dnhayilemikael | Unsorted

Telegram-канал dnhayilemikael - ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

1867

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Subscribe to a channel

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም

ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።

ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።

ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።

እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።

መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።

ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡

ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።

(ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ገጽ 334 - 336  በዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው የተተረጎመ)


የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )

                  ⬇️

➡️      መሰረተ ሚዲያ   ⬅️

                  ⬆️

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መጽሐፍ_ቅዱስን_የሚያነቡ_ሰዎች_በ፭ ይመደባሉ

በ፭ የመደብኳቸው እራሴ በተለያየ ምክንያት ያገኘኋቸውን ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ያላቸውን ልምድ በመጠየቅ ካገኘሁት መልስ የተነሳ ነው።

አጭር ስለሆነ እስከ መጨረሻ አንብባችሁ ሐሳብ ስጡበት።

በዚህ አጋጣሚ የመምህር #በትረ_ማርያምን ምክረ ሐሳብ እንከተል እላለሁ።
የእኔም ልምዴ ሁሌም ጧት ጧት ከጸሎት በኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ከብሉይ ኪዳን ፫ ምዕራፍ ፣ ከሐዲስ ኪዳን ፪ ምዕራፍ ከዚያ ቀጥሎ የዕለት ስንክሳር ሳላነብ አልወጣም።
ምናልባት ልምዱ ከጠቀማችሁ ብየ ነው እንጂ ይህን ማውራት ፈልጌ አይደለም ።
ግን ማልዶ መነሣትን ይጠይቃል።

✝️፩ኛ, በአጋጣሚ የሚያነቡ፦ እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡት እንደ ማንኛውም መጽሐፍ በአጋጣሚ ካገኙትና እጃቸው ከገባ ምን እንደሚል ሳያስተውሉ የሚያነቡ ናቸው።
ለምሳሌ፦አንዱ ጓደኛው ጋዜጣ ሲያነብ ሲያየው ቀበል ብሎ አንዳንድ ነገሮችን አንብቦና ፎቶ አይቶ ጋዜጣውን እንደሚመልስ ሰው ናቸው።
በአጋጣሚ ስለሚያነቡትም አይጠቀሙበትም።

✝️፪ኛ, ለጥናትና ለዕውቀት የሚያነቡ፦ እነዚህ ሃይማኖት ከየት መጣ? ማን ጀመረው? ወዘተ የሚለውንና ሌሎች ተዛማጅ ነገሮችን ለማጥናትና ለማወቅ የሚያነቡ ናቸው።
ስለሆነም ለጥናትና ለዕውቀት ብቻ ስለሚያነቡት አይጠቀሙበትም።

✝️፫ኛ, ለትችት የሚያነቡ ፦ እነዚህ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሕይወት እንደሆነ ለማወቅና እንደ ቃሉ ለመኖር ሳይሆን ለመተቸትና የሚቀበሉትን ሰዎች ለማወናበድ የሚያነቡ ናቸው።
ለትችት ስለሆነ የሚያነቡት በቃሉ አማካኝነት በእግዚአብሔር አምነው ወደ ሕይወት አይደርሱም።

✝️፬ኛ, በመስማት የሚያነቡ፦ እነዚህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ሲባል ይሰሙና ውይ ደስ ሲል ብለው ማንበብ ብቻ ስለሚወዱ ያነቡታል።
ነገር ግን የማይገባቸውና ለሕይወት የማይበቁ ናቸው።
ተግተውና ደጋግመው ቢያነቡት ልባቸው ተለውጦ ሊድኑ ይችላሉ።

✝️፭ኛ, ለሕይወት የሚያነቡ ፦ እነዚህ የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት እንደሆነና ቃሉን በመስማት ድኅነት እንደሚገኝና ወደ ድኅነት እንደሚያደርስ በማመን የሚያነቡ ናቸው።
"ወዝኒ ቃል ዘአነ ነገርኩክሙ መንፈስ ውእቱ ወሕይወት ውእቱ = ይኽ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወት ነው" እንዲል (ዮሐ፮፥፷፫)።
✔️እነዚህ አንባቢዎች ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ
"ዘዳዕሙ ሕገ እግዚአብሔር ሥምረቱ
ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ
ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ
እን ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ
ወቈጽላኒ ኢይትነገፍ
ወኵሎ ዘገብረ ይፌጽም (መዝ፩፥፪-፫) በማለት እንደነገረን ነው የሚሆኑት።

እኛስ መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበው ለምን ዐላማ ነው❓
✔️በአጋጣሚ
✔️ለጥናትና ለዕውቀት ብቻ
✔️ለትችት
✔️በመስማትና ጥቅሱ ደስ ስላለን
✔️ለሕይወት
ወይስ ሰባኪና አስተማሪ ለመሆንና ተቀጥሮ ደሞዝ ለማግኘት ለምን❓

እንደእኔ ፭ኛውን ብንመርጥ በነፍስም በሥጋም ተጠቃሚዎች እንሆናለን።
እናንተስ❓
ሌላም ከአምስቱ ውጪ ቢጨመሩ የምትሉትን መጨመር ትችላላችሁ እኔ ግን አንዳንድ ሰዎችን ስጠይቅ ያገኘሁት መልስ ባብዛኛው በአምስቱ የሚጠቃለል ነው።

መልካም ንባብ።

ወጣቱን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነብ እያበረታቱ ለሚገኙት ለመምህር #በትረ_ማርያም እድሜና ጤና ይስጥልን።

@መምህር ዳንኤል አለባቸው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ቅዱስ መስቀል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በመስቀል ከጠላትነት ድነናል፤ በመስቀል ወደ እግዚአብሔር አንድነት ተመልሰናል፡፡ በመስቀል ዲያብሎስ አርነት ወጥተናል፤ በመስቀል ከሞትና ከጥፋት ድነናል፡፡

ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን በሞት ጥላ ሥር ተይዘን ነበር፤ አሁን ብሥራተ መስቀል በተገለጠበት ጊዜ ግን ህልውና እንኳን እንደሌለው አድርገን ቈጥረን የዘለዓለም ሕይወትን እየናፈቅን ሞትን ንቀነዋል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን ለገነት እንግዶች ነበርን፤ መስቀል በተገለጠ ጊዜ ግን ወንበዴስ እንኳን ለገነት የተገባ ሆኖ ተገኘ፡፡

የሰው ልጅ እንደዚህ ካለ ጨለማ መጠን ወደ ሌለው ብርሃን፣ ከሞት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት፣ ከመዋቲነት ወደ ኢመዋቲነት ታድሶ ተሸጋገረ፡፡ ዓይነ ልቡና ባለማወቅ ጽልመት ከመታወር ድኖ በመስቀል የዕውቀት ብርሃን ተጥለቀለቀ፡፡ እዝነ ልቡና ካለማመን ድንቁርና ወጥቶ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ መስማት ተመለሰ፤ ዕውራንም ብርሃናቸው ተመልሶላቸው የእግዚአብሔርን ክብር ማየት ተችሎአቸዋል፡፡ በቅዱስ መስቀሉ የተሰጡን ሀብታት እነዚህ ናቸው፡፡ በቅዱስ መስቀሉ ያልተሰጡን በረከቶችስ ምን አሉ?

እነሆ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእግዚአብሔር ማመንም ተመልሷል፤ የእውነት ወንጌልም ወደ ዓለም ሁሉ ደርሷል፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ ሰማዕታትም ከመስቀል በኋላ ሞት ሞት መኾኑ እንደ ቀረና የሹመት የሽልማት ማሳ መኾኑን ዐውቀው አብረው ተገልጠዋል፤ በክርስቶስ ማመንም በሁሉም ዘንድ ተሰራጭቷል፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእርሱም ሞት ራሱ ሞቷልና ትንሣኤ ሙታንም ተገልጧል፤ ሕይወትም ታይታለች፤ መንግሥተ እግዚአብሔርም እንደዚሁ እርግጥ ኾናለች፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ለእነዚህ ኹሉ ነገሮች ምክንያት ኾኗል፡፡ በመስቀሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ተማርን፡፡ እንግዲህ ከቅዱስ መስቀሉ ይልቅ ሌላ የተወደደ ምን አለ? እኮ ከቅዱስ መስቀሉ በላይ ለነፍሳችን የሚረባት ወይም የረባትና የጠቀማት ሌላ ምን አለ? ስለዚህ በሙሉ ልባችን ይህን እንመስክር እንጂ ስለ ቅዱስ መስቀሉ ለመናገር ቅንጣት ታህልስ እንኳን አንፈር፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"የክርስቶስ መስቀል ታላቅ በረከትንና ድኅነትን እንድናገኝ ምክንያት እንደ ሆነ እናስተውላለን፡፡ የክርስቶስ መስቀል ስናስበው ሐዘንና ምሬት ነው ነገር ግን እውነታው ደስታና ሐሴትን የሚሞላ ነው፡፡ መስቀል ለቤተ-ክርስቲያን ድኅነት ነው መስቀል ተስፋ ለሚያደርጉት መመኪያ ነው መስቀል የእግዚአብሔር ጠላቶች የነበሩት የታረቁበትና ኃጢአን ወደ ክርስቶስ የቀረቡበት ነው፡፡ በመስቀል ከጠላትነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ተሸጋግረናል በመስቀል ከዲያብሎስ ቀንበር ወጥተናል ከሞት ወደ ሕይወት መጥተናል፡፡ ስለ መስቀል የማንሰብክ ከሆነ አሁንም በሞትና በፍዳ እንደ ተያዝን ነው ማለት ነው፡፡
            ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"አቤቱ ጥበብንና ኃይልን ልብንና እና ልቡናን ዕውቀትንም ስጠን። እንግዲህ ከሚፈታተነን ከሰይጣን ሥራ ሁሉ እስከ ዘላለሙ እንርቅ እንሸሽም ዘንድ። አቤቱ ሁልጊዜ ፈቃድህን ውድህንም እንሠራ ዘንድ ስጠን።"
   ሥርዓተ ቅዳሴ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

+ ምቹ ቀን ሆነላት +
ማር 6:21
ብዙ ጊዜ ክፉ ሰዎች የሚጠሉትን ሰው ለማጥቃት ምቹ ጊዜ ይጠብቃሉ።መጽሐፍ ቅዱስ ይሁዳ ጌታውን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ ጊዜ ይጠብቅ ነበር ይላል።"ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።"(ማቴ 26:16 ) ስለዚህ ወዳጄ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ስትስቅ የሚስቁት እንቅፋት ሲመታህ እኔን የሚሉ ሁሉ ይወዱሃል ማለት አይደለም አንተ የምትወድቅበትን ምቹ ቀን እየጠበቁ ነው።ጠላት ሁልጊዜም አንተን ለማጥቃት ወደ አንተ የሚቀርበው ደካማ ጎንህን አይቶ ነው።ይህን ያነሳሁበት ያለ ምክንያት አይደለም የጌታ መንገድ ጠራጊ ባሕታዊ መናኝ ካህን የሆነውን የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን ራስ ያስቆረጠችው የሄሮዳዳ ልጅ የዚህን ቅዱስ ራስ ለማስቆረጥ መጽሐፍ እንደሚናገር ራሱን የምታስቆርጥበት ምቹ ቀን ትጠብቅ ነበር። ለንጉሡና ለእርሷ ምቹ ቀን ሆነላትና የቅዱሱን ራስ አስቆረጠችው።ሁልጊዜም አምነኸው የማይከዳህ ተደግፈኸው የማይጥልህ ለምነኸው ፊቱን የማያዞርብህ ቀን አይቶ ብቻህን የማይተውህ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
አዲሱ ዓመት የሰላም የጤና ይሁንልን።
Dn Sintayehu Emagnu
መስከረም 01/01/2017 ዓ.ም

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

“ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንደሚሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋል” ዕብ 11፥6 እንዲል!
@ ጃንደረባው ሚዲያ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"ለነፍስህ የምታደርግላት ታላቅ ነገር አለ ይኼውም ራስህን በሚገባ መርምረህ ማወቅ ነው።"
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ፍኖተ #እንድርያስ
ብዙዎቻችን ለብዙ ደቂቃ ስላወራን የሰበክን ሊመስለን ይችላል። ለስብከት አርዓያ ብናደርጋቸው ብዬ የማስባቸው አራት ዓይናውን ሊቅ አቡነ እንድርያስን ነው። ብዙ ጊዜ ሲሰብኩ በቦታ ተገኝቼ ሰምቻለሁ። እኔ በተሳተፍኩባቸው ስብከቶች ረጅም ደቂቃ የሰበኩት 21 ደቂቃ ነው። ነገር ግን ከዐሥር ዓመት በፊት በአጭር ደቂቃ የሰበኩትን ስብከት እስካሁን አስታውሰዋለሁ።

በግሌ ስብከት ከ30 ደቂቃ ባይበልጥ ባይ ነኝ። በሠላሳው ደቂቃ ግን ቧልት፣ ፌዝ፣ ቀልድ ያልተቀላቀለበት ጉዳይ ተኮር፣ ሕይወት ተኮር ስብከት ቢሰበክ መልካም ነው። ስብከት እንዲህ ከሆነ ሥልጠና ግን ቀኑን ሙሉም ቢሰጥ ለውጥ ያመጣል ብየ አስባለሁ። ሥልጠና አንድን ጉዳይ አጥርቶ የማሳወቅ አቅሙ ከፍተኛ ነው።

ዓውደ ምሕረቶች ነገረ ክርስቶስ፣ ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ ማርያም፣ ነገረ ሃይማኖት፣ የሥርዓትና የሥነ ምግባር ትምህርቶች ቢሰጥባቸው አትራፊ እንሆናለን። የሙገሣ የጭብጨባ የግርግር ሰዓት ባይሆኑ ይመረጣል። ብፁዕ አባታችን አቡነ እንድርያስ በስብከት መካከል ጭብጨባንና እልልታን አጥብቀው ይቃወማሉ። እንኳንስ መንፈሳዊ ማዕድ ሥጋዊ ማዕድ ቀርቦ ምግቡ ቢጣፍጠን እንኳ ጣፈጠን ብለን መካከል ላይ እልል አንልም አናጨበጭብም። ምግቡን እያጣጣምን በሥርዓት እንመገባለን። በስብከት ሰዓት ጭብጨባና እልልታ ተገቢ አይደለም።

የጭብጨባና የእልልታ ሰዓት ማኅሌት ነው እንጂ ስብከት አይደለም። ፍኖተ እንድርያስን እንከተል ስል

፩ኛ ስብከታችን አንድን ጉዳይ ዓለማዊ ፍልስፍና ሳንቀላቅልበት እንደእርሳቸው መንፈሳዊውን ጉዳይ አሥርፀን ማጠቃለል ብንችል።

፪ኛ ሰዓት ማርዘም ሳይሆን ማስተማር የፈለግነውን ጉዳይ ግልጽ በሆነ አቀራረብ እስከ ሠላሳ ደቂቃ ባለው መጨረስ ብንችል። ከሠላሳ ደቂቃ በኋላኮ አብዛኛው የመስማት አቅሙ ይቀንሳል።

፫ኛ በስብከታችን መካከል ቧልት፣ ፌዝ፣ ቀልድ ባንቀላቅል።

ማለቴ ነው። የክርስትና ሕይወትና ትምህርት የሚሰለች አይደለም። በሕይወት እየተረጎምነው ስንሄድ ሁልጊዜ አዲስ (እንደገና አዲስ)፣ እያደር አዲስ ነው። የምናውቀውን ታሪክ መምህሩ ሲደግመው ብንሰማ እንኳ በዚህ ታሪክ ምን ያህል እንደተለወጥን ራሳችንን መመርመር ይገባናል።

© በትረ ማርያም አበባው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ደብረ ታቦር  


❖በዓለ  ደብረ  ታቦር  የሚውለው  በነሐሴ  13  ቀን  በመሆኑ ለጾመ ፍልሰታ ሱባዔ ልዩ ምዕራፍ ሆኖ በታላቅ መንፈሳዊ ተመስጦና  ማኀሌት  ይከበራል።  ከዘጠኙ  ዐበይት የጌታችን  በዓላት  አንዱ  ነው።  ምን  አድርጎበታል  ቢሉ ብርሃነ  መለኮቱን  ለሐዋርያት  በደብረ  ታቦር    ገልጾበታል። ደብር  ተራራ  ታቦር  የተራራ  ስም  ነው።  ጌታ  በመዋዕለ ስብከቱ  ብዙውን  ጊዜ  የሚያስተምረው  ተአምራት የሚያደርገው  በተራራ  ላይ  ነበር።  በዚህም  ዕለት ዘጠኙን  ከእግሩ  ደብር  ትቶ  ሶስቱ  ጴጥሮስን  ዮሐንሰንና ያዕቆብን  አስከትሎ  ከርእሰ ደብር ወጣ። ወተወለጠ ራዕዩ በቅድሜሆሙ  ወአብርሀ  ገጹ  ከመ  ፀሐይ  ወአልባሲሁኒ ኮነ  ጸዓዳ  ከመ  በረድ  ይላል  መልኩ  ተለውጦ  ፊቱ  እንደ ጸሐይ  አብርቶ  ልብሱ  እንደ  በረድ  ነጽቶ  ሙሴና  ኤልያስ በቀኝ  ሆነው  ታዩአቸው።  ሙሴንና  ኤልያስን  መምረጡ  ስለምንድነው  ቢሉ  ሙሴ  570    ጊዜ  ቃል በቃል  ተነጋግሮ    ባይህ  እወዳለሁ  አለው  ፊቴን  አይቶ  አንድ  ሰዓት  እንኳ  መቆም  መቆየት  የሚቻለው የለም  አለው  ።  ይህማ  ካልሆነማ  ባለሟል  መባሌ  ምኑ  ላይ  ነው።  ቢለው  ኃላ  ሰው  ሆኜ  ስመጣ እታይሃለው  ብሎት  ነበርና  ዘጸ  33:18-23  ነው።  ያን  ለመፈጸም  ኤልያስም  እንዲሁ  ተስፋ  ነበረውና አንድም  ጌታ  ዕውር  ቢያበራ  ሙት  ቢያነሳ  ሙሴ  ነው  ኤልያስ  ነው  ብለውት  ነበርና  የኛን  ጌታ  ማን ሙሴ   ማን ኤልያስ ይልሀል የሙሴ የኤልያስ ጌታ ይበሉህ እንጂ ብለው እንዲመሰክሩ አምጥቷቸዋል። ፍጻሜው  ግን  ደብረ  ታቦር  የመንሥተ  ሰማያት  ምሳሌ  ናት።  ሕጋውያንም  ደናግልም  እንዲወርሷት ለማጠየቅ ከሕጋውያን ሙሴን ከደናግል ኤልያስን አመጣ። ጴጥሮስ እመሰ ትፈቅድ ንንበር ዝየ ወንግበር ሠለስተ ማኅደረ አሐደ ለከ አሐደ ለሙሴ ወአሐደ ለኤልያስ ብትወድስ  አንዱን  ላንተ  አንዱን  ለሙሴ  አንዱን  ለኤልያስ  ሶስት  ጎጆ  ሠርተን  በዚህ  እንኑር  አለው። መጽአ  ደመና  ብሩህ  ወጸለሎሙ  ይላል  ።  ይህን  ሲናገር  ብሩህ  ደመና  መጥቶ  ጋረዳቸው  ወዲያውም ዝንቱ  ውእቱ  ዘአፈቅር  ወሎቱ  ስምዕዎ  ቢሉ  ደስ  የሚለኝ  ልጄ  ይህ  ነው።  እሱን  ስሙት  የሚል  ድምፅ ከወደ  ላይ  ተሰምቷል  ።እነ  ጴጥሮስ  ደንግጠው  ወደቁ  ተንሥኡ  ወኢትፍርሁ  ብሎ  አንስቷቸዋል  ። ከርእሰ  ደብር  ሲወርዱም  ያዩትን  የሰሙትን  እስከ  ትንሳኤው  ለማንም  እንዳይናገሩ  አዟቸዋል ።ማቴ  17  :3-9  ዘጠኙን  በእግረ  ደብር  ትቶ  ሶስቱን  አስከትሎ  መውጣቱ  ስለምንድነው  ቢሉ ከዘጠኙ  ብርሃነ  መለኮት  ሊያይ  የማይገባው  ይሁዳ  ነበርና  ትቶትም  ቢሄድ  ለየኝ  ባለ  ነበርና  አንድም ጴጥሮስ  እሞታለሁ  እነሣለሁ  ቢለው    ካንተ  ይራቅ  ብሎት  ነበርና  እሱን  ስሙት  የሚለውን  እንዲሰማ አምጥቶታል። ዮሐንስና ያዕቆብንም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ በቀኝ በግራ መቀመጥን ሽተው ነበርና ነው።  ያስ  ቢሆን  ከተራሮች  ሁሉ  ታቦርን  ስለምን  መረጠ  ቢሎ ዳዊት ታቦር  ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ መዝ 87:12ብሎ ያን ለመፈጸም ነው።

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

†††እንኳን ለቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ : ቅዱስ ዋርስኖፋ እና አባ ዮሐንስ ዘጐንድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

††† ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ †††

††† ቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተከተሉበት ሰዓት እድሜአቸው በ3 ደረጃ የተከፈለ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሳያል:: እንደ ዮሐንስ ወንጌላዊ ያሉት በ20ዎቹ ውስጥ : ቅዱስ ታዴዎስን የመሰሉት ደግሞ በ30ና በ40ዎቹ ውስጥ የነበሩ ሲሆን እነ ቅዱስ ዼጥሮስ ደግሞ በ50ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ::

ደቀ መዛሙርቱ ከወጣቶችም : ከጐልማሶችም : ከአረጋውያንም የተዋቀሩ ነበሩ ማለት ነው:: ቅዱስ ታዴዎስ በቀደመ ስሙ ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ (በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች) ስምዖን እና ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል::

ቅዱሱ ጌታችን ተከትሎ : ከ12ቱ አንዱ ሆኖ በፈጣሪው ተመርጦ : 3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታ እግር ተምሮ : በዕርገቱ ተባርኮ : በበዓለ ሃምሳም 71 ልሳናትን ተቀብሎ : ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ የበኩሉን አሕጉረ ስብከት ተካፍሎ ዓለምን ዙሯል::

ቅዱስ ታዴዎስ እስከ እርጅናው ድረስ ለወንጌል ሲተጋ ኑሯል:: ጌታችንም በየጊዜው በአካል እየተገለጸ አጽናንቶታል:: ከብዙ የድካምና የመከራ ዘመናት በሁዋላም ሐምሌ 2 ቀን ዐርፏል::

ቅዱሱ ሐዋርያ ያረፈው ሶርያ ውስጥ ሲሆን ከ250 ዓመታት በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ ታንጾለት በዚህች ቀን ወደ ቁስጥንጥንያ ፈልሷል:: ይህንን ያደረገው ደግሞ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ነው:: ከሐዋርያው ዘንድም ብዙ ተአምራት ተደርገዋል::

††† ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት †††

††† ቅዱሱ በትውልድ ግብፃዊ ሲሆን ገና ከልጅነቱ ጣዕመ ክርስትና የገባው ነበር:: መጻሕፍትን በማንበብ: ክርስትናንም በመለማመድ ስላደገ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት የመወደድ ሞገስ ነበረው:: በእድሜው እየጐለመሰ ሲሔድ በተጋድሎውም እየበረታ ሔደ::

በወቅቱ እርሱ የነበረባት ሃገር ዻዻስ በማረፉ ሊቃውንቱና ሕዝቡ ተሰብስበው አምላክን ጠየቁ:: እንደሚገባም መከሩ:: በደንብ አስተውለዋልና እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው ሁሉም ቅዱስ ዋርስኖፋን መረጡ::

ዛሬን አያድርገውና በአባቶቻችን ዘመን ሕዝቡም ሆነ ሊቃውንቱ መሪ መምረጥን ያውቁ ነበር:: ተመራጮቹ ደግሞ እንኩዋን እንደ ዘመናችን "ሹሙኝ : ምረጡኝ" ሊሉ በአካባቢውም አይገኙም ነበር::

ቅዱስ ዋርስኖፋ ለዽዽስና እንደ መረጡት ሲያውቅ "ጐየ" እንዲል መጽሐፍ: ጨርቄን ማቄን ሳይል በሌሊት ጠፍቶ በርሃ ገባ:: (እንዲህ ነበሩ አበው) በገባበት በርሃ ውስጥ በዓት ሠርቶ በጾም: በጸሎትና በስግደት በርትቶ ዓመታትን አሳለፈ:: እርሱ በበርሃ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ጀምሮ ብዙ ክርስቲያኖች አልቀው ነበር::

እርሱ ግን ከዓለም ርቁዋልና ይህንን አላወቀም ነበር:: አንድ ቀን መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ "አንተ በስሙ ደማቸውን ለሚያፈሱ አክሊላት እየታደለ : ሰማያዊ ርስትም እየተካፈለ ነውኮ! አልሰማህም?" አለው::

ቅዱስ ዋርስኖፋም "ለካም እንዲህ ያለ ክብር አምልጦኛል" ብሎ: በርሃውን ትቶ ወደ ከተማ ወጣ:: መልአኩ እንዳለውም ክርስቲያኖች ሲሰቃዩ ደረሰ:: ቅዱሱም ሳያመነታ ስመ ክርስቶስን ሰብኮ: ብዙ ተሰቃይቶ በዚህች ቀን አክሊለ ሰማዕትን በአክሊለ ጻድቃን ላይ ደርቧል::

††† እጨጌ አባ ዮሐንስ ዘጐንድ †††

††† ጻድቁ ተወልደው ያደጉት በኢየሩሳሌም ሲሆን ነገዳቸውም እሥራኤላዊ ነው:: ነገር ግን ተጋድሏቸውን የፈጸሙት በሃገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ ነው:: እጨጌ አባ ዮሐንስ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ ባለ ረዥም እድሜ ጻድቅ መሆናቸው ይነገራል::

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያረፉት በ562 ዓመታቸው ሲሆን እጨጌ አባ ዮሐንስ ደግሞ በ500 ዓመታቸው ነው:: የሚገርመው ጻድቁ የታላላቁ ጻድቃን ገብረ መንፈስ ቅዱስ : ተክለ ሃይማኖት: ሳሙኤል: ዜና ማርቆስ እና ሌሎችም ባልንጀራ ነበሩ::

በዛ ዘመን ዘረኝነት በቅዱሳኑ ዘንድ አልነበረምና ነጭ ሆነ ጥቁር : ከየትም ይምጣ የሰው ልጅ መሆኑ ብቻ በቂ ነበር:: እጨጌ አባ ዮሐንስ በሃገራችን 5 በዓቶች የነበሯቸው ሲሆን በአንድ በዓት የሚኖሩት ለ50 ዓመት ነበር::

በዚህም በኢየሩሳሌም ለ50 ዓመት : በኢትዮዽያ ደግሞ ለ450 ዓመታት ኑረዋል:: ከበዓቶቻቸው አንዱ ደብረ ሊባኖስ ሲሆን በገዳሙ ለ50 ዓመታት አበ ምኔት(እጨጌ) ሆነው አገልግለዋል:: "እጨጌ" የሚባሉትም በዚህ ምክንያት ነው::

ጻድቁ የመጨረሻ ዘመናቸውን ያሳለፉት በጐንድ (ጉንድ) ተክለ ሃይማኖት ገዳም ነው:: ገዳሙ የሚገኘው በሰሜን ጐንደር ዞን : በለሳ ወረዳ ውስጥ ሲሆን የመሠረቱትም ራሳቸው ናቸው:: ነገር ግን በራሳቸው እንዲጠራ አልፈለጉምና ገዳሙ የሚጠራው በወዳጃቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም ነው::

ጐንድ እኛ ኃጥአን ሳይገባን ያየነው ገዳም ነው:: ዛሬም ድረስ ድንቅ የሆኑ አበው የሚኖሩበት : ተአምራትም የማይቋረጥበት : ፈዋሽ ጠበል ያለው ደግ ገዳም ነው:: ጻድቁ እጨጌ አባ ዮሐንስ ግን አስታዋሽ አጥተው እየተዘነጉ ካሉ ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ምንም ዛሬ አጽማቸው ፈልሶ ወደ ደቡብ ኢትዮዽያ አካባቢ ቢሔድም እርሳቸው በ500 ዓመታቸው ያረፉት በዚህ ገዳም ውስጥ ነው::

††† እግዚአብሔር ከሐዋርያው : ከሰማዕቱና ከጻድቁ ክብርን : በረከትን ያሳትፈን::

††† ሐምሌ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት
3.እጨጌ አባ ዮሐንስ (ዘጐንድ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)

††† "ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል::" †††
(1ዼጥ. 5:3)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

🌧☔️
በአንድ ሀገር ዝናብ ጠፋና ህዝቡ ሁሉ ተጨነቀ በመጨረሻም ምህላ እንዲደረግ ተወሰነ።
ህዝቡ ሁሉ ወደ ቤተክርስትያን ጉዞ ጀመረ አንዲት ህፃን ግን በጉዞው መሃል ዣንጥላ ይዛ ነበር። ለምን እንደያዘች ስትጠየቅ ወደ ቤተክርስትያን እምንሄደው ዝናብ እንዲዘንብ ለመለመን አይደለም? ታዲያ ስንመለስ በምን እንጠለላለን ስትል መለሰች።
ስለዚህች ህፃን እምነት በዛች ቀን ዝናብ ዘነበ ህዝቡ ሁሉ በዝናብ ሲደበደብ እርሷ ግን በያዘችው ዣንጥላ ተጠልላ ነበር።

ብዙዎቻችን የዚችን ህፃን ያህል ቅንጣት ታህል እምነት የለንም፣ ብዙ ነገር እንጠይቃለን የጠየቅነው ነገር እንደሚሰጠን ግን እርግጠኛ ሆነንና ተዘጋጅተን አንጠብቅም።

ከአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ የተወሰደ

አምላከ ህጻናት ክብር ምስጋና ይድረሰው!!

ተወዳጆች ሆይ እኛስ በእምነታችን ምን ትሩፋት አገኘን?

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል አሁናዊ ሥርዓተ ዋዜማ በዚህ መልኩ ቀጥሏል

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ቅዱሳንን ማክበር ጥቅሙ ለማን ነው?

ፀሐይን የሚያይ ሰው የፀሐይቱን ብርሃን ይበልጥ ብሩህ እንዲኾን
አያደርገውም፤ የገዛ ራሱን የማየት ዓቅሙን እንዲጨምር ያደርጋል
እንጂ፡፡ ልክ እንደዚሁ፡ ሰማዕታትን (ቅዱሳንን) የሚያከብር ሰውም
ሰማዕታቱን ይበልጥ እንዲከበሩ አያደርጋቸውም፤ እርሱ
ከሰማዕታቱ (ከቅዱሳኑ) የሚቀድስ በረከትን ይቀበላል እንጂ፡፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ሺ_ዓመት_አይኖር

🥀ብዙ ጊዜ ለስንፍናችን ምክንያት ወይም ተስፋ ለመቁረጥ ሰበብ ከሚሆኑን ነግሮች አንዱ "ሺ ዓመት አይኖር" የሚለው አባባል ነው በእርግጥ በምድር ሺ ዓመት መኖር የቻለ የለም ረጅም ዓመት እንደኖረ የሚነገርለት ማቱሳላ እንኳን ሺ ዓመት አልኖረም ወዳጄ በተለይ እኛ ባለንበት በዚህ ዘመን ደግሞ እንኳን ሺ ዓመት ሊኖር ቀርቶ መቶ የሞላ እንኳን ቢገኝ የሚድያ የአንድ ወቅት የዜና ሽፋን መሆኑ የማይቀር ነው ስለዚህ ወደ ዘመናችን አባባሉን ማምጣት ከፈለግን መቶ ዓመት አይኖር በሚል ልንቀይረው ያስፈልጋል።

🥀የሚያሳዝነው ሺ ዓመት አይኖር የምንለው ለመዝናናት ለመጨፈር ራስን ለመርሳት ፈቃደ ሥጋን እንደ ልብ ለመፈጸም ብቻ እንጂ ለመንፈሳዊ ሕይወት ለመሰናዳት አይደለም "አንቂ" የሚባሉ አካላት የዕድሜህን አጫርነት የሚነግሩህ ከሞት በኋላ ላለው ረጅሙ ዕድሜ በዚህች በአጭሯ የምድር ዕድሜህ በጎ ሰርተህ እንድታልፍ ሳይሆን እንዳትጨናነቅ ፈታ ብለህ(በእነርሱ አማርኛ) እንድትኖር ለማስታወስ ብቻ ነው።

🥀ወዳጄ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ግን በምድር ስለምትኖርበት ዕድሜህ ሲነግርህ ቢበዛ(ቢበረታ) ሰማንያ ይልሃል ሺ ዓመት አይኖር ሲሉህ ቢበዛ ሰማንያ እርሱም በተገኘ በላቸው ታድያ በምድር የምትኖርበት ዕድሜህ ጥቂት ከሆነ ከዚያ በኋላ በሞት ይህን ምድር ከተሰናበትክ ከሞት በኋላ የት ትሄድ ይሆን?? የዚህ ምድር ኑሮህ በሞት ከተቋጨ በኋላ ሞተህ የምትቀር መስሎ እንዳይሰማህ ከሞት በኋላ ሕይወት አለህ ያውም እንደሰው ኖረህ ከሞትክ የምትነሳው እንደ ሰው ሆነህ የምትኖረውን ሕይወት ለመድገም

🥀እንዳይመስልህ ከትንሣኤ በኋላ የምትኖረው እንደ መላእክት ነው “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ”ማቴ 22፥30
ስለዚህ አስታውስ የምድር ኑሮህ ቢበዛ ሰማንያ ነው ያ ማለት ጥቂት ነው መጽሐፍ
እንደሚነግርህ

🥀ሕይወታችሁ ምንድር ነው ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና”
ያዕ 4፥14

🥀ስለዚህ በምድር የምትቆየው ጥቂት ጊዜ ነውና:-*
ዛሬ የንስሐ አባት ያዝ
ዛሬ ንስሐ ግባ
ዛሬ ከተጣላሃቸው ታረቅ
ዛሬ ያስቀየምካቸውን ይቅር በል
ዛሬሥጋ ወደሙን ተቀበል

ነገ ሳይሆን ዛሬ መልካም ነገሮችህን ሁሉ ጀምር ምክንያቱም
“እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
2ኛ ቆሮ 6፥2   የሞዐ
     Join  ቴሌግራም ቻናል

  አምላከ ቅዱሳን ለንስሐ የተዘጋጀ ልብ ያድለን
ለንስሃ ሞት ያብቃን🙏

❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ


👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እመኑ ብየ
https://youtube.com/watch?v=8NxHAUlTxDg&feature=shared

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
መስከረም 21-ብዙኃን ማርያም (የእመቤታችን የበዓሏ መታሰቢያ ነው፡፡)
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አስቀድሞ ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው ቅዱስ ቆጵርያኖስ በሰማዕትነት ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
+ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ በነው የጠፉት ድንግሊቱ ዮስቴናም በሰማዕትነት ያረፈችው በዚሁ ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም ይህች ዕለት የከበሩ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ አበው ሊቃውንት በ325 ዓ.ም አርዮስን አስተምለው ለመመለስ በኒቅያ የተሰበሰቡባት ዕለት ናት፡፡ የጉባኤውም ፍጻሜ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ኅዳር ዘጠኝ ነው፡፡
+ የጌታችን ቅዱስ መስቀል ግሸን ደብረ ከርቤ የገባበት ዕለት ነው፡፡ (የመስከረም ዓሥራ ሰባቱን ይመለከቷል፡፡)
+ ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጢባርዮስ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

"የክርስቶስ መስቀል ታላቅ በረከትንና ድኅነትን እንድናገኝ ምክንያት እንደ ሆነ እናስተውላለን፡፡ የክርስቶስ መስቀል ስናስበው ሐዘንና ምሬት ነው ነገር ግን እውነታው ደስታና ሐሴትን የሚሞላ ነው፡፡ መስቀል ለቤተ-ክርስቲያን ድኅነት ነው መስቀል ተስፋ ለሚያደርጉት መመኪያ ነው መስቀል የእግዚአብሔር ጠላቶች የነበሩት የታረቁበትና ኃጢአን ወደ ክርስቶስ የቀረቡበት ነው፡፡ በመስቀል ከጠላትነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ተሸጋግረናል በመስቀል ከዲያብሎስ ቀንበር ወጥተናል ከሞት ወደ ሕይወት መጥተናል፡፡ ስለ መስቀል የማንሰብክ ከሆነ አሁንም በሞትና በፍዳ እንደ ተያዝን ነው ማለት ነው፡፡
            ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
/channel/dnhayilemikael

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ልብሰ ተክህኖን ክህነት የሌለው ሰው መንካትና ማጠብ አይችልም። ሥርዓት አይደለም። በቅንነት አንዳንድ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት አድርጋችሁት ከነበረ ከእንግዲህ እንዳታደርጉ ትምህርት ይሁናችሁ። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፰ ላይ ከዲያቆናት፣ ከቀሳውስትና፣ ከዚያ በላይ ከሆኑት በስተቀር ንዋየ ቅድሳትን እንዲነኩ አልተፈቀደም። ስለዚህ ካህናት ሆይ ክህነት የሌላቸው ሰዎች ንዋየ ቅድሳትን እንዲነኩና እንዲያጥቡ አታድርጉ።

መ/ር በትረ ማርያም አበባው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

✓•ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?

✓•ተወዳጆች_ሆይ!
አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡

✓•ልብ_በሉ!
ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

✓•ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን?
እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና።

ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ይብሰተ_አእምሮ
#የአእምሮ_ድርቀት

የወንጌል አንድምታ ትርጓሜያችን እንዲህ ይላል 👇
"አሥራ ሁለት መሳክወ ነፋሳት አሉ
አራቱ መሳክው (መስኮቶች) የአራት
#ነፋሳተ_ምሕረት መውጫ ሲሆኑ
ስምንቱ መሳክው ደግሞ የስምንቱ ነፋሳተ መዓት መውጫ ናቸው
#ስምንቱ ነፋሳተ መዓት ሲታዘዙ በዓለም ላይ አምስት ዓይነት መቅሠፍት ይወርዳል
ከነዚያ ውስጥ አንዱ
#ይብሰት/ድርቅ ነው ይልና ይብሰት በሁለት እንደሚከፈል ይናገራል
የመጀመሪያው የእህል የውሃ መታጣት ሲሆን
ሁለተኛው ግን
#ይብሰተ_አእምሮ (የአእምሮ ድርቀት) ነው
👉በዚህ ዘመን የገጠመን ዋና በሽታ ይህ ይመስለኛል
በዓለም ላይ እየከተሠቱ የምናያቸውና የምንሰማቸው ችግሮች ሁሉ
#በይብሰተ_አእምሮ የተቀደሙ ናቸው
• የእርስ በእርስ ጦርነት
• የሀገራት ጦርነት
• የኅፃናት መደፈርና መገደል
• የታላላቅ ሰዎች አለመከበር
• የሙስና መስፋፋት
• የተመሳሳይ ፆታ መጋባት
• መተሳሰብና መተዛዘን መጥፋት ...እነዚህ ሁሉ የ
#ይብሰተ_አእምሮ ውጤቶች ናቸው

የሰውነት ልክ የደረቀበት
እውነት የማይታመንበት
እውነት ተናጋሪ የሚሰቀልበት
ውሸት የለመለመበት
ጩኸት የሚቀማበት
ዕውቀትና አዋቂዎች የሚገፉበት ይህ ዘመን ነው
ይኸውም ይብሰተ አእምሮ ነው
ይብሰተ አእምሮ ሲከሠት በሁሉም ቦታ
#ደህና_ሰው ይታጣል
ጽኑ ተስፋ በሚጣልባቸው በሃይማኖት ቦታዎች ሳይቀር
#ደግ_ሰው ይታጣል
ፍርድ ይዛባል፤ ድሃ ይገፋል....መደማመጥ የለም ...ሁሉም አውቃለሁ ይላል...ጫጫታ እንጂ ንግግር የለም!!!
ይህ
#ይብሰተ_አእምሮ ይባላል

መፍትሔው በሃይማኖትና በምግባር መታነጽ ዕውቀት ንባብና መደማመጥ ነው !!!!!

የራስ ቅል ድርቀት በቅባት እንደሚርስ
የዕውቀት ማጣትም በንባብ ይርሳል ይታደሳል!

መጪውን ዘመን የደረቀውን አእምሯችንን በንስሐ አለምልመን
በሥጋ ወደሙ አፍርተን
በንባብና በዕውቀት ታድሰን የምንኖርበት ያድርግልን !!!

ለሀገራችን ሰላምን ይስጥልን!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

++ ከእምነት በፊት መዳን ++

( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ )

የተፈጠርነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ሰው ሆነን ወደ ምድር የመጣንበትን ዘመን፣ የተገኘነበትን ምድር፣ የወጣንበትን ማኅበረ ሰብእ እና ሌሎችንም ጉዳዮች የመረጠ እርሱ እግዚአብሔር ነው። አዳም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ በራሱ ምርጫ ራሱን ያስገኘ ማን አለ? አጭር ወይም ረዥም፣ ቀጭን ወይም ወፍራም፣ ነጭ ወይም ጥቁር ሆኖ ስለመወለዱ ከእግዚአብሔር ጋር የተማከረስ ማነው? ሁሉም በእግዚአብሔር ፈቃድ የተከናወነ ነው። ገበሬ ዘሩን በምድር ላይ በበተነ ጊዜ ምድሩን ለዘሩ የሚመርጥለት ገበሬው ነው እንጅ ዘሩ እንዳልሆነ ሁሉ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ምርጫ እንጅ በራሱ ምርጫ ወደ ዓለም ሊመጣ አይችልም።

በዚህ መንገድ ወደ ምድር የመጣ የሰው ልጅ የሚኖረውም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መሠረት አድርጎ ነው። በማኅፀን በሠራን ጊዜ ለሕይወታችን የሚያስፈልገንን አንዳች ሳያጎድል ሠርቶ ከማኅፀን ስላወጣን በምድር ላይ ስንኖር የምንኖርበትን ትዕዛዝ ቢያዝዘን አንዳች እንደሚያጎድልብን ሳንጠራጠር አምነን እንታዘዝለታለን። በባሕር የሚኖሩትን በባሕር ለመኖር የሚያበቃቸውን፣ በየብስም የሚኖሩትን በየብስ ለመኖር የሚያስችላቸውን አካል ሰጥቶ ፈጥሯቸዋል። አካላችንን ከሥርዓተ ዓለም ጋር አስማምቶ ምንም የማይጠቅም አካል ሳይጨምር የሚበቃንን እና የሚያስፈልገንን ብቻ ሰጥቶ ወደ ዓለም እንድንመጣ ማድረጉ ለእኛ የሚያስፈልገንን ሁሉ በመስጠት የሚያኖረን እርሱ ብቻ መሆኑን እንድናምን ያስገድደናል።

ከዚህም የተነሣ ነው ሰባኪዎቻችን፥ በሰው እንዳንታመን “ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆችም አትታመኑ ነፍሳቸው ትወጣለች ወደ መሬትም ይመለሳሉ” መዝ 145፥3 ብለው ብለው መታመናችንን በሥጋዊና በደማዊ ፍጥረት ላይ እንዳናደርግ የመከሩን።

ልንኖረው ከተፈቀደልን ሦስት ክፍል ካለው ኑሯችን የመጀመሪያውን ያለ እግዚአብሔር በቀር ከእኛም ሆነ ከሰዎች አንዳች ምክር የሰጠበት የለም። ከማኅፀን ከወጣንም በኋላ የምንኖረው ሁለተኛውን ክፍል ኑሯችንን ሲሆን ከማኅፀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ ራሳችንን በሰዎች ዕቅፍ ስለምናገኘው ነው መሰለኝ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ይልቅ በራሳችንና በሰዎችም ፈቃድ የመኖር ዝንባሌ ይታይብናል።

በውስጣችን ባለው አድሮብን፣ ተዋሕዶን ከሚኖረው አምላካችን ይልቅ አጠገባችን ከጎናችን ባሉ ሰዎች ተስፋ እናደርጋለን። ይልቁንም በቤተ እግዚአብሔር ለሚኖሩ ሰዎች በሰው መታመን እንዴት ያለ አስቸጋሪ ነገር መሰላችሁ?

ይህንን ያልሁት የዛሬውን መጻጉዕን ጉዳይ ሳስብ ቀድሞ የሚመጣብኝ እግዚአብሔር ሰዎችን ወድ ሚያድንበት ስፍራ ሂዶ ሰው መጠበቁ ስለሚያስገርመኝ ነው። የመጻጉዕን መዳን ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያዘገየበት በሰው ስለሚታመን ሳይሆን አይቀርም። “ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት” ዮሐ 5፥5 በሚለው የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የሚታየው ሀሳብ መጻጉዕ በእግዚአብሔር ደጅ እየኖረ በሰው የሚታመን በሽተኛ እንደነበረ የሚያሳይ ነው። ከሩቅ ቦታ አምጥቶ የመጠመቂያው ስፍራ ያደረሰው ማነው? ይሄ ሰው ይህንን ያኽል ዘመን እንዴት አንድ ሰው ወደ መጠመቂያው እንዲወርድ ሊረዳው አልፈቀደም? አብረውት በመጠመቂያው ስፍራ ተኝተው የሚሰነብቱ አንካሶችን በሽተኞች ከዳኑ በኋላ እንኳን ይህንን ሰው ወደ መጠመቂያው ስፍራ አውርደውት ድኖ እንዲመለስ እንዴት አላደረጉትም? እያልሁ ብዙ ጊዜ አስቤ አውቃለሁ።

ይህ ሰው ከመጀመሪያው እምነት የጎደለው ነው። የዳኑት ሁሉ እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው ሳይሆን ሰው ስላላቸው ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ነው። የመጣው የእግዚአብሔር መልአክ በወረደ ጊዜ በሚናወጠው ውኃ ውስጥ ገብቶ ተጠምቆ ፈውስ ለማግኘት ነው ነገር ግን በሃይማኖቱ ላይ የሰዎችን እርዳታ ካልተጨመረበት በቀር መዳን እንደማይችል በማሰብ ይሄንን ሁሉ ዘመን ሰው ሲፈልግ ነው የኖረው። በእግዚአብሔር ፊት ሆኖ ሰው መጠበቅ የሚያስገርም ነገር ነው። ለዚህም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ካዳነው በኋላ ራሱን ሳይገልጥለት በሰዎች መካከል ሆኖ የሄደው። እሱም ያዳነው ማን እንደሆነ ሊመረምር አልተመለሰም። ሰው ሲጠብቅ የኖረ ሰው እግዚአብሔር አዳነኝ ማለት እንዴት ይችላል? አይሁድ በጠየቁትም ጊዜ “ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ” ነው እንጅ ያለው እግዚአብሔር አዳነኝ አላለም።
እምነታችን ሳይጸናልን ገንዘብ ብንቀበል፣ ሥልጣን ብናገኝ፣ ጤና ቢኖረን፣ ጉልበታም ብንሆን፣ ውበትና ደም ግባት ቢስማማልን፣ ዓለምን በመላው የእኛ ማድረግ ብንችል ምንም ጥቅም እንደሌለው ተመልከቱ።

መጻጉዕ ያዳነውን ትቶ አልጋውን ተሸክሞ መሄዱ ያሳዝናል። ከዚያች ቀን ጀምሮ ሰይጣን ዝም ብሎ ሊተወው አልወደደም። እስከ ዕለተ ዐርብ ድረስ ተከታትሎ ፍጹም ኃጢአት አሠርቶታል። በሕይወቱ ውስጥ ከሕማሙ ቀጥሎ ሌላ ፈተና ይዞበት የመጣው ፈውሱ ከእምነቱ በመቅደሙ ነው። ከዳነ በኋላ ከዐሥሩ ለምጻሞች እንደ አንዱ እግዚአብሔርን እያመሰገነ በቤተ መቅደስ ሊገኝ ይገባው ነበር እርሱ ግን ይህንን ሲያደርግ አልታየም። ያለ ሃይማኖት የሆነ ነገር ሁሉ ፈተናው ከባድ ነው።

ከሁሉም ነገር በፊት ሃይማኖትህን እንዲያጸናልህ ለምን። ሕይወትህን ከሚገጥምህ ፈተና ሁሉ ጠብቆ ሊያኖራት የሚችል በልብህ ውስጥ ያለው ሃይማኖትህ ነው። ሁሉንም ነገር ከተቀበልህ በኋላ ከሁሉም አስቀድሞ እግዚአብሔርን ለማመስገን ጊዜ ይኑርህ። ንብረትህን ከመሰብሰብህ በፊት ልብህን ሰብስበህ አስብ። ቀጥሎ ለምትጓዝበት መንገድ የሚረዳህ ይህ ነውና። ዳዊት ጎልያድን በማሸነፉ “አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሀለሁ” ብሎ ዘመረ እንጅ በራሱ ወይም በሌላ ሰው አልተመካም። ስለዚህም እግዚአብሔር ለሌላ ከፍ ላለ ጸጋ መረጠው። በሰዎች ላይ የጀመረውን ማሸነፍ በአጋንንት ላይ ደገመው። ሳኦልን ከሰዎች እጅ ብቻ ሳይሆን ከመናፍስትም እጅ የሚያድንበትን መንፈሳዊ ጉልበት ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበለ። ራሱ ለእግዚአብሔር መዝሙር እያዘጋጀ ስለነበረ ጎልያድን በመግደሉ ሰዎች ስለራሱ የዘመሩትን ዝማሬ አልሰማቸውም።

ወንድሜ ከእግዚአብሔር እጅ ከዚህ የሚበልጥ ሌላ ስጦታ ስለሚጠብቅህ ያዳነህን መርምረህ ሳታውቅ የተሰጠህን አልጋ ብቻ ይዘህ አትውጣ። ከግዚአብሔር ፊት ስትወጣ የሚያገኙህ ሁሉ የሚመለከቱት መዳንህን ሳይሆን የተሸከምኸውን አልጋ ነው። ስንት ዘመን ታመህ እዚህ እንደደረስህ እነሱ አይገባቸውም። ለሕጋቸው እንጅ ለሰው የሚጨነቁ አይደሉም። ስህተቱ፥ ላንተ የሚያስብ እግዚአብሔርን ትተህ እነሱ ወዳሉበት መሄድህ ነው። ሰው አድርጎ በፈጠረህ ጊዜ ለሰውነትህ የሚያስፈልጋትን ሁሉ አስማምቶ የፈጠረህ ጌታ ዛሬም አንተን ለማኖር የሚበቃ ኃይልና ፈቃድ ስላለው ሁልጊዜም ከፊቱ አትጥፋ። ሳታምን ምንም እንዲደረግልህ አትለምን። በእምነት ድል ወደማትነሣው ክብር ለመግባትም አትሞክር።

በጸና እምነት ወስጥ ካልኖርህ፦ ክብር ቢኖርህ ከንቱ ውዳሴ ይጥልሃል። ሀብት ቢኖርህ ጥጋብ ያጠፋሃል። ዝና ቢኖርህ መታበይህ ማዕበል ሆኖ ያሰጥምሃል። ውበት ቢኖርህ ለዝሙት አሳልፎ ይሰጥሃል። ጌጠኛውን ልብስ የመልበስ ዕድል ቢያጋጥምህ ለትውዝፍት ይዳርግሃል። ወንድሜ ያለ እምነት ከሆነ በምንም ነገር እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልምና ከሁሉም ነገር በፊት እግዚአብሔር ሃይማኖትህን እንዲያጸናልህ ለምን።

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 8

ቁጥር 16 ካህናት ከሠርግ አዳራሽ ሄደው ዘፈን መስማት አይገባቸውም። የሚፈክሩት የሚዘፍኑት ሳይመጡ በልተው ጠጥተው መርቀው ይመለሱ እንጂ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

የእመቤታችን ዕረፍትና ዕርገት በቅዱስ ያሬድና በአባ ጽጌ ድንግል
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ እያለ ያወድሳታል፦
╬ “ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”
(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)

╬ “በደመና ተጋቢኦሙ ሐዋርያት ለድንግል ንጽሕት
ገነዝዋ በክብር ወበስብሐት
ለቀበላሃ ወረዱ ኀይላት
ወቀበርዋ ውስተ ገነት”
(ሐዋርያት በደመና ተሰብስበው ንጽሕት ድንግልን በክብር በምስጋና ገነዟት፤ ለአቀባበሏ ኀይላት ወረዱ፤ በገነት ውስጥም ቀበሯት)

╬ “ተጋቢኦሙ ሐዋርያት እምኲለሄ
በደመናት ዘምሉእ ሡራኄ
ገነዙ በክብር ወበስባሔ
ሥጋ ድንግል ዘይምዕዝ እምርሔ”
(ብርሃንን የተመላ በኾነ በደመናት ሐዋርያት ከአራቱ ማእዝን ተሰብስበው ልብን ከሚመስጥ ሽቱ ይልቅ የሚሸትት የድንግልን ሥጋ በክብርና በምስጋና ገነዙ)

╬ “ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ
ሐዋርያት ሥርግዋን በዕበይ
ገነዝዋ ለድንግል በብዙኅ ግናይ
ዳዊት ዘመራ በመሓልይ”
(በገናንነት የተጌጡ ሐዋርያት በሰማይ ደመና ተሰብስበው ድንግልን በብዙ ምስጋና ገነዟት፤ ዳዊትም በምስጋና አመሰገናት፡፡)

╬“ተጋቢኦሙ አርድዕተ ወልዳ
በደመና ብርሃን ጸዐዳ
ገነዝዋ በስብሐት ለጽርሕ ሳይዳ”
(ጸዐዳ በኾነ በብርሃን ደመና የልጇ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበው፤ ውቢቱ አዳራሽን በምስጋና ገነዟት)

╬ “ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት
ብፁዓን ሐዋርያት
ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ
በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ”
(ንኡዳን ክቡራን ሐዋርያት ቅድስት የምትኾን የጌታ እናቱን ለመገነዝ በቅጽበት ተሰበሰቡ፤ ወደ ርሷ ገብተው በሰላምታ ርሷን እጅ ነሧት፤ ሥጋዋንም በምስጋና ገነዙ)

╬  “ፃኢ እምሊባኖስ ሥነ ሕይወት ርቱዕ አፍቅሮትኪ ቡርክት አንቲ እምአንስት ማኅደረ መለኮት ሰላም ለኪ፤ ማርያም እመ አምላክ ወልድኪ ይጼውዐኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር”
(የሕይወት ደም ግባት የአምላክ እናት ከሊባኖስ ውጪ፤ ፍቅርሽ የቀና ነው፤ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ፤ የመለኮት ማደሪያ ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ የአምላክ እናት ማርያም ሆይ ልጅሽ ወደ ዘላለማዊ ሕይወትና ወደ ክብር መንግሥት ይጠራሻል)

╬ “ፈለሰት ማርያም በስብሐት ውስተ ሰማያት መላእክት ወሊቃነ መላእክት ወረዱ ለተቀብሎታ”
(እመቤታችን በምስጋና ወደዚያኛው ዓለም በተለየች ጊዜ ለአቀባበሏ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ወረዱ)።
                 ☀️☀️☀️
💥 አባ ጽጌ ድንግል እንዲኽ እያለ ያወድሳታል:-
❖ "እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ
አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ
ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘትጼንዊ ለአንፍ
እንዘ ይትጓድዑ አክናፈ በክንፍ
ለቀበላኪ ወረዱ አእላፍ”
(ለአፍንጫ መዐዛን የምትሰጪ የገነት ዛፍ ማርያም ሆይ፤ ልጅሽ በክንዱ ዐቅፎ በአፉ እየሳመ በቀኙ ሊያሳርፍሽ ባሳረገሽ ጊዜ፤ አንቺን ለመቀበል ክንፍ ለክንፍ እየተጋጩ እልፍ አእላፋት መላእክት ወረዱ)

❖ “ትእምርተ ፍልሰትኪ እምድረ ጽጌ ድንግል በክልኤ
በደመና ሰማይ አርአየ ዘሐዋርያት ጉባኤ
ወእለ ሞቱ አንቅሐ እምከርሠ መቃብር ቀርነ ጽዋዔ
ለነሰ እንዘ ይብሉ ሶበ ሰማዕነ ውዋዔ
መሰለነ ዘበጽሐ ትንሣኤ”
(በኹለት ወገን ድንግል የኾንሽ ማርያም ሆይ አበባ ካለበት ምድር ወደ ሰማይ የማረግሽ ተአምር በሰማይ ደመና የሐዋርያት ጉባኤን አሳየ፤ የሞቱትንም ከመቃብር ውስጥ በተአምር ነጋሪት ድምፅ አስነሣ፤ ለእኛስ የምስጋና ከፍተኛ ድምፅን በሰማን ጊዜ የሙታን መነሣት የደረሰ መሰለን እስኪሉ ድረስ)።

❖ “አመ ነሥኡኪ እምኤዶም አዕላፈ ማሕሌት ጾታ
እንዘ ይጼልሉኪ ድንግል በአክናፈ መባርቅት ከመ ወልታ
ሰራዊተ ሰማይ ይቤሉ ለክብረ ፍልሰትኪ ግርማ ትርሲታ
መኑ ይእቲ ዛቲ ዘገዳመ ጽጌ ዕጥነታ
ወከመ ሠርጸ ጢስ ዘስኂን ይምዕዝ ዕጥነታ”
(ድንግል ወገኖች አመስጋኞች መላእክት በየነገድ በየነገድ ኾነው በመባርቅት ክንፎች እንደ ጋሻ ጋርደው ከኤዶም ገነት በተቀበሉሽ ጊዜ የሚያስደንቅ ክብር ለተገለጸባት ለዕርገትሽ የሰማይ ሰራዊት አበባ ካለበት በረሓ የምትወጣ መዐዛዋም ከነጭ ዕጣን ይልቅ የሚሸትት አወጣጧም እንደ ጢስ አወጣጥ የኾነችይኽቺ ማናት? ይኽቺ ማን ናት ይላሉ (መሓ ፫፥፲፮))።
[የአምላክ እናት ሆይ እወድሻለሁ]
✍️ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

ኦያያያያያያያያያ ወልደ እንትና ዐሥር ሺ ብር ሰጥተዋል። ምእመናን ሴቶች በእልልታ ወንዶች በጭብጨባ አመስግኑልን_እልልልልልል_ጨብጨብጨብጨብ_ወዘተ። ጨረታ ዐውደ ምሕረት ላይ ለምን???

በአንድ መግለጫ ብቻ መስተካከል የሚችል ነገር ግን ቸል የተባለ ጉዳይ፦

፩. አዲስ አበባም ሌሎች ከተሞች ላይም ቄሶች ነን የሚሉ፣ መነኮሳት ነን የሚሉ መንገድ ላይ ሰው ከተሳለማቸው በኋላ አስገድደው ውዳሴ ማርያም ወይም ሌላ የጸሎት መጽሐፍ ካልገዛችሁን የሚሉ ብዙ ናቸው። ይህ እኔንም ገጥሞኛል። ይህን ሙሉ በሙሉ ለምእመኑም አሳውቆ ማስቀረት።

፪. ጥላ ዘቅዝቆ በዐውደ ምሕረት ውስጥ መለመን ቢቀር። በተጨማሪ ዐውደ ምሕረት ላይ ጨረታ፣ መጽሐፍ መሸጥና የመሳሰሉ ንግዶች መቅረት አለባቸው። በእግዚአብሔር ቤት ንግድና ጨረታ ማድረግ ታላቅ ኃጢአት አይደለምን????

፫. የገጠሪቷ ቤተክርስቲያን ጧፍ፣ ዘቢብ፣ ዕጣን አጥታ ተቸግራ ሳለ በየዐውደ ምሕረቱ ዝም ብሎ የሚነድ ጧፍ መኖር የለበትም። በፍትሐ ነገሥት እንደተነገረው የሐዋርያት መልእክት ሲነበብ ጧፍ መበራቱ አንትሙ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም ብሏቸዋልና የዚያ ምሳሌ ነው። ወንጌል ሲነበብ ብዙ መብራት እንዲበራ ታዟል። ጌታ አነ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም ብሏልና የዚያ ምሳሌ ነው። በወንጌል ጊዜ ብዙ ይብራ መባሉ የጌታ ብርሃንነት የባሕርይ ስለሆነ ይህንን በሥርዓታችን ለመመስከር ነው።

፬. በበዓላት ወቅት በዓሉን ለማክበር የመጣው ሕዝብ የወንጌልን ትምህርት መማር ሲገባው የስለት ጊዜ እየተባለ ምእመናንን ማሰልቸት ተገቢ አይደለም። ስለት የሚቀበል ለብቻው መድቦ በዐውደ ምሕረቱ ግን ወንጌል ነው መሰበክ ያለበት።

፭. ቤተክርስቲያን አሥራት የምትቀበልበት፣ በውስጧ ላሉ አግልጋዮች ደመወዝ የምትከፍልበት የራሷ ባንክ ለምን አይኖራትም??? ይህ ቢሆን ምእመናንም አሥራታቸውን ቀጥታ በባንክ ይከፍላሉ። ስለታቸውንም ሌላውንም በዚያ ያስገባሉ። ይህ ሆነ ማለት ደግሞ የሙዳየ ምጽዋት ሌቦች ምክንያት ያጣሉ ማለት ነው።

፮. ማዕከላዊ የሆነ የደመወዝ ክፍያ ለምን አይኖርም? ለምንድን ነው መምህራን አዲስ አበባና ከትልልቅ ከተሞች የተከማቹት?? በረሓ የሚሄደው ቀነሰ፣ የገጠር አጥቢያዎች ላይ አገልጋይ እየጠፋ ነው። ይህ እንዳይሆን መምህራንን ወደየቦታው መበተን አስፈላጊ ነው። በረሓ ለሚሄዱት ከተማ ካለው የበለጠ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ማድረግ። ይህ ቢደረግ ወንጌል ትሰፋለች።

አንድም ካህን ጎዳና ላይ ሲለምን እንዳይገኝ፣ ከተገኘ ግን ምእመናን ለአቅራቢያ ቤተክህነት አሳውቀው እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ ይቻላል።

© በትረ ማርያም አበባው

🌹

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

እንኳን አደረሰን!

በዓለ ቅዱሳን፦
❖ዮሴፍ አረጋዊ (ትሩፍ)
❖ወጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት (ዘአልቦ ጥሪት)
❖ፍሬምናጦስ ሰላማ (ከሣቴ ብርሃን)
❖ወሳሙኤል (ዘሃሌ ሉያ)

ሐምሌ ፳፮፦

✝ሰላም ለስዕርተ ርዕስከ ዘአስተርአየ ጸዓዳ፤ ወለገጽከ ውኩይ ከመ ርዕየቱ ለተቅዳ፤ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት እምዘርዓ ያዕቆብ ዘይሁዳ፤ ዘጻመውከ ምስለ ማርያም ወምስለ ክርስቶስ ወልዳ፤ በጊዜ ኮነ ስደት እምኀበ ንጉሥ ኄሮዳ!

✝ዮሴፍ አረጋዊ በዓለ ርስእ ሠናይ፤ ዘኢተረክበ በውስቴቱ ኅሊና እኩይ፤ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ለብሔረ አግአዚ ዐባይ፤ ሊቀ ጳጳሳት ክቡር ጢሞቴዎስ ነዳይ፤ ሮዲስ ጻድቅ ወሳሙኤል ኅሩይ!

✝ሰላም ለዮሴፍ ዘተኃርየ በበትር፤ ከመ ይኩን ሐጻኒሁ ለአማኑኤል ሔር፤ ፍሬምናጦስ ሰላማ ሐዋርያዊ ክቡር፤ ወለጢሞቴዎስ ዘይብልዎ ብእሲ ግዩር፤ ወሳሙኤል ዘፈለሰ ውስተ ብሔር ስዑር!

©ዝክረ ቅዱሳን

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
እግዚአብሔር ያልተቀየማቸው ተጠራጣሪዎች        
    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ አለ
አረጋዊው ስምዖን ‘እነሆ ድንግል ትጸንሳለች’ የሚለውን ትንቢት ተጠራጠረ፤ ይህ ጥርጣሬው ግን በደል ሆኖ አልተቆጠረበትም ይልቁንም ስሙ አማኑኤል የተባለውን ሕፃን ለማቀፍ አበቃው እንጂ፡፡

✍️"ወኢተኈልቈ ሎቱ ኑፋቄሁ ኀበ ጌጋይ አላ አብጽሖ ኀበ ሑቃፌ ሕፃን ዘስሙ አማኑኤል"

❖ ቶማስም የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠረ፤ ትንሣኤውን መጠራጠሩ ግን የጌታን ጎን ለመዳሰስ በችንካሩ እጁን ለማስገባት አበቃው፡፡

✍️ "ወአብጽሖ ኑፋቄሁ ኀበ ገሢሠ አጽልእቲሁ ለመድኃኔ ዓለም"

✍️ በእውነት ‘መተላለፉ የቀረችለት ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው’ እግዚአብሔር የወደደው ሰው ቍስሉ አይመረቅዝም በደሉም አይታሰብም፡፡ 
📖መዝ 32፥1

❖ ጌታ ሆይ እኔንም ስለ መጠራጠሬ አትቀየመኝ ልደትህን የተጠራጠረው ስምዖንን እንዲያቅፍህ ፈቀድክለት፤ ትንሣኤህን የተጠራጠረውን ቶማስ ጎንህን አስነካኸው፤ ያኛው ‘ዓይኖቼ ማዳንህን አዩ’ ብሎ ዘመረልህ ይኼኛው ደግሞ ‘ጌታዬ አምላኬ’ ብሎ መሰከረልህ፡፡

❖ ጌታ ሆይ እኔ እምነተ ቢሱንም መጠራጠሬን አትመልከትብኝ፤ የሚዋዥቅ ሕሊናዬን አጽናልኝ እንደዚያ የልጅ አባት ‘አለማመኔን እርዳው’ እንደ ጴጥሮስ ‘ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ’ በመጠራጠሬ አትቀየመኝ፡፡

❖ መጠራጠሬን አይተህ አትቀየመኝ፤ አንድ ትቢያ ቢጠራጠርህ እንደማይጎድልብህ አውቃለሁ፤ ስለዚህ ራርተህ እምነትን አድለኝ፤ ምናለ ለእኔም ማዳንህን አይቼ እስካምን እንደ ስምዖን ዕድሜ ብትጨምርልኝ? መቼም ላንተ ዘመን አይቸግርህም፤ ሺህ ዓመት ለአንተ አንድ ቀን አይደለች? ቢያንስ አምኜ አሰናብተኝ እስክልህ እስከ ቀትር አቆየኝ፡፡

❖ አንተን በእምነት እንዳቅፍህ እርዳኝ እንጂ ስምዖን አሰናብተኝ እንዳለህ እኔም ደስ ብሎኝ አርፋለሁ፤ ማዳንህን ሳልረዳ ፣ አንተን በእምነት መዳፍ ሳላቅፍህ መሞትን ግን እፈራለሁ፡፡

❖ "አምላኬ ጌታዬ" ብዬ ብዘምርም እንደ ቶማስ ካልዳሰስሁህ ሰውነቴ በእምነት አይኮማተርም፤ ተጠራጣሪውን የማትንቀው ሆይ ጥያቄው የማያባራ ልቤን ጥርጣሬው የማያልቅ ከንቱ ሕሊናዬን እንደ ቶማስ ራራለት፤ ለእኔ የቆሰልከውን ቁስል በእምነት መዳፍ ካልነካሁ ፤ እጄን ከችንካርህ ካላገባሁ የፍቅርህ ጥልቀት አይሰማኝምና እባክህን ‘ና ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን’ በለኝ፡፡

❖ ሳላውቅህ የኖርኩት ጌታዬ ሆይ እንደዚያ መቶ አለቃ ‘ለካስ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ’ ብዬ ሳልመሰክርልህ አልሙት፤ እንደ ሌንጊኖስ ወግቼህ በፈሰሰው በጎንህ ውኃ ዓይኔን አብርተህ ካለማመን ብታወጣኝ ምናለ? ያላመኑትን የማትንቀው ሆይ ተጠራጣሪዎችን ያልተቀየምከው ሆይ የሚጠራጠርህን ልቤን አትቀየምብኝ፤ የሚያስብ የሚጠይቅ አእምሮ ሠጥተህ ለምን ተጠቀምክበት ብለህ አትቀየምምና ስምዖን አቀፈህ ቶማስም ዳሰሰህ።

"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ"
📖ኤፌ 4፥29

✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

📌 ምንጭ
✍️ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
 🧲  /channel/dnhayilemikael
 ───────────

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

@በእንተ ዲያቆናት(ስለ ዲያቆናት)

የቅድስትና ሐዋርያዊት ኵላዊት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ይላሉ?
፩. ዲያቆንም ኾነ ቄስ ሰሞነኛም ይኹን አይኹን፤ ለመቀደስም ኾነ ለጸሎት ቤተ መቅደስ ውስጥ መግባት ያለባቸው ሌሊት ነው። ሥርዐተ ቅዳሴ እንዲህ ይላላ፦
👌 "ሌሊት ለጸሎት ያልመጡ ቀሳውስትና ዲያቆናት ወደ ቤተ መቅደስ ይገቡ ዘንድ ያገለግሉም ዘንድ አይገባቸውም። ይኽን ትእዛዝ ቢደፋፈሩ ግን ከሕግ ትእዛዝ የወጡ ይኾናል።" [ሥርዐተ ቅዳሴ]
፪. ብዙዎቹ ዲያቆናት ልብሰ ተክህኖ ለብሶ መቀደስ፥ ሰዓታትና ማኅሌት መቆምና በንግሥ ሰዓት መስቀልና ቃጭል ይዘው ቅድመ ታቦት መኼድ እንጂ የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር መረዳት የስብከተ ወንጌል ግብር ብቻ ይመስላቸው። ፍጹም ስሕተት ነው።  ከመቀደስ ባለፈ እውነተኛውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት
መማር፥ መረዳት፤ ከክህደት ትምህርት አንጥሮ መገንዘብም የመለየት ኃላፊነት አለባቸው።
➺ቅጥረኛ ስለኾንኩ እንጂ...በሚል ሳይፈልገው የሚቀድስ፦ ከታማኝ አገልጋይ ጋር ምን አንድነት አለው?
➾ቅባት ከተዋሕዶ ጋራ፥ ኑፋቄ ከአሚን(ከእምነት) ጋራ፥ ምርግትና ከጥንቆላ ጋራ፥ አውደ ነገሥት ከፍትሐ ነገሥት ጋር፥ ክህደት ከእውነተኛዋ ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ትምህርት ጋር፤ ምንም ኅብረት እንደሌላቸው አንጥሮ፥ ኵልል አድርጎ የመረዳት የማስረዳትም ግዴታ አለባቸው። ለዚኽም ነው፦
👌"የቤተ ክርስቲያን መብራት አገልጋዮቹዋም የምትኾኑ ዲያቆናት ኾይ ተኵላ ከበግ ጋራ፤ ጭላት(ጭልፊ) ከርግብ ጋራ፤ ክርዳድ ከስንዴ ጋራ እንዳይኖር ከውስጥዋ ንቀሉ፤[ቅዳሴ አትናቴዎስ] እንዲል።
፫. ደጀ ሰላም፦ የሰላም ደጅ ናት። የዲያቆናት አብነት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ መጽሐፈ ገድሉ ላይ "የቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ አምላክ እግዚአብሔርም የዚኽን ሰው የንስሓ እንባ ተመልክቶ ይቅር አለው። ይኽ ሰውም በዚያች ቤተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም ተቀምጦ የደረሰበትን ለሚገባውና ለሚወጣው ኹሉ መሰከረ።" [ገድለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ዘወርኃ መጋቢት]
✍️ አኹንማ የተጣሉ የሚታረቁባት፦ የሰላም ደጅ የተሰኘችው "ደጀ ሰላም" ድረስ ቢራና ዘር ማንዘሮቹ ገብተው "ምን ይኹንልህ?!" ብለን ግሮሰሪ አደረግነው። በርግጥ መጠጥ ፈጽሞ የተከለከለ ባይኾንም፤ አብዝቶ መጠጣት ግን የተገባ አለመኾኑ ለኹላችንም ግልጽ ነው። ደጀ ሰላም "የሰላም ደጅ" እንጂ 'የቢራዎች ደጅ' አይደለችምና ባይገባ ይመከራል።
✍️በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ተፈቅደው ነገር ግን ከማይበረታቱ ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው። ፈጽሞ አይጠጣም፥ ርኵስ ነው ባንልም የማይጠጣ የተሻለ አደረገ።
➣"ከስካር ተጠበቁ ሙሴ በኦሪት ዘሌዋውያን እንዳይሰክሩ አዟቸዋል። እንዲሁ እናንተ ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስትና ዲያቆናት መጠጥን ከማብዛትና ከስካር ተጠበቁ፤ መዳራት፣ ዝሙት፣ ስግብግብነት፣ ሰውን መስደብና ማስቀየም፣ መታበይ፣ በሐሰት መማል፣ ብዙ ቁም ነገሮችን መዘንጋትና ሌሎችም ከስካር የሚመነጩ ናቸው።"[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፲፤ ቍጥር 56]
➛"ከስካርና ወይንን ከማብዛት ተጠበቁ፤ ቃለ እግዚአብሔር የሠፈረባቸውን መጻሕፍት መጠጣትን አዘውትሩ እንጂ።" [ዝኒ ከማሁ(Ibid) ቍጥር 57]
፬. የበቁ ዲያቆናት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅድስና ሥጋወደሙን ለመለወጥ ሲወርድ ማየት ይችላሉ።
➤"ካህን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ ላክ ባለጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመስዋዕትነት በቀረቡ ፅዋዕና ሕብስት ላይ መንፈስ ቅዱስ ይወርዳል፤ ዲያቆናት በቅድስና ሥጋወደሙን ለመለወጥ ሲወርድ ማየት ይችላሉ። የዲያቆናት ክብር በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ቅዱስ እስጢፋኖስ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ የክብር ቦታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሊሠጠው እንደቻለ ለነሱም ይሠጣል።"
[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፲፩፤ ቍጥር 33]
፭. ዛሬ ላይ ዲያቆናት የት ይገኛሉ? ምን ሲያደርጉ ይገኛሉ? ክቡር ዲያቆን ሆይ! "ዙረታም" ነኝ ካልክ የት መዞር እንዳለብህ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ይመክሩናል።
➣"ዲያቆናት የክርስቲያኖችን የመኖሪያ ቤት ወዳለበት ኹሉ እየዞሩ የተቸገሩትን ኹሉ ይጎብኙ፤ ችግራቸውንም ይመልከቱ። ጥዋትም ኾነ ማታ ምእመናኑ በስንፍና እንዳይያዙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲተጉ ያነቃቁዋቸዋል። በሠርክ በጧትና በማታም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ እየኼዱ ያመስግኑት፤ እግዚአብሔር የዕለት ብርሃን ነው፤ ኹሉንም ይረዳል።" [መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፱፤ ቍጥር 66]
፮. ዲያቆናት ምንም ዓይነት ጉቦ መቀበል፥ በደም ግባት ማዳላት፤ ድሀን አይቶ ባላየ ማለፍ፤ ዝም ብሎ ስለ ሴትና ወንድ በማውራት ዋዛ ፈዛዛ በመስማት- ነገረ ዘርቅ መስማት የለባቸውም።
➤ "እናንተም የመንጋዎች ጠባቆችና ዲያቆናት ሆይ መማለጃ በመቀበልና ፊት አይቶ በማድላት ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን ታወጡት ዘንድ በደል በሌለው በንጹህ ሰው ላይ ነገር ሥራንና የሐሰት ነገርን ትሰሙ ዘንድ አይገባም። እንደዚህ ያለ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች የዲያብሎስ ወዳጆች ይኾናሉና።" [መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፲፥ ቍጥር 55]
➣ "ዲያቆናት ድኆች ሳይለምኗቸው ፈቃዳቸውን ሊያደርጉላቸው አገባብ ነው።"[መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፲፮፥ ቍጥር 55]
፯. ዲያቆን በድቁና የተካነ ካህን ነው። ቄስም በቅስና የተካነ ካህን ነውና በአጠቃላይ ማኅበረ ካህናት አይደለም በfb በሕዝባውያን መዋኛ ገንዳዎች እንዲዋኙና ለሕዝባውያን ገላቸውን እንዲያሳዩና ተገላልጠው እንዲታዩ፥ ቁንጣ፥ ጃፖኒ፣ ጥብቅብቅ የሚያደርጉ አልባሳት አድርጎ ውጭ መታየት ፈጽሞ አይፈቀድላቸውምና....
✍️ "አንተ ግን ትታጠብ ዘንድ በወደድህ ጊዜ የሕፃንነትህን ደም ግባትና  የሰውነትህን ማማር እንዳያዩ በአንተም እንዳይሰናከሉ። አንተም እንዳትበድል፤ በእነርሱም እንዳትሰነካከል፤ ሴቶች ወደሚታጠቡበት መታጠቢያ ቤት አትግባ።"[መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፪]
👌ጸጉር አቆራረጥንም በተመለከተ ለምዕመናን ሲገልጽ የቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን የሕግና የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው ፍትሕ መንፈሳዊ ወሥጋዊ "በተፈጠርህ ጊዜ እግዚአብሔር በሰጠህ መልክ ላይ መልክ አትጨምር። ያድግ ዘንድ ፀጉርህን አትከባከበው ተላጨው እንጂ አታሳድገው። ወጥመዳቸው ቅርብ የሆነ ሴቶችን ወደ አንተ ያመጣብህ ዘንድ አታሳምረው። ረቂቅ ልብስ አትልበስ፤ ይህች ስሕተትን ታመጣለችና፤ ቀለም የተቀባ ጫማ አትጫማ፤ በጣቶችህ የወርቅ ቀለበትን አታድርግ፤ ይህ ሁሉ የዝሙት ምልክት ነውና። ጠጉርህን ግልስልስ ብጥር አታድርገው፤ አትሠራው፤ " [ፍትሕ መንፈሳዊ፤ አንቀጽ ፲፩፤ ገጽ. 123] ካለ ለካህናቱ እንዴት ጥብቅ ይሆን???



💚💛❤     
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#ሺ_ዓመት_አይኖር

🥀ብዙ ጊዜ ለስንፍናችን ምክንያት ወይም ተስፋ ለመቁረጥ ሰበብ ከሚሆኑን ነግሮች አንዱ "ሺ ዓመት አይኖር" የሚለው አባባል ነው በእርግጥ በምድር ሺ ዓመት መኖር የቻለ የለም ረጅም ዓመት እንደኖረ የሚነገርለት ማቱሳላ እንኳን ሺ ዓመት አልኖረም ወዳጄ በተለይ እኛ ባለንበት በዚህ ዘመን ደግሞ እንኳን ሺ ዓመት ሊኖር ቀርቶ መቶ የሞላ እንኳን ቢገኝ የሚድያ የአንድ ወቅት የዜና ሽፋን መሆኑ የማይቀር ነው ስለዚህ ወደ ዘመናችን አባባሉን ማምጣት ከፈለግን መቶ ዓመት አይኖር በሚል ልንቀይረው ያስፈልጋል።

🥀የሚያሳዝነው ሺ ዓመት አይኖር የምንለው ለመዝናናት ለመጨፈር ራስን ለመርሳት ፈቃደ ሥጋን እንደ ልብ ለመፈጸም ብቻ እንጂ ለመንፈሳዊ ሕይወት ለመሰናዳት አይደለም "አንቂ" የሚባሉ አካላት የዕድሜህን አጫርነት የሚነግሩህ ከሞት በኋላ ላለው ረጅሙ ዕድሜ በዚህች በአጭሯ የምድር ዕድሜህ በጎ ሰርተህ እንድታልፍ ሳይሆን እንዳትጨናነቅ ፈታ ብለህ(በእነርሱ አማርኛ) እንድትኖር ለማስታወስ ብቻ ነው።

🥀ወዳጄ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ግን በምድር ስለምትኖርበት ዕድሜህ ሲነግርህ ቢበዛ(ቢበረታ) ሰማንያ ይልሃል ሺ ዓመት አይኖር ሲሉህ ቢበዛ ሰማንያ እርሱም በተገኘ በላቸው ታድያ በምድር የምትኖርበት ዕድሜህ ጥቂት ከሆነ ከዚያ በኋላ በሞት ይህን ምድር ከተሰናበትክ ከሞት በኋላ የት ትሄድ ይሆን?? የዚህ ምድር ኑሮህ በሞት ከተቋጨ በኋላ ሞተህ የምትቀር መስሎ እንዳይሰማህ ከሞት በኋላ ሕይወት አለህ ያውም እንደሰው ኖረህ ከሞትክ የምትነሳው እንደ ሰው ሆነህ የምትኖረውን ሕይወት ለመድገም

🥀እንዳይመስልህ ከትንሣኤ በኋላ የምትኖረው እንደ መላእክት ነው “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ”ማቴ 22፥30
ስለዚህ አስታውስ የምድር ኑሮህ ቢበዛ ሰማንያ ነው ያ ማለት ጥቂት ነው መጽሐፍ
እንደሚነግርህ

🥀ሕይወታችሁ ምንድር ነው ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና”
ያዕ 4፥14

🥀ስለዚህ በምድር የምትቆየው ጥቂት ጊዜ ነውና:-*
ዛሬ የንስሐ አባት ያዝ
ዛሬ ንስሐ ግባ
ዛሬ ከተጣላሃቸው ታረቅ
ዛሬ ያስቀየምካቸውን ይቅር በል
ዛሬሥጋ ወደሙን ተቀበል

ነገ ሳይሆን ዛሬ መልካም ነገሮችህን ሁሉ ጀምር ምክንያቱም
“እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
2ኛ ቆሮ 6፥2   የሞዐ
     Join  ቴሌግራም ቻናል

  አምላከ ቅዱሳን ለንስሐ የተዘጋጀ ልብ ያድለን
ለንስሃ ሞት ያብቃን🙏

❀:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ


👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️═
/channel/Meseretemedia

Читать полностью…

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

† የድፍረት ኃጢአት በእግዚአብሔር ቤት †

"በመገናኛው ድንኳን ደጅ ከሚየገለግሉ ሴቶች ጋር እንደተኙ ሰማ።"(1ኛ ሳሙ 2፡22)

★ የአገልጋዮች ማመንዘርና ውጤቱ ★

34 ሺህ እስራኤላውያን በጦርነት ከሞቱበትና ታቦተ ጽዮን ከተማረከችበት የድፍረት ኃጢአቶች መካከል አንዱ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያውቁና በውስጥና በውጭ የሚገለግሉ ወንዶችና ሴቶች ያደረጉት ማመንዘር ነው፡፡

ማመንዘር ኃጢአት ነው፡፡ ማመንዘር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ ሲሆን ደግሞ ቅጣቱ እጅግ የከፋ ነው ማለትም ወንድ ከወንድና ሴት ከሴት ጋር ሲሆን ሀገርን ከነሙሉ ሀብትና ንብረቷ በእሳት ተቃጥላ እንድትጠፋ ያደርጋል፡፡ ግብሩም ግብረ ሰዶም ይባላል፡፡ (ዘፍ 19፡24)
አንድ ተራ ግለሰብ ከሕግ አግባብ ውጪ ቢያመነዝር ኃጢአቱ በራሱ ላይ ይሆናል፡፡
ኃይልንና ሥልጣንን ተtመክቶ በትዳር ያለችን ሴት ቢመነዝር በደሉ ከፍ ያለ ቅጣትን ያስከተላል፡፡ ቅጣቱም ከራስ ወደ ልጅ ይወርዳል፡፡ (2 ሳሙ 12፡10)

በቤተ እግዚአብሔር ቃሉን እየሰሙ ኖረው እያገለገሉ ያሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራት ትተው በድፍረት ከሌሎች አገልጋዮች ጋር ቢያመነዝሩ ለኃጢአታቸው የሚከፈላቸው ደመወዝ ቤተ ክርስቲያንን ሁሉ አደጋ ውስጥ ይጥላል፡፡
ከላይ በርዕሱ ለመጠቀስ እንደተሞከረው ሁለቱ የሊቀ ካህኑ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከክህነታቸው በተጨማሪ በትዳራቸው ላይ ይማግጡ፣ ያመነዝሩ የነበሩት በእግዚአብሔር ቤት ከሚያገለግሉ እግዚአብሔርን ከሚያውቁ ሴቶች ጋር ነበር፡፡ በየአብያተ ክርስቲያናቱ የንግስ በዓልን ምክንያት አድርጎ በሰንበት ትምሕርት ቤቶች አዘጋጅነት የሚካሄዱ የአዳር መርሐ ግብሮች ፈተና እየሆኑብን አይደለ ?፣ የጉዞ መርሐ ግብሮችስ ከመንፈሳዊ ዓላማቸው እያፈነገጡብን አይደለ?

አሁን ይህን ቃል ሰምተንና አንብበን በነ አፍኒንና ፊንሐስ ላይ ለመፍረድ አንነሳ በዘመናችንስ እንደዚህ ዓይነት የድፍረት ኃጢአቶች በአገልጋዮች ዘንድ የሉም? . . . የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ትምሕርት ቤት አመራሮች ቃሉን ከማወቅ በዘለለ በዲያቆናትና በሰንበት ትምሕርት ቤት ወጣት ሴቶች፣ በሰንበት ትምሕርት ቤት ወጣት ሴቶችና ወንዶች መካከል የሚታዩና የሚሰሙ አዝማሚያዎችን በዝምታ ማለፍ እንደ ዔሊ አያስቀስፈንም ብላችሁ ታምናላችሁ? ቤተ ክርስቲያንን አደጋ ውስጥ አይከታትም ብላችሁ ታስባላችሁ? . . . በሀገራችን እየደረሰ ላለው ብዙ ምስቅልቅሎችስ የአገልጋዮች በቤተ መቅደስ የሚደረጉ ዘርፈ ብዙ የድፍረት ኃጢአቶች ምክንያት አይደለም ብላችሁ ታስባላችሁ? ይህንን የማስጠንቀቂያ ደውል የሰማን ሁላችን ዛሬ ንስሐ እንግባ።

ለሌሎችም ሼር አድርጉት

መምህር ኢንጂነር ታርኩ አበራ

Читать полностью…
Subscribe to a channel