emislene | Unsorted

Telegram-канал emislene - Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

-

ይህ ይፋዊ የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው፡፡ በዚህ ገጽ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡ - የቅድስት ቤተክስቲያናችን እና የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እናደርስበታለን፡፡ ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡ @EMislene_28Bot

Subscribe to a channel

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🎙የገቢ ማሰባሰቢያ መዝጊያና የምስጋና መርሐግብር ተካሔደ።
    
      በነበረው የኪነ ጥበብ ምሽትም ለህጻን ነብዩ ዮናስ ሲደረግ የነበረው የልግስና መርሐግብር በይፋ ቆሟል። ለሕክምና የሚያስፈልገውን ሙሉ ወጪም ተሰብስቧል። እግዚአብሔር ይመስገን ከማለት ውጪ ምን እንላለን።

እግዚአብሔር ልጃችንን ጨርሶ ይማርልን።በሰላም ድኖ ይመለስል ዘንድም ዘወትር በጸሎታችሁ ኃይለ ማርያም እያላችሁ አስቡት።

ሁላችሁንም በቅዱስ አማኑኤል ስም እናመሰግናለን።

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!!

/channel/EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

✨✨ምኩራብ ✨✨
የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት

ምኩራብ ማለት ቤተ-ጸሎት ሲኾን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ቀን ከአይሁድ ምኩራብ ገብቶ ቢመለከት ምኩራቡን ገበያ አድርገው ሲገበያዩበት አገኛቸው።

"ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል" ያለውን አላነበባችኹምን?
ትንቢተ ኢሳይያስ ፭፮፥፯
እናንተ ግን ገበያ አደረጋችኹት በማለት በተናቸው! ዕቃውንም ገለባበጠባቸው በሮቹንም፣ በጎቹንም በገመድ እየገረፈ አባረራቸው። የዮሐንስ ወንጌል ም. ፪፥፩፯ (ማቴዎስ ፪፩፣፩፫)

🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
https://youtu.be/qprpfEqVSG4
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

የአብርሃም አምላክ

የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ /2/
ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ /2/

የሀሰት ምስክር አቁመው ከሰሱት /2/
በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት/2/

ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ /2/
ከሮማዊው መንግስት እንዲኖር ተባብሮ/2/

ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ/2/
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ/2/

በብርሐን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ/2/
በችንካር ላይ ቆዩ ምንም ሳይሰለቹ/2/

የብርሐን አክሊልን ለሰማዕታት ያደለ/2/
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ።/2/

🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.comS/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📖ጾም በአንተ ውስጥ የሆነ አንድ ነገር መለወጡን ተመልከት!!!

      ከጾም የምታገኝው ነገር የምግብ ለውጥ  መሆኑን ብቻ አትመልከት ። ለተሻለ ህይወት  የሚደረግ ለውጥ መሆኑን ተመልከት ።

ይህም ማለት በአንተ ውስጥ ያለ ጉድለትንና በውስጥህ እንዳለ የሚሰማህን ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር የሚሆን ድክመት ተመልከት ማለት ነው ። ይህ ሳይሆን ከቀረ በሃምሳ አምስቱ የሁዳዴ ጾም ቀናት ውስጥ ራስህን አሸንፈህ ከቆየህ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር የፍቅር ዝምድና እና የተረጋጋ ግንኙነት ሳትፈጥር ከጾሙ  አስቀድሞ የነበረህን አቋም ሙሉ ለሙሉ  ይዘህ ለመውጣት ከሆነ የነፍስህ ጥቅም ምን ሊሆን ነው ❓

  አንተ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳታመጣና አስቀድመህ በነበርክበት ሁኔታ ውስጥ እያለህ እስከ አሁን ድረስ ስንት አጽዋማት እንዳለፉህ አስብ !!

በሁሉም አጽዋማት ውስጥ ፈቃድህ
ደካማ ጎንህን ለማሸነፍ ስኬታማ እንድትሆን  አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር እንድትታረቅ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም የእርሱን ፈቃድ ጣፋጭነት እንድትቀምስ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖርህ ዝምድና እስከ አሁን ድረስ እንደምን የሰፋና የጠለቀ ይሆን ነበር❓
እስከ አሁን ድረስ እንደምን የሰፋና የጠለቀ ይሆን ነበር !!
  
       ስለዚህ ንስሐ በመግባት ጾምህን ጀምር ። ጾምህን በጸሎት በምጽዋት በስግደት በመንፈሳዊ ንባባት በቅዳሴ በኪዳን ጸሎቶች አጅበው ። እነዚህን ሁሉ በማድረግህ ከእግዚአብሔር ጋር ትወዳጃለህ ጾም የያዛቸው በረከቶች ብዙ ናቸውና ። እነኚህን ካደረክ በመጨረሻ ላይ ውጤቱን ከአምላክህ ትቀበላለህ ።

✍አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

http://t.me/Emislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📌 የማየ ሕይወት ቅጽ 2 ዲጂታል መጽሔታችንን እነሆ!!!

በተጨማሪም ከዚህ በፊት የተዘጋጁትን

👉ማየ ሕይወት ዲጂታል መጽሔት ልዩ እትም

👉ማየ ሕይወት ቅጽ 1 ዲጂታል መጽሔት

በዚሁ በቴሌግራም ቻነላችን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📌ለ 2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈተኞች በሙሉ

የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕጻናትና ማዕከላዊያን ክፍል ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ የሚሆን ለብሔራዊ ፈተና የሚያዘጋጃቸውን የማጠናከሪያ ትምህርት (Tutorial Class ) አዘጋጅቷል።

    📅  ሐሙስ መጋቢት 12 / 2016 ዓ.ም

              🕐 ከ 10፡ 45 ጀምሮ

         🏘 በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል
                     ጠበል ቤት አዳራሽ 


   "ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

✈️መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም

🗓ለትንሳኤ ምዝገባ ተጀምሯል።
(ከሚያዝያ 22- ግንቦት 5)

- የታደሰ ፓስፖርት ፣ 2 ከለር  ፎቶ ግራፍ

- 90,000 ብር (ለትኬት ፣ ለቪዛ ፣ለመመዝገቢያ ፣ ለጉዞ ኢንሹራንስ )
     እና

- 2375 USD ዶላር ኢየሩሳሌም ሲደረስ የሚከፈል ( ለ ሆቴል ፣ለምግብ ፣
ለትራንስፖርት ፣ለአስጎብኚና ጉብኝት ቦታ፡ ለመጠመቂያ ልብስ የሚከፈል)

አዘጋጅ :- የ/ደ/ገ/ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ከ ዮድ አቢሲኒያ አስጎብኚ እና የጉዞ ወኪል ጋር በመተባበር

📞ስልክ :- 0921899103
                 0946817753
                 0913734590
                 0910067211 


🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtu.be/HO6OSol2yuU

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtube.com/shorts/Beqqj0b2S8U?feature=share

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

✨ ልዩ የኪነ ጥበብ ምሽት ✨

#ነብዩ_ዮናስን_እናሳክመዋለን!

📌በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል 

  ከመልካም ተግባር ጋር የሕይወት ቃል እናድምጥ

📅 ሐሙስ መጋቢት 12 /2016

⏰  11፡30 ጀምሮ

📖 ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተሰቦች መልካም እናድርግ ገላ 6:10 

መግቢያ :- 200 ብር

- ትኬቱን ባሉበት ሆነው መቁረጥ ይችላሉ

ለበለጠ መረጃ እና ትኬት ለመቁረጥ በዚህ ይደውሉ :- 0912026223

ሙሉ ገቢው ለህጻን ነብዩ ዮናስ የሚውል
t.me/Emislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

✨✨ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ✨✨

🎙የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ሕጻናትና ማዕከላዊ ክፍል ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች በመደበኛ የአስኳላ መምህራንና ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ውጤት ባስመዘገቡ ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና የሚያዘጋጃችሁን የማጠናከሪያ ትምህርት አዘጋጅቷል።        

    
🗓  ዘወትር ሐሙስ

🕰 ከ 10:45  ጀምሮ
  
📪   በጠበል ቤት አዳራሽ               

አድራሻ : -  ከመሳለሚያ እህል በረንዳ ወረድ ብሎ/    
                ከመርካቶ ሰባተኛ ትንሽ ወረድ ብሎ

         "ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtu.be/o5w4wIwYnfU

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🎙ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የነፍስ ምግብ እንጂ

  👉አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ ።

👉ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም ጠባዩን ለመግራት እንጂ ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው ።

👉ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ ብቻውን አይጓዝም ።

👉ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ ።
       
👉 ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም ፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ ።

👉 ጾም ነፍስ ከፍ ብላ ሥጋን ከእርስዋ ጋር ከፍ የምታደርግበት ጊዜ ነው ።

  👉ይህ ጊዜ ሥጋ ጓዙንና ሸክሙን የሚያራግፍበት ጊዜ ስለሆነ እግዚአብሔር ያለ ምንም እገዳ ለመንፈሳዊ ዘላለማዊነት ደስታ የሚሠራበት ጊዜ ይሆናል ።

  👉ጾም ማለት ነፍስና ሥጋ በኀብረት መንፈሳዊ ተግባር ለማከናውን የሚጠቀሙበት ጊዜ ነው ።

👉በጾም ወቅት ነፍስና ሥጋ የነፍስን ሥራ ለመሥራት ይተባበራሉ ። ይህም ማለት ለጸሎት ለተመስጦ ለክብርና ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ለመጋራት ይተባበራሉ ማለት ነው ።

✍ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
እግዚአብሔር ምስሌነን መሰባሰባችን አንተው!


🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtu.be/wwm5aD82FrY

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📚የካቲት ፴ (30)

እንኳን ለታላቁ ነቢይ፣ ሰማዕት፣ ሐዋርያ ፣ካህን ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ሕግ አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ኄሮድስ እጅ አንገቱን ከተሰየፈ በኋላ አንገቱ ክንፍ አውጥታ በዓለም ላይ በመዞር ዐሥራ አምስት ዓመት አስተምራ ከዐረፈች በኋላ በዓረቢያ ምድር የከበረች ራሱ ለተገኘችበት በዓል በሰላም አደረሰን።

📎በዚያንም ወራት በገንዘብ ድኆች በሃይማኖት ባለጸጎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ እነርሱም ሊሰግዱ የከበረች የአርባ ቀን ጾምንም ሊጾሙ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዙ ይህም ከብዙ ዘመን በኋላ ነው። ምሽትም በሆነ ጊዜ ምድረ በዳ በሆነ በኄሮድስ ቤት ውስጥ አደሩ ቅዱስ ዮሐንስም ከእርሳቸው ለአንዱ በሕልም ተገለጠለትና የከበረች ራሱ ያለችበትን ቦታ አስረዳው ወደቤቱም ተሸክሞ ይወስዳት ዘንድ አዘዘው በነቃም ጊዜ ራእይን እንዳየ ለባልንጀራው ነገረው። ቅዱስ ዮሐንስም ወደአመለከተው ወደዚያ ቦታ ተነሥተው በአንድነት ሔዱ በቆፈሩም ጊዜ

👉ሙሉውን ያንብቡ

ከመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtu.be/yBql8GT5IPg

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtu.be/EBm0iIlmweE

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📌ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ           

            ✨ 2ኛ ዙር ሴሚናር ✨
                      
   የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ሕጻናትና ማዕከላዊያን ክፍል ከመምህራንና ከቀድሞ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ ልምድና ለጥያቄዎቻችሁ መልሶችን የምታገኙበትን መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።

  📋
እሑድ      

🗓            
         መጋቢት 15     

  🕰             
                       ከ8:00 ጀምሮ  

⛪️ በሰንበቴ አዳራሽ እንገናኝ።


"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ነገ በተቀጣጠርነው መሠረት እንዳይቀሩብን አደራ!

#Live
#ነብዩ_ዮናስን_እናሳክመዋለን
#መጋቢት_12
t.me/Emislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

"እግዚአብሔርሰ ገሐደ ይመጽእ "
                   መዝ 49፥2

👉እግዚአብሔር አምላካችን ኃያል ነውና አዳምን እና ሔዋን በቃሉ ማዳን እየቻለ  መሰቀል(ስቅለት) ለምን አስፈለገው❓

👉ጾም እስከ ስንት ሰዓት ሊጾም ይገባል❓

👉የዐቢይ ጾምን እንዴት እናሳልፍ❓

👉የሳማ ብሔረ ሕያዋን እግዚእ ለሰንበት
ቤተክርስቲያን (ሳማ ሰንበት) ታሪክ

👉ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ሳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመስቀሉ እግር ቆማ ስለእርሱ ያለቀሰችውን ልቅሶና የተሰጣት ቃልኪዳን

👉ነገረ ምጽአት

👉ጥንተ ስቅለት

👉የእግዚአብሔር ቸርነት ምሕረትና ዘለዓለማዊ እውነት

👉ምክረ ሰናይ

👉ተረት ተረት

👉የመዝሙር ግጥም

👉ስነጽሑፍ፡ የመጽሐፍ ጥቆማና  ሌሎችንም

📌 💻 ዛሬ ማታ በቅጽ 2 ዲጂታል መጽሔታችን ይጠብቁ። 📱

"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

በዩቲዩብ የምትከታተሉን በሙሉ እናመሠግናለን

📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

  "ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📖ልቡናውን ሰብስቦ መጸለይ አልችል ያለው ሰው አንድ ታላቅ አባትን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው ፦ "አባቴ! የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ሳነብ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፡፡ አፌ ቢያነብም ልቡናዬ አይተረጕምም፡፡ እርስዎ እንደነገሩኝ ደግሞ ቅዱሳን በፍጹም አሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የደረሱትን እኛ በልባችን ሌላ እያሰብን በአፋችን ብቻ እንደነርሱ ብንናገር እንደ ገደል እንደ ዋሻ ሆነን በእግዚአብሔር እንደመቀለድ ነው፡፡ ጸሎትም አይሆንልንም፡፡ እንግዲህ ያፍ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል ? "

    እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ "ዕውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው ድምጹን ሰምቶ ይመታኛል ብሎ እንደሚሸሽለት ሁሉ አንተም አስተውለህ ባትጸልይም ባፍህ ውስጥ የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት እየሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና ምንም ቅድመ እግዚአብሔር ባይደርስም ጸሎትህን አትተው፡፡ አጋንንትን ማባረርም ጥቅም ነውና፡፡ ብዙ ከምትጸልየውም አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ትደርሰልሃለች ምንም ዝርወ ልብ ብትሆንም አፍህም ፍጥረቱ ነውና አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ እንዳትሆን ባፍህም ብቻ ቢሆን መነጋገሩን አትተወው፡፡"

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሐ እስከምትገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሐ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት እራሱ እውነተኛ ንስሐ መግቢያ በር ነው። "

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ


የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

✞ ዐብይ ጾምን እንዴት እንጹም? ✞

አባ ሱርኤል የተባሉ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህን የጻፉት "A Practical Journey through Lent" የሚል መጽሐፍ አለ። መጽሐፉ እጅግ ትንሽ ሲሆን፥ የዐብይ ጾምን በምንጾምበት ወቅት ሊረዱን የሚችሉ ነጥቦችን ያስቀምጣል። እነዚህን ነጥቦች እንመልከት።

ዐቢይ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ከፍተኛውን አጽንኦት የሚሰጠው ጾም ነው። አባ ሱርኤል ሲገልጹትም "ዓመቱን ሙሉ የሚዘልቅ መንፈሳዊነትን ስንቅ አድርገን የምንይዝበት ጾም ነው" በማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ "እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።" [ፊል 3:10] እንዳለው ሁሉ፥ እኛም በዚህ የጾም ወቅት ክርስቶስን በሚገባ የምናውቅበት እንዲሆንልን መጣር ይኖርብናል።

- ጊዜያችሁን መንፈሳዊ መጽሐፍት ለማንበብ እና ለመጸለይ ተጠቀሙበት።

መልካም ጾም ለሁላችን!

  "ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ጌታ ሆይ

ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን ሰቀሉህ ወይ
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ /2/

የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመስቀል
የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት  /2/

ንጹሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ ብለህ ስለኛ
መስቀል አሸክመው አስረው ገረፉህ እያዳፉህ  /2/

ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ /2/

እጅና እግርህ በችንካር ተመታ የዓለም ጌታ
የሾህ አክሊል ደፋህ ጎንህም ተወጋ አልፋ ኦሜጋ /2/

በመስቀል ላይ ተጠማው ስትል ታላቅ በደል
ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው /2/

ይቅር ባይ ግልጽ በደላችን ሁሉን ሳታይ
አንተ ይቅር በለን በኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2/

የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

✨እንኳን ተአምራታቸውና ትሩፋታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት ለበዛ የእግዚአብሔር ማደርያ ተጋዳይ ለሆኑ በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን ለለመኑት ለታላቁ አባት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
                                     
📖አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
                                   
   የአባታቸው ስም ስምዖን ፣የእናታቸው ደግሞ አቅሌስያ ይባላሉ። በደቡባዊ ግብፅ ይኖሩ ነበር።በትዳር ሲኖሩ ልጅ ባለመውለዳቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እየሄዱ ልጅ እንዲሰጣቸው ይጸልዩ ነበር ።

👉ሙሉውን ያንብቡ።

"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

✨ ጾም ማለት ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡ (ፍትሃ ነገስት አንቀፅ.15) “ጾምሰ ተከልኦተ ብዕሊ ዕምመብልዕ በጊዜ እውቅ” ጾም ማለት በታወቀው ዕለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡ መብል መጠጥ የኀጢአት መሠረት ነው በመብል ምክንያት ሞት በሰው ልጆች ላይ መጣ “ይችን ዕፀ በለስ ብትበሉ ሞትን ትሞታላችሁ” ዘፍጥረት 2፥17 ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጐመዥውን ነገር መተው ማለት ነው።

     መብል መጠጥ ከልክ ሲያልፍ ከተዘወተረም ከእግዚአብሔር ይለያል፤ “ያዕቆብ በላ ጠገበ ወፈረ ገዘፈ ደነደነ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ተወ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር ተለየ” ዘዳግም 32፥15-17 “የእግዚአብሔር መንግሥት መብልና መጠጥን አትሰብክም” ሮሜ 14፥16፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፥8-13 “ዛሬ የሚራቡ የሚጠሙ ብፁአን ናቸው ይጠግባሉና ማቴዎስ 5፥6 ጾም የሥጋ መቅጫ ነው፤ “ነፍሴን /ሰውነቴን/ በጾም ቀጣኋት መዝሙር 68፥10 ጾም በነቢያት የተመሠረተ በክርስቶስ የጸና በሐዋርያትም የተሰበከና የተረጋገጠ ለክርስቲያኖች ዲያብሎስን ድል የምንነሣበት መንፈሳዊ የጦር ዕቃ ነው፡፡

        ስለዚህ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንደምታስተምረን ይህን ጾም ከምግብ ለመከልከል ጋር ጸሎትን፥ ስግደትን፥ ምጽዋትንና የንስሐ ዕንባን ጨምረን እንጹመው፡፡ ጌታችንና ነቢያት፣ ሐዋርያት የተውልን መንፈሳዊ መሣሪያ ነውና።

    ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጾም የጾመው ለአብነት፣ ለማስተማር፣ ለአርዓያ ነው፡፡ በዚህ ታላቅ ጾም ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ፣ ከሰው የሥጋ ጠባይ የሚመጣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ድል የተነሱበት ነው፡፡ እኛም ይህን እያሰብን በተለያየ መንገድ የሚመጣብንን ፈተና ለማራቅ ከዚህ ታላቅ ጾም በረከት እንድናገኝ እንጾማለን፡፡ ጸልዮ ጸልዩ፣ ጾሞ ጹሙ ብሎናል፡፡ ማቴዎስ 6፥16 ስለዚህም ትእዛዙን ለማክበር እንጾማለን።

✨የዚህ ታላቅ ጾም ስያሜዎች፦

👉ዐቢይ ጾም
የባሕርይ አምላክ በሆነዉ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ ወይም ታላቅ ጾም ይባላል።

👉ጾመ ሁዳዴ
በጥንት ጊዜ ገባሮች ለባለ ርስት የሚያርሱት መሬት ሁዳዴ ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ እኛም ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰብን የምንጾመው በመሆኑ ጾመ ሁዳዴ ተብሏል።

👉የካሳ ጾም
አዳምና ሔዋን ከገነት የተባረሩት ለውርደት ሞት ለሲዖል ባርነት የበቁት በመብል ምክንያት ነው፡፡በመብል ምክንያት የሞተውን የሰው ልጅ ጌታችን በፈቃዱ በፈጸመው ጾም ካሰው፤ መንፈሳዊ ረሃብን በረሃቡ ካሰለት፡፡ ስለዚህም የካሳ ጾም ተባለ።

👉የድል ጾም
አርዕስተ ኃጣውእ /ማቴዎስ 4/ ድል የተነሱበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል.

👉የመሸጋገሪያ ጾም
ጌታችን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሊያሸጋግረን የጾመው ጾም በመሆኑ የመሸጋገሪያ ጾም ተብሏል።

👉ጾመ አስተምህሮ
ጌታችን የጾመው ለትምህርት ነው፡፡ እርሱ መጾም ያለበት ሆኖ አይደለም፡፡ ስለዚህም ይህ ጾም ጾመ አስተምህሮ ይባላል፡፡ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ። ማቴዎስ 4፥2

👉የቀድሶተ ገዳም ጾም
ጌታችን ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ በመጾም ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ በብሕትውና መኖርን ቀድሶ የሰጠበት፣ የመጥምቁ ዮሐንስና የነቢዩ ኤልያስን ገዳማዊነት የባረከበት በመሆኑ የቀድሶተ ገዳም ጾም ተብሏል።

👉የመዘጋጃ ጾም
ሕዝበ እሥራኤል የፋሲካውን በግ ከመመገባቸው በፊት ዝግጅት ያደርጉ ነበር፡፡ እኛም ትንሣኤን ከማክበራችን፣ ሥጋና ደሙን ከመቀበላችን በፊት በጾምና በጸሎት ዝግጅት የምናደርግበት በመሆኑ የመዘጋጃ ጾም ተብሏል።

👉የሥራ  መጀመሪያ ጾም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ሥጋ ለብሶ በምድር ሳለ ስብከት፣ ተዓምራት ከመጀመሩ በፊት የጾመው ጾም ነውና የሥራ መጀመሪያ ጾም ይባላል።


የበረከት ጾም ያድርግልን። በሰላም አስፈጽሞ በቸርነቱ ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን አሜን።


የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

✈️መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም

🗓ከ መጋቢት 26 እስከ ሚያዝያ 5
ለ ደብረ ዘይት (ምዝገባ ተጀምሯል)።

- የታደሰ ፓስፖርት ፣ 2 ከለር  ፎቶ ግራፍ

- 85,000 ብር (ለትኬት ፣ ለቪዛ ፣ለመመዝገቢያ ፣ ለጉዞ ኢንሹራንስ )
     እና

- 1650 USD ዶላር ኢየሩሳሌም ሲደረስ የሚከፈል ( ለ ሆቴል ፣ለምግብ ፣
ለትራንስፖርት ፣ለአስጎብኚ ጉብኝት ቦታ የሚከፈል ፣ የመጠመቂያ ልብስ)

አዘጋጅ :- የ/ደ/ገ/ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ከ ዮድ አቢሲኒያ አስጎብኚ እና የጉዞ ወኪል ጋር በመተባበር

📞ስልክ :- 0921899103
0946817753
0913734590
0910067211 


🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🎙ሰንበት ት/ቤታችን 70 የሚሆኑ  የደቂቅ ክፍል ህጻናትን ለመጀመሪያ ጊዜ በየካቲት 30 2016 ዓ.ም ወደ ቀዳማይ ክፍል አዘዋውሯል።

   በዕለቱ የህጻናቱ ወላጆች የተገኙ ሲሆን ህጻናቱም ዝማሬና ሌሎች  ልዩ ልዩ መርሐግብራትን አቅርበዋል።

🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene

የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ

ዘወረደ

የመጀመሪያ የዐቢይ ጾም መግቢያ እሑድ ዘወረደ /ጾመ ሕርቃል/ ይባላል፡፡

«ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡  አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤  ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት  የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት   ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባው ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ”ገላ 4፥4 እንዳለ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የጠፋውን አዳም ፍለጋ ከአባቱ ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መውረዱን የምናዘክርበት ነው።

      ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ጾመ ሕርቃል ተብሎም ይጠራል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው ፡፡ ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም  ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፥ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው።


🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene

የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📚ዝክረ ቅዱሳን (የካቲት 29)

እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ በአጤ (ዐፄ) ሱሱንዮስ አንገቷን ተሰይፋ ሰማዕት ለሆነችና ታላቁን ገዳም ራማ ኪዳነ ምሕረትን ላቀናች ለታላቋ ለጻድቅ ወሰማዕት ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ (እመ ምዑዝ) ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን (የካቲት 29) ።

         📎... በዚህም ጊዜ  እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሱስንዮስ በአደባባይ ሲያስገርፋቸው ሥጋቸው እየተቆራረጠ መሬት ላይ የወደቀውን የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ሰብስባ "ይህን ለንጉሡ እጅ መንሻ ስጡልኝ" ብላ ላከችለት፡፡ ይህን ጊዜም. ...

👉ሙሉውን ያንብቡ

ከእናታችን ከቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን። በጸሎቷም ይማረን!።

Читать полностью…
Subscribe to a channel