Hawalle sidamu Haru Diru Sorro Fichee- Chambalaalate Ayanira Keerunni illishinonke!
ayide Chambalaala!
እንኳን ለሲዳማ ቤሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ አዲስ ዓመት በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
ለክቡራን ደንበኞቻችን!!
ዶ/ር ሰለምን የቀዶ ህክምና ማዕከል አገልግሎቱን በሁሉም አገልግሎት ዘርፍ በእስፔሻሊስት ሀክሞች ማለትም፣ ቀዶ ህክምና፣የውስጥ ደዌ ህክምና፣ የስነ ደዌ ምርመራ፣ የማህፄንና ፅንስ ምርመራ፣ በዘመናዊ ህክምና መሣሪያ ላቡራቶሪ ምርመራ፣ የድጂታል ራጅና ዶፕላር ሶኖግራፊ ምርመራና የ 24 ሰዓት መድኃኒት አገልግሎት በተጠናከረ ሁኔታ እሰጠን መሆኑን እየገለፅን፣ በየዕለቱ ህክምናውን የሚሰጡ ስፔሻሊስት ሀኪሞቻችንች እንደምከተለው ከሰኞ - ቅዳሜ ሙሉ ቀን ቀዶ ህክምና ማዕከላችን እንደምገኙ እናሳዉቃለን።
1/ የውጥ ደዌ እስፔሻሊስት ሀኪም
1. ዶ/ር ዘርሁን ነጋሽ
2. ዶ/ ር መስፍን ግዛው
3. ዶ/ር ረቂቅ አዲሱ
2/ራዲዮሎጅ እስፔሻሊስት ሀኪም
1.ዶ/ር ሰለሞን በቀለ
2.ዶ/ር ነብዩ ነጋሽ
3/ስነ ደዌ እስፔሻሊስት ሀክም
ዶ/ር አበባው አማረ
4/ ጠቅላላ ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ሀኪም
1.ዶ/ር ተስፋፅዮን
2.ዶ/ር ገዛሃኝ ገዳ
5/የአጥንት ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ሀኪም
ዶ/ር ይስሐቅ ዘርሁን
6/የማህፄንና ፅንስ እፔሻሊስት ሀኪም
ዶ/ር ደመነ ደባልቄ
7/ ጠቅላላ ሀኪም(GP)
1.ዶ/ር ተሻለ ታደሰ
2.ዶ/ር ደሳለኝ ዋኤ
3.ዶ/ር ሀብታሙ አኔሳ
4.ዶ/ር ደምስ ሀምሶ
5.ዶ/ር አበራ እቴና
አድራሻ፣ከአሮገው መናኸርያ 100m ከፍ ብለው ተስፋየ ግዛው ህንፃ
ስልክ፣0462123725
ጤና ለሁሉም!!
House Of Healing.
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
የሽንት ቧንቧ አካላት(urinary tract) በሁሉት ይከፈላሉ እነዚህም :-
I. የላይኛው የሽንት ቧንቧ አካል ( upper urinary tract)
• ኩላሊት
• ዩሬ-ተር{ኩላሊትን ከ ከሽንት ቀረጢት የሚያገናኝ ቱቦዎች } ያጠቃልላል ::
II. የታችኛው የሽንት ቧንቧአካል( lower urinary tracts) ይህም
•የሽንት ከረጢት(ፊኛ)
• ዩሬ-ትራ{ ከሽንት ከረጢት እስከ ብልት ጫፍ ያለው እና ሽንት ለመጸዳዳት የሚረዳን ቱቦ ያጠቃልላል።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዴት ይከሰታል?
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ባክቴሪያ ወደ ዩሬ-ትራ ገብቶ ወደ ሽንት ቀረጢት ሲያመራ ሲሆን ነገር ግን ኢንፌክሽኑ በሽንት ቀረጢት ውስጥ ከቀረ የሽንት ቀረጢት ኢንፌክሽን ይባላል ሆኖም ወደ ላይ አምርቶ ኩላሊትን ካጠቃ የኩላሊት ኢንፌክሽን ይባላል።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች
•የታችኛው ️የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ይህ በጣም የተለመደ የሽንት ቧንቧ የኢንፌክሽን አይነት ሲሆን ታማሚው
-ሲሸና ማቃጠል
-ቶሎ ቶሎ ለመሽናት መፈለግ
-ከእንብርት በታች የሆድ ህመም
-የደፈረሰ ሽንት
-ሽንት ለመቋጠር መቸገር እና
-ደም የቀላቀለ ሽንት መሽናት ዋና በታማሚው ላይ የሚታዩ ምልክት ናቸው።
የኩላሊት ኢንፌክሽን(ወይም የላይኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን) እንደ የሽንት ከረጢት ኢንፌክችን በጣም የተለመደ ባይሆንም ተመሳሳይ የሆነ ምልክት ይኖራቸዋል ከላይ ከተገለጹት ምልክቶች በተጨማሪ የኩላሊት ኢንፌክሽን ታማሚ ሰው እነዚህን ምልክት ሊያስተዉል ይችላል:-
-ሽንጥ እና ወገብ አካባቢ ዉጋት በግራ ፡በቀኝ ወይም በሁለቱም በኩል ሊሆን ይችላል
-ከፍተኛ ትኩሳት
-ብርድ ብርድ ማለት፡ማንቀጥቀጥ
-ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
-የምግብ ፍላጎት መቀነስ/ማጣት
ለሽንት_ቧንቧ_ኢንፌክሽን_አጋላጭ_ምክንያቶች (Risk factors):-
-የስኳር በሽታ ታማሚ
-ባለፈው 1 አመት ዉስጥ ተመሳሳይ ችግር ከነበረ
-በብልት ዉስጥ የሚቀመጥ የወሊድ መቆጣጠርያ መጠቀም
-ወንድ ልጅ ከሆነ እና ካልተገረዘ
ሴቶች ላይ ሽንት_ቧንቧ_ኢንፌክሽን በብዛት የሚታይበት ምክንያት በተፈጥሮ የሴቶች ዩሬ-ትራ ከወንዶች አጭር በመሆኑ ባክቴሪያዎች በቀላሉ ወደ ሽንት ከረጠት ስለሚገቡ ነው ::
እንዴት በሽታው እንዳለ ማወቅ ይቻላል?
ይህ እክል በአብዛኛው ታካሚ በሚያሳየው ምልክት እና የሽንት ምርመራ በማድረግ የሚታወቅ ነው።
ህክምናው
ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሕክምና እንደ በሽታው አይነት(የታችኛው ወይስ የላይኛው ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን)÷የታማሚው የህመም ደርጃ(የተባባሰ/ቀለል ያለ)÷ከዚህ በፊት የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መደጋገም መኖር የሚሉ ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት የሚሰጥ ነው :: ከዚህ በታች በዝርዝር አንድ በአንድ እናያለን :-
የሽንት ከረጢት ኢንፌክሽን( (cystitis) ሕክምና
-አንቲባዮቲክ(ፀረ-ደቂቅ ፈጣረታት ) ኪኒን የታዝሎታል:: ለምሳሌ:- ሲፕሮፍሎክሳሲሊን ÷ኖርፍሎክሳሲሊን ትሪይሜቶፕሪም ሰልፋሜቶክዛዞል ወዘተ ከሚባሉት ውስጥ አንዱን ይታዘዝሎታል::
-ስለ አጋላጭ ምክንያት እና እንዴት መከላከል እንደሚቻል የጤና ባለሞያው ያስረዳዎታል ::
የፊኛ ኢንፌክሽን ካለብዎት፤ ከ 3 እስከ 5 ቀናት ውስጥ አንቲባዮቲኮችን መውሰድ ይኖርብዎታል።
የ ኩላሊት ኢንፌክሽን ሕክምና (pylonephritis)
ይህ ህክምናው እንደ እክሉ ግዝፈት(ሃይለኛነት)ላይ ይወሰናል።ታካሚው ትኩሳት እና ዉጋቱ ከባድ ካልሆነ በተጨማሪ ምግብ መብላት እና መጠጣት የሚችል ከሆነ በቤት ዉስጥ ህክምናዉን መከታተል ይችላል።
ለትኩሳት እና ለህመም ፓራስታሞል መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን ከባድ ዉጋት እና ትኩሳት ካለ እንዲሁም በተጨማሪ ምግብ መብላት እና መጠጣት የማያችሉ ከሆነ ሆስፒታል ተኝተው በመርፌ በሚሰጥ መድሃኒት መታከም እና በቂ ፈሳሽም በተጓዳኝ ማግኘት ይኖርቦታል።
የኩላሊት ኢንፌክሽን ካለብዎ ለረዥም ጊዜ አንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን መውሰድ ያስፈልጋል ።
የታዘዘሎትን መድሃኒት ሰዓቱን አዛብቶ መውሰድም ይሁን ከታዘዘው ቀናት ቀደም ብሎ ማቆም መድሃኒቱ ከባክቴሪያዎች እንዲለመድ ከማድረጉም በተጨማሪ ከህመም በቶሎ እንዳያገግሙ ና እንዲደጋም ያደርጋል!!
ተደጋጋሚ የሽንት ቀረጢት ኢንፌክሽን (recurrent Urinary tract infection) ቢያጋጥመኝስ?
ጥቂት አዋቂ ታካሚዎች(adult) በተለየ ደግሞ ሴቶች ተደጋጋሚ የሆነ የሽንት ቀረጢት ኢንፌክሽን ሊያጋጥማቸው ይችላል በዚህ ወቅት ሃኪሙ እንደገና የተለያዩ ምርመራ ሊያዝ ይችላል ምክንያቱም አብዛኛው በዚህ አካባቢ የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖች ተመሳሳይ የሆነ ምልክት ይኖራቸዋል።
ከምርመራው በኋላም መድሃኒት ሊቀየርም ይችላል በተገኘው የምርመራ ውጤት ላይ በመመርኮዝ የሚወሰን ይሆናል።
House Of Healing!!
7/1/2014
Hawassa.
ዶ/ር ሰለምን ስፔሻላዝድ የቀዶ ህክምና ማዕከል
የሳንባ ነቀርሳ/Tuberculosis
ምንነት
> የሳንባ ነቀርሳ በሽታ 'ማይኮባክቴሪዬም/mycobacterium Tuberculosis' በተባለ ባክቴሪያ አማካኝነት የሚከሰት በዋናነት ሳንባን የሚያጠቃ ተላላፊ በሽታ ሲሆን አልፎ አልፎም የተለያየ የሰውነት አካላትን(አጥንት፣ አንጀት፣ ጭንቅላት...) ሊያጠቃ ይችላል።
መተላለፊያ መንገድ
> በትንፋሽ
አጋላጭ ነገሮች
> ብዙ ጊዜ ከሚያስላቸው/የታወቀ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ካለባቸው ጋር ለረጅም ጊዜ አብሮ መሆን/መኖር
> በተጨናነቀና በታፈነ አካባቢ(crowded environment) መኖር
> ከዚህ በፊት የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ መሆን
> የሳንባ ነቀርሳ ካለባቸውን ሰዎች ጋር ንክኪ መኖር(ቤተሰብ፣ የጤና ባለሙያ...)
> የሳንባ ነቀርሳ ወደሚበዛበት አካባቢ መሄድ/travel history to TB endemic area
> ሲጋራ ማጨስ
> አልኮል መጠጣት
> ህፃን መሆን(በተለይ ከ5 አመት በታች)
> የተለያየ ተጓዳኝ በሽታ ካለ(ኤድስ፣ የምግብ እጥረት፣ ካንሰር፣ ስኳር በሽታ...)
ምልክቶች
> አክታ ያለው ሳል
> ደም የቀላቀለ አክታ
> የሰውነት ክብደት መቀነስ
> የሰውነት ሙቀት
> ማታ ማታ ከፍተኛ ላብ ማላብ
> የምግብ ፍላጎት መቀነስ
> የደረት ህመም
> ድካም
.....
ከሳንባ ውጭ በTB ከተጠቃን
> ከፍተኛ ራስ ምታት
> አንገት ወይም የጀርባ ህመም
> እግር አልታዘዝም ማለት/lower extrimities paralysis
> የመገጣጠሚያ ህመም
> ሆድ ህመም፣ ሆድ ማበጥ፣ ተቅማጥና ትውኪያ...
> ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል፣ የሽንት ቀለም መቀየር፣ በግራና በቀኝ ወገብ ህመም...
ጠንቅ፦ በዋናነት በሽታው ከሳንባ ውጭ ሲከሰት(extrapulmonary TB) ይፈጠራል
> አጥንት መሰበር/pott disease
> ማጅራት ገትር/meningitis
> የልብ በሽታ/pericarditis
> የአንጀት መቁሰል/intestinal TB
> የአይን በሽታ/uveitis
> የኩላሊት በሽታ/genitourinary TB
> የቆዳ በሽታ/cutaneous TB
.
> መድኃኒት የተላመደ የሳንባ ነቀርሳ(MDR TB)፦ ይህ በዋናነት የጤና ባለሙያ የሚያዘውን መድኃኒት በአግባቡና በትክክል ካለመውሰድ የሚመጣ ለህክምና አስቸጋሪና በሽተኛን ለሞት የሚዳርግ አሁን አሁን እየበዛ የመጣ በሽታ ነው።
> የሳንባ በሽታ(ምሳሌ፦ bronchiolitis, lung fibrosis, COPD)
> ካንሰር
ምርመራ
> የአክታ ምርመራ
> የደረት ራጅ ምርመራ
> የደም ምርመራ
> የሽንት ምርመራ
> የኩላሊትና የጉበት ምርመራ
> የ HIV AIDS ምርመራ
> የአንጎልና የህብለ ሰረሰር ፈሳሽ ምርመራ(CSF analysis)
> CT scan, MRI
ህክምና
> በሽተኛውን የተለየ ቦታ ማስቀመጥ/ማስተኛት/isolate the patient
> በአፍ የሚዋጡ እንክብል መድኃኒቶች
> በደም ስር የሚሰጡ መድኃኒቶች
> የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
.
> ቀዶ ጥገና
ምን እናድርግ?
× ብዙ ጊዜ ሳል ካለባቸው/የታወቀ የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ ከሆኑ ሰዎች ጋር ለረጅም ሰአት አለመቀራረብ
× የቤታችንን መስኮትና በር በቀን ጊዜ በመክፈት ቤታችን በቂ አየር እንዲገባ ማድረግ
× በተለያዬ አጋጣሚ ከሳንባ ነቀርሳ ታማሚዎች ጋር የምንገናኝ ከሆነ ቢያንስ የአፍ መሸፈኛ/Mask ለታማሚውም ለኛም ማድረግ
× ከላይ የተጠቀሱ አጋላጭ ነገሮችን ማስወገድ
× ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ካሉ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም መሄድና መታየት
የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ ከሆን፦
1. ሐኪም/የጤና ባለሙያ የሚያዝልንን መድኃኒት ከተቻለ ሁሌም በጤና ባለሙያ ፊት መዋጥ(DOT) አለበለዚያ በታዘዝነው አግባብና ልክ መድኃኒቱን ሳያቋርጡ መውሰድ
2. በቀጠሮ ሰአት ሳናቋርጥ መከታተል
3. መድኃኒት በጀመርን በ2ኛውና በ5ተኛው ወር ላይ የአክታ ምርመራ ማድረግ
4. የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
5. መድኃኒቱን ስንጨርስ መዳን አለመዳናናችንን check ማድረግ
NB፡ ከሐኪም ትዕዛዝ ውጭ በምንም አይነት መንገድ የሳንባ ነቀርሳ መድኃኒት አላግባብ መውሰድ አይመከርም።
ማንኛው ከላይ የተጠቀሱ ችግር የምታይበት ሰው ወደ ቀዶ ህክምና ማዕከላችን በመምጣት ስፔሻሊስት ሐክሞቻችንን ማማከርና በዘመናዊ ህክምና መሳሪያዎቻችን ምርመሪያ ማድረግ ይችላሉ።
ዶ/ር ሰለሞን ስፔሻላይዝድ የቀዶ ህክምና ማዕከል።
አድራሻ ወንዛ ተስፋየ ግዛው ሕንፃ ከአሮገው መናኸርያ ከፍ ብሎ
ሀዋሳ
House of Healing!!
14/12/13
250 መካኒካል ቬንቲሌተር በመላ ሀገሪቱ እየተሰራጩ መሆኑ ተገለጸ
ኤጀንሲው ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ ያገኘውን 250 መካኒካል ቬንትሌተር በአገሪቱ ለሚገኙ የኮቪድ 19 ህክምና መስጫዎች ከጤና ሚኒስቴር በተላከው ድልድል መሠረት እያሠራጨ መሆኑን የመድኃኒትና ሕክምና መገልገያዎች ክምችትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገዳምነሽ አስፈራው አስታወቁ፡፡
55 ቬንትሌተሮች ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተሠራጨ መሆኑን ዳይሬክተሯ ገልፀው ስርጭቱም ለቅዱስ ጳውሎስ፣ ኤካ ኮተቤ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ጥቁር አንበሳ፣ አቤት፣ ሚሊኒየም፣ የካቲት 12፣ አማኑኤል፣ ጋንዲ፣ ለምኒልክ፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ፣ ራስ ደስታ እና ዘውድቱ ሆስፒታሎች እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሯ አክለውም ለድሬደዋ ከተማ አስተዳደር 4፣ ለትግራይ ክልል 12፣ ለአማራ ክልል 40፣ ለኦሮሚያ ክልል 62፣ ለደቡብ ክልል 30፣ ለሲዳማ ክልል 7፣ ለሶማሌ ክልል 14፣ ለቤኒበሻንጉል ጉምዝ ክልል 4፣ ለጋንቤላ ክልል 2፣ ለአፋር ክልል 6 ፡ ለሀረሪ ክልል 4 ቬንትሌተሮች እየተሠራጩ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም ለመከላከያ እና ለፖሊስ ሆስፒታል አምስት አምስት ቬንትሌተሮች እየተሠራጩ እንደሆነ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
ቬንትሌተሮቹ ለኮቪድ 19 ፅኑ ህሙማን መተንፈሻነት የሚረዳ ሲሆን በዚህ ወቅት በአለማች ላይ አጅግ ተፈላጊ የህክምና ግብዓት ሲሆን ስርጭቱም በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት እንደሚካሄድ በቃለ መጠይቁ ተገልጿል፡፡
ቬንትሌተሮቹ ሐምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ከአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ የአሜሪካ ኤምባሲ አምባሣደር እና የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በተገኙበት ርክክብ መደረጉ ይታወሳል፡፡
Source EPSA
👉🖊🖍 ሳይነስ(sinusitis)
👉 ምንነት
🥅 ሳይነስ ማለት ከፊታችት ጀርባ የሚገኙ በአየር የተሞሉ ቀዳዳዎች (sinuses) ብግነት(inflammation) ነው፡፡
🥅 ይኽ ህመም በአብዛኛው በራሱ ጊዜ የሚድን ሲሆን በአፍንጫ እና በአይን ዙሪያ ህመምን ያስከትላል፡፡
🥅 ከፊታችን ጀርባ በአፍንጫ ቀዳዳ ዙሪያ አራት ጥንድ የሆኑ ቀዳዳዎች(sinuse) ይገኛሉ፡፡ እነዚህም አየር፣ ፈሳሽ እና ንፍጥ እንደፈለገው እንዲሄድ ይረዳሉ፡፡ ቀዳዳዎቹ ውስጥ የሚመረተው ንፍጥ በጤናማ ጊዜ ቀዳዳዎቹ ውስጥ አይጠራቀምም፡፡ ነገር ግን ቀዳዳዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ከተዘጉ አሊያም የትንንሽ ፀጉሮቹ እንቅስቃሴ ከተገታ ፈሳሹ በመጠራቀም የሳይነስ በሽታ ምልክቶች እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
👉 መንስኤዎች
☑️ ጉንፋን
☑️ የአፍንጫ ክፍል መቆጣት
☑️ የውስጠኛው አፍንጫ ክፍል እብጠት
👉 የሳይነስ አይነቶች
1. አጣዳፊ ሳይነስ (acute sinusitis)፦ አብዛኛውን ጊዜ እንደ አፍንጫ ፈሳሽ ፣ቅዝቃዜ እና የፊት ላይ ህመም የመሳሰሉ ምልክቶች ይኖሩታል ከ 2-4 ሳምንታት ሊቆይ ይችላል።
2. በጣም ከፍተኛ ሳይነስ (sub-acute sinusitis)፦ በአብዛኛው ከ 4 እስከ 12 ሳምንታት ውስጥ ይቆያል።
3. ስር የሰደደ (chronic sinusitis)፦ የሳይነስ ምልክቱ ከ 12 ሳምንታት ለበለጠ ጊዜ ሊቆይ ይችላል።
👉 ምልክቶች
🖍 የፊት አካባቢ ህመም ወይም መክበድ
🖍 የአፍንጫ መዘጋት
🖍 የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት
> ማሽተት አለመቻል
🖍 ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ድካም፣ የአተነፋፈስ መቀየር፣ የጥርስ ህመም
🖍 የአፍንጫ ቀዳዳ ቦታዎች ላይ መግል መያዝ
👉 ምርመራ
> አካላዊ ምርመራ
> የደም ምርመራ
> cytology, biopsy
> CT scan
👉 ሕክምና
🕺 እረፍት ማድረግ
🕺 ብዙ ፈሳሽ መውሰድ
🕺 በሙቅ ውሀ መታጠን ወይም እስቲም መጠቀም
🕺 በሀኪም የታዘዙ መድሀኒቶችን መጠቀም
🕺ቀዶ ጥገና
👉 ምን እናድርግ
🖊አለርጂክ ካለ በአግባቡ ማከም
🖊 የመተንፈሻ አካላት ችግር እንዳይከሰት መከላከል
🖊 ሲጋራ አለማጨስ
🖊 ንጹህ አካባቢን ለመፍጠር መሞከር
በተደረገው ምርመራ 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ በመያዛቸው በክልሉ ጠቅላላ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች
ቁጥር 107 ደረሰ
የኮቪድ19 ወረርሽኝ በአገራችንና በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 21/2012 ዓ.ም ባለፉት 24 ሰዓታት ዉስጥ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ በተደረገ
288 የናሙና ምርመራ በጤና ሚኒስትር በተገለጸው መሰረት በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት 6 ሰዎች
በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ እስከአሁን ድረስ በተደረገው ምርመራ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 107 ደርሷል፡፡ እንዲሁም በዛሬው ዕለት አንድ ከስልጤና አንድ ከሐድያ በድምሩ ሁለት ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው የታወቀ ሲሆን በድምሩ 20 ሰዎች በማገገማቸው አሁን 85 ሰዎች በህክምና ማዕከል ላይ ይገኛሉ፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ
ህይወታቸው ያለፈ 8 ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
1. የ40 ዓመት ወንድ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።
2. የ26 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።
3. የ70 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበሩ።
4. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።
5. የ27 ዓመት ሴር የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠ።
6. የ65 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።
7. የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።
8. የ60 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,675 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ አንድ (141) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 81 ወንድ እና 60 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ2 ወር - 87 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 139 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 2 የውጭ ዜጋ ናቸው።
113 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 15 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ 6 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 1 ሰው ከድሬዳዋ ከተማ እና 1 ሰው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (4 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኝበት ናሙና የለም።
ከዚህ ባለፈ ሶስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል።
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
1. የ52 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።
2. የ72 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።
3. የ62 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 81 ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 58 ሰዎች (44 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,544 ደርሷል።
የውጭ ጫማዎን ቤት ውስጥ ባለመጠቀም የኮሮና ቫይረስ በሽታን ይከላከሉ!
(ጤና ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ)
- ውጪ ያደረጉትን ጫማ በቤትዎ በር በማውለቅ የቤት ጫማ ይቀይሩ፤
- ያወለቁትን ጫማ በፌስታል ወይም ለጫማ በተዘጋጀ ቦታ ያስቀምጡ፤
- ልብስዎን ይቀይሩ ከዚያም በውሃ እና በሳሙና እጅዎን ይታጠቡ ፤
ዶ/ር ሰለሞን የቀዶ ህክምና ማዕከል በተጠናከረ ሁኔታ በስፔሻሊስት ሐኪሞች ለ 24 ሰዓት እንደምከተለው የተገለፀወን ህክምና እየሰጠን እገኛለን።
# ከፍተኛና መለስተኛ የቀዶ ህኪምና
# የአጥንት ስብራትን ጨምሮ መለስተኛና ከፍተኛ የአጥንት ቀዶ ህክምና
# ከአንገት በላይ ህክምና፣ክትትልና ቀዶ ህክምና
# የካንሰር ህክምና ክትትል በካንሰር ስፔሻሊስት ሀኪም
# የውስጥ ደዌ ህክምና በስፔሻሊስት ሀኪምየሚሰጥ ሲሆን
#የዲጂታል ራጅና ዶፕለር አልትራሳውድ አገልግሎት ልምድ ባላቸው ስፔሻሊስት ሀኪም
# ድንገተኛና ተመላላሽ ህክምና
# የ24 ሰዓት የፋርማስና ላብራቶር አገልግሎት የምንሰጥ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
ጤና ለሁሉም!!
አድራሻ፡ሀዋሳ ከአሮገው መናኸሪያ 100ሜ ከፍ ብለው ዋንዛ አደባባይ ተስፋየ ግዛው ሕንፃ እንገኛለን።
ስልክ፣ 0462123725/0911412490
ክቡራን ዶ/ር ሰለሞን ስፔሻላዝድ ቀዶ ህክምና ማዕከል ደንበኞቻችን ቀዶ ህክምና ማዕከላችን ለ24 ሰዓት የተቀናጀና የተቀላጠፈ አገልግሎት የምሠጠውን በተጠናከረ ሁኔታ ለመላዉ ህብረተሰብ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን እናሳዉቃለን።
ጤና ለሁሉም!!
የመዲኀንታችንና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል (ገና ) ዋዜማ የዶ/ር ሰለሞን ቀዶ ህክምና ማዕከል ባለሙያዎችና አጠቃላይ የጊቢው ማህበረሰብ በዝህ መልኩ አክብረዋል።
Читать полностью…የኪንታሮት በሽታ
ኪንታሮት ለበሽታው በትክክል ገላጭ ስም ባይሆንም፤ የኪንታሮት በሽታ በፊንጢጣ እና በታችኛውየአንጀት ክፍል የሚገኙ የደም መላሽ ስሮች መላላትና መለጠጥ እንዲሁም በደም በመወጠር ማበጥ ነው፡፡ ኪንታሮች በአንጀት ታችኛው ክፍል ሲፈጠር የውስጥ ኪንታሮት ሲባል በፊንጢጣ ላይ ከሆነ ደግሞ የውጪ ኪንታሮት ይባላል፡፡
በእድሜ ዘመን ከአራት አዋቂዎቸወ ሶስቱ (75%) የኪንታሮት በሽታ ሊያዛቸው ይችላል። ኪታሮት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖረው ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን የሚታወቅ አይደለም፡፡
ብዙ ውጤታማ የህክምና ዘዴዎች እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለበሽታው መፍትሔ የሚሆኑ ናቸው ፡፡
ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው?
• ፊንጢጣ አካባቢ መብላት
• ህመም ወይም አለመመቸት
• ፊንጢጣ አካባቢ እብጠት
• ይሄኛው አይነት የታችኛው የአንጀት ክፍል ላይ ስለሚወጡ ማየትም መዳሰስም አይቻልም፡፡ ብዙውን ጊዜ ህመም አይኖራቸውም፤ ነገር ግን ሰገራ በሚያልፍ ጊዜ የሚኖር ማማጥ እና መቆጣት ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡
• ደም የቀላቀለ ሰገራ
• ኪንታሮቱ በፊንጢጣ በኩል ከወጣ ህመም እና መቆጣት ይኖራል
• ደም የቋጠረ የውጭ ኪንታሮት ከፍተኛ ሀመም፣ እብጠት፣ መቆጣት እና ፊንጢጣ አካባቢ እባጭ ሊያመጣ ይችላል፡፡
በምን ምክንያት ይመጣል?
• ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ የደም ስሮች በግፊት ውስጥ ሲሆኑ የመለጠጥ እና የማበጥ ባህሪ አላቸው፡፡ ኪንታሮት የሚፈጠረው በታኛው የአንጀት ክፍል ላይ ከፍተኛ የሆነ ግፊት ሲኖር እና የሚከተሉት ካሉ ነው፤
• በመፀዳዳት ወቅት ማማጥ
• ለረጅም ሰዓት ሽንት ቤት መቀመጥ
• ለረጅም ጊዜ ተቅማጥ ወይም ድርቀት ሲኖር
• ከልክ ያለፈ ውፍረት
• እርግዝና
• የፋይበር መጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ምግብ መውሰድ
• ለብዙ ጊዜ ክብደት ማንሳት
ተጋላጭነት
• ከእድሜ ጋር የኪንታሮት ተጋላጭነት ይጨምራል፡፡ ምክንያቱም ከእድሜ ጋር ተያይዞ በፊንጢጣ እና በታኛው የአንጀት ክፍል የሚገኙ የደም ስሮች ይደክማሉ፡፡ በእርግዝናም ወቅት የፅንሱ ክብደት በፊንጢጣ አካባቢ የሚኖረውን ግፊት ስለሚጨምረው ተመሳሳይ ለውጦች ይኖራሉ፡፡
ኪንታሮት ምን ሊያመጣ ይችላል?
• ደም ማነስ - ብዙ ደም የሚፈስ ከሆነ
• ኪንታሮቱ የደም ምንጩ ከተቋረጠ እጅግ ከፍተኛ ህመም
• የደም መርጋት
እንዴት እንከላከለው?
• ዋነኛው የመከላከያ መንገድ ሰጋራን ለስላሳ በማድረግ በቀላሉ እንዲያልፍ ማድረግ ነው፡፡
ኪንታሮትን ለመከላከልና ምልክቶችን ለመቀነስ የሚከተሉት ይመከራሉ፤
• በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
• ፈሳሽ ነገሮችን በሚገባ መውሰድ
• የፋይበር ሰፕሊመንቶችን መውሰድ
• በሚፀዳዱ ወቅት አለማማጥ
• ለመፀዳዳት በፈለጉ ጊዜ ሳይቆዩ መፀዳዳት
• አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ
• በአንድ ቦታ ለረጅም ጊዜ አለመቀመጥ
ምርመራ
• ሀኪሞት በማየት የውጭ ኪንታሮትን ሊመረምር ይችላል፡፡ ለውስጥ ኪንታሮት ደግሞ ንፁህ ጓንት በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ሀኪሞት የሚከተሉት ካለቦት ግን ሁሉንም የአንጀት ክፍል በፊንጢጣ በሚገባ መሳሪያ ሊመረምር ይችላል፤
• ያሎት ምልክቶች የሌላ የአንጀት በሽታ ምልክት ጋር ተመሳሳነት ካለው
• ለአንጀት ካንሰር ተጋላጭ ከሆኑ
• እድሜዎት ከ45 በላ ከሆነ
ህክምና
• በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መውሰድ
• የሚቀቡ መድሀኒቶችን መጠቀም
• ለብ ያለ ውሀ ላይ ትንሽ ጨው በማድረግ ፊንጢጣ አካናኒ ማጠን
• ህመም ማስታገሻ መውሰድ
• ቀዶ ህክምና
ማንኛው ከላይ የተጠቀሰው ችግር የምታይበት ሰው ወደ ቀዶ ህክምና ማዕከላችን በመምጣት ስፔሻሊስት ሐክሞቻችንን ማማከርና በዘመናዊ ህክምና መሳሪያዎቻችን ምርመሪያ ማድረግ ይችላሉ።
አድራሻችን ወንዛ ከአሮገ መናኸሪያ ከፍ ብሎ ተስፋየ ግዛው ሕንፃ
ሀዋሳ
14/12/13
House of Healing!!!
ኮሮና ቫይረስ የገንዘብ ኖቶች ላይ ፣ የስልክ ስክሪኖች ላይ እና በማይዝጉ ብረቶች ላይ ለ28 ቀናት ሳይሞት ቆይቶ በሽታ ሊያስተላለፍ እንደሚችል ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ።
የአውስትራሊያ ብሔራዊ ሳይንስ ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው ጥናት ሳርስ-ኮቭ-2 የሚል ሳይሳዊ መጠሪያ ያለው ኮሮናቫይረስ ከተገመተው በላይ ለረዥም ጊዜ በቁሶች ላይ እንደሚኖር ያረጋገጠ ነው።
ኮሮናቫይረስ በብዛት የሚተላለፈው ሰዎች ሲያስሉ ፣ ሲያስነጥሱ ወይም ሲነጋገሩ እንደሆነ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ አዲሱ የተመራማሪዎች ግኝት ቫይረሱ ከቁሶች ወደ ሰዎች የሚተላለፍበት መጠንም ከተገመተው በላይ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ምንጭ፦ BBC
አጫጭር መረጃዎች ፦
- ትላንት በሀገራችን በኮቪድ-19 ህይወታቸው ካለፈ 28 ሰዎች መካከል ሃያ ስድስቱ (26) ከአ/አ ከተማ ናቸው። 24 በአስክሬን ምርመራ እና 2 ከጤና ተቋም እንደሆኑ ተገልጿል።
- በኦሮሚያ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,425 ደርሰዋል፤ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 21 ነው።
- በደቡብ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 201 ደርሰዋል፤ እስካሁን የ3 ሰው ህይወት አልፏል፤ 52 ሰዎች አገግመዋል።
- በትግራይ ክልል አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 836 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 489 ሰዎች አገግመዋል።
- በአማራ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 565 ደርሰዋል፤ 6 ሞት ሲመዘገብ 446 ሰዎች አገግመዋል።
- በቤኒሻንጉል ክልል በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 213 ደርሰዋል ፤ ስልሳ ሁለቱ (62) ከበሽታው አገግመዋል።
- በሲዳማ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 224 ደርሰዋል፤ ትላንት ብቻ 40 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ሃያ ሁለቱ (22) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።
- በአፋር ክልል እስከዛሬ 284 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፥ ከነዚህ መካከል 117 ሰዎች አገግመዋል።
- በሱማሌ ክልል አጠቃላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 705 ደርሰዋል፤ 406 ሲያገግሙ 18 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 805 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,786 የላብራቶሪ ምርመራ 805 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 78 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 16,615 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 263 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,763 ናቸው።
#ጤና #ሚኒስትር
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5552 የላብራቶሪ ምርመራ 145 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5570 ደርሷል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5414 የላብራቶሪ ምርመራ 250 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5425 ደርሷል።
Читать полностью…በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ5,000 አለፉ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,034 የላብራቶሪ ምርመራ 186 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5,034 ደርሷል።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 35 (15 ከጤና ተቋም እና 20 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ሁለት ናሙናዎች ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበቸዋል።
በተጨማሪ አንድ በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበር ሰው ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ ስምንት (78) ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አራት (74) ሰዎች (63 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከትግራይ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ሐረሪ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1486 ነው።
#DrTedrosAdhanom
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በሰጡት መረጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ከተያዙት ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከል የመጀመሪያው 1 ሚሊዮን የተመዘገበው በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን የኃለኛው 1 ሚሊዮን ግን በ8 ቀን ጊዜ ውስጥ ነው የተመዘገበው።