#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn
📌 "አስታውስ"
➯ ደካማነትህን አስታውስ፣ ያንጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም፡፡
➯ የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል፤ በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል፤ ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል፡፡
➯ የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፤ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል፡፡
➯ ሞት እንዳለ አስታውስ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ
✍️"ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው፡፡" ማለትን ትረዳለህ፡፡
📖መኬ 1፥14
➯ በእግዚአብሔርፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፣ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና፡፡
➯ ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፤ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣
✍️"በዋጋ ተገዝታችኋልና" እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡
📖1ኛ ቆሮ 6፥20
➯ በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ፡፡
➯ በዚህ ዓለም እንግዳመሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፤ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ፡፡
➯ በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ፤ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና፤ ዘላለማዊው ሕይወትህን አስታውስ፣ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ፡፡
➯ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ፤ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል፡፡
➯ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፡፡ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን፤ ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን፡፡
📌 ምንጭ
✍️አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
አባታዊ ምክር
✥እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።
✥የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።
✥የተወደዳችሁ ልጆቼ ፡ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።፡
✥የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።
✥ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።
✥ልጆቼ እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡
✥ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✥
ሰኔ ፴ ልደቱ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
👉በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር፤ ሚስቱም ኤልሣቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ እርሷም የመውለጇ ዘመን አልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ሁለቱም በእግዚአብሔር የታመኑ ጻድቃን ነበሩ፡፡
👉ከዕለታት በአንድ ቀንም ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ለአገልግሎት በገባበት ሰዓት በዕጣን መሠውያው በቀኝ በኩል የእግዚአብሔር መልአክ ቆሞ ታየው፤ እንዲህም አለው ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ አትፍራ፤ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ተሰምቷልና፤ ሚስትህ ኤልሣቤጥም ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ደስታና ሐሤትም ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል፡፡ እርሱም የአባቶቻችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓዲያንንም ዐሳብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስ ቅዱስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል፡፡›› ዘካርያስም መልአኩን እንዲህ አለው፤ ‹‹ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ? እነሆ፥ እኔ አርጅቻአለሁ፤ የሚስቴም ዘመንዋ አልፏል፡፡›› መልአኩም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንም እነግርህና አበሥርህ ዘንድ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጸመውን ነገሬን አላመንኽኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም ይሳንሃል፡፡›› (ሉቃ.፩፥፲፫-፳)
👉ከዚህም በኋላ ሚስቱ ኤልሣቤጥ ፀነሰች፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ እናቱ ኤልሣቤጥን ለመጠየቅ በሄደችበት ወቅት በማሕፀኗ ውስጥ ሳለ ሕፃኑ ለእግዚአብሔር ልጅ ሰገደ፡፡ (ሉቃ.፩፥፴፱-፵፩)
👉ኤልሣቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች፡፡ መውለዷን የሰሙ ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም ደስ ተሰኙ፤ ልጁንም ስምንት ቀን በሞላው ጊዜ ሊገረዙት መጡ፤ ስሙንም በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ወደዱ፤ ነገር ግን እናቱ ዮሐንስ ተብሎ መጠራት እንዳለበት ተናገረች፡፡ ሆኖም ግን ከዘመዶቿ መካከል ስሙ ዮሐንስ የሚባል ባለመኖሩ አባቱ እንዲወስን ካህኑ ዘካርያስን በጠየቁት ጊዜ መናገር የተሣነው ዲዳ ነበርና ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ሲጽፍ ሁሉም ተደነቁ፤ በዚያን ጊዜም የዘካርያስ አንደበት ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡
👉ካህኑ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ በመላበት ጊዜ እንዲህ ብሎ ትንቢት መናገር ጀመረ፤ ‹‹ይቅር ያለን፥ ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ከባርያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፤ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ በቅዱሳን በነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፡፡ ከጠላቶቻችን እጅ፥ ከሚጠሉንም ሁሉ እጅ ያድነን ዘንድ፤ ቸርነቱን ከአባቶቻችን ጋር ያደርግ ዘንድ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም ያስብ ዘንድ፤ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ያስብ ዘንድ፤ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ ያለ ፍርሃት፥ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ በዘመናችን ሁሉ እንድናመልከው ይሰጠን ዘንድ፤ አንተም ሕፃን፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱንም ትጠርግ ዘንድ በፊቱ ትሄዳለህና፡፡ ኃጢአታቸው ይሰረይላቸው ዘንድ መድኃኒታቸውን እንዲያውቁ ለአሕዛብ ትሰጣቸው ዘንድ፤ ከአርያም በጎበኘን በአምላካችን በይቅርታውና በቸርነቱ፤ በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩት ብርሃኑን ያሳያቸው ዘንድ፥ እግሮቻቸውንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ፡፡›› ሉቃ.፩፥፷፰-፸፱
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነት እና ተራዳኢነት አይለየን፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!
/channel/dnhayilemikael
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ማንም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ከመጀመሪያ ጀምሮ መልካም ነገርን መምረጥ መልካም ነው፤ በመልካምነት አለመቀጠል ግን ብዙ ወቀሳን ያመጣል፤ የብዙ ሰዎች ክፉ መኾን በዚሁ የሚመደብ ነው ፤ ብዙዎች ሕይወታቸውን በመልካም ጀምረው በኋላ ግን በክፋት መርዝ ተጠምቀው ሲሰክሩ ተመልክቻለሁ፡፡
❖ እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ ምንም እንኳን አሁን ወደ ክፋት ጥልቅ ወርዳችሁ ቢኾንም
✍️"ከዚሁ ተመልሰን መውጣት አይቻለንም ፤ መለወጥም አይኾንልንም" በማለት ተስፋ የምትቆርጡ አትኹኑ፤ እናንተ ስትፈቅዱ እግዚአብሔርም ሲረዳችሁ ከክፋት ዐዘቅት መውጣት በእጅጉ ቀላል ነውና፡፡
❖ ከኹሉም በላይ አመንዝራ ተብላ በከተማው ትታወቅ የነበረችውን ሴት በመልካምነቷ እንዴት እንደምትወደስ አልሰማችሁምን? እየነገርኳችሁ ያለሁት በወንጌለ ዮሐንስ ስለተጠቀሰችው ሴት አይደለም ፤ በእኛ ዘመን ስላለችውና ፍኒሳ ከተባለችው ክፉ ከተማ ስለተገኘችው ሴት እንጂ ይህቺ ሴት አስቀድማ በመካከላችን በአመንዝራነቷ ትታወቅ ነበር፤ በክብር ቦታ ሁሉ የመጀመሪያውን ስፍራ የምትይዝ ሴት ነበረች፤ ስሟ በሀገሩ ሁሉ የገነነ ነበር በእኛ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በሲልስያና በቀጰዶቅያም የታወቀ ነበር፡፡
❖ ይህቺ ሴት ብዙ ከተሞችን አፍርሳለች ፤ የብዙ ወላጅ አልባ ሕፃናትን ንብረት በልታለች፤ ብዙዎች "መተተኛ ናት" ይሏታል ውበቷን ብቻ ሳይኾን መድኃኒትም ጭምር ትጠቀም ነበርና፡፡
❖ ከዚሁ የተነሣ በአንዱ ቀን የንግሥቲቱን ልጅ እስከ ማማለል ደርሳለች፤ ጭካኔዋ ክፉ የክፉ ክፉ ነበር፤ ከዕለታት በአንዲቱ ቀን ግን ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ተለውጣ አየኋት፤ ራሷን በእግዚአብሔር የጸጋው ዙፋን ፊት ድፍት ብላ ስታለቅስ አየኋት አሁን የቀድሞ ክፉ ሥራዎቿ ኹሉ ርግፍ አድርጋ ትታለች በእርሷ ላይ ከነበሩት አጋንንት ጭፍራ ተፋትታ የክርስቶስ ሙሽሪት ኾናለች፡፡
❖ በእውነት ከእርሷ የሚከፋ ሰው በዓይኔ አላየሁም አሁን ግን ራሷን ከእንደዚህ ዓይነቱ ክፉ ሥራ ከልክላለች፤ ከዚህ በፊት ስትለብሳቸው የነበሩት የምንዝር ጌጦች ስፍር ቁጥር የላቸውም አሁን ግን እነዚህን ኹሉ አወላልቃ ጥላ ለእግዚአብሔር በሚገባ የማቅ ልብስ ራሷን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር አድርጋለች፡፡
❖ ይህቺን ሴት ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ለመመለስ የሀገሪቱ መኳንንት ከዙፋናቸው ወርደው ለምነዋት ነበር ወታደሮች ከነትጥቃቸው መጥተው አስፈራርተው ሊወስዷት ሞክረው ነበር፤ ነገር ግን ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ይመልሷት ዘንድ አልተቻላቸውም፡፡
❖ ይህቺ ሴት ከዚያ አስነዋሪ ሕይወቷ ተመልሳ ለቅዱስ ቁርባን በቅታለች፤ ለእግዚአብሔር ጸጋ የተገባች ኾና ተገኝታለች ኃጢአቷን ኹሉ በጸጋው አጥባለች ከተጠመቀች በኋላ ራሷን መግዛት ችላለች፤ ይህቺ ሴት የቀድሞ ሕይወቷን ፣ ገላዋን ለብዙ ወዳጆቿ ያሳየችበትን ሕይወት "የእስር ቤት ሕይወት" ብላ ትጠራዋለች፤ በእውነት "ኋለኞች ፊተኞች ይኾናሉ ፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይኾናሉ" የሚለው የከበረ ቃለ ወንጌል በእርሷ ሲፈጸም አየነው፤ መለወጥ ከፈለግን እኛን ማሰናከል የሚቻለው ኃይል እንደሌለ ዐወቅን ፤ ተረዳን፡፡
❖ እንኪያስ እኛም ተስፋ በመቁረጥ ፥ በኃጢአት ዐዘቅት ሰምጠን የምንቀር አንኹን፤ ከእኛ መካከል በጽድቅ በረኻነት የሚኖር ማንም አይገኝ ፊተኛ ነኝ የሚል ማንም አይገኝ ፤ ብዙ አመንዝሮች እርሱን አልፈውት ሊሔዱ ይችላሉና፤ ማንም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ ፤ ከልቡ ከተጸጸተና ከተመለሰ ፊተኛ መኾን ይቻለዋልና፡፡
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
📌 ምንጭ
✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
───────────
Channel
/channel/dnhayilemikael
ብሒለ አበው
❖እግዚአብሔር የአንተን ድካም ስህተት ጉድለት እንደተሸከመ ሁሉ አንተም የሌሎችን ተሸከም᎓᎓
❖እግዚአብሔር በራሱ ሁሉን ማድረግ ይችላል፤ አንተ ግን አብረኸው ትሠራ ዘንድ ይሻል፣ እንድትሠራ ብቻ አይደለም
እንድትለፋ እንድትጥርም ነው እንጂ።
❖እግዚአብሔር ከእርሱም በፊት ሓላፊነት እንድትወስድባት ነፍስህን አደራ ሰጥቶሃል፤ ታዲያ ለአደራው ታማኝ እንደሆነ ባለአደራ ለዚህ ጊዜ ሰጥተሃል ወይስ በሌላ ተይዘሃል!
❖እግዚአብሔር ለምን ኃጢአት ሠራችሁ ብሎ አይጠይቀንም፤ ለምን ንስሓ አልገባችሁም ብሎ እንጂ፡፡
❖በጎልጎታ የተሰቀለው እርሱ እንደ ኃጢአተኛ ተቆጠረ፤ ብዙ
ስድብና ንቀትን ታገሠ፤ ከሞት በክብር ተነሣ፤ በክብርም ወደ
ሰማይ ዐረገ፤ በአብም ቀኝ በክብር ተቀመጠ፡፡
❖አንዳንዴ ስለ እግዚአብሔር ብለን በመልካም ቁጣ ውስጥ
ልናልፍ እንችላለን፤ ነገር ግን እንዲህ ሲሆን መረበሽና ራስን ያለመግዛት ነገር አይኖርበትምና በዚህ ጊዜ መንፈሳዊ ቅናት
ነው።
❖ አንተ ታማኝ ሆነህ በሰዎች ላይ በቃልህ የማትፈርድ ከሆነ እግዚአብሔር ደግሞ እጅግ ፈታኝ ከሆነው በሐሳብ መፍረድ
ይጠብቅሃል።
❖ሌሎችን አመስግን ያለህን አድናቆት ግለጽላቸው፤ መልካም
ሥራቸውን እንዳወቅህ እንዲረዱ አድርግ፤ አክብራቸውም።
ሠናይ ሰንበት
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን
➡️ መሰረተ ሚዲያ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ
👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═/channel/Meseretemedia
1፣3፣6፣16፣21 የቅድስት ድንግል ማርያም ቀኖች ናቸው፡፡
የእርሷ የኾኑት በዙ ብለህ እንዳታስብ!
ዕንኳን ዕለታቱ የዕለታቱ ፈጣሪ ክርስቶስም የእርሷ ኾኗል፡፡
በ፶፪ ዐ/ም በዛሬው ዕለት ከሦስት ድንጋዮች አንድ መቅደስ በእመቤታችን ስም በፊልጵስዩስ ተሠራ፡፡
ወራሴ ተአምራት ቅዱስ ላሊበላ ደግሞ ከሺ ዐመት በኋላ በኢትዮጵያ ከአንድ ድንጋይ አንድ ሙሉ መቅደስ ገነባ፡፡
ጌታ ኾይ ድንጋዩን ልብ የአንተ መቅደስ አድርገው
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።
ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። "የምን ቤት?" ብለህ ብትጠይቀኝ "ልብህ ነዋ" ብዬ እመልስልሃለሁ፤ "ማን ይኖርበታል?" ካልኸኝም "እግዚአብሔር ነዋ" እልሃለሁ።
አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?
እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል?
(Dn Abel Kassahun Mekuria )
@MoaeTewahedoB
2ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፈ 5
6 እንግዲህ ሁልጊዜ እመኑ ጨክኑሞ በዚህ ሥጋ ሳላችሁም እናንተ እንግዶች እንደ ሆናችሁ ታውቃላችሁ ከሥጋችሁ ተለይታችሁ በሄዳችሁ ጊዜ ወደ ጌተችን ትሄዳላችሁ ።
7 በእምነት እንሄዳለን በማየትም አይደለም
8 ታምነናል ይልቁንም ከሥጋችን ተለይተን ወደ ጌታችን እንሄዳለንና ደስ ይለናል ።
9 አሁንም ብንኖርም ብንሞትም እርሱን ደስ ለማሰኘት እንጥራለን ።
10 መልካም ቢሆን ክፉም ቢሆን በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንሰማለንና ።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
❖❖❖❖ ታማኝነት ❖❖❖
መጽሐፍ : ቅዱስ : እንዲህ : ይላል :- «በጥቂቱ : ታምነሃል : በብዙ : እሾምሃለሁ፤..." (ማቴ. 25 ፥ 2።)
ይህም ፡ ማለት ፡ በምድራዊ ፡ ነገሮች ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ስትገኝ ፡ በሰማያዊ ፡ ነገሮች ፡ ላይ ፡ እሾምሃለሁ ፡ ማለት ፡ ነው። በዚህኛው ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከቆየህ ፡ በዘላለማዊነት ፡ ውስጥ ፡ እሾምሃለህ ፡ ማለትም ፡ ነው።
ይህ ፡ መመሪያ ፡ በብዙ ፡ መስኮች ፡ ላይ ፡ ተግባራዊ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል . . .
༒ ዘመዶችህን ፡ በመውደድ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጠላቶችህንም ፡ በመውደድ ፡ ላይ ፡ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን ፡ የምትወድበትን ፡ ጸጋ ፡ ያድልሃል ፡ ማለት ፡ ነው፡፡
༒ በትርፍ ፡ ጊዜዎችህ ፡ እግዚአብሔርን ፡ የምታገለግል ፡ ከሆንህ ፡ በሕይወትህ ፡ ጊዜ ፡ ሙሉ ፡በእርሱ ፡ ላይ ፡ ትኵረት ፡ የምታደርግበትን ፡ ፍቅር ፡ ያድልሃል፡፡
༒ የፈቃድ ፡ ኃጢአቶችን ፡ ከአንተ ፡ በማስወገድ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ፈቃድህ ፡ ከሚመጡ ፡ ኃጢአቶች ፡ ነጻ ፡ ያወጣሃል።
༒ ንቁ ፡ ኅሊናህን ፡ ከክፉ ፡ ሀሳቦች ፡ የምትጠብቅ ፡ ከሆንህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ንቁ ፡ ያልሆነው ፡ ኅሊናህን ፡ ንጽሕና ፡ ይጠብቅልሀል። ከዚህ ፡ በተጨማሪ ፡ የሕልሞችህን ፡ ንጽሕናም ፡ ይጠብቅልሀል።
༒ ልጅ ፡ እያለህ ፡ ታማኝ ፡ ከሆንህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ውጊያዎች ፡ በሚበዙበት ፡ በወጣትነት ፡ ዘመንህ ፡ ውስጥም ፡ ታማኝነትን ፡ ያድልሃል፡፡
༒ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ላይ ፡ በቃላት ፡ ብቻ ፡ የማትፈርድባቸው ፡ ሆነህ ፡ ለመገኘት ፡ ታማኝ ፡ ከሆንህ ፡ ይበልጥ ፡ አስቸጋሪ ፡ በሆነው ፡ በሀሳብ ፡ እንዳትፈርድባቸው ፡ ያስችልሃል፡፡
༒ ልክ ፡ እንደዚሁ ፡ ራስህን ፡ ከውጪያዊ ፡ ንዴት ፡ በመጠበቅ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከውስጣዊ ፡ ቁጣ፣ ንዴትና ቅናት ፡ ነጻ ፡ ያወጣሃል።
༒ በተለመዱ ፡ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፡ ፍሬዎች) ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ የመንፈስ ፡ ስጦታዎችን ፡ ያድልሃል!
በመጀመሪያው ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ካልተገኘህ ፡ ሁለተኛውን ፡ ፈጽሞ ፡ ልታገኘው ፡ አትችልምና፡፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ ፡ የሚፈትሽህ ፡ በጥቂት ፡ ነገር ፡ ነው:: በዚህች ፡ በጥቂቷ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ መሆንህን ፡ ካረጋገጥህ ፡ እርሱ ፡ በሚበልጠው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና ፡ አለመታመንህን ፡ በጥቂቷ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ከገለጽህ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ በሚበልጠው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ አይሾምህም። መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ እንዲህ ፡ ይላልና:- «ከእግረኞች ፡ ጋር ፡ በሮጥህ ፡ ጊዜ ፡ እነርሱ ፡ ቢያደክሙህ ፡ ከፈረሶች ፡ ጋር ፡ መታገል ፡ እንዴት ፡ ትችላለህ?» (ኤር. 12 ፥ 5።)
ብዙ ፡ ሰዎች ፡ ዝቅተኛውን ፡ ኃላፊነት ፡ መወጣት ፡ ሳይችሉ ፡ ከፍተኛውን ፡ ኃላፊነት ፡ ለመቀበል ፡ ማሰባቸው ፡ እጅግ ፡ አስደናቂ ፡ ነገር ፡ ነው። እነዚህ ፡ ሰዎች ፡ በተሰጣቸው ፡ ጸጋ ፡ ሳይጠቀሙ ፡ ተጨማሪ ፡ ጸጋ ፡ እንዲሰጣቸው ፡ የሚጠይቁ ፡ ናቸው። ይህን ፡ ሲያደርጉም ፡ «በጥቂቱ ፡ ታምነሃል ፡ በብዙ ፡ እሾምሃላሁ፤...» የሚለውን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ በመዘንጋት ፡ ነው። ይህ ፡ ቃል ፡ ለእነርሱ ፡ እንደ ፡ ሁኔታው ፡ የሚወሰንበት ፡ ነው ፡ የሚሆነው፡፡
════•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ════
✞❀ /channel/dnhayilemikael ❀✞
════•ೋ•✧๑♡๑✧• ════
✝ስለ ምሥጢራተ ቅድሳት ✝
✝✝✝ ከኢትዮዽያ #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ ምዕመናን አብዛኛው #ከቅዱስ_ሥጋውና_ክቡር_ደሙ የራቀ መሆኑን ሳስብ በጣም አዝናለሁ! ✝✝✝
✝ ግን ለምን ??? ✝
✝ ለምን ብዙዎቻችን #ሕይወት_መድኃኒት ከሆነው ማዕድ ተለየን ??? ✝
✝ ከቅዱስ ሥጋው ሳይበሉ: ከክቡር ደሙ ሳይጠጡ መዳን ይኖር ይሆን ??? ✝
✝ በሰማያዊው ዙፋን #በዘለዓለም_አምላክ_በክርስቶስ ፊትስ በቂ መልስ ይኖረን ይሆን ??? ✝
✝ሁልጊዜ ባልረባ ምክንያት ሕይወት ከሆነው #ማዕደ_ክርስቶስ እስከ መቼ እንርቃለን ???
+እርሱ ግን አሰምቶ ይጠራናል:: "ኑ! ሥጋየን ብሉ: ደሜንም ጠጡ" ይለናል:: "ሥጋየን የሚበላ: ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በእርሱ አድሬበት እኖራለሁ" ይለናል:: (ዮሐ. 6:56)
+ሌላ መንገድ አለ እንዳይመስለን ደግሞ "የሰውን ልጅ (የክርስቶስን) ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም" (ዮሐ. 6:53) የሚል ተግሣጽን ልኮልናል::
+ቤተ ክርስቲያን እኛን ወደ #ምስጢረ_ቁርባን ለማድረስ ከእነዚህ የተረፈ ነገር አልጫነችብንምኮ!
¤በሃይማኖት መኖር (መመላለስ)
¤ከክርስቶስ (ከጌታችን) ጋር ለመኖር ቁርጥ ውሳኔ
¤በመምሕረ ንስሃ ሥር መጠለል
¤በንስሃ ሕይወት መመላለስና
¤ቀዋሚ የሕይወት መሥመር (ጋብቻ ወይ ምናኔ) መያዝን ትሻለች እንጂ መቼ ሌላ ቀንበር ጫነችብን!
+እናም የመንፈስ ወንድሞቼና እህቶቼ . . .
¤የራቅን እንቅረብ!
¤የቀረብንም እንበርታ!
¤የበረታንም እንጽና!
¤የጸናንም ደካሞቹን እንርዳ! (ይህ በጌታ ዘንድ ዋጋው ትልቅ ነውና!)
☞#የምሕረት_ጌታ #ለምሥጢራተ_ቅድሳት የምንበቃበትን የምሕረት ዘመን ያምጣልን::
☞ግን እናስብበት!!!
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
. Dn Yordanos Abebe
/channel/Meseretemedia
ሰው ሃይማኖቱን መጠበቅ የሚችለው ስለ ሃይማኖቱ አምስት ነገሮች ሲያውቅ ነው ፡፡
💠 1/ ምን እንደሚያምን
💠 2/ ለምን እንደሚያምን
💠 3/ ያመነውን እንዴት መፈጸም እንዳለበት
💠 4/ ያመነውን እንዴት ለሌሎች ማሳወቅ እንዳለበት
💠 5/ እምነቱን የሚፈተን ነገር ሲመጣ እንዴት መከላከል እንዳለበት
ማወቅ አለበት
ሃይማኖታችንን ለመጠበቅና በሃይማኖታችን ጸንተን ለመኖር መንፈሳዊ ትምህርትእንማር
መሰረተ ሚዲያ
የቴሌግራም አድራሻ/channel/Meseretemedia
በሰርጓ ቀን ካህኑ አባቷ ሁለት ዲያቆን ወንድሞቿ እና ዲያቆን ባሏ ቀድሰው ያገባችው ሙሽሪት።
Читать полностью…+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? +
ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት::
"ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39
ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ::
"ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ::
ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20)
እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም?
ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ?
"ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር::
የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23)
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን?
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ::
"ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም::
ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13)
ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ::
ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ::
አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር::
የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 21 2016 ዓ.ም. ተጻፈ
"ማርያም ገጸኪ እፈቱ ርእየ
ድንግል ድንግል ንዒ ኀቤየ
እስመ ኪያኪ ጸምአት ነፍስየ"
ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪኀ ማርያም ኃይለ ሚካኤል
/channel/dnhayilemikael
ገለባ ልብ ስላለን እንጂ፣ታዋቂ ሰባኪ ካልተጋበዘ ቤተክርስቲያን ሂደን ወንጌል የማንሰው? ከእግዚአብሔር በላይ ዝነኛ ኑሮ ነው? ካለ ንገሩኝ።ይህንን ትውልድ የእውነት ታዘብሁት። እርሱ ግን በወደደው አድሮ ይናገራል።( ጸጋ የበዛላችሁ የምትባሉ አትቀየሙኝ ፡ )
-
ኦርቶዶክሳዊ ሚዛን
ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ክፍል ፩
ብዙው ሰው እጁ እስኪላጥ ሲያጨበጭብ ከርሞ አሁን ደግሞ ላንቃው እስኪሰነጠቅ እየጮኽ ነው። በእርግጥ የመንጋነት ፍጻሜው ውድቀት እና ማፈር እንዲሁም ፀፀት ነው። አብዛኛው ሰው መንጋ ነው። የሰባኪ መንጋ አለ። የአጥማቂ ነኝ ባይ መንጋ አለ። የፖለቲከኛ መንጋ አለ። የአክቲቪስት መንጋ አለ። አንዳንዱ አሁንም ከመንጋነት ወደ መንጋነት የተዘዋወረ አለ። የሆነ ሰው መንጋ ሆኖ ይከርምና የተከዳ ሲመስለው እገሌ ግን ያን ጊዜም ትክክል ነበር ብሎ ለዚያ ሰው ወዶ ገብ መንጋ ይሆናል። እኒህ ሁሉ መንጋቸውን እንደፈለገ ይነዱታል። መንጋው ደግሞ አያሰላስልም። መንጋ እንደ ሸንበቆ ነው። ሸንበቆ ነፋስ ወደነፈሰበት ነው ሁል ጊዜም የሚያዘነብለው። ነገር ግን ነፋሱ በጣም አይሎ ነቃቅሎ ሲጥለው ያን ጊዜ ያማርራል። አብዛኛው ሰው መለኪያ የለውም። መስማት የሚፈልገውን እየነገሩ የሚወስዱት ሰዎች ብዙ ናቸው። በርበሬ ተወዶ ከሆነ ቤተክርስቲያን ሰባኪው አስተምሮ ሲጨርስ "ፈጣሪያችን የበርበሬን ዋጋ ይቀንስልን" ሲል "አሜን" የሚለውን መንጋ ብዛት አስተውልማ። ደንበኛው ሊቅ መጥቶ አስተምሮ ሲጨርስ "ንሥሓ ገብተን ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ያብቃን" ሲል አሜን የሚለው ይቀንሳል። ይሄ በጣም አሳዛኙ ክስተት ነው። ሰው መስማት ያለበትን ከሚሰማ ይልቅ መስማት የሚፈልገውን መስማትን እየመረጠ ነው። ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተዋጀችው የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችው ስለበርበሬ እንዲወራ ነው እንዴ!?። ማንኛውም ሰው ፕሮፌሰርም፣ ዶክተርም፣ ኢንጂነርም፣ ሳይንቲስትም፣ ፖለቲከኛም፣ ፓትርያርክም፣ ቄስም፣ ጳጳስም፣ መምህርም፣ ምእመንም፣ ዲያቆንም ሁሉም ፍጡራን ናቸው። እንደፍጡርነታቸው የሚለኩበት መለኪያም አንድ ነው። አንተ ሰው ለምን የፖለቲከኛ መንጋ ትሆናለህ!? ፖለቲከኛም እንደ አንተ ሰው መሆኑን ዘነጋሃው እንዴ!? እንደ አንተ ሰው ከሆነ አንተም እርሱም የምትዳኙበት መለኪያ አንድ ዓይነት ነው። አንድ ዓይነት ከሆነ ደግሞ ለምን ራስህን የፖለቲከኛና የሰባኪ መንጋ ታደርጋለህ!? የማንም መንጋ አትሁን። እግዚአብሔር ራስህን አስችሎ ስለፈጠረህ ራስህን ችለህ አስብ። በሌሎች ጭንቅላት ካልተመራሁ አትበል። ሩጥ ሲሉህ የምትሮጥ ቁጭ በል ሲሉህ ቁጭ የምትል ከሆነ ፈጣሪ በነጻነት ራስህ ተመራምረህ እንድትመርጥ የሰጠህን እድል መንጋ ለሆንክለት አካል አሳልፈህ ሰጠኽው ማለት ነው። ይህ ደግሞ እገሌ አይሳሳትም ወደማለት ጽንፍ ያወርድሀል። ከዚያ ያ ሰው ሲሳሳት አንተ ማፈሪያ ሆነህ ትቀራለህ። ኦርቶዶክሳዊው ሰው ግን ሁሉን የሚመረምርበት አእምሮ ከፈጣሪ ስለተሰጠው በራሱ መንገድ በራሱ መለኪያ ነገሮችን ይመረምራል እንጂ የማንም መንጋ አይሆንም። ታድያ በዓለማችን የሚደረጉ ነገሮችን ለመመርመር ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ያስፈልገናል። ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ሁልጊዜም ትክክል ነው። አያጸጽትም። ዘመናትን ተሻጋሪ ነው። ልበ ሙሉ ያደርጋል። ምክንያቱም የኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ባለቤት እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ምንድን ነው?! ከመንጋነት እንዴት እንላቀቅ የሚሉ ጉዳዮችን በ7 ክፍል እንመለከታለን።
ይከታተሉ። ክፍል 2 ይቀጥላል ..
መ/ር በትረ ማርያም
#share
ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉЧитать полностью…
╭═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን
➡️ መሰረተ ሚዲያ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇፦
ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ
👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═/channel/Meseretemedia
+"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን
አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+
=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)
የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
#እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ
በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና
በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ
ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ "
እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም::
የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::
+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል
በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን
#ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን
በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ
አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር
ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::
+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ
ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን
አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!)
ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው
ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች::
እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት
የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ"
ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::
+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል
እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ
ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ
ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::
+"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+
=>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::
+ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ
አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን
(መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ
ጋር የተነጋገረ
¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ
አባት ነው::
+በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ
እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ
#አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም
ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: )
+ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::
+በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው
#አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው
አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::
+"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( #GIYORGIS_OF_SEGLA )
+"+
=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ
ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ
ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ
"ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር
ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ
#አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና
ይማጸናት ገባ::
+ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም
ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል
እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ
መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው::
"ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው
ተሠወረችው::
+ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ
ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው:
መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና
ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ
ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ
መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ)
+ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/
ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:-
1. #ሊቀ_ሊቃውንት
2. #በላዔ_መጻሕፍት
3. #ዓምደ_ሃይማኖት
4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ
5. #ጠቢብ_ወማዕምር
+ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን
ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን
ነው::
=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና
አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::
=>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)
2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ)
4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ)
5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)
6.አባ መቃቢስ
7.አባ አግራጥስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
2.አባ ባውላ ገዳማዊ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
=>+"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:-
'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ'
ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ::
እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+ (ዕብ.
6:13)
=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር:
የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+
(ቆሮ. 13:14)
+++ ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር +++
©ዝክረ ቅዱሳን
•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን
➡️ መሰረተ ሚዲያ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ
👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═/channel/Meseretemedia
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....
ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡
"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡
አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ መስራቱን አቁም፡፡
#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ
/channel/dnhayilemikael
" ራስህን ከቤተክርስቲያን ፈፅሞ አትለይ፤ ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን ደኅንነትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መጠጊያህ ናት።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
" ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና..."
ኢሳ. ፶፮፥፯ /56፥7/
❤ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት የጸሎት ቤት ነው። በእዚያም እርሱ አለና።
ጊዜ የለኝም መምህራኑ ገዳማውያኑ ያንብቡ !!!
❖ "ሰው ወደሚበዛበትና የዚህን ዓለም ፍርድ ወደሚሰጡ ቦታዎች አለመኼድ ስለማልችል፣ የምመራው ትልቅ የንግድ ድርጅት ስላለኝ፣ ሥራዬ ጥበበ እድ ስለሆነ፣ ጊዜ ስለሌለኝ፣ ትዳር ስላለኝ፣ ልጆችን ስለማሳድግ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ስለሆንኩ፣ እኔ የዓለም ሰው ስለሆንኩ መጻሕፍትን ማንበብ አይጠቅመኝም፤ "መጻሕፍትን ማንበብ በገዳም ለሚኖሩ መነኮሳት ነው" ብለህ አትንገረኝ።
❖ "አንተ ሰው! ምን ማለትህ ነው?" "ብዙ የዚህ ዓለም አሳብ ስላለብኝ መጻሕፍት ማንበብ ለእኔ አይደለም" ትለኛለህን? እንዲያውም ልንገርህ! አንተም ስማኝ! ከእነዚያ መነኮሳት ይልቅ ማንበብ ያለብህ አንተ ነህ፤ መጻሕፍትን በብዛት ማንበብ የሚገባቸው ብዙ የዓለም አሳብ ያላቸው ሰዎች እንጂ በምግባር በትሩፉት የተጠመዱ መነኮሳት አይደሉምና::
📌 ምንጭ
✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
📚"የክርስቲያን መከራ"
═══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮
የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን
➡️ መሰረተ ሚዲያ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ
👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═/channel/Meseretemedia
ሰው ሃይማኖቱን መጠበቅ የሚችለው ስለ ሃይማኖቱ አምስት ነገሮች ሲያውቅ ነው ፡፡
💠 1/ ምን እንደሚያምን
💠 2/ ለምን እንደሚያምን
💠 3/ ያመነውን እንዴት መፈጸም እንዳለበት
💠 4/ ያመነውን እንዴት ለሌሎች ማሳወቅ እንዳለበት
💠 5/ እምነቱን የሚፈተን ነገር ሲመጣ እንዴት መከላከል እንዳለበት
ማወቅ አለበት
ሃይማኖታችንን ለመጠበቅና በሃይማኖታችን ጸንተን ለመኖር መንፈሳዊ ትምህርትእንማር
መሰረተ ሚዲያ
የቴሌግራም አድራሻ/channel/Meseretemedia
+• የእንባችን ዋጋ ምን ያህል ነው? •+
አንብቡት🙏
🥀አባ አንቶኒ ኮኒያሪስ የተሰኙ የግሪክ ኦርቶዶክስ ካህን በጻፉት "ፊሎካሊያ: የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት ቅዱስ መጽሐፍ" (Philokalia: The Bible of Orthodox Spirituality) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ለማስተማሪያነት ያሰፈሩት እንዲህ የሚል አንድ ጥንታዊ አፈታሪክ አለ:-
🥀እግዚአብሔር ከዕለታት በአንዱ ቀን ቅዱሳን መላእክቱን "ወደ ምድር ወርዳችሁ ከሁሉ ይልቅ እጅግ ብርቅዬ የሆነውን ነገር ይዛችሁልኝ ኑ" ብሎ ያዛቸዋል::
🥀አንድ መልአክ ሌላ ሰው ለማዳን ብሎ ራሱን መስዋእት ያድረገን ሰው የደም ጠብታን ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በእርግጥ ይህ በእኔ ዓይን እጅግ የተወደደ ነው:: በዓለም ያለው እጅግ ብርቅዬ ነገር ግን አይደለም::" አለው::
🥀ሌላኛው መልአክ ደግሞ ሌሎችን ስታስታምም በያዛት በሽታ ምክንያት ያረፈችን የአንዲት ነርስ የመጨረሻ እስትንፋስ ይዞ መጣ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በእርግጥ ስለሌሎች የሚከፈል መስዋእትነት በእኔ ዓይን እጅግ ታላቅ ዋጋ አለው:: ሆኖም ግን በዓለም ያለው እጅግ ብርቅዬው ነገር ይህ አይደለም" አለው::
🥀በመጨረሻም አንድ መልአክ ንስሃ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰን ኃጢአተኛ አንድ ዘለላ እንባ ይዞ መጣ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በዓለም ላይ ያለውን እጅግ ብርቅዬ ነገር አመጣህ - ይኸውም የገነትን በር የሚከፍት የንስሃ እንባ ነው!" በማለት ተናገረ::
🥀የጌታ ቃል “እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።"(ሉቃ 15:10) ብሎ ስለ ንስሃ ዋጋ ይነግረናል:: ንስሃ ደግሞ በተሰበረ ልብና በእንባ ሲሆን ይሰምራልና ፥ በዚህ መንገድ ሆነን ንስሃ ለመግባት እንፋጠን፤ እርሱ ይቅር ይለን ዘንድ ሁሌም ዝግጁ ነውና::
🥀 አምላከ ቅዱሳን ለንስኃ የተዘጋጀ ልብ ይፍጠርልን
ለንስኃ ሞት ያብቃን🙏
ተቀላቀሉ ቴሌግራም
/channel/dnhayilemikael
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ (በዓለ ሃምሳ )
በሰላም አደረሳችሁ ።
በዓለ ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው።
ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ የግሪክ ነው። “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም
👉መጽንኢ (በእምነት የሚያጸና)፣
❖መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ)፣
❖ናዛዚ (ያዘኑትን የሚያረጋጋ)፣
❖መስተፍስሒ (የተጨነቁትን የሚያስደስት)፣
❖ከሣቲ (ምስጢርን የሚገልጽ) ማለት ነው
ከበዓሉ በረከት ረድኤት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያሳትፈን።
/channel/dnhayilemikael
*በዓለ ጰራቅሊጦስ*
❖ጰንጠቆስጤ ቃሉ የግሪክ ቃል ነው፡፡ ትርጓሜውም ሃምሳኛ ማለት ነው፡፡
❖ ጰራቅሊጦስ ማለትም የሚረዳ፤ የሚያጽናና ማለት ነው፡፡
❖በብሉይ ኪዳን በዓላት ለምሳሌ የአይሁድ የፋሲካ በዓላቸውን ካከበሩ በኋላ አምሳውን ቀን የነጻነት በዓላቸው አድርገው ከሰነበቱ በኋላ ኃምሳኛውን ቀን በተለየ ሁኔታ በዓለ ሰዊት ብለው ያከብራሉ፡፡
❖ በእነርሱ ሀገር ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለው ወቅት ጸደይ /የእሸት ወራት/ ነው፡፡
ጌታችን እርሱ ባወቀ ይህን በዓል /በዓለ ሠዊትን/ ለሐዲስ ኪዳን በዓላችን ፪ ጥቅሞችን እንዲያስገኝ አድርጓል””
✢ የመጀመሪያ ለበዐለ ጰራቅሊጦስ ምሳሌ መንገድ ጠራጊ፤ መተርጐሚያ ፤ ማሳመኛ መሆኑ ነው፡፡
✢ ሁለተኛው በዓሉ እንዲከበር ምክንያት የሆነው ርደተ-መንፈስ ቅዱስ /የመንፈስ ቅዱስ መውረድ/ ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሳ በአምሳኛው ቀን በወረደበት ዕለት በዝርዎት የነበሩ አይሁድ ሁሉ ለበዓለ ፋሲካና ከዚሁ ተያይዞ ለሚከበረው ለበዓለ ሠዊት እንደተሰበሰቡ የተፈጸመ መሆኑ ነው፡፡
❖ ሰዎቹም በጸሎት የተጉ መሆናቸውና ከእግዚአብሔር የሆነውን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው በክርስቶስ አምላክነት አምነው የቤተክርስቲያን መሠረት እንዲጣል ምክንያት ሆኖአል፡፡ ማስረጃ፡- ሐዋ.፪÷፭-፮ “ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምጽ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ ….” ሕዝቡም እንደተጻፈውም ነገሩ ከእግዚአብሔር መሆኑን ለመመርመር ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ሐዋ.፪÷፯-፲፩ “ ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ፡- ❖እነሆ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን?
❖እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?... እግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን፡፡”
❖ተገርመው ተደንቀውም አልቀሩም -
👉አለ -የቅ/ጴጥሮስን ስብከትሰምተው አምነው የተጠመቁ ብዙዎች ናቸውና ይህንን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ሐዋ.፪÷፵፩-፵፪ “ ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤በሐዋርያትም ትምህርትና በኀበራት እንጀራውንም በመቁረስ በጸሎትም ይተጉ ነበር”
❖ ይህዊ ዕለት፤ የቤተክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውም ለዚህ ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ የወረደበት፤ በሦስት ሺህ ✢ሰዎች ጥምቀት መስፋፋት የጀመረችበት፤ ሐዋርያትም ፍሩሃኑ ጥቡዓን /ደፋሮች/ ሆነው፤ በዕውቀት በልጽገው፣በአእምሮ ታድሰው ዓለሙን ለመለወጥ ኃይል ያገኙባት ዕለት ናት፡፡
❖ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ እነዚህን ነገሮች አስታውጦ ሲናገር “መንፈስ ቅዱስ ባይወርድላት ኑሮ የቤተክርስቲያን ሕልውና ከስሞኖ ቀጭጮ ይቀር ነበር፤ ስለዚህም በሚገባ አነጋገር ይህች ዕለት የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ትባላለች” ብሎአል፡፡
👉ከዚህም የተነሳ ሌሎች ሊቃውንትም ዕለቲቱን የበዓላት ሁሉ እመቤት እንደሚሏት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ገልጸውታል፡፡
በዓሉ ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ለቤተክርስቲያን “ ከእናንተ ጋር ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤ እኮ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል” እና “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤በስሜ አጋንንትን ያወጣኑ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤…” ሲል የገባው ኪዳን የተፈጸመበት ተደርጎም ይከበራል፡፡
👉 በእኛ በቤተክርስቲያን ሊቃውንት በፍትሐነገሥት የገለጹትን በማሰብ ለመንፈሳዊ ሐሴት በቃለ -እግዚአብሔር ይከበራል ፡፡ ፍትሐ ነገሥታችን “ ትንሣኤን በአከበራችሁ በአምሳኛው ቀን ዕርገቱን በአከበራችሁ በዐሥረኛው ቀን በዓለ ጰራቅሊጦስን አክብሩ በዓል ይሁንላችሁ" እንዳለ ቤ/ክ ታከብራለች!
ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
╭═/channel/dnhayilemikael
‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ››
Читать полностью…__ደግ ዓለም፣ ሕይወተ ቡሩካን_
፩. ክፉ ከማሰብ፣ ክፉ ከመናገር፣ ክፉ ከመሥራት ራስን መጠበቅ።
፪. ሌላውን ሰው ክፉ ከሚያሳስብ፣ ክፉ ከሚያናግር፣ ክፉ ከሚያስደርግ ተግባር ራስን መጠበቅ።
፫. መልካም ማሰብ፣ መልካም መናገር፣ መልካም ማድረግ።
፬. ሌላው ሰውም መልካም ሐሳብን ያስብ ዘንድ፣ መልካም ንግግርን ይናገር ዘንድ፣ መልካም ድርጊትን ያደርግ ዘንድ በጎ አስተዋጽኦ ማድረግ።
፭. ክፋትን ከመኮነናችን በፊት እኛ ራሳችንም በብዙ መንገድ ከክፋት የራቅንና በመልካምነት የጸናን ልንሆን ይገባል።
፮. ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ነገ የተሻልን ሆነን ለመገኘት መጣር አለብን።
፯. ከዚህ ቀደም ያጠፋናቸውን ጥፋቶች በንስሓና በይቅርታ ሽረን ለወደፊቱ ደግሞ እንዳናጠፋ መጠንቀቅ። ንስሓ የገባንበትን ኃጢአት ላለመድገም እስከ ሞት መታመን።
፰. ሰውን በመልካም ሥራው እንዲቀጥልበት ማበረታታት፣ ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ደግሞ በቅንነት መንገር።
፱. ለሰሚው የማይጠቅምና ሰሚውን የሚጎዳ ነገርን አለመናገር። ከሰይጣን ጋር አለመተባበር። ከከንቱ ውዳሴ፣ ከትዕቢት፣ ከሐሜት፣ ከውሸት፣ ከስርቆትና በጠቅላላው የሰይጣን ገንዘብ ከሆኑት ነገሮች ራስን ማራቅ።
፲. ለእኛ ሊደረግልን የምንፈልገውን ለሌሎችም ማድረግ፣ በእኛ እንዲደረግ የማንፈልገውን በሌሎችም እንዳይደረግ መመኘት።
፲፩. ክርስቶስ በዚህ ምድር እየተመላለሰ ሲያስተምር ክፉዎችን አላጠፋቸውም። ነገር ግን በክፉዎች መካከል እንዴት መኖር እንዳለብን አስተማረን።
፲፪. ለእግዚአብሔር ሕግ እስከ ዕለተ ሞት ድረስ መታመን። ሰማዕትነትን መውደድ። ሰማዕትነትን ፈርቶ የእግዚአብሔር ሕግ ሲጣስ ዝም አለማለት።
የቡሩካን ሕይወት ከላይ ያሉትንና ሌሎችንም መልካም ሥራዎች በመሥራት ላይ የተመሠረተ ነው። መልካም እየሠሩ መኖር ደግ ዓለም ነው።
© በትረ ማርያም
/channel/dnhayilemikael
ብፁዓን ጳጳሳትን እንወዳቸዋለን። ይህ ማለት ግን እንደ ይሁዳ ለገንዘብ የሚሯሯጥና እንደ ኬልቄዶናውያን ፈቃደ ንጉሥን ለመፈጸም የሚሯሯጥ ጳጳስ ሲኖር አካሄዱን በግልጽ እንተቻለን። ያ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ይሁዳን ሌባ ነበረ ብሎ እንደተናገረው እኛም በስማቸው ዘረኛውን ዘረኛ፣ ሙሰኛውን ሙሰኛ፣ ሌባውን ሌባ፣ ቀኖና ያፈረሰውን ቀኖና አፍራሽ ብለን እንጠራዋለን። ሐዋርያትን ስናከብር ጎን ለጎን በሐዋርያነት ስም ብር ያሳድድ የነበረውን ይሁዳን ግን ሌባና ከሓዲ እያልን እውነቱን እንናገራለን።
_የንስር ዓይን__
ንስር በሰማይ እየበረረ ከምድር ያሉ ረቂቅ ነገሮችን ሳይቀር ያያል ይባላል። ዮሐንስ ወንጌላዊ በንስር የተመሰለው ረቂቅ ምሥጢረ ሥላሴን አስፍቶ በመጻፉ ነው። ከንስር ምን እንማር??
፩) አጥርቶ ማየት:- እውነትን ከሐሰት፣ መልካምን ከክፉ፣ ጽድቅን ከኃጢአት ለይቶ የሚረዳ ልቡና ሊኖረን ይገባል። ሐዋርያነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ የአገልግሎት መዓርግ ነው። ስለዚህ ሐዋርያነትን፣ ጵጵስናን፣ ክህነትን እናከብራለን። ይህ ማለት ግን ይሁዳ ሐዋርያነትን እንደምናከብር አውቆ በሐዋርያነት ካባ ክርስቶስን ሲክደው ዝም የምንለው አይደለንም። ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ይሁዳ ሲጽፍ ሌባ ነበረ ብሎታል። በጳጳስ ስም እየነገዱ ቀኖና የሚሽሩ፣ የንጉሥ አገልጋይ መለካዊ የሆኑ ካሉ በስማቸው ሌባ፣ መለካዊ፣ አጭበርባሪ እያልን እንጠራቸዋለን። እስከ መጨረሻውም ድረስ እንቃወማቸዋለን እንጂ ዝም አንልም። ለእውነት የሚታገሉ እንደ ሐዋርያት እስከሞት ድረስ የታመኑ ብፁዓን አባቶቻችንን ደግሞ ከልባችን እናከብራቸዋለን።
፪) ከፍ ብሎ መብረር:- ኅሊናችን ምጡቅ ይሆን ዘንድ መጻሕፍትን ማንበብና መልካም ምግባራትን መሥራት። ሰማያዊ ነገርን ሁልጊዜም ማሰብ ይገባናል። "በሰማይ የሀሉ ልብክሙ" እንዲል። ወደላይ ከፍ እያልን በሄድን ቁጥር በዚህች ምድር ትልቅ የሚመስሉን ነገሮች ሁሉ ትንሽ መሆናቸውን እንረዳለን።
© በትረማርያም አበባው
ኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ክፍል ፪
የኦርቶዶክሳዊው ሚዛን መሠረቱ ፍቅር እና እውነት ነው።
❖ ዓለምን የምንመዝናት ከእግዚአብሔር ቃል አኳያ ነው። አንድን ነገር እውነት ነው ወይም ውሸት ነው፣ ውብ ነው ወይም አይደለም፣ የሚለውን የምንለካው በቃሉ መሠረት ነው። ለምሳሌ እግዚአብሔር ፈራጅ ነው። በፈራጅነቱ ፈርዖንን በውሃ አስጥሟል። እግዚአብሔር መሐሪ ነው። በመሐሪነቱ ደግሞ አዳምን ከሲኦል አድኖታል። በደንብ ልንጠነቀቅበት የሚገባን ጉዳይ ለእግዚአብሔር ፈታሒነትም መሐሪነትም ገንዘቡ መሆናቸውን ነው። ለማንኛውም ኃጢኣታችን ፍርድ ይሰጥበታል። የምሕረት ደጁም ክፍት ነው። አዳም እግዚአብሔርን በደለ። ሕግ ተላለፈ። ለሕግ መተላለፉ 5500 ዘመን ያህል በሲኦል እንዲሰቃይ ፈርዶበታል። እንደገና አዳም ንሥሓ በመግባቱ ይቅር ብሎ ፍርዱ ካለቀ በኋላ ምሮታል። ለአዳም መማር ትልቁ ምክንያት ግን መጀመሪያ እግዚአብሔር መሐሪ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ግን አዳም ጥፋቱን አምኖ አጥፍቻለሁ ብሎ ፍርዱን በመቀበሉ ነው። ወደፊትም ጌታ በኃጥዓን ሊፈርድባቸው ለጻድቃን ሊፈርድላቸው በዳግም ምጽአት ይመጣል። ያን ጊዜ በኃጥዓን የሚፈርደባቸው ኃጢዓተኝነታቸው ተረጋግጦ ነው። ምሕረት ለማያስፈልገው ሰው ለዘላለም ይኖርበት ዘንድ ወደ ገሐነመ እሳት ይወረወራል። ምሕረት ለሚገባው ኃጢዓቱን አምኖ የቀደመ ሥራውን ለተወ፣ የቀደመ ክፉ ሥራውን የሚኮንን፣ ባለፈው ክፉ ሥራው ተጸጽቶ ንሥሓ ገብቶ ሥጋውን ደሙን ለተቀበለ ደግሞ ጌታ ምሕረት ሰጥቶ ዘላለማዊ ደስታ ወዳለባት መንግሥተ ሰማያት ያስገባዋል። ኦርቶዶክሳዊ ሰው ዋና ሚዛኑ ዘላለማዊ ሕይወት ነው። ይህም ማለት የሚያደርገው ነገር ዘላለማዊውን መልካም ሕይወት ለመውረስ ያበቃል ወይስ አያበቃም? የእግዚአብሔርን ሕግ ይቃረናል ወይስ አይቃረንም? የሚለውን ይመረምራል። ኦርቶዶክሳዊው ሰው ሁሉንም ሰው እንደራሱ አድርጎ ስለሚወድ ስለሌላው ሰው የሚናገረውን ነገር ሁሉ ለእርሱ እንደሆነ አስቦ ይናገራል። ምክንያቱም ትእዛዛት በፍቅር ይጠቃለላሉ። ፍቅር ደግሞ ፍቅረ እግዚአብሔርና ፍቅረ ቢጽ ተብሎ ይከፈላል። ፍቅረ ቢጽ ለእኛ ሊደረግልን የምንፈልገውን ለሌሎች ማድረግና እንዲደረግላቸው መመኘት ነው። በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ነው። የፍቅር ትርጓሜ ይህ ነው። ስለዚህ የኦርቶዶክሳዊ ሰው እይታው አመለካከቱ ፍቅርን መሠረት ያደረገ መሆን አለበት። ዮሐንስ አፈወርቅ ኃጥዓን ሲሞቱ ደስ ሊለን ይገባል ይላል። ምክንያቱም በህይወት ቢቀጥሉ ኖሮ ኃጢኣታችውን ጨምረው ፍዳቸውን ያበዙ ነበር። ቶሎ በመሞታቸው ግን ፍዳቸው ይቀንሳል ይላል። ስለዚህ የኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ዋና መሠረቱ ፍቅር ነው። ሌላው እውነት ነው። ፍቅር እውነትን የያዘ ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ አንድ ሰው ኃጢኣተኛ ቢሆን ለኃጢኣቱ ቅጣት ያስፈልገዋል። ይህ እውነት ነው። ነገር ግን ቅጣቱን እኛ በእሱ ቦታ ብንሆን ምን እንድንቀጣ ነው የምንፈልገው? የሚለውን የያዘ መሆን አለበት። እኛ የፈለገ ብንበድል መቼም ሲኦልን አንመኛትም። ሲኦልን የሚመኝ ሰው ይኖር አይመስለኝም። ስለዚህ ሌላው ሰውም የፈለገ ትልቅ በደል ቢበድል ለእኛ ሲኦልን እንዳልተመኘናት ሁሉ ለዚያም ሰው አለመመኘት ነው። በጥፋቱ መቀጣት እንዳለበት ማመን እውነት ነው። ቅጣቱ ምድራዊ እንዲሆንለት መመኘት ደግሞ ፍቅር ነው። ስለዚህ የኦርቶዶክሳዊው ሚዛን ዋና መሠረቶቹ ፍቅር እና እውነት ናቸው። ቅዱሳን መምህራን እውነትን የሚያስተምሩ እውነት እግዚአብሔር ስለሆነ እውነትን መናገር እውነትን ማወቅ ለእኛ ለሰውነታችን ከምንም በላይ ታላቅ ጥቅም ስላለው ነው። ይህንን እውነት ሌላውን ለማስተማር የተጉት እስከ ሞት የደረሱት ደግሞ ሰውን ስለሚወዱ እና ሌላው ሰውም እውነቱን አውቆ እንዲጠቀም ካላቸው መልካም እሳቤ እና ፍቅር የተነሳ ነው።
ክፍል 3 ይቀጥላል
" የፈጠራችሁን እስከ ዛሬም ድረስ የጠበቃችሁን እግዚአብሔርን ፍሩት " መቃብያን ካልዕ 10 ÷1
ሰንበት ትምህርት ቤት
ሰንበት ትምህርት ቤት ሕጻናት እና ወጣቶች እንደ ዕድሜ ደረጃቸው በተዘጋጁ መንፈሳዊ ትምህርቶች ተኮትኩተው የሚያድጉበት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋም በቃለ እግዚአብሔር የታነጸ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ እና ሥርዓት የሚያውቅ ሀገሩን የሚወድ ለራሱ ፣ለቤተሰቡ ለሀገር እና ለወገን የሚጠቅም ትውልድ በቃለ እግዚአብሔር የሚታነጸበት ቦታ ነው