elolam_elolam | Unsorted

Telegram-канал elolam_elolam - Coram Deo

1764

In the Presence of God ( Coram Deo) For Question and Suggestion Purpose use @sami_f_k_1 @Sami_inchrist @Amuti18

Subscribe to a channel

Coram Deo

አንዳንዴ ሁሉ ነገር ይጨልምና መውጫ የሌለ እስኪመስል ድረስ ይሆናል ተንበርክኮ መፀለይ ፣ ቃሉን ማንበብ ዳገት ይሆንብኛል ። የኅጢአቶቼ ክምር በውስጤ ሞልቶ በእግሩ ውስጥ ሄዶ ለመውደቅ ድፍረት እንኳን ያሳጡኛል ።
ተስፋዬ የምር ሟጥጦ ነገ እየራቀብኝ ሲሄድ ይሰማኛል ። ቃሉን መጣሴ ፍቅሩ እየወቀሰኝ እስክዝል ድረስ ያስነባኛል ። እሱን ዕለት ዕለት ማሳዘኔ ልቤን በሀዘን ይወጋዋል ።

ፊቴን ላዞርኩበት ለእኔ ሲል የሚወደው አባቱ ፊቱን እንዲያዞርበት መርጦልኝ ዛሬም ግን ይኸው የማልገራው እኔም ስጋዬ ከጅሎኝ አንዳንዴ ፊቴን አዞራለው እንዴት ደካማ ነኝ ምን ዓይነቱስ ከንቱ ነኝ አቤት ስጋ ግን እንዴት ክፉ ነው ። በራሴ ፍቅር ሰክሬ ከእኔ ውጪ እንዳይታየኝ ሆኜ ታውሬያለው ። አንዳንዴማ የምን አንዳንዴ እንደውም ብዙ ጊዜ ፀሎቴም መዝሙሬም ራሱ ኅጢአት ነው ። ሲበዛ ራስ-ተኮር ነዋ ። ግን መሀሪ ነውና አሁንም ቢሆን ከእግሩ ስር አልጠፋም ከተስፍሽ ጋር እኔም እንዲሁ " ስብራቴ" እያልኩኝ እቃትታለው።

Читать полностью…

Coram Deo

እናውቀዋለን ራሳችንን፤ ግን አንተ ከራሳችንም ታስጥለናለህ እና ለውጠን😭😭😭😭😭
@Elolam_the_Everlasting_God

Читать полностью…

Coram Deo

Heidelberg Catechism

Q. 1. What is thy only comfort in life and death?

A. That I with body and soul, both in life and death, am not my own, but belong unto my faithful Saviour Jesus Christ; who, with his precious blood, has fully satisfied for all my sins, and delivered me from all the power of the devil.

Читать полностью…

Coram Deo

😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭🫠🫠🫠🫠🫠🫠🫠🫠🫠🫠🫠🫠🫠🫠
በቃ ያለኸን እኮ አንተ አይደለህ ማወራው ባይኖረኝም እግርህ ስር ነኝ እንባዬን ታነበዋለህ ልቤ ከውስጥ ሆና ምትጮኸውን ጩኸቷን ታደምጠዋለህ😭😭
@Elolam_the_Everlasting_God

Читать полностью…

Coram Deo

<<ሮሊ-ፖሊ ስለሚባሉ ነፍሳት ታውቃላችሁ? ግራጫ ቀለም ያላቸው በእግረኛ መንገድ ላይ የምታገኟቸው አነስተኛ ነፍሳት ናቸው። ስትቀርቧቸው እንደ ትንንሽ ኳሶች ይጠቀለላሉ። ጥቅልል ሲሉ ልታዩአቸው የማትችሉ ይመስላቸዋል ብዬ እገምታለሁ። ነገር ግን እንዲጨፈለቁ ራሳቸውን ይበልጥ ያመቻቻሉ! የቆሰሉ ሰዎችም ብዙውን ጊዜ እንዲሁ ነው የሚያደርጉት-ራሳቸውን ከዓለም ደብቀው፣ ወደ ውስጥ ታጥፈው፣ እንደ ትንንሽ ኳስ ይጠቀለላሉና ከጥቃት እንደሚያመልጡ ያስባሉ። እውነታው ግን በንዴት፣ በምሬትና በመብለክለክ ለመጠመድ ይበልጥ ቀላል ዒላማ ይሆናሉ።

ከቆሰሉቱ ብዙዎቹ ሌላ ሰው ዳግመኛ ላለማፍቀርና ላለማመን በመፈለግ መደበቂያ ዋሻዎችንና ልባቸውን ያጠነክራሉ። ማንም እንዲጠጋቸው አይፈቅዱም፤ እነርሱም ወደ ማንም አይጠጉም። ይህ ጠባይ ችግር አለበት። ቁስል የደረሰባቸው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሆነ፣ ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ይሄዳሉ ወይም ጭራሹኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄዱን እርግፍ አድርገው ይተዉታል። የቆሰሉ አገልጋዮች ብዙ ጊዜ አገልግሎት ይተዋሉ። እንደ ኤርሚያስ፦
"ሕዝቤ ትቼ፣ ርቄ እንድሄድ
በምድረበዳ የእንግዶች ማደሪያ ማን በሰጠኝ!
ሁሉም አመንዝሮች፣
የአታላዮች መንጋ ሆነዋላ!
ሐሰተን መናገር፣
ምላላሳቸውን እንደ ቀሰት ገተሩ።"
(ኤር. 9፥2-3 አ.መ.ት)

የማያመሰግን ነቢይ ከመሆን የሆቴል አስተናጋጅ መሆን ይሻላል።

የቆሰሉና ወደ ትንሽ ኳስነት የተጠቀለሉ ሰዎች ማንንም የማያምኑና ተጠራጠሪ ይሆናሉ፤ ጥንቃቄ የማይደረጉ ከሆነማ እነርሱም ጦር ወርዋሪዎች ሆነው ያርፉታል። ቁስላቸውም አላግባብ የደረሰባቸውን ጉዳት ያለማቋረጥ እየተመገበ የሕይወታቸውን ትርጓሜ እስከ መሆን ይደርሳል።

ይህ አንድ ምርጫ ነው። ወይም ልክ እንደ ዳዊት የጽድቅ ምላሽ በመስጠት እግዚአብሔር እንዲታደጋችሁና እንዲፈውሳችሁ መፍቀድን መምረጥ ትችላችሁ። የጉዳት ሰለባ ወይም ድል ነሺ መሆን የእናንተ ምርጫ ነው።[..] >>

-ሮናል ደን፡የወዳጅ ፍላጻ(ትርጉም ጳውሎስ ፍቃዱ) ገጽ 48-49

@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

እኛማ እንዳንተ አይደለንም
********************
አንተ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የሚሸቅጡ በዙ ብለህ ጅራፍ ታነሳለህ፡፡እኛ ግን እንደዛ አናደርግም፡፡ለኛ እንዲያውም ይሄ ደስታችን አለማችን እና አላማችን ነው፡፡እኛ ጨዋዎች ነን፡፡ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በግልጥ ጅራፍ አናነሳም፡፡ውስጥ ለውስጥ ለመወጋጋት የገመድነው የምላስ ጅራፍ የት ሄደና ለማን ሆነና፡፡
እኛማ እንዳንተ አይደለንም፡፡አንተ የቅባት ምስጢር አልገባህም፡፡አንተ እኮ ስንት እና ስንት ድንቅና ተአምራት ያውም በራስህ ስልጣን አድርገህ ዮሐንስ ሲጽፍ ኢየሱስ ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደሞ አለ፡፡ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸው ይመስለኛል፡፡ተባለ እንጅ አንድ በአንድ አላዘረዘርክም፡፡እኛ እኮ አጋንንት ባንተ ስም እንዲጮህ አዘን እንደምንም በትግል አንድ ከግማሽ አስጩኸን በአስር ካሜራ የምናስቀርፅ የሙዚቃ መሳሪያ የምናስደልቅ ፌስቡኩን ዩቲዩቡን ቴሌቪዥኑን የምናጨናንቅ እኮ ነን፡፡አንተ በራስህ ስልጣን ያን ሁሉ አድርገህ ትንሽ እንኳን ኩራት ቢጤ አልተሰማህም፡፡ይቅርታ አድርግልንና ይሄ በኛ እይታ ጤነኝነት አይደለም፡፡ባንተ ስም አጋንንት አውጥተን ልባችን በትዕቢት የተወጠረ በራሳችን ስም አጋንንት ብናወጣ ምን እንደምናደርግ እኛ አናውቅም አንተ ታውቃለህ፡፡
አንተ በውሀ ላይ ተራምደህ ምንም አልመሰለህም፡፡እኛ እኮ ወዳንተ ቤት በገባው አስራት እና መባ የ 3000 ብር ጫማ አድርገን ተራምደን ሰውን መግቢያ መውጫ እናሳጣለን፡፡
እኛማ እንዳንተ አይደለንም፡፡አንተ እኮ 3 አመት ያስተማርካቸው ያበላሀቸው በመከራ ቀን ጥለውህ ሲሸሹ ሰው ያጣህ ይመስል ተመልሰህ መጥተህ ያሉበት ድረስ ፈልገህ ዳግመኛ እነሱ ጋር ትሆናለህ፡፡እናም ከላይ እንዳልኩት በኛ እይታ ይሄ የጤናማ ሰው ምልክት አይደለም፡፡እኛ እኮ አይደለም 3 አመት አስተምረናቸው ቀርቶ 3 ሳምንት ያስተማርናቸው "ዳዲ" ካላሉን "እዚህ ላይ ሀሳብ አለኝ ካሉን" አይነ ውሀቸውን ካልወደድነው እና ከተቃወሙን ፊት እንነሳቸዋለን፡፡ "ከዳተኞቹ" በሚል ርዕስ ፌስቡክ ላይ እንፅፍባቸዋለን ገንዘብ ከፍለን እናፅፍባቸዋለን፡፡"ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" የሚል መጽሐፍ እንፅፍባቸዋለን፡፡"ዮሴፍን ወንድሞቹ ለምን ጠሉት" በሚል ርዕስ እንሰብክባቸዋለን፡፡"ፍሬ የማያፈሩ ሰዎች 17 በሀርያት" የሚል ተከታታይ ትምህርት እናስተምርባቸዋለን፡፡"ወዳጅ መሳይ ጠላት" በሚል ርዕስ ግጥም፣ወግ መነባንብ ወዘተ እንፅፍባቸዋለን፡፡አንተ ግን ያውም በገረድ ፊት 3 ጊዜ ክዶህ 3 ጊዜ ትወደኛለህን ብለህ ትጠይቀዋለህ፡፡ይሄ አግባብ አይደለም፡፡
አንተ እኮ ገንዘባቸውን በመዝገብ ሲጥሉ አይተህ የልባቸውን እንጂ የእጃቸውን አላየህም፡፡ለዛም ባለዲናሯ መበለት አብዝታ ጣለች አልክ፡፡ይሄ እሳቤ የሚያዋጣ አይደለም፡፡እኛ እኮ ዳጎስ ያለ ካልጣለ ምኑን ጣለ ብለን ነው የምናምነው፡፡ያች መበለት በኛ ዘመን ብትኖር ኑሮ እመነኝ አንዳችንም በዘይት አንፀልይላትም ወንበርም አታገኝም ነበር፡፡እየሰረቁ፣እየዘረፉ ድሀውን እየበደሉ ያመጡት ያመፅ ገንዘብ ይሁን በላባቸው ሰርተው ያመጡት የፅድቅ ገንዘብ እሱ እኛን አይመለከትም፡፡ብቻ በሽዎች የሚቆጠር ገንዘብ ያምጡ ቅድሚያ ለነሱ ነው፡፡ይፈወሱ አይፈወሱ የኛ ጉዳይ አይደለም፡፡ደሞ ረስቼው 12 አመት ደም ሲፈሳት የኖረችው ሴት በቀላሉ እንድትነካህ አድርገሀል፡፡በዚህ ደሞ ክብርህን እንዳስነካህ ቁጠረው፡፡ለመንካት የተዳፈረችው እኛን ቢሆን ኑሮ እሷን አሽቀንጥሮ ለመጣል ከ 5-10 ከሚደርሱ ወጠምሻ ጋርዶቻችን መካከል አንዱ ይበቃት ነበር፡፡በዚሁ አያይዤ አስደፍረውሀልና ደቀመዝሙሮችህን ሳልነቅፍ አላልፍም፡፡ ደሞ ቀኑን ሙሉ በማስተማር ደክመህ 5000 ሰዎችን ትመግባለህ፡፡መቸም እኛን ለማስኮነን ካልሆነ በቀር ይሄ ምን የሚሉት ደግነት ነው?እኛ እኮ 45 ደቂቃ አስተምረን የሚበሉትን ነው የምናሳጣቸው፡፡አሁን አንተ አንድ ቀን ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ብለህ ያስተማርከው ትምህርት ያስተዛዝባል፡፡እኛ እኮ መንግስተ ሰማይ ለባለጠጋ በሯ ምንጊዜም ክፍት ነው ብለን ነው የምናስተምረው፡፡
ብቻ አንተ ለህዝቡ ጥሩ የህይወት ምርጫ ህዝቡ ደሞ ለኛ ጥሩ የስራ ምርጫ ናቸው፡፡ባንጠቅማቸውም ተጠቅመናል፡፡
እኛ እኮ ባንተ ስም ለራሳችን የምንሰራ ላንተ የሚሰሩትንም የምናሰድብ ነጋዴዎች ነን፡፡
እናም እባክህን ማራናታ የሚሉህን አትስማቸው፡፡አንተም እነሆ በቶሎ እመጣለሁ አትበል፡፡
(በስምህ እንሸቅጣለን እናተርፍማለን የነጋዴዎች ማህበር የቦርድ ሊቀመንበር)

#በሄኖክ አሸብር
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

ከናዝሬት መልካም-
በፓስተር ሚኪ

ተሳድጄ ነበር ወደ ናዝሬት የሄድኩት። ወትሮም መጠጣት ልማዴ ነው፣ ናዝሬት ከሄድኩ በኋላ ደግሞ ባሰብኝ። ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ የከተተኝ ደግሞ አዲስ አበባ በፖሊስ መታደኔ ነበረ። "ደሞ ነገ ልያዝ" እያልኩ አልኮል መጠጣቴ ጨመረ። አንድ ቀን እንደተለመደው በመጠጥ ጢምቢራዬ ዞሮ በአንዲት እህት ጋባዥነት ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ። ሰፈሬ ጌጃ ሰፈር ስለነበረ ጌጃ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ሰርግ ሲኖር ምግብ ለመብላት ከሰፈር ልጆች ጋር እየገባን ምግቡ እስኪጀመር ድረስ ስብከት ከምንሰማው በቀር ብዙም ሃይማኖታዊ ስብከት ለመስማት ፍላጎቱም አልነበረኝ። ዛሬ የምሰማው ስብከት ግን ለየት አለብኝ። ሰክርያለሁ ግን የምሰማው የእግዚአብሔር ቃል ሰርስሮ ውስጤ እየገባ ነበር። የደነደነው ልቤ በቃሉ ጉልበት ሲቀልጥ ይታወቀኛል ። ከሰፈሬ፣ከጓደኞቼ ፣ከቤተሰቤ እርቄ ተሳድጄ ባለሁበት፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ በናዝሬት ተገናኘኝ። ተምበርክኬ በእንባ ኃጢአቴን ተናዘዝሁ። ለረጅም ሰአት ብንበረከክም የአሸዋው ቁርቋሬ አልተሰማኝም ነበር። ተሰብኮ እንዳለቀ እጄን አንስቼ የሁሉ ወዳጅ የሆነውን ኢየሱስን የህይወቴ አዳኝና ጌታ አድርጌ ተቀበልኩኝ። ለመጀመሪያ ግዜ ገንዘቤ ቁም ነገር ላይ የዋለው መፅሐፍ ቅዱስ የገዛሁ ቀን ነበር። በጣም ደስ አለኝ። አንብቤ አልጠግብ አልኩኝ። የምኖርበት ቤት ሲመሽ ከተወሰነ ሰአት በኋላ መብራት ስለሚያጠፉ ሻማ ገዝቼ በሻማ ማንበቤን ቀጠልኩ። እስከ አሁን ይገርመኛል እስር ቤት ገብቶ የሻማ ከመጠየቅ በሻማ ወደማንበብ ገበሁ። ክብር በድንቅ ላዳነኝ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን። በሚገርም ፍጥነት ህይወቴ ተለውጦ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ። የቀደመው ድርጊቴ ተለወጠ። ብዙም ከቤት አልወጣም ነበር። ቤቴ ተቀምጬ መፅሐፍ ቅዱሴን አነባለሁ። ቸርች እሄዳለሁ። ቤተሰቦቼ ቤት መዋሌ አሳሰባቸው። የድሮው ብስኩቴ እንዳልሆንኩ ገብቷቸዋል። በኋላም የመለወጤን ምስጢር ደረሱበት። አንድ ቀን ከቸርች ስመለስ ቤታችን ሽማግሌዎች በኔ ጉዳይ ተጨንቀው ተሰብስበዋል። ቁጭ አርገው ይመክሩኝ ጀመር። "ተው ሃይማኖትህን አትለውጥ" አሉኝ። ህይወቴ እንጂ ሃይማኖቴ እንዳልተለወጠ ነገርኳቸው። ናዝሬት ሄዶ ብሶበት ይመጣል ብለው ሲጠብቁኝ ከናዝሬት መልካም ሆኜ ተመለስኩ። ዛሬ የጌታ ፀጋ ባገዘኝ መጠን በኑሮ የተጎዱ ወገኖችን ስረዳ እንባዬ ይመጣል። እንኳን ሰው ለማገዝ ቀርቶ ራስን ችሎ መኖር በአዕምሮዬ አስቤውም አላውቅም። ክብር የሁሉ ወዳጅ ለሆነ ለኢየሱስ ይሁን። በልዩ ልዩ ጉዳይ ህይወታችሁ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያላች ወገኖቼ ፣ዛሬ የቃሉ ሰባኪ ሆኜ # ሃያ_አንድ አመት ጌታ በኔ ሆኖ በተከላት ቤተክርስቲያን አገለገለ የተባልኩት እኔ ህያው ምስክር ነኝ እግዚአብሔር ሰውን ይለውጣል። ህይወትን መልካም ያደርጋል። በብዙ ነገር ተስፋ ብትቆርጡም በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ አትቁረጡ እርሱ አዳኝ ነው።
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

“በወንጌል አላፍርም” ... (፪)

በመጋቢ ሰሎሞን አበበ ገ/መድኅን
***
ወንጌል ግን ምንድር ነው?

ትንሽ ወደ ኋላ እንኺድ...

እግዚአብሔር ከዘላለም የነበረው ዐቢይ አጀንዳ በሰማይና በምድር ያለውን ኹሉ በክርስቶስ ለራሱ ክብር መጠቅለል ነው። እርሱ እንደ ፈጣሪ-ንጉሥነቱ ኹሉ በኹሉ ከሚኾንበትና መላለማዊ ክብር ብቻውን ከሚቀዳጅበት እውነታ በላይ የላቀ ዓላማ አልወጠነም። መነሻውም መደምደሚያውም የእግዚአብሔር ክብር ብቻ ነው። ለእርሱ ክብር ዓለማት ተፈጠሩ።
.

የዚህ ዓላማው አካል ይኾን ዘንድ ራሱ በሠራው ዓለም ውስጥ በገዛ መልኩና ምሳሌው የፈጠረውን የሰው ልጅ በልዩ ክብርና ቅርበት ከአምላኩ ጋር ኅብረት እንዲኖረው አደረገው። በፍጥረት ኀላፊነቱ የእግዚአብሔር መልክ ነጸብራቅ አድርጎት የእግዚአብሔር በኾነችው ምድር ላይ በእንደራሴነት ሾመው። ሰው በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ የዘላለሙ አምላክ መልክ ነጸብራቅ (image bearer) እና የፍጥረቱ ደግሞ ባለ ዐደራ ገዢ (መጋቢ) ነበር (ዘፍ. 1፥26-28)።
.

ኾኖም የሰው ልጅ በኀጢአት ምክንያት በአምላኩ ላይ ዐምፆ በመውደቁ ምክንያት፥ ከእግዚአብሔር ስለ ተለየ የፍዳና የኵነኔ ባለ ዕዳ ኾነ (ዘፍ. 3)። በሰውም ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባ (ሮሜ 5፥12)። የእግዚአብሔርም ዓለም በኀጢአት፥ በዐመፅ፥ ባለመታዘዝና በግፍ ስለ ተሞላ ፍርድና ጥፋት በዓለሙ ኹሉ ነገሠ (ዘፍ. 6፥11-12)።
.

ኾኖም እግዚአብሔር የወደቀውን ሰው ለማዳንና ዓለሙን ለመቤዠት በዘላለም ዕቅዱ አንድ ልጁን አሳልፎ በመስጠት የማደስን ሥራ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ መርቆ ከፈተ (ዘፍ. 3፥15፤ ቈላ. 1፥21)። የእግዚአብሔር መንግሥት ድል ነሺ አገዛዝም መጣች። የመንግሥቱ ኹለንተናዊ የአገዛዝ ትፍጽምት ተስፋም በክርስቶስ ዳግም መመለስ እውን እስኪኾን በተስፋ እየተጠበቀች አለች። የዚህ የመንግሥቱ መምጣትና ሰውም በክርስቶስ ጸጋ በእምነት አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቅበት የንስሐ ጥሪ የምሥራች ታወጀ። ይህ የምሥራች መልእክት ወንጌል ተብሎ ይጠራል።

እኮ፥ ወንጌል ምንድር ነው?

(የሚቀጥል)
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

“በወንጌል አላፍርም” የምትሰኝ ብፅዕና (፩)
***
በመጋቢ ሰሎሞን አበበ ገ/መድኅን

ወንጌሉን የሰበክን አስመስለን የኛን እንቶ ፈንቶ ኹሉ በውስጡ እምናጕርበት ምን ይረባናል ብለን ነው? የወንጌላችን ዋና ነገር የእግዚአብሔር ልጅ የኾነው ክርስቶስ ኢየሱስ እንጂ ማንምና ምንም አይደለም (ሮሜ 1፥4)። “ኹለት እግር አለን ብለን ኹለት ዛፍ ላይ መውጣት” ብንከጅል አይኾንም። የእግዚአብሔርና የቄሳር መልእክተኛ መኾንም አይቻልም። ወንጌል ሰባኪነት መልእክቱን ሳይቀይጡ ወይም ሳያቀጣጥኑ የማቅረብን ታማኝነት ይጠይቃል። የታሪክ ትልቅነትም፥ ትውፊታዊ ገናናነትም ቢኖረን እንኳ፥ ክርስቶስን ከሸፈነ የሕይወት ጠንቅ ነው። ሐዋርያቱ እኮ፥ “ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ፥ ራሳችንን አንሰብክም” (2ቆሮ. 4፥5) ብለዋል። የታዋቂነት ቅዠት ክፉ ገጀራ ተሸክሟል። ለክርስቶስና ለወንጌሉ ያለንን የታማኝነታችንን ኅብለ ሰረሰር እንዲያጭደው አጐንብሰን አንመታ። [ጆን ስቶት (ይመስለኛል) እንዳሉት ብጤ፥ You cannot be both popular and faithful at the same time.] ሲቀር ለሚቀር ምድራዊና ውራጅ “ክብር” ሰማያዊውን እውነት ማድበስበስና ሲብስም ማልኰስኰስ ለዘላለም ያኰስሳል።
.

አይገርምላችሁም! ሰው ወደ ሠራት ምድራዊ መቅደስ ተመልሶ እስከ መጐምዠት መቃዠት?! አይገባም። ወደ ጌታ ዘወር ስንል የሚወሰደውንና በሚሻለው ክብር ምክንያት የተሻረውን ፊተኛ “መጋረጃ” ወደ ኋላ ዞረን የሙጥኝ በማለት፥ ትውልድን ለመኮድኮድ እያደባንና የዐዞ እንባ እያነባን አብርሆት እንዳገኘ ክርስቲያን ተመስለን ብናንገራብድ እውነት ትዘልፈናለች፤ ወንጌል ራሷ ትንቀናለች። የሕይወት ክብርም ትርፍም አይኾንልንም። ሕይወትን የሚፈቅድ በጎውንም ዘመን ለማየት የሚወድ ከዚህ ይራቅ።
.

የወንጌል መልእክተኞች ነን ካልን፥ እግዚአብሔር ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን ያወጣበትን ወንጌል (2ጢሞ. 1፥10) እቅጯን መናገር አለብን። በዐጭሩና በግልጽ ቋንቋ “የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፥ ወይም ጥፉ” የማለት ያህል ግልጽነትና ታማኝነት ይጠበቅብናል። ወገኔ፥ የምኞታቸው መታለል የሚያንከወክዋቸውን ሞኞች ስሕተት (Deceptiveness of the Sensual) የምትጋፈጠው ቃሉን ብቻ ስትሰብክ ነው (2ጢሞ. 4፥1-4)።
.

ጌታችንና መድኀኒታችን የኾነው ክርስቶስስ ያደረገው ይኸንኑ አልነበረምን? “ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና ‘ዘመኑ ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ’ እያለ ወደ ገሊላ መጣ” (ማር. 1፥14-15)።
.

ለብዙዎች ባይመችም፥ አንዳንዶችን ጆሮዎቻቸውን ባያክላቸውም፥ ታማኝ የወንጌል አገልጋይ ሙሉውን የወንጌል እውነት ያውጃል፤ ሰዎች ስሜታቸውን ከሚያሟሙቅ ነገር ተላቀው ድኅነት እንዲያገኙ የሚያበቃቸው ብቸኛው ዐዋጅ በታማኝነት የምንሰብከው የክርስቶስ ወንጌል ብቻ ነው። መድኅኑ ኢየሱስ ብቻውን በቂ ነው፤ ከኹሉ በላቀው ጌትነቱ ኹሉን ይገዛ ዘንድ መላለማዊ ምሥፍና ተቀዳጅቷል። አዳኝነትና ጌትነቱን ትሰብከዋለህ፤ እርሱም ያድናል። ሲያድን ታየዋለህ እንጂ፥ እንዲያድን አታግዘውም። እግዚአብሔር ከንቱ ባደረገው ሰብአዊ ጥበብና አዋርዶ በጣለው ምድራዊ ብልኀት የምትናጠቀው አንዳችም ነፍስ የለም። ሰዎች የዳግም ልደት ብርሃንን እንዲያገኙ ሳይኾን፥ ጠባያቸው እንዲሻሻል ከፈለግን የጠባይ ማረሚያ ማቋቋም እንችላለን።
.

የወንጌልን እውነት፥ እውነትን ብቻና ሙሉውን እውነት በማወጅ ያልተጋፈጥናት ነፍስ በሰው ሐሳብና ምድራዊ ጥበብ መዳን አትችልም። በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ኀይል ከጌታው ጋር የመነሣትን ተካፍሎትን በመንፈስ ኀይል ያላገኘ ሰው ምንኛም ዐይነት ትንሣኤ የለውም፤ ያን ታላቅ ግብ ለማሳካት “ቃሉን ስበክ”። ጥያቄው ግልጽ ነው፤ “የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን” የሚለውን ጥቅስ በየግድግዳችን ላይ እንለጥፈዋለን? ወይስ ጥቅሱ የሚለውን በተግባር እናደርገዋለን? ርግጥ ነው፤ የወንጌል መልእክት በፍቅር መቅረብ አለበት። እውነት ያለፍቅር ጭካኔ ይኾናል። ፍቅር ደግሞ ያለ እውነት ግብዝነት ይባላል። ስለ ኾነም፥ መጽሐፍት እንደሚመሰክሩ፥ ወንጌል ሳይሸቃቀጥ መሰበክ አለበት። ሰዎችን ለማስደሰት ተብሎ ከሥፍሩ አይጐድልም። ከልኩም አይዘናበልም።

.
ቢሊ ሰንደይ የተናገራት አገላለጽ ሐሳቤን የበለጠ ታስረዳልኝ ይመስለኛል፤ “I am an old-fashioned preacher of the old-time religion that has warmed this cold world’s heart for two thousand years.”

እንግዲያውስ፥ በሉ ተነሡና ወንጌሉን ስበኩ … ከዘማሪ ዐዲሱ ወርቁም ጋር እንዲህ ተቀኙ፤ …

“የሚያሳፍር ሰም አይደለም፥ የሰጠኸን ጌታችን፥
ክርስቲያን ጀግንነት እንደሁ፥ ይረዳልን ልባችን፤
ክፉውን ኹሉ ተቃውመን፥ ከኀጢአት ጋራ ታግለን፥
ጕዟችን በድል ያከትማል፥ የጌታን መስቀል ይዘን።
.
(የሚቀጥል)
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

==="ወንድምህ ወደየት አለ?"===

በመጋቢ ሰሎሞን አበበ ገ/መድኅን
**
መጽሐፍ እንዲህ ይላል፤ "እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር። ... እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው" (ዘፍ. 1፥26-27)።
.

ሰው በአምሳለ እግዚአብሔር መፈጠሩ የሰብአዊ ክብሩ መሠረት፥ የሥነ ፍጥረት ኀላፊነቱ መገኛ ነው። የሥነ ፍጥረት ኀላፊነቱ (creation mandate) የእግዚአብሔርን መልክ ማንጸባረቅ እንጂ ከቶ ሌላ አልነበረም፤ አይኾንምም። መልክአ-ፈጣሪ (Imago-Dei) ነውና ራሱን ሳይኾን አምላኩን ያከብራል፤ በመጋቢያዊ አደራውም በአምላኩ ዓለም ላይ የእግዚአብሔርን ፍጥረት በውክልና ያስተዳድራል።

ኀጢአት ቢያንኮታኩተውም፥ በተሰበረ ማንነቱ እንጥፍጣፊ ውስጥ ሰው የመኾኑ መሠረት ከናካቴው አልወደመም። ቤዝዎትም የሰውን ልጅ ለድኅነትና ዳግም ልደት የሚያበቃው ያው በአምላክ መልክ የመፈጠሩ እውነታ ስላለ ነው።
.
ሰው ታዲያ የራሱን ብጤ ሰው እንዲወደው፥ እንዲያከብረውና እንዲጠነቀቅለት ይገባዋል። እግዚአብሔር ለኖሕ እንዲህ ብሎ አዝዞት ነበር፤ "የሰውን ደም የሚያፈስስ ኹሉ ደሙ ይፈስሳል፤ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና" (ዘፍ. 9፥6)። ሰው ደሙ በከንቱ መፍሰስ የሌለበት መሠረታዊ ምክንያት ከእንስሳት ኹሉ ከፍ ብሎ የሠለጠነና የዳበረ አንጎል የተሸከመ እንስሳ ስለኾነ አይደለም። በእግዚአብሔር መልክ ስለ ተፈጠረ ነው። ... አትግደለው!

.
የሰው ልጅ በኀጢአቱ ምክንያት ከአምላኩ ጋር ተጣልቶ ከተለየ በኋላ ግን የጠብ እሾኽ በኹለንተናው ሳይተከልበት የቀረ አይመስልም። የመጀመሪያዎቹ ወንድማሞች፥ ማለትም ቃየልና አቤል፥ የኅብረታቸው ታሪክ የተጻፈበት ገጽ እንደ ሐምሌ ደማና በጨፈገገ ስሜት የታፈነ ነው (ዘፍ. 4፥1-5)። ቃየል በክፋት ጐርፍ ልቡናው ተጠርጎ ከማደፉ የተነሣ በወንድሙ ላይ በጠብ ተነሣሥቶ ሲያበቃ፥ "እንውረድ" ብሎ አውርዶ ገድሎት ተመለሰ። ገጣሚው አበባው በ"እስከ ማእዜኑ" እንዳመሰጠረው፥
.

"ክልኤቱ አኀው መንገለ ቀላይ ወረዱ፥
እኒህ ኹለት ወንድሞች ወደ አዘቅት የኼዱ፥
አሐዱ ተመይጠ ወኢተመይጠ አሐዱ፤
አንደኛው ሲመለስ ኹለተኛው በዚያው የቀረ፥
ውረድ እንውረድ ያለው ወንድሙ ገድሎት ነበረ።"
.

ውድቀት በውጤቱ ቍልቍል የሚነዳ አባዜ ነበረውና፥ የቀዳሚውን ቤተ ሰብ ኅብረት የጠብ ጽልመት በኀዘን ማቅ ሊከድነው በቃ። ምንም እንኳን ሞት ኀጢአትን ተከትሎ ወደ ዓለም ቢገባም፥ በሰው ታሪክ ውስጥ፥ የሰው ሕይወት ለመጀመሪያ ጊዜ በሞት የጠፋው በራሱ በሰው እጅ መኾኑ መራሩ ምጸት ነው።
.

"እነሆ፥ ከዚያ ክኽደት በኋላ፥ ሰው የተባለው ፍጡር የእርስ በርስ ጠላት ኾኖ ኖሯል። አንዱ አንዱን ሊያጠፋና ሊገድል ወንድም በወንድሙ ላይ ያሤራል። ሰው በጎረቤቱ ላይ ያቄማል። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ጥላቻን ተሞልቶ ይነሣል፤ ሲከፋም ጦር ሠብቆ ይተራመሳል። የአዳም ዘር (ልቡ በጠብ ታፍኖ) በጥቅም ምክንያት ሲጋጭ ዘመናት ዐልፈዋል። በቅንአት፥ በዘር፥ በጎሳ፥ በቋንቋ፥ በሃይማኖት ልዩነት እያመካኘ ሲፋጅና ሲጫረስ ታሪኩን በደም አጥቍሮ ኖሯል" (ጠብን እንጠብ፥ የትሩፋን ናፍቆት)።
Part one
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

የሚገርም ህጻን
************
ኢየሱስ ራሱን #ሰጪ እና #ስጦታ ባደረገበት ልዩ ቀን ራሱን አሳልፎ ሰጥቶናልና #ሰጪ ነው፡፡
ተቀብለነዋልና #ስጦታ ነው፡፡
ኢየሱስ ስጦታ ሰጭያችን ብቻ ሳይሆን ሰጪ ስጦታችንም ነው፡፡የሚገርም ህጻን የሚገርም አምላክ ነው ለዘልዓለሙ አሜን!!

#ሄኖክ አሸብር

Читать полностью…

Coram Deo

ብዙ መንፈሳዊ ርዕሶች ዳስሳለች አንብቧት።

📔ርዕስ፦ያልተንኳኩ በሮች
👤ደራሲ፦ ጳውሎስ ፈቃዱ 📑የገጽ ብዛት:-168
አስተማሪ የአጫጭር ጽሁፎች ስብስብ ነው። ዘና እያሉ ቁም ነገር ይጨብጡ። ጳውሎስ የመጻፍ ችሎታውን ያስመሰከረበት ምርጡ መጽሐፍ ነው።

Читать полностью…

Coram Deo

እግሮችም የሉኝም ፊትህ የምቆምበት
አይኖችም የሉኝም አንተን የማይበት
የጠራኸኝ አምላክ ውርደቴን ተመልከት
ከገባሁበት ማቅ አውጣኝ በአንተ ምህረት

ስብራቴ የማይፈወስ ይመስላል
መድሀኒቴ አንተ ግን ምን ይሳንሀል
ምህረትህ ካለ ማጉረምረም ምን ይጠቅመኛል
በእጅህ ውስጥ መውደቅ ኦ እጅግ ይሻለኛል

ከአንተ የተሰወረ ምን አለ ጌታ ሆይ
ከቶም ሳይገለጥ ተደብቆ የሚቆይ
የልቤ መርማሪ የእኔ ውስጥ አዋቂ
ቅሌቴን ይቅር በል የነፍሴ ጠባቂ

ምንም ቸር ብትሆን በአንተ አይዘበትም
ጉዴን ለመሸፈን ምክንያት አላቀርብም
ያው ከነ በደሌ ራሴን ሰጥቻለው
ምረህ ተቀበለኝ ቃልህን ጥሻለው

ምንም እንኳን ዛሬ ሀፍረት ቢሸፍነኝ
ፊትህን ለማየት ከቶ ቢያዳግተኝ
በተስፋ ዝም ብዬ ቀኔን እጠብቃለው
በድል ልታድሰኝ እንደምትችል አምናለው

Читать полностью…

Coram Deo

@Elolam_the_Everlasting_God

Читать полностью…

Coram Deo

የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6ን ሳነብ እውነተኛው ወንጌል እንዴት እውነተኛውን ከሀሰተኛው እንደሚለይ ያስረዳል ። እንጀራ ፈልጎ ለመጣ የመስቀሉ ነገር ሞኝነት እና የሚያስጨንቅ ነው ።

⁶⁰ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ይህን ሲሰሙ፣ “ይህ የሚያስጨንቅ ቃል ነው፤ ማንስ ሊቀበለው ይችላል?” አሉ።

⁶¹ ደቀ መዛሙርቱም በዚህ ነገር ማጒረም ረማቸውን ኢየሱስ በገዛ ራሱ ተረድቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ዕንቅፋት ይሆንባችኋልን?


በገዛ ራስ ምኞታቸው ተጠላልፈው ቅድም መምህር ነቢይ ብለው ያሞጋገሱትን ሊያነግሱትን የሻቱን ያንን ጌታ ዋናውን ህይወት ያለበትን እውነት ሲነግራቸው አልዋጥ ሲላቸው እንመለከታለን።እርግጥም ጌታን አይንን ካልከፈተ አይን ለራስ ቅርብ ነው ።

¹⁴ ሰዎቹም ኢየሱስ ያደረገውን ታምራዊ ምልክት ካዩ በኋላ፣ “ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ በርግጥ ይህ ነው” አሉ።

በዚህ ታሪክ ውስጥ እጅግ ሚገርሙኝ ብዙ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ይህን የሚያህል ህዝብ ( ዮሐንስ የወንዶቹ ብዛት 5000 እንደነበረ ይነግረናል ግን አጠቃላይ ከሴቶች እና ልጆች ጋር ወደ 20000 እንደሆነ ይገመታል) በ 5 እንጀራ እና 2 ዓሳ አጥግቦ እያዩ መሲሁ እንደሆነ ሲነግራቸው ሌላ ምልክት መጠየቃቸው እጅን በአፍ የሚያስጭን ነገር ነው

³⁰ ስለዚህ እንዲህ ብለው ጠየቁት፤ “አይተን እንድናምንህ ምን ታምራዊ ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?

³¹ ‘ይበሉ ዘንድ ከሰማይ እንጀራን ሰጣቸው’ ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ።”

ይሄ ዘመን ይሄን ምዕራፍ ያስታውሰኛል ። ለብልፅግና እና ለትርኪ ምርኪ እቃቃ ኢየሱስን ተከተልኩ የሚል የመስቀሉ ወንጌል ሲነግረው ያዙኝ ልቀቁኝ የሚል እብሪተኛ ዘመን! Sorry for Being Harsh but This is the Truth.

ኢየሱስን መከተል ብቻውን ፋይዳ የለውም። ለምንድን ነው የምንከተለው ነው ዋናው ጥያቄ ! ሀብትን ጤናንን አስበን ከሆነ ምንከተለው የመስቀሉ ዜና ለኛ ትልቅ Offense ነው የሚሆነው።አለመቻላችን ሲነገረን ደስ አይለንም።

ሁሉ ነገር መድረክ ላይ አነቃቂ እና Entertaining ሆኖአል።ይሄ የሚያም እውነት ቢሆንም ራስን ፈትሾ መመለስ ያሻል። ሰው በነፈሰበት ሁሉ መዋለሉን ለምን እንወዳለን ? የምር ኢየሱስ ጠልቆ የገባው ሰው እንዴት ሆዱና ኪሱ አዕምሮው ይሆናል ?

ለኛ ኢየሱስ ማን ነው ? እስኪ አንዴ ራሳችንን እንጠይቅ ! እንደ ጴጥሮስ ካለሱ መሄጃ የሌለን እሱ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑን ያመንን ልንሆን ነው የምንገባው ! Nothing less than that.ጌታ ደግሞ ያኔም እሱን ሳይሆን ምግቡን ፈልገው ሊያነግሱት የፈለጉትን እንደሸሸ ዛሬም እንደነዚህ ያሉትን ይሸሻል።

Читать полностью…

Coram Deo

Paul Washer

"I Have Needed Christ the Most."

Читать полностью…

Coram Deo

እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው ። በማወቁ አይጠረጠርም ። እግዚአብሔር ግን የማያውቃቸው ነገሮች አሉ ።

1- ይቅር ያለውን ኃጢአት አያውቀውም ፣
2- ተስፋ የሌለውን ኃጢአተኛ አያውቀውም ፣
3- ብቻውን የሚበረታ ፍጡርን አያውቀውም ፣
4- የፈጠረውን ትንሽ ሰው አያውቀውም ፣
5- የሠራውን ከንቱ ቀን አያውቀውም ፣
6- የማይነጋውን ሌሊት አያውቀውም ፣
7- የማያልፈውን መከራ አያውቀውም ፣
8- የማይችለውን ኃይለኛ አያውቀውም ፣
9- ፍቅሩ ያልያዘውን ሰው አያውቀውም ፣
10- የማይጠገነውን ሰባራ አያውቀውም።
አሸናፊ መኮንን
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

እፅፍልሀለሁ
********
********
በስትንፋስህ ፊርማ ህያው ሆኘ ቁሜ
አንተ አበጅተኸኝ ባንተው ተገርሜ
ውዴ ሆይ ወዳጄ የህይወቴ መድህን
ላልጠግብ እያነሳሁ መልካሙን ስምህን
ብዕሬ በትጋት ፊደላት ይተፋል
ከዜማ ከቅኔ ፍቅርህ ከቃል ያልፋል
ከመታወቅ ሁሉ ከአዕምሮ በላይ ነህ
ቃላት የማይገልጹህ ቃል ነህ ቃልም አለህ
በዘመናት ልኬት በቀን ማትገደብ
ለመርታት ማትገጥም የማትሮጥ ለመቅደም
የምትባላ እሳት ፍቅርም ነህ ምልህ
ጌታዬ ነህ እያልኩ ጓደኛዬ ስልህ
አምላክ የኔ ወዳጅ እንዴት ሆነ እላለሁ
ደስ ብሎኝ ገርሞኝ ደንቆኝ እስቃለሁ
የምለው አጥቼ ከወረቀቴ ጋር ብዕር አነሳለሁ
ምን ልበል እላለሁ.................
ምን ልፃፍ እላለሁ..................
ቃላት እመርጥና ቃላት እጥላለሁ
ፊደል ገጣጥሜ ቃላት ተጠቅሜ እፅፍልሀለሁ

ለትልቅነትህ ጥግ ልክ የሌለው
የሰው ልጆች ቁጥር በፊትህ ምን አለው
በገንቦ እንዳለ ትንሽ ጠብታ ነው
አቤት ጌታ እያልኩኝ ደሞ እገረማለሁ
ከዛች ጠብታ ውስጥ እኔን አስባለሁ
የምለው አጣና ከወረቀቴ ጋር ብዕር አነሳለሁ
ምን ልበል እላለሁ..................
ምን ልፃፍ እላለሁ...................
ቃላት እመርጥና ቃላት እጥላለሁ
ፊደል ገጣጥሜ ቃላት ተጠቅሜ እፅፍልሀለሁ

ፊትህን ፍለጋ ሳልባክን ወዴትም
ምንጩን አንተን ሽቸ ስለ ህይወቴ ጥም
ትገኝልኛለህ ሁሌም ከኔ ጋር ነህ
ባንተ እንደምኖረው በ'ኔም ትኖራለህ
በህልውናህ ውስጥ እረሰርሳለሁ
ነፍሴ ትረካለች ሀሴት አደርጋለሁ
የምለው አጣና ከወረቀቴ ጋር ብዕር አነሳለሁ
ምን ልበል እላለሁ..........
ምን ልፃፍ እላለሁ..........

ግን እኮ ጌታ ሆይ ግጥሞቼ ቢበዙ
እድሜ ልኬን ብፅፍ ስራህን ቢያወሱ
የአንተን አንተነት አይገልፁም አውቃለሁ
ይሄን በማወቄም ባንተ እገረማለሁ
እንኳንም ያንተ ሆንኩ እያልኩ እኖራለሁ
ብዕሬ አይነጥፍም እፅፍልሀለሁ

#ሄኖክ አሸብር
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

ወደ ኋላ ለመመለስ ያፈረውን፣ ወደፊት ለመጓዝ የፈራውን የምታበረታ መጽናናት ሆይ ይቅር በለን። የማትፈርሰው የድሆች አዳራሽ ሆይ በመልካም አስበን። - ዲአመ
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

#ንጉሴ ቡልቻ ሊያገለግሉ በቆሙበት አንድ ምስባክ የገጠማቸውን እንዲህ ያስረዳሉ፤ “አንድ ቀን ለአገልግሎት ተጠርቼ ወደ ስብሰባ ቦታ ሄድኩ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሴን ይዤ ማስታወሻ ደብተሬን አመቻችቼ ስጠራ ወደ ምስባኩ ወጣሁና ልናገር አፌን ገና ሳልከፍት በምስባኩ (ፑልፒቱ) የውስጥ ጉበን ላይ በእንግሊዝኛ የተጻፈ ጥቅስ አየሁ፡፡ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ጌታው እኛ ማየት የምንፈልገው ኢየሱስን ነው፡፡››… ጥቅሱ አቆፈጠነኝ፣ ገራኝ፣ ልክ አስገባኝ፣ ትሁት አደረገኝ፣ ቦታዬን ነገረኝ፣ ተልዕኮዬን አስታወቀኝ፣ ያ ጥቅስ ባለውለታዬ ነው፡፡” ...(“መስተአየት”፣ 37)
በሌላ ወቅት በጻፉት መጽሐፋቸው ደግሞ ይህንን እውነት ፍንትው አድርገው ያስቀምጣሉ፡፡
“ወንጌል ስለ ክርስቶስ ነው፡፡ ድሩም፣ ማጉም፣ ቋሚውም፣ ወራጅ ምሰሶውም፣ መሠረቱም ቢሆን መሲሑ # ኢየሱስ ነው፡፡ ስለ ሰው ማንሣታችን ባይቀርም (በወንጌል የሚድነው ሰው ነውና) ስለ ድነት በረከቶች መዘርዘራችን ቢጠቅምም፣ የወንጌል አንጽሮት (focus) የኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነትና ጌትነት ነው፡፡ ወንጌልን የምንሰብከው ሌላ አማራጭ ስለሌለ ነው፡፡ የሰው ልጅ ወዲህም ወዲያም መፈናፈኛ በሌለው ሁኔታ ላይ ወድቋል፤ ከየትም ፍልስፍና (ሃይማኖት) የተመዘዘ የመዳን ክር የለም፡፡ # ክርስትና አጥላይ (exclusive) እምነት ነው፡፡…መንገዶች ሁሉ ወደ ሮም ቢወስዱም፣ የሕይወት መንገድ ግን አንድ ብቻ ነው፡፡ ‹‹በእኔ በቀር›› የሚለው የጌታችን ግልጽ ንግግር ደባል ለማስተናገድ አይመችም!”.....(“ወቅታዊ ዘላለማዊ”፣ 24
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

ዲዮጋን ከዕለታት አንድ ቀን መብራት አብርቶ ከገበያው መካከል ገብቶ ውድያና ወዲህ ሲመላለስ አንድ ግብሩን የሚያውቅ ሰው ቀርቦ "ዲዮጋን! ዛሬስ በቀትር ጊዜ መብራት ይዘህ በገበያ መካከል ትዞር ጀመር? ለምንድነው?" ቢለው።
"ሰው ጠፍቶብኝ እፈልጋለሁ" አለው ዲዮጋን። "ይህ የምታየው ሁሉ ሰው አይደለምን?" ቢለው፣ "አይ! እኔ ይህ እዚህ የሚታየው ሕዝብ ሁሉ ሰው አልለውም" ዲዮጋን መለሰ። "እንዴት?" ቢለው፣ "ይህ የምታየው ሕዝብ ሁሉ ከእውነት የራቀ ሐሰትን ያጸደቀ የራሱን ጥቅም ያወቀ ለግል ምኞቱ የሚገዛ የሰው አካል የለበሰ ውስጡ ከእንስሳዎች ያነሰ ስለሆነ ሰው አልለውም" አለው።
"ታዲያ፣ አንተ የምትፈልገው ሰው እንዴት ያለ ነው?" ቢለው። ዲዮጋንም አለ "የግል ጥቅሙን የማይሻ ሰውን እንደራሱ የሚያይ ሐሰትን የጠላ ለእውነት ያደላ ሲሆን ነው::"
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

“በወንጌል አላፍርም” (፫)

በመጋቢ ሰሎሞን አበበ ገ/መድኅን
***

በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አረዳድ መሠረት፥ የወንጌል ይዘቱ እንደሚከተለው ሊተነተን ይችላል። ከመጀመሪያው እግዚአብሔር ዓለሙን በክርስቶስ ለማዳን ዐቅዷል (1ቆሮ. 2፥7፤ ሮሜ 16፥25)። ይኸን የማዳን ዓላማውን በነቢያቱ በኩል አስቀድሞ አስታወቆ ነበር (ሮሜ 1፥2፤ 16፥26)። በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነትም አጽንቶታል (1ቆሮ. 15፥3-4፤ ገላ. 3፥8)። የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም ላከ (ገላ. 4፥4-5)። በመስቀል ላይ ሞቱና በትንሣኤው ኀይል ዓለሙንና ሰውን ባዳነው በአንድያ ልጁ በኩል (ሮሜ 1፥3-4፤ 15፥8፤ 2ቆሮ. 1፥20) ተስፋው ተፈጸመ።
.

እስከ ልጁ መምጣት ድረስ አይሁድና አሕዛብ የእግዚአብሔርን የአድኅኖት ፈቃድ በመሳትና ባለማወቅ ሲባዝኑ ኖረዋል። አኹን ግን፥ በልጁ መገለጥ፥ ወንጌሉ ስለ ተበሠረ ሕይወትና አለመጥፋት ወደ ብርሃን ወጥቷል። ለሚያምኑ ኹሉ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ኾኖ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቋቸዋል። ስለ ኾነም፥ በልጁ በኩል የተገለጠው የእግአዚብሔር ዋና የማዳን ፈቃድ በወንጌሉ መልእክት ተጠቃሎ ቀርቧል ማለት ነው። ያለ ልጁ ወንጌሉ የለም። ይኸውም ወንጌሉ የስቁሉ የእግዚአብሔር ልጅ መልእክት ወይም የምሥራች ነው (1ቆሮ. 1፥17፤ 2፥3)። በልጁ ሕማምና ትንሣኤ እግዚአብሔር የአድኅኖት ፈቃዱን በመግለጥ የማዳን መልእክቱን እንዲያውጁ ሐዋርያቱን ላከ። ወንጌል የሐዋርያቱን የስብከት አገልግሎት ዐዋጅ የሚቈጣጠርና ራሱንም እንደ ፍጻሜ ዘመን የእግዚአብሔር የማዳን ኀይል የሚገልጥ ነው። በቀጥታም ለሰው ዘር ኹሉ “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ” (2ቆሮ. 5፥20) የሚል ልመና ያቀርባል።
.

በመኾኑም፥ ወንጌል አማራጭ የሌለውና ብቸኛው መፍትሔ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ኀይል ነው (ሮሜ. 1፥16)። የትኛውም ዘዴ፥ ማንኛውም የመልእክት ዐይነት፥ የማንም ተቋምና አቋም ሰዎችን ሊያድናቸው አይችልም። ለሙታን ሕይወትን የሚሰጥ ጸጋ በክርስቶስ ወንጌል ብሥራት በኩል በእምነት ለሚቀበሉት ይገለጣል። በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ የሚያመጣው የእግዚአብሔር ኀይል ብቻ ነው፤ ይኸም ኀይል በወንጌል በኩል ይገኛል። በዚህ ወንጌል እግዚአብሔር መላለማዊ ክብርን ለራሱ ይወስድ ዘንድ ዘላለማዊ ዓላማውን በተደላደለ መሠረት ላይ አኑሯል። አይለወጥም፤ አይናወጥም።
.

ወንጌል የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት፥ አገልግሎት፥ ሞትና ትንሣኤ ብሥራት ጭምር ሲኾን የሚያምኑበትን ደግሞ ድኅነት እንደሚሰጣቸው የሚያሳስብ ነው። ኹሉ እስኪታደስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ በክብር ያረገው ልጁ በዘመን መጨረሻ ትፍጽምት ይደረግ ዘንድ ባለው ዳግመኛ መምጣቱ የማዳን ታሪክን ይደመድማል። ተመርቆ የተከፈተው የዐዲስ ፍጥረት ሥርዐትም ፍጻሜውን ያገኛል። እግዚአብሔር ኹሉን ለራሱ የሚያስገዛበት የመንግሥቱ ሥፋኔ የሚጠናቀቀው በወንጌል አሸናፊነት ነው። ስለኾነም ስበኩት። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፤ አሊያም ጥፉ።
.

ስለኾነም፥ ወንጌሉን አትነካኩት፤ አታድበስብሱት። የጸናውንና አንዱን ወንጌል በመጨመር፥ በመቀነስም ይኹን በመሸፋፈን አትነካኩት። ያንን ማድረግ በተሞከረ ጊዜ የሰውን ሕይወት ከመፈወስ ይልቅ ማቍሰልን ያስከትላል። ቤተ ክርስቲያንንም ይበጠብጣል።
.

“ኹልጊዜም ቢኾን፥ ወንጌልን ለማጣመም መነካካት ብጥብጥን ወደ ቤተ ክርስቲያንን ያመጣል። ወንጌልን ነካክተህ ቤተ ክርስቲያንን ሳታቈሥል መተው አትችልም፤ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረችውም ኾነ የምትኖረውም በወንጌል ነው። በርግጥ፥ ዛሬም እንደ ጥንቱ፥ የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ችግር ፈጣሪዎች ከውጭ ኾነው የሚቃወሟት፥ የሚየሳድዷትና የሚሣለቁባት ጠላቶቿ ሳይኾኑ በውስጧ ተቀምጠው ወንጌልን ለማጣመም የሚሞክሩቱ ናቸው። አዎ፥ እነርሱ ናቸው የሚበጠብጧት። በአንጻሩም፥ ጥሩ የቤተ ክርስቲያን ሰው የመኾን ምስጢሩ ጥሩ የወንጌል ሰው መኾን ነው። ቤተ ክርስቲያንን የማገልገል ምርጡ መንገድ ደግሞ በእውነተኛው ወንጌል ማመንና እርሱን መስበክ ነው።" (Stott, "The Message of Galatians", s 23.)
.

እናም "ወንጌልን ባ[ን]ሰብክ...." (1ቆሮ. 9፥16) እናንተው ጨርሱት
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

ኢየሱስ ታቦቴ!
የጥምቀት በዐሌ ዛሬና ትናንቴ
ዐውደ ዓመቴ ኢየሱስ እስከለተ ሞቴ
ታቦቴ ታቦቴ ኢየሱስ ታቦቴ
ማደሪያ የሆንኸኝ የዘላለም ቤቴ።
ወደ አብ ገባሁኝ በአንተ በኩል
አባትህን አየሁት በፊትህ ጸዳል
እከተልሃለሁ ግራ ቀኝ ሳልል
ብርሃኔ ነህና የሕይወቴ አክሊል።
ደምህ ድፍረቴ ነው የምሰብከው ጸጋ
ባንተ ጋሻነት ነው ከጠላት ምዋጋ
እንዳልጠራጠር ፍጹም እንዳልሰጋ
በደምህ ተከፍሏል ታውቋል የኔ ዋጋ።
ምንጣፌን አንጥፌ በመንገዱ ሁሉ
እማሆይ አቡሃይ ምንም እልል ባይሉ
የደምህ ጉልበቱ የመስቀልህ ኀይሉ
ያለ መጋረጃ እስኪታይ ለሁሉ
ኢየሱስ ታቦቴ እስኪታይ ለሁሉ
ስምህን ያላወቁ ያላመኑህ ካሉ
ለሁሉ እሰብካለሁ አሜን እስከሚሉ።
ሌሊቱ ቢነጋ ቀኑ ቢመሽብኝ
የጽድቅ ፀሐየ አንተ ስላለኸኝ
መንገዶችን ሁሉ አዳርሳለሁኝ
ማዳንህን እያወጅሁ ባገኝ የሚሰማኝ።
ፈጽሞ እስኪጨልም የሰይጣን ፀሓዩ
ያላወቁህ ሁሉ ክብርህን እስኪያዩ
በክብርህ እስኪናጥ ምድርና ሰማዩ
እንሰብክሃለን ሰዎች ቢለያዩ።
ዩኔስኮ ባያውቅህ ባይመዘግብህ
ቱሪስቶች ከሩቁ ባይመጡ ሊያዩህ
በሰማይ በምድር ሙሉ ነው ክብርህ
ያለ ልክ አክብሮህ ልዑሉ አባትህ።
ሰው ሣይሸከምህ ሁሉን ተሸካሚ
የሁሉ መድኀኒት የበሽተኛ አካሚ
በአብ ቀኝ ሆነህ ሁሌም አይሃለሁ
ባመት በዓል ሳይሆን ሁሌ አከብርሃለሁ።
ዮርዳኖስ አልሄድም ጸጋህን ፈልጌ
ደብረ ታቦርንም አልናፍቅም እኔ
ዮርዳኖስ ሆኛለሁ ባመንሁህ ሰአት
ደብረ ታቦርህም የክብርህ ታቦት።
ውድ መጋረጃ አይሸፋፍንህም
የሚያንጸባርቀው ክብርህን አያልፍም
ሥጋ ለባሽ ካህን አይሸከምህም
አንተ በአብ ቀኝ ነህ ነግሠህ በከፍታ
ክብርህ ለማወጅ ከበሮየን ልምታ።
መለከት ይነፋ ይታወጅ ክብርህ
በአብ ቀኝ ያለኸው ማንም አይመስልህ
ብቻህን ሞተሃለል አንዱ ስለ ሁሉ
ባንዱ ባንተ ሞትም ሁሉም ይድናሉ።
ከዚህ የተለየ እንቶ ፈንቶ ስብከት
ቢሰበክ በመድረክ በዐውደ ምሕረት
አልሰማም አላምንም አልቀበለውም
ኢየሱስ ያላንተ መዳን አይቻልም።
ጥምቀቴ ጥምቀቴ ደማቁ በዓሌ
መስቀሌ መስቀሌ የማከብርህ ሁሌ
ታቦቴ ታቦቴ ማደሪያየ ሆንኸኝ
ኢየሱስ አንተ ነህ ሁሉን ያስረሳኸኝ
ዘና ብየ ልኑር ያለ ስጋት ልኑር ዋስና ስላለኝ።
#✍ዘርፌ ከበደ
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

.==="ወንድምህ ወደየት አለ?"===

በመጋቢ ሰሎሞን አበበ ገ/መድኅን
**
Part two
እንግዲያስ፥ ለሰው ልጅ ሕይወት ግድ የመሰኘት ኀላፊነታችንን እንወጣ። ሰብአዊ ክብር (human dignity) እና ንጽሐ ሕይወት (sanctity of life) ወርቃማ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖዎች ናቸው። የጌታችንም ትምህርት ይችው ናት፤ "እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ኹሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና" (ማቴ. 7፥12)።

.
ዓለሙ ግን በሁከትና ትርምስ ተሞልቷል። ሰው የራሱ ጠላት ኾኖ ሲጠፋፋ እዘመናችን ደርሷል። በሰበብ አስባቡ የሰው ልጅ ሕይወት እንደ ሙጃ ይታጨዳል። ቢቻለንስ ከሰው ኹሉ ጋር በሰላም እንኑር፤ በቻልነው ኹሉ፥ ለከበረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሕ እንገዛ። የሰውን ዘር ከሰው ዘር እናድን። እንግዲያውስ ወንድማችንን እንፈልገው፤ የሰው ሕይወት መነካት ይጐፍንነን።
.

“ብሔራዊና መንፈሳዊ ውድቀት በበዛበት ዘመን ተነሥተው የአገርን ታሪክ የለወጡ ሰዎች በነበረው ፍትሕ አልባነትና ሥርዐት መጓደል ላይ የጽድቅ ቍጣ (indignation) ያደረባቸው ሰዎች ነበሩ። የእግዚአብሔርን ክብር የሚዳፈር በአምሳሉ የተፈጠሩ የሰው ልጆችን የሚያዋርድ ሥርዐት ተዘርግቶ በማየታቸው ቍጣቸው ነደደ። ዊልበር ፎርስ የተባለውን ሰው የነጻነት እንቅስቃሴን እንዲያቀጣጥል ያነሣሣው ምክንያት ሰዎች እንደ ዕቃ ሲሸጡና ሲለወጡ መመልከቱ ያሳደረበት ቅዱስ ቍጣ ነበር።” (J. Oswald Sanders, "Spiritual Leadership")
.
Stand for human dignity and sanctity of life!
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

የማለዳ እንጀራ
"Egziabeheren Mefeleg "
Part 7
@ElOLAM_ElOLAM

Читать полностью…

Coram Deo

ብዙ መንፈሳዊ ርዕሶች ዳስሳለች አንብቧት።

📔ርዕስ፦ያልተንኳኩ በሮች
👤ደራሲ፦ ጳውሎስ ፈቃዱ 📑የገጽ ብዛት:-168
አስተማሪ የአጫጭር ጽሁፎች ስብስብ ነው። ዘና እያሉ ቁም ነገር ይጨብጡ። ጳውሎስ የመጻፍ ችሎታውን ያስመሰከረበት ምርጡ መጽሐፍ ነው።

Читать полностью…

Coram Deo

ብዙ መንፈሳዊ ርዕሶች ዳስሳለች አንብቧት።

📔ርዕስ፦ያልተንኳኩ በሮች
👤ደራሲ፦ ጳውሎስ ፈቃዱ 📑የገጽ ብዛት:-168
አስተማሪ የአጫጭር ጽሁፎች ስብስብ ነው። ዘና እያሉ ቁም ነገር ይጨብጡ። ጳውሎስ የመጻፍ ችሎታውን ያስመሰከረበት ምርጡ መጽሐፍ ነው።

Читать полностью…
Subscribe to a channel