ ሰዎች ለምስጋና ሲሆን ግን እንሽኮረመማለን::
ፊት ለፊት አሳምረን የምንሳደብ ሰዎች ለማመስገን ሲሆን "በፊትህ ማመስገን እንዳይሆንብኝ" እንላለን::
ሆኖም ብናወጣው ሰዎች የሚነገራቸው ጥቂት በጎ ቃል ሰብእናቸውን ይገነባል:: ፈጣሪ "ብርሃን ይሁን" ብሎ በቃሉ እንዳበራው ማድረግ ባይቻልህ እንኩዋን በጥቂት በጎ ቃላት የአንድን ሰው ቀን ማብራት ትችላለህ::
ከምንም ሥጦታ በላይ መልካም የምስጋና ቃላት በሰው ልብ የሚቀር ውድ ሥጦታ ነው::
ባል ለሚስቱ ከሚገዛው ሥጦታ በላይ "ባልዋም ያመሰግናታል" የሚለውን ቃል ቢፈጽምላት ደስታ ይሆንላታል:: ልጆች ከብዙ ሥጦታዎች በላይ ከወላጆቻቸው የሚሰሙት የፍቅር ቃል ይሠራቸዋል::
የእስክንድርያው ፊሎ ለልጅ አባትና እናቱ ከሀገሪቱ ንጉሥና ንግሥት በላይ ናቸው ይላል:: የንጉሥ ቃል የሹመት ቃል ነውና ልጆች በወላጆቻቸው የሚሰሙት "ጎሽ" የሚል ቃል ከፍ ያደርጋቸዋል::
"ልጅሽ ትምህርት የማይገባው ደደብ ስለሆነ ትምህርት ቤት አትላኪው" የሚልን ደብዳቤ "ልጅሽ በጣም ጎበዝ ስለሆነ እሱን ማስተማር ስለማንችል በቤት አስተምሪው" ብላ ያነበበች እናት ትልቅ ሳይንቲስት አፍርታለች::
ብርሃን ይሁን ! ምድር ታብቅል! ብሎ የፈጠረን አምላክ በአርኣያው ፈጥሮናልና በቃላችን የምናሳምም ሳይሆን የምንፈውስ እንሁን::
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ "ወንድሙን የሚሰድብ ነፍሰ ገዳይ ነው" ብሎአል:: ስድብ ከመግደል እኩል ነው ሲል ነገሩን ለማግነን የተጠቀመው አገላለጽ ሳይሆን በእርግጥም መሳደብ ከመግደል ብዙም ስለማይለይ ነው:: ሀገራችን ላይ ያንዣበበው የዘር ጭፍጨፋ ብዙዎቻችንን ያሳስበናል:: እንደ ሩዋንዳ ልንሆን ነው? እንላለን:: ወዳጄ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት መነሻው እኮ የሚዲያ የጥላቻ ንግግር ነበር:: እውነት ለመናገር ዘር ነክ ስድቦችና በቀልድ መልክ የሚነገሩ የንቀት ንግግሮች ሁሉ የዘር ማጥፋት ዋዜማ ናቸው:: የጥላቻ ንግግር (hate speech) የዘር ማጥፋት እጅግ ወሳኙ መቆስቆሻ ነው:: ስለዚህ "በለው በለው" ብለህ በምትጽፈው comment ወንድሙን ከገደለው እኩል በፈጣሪ ፊት ትጠየቃለህ:: ቅዱሱ እንዲህ ይላል "እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል" ማቴ 5:22
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 11 2012 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ!
/channel/dnhayilemikael
ቅድስት ቤተክርስቲያን:-
-ጥንቆላን
-ሙስናን
-ዘረኝነትን
አምርራ ትጠላለች። በውስጧ የሚኖሩ አንዳንድ ቄሶች፣ ዲያቆናት፣ መምህራን፣ ጳጳሳት፣ ምእመናን ወዘተ እኒህን ነገሮች ሲያደርጉ ቢገኙ በሕግ አፍራሽነት እንዳደረጉት ማስተዋል ይገባል። በእነርሱ ምክንያት ክርስቶስ ራሷ የሆነላትን ቤተክርስቲያን መሳደብ አላዋቂነት ነው።
የቤተክርስቲያን ልኳ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ ሁልጊዜም ትክክል የሆነውንና የሕይወት አባት እርሱ ጌታን ማሰብና በፍጹም ልቡና መከተል ይገባል
።/channel/Meseretemedia
እኛ ስለምን እንጾማለን?
🛐 ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ::
💠 እኛ ስለምን እንጾማለን?
💠ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን?
👉አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::
🛐 ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን?
💠እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? 💠ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?
💠የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ?
💠የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ?
💠 የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?
💠ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን::
🛐 ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው::
🛐 ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ::
💠 የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣
💠የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣
💠የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣
💠 ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ::
💠 ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ?
🛐የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር?
💠ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ?
💠 ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም?
💠 ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ?
ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው::
💠ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጾመ ነቢያት 2015 ዓ.ም. የተጻፈ
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
እኛ ስለምን እንጾማለን?
🛐 ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ::
💠 እኛ ስለምን እንጾማለን?
💠ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን?
👉አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::
🛐 ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን?
💠እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? 💠ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?
💠የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ?
💠የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ?
💠 የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?
💠ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን::
🛐 ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው::
🛐 ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ::
💠 የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣
💠የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣
💠የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣
💠 ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ::
💠 ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ?
🛐የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር?
💠ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ?
💠 ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም?
💠 ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ?
ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው::
💠ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጾመ ነቢያት 2015 ዓ.ም. የተጻፈ
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
/channel/dnhayilemikael
ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመላው ዓለም ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን የታወጀውን አዋጅ አስተላልፈዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ያለፈውን በይቅርታና በምህረት ዘግተን በእውነተኛ ንሥሓ ልቅሶና በምህላ፣ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንድንቀርብ፣ በመካከላችንም ፍቅርና አንድነት እንዲመጣ ይኽንን ጾመ ነቢያት ወይም የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንድንጾም መንፈሳዊ አዋጅ ተላልፏል፡፡
አፈጻጸሙ
፩ኛ. የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር ፲፭ እስከ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ፣ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን፤
፪ኛ. በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ መነኰሳት፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ፤
፫ኛ. በላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ፣ በፍቅርና በአንድነት፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ፤
፬ኛ. በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር ፲፭ ቀንና፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር ፳፩ ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤
፭ኛ. በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም፣ ስለንሥሓና ጸጸት፣ ስለ ፍቅርና አንድነት፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን፤
፮ኛ. በሰፊህና በአንቀዓድዎ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ፣ ምኅላው ከደረሰና፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ፤
፯ኛ. ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም፤
፰ኛ. አስቀድሞ የደረሰውንና፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም፤
፱ኛ. ይኽንኑ መልእክት መላው ዓለም እንዲውቀው፣ በተለይም የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጸሎት እንዲያስቡን፣ የጸሎታችንና የምኅላችን መነሻ ምክንያቱ የሀገራችን ወቅታዊ ችግር ቢሆንም የምንጸልየው ለመላው ዓለም መሆኑ ተገልጾ በደብዳቤ እንዲላክ እንዲደረግ፣ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን በእንባና በንሥሓ የምናቀርበውን ጸሎተ ምኅላችንን በምህረቱ ተቀብሎ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፣ ሕዝባችንን ይጠብቅልን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ
ኅዳር ፲፩ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም፡
አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ
/channel/dnhayilemikael