#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
🌹🌹🌹🌹🌹ወይን እኮ የላቸውም🌹🌹🌹🌹🌹
የቃና ዘገሊላ ታሪክ ውስጥ አስደናቂ ከኾኑ ክስተቶች ውስጥ አንዱ የወይን ማለቅ ጉዳይ ነው። በእርግጥ ቃና ዘገሊላ ውስጥ የተፈጸመው የሰርግ ጉዳይ ጥልቅ መልእክቶችን የተሸከመ መኾኑ በብዙ የሚብራራ ነው። ታሪኩን በጥልቀት ለመረዳት ግን ወደ ታሪኩ ጥልቀት ውስጥ የምንገባበትን በር ማግኘት አለብን። የዮሐንስን ወንጌል ምሥጢራዊነት ወደ መረዳት ከፍታ እስካልወጣን ድረስ በወንጌሉ ውስጥ የተፈጸሙትን አስደናቂ ክስተቶች በአግባቡ መረዳት አንችልም። ማክሲመስ ተናዛዚው መጽሐፍ ቅዱስን በጥቅሉ በቤተ ክርስቲያን ይመስልና የዮሐንስን ወንጌል ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለችውን ቅድስተ ቅዱሳን ትመስላለች ይላል። ይህ የሚያመለክተው ወንጌሉ የተሸከመውን ጥልቅ ምሥጢር ነው። እንዲያውም ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ ሦስቱን ወንጌላት በሥጋ የዮሐንስን ወንጌል ደግሞ በመንፈስ ይመስላል። የሌሎቹ ወንጌላት እስትንፋሳቸው የዮሐንስ ወንጌል ነውና!!
ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የዮሐንስን ወንጌል ለመረዳት ሊቁ ኦሪገን እንዳለው ወደ ጌታ ደረት ጋር ጠጋ ብሎ እንደ ዮሐንስ ከጌታ እመቤታችንን መቀበልን ይጠይቃል። ይህ ኹሉ የሚያመለክተው በወንጌሉ ላይ የተጻፉ ክስተቶችን በችኩልነትና በለብ ለብ ስሜት አልፈን እንዳንሄድና በጥልቀት እንድንመረምር ነው። ሰርግ የተፈጸመባት የገሊላዋ ቃና ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያምን በመያዟ ከሚመጣባት ጉድለት ስትድን እንመለከታለን። ከክርስቶስ ጋር ለምናደርገው ግንኙነት የእመቤታችን ልመና እጅግ አስፈላጊ ነው። እርሷ ቀድማን ጉድለታችንን ባታሰማልን ኖሮ መሽራው ክርስቶስ እንዴት ይቀበለን ነበር!!
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከቤተ አይሁድ ወገን ስለ ኾነች የአይሁድን ጉድለት በእጅጉ ታውቀዋለች፤ ስለዚህ የሚጠቅማቸውን ወይን ይሰጣቸው ዘንድ ትለምናለች። በመጽሐፍ እንዲህ ተብሏል “እናንተ ሰካራሞች ንቁ ለመስከርም ወይን የምትጠጡ እናንተ ሁላችሁ! ተድላና ደስታ ከአፋችሁ ጠፍተዋልና አልቅሱ፤ እዘኑም።" ኢዩ 1፥5። በመኾኑም አይሁድ የድኅነትን ደስታ በማጣት በኀዘን ውስጥ ናቸው፤ ይህ ነውና የወይን ማጣት!! ወይን እኮ የላቸውም የድኅነት ደስታ ከደጃቸው ጠፍታለችና ስጣቸው ማለቷ ነበር። በተራው ምድራዊ ወይን ሰክረው የድኅነትን ወይን በማጣት ጨለማ ውስጥ ገብተው ነበርና ጉድለታቸውን የምታውቅ ፈጣኗ እናት ለመነችላቸው።
ወይን እኮ የላቸውም ርቱዕ እምነት የላቸውም። አኹንም በኦሪታቸው ውስጥ የምትታየውን አንተን ወደ ማወቅ አልመጡምና አይኖቻቸውን ከፍተህ ብርሃነ ወንጌልህን ግለጥላቸው። በጨለማ ውስጥ ያለን ነገር ለማየት የግድ ብርሃን እንዲያስፈልግ በእምነት ጨለማ ውስጥ ያሉትን ወይን ርቱዕ እምነትን ሰጥተህ አድናቸው ማለቷ ነው። ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ተናገረው በሐዲስ ኪዳኗ ትክክለኛዋ እምነት በኩል ከእግዚአብሔር ጋር እስካልተገናኘን ድረስ በእርግጥም ወይን እኮ የለንም!!
እመቤታችን ወይን እኮ የላቸውም ማለቷ ሰዎች ከፈሪሓ እግዚአብሔር በመራቃቸው ምክንያት የደረሱበትን መልከ ጥፉነት ለማመልከትና ከዚያ እንድንፈወስ ለማስደረግ ነው። መዝ 127 “ብፁዐን ኩሎሙ እለ ይፈርሕዎ ለእግዚአብሔር ወለ እለ የሐውሩ በፍናዊሁ። ፍሬ ጻማከ ተሴሰይ፣ ብፁዕ አንተ ወሠናይ ለከ፤ ብእሲትከ ከመ ወይን ሥሙር ውስተ ጽርዓ ቤትከ - እግዚአብሔርን የሚፈሩ ኹሉ የተመሰገኑ ናቸው፣ የድካምህን ዋጋ ትበላለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይኾንልሀል፤ ምስትህም በቤትህ ውስጥ እንደ ወይን የተወደደች ናት።" በማለት በብዙ አንቀጽ ጀምሮ በአንድ አንቀጽ ወደ ማውራት ይመጣል። ይህ የሚያመለክተው የክርስቶስንና የእርሱ የኾነችውን ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት ነው። በቤትህ እንደ ወይን የተወደደች ናት በማለት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ውበት ያነሣል። ስለዚህ በፈሪሓ እግዚአብሔር ውስጥ የሚኖሩ የቤተ ክርስቲያን አካሎች የምግባር ውበታቸውን ሳያጡት እንደሚኖሩ፤ ወይን እኮ የላቸውም የተባሉት በዚህ ዓለም ፍልስፍናና ፍቅር የነጎዱትን ነው። የጠፉትን ወደ በረቱ ለመሰብሰብ የተደረገ የፍቅር ጥሪ ነው!!
ወይን እኮ የላቸውም። ፍቅረ ቢጽ ወፍቅረ እግዚአብሔር የላቸውም። የራሳቸውን ስሜት በመውደድ የሠለጠኑ ናቸውና ወይን ፍቅር የላቸውም!! ወይን ጣዕሟ እንደሚያረካ ነፍሳቸው የምትረካባቸው ቃለ እግዚአብሔር የላቸውም!! ቃልህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው ተብሏል እነርሱ ግን ይህ በአንተ ቃል የመመራት ሐሳብ የላቸውምና በቃልህ የመመራት ኃይልን ሙላባቸው!! እንግዳ ክፉ ፈቃድ ተነሥቶባቸዋልና ይህን ድል የሚያደርጉበትን ወይን ትዕግሥትን ስጣቸው። መናፍቃን ለሚያቀርቡባቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተው ሰውነታቸውን በእውነት መሠረት ላይ ይገነቡት ዘንድ ወይን ማስተዋል የላቸውምና ማስተዋሉን አድላቸው!!
ወይን ሕገ ወንጌል ናት። በሕገ ወንጌል ወይን ውስጥ ገብተው ይኖሩ ዘንድ ወይን የወንጌል ምሥጢራትን የሚረዱበት ሀብተ ትርጓሜ የላቸውም። በወንጌል ውስጥ የተዘገበው ሰላም ቀድሞ ባለበሳቸው ጥላቻ ምክንያት አልተገኘላቸውምና “ወይን እኮ የላቸውም" ። የሕይወት ወይን አንተን ራስህን በማጣት ሕማም ውስጥ ገብተው ቆስለዋልና አምላክነትህን ገልጠህ አሳያቸው። በሕይወት ውጣ ወረድ ውስጥ የሚገጥማቸውን መከራ በጽናት ይቀበሉ ዘንድ ወይን እኮ የላቸውም። በእርግጥ የእመቤታችን ድምጿ በልጇ ዘንድ ይሰማል። የእኛ ጉድለትም ስለ እርሷ ሲባል ይሟላል። ብቻ እናችን ቅድስት ኾይ ከመዝሙር ይልቅ ዘፈን ደስ የሚያሰኘንን እኛን ወይን እኮ የላቸውም በይልን!! ጌታ ሆይ ወይን ደምህን ጠጥተን ምሬተ ኃጢአታችንን ታስወግድ ዘንድ ስለ እናትህ ብለህ ወይንህን ስጠን!! አሜን።
#ከዲያቆን_ዮሐንስ_ጌታቸው
/channel/dnhayilemikael
#ጥር_10
#ጾመ_ገሃድ
ጥር አስር በዚህች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።
እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።
በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።
በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።
የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህም ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።
መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረቡዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው።
ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
/channel/dnhayilemikael
#በጥምቀት_ዙሪያ_የሚነሱ_ጥያቄዎች_እና_መልሶቻቸው
#ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ?
1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/
2. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
በመዝሙር 46/47/፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡
3. አርአያ ሊሆነን፡-
ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ 11፥29/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. 13፥1-17/
4. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ
ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14
#ጌታችን_መች_ተጠመቀ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. 3፥23/
#ጌታችን_ስለምን_በ30_ዓመት_ተጠመቀ?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ. 3፥6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡
ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡
ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ‹‹ይህ ልጄ ነው›› ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ /ማቴ. 3፥16/
#ጌታችን_በዮሐንስ_እጅ_ለምን_ተጠመቀ?
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን ‹‹መጥተህ አጥምቀኝ ›› ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ›› ሲል ነው፡፡
ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ጌታችንን_በማን_ስም_አጠመቀው?
ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ "ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?" ብሎ ቢጠይቀው ጌታም ‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡
#ዮሐንስ_ጌታን_ሲያጠምቀው_እጁን_ለምን_አልጫነበትም?
- ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል፡፡
- መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል
#ጌታችን_ጥምቀቱን_ለምን_በዮርዳኖስ_አደረገው?
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ.113፥3/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቈላ. 2፥14/
#ጌታችን_ለምን_በውሃ_ተጠመቀ?
እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)
አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡
አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡
አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡
አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡
አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)
ልዩ የመንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ዝግጅት
በሀ/ማ/ደ/ገ/ቅ/ማ/ቤ/ክ በቀን 5/5/2016 ከቀኑ 10 ሰዓት
በታቦት ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች በሊቃውንተ ቤተ መልስክርስቲያን መልስ ስለሚሰጥበት ሁላችሁም ምዕመናን ተጋብዛችኋል
አዘጋጅ መሠረተ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት
ቦታ= ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን :ዓውደ ምህረት
#ጥር_1_ቅዱስ_እስጢፋኖስ_የተወለደበት_እና_የሰማዕትነት_አክሊል_የተቀበለበት_ዕለት_ነው ።
#እስጢፋኖስ፦የስሙ ትርጉም በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡
አባቱ ስምኦን፣ እናቱ ሃና ይባላሉ፡፡ የተወለደው - ጥር 1 ቀን በእስራኤል ሃገር ውስጥ በብፅዓት / በስለት/ ነው፡፡ ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለ ቦት ተወለደ ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡
በደሙ የመሠረታት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በጽርሐ-ጽዮን ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከተቀበለች በኋላ የትንሣኤውን ወንጌል ለትውልድ ማድረስ ጀመረች፡፡ ወንጌል እየተስፋፋ አማኞች እየበዙ መጡ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት የሚያግዟቸው ሰባት ጠቢባን ወጣቶችን መርጠው የዲቁና ሥልጣን ሰጡአቸው፡፡
ከተሾሙት ዲያቆናት መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ነው፡፡ ሐዋ. 6÷5. ቅዱስ እስጢፋኖስ ጥቅምት 17 ቀን የዲያቆናት አለቃ ሆኖ ሊቀ ዲያቆናት ተብሏል፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ ከግሪክ አገር የመጡ አይሁድ በተከራከሩት ጊዜ በመንፈስና በጥበብ መለሰላቸው፡፡ አይሁድም ዳኞች በተሰየሙበት ሸንጎ ፊት አቅርበው በሐሰት ከሰሱት፤ ሸንጎውም በድንጋይ እንዲወገር ፈረደበት፡፡ እስጢፋኖስ ግን በታላቅ ኃይልና በብዙ መረዳት ከአባቶቻቸው ታሪክ ተነሥቶ የዓለም መድኃኒት የሆነውን ክርስቶስን ሰበከላቸው፡፡ ጥላውን ከአካሉ ጋር እያጋጠመ ወደ ፍጹማን ጥበብ በጽድቅ ቃል መራቸው፡፡ አይሁድ በጣም ተቆጡ፤ ሁሉም በአንድነት ሆነው በድንጋይ ወገሩት፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰውነቱ ቆስሎና ዝሎ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ባነሣ ጊዜ የልዑልን ክብር ተመለከተ፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቱ ቀኝ ቆሞ አየ፡፡ ሐዋ. 7÷55፡፡
ቅዱስ አሰስጢፋኖስ “እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) በአባቱ ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አላቸው፡፡ አይሁድ ግን ልበ-ደንዳኖች (የማይራራ ጨካኝ ልብ ያላቸው) ስለሆኑ እስጢፋኖስን ከከተማ ወደ ውጭ አውጥተው ደበደቡት፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰውነቱ ደከመ፤ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በደረሰች ጊዜ በሞት ጣር ሆኖ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው፤ ነፍሴን ተቀበል” ብሎ ጸለየ፡፡ ነፍሱንም ለታመነው ፈጣሪ አደራ ሰጥቶ ጥር 1 ቀን በ34 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
የሰማዕትነት ሕይወትን በመጀመሩ ስለ ክርስቶስ ፍቅር መራራ ሞትን በመታገሡ ቀዳሜ ሰማዕት ተብሏል፤ የቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ሰማዕት ነውና፡፡
ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን አሜን !!!
@dnhayilemikael
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለኢየሱስ ክርስቶስ
እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
በቤተልሔም የተወለደው ጌታ ዛሬ ልባችን እንደ ቤተልሔም ጌታን ለመቀበል ከኃጢአት ከክፋት ተለይቶ በንስሐ ተዘጋጅቶ በቤተልሔም ሰውና መላእክት በአንድነት እንደ ዘመሩ በእኛ መመለስ ቅዱሳን ሰዎችና መላእክት ይደሰቱ ዘንድ በቤተልሔም የተወለደ ጌታ የበቃን ያድርገን
መልካም በዓል ይሁንላችሁ
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
አርበኛና ካህን ሞትን የማይፈራ፣ ለሆዱ ሳይሆን ሁልጊዜም ለእውነት የሚኖር መሆን ይገባዋል። በዚህ ምድር የምንኖረው ለአጭር ጊዜ ነው። ስለዚህ ለዚህች አጭር ሕይወት ብሎ ዘለዓለማዊውን ሕይወት የሚያሳጣ ድርጊት ማድረግ አይገባም። መፍራት ያለብን እግዚአብሔርን ብቻ ነው። አድርባይነት፣ ዘረኝነት፣ የሥልጣን ጥማት፣ ግላዊ ክብርና የመሳሰሉ ጉዳዮች ፍጻሜያቸው ውርደት ነው። እውነትን ይዘን ውሸትን እስከሞት ድረስ መታገል ያጸድቃል እንጂ አያስወግዝም። እውነትን ይዘው ለሚታገሉ ጀግኖች እግዚአብሔር እድሜንና ጤናን ይስጥልን።
ከእውነተኞች ጋር እውነት የሆነው መድኃኔ ዓለም ሁልጊዜም ከእነርሱ ጋር አለ። ከሐሰተኞች ጋር ደግሞ የውሸት አባት ዲያብሎስ ከዚያ አለ። ሰይጣን ቢረዳህ እስኪያዋርድህ ድረስ ብቻ ነው። የእግዚአብሔር እርዳታ ግን ዘለዓለማዊ ሕይወትን እስከማግኘት ያደርሳል።
የሚዲያ ጋጋታ መሬት ላይ ያለውን እውነታ አይቀይረውም። ነጩን ጥቁር ቢሉት ነጭነቱን አይቀይረውም። ጥቁሩን ነጭ ቢሉትም ጥቁርነቱን አይለውጠውም።
መ/ር በትረ ማርያም
ለሥጋም ለነፍስም የማይጠቅም መልካም ሐሳብ የለም። እንዲሁ በሥጋም በነፍስም ጉዳትን የማያመጣ ክፉ ሐሳብም የለም። ሐሳብ ሲቀደስ ንግግርና ተግባርም ይቀደሳሉ። ሐሳብ ሲረክስ ደግሞ ንግግርና ተግባርም ይረክሳሉ። ሰው ልዑል ኅሊና ሲኖረው በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል። ትምክህቱም፣ ደስታውም እግዚአብሔር ይሆናል።
በሥጋዊ ጥቅም የማይታለል፣ ሥጋዊ መከራን የማይሰቀቅ፣ ለእውነት ያደላ ንጹሕና ልዑል ኅሊና ሊኖረን ይገባል።
(መምህር በትረ ማርያም አበባው)
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
+++የማይተወን እረኛችን! ኖላዊ ዘበአማን!+++
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ‹‹እረኞች ያመሰገኑት በግ እና እረኛ›› ብሎ ክርስቶስን ይጠራዋል (Select Orations of Saint Gregory Nazianzen, Nicene and Post Nicene Fathers Series II, Volume 7, 1893; Page 436) ፤ እርሱ ስለ እኛ ስለበጎቹ መዳን የሚሰዋ በግ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ፤ በሌላ በኩል ስለ በጎቹ ነፍሱን የሠጠ ቸር እረኛም ነው ፤ በወንጌል ‹‹ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል” ካለ በኋላ “እንደ ገና አስነሣት ዘንድ እኔ ነፍሴን እሰጣለሁና” (ዮሐ. 10፡17) ይላል፡፡ “እርሱ ሞቶ በጎቹን የሚያድን ከሞት የሚያስነሣ እንዲህ ያለ እረኛ ከወዴት ይገኛል? የበጎቹን ሕመም ሕመሙ አድርጎ መድኃኒቱን ቀምሶ የሚያቀምስ እረኛ እንደምን ያለ እረኛ ነው?”
+++
አቤቱ መልካሙ እረኛዬ ሆይ! እኔ ለዐይኖቼ የቀረበውን ለጊዜው የታየኝን አረንጓዴውን ለምለም መስክ እያየሁ ከፊት ያለው ገደል ተዘንግቶኛል ፤ ጤና ፤ ትዳር ፤ ልጅ ፤ ገንዘብ ፤ ጊዜያዊ የሕሊና ዕረፍት ፤ እንዲሁም ምኞትና መሻቴን የማገኝበትን የትኛውንም ፈጣንና አቋራጭ መንገድ ስለመጠቀም እንጂ ፤ ከበስተኋላው ያለውን ጥፋት አስቀድሞ ማስተዋል ተስኖኛል ፤ ቸሩ እረኛዬን አንተን መከተል ከተውኹኝ ሰነባበትኹኝ፡፡
የጨበጥኹትና ያገኘሁ የመሰለኝ ነገር ፤ አንተንና ቅዱሱ በረትህን አስረስቶኛል ፤ ጌታ ሆይ የአንተ እረኝነት ልክ እንደ ትላንቱ ዛሬም አልተለወጠም በትዕግሥት ለሚጠብቁህ ፤ ቃልህን ጠብቀህ እንደምትሠጣቸው እንደምታድናቸው ፤ ከሚያስጨንቃቸውም እንደምታሳርፋቸው ፤ ሕይወትህን ስለ በጎችህ የምትሠጥ ቸር እረኛ መሆንህን አውቃለሁ፡፡
የማውቀውን መኖር በሕይወት መተርጎም ግን እጅጉን ከብዶኛል ፤ እኔ ደካማ በግህ የጊዜ ሠሪና ፈጣሪ አንተ መሆንህ ከልቡናዬ እየተሰወረብኝ ፤ አንተን በመጠበቅ ከነገሮች የዘገየሁ ይመስለኛልና ማስተዋልን አድለኝ!!! በማይጠቅም ሀሳብ የሞተው ልቤን ፤ በቅዱስ ቃልህ ትንሣኤውን አውጅለት ፤ በልቤ የመላውን አንደበቴ እንዲህ እያለ ይመስክር “እርሱ ሞቶ በጎቹን የሚያድን ከሞት የሚያስነሣ እንዲህ ያለ እረኛ ከወዴት ይገኛል? የበጎቹን ሕመም ሕመሙ አድርጎ መድኃኒቱን ቀምሶ የሚያቀምስ እረኛ እንደምን ያለ እረኛ ነው?”
+++
Image Credit: monasteryicons (Pinterest)
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ታኅሣሥ 20 2016 ዓ.ም ምሽት
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
"አሁን እየጾምክ ነው?
እስቲ ጾምህን በተግባር አሳየኝ?
የቱን ሰራህ?
💠 ድሃውን ባየህ ጊዜ ምህረትን አሳየው።
💠 ጠላትህን ስታየው ታረቀው።
💠 ስኬታማ የሆነ ወንድምህን ስታየው አትቅናበት በመንገድ የምትሔድ ሴትን ስታይ ዝም በለህ እለፋት።
🛐በአጠቃላይ አፍህ ብቻ አይጹም ነገር 👉ግን ዓይንህ፣
👉 እግርህ፣
👉እጅህ ሁሉም አካልህ ይጹም።
💠 እጅህ ከመስረቅና ከስስት ይጹም፣ 💠እግሮችህ ወደ ኃጢአት ከመጓዝ ይከልከሉ፣
💠 አይኖችህም በሌሎች ሰዎች ውበት ላይ ተተክለው ከመዋል ይጹሙ።
❤💠አሁን ስጋ እየበላህ አይደለም አይደል?
👉በዓይንህም መጥፎ ነገር አትመልከት፤ 👉መስማትንም ጹም።
💠የፈውስ ጾም ክፉን አለመስማት የሌሎችንም ስም አለማጥፋት ነው።
💠 አንደበትም ከክፉና ከአጸያፊ ንግግር ይጹም።
🛐 የዶሮና የአሳ ስጋ ከመብላት እንከለከላለን ነገር ግን የወንድማችንን ስጋ ስናኝክና ስንበላ እንውላለን።
💠የወንድሙን ስጋ የሚበላ ደግሞ የተረገመና አሳች ነው።👉 ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ” እንዳለን። ገላ.5:15
💠ሆዳችንን ከምግብ ብቻ ባዶ ማድረግ አይደለም። ነገር ግን ሁለንተና ሕይወታችንን ራሳችንንም የምንቆጣጠር እኛ ወደ መንፈሳዊ ነገሮች የምንመራ መሆን አለብን።"
የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን ውርስ ትርጉም #መምህር_ንዋይ_ካሳሁን
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
ወደ እስራኤል ለሥራ ወይም ለትምህርት መሄድ ይፈልጋሉ⁉️
👇👇
@Hebrewethio
@Hebrewethio
የቃናውን ወይን የቃና ሰርገኞች ጠጥተው ጨርሰውታል። ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳይተላለፍ በታሪክ ብቻ እንማረዋለን። የቀራንዮውን ወይን ግን እስከ ዕለተ ምጽአት ምእመናን ንሥሓ እየገቡ ይጠጡታል። እርሱም ንጽሐ ሥጋን ንጽሐ ነፍስን ያጎናጽፋቸዋል። ለምእመና ልዩ ቀን (ዕለት ኅሪት) ንሥሓ ገብተው ከዘለዓለማዊው ወይን የሚጠጡበት ቀን ናት።
#ዕለት #ኅሪት #ዕለተ #መድኃኒት
እስራኤላውያን ከግብፅ የወጡባት ቀን ዕለት ኅሪት ትባላለች። ባሕረ ኤርትራን የተሻጉረባት ቀን ደግሞ ዕለተ መድኃኒት ትባላለች። ጌታ የተፀነሰባት ዕለት ዕለት ኅሪት ትባላለች። የተወለደባት ቀን ደግሞ ዕለተ መድኃኒት ትባላለች። አንድም የተወለደባት ቀን ዕለት ኅሪት ትባላለች። የተሰቀለባት ቀን ዕለተ መድኃኒት ትባላለች። አንድም የተሰቀለባት ቀን ዕለት ኅሪት ትባላለች። ከሙታን የተነሣባት ቀን ዕለተ መድኃኒት ተብላበች። ሰው ንሥሓ የሚገባባት ቀን ዕለት ኅሪት ትባላለች። ሥጋውን ደሙን የሚቀበልባት ቀን ደግሞ ዕለተ መድኃኒት ትባላለች። ዕለት ኅሪት፣ ዕለተ መድኃኒት በንባብ እንጂ በምሥጢር አንድ ናቸው።
ጌታ ጥር ፲፩ በውሃ ተጠመቀ። በዕለተ ዐርብ ከጎኑ በፈሰሰው ንጹሕ ውሃ (ማየ ገቦ) ደግሞ እኛ እንድንጠመቅ አደረገን። ጌታ በቃና ዘገሊላ ውሃውን ወደ ወይን ለውጦ ሠርገኞችን አስደሰታቸው። ወይን ያስተፌሥሕ ልበ ሰብእ ማለትኮ ይህ ነው። ወይን ደመ ክርስቶስ ምእመናንን ያስደስታል። በዕለተ ዓርብ ደሙን አፍስሶ አነጻን። ወይን ክርስቶስ እስከ ዕለተ ምጽአት ለሚነሡ ምእመናን መድኃኒት የሚሆን መጠጥን ሰጠን።
ስለ ቃና ወይን ስንናገር ንሥሓ ገብተን ዋናውን ወይን ደመ ክርስቶስን መቀበል ይገባናል።
/channel/dnhayilemikael
ጌታ በሌሊት ለምን ተጠመቀ ?
ይቀጥላል ......
ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
╭╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
እንኳን ለወንጌላዊ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ሰላም ለከ ዮሐንስ ታኦሎጎስ
ሰላም ለከ ዮሐንስ አቡ ቀለምሲስ
ሰላም ለከ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
ሰላም ለከ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚዕ
ሰላም ለከ ዮሐንስ ነባቤ መለኮት
ሰላም ለከ ዮሐንስ ወንጌላዊ
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
ክርስቲያን መሆንህን በቃል ሳይሆን በተግባር አሳየኝ !
ክርስቲያኖች ግን ክርስቲያኖች ለመሆናቸው መታወቅ የሚገባቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተው ምሥጢራትን ሲቀበሉ ብቻ ሳይሆን የትም ቦታ በሚኖሩት የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ በአፍአ የከበሩ ሰዎች በአፍአ ከሚያሳዩት ምልክት እንደሚታወቁ ኹሉ፥ እኛም ልንታወቅ የሚገባን በነፍሳችን ክብር ነው፡፡ በሌላ አገላለጥ አንድ ክርስቲያን መታወቅ ያለበት በተሰጠው ልጅነት ብቻ ሳይሆን ለልጅነቱ እንደሚገባ በሚያሳየው አዲስ ሕይወትም ጭምር ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ክርስቲያን ለዓለም ብርሃንና ጨው ሊኾን ይገባዋል፡፡ ለዓለም ብርሃን መሆንህስ ይቅርና ለራስህ እንኳን ብርሃን መኾን ካልተቻለህ፣ የሚሰፋ ቁስልህን በዘይት ማሰርም ካቃተህ፥ ክርስቲያን መሆንህን የምናውቀው እንዴት ነው? ወደ ተቀደሰው ውኃ ገብተህ በመጠመቅህ ነውን? በዚህስ አይደለም ! ይህስ እንዲያውም ዕዳ ፍዳ ይሆንብሃል [እንጂ ክርስቲያን መሆንህን እንድናውቅህ አያደርገንም]፡፡ ይህ ሀብት (ልጅነት) ታላቅ ነውና ለዚህ ሀብት እንደሚገባ ለማይኖሩት ሰዎች ዕዳ ፍዳ መጨመሪያ ነው፡፡ አዎን፥ ክርስቲያን ለዓለም ብርሃኑን ማብራት ያለበት ከእግዚአብሔር በተቀበለው ጸጋ ብቻ ሳይሆን እርሱ ራሱም ድርሻውን በመወጣት ነውና፡፡ ክርስቲያን ካልሆኑት ይልቅ በኹለንተናው - በአረማመዱ፣ በአተያዩ፣ በአለባበሱ፣ በአነጋገሩ - ብልጫ ሲኖረው ነውና፡፡ ይህንም የምለው ልጅነትን የተቀበሉ ክርስቲያኖች ልጅነትን ተቀበሉ በመባል ብቻ ሳይሆን የሌሎች ሰዎች ረብ ጥቅም ይሆን ዘንድ ለተቀበሉት ልጅነት የሚገባና ሥርዓት ያለው ሕይወት እንዲኖሩ ስለምሻ ነው፡፡
#ይቀጥላል...
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
የጌታችንና የመዲሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አከባበር በላሊበላ
ይሄን ይመስል ነበር
‹‹ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ኾኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚኾን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፡፡ ይህን ወዷልና፤››
(ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ፷፮፥፲፯)፡፡
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ።
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
ዋዛ ፈዛዛ ነገር ማውራት
"... ልጆቼ! የሚያሳፍር ነገር፣ የስንፍና ንግግር ወይም ዋዛ ፈዛዛ የማይገቡ ናቸውና በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ ከቶ አይሰሙ፡፡ እስኪ ንገሩኝ! የዋዛ ፈዛዛ ንግግር ጥቅሙ ምንድን ነው? እስኪ ንገሩኝ፤ አንድ ጫማ ሰፊ፣ ጫማ እየሰፋ በአንድ ጊዜ ሌላ ሥራ መሥራት ይችላልን? አይችልም፡፡ ከዋዛ ፈዛዛ የሚያሳፍር ንግግር ይወለዳል፡፡ የአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለእኛ ለክርስቲያኖች ዋዛ ፈዛዛ የምንናገርበት ሳይኾን የንስሐችን ጊዜ ነው፡፡ እስኪ አሁንም ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! አንድ ቦክስ የሚጫወት ሰው ውድድሩን ችላ ብሎ ዋዛ ፈዛዛን ይናገራልን? እንዲህ የሚያደርግ ከኾነስ በተጋጣሚው በቀላሉ የሚሸነፍ አይደለምን? ታዲያ ባለጋራችን ዲያብሎስ‘ኮ የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙርያችን ቁሟል፡፡ ጥርሱን እያንቀጫቀጨብን ነው፡፡ እኛን የሚጥልበት ወጥመድ በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ የደኅንነታችን መንገድ ላይ እሳት እየተነፈሰ ነው፡፡ ታዲያ ዲያብሎስ እንዲህ እኛን ለመጣል ሲተጋ እኛ ዋዛ ፈዛዛን፣ የሚያሳፍር ነገርን፣ የስንፍናንም ንግግር ስንናገር ቁጭ ልንል ይገባናልን?
የምወዳችሁ ልጆቼ! ጊዜው የምንተኛበት ጊዜ አይደለም፡፡ የተጋድሎ ጊዜ ነው እንጂ፡፡ ቅዱሳን ጊዜያቸውን እንደ ምን እንደሚያሳልፉት ማወቅ ትፈልጋላችሁን? እስኪ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን አብረን እንስማው፤ እንዲህ ያለውን፡- “ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ”፤ … “በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችኋለሁ…”፡፡ … “የሚደክም ማን ነው፤ እኔ አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፤ እኔም አልናደድምን?”፤ “… በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን”፡፡ ታዲያ እነ ቅዱስ ጳውሎስ ጊዜያቸውን እንዲህ ካሳለፉ፣ ኃጥአን የምንኾን እኛ ጊዜያችንን በሳቅና ስላቅ ልናጠፋ ይገባናልን? በክርስቶስ ፍቅር የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በንግግሬ አትማረሩ፡፡
ጊዜው የተጋድሎ ጊዜ ነው፤ ታዲያ ስለ ምንድን ነው የዘፋኞችን መሣርያ አንሥተን ከዓለም ጋር የምንዘፍነው? በጦር ግንባር ያለ ወታደር ከጠላት ሊመጣ የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል ከመዘጋጀት ይልቅ ጊዜውን በዋዛ ፈዛዛ ያጠፋልን? አያጠፋም፡፡ ታዲያ እኛም‘ኮ የክርስቶስ በጎ ወታደሮች ነን፡፡ ..."
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
በሁሉም ነገሮች ውስጥ ራሱን የሚወቅስ ሰው ብሩክ ነው እርሱ ስለዘለዓለማዊነቱ ትኩረት ይሰጣል ጂ በሰዎች ላይ ስላለ እፍረት ትኩረት አይሰጥም።
ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ፫
/channel/dnhayilemikael
#ሥጋዊ_አሳቤ
#አንብቡት_እስቲ_እራሳችን_እንፈትሽበት
🥀እንደ ሰላይ ወዳጅ መስሎ አቅሜን ይለካኛል ። አብሮኝ እየተጋበዘ መድከሜን ለጠላቴ ሰይጣን ያሳብቅብኛል ። የውጭውን ጠላት ስታገል በውስጤ ሥጋዊ አሳቤ ያደባብኛል ። ስቆጣ ሎሌ ፣ ስበርድ ጌታ እየሆነ ይመጣብኛል ። ክረምት ከበጋ ይተጋብኛል ፣ እኔ ተኝቼ ሥጋዊ አሳቤ ከተማ ያስሳል ። ለማመስገን ስነሣ ጉድለቴን ይቆጥርብኛል ። ለመንፈሳዊ ነገር ስታጠቅ በከንቱ ነገሮች ጊዜዬን ይበላል ። ሥጋዊ አሳቤ እንደ ክፉ ጎረቤት ይነዘንዘኛል ። አብረን ማርጀታችን ፣ ስንጣላ ስንታረቅ ዘመን ማሳለፋችን ይደንቀኛል ። ሥጋዊ አሳቤ አካሌ ደክሞ ሳለ ነፍሴን አባብሎ ይወስድብኛል ። ልብ አይሞትምና ነፍሴ ማድረግ ቢያቅታት በአሳብ ስትዘምት ትውላለች ። ነፍሴ በተመስጦ ወደ ሰማይ ስትሄድ ሥጋዬን ይሻረክብኛል ። ሥጋዬ አገሯ መሬት ነውና ከመሬት ስበት ጋር ወደ ታች ትጎትተኛለች ።
🥀በሁለት አሳብ በደግነትና በክፋት ስንገላታ ሥጋዊ አሳቤ ብዙ መረጃዎችን እየጠቀሰ ክፋት ያስከብርሃል ይለኛል ። ነፍሴም መረጃ ከእምነት አይበልጥም ትለኛለች ። አስታራቂ መስሎ ሥራውን የሚሠራ ፣ ለደግነት ትቶ ለክፋት የሚያደላ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ይሞግተኛል ። መቅዘፊያዋን እንደ ጣለች ጀልባ አቅጣጫ እያሳተ ፣ የአሳብ ሰይፍ ፣ የበቀል ስለት እያስጨበጠ ሥጋዊ አሳቤ በቂም ያዘምተኛል ። ከክርስቶስ መከራ ያንተ ይበልጣል እያለ ያስታብየኛል ። ሥጋዊ አሳቤ ገላጋይ መስሎ የሚያስደበድበኝ ፣ ጠበቃ መስሎ የሚያስረታኝ ፣ ወዳጅ መስሎ ወደ ገደል የሚገፈትረኝ እርሱ ነው ። በዝማሬ ውዬ በልቅሶ እንዳድር ፣ በፍቅር ውዬ በቂም እንድሰክር የሚያደርገኝ ፣ አንዱን ቀን ሁለት የሚያደርግብኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ።
🥀እንደ ማጥ ጉዞ ወጣሁ ስል የሚይዘኝ ፣ ጨረስሁ ስል የሚያስጀምረኝ ፣ ሸመገልሁ ስል ልጅ የሚያደርገኝ ፣ ታጠብሁ ስል መልሶ የሚያቆሽሸኝ ፣ ተፋሁ ስል እንደ ውሻ የሚያስልሰኝ ሥጋዊ አሳቤ በክለሳ ኑሮ የሚያደክመኝ እርሱ ነው ። በእምነት ሰላሜን አገኘሁ ስል በአዳዲስ ጉድ የሚያናውጠኝ ፣ እጆቼን ፣ ዓይኖቼን ፣ ጆሮዎቼን እየኮረኮረ ክፉ ወሬ የሚያስቃኘኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። አዳም ሲወድቅ ውስጤ የገባው ረቂቅ መንግሥት ሥጋዊ አሳቤ ነው ። ሳላውቀው ከእኔ ጋር የኖረው ፣ ተገላገልሁት ለማለት የማልደፍረው ጠላቴ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። አገሬ በሰማይ ነው ስል ጎሣ የሚያስቆጥረኝ ፣ ተበደልሁ እንጂ በደልሁ የማያሰኘኝ ፣ መንግሥተ ሰማያት ላያስገባኝ ትክክል ነህ እያለ የሚያጸድቀኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። አገልግሎት ሕይወትህ ነው እያለ ከሰው የሚያጋድለኝ ፣ ሕይወት ክርስቶስ መሆኑን በዘዴ የሚያስጥለኝ ፤ ከመድረክ አትጉደል እያለኝ ከጽሞና የሚያጎድለኝ ፣ በዘዴ የጠለፈኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ።
🥀ኃጢአትን ጽድቅ ለማድረግ ሱባዔ የሚያስገባኝ ፣ ሃይማኖቴን ለመለወጥ የሚያጸልየኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። እንደ አቡን ሥልጣነ ክህነት የሚሰጠኝ ፣ ሳልሾም የተሾሙትን የሚያስንቀኝ ፣ የሕልም ዓለም የሚያወርሰኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነውና በቁም የሚያቃዠኝ ። ሚስቴን አመንዝራ ፣ ወዳጄን ጉድጓድ ማሽ አድርጎ የሚስልብኝ አእምሮዬን የሚያቆሽሸው ፣ ባልተጨበጠ ነገር የተጨበጠ ጦርነት የሚሰጠኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ።በስግብግብነት ከተማውን ካልገዛህ የሚለኝ ፣ አልጠግብ ብዬ ስተፋ የሚያሳድረኝ ፣ የኪስ ጣዖት የሆነውን ገንዘብ የሚያሳየኝ እርሱ ሥጋዊ አሳቤ ነው ። በአሥራት ታማኝ አድርጎ ለድሀ የሚያስጨክነኝ ፣ ሬሳ እየተራመድሁ እንዳልፍ የሚያደርገኝ እርሱ ነው ፤ ሌላ ጊዜም ለድሀ ቸር አድርጎኝ የእግዚአብሔር ሥራ እንዲበደል አሥራቴን የሚያሰርቀኝ ሥጋዊ አሳቤ ነው ፣ ጎዶሎ ጽድቅ ውስጥ የሚያስዋኘኝ ። ከሥጋው ጦመኛ ነኝ ፣ ከመረቁ አውጡልኝ የሚያሰኘኝ ፣ ከወገብ በላይ ታቦት ፣ ከወገብ በታች ጣዖት የሚያደርገኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው በሁለት ማንነት የሚያኖረኝ ።
🥀ካድሁ እንዳልል በሃይማኖታዊ ፉከራ እየጠመደኝ ፣ ቀጥሎ ሁሉን የሚያስረሳኝ ፣ በስሜት እሳት የሚያሟሙቀኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው እኔን ለእኔ ያስጠፋኝ ። እያደባ የሚይዘኝ አውሬ ፣ እንደ እባብ ለመንደፍ የሚለሰልሰኝ ጠላቴ እርሱ ሥጋዊ አሳቤ ነው ። ሁሉም ሰው ኀጥእ ነው ብሎ ኃጢአት አሠርቶኝ ፣ ቀጥሎ አንተማ ከእንግዲህ ክርስቲያን አይደለህም የሚለኝ ፣ አሳስቶ የሚከሰኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። የሰይጣን ቆንሲል ሁኖ በውስጥ የሚዋጋኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። እንደ ክፉ ጎረቤት የሚነዘንዘኝ ፣ እንደማይሸጡት ልጅ መላቀቂያ ያሳጣኝ ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። እንደ ባሕር ንውጽውጽታ የማያጣው ሥጋዊ አሳቤ እርሱ ነው ። የዘመኑ ሰማዕትነት ሥጋዊ አሳብን ማሸነፍ ነው ። እባክህ ጌታዬ ሥጋዊ አሳቤን አሸንፌ መንፈሳዊ እንድሆን ፣ የጨለማን አሳብ ጥላቻን ድል ነሥቼ ውሉደ ብርሃን እንድሆን እርዳኝ ። ክፉ ከሆንሁት ከራሴ አድነኝ አሜን።(ፍቅርተ ኢየሱስ)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን 🤲
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
#ዕለታዊ_መልዕክት
አንዳንዶቻችን መንፈሳዊ ጽሁፍ መጻሕፍት ስብከት መዝሙር ጊዜ የለኝም እንጂ ቢያነብ ቢያዳሚጥ ጥሩ ነው እንላለን !!!
። አንዳንዶቻችሁ ደሞ ጊዜ የለንም ትላላችሁ ለማንበብ። ቆይ ከጓደኞቻችን ጋር ለመጫወት፣ ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ facebook , Tik Tok , YouTube እና ሌሎች ማህብረዊ ድህረ ገፆች ላይ የተለቀቁ ቪዲዮዎችን ለማየት፣ ስለ ሰዎች ለማወቅ፣ ዜና ለመስማት፣ ወሬ ለመስማት፣ ለኳስ.... ለብዙ ብዙ ስጋዊ ነገሮች ጊዜ አለን ይሄ ጊዜ ከ24 ⌚ ሰዓት በተጨማሪ ከዬት የመጣ ነው፣ መንፈሳዊ ፅሁፎችን በቀን 5 ደቁቃ እንኳን ለማንበብ ረዘመ እንላለን። በቀን አንድ ምዕራፍ ከመፅሀፍ ቅዱስ ለማንበብ እንኳን በዛ እንላለን። ዘፈን ለማዳመጥ ሲሆን ጊዜ አለን መዝሙር እና ትምህርቶችን ለመስማት ግን ጊዜ የለንም። ለምን??
ሰንበት ትምህርት ተማሩ ስንባል አብዛኞቻችን ጊዜ የለኝም አይመችም እንላለን። በሳምንት 6ቀን የአለማዊ ትምህርት ለመማር እና ስድስት ቀን ለመስራት ጊዜ አለን በሳምንት 1 ቀን ግን ለነፍሳችን ሚጠቅመውን ቃለ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ሄዶ ለመማር ጊዜ የለንም ለምን??
እስኪ ልጠይቃችሁ ሁለት ፍቅረኛሞች በጣም እንዋደዳለን እንፋቀራለን ቢሉ ግን ባይገናኙ፣ ባይደዋወሉ፣ አንዱ ስለ አንዱ ማንነት የማያውቅ ከሆነ፣ ካልተጠያየቁ በችግርም በደስታም አብረው ካልተባበሩ ምኑ ላይ ነው ፍቅራቸው?? እኛም እኮ እንዲው ነን፣ እግዚአብሔርን እንወዳለን እንላለን፣ ለስሙ ክርስቲያን ነን ግን ከእግዚአብሔር ብዙ ርቀናል። በህይወታችን እኮ ቦታ ስንሰጠው ነው መውደዳችን ሚገለጠው። በነገሮች ሁሉ እሱን ስናስቀድም ነው መውደዳችን ሚታወቀው። እንወደዋለን ግን ለሱ ጊዜ የለንም።
ግን እንደው አንዳንዴ ሳስበው ግርም ይለኛል። የሰማይ እና የምድር ንጉስ፣ መላእክት በፊቱ የሚንቀጠቀጡለት፣ ሁሉ የሚታዘዝለት ሁሉን የሚችል አምላክ እኛን ለማናገር ጊዜ የለኝም ሳይለን እኛ ግን እሱን ለማናገር(ለመፀለይ) ጊዜ የለኝም እንላለን። እንደው ምሳሌ ልስጣችሁ አሁን ጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር አብይ ልናገኛቸው ልናወራቸው ብንሄድ እንዴት በአክብሮት እንዴት በስርዓት እንዴት በተጠንቀቅ እና በጉጉት ነው ሚሆነው። እግዚአብሔርንስ ለማናገር ሲሆን ምን ያህል ደስተኞች ነን? ምን ያህል እንደ ትልቅ ነገር እንቆጥረዋለን ከሱ ጋር ማውራታችንን? ምንስ ያህል በስርዓት እና በቁምነገር ነው??
እለት እለት በምናደርጋቸው ነገር ሁሉ እራሳችንን እየመረመርን ከራሳችን ጋር መታገል ያስፈልጋል። አካሄድን መመርመር። ውሳኔያችንን መመርመር። እርምጃችንን መመርመር? አንድ ነገር ከማድረጋችን በፊት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ወይስ ይህ ነገር ሀጥያት ነው ብለን ማስብ አለብን መጀመርያ። ምንም አይነት ነገር ከማድረጋችን አስቀድሞ እኮ ሊታሰብ የሚገባው አምላክ አለን። በስጋዊ ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊውም ጉዳዬች።
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
አንዳንድ ሰዎች እጅግ የጠለቀ ሃዘንና መቆርቆር ውስጥ ሲገቡ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ረስቶኛል” ብለው ሲያማርሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ነቢዩ እንዲህ ከሚሉ ሰዎች ጋር ክርክር አለው፡፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀኗ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃኗን ትረሳ ትችላለችን?” በማለትም ይጠይቃቸዋል (ኢሳ.49፥14)፡፡ ይህም ማለት ሴቷ ከማኅፀኗ የተወለደው ልጇን ልትረሳ ዘንድ እንደማይቻላት እግዚአብሔርም ሰውን ይረሳ ዘንድ ባሕርይ አይደለም እያላቸው ነው፡፡
ነቢዩ ይህን ምሳሌና ማነጻጸርያ አንሥቶ ክርክር መግጠም የፈለገው እያንዳንዷ እናት ለልጇ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኾኖም ይህን ያህል የምናንቆለጳጵሰው የእናት ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው “አዎን እርሷ ትረሳ ይኾናል፤ እኔ ግን አልረሳሽም… ይላል እግዚአብሔር” በማለት የሚቀጥለው፡፡ እንግዲህ የአምላካችን ፍቅር እንደምን የበዛ እንደ ኾነ ታስተውላላችሁን?
እንግዲያውስ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አባት ለልጆቹ እንዲያዝን እንዲራራ እንደዚህም ኹሉ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይራራለቸዋል” ብሎ እንደተናገረ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ትቶኛል” የሚል ማንም አይገኝ (መዝ.102፡13)፡፡ ጆሮን የፈጠረ እርሱ ይሰማል፤ ዐይንን የፈጠረ እርሱ ያያል፡፡ እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ የቀረጻቸው ልጆቹን አይረሳም፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯
#የመጨረሻ_ክፍል
#ራስን_መግዛት (ክፍል- ፭)
#ምኞትና_የበላይነት
መንፈሳዊው ሰው ምኞቱን፣ ደስታውን መውደዱንና የበላይነቱን አስመልክቶ ራስን መግዛት አለው:: በራሱ ዓይኖች ፊት ራሱን አዋቂ አድርጎ ሲያገኘው ወይም በአመለካከቱ ውስጥ ራሱን አጽድቆ ሲመለከት ወይም ደግሞ ራሱን ከሚያስበው በላይ ከፍ አድርጎ ሲያስብ ራሱን ለመግዛት ይጥራል፡፡ ሮሜ 12፥3
ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔር ከሰጠው ጸጋ በላይ ራሱን ሊያልቅ አይሞክርም፡፡ ዲያብሎስ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ብሎ በትዕቢት የተነሣው ራሱን መግዛት ባለመቻሉ ስለሆነ ወድቋል። ኢሳ. 14፥14
መንፈሳዊው ሰው ራሱን የሚገዛው ውዳሴ ከንቱን አስመልክቶ ብቻ ሳይሆን ስጦታዎችንም በተመለከተ ነው:: ወይም ደግሞ ሰውየው ራሱን ከፍ ከፍ እንዳያደርግ እግዚአብሔር እርሱነቱን የሚገዛበትን መንገድ ያመቻችለታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ የተናገረውን ቃል አትርሱ! «ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።» 2ኛ ቆሮ. 12፥7።
#ወንድሜ_ሆይ! አሳብህ ከፍ ከፍ ባለብህ ጊዜ ሁሉ ተቆጣጠረው። ራስህን ከተሰጠህ በላይ አድርገህ አትገምት፡፡ አንተነትህን ከሌሎች ጋር አነጻጽረህ ወደምትመለከትበት ደረጃ የሚመሩህ ምኞቶችህን ግታቸው፡፡ ራስህን ከፍ ከፍ ብሎ ስታየው ወይም ደግሞ በፊትህ ታላቅ ሆኖ ስታገኘ ው ታዛዥነትህን፣ ትሕትናህን፣ ለሌሎች ያለህን ክብር በማጣት ላይ መሆንህን እወቅ፡፡ በማንኛውም ጊዜ ከፊት ለፊትህ የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አኑር። «ትዕቢት ጥፋትን ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።» ምሳ. 16፥18::
#በሕይወት_ዙሪያ
ራስን መግዛት መላ ሕይወትን ያጠቃልላል፡፡ መንፈሳዊው ሰው ምቾትንና ድሎትን አስመልክቶ ራስን መግዛት አለው፡፡ እርሱ ሰዓቱን በትክክል ይጠቀማል፡፡ በመሆኑም ጊዜውን ለሚሠራው መንፈሳዊ ሥራ ያከፋፍላል። ቀጠሮ ያከብራል:: በተሰደበ ወይም በተጠቃ ጊዜ ሰራሱ ሊበቀል እንዳይነሳሳ ራሱን ይገዛል፡፡ ገንዘብን በተመለከተም ስለሚቀበለውና ስለሚስጠው ገቢና ወጪ ላይ ራሱን ይገዛል። ከሌሎች ጋር የሚያደርገው ግንኙነት እስከ ምን ድረስ መሆን እንዳለበት ይረዳል:: ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ እንዳያጋድል የልቡን ስሜታዊነትና ፍላጎት ይቆጣጠራል:: ሌላው ቢቀር በአምልኮ፣ በአገልግሎት፣ሌሎችን በመቆጣጠርና ሌሎችም ባሉበት ኃላፊነቶች ውስጥ ራሱን ይገዛል::
#ለማጠቃለል
በዚህ ጉዳይ ላይ የምስጠው ጠቃሚ አስተያየት ራሱን ከውስጥ መቆጣጠር የማይችል ስው ከውጪ የሌሎች ቁጥጥር እንደሚያስፈልጉት የሚገልጽ ነው:: እርሱ ራሱን ከውስጥ መቆጣጠር ካልቻለ ቁጥጥሩ ያለ ፈቃዱ ከውጪ ይመጣል። ከውጪ የሚመጡት ኃይላትም አመሉን በቅርብ የሚያውቀውና ኃላፊነቱን የሚጠይቀው ኅብረተሰብ አንዱ ሲሆን የሚመለከቱት ዓይኖችና የሚሰሙት ጆሮዎች ተጠያቂ ያደርጉታል። ከዚህ በኋላ በፍርሃት ይገዛል ወይም በእፍረት ይሸማቀቃል፡፡ በመጨረሻም በሕግና ከበላይ አካላት በሚመጡ ውሳኔዎች እንዲቆጣጠሩት ይሆናል::
ወይም ደግሞ በመንፈሳዊ ምክሮች ከገደቡ እንዳያልፍ አድርገው ያቆሙታል፡፡ ከዚህ ካለፈ ስህተቱን እንዳይደግም በሚያደርጉት ውጪያዊ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ይወድቃል:: ነቢዩ ዳዊት ራሱን ባለመግዛቱ ብቀላ ከመውሰድ ራሱን ሊከለክል አለመቻሉ በጣም ያስደንቀኛል። በዚያን ወቅት ለእርሱ ውጪያዊ ኃይል ስላስፈለገው አቢግያ በጥበብና በእውቀት እንድትገሥጸው ሆኗል። 1ኛ ሳሙ. 25::
አንድ ሰው ያለራሱ ፈቃድ በሌላ ቁጥጥር ውስጥ ከሚገባ ወይም በውጪያዊ ኃይል ከሚገዛ ይልቅ ራሱን በመንፈሳዊነት ገዝቶ መለኮታዊውን ዋጋ ቢያገኝ ይሻለዋል ይበጀዋልም:: መንፈሳዊው ሰው ግን ራሱን የሚገዛው ከውስጥ ነው:: በዚህ ጊዜ ውጊያዎች ከመጡበትም ምንጊዜም ቢሆን የሚፈልገው የልቡን ንጽሕና እና የተቀደሱ ሥራዎቹን ስለሆነ የተለያዩ መንፈሳዊ እርምጃዎችን ይወስዳል::
(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)
#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ !
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
/channel/dnhayilemikael
╰═══•ೋ•✧๑♡๑✧• ═══╯