dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ (በዓለ ሃምሳ )
በሰላም አደረሳችሁ ።


በዓለ ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው።

ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ የግሪክ ነው። “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም

👉መጽንኢ (በእምነት የሚያጸና)፣
❖መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ)፣
❖ናዛዚ (ያዘኑትን የሚያረጋጋ)፣
❖መስተፍስሒ (የተጨነቁትን የሚያስደስት)፣
❖ከሣቲ (ምስጢርን የሚገልጽ) ማለት ነው

ከበዓሉ በረከት ረድኤት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያሳትፈን።

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

*በዓለ ጰራቅሊጦስ*

❖ጰንጠቆስጤ ቃሉ የግሪክ ቃል ነው፡፡ ትርጓሜውም ሃምሳኛ ማለት ነው፡፡

❖ ጰራቅሊጦስ ማለትም የሚረዳ፤ የሚያጽናና ማለት ነው፡፡
❖በብሉይ ኪዳን በዓላት ለምሳሌ የአይሁድ የፋሲካ በዓላቸውን ካከበሩ በኋላ አምሳውን ቀን የነጻነት በዓላቸው አድርገው ከሰነበቱ በኋላ ኃምሳኛውን ቀን በተለየ ሁኔታ በዓለ ሰዊት ብለው ያከብራሉ፡፡

❖ በእነርሱ ሀገር ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለው ወቅት ጸደይ /የእሸት ወራት/ ነው፡፡
ጌታችን እርሱ ባወቀ ይህን በዓል /በዓለ ሠዊትን/ ለሐዲስ ኪዳን በዓላችን ፪ ጥቅሞችን እንዲያስገኝ አድርጓል””

✢ የመጀመሪያ ለበዐለ ጰራቅሊጦስ
ምሳሌ መንገድ ጠራጊ፤ መተርጐሚያ ፤ ማሳመኛ መሆኑ ነው፡፡

ሁለተኛው በዓሉ እንዲከበር ምክንያት የሆነው ርደተ-መንፈስ ቅዱስ /የመንፈስ ቅዱስ መውረድ/ ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሳ በአምሳኛው ቀን በወረደበት ዕለት በዝርዎት የነበሩ አይሁድ ሁሉ ለበዓለ ፋሲካና ከዚሁ ተያይዞ ለሚከበረው ለበዓለ ሠዊት እንደተሰበሰቡ የተፈጸመ መሆኑ ነው፡፡

❖ ሰዎቹም በጸሎት የተጉ መሆናቸውና ከእግዚአብሔር የሆነውን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው በክርስቶስ አምላክነት አምነው የቤተክርስቲያን መሠረት እንዲጣል ምክንያት ሆኖአል፡፡ ማስረጃ፡- ሐዋ.፪÷፭-፮ “ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምጽ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ ….” ሕዝቡም እንደተጻፈውም ነገሩ ከእግዚአብሔር መሆኑን ለመመርመር ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ሐዋ.፪÷፯-፲፩ “ ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ፡- ❖እነሆ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን?
❖እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?... እግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን፡፡”

❖ተገርመው ተደንቀውም አልቀሩም -
👉አለ -የቅ/ጴጥሮስን ስብከትሰምተው አምነው የተጠመቁ ብዙዎች ናቸውና ይህንን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ሐዋ.፪÷፵፩-፵፪ “ ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤በሐዋርያትም ትምህርትና በኀበራት እንጀራውንም በመቁረስ በጸሎትም ይተጉ ነበር”

ይህዊ ዕለት፤ የቤተክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውም ለዚህ ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ የወረደበት፤ በሦስት ሺህ ✢ሰዎች ጥምቀት መስፋፋት የጀመረችበት፤ ሐዋርያትም ፍሩሃኑ ጥቡዓን /ደፋሮች/ ሆነው፤ በዕውቀት በልጽገው፣በአእምሮ ታድሰው ዓለሙን ለመለወጥ ኃይል ያገኙባት ዕለት ናት፡፡

❖ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ እነዚህን ነገሮች አስታውጦ ሲናገር “መንፈስ ቅዱስ ባይወርድላት ኑሮ የቤተክርስቲያን ሕልውና ከስሞኖ ቀጭጮ ይቀር ነበር፤ ስለዚህም በሚገባ አነጋገር ይህች ዕለት የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ትባላለች” ብሎአል፡፡

👉ከዚህም የተነሳ ሌሎች ሊቃውንትም ዕለቲቱን የበዓላት ሁሉ እመቤት እንደሚሏት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ገልጸውታል፡፡
በዓሉ ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ለቤተክርስቲያን “ ከእናንተ ጋር ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤ እኮ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል” እና “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤በስሜ አጋንንትን ያወጣኑ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤…” ሲል የገባው ኪዳን የተፈጸመበት ተደርጎም ይከበራል፡፡

👉 በእኛ በቤተክርስቲያን ሊቃውንት በፍትሐነገሥት የገለጹትን በማሰብ ለመንፈሳዊ ሐሴት በቃለ -እግዚአብሔር ይከበራል ፡፡ ፍትሐ ነገሥታችን “ ትንሣኤን በአከበራችሁ በአምሳኛው ቀን ዕርገቱን በአከበራችሁ በዐሥረኛው ቀን በዓለ ጰራቅሊጦስን አክብሩ በዓል ይሁንላችሁ" እንዳለ ቤ/ክ ታከብራለች!



ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
   ╭═
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ››

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አሁንም የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ
የጸናችሁና የማትናወጡ ሁኑ
ዘወትር በጎ ሥራ አብዝታችሁ ለእግዚአብሔር አበርክቱ
ስለ ጌታችን መድከማችሁ ለከንቱ እንዳይደለ ታውቃላችሁና።

1ቆሮ 15÷58

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

__ደግ ዓለም፣ ሕይወተ ቡሩካን_

፩. ክፉ ከማሰብ፣ ክፉ ከመናገር፣ ክፉ ከመሥራት ራስን መጠበቅ።

፪. ሌላውን ሰው ክፉ ከሚያሳስብ፣ ክፉ ከሚያናግር፣ ክፉ ከሚያስደርግ ተግባር ራስን መጠበቅ።

፫. መልካም ማሰብ፣ መልካም መናገር፣ መልካም ማድረግ።

፬. ሌላው ሰውም መልካም ሐሳብን ያስብ ዘንድ፣ መልካም ንግግርን ይናገር ዘንድ፣ መልካም ድርጊትን ያደርግ ዘንድ በጎ አስተዋጽኦ ማድረግ።

፭. ክፋትን ከመኮነናችን በፊት እኛ ራሳችንም በብዙ መንገድ ከክፋት የራቅንና በመልካምነት የጸናን ልንሆን ይገባል።

፮. ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ነገ የተሻልን ሆነን ለመገኘት መጣር አለብን።

፯. ከዚህ ቀደም ያጠፋናቸውን ጥፋቶች በንስሓና በይቅርታ ሽረን ለወደፊቱ ደግሞ እንዳናጠፋ መጠንቀቅ። ንስሓ የገባንበትን ኃጢአት ላለመድገም እስከ ሞት መታመን።

፰. ሰውን በመልካም ሥራው እንዲቀጥልበት ማበረታታት፣ ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ደግሞ በቅንነት መንገር።

፱. ለሰሚው የማይጠቅምና ሰሚውን የሚጎዳ ነገርን አለመናገር። ከሰይጣን ጋር አለመተባበር። ከከንቱ ውዳሴ፣ ከትዕቢት፣ ከሐሜት፣ ከውሸት፣ ከስርቆትና በጠቅላላው የሰይጣን ገንዘብ ከሆኑት ነገሮች ራስን ማራቅ።

፲. ለእኛ ሊደረግልን የምንፈልገውን ለሌሎችም ማድረግ፣ በእኛ እንዲደረግ የማንፈልገውን በሌሎችም እንዳይደረግ መመኘት።

፲፩. ክርስቶስ በዚህ ምድር እየተመላለሰ ሲያስተምር ክፉዎችን አላጠፋቸውም። ነገር ግን በክፉዎች መካከል እንዴት መኖር እንዳለብን አስተማረን።

፲፪. ለእግዚአብሔር ሕግ እስከ ዕለተ ሞት ድረስ መታመን። ሰማዕትነትን መውደድ። ሰማዕትነትን ፈርቶ የእግዚአብሔር ሕግ ሲጣስ ዝም አለማለት።

የቡሩካን ሕይወት ከላይ ያሉትንና ሌሎችንም መልካም ሥራዎች በመሥራት ላይ የተመሠረተ ነው። መልካም እየሠሩ መኖር ደግ ዓለም ነው።

© በትረ ማርያም

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ብፁዓን ጳጳሳትን እንወዳቸዋለን። ይህ ማለት ግን እንደ ይሁዳ ለገንዘብ የሚሯሯጥና እንደ ኬልቄዶናውያን ፈቃደ ንጉሥን ለመፈጸም የሚሯሯጥ ጳጳስ ሲኖር አካሄዱን በግልጽ እንተቻለን። ያ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ይሁዳን ሌባ ነበረ ብሎ እንደተናገረው እኛም በስማቸው ዘረኛውን ዘረኛ፣ ሙሰኛውን ሙሰኛ፣ ሌባውን ሌባ፣ ቀኖና ያፈረሰውን ቀኖና አፍራሽ ብለን እንጠራዋለን። ሐዋርያትን ስናከብር ጎን ለጎን በሐዋርያነት ስም ብር ያሳድድ የነበረውን ይሁዳን ግን ሌባና ከሓዲ እያልን እውነቱን እንናገራለን።

_የንስር ዓይን__
ንስር በሰማይ እየበረረ ከምድር ያሉ ረቂቅ ነገሮችን ሳይቀር ያያል ይባላል። ዮሐንስ ወንጌላዊ በንስር የተመሰለው ረቂቅ ምሥጢረ ሥላሴን አስፍቶ በመጻፉ ነው። ከንስር ምን እንማር??

፩) አጥርቶ ማየት:- እውነትን ከሐሰት፣ መልካምን ከክፉ፣ ጽድቅን ከኃጢአት ለይቶ የሚረዳ ልቡና ሊኖረን ይገባል። ሐዋርያነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ የአገልግሎት መዓርግ ነው። ስለዚህ ሐዋርያነትን፣ ጵጵስናን፣ ክህነትን እናከብራለን። ይህ ማለት ግን ይሁዳ ሐዋርያነትን እንደምናከብር አውቆ በሐዋርያነት ካባ ክርስቶስን ሲክደው ዝም የምንለው አይደለንም። ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ይሁዳ ሲጽፍ ሌባ ነበረ ብሎታል። በጳጳስ ስም እየነገዱ ቀኖና የሚሽሩ፣ የንጉሥ አገልጋይ መለካዊ የሆኑ ካሉ በስማቸው ሌባ፣ መለካዊ፣ አጭበርባሪ እያልን እንጠራቸዋለን። እስከ መጨረሻውም ድረስ እንቃወማቸዋለን እንጂ ዝም አንልም። ለእውነት የሚታገሉ እንደ ሐዋርያት እስከሞት ድረስ የታመኑ ብፁዓን አባቶቻችንን ደግሞ ከልባችን እናከብራቸዋለን።

፪) ከፍ ብሎ መብረር:- ኅሊናችን ምጡቅ ይሆን ዘንድ መጻሕፍትን ማንበብና መልካም ምግባራትን መሥራት። ሰማያዊ ነገርን ሁልጊዜም ማሰብ ይገባናል። "በሰማይ የሀሉ ልብክሙ" እንዲል። ወደላይ ከፍ እያልን በሄድን ቁጥር በዚህች ምድር ትልቅ የሚመስሉን ነገሮች ሁሉ ትንሽ መሆናቸውን እንረዳለን።

© በትረማርያም አበባው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ክፍል ፪

የኦርቶዶክሳዊው ሚዛን መሠረቱ ፍቅር እና እውነት ነው።


❖ ዓለምን የምንመዝናት ከእግዚአብሔር ቃል አኳያ ነው። አንድን ነገር እውነት ነው ወይም ውሸት ነው፣ ውብ ነው ወይም አይደለም፣ የሚለውን የምንለካው በቃሉ መሠረት ነው። ለምሳሌ እግዚአብሔር ፈራጅ ነው። በፈራጅነቱ ፈርዖንን በውሃ አስጥሟል። እግዚአብሔር መሐሪ ነው። በመሐሪነቱ ደግሞ አዳምን ከሲኦል አድኖታል። በደንብ ልንጠነቀቅበት የሚገባን ጉዳይ ለእግዚአብሔር ፈታሒነትም መሐሪነትም ገንዘቡ መሆናቸውን ነው። ለማንኛውም ኃጢኣታችን ፍርድ ይሰጥበታል። የምሕረት ደጁም ክፍት ነው። አዳም እግዚአብሔርን በደለ። ሕግ ተላለፈ። ለሕግ መተላለፉ 5500 ዘመን ያህል በሲኦል እንዲሰቃይ ፈርዶበታል። እንደገና አዳም ንሥሓ በመግባቱ ይቅር ብሎ ፍርዱ ካለቀ በኋላ ምሮታል። ለአዳም መማር ትልቁ ምክንያት ግን መጀመሪያ እግዚአብሔር መሐሪ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ግን አዳም ጥፋቱን አምኖ አጥፍቻለሁ ብሎ ፍርዱን በመቀበሉ ነው። ወደፊትም ጌታ በኃጥዓን ሊፈርድባቸው ለጻድቃን ሊፈርድላቸው በዳግም ምጽአት ይመጣል። ያን ጊዜ በኃጥዓን የሚፈርደባቸው ኃጢዓተኝነታቸው ተረጋግጦ ነው። ምሕረት ለማያስፈልገው ሰው ለዘላለም ይኖርበት ዘንድ ወደ ገሐነመ እሳት ይወረወራል። ምሕረት ለሚገባው ኃጢዓቱን አምኖ የቀደመ ሥራውን ለተወ፣ የቀደመ ክፉ ሥራውን የሚኮንን፣ ባለፈው ክፉ ሥራው ተጸጽቶ ንሥሓ ገብቶ ሥጋውን ደሙን ለተቀበለ ደግሞ ጌታ ምሕረት ሰጥቶ ዘላለማዊ ደስታ ወዳለባት መንግሥተ ሰማያት ያስገባዋል። ኦርቶዶክሳዊ ሰው ዋና ሚዛኑ ዘላለማዊ ሕይወት ነው። ይህም ማለት የሚያደርገው ነገር ዘላለማዊውን መልካም ሕይወት ለመውረስ ያበቃል ወይስ አያበቃም? የእግዚአብሔርን ሕግ ይቃረናል ወይስ አይቃረንም? የሚለውን ይመረምራል። ኦርቶዶክሳዊው ሰው ሁሉንም ሰው እንደራሱ አድርጎ ስለሚወድ ስለሌላው ሰው የሚናገረውን ነገር ሁሉ ለእርሱ እንደሆነ አስቦ ይናገራል። ምክንያቱም ትእዛዛት በፍቅር ይጠቃለላሉ። ፍቅር ደግሞ ፍቅረ እግዚአብሔርና ፍቅረ ቢጽ ተብሎ ይከፈላል። ፍቅረ ቢጽ ለእኛ ሊደረግልን የምንፈልገውን ለሌሎች ማድረግና እንዲደረግላቸው መመኘት ነው። በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ነው። የፍቅር ትርጓሜ ይህ ነው። ስለዚህ የኦርቶዶክሳዊ ሰው እይታው አመለካከቱ ፍቅርን መሠረት ያደረገ መሆን አለበት። ዮሐንስ አፈወርቅ ኃጥዓን ሲሞቱ ደስ ሊለን ይገባል ይላል። ምክንያቱም በህይወት ቢቀጥሉ ኖሮ ኃጢኣታችውን ጨምረው ፍዳቸውን ያበዙ ነበር። ቶሎ በመሞታቸው ግን ፍዳቸው ይቀንሳል ይላል። ስለዚህ የኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ዋና መሠረቱ ፍቅር ነው። ሌላው እውነት ነው። ፍቅር እውነትን የያዘ ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ አንድ ሰው ኃጢኣተኛ ቢሆን ለኃጢኣቱ ቅጣት ያስፈልገዋል። ይህ እውነት ነው። ነገር ግን ቅጣቱን እኛ በእሱ ቦታ ብንሆን ምን እንድንቀጣ ነው የምንፈልገው? የሚለውን የያዘ መሆን አለበት። እኛ የፈለገ ብንበድል መቼም ሲኦልን አንመኛትም። ሲኦልን የሚመኝ ሰው ይኖር አይመስለኝም። ስለዚህ ሌላው ሰውም የፈለገ ትልቅ በደል ቢበድል ለእኛ ሲኦልን እንዳልተመኘናት ሁሉ ለዚያም ሰው አለመመኘት ነው። በጥፋቱ መቀጣት እንዳለበት ማመን እውነት ነው። ቅጣቱ ምድራዊ እንዲሆንለት መመኘት ደግሞ ፍቅር ነው። ስለዚህ የኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ዋና መሠረቶቹ ፍቅር እና እውነት ናቸው። ቅዱሳን መምህራን እውነትን የሚያስተምሩ እውነት እግዚአብሔር ስለሆነ እውነትን መናገር እውነትን ማወቅ ለእኛ ለሰውነታችን ከምንም በላይ ታላቅ ጥቅም ስላለው ነው። ይህንን እውነት ሌላውን ለማስተማር የተጉት እስከ ሞት የደረሱት ደግሞ ሰውን ስለሚወዱ እና ሌላው ሰውም እውነቱን አውቆ እንዲጠቀም ካላቸው መልካም እሳቤ እና ፍቅር የተነሳ ነው።

ክፍል 3 ይቀጥላል

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

" የፈጠራችሁን እስከ ዛሬም ድረስ የጠበቃችሁን እግዚአብሔርን ፍሩት " መቃብያን ካልዕ 10 ÷1

ሰንበት ትምህርት ቤት

ሰንበት ትምህርት ቤት ሕጻናት እና ወጣቶች እንደ ዕድሜ ደረጃቸው በተዘጋጁ መንፈሳዊ ትምህርቶች ተኮትኩተው የሚያድጉበት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋም በቃለ እግዚአብሔር የታነጸ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ እና ሥርዓት የሚያውቅ ሀገሩን የሚወድ ለራሱ ፣ለቤተሰቡ ለሀገር እና ለወገን የሚጠቅም ትውልድ በቃለ እግዚአብሔር የሚታነጸበት ቦታ ነው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ኦርቶዶክሳዊ  ሚዛን

ኦርቶዶክሳዊው  ሚዛን    ክፍል  ፩

ብዙው  ሰው  እጁ  እስኪላጥ  ሲያጨበጭብ  ከርሞ  አሁን  ደግሞ  ላንቃው  እስኪሰነጠቅ  እየጮኽ ነው።  በእርግጥ  የመንጋነት  ፍጻሜው  ውድቀት  እና  ማፈር  እንዲሁም  ፀፀት  ነው።  አብዛኛው ሰው  መንጋ  ነው።  የሰባኪ  መንጋ  አለ።  የአጥማቂ  ነኝ  ባይ  መንጋ  አለ።  የፖለቲከኛ  መንጋ  አለ። የአክቲቪስት  መንጋ  አለ።  አንዳንዱ  አሁንም  ከመንጋነት  ወደ  መንጋነት  የተዘዋወረ  አለ።  የሆነ ሰው  መንጋ  ሆኖ  ይከርምና  የተከዳ  ሲመስለው  እገሌ  ግን  ያን  ጊዜም  ትክክል  ነበር  ብሎ  ለዚያ ሰው  ወዶ  ገብ  መንጋ  ይሆናል።  እኒህ  ሁሉ  መንጋቸውን  እንደፈለገ  ይነዱታል።  መንጋው ደግሞ  አያሰላስልም።  መንጋ  እንደ  ሸንበቆ  ነው።  ሸንበቆ  ነፋስ  ወደነፈሰበት  ነው  ሁል  ጊዜም የሚያዘነብለው።  ነገር  ግን  ነፋሱ  በጣም  አይሎ  ነቃቅሎ  ሲጥለው  ያን  ጊዜ  ያማርራል።  አብዛኛው ሰው  መለኪያ  የለውም።  መስማት  የሚፈልገውን  እየነገሩ  የሚወስዱት  ሰዎች  ብዙ  ናቸው። በርበሬ  ተወዶ  ከሆነ  ቤተክርስቲያን  ሰባኪው  አስተምሮ  ሲጨርስ  "ፈጣሪያችን  የበርበሬን  ዋጋ ይቀንስልን"  ሲል  "አሜን"  የሚለውን  መንጋ  ብዛት  አስተውልማ።  ደንበኛው  ሊቅ  መጥቶ አስተምሮ  ሲጨርስ  "ንሥሓ  ገብተን  ሥጋውን  ደሙን  ለመቀበል  ያብቃን"  ሲል  አሜን  የሚለው ይቀንሳል።  ይሄ  በጣም  አሳዛኙ  ክስተት  ነው።  ሰው  መስማት  ያለበትን  ከሚሰማ  ይልቅ  መስማት የሚፈልገውን  መስማትን  እየመረጠ  ነው።  ቤተ  ክርስቲያን  በክርስቶስ  ደም  የተዋጀችው የክርስቶስ  ሙሽራ  የሆነችው  ስለበርበሬ  እንዲወራ  ነው  እንዴ!?።  ማንኛውም  ሰው  ፕሮፌሰርም፣ ዶክተርም፣  ኢንጂነርም፣  ሳይንቲስትም፣  ፖለቲከኛም፣  ፓትርያርክም፣  ቄስም፣  ጳጳስም፣ መምህርም፣  ምእመንም፣  ዲያቆንም  ሁሉም  ፍጡራን  ናቸው።  እንደፍጡርነታቸው  የሚለኩበት መለኪያም  አንድ  ነው።  አንተ  ሰው  ለምን  የፖለቲከኛ  መንጋ  ትሆናለህ!?  ፖለቲከኛም  እንደ አንተ  ሰው  መሆኑን  ዘነጋሃው  እንዴ!?  እንደ  አንተ  ሰው  ከሆነ  አንተም  እርሱም  የምትዳኙበት መለኪያ  አንድ  ዓይነት  ነው።  አንድ  ዓይነት  ከሆነ  ደግሞ  ለምን  ራስህን  የፖለቲከኛና  የሰባኪ መንጋ  ታደርጋለህ!?  የማንም  መንጋ  አትሁን።  እግዚአብሔር  ራስህን  አስችሎ  ስለፈጠረህ ራስህን  ችለህ  አስብ።  በሌሎች  ጭንቅላት  ካልተመራሁ  አትበል።  ሩጥ  ሲሉህ  የምትሮጥ  ቁጭ በል  ሲሉህ  ቁጭ  የምትል  ከሆነ  ፈጣሪ  በነጻነት  ራስህ  ተመራምረህ  እንድትመርጥ  የሰጠህን እድል  መንጋ  ለሆንክለት  አካል  አሳልፈህ  ሰጠኽው  ማለት  ነው።  ይህ  ደግሞ  እገሌ  አይሳሳትም ወደማለት  ጽንፍ  ያወርድሀል።  ከዚያ  ያ  ሰው  ሲሳሳት  አንተ  ማፈሪያ  ሆነህ  ትቀራለህ። ኦርቶዶክሳዊው  ሰው  ግን  ሁሉን  የሚመረምርበት  አእምሮ  ከፈጣሪ  ስለተሰጠው  በራሱ  መንገድ በራሱ  መለኪያ  ነገሮችን  ይመረምራል  እንጂ  የማንም  መንጋ  አይሆንም።  ታድያ  በዓለማችን የሚደረጉ  ነገሮችን  ለመመርመር  ኦርቶዶክሳዊው  ሚዛን  ያስፈልገናል።  ኦርቶዶክሳዊው  ሚዛን ሁልጊዜም  ትክክል  ነው።  አያጸጽትም።  ዘመናትን  ተሻጋሪ  ነው።  ልበ  ሙሉ  ያደርጋል። ምክንያቱም  የኦርቶዶክሳዊው  ሚዛን  ባለቤት  እግዚአብሔር  ነው።  ስለዚህ  ኦርቶዶክሳዊው  ሚዛን ምንድን  ነው?!  ከመንጋነት  እንዴት  እንላቀቅ  የሚሉ  ጉዳዮችን  በ7  ክፍል  እንመለከታለን።

ይከታተሉ። ክፍል 2  ይቀጥላል ..

መ/ር በትረ ማርያም

#share

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ግንቦት 11 በዓሉ ለቅዱስ ያሬድ ማሕሌታይ

" ከመ ተሰወርከ ያሬድ እምቅድመ ዓይኑ ለሞት
አድህነነ በጸሎትከ እምእለተ እኪት
ወባለሐነ እምኩሉ መንሱት"

ቅዱስ ያሬድ ሆይ ከሞት ፊት እንደተሰወርክ ሁሉ በጸሎትህ እኛን ከክፉ ቀን እና ከክፉ ነገር አድነን

የቤተ ክርስቲያን ጌጥ የዜማ አባት የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር የቅኔ እና የሥነ መለኮት ሊቅ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ ደብረ ሐዊ በተባለ ቅዱስ መካን በምናኔ ለብዙ ዘመን ከኖረ በኃላ ሞት ሳይቀምስ በሰባ አምስት አመቱ የተሰወረው ግንቦት 11 ቀን ነው

በገድለ ቅዱስ ያሬድ ተጽፎ እንደምናገኘው በዘመኑ የነበሩ ሁሉ እንደ መበረቅ የሚደምቅ፣ ምሥጢሩ እንደ መስታወት የሚያንጸባርቅ ጥበብ የተሞላበትን ድንቅ ዜማውን ለመስማት ከህጻናት እስከ ንጉሡ ድረስ ይከቡት የነበረ ማሕሌታይ ነው

" ንጉሥ ገብረ መስቀል ይህን ታላቅ ጣዕም ያለው ዜማ በሰማ ጊዜ ጫማውን ከእግሩ አልጨመረም ንግሥቲቱም አገልጋዮቿን ተወች ያንን ጥዑም ዜማ ትሰማ ዘንድ በአንድነት ሮጡ ጳጳሳት ካህናት የቤተ መንግሥቱ ወይዛዝርት ሹማምንት ወደ ቅዱስ ያሬድ መጡ ሲሰሙት ዋሉ፤ ከድምፀ ቃናው ጣዕም የተነሣ አጥንትን የሚያለመልም ልቡናን የሚያስደስት ነገር አግኝተዋልና፤ የቃሉን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሮጡ ወደ እርሱ ደረሱ ንጉሡም ንግሥቲቱም ከካህናቱ ጋር፣ ከመንግሥት ሹማምንትና ከሕዝቡ ጋር በመኾን ሲያዳምጡት ዋሉ›› እንዲል ገድለ ቅዱስ ያሬድ

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ የክብርህ ምስጋና ሰማያትንና ምድርን የመላ ነው እያሉ በስማይ ከሚኖሩ ከቅዱሳን መላእክት የሰማሁት ዜማ ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ እንደምን ያለ ረቂቅ ነው ለዚህ አንክሮ ይገባል እያለ በምስጋና ሥርዓታቸው ሲደነቅባቸው ከነበሩ ከቅዱሳን መላእክት ጋራ ሊያመስገን ከዚህ ዓለም መከራ እና ድካም ሊያርፍ ሞትን ሳይቀምስ ተሰወረ በድርሣነ ቅዱስ ዑራኤል የስኔ ወር ምንባብ ላይ " ከሰው ዓይን ተሰወረ አኗኗሩም ከሰማይ መላእክት ጋር ሆነ " እንዲል

ተዓምረ ኢየሱስ የተሰኘው የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍም

" ካህኑ ያሬድ ከዚህ ዓለም የሚለይበት ሰአት በደረሰ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዓት እንድታይ እና ወደ ምድር አስተላልፈህ ይህንኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኩ ሁሉ አሁንም ከዚህ ዓለም በምትለይበት ሰዓት እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሳቸው ህጻናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊል እና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልሃል ብሎት ወደ ሰማይ ዐረገ " ሲል ሞትን ሳይቀምስ መሰወሩን ይገልጻል

+ የቅዱስ ያሬድ በረከት በሁላችን ይደር በምልጃው ሀገራችንን ከክፉ ነገር ይሰውርልን

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሃሌ ሉያ
ርኢክዋ፣ አእመርክዋ፣ አፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን

ሃሌ ሉያ
ቤተ ክርስቲያንን አየኋት፣ አወቅኋት፣ ወደድኋት።
"ቅዱስ ያሬድ"

የቅዱስ ያሬድ በረከት አይለየን ።



#share

ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ለኤማሁስ መንገደኞች የቀረበው ጥያቄ

ሐዋርያት ቤት ዘግተው ተቀምጠው ሳለ ፥ ነገሩን ለማየት አንዳንዶችም ወደ ኢየሩሳሌም በሚመጡበት ዕለት ሁለት ሰዎች ደግሞ ኢየሩሳሌምን ለቀው ወደ መንደራቸው መንገድ ጀምረዋል ፤ እኒህ ሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ የነበሩት ሰዎች ሉቃስና ቀለዮጳ ሲባሉ መዳረሻቸውም ኤማሁስ የምትባል መንደር ነበረች። (ማር16፥12 |ሉቃ 24፥13) አስቀድሞ ሁለት ሁለት አድርጎ ለአገልግሎት ልኳቸው ነበር በዚህ መንገድ ግን ሁለት ሆነውና ጠውልገው ተልዕኮ የሌለውን ጉዞ እያደረጉ ነው።

ከእኛ ዘንድም እንደነዚህ መንገደኞች ለአገልግሎትና ለድኅነት ተጠርተው እስከመጨረሻው ጸንተው እንዲቆዩ ከታዘዙባት ኢየሩሳሌም ተስፋ ማድረግ ተስኗቸው በዚህ መሆን ለኛ መልካምነቱ ምኑ ላይ ነው ? ብለው ፥ ልቡናቸው ደክሞ መንገድ የጀመሩ ግን ሁለት ሳይሆኑ ብዙዎች ናቸው ።

እኔ መንገድ ነኝ ያለ ከሦስቱ አካል አንዱ የሆነ ጌታ በመንገዳቸው ሦስተኛው ሰው ሆኖ ፤ ስለሚነጋገሩት ነገር ጠየቃቸው መንገደኞቹ በእነዚያ ዕለታት ስለሆነውና ስለእምነታቸው ተስፋ ያደረጉት ባለመሆኑም ማዘናቸውን ነገሩት። (ሉቃ 24፥17)

እኒህን የ 60 ምዕራፍ መንገደኞችን ነገር ገታ እናድርግና ፤ እኛስ በመንገዳችን ስለምን እየተነጋቨገርን አለን ? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ

ወደ ኢየሩሳሌም ስንመጣ እንደ ሰብአ ሰገል እርሱን ለማየት ወደን የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው ? ብለን ከልባችን እየፈለግነው ወይስ እንደእነዚህ መንገደኞች በመንገድ ደክመን በሥራና በቃል ግን ብርቱ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ እየተጠያየቅንና እየተመራመርን ነን ?
እንጀራውን {ሥጋውን} በልተን ያንንም ጽዋ {ደሙን} ጠጥተን ስንመለስ ሐዋርያው እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ እንዳለን ስለኛ መሞቱን እየተናገርን ነው ? (1ኛ ቆሮ 11 ፥26) በመጓጓዣ ተቀምጠን ስንሳፈርስ የሀገራችን ሰው እንደሆነው ጃንደረባ ነቢዩ ይህን ስለማን ይናገራል ? ብለን ስለክርስቶስ ሰው መሆን ለማወቅ እየወደድን ይሆን ? እንጀራ ቆርሰን እየተመገብን ሳለን ስለሕይወት እንጀራ ስለሆነው እርሱ ፥ እንጀራን አበርክቶ መመገቡንም እያደነቅን በልባችን እናንግሰው ብለንስ መክረናል ? መዝሙርና ዝማሬ መንፈሳዊም ቅኔን እየተቀኘንስ ዘምረናል ?

በሕይወታችና በውሏችን በምናደርጋቸው ነገራት ሁሉ መንፈሳዊ ጉዳዮችን እርስበእርስ ለመነጋገር ብዙ ምርጫዎች ቢኖሩም እኛ ግን "ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን ?" እየተባባልን እርስበርስ ምንፎካከር ፥ ርስት ለመውሰድ እንደ ገበሬዎቹ ኃጢአት ለማድረግ የምንማከር ፥ " እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ" (ዘካ 8፥16) ብንባልም ሐሰትና ሽንገላን ስለሰውም በሹክሹክታ የምነጋገር ነን ፤ የታዘዝነውን ቃል መናገር ትተን በመንገዳችን ዱላ የምናነሳ በለዓሞች ሆነናል ።

እንዳናውቀው የልባችን ዓይን ተይዞ የማናስተውል ፥ መጻሕፍትና መምህራን የተናገሩትን ሁሉ ከማመን ልባችን የዘገየ ፥ በሩቅ በምናያት በሰማይ ብቻ ያለን መሰለን እንጂ እርሱ በሁሉ የመላ ጌታ ነውና በእኛ መካከልም ተገኝቶ እንደ ሁለቱ መንገደኞች እንዲህ ሲል ይጠይቀናል < እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሯቸው እነዚህ ነገሮች ምንድን ናቸው ? > (ሉቃ 24፥17)

✍ ዲያቆን ኃይለሚካኤል ዳንኤል
ግንቦት 7፥ 2016 ዓ.ም

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ዕለታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት 1

1ኛ ቆሮንቶስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
¹⁷ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።



ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    /channel/dnhayilemikael
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ፋሲካ አልባ ፋሲካ

ለሃምሳ ቀናት ጾመን  ደርሰን ከኀዘን አጽናፍ
በስግደት በለቅሶ ከርመን ቆመን ከሰቆቃ ጫፍ
እንደ ሐዲስ ኪዳንናዊ ሰው ከርመን ወንጌል ስናጠና
እግዚኦ መሐረነ ጌታ ብለን ጮኸን ሆሳዕና

ሕማምህ መከራህ አልፎ ትንሣኤህ ሲመጣ ፋሲካ
ልክ እንደ ኦሪት ሰው ሆንን ሮጥን እንስሳ ፍለጋ
እንደ ክርስቲያኖች ወግ ሥጋህንበልተን እንደመዳን
በግና ዶሮ ልናሳድድ ሔድን ወደ ብሉይ ኪዳን

ስንት ሰዓት ልቁረብ ማለት ትተን የእርዱ ነገር አስጨነቀን
ከትንሣኤህ ዕለት ቆመን የልብ ትንሣኤ ራቀን
የመቃብርህን ውጪ ቆመው ደጅ ደጁን ከጠበቁ
ሕያው ጌታ መሆንህን  ክብርህን ጭራሽ ካላወቁ
ከሮማውያን ወታደሮች በምን ተለየን እኛ
ሥጋህን ተቀብለን ካልሆነን የነፍስ መዳኛ

ከቶ እንዴት ይከበራል ወደ አንተ ሳይቀርቡ ትንሣኤ?
ለእኛ አልነበረም ወይ ያ ዕንባ ያ ሁሉ ኤሎሄ ኤሎሄ
የከበረው ሥጋህ ዛሬ በእኛ ውስጥ ካልተቀበረ
ምኑን ትንሣኤ ተበሰረ ምኑን ፋሲካ ተከበረ?

ይቅር በለን ጌታችን ሆይ በዶሮ ሥጋ ላከበርንህ
የሥጋችንን ስናሳድድ በትንሣኤህ ቀን ለቀበርንህ
በሞትህ ሙት ያስነሣህ ሆይ እኛንም አስነሣን ዛሬ
ደርቀን አንቅር በኃጢአት አድርገን የትንሣኤህ ፍሬ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ቀዳም ስዑር
ሚያዝያ 2016 ዓ.ም.
🌿


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

2ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፈ 5

6 እንግዲህ ሁልጊዜ እመኑ ጨክኑሞ በዚህ ሥጋ ሳላችሁም እናንተ እንግዶች እንደ ሆናችሁ ታውቃላችሁ ከሥጋችሁ ተለይታችሁ በሄዳችሁ ጊዜ ወደ ጌተችን ትሄዳላችሁ ።
7 በእምነት እንሄዳለን በማየትም አይደለም
8 ታምነናል ይልቁንም ከሥጋችን ተለይተን ወደ ጌታችን እንሄዳለንና ደስ ይለናል ።
9 አሁንም ብንኖርም ብንሞትም እርሱን ደስ ለማሰኘት እንጥራለን ።
10 መልካም ቢሆን ክፉም ቢሆን በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንሰማለንና

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖


❖❖❖❖ ታማኝነት ❖❖❖


መጽሐፍ : ቅዱስ : እንዲህ : ይላል :- «በጥቂቱ : ታምነሃል : በብዙ : እሾምሃለሁ፤..." (ማቴ. 25 ፥ 2።)

ይህም ፡ ማለት ፡ በምድራዊ ፡ ነገሮች ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ስትገኝ ፡ በሰማያዊ ፡ ነገሮች ፡ ላይ ፡ እሾምሃለሁ ፡ ማለት ፡ ነው። በዚህኛው ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከቆየህ ፡ በዘላለማዊነት ፡ ውስጥ ፡ እሾምሃለህ ፡ ማለትም ፡ ነው።

ይህ ፡ መመሪያ ፡ በብዙ ፡ መስኮች ፡ ላይ ፡ ተግባራዊ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል . . .

༒ ዘመዶችህን ፡ በመውደድ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጠላቶችህንም ፡ በመውደድ ፡ ላይ ፡ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን ፡ የምትወድበትን ፡ ጸጋ ፡ ያድልሃል ፡ ማለት ፡ ነው፡፡

༒ በትርፍ ፡ ጊዜዎችህ ፡ እግዚአብሔርን ፡ የምታገለግል ፡ ከሆንህ ፡ በሕይወትህ ፡ ጊዜ ፡ ሙሉ ፡በእርሱ ፡ ላይ ፡ ትኵረት ፡ የምታደርግበትን ፡ ፍቅር ፡ ያድልሃል፡፡

༒ የፈቃድ ፡ ኃጢአቶችን ፡ ከአንተ ፡ በማስወገድ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ፈቃድህ ፡ ከሚመጡ ፡ ኃጢአቶች ፡ ነጻ ፡ ያወጣሃል።

༒ ንቁ ፡ ኅሊናህን ፡ ከክፉ ፡ ሀሳቦች ፡ የምትጠብቅ ፡ ከሆንህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ንቁ ፡ ያልሆነው ፡ ኅሊናህን ፡ ንጽሕና ፡ ይጠብቅልሀል። ከዚህ ፡ በተጨማሪ ፡ የሕልሞችህን ፡ ንጽሕናም ፡ ይጠብቅልሀል።

༒ ልጅ ፡ እያለህ ፡ ታማኝ ፡ ከሆንህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ውጊያዎች ፡ በሚበዙበት ፡ በወጣትነት ፡ ዘመንህ ፡ ውስጥም ፡ ታማኝነትን ፡ ያድልሃል፡፡

༒ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ላይ ፡ በቃላት ፡ ብቻ ፡ የማትፈርድባቸው ፡ ሆነህ ፡ ለመገኘት ፡ ታማኝ ፡ ከሆንህ ፡ ይበልጥ ፡ አስቸጋሪ ፡ በሆነው ፡ በሀሳብ ፡ እንዳትፈርድባቸው ፡ ያስችልሃል፡፡

༒ ልክ ፡ እንደዚሁ ፡ ራስህን ፡ ከውጪያዊ ፡ ንዴት ፡ በመጠበቅ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከውስጣዊ ፡ ቁጣ፣ ንዴትና ቅናት ፡ ነጻ ፡ ያወጣሃል።

༒ በተለመዱ ፡ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፡ ፍሬዎች) ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ የመንፈስ ፡ ስጦታዎችን ፡ ያድልሃል!

በመጀመሪያው ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ካልተገኘህ ፡ ሁለተኛውን ፡ ፈጽሞ ፡ ልታገኘው ፡ አትችልምና፡፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ ፡ የሚፈትሽህ ፡ በጥቂት ፡ ነገር ፡ ነው:: በዚህች ፡ በጥቂቷ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ መሆንህን ፡ ካረጋገጥህ ፡ እርሱ ፡ በሚበልጠው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና ፡  አለመታመንህን ፡ በጥቂቷ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡  ከገለጽህ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ በሚበልጠው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ አይሾምህም። መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ እንዲህ ፡ ይላልና:- «ከእግረኞች ፡ ጋር ፡ በሮጥህ ፡ ጊዜ ፡ እነርሱ ፡ ቢያደክሙህ ፡ ከፈረሶች ፡ ጋር ፡ መታገል ፡ እንዴት ፡ ትችላለህ?» (ኤር. 12 ፥ 5።)

ብዙ ፡  ሰዎች ፡ ዝቅተኛውን ፡ ኃላፊነት ፡ መወጣት ፡ ሳይችሉ ፡ ከፍተኛውን ፡ ኃላፊነት ፡ ለመቀበል ፡ ማሰባቸው ፡ እጅግ ፡ አስደናቂ ፡ ነገር ፡ ነው። እነዚህ ፡ ሰዎች ፡ በተሰጣቸው ፡ ጸጋ ፡ ሳይጠቀሙ ፡ ተጨማሪ ፡ ጸጋ ፡ እንዲሰጣቸው ፡ የሚጠይቁ ፡ ናቸው። ይህን ፡ ሲያደርጉም ፡ «በጥቂቱ ፡ ታምነሃል ፡ በብዙ ፡ እሾምሃላሁ፤...» የሚለውን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ በመዘንጋት ፡ ነው። ይህ ፡ ቃል ፡ ለእነርሱ ፡ እንደ ፡ ሁኔታው ፡ የሚወሰንበት ፡ ነው ፡ የሚሆነው፡፡


════•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ════
  ✞❀
/channel/dnhayilemikael ❀✞
════•ೋ•✧๑♡๑✧•  ════

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✝ስለ ምሥጢራተ ቅድሳት ✝

✝✝✝ ከኢትዮዽያ #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ ምዕመናን አብዛኛው #ከቅዱስ_ሥጋውና_ክቡር_ደሙ የራቀ መሆኑን ሳስብ በጣም አዝናለሁ! ✝✝✝

✝ ግን ለምን ??? ✝

✝ ለምን ብዙዎቻችን #ሕይወት_መድኃኒት ከሆነው ማዕድ ተለየን ??? ✝

✝ ከቅዱስ ሥጋው ሳይበሉ: ከክቡር ደሙ ሳይጠጡ መዳን ይኖር ይሆን ??? ✝

✝ በሰማያዊው ዙፋን #በዘለዓለም_አምላክ_በክርስቶስ ፊትስ በቂ መልስ ይኖረን ይሆን ??? ✝

✝ሁልጊዜ ባልረባ ምክንያት ሕይወት ከሆነው #ማዕደ_ክርስቶስ እስከ መቼ እንርቃለን ???

+እርሱ ግን አሰምቶ ይጠራናል:: "ኑ! ሥጋየን ብሉ: ደሜንም ጠጡ" ይለናል:: "ሥጋየን የሚበላ: ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በእርሱ አድሬበት እኖራለሁ" ይለናል:: (ዮሐ. 6:56)

+ሌላ መንገድ አለ እንዳይመስለን ደግሞ "የሰውን ልጅ (የክርስቶስን) ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም" (ዮሐ. 6:53) የሚል ተግሣጽን ልኮልናል::

+ቤተ ክርስቲያን እኛን ወደ #ምስጢረ_ቁርባን ለማድረስ ከእነዚህ የተረፈ ነገር አልጫነችብንምኮ!

¤በሃይማኖት መኖር (መመላለስ)
¤ከክርስቶስ (ከጌታችን) ጋር ለመኖር ቁርጥ ውሳኔ
¤በመምሕረ ንስሃ ሥር መጠለል
¤በንስሃ ሕይወት መመላለስና
¤ቀዋሚ የሕይወት መሥመር (ጋብቻ ወይ ምናኔ) መያዝን ትሻለች እንጂ መቼ ሌላ ቀንበር ጫነችብን!

+እናም የመንፈስ ወንድሞቼና እህቶቼ . . .
¤የራቅን እንቅረብ!
¤የቀረብንም እንበርታ!
¤የበረታንም እንጽና!
¤የጸናንም ደካሞቹን እንርዳ! (ይህ በጌታ ዘንድ ዋጋው ትልቅ ነውና!)

☞#የምሕረት_ጌታ #ለምሥጢራተ_ቅድሳት የምንበቃበትን የምሕረት ዘመን ያምጣልን::

☞ግን እናስብበት!!!

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

. Dn Yordanos Abebe
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሰው ሃይማኖቱን መጠበቅ የሚችለው ስለ ሃይማኖቱ አምስት ነገሮች ሲያውቅ ነው ፡፡

💠 1/ ምን እንደሚያምን
💠 2/ ለምን እንደሚያምን
💠 3/ ያመነውን እንዴት መፈጸም እንዳለበት
💠 4/ ያመነውን እንዴት ለሌሎች ማሳወቅ እንዳለበት
💠 5/ እምነቱን የሚፈተን ነገር ሲመጣ እንዴት መከላከል እንዳለበት

ማወቅ አለበት

ሃይማኖታችንን ለመጠበቅና በሃይማኖታችን ጸንተን ለመኖር መንፈሳዊ ትምህርትእንማር


መሰረተ ሚዲያ


የቴሌግራም አድራሻ/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

በሰርጓ ቀን ካህኑ አባቷ ሁለት ዲያቆን ወንድሞቿ እና ዲያቆን ባሏ ቀድሰው ያገባችው ሙሽሪት

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? +

ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት::

"ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39

ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ::

"ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ::
ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20)

እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም?
ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ?
"ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር::

የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23)

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን?

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ::

"ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም::

ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13)

ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ::

ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ::

አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር::

የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ?

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 21 2016 ዓ.ም. ተጻፈ

"ማርያም ገጸኪ እፈቱ ርእየ
ድንግል ድንግል ንዒ ኀቤየ
እስመ ኪያኪ ጸምአት ነፍስየ"
ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪኀ ማርያም ኃይለ ሚካኤል

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ገለባ ልብ ስላለን እንጂ፣ታዋቂ ሰባኪ ካልተጋበዘ ቤተክርስቲያን ሂደን ወንጌል የማንሰው? ከእግዚአብሔር በላይ ዝነኛ ኑሮ ነው? ካለ ንገሩኝ።ይህንን ትውልድ የእውነት ታዘብሁት። እርሱ ግን በወደደው አድሮ ይናገራል።( ጸጋ የበዛላችሁ የምትባሉ አትቀየሙኝ ፡ )
-

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ኦርቶዶክሳዊ ሚዛን

ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ክፍል ፩

ብዙው ሰው እጁ እስኪላጥ ሲያጨበጭብ ከርሞ አሁን ደግሞ ላንቃው እስኪሰነጠቅ እየጮኽ ነው። በእርግጥ የመንጋነት ፍጻሜው ውድቀት እና ማፈር እንዲሁም ፀፀት ነው። አብዛኛው ሰው መንጋ ነው። የሰባኪ መንጋ አለ። የአጥማቂ ነኝ ባይ መንጋ አለ። የፖለቲከኛ መንጋ አለ። የአክቲቪስት መንጋ አለ። አንዳንዱ አሁንም ከመንጋነት ወደ መንጋነት የተዘዋወረ አለ። የሆነ ሰው መንጋ ሆኖ ይከርምና የተከዳ ሲመስለው እገሌ ግን ያን ጊዜም ትክክል ነበር ብሎ ለዚያ ሰው ወዶ ገብ መንጋ ይሆናል። እኒህ ሁሉ መንጋቸውን እንደፈለገ ይነዱታል። መንጋው ደግሞ አያሰላስልም። መንጋ እንደ ሸንበቆ ነው። ሸንበቆ ነፋስ ወደነፈሰበት ነው ሁል ጊዜም የሚያዘነብለው። ነገር ግን ነፋሱ በጣም አይሎ ነቃቅሎ ሲጥለው ያን ጊዜ ያማርራል። አብዛኛው ሰው መለኪያ የለውም። መስማት የሚፈልገውን እየነገሩ የሚወስዱት ሰዎች ብዙ ናቸው። በርበሬ ተወዶ ከሆነ ቤተክርስቲያን ሰባኪው አስተምሮ ሲጨርስ "ፈጣሪያችን የበርበሬን ዋጋ ይቀንስልን" ሲል "አሜን" የሚለውን መንጋ ብዛት አስተውልማ። ደንበኛው ሊቅ መጥቶ አስተምሮ ሲጨርስ "ንሥሓ ገብተን ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ያብቃን" ሲል አሜን የሚለው ይቀንሳል። ይሄ በጣም አሳዛኙ ክስተት ነው። ሰው መስማት ያለበትን ከሚሰማ ይልቅ መስማት የሚፈልገውን መስማትን እየመረጠ ነው። ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተዋጀችው የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችው ስለበርበሬ እንዲወራ ነው እንዴ!?። ማንኛውም ሰው ፕሮፌሰርም፣ ዶክተርም፣ ኢንጂነርም፣ ሳይንቲስትም፣ ፖለቲከኛም፣ ፓትርያርክም፣ ቄስም፣ ጳጳስም፣ መምህርም፣ ምእመንም፣ ዲያቆንም ሁሉም ፍጡራን ናቸው። እንደፍጡርነታቸው የሚለኩበት መለኪያም አንድ ነው። አንተ ሰው ለምን የፖለቲከኛ መንጋ ትሆናለህ!? ፖለቲከኛም እንደ አንተ ሰው መሆኑን ዘነጋሃው እንዴ!? እንደ አንተ ሰው ከሆነ አንተም እርሱም የምትዳኙበት መለኪያ አንድ ዓይነት ነው። አንድ ዓይነት ከሆነ ደግሞ ለምን ራስህን የፖለቲከኛና የሰባኪ መንጋ ታደርጋለህ!? የማንም መንጋ አትሁን። እግዚአብሔር ራስህን አስችሎ ስለፈጠረህ ራስህን ችለህ አስብ። በሌሎች ጭንቅላት ካልተመራሁ አትበል። ሩጥ ሲሉህ የምትሮጥ ቁጭ በል ሲሉህ ቁጭ የምትል ከሆነ ፈጣሪ በነጻነት ራስህ ተመራምረህ እንድትመርጥ የሰጠህን እድል መንጋ ለሆንክለት አካል አሳልፈህ ሰጠኽው ማለት ነው። ይህ ደግሞ እገሌ አይሳሳትም ወደማለት ጽንፍ ያወርድሀል። ከዚያ ያ ሰው ሲሳሳት አንተ ማፈሪያ ሆነህ ትቀራለህ። ኦርቶዶክሳዊው ሰው ግን ሁሉን የሚመረምርበት አእምሮ ከፈጣሪ ስለተሰጠው በራሱ መንገድ በራሱ መለኪያ ነገሮችን ይመረምራል እንጂ የማንም መንጋ አይሆንም። ታድያ በዓለማችን የሚደረጉ ነገሮችን ለመመርመር ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ያስፈልገናል። ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ሁልጊዜም ትክክል ነው። አያጸጽትም። ዘመናትን ተሻጋሪ ነው። ልበ ሙሉ ያደርጋል። ምክንያቱም የኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ባለቤት እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ምንድን ነው?! ከመንጋነት እንዴት እንላቀቅ የሚሉ ጉዳዮችን በ7 ክፍል እንመለከታለን።

ይከታተሉ። ክፍል 2 ይቀጥላል ..

መ/ር በትረ ማርያም

#share

ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇፦
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ይህንን የመሰለ ሕንጻ ቤተ መቅደስ 👇
👉• መቅደስ ቢኖረውም ይጎበኛል እንጂ አይቀደስበትም
👉• አሁን ምዩዚዬም ነው
👉• ሁሉ ተሟልቶ የተሠራለት ቢሆንም አምልኮ አይፈጸምበትም
👉• መጠመቂያ ቢኖረውም የሚጠመቅበት የለም
ምክንያቱም የሀገሩ ሰዎች ሃይማኖታቸውን ትተዋል ሃይማኖት አልባ ሆነዋል ....ከሃይማኖት ባዶ መሆናቸውን በኩራት ያስጎበኛሉ...የካቴድራሉን ሕንጻ ከአገልግሎት ባዶ መሆኑን በኩራት ይናገራሉ!!!!

እኛም ይህንን አይተን ጎብኝተን ስለ ራሳችን
👉• ሀገር
👉• ሃይማኖት
👉• ቤተ ክርስቲያን
👉• ባህል ...ተነጋግረን ከመቅደሱ ወጣን
እኔም ይህንን ቃል አስቤ አዘንኩ 👇
ማቴዎስ 23
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁸ እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።
³⁹ እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።"

👉እንደ አማኝና አገልጋይ ሁሌም የሚሰማኝ ይህ ነው !

👉ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ቤተክርስቲያኗን ከነሥርዓቷ በምን ያህል መጠን ይረከባታል?

👉እኛ ስለ ዘርና ስለ ብሔር ስለ ሥልጣንና ሢመት ስለ ገንዘብና ኑሮ ስናስብ ትውልዱን ከእጃችን እየተቀማን ቤተ ክርስቲያንን ዝቅ አድርገን የኛን ልዕልና ብቻ ለማሳየት እየተጋን የት እንደርስ ይሆን?....

👉የቤተ ክርስቲያን አምላክ ትውልዳችንን በሃይማኖት ያጽናልን ይጠብቅልን
ተረካቢ አያሳጣን!!!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

ከ ኖርዌይ ትሮንዳሂም
ግንቦት 5 /2016 ዓ.ም

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ክርስቲያን_የሆነ_ሰው_ሳያነብ_እንዳያልፍ!!!

#ስንት_ዓመት_ተማርን?

❖አሁን የምንሰራው ስራ ለሥጋዊ ኑሮ የሚሆን የሚጠቅም ነው በዚች ምድር ላይ ሳለን እንዳይርበን እንዳይጠማን እንዳይበርድን ኑሮአችን ለማመቻቸት እንወጣለን እንወርዳለለን🤔
✟👉✥ከሕፃንነታችን ጀምሮ እንማራለን
ሶስት ዓመት ጊዜ ወስደን መዋእለ ሕፃናት ተምረናል
👉 አስራ ሁለት ዓመት ጊዜ ሰጥተን 12 ክፍል ጨርሰናል(አቋርጠንም ያለን ልንኖር እንችላለን
👉 አምስት ዓመት በላይ ጊዜ ሰጥተን በድግሪ በማስተር ተመርቀናል
👉ባጠቃላይ የሥጋ ሥራ ለመያዝ ከሃያ ዓመት በላይ ተምረናል
🤔እንደዚህም ተምረን ስራ አጥተን በስራ ፍለጋ ደክመናል ወንድሜ(እህቴ) ሆይ አሁን ከ20 ዓመት በላይ የተማርነው ትምህርት ለስንት ዓመት ያሰራናል ?
🤔ጡረታ እስክንወጣ ነው ከዛ በሇላ የተማርነው ትምህርት አያገለግለንም
ከ20 ዓመት በላይ ስንማር የፈተፈተነው ጊዜ እናስብ ጭንቀቱን ድካሙን እንቅልፍ ማጣቱን
ከትምህርት ቤት ለመድረስ የእግር ጉዞውን ሁሉ አንርሳ ያ ሁሉ ደክመን የተማርከው ስንሞት አይጠቅመንም 🙊
🤔ሥጋችን መቃብር ሲገባ ምድራዊ እውቀታችን አብሮ ይቀበራል
👉በህይወት እያለን ጡረታ የምንወጣው መስራት አትችሉም ተብለን ነው
👉🤔ከ20 ዓመት በላይ በተማርነው ትምህርት ብንሰራበት 30 ዓመት ቢሆን ነው ያም እድሜ ከታደለህ ነው።
👉🤔ወንድሜ(እህቴ) ሆይ እስቲ ልጠይቃችሁ
ለሥጋችን ስራ ለመስራት ከ20 ዓመት በላይ ተምረናል
#ለነፍሳችን ስንት ዓመት ተማርን?
👉ለነፍሳችን የተማርነው ትምህርት ጡረታ የለውም
በሥጋ የተማርነው የመንግሥት ስራ ያስይዘናል
👉በነፍስ የተማርነው የእግዚአብሔር ስራ ያስይዘናል
የነፍስ ትምህርት ምን ይመስለናል ቃለ እግዚአብሔር ነው
✥#የእግዚአብሔርን ቃል በወር ስንት ሰዓት ተምረናል ?
👉✥በዓመት ስንት ቀን ይሆናል የተማርንበትም ጊዜ እስቲ እንደምረው?
✥ባጠቃላይ የተማርንበት ጊዜ እስክንሞትስ ስንት ዓመት ይሆናል?
👉✥ መቼም የሥጋውን የተምህርት ጊዜ አያክልም
✥በነፍስ የተማርነው ትምህርት ስንት ዓመት እንደሚያሰራልን እናውቃለን ?
✥ቁጥር የማይደርስበት ጊዜ ነው
ዘመናት አልፈነው እንሰራበታለን ለዘላለም ጡረታ አያወጣንም
👉✥እኛ ግን ይሄን ረስተናል ቀኑን ሙሉ ለሥጋችን እንሮጣለን ለነፍሳችን የምንማርበት ጌዜ አጥተናል በሚያልፈው ነገር እራሳችንን ቢዚ አድርገናል ::
👉✥ሁለት ሰኣት ቁጭ ብለን የተለያዩ ፊልም እናያለን 30 ደቂቃ ቁጭ ብለን ወንጌል መማር ይሰለቸናል::
👉✥ሁለት ሰአት ቆመን እያጨበጨብን ኳስ እንደግፋለን 2 ሰአት ቆመን ቅዳሴ ማስቀደስ አቅቶን በዕለተ ሰነበት ተኝተን እናረፍዳለህን
👉✥ልብ ወለድ ዝሙታዊ የሆኑ መጻፎችን በየቀኑ እናነባለን የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍን ለማንበብ ይሰለቸናል
👉✥ለዘፈን የከፈትነውን አፋችንን ለምስጋና ይዘጋል
👉✥ለሀሜት የሚፈጥነው አፋችን ለጸሎት ይዘገያል
👉✥ለእስፓርት የጠነከረው ጉልበታችን ለስግደት ይዝላል
👉✥ለስርቆት የሚላከው እጃችን ለምጽዋት አይታዘዝም
👉✥ወደጭፈራ ቤት የሚገሰግሰው እግራችን ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይተሰሰራል
👉✥ሀሜት የሚሰማው ጆሮአችን ወንጌል ለመስማት ይደነቁራል
👉✥የዝሙት ሸቶ የሚያሸተው አፍንጫችን የመቅደሱን እጣን ሽታ ይፀየፈዋል
👉✥ጫት የለመደው አፋችን ሥጋውን እና ደሙን ረስቶአል
👉✥አልኮል የለመደው አፋችን ፀበሉን ተፀይፎታል
👉✥ ቂም የሚቋጥረው ልባችን ፍቅርን ረስቷል
🤔✥ስናጣ እግዚአብሔርን እንቀርበዋለን ስናገኝ ግን እንርቀዋለን
🤔👉ስንጨነቅ አምላካችንን እንጠራዋለን ስንደሰት እንረሳዋለን
🤔✥ወንድሜ(እህቴ) ሆይ በህይወታችን አንቀልድባት
👉✥ከእኛ በፊት የነበሩት ተዋቂው አዋቂው ሁሉ የት አሉ? 👉✥መቃብር ውስጥ አይደሉምን ?
✟✥✟ይህንን አስበን ከፈጣሪያችን ጋር የሚያገናኝ ስራ እንስራ
✟✥✟ በአዲስ ዓመት አዲስ እቅድ ያስፈልገናል
✟✥✟ወደቤተ ክርስቲያን ሄደን ዘወትር ወንጌል እንማር
✟✥✟ ለማስቀደስ ለመፆም ለመስገድ እንትጋ
✟✥✟ ለንስሐ እንዘጋጅ ቅድሚያ ለነፍሳችን ሁሉን ነገር እናድርግ
❖አንደበታችን ለጸሎት ይትጋ
❖እጅአችን ለምጽዋት ይዘርጋ
❖ልባችን ለምህረት ይነሳሳ
❖ሥጋውን እና ደሙን ለመቀበል እንወስን

👉👉✥ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከአካፈልኩ በኁላ ቻነላችንን ይቀላቀሉ👉 @dnhayilemikael
ሌሎችም እንድማሩበት #ሸር ያድርጉ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔም ጸልዩ!
✥"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን

#ሌሎች_እንዲያነቡትና_እንድማሩበት_አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁ_ሼር_ያድርጉ!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#እንኳን_ለኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን_ታላቁ_ሊቅ_ቅዱስ_ያሬድ_ዓመታዊ_መታሰቢያ_በዓል_አደረሰን!

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ፍትሐ ነገሥት ክፍል ፲__ አንቀጽ 11 ስለ ሕዝባውያን ይናገራል

፩) ወደ ኃጢአት ሥራ የሚሄድ አንድ ሰው ስንኳ ቢኖር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አፍርሷልና ከዓላዊ ጋር ይቆጠራል።

፪) እግዚአብሔር በሰጠህ መልክ ላይ ሌላ መልክ አትጨምር። አትከተብ፣ አትጠቆር።

፫) ያድግ ዘንድ ጸጉርህን አትንከባከበው። ጺምህ አትላጭ። (ለወንዶች)። ሰው ከባሕርይው ያገኘውን መልክ አይለውጥ።

፬) ረቂቅ (ስስ) ልብስ አትልበስ። ለጣትህም የወርቅ ቀለበት አታድርግ። ይህ ሁሉ የዝሙት ምልክት ነውና።


፭) ከደጋግ ሰዎች ጋር ሕይወት የሚገኝባትን የወንጌልን ነገር ተነጋገር። ሁልጊዜ መልካም ነገርን ሥሩ።


፮) የወንድሞቻችሁን በደል ፈጥናችሁ ይቅር ማለት ይገባችኋል። ብትቆጡ ይቅር ሳትሉ አትደሩ።

፯) በክርስቶስ ያመንን እኛ ሥራ ፈት ሁነን መኖር አይገባንም [ቁጥር ፬፻፴፬]። ምእመናን ሆይ ከሚያሳፍር ነገር ራቁ። የማይረባ የማይጠቅም ነገር አትናገሩ።


፰) በአንድ ሰውስ እንኳ ክፉ ነገር አትናገር። ሁለት አንደበት አትሁን። ክፉ ምክር አትምከር። ቀናተኛ አትሁን። ቁጡ ብስጩ፣ ጠብ ክርክር ወዳጅ አትሁን።


፱) ሰው የሰይጣን ማደሪያ የሚሆነው በነፍስ ጽነት ሲገኝባት ነው።

፲) ያገኘኽውን ሁሉ አመስግነህ ተቀበል።

፲፩ ......ይቀጥላል ....



#share

ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
   ╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ትንሣኤ ልቡና

✟ሰው አስቀድሞ በልቡ ካልተነሣ የኋለኛውን ትንሣኤ ማለትም ትንሣኤ ዘለክብርን ገንዘብ ማድረግ አይችልም።

❖“ዝናቡ እንዴ ነበር?” ለሚለው የአበው ጥያቄ ምላሹ “በየደጅህ እየው” እንደኾነ
ሁሉ በኋለኛው ዘመን በቀኝ የምንቆምበትን፣ “እናንተ የአባቴ ቡሩካን
ኑ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ"

የምንባልበትን ትንሣኤ ዘለክብርን ዛሬ በየልቡናችን ማየት አለብን።

ያኔ ለመነሣትና ክብር ለማግኘት አሁን በንስሓና በሥጋ ወደሙ ተወስኖ መጓዝ ያስፈልጋል እሱ ነው ትንሣኤ ልቡና።

✣ ይኽንን ነው አስቀድመን ገንዘብ ማድረግ ያለብን፡፡
❖ዛሬ በቃለ እግዚአብሔር እየተመራን፣ በምክረ ካህን፣ እየተጠበቅን በንስሓ
ሕይወት እየኖርን በቅዱስ ቁርባን ታትመን ልባችንን ለአግዚአብሔር
አያስገዛን ከተገኘን የፊተኛው ትንሣኤ ባለቤት ኾነናል ማለት ነው
“በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፡፡ሁለተኛው ሞት
በእርሱ ላይ ሥልጣን የለውም
፡፡

❖ ማለትም ከትንሣኤ አስድማ በምትሆን
በትንሣኤ ልቡና ከምስጢረ ንስሓ ከምስጢረ ቁርባን ዕድል ፈንታ
ጽዋዕ ተርታ ያገኘ ሰው ንዑድ ክቡር ነው” ራእ. ፳፥፮

ስለኾነም ርስተ መንግሥተ ሰማያትን ለምንወርስበት የትንሣኤ ዘለክብር ባለቤቶች ለመኾን እንድንበቃ ከወደቅንበት ለሚያነሣን ከረከስንበት ለሚያነጻን ከራቅንበት ለሚያቀርበን ለምስጢረ ንስሓ /ትንሣኤ ልቡና/ እንዘጋጅ ዘንድ ፈቃደኞች እንሁን የፊተኛው ትንሣኤ ይኽ ነውና፡፡
አምላክ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ጅማሬያችንንና ፍጻሜያችንን
ሁል ጊዜም ያሳምርልን አሜን፤
ይቆየን።


/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ግንቦት_ልደታ ስናከብር ፈጽሞ ማድረግ የሌለብን ነገሮች

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ !!!

#ነገር ግን በበጎ ነገሮች #ሰበብ_ክፉ_ዓላማዉቅ ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ #የግንቦት_ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡

#በዚህ ዕለት አንዳንዶች #ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ #በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡
#እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡
#እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ በምሕረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel