dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ተራ የማይደርሰው ተጠማቂ +

"ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው ሰውዬውም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፡ ብሎ መለሰለት" ዮሐ.5:5-7

ይህንን ጥያቄና መልስ ሳይ በሽተኛውን ማናገር ያምረኝና እንዲህ በል ይለኛል :-

አንተ በሽተኛ ግድ የለህም የተጠየቅከውን ብቻ መልስ:: እመነኝ ጠያቂህ ተራ ጠያቂ አይደለም:: የሚጠይቅህ ሲያደርቁህ እንደኖሩት ሌሎች አሰልቺ ጠያቂዎች አይደለም:: ጥያቄውም የሌሎችን ሰዎች ዓይነት ጥያቄ አይደለም:: ከፊትህ የቆመው የመጠመቂያውን ውኃ ብቻ ሳይሆን በዓለም የሞላውን ውኃ የፈጠረ አምላክ ነው::

"ወደ መጠመቂያው የሚያኖረኝ ሰው የለኝም" አልክን? የተጠየቅከውን መልስ እንጂ! ወደ መጠመቂያው መግባት ትወድዳለህን? ብሎ ማን ጠየቀህ? የጠየቀህ ማን እንደሆነ ባታውቅ እንኩዋን ጥያቄውን እንኳን በደንብ ስማ እንጂ!

ሰው የለኝም አትበለው : ስለመጠመቂያው ወረፋ አትንገረው : ስንት ሰው ቀድሞህ እንደዳነ አትቁጠርለት:: የጠየቀህ ግልፅ ጥያቄ ነው::

ልትድን ትወዳለህን?

እግዚአብሔር ፊት ስለ ችግርህ ክብደት ለምን ታወራለህ? ምን እንደሌለህማ እሱም ያውቃል:: አዎን እድን ዘንድ በለው:: ችግርህን ትተህ የምትፈልገውን ንገረው:: የችግርህ መወሳሰብና ሥር መስደድ ለእሱ የሚከብድ አይደለምና መዳን እንደምትሻ ብቻ በእምነት ንገረው የሚል ተግሣፅ በበሽተኛው በኩል ወደ እኛ ደረሰ::

🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌

መጻጉዕ (በሽተኛው) ቤተ ሳይዳ ከመጣ 38 ዓመት ሆነው:: ዳዊትና ሰሎሞን 40 40 ዓመት ነግሠው እንኳን ብዙ የምሬት ቅኔ ተቀኝተዋል:: ይህ ሰው አልጋ ላይ ሆኖ አርባ ዓመት ሊሞላው ሲል ምንኛ ተንገሽግሾ ይሆን?

ልብ በሉ ጌታችን በቤተልሔም ሲወለድ ይህ በሽተኛ በአልጋው ላይ ነበረ:: እረኞች ከብዙ መላእክት ጋር ሲዘምሩ እሱ የአንድን መልአክ መውረድና ውኃውን ማናወጥ እየጠበቀ ስድስተኛ ዓመቱን ደፍኖ ነበር:: ጌታችን የሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ ላይ ደርሶ ወደ መጠመቂያው ሥፍራ ሲመጣም ይህ ሰው አልጋው ላይ ነው:: መጠመቂያዋን 38 ዓመት በተስፋ ሲጠብቅ ቆይቶ ሳይጠመቅባት ቀረ::

ጌታ ሆይ የማይደርሰኝን ወረፋ ከመጠበቅ አድነኝ:: እንድፈወስበት ባልፈቀድክበት ሥፍራ ዕድሜዬን እንዳልጨርስ ጠብቀኝ::

ወደ ሐዲስ ኪዳንዋ ቤተ ሳይዳ ወደ ቤተክርስቲያን ከመጣሁ ብዙ ዘመን አስቆጠርኩኝ:: ግን እስካሁንም ድረስ ከኃጢአት አልጋ ላይ አልወረድሁም:: መነሣት እፈልጋለሁ ግን አቃተኝ:: ልቤ እንጂ እግሬ ጸንቶ መቆም አልቻለም::

ፈረቃ የሌለብህን የሕይወት ውኃ አንተን ሊጠጡ ሲመጡ በዓይኔ እየተቀበልኩ ብዙዎች ጠጥተውህ ሲድኑ በዓይኔ እየሸኘሁ አልጋዬ ላይ ቀረሁ::

እኔ እንደተኛሁ ስንቱ ቀድሞኝ እንደዳነ ባየህልኝ:: ከእኔ በኁዋላ መጥተውስ ከእኔ በፊት ስንቶች ዳኑ?
ስንቱ ከኃጢአት አልጋ በንስሓ ተነሥቶ ያንተን ሥጋና ደም ተቀብሎ ተፈወሰ?

የቤተ ሳይዳው ሐኪም ሆይ ወደ አንጋፋው በሽተኛህ ወደ ጽኑዕ ሕመምተኛህ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ይሆን? ያን ሕመምተኛ "ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደነበረ" አውቀህ ያናገርከው ሆይ እኔን የምታናግረኝ መቼ ይሆን? እኔስ ብዙ ዘመን እንደሆነኝ አታውቅምን? ሰው የለኝም : ልብ የለኝም : ኃይል የለኝም : አቅም የለኝም ብዬ ብሶቴን የምነግርህ መቼ ይሆን?

"ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ" ዮሐ.5:8-9

አንተ ተነሥ ብለኸው የማይነሣ ማን ነው? እንኳንስ ከአልጋ ከመቃብርም ተነሥ ያልከው ይነሣ የለምን?
ግዴለህም እኔንም ተነሥ በለኝ:: ተነሥ ኃይልን ልበስ ያልከኝ እንደሆነ እንኳንስ "ሸክሜም ቀሊል ነው" ያልከው አንተ ያዘዝከኝ የራሴን ሸክም ቀርቶ የወንድሜን ሸክምም ተሸክሜ የአንተን ሕግ እፈጽማለሁ:: (ገላ. 6:2)

🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌

"ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ... ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ፡ አለው" ይላል::

በሽተኛው ድኖ አልጋውን ተሸክሞ እንደሔደ ሳነብ አንድ ነገር ልቤን አስጨነቀው:: ይህ ሰውዬ 38 ዓመት ሙሉ የኖረው በቤተ ሳይዳ ነው:: ክርስቶስ ድንገት ፈውሶት ሒድ ሲለው እሺ ብሎ ከዚያ መጠመቂያ ሥፍራ ከወጣ በኁዋላ ወዴት ሔደ?

የሠላሳ ስምንት ዓመት ሕመምተኛው ሆይ እውነት ወዴት ሔድህ? ከመጠመቂያው መውጣትህን ሰምተን አድንቀናል:: ከዚያስ ወዴት ሔድክ? ዙሪያ ገባው አልተለወጠብህም? መንገድስ አልጠፋብህም?
ወደ ዘመዶች ቤት ሔድክ እንዳልል "ሰው የለኝም" ስትል ሰምቼሃለሁ::

አልጋህንስ የት አደረስካት? መቼም ሰባብረህ እንደማትጥላት የታወቀ ነው:: አልጋ ለታመመ ብቻ ሳይሆን ለጤነኛም ያስፈልጋልና አራት እግር እያላት ጥላህ ያልሔደችውን ዘመድህን መቼም በክብር ማስቀመጥህ አይቀርም::

ለማንኛውም እዚያው ምዕራፍ ላይ ኢየሱስ ይህንን በሽተኛ ዳግም በመቅደስ አገኘው ይላል:: ዮሐ. 5:14 ጌታ ከመጠመቂያ ቦታ አድኖ ያስነሣውን ሰው በመቅደስ ቆሞ አገኘው:: ይህ በሽተኛ እግሩ ሲጸናለት የሔደው ወደ ፈጣሪ ደጅ መሆኑ ያስመሰግነዋል::

ጌታ በመጠጥ ቤት ቢያገኘው ኖሮ ያሳዝን ነበር:: እግርህን ያጸናሁልህ ለዚህ ነው ወይ ብሎ ባዘነበት ነበር:: አሁን ግን ያዳነው ጌታ በመቅደስ አግኝቶት "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" አለው::

ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ክርስቶስ አንተንስ አላዳነህም? "ኸረ እኔ ሽባ ሆኜ አላውቅም:: ማንም እኔን ከአልጋ አላስነሣኝም ትለኝ እንደሆን እመነኝ ክርስቶስ እንደ አንተ ያዳነውስ የለም:: እርሱ እኔና አንተን ተነሡ ብሎ ያስነሣን ከ38 ሳይሆን ከዘላለም የሲኦልና የኃጢአት አልጋ ነው::

እኛን የፈወሰን አልጋችንን አሸክሞ ሳይሆን እሱ ራሱ እኛን ከነአልጋችን ተሸክሞን ነው:: ካላመንከኝ ነቢዩ ኢሳይያስን ጠይቀው "እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ" ሲልህ ትሰማዋለህ:: ኢሳ. 53:12 የእኛን በደል ተሸክሞ ጀርባው ምን ያህል እንደ ቆሰለ ባየህ:: ይህንስ ጀርባዬን ታያለህ የተባለውን ሙሴን ብትጠይቀው ሳይሻል አይቀርም::

ያዳነህ አምላክ አንተንስ የት ነው የሚያገኝህ? እንደዚህ ሰውዬ መቅደስ ያገኝህ ይሆን?

የትም ቢያገኝህ ግን ቃሉ አንድ ነው "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" ከሠላሳ ስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኝነት የሚብስ ምን ሊመጣ ነው? ካልክስ እሱን ከማየት ይሠውረኝ ብትል ይሻልሃል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 10 2014 ዓ.ም. ተጻፈ
ባሕር ዳር ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ክርስቲያን ነህ?

ወዳጄ ሆይ !
እንኪያስ ክርስቶስ የሰጠህን ስጦታ ላልተፈለገ ግብር (ሥራ ) አታውለው

💠እጅን የሰጠህ እንድትሰርቅበት ሳይሆን
ትእዛዛቱን እንድትፈጽምበት :
በጎ ምግባርን እንድትሠራበት
ለጸሎት እንድትነሳበት
የወደቁትን እንድታነሣበት ነው ።

ጆሮን የሰጠህ ተርታ ወሬ እንድትማበት ሳይሆን
ቃሉን እንድታዳምጥበት ነው

አንደበትን የሰጠህ እንድትሰድብበትና እንድትረግምበት ሳይሆን
እንድትዘምርበት
እንድታመሰግንበት
እንድትመክርበት ነው።

እግርን የሰጠህ ወደ ክፋት ሳይሆን
ወደ በጎ ሥራ እንድትፋጠንበት ነው ።

ሆድን የሰጠህ ለመብል ሳይሆን ጥበብን እንድትማርበት ነው ።

ፈቲውን የሰጠህ እንድታመነዝርበትና እንድትዳራበት ሳይሆን ልጆችን ትወልድበት ዘንድ ነው ።


ልቡናን የሰጠህ ሰዎችን እንድትወቅስበት ሳይሆን
እውነትን ታውቅበት ዘንድ ነው ።

ገንዘብና ጉልበትን የሰጠን
ሰማያዊ ቤታችንን እንድንሠራበት ነው

እንኪያስ የክርስቶስን ስጦታ በአግባቡ ተጠቀምበት


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቂ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እየጦሙ አለመጦም


ተወዳጆች ሆይ ! እየጦሙ የጦምን ፍሬ ጻማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ

ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም :-

💠ከምግበ ሥጋ ተከልክለው ሳለ ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደሆነ

💠ከጥሉላት ርቀን ሳለ ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ

💠ወይን ከመጠጣት ታቅበን ሳለ በክፋ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ

💠ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን ሳለ በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትእይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደ ሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለሁ ።

✝️ስለዚህም እየጦሙ አለመጦም እንዳለ እወቁ : ተረዱም።


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

                        †                        

          🕊   [    ጾም   ]    🕊

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

       [       ሦስት ነገሮችን !       ]

" በጾም ሰዓታችሁ ጊዜም ይኹን በሌላ ጊዜ ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እንመክራችኋለን፡፡

እነርሱም ክፉ ከመናገር መከልከልንማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና እንደልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ !

በአጨዳ ላይ ያለ ገበሬ እህሉን ከማሳው በአንዴ እንደማይሰበስብ ነገር ግን በጥቂት በጥቂቱ እንደሚሰበስብ ኹሉ እኛም እነዚህን ምክሮች ተግባራዊ በማድረግ በዚህ የጾም ወቅት ልንለማመዳቸው እና መልካም ልምዶቻችን ልናደርጋቸው ይገባናል፡፡

እንዲህ በማድረጋችንም በቀላሉ መንፈሳዊ ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ይቻለናል፡፡ በዚህም ዓለም ሳለን መልካም ተስፋ ያለውን አዝመራ እናፈራለን። በሚመጣውም ዓለም በክርስቶስ ፊት ያለፍርሐት በደስታ ተሞልተን እንድንቆም ይረዱናል፡፡ ለዚህ የሚያበቃንን ጸጋ አግኝተን የክብሩ ወራሾች ያድርገን፡፡ " †

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ልትረዳ የምትችለው ሁልጊዜ አንተ በምትፈልገው መንገድ ብቻ እንዲሠራ ባለመጠበቅ ነው። አንዳንዴ በአንተ እና በአምላክህ ሐሳብ መካከል የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ሊኖር ይችላል። ራሱ ባለቤቱም "ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው” ብሎናል።(ኢሳ 55፥9)

"ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ከጸለይህ በኋላ "የምትፈልገውን ብቻ በመጠባበቅ ፈጣሪህን የፈቃድህ አገልጋይ አታድርገው። በጸሎትህ አምላክ የሚወደውን ወይም ፈቃዱን ማወቅ ከፈለግህ "አንተ የምትወደውን እንደ ብቸኛ መልስ አትጠባበቅ።

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#10_የነፍስ_ጉርሻዎች_ከቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ



#አንድ
"ቃላቶችህ ምንም ያህል ትክክል ቢሆኑም በቁጣ ስትናገር ሁሉንም ነገር ታበላሻለህ።"


#ሁለት
"ብል ልብስን እንደሚበላው ሰውንም ቅናት ይበዋል።"


#ሶስት
"እግዚአብሔር የሚጠይቀው ጥቂት፣ የሚሰጠው ብዙ ነው"


#አራት
"እያንዳንዱ ሰው የህይወቱ ሠዓሊ እና ቀራፂ ነው።"


#አምስት
"ባለጠጋ ብዙ ያለው ሳይሆን ብዙ የሚሰጥ ነው።"


#ስድስት
“ምሕረት አምላክን ይመስላል ሰይጣንንም ያሳዝነዋል።"


#ሰባት
" ኃጢአት ስትሠራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አትፈር"


#ስምንት
"ለምን በትንንሽ ነገሮች መደሰትን አትማርም - በጣም ብዙ ናቸው።"


#ዘጠኝ
"ጸሎት የጭንቀት ሁሉ መሸሸጊያ፣የደስታ መሠረት፣ ከሐዘን መከለያ ናት። "


#አስር
"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ ባለው ነዳይ ውስጥ ማግኘት ካልቻላችሁ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ አታገኙትም።"

ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ


👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️═/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቃችንን እናረጋግጥ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳንሆን 👉በትምህርት_እንወቃት፤
እንደ ፈሪሳውያን እንዳንሆን👉 በኑሮ_እንወቃት።
ለሥርዓቷ ታማኝ እንሁን ፥
እኛ ወደ ሥርዓቷ እንደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ እኛ ፈቃድ እንዲወርድልን አንውደድ፤
ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልን አንፍቀድ። በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍን ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየን እንደሆነ እንወቅ። እነዚህም
👉ኪዳን ማስደረስ፥
👉ማስቀደስና
👉ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥
👉 በምህላ ጸሎቶቿ
👉 በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።
ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀን በየቀኑ ወደ እርስዋ እንገሥግሥ። በሕይወታችን ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ እንሁን!።
(ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ካስተማሩት!)

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ዐቢይ_ጾምን_ለምን_55_ቀን_እንጾማለን?

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይህንን የዐቢይን ጾም የቀናት ቁጥር 55 አድርገው ሲወስኑ ያለ አንዳች ምክንያት ሳይሆን በምስጢር ነው። ይሄውም እንዴት ነው ቢሉ ጾሙ 55 ቀን የሆነበት የመጀመረያው ምክንያት በነዚህ በሚጾሙት በ55ቱ ቀናት መሀከል (8 ቅዳሜና፣ 7 እሁዶች በአጠቃላይ 15 ሰንበታት) አሉና እነዚህ ሰንበታት ደግሞ ስለማይጾሙ እነርሱን ጌታችን ከጾማቸው ከ40ው ቀናት ጋር በመደመር 55 ቀናትን እንድንጾም አድርገውናል ።

ሌላውና የዐቢይ ጾምን 55 ቀን የምንጾምበት ሁለተኛው ምክንያት በጾሙ የመጀመሪያና የመጨረሻውን ሳምንታት በመቁጠር ነው። እነዚህ ሁለት ሳምንታት የመጀሪያው ሳምንት "#ጾመ_ሕርቃል" ሲሆን የመጨረሻው ሳምንት "#ሰሞነ_ሕማማት" ይባለል።

#ሕርቃል የአንድ ንጉሥ ስም ነው። ታሪኩ እንዲህ ነው በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺህ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺህ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገ*ደ*ለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡

በተመሳሳይ በዐቢይ ጾም ከሆሳዕና በኋላ ያለው የመጨረሻውን ሳምንት የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል የምናስብበት ጊዜ ነውና ሰሞነ ህማማት ተብሎ እንዲታወስና እንዲጾም አድርገዋል።

በእነዚህ ከፊትና ከኋላ በገቡት ሁለት ሳምንታት አማካኝነት የጾሙ ቀናት ቁጥር ከፍ ብሏል ማለት ነው። ልክ እንደ ላይኛው ሁሉ እነዚህንም ሁለት ሳምንታት ብናነሳቸው የምንጾመው 40 ቀናት ይሆናል ማለት ነው።
በአጠቃላይ የዐቢይ ጾምን 55 ቀን አድርገን የምንጾመው ከላይ ባየናቸው ምክንያቶች ነው።

       
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን ለአባታችን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ዓመታዊ የእረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።🌸

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

ዘወረደ


በዚህ ሳምንት የቃል ርደት፣ የወልድ ልደት፣ የአዳም ድኅነት ቢነገርም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ፣ በክብር ያረገ በኩረ ትንሣኤ መሆኑ አይዘነጋም፡። ለዚህም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም። በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ፥ በሰማይ ያለውን ብነግራችሁ እንዴት ታምኑኛላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው። ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለው የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዳይጠፋ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶታልና” እንዳለ እርሱ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ነው። (ዮሐ.፫፥፲፩-፲፮)  “ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ” ስለ ፍቅሩ በፈጠረው የተጠመቀ ሰማያዊ ነው።

ጾመ ድጓው የሚጀምረውም እንዲህ በማለት ነው፤ “ዘወረደ እምላዕሉ፣ አይሁድ ሰቀሉ…. እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ፤ ….በቃሉ የሚያድነውን ከላይ የወረደውን የሁሉን ጌታ አይሁድ ሰቀሉት…”

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ እንኳን አደረስዎ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የነነዌ ሰዎችና እኛ

ከነነዌ ሰዎች በላይ ማን ክፉ ነበር? ከእነርሱ በላይ አላዋቂስ ማን ነበር? ("ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ" ተብለው ተጠርተዋልና፡፡) ነገር ግን እነዚህ አሕዛብ፣ እነዚህ አላዋቂ፣ እነዚህ አንድ ሰውስ እንኳን የጥበብን ነገር አስተምሮአቸው የማያውቁ፣ እነዚህ ከማንም ይኹን ከማን እንደዚህ ዓይነት ትእዛዝን ያልተቀበሉ ሰዎች ነቢዩ፡- “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” ሲል በሰሙት ጊዜ ክፉ ልማዳቸውን ኹሉ በሦስት ቀናት ውስጥ አስወግደዋል (ዮና.3፥4)፡፡

ዘማዊው ንጹህ፣ ደፋሩ ትሑት፣ ስስታሙና ጨቋኙ ራሱን የሚገዛና ደገኛ፣ ሐኬተኛውም ትጉህ ኾነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ያሻሻሉት ክፋታቸውን ኹሉ እንጂ አንዱን ወይም ኹለቱን ወይም ሦስቱን ወይም አራቱን አይደለም፡፡ “እንዲህ የሚልስ የት አለ?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነርሱን ሲወቅሳቸው የነበረውና፣ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” ብሎ የተናገረው ነቢይ መልሶ ደግሞ የዚሁ ፍጹም ተቃራኒ የኾነን ምስክርነት አስቀምጧልና፤ እንዲህ ሲል፡- “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ” (ዮና.1፡5፣ 3፡10)፡፡ ተመልከት! ከዝሙት ወይም ከአመንዝራነት ወይም ከሌብነት ራቁ አላለም፤ “ከክፉ መንገዳቸው” እንጂ፡፡ እንዴትስ ከዚያ ሊርቁ ቻሉ? ይህን እግዚአብሔር ያውቋል እንጂ ሰው ሊመረምረው አይችልም፡፡

እንግዲህ አሕዛብ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ክፋታቸውን ኹሉ ማስወገድ ከቻሉ፥ ለአያሌ ቀናት የተመከርንና የተዘከርን እኛ ግን አንዲት ክፉ ልማድን [ለምሳሌ መሐላን] ሳናስወግድ ስንቀር ልናፍር አይገባንምን? ከዚህም በላይ እነዚህ ሰዎች ቀድሞ ክፋታቸው ጣሪያ ደርሶ ነበር፤ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” የሚለውን ስትሰማ ከክፋታቸው ብዛት በቀር ሌላ ምንም ልትገነዘብ አትችልምና፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መልካም ምግባር ፍጽምና መድረስ ተችሏቸዋል፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለበት ቀናት ወይም የጊዜ ብዛት አያስፈልግምና፡፡ በተቃራኒው ይህ ፍርሐት በሌለበት ደግሞ የጊዜ ብዛት ምንም ጥቅም የለውም፡፡

የዛጉ ብረቶችን በውኃ ብቻ የሚያጥባቸው ሰው ምንም ያህል ጊዜ እነርሱን በማጠብ ቢያሳልፍም እነዚያን ዝገቶች ኹሉ ማስለቀቅ አይቻለውም፡፡ ወደ እሳት ጨምሮ የሚያወጣቸው ሰው ግን አዲስ ከተሠሩ ብረቶችም ጭምር ሳይቀር እጅግ ጽሩያን ያደርጋቸዋል፡፡ በኃጢአት የዛገ ልብም እንዲሁ በትንሽ በትንሹና በግድየለሽነት ኾኖ ዕለት ዕለት ንስሐ ቢገባም ምንም ጥቅም አያገኝም፡፡ ራሱን ወደ እቶን - ይኸውም ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሚጥል ከኾነ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ኹሉንም ማስወገድ ይቻለዋል፡፡

(በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፥ ፳:፳፩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እግዚአብሔር የረሳን ለምን ይመስለናል?
....እኛ ስለምንረሳው...

.... ከላይኛው የቀጠለ
ጥያቄ:- ስለ ምን ጦምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም?
መልስ:- እነሆ፥ በጦማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ። እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጦማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
እኔ የመረጥሁት ጦም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጦም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
እኔስ የመረጥሁት ጦም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። (ኢሳ 58÷3-8)

እግዚአብሔር ፍጥረቱን ዘንግቶ ሳይሆን ፍጥረት እግዚአብሔርን ሲዘነጋው እግዚአብሔር ረሳኝ ይላል። እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ፈቃዱን ማግኘት ማለት ነው። እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ፈቃዱን ማግኘት ከሆነ ፈቃዱን ለማግኘት መጀመሪያ የማይፈቅደውን ለይቶ መተው ይገባል። እግዚአብሔር የሚፈቅደውን ነገር በማይፈቅደው መንገድ የቀረበ እንደሆነ አሁንም ረስተናል ማለት ነው።

አንድ ሰው ማር ይወዳል እንበል የሚወደውን ማር በሬት ለውሰን ከሰጠነው የሚወደውን በማይወደው መንገድ ሰጠነው ማለት ነው። ይደሰት ዘንድ ወይን ለሚወድ ሰው በመርዝ ዕቃ የሰጠነው እንደሆነ ደስታውን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱንም ነጠቅነው ማለት ነው።
ለፍጡር እንዲህ ማድረግ መልካም ካልሆነ ለፈጣሪማ እንዴት?

እግዚአብሔር ጦም ይወዳል፤ ጦሙ ግን ግፍ፣ ዓመጻ፣ ዝርፊያ፣ ዝሙት፣ ደም ማፍሰስ፣ ዘፈን፣ ድልቂያ፣ ግፍን በተመላ ሥጋ ካቀረብነው ፈቃዱን በማይፈቅደው ተቃወምነው ማለት ነው። እግዚአብሔር ምጽዋት ይወዳል፤ ምጽዋቱ ግን ተዘርፎ የተሰጠ ከሆነ ማሩን በሬት አቀረብነው ማለት ነው። እግዚአብሔር ጸሎት ይወዳል፤ ጸሎቱ ቂም ቋጥሮ ከሆነ መድኃኒቱን በመርዝ አቀረብነው ማለት ነው። እየቀማ ቢጦም ቆጠበ እንጂ ጦመ አይባልም ስለዚህ ፈቃደ እግዚአብሔር ኂሩት፣ ቸርነት፣ ምሕረት፣ ፍቅር፣ ሰላም፣ ምጽዋት፣ ልግስና፣ ሃይማኖት፣ ጽድቅ ማለት ነው።

"ለምን ረሳኸኝ?" ላሉት እርሱ የመለሰው "መቼ ጠራችሁኝ?" ነው ያላቸው። ከላይ የዘረዘርናቸውን የጽድቅ ተግባራት ከዘረዘረ በኋላ "ያንጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል" ነበር ያለው። ይህ ማለት እግዚአብሔርን የምንጠራባቸው ሁለቱ አንደበቶች ንጽሕናና ምግባረ ሠናይ ናቸው ማለት ነው።

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! አንተ የረሳኸውን አስታውስ እንጂ እግዚአብሔር ረሳኝ አትበል። ስትጸልይ ቂም መያዝህን ረስተህ እንደሆነ፣ ስትሰጥ ሰርቀህ እንደሆነ፣ ስትጦም ደም አፍስሰህ፣ ስትዘምር እየዘፈንህ እንደሆነ የረሳኸውን አስታውስ።

ለ. መከራ ሲጸና እግዚአብሔር የረሳቸው የሚመስላቸው እንዳሉ ቅዱስ ጳውሎስ በራሱ አስመስሎ እንዲህ ሲል ገልጦታል:-

ይቀጥላል....

ከጸያሔ ፍኖት (በአባ ገብረ ኪዳን) ገጽ 70-71
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዛሬ

ወዳጄ ሆይ !በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት በግልጽ እንዳይወቅስህ ዛሬ ስለ ሠራሄው ኃጢአት ወደ ንስሐ የሚመራ ወቀሳን ይወቅስህ ዘንድ ቤትህን ዘግተህ ሕሊናህን ተቀስቅሰው !


ቅ ዮ አፈ ወርቅ


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

❖ ተወዳጆች ሆይ የምታደምጡ ብቻ አትኹኑ፤ ያስተማርኳችሁን ትምህርት ለሌሎችም በማስተላለፍ መምህራን ትኾኑ ዘንድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ✍️“አንዱ ሌላውን ያንጸው”
📖1ኛ ተሰ 5፥11

✍️ ዳግመኛም “በፍርሐትና በመንቀጥቀጥም የራሳችኁን መዳን ፈጽሙ” ብሎ እንደ ተናገረው በስሕተት ጐዳና ያሉትን ታድኑ ዘንድ መረባችሁን ጣሉ ብዬ እማፀናችኋለሁ።
📖ፊልጵ 2፥12

❖ ይህን ስታደርጉ ቤተክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትሰፋለች፤ እኛም ይህን ዐይተን እጅግ ደስ እንሰኝባችኋለን፤ እናንተም ለወንድሞቻችሁ፣ ለእኅቶቻችሁ ባሳያችሁት ፍቅር በሰማያት ዘንድ ታላቅ ማዕረግና ክብር ታገኛላችሁ።

❖ እንደምታውቁት የእግዚአብሔር ፈቃድ እያንዳንዱ ክርስቲያን ስለ ራሱ መዳን ብቻ እንዲያስብ አይደለም፤ ወንድሙንም እንዲያንጽ ነው እንጂ፤ ሲያንጸውም በቃል ብቻ አይደለም፤ በተግባርም ጭምር እንጂ፤ የእግዚአብሔር ፈቃዱ እያንዳንዳችን በአኗኗራችን ክርስቶስን መስለን ታምነን እንድንኖርና ፍጥረት ኹሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡

❖ ይኸውም ሰዎች ከምንናገረው በላይ የምንኖረውን ስለሚያምኑና ስለሚማርካቸው ነው፤ ብዙውን ጊዜ በተዋቡ ቃላት ስለ ይቅርታ ብንናገር ነገር ግን በሕይወታችን እጅግ ቂመኞችና ይቅርታን የሚቀበል ልብ የሌለን ከኾነ ቃላችንና ሕይወታችን ስላልተስማማላቸው ሰዎች የምንለውን ነገር አያምኑንም፡፡

❖ የምንናገረውንና የምናስተምረውን የምንኖረው ከኾነ ግን ያምኑናል፤ እውነቱን ለመቀበልም አይቸገሩም፤ በቃል መነገሩ፣ በልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ያለውን ክርስቲያን እንዲህ ሲል አመስግኖታል።

✍️“የሚያደርግም የሚያስተምርም እርሱ ንዑድ ክቡር ነው”
📖ማቴ 5፥19

❖ እንግዲህ ጌታችን ሲያስተምር በተግባር የሚሰጠውን ትምህርት በቃል ከሚሰጠው ትምህርት ይልቅ እንዳስቀደመው ታስተውላላችሁን? አያችሁ! ከተግባራችን በኋላ ቃላችን ባይከተል እንኳን ሰዎችን ወደ እውነት (ኢየሱስ) ለማምጣት በቂ ነው፡፡

❖ የቅድስና ሕይወት ለፈለገውና ለመረጠው ሁሉ ይቻላል፤ አሁን ካለንበት ደረጃ ከፍ ብለን የእግዚአብሔር ጸጋ በየልባችን እንዲሠራ እግዚአብሔር ፈቃዱ ነው፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ነፍስን ወደ እግዚአብሔር በመምራት ልዩ ሀብቶችን በመስጠትና በረድኤት ከክርስቲያኖች ጋር ይሠራል።

❖ ቅዱሳን የሠሩት የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣቸው የሠራውን ነው፤ ታሪካቸውን ስታስብ በሕይወታቸው ውስጥ እግዚአብሔር እንዴት እንደሠራና በእነርሱ እንደተመሠገነ አስተውለሃል? የእነዚህ ሁሉ የጀግንነት ሥራዎቻቸው ምክንያትስ ገብቶሃል? በሚሠሩት ሥራ ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጠንካራ ሕብረት እንደነበራቸው አትረዳም?
📖2ቆሮ 13፥14

📌 ምንጭ
✍️ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የእውነተኛ ክርስቲያን መገለጫው ምንድንነው ?

💠ፀሀይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሀይ አትባልም ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሯዋ አይደለምና
💠እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባልም መተንፈስ ተፈጥሯቸው ነውና 💠ዓሳ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ሕይወት ያለ ዓሳ መሆኑ ይቅርና ይሞታል

✝️ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው :-

1/ ሲጸልይ ነው። ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ነውና ። ልጅ ከሆኑ ደግሞ አባት ማናገር ተፈጥሮው ነውና ።

2/ ሲያመሰግን ነው። ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ብሎ የሚያምን ነው ። ስለዚህ ለአንድ ክረስቲያን የሰማይና የምድር ፍሬ እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው ።

3/ ሲመጸውት ነው ። ክርስቲያን ማለት ሀብት ሁሉ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ መመስከር ነው ። ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌለው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው።

4/ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ነው ። ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና ። ይህን ለማድረግ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል መናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

(አምስቱ የንስሐ መንገዶችና ሌሎች =ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ )

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እርስዎስ ስለራስዎ ምን ይላሉ?

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የሰው ልጅ ሆይ፦
ሰው ቢጥልህ እግዚአብሔር ያነሳሃል፣ ሰው ቢጠላህ የፍቅር አምላክ ይወድሃል፣ ሰው ቢንቅህ የፈጠረህ አምላክ ያከብርሃል፣ ሰው ቢገፈትርህ ቸሩ አምላክህ ይደግፍሃል፣ ሰው ቢያስከፋህ አምላክ እርሱ ያጽናናሃል፣ ሰው ቢፈርድብህ እውነተኛው ዳኛ እግዚአብሔር ይፈርድልሃል።

ከሰው ያጣኸውን ከቸሩ አባትህ  ከዓለም ፈጣሪ ከጌቶች ጌታ ከኃያሎች ኃያል ከነገሥታት ንጉሥ ከእግዚአብሔር ታገኛለህና ለዘለዓለም በእርሱ ታመን፡፡ እግዚአብሔር መልካም በመከራ ቀንም መሸሸጊያችን ነውና።


/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን ለመስቀለ ክርስቶስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

በዚህች ቀን
ክብር ይግባውና የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ
ከኖረበት የቆሻሻ ክምር ቦታ የወጣበት ቀን ነው።


በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የጌታችን
የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል በዓል ታላቅ ክብር
ይሰጠዋል፡፡ ይህም የመስቀል በዓልም ከዘጠኙ የጌታችን ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው ።ለኛ
ለኦርቶዶክሳውያን መስቀል ማለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋጋ የከፈለበት ቤዛ
ዓለም የተከናወነበት እንደመሆኑ መስቀል በቤተ ክርስቲያናችን በሁሉ አገልግሎት ሰፊ
ድርሻ ያለውና እንዲሁም በንዋያተ ቅድሳት ላይ
የሚውል አቢይ ምልክት ነው:: በቤተክርስቲያን
አስተምህሮ “መስቀል” የሚለው ቃል ሦስት
መሠረታዊ ቁም ነገሮችን ያመለክታል።
የመጀመሪያው ጌታችን አምላካችን
መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ
ከሞተ ነፍስ ለማዳን ሲል የተቀበለው መከራና
የከፈለው መሥዋዕትነት (የክርስቶስ መከራ
መስቀል) ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በክርስትና
ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥም ልዩ ልዩ ዓይነት
መከራም (መከራ መስቀለ ክርስቲያን)
ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል
ነው፡፡ መስቀል የሰላማችንና የድኅነታችን
የመቀደሳችን ዓርማ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን
ልጆች ለማዳን፥ የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት
መስዋዕትነት የከፈለበት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር
ደሙን ያፈሰሰበት መንበር፥ ሲሆን አምላካችንን
የምንመለከትበት መስታወት ነው። በዚህች ቀን
ክብር ይግባውና የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ
ከኖረበት የቆሻሻ ክምር ቦታ የወጣበት ቀን ነው። ደገኛዋ እናት እሌኒ ቅድስት በመንፈስ
ቅዱስ አነሳሽነት :በቅዱስ ኪራኮስ መሪነት :በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት።
መስከረም 17
ቀን በደመራው ጢስ አማካኝነት የተጀመረው ቁፋሮ ከተጀመረ ከ 6 ወር ዕፀ መስቀሉ
ከቀበረ ከ 300 ዘመናት በኋላ መጋቢት 10 ቀን ተጠናቆ ቅዱስ መስቀሉ ወቶ
ብርሀን ለዓለሙ የበራበት ድንቅ ተአምራት የተደረገበት ቀን ነው ።ከ 10
አመት በኋላም ቤተ መቅደስ ተሰርቶ መስከረም 17 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ከብሯል።


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አንተ ማን ነህ?

💠በቃላት ሳይሆን በሥራ የሚገለጥ ማንነት አለህ ?
✝️መኑ አንተ ? ብተባል አንደበትህ ሳይተሳሰር የምትጠራ ስም አለህ?

💠ሌሎችን ከማገልገልህ በፊት ነፍስህን አገልግለሃል ?
💠ወይ እንደ ማርታ ከቃለ እግዚአብሔር ርቀህ በአገልግሎት ባክነሃል?

💠አውደ ምህረት ወጥተህ ከማገልገል በፊት ግን መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት ተምረዋል ?

ግን አንተ ማን ነህ?

💠ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነህን?

✝️በክርስቲና እምነት ስንት ዓመት ሆኖሃል?
ሰው 17 ዓመት ተምሮ ዶክተር እንጅነር.. ይሆናል ግን አንተ ለዘመናት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ኖረህ ሃይማኖትህን ያለ ፍርሃት ለመመስከር በቅተሃል?

💠ሃይማኖትህ ላይ የሚነሳውን ጥያቄ መጻሕፍትን ጠቅሰ ምላሽ ትሰጣለህን?

ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?

💠ባይሆን እንኳን ከወዴት ወገን ነህ?

✝️ካልጠፋት ከዘጠና ዘጠኙ መካከል ነህ?
💠ወይስ ጠፍቶ የተገኘው በግ የሚሉህ አንተን ይሆንን?

✝️ንስሐ ከማይሹ ወገን ነህን?
💠ንስሐ በመግባታቸው ደስታ ከተደረገላቸው መካከል ብትሆንስ?

✝️ነው ሙሽራው እስክመጣ ድርስ ባዶ ዘይት ይዞ ከተቀመጡት ወገን ነህ?

ለመሆኑ አንተ ማን ነህ
💠💠💠💠💠


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ሐዋርያው "የአጋንንት ልጆችና የእግዚአብሔር ልጆች በምድር ላይ የታወቁ ናቸው " እንዳለ። ፩ዮሐ ፫-፲ ትሑታን ግን ሁሉ ሲረግጣቸው አይታወቁም ። ቅዱስ ጳውሎስ "መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሁሉን ያውቃል /ይመረምራል/ እርሱን ግን የሚያውቀው /የሚመረምረው/ የለም" እንዳለ ። ፪ኛ ቆሮ ፪-፲፭ #ከጾም የሥጋ ንጽሕና ፣ ከሥጋ ንጽሕናም የነፍስ ቅድስና ይወለዳል ፤ ከነፍስ ቅድስናም ፍጹም የሆነ ርኅራኄ ይወለዳል ። ይህውም ለሰው ብቻ መራራት አይደለም ። ለፍጥረት ሁሉ ደኀንነት /ሕይወት/ ይሻላቸዋል ።  ማንኛውም ክፍ ነገር ካልተጨመረበት ርኅራኄ ይህ ነው ።

#ከርኅራኄ መልካምን ማድረግ ይወለዳል። መላካም ማድረግም መልካም ለሚያደርጉ ብቻ አይደለም ክፍ ለሚያደርጉብንም መልካም  እናደርጋለን እንጂ ። ጌታችን እንዳስተማረን " መልካም ላደረጉላቹሁ መልካምን ብታደርጉ ዋጋቹሁ ምንድን ነው ? የህንንስ ቀራጮችም ያደርጉታል። እናንተስ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ለሚጠሏሁም መልካምን አድርጉላቸው ።

( ርቱዓ ሃይማኖት )



/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ነው። ስያሜውም የቅዱስ ያሬድ ነው። ትርጉሙም “ከሰማያት የወረደ” ማለት ነው። ቅድመ ዓለም ከአባቱ ከአብ የተወለደ ፣ድኅረ ዓለም ከድንግል ማርያም የተወለደ ነው። ስም አጠራሩ  ያለና የነበረ፣ እግዚአብሔር፣ በፈቃዱ ዓለምን ለማዳን የመምጣቱን ምሥጢር የምንረዳበት ሳምንት ነው። ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጾም ጥቅምና እንዴት መጾም እንዳለብን ታስተምረናለች፡፡ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው “አከለክሙ መዋዕል ዘኃለፈ ዘተቀነይክሙ ለግዕዘ ሥጋክሙ፤ ለሥጋቸሁ ፈቃድ የተገዛችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃችኋል፤ ከአሁን በኋላ ግን ጹሙ፣ ጸልዩ ለእግዚአብሔር ተገዙ” እያለ የጾም አዋጅ ያውጃል። ጾም ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ፣ ፈቃደ ነፍስን ለፈቃደ እግዚአብሔር የምናስገዛበት መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡

ጾሙ በሚጀመርበት ሰንበት በሚሰበከው ምስባክ እንዲህ ብሎ ያሳስበናል፤ “ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፣ በረዓድም ደስ ይበላችሁ” ጾም ከምግብና ከመጠጥ እንዲሁም ከሌሎች ምቾቶችና ደስታዎች ከመከልከል ያለፈ ጥልቅ ትርጉም ያለው ተግባር ነው። (መዝ.፪፥፲፩-፲፪) “ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ከመ ያብርህ ብርሃነ ስብሐቲሁ በላዕሌነ፤ (የእግዚአብሔር) የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ወንድማችንንም እንውደድ” እንዲል። (ጾመ ድጓ)

በዘወረደ እሑድ የሚነበቡት ምንባባትም ይህንን የጾምን ጸጋ የያዙ ናቸው።

“ነገር ግን ፈጣሪያችን የምትበልጠውን ጸጋ ይሰጣል፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት፤ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት፤ ከእናንተም ይሸሻል፡፡ እግዚአብሔርን ቅረቡት፤ ይቀርባችሁማል፤ እናንተ ኃጥኣን እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ፡፡ እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ÷ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል፡፡” (ያዕ.፬፥፮-፲)

“በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን? ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና፡፡” (ዕብ.፲፫፥፲፭-፲፮)

በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳንን እያሰብን ለጾም እንድንተጋም ወደ እነርሱ እንድንመለከት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡“ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።” (ዕብ.፲፫፥፱) ሳምንቱ በሚጀምርበት ሳምንት የሚነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት እንዲህ ይላል፡፡ ጾመ ድጓው አባቶቻችን ያገኙትን በረከት እንደምናገኝበት ሲገልጽ “የእግዚአብሔር የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ ወንድሞቻችንም እንውደድ፤ ኤልያስ በጾም ወደ ሰማይ አርጓልና፤ዳንኤልም ከአናብስት አፍ ድኗልና፡፡”

ጾም ፈቃደ ነፍስን በፈቃደ ሥጋ ለማሠልጠን የአጋንንት ኃይል ለመቋቋም የሚያስችል የክርስቲያኖች ጋሻ በመሆኑ በሃይማኖት ለሚመሩ ምእመናን እጅግ አስፈላጊና ከምንም በላይ የሕይወታቸው መርሕ መሆን እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ በማለት   ያስተምራል፡፡ ” አሁንም ወንድሞቻችን በዚህ በሥጋችን ሳለን ፈቃደ ሥጋችንን ልንሠራ አይገባም፤ ፈቃደ ሥጋቸውን የሚሠሩ ሰዎች በወዲያኛው ዓለም ምውታን ናቸውና፡፡ የሥጋችሁን ፈቃድ በነፍሳችሁ ፈቃድ ድል ከነሣችሁት ለዘለዓለም ሕያዋን ትሆናላችሁ፡፡ የነፍሳቸውን ፈቃድ የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና፡፡" (ሮሜ ፰፥፲፪-፲፬)

ጾም አበው ቅዱሳን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቀምረው፣ በበታ ወስነው፣ በሁኔታ ገድበው... ባስቀመጡልን ወቅት ከእህልና ከውኃ በመከልከልና ሰውነትን በማድከም ብቻ ሳይሆን ለስሕተት ከሚዳርጉ ነገሮችና ቦታዎች ተቆጥቦ በጸሎት መትጋትም እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ይህንን እውነታ በተመለከተ እንዲህ ይላል፡፡ “እኔ ግን እዘንልን፤ ለምንልን ባሉኝ ጊዜ ማቅ ምንጣፍ ለብሼ አዘንኩላቸው፤ ሰውነቴን በጾም አደከምኩዋት፤ ልመናዬም እኔም ወደመጥቀም ተመለሰችልኝ፡፡” (መዝ. ፴፬/፴፭፥፲፫)

ጾም ከሥነ ምግባራት ሕግ አንዱ በመሆኑ እንኳንስ ያልተፈቀደውን የተፈቀደውም ቢሆን የማይጠቅም ከሆነ ፈጽሞ በመተው ለእግዚአብሔር ያለንን ፍጹም ፍቅር የምናስመሰክርበት ምሥጢር ነው፡፡

ጾም ከመብልና ከመጠጥ ጋር የተያያዘም በመሆኑ መብል ጊዜያዊ ስለሆነ ማለትም በዚህ ዓለም እስካለን ብቻ የምንገለገልበት እንጂ ዘለዓለማዊ ስላይደለ ለጊዜያዊ መብልና መጠጥ ምክንያት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር እንዳንወጣ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ሲመክሩ “መብል በእግዚአብሔር ዘንድ ግዳጅ አይፈጽምልንም ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ብንበላም አይረባንም፤ አይጠቅመንም፤ ብንተወውም አይጎዳንም” በማለት ሲመክሩን ቅዱስ ጳውሎስም የመብልና የሆድ ጊዜያዊነት አስመልክቶ እንዲህ በማለት አስተምሯል፡፡ (፩ኛቆሮ.፰፥፰)

“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅመኝም፡፡ ሁሉ ተፈቅዶልኛል በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳን አይሠለጥንብኝም፡፡ መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያሳልፋቸዋል”፤ (፩ኛቆሮ.፮፥፲፪-፲፫) “ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት ስለሚሆን ምግብ ሥሩ” እንደ ተባለ (ዮሐ. ፮፥፳፯) ካለን ጊዜ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጊዜ በመስጠት ቢበሉት የማያስርበውን፣ ቢጠጡት የማያስጠማውን፣ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን ሥጋ እና ደሙን ተቀብለን መንግሥቱን እንድንወርስ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

ሥርዓት ቅዳሴ
ከሠራኢ ካህን፣
ቅዳሴ፡
ዘእግዚእነ
“ዘበእንቲኣነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ፡ ወረደ እምሰማያት። ተሰብአ፡ ወተሠገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብር  ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፡፡”

ወንጌል፡ ዮሐ.፫፥፲-፳፬
የዕለቱ ምንባባት:-
•  በሠራኢ ዲያቆን (ዕብ.፲፫፥፯-፲፯)
•  በንፍቅ ዲያቆን (ያዕ.፬፥፮-ፍጻሜ)
•  በንፍቅ ካህን (የሐዋ. ፳፭፥፲፫-ፍጻሜ)

ምስባክ፡ “ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር” (መዝ.፪፥፲፩)

ወንጌል፡ ዮሐ.፫፥፲-፳፬

ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ፤ እንድናመልከው እኛን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን!

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#በዐቢይ_ጾም_መግቢያ_የተሰጠ_ትምህርት

የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ በልጆቿ ስትደምቅ እናንተም ጉባኤውን ለመታደም ደስ ብሏችሁ ተሰባስባችሁ ስትመጡ ዐይቼ ሐሴት አደረግሁኝ፤ ደስም አለኝ፡፡ ፊታችሁ እንዴት በደስታ እንደ ተመላ ስመለከት ጠቢቡ “ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል” እንዳለው ልባችሁ ምን ያህል እንደ ተደሰተ ተገነዘብሁኝ (ምሳ.15፥13)፡፡ በመኾኑም፥ ዛሬ ማለዳ የተነሣሁት ከወትሮው በተለየ ትጋት ነው፡፡ ይኸውም ይህን መንፈሳዊ ደስታ ከእናንተ ጋር እንድካፈልና ቀጣዩ ወራት ቁስለ ነፍሳችሁ ድኅነት የሚያገኝበት ወርሐ ጾም መኾኑን አበሥራችሁ ዘንድ ነው፡፡ የኹላችንም ጌታ ልዑል እግዚአብሔር፥ ልክ እንደ ደግ አባት ባለፉት ወራት ለሠራነው ኃጢአት ሥርየት እናገኝበት ዘንድ ሽቶ መድኃኒት የሚኾን ቅዱስ ጾምን አዘጋጅቶልናልና፡፡

ስለዚህ የነፍሳችን ጠባቂ (እግዚአብሔር) የሕመማችንን ፈውስ የምናገኝበትን መድኃኒት ስላዘጋጀልን እያመሰገንን ወርሐ ጾሙን ደስ ብሎን ልንቀበለው ይገባናል፡፡ ከእኛ መካከል ጾም በመግባቱ አንድስ እንኳን የሚከፋው ወይም የሚበሳጭ ሊኖር አይገባም፡፡ ወርሐ ጾሙን እንዲህ ደስ ተሰኝተን መቀበላችንን ዐይተውም አሕዛብ ይፈሩ፤ አይሁድም ይራዱ፡፡ በእኛና በእነርሱ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ዐይተውም ይማሩ፡፡ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በዓል የምትሠራው ምእመናን ራሳቸውን መግዛት እንዲችሉ፣ በበጎ ምግባር ያጌጡ ያሸበረቁ እንዲኾኑ እንደ ኾነ፥ እነርሱ ግን በዓላትን የሚያደርጉት በዘፈንና በስካር ይህንም በመሰለ በሌላ ጸያፍ ግብር ለመንከባለል እንደ ኾነ ለይተው ይወቁ፡፡ በእርግጥም በዓል ተከበረ የሚባለው፡- ሰዎች ነፍሳቸውን ካዳኑበት፣ ውስጣዊ ሰላምንና ፍቅረ ቢጽን ገንዘብ ካደረጉበት፣ ዕለት ዕለት ከሚያጋጥማቸው የነፍስ መታወክ ካረፉበት፣ ያለ ሁካታና ጋጋታ እንዲሁም እንስሳትን በማረድ ከልክ በላይ ከኾነ መብልና መጠጥ ርቀው ያከበሩት እንደ ኾነ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓል ተከበረ የሚባለው፡- አርምሞንና ጸጥታን፣ ፍቅርንና ደስታን፣ ሰላምንና ራስን መግዛትን፣ እንዲሁም ሌሎች እዚህ መዘርዘር የማንችላቸው ብዙ ምግባር ትሩፋቶችን ገንዘብ ያደረግንበት እንደ ኾነ ነው፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ቂም ይዞ ጸሎት +

አበው እንዲህ ይላሉ ''ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት'' የማይታሰብ ነው ይላሉ።ለምን አንድ ሰው ለጸሎት ሲቆም የበደለውን ክሶ የወሰደውን መልሶ በንጹህ ልብ ሆኖ ለአምላኩ ጸሎት ማቅረብ አለበት ምክንያቱም ጸሎት ምስጋና ነው ጸሎት ልመና ነው እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን እና የምንፈልገውን እንዲሰጠን መጀመሪያ እኛ የምንጠላውን ሰው ይቅር ማለት አለብን።

''አንድ ሰው ከልጃቸው ጋር ቤተ ክርስቲያን ይሄዱና ዳዊታቸውን ዘርግተው ጸሎት ይጸልያሉ።
ጸሎት እስኪ ጨርሱ ልጁን አጠገባቸው አረፍ እንዲል ይነግሩታል ከዚያ የዳዊትን መዝሙር በተመስጦ መጸለይ ይጀምራሉ በመሐል አንድ እጅግ በጣም የሚጠሉት ሰው በአጠገባቸው ያልፋል ልጅ ''አባዬ አባዬ ያ የምትጠላው ሰው መጣ ''ይላል አባትም ጸሎቱ እንዳይቋረጥባቸው በማሰብ ድምጽ ሳያሰሙ በእጃቸው በምልክት አንገቱን በለው ይሉታል።''

ይገርማል ይህ ሰው የተጣላውን ሰው ይቅር ሳይል ነበር እግዚአብሔር ይቅር እንዲለው ይጸልይ የነበረው።ይህ ሰው ስለ ጸሎት አንድ ነገር ያውቃል በጸሎት ጊዜ ከሌላ ሰው ጋር መነጋገር እንደማይቻል ያውቃል ነገር ግን ከቂም ከበቀል ራሱን ማንጻት እንዳለበት ግን አያውቅም ለዚህ ነው መዝሙረ ዳዊት እየጸለየ እንዳይናገር ለልጁ በምልክት እንዲመታው ያዘዘው።

ይህ ሰው የፈሪሳውያን ጠባይ ነው ያለው ለውጩ ስርዓት በጣም ተጠንቅቋል ውስጡ ግን በኖራ እንደተለሰነ መቃብር ነበር። ይህ ሰው ከሁሉ አስቀድሞ ከመጸለያችን በፊት የተጣላነው ሰው ካለ ይቅር ማለት እንዳለብን ያስተምረናል በቂም ውስጥ ሆኖ የሚጸለይ ጸሎት ጥቅም የለውም። ጌታም ከሁሉ አስቀድሞ ይቅርታን ገንዘብ ማድረግ እንዳለብን ሲያስተምር " ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ።"( ማቴ 12:7)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ከምናቀርበው የጸሎት ምሥዋዕት በላይ ለሌላው ሰው የምናደርገው ይቅርታ ያስደስተዋል። ምህረትን እወዳለሁ መሥዋዕትን አይደለም ማለት ይህ ነው።
ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።
እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ( ማር 12:25-26 )

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የአሥርቱ ትዕዛዛት አከፋፈል

  የክርስቲያን ሕግ የፍቅር ሕግ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታል ካለ በኋላ ከአሥርቱ ትዕዛዛት የተወሰኑትን በመጥቀስ ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። /ሮሜ 13÷8-10/

  እንዲሁም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ፍቅር በሁለት ይከፈላል። /ማቴ 22÷34-41/
1, ፍቅረ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን መውደድ)
2, ፍቅረ ቢጽ (ወንድምን መውደድ)

- በተጨማሪም ጌታችን ሕግም ነቢያትም በነዚህ በሁለቱ ትዕዛዛት ተጠቃለዋል ብሎ ስለተናገረ በዚህ መነሻነት አሥርቱን ትዕዛዛት በሁለት እንከፍላቸዋለን።

1, #ፍቅረ_እግዚአብሔር ፦ ከ1ኛው ትዕዛዝ አስከ 3ተኛው ትዕዛዝ ድረስ ያሉት።
- ከኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁንልህ
- የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
- የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ

2, #ፍቅረ_ቢጽ ፦ ከ4ተኛው ትዕዛዝ እሰከ 10ኛው ትዕዛዝ ያሉት።
- አባትና እናትህን አክብር 
- አትግደል
- አታመንዝር
- አትስረቅ
- በሐሰት አትመስክር
- የባልንጀራህን ቤት አትመኝ
- ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ


#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ጊዜ እስኪ ደርሰ
ወደ አንተ መምጫዬ
ለንስሐ አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ
ለቁርባን አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሰበር መረጃ
+++++++++++++++++++++++++++++
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡
ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ:---
1.  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2.  የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3.  የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4.  በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም የተባሉት የገዳሙ የሥራ ሓላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገልጸዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሙ ጸጥታውን የሚያስከብረበት  መሣሪያዎች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ገዳማውያን በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

©የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዮሐንስ ዘደማስቆ ሊቁ እንዲህ ይላል ፦ ወዳጆች ሆይ በመስቀል ፈት በሰገድን ጊዜ በቀጥታ በመስቀሉ ላይ ለተሰቀለው እየሰገድን እንጂ ለእንጨቱ እንዳልሆነ እርግጠኛ እንኹን አለበዚያማ በመንገድ ላይ በሚገኘው ዛፍ ፈት እንድንበረክክ ታዘናል ማለት ነው ። "በማለት መስቀል ልዩ መኾን የቻለው ኢየሱስ ስለተሰቀለበት መኾኑን መስቀልን ስንመለከት እንጨቱን ሳይኾን የምናስታውሰው ዓለምን ለማዳን ሲል በላዩ ላይ የተሰቀለውን አምላካችንን ነው ።እንግዲህ ቅዱስ መስቀሉ ወደ ክርስቶስ ሕሊናችንን እንደሚያሳርግ ሁሉ ቅዱሳት  ሥዕላትም ወደ ሥዕሉ ባለቤት ያሳርጉናል
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…
Subscribe to a channel