dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አንተ ማን ነህ?

💠በቃላት ሳይሆን በሥራ የሚገለጥ ማንነት አለህ ?
✝️መኑ አንተ ? ብተባል አንደበትህ ሳይተሳሰር የምትጠራ ስም አለህ?

💠ሌሎችን ከማገልገልህ በፊት ነፍስህን አገልግለሃል ?
💠ወይ እንደ ማርታ ከቃለ እግዚአብሔር ርቀህ በአገልግሎት ባክነሃል?

💠አውደ ምህረት ወጥተህ ከማገልገል በፊት ግን መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት ተምረዋል ?

ግን አንተ ማን ነህ?

💠ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነህን?

✝️በክርስቲና እምነት ስንት ዓመት ሆኖሃል?
ሰው 17 ዓመት ተምሮ ዶክተር እንጅነር.. ይሆናል ግን አንተ ለዘመናት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ኖረህ ሃይማኖትህን ያለ ፍርሃት ለመመስከር በቅተሃል?

💠ሃይማኖትህ ላይ የሚነሳውን ጥያቄ መጻሕፍትን ጠቅሰ ምላሽ ትሰጣለህን?

ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?

💠ባይሆን እንኳን ከወዴት ወገን ነህ?

✝️ካልጠፋት ከዘጠና ዘጠኙ መካከል ነህ?
💠ወይስ ጠፍቶ የተገኘው በግ የሚሉህ አንተን ይሆንን?

✝️ንስሐ ከማይሹ ወገን ነህን?
💠ንስሐ በመግባታቸው ደስታ ከተደረገላቸው መካከል ብትሆንስ?

✝️ነው ሙሽራው እስክመጣ ድርስ ባዶ ዘይት ይዞ ከተቀመጡት ወገን ነህ?

ለመሆኑ አንተ ማን ነህ
💠💠💠💠💠


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ሐዋርያው "የአጋንንት ልጆችና የእግዚአብሔር ልጆች በምድር ላይ የታወቁ ናቸው " እንዳለ። ፩ዮሐ ፫-፲ ትሑታን ግን ሁሉ ሲረግጣቸው አይታወቁም ። ቅዱስ ጳውሎስ "መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሁሉን ያውቃል /ይመረምራል/ እርሱን ግን የሚያውቀው /የሚመረምረው/ የለም" እንዳለ ። ፪ኛ ቆሮ ፪-፲፭ #ከጾም የሥጋ ንጽሕና ፣ ከሥጋ ንጽሕናም የነፍስ ቅድስና ይወለዳል ፤ ከነፍስ ቅድስናም ፍጹም የሆነ ርኅራኄ ይወለዳል ። ይህውም ለሰው ብቻ መራራት አይደለም ። ለፍጥረት ሁሉ ደኀንነት /ሕይወት/ ይሻላቸዋል ።  ማንኛውም ክፍ ነገር ካልተጨመረበት ርኅራኄ ይህ ነው ።

#ከርኅራኄ መልካምን ማድረግ ይወለዳል። መላካም ማድረግም መልካም ለሚያደርጉ ብቻ አይደለም ክፍ ለሚያደርጉብንም መልካም  እናደርጋለን እንጂ ። ጌታችን እንዳስተማረን " መልካም ላደረጉላቹሁ መልካምን ብታደርጉ ዋጋቹሁ ምንድን ነው ? የህንንስ ቀራጮችም ያደርጉታል። እናንተስ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ለሚጠሏሁም መልካምን አድርጉላቸው ።

( ርቱዓ ሃይማኖት )



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ነው። ስያሜውም የቅዱስ ያሬድ ነው። ትርጉሙም “ከሰማያት የወረደ” ማለት ነው። ቅድመ ዓለም ከአባቱ ከአብ የተወለደ ፣ድኅረ ዓለም ከድንግል ማርያም የተወለደ ነው። ስም አጠራሩ  ያለና የነበረ፣ እግዚአብሔር፣ በፈቃዱ ዓለምን ለማዳን የመምጣቱን ምሥጢር የምንረዳበት ሳምንት ነው። ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጾም ጥቅምና እንዴት መጾም እንዳለብን ታስተምረናለች፡፡ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው “አከለክሙ መዋዕል ዘኃለፈ ዘተቀነይክሙ ለግዕዘ ሥጋክሙ፤ ለሥጋቸሁ ፈቃድ የተገዛችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃችኋል፤ ከአሁን በኋላ ግን ጹሙ፣ ጸልዩ ለእግዚአብሔር ተገዙ” እያለ የጾም አዋጅ ያውጃል። ጾም ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ፣ ፈቃደ ነፍስን ለፈቃደ እግዚአብሔር የምናስገዛበት መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡

ጾሙ በሚጀመርበት ሰንበት በሚሰበከው ምስባክ እንዲህ ብሎ ያሳስበናል፤ “ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፣ በረዓድም ደስ ይበላችሁ” ጾም ከምግብና ከመጠጥ እንዲሁም ከሌሎች ምቾቶችና ደስታዎች ከመከልከል ያለፈ ጥልቅ ትርጉም ያለው ተግባር ነው። (መዝ.፪፥፲፩-፲፪) “ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ከመ ያብርህ ብርሃነ ስብሐቲሁ በላዕሌነ፤ (የእግዚአብሔር) የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ወንድማችንንም እንውደድ” እንዲል። (ጾመ ድጓ)

በዘወረደ እሑድ የሚነበቡት ምንባባትም ይህንን የጾምን ጸጋ የያዙ ናቸው።

“ነገር ግን ፈጣሪያችን የምትበልጠውን ጸጋ ይሰጣል፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት፤ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት፤ ከእናንተም ይሸሻል፡፡ እግዚአብሔርን ቅረቡት፤ ይቀርባችሁማል፤ እናንተ ኃጥኣን እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ፡፡ እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ÷ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል፡፡” (ያዕ.፬፥፮-፲)

“በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን? ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና፡፡” (ዕብ.፲፫፥፲፭-፲፮)

በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳንን እያሰብን ለጾም እንድንተጋም ወደ እነርሱ እንድንመለከት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡“ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።” (ዕብ.፲፫፥፱) ሳምንቱ በሚጀምርበት ሳምንት የሚነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት እንዲህ ይላል፡፡ ጾመ ድጓው አባቶቻችን ያገኙትን በረከት እንደምናገኝበት ሲገልጽ “የእግዚአብሔር የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ ወንድሞቻችንም እንውደድ፤ ኤልያስ በጾም ወደ ሰማይ አርጓልና፤ዳንኤልም ከአናብስት አፍ ድኗልና፡፡”

ጾም ፈቃደ ነፍስን በፈቃደ ሥጋ ለማሠልጠን የአጋንንት ኃይል ለመቋቋም የሚያስችል የክርስቲያኖች ጋሻ በመሆኑ በሃይማኖት ለሚመሩ ምእመናን እጅግ አስፈላጊና ከምንም በላይ የሕይወታቸው መርሕ መሆን እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ በማለት   ያስተምራል፡፡ ” አሁንም ወንድሞቻችን በዚህ በሥጋችን ሳለን ፈቃደ ሥጋችንን ልንሠራ አይገባም፤ ፈቃደ ሥጋቸውን የሚሠሩ ሰዎች በወዲያኛው ዓለም ምውታን ናቸውና፡፡ የሥጋችሁን ፈቃድ በነፍሳችሁ ፈቃድ ድል ከነሣችሁት ለዘለዓለም ሕያዋን ትሆናላችሁ፡፡ የነፍሳቸውን ፈቃድ የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና፡፡" (ሮሜ ፰፥፲፪-፲፬)

ጾም አበው ቅዱሳን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቀምረው፣ በበታ ወስነው፣ በሁኔታ ገድበው... ባስቀመጡልን ወቅት ከእህልና ከውኃ በመከልከልና ሰውነትን በማድከም ብቻ ሳይሆን ለስሕተት ከሚዳርጉ ነገሮችና ቦታዎች ተቆጥቦ በጸሎት መትጋትም እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ይህንን እውነታ በተመለከተ እንዲህ ይላል፡፡ “እኔ ግን እዘንልን፤ ለምንልን ባሉኝ ጊዜ ማቅ ምንጣፍ ለብሼ አዘንኩላቸው፤ ሰውነቴን በጾም አደከምኩዋት፤ ልመናዬም እኔም ወደመጥቀም ተመለሰችልኝ፡፡” (መዝ. ፴፬/፴፭፥፲፫)

ጾም ከሥነ ምግባራት ሕግ አንዱ በመሆኑ እንኳንስ ያልተፈቀደውን የተፈቀደውም ቢሆን የማይጠቅም ከሆነ ፈጽሞ በመተው ለእግዚአብሔር ያለንን ፍጹም ፍቅር የምናስመሰክርበት ምሥጢር ነው፡፡

ጾም ከመብልና ከመጠጥ ጋር የተያያዘም በመሆኑ መብል ጊዜያዊ ስለሆነ ማለትም በዚህ ዓለም እስካለን ብቻ የምንገለገልበት እንጂ ዘለዓለማዊ ስላይደለ ለጊዜያዊ መብልና መጠጥ ምክንያት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር እንዳንወጣ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ሲመክሩ “መብል በእግዚአብሔር ዘንድ ግዳጅ አይፈጽምልንም ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ብንበላም አይረባንም፤ አይጠቅመንም፤ ብንተወውም አይጎዳንም” በማለት ሲመክሩን ቅዱስ ጳውሎስም የመብልና የሆድ ጊዜያዊነት አስመልክቶ እንዲህ በማለት አስተምሯል፡፡ (፩ኛቆሮ.፰፥፰)

“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅመኝም፡፡ ሁሉ ተፈቅዶልኛል በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳን አይሠለጥንብኝም፡፡ መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያሳልፋቸዋል”፤ (፩ኛቆሮ.፮፥፲፪-፲፫) “ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት ስለሚሆን ምግብ ሥሩ” እንደ ተባለ (ዮሐ. ፮፥፳፯) ካለን ጊዜ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጊዜ በመስጠት ቢበሉት የማያስርበውን፣ ቢጠጡት የማያስጠማውን፣ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን ሥጋ እና ደሙን ተቀብለን መንግሥቱን እንድንወርስ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

ሥርዓት ቅዳሴ
ከሠራኢ ካህን፣
ቅዳሴ፡
ዘእግዚእነ
“ዘበእንቲኣነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ፡ ወረደ እምሰማያት። ተሰብአ፡ ወተሠገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብር  ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፡፡”

ወንጌል፡ ዮሐ.፫፥፲-፳፬
የዕለቱ ምንባባት:-
•  በሠራኢ ዲያቆን (ዕብ.፲፫፥፯-፲፯)
•  በንፍቅ ዲያቆን (ያዕ.፬፥፮-ፍጻሜ)
•  በንፍቅ ካህን (የሐዋ. ፳፭፥፲፫-ፍጻሜ)

ምስባክ፡ “ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር” (መዝ.፪፥፲፩)

ወንጌል፡ ዮሐ.፫፥፲-፳፬

ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ፤ እንድናመልከው እኛን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን!

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#በዐቢይ_ጾም_መግቢያ_የተሰጠ_ትምህርት

የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ በልጆቿ ስትደምቅ እናንተም ጉባኤውን ለመታደም ደስ ብሏችሁ ተሰባስባችሁ ስትመጡ ዐይቼ ሐሴት አደረግሁኝ፤ ደስም አለኝ፡፡ ፊታችሁ እንዴት በደስታ እንደ ተመላ ስመለከት ጠቢቡ “ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል” እንዳለው ልባችሁ ምን ያህል እንደ ተደሰተ ተገነዘብሁኝ (ምሳ.15፥13)፡፡ በመኾኑም፥ ዛሬ ማለዳ የተነሣሁት ከወትሮው በተለየ ትጋት ነው፡፡ ይኸውም ይህን መንፈሳዊ ደስታ ከእናንተ ጋር እንድካፈልና ቀጣዩ ወራት ቁስለ ነፍሳችሁ ድኅነት የሚያገኝበት ወርሐ ጾም መኾኑን አበሥራችሁ ዘንድ ነው፡፡ የኹላችንም ጌታ ልዑል እግዚአብሔር፥ ልክ እንደ ደግ አባት ባለፉት ወራት ለሠራነው ኃጢአት ሥርየት እናገኝበት ዘንድ ሽቶ መድኃኒት የሚኾን ቅዱስ ጾምን አዘጋጅቶልናልና፡፡

ስለዚህ የነፍሳችን ጠባቂ (እግዚአብሔር) የሕመማችንን ፈውስ የምናገኝበትን መድኃኒት ስላዘጋጀልን እያመሰገንን ወርሐ ጾሙን ደስ ብሎን ልንቀበለው ይገባናል፡፡ ከእኛ መካከል ጾም በመግባቱ አንድስ እንኳን የሚከፋው ወይም የሚበሳጭ ሊኖር አይገባም፡፡ ወርሐ ጾሙን እንዲህ ደስ ተሰኝተን መቀበላችንን ዐይተውም አሕዛብ ይፈሩ፤ አይሁድም ይራዱ፡፡ በእኛና በእነርሱ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ዐይተውም ይማሩ፡፡ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በዓል የምትሠራው ምእመናን ራሳቸውን መግዛት እንዲችሉ፣ በበጎ ምግባር ያጌጡ ያሸበረቁ እንዲኾኑ እንደ ኾነ፥ እነርሱ ግን በዓላትን የሚያደርጉት በዘፈንና በስካር ይህንም በመሰለ በሌላ ጸያፍ ግብር ለመንከባለል እንደ ኾነ ለይተው ይወቁ፡፡ በእርግጥም በዓል ተከበረ የሚባለው፡- ሰዎች ነፍሳቸውን ካዳኑበት፣ ውስጣዊ ሰላምንና ፍቅረ ቢጽን ገንዘብ ካደረጉበት፣ ዕለት ዕለት ከሚያጋጥማቸው የነፍስ መታወክ ካረፉበት፣ ያለ ሁካታና ጋጋታ እንዲሁም እንስሳትን በማረድ ከልክ በላይ ከኾነ መብልና መጠጥ ርቀው ያከበሩት እንደ ኾነ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓል ተከበረ የሚባለው፡- አርምሞንና ጸጥታን፣ ፍቅርንና ደስታን፣ ሰላምንና ራስን መግዛትን፣ እንዲሁም ሌሎች እዚህ መዘርዘር የማንችላቸው ብዙ ምግባር ትሩፋቶችን ገንዘብ ያደረግንበት እንደ ኾነ ነው፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ቂም ይዞ ጸሎት +

አበው እንዲህ ይላሉ ''ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት'' የማይታሰብ ነው ይላሉ።ለምን አንድ ሰው ለጸሎት ሲቆም የበደለውን ክሶ የወሰደውን መልሶ በንጹህ ልብ ሆኖ ለአምላኩ ጸሎት ማቅረብ አለበት ምክንያቱም ጸሎት ምስጋና ነው ጸሎት ልመና ነው እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን እና የምንፈልገውን እንዲሰጠን መጀመሪያ እኛ የምንጠላውን ሰው ይቅር ማለት አለብን።

''አንድ ሰው ከልጃቸው ጋር ቤተ ክርስቲያን ይሄዱና ዳዊታቸውን ዘርግተው ጸሎት ይጸልያሉ።
ጸሎት እስኪ ጨርሱ ልጁን አጠገባቸው አረፍ እንዲል ይነግሩታል ከዚያ የዳዊትን መዝሙር በተመስጦ መጸለይ ይጀምራሉ በመሐል አንድ እጅግ በጣም የሚጠሉት ሰው በአጠገባቸው ያልፋል ልጅ ''አባዬ አባዬ ያ የምትጠላው ሰው መጣ ''ይላል አባትም ጸሎቱ እንዳይቋረጥባቸው በማሰብ ድምጽ ሳያሰሙ በእጃቸው በምልክት አንገቱን በለው ይሉታል።''

ይገርማል ይህ ሰው የተጣላውን ሰው ይቅር ሳይል ነበር እግዚአብሔር ይቅር እንዲለው ይጸልይ የነበረው።ይህ ሰው ስለ ጸሎት አንድ ነገር ያውቃል በጸሎት ጊዜ ከሌላ ሰው ጋር መነጋገር እንደማይቻል ያውቃል ነገር ግን ከቂም ከበቀል ራሱን ማንጻት እንዳለበት ግን አያውቅም ለዚህ ነው መዝሙረ ዳዊት እየጸለየ እንዳይናገር ለልጁ በምልክት እንዲመታው ያዘዘው።

ይህ ሰው የፈሪሳውያን ጠባይ ነው ያለው ለውጩ ስርዓት በጣም ተጠንቅቋል ውስጡ ግን በኖራ እንደተለሰነ መቃብር ነበር። ይህ ሰው ከሁሉ አስቀድሞ ከመጸለያችን በፊት የተጣላነው ሰው ካለ ይቅር ማለት እንዳለብን ያስተምረናል በቂም ውስጥ ሆኖ የሚጸለይ ጸሎት ጥቅም የለውም። ጌታም ከሁሉ አስቀድሞ ይቅርታን ገንዘብ ማድረግ እንዳለብን ሲያስተምር " ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ።"( ማቴ 12:7)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ከምናቀርበው የጸሎት ምሥዋዕት በላይ ለሌላው ሰው የምናደርገው ይቅርታ ያስደስተዋል። ምህረትን እወዳለሁ መሥዋዕትን አይደለም ማለት ይህ ነው።
ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።
እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ( ማር 12:25-26 )

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የአሥርቱ ትዕዛዛት አከፋፈል

  የክርስቲያን ሕግ የፍቅር ሕግ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታል ካለ በኋላ ከአሥርቱ ትዕዛዛት የተወሰኑትን በመጥቀስ ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። /ሮሜ 13÷8-10/

  እንዲሁም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ፍቅር በሁለት ይከፈላል። /ማቴ 22÷34-41/
1, ፍቅረ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን መውደድ)
2, ፍቅረ ቢጽ (ወንድምን መውደድ)

- በተጨማሪም ጌታችን ሕግም ነቢያትም በነዚህ በሁለቱ ትዕዛዛት ተጠቃለዋል ብሎ ስለተናገረ በዚህ መነሻነት አሥርቱን ትዕዛዛት በሁለት እንከፍላቸዋለን።

1, #ፍቅረ_እግዚአብሔር ፦ ከ1ኛው ትዕዛዝ አስከ 3ተኛው ትዕዛዝ ድረስ ያሉት።
- ከኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁንልህ
- የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
- የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ

2, #ፍቅረ_ቢጽ ፦ ከ4ተኛው ትዕዛዝ እሰከ 10ኛው ትዕዛዝ ያሉት።
- አባትና እናትህን አክብር 
- አትግደል
- አታመንዝር
- አትስረቅ
- በሐሰት አትመስክር
- የባልንጀራህን ቤት አትመኝ
- ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ


#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጊዜ እስኪ ደርሰ
ወደ አንተ መምጫዬ
ለንስሐ አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ
ለቁርባን አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሰበር መረጃ
+++++++++++++++++++++++++++++
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡
ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ:---
1.  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2.  የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3.  የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4.  በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም የተባሉት የገዳሙ የሥራ ሓላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገልጸዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሙ ጸጥታውን የሚያስከብረበት  መሣሪያዎች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ገዳማውያን በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

©የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዮሐንስ ዘደማስቆ ሊቁ እንዲህ ይላል ፦ ወዳጆች ሆይ በመስቀል ፈት በሰገድን ጊዜ በቀጥታ በመስቀሉ ላይ ለተሰቀለው እየሰገድን እንጂ ለእንጨቱ እንዳልሆነ እርግጠኛ እንኹን አለበዚያማ በመንገድ ላይ በሚገኘው ዛፍ ፈት እንድንበረክክ ታዘናል ማለት ነው ። "በማለት መስቀል ልዩ መኾን የቻለው ኢየሱስ ስለተሰቀለበት መኾኑን መስቀልን ስንመለከት እንጨቱን ሳይኾን የምናስታውሰው ዓለምን ለማዳን ሲል በላዩ ላይ የተሰቀለውን አምላካችንን ነው ።እንግዲህ ቅዱስ መስቀሉ ወደ ክርስቶስ ሕሊናችንን እንደሚያሳርግ ሁሉ ቅዱሳት  ሥዕላትም ወደ ሥዕሉ ባለቤት ያሳርጉናል
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

❖ ወዳጄ እስኪ ልጠይቅህ፤ አንተም አንቺም መልሱልኝ!

❓ጌታችን ዛሬ ቢመጣ የምትመልሰው የምትመልሺው መልስ ምንድን ነው

✍️"ንስሐ ያልገባሁት፣ ሥጋ ወደሙን ያልተቀበልሁት፣ ምግባር ትሩፋት ያልያዝሁት ዕድሜዬ ገና ነው ብዬ አስቤ ነው፤ ሥራ በጣም በዝቶብኝ ስለ ነበረ ጊዜ አጥቼ ነው፤ ዛሬ ነገ እያልኩ እየረሳሁት እንጂ እንደዚያ ማድረግ አቅቶኝ አልነበረም"

❓ምክንያትህ እነዚህ ናቸው
❓እኅቴ! ሰበቦችሽ እነዚህ ናቸው

❖ በዚያ ሰዓት ግን እነዚህ ኹሉ ጥቅም የላቸውም፤ እናት ልጇን በማታድንበት ሰዓት እነዚህ ምክንያቶች ምንም አይረቡም፡፡

❓ ታዲያ ለምን ትዘገያለህ
❓ እኮ ለምን ትዘገያለሽ
❓ያኔ ዋይ ዋይ ከምትዪ... ያኔ የማይጠቅም ጸጸት ከምትጸጸት ለምን ዛሬ አትጠቀምበትም
❓ለምን ራስህን አታድንም

📌 ምንጭ
✍️ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ተስፋ መቍረጥ

ዮሐንስ ዘሰዋስው ስለ ቀቢጸ ተስፋ ሲያስረዳ፦ "ቀቢጸ ተስፋ  የመቀባጠር አንዱ ቅርንጫፍ፣ የእርሱም የበኲር ልጅ ናት። ... ቀቢጸ ተስፋ የነፍስ ልምሾነት (መሰልሰል)፣ የአእምሮ መዛል (መድከም)፣ ተጋድሎን ቸል ማለት፣ ብፅዓትን (ቃል ኪዳንን) መጥላት ነው። ... እግዚአብሔርንም ምሕረት የለሽና ሰዎችን የሚጠላ እንደ ኾነ አድርጋ ትከሳለች። መዝሙራትን ለመዘመር የምትዝል፣ ለጸሎት የምትደክም፣ ለአገልግሎት እንደ ብረት የጸናች (ግትር የኾነች)፣ ለተግባረ እድ የምትተጋ፣ ለመታዘዝ ኹኔታ (ብቃት) ቸልተኛ ናት።" ይላል። (ሳሙኤል ፍቃዱ (ሐተታና ትርጒም)፣ ምዕራግና ድርሳን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 173)። ከዚህ ትርጒም ተነሥተን ተስፋ መቍረጥ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ያለንን ስልቹነት፣ ወይም ጥላቻ የሚያመለክት ነው ማለት እንችላለን። ልበ አምላክ ዳዊት "ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል" እንዳለ በንዝኅላልነታችን ምክንያት እግዚአብሔር የለም ብለን እስከ ማመን የምንደርስበት ክፉ አኗኗር በቀቢጸ ተስፋ ኾኖ መኖር ነው። ተስፋ የሚቈርጥ ሰው ስኬት ላይ መድረስ አይችልም። ሕይወቱን በበጎ ጎዳና መምራት አይኾንለትም። ምክንያቱም ማንኛውም ነገር ጥረትንና ተጋድሎን ይሻልና። አንዴ ወደሚፈልገው መንገድ እየሄደ ውድቀት ካገጠመው ኹሉም ነገር ወዲያ ጨለማ መስሎ ይታየዋል።

በዋናነት ብዙ ሰዎች በተስፋ መቍረጣቸው ምክንያት ራሳቸውን ለማጥፋት ይወስናሉ። ተስፋ መቍረጥ የእግዚአብሔርን ምሕረት የመርሳትና ይሁዳን የመምሰል ሕይወት ነው። ተስፋ የሚቈርጥ ሰው ከዚህ ሐሳቡ ለመውጣት ሲል ወደ ሱስ ይጓዛል። በጽኑ ሱስ ሲያዝ ደግሞ የበለጠ የሕይወትን ጣዕም እያጣ ይሄዳል፤ ኋላም ራስን ማጥፋትን እንደ ቀላል ነገር አድርጎ ሊመለከት ይችላል። ቅዱስ ይስሐቅ ዘሶርያ "በመሰናክልህ ምክንያት ተስፋ አትቍረጥ። ይኸውም ኃጢአትህን በማሰብ አትጸጸት ማለቴ ሳይኾን፥ ነገር ግን የማይድኑ አድርገህ አታስብ ማለቴ ነው።" በማለት የገለጸው ብዙውን ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ከኃጢአቴ አልነጻም፣ መዳን አልችልም ብሎ ከማሰብ የሚመጣ ስለ ኾነ ነው። The Ascetical Homilies of St. Isaac the Syrian, Homily 64, “On Prayer, Prostrations, Tears, Reading, Silence, and Hymnody”። ወንድሜ ሆይ! ምንም ዓይነት መሰናክል ሊገጥምህ ይችላል፤ ነገር ግን ከልብህ ተጸጽተህ ንስሓ ከገባህ የሚድን መኾኑን አትዘንጋው። ከማንኛውም ውድቀትህ በላይ እግዚአብሔር የሚያዝንብህ አይምረኝም ብለህ ማመን ስትጀምር ነው። ንስሓ ከተገባበት የማይድን ምንም ዓይነት አደገኛ የኃጢአት በሽታ የለምና። የደማስቆው ጴጥሮስ "ነፍስን የሚገድለውን ተስፋ መቍረጥን፥ ጽኑ ተአጋሲነት ይገድለዋል።" በማለት ያስረዳል። St. Peter of Damaskos, “Book II: Twenty-Four Discourses,” V Patient Endurance, The Philokalia: The Complete Text (Vol. 3)።  እንግዲህ ይህ የሊቁ አገላለጽ በአንድ በኩል ተስፋ መቍረጥ ነፍስን የሚገድል መርዝ መኾኑን የሚጠቁም ሲኾን፥ በሌላ በኩል በትዕግሥት ሊነቀል የሚችል መኾኑን ያስረዳል። ስለዚህ ተስፋ መቍረጥ ትዕግሥትን በማጣት የሚበቅል ክፉ አረም መኾኑን በዚህ እናስተውላለን።

ዮሐንስ ዘካርፓቶስ እንዲህ ይላል "ፈርዖን ፈርቶ እንዲህ አለ፦ "ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፦ አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ፥ አኹን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፥ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ፣ አላቸው። ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።"  ፈርዖንም ተሰማለት። በተመሳሳይ ኹኔታ አጋንንትም ጌታችንን ወደ ገደል እንዳይከታቸው ለመኑ፥ ጥያቄያቸው ተመለሰላቸው። ሉቃ 8፡31። እንግዲያው አንድ ክርስቲያን ከመንፈሳዊ ሞት ይወጣ ዘንድ ቢለምን ምን ያህል የበለጠ ይሰማለት ይኾን?" በማለት በምንም መንገድ ተስፋ ወደ መቍረጥ መሄድ እንደ ሌለብን ነው።(St. John of Karpathos, For the Encouragement of the Monks in India who had Written to Him: One Hundred Texts (69)። ያን ጨካኙን ፈርዖንን የሰማ አምላክ አንተን እንዴት አይሰማህም? በመስቀል ላይ የሚሰቅሉትን እኒያን አይሁድን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ የምሕረት ድምፁን ያሰማ እርሱ አይምረኝም ብለህ ስለምን ትጨነቃለህ? ይልቅስ ኃጢአትህን አምነህ ይቅር ይልህ ዘንድ ወደ ፈጣሬ ዓለማት ወደ ኾነው ጌታ በአንብዓ ንስሓ ብትቀርብ አይሻልህምን? ተስፋ ስንቈርጥ ሁሉንም ነገር አጥርተን ማየት አንችልም። ልክ በጨለማ ውስጥ ያለ ሰው በብርሃን አለመኖር ምክንያት ከፊት ለፊቱ ያሉ ነገሮችን አጥርቶ ማየት እንደ ማይችል፥ ተስፋ በመቍረጥ ጨለማ ውስጥ ያለም ሰውም  እንዲሁ አጥርቶ ማየት አይችልም።
/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ብዙዎቻችን ለምን እንደምንኖር አላወቅንም። በዚህ ምድር ሳለን የምንናገረው፣ የምናስበው፣ የምናደርገው ነገር ሁሉ ከሞት በኋላ ለምንኖረው ዘለዓለማዊ ሕይወት ግብዓት የሚሆን መሆን ሲገባው በቀልድ፣ ለማንም በማይጠቅም ንግግር፣ ጊዜያችንን ስናባክን ይስተዋላል። እያንዳንዱ ድርጊታችን ከፈጣሪ ዘንድ እንጠይቅበታለን። መልካም ከሆነ እንሸለምበታለን። ክፉ ከሆነ ለዘለዓለም እንሰቃይበታለን።

ስለዚህ ያለንበትን ሁኔታ ቆም ብለን አስበን በክፉ መንገድ ካለን ንስሓ ገብተን ወደ መልካም መመለስና በመልካም መንገድ ካለን ደግሞ በዚሁ ለመጽናት መጣር አለብን።

© በትረ ማርያም አበባው


                        
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፱
ወልደ እግዚአብሔር በከዊን ስሙ ቃል ይባላል። ሥላሴ በባሕርይ አንድ ናቸው። ባሕርይ የሚባለው የሦስቱ ኵነታት ማለትም የቃል፣ የልብ፣ የእስትንፋስ መገናዘብ ነው። ባሕርይ አካላዊ ይባላል እንጂ አካል አይባልም። ባሕርየ ሥላሴ በቃል ከዊነ ሰው ሆነ ይባላል እንጂ በልብ ከዊን ወይም በእስትንፋስ ከዊን ሰው ሆነ አይባልም። ቃል ሰው ሲሆነ ከልብነት ከእስትንፋስነት ተገናዝቦ ሳይለይ ነው። ሥጋ የቃልን ገንዘብ ሲወርስ አብ ልቡ፣ መንፈስቅዱስ እስትንፋሱ ሆነዋል። ሥጋም በቃል ርስት የአብ ቃል፣ የመንፈስ ቅዱስ ቃል ተባለ።

ሥላሴ ስንል አብን፣ ወልድን፣ መንፈስ ቅዱስን ለማመልከት ነው። አብ የራሱ የሆኑ ፍጹም አካል አለው። ወልድም የራሱ ፍጹም አካል አለው። መንፈስቅዱስም የራሱ ፍጹም አካል አለው። እነዚህ አካላት አንዱ አካል በአንዱ አካል ህልው ሆነው ይኖራሉ። ህልው መሆን ብቻ ሳይሆን አንዱ ከአንዱ ተገነዛዝበው ይኖራሉ። ለምሳሌ ከምድር በላይ የፀሐይ ብርሃን በአየር ላይ ህልው ሆኖ ይኖራል። መገነዛዘብ ግን የለውም። አብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ፣ ወልድ በአብና በመንፈስ ቅዱስ፣ መንፈስ ቅዱስ በአብና በወልድ አለ (ህልው ሆኖ ይኖራል) ስንል ግን መገነዛዘብ ያለበት ህልውና ነው።

ሦስቱ አካላት የሚገነዛዘቡት ደግሞ በከዊን ነው። አብ በልብ ከዊኑ የወልድም የመንፈስቅዱስም ልብ ነው። ወልድ በቃል ከዊኑ የአብም የመንፈስቅዱስም ቃል ነው። መንፈስቅዱስ በእስትንፋስነት ከዊኑ የአብም የወልድም ሕይወት ነው። ስለዚህ አብን ልብ፣ ለባዊ፣ አለባዊ፣ ነባቢ፣ አንባቢ፣ ሕያው፣ ማሕየዊ እንለዋለን። ወልድን ቃል፣ ነባቢ፣ አንባቢ፣ ለባዊ፣ አለባዊ፣ ሕያው፣ ማሕየዊ እንለዋለን። መንፈስቅዱስን ደግሞ እስትንፋስ፣ ሕያው፣ ማሕየዊ፣ ለባዊ፣ አለባዊ፣ ነባቢ፣ አንባቢ እንለዋለን። የእነዚህ የሦስቱ ኵነታት ተገናዝቦ ባሕርይ ይባላል። ወልድ ሰው ሲሆን አካለ ቃል ከአካለ ትስብእት ጋር ተዋሕዷል። ባሕርየ ወልድ (ቃልነት) ከባሕርየ ትስብእት ተዋሕዷል ማለታችን ነው።

© በትረማርያም አበባው

/channel/dnhayilemikael
ክፍል ፲ ይቀጥላል

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፯
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደጻፈው በመሢሕ መሢሓውያን እንባላለን። ክርስቶስ ማለት መሢሕ ማለት ነውና። ይህንን ቅድስት ቤተክርስቲያን ስታስተምረው የኖረችውና ወደፊትም እስከ ዕለተ ምጽአት የምታስተምረው ትምህርት ነው። ሥጋ የአምላክነትን ክብር ሲያገኝ ክብር የሆነው ማን ነው የሚለውን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል። የቅባት እምነት አራማጆች ለሥጋ ቅብዕ (ክብር) የሆነው መንፈስ ቅዱስ ነው ይላሉ። ነገር ግን ቅዱስ አትናቴዎስ የሚነግረን ለሥጋ ክብር የሆነው ራሱ ቃል መሆኑን ነው። ይህንንም "ሥጋ ረከበ ዕበየ ወብዝኀ ፍድፍድና በተሳትፎቱ ወበተዋሕዶቱ ምስለ ቃል" ብሎ በማያሻማ ቃል ነግሮናል (ሃይ. አበ. ፴፫፣፳፱)። ሥጋ የአምላክነትን ክብር ያገኘው ከቃል ጋር በመዋሐዱ ነው እንጂ መንፈስ ቅዱስ ክብር ሆኖት አይደለም።

መቀባት (ማክበር) ግን የሦስቱም የአንድነት ሥራ ስለሆነ አብ ቀባው፣ መንፈስ ቅዱስ ቀባው ቢል አንድ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ቀባው ሲል ቢገኝ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ነው የሚል ትርጉምን አይሰጥም። ቅዱሳት መጻሕፍት ረቂቅ ሥራዎችን ሁሉ ለመንፈስ ቅዱስ አድለው መናገር ልማዳቸው ነው። ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ ለመንፈስቅዱስ የተጠቀሰው ከአካላዊ ግብር በስተቀር ለአብም ለወልድም ይሆናል። ለምሳሌ "ከውሃና ከመንፈስቅዱስ ያልተወለደ መንግሥተ ሰማያት አይገባም" ይላል። የተጠቀሰው መንፈስቅዱስ ስለሆነ የምንወለደው ከመንፈስቅዱስ ብቻ ነው አንልም። ከወልድም ከአብም ያልተወለደ ማለት እንደሆነ ልብ ማድረግ ያስፈልጋል።

በዚህ አግባብ የተነገሩትን ቃላት ለመንፈስቅዱስ አካላዊ ግብር አድርጎ መውሰድ የጠማማ ኅሊና ሥራ ነው። ግብረ ባሕርይን ከግብረ አካል ጋር ማቀላቀል ትልቅ በደል ነው። ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ስንል ምንጫችን ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ ሥጋ ከቃል ጋር በመዋሐዱ ክብርን አገኘ በማለቱ ምንታዌ ነው አንልም። ምክንያቱም ሲከፈልም፣ ሲዋሐድም፣ ሲቀባም አንድ ጊዜ ነውና። ስለዚህ በምንም ተአምር ምንታዌ አያሰኝም። ቃል አክባሪ ሥጋ ከባሪ ካላችሁ የካቶሊክ ትምህርት ነው የሚሉ ሰዎች አሉ። ይህ አስቂኝ ነው። የካቶሊክ ትምህርት አንድ አካል ሁለት ባሕርይ የሚል ነው። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ግን አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሚል ነው። ከተዋሕዶ በፊት ቃል በቃልነቱ በክብሩ ጸንቶ ይኖር ነበር። ሥጋ ቃልን በተዋሐደበት ቅጽበት ደግሞ መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስ "እንቲኣሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ዘእንበለ ኃጢአት ወእንቲኣሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል" ብሎ እንደተናገረው የቃል ገንዘብ ሁሉ ለሥጋ ሆነ የሥጋ ገንዘብ ሁሉ ደግሞ ለቃል ሆነ። ከቃል ገንዘቦች አንዱ ክቡርነት ነው። የቃል ክቡርነት ለሥጋ ሆነ። ስለዚህም በጊዜ ተዋሕዶ ቅዱስ አትናቴዎስ እንደተናገረው ሥጋ በቃል ከበረ እንላለን።

© መ/ር በትረማርያም አበባው (የመጻሕፍተ ሊቃውንት፣ የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ መምህር)


/channel/dnhayilemikael
ክፍል ፰ ይቀጥላል።

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ዐቢይ_ጾምን_ለምን_55_ቀን_እንጾማለን?

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይህንን የዐቢይን ጾም የቀናት ቁጥር 55 አድርገው ሲወስኑ ያለ አንዳች ምክንያት ሳይሆን በምስጢር ነው። ይሄውም እንዴት ነው ቢሉ ጾሙ 55 ቀን የሆነበት የመጀመረያው ምክንያት በነዚህ በሚጾሙት በ55ቱ ቀናት መሀከል (8 ቅዳሜና፣ 7 እሁዶች በአጠቃላይ 15 ሰንበታት) አሉና እነዚህ ሰንበታት ደግሞ ስለማይጾሙ እነርሱን ጌታችን ከጾማቸው ከ40ው ቀናት ጋር በመደመር 55 ቀናትን እንድንጾም አድርገውናል ።

ሌላውና የዐቢይ ጾምን 55 ቀን የምንጾምበት ሁለተኛው ምክንያት በጾሙ የመጀመሪያና የመጨረሻውን ሳምንታት በመቁጠር ነው። እነዚህ ሁለት ሳምንታት የመጀሪያው ሳምንት "#ጾመ_ሕርቃል" ሲሆን የመጨረሻው ሳምንት "#ሰሞነ_ሕማማት" ይባለል።

#ሕርቃል የአንድ ንጉሥ ስም ነው። ታሪኩ እንዲህ ነው በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺህ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺህ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገ*ደ*ለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡

በተመሳሳይ በዐቢይ ጾም ከሆሳዕና በኋላ ያለው የመጨረሻውን ሳምንት የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል የምናስብበት ጊዜ ነውና ሰሞነ ህማማት ተብሎ እንዲታወስና እንዲጾም አድርገዋል።

በእነዚህ ከፊትና ከኋላ በገቡት ሁለት ሳምንታት አማካኝነት የጾሙ ቀናት ቁጥር ከፍ ብሏል ማለት ነው። ልክ እንደ ላይኛው ሁሉ እነዚህንም ሁለት ሳምንታት ብናነሳቸው የምንጾመው 40 ቀናት ይሆናል ማለት ነው።
በአጠቃላይ የዐቢይ ጾምን 55 ቀን አድርገን የምንጾመው ከላይ ባየናቸው ምክንያቶች ነው።

       
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን ለአባታችን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ዓመታዊ የእረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።🌸

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

ዘወረደ


በዚህ ሳምንት የቃል ርደት፣ የወልድ ልደት፣ የአዳም ድኅነት ቢነገርም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ፣ በክብር ያረገ በኩረ ትንሣኤ መሆኑ አይዘነጋም፡። ለዚህም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም። በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ፥ በሰማይ ያለውን ብነግራችሁ እንዴት ታምኑኛላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው። ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለው የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዳይጠፋ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶታልና” እንዳለ እርሱ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ነው። (ዮሐ.፫፥፲፩-፲፮)  “ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ” ስለ ፍቅሩ በፈጠረው የተጠመቀ ሰማያዊ ነው።

ጾመ ድጓው የሚጀምረውም እንዲህ በማለት ነው፤ “ዘወረደ እምላዕሉ፣ አይሁድ ሰቀሉ…. እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ፤ ….በቃሉ የሚያድነውን ከላይ የወረደውን የሁሉን ጌታ አይሁድ ሰቀሉት…”

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ እንኳን አደረስዎ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የነነዌ ሰዎችና እኛ

ከነነዌ ሰዎች በላይ ማን ክፉ ነበር? ከእነርሱ በላይ አላዋቂስ ማን ነበር? ("ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ" ተብለው ተጠርተዋልና፡፡) ነገር ግን እነዚህ አሕዛብ፣ እነዚህ አላዋቂ፣ እነዚህ አንድ ሰውስ እንኳን የጥበብን ነገር አስተምሮአቸው የማያውቁ፣ እነዚህ ከማንም ይኹን ከማን እንደዚህ ዓይነት ትእዛዝን ያልተቀበሉ ሰዎች ነቢዩ፡- “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” ሲል በሰሙት ጊዜ ክፉ ልማዳቸውን ኹሉ በሦስት ቀናት ውስጥ አስወግደዋል (ዮና.3፥4)፡፡

ዘማዊው ንጹህ፣ ደፋሩ ትሑት፣ ስስታሙና ጨቋኙ ራሱን የሚገዛና ደገኛ፣ ሐኬተኛውም ትጉህ ኾነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ያሻሻሉት ክፋታቸውን ኹሉ እንጂ አንዱን ወይም ኹለቱን ወይም ሦስቱን ወይም አራቱን አይደለም፡፡ “እንዲህ የሚልስ የት አለ?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነርሱን ሲወቅሳቸው የነበረውና፣ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” ብሎ የተናገረው ነቢይ መልሶ ደግሞ የዚሁ ፍጹም ተቃራኒ የኾነን ምስክርነት አስቀምጧልና፤ እንዲህ ሲል፡- “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ” (ዮና.1፡5፣ 3፡10)፡፡ ተመልከት! ከዝሙት ወይም ከአመንዝራነት ወይም ከሌብነት ራቁ አላለም፤ “ከክፉ መንገዳቸው” እንጂ፡፡ እንዴትስ ከዚያ ሊርቁ ቻሉ? ይህን እግዚአብሔር ያውቋል እንጂ ሰው ሊመረምረው አይችልም፡፡

እንግዲህ አሕዛብ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ክፋታቸውን ኹሉ ማስወገድ ከቻሉ፥ ለአያሌ ቀናት የተመከርንና የተዘከርን እኛ ግን አንዲት ክፉ ልማድን [ለምሳሌ መሐላን] ሳናስወግድ ስንቀር ልናፍር አይገባንምን? ከዚህም በላይ እነዚህ ሰዎች ቀድሞ ክፋታቸው ጣሪያ ደርሶ ነበር፤ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” የሚለውን ስትሰማ ከክፋታቸው ብዛት በቀር ሌላ ምንም ልትገነዘብ አትችልምና፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መልካም ምግባር ፍጽምና መድረስ ተችሏቸዋል፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለበት ቀናት ወይም የጊዜ ብዛት አያስፈልግምና፡፡ በተቃራኒው ይህ ፍርሐት በሌለበት ደግሞ የጊዜ ብዛት ምንም ጥቅም የለውም፡፡

የዛጉ ብረቶችን በውኃ ብቻ የሚያጥባቸው ሰው ምንም ያህል ጊዜ እነርሱን በማጠብ ቢያሳልፍም እነዚያን ዝገቶች ኹሉ ማስለቀቅ አይቻለውም፡፡ ወደ እሳት ጨምሮ የሚያወጣቸው ሰው ግን አዲስ ከተሠሩ ብረቶችም ጭምር ሳይቀር እጅግ ጽሩያን ያደርጋቸዋል፡፡ በኃጢአት የዛገ ልብም እንዲሁ በትንሽ በትንሹና በግድየለሽነት ኾኖ ዕለት ዕለት ንስሐ ቢገባም ምንም ጥቅም አያገኝም፡፡ ራሱን ወደ እቶን - ይኸውም ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሚጥል ከኾነ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ኹሉንም ማስወገድ ይቻለዋል፡፡

(በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፥ ፳:፳፩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እግዚአብሔር የረሳን ለምን ይመስለናል?
....እኛ ስለምንረሳው...

.... ከላይኛው የቀጠለ
ጥያቄ:- ስለ ምን ጦምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም?
መልስ:- እነሆ፥ በጦማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ። እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጦማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
እኔ የመረጥሁት ጦም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጦም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
እኔስ የመረጥሁት ጦም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። (ኢሳ 58÷3-8)

እግዚአብሔር ፍጥረቱን ዘንግቶ ሳይሆን ፍጥረት እግዚአብሔርን ሲዘነጋው እግዚአብሔር ረሳኝ ይላል። እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ፈቃዱን ማግኘት ማለት ነው። እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ፈቃዱን ማግኘት ከሆነ ፈቃዱን ለማግኘት መጀመሪያ የማይፈቅደውን ለይቶ መተው ይገባል። እግዚአብሔር የሚፈቅደውን ነገር በማይፈቅደው መንገድ የቀረበ እንደሆነ አሁንም ረስተናል ማለት ነው።

አንድ ሰው ማር ይወዳል እንበል የሚወደውን ማር በሬት ለውሰን ከሰጠነው የሚወደውን በማይወደው መንገድ ሰጠነው ማለት ነው። ይደሰት ዘንድ ወይን ለሚወድ ሰው በመርዝ ዕቃ የሰጠነው እንደሆነ ደስታውን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱንም ነጠቅነው ማለት ነው።
ለፍጡር እንዲህ ማድረግ መልካም ካልሆነ ለፈጣሪማ እንዴት?

እግዚአብሔር ጦም ይወዳል፤ ጦሙ ግን ግፍ፣ ዓመጻ፣ ዝርፊያ፣ ዝሙት፣ ደም ማፍሰስ፣ ዘፈን፣ ድልቂያ፣ ግፍን በተመላ ሥጋ ካቀረብነው ፈቃዱን በማይፈቅደው ተቃወምነው ማለት ነው። እግዚአብሔር ምጽዋት ይወዳል፤ ምጽዋቱ ግን ተዘርፎ የተሰጠ ከሆነ ማሩን በሬት አቀረብነው ማለት ነው። እግዚአብሔር ጸሎት ይወዳል፤ ጸሎቱ ቂም ቋጥሮ ከሆነ መድኃኒቱን በመርዝ አቀረብነው ማለት ነው። እየቀማ ቢጦም ቆጠበ እንጂ ጦመ አይባልም ስለዚህ ፈቃደ እግዚአብሔር ኂሩት፣ ቸርነት፣ ምሕረት፣ ፍቅር፣ ሰላም፣ ምጽዋት፣ ልግስና፣ ሃይማኖት፣ ጽድቅ ማለት ነው።

"ለምን ረሳኸኝ?" ላሉት እርሱ የመለሰው "መቼ ጠራችሁኝ?" ነው ያላቸው። ከላይ የዘረዘርናቸውን የጽድቅ ተግባራት ከዘረዘረ በኋላ "ያንጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል" ነበር ያለው። ይህ ማለት እግዚአብሔርን የምንጠራባቸው ሁለቱ አንደበቶች ንጽሕናና ምግባረ ሠናይ ናቸው ማለት ነው።

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! አንተ የረሳኸውን አስታውስ እንጂ እግዚአብሔር ረሳኝ አትበል። ስትጸልይ ቂም መያዝህን ረስተህ እንደሆነ፣ ስትሰጥ ሰርቀህ እንደሆነ፣ ስትጦም ደም አፍስሰህ፣ ስትዘምር እየዘፈንህ እንደሆነ የረሳኸውን አስታውስ።

ለ. መከራ ሲጸና እግዚአብሔር የረሳቸው የሚመስላቸው እንዳሉ ቅዱስ ጳውሎስ በራሱ አስመስሎ እንዲህ ሲል ገልጦታል:-

ይቀጥላል....

ከጸያሔ ፍኖት (በአባ ገብረ ኪዳን) ገጽ 70-71
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እግዚአብሔር የረሳን ለምን ይመስለናል?
1. እኛ ስለምንረሳው
    የመከራ ጽናት የዘመን ብዛት እግዚአብሔር ረስቶኛል ብቻ ሳይሆን (ሎቱ ስብሐት) እግዚአብሔር የለምም ያስብላል። የሰው ልጅ መከራው ጽኑ በሆነ ጊዜ፣ ዘመን በራቀበት ጊዜ፣ ለጥያቄው መልስ ባጣ ጊዜ በእነዚህ በሦስቱ በሃይማኖት እንቅፋት ይገጥመዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ረስቶኛል፣ አይወደኝም ይልና ቀቢጸ ተስፋ ላይ ሲደርስ ደግሞ እግዚአብሔር ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርማ ማለት ይጀምራል። በመጨረሻም የለም ብሎ ይክዳል።
     ሰይጣን ሰውን ወደ ምንፍቅና ወደ ክህደት የሚወስድባቸው 3ቱን መንገዶች መጠንቀቅ ይገባል። ይህንን ይበልጥ ለመረዳትም የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳቦችን እንመልከት:-
👉ሀ. "ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተን አላወቅህም?" (ኢሳ58÷3)
    እዚህ ላይ ጹመው ለጥያቄያቸው ምላሽ በማጣታቸው እግዚአብሔርን አልተመለከትከንም፣ አላወቅኸንም እስከማለት ደርሰው ነበር። "የእግዚአብሔር ዓይኖች ምን ሆነው አልተመለከቱም?፣ አይወሰኑ ምሉዓን፣ አይሞቱ ሕያዋን፣ አያዳሉ ጻድቃን ናቸው። ታዲያ ለምን አልተመለከትከንም አሉ?" ብንል መልሱ "ጥያቄያቸው ባለመመለሱ እግዚአብሔር የተዋቸው የገፋቸው የረሳቸው መስሏቸዋል" የሚል ይሆናል።
     የፈለጉትን በማጣታቸው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እግዚአብሔር የሌለ እየመሰላቸው ወዲያ ወዲህ የሚቅበዘበዙ ወገኖች በዚህ ዘመንም አይታጡም። ግን እግዚአብሔር አላይ ብሎ ሳይሆን እኛ አንታይም አትየን ብለነው ነው። "ገዳም ሄድኩ፣ ንስሐ ገባሁ፣ እጸልያለሁ፣ እጦማለሁ፣ በቅዱሳን አምናለሁ፣ እቆርባለሁ ነገር ግን እስከዛሬ ከነበርኩበት ነኝ ምን ይሻለኛል?" የሚሉ ብዙዎች ናቸው። መልሱን ለእነዚህ ጦመኞች የመለሰውን እንስማ!
    "በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትቾላለችን? አዎ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም" ይላል (ኢሳ 49÷15)። እናት 9 ወር ፀንሳ፣ ከደምዋ ተከፍሎ፣ በምጥ በፃዕር በጭንቅ የወለደችውን፣ 3 ዓመት ያጠባችውን፣ ሁሉን ታግሳ በንጽሕና ያሳደገችውን ልጇን ትረሳለችን? አትረሳም። ዳሩ ግን ቢያንስ ሙቶ እንኳን አልቅሳ አልቅሳ ስታንቀላፋ በዕለቱም ቢሆን ትረሳለች። እግዚአብሔር ግን ይህ ሁሉ በባሕርዩ የለበትምና አይረሳም። "እንግዲያውስ ስለምን አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተም አላወቅኸንም?

ጥያቄ:- ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተም አላወቅኸንም?

መልስ.......
                          ይቀጥላል
ከጸያሔ ፍኖት (በአባ ገብረ ኪዳን) ከገጽ 68-69 የተወሰደ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

“ብዙ እናቶች ስቃይ ካለበት የወሊድ ሰዓት በኋላ ልጆቻቸውን ሌሎች እንዲመግቡላቸው ለእንግዶች ይሰጣሉ። ክርስቶስ ግን እኛ ልጆቹን በብዙ መከራ እና ስቃይ በመስቀል ላይ ከወለደን በኋላ ሌሎች እስኪመገቡን ድረስ አይተወንም። በገዛ ሥጋ እና ደሙ እየመገበ ራሱ ያሳድገናል። በዚህ ሁሉ መንገድም ከራሱ ጋር አንድ ያደርገናል።”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ስለዚህ ከሥጋውና ደሙ ርቃ በኃጢአት በበደል ተይዛ ተርባ ያለች ነብሳችንን ንስሐ ገብተን ከኃጢአታችን ታጥበን ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን እናጠግባት ከክርስቶስ ጋር አንድነትን እናደርግላት ።

ዲን እስራኤል

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ስደክም_ያን_ጊዜ_ኃይለኛ_ነኝና»

ድካም ለሃይማኖት ጌጥ ነው፡፡
ድካሞ ለእምነት ኃይል ነው፡፡
ድካም ለእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፡፡
ድካም ለነፍስ ዋጋ የመስጠት ማሳያ ነው፡፡ ድካም ዓለምንና ኃጢአቷን የመናቅ ውጤት ነው፡፡
ድካም የልምድ እስራትን የመበጠሻ መጋዝ ነው፡፡
ድካም መንፈሳዊ ለውጥን የማምጫ የከፍታዎች ደረጃ ነው፡፡
"ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፥10)

"ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና፡፡" የቃሉን እውነት ከኛ ውስጥ ገልብጦ የሚመራን ዲያቢሎስ ደግሞ፤ "ሳልደከም ያን ጊዜ ልፍስፍስ ነኝና" የሚል ኑሮን ሊያሰለጥነን ስለ ሃይማኖት መድከምን የሚጠየፍ አመለካከትና ተክለ ቁመና ሲቀርጽልን፤ ስንድከም የበለጠ የምንደክም እየመሰለን ከበረከት ተልፈስፍሰን፣
ከጸጋ ተልፈስፍሰን፣ ከመገለጥ ተልፈስፍሰን፣ ከእምነት መፍትሔ ተልፈስፍሰን፣ ከራእይ ተልፈስፍሰን ይኸውና ሁሌ ድካም ያልተለየው ደካማ ጊዜን እንገፋለን፡፡

ሰው በሠራው ልክ ደመወዙን እንደሚቀበል በመንፈሳዊው ሕይወትም እንዲሁ ነው፡፡ እስከ አቅማችን እውነተኛው ጥግ መንፈሳዊ ጠባያችንንና ሥራችንን ቅዱስ ለማድረግ በደከምንበት ልክ፤ እግዚአብሔር ዋጋችንን ይሰጣል፡፡

ስለዚህሳ? "ስለዚህማ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና" እያልን ስለ መንፈሳዊ ብርታት መድከም ኃይል እንደሆነ ልናውቅና ልንኖርበት ይገባናል፡፡



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ልክ በዛሬዋ ቀን ነበር
ዛሬ አመት ሆናችሁ
ጥቁር የለበስንበት ቀን
ወጣቶች በግፍ የተረሸኑት
ልክ የዛሬዋ ቀን ነበር በቤተ ክርስትያን ቅጥር ውስጥ የደም ጅረት የፈሰሰበት
ልክ የዛሬዋ ቀን ነበር ምዕመናን የተጋደሉላት
ልክ በዛሬዋ ቀን ነው የወጣቶቹ ደም የተገበረው
ልክ በዛሬዋ ቀን ነው የጥይት ዝናብ የዘነበባቸው
ልክ የዛሬዋ ቀን ነበር ህገወጦቹ የተዘባበቱበት በደማችሁ
ልክ በዛሬዋ ቀን ነው ሰማዕትነት የተቀበላችሁት

እናንተ በጥይት ደማችሁ ሲፈስ እኔ ግን ዛሬ ላይ ቁሜ ልቤተ ክርስትያን ሸክም ሆንኩባት በእናንተ ሞት በእናንተ ደም ቤተ ክርስትያን ታጠበች ከበረክ አፅዷን በደማችሁ ጠበቃችሁላት በሞታችሁ አገበራችኋት ምንም የምናገረው የለኝም ግን የእናንተ ሞት መከራዋ ህመሟ ይቆማል ብዬ አስቤ ነበር ያልጠርጥር እራሳችሁን አሳልፋችሁ ስለሰጣችሁ ግን አልቆመም እንደውም ብሷል ወንድሞቼ ብቻ ከአምላካችን አሳስቡልን እየሆነ ያለውን ።

ቤተ ክርስትያን መቼም አረሳችሁም
ተዋህዶ መቼም አረሳችሁም
ሁሌም እናንተን ስናስብ እና ስንዘክር እንኖራለን😭😭😭😭
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ነፍስ ይማር ጥር 27/2016
/channel/MoaeTewahedoB

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፲
የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ
አንዳንዶች ሰውነቱን ብቻ አይተው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) ይመስላቸዋል። አንዳንዶች ደግሞ አምላክነቱን ብቻ አይተው ሰውነቱን ይዘነጉታል። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነ አምላክ፣ አምላክ የሆነ ሰው ነው። አምላክም ሰውም የሆነ አንድ ልጅ (ወልድ ዋሕድ) ነው።

ሰው እንደመሆኑ በየጥቂቱ አደገ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ስለእኛ መከራን ተቀበለ። አምላክ እንደመሆኑም የተራቡትን አጠገበ። ከኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ ሁሉ ሠራ። በዚህም ሰውን አዳነ። ወንጌላዊው ሉቃስ የኢየሱስ ክርስቶስን የትውልድ ሐረግ ሲገልጽ "የእግዚአብሔር ልጅ የአዳም ልጅ" ብሎ ይናገራል (ሉቃ. ፫፣፴፰)። ሙስሊሞች አምላክ አይወልድም አይወለድም ብለው ይናገራሉ። ነገር ግን ይህ እግዚአብሔር የሆነውን ሳይሆን እንዲሆን የሚፈልጉትን ሐሳብ የሚያንጸባርቁበት ንግግር ነው። ቁርኣን ከመጻፉ በፊት የነበሩ የነቢያትና የሐዋርያት መጻሕፍት የሚናገሩት እግዚአብሔር ወልድ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ መሆኑን ነውና። "ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድኩህ" እንዲል (መዝ. ፻፱፣፫)። እንግዲህ አላህ በቁርኣን ወንጌልንም ኦሪትንም ለዒሣ ገለጥኩ ብሎ ከተናገረ ወንጌልም ኦሪትም የአብ አንድ ልጅ ወልድ እንዳለው ይናገራሉ። ስለዚህ በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ማመን ይገባቸው ነበር።

የሃይማኖት ትምህርት በነጻነት የሚማሩት ነው። ስለዚህ ኅሊናን ነጻ አድርጎ፣ እውነታውን እየመረመሩ መረዳት አስፈላጊ ነው። ስለሆነም ፕሮቴስታንቶችም፣ ሙስሊሞችም፣ ቅባቶችም፣ ካቶሊኮችም፣ ሃይማኖት አልባዎችም ካላችሁ በነጻነት መነጋገር እንችላለን። ኑ።

© በትረማርያም አበባው

/channel/dnhayilemikael
ክፍል ፲፩ ይቀጥላል

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፰
በሥላሴ ዘንድ ያለው አካላዊ ግብር የሚከተለው ነው። የአብ መውለድ ማሥረጽ፣ የወልድ መወለድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ደግሞ መሥረጽ ነው። ከዚህ ውጭ መቅባት፣ መቀባት፣ ቅብዕ መሆን የሚል አካላዊ ግብር የለም።

ለግብረ ባሕርይ የተነገረውን ለግብረ አካል፣ ለግብረ አካል የተነገረውን ለግብረ ባሕርይ አድርገው ከተናገሩት ትልቅ ተፋልሶን ያመጣል። በግብረ አካል ሕይወትነት በተለየ የመንፈስቅዱስ ነው። በግብረ ባሕርይ ሲነገር ግን ሦስቱ አንድ የሚሆኑበት አፍኣዊ ግብር ነው። ይህ በሦስቱ ኵነታት ተገናዝቦ የሚገኝ ሕይወትነት ነው እንጂ ከሦስቱ ኵነታት አንዱ አይደለም። ለምሳሌ በሃይማኖተ አበው "አብ ሕይወት፣ ወልድ ሕይወት፣ መንፈስቅዱስ ሕይወት" ሲል ይገኛል። ይህ ሕይወትነት ሦስቱ አካላት አንድ የሚሆኑበት ሕይወትነት ነው እንጂ በግብረ አካል የተጠቀሰው እስትንፋስነት (ሕይወትነት) አይደለም። ምክንያቱም ሦስቱም አካላት በየአካላቸው ጸንተው የሚኖሩ ስለሆነ አብ መንፈስቅዱስን፣ መንፈስ ቅዱስም አብን አይሆኑምና ነው።

በግብረ ባሕርይ አብን አባታችን እንደምንለው ሁሉ ወልድንም አባታችን ሆይ እንለዋለን። እኛን በመንፈሳዊ ልደት መውለድ የአብም፣ የወልድም፣ የመንፈስ ቅዱስም (ሦስቱም አንድ የሚሆኑበት) ሥራ ነው። በዚህኛው ግብረ ባሕርይ አብንም ወልድንም መንፈስቅዱስንም ወላዲ ወላዲ ወላዲ ልንላቸው እንችላለን። በግብረ አካል ወላዲ የሚባል ግን አብ ብቻ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። ለግብረ ባሕርይ የተነገረውን ለግብረ አካል፣ ለግብረ አካል የተነገረውን ለግብረ ባሕርይ መናገር አይገባም ያልነው ይህ ነው።

አፍቀርከ ጽድቀ ወዐመፃ ጸላእከ ወበእንተዝ ቀብዐከ እግዚአብሔር ቅብዐ ትፍሥሕት እምእለ ከማከ ብሎ ቅዱስ ዳዊት የተናገረው በመቅባት ሦስቱም አካላት አንድ ስለሆኑ ስለሦስቱም የተነገረ ቃል ነው። እለ ከማከ ተብለው ("እለ" የሚለው አገባብ በቂ ሆኖ ማለት ነው) ከተገለጹት ነቢያት የሚበልጥ ቅብዐ ትፍሥሕትን ቀባህ ተብሏል። ቅብዐ ትፍሥሕት ክብር ነው። የነቢያት ክብር የጸጋ ክብር ነው። አምላክ የተባሉ ነቢያት እንኳ ቢኖሩ አምላክነታቸው፣ ክብራቸው የጸጋ ነው። ረሰይኩከ አምላኮ ለፈርዖን እንዲል። ሥጋ አምላክነትን (ክብርን) ገንዘብ ያደረገው ግን በጸጋ ሳይሆን በባሕርይ በተዋሕዶ ነው።


/channel/dnhayilemikael
ክፍል ፱ ይቀጥላል

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፮
ኢየሱስ ክርስቶስ በአደገባት ከተማ ምክንያት ናዝራዊ እየተባለ ይጠራል። ማቴ. ፪፣፳፫ "በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደ ምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ" እንዲል። ክርስቶስ በቤተልሔም እንደተወለደ ዕለቱን በአንድ ጊዜ ልደግ አላለም። ሰው እንደመሆኑ እንደሰው በየጥቂቱ አደገ። በበሕቅ ልሕቀ እንዲል። ሥጋ መቼም ቃልን ተዋሕጃለሁ ብሎ በአንድ ጊዜ የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ልሁን አላለም።

ክርስቶስ በሥጋ በቤተልሔም ተወልዶ በናዝሬት አደገ። መድኃኒትነቱ ግን ለዓለም ሁሉ ስለሆነ መድኃኔዓለም እየተባለ ይጠራል። ካህናትም በእርሱ የተሾሙ እርሱን የሚያገለግሉ ስለሆኑ ለሰው ልጅ ሁሉ እኩል ያስባሉ። ለሁሉም ጸሎትን ያቀርባሉ። በብሉይ ኪዳን ናዝራውያን የሚባሉት ለእግዚአብሔር ራሳቸውን የተለየ የሚያደርጉ ሰዎች ነበሩ (ዘኍ. ፮፣፪)። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ክርስቶድ ናዝራዊ እንደተባለ ሁሉ በጥምቀት ተወልደን ከዓለም ተለይተን ውሉደ እግዚአብሔር የሆንን እኛ ክርስቲያኖች ናዝራውያን እንባላለን።

/channel/dnhayilemikael።

Читать полностью…
Subscribe to a channel