የዚህ ዓለም ሰዎች "ፍሩን፣ አክብሩን፣ አመስግኑን" ብለው ደጅ ይጠናሉን? እንዲህ ቢያደርጉስ ሰው ሁሉ የሚስቅባቸው የሚሳለቅባቸው አይደለምን? ታድያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ክርስቲያን ምስጋናው ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም" (ሮሜ. ፪፥፳፱) ብሎ አስተምሮን ሳለ ክርስቲያኖች ነን የምንል እኛ ለምንድነው ሰዎች እንዲያደንቁን የምንፈልገው? ለምንድነው ከእግዚአብሔር ይልቅ ከሰዎች ምስጋናን የምንሻው?
✍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📌 የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
📌 የዩቲዩብ ቻናል፡
http://youtube.com/
@EMislene
📚ከመደርደሪያችን
የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የመጽሐፍ ዳሰሳ አዘጋጅቷል።
🗓ሐሙስ ኅዳር 5 - 2017 ዓ.ም
⏰ከምሽቱ 12:30
🪧በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
እንኳን ለዘመነ ጽጌ የመጨረሻ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ።
📌በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን የተፈጸመ ጽጌ ማኅሌትን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።
💻ዛሬ ማታ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ በዩቲዩብ ገጻችን ፤ የቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
🌸🌺🌹🌷💐🌸🌺🌹🌷💐🌸🌺
ባርከነ አማኑኤል አምላክ/2/
አማኑኤል አምላክ/4/ ባርከነ አማኑኤል አምላክ/2/
📷የአምላካችን አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በፎቶ።
ጥቅምት 28 -2017 ዓ.ም
በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
ቤተክርስቲያን ስንገባ ምን ማድረግ የለብንም???
ሥርዓት የሃይማኖት መገለጫ እንደመሆኑ ከመሠረቱ የምናምንባቸውን ተግባራዊ የምናደርግበት መንገድ ነው። ጸሎት ፣ ቅዳሴ፣ ቁርባን፣ ጾም፣ ስግደት እንዲሁም ሌሎች የሃይማኖት ምሥጢራትን ለመፈጸም በማመን ብቻ የሚያበቁ ሳይሆኑ የአፈጻጸምና አተገባበር መንገድ (ሥርዓት) ያስፈልጋቸዋልና፡፡
ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ከመግባታችን በፊት
"ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተክርስቲያን አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ምሳአል ወምስጋድ ወምሥተሠርይ ኃጢአት" ይህም ማለት "ልመና እና ስግደት የሚቀርብብሽ፣ የኃጢአት ሥርየት የሚገኝብሽ የኢየሩሳሌም ሰማያዊት አምሳያ የምትሆኚ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል።" ብለን መግባት አለብን።
በአሁኑ ጊዜ ሥርዓቱን እየተገበርን አይደለም ለምሳሌ: የቅዳሴ ሥርዓትን አቋርጦ መግባትና መውጣት፣ በትምህርተ ወንጌል በቅዳሴም እንዱሁም በሌሎች የጸሎት ሰዓታት ላይ ማውራትና ሌሎችንም አላስፈላጊ ተግባራት ማስተዋል ከጀመርን ቆየን።
ሥርዓቱን ማወቅ ሲገባ ግን የመተላለፋችን ምክንያት አንድም ሥርዓቱን ባለማወቅ ስለሆነ እያንዳንዱ ምእመን መጠበቅ ያለበትን ሥርዓት ማወቅና መተግበር ይጠበቅበታል።
http://t.me/EMislene
ገንዘብ ለማጠራቀም መነሣት አለባችሁ! ሥራ መሥራት አለባችሁ። በዚህ ዓለም ላይ ብዙ ኃይሎች አሉ፤ ከእነርሱ መካከልም አንዱ ገንዘብ ነው። ገንዘብ መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው። ሳትይዘው ስትቀር ደግሞ ባሪያ ያደርግሃል። መሥራት የምትችለውን እንዳትሠራ ያደርግሃል። ቤተ ክርስቲያንን ይይዛታል። ስለዚህ ሠርታችሁ ገንዘብ ሊኖራችሁ ይገባል። ገንዘብ መውደድ እና ገንዘብን ሠርቶ ማግኘት ልዩነት አለው። ሌብነት እና ስስትን እናጠፋዋለን። ስለዚህ ለሥራ መትጋት አለብን "ሊሠራ የማይወድ ሰው ቢኖር አይብላ! " ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ። መሥራትን የማይወድ ሰው መብላት እንደማይቻል እና እንደማይገባ ሲነግረን እንዲህ አለ።
ርእሰ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረኪዳን
http://t.me/EMislene
🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
እንኳን ለዘመነ ጽጌ 4ኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ።
📌በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን የዐራተኛ ሳምንት የጽጌ ማኅሌትን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።
🎬ምሽት 3፡30 ጀምሮ በዩቲዩብ ገጻችን በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
🎙የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል መራሔ ድኅነት ሰንበት ት/ቤት 56ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ደረሰ።
📌ጥቅምት 19 - 2017 በገዳሙ ዐውደ ምሕረት ላይ እንገናኝ።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!
http://t.me/EMislene
ባርከን አባታችን
ባርከን አባታችን ጻድቁ መነኩሴ/2/ አቡነ አረጋዊ /2/
አሳርግ /3/ ስማን ጸሎታችንን/2/
📷 የጻድቁ የአቡነ አረጋዊ ዓመታዊ በዓል በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል።
ጥቅምት 14 -2017 ዓ.ም
http://t.me/EMislene
ንግሥተ ሰማይ
ንግሥተ ሰማይ ወምድር ማርያም ድንግል/2/
ተፈጸመ/5/ ማኅሌተ ጽጌ/2/
ትርጉም :- የሰማይ የምድር ንግሥት የሆንሽ እመቤታችን ሆይ ያንቺ ማኅሌት ጽጌ ተፈጸመ።
📌 የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
📌 የዩቲዩብ ቻናል፡
http://youtube.com/
@EMislene
ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን።
📷የአምላካችን አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በፎቶ።
ጥቅምት 28 -2017 ዓ.ም
በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
📚ከመደርደሪያችን
የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የመጽሐፍ ዳሰሳ አዘጋጅቷል።
🗓ሐሙስ ኅዳር 5 - 2017 ዓ.ም
⏰ከምሽቱ 12:30
🪧በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
💐🌸🌺🌹🌷🌺🌸💐🌸🌺🌹🌷
እንኳን ለወርኃ ጽጌ የመጨረሻ ሳምንት ማኅሌት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!!!
"ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት"
💻ዛሬ ማታ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ በዩቲዩብ ገጻችን ፤ የቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን ።
🌸🌺🌹🌷💐🌸🌺🌹🌷💐🌸🌺
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
እንደበደሌ ስላልከፈልከኝ
ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ?
አማኑኤል ተመስገን
ለዚህ ፍቅርህ ምን ልክፈልህ?
📷የአምላካችን ዐማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በፎቶ።
ጥቅምት 28 -2017 ዓ.ም
በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
ጥቅምት 20 ዓመታዊ በዓሉን የምናከብረው ቅዱስ ” ዮሐንስ ሐጺር- አጭሩ አባ ዮሐንስ” ማነው?
ሥዕሉን ወይንም ርዕሱን በመጫን ሙሉውን ያንብቡ!!
from debregelila.org
በድሮ ጊዜ አርበኛ ሜዳ ተብሎ የሚጠራ ዱር ውስጥ የሚኖሩ አንድ አጋዘንና በሌላኛው የዱር ክፍል ውስጥ ጥቅጥቅ ባለ ደን ውስጥ የሚኖር አንድ ነብር ነበሩ። አጋዘኑ ምንም ያህል በተመቻቸ አረንጓዴና ለምለም የሆነ የሚያምር ደን ውስጥ ቢኖርም በአንድ አካባቢ ከነብር ጋር መኖሩ ምንም ምቾት አልሰጠውም ነበር። እንደውም በየጊዜው ፍርሀቱ እየጨመረና ኮሽ ባለ፣ ድምጽ በተሰማ ቁጥር እየደነበረ ድንጋጤው እየጨመረ በዐሳብና በሰቀቀን ከሳ። በሌላ በኩል ደግሞ ነብሩ የአጋዘኑ መክሳት አሳስቦት ነበር። ምክንያቱ ደግሞ "አንድ ቀን ዘልዬ ስበላው የሚያጠግብ ስጋ አላገኝበትም፤ አልጠግብምም" የሚልነበር።
ቀን አልፎ በቀን ሲተካ አያ ነብሮ አጋዘኑ ወፈር እስኪልና እስኪበላው ይጠባበቅ ነበር። ይሁን እንጂ አጋዘን ለውጥ አላመጣም። ይህን ጊዜም ነብሩ አስቦ አስቦ በስምምነት አብረው እንዲኖሩ ሃሳብ አቀረበ። ይህን ጊዜ አጋዘኑ በጣም ደስ አለው። ስምምነታቸውም ነብሮ አጋዘኑን ላይበላውና በሌሎች አውሬዎችም እንዳይበላ በደንብ ሊጠብቀው ነበር። ታድያ ጓደኛሞች ሆነው ሲኖሩ፣ ሲኖሩ ያለ ሳብ በደስታ መኖር የጀመረው አጋዘን ሰውነቱ ወፈር እያለና እያማረበት ነብሩም ፍላጎቱና መሃላውም እየተጋጩበት መጣ።
ከዕለታት አንድ ቀን ነብርና አጋዘኑ ጋደም ብለው ወሬ እያወሩ እያለ ነብሩ ጥያቄ እንዳለው በመጠቆም አጋዘኑን እንዲህ አለው።
"እኔ የምልህ ጓደኛዬ፣ መሃላውን ያፈረሰ ግን ምንድን ነው የሚሆነው? መጨረሻውስ ምንድን ነው?" አጋዘኑ ይህን ጊዜ በጣም የፈራ ቢሆንም ምንም እንዳልፈራ ሆኖ "አያ ነብሮ፣ ያው እንደሚታወቀው ግፉ በልጅ ልጆቹ ላይ ይደርሳል።" ሲል መለሰለትና ይህንን ጥያቄ ለምን እንደጠየቀው ግራ ተጋብቶ ትኩር ብሎ ያየው ጀመር። በሌላ በኩል ነብሩ በጣም ተደስቶ "ይህንን ጥፋት አጥፍቼ በልጆቼ ቢደርስ እኔ ምን አግብቶኝ?" ብሎ ነብሩ ዘሎ አጋዘኑ ላይ ሲከመርበት በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ በነብሩ ድንገተኛ ጥቃት የተደናገጠው አጋዘን ደንግጦ ከተጋደመበት ሲነሳ የነብሩን ሆድ ይቀድደውና የነብሩ አንጀት ይዘረገፋል። ታድያ በሞትና በሕይወት መካከል የሆነው ነብር እያጣጣረ 'ምነው፣ ምነው "መሃላ ያፈረሰ ሰው ጥፋቱ ልጅና የልጅ ልጁ ላይ ይሆናል" አላልኸኝም ነበር?' በማለት በሰለለ ድምጹ ሲጠይቀው የነብር እራት ከመሆን በተዓምር የተረፈው አጋዘን "አያ ነብሮ የአንተ እናትና አባት የሰሩት ግፍ አንተ ላይ ደርሶ ይሆናላ!" በማለት በጓደኛው ክሕደት እያዘነ ነብሩን ከተኛበት ጥሎት ሄደ ይባላል።
መሃላችሁን ምን ያህል ትጠብቁ ኖሯል?
መልካም ዕለተ ሰንበት።
http://t.me/EMislene
🎬ምሽት 3፡30 ጀምሮ በዩቲዩብ ገጻችን በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
ከእኔ የጎደለው ምንድን ነው?
የአብርሃምን ታሪክ አውቃለሁ! ገና በወጣትነቱ "ዘርህን እንደምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለው።" ተብሎ ቃል ተገብቶለት ዘጠና ዘጠኝ ዓመት እስኪሞላው ድረስ ግን ልጅ ሳይወልድ መቆየቱን ተምሬአለሁ። ነገር ግን እስኪሰጠው ድረስ ፈጣሪውን 'መቼ ነው የምትሰጠኝ "ዘርህን አበዛዋለሁ" አላልኸኝም እንዴ? ምነው ዝም አልከኝ? የሰጠኸኝ ተስፋ ለከንቱ ነውን?" ብሎ እግዚአብሔርን አልጠየቀም ስሙንም አላማረረም ደግሞም፤ የዮሴፍን ታሪክ ሰምቻለሁ! ህልምን አልሞ ቢያስፈታ ወንድሞቹ እንደሚሰግዱለት እንደሚነሥስ ቢነገረውም ወንድሞቹ በመስገድ ፋንታ ለባዕዳን ሐገር ሰዎች ሸጡት። በሐሰት ተመስክሮበት በወህኒ ተወረወረ ፤ ባመናቸው ተካደ፤ ነገር ግን "ቃል የተገባልኝ ይህ አልነበረም፤ ይህንን አላልኸኝም፤ ለምን በእስር ተጣልሁ? ለምን ወንድሞቼ እንዲጥሉኝ ፈቀድህ?" ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ሙግት አልገጠመም።
እኔም ይህንን ሰምቼአለሁ፣ አውቄአለሁ፣ ታድያ በማዕበል ውስጥ መንገድ ያለው አምላክ እንዳለኝ እያወቅሁ በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ለቀናት ባድር እንኳን የሚያወጣ አምላክ እንዳለኝ እየተማርኩ ለምን አምኖ መጠበቅ ተሳነኝ? ታዲያ ከእኔ የጎደለው ምንድን ነው?
http://t.me/EMislene
🎙በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል የእግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት
ሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል የሚደረገው ወርኃዊ የጸሎት መርሐግብር 26ኛ ዓመቱን ያዘ።
ዜና አበው "ሰው ለጸሎት ሲቆም ሰይጣን ይቀመጣል፤ ሰው ጸሎት ሲያቋርጥ ሰይጣን ሥራ ይጀምራል" እንዲል፣ የሚከናወን አገልግሎት ሁሉ በጸሎት ካልታገዘ ሊሰምር፣ ፈተናዎችን ሊያልፍና በፍቅር የተሞላ ሊሆን አይችልምና በሰ/ት/ቤታችን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የአገልግሎት ክፍላት የጸሎት መርሐ ግብራት ይከናወናል።
ለዛሬ በሰንበት ት/ቤቱ ከሚከናወኑት የጸሎት መርሐ ግብራት መካከል በትላንትናው ዕለት 26ኛ ዓመቱን ስለያዘው የአቡነ አረጋዊ የጸሎት መርሐግብር ልንነግራችሁ ወደድን።
ወር በገባ በ14ኛው ቀን ታዳጊ ሕፃናት ነጠላ ለብሰው በካቴድራሉ ቅጥር ግቢ ለጸሎት ሲሰባሰቡ ማየት የተለመደ ነው። በዚህ የሕጻናትና ማዕከላውያን የጸሎት መርሐ ግብር ላይ መገኘት ለታዳጊ ሰንበት ተማሪዎች እንደ ግዴታ የሚታይ ሲሆን ሁሉም ሰው ሊሳተፍበትና ከጻድቁ አባታችን ረድኤት በረከት ሊያገኝ የሚችልበት ነው።
ለ 26 ዓመታት ትውልድ በትውልድ እየተተካካ ይህንን የጸሎት መርሐ ግብር ሲያደርግ በቆየባቸው ዓመታት የጸሎት መርሐ ግብሩ አገልግሎቱን ከማጠናከር ባለፈ ለታዳጊ ሕፃናቱ የጸሎት ሕይወትን በማለማመድ ፣ የጻድቁ አባታችን የአረጋዊን ፍቅር በልቡና ላይ በማሳደር እንዲሁም የተለያዩ የሕይወት ፈተናዎችን ለማለፍ በማገዝ በኑሯቸው ላይ ትልቅ አሻራ እንዳለው አባላቱ ይመሰክራሉ።
የአቡነ አረጋዊ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!
http://t.me/EMislene
እንኳን አደረሳችሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/live/xPcoSkMJXJQ?si=uDyjiewzV5bRtB0E